ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
24 октября 2024 05:00
ፍቅርህ ማረከኝ
ፍቅርህ ማረከኝ በሕይወቴ በዘመኔ/2/
እግዚአብሔር ለእኔ መድሃኒቴ
ፍቅርህ ማረከኝ በህይወቴ በዘመኔ/2/
አዝ
ተገዝቻለሁ በወርቅ ደምህ
ዓለምን ትቼ ላገለግልህ
ሞትህ ህይወቴ ለእኔ ሆኖኛል
በአንተ መከራ ሸክሜ እርቋል
ለክብርህ ቆሜ እዘምራለሁ
እንደ አቅሜ አገንሃለሁ/2/
አዝ
ምድርና ሰማይ እልል ይበሉ
ምስጋና ለአንተ ይድረስ እያሉ
መሳይ የለህም ለቅድስናህ
አቀርባለሁኝ ለአንተ ምስጋና
ጣቴ በገና ይደረድራል
በቀን በሌሊት ያመስግናል/2/
አዝ
ክብርህን አይተው ጠላቶች ፈሩ
ለጌትነትህ ወድቀው ተገዙ
እንዲህ ነህ አምላክ እንዲህ ነህ ጌታ
ሁሉን በፍቅር የምትረታ
በአንተ ተመካሁ በፈጣሪያችን
አዳኝ በሆንከው በንጉሳችን/2/
ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
23 октября 2024 12:01
በዋጋ ገዝተኸኛልና
በዋጋ ገዝተኸኛልና
ስለ እኔ ደም ከፍለሀልና/2/
ልሳኔ ያውጃል ክብርህን
አልረሳም ጌታ ውለታህን/2/
አዝ
ህይወት ሠላምን ትቼ
የማይታይ አይቼ
ላንተ ብሰጥ ጀርባዬን
ልተዋወቅ ጠላቴን
የጠበቀኝ ውጊያ ነው
የተረፈኝ ፀፀት ነው
የሻረልኝ ቁስለቴ
ተሰቅለህ ነው አባቴ
አዝ
እጓዛለሁ በምናብ
ወደ ሠላሜ ወደብ
እጄን በአፌ እጭናለሁ
ዛሬም እፁብ እላለሁ
ለክብርህ መሠለፌ
በለምለሙ ማረፌ
ዋጋ ከፍለህ ነው ጌታ
ያኖርከኝ በፀጥታ
አዝ
ከወሃ ከመንፈስ
ተወልጄ በመቅደስ
ልጅህ ሆንኩኝ ዳግመኛ
የመስቀልህ ምርኮኛ
በአንተ ስለመዳኔ
ምስክርህ ነኝ እኔ
ላይታጠፍ ምላሴ
እቀኛለሁ በነፍሴ
ዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረፃዲቅ
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
23 октября 2024 05:01
ስድቤን አርቀሽ
ስድቤን አርቀሽ ነውሬን ሸፈንሽው
እመ አምላክ በአንቺ መቼም አላፍር
ስምሽን ጠርቼ እጽናናለሁኝ
ሀዘኔን በአንቺ እረሳለሁኝ
አዝ
ነውር አለብኝ ብዙ ስድብ
አንጀት የሚልጥ ልብ የሚያቆስል
ስሜን ለውጠው ቢያንቋሽሹኝ
በሀዘን በለቅሶ ድንግል መጣሁኝ
እንደ ሃና ሆኜ ከቤተ መቅደስ
በመረረ ሐዘን ነው የማለቅስ
ፍረጅልኝና ልመለስ ከቤቴ
ሐዘኔን በደስታ ለውጪው እናቴ
በግራም በቀኝም ጠላት ቢከበኝ
አብዝቼ እጮሃለው እናቴ ስሚኝ
አዝ
መከራው በዝቶ ግራ ገብቶኛል
ድምፅሽን ልስማ ያረጋጋኛል
የሰው ህይወቱ ብርቱ ሰልፍ ነው
ደስታና ሐዘን የማይለየው
በእጃችን ወድቋል ሲሉ ጠላቶቼ
አመለጥኳቸው ስምሽን ጠርቼ
ሰው የዘራውን ያንኑ ያጭዳል
በቆፈረው ጉድጓድ ራሱ ይገባል
እናቴ እመቤቴ ብዬ ስጠራሽ
ከመከራ ሁሉ ታወጪኛለሽ
አዝ
በምርኮ ሳለሁ በሰው ሀገር
ግፍ ውለውብኝ ስኖር በእስር
ምልጃሽ ደርሶልኝ ተፈትቻለሁ
በታምራትሽ እኔ ድኛለሁ
ቃልሽን ሰምቶ ጽንሱ ሰገደ
ብላለች ኤልሳቤጥ ነውሬ ተወገደ
የጌታዬ እናት እኔን አሰበችኝ
ታሪኬን ቀይራ ይኽው ባረከችኝ
የእመቤቴ ከሆንኩ ማን ይቃወመኛል
ወጀቡም ማእበሉም ይታዘዝልኛል
አዝ
ወይን እኮ አልቋል የዶኪማስ ቤት
ድንግል አማልጅው ነይ የእኛ እመቤት
ስምሽ ሲጠራ በየቦታው
ይሞላልና የጎደለው
ግራ የገባው የቸገረው
ድንግልን ይጥራት እንድትረዳው
ሳዝን ስተክዝ የምታጽናና
እናት አለችኝ እርህርህይተ ልቦና
እናቴ እመቤቴ ብዬ ስጠራሽ
ከመከራ ሁሉ ታወጪኛለሽ
ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
22 октября 2024 06:02
ጥቅምት ፲፪ /12/
በዚች ዕለት የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።
በዚችም ቀን ወደ ነቢይ ሳሙኤል እግዚአብሔር ልኮታልና ለእስራኤል ልጆች ዳዊትን እንዲያነግስላቸው ይቀባው ዘንድ አዘዘው። ሳሙኤልም ወደ እሴይ ቤት ሔዶ ልጆችህን ሁሉንም አቅርብልኝ ብለው እሴይም ከዳዊት በቀር ሁሉንም አቀረባቸው እርሱ በእርሻ ውስጥ በጎችን ይጠብቅ ነበርና ።
ሳሙኤልም የመንግሥት ቅባት ያለበትን ብልቃጥ በራሳቸው ላይ ከፍ ከፍ በአደረገ ጊዜ እግዚአብሔር አልመረጣቸውም። ሳሙኤልም እሴይን ልጆችህ እነዚህ ብቻ ናቸውን አለው ዕሴይም በጎች የሚጠብቅ አንድ ትንሽ ልጅ አለ አለው።
ሳሙኤልም ደግሞ ዕሴይን እሱ ሳይመጣ ምሳ አልበላምና ልከህ አስመጣው አለው። እርሱም ልኮ አስመጣው መልኩም ቀይ ዐይኖቹም የተዋቡ አርአያውም ያማረ ነው እግዚአብሔርም ሳሙኤልን ይህ ይበልጣቸዋልና ተነሥተህ ቀባው አለው። በዚያንም ጊዜ ሳሙኤል የመንግሥት ቅባት ያለበትን ቀንድ አምጥቶ በወንድሞቹ መካከል ቀባው ከዚያችም ቀን ጀምሮ ለሁል ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በዳዊት ላይ አደረበት በእስራኤል ልጆችም ላይ ነገሠ።
ደግሞ ሁለተኛ በዚች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ሚካኤልን ወደ ዳዊት ላከው ረዓይታይ ጎልያድን እስኪገድለውና የእስራኤልን ልጆች እስከሚያድናቸው ረድቶ ኃይልን ሰጠው።
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
21 октября 2024 19:22
ጻድቃን በበግ ኃጥአን በፍየል የተመሰሉት ለምንድን ነው?
የበጎች ተፈጥሮ ከጻድቃን፤ የፍየሎች ተፈጥሮ ከኃጥአን ጋር ይመሳሰላሉ፤
ከበጎች መካከል አንዲቱን ተኩላ ቢነጥቃቸው በረው ወደ ዱር ይገባሉ ወደዚያ ቦታ ተመልሰው አይሄዱም። ጻድቃንም ከሰው መካከል አንዱ በሞት ቢነጠቅ ይሄ እጣ ነገ ለእኔም ይደርሳል ብለው ከኃጢአት ርቀው እግዚአብሔርን በንጽሕና ያገለግሉታል እንጂ ዳግም ወደዚያ የኃጢአት ሥራቸው አይመለሱም።
ፍየሎች ግን ከመካከላቸው አንዲቱን ተኩላ ቢነጥቅባቸው ለጊዜው ከዚያ ቦታ ይሸሹና ተመልሰው እዚያው ይገኛሉ፡ ኃጥአንም ከመካከላቸው አንዱ ቢሞት ለጊዜው ደንግጠው ከኃጢአት ቢርቁም ኋላ ወደ ጥፋታቸው ይመለሳለና በፍየል መሰላቸው።
በግ ኃፍረቷን አታሳይም፡ በላቷ ትሸፍነዋለች። ጻድቃንም ኃጢአት ቢሠሩ እንኳ ኃጢአታቸውን በንስሐ ይሸፍናሉ።
ፍየል ኃፍረቷ የተገለጠ ነው፤ ላቷም የተሰቀለ ነው ኃጥአንም ኃጢአት በሠሩ ጊዜ በንስሐ እናጥፋው አይሉም፣ እንዲያውም ኃጢአታቸው በሰው ሁሉ ፊት የተገለጠ ነው።
በግ ያለችበት፤ የዋለችበት ቦታ አይታወቅም ጻድቃንም በትሕትናቸው፣ በዝምታቸው ያሉበት ቦታ አይታወቅም።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :-ትምህርተ ሃይማኖት
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
21 октября 2024 06:00
ጥቅምት ፲፩ /11/
በዚችም ቀን ገድለኛዋ ቅድስት ጲላግያ አረፈች።
ይቺም ከአንጾኪያ አገር የሆነች ናት፤ ወላጆቿም ከሀድያን ናቸው እርሷም አስቀድማ ከረከሰ ሃይማኖቷ ጋር በረከሰ ሥራ ጸንታ መኖርን ገንዘብ አደረገች። እርሷም በመሸታ በጨዋታ ቤት በመዋል ስትሣለቅና ስታመነዝር ስትዘፍንም ትኖራለች ።
በአንዲት ቀንም የገሀነም እሳትና የዘላለም ሥቃይ እንደሚጠብቃቸው እያሳሰበ ዝንጉዎችንና አመንዝራዎችን ሲገሥጻቸው ኤጲስቆጶስ ጳውሎስን ሰማችው ምክሩም በልቧ አደረ። ከዚህም በኋላ ወደርሱ ሒዳ የሠራችውን ሁሉ ተናዘዘች እርሱም አጽናንቶ የቀናች ሃይማኖትን አስተማራትና አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃት።
በቀደመው ሥራዋም እየተጸጸተች በጾም በጸሎት በስግደት ሰውነቷን ማድከም ጀመረች ከዚህም በኋላ የወንድ ልብስ ለብሳ ወደ ኢየሩሳሌም ሒዳ በከበሩ ቦታዎች ሁሉ ሰግዳ ሁሉንም ቦታዎች ተሳለመች ወደ ኢየሩሳሌሙ ሊቀ ጳጳሳትም ተመለሰች። እርሱም ከኢየሩሳሌም ከተማ ውጭ ከደናግል ገዳማት ወደ አንዱ ላካት የምንኵስናንም ልብስ ለብሳ በጽኑዕ ገድልም ተጠምዳ ሠላሳ ዓመት ያህል ኖረች እግዚአብሔርንም አገልግላ በሰላም አረፈች።
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
20 октября 2024 12:00
እንዴት ልደብቀው
እንዴት ልደብቀው ጌታዬ አንተ ያረክልኝ
ቤቴ እንጀራ ባይኖር ሸሽገህ የምታጎርሰኝን
ባለቅስ እንኳን እንባ ባፈስ ዛሬ ፊትህ ቆሜ
የሃዘን አይደል የደስታ ነው ተሳክቶልኝ ህልሜ
አዝ
ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች ደግሞም ትሁን በምድር
የዕለት እንጀራዬን አትንፈገኝ መጋቢዬ እግዚአብሔር
በከንቱ ነው የምጨነቀው
መሆኑ አይቀር ጌታዬ ያልከው
የሰማዩን ስሻ መንግስቱን
ይጨመራል የምድሩ ነገር
አዝ
በለስ ባታፈራ ዘይት ባይኖር
ከጎጆዬ አንዳች ነገር
ኤልሻዳዩ ጌታ ሁሉ ያለህ
አንተ አለህኝ አልቸገር
አባክኜ ያላዘንክብኝ
በጥፋቴ ያልጨከንክብኝ
ከእኔ በላይ የምታስብ ለእኔ
ምን አጉድለህ ያማሃል ልሳኔ
አዝ
ማጎንበስ ማንባቴን ማቀርቀሬን
ዝቅ ብዬ መራመዴን
ከሰው ጋር እየዋልኩ ሰው አላየው
የተጎዳው ስሱን ልቤን
ከላይ ሆነህ የምትመለከት
የማትረሳ የእጅህን ፍጥረት
ያልተለየህ ያራክ ከነፍሴ
አንተ አየህኝ ሳትንቀኝ ሥላሴ
አዝ
አንገቴን ደፍቼ በእግሬ መኃል
ሳለቅስብህ እንደ ሕፃን
ከእኔ ጋር ሆነህ አጠገቤ
በእኔ ሐዘን አንተ አዝነሃል
መቼ ይሆን መቼ ነው ስልህ
ለእንባዬ ጌታዬ መልስህ
በማለዳ ልከህ መልዕክተኛ
አዘመርከኝ ሆንክልኝ መፅናኛ
ዘማሪት ጽጌ ማርያም 💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
20 октября 2024 04:57
የማርያም ነህ ይሉኛል
ልቡ ያዘነ እና የተከዘ
ይፅናናል ይለብሳል በአንቺ የታረዘ
ስምሽን ጠርቼ መቼ አፍራለሁ
እመ አምላክ ብዬ እጣራለሁ
ኪዳነ ምሕረት እልሻለሁ
አዝ
ወዳጅ መስሎ ነው ያጠቃኝ
ከሲኦል ረግረግ የጣለኝ
በስጋ ከይሲ ተሰውሮ
አበካከነኝ ልቤን ሰብሮ
የጠገነልኝ ስብራቴን
ከሩቅ አየሁት መድኃኒቴን
የወደለችው ቤተልሔም
ተኝቶ አየሁት ከግርግም (2)
አዝ
ሰባስምንት ነፍስ የበላው
ስምሽን ሰምቶ ነው የዳነው
ጥላሽ ቢያጠላ ከሚዛኑ
መዳን ሆነለት ሆና ቀኑ
በደቀ መዝሙር ስም ያጠጣ
ያገኛል ክብር ጌታ ሲመጣ
በእናታችን ስም የዘከረ
በሰማይ ሆኗል የከበረ (2)
አዝ
በማጣቴ እና በስደቴ
አንቺው ግቢበት በህይወቴ
እየጠራሁት ስምሽን
ሞትን ተሻገርኩ መከራን
እሱ የማሪያም ነው ይሉኛል
ማን ነገራቸው አዉቀዉኛል
እናቱ ማሪያም የእግዚአብሔር
መታወቂያዬ የእኔ ክብር (2)
ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ 💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
19 октября 2024 12:25
እኔ አንተ ፊት
እኔ አንተ ቤት እኔ አንተ ፊት
የምቆም ሰው አይደለሁም
ግን ፍቅር ነህ ለዘለዓለም
የሚመስልህ ማንም የለም (2x)
አዝ
ጸሎቴ ቢሆን ለወረት
ጎዶሎ ቢሆን የኔ እምነት
ባረከኝ እኔን ከሰማይ
በደል ጥፋቴንም ሳታይ
ቀባኸኝ ጠርተኸኝ ከዱር
ሰጠኸኝ ከፍ ያለ ወንበር
ሳይኖረኝ አንድም በጎነት
ባረከኝ በእጅህ በረከት
አዝ
ቃልኪዳንህን አክባሪ
ታማኝ ነህ ሁሌም መሀሪ
የማልከውንም መሀላ
አትረሳም አትልም ችላ
መካሪ ድንቅ መምህሬ
ላንተ ነው ዜማ መዝሙሬ
ፍቅር ነህ ከአባትም በላይ
የሰማይ የምድር ሲሳይ
አዝ
ቃልኪዳንህን አክባሪ
ታማኝ ነህ ሁሌም መሀሪ
የማልከውንም መሀላ
አትረሳም አትልም ችላ
መካሪ ድንቅ መምህሬ
ላንተ ነው ዜማ መዝሙሬ
ፍቅር ነህ ከአባትም በላይ
የሰማይ የምድር ሲሳይ
አዝ
መሻቴን ብቻ ስላየህ
ደካማ ልጅክን ጎበኘህ
ብቃቴ መቼ ሆነና
ያቆመኝ ላንተ ምስጋና
አንኳኩ ስላልክ አንኳኳው
ጠይቁ ስላልክ ጠይኩህ
ከፍተሀል በርህን ለኔ
የታተምኩብህ መድህኔ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
19 октября 2024 04:57
በምን ደስ ላሰኝህ ጌታዬ ሆይ
በምን ደስ ላሰኝህ ጌታዬ ሆይ
በምን ደስ ላሰኝህ አምላኬ ሆይ
አለምና መላው ያንተው አይደለም ወይ
የፈጠርከው ሁሉ ያንተው አይደለም ወይ
አዝ
ኪሩቤል ሱራፌል ቅዱስ ሥሉስ ያሉህ
መላዕክት በራማ የሚያመሰኑህ
ድንቅ መካር ኃያል ኤልሻዳይ ነህና
ትንቢያ ነኝ ምን ልስጥህ ምንስ አለኝና/2/
አዝ
ቅዱሱን መስዋዕት ልዑል ስለሚወድ
ምን ይዤ ልምጣና በአምላኬ ፊት ልስገድ
ወደ ላይ በሰማይ ወደ ታች በጥልቀት
አምላኬ የት አለ የማትገኝበት
ጌታ ሆይ የት አለ የማትገኝበት
አዝ
በኪዳን በፀሎት ቅዳሴ ሰዓታት
አንተ የሰጠኸኝ የመንፈስ ቅዱስ ሀብት
መልሰን ወደ አንተ ብንሰጥ ምን አለ
ተወው ጉዳችንን ስስታችን ይኸው(2)
አዝ
ሀብትና ንብረቴስ ጉልበቴስ ምንድነው
ጤናዬ የሰጠኝ ከአንተ በቀር ማነው
በሰጠኸኝ እድሜ በሕይወት ዘመኔ
ከገላዬስ ቢሆን የትኛው ነው የኔ
ከአካላቴስ ቢሆን የትኛው ነው የኔ
ዘማሪ ዳግማዊ ደርቤ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
18 октября 2024 11:56
የማትረግፍ አበባ
የማትረግፍ አበባ የማትጠወልግ ዘወትር የምታብብ
መአዛ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ናት መድኃኒተ ሕዝብ
አዝ
የሲና ሐመልማል እሳት የተስማማት
መቃጠልን የማታውቅ የመለኮት ሌማት
የእርሷ ድንግልና ዘለዓለማዊ ነው
የማትረግፍ ሲላት ያሬድን አየነው
አዝ
ተቀጥፋ የቆየች የአቤሜሌክ ቅጠል
ስልሳ ስድስት ዓመት ደርቃ ሳትቃጠል
መስጠት ያላቆመች የልምላሜዋን ጠል
ፍሬዋ ክርስቶስ አበባ ናት ድንግል
አዝ
ከአሮን በትር ላይ አብባ የተገኘች
የደረቀን ዓለም ማለምለም ታውቃለች
አባ ጊዮርጊስም አላት ፈርከሊሳ
እዳትረሳ ኃጢያቱን ድል እንድትነሳ
አዝ
የምታሳሳ ናት ውብ ናት እንደ አበባ
በምልጃዋ የአመነ ስንቱ ገነት ገባ
አባ ጽጌ ድንግል ማበቧን ያወቀው
ማህሌቷን ታጥቆ ተመስጦ ነጠቀው
አዝ
በጽጌ ማህሌት ንኢ ንኢ እያልን
እኛም ከሊቁ ጋር እንጠራታለን
አበባ ነፍሳችን ጠውልጋ እንዳትረግፍ
የምልጃዋ ጥላ በእኛ ላይ ይረፍ
ሊቀ መዘምራን ቀሲስ ግርማ 💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
18 октября 2024 05:01
እንዘ ትሐቅፊዮ
እንዘ ትሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ንኢ ማርያም(2)
ንኢ(3)ማርያም (2)
አዝ
የዋኖስ እናት ነሽ የእርግብ ወላዲቱ
ንኢ ሰናይትዬ ንኢ ናዛዚቱ
የእምነታችን ሙዳይ መንበር ለመስዋዕቱ
አዝ
ገብርኤልም ይምጣ የደስታው አብሳሪ
ነይ ከሚካኤል ጋር ጨለማውን አብሪ
የሕግ ታቦት ሆይ በእኛ መሃል ኑሪ
አዝ
ነጭ እና ቀይ ነው የአንቺ ፅጌሬዳ
የተዋህዶ አክሊል መለኮት ፀአዳ
በቀይ ስጋ ደሙ አራቀን ከፍዳ
አዝ
በሰቆቃው ሐዘን በማህሌት ደስታ
በአንድ የሚሰማብሽ ለቅሶ እና እልልታ
የፅጌ ምስጢር ነሽ የእጣኑ ሽታ
ዘማሪት ትዕግስት 💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
17 октября 2024 06:00
ጥቅምት ፯ /7/
በዚች ዕለት ጠመው ከሚባል አገር የሆነ የከበረ አባት አባ ባውላ አረፈ።
ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ መስተጋድል መነኲሴ ሆነ የሚኖረውም በላይኛው ግብጽ ባለ በእንጽና ገዳም ነው ስሙ ሕዝቅኤል የሚባል ረድእ አለው። እርሱም ስለ ትሩፋቱና ስለ ተጋድሎው ምስክር ሆነ ይህ አባ ባውላ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ራሱን ሰባት ጊዜ ገድሏልና።
ክብር ይግባውና ጌታችንም አስነሣው እንዲህም ብሎ አጽናናው ወዳጄ ባውላ ሆይ ራስህን ሰባት ጊዜ እስከምትገድል ድረስ ሰውነትህን አደከምክ እንግዲህ ድካምህ ይብቃህ።
አባ ባውላም ለመድኃኒታችን እንዲህ ብሎ መለሰለት ጌታዬ ሆይ ስለ ከበረው ስምህ እደክም ዘንድ ተወኝ አንተ አምላክ ስትሆን ስለኛ በመከራ ደክመህ ስለ ሰው ወገን ሞትክ ለእኛ ይህ አይገባንም ነበር በቸርነትህ ይህን የማዳንህን ሥራ ሠራህልን እንጂ። ጌታችንም ከአጽናናው በኋላ ከእርሱ ወደ ሰማይ ወጣ።
ከዚህም በኋላ አባ ብሶይ ወደ እንጽና ገዳም ሒዶ ከአባ ባውላ ጋር ተገናኘ ጌታችንም ለአባ ባውላ ተገልጾለት ሥጋህ ከአባ ብሶይ ሥጋ ጋር በአንድነት ይኑር አለው ሁለቱም በአረፉ ጊዜ ሥጋቸውን በአንድነት አኖሩ።
ወገኖቹም የአባ ብሶይን ሥጋ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሊወስዱ በወደዱ ጊዜ በመርከብ ጫኑት መርከቢቱ ግን መንቀሳቀስን እምቢ አለች። ከዚህም በኋላ ተመልሰው የአባ ባውላን ሥጋ አምጥተው በመርከብ ላይ ጫኑት ያን ጊዜ መርከቢቱ ተጓዘች። እንዲህም የቅዱሳኑን ሥጋቸውን ወደ አስቄጥስ ገዳም አድርሰው በአባ ብሶይ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአንድነት አኖሩ እስከ ዛሬም በዚያ ይኖራሉ።
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር 💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
16 октября 2024 19:32
አቡዬና አንበሳ
ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዜግነት ግብፃዊ ናቸው። በተጋድሎ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ቁጥራቸው ከባሕታዊያን እንደመሆኑና ተጋድሎአቸው በኢትዮጵያ እንደመሆኑ ግብፃውያን ጨርሶ አያውቁአቸውም። ስለ እርሳቸው ቅድስናም የሚሰሙት ከእኛ አንደበት ነው።
በአንጻሩ እኛም ስለ ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ሙሴ ጸሊም የምንሰማው ከግብፃውያኑ አንደበት ነው። በእነርሱ አንደበት ኢትዮጵያዊው ሲባል ብንሰማም እኛ ግን በለመድንበት ጥቁሩ ሙሴ ብለን መጥራት ይቀናናል እንጂ ኢትዮጵያዊነቱን ብዙም አጉልተን አናነሳም። በዛሬይቱ ኤርትራ ሐማሴን የተወለደው ቅዱስ አብደል መሲህ አል ሐበሺንም እንዲሁ ግብፃውያን የሚያከብሩትን ያህል በኤርትራውያንና በኢትዮጵያውያን እምብዛም አይታወቅም። ቅዱሳኑ የዚህ ዓለም ስደተኞች መሆናቸውን ስለሚያስተውሉ መነኩሴ ሀገር የለውም ብለው የሔዱበት ሀገር አድርገው ይኖራሉ።
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዙሪያቸውን በአንበሳ እና በነብር ተከብበው የሚሔዱ አባት ነበሩ። አቡነ አረጋዊን ደግሞ ከዘንዶ ጋር እናያቸዋለን። ይህ ነገር ምንድን ነው? ቅዱሳኑ ከአራዊት ጋር ምን አላቸው?
ነገሩ ወዲህ ነው ሰው በጥንተ ተፈጥሮ በቅድስና ይኖር በነበረበት በአዳምና ሔዋን ዘመን ከአራዊት ጋር ሰላም ነበረ። አራዊትን ሳይቀር ያዝዛቸው ያነጋግራቸው ነበረ። ሔዋን ከዕባብ ጋር በተነጋገረች ጊዜ ዕባብ አፍ አውጥቶ መናገሩ ብርቅ ያልሆነባት ለዚህ ነው:: ሰው ከእግዚአብሔር ሲጣላ ግን የሚፈሩትንና የሚታዘዙለት አራዊት መፍራት ጀመረ።
በሐዲስ ኪዳን የሰውን ክብር ወደ ቀድሞ ሥፍራው የመለሰው ሁለተኛው አዳም መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ግን "በምድረ በዳም ከሰይጣን እየተፈተነ አርባ ቀን ሰነበተ ከአራዊትም ጋር ነበረ'' ማር10:13
እኔ ክርስቶስን እመስላለሁ ያለው ጳውሎስም የበረሃ ዕባብ ስትነድፈው ትንኝ እንደነካችው ያህል ምንም ሳይሆን ወደ እሳት አራግፎአት ቁጭ ብሎአል። በዙሪያው የነበሩ አሕዛብ ከባሕር አደጋ ተርፎ በዕባብ መነደፉን አይተው "ይኼስ ነፍሰ ገዳይ ነው ከባሕር ስንኳ በደህና ቢወጣ እግዚአብሔር በሕይወት ይኖር ዘንድ አልተወውም'' ብለው ከፈረዱበት በኁዋላ ተነድፎ ምንም እንዳልሆነ ሲያዩ ይህስ አምላክ ነው እስከማለት ደርሰው ነበር። ሐዋ 28:6
ወደ ጥንተ ተፈጥሮ አዳማዊ ቅድስናህ ስትመለስ አራዊት ይገዙልሃል። ክርስቶስን ስትመስል እንደ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንበሳ እና ነብር ይሰግዱልሃል።
አንበሳና ነብር ባታገኝ አውሬው ምላስህ አራዊት ምኞቶችህ ይታዘዙልሃል። ቅዱስ ላሊበላ በአት ላንጽልዎ እያለ እየተማጸናቸው እንቢ ብለዉ የዝቋላን በረሃ የመረጡት መናኝ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወደ ጥንተ ተፈጥሮ ቅድስና ተመልሰው ከውድቀት ወዲህ የመጣውን የቆዳና የቅጠል ልብስ ሳይሹ በጸጋ እግዚአብሔር በብሩህ ጠጉር ተሸፍነው ለሀገራችን ጸልየዋል። ጻድቁ አባታችን አራዊትን በገሰፁበት ጸሎት ዛሬም በሀገራችን የተሰማራውን የጥላቻና የመለያየት አራዊታዊ ጠባይ ይገሥጹልን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- የግዮን ወንዝ
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
16 октября 2024 11:56
በዙሪያችን ካሉ
በዙሪያችን ካሉ ድንቅ ምስክሮች
በእምነት በምግባር ከፀኑት እናቶች
ከፍ ብላ ታየች በገድሏ ብዛት
ንዕድ ክብርት ነች አርሴማ ቅድስት
ንዕድ ክብርት ነች አርሴማ ሰማዕት
አዝ
ሀብት እና ንብረቷን ውበቷን የናቀች
ንግሥት መባልን በእምነት የተወች
የኢየሱስ ክርስቶስ የስሙ ምስክር
የቅድስት አርሴማ እፁብ ነው የእርሷ ክብር (2)
አዝ
እግዚአብሔር ፅናቷን የመሰከረላት
በቤቱ በቅፅሩ መታሰቢያ አላት
የወንጌሉን ብርሃን ለዓለም ያበራች
ሰማዕቷ አርሴማ ለእኛም አማላጅ ነች(2)
አዝ
ይሄው በዚህ ዘመን እግዚአብሔር ገለፃት
ለረድኤት በረከት ምክንያት አደረጋት
አክሊል ተጎናፅፋ ታይታለች በክብር
ዛሬም ለልጆቿ በረከቷ ይደር
ዛሬም በልጆቿ በረከቷ ይደር
አዝ
እንደተናገረው ጌታችን በቃሉ
በእኔ የሚያምኑ ድንቅን ይሰራሉ
ደዌ እንዲርቅለት ፈውስን የተጠማ
ከደጇ ላይ ይውደቅ ይበላት አርሴማ (2)
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
23 октября 2024 19:39
ሕልመ ሌሊት (Nocturnal Emission)
ሕልመ ሌሊት (Nocturnal Emission) በሌላ አጠራር ርጥብ ሕልም (wet dream) እየተባለ የሚጠራ ሲኾን በእንቅልፍ ጊዜ ከወንዶች አባለ ዘር የሚወጣን የዘር ፈሳሽን የሚያመለክት ነው፡፡ በመጀመሪያ ማወቅ ያለብን መሠረታዊ ነገር ይህ ሁኔታ በራሱ ተፈጥሯዊ ወደ መሆን ስለ መጣ በቀጥታ ኃጢአት ነው ሊባል የማይችል መሆኑን ነው፡፡
ይህን በተመለከተ ቅዱስ አትናቴዎስ "ምን ዓይነት ኃጢአት ወይም ክፋት ነው ከተፈጥሮ የሚመነጨው? ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሔር ከኾነ፥ እንዴት መልካም የኾነው ፈጣሪ ርኵስ የኾነ ነገር ሊያመጣ ይችላል? ኾኖም ኃጢአትን ስናደርግ ያንጊዜ እንረሳለን ይላል። ይህ ማለት ከወንድ በሕልም ምክንያትነት የሚወጣው ዘር በራሱ በተፈጥሯዊ ሂደቱ ብቻ ከታየ ርኵስ ሊባል የማይችል መኾኑን ነው፡፡ ይህን ሰውየው ፈቅዶ ያመጣው ሳይኾን በተፈጥሮ እንዲያይ ስለ ኾነ እንጂ።
አንድ ሰው በንቁ ልቡና ሳለ ወደ ኃጢዓት የሚያመሩትን ነገሮች ተግቶ እየተቃወመ ነገር ግን በተኛበት ባንቀላፋ ጊዜ ዝንየት (ሕልመ ሌሊት) ቢያገኘው በተራክቦ፣ ዘር በማፍሰስ ያያት ሕልሙ ዕዳ ኾና አትቆጠርበትም፡፡ መሐሪ የኾነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውየው ተቃወማት እንጂ ወዶ ወደ እርሷ እንዳልተሳበ ያውቃልና፡፡ አንቀላፍቶ ሳለ ዘሩ ቢወርድ ፈልጎ አላመጣውምና ዕዳ አይኾንበትም።
ሕልመ ሌሊት ኃጢአት አይደለም ማለት ግን በተፈጥሯዊ ኹኔታው ብቻ እንጂ በእኛ ችግር ወይም ድክመት ምክንያት የሚከሰተው ኹሉ ችግር የለውም ማለት አለመኾኑን ልብ ይሏል፡፡ ሕልመ ሌሊት በተደጋጋሚ እንዲከሰት የሚያደርግ፣ በሕልመ ሌሊት በሚመታበት ጊዜ ለዚያ ምላሽ (Reaction) የሚያደርግ ከሆነ፣ ደስ የሚለውና ነገም ቢመጣ እያለ የሚመኝ ከሆነ እንቅልፍን ሰበብ አድርጎ ዝሙትን ሽቷል ማለት ነው፡፡ ያኔም ሕልመ ሌሊት ወደ ኃጢአት እንዲቀየር ይሆናል፡፡ ክፉ እያደረጎ ወደ እውናዊ የዝሙት ትግበራ ሊያመጣን ይችላል። ስለሆነም የሕልመ ሌሊት መፍትሔው ከመተኛታችን በፊት በምንተኛበትን አልጋ ላይ መጸለይ፤ የመስቀል ምልክት እያደረግን እግዚአብሔር ከክፉ ሕልም እንዲጠብቀን መማጸን፤ እንቅልፍ እስኪወስደን ድረስ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ያለ ማቋረጥ መጥራት ያስፈልጋል።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :-መጽሔተ ወራዙት ዘኦርቶዶክስ
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
23 октября 2024 06:00
ጥቅምት ፲፫/13/
በዚችም ቀን ደግሞ የመነኰስ ዘካርያስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ። የዚህም መስተጋድል የአባቱ ስም አቃርዮስ ነው። ይህም አቃርዮስ ምንኩስናን ሽቶ ሚስቱን አስፈቅዶ ሁለት ልጆቹን ትቶ በገዳመ አስቄጥስ መነኰሰ።
ከጥቂት ወራትም በኋላ በሀገር ውስጥ ረኃብ ሆነ ሚስቱም ልጆቿን ይዛ ወደ አስቄጥስ ገዳም ወደባሏ መጣች የሆነውን ችግር ነገረችው አቃርዮስም እነሆ እግዚአብሔር በመካከላችን ፍርድን አድርጎ ልጆቻችንን አካፈለን እኔም ወንዱን ልጄን እወስዳለሁ አንቺም ሴት ልጅሽን ውሰጂ አላት ይህንንም ብሎ ልጁን ዘካርያስን ወሰደ። ዘካርያስም በበጎ ሥራ በገዳም ውስጥ አደገ። መነኰሳትም ከመልኩ ማማር የተነሳ በመነኰሳት መካከል እንዴት ይኖራል ተባባሉ።
ዘካርያስም መነኰሳት ስለእርሱ እንዳንጐራጐሩ በሰማ ጊዜ ናጥራን ወደሚባል ተራራ ስር ወደአለች ዐዘቅት ሔደ ልብሱንም አውልቆ በረግረግ ውስጥ ተኛ ሥጋውም ተነፋፍቶ ጠቆረ ተመላልጦም ቆሰለ ብዙ ዘመንም በደዌ እንደኖረ ሆነ ከዚህም በኋላ ወደ ገዳም መጣ ያወቀውም የለም። ከብዙ ቀኖችም በኋላ አባቱ አስተውሎ ልጁ ዘካርያስ እንደ ሆነ አወቀውና መልክህን የለወጠው ምንድን ነው ብሎ ጠየቀው እርሱም ያደረገውን ሁሉ ነገረው።
አንድ ቀንም እግዚአብሔር ሥራውን ለአባ ኤስድሮስ ገለጸለት እርሱም ለመነኰሳት ነገራቸው። እነርሱም አስቀድሞ እንደ ሰው ሁነህ መጣህ ዛሬ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ሁነህ መጣህ አሉት። አባቱም ስለእርሱ እኔ በገድል ብዙ ደክሜአለሁ ነገር ግን ከልጄ ሥርዓተ ገድል አልደረስኩም ብሎ ተናገረ። በዚህ ተጋድሎውም ፵፭ (45) ዓመት እግዚአብሔርን አገልግሎ በ፶፪ (52) ዓመቱ አረፈ።
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን !ወስብሐት ለእግዚአብሔር💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
22 октября 2024 11:59
የእግዚአብሔር መልአክ
የእግዚአብሔር መልአክ ስሙ ድንቅ ነው
ለጶርዓ ሰው ለማኑሄ እንደነገረው
በመሰዊያው ነበልባል ውስጥ ዐረገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ(2)
አዝ
ከዳን ወገን የሆነ
በእግዚአብሔር ያመነ
ማኑሄ የሚባል ሰው
የጌታ መልአክ ታየው
ሚስቱ መካን ነበረች
ልጅንም ያልወለደች
ሚካኤል ተገልጦላት
በዘር ፍሬ ባረካት
የእግዚአብሔር መልአክ ስሙ ድንቅ ነው
በኦፍራ አድባር ለጌድዮን የተገለጠው
እስራኤልን ከመድያም እጅ ታደገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ(2)
አንተ ጵኑ ኃያል ሰው
እግዚአብሄር ከአንተ ጋር ነው
ክንድህን ላበረታ
ተልኬያለሁ ከጌታ
ዓይዞህ ጌዴዎን ያለው
ቁርባኑን ያሻተተው
ከእኛ ጋር ነው ሚካኤል
ሰልፋችንን ይመራል
የእግዚአብሔር መልአክ ስሙ ድንቅ ነው
በኦርን አውድማ ሰይፍን ቆሞ የታየው
ዳዊት በመንቀጥቀጥ ፊቱን ፈለገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ(2)
በሶስት ቀን ችነፈር
እንዳትጠፋ ምድር
ሰባ ሺህ ሰዎች ወድቀው
መልአኩን በቃህ አለው
ለምህረት ይመጣሉ
ለመአት ይላካሉ
ሰይፉን በአፎቱ ከቷል
ሚካኤል ለህዝቡ ቆሟል
የእግዚአብሔር መልአክ ስሙ ድንቅ ነው
ስምዖን ጴጥሮስን ከወህይኒ ቤት ገብቶ ያወጣው
የእጆቹን ሰንሰለት ፈቶ አረገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ(2)
በጠባቂዎች መሃል
ኬፋን ከእንቅልፍ አንቅቷል
የተዘጋውን ደጃፍ
አልተሳነውም ማለፍ
ሚካኤል እየመራው
ጴጥሮስ እግሩ የቀናው
አውቆታል ልቡ በርቶ
ዘለለ ስሙን ጠርቶ
ዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረፃዲቅ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
22 октября 2024 05:00
ቅዱስ ሚካኤል
ቅዱስ ሚካኤል ወዳጅ ነህ ለሁሉ
ዛሬም ቆመሀል በኪዳንህ ላሉ
አዝ
ክንፍህን ዘርጋ ሚካኤል ቅደም ከፊቴ
ምራኝ መንገዱን እንዳይመሽ ልድረስ ከአባቴ
እንዴት ይገፋል ጎዳናው ያላንተ እርዳታ
ጥሜን ቁረጠው በትርህ ጭንጫውን ምታ
አዝ
ተጠመጠመ ጠላቴ በእሳት ሰንሰለት
የጌታ መልአክ ሚካኤል በሰይፍ ወድቆበት
የለም በቦታው ስመለስ አጥቼዋለሁ
የሚረዳኝን ተሹሞ አይቼዋለሁ
አዝ
ከመቃብሩ ድንጋዩን አንከባለሃል
ስለረዳኸው ዳንኤል እጅግ ወዶሃል
ይነዋወጻል ባሕሩም አንተ ስትመጣ
እግዚአብሔር ይንገስ ዲያብሎስ መድረሻ ይጣ
አዝ
አለኝ ትዝታ በቤትህ ከልጅነቴ
ስትሳሳልኝ እያየሁ ፀንቷል ጉልበቴ
ልዘምር እንጂ ላመስግን ታላቁን ጌታ
አንተን የሰጠኝ ጠባቂ በቀን በማታ
ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
21 октября 2024 11:59
አንደበቴም ያውጣ
አንደበቴም ያውጣ የምስጋና ቅኔ
የአምላኬን ማዳን አይቻለሁ በዓይኔ
በገባዖን ሰማይ ፀሐይን ያቆመ
ዛሬም ጎብኝቶኛል እየደጋገመ
አዝ
ወጥመድ ተሰበረ እኔም አመለጥኩኝ
ከኃጢያት ፍላፃ ከሞት አተረፈኝ
የአናብስቱን አፍ በኃይሉ የዘጋ
የዳንኤል አምላክ ይኖራል ከእኛጋ
አዝ
በዳዊት ምስጋና በያሬድ ዝማሬ
ከቅዱሳን ጋር ስዘምር አብሬ
እርሱን ሳመሰግን ሜልኮል ብትስቅብኝ
ለጌታዬ ክብር እዘምራለሁኝ
አዝ
አስፈሪው ነበልባል እሳቱ ቢነድም
ለጣኦት እንድሰግድ ነገስታት ቢያውጁም
ሁሉም ቢተወኝም ቢጠላኝም ዓለም
ፅናት ይሆነኛል ጌታ መድሃኔዓለም
አዝ
ወጥመድ ተሰበረ እኔም አመለጥኩኝ
ከኃጢያት ፍላፃ ከሞት አተረፈኝ
የአናብስቱን አፍ በኃይሉ የዘጋ
የዳንኤል አምላክ ይኖራል ከእኛጋ
ዘማሪት ፋንቱ ውልዴ
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
21 октября 2024 05:00
እውነት ነው አዎ እውነት ነው
እውነት ነው አዎ እውነት ነው
መንገድ ነው አዎ መንገድ ነው
ህይወት ነው በእርግጥ ህይወት ነው
ኢየሱስ የጌቶች ጌታ ነው
አዝ
ወደ እግዚአብሔር አብ የምንደርስበት
አንድያ ልጁን የምናምንበት
የህይወት መንገድ እርሱ ብቻ ነው
የባሕርይ አምላክ ብለን ስናምነው
አዝ
በማርያም ስጋ የተገለጠው
ወልድን ስናውቅ ነው አብን ያወቅነው
አብ በእርሱ እንዳለ እርሱም በአብ አለ
በኃይል በሥልጣን የተካከለ
አዝ
ሥጋዉን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ
ህይወት የሰጠን በደልን ክሶ
እኛም ዳሰስነው በላን ጠጣነው
በዝግ ቤት ሳለን ገብቶ ያየነው
አዝ
ፈቅዶ ቢወሰን በአጭር ቁመት
ረቂቁ ቢገዝፍ በጠባብ ደረት
መንሹ በእጁ ነው ሁሉን ያጠራል
በዓለም ሊፈርድ ዳግም ይመጣል
ዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረፃዲቅ
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
20 октября 2024 06:00
ጥቅምት ፲ /10/
በዚህች ቀን የቅዱስ ባኮስና ቅዱስ ሰርጊስ መታሰቢያ ነው።
ባኮስ እና ሰርጊስ ከልጅነት ጀምሮ ባልንጀሮች ናቸው። ጾምን ጸሎትንና በጐ ምግባራትን ሁሉ ይከተሉ ነበር። ሠርቶ መብላት ይገባልና ሥራ ሲፈልጉ መክስምያኖስ ሠራዊት መሰብሰብ ጀመረ። እነርሱም ከሠራዊቱ ዘንድ ተቆጥረው የምድራዊ ንጉሥ ጭፍሮች ሆኑ። ከቆይታ በሁዋላ ግን ሰይጣን ያደረበት ንጉሡ መክስምያኖስ ጣዖት አመለከ። በአዋጅም ክርስቲያኖችን ያሰቃይ ይገድልም ያዘ።
በማግስቱም ንጉሡ ወደ ሾመው አለቃቸው ቀረቡና "የምንነግርህ ነገር አለን" አሉት። "እሺ" ሲላቸው በወገባቸው ያለውን የክብር መታጠቀያና የክብር ልብሳቸውን በፊቱ ወረወሩለትና "
እኛ የክርስቶስ ጭፍሮች ነንና ከዚህ በሁዋላ ላንተ ለጣዖት አምላኪው አንታዘዝም" አሉት። መኮንኑም በጽኑ አሰቃያቸው። እነርሱ ግን ጽኑዓን ነበሩና አልቻሏቸውም። ጥቅምት 4 ቀን በሆነ ጊዜ ግን 2ቱን ለያዩዋቸው።
ቅዱስ ባኮስን ትልቅ ድንጋይ በአንገቱ ላይ አሠሩበትና ባሕር ውስጥ አሰጠሙት። ነፍሱም ከስጋው ስትለይ ባሕር ወደ ዳር አስወጣችው። በአካባባቢውም ባባ እና ማማ የሚባሉ ባሕታውያን ነበሩና እግዚአብሔር እንዲገንዙት አዘዛቸው። ሲሔዱም ቅዱስ ሥጋውን አንበሳና ተኩላ ሲጠብቁት አግኝተው በታላቅ ዝማሬ ገንዘው በበዓታቸው ውስጥ ቀበሩት።
ቅዱስ ሰርጊስን ደግሞ በዚህች ቀን እጁንና እግሩን በእንጨት ላይ ቸንክረው በእንስሳት ጭራ ላይ አስረው ሲጐትቱት ውለዋል። አንገቱን በሰየፉት ጊዜም አንዲት ወጣት ደሙን ተቀብላ በረከትን አግኝታለች። የመከራ ዘመን ካለፈ በሁዋላም ለቅዱሳኑ ቤተ ክርስቲያን ታንጾ በዚህች ቀን ተቀድሷል።
በረከታቸው ይደርብን!አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
19 октября 2024 14:34
አስደሳች ዜና ለዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች
እግዚአብሔር ጸጋውን ሰጥቷችኋል፤ ስትዘምሩ ሰው ሁሉ ተመስጦ ነው የሚሰማችሁ። ሰውም ያለህን/ያለሽን ጸጋ ተመልክተው "አረ አንተ/ቺ ልጅማ ዘማሪ ነው የምትሆነው/የምትሆኚው" ይሏቹሃል!
እናንተም ጸጋው እንዳላችሁ ታውቃላችሁ ግን እንዴት ጸጋችሁን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ማዋል እንደምትችሉ አላወቃችሁም፤ ወይም ደግሞ ሞክራቹ መንገዱን የሚያሳያችሁ አላገኛችሁም። በተቃራኒው ደግሞ ጸጋቸው ሌላ ሆኖ ሳለ መድረኩን ስላገኙ ብቻ ዘማሪ የሆኑ ስንት አሉ መሰላችሁ፤ ጸጋው ተሰጥቷቸው ደግሞ መድረክ ያላገኙ በየቤታችን ብዙዎች አሉ።
"የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው፤" 1ኛ ቆሮ 12:4
ሁሉም ከእግዚአብሔር የተቀበለው ጸጋ አለ። ያንን አውጥቶ እግዚአብሄርን አለማገልገል ወይም ደግሞ ጸጋውን ላልተገባ ተግባር/ዘፈን/ ማዋል እንደዚያ መክሊቱን እንደቀበረው አገልጋይ ንፉግ ያሰኘናል።
የዝማሬ ዳዊት ገጽም ይህንን በማስተዋል ብዙ አዳዲስና ጸጋውን የተላበሱ ዘማርያንን ለማውጣት እየሰራ ይገኛል።
ይህንን የምትመለከቱ በሙሉ፤ መልዕክቱ እናንተን ባይመለከትም እንኳን የምታውቋቸው፤ በየሚዲያው የምትመለከቷቸው የዝማሬ ጸጋ የተሰጣቸውን ወንድም እህቶቻችንን ወደኛ መጥተው ቤተ ክርስቲያናችንን እንዲያገለግሉ መልዕክቱን እንድታስተላልፉ በክርስቶስ ፍቅር እንጠይቃለን።በዚህም መሰረት በ @ ላይ
ስም፣
ስልክ፣
አድራሻ እንዲሁም
ከሁለት ደቂቃ ያልበለጠ ከድምጻችሁ ጋር የሚጣጣም ዝማሬ በመላክ መቀላቀል ትችላላችሁ። መልሳችንን በአጭር ግዜ ውስጥ በዛው እናሳውቃቹሀለን።
መልዕክቱን ለሁሉም አድርሱ!
👉 @
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
19 октября 2024 06:00
ጥቅምት ፱ /9/
በዚችም ቀን በሕንድ አገር ቅዱስ ሐዋርያ ቶማስ ላደረገው ድንቅ ተአምር መታሰቢያ ሆነ።
ሐዋርያ ቶማስ እንደ ባሪያ ተሽጦ ወደ ሕንድ አገር ከአበኒስ ጋር በገባ ጊዜ አበኒስ ወደ ንጉሥ ጎንዶፎር አቀረበውና ሐናፂ እንደሆነም ለንጉሡ ነገረው ንጉሡም ጠየቀው ቅዱስ ሐዋርያ ቶማስም እንዲህ ብሎ ለንጉሥ መለሰለት እኔ የጥርብ ሥራን ሁሉ ቀንበሮችን ሚዛኖችን ሠረገላዎችን መርከቦችን በግንብ ሥራም ቤተ መንግሥትን እሠራለሁ ንጉሡም እጅግ ደስ አለው።
ቤተ መንግሥቱንም እንዲሠራለት ከሚሻው ቦታ ወሰደውና ንጉሡ ለራሱና ከእርሱ ለሚሠሩ ሠራተኞች የሚሆን ብዙ ገንዘብን ሰጠው ቅዱስ ሐዋርያ ቶማስም ተቀብሎ ሔደ። ገንዘቡ ለድሆች ምጽዋት አድርጎ ሰጣቸው ንጉሱም እጅግ ተቆጣ በሚገድለውም ነገር እስኪመክር ድረስ ሐዋርያ ቶማስን ከአመጣው ከአበኒስ ጋር አሠረው።
በዚያችም ሌሊት የንጉሡ ወንድም ጋዶን በድንገት ታመመና ሞተ መላእክትም ነፍሱን ወስደው ተመሳሳይ የሌለው በወርቅና በዕንቍ የተሠራ ቤተ መንግሥትን አሳዩት። ጋዶንም መላእክትን "ይህ ቤተ መንግሥት የማነው አላቸው" መላእክትም ለጋዶን "ሐዋርያ ቶማስ ለንጉሥ ጎልዶፎር የሠራለት ነው" አሉት ከዚህም በኋላ ጋዶን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ያየውንም ሁሉ ለወንድሙ ለንጉሥ ጎልዶፎር ነገረው።
በዚያንም ጊዜ ወደ እሥር ቤት ሮጡ ከወህኒ ቤትም አወጡአቸው። ለሐዋርያውም ሰገዱለት የሀገር ሰዎችም ሁሉ ከንጉሥ ጎልዶፎር ጋር አምነው ተጠመቁ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም ቅዱስ ሥጋውን እና ክቡር ደሙን አቀበላቸው። ከዚህም በኋላ ባረካቸውና ከእርሳቸው ዘንድ ወጥቶ ወደ ሌላ ቦታ ሔደ።
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
18 октября 2024 19:54
ለምን ዝም ብለን ሰው እንጠላለን
ከሩቅ የምናውቀው አንዳንድ ሰው የለም?
ብዙም አናውቀውም። ቀርበን አውርተነው አናውቅም። ስናየው ግን እንዲሁ ደስ የማይለንና ያለ ምክንያት የምንጠላው ሰው የለም?
"እሱን ሰውዬ ጥሎብኝ አልወደውም"
"አይ እሱን ልጅ ቀልቤ ትከሻዬ አልወደደውም"
"እኔ እንጃ ለምን እንደሆነ ባላውቅም አልወዳትም"
"ምክንያቴን አትጠይቀኝ ግን በቃ እንዲሁ አልወዳትም"
ምንም ምክንያት ሳይኖረን እንዲሁ የምንጠላው ሰው አለ። እግዚአብሔር ግን :-
"አንድያ ልጁን እስኪሠጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአል'' (ዮሐ 3:16)ጠላቶቹ ሳለን በልጁ ሞት አዳነን እንደሚል እርሱ እኛን ለመጥላት ብዙ ምክንያት ነበረው። እርሱ ግን እንዲሁ ወደደን። ከእኛ ምንም ባያገኝም ስለ እኛ ያለው ፍቅር የእንዲሁ ፍቅር (unconditional love) ነበረ። እርሱ እንዲሁ ወዶናል እኛ ግን እንዲሁ ሰው እንጠላለን።
ያለ ምክንያት መውደድ ቢያቅተን እንኳን ያለ ምክንያት መጥላታችን (unconditional hate) ቢቀር ምን አለ። የሚያሳዝነው ያለ ምክንያት የጠላናቸውን ሰዎች የበለጠ ለመጥላት በልባችን እስር ቤት ውስጥ በጥላቻ ሰንሰለት እናስራቸውና የበለጠ ለመጥላት ስለእነርሱ ክፉ ክፉ ማስረጃ ለመስማት እንተጋለን።
ጥሩ ነገራቸውን ለመስማት አንፈልግም። ክፉ ስንሰማ ግን "
እኮ እኔ እኮ ዝም ብሎ ትከሻዬ ይነግረኝ ነበር" ብለን በደስታ እንፈነድቃለን። እንዲሁ የጠላነውን ሰው በምክንያት ለመጥላት በመቻላችን ደስ ይለናል። እኛ ሰውን ለመጥላት ምክንያት የምንፈልገውን ያህል እንዲሁ የወደደን እግዚአብሔር ግን እኛን ለመማር ሰበብ ይፈልጋል። ትንሽ በጎነት ቅንጣት ቅንነት ሲያገኝ እጅግ ይደሰታል::
ባለቅኔው "እግዚአብሔር መንግሥቱን በርካሽ ዋጋ ሸጠው:: በቀዝቃዛ ውኃ በዘለላ ዕንባ እና ማረኝ በሚል የወንበዴ ጩኸት!" እንዳሉት እሱ እኛን ይቅር ለማለት የሚታይ በጎነት ቢያጣ ልባችን ውስጥ ገብቶ ትንሽ መጸጸት ካለ ይፈልጋል። እንዲሁ ወዶናልና እንዲሁ ሊተወን አይፈልግም።
"እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለሆነ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳን በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወትን ሠጠን" ኤሬ 2:4
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ:- የግዮን ወንዝ
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
18 октября 2024 05:59
ጥቅምት ፰ /8/
በዚህች ቀን ቅዱስ አባት መጥራ በሰማዕትነት አረፈ።
ይህም ቅዱስ ከእስክንድርያ አገር አማኒ ክርስቲያን ነው። ከሀዲ ንጉሥ ዳኬዎስ በነገሠ ጊዜ የጣዖትን አምልኮ አቁሞ የክርስቲያንን ወገኖች አሠቃያቸው። ትእዛዙም ወደ እስክንድርያ አገር ደርሶ ሰዎቿን ሁሉንም አሠቃያቸው የብዙዎች ምእመናንንም ደማቸውን አፈሰሰ።
ያን ጊዜ ክርስቲያን እንደ ሆነ ቅዱስ መጥራን በመኰንኑ ዘንድ ወነጀሉት መኰንኑም ወደርሱ አስቀረበው እርሱም ብቻውን እውነተኛ አምላክ እንደ ሆነ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ። መኰንኑም ለአማልክት ስገድ እኔም ብዙ ገንዘብን እሰጥሃለሁ ታላቅ ክብርንም አከብርሃለሁ አለው። እርሱም ቃል ኪዳኑን አልተቀበለም ኪዳንህና ገንዘብህ ካንተ ጋራ ወደ ጥፋት ይሒድ አለው እንጂ። መኰንኑም በእርሱ ላይ ተቆጥቶ ጽኑዕ ሥቃይ እቀጣሃለሁ አለው።
ለፈጠረ ለሕያው እግዚአብሔር እሰግዳለሁ። ለረከሱ ጣዖታት ከደንጊያና ከዕንጨት ለተሠሩ ለማያዩ ለማይሰሙ ለማይናገሩ ለማያሸቱ ለማይንቀሳቀሱ እንሰግድ ዘንድ እንዴት ይገባል አለው። መኰንኑም በሰማ ጊዜ አፈረ ጽኑ ግርፋትንም እንዲገርፉት አዘዘ ከዚህም በኋላ በክንዱ ሰቀሉት በደረቀች ሽመልም ጎኖቹን ሠነጠቁ ቀደዱትም ክብር ይግባውና ጌታ ኢየሱስም አዳነው ያለ ጥፋትም በጤንነት አስነሣው መኰንኑም ማሠቃየቱን በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። ከከተማውም አውጥተው የከበረች ራሱን ቆረጡ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ ።
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
17 октября 2024 12:00
ቅድስት ሥላሴ
ገፄን አማትቤ ልጀምር ውዳሴ
በትምህርተ መስቀል በስመ ሥላሴ
ይርቃል ከጎኔ ጠላት ዲያብሎስ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አዝ
ከትቢያ ከአፈር አንስቶ የሰራኝ
በአፉም እስትንፋስ ሕይወትን ያደለኝ
የሥላሴ ሥራ ድንቅ ነው ጥበቡ
ከአይምሮ በላይ ነው የእግዚአብሔር ሃሳቡ
አዝ
እክሕደከ ሰይጣን ጠላቴን ክጃለውሁ
ለዚህም ምስክር ማርያም ናት ብያለሁ
በቤተክርስቲያ ቆሜ በመቅደሱ
ለቅድስት ሥላሴ ዘመርኩ ለንጉሡ
አዝ
አልነበረም ዘመን እርሱ ያልነበረበት
ዳግመኛም አይኖርም እርሱ ማይኖርበት
የሕይወቴ ጣዕም ክብሬ እና ሞገሴ
የማይሾሙት ንጉስ ዘላለም ሥላሴ
አዝ
ኪሩቤል ሱራፌል ኃይላት ሊቃናት
መናብርት ስልጣናት ቆመው በአንድነት
ያለአንዳች ዝምታ ይሉታል በክብር
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
17 октября 2024 05:02
ሥላሴን አመስግኑ
ሥላሴን አመስግኑ(2)
የምድር ፍጥረታት ዘምሩ እልል በሉ
አዝ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
ምስጋና ይገባል ከምንም በፊት
ዓለማትን ሁሉ ለፈጠረ ጌታ
ምስጋና ይገባል ከጠዋት እስከ ማታ
አዝ
ኪሩቤል ሱራፌል የሚያመሰግኑት
መላእክት በሰማይ የሚዘምሩለት
እኛም የአዳም ልጆች እንዘምራለን
በሰማይም በምድር እንጠራሃለን
አዝ
ብራብ በሥላሴ እጠግባለሁኝ
ብጠማም በአምላኬ እረካለሁኝ
ሥላሴም አምባዬ ክብሬም ናቸው እና
ሁሌ ይመሩኛል በሕይወት ጎዳና
አዝ
ብራብ በሥላሴ እጠግባለሁኝ
ብጠማም በአምላኬ እረካለሁኝ
ሥላሴም አምባዬ ክብሬም ናቸው እና
ሁሌ ይመሩኛል በሕይወት ጎዳና
ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
16 октября 2024 16:23
አስደሳች ዜና ለዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች
እግዚአብሔር ጸጋውን ሰጥቷችኋል፤ ስትዘምሩ ሰው ሁሉ ተመስጦ ነው የሚሰማችሁ። ሰውም ያለህን/ያለሽን ጸጋ ተመልክተው "አረ አንተ/ቺ ልጅማ ዘማሪ ነው የምትሆነው/የምትሆኚው" ይሏቹሃል!
እናንተም ጸጋው እንዳላችሁ ታውቃላችሁ ግን እንዴት ጸጋችሁን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ማዋል እንደምትችሉ አላወቃችሁም፤ ወይም ደግሞ ሞክራቹ መንገዱን የሚያሳያችሁ አላገኛችሁም። በተቃራኒው ደግሞ ጸጋቸው ሌላ ሆኖ ሳለ መድረኩን ስላገኙ ብቻ ዘማሪ የሆኑ ስንት አሉ መሰላችሁ፤ ጸጋው ተሰጥቷቸው ደግሞ መድረክ ያላገኙ በየቤታችን ብዙዎች አሉ።
"የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው፤" 1ኛ ቆሮ 12:4
ሁሉም ከእግዚአብሔር የተቀበለው ጸጋ አለ። ያንን አውጥቶ እግዚአብሄርን አለማገልገል ወይም ደግሞ ጸጋውን ላልተገባ ተግባር/ዘፈን/ ማዋል እንደዚያ መክሊቱን እንደቀበረው አገልጋይ ንፉግ ያሰኘናል።
የዝማሬ ዳዊት ገጽም ይህንን በማስተዋል ብዙ አዳዲስና ጸጋውን የተላበሱ ዘማርያንን ለማውጣት እየሰራ ይገኛል።
ይህንን የምትመለከቱ በሙሉ፤ መልዕክቱ እናንተን ባይመለከትም እንኳን የምታውቋቸው፤ በየሚዲያው የምትመለከቷቸው የዝማሬ ጸጋ የተሰጣቸውን ወንድም እህቶቻችንን ወደኛ መጥተው ቤተ ክርስቲያናችንን እንዲያገለግሉ መልዕክቱን እንድታስተላልፉ በክርስቶስ ፍቅር እንጠይቃለን።በዚህም መሰረት በ @ ላይ
ስም፣
ስልክ፣
አድራሻ እንዲሁም
ከሁለት ደቂቃ ያልበለጠ ከድምጻችሁ ጋር የሚጣጣም ዝማሬ በመላክ መቀላቀል ትችላላችሁ። መልሳችንን በአጭር ግዜ ውስጥ በዛው እናሳውቃቹሀለን።
መልዕክቱን ለሁሉም አድርሱ!
👉 @
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
16 октября 2024 06:00
ጥቅምት ፮ /6/
በዚች ዕለት ቅዱስ አባት አባ ጰንጠሌዎን የእረፍታቸው መታሰቢያ ነው።
ታላቁ ጻድቅ፣ ሰባኬ ወንጌልና ገዳማዊ አባ ጰንጠሌዎን የተስዓቱ (ዘጠኙ) ቅዱሳን መሪ ናቸው። ጻድቁ ሃገረ ትውልዳቸው ሮም ቢሆንም ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮጵያ ነው። በገዳም ትምህርቱን ካጠነቀቁ በኋላ በዚያው ጠፍተው ወደ ግብጽ ወረዱ፤ በዚያም መነኮሱ። እድሜአቸው እየገፋ ሲሔድ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ስምንቱን ቅዱሳን ሰብስበው በአቡነ አረጋዊ መሪነት ወደ ሃገራችን መጡ። በአራት መቶ ሰባዎቹ አካባቢ የነበረው ንጉሥ አልዓሜዳም በክብር ተቀብሎ አክሱም ውስጥ ''ቤተ ቀጢን” የሚባል ቦታን ሰጣቸው።
አባ ጰንጠሌዎን 'ጾማዕት' ወደ ሚባል ረዥም ተራራ ወጡ። በዚያም አስቀድመው ለወንጌል አገልግሎት እየተጉ ድውያንን ፈወሱ፣ ሙታንን አስነሱ፣ አጋንንትን አሳደዱ። ብዙ ተአምራትንም አደረጉ። እንዲያውም አንድ ቀን ወይራውን በጧት ተክለው በሠርክ ትልቅ ዛፍ ሆነላቸው። ከዚያ ዘንጥፈው እሳቱን በቀሚሳቸው ላይ አፍመው ማዕጠንት አሳርገዋል። የሚገርመው ያ ዛፍ ዛሬም ድረስ ለምስክርነት ቁሟል። በመጨረሻ ዘመናቸው ግን ጻድቁ አምስት ክንድ ርዝመት ባላት ጾማዕት (በዓት) ውስጥ ገብተው ቆሙ።
ለአርባ አምስት ዓመታት ሳይቀመጡና ሳይተኙ በእንባ ቢጸልዩ ቅንድባቸው ተላጠ። አካላቸውም በአጥንቱ ብቻ ቀረ። በዚህች ዕለት የክብር ባለቤት መድኃኔዓለም መጥቶ ''ወዳጄ! ስምህን የጠራ መታሰቢያህን በእምነት ያደረገውንም ሁሉ እምርልሃለሁ።'' አላቸው። ያን ጊዜ አጥንቶቻቸው ተወዛወዙና ነፍሳቸው በክብር ዐረገች።
የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…