ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ
ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ
የአንድ አባት ልጆችኮ ነን
ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ
የአንድ የእናት ልጆችኮ ነን
ብዙ ነዉ መንግስቱ አብረን እንወርሳለን
ሰፊ ነው ግዛቱ አብረን እንወርሳለን
የተካፈልኩትን ንብረት
አጥፍቼ ብመለስ ዛሬ
አባቴ ናፍቆኝ ብመጣ
ልቤን አንገቴን ሰብሬ
ለሁላችንም ይበቃል
ብዙ ነው የርሱ መንግስት
አይክፋህ እባክህ ወንድሜ
ፍቅር ይበልጣል ከሃብት
#አዝ
ፊትህ በሐዘን አይጥቆር
ድንጋዩን ጣለው ወንድሜ
ተቅበዝባዥ እንዳያደርግህ
እጅህ ቆሽሾ በደሜ
ልብህን መልካም ብታደርግ
ያንተም መስዋዕት ያርጋል
ጌታ ለሁሉም እኩል ነው
መታዘዝ ንጉሥ ያደርጋል
#አዝ
ብልጥ ስለሆንኩ አይደለም
የተባረኩት በጌታ
ጽኑ መሻቴን አይቶ ነው
በኩር ያደረገኝ ስመታ
የበቀል ጦርክን ሸሽቼ
በባዕድ አገር ብኖርም
በልጅ በትዳር ባርኮኛል
አብረን እንኑር በሰላም
#አዝ
ብልጥ ስለሆንኩ አይደለም
የተባረኩት በጌታ
ጽኑ መሻቴን አይቶ ነዉ
በኩር ያደረገኝ ስመታ
የበቀል ጦርክን ሸሽቼ
በባዕድ ሀገር ብኖርም
በልጅ በትዳር ባርኮኛል
አብረን እንኑር በሰላም
ሊቀ መዘምራን
ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
15/07/16 ዓ.ም
✝ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚሰበክ
ምስባክ።
ምስባክ፦ መዝ ፷፰፥፱
እስመ ቅንዓተ ቤትከ በልዐኒ
ትእይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ
ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ
ትርጉም፦
የቤትህ ቅናት በልቶኛልና
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቋልና
ስውነቴን በጾም አደከምኋት
የዕለቱ ወንጌል፦
ዮሐ ፪፥፲፪ - ፍጻሜ
ቅዳሴ፦ ዘእግዚእነ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
🔰የመጋቤ ስብሐት አለሙ አጋ መዝሙሮች ቁ.3
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ጊዜ ሱባዔ /በሱባዔ ጊዜ/
በጸሎት ሰዓት ዓምድና ግድግዳ ሳይደገፉ መቋሚያ ሳይዙ በሁለት እግር ቀጥ ብሎ በመቆም መጸለይ ይኖርብናል፡፡ እንዲሁም ፊትን ወደ ቤተ ክርስቲያን ወይም ወደ ምሥራቅ መልሶ መቆም ወዲያና ወዲህ ወደ ግራ ወደ ቀኝ አለመዟዟር በሰፊሐ እድ በሰቂለ ኅሊና ኾኖ መጸለይ ይገባል፡፡ መዝ.5፡3፤ መዝ.133፡2፤ ዮሐ.11፡41፡፡
በሱባዔ ወቅት በቅደም ተከተል መጸለይ አለብን፡፡ መጀመሪያ «በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አአትብ ገጽየ ወኩለንታየ በትእምርተ መስቀል በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ መላ ሰውነቴን በትእምርተ መስቀል አማትባለሁ» እያለ ሰጊድን ከሚያነሣው ሲደርስ መስገድ መስቀልን ከሚያነሣ ላይ ስንደርስ ማማተብ ይገባል፡፡
በማስከተል አቡነ ዘበሰማያት፣ መዝሙረ ዳዊት፣ ውዳሴ ማርያምና ሌሎች በመዝገበ ጸሎት የተካተቱትን መጸለይ፤ ቀጥሎ አቡነ ዘበሰማያት፣ ጸሎተ እግዝእትነ ማርያምን፣ ጸሎተ ሃይማኖትን ከጸለይን በኋላ አቡነ ዘበሰማያት መድገም፤ ከዚያ 41 ጊዜ ኪርያላይሶን ይባላል፡፡ ሌላው በሱባዔ ጊዜ ከተሓራሚ የሚጠበቀው ነገር ኃጢኣቱን እያሰበ ማዘን ማልቀስ ነው፡፡ ሲያለቅስም ለእያንዳንዱ በደል እንባ ማፍሰስ ያስፈልጋል፡፡
በመጨረሻም ሱባዔ የገባ ሰው ሱባዔውን ሳይጨርስ ወይም ሱባዔውን አቋርጦ ከማንም ሰው ጋር ፈጽሞ መገናኘት የለበትም፡፡
ድኅረ ሱባዔ /ከሱባዔ በኋላ/
ለቀረበ ተማኅፅኖ እግዚአብሔር የሚያደርግልንን ነገር መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ እግዚአብሔር ላቀረብንለት ምልጃና ጸሎት እንደ ልባችን መሻት እንደ እርሱ ቸርነት እርሱ በወደደ ጊዜ ያደርግልናል፡፡ ሱባዔ የገባ ሰው ሁሉ ራዕይ ላያይ ይችላል፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር መልስ አሰጣጥ ለማንም ግልጽ አይደለም፡፡
ከሱባዔ በኋላ መጀመሪያ የምናገኘው የኅሊና ሰላምን ነው፡፡ ይህ ትልቅ የአምላክ ስጦታ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ሱባዔ ገብተን ያሰብነውን ካላገኘን ዳግመኛ ተዘጋጅተን እስከ መጨረሻው ሰዓት መማጸን መጽናት ይኖርብናል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወንድም እህቶቻችን ይማሩበት ዘንድ አጋሩ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሙሉው መዝሙር እንዲለቀቅላችሁ ከፈለጋችሁ።
በኮመንት
ሙሉውን ይለቀቅልን
ምኩራብ (የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት)
#ምኩራብ ማለት፦ ቤተ-ጸሎት ሲሆን፤ ኢየሱስ በሰንበት ቀን ከአይሁድ ምኩራብ ገብቶ ምኩራቡን ገበያ አድርገው ሲገበያዩበት አገኛቸው።
ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል ያለውን አላነበባችሁምን? ትዕንቢተ ኢሳይያስ ፭፮፥፯ እናንተ ግን ገበያ አደረጋችሁት በማለት በተናቸው እቃውንም ገለባበጠባቸው በሮቹንም፤በጎቹንም በገመድ አየገረፈ አባረራቸው። የዮሐንስ ወንጌል ም. ፪፥፩፯ (ማቴዮስ ፪፩፣፩፫) ደቀ መዛሙርቱም የቤትሕ ቅንዓት በላኝ ተብሎ የተጻፈው ለካ ኣሁን ተፈጸመ
ብለው አስተዋሉ። መዝ. ዳዊት ፮፰፤፱
✙ የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)
ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት አነ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያው ኢትግበሩ ቤተ አቡየ ቤተ ምስያጥ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ ቦአ ምኩራቦሙ ወገሠፆሙ ያርምሙ አንከሩ ምህሮቶ ሞገስ ቃሉ ወጣዕመ ነገሩ ወሣዕሣዓ አፉሁ፡፡
ትርጉም:- ጌታችን ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ፤ የሃይማኖት ቃልን አስተማረ፤ ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ፤የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባቷም እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም የሰንበት ጌታዋ ነው፡፡ ያባቴን ቤት የንግድ ቦታ አታድርጉት፤ ቤቴስ የጸሎት ቤት ይባላል (እያለ የሃይማኖትን ቃል አስተማራቸው) ፤ ወደ ምኩራባቸውም ገብቶ ዝም ይሉ ዘንድ ገሠፃቸው፤ እነርሱም ትምህርቱን፣ የቃሉን ግርማ፣ የአነጋገሩን ጣዕምና፣ የአንደበቱን ቅልጥፍና አደነቁ።
✙ ምንባባት መልዕክታት
(ቆላ. 2÷16-ፍጻ.) እንግዲህ በመብልም ቢሆን÷ በመጠጥም ቢሆን÷ በልዩ ልዩ
በዓላትም ቢሆን÷ በመባቻም ቢሆን÷ በሰንበትም ቢሆን የሚነቅፋችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፡፡
(ያዕ.5÷14) ወንድሞቻችን ሆይ÷ እምነት አለኝ፤ ምግባር ግን የለኝም የሚል ሰው ቢኖር÷ ምን ይጠቅመዋል?
በውኑ እምነቱ ልታድነው ትችላለችን? ከወንድሞቻችን÷ ወይም ከእኅቶቻችን÷ የታረዙ ወይም የዕለት ምግብ ያጡ ቢኖሩ÷ ከእናንተም አንዱ .......
ግብረ ሐዋርያት (የሐዋ.10÷1-8.) በቂሳርያም ቆርኔሌዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ ኢጣሊቄ ለሚሉት ጭፍራም የመቶ አለቃ ነበር፡፡ እርሱም ጻድቅና ከነቤተሰቡ እግዚአብሔርን የሚፈራ ነበር፤ ለሕዝቡም ብዙ ምጽዋት ይሰጥ ነበር፤ ዘወትርም ወደ እግዚአብሔር ይጸልይ ነበር፡፡
✙ ምስባክ:- መዝ 68፡9
እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ
ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ
ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ፡፡
ትርጉም፦ የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና
ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት፡፡
✙ ወንጌል
• ዮሐ. 2÷12-ፍጻ. ከዚህም በኋላ እርሱና እናቱ÷ ወንድሞቹና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ቅፍርናሆም ወረዱ፤ በዚያም ብዙ ያይደለ ጥቂት ቀን ተቀመጡ፡፡ ........
✙ ቅዳሴ: - ቅዳሴ ዘእግዚእ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️