ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

📣የዛሬው ምሽት ስለ ነገረ ማርያም የነበረን ትምህርት በእዚህ ላይ እናበቃለን📣


ነገ ምሽትም በተመሳሳይ ሰዓት 2:00 ላይ ቀጣዩን ክፍል የምንቀጥል ይሆናል። ሁላችሁም ነገ 2:00 ላይ ጠብቁን።


👉እስከ አሁን የነበረውን ትምህርት ከወደዳችሁት በኮመንት ላይ አሳውቁን።

ከ8,000 ሰው በላይ ይሄንን ቻናል በአንድ ቀን ውስጥ እየተመለከተው ግን ለምትወዷቸው ኦርቶዶክሳዊያን እህት ወንድሞቻችሁ የእኛን ቻናል እንዲቀላቀሉ ለምን እንደማትልኩላቸው አላውቅም።


🤲እባካችሁ ድንግል ማርያምን አትወዷትም? ጓደኞቻችሁስ በደንብ ፍቅሯ እንዲያድርባቸው አትፈልጉም? ለምን አትልኩላቸውም?


አሁን ድንግል ማርያምን ከወደዳችኋት ለ20-30 ጓደኞቻችሁ አሁን በኃላፊነት የቻናላችንን ሊንክ ላኩላቸው አሁን። ከእዛም ከላካችሁ በኋላ ልከናል ብላችሁ ኮመንት አድርጉ🙏🙏🙏

ሊንኩ 👉 /channel/ortodoxmezmur
/channel/ortodoxmezmur
/channel/ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

"እነሆ የጌታ ባርያ" ሉቃ 1:38

       🤲ክፍል ፬🤲

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የእመቤታችን የድንግል ማርያም ንጽሕና እና ቅድስና እንዴት ነው?🤔

📣ክፍል ፪📣

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🤲🤲🤲ስለ ነገረ ማርያም🤲🤲🤲


ዛሬ ማታ 2:00 ላይ ትምህርታችንን የምንጀምር ስለሚሆን ሁላችሁም 2:00 ላይ ተሰብስባችሁ እንድትገኙ እናሳስባለን።

መምህር ዲያቆን ዳግማዊ ሰለሞን

ይሄንን ትምህርት ጓደኞቻችሁ እንዲማሩ ይሄንን ማስታወቂያ ላኩላቸው ከታች ያለውን ሊንክ በመግባት ይቀላቀሉን።


🌙 የማታ ሰው ይበለን 🌙

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✝እንድታማሩ ያዘጋጀናቸው የትምህርት ርዕሶች ከታች የተዘረዘሩት ናቸው✝

ከእነርሱ ውስጥ መማር የምትፈልጉትን ተራ ቁጥር፤ ቁጥሩን ብቻ ትልኩልናላችሁ።

1.ትምህርተ ሃይማኖት(ስለ ሥነ ፍጥረት)
2.አምስቱ አእማደ ምሥጢራት(ከእዚህ በፊት የተማርነው አለ ይላክልናል)
3.ነገረ ማርያም
4.ነገረ ክርስቶስ(ክርስቶስ ፈራጅ ወይስ አማላጅ)
5.ነገረ መልአክት
6.ታቦት፣ጽላት፣ቤተክርስቲያን


መማር የምትፈልጉትን ተራ ቁጥር ላኩልን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​እንኳን ለታላቁ ነቢይና ሰማዕት ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

#ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ

ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነ ዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: #ቅዱስ_ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "#ዘካርያስ ካህኑና #ቅድስት_ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)

¤የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል!

¤እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር::

¤ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::

¤ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል #እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::

¤የአምላክ እናቱ ስትደርስና "#ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በሁዋላ ሰኔ 30 ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::

¤ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ 2 ዓመት ከ6 ወር በሆነው ጊዜ #ሰብአ_ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ::

¤እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 (5) ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ 5 (7) ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና #ስምዖን ወርደው ቀበሯት::

¤ሕጻኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ #ድንግል_ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ::

¤ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በሁዋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ25 (23) ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም::

¤ከዚህ በሁዋላ 30 ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጀን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" (ሉቃ. 1:76) ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና::

¤ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ #መንፈስ_ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና::

¤ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሃ ሰበከ:: ለንስሃም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ6 ወራት ቆይቶ ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነ ልብሱ የያዘ ፈጣሪ 'አጥምቀኝ' ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው::

¤"እንቢ ጌታየ! አንተ አጥምቀኝ" አለው:: ጌታ ግን "ፈቅጄልሃለሁ" አለው:: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ ዛሬም "#መጥምቀ_መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ ለ7 ቀናት አሠረው::

ሔሮድስን ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: (ማቴ. 3:1, ማር. 6:14, ሉቃ. 3:1, ዮሐ. 1:6)

ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በሁዋላ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት ጌታችን ወዳለበት #ደብረ_ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች:: #ቅዱሳን_ሐዋርያት በአዩት ነገር ተገርመው ራሱን እጅ ነሷት::

ከዚሕ በሁዋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት:: በመላው ዓለም ለ15 ዓመታት ስትሰብክ ኑራ በዚህች ቀን ዓረቢያ ውስጥ ዓርፋለች::

<< አስማተ-ዮሐንስ መጥምቅ (የመጥምቁ ዮሐንስ ስሞች) >>
1.ነቢይ
2.ሐዋርያ
3.ሰማዕት
4.ጻድቅ
5.ካሕን
6.ባሕታዊ/ገዳማዊ
7.መጥምቀ መለኮት
8.ጸያሔ ፍኖት (መንገድ ጠራጊ)
9.ድንግል
10.ተንከተም (የብሉይና የሐዲስ መገናኛ ድልድይ)
11.ቃለ አዋዲ (አዋጅ ነጋሪ)
12.መምሕር ወመገሥጽ
13.ዘየዐቢ እምኩሉ (ከሁሉ የሚበልጥ)

ጌታችን #መድኃኔ_ዓለም የመጥምቁ ዮሐንስን ምትረት አስቦ ይቅር ይበለን:: ጸጋውን: በረከቱንና ክብሩንም ያሳድርብን::

ምንጭ - ዝክረ ቅዱሳን
#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🌺 ሰላም፡ለኵልክሙ
እነሆ ግእዝን በክረምቱ ጊዜ በልዩ ዝግጅት የሚማሩበት የግእዝ ቋንቋን ኮርስ ለመስጠት ምዝገባ ጀመርን።

📜 እርስዎም የግእዝ ቋንቋን ቀለል ባለና ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅታችንን አጠናቀናልና ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመመዝገብ ጥንታዊና ውዱ ቋንቋችንን እናጥና ፥ ዕንወቅ።


✅ ምዝገባውን ለማካሄድ ከታች ባለው የቴሌግራም አድራሻ ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር በመላክ የመማማሪያ ቦታዎችን ያገኛሉ  ✅

ለመመዝገብ 👇
@Geez202
@Geez202
@Geez202 👈
                

ትምህርቱን ከ14 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው ፤  ስልክ፣ ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ በመጠቀም መማር ይቻላል።

📲 የበለጠ መረጃ በምዝገባው ሂደት ይደርስዎታል። ጥያቄ ሲኖር ከታች በተቀመጠው በስልክ ያግኙን። ሠናይ፡ጊዜ።

🌺 መሠረተ፡ግእዝ 🌺
@MesereteGeez - 0918026533
ለሌሎችም ሼር በማድረግ እንድናዳርስ በአክብሮት እንጠይቃለን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🌸🌸🌸🌸መፍትሔዎች🌸🌸🌸🌸🌸

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🌺 ሰላም፡ለኵልክሙ
እነሆ ግእዝን በክረምቱ ጊዜ በልዩ ዝግጅት የሚማሩበት የግእዝ ቋንቋን ኮርስ ለመስጠት ምዝገባ ጀመርን።

📜 እርስዎም የግእዝ ቋንቋን ቀለል ባለና ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅታችንን አጠናቀናልና ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመመዝገብ ጥንታዊና ውዱ ቋንቋችንን እናጥና ፥ ዕንወቅ።


✅ ምዝገባውን ለማካሄድ ከታች ባለው የቴሌግራም አድራሻ ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር በመላክ የመማማሪያ ቦታዎችን ያገኛሉ  ✅

ለመመዝገብ 👇
@Geez202
@Geez202
@Geez202 👈
                

ትምህርቱን ከ14 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው ፤  ስልክ፣ ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ በመጠቀም መማር ይቻላል።

📲 የበለጠ መረጃ በምዝገባው ሂደት ይደርስዎታል። ጥያቄ ሲኖር ከታች በተቀመጠው በስልክ ያግኙን። ሠናይ፡ጊዜ።

🌺 መሠረተ፡ግእዝ 🌺
@MesereteGeez - 0918026533
ለሌሎችም ሼር በማድረግ እንድናዳርስ በአክብሮት እንጠይቃለን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✝ሰላም የተወደዳችሁ የዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች✝

👉ከእዚህ በፊት ስናደርግ እንደነበረው
⁉️የጥያቄ እና መልስ ፕሮግራም አዘጋጅተናል⁉️

🤔ሁላችሁም በሃይማኖታችሁ ሊሆን ይችላል ወይም በመንፈሳዊ ሕይወታችሁ ጥያቄ የሆነባችሁ ወይም ግራ የገባችሁ እንዲመለስላችሁ የምትፈልጉትን ጥያቄዎች ሁሉ🤯

🕝ከአሁን ጀምሮ መጠየቅ ትችላላችሁ እዚሁ ላይ።

ጥያቄዎቹን ሰብስበን በእዚህ ሳምንት መመለስ እንጀምራለን


🫵ከአንተ/ከአንቺ ምን ይጠበቃል?🫵

1ኛ የፈለጋችሁትን ጥያቄዎች መጠየቅ
2ኛ እነዚህን ጥያቄዎች እንዲሁም ሌሎች ትምህርቶችን እንዲያገኙ ለምትወዷቸው እህት👩‍🦰ወንድም👨 ጓደኞቻችሁ ሁሉ የቻናላችንን ሊንክ በመላክ እንዲቀላቀሉ እና እነርሱም ከመልሶቹ እንዲማሩ፣ በተጨማሪም እነርሱም ጥያቄዎች ያሏቸውን በመጠየቅ ቤተሰብ እንዲሆን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።

🏃‍♂አሁን ቶሎ ቶሎ ቢያንስ ለ10 ሰው እና ከእዛ በላይ ይህንን መልእክት በመላክ እንዲቀላቀሉ እናድርግ🏃‍♂

እኛም ታሪክ እንስራ 135,809 አባላት አሉ።

በእዚህ ሳምንት እጅግ ከፍ ያለ ቁጥር እናስመዝግብ።

                 🎁ተጀምሯል⌛️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🌺 ሰላም፡ለኵልክሙ
እነሆ ግእዝን በክረምቱ ጊዜ በልዩ ዝግጅት የሚማሩበት የግእዝ ቋንቋን ኮርስ ለመስጠት ምዝገባ ጀመርን።

📜 እርስዎም የግእዝ ቋንቋን ቀለል ባለና ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅታችንን አጠናቀናልና ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመመዝገብ ጥንታዊና ውዱ ቋንቋችንን እናጥና ፥ ዕንወቅ።


✅ ምዝገባውን ለማካሄድ ከታች ባለው የቴሌግራም አድራሻ ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር በመላክ የመማማሪያ ቦታዎችን ያገኛሉ  ✅

ለመመዝገብ 👇
@Geez202
@Geez202
@Geez202 👈
                

ትምህርቱን ከ14 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው ፤  ስልክ፣ ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ በመጠቀም መማር ይቻላል።

📲 የበለጠ መረጃ በምዝገባው ሂደት ይደርስዎታል። ጥያቄ ሲኖር ከታች በተቀመጠው በስልክ ያግኙን። ሠናይ፡ጊዜ።

🌺 መሠረተ፡ግእዝ 🌺
@MesereteGeez - 0918026533
ለሌሎችም ሼር በማድረግ እንድናዳርስ በአክብሮት እንጠይቃለን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✝ሰላም የተወደዳችሁ የዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች✝

👉ከእዚህ በፊት ስናደርግ እንደነበረው
⁉️የጥያቄ እና መልስ ፕሮግራም አዘጋጅተናል⁉️

🤔ሁላችሁም በሃይማኖታችሁ ሊሆን ይችላል ወይም በመንፈሳዊ ሕይወታችሁ ጥያቄ የሆነባችሁ ወይም ግራ የገባችሁ እንዲመለስላችሁ የምትፈልጉትን ጥያቄዎች ሁሉ🤯

🕝ከአሁን ጀምሮ መጠየቅ ትችላላችሁ እዚሁ ላይ።

ጥያቄዎቹን ሰብስበን በእዚህ ሳምንት መመለስ እንጀምራለን


🫵ከአንተ/ከአንቺ ምን ይጠበቃል?🫵

1ኛ የፈለጋችሁትን ጥያቄዎች መጠየቅ
2ኛ እነዚህን ጥያቄዎች እንዲሁም ሌሎች ትምህርቶችን እንዲያገኙ ለምትወዷቸው እህት👩‍🦰ወንድም👨 ጓደኞቻችሁ ሁሉ የቻናላችንን ሊንክ በመላክ እንዲቀላቀሉ እና እነርሱም ከመልሶቹ እንዲማሩ፣ በተጨማሪም እነርሱም ጥያቄዎች ያሏቸውን በመጠየቅ ቤተሰብ እንዲሆን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን።

🏃‍♂አሁን ቶሎ ቶሎ ቢያንስ ለ10 ሰው እና ከእዛ በላይ ይህንን መልእክት በመላክ እንዲቀላቀሉ እናድርግ🏃‍♂

እኛም ታሪክ እንስራ 135,769 አባላት አሉ።

በእዚህ ሳምንት እጅግ ከፍ ያለ ቁጥር እናስመዝግብ።

🎁ተጀምሯል⌛️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​ሰኔ 21/10/2016 ዓ.ም

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌልና ምስባክ።

ምስባክ ፦ መዝ 45፥4-6
ቀደሰ ማኅድሮ ልዑል
እግዚአብሔር ውስተ ማዕከላ ኢትትሀወክ
ወይረድኣ እግዚያብሔር ፍጹመ

ትርጉም
ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ
እግዚያብሔር በመካከሏ ነው አትናወጥም
እግዚያብሔርም ፈጥኖ ይረዳታል

ወንጌል ፦ ማቴ 16÷13-20
ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ(የጌታ ቅዳሴ)

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 የሰኔ ማርያም ዚቅ

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 የሰኔ ማርያም ዋዜማ

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

"ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል" ሉቃ 1:48

🤲ክፍል ፭🤲

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🙏አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ🙏
       

      🤲ትርጓሜ ክፍል ፫🤲

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🤲ነገረ ማርያም መግቢያ🤲

📣ክፍል ፩📣

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እሺ በጣም ጥሩ በጠየቃችሁት ጥያቄ መሰረት።


በእዚህ ሳምንት ነገረ ማርያምን ወይም ስለ ድንግል ማርያም የምንማማር ይሆናል።

👉ይህ ክፍል እጅግ ሰፊ ስለሆነ በመጠኑ እንደ አቅማችን የምንማር ይሆናል። ይሄንን ትምህርት ለመማር እንዲረዳችሁ እንደ ንባብ ማጣቀሻ ሁላችሁም መጠቀም ያለባችሁ Application አለ እርሱም፦
⛔️ትምህርተ ተዋሕዶ ይባላል⛔️

ከታች እንልክላችኋለን አፕሊኬሽኑን እርሱን አውርዳችሁ በእዛ ማንበብ ትጀምራላችሁ ማለት ነው። ተዘጋጁ።👇👇👇👇👇👇

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🤲ሰላም የተወደዳችሁ የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮቻችን🤲

በባለፈው ማንኛውም አይነት ጥያቄዎች ካላችሁ እንድትጠይቁ ያዘጋጀን ሲሆን የጠየቀ ሰው ግን አልነበረም።

👉አሁን ይሄንን ክረምት መሠረት በማድረግ የሃይማኖት ትምህርት በእዚሁ በቻናላችን መማር ልንጀምር ስለሆነ።

መማር የምትፈልጉ ኦርቶዶክሳዊያን በቅድሚያ

መማር እንፈልጋለን

ብላችሁ ኮመንት ላይ ሁላችሁም ላኩልን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አምላከ ተክለሃይማኖት ማረን

አምላከ ተክለሐይማኖት ማረን 2×
አምላከ ቅዱሳን ታረቀን 2×
ስለቃልኪዳንህ በቁጣ አታጥፋን
አዝ
ሐዋርያው ቅዱስ ተክለሃይማኖት
የኢቲሳ አንበሳ የኔ አባት
ቁጣውን አብርደው ተክለሐይማኖት
ለምልጃ ተነሳ የኔ አባት
ከሰማይ ካህናት ተክለሐይማኖት
ቤተሰብ ሆነሃል የኔ አባት
የሥላሴን መንበር ተክለሐይማኖት
ለማጠን በቅተሀል የኔ አባት
አዝ
ከከርቤ ከሚያ ተክለሃይማኖት
ከሰሊክም በልጧል የኔ አባት
የፃድቁ ፀሎት ተክለሐይማኖት
በእግዚአብሔር ፊት ሸቷል የኔ አባት
ስለቃልኪዳንህ ተክለሐይማኖት
አምላክ ይለመናል የኔ አባት
ፀሎትህ ሲደርስ ተክለሐይማኖት
እኛን ይታረቃል የኔ አባት
አዝ
ተማፅነንብሃል ተክለሃይማኖት
ጌታ ሆይ በስሙ የኔ አባት
በፃዲቁ ፀሎት ተክለሐይማኖት
በሰባረ አፅሙ የኔ አባት
ኢትዮጲያን በሙሉ ተክለሐይማኖት
አስተምሮ ሲመለስ የኔ አባት
አፅመ ርስቱ ሆነች ተክለሐይማኖት
ደብረ ሊባኖስ የኔ አባት
አዝ
የፃዲቁ መንፈስ ተክለሃይማኖት
ከቅዱሳን ጋራ የኔ አባት
ከልባችን ገብተህ ተክለሐይማኖት
ብርሃንን አብራ የኔ አባት
በፀሎት ስቆም ተክለሐይማኖት
ስምህን ስጠራ የኔ አባት
ነፍሴ ተደሰተች ተክለሐይማኖት
ሲርቀኝ መከራ የኔ አባት

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ይህንን አስደናቂ ቪዲዮ ሁላችሁም እንድታዩት እለምናለሁ
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን✝

በእግዚአብሔር ፍጹም ሠላም እንደምን አላችሁ?

እንደ አምላካችን መልካም ፈቃድ በእዚህ ድምጽ:-
🤲የክርስቶስ ዳግም መምጣት ምልክቶቹ ምንድናቸው?
🤲በዓለም ላይ አሁን ላይ እየተከናወኑ ያሉ ለውጦች ምን ምን ናቸው?
🤲ስለ ሀሰተኛ ክርስቶሶች ታሪካዊ አመጣጦች
🤲ምን ማድረግ እንችላለን?

🤲በቅርብ ቀን ይጠብቁን🤲

በይሳኮር

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ይሄንን ማስታወቂያ ትላንት የለቀቅን ሲሆን እስከ አሁን 3 ጥያቄ ተጠይቋል። ሌሎችም ጥያቄ መጠየቅ የምትፈልጉ ካላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ድንግል_ማርያም_ብዬ

ድንግል ማርያም ብዬ
ስማጸን በስምሽ (፪)
በቅድመ እግዚአብሔር
ልመናዬን አድርሽ (፪)

እኔ ደካማ ነኝ ኃጢአቴ የበዛ
እኔ ጎስቋላ ነኝ በደሌ የበዛ
ጊዜዬን ያባከንኩ በዋዛ ፈዛዛ
ጊዜዬን ያሳለፍኩ በከንቱ በዋዛ

እመብርሃን ስልሽ ፈጥነሽ ድረሽልኝ(፪)
ልመናዬን ሰምተሽ ቆመሽ ለምኝልኝ
ኃጢአቴ ቢበዛም ይዣለሁ አንቺን(፪)
አስምረሻልና በላዒ ሰብን
#አዝ
አንገት የሚያስደፋ በዝቶብኝ ኃጢአቴ
ምልጃሽን ፈለኩኝ ድንግል ሆይ እናቴ
ያን ክፉ ጨለማ እንዳላይ አደራ(፪)
ድንግል ሆይ ከልይኝ ከዲያብሎስ ጭፍራ
#አዝ
እመብርሃን እያልኩ ቆሜ ከደጅሽ
በብርሃን እጆችሽ እንባዬን አብሽ
ዓለም አታላይ ነች ወደሷ ተሳብኩኝ
ታማልጂኝ ብዬ አንቺኑ ተራብኩኝ

ሊቀ መዘምራን
ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ

"ጻድቃን እኔን ይጠብቃሉ"
መዝ፻፵፩፥፯

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#የያረድ_ዉብ_ዜማ

የያረድ ዉብ ዜማ ድንግል እመቤቴ
ስጦታዬ ነሺ /2/ በምን አንደበቴ
እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ/2/

ምድርና ሰማዩ ተአምርሺን ይንገሩ 
ፍጥረታት በሙሉ ስለ አንቺ ይመስክሩ 
ተነግሮ የማያልቅ ድንቅ ነው ስራሽ 
ድንግል ሆይ እናቴ አምሳያም የለሺ 
ማርያም ድንግል እረዳቴ
የምትደርሺልኝ ነይ ስልሽ በጭንቀተ 
ታምርሺንም በአይነ አይቻለሁ 
ጽዮን ሆይ ስልሽ ድንግል ሆይ እጠግባለሁ 
#አዝ
የእግዚአብሄር ጥበቡ በአንቺ ተገለጠ 
የአዳም ዘር በሙሉ ከሞት አመለጠ 
የመዳን ምክንያት ማርያም አንቺ ነሽ
ለፍጥረቱ ሁሉ መሰላል የሆንሺ
ነገን ባላውቅ እኔን ቢያስፈራኚ 
አንቺ ካለሺኝ በፍጹም አልወድቅም 
በፊትሺም እንድቆም ለምስጋና 
ማርያም ልበልሽ በትህትና 
#አዝ
ትውልዱ በሙሉ ለምስጋና ይቁም 
ባንቺ ስለሆነ የቀረለት መርገም 
አዳም ከነልጁ በሰማይ በምድር 
ማርያም ማርያም ይበል ተአምርሺን ይናገር 
ጨለማው ከፊቴ ተገፈፈ 
ማርያም በምልጃሽ ልቤ አረፈ 
ከጎኔ ነይ ስልሺ እጽናናለሁ 
እሳት ገደሉን ሁሉንም አልፈዋለሁ 

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​​​ሰኔ 21 ለሚከበረው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

#ሰኔ_20_እና_21

👉 ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ ህንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል።

የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የታነጸው በዛሬዋ ቀን ነው አናጺውም እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው።

ጴጥሮስ፤ ዮሐንስ በርናባስና ሌሎችም ሐዋርያት በፊልጰስዩስ ተሰብስበው ሳለ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፤ 3 ድንጋዮችን አንስቶ ጎተታቸው እንደ ሰም ተለጠጡ እንደ ግድግዳም ሆኑ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ እየሩሳሌም አምሳያ አድረጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፤ ዳግመኛ በበነጋው ሰኔ 21 ቀን እመቤታችንን እና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል ቅዳሴ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቆረባቸው ፍጹም ደስታም ሆነ።

ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታ እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተክርስቲያን አንጸዋል። ከዚያ በፊት የነበረው የነሶሎሞን ቤተ መቅደስ የአይሁድ ምኩራብ የአይሁድ ስርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ስርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፤ ታዲያ ሐዋርያት የት ነበር ህዝቡን የሚያጠምቁት የሚያቆርቡት ካሉ በየሰው ቤት ነበር።

ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን ታላቁ ነብይ ኤልሳዕ አረፈ። ይህ ነብይ በ 12 ጥማድ በሬ ሲያርስ ቴስቢያዊው ነብዩ ኤልያስ ተከተለኝ አለው ምንም ሳያቅማማ ሀብት ንብረቱን ትቶ ተከተለው፤ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ከማረጉ በፊት ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ ይለዋል ባንተ ላይ ያደረ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርቢኝ ይለዋል፤ እንደ ቃሉ ሆነለት ተደረገለት፤ ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል።

የእምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች፤ የዚህ ነብይ ድንቅ ታሪኩ 2ኛ ነገስት ላይ በስፋት ተጽፏል ሰኔ 20 ቀን እረፍቱ ነው ቤተክርስቲያን የዛሬውን ቀን እመቤታችንን እና ነብዩን አስባ ትውላለች።

ከበዓሉ ያሳትፈን የእመቤታችን ምልጃና ረዳትነት አይለየን!

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 የሰኔ ማርያም ወረብ

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 የሰኔ ማርያም እስመለ ዓለምና
ምልጣን

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…
Подписаться на канал