ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
24 сентября 2024 11:00
ተገኘ መስቀሉ
ለእኛ ለምናምነው መስቀል ኃይላችን ነው
ጠላትን ድል መንሻ መስቀል አርማችን ነው
ተነሱ ዘምሩ ክርስቲያኖች ሁሉ
ተገኘ መስቀሉ እሰይ እልል በሉ (2)
አዝ
አይሁድ በክፋት መስቀሉን ቀበሩት
ተዓምር እንዳይሰራ ሸሽገው ቢያኖሩት
ለብዙ ዘመናት ቀብረው ቢያኖሩትም
ተዓምር ከመስራቱ ከቶ አላስቀሩትም
እሰይ እልል በሉ እንደ አይሁድ ክፋት
እሰይ እልል በሉ አልቀረም ተቀብሮ
እሰይ እልል በሉ በእሌኒ ንግሥት
እሰይ እልል በሉ ወጣ ተቆፍሮ
መስቀሉ ተቀብሮ ከቶ እንዳይረሳ
እሌኒም አገኘች ደመራ ለኩሳ
አዝ
የእሌኒ ንግሥት ፀሎቷ ተሰማ
መስቀል ለመፈለግ ጸናች በዓላማ
ደመራ ደምራ እጣኑን አጢሳ
አስገኘች መስቀሉን ተራራውን ምሳ
እሰይ እልል በሉ ክብራችን ነው ለእኛ
እሰይ እልል በሉ የሆነን መዳኛ
እሰይ እልል በሉ መስቀል ኃይላችን ነው
እሰይ እልል በሉ ለምናምነው ለእኛ
መስቀሉ ያበራል እንደ ፀሐይ ጮራ
ድውይ እየፈወሰ እውር እያበራ
አዝ
መስቀልን በመስቀል እንዳለ በቃሉ
አንብር መስቀልዬ በድበ መስቀሉ
በኢትዮጵያ ምድር ተዓምር እየሰራ
በቤቱ ከበረ በግሸን ተራራ
እሰይ እልል በሉ መስቀል ሞገሳችን
እሰይ እልል በሉ ምልክት አርማችን
እሰይ እልል በሉ ጠላትን ድል መንሻ
እሰይ እልል በሉ የእምነት ጋሻችን
በኢትዮጵያ ምድር በግሸን ተራራ
ግማደ መስቀሉ ዛሬም ተዓምር ሰራ
ዘማሪ ጥላሁን ፍቃዱ 💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
24 сентября 2024 05:00
መስቀል ኃይላችን
መስቀል ኃይላችን መስቀል ተፈጥሮአችን
መስቀል(2) ይላል መላው አካላችን
ሞትን ድል ነስተናል በከበረው ስሙ
ቀድሶታል እና ክርስቶስ በደሙ(2)
አዝ
በአይሁድ አደባባይ ታየ በከፍታ
ጎባጣ እያቀና ሞትን እየረታ
ትንሹም ትልቁም ከአንገቱ የማይለየው
የእሌኒ ሞገስ መስቀል ቤዛችን ነው (2)
አዝ
የአምላክ ዙፋኑ ባለውለታችን
በአንተ የፈሰሰው ሆነ ሕይወታችን
አይሁድ አዋጅ ነግረው አመድ ሲደፉብህ
እሌኒ በጢሱ ፈልጋ አገኘችህ (2)
አዝ
እኛም አንተን ስንል ለሞት ብንሰጥም
ፍፁም ከአንገታችን ልንለይህ አንችልም
የፍቅር ፍፃሜ ሆነኸናልና
ከፅንፍ እስከ አፅናፍ ታብባለህ ገና
ከፅንፍ እስከ አፅናፍ ታበራለህ ገና
አዝ
በዕለተ ሠሉስ ለፈጠረህ ጌታ
ዙፋን ልትሆነው ወጣህ ጎልጎታ
አርብ ዕለት ተፈጥረው አርብ ዕለት ለዳኑት
ለአዳም እና ሄዋን ሆንካቸው መድኃኒት (2)
ዘማሪት ኤልሳቤጥ እያዬ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
23 сентября 2024 18:00
በመስቀሉ ኮነ ሕይወትነ
በመስቀሉ ኮነ ሕይወትነ ሃሌሉያ
ሃሌሉያ ኮነ ሕይወትነ
እንዘምር ሆነን በደስታ ሃሌሉያ
ሃሌሉያ ሆኖናል ከፍታ
አዝ
የፍቅሩ ዙፋን መስቀሉ
ተገልጦ በኛ ላይ ኃይሉ
በድል ነሺዎች ጎዳና
መራን መስቀሉ እንደገና
መስቀል ኃይልነ ዘምሩ መስቀል ኃይልነ
ተነሱ ዛሬ ለፍቅሩ መስቀል ኃይልነ
ቁሙ በፅናት በእውነቱ መስቀል ኃይልነ
ያዳነን ጌታ በሞቱ መስቀል ኃይልነ
አዝ
በጲላጦስ ፊት ተከሶ
የእሾህ አክሊልን ለብሶ
ከምድረ ፋይዳ አወጣን
መስቀሉ ኃይል አስታጠቀን
የቀሪናው ሰው ስምዖን መስቀል ኃይልነ
በእጁ እንደያዘ መስቀሉን መስቀል ኃይልነ
ደም ለጋረደው ለፊቱ መስቀል ኃይልነ
ምግባችን ሆነው አፅርቅቱ መስቀል ኃይልነ
አዝ
ፍኖተ መስቀል መከራ
ዜማ አስታጠቀን እንዚራ
ወርዶ መቃብር ንጉሡ
ጽድቃችን ሆነ ሞገሱ
የቆስጠንጢኖስ ራዕይ መስቀል ኃይልነ
ቃል አለው ጸፍጸፈ ሰማይ መስቀል ኃይልነ
ጠላት ይረታል በቃሉ መስቀል ኃይልነ
ላመነ መስቀል ነው ድሉ መስቀል ኃይልነ
አዝ
ተነሽ እሌኒ በደስታ
መስቀሉ ይታይ የጌታ
የእጣኑ ጢስ ከፍ ይበል
የክፋት ድልድይ ይነደል
ነካ ደመራው በሳ መስቀል ኃይልነ
ያለ እርሱ የለንም እረፍት መስቀል ኃይልነ
ምርኩዝ ነውና ለምድሩ መስቀል ኃይልነ
መስቀል ማርኮናል በፍቅሩ መስቀል ኃይልነ
ዘማሪ ዲያቆን ገዛኸኝ ኤርባ 💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
23 сентября 2024 11:00
መስቀል ክብሬ ነው
ምልክቴ ነው ከቀስት ማምለጫዬ
መስቀል ክብሬ ነው ከክፉ መውጫዬ
አዝ
የእባቡ ራስ ሚቀጠቀጥበት
በመስቀል ቤዛነት መርገም ተሻረበት
ሰው በእጸ መስቀል ከእግዚአብሔር ታረቀ
የምሕረት ቀን ወጣ መከራው እራቀ
ኦ በመስቀል ጠላት ተቸገረ
ኦ በመስቀል ጨለማው ተሻረ
ኦ በመስቀል ደሙን አፈሰሰ
ኦ በመስቀል ሥጋውን ቆረሰ
አዝ
ፊቴን ሰውነቴን በእርሱ አማትባለሁ
በልቤ አትሜ በአንገቴ አስረዋለሁ
አይሁድ በሚክዱት እኔ ግን አምኜ
እግሩ ለቆመበት እሰግዳለሁ ድኜ
ኦ በመስቀል እስረኛ ተፈታ
ኦ በመስቀል ከሳሹ ተረታ
ኦ በመስቀል ሞትን ገደለልን
ኦ በመስቀል በሩን ከፈተልን
አዝ
የቤዛ ክርስቶስ የክብሩ ዙፋን ነው
በእምነት የሚያጸና በስሙ ላመነው
የቅድስና የሕይወት ማኅተም
መስቀል ትምክህት ነው እስከ ዘለዓለም
ኦ በመስቀል ፍቅሩን ገለጠልን
ኦ በመስቀል ነፍሱን ለእኛ ሰጠ
ኦ በመስቀል እምባችን ታበሰ
ኦ በመስቀል ጸጋ ተለበሰ
አዝ
ፊቴን ሰውነቴን በእርሱ አማትባለሁ
በልቤ አትሜ በአንገቴ አስረዋለሁ
አይሁድ በምክዱት እኔ ግን አምኜ
እግሩ ለቆመበት እሰግዳለሁ ድኜ
ኦ በመስቀል እስረኛ ተፈታ
ኦ በመስቀል ከሳሹ ተረታ
ኦ በመስቀል ሞትን ገደለልን
ኦ በመስቀል በሩን ከፈተልን
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
23 сентября 2024 05:00
መስቀል ኃይላችን
መስቀል (2) ኃይላችን ጠላትን ማጥፊያችን (2)
በመስቀል እንመካለን እንድንበታለን (2)
አዝ
የክርስቲያን ጋሻ መስቀል ኃይላችን
የክርስቲያን ጦር መስቀል ኃይላችን
ዕፀ መስቀሉ ነው መስቀል ኃይላችን
የማያሳፍር መስቀል ኃይላችን
አዝ
መድኃኒት የሚሆን መስቀል ኃይላችን
ደሙ ፈሶበታል መስቀል ኃይላችን
መስቀሉን ጥግ አድርጉ መስቀል ኃይላችን
እርሱ ይፈውሳል መስቀል ኃይላችን
አዝ
ክርስቶስ በደሙ መስቀል ኃይላችን
ስለቀደሰው መስቀል ኃይላችን
መስቀል ላመነበት መስቀል ኃይላችን
ድል ማድረጊያ ነው መስቀል ኃይላችን
አዝ
የክርስቶስ ሥጋ መስቀል ኃይላችን
የተፈተተበት መስቀል ኃይላችን
መስቀል ኃይላችን ነው መስቀል ኃይላችን
የምንድንበት መስቀል ኃይላችን
አዝ
ሕይወትን ለማግኘት መስቀል ኃይላችን
ከሞት ለመዳን መስቀል ኃይላችን
መመኪያ ኃይላችን መስቀል ኃይላችን
መስቀል አለልልን መስቀል ኃይላችን
ዘማሪ ሚኪያስ ፀጋዬ
ዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜፀጋ ዮሐንስ
ዘማሪ ሊቀ ዲያቆናት ነቢዩ ሣሙኤል
ዘማሪ አቤል ተስፋዬ
ዘማሪ በርሱፈቃድ አንዳርጋቸው 💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
22 сентября 2024 07:55
ሰላም ውድ የዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች እንደምን አደራችሁ? እግዚአብሔር ይመስገን።
መንፈሳዊ የዜማ ስቱዲዮ ያላችሁ ወንድም እህቶች በውስጥ በኩል መልዕክት ይላኩልን። የምታውቁም ካላችሁ ጠቁሙልን @ 📩
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
22 сентября 2024 05:00
ይለይብኛል
ጠብቆ አሳድጎ ከልጅነቴ
አባት እየሆነኝ ሚካኤል አባቴ
ይለይብኛል ሚካኤል ይለይብኛል
በክንፉ ሸፍኖ በቤቱ አሳድጎኛል /2/
አዝ
አያምርብኝ ብዘነጋው ታሪኬን
ሚካኤል ነው ያስጌጠልኝ ህይወቴን
አረሳብኝ እርሱ አትርሳብኝ ያልኩትን
ለካስ ሰምቶኝ ኖሯል የልጅነት ጸሎቴን
ሚካኤል ያን ሁሉ ዘመን የታገሰኝ
ሚካኤል ፍሬ ጠብቆ ያልቆረጠኝ
ሚካኤል የከፍታዬ መሰላል
ሚካኤል መነሻዬ ሆነሀል
አዝ
እንዳይከፋኝ አንዳልደፋ አንገቴን
እንዳላለቅስ እንዳላፈስ እንባዬን
እንዳይርቀኝ ደስታ በመንፈሴ እንዳልዝል
ካጠገቤ አይርቅም ያሳደገኝ ሚካኤል
ሚካኤል ቀኔም ቀን አይሆን ሳልጠራህ
ሚካኤል ና ድረስልኝ ሳልልህ
ሚካኤልእንዳስጀመርከኝ ጅማሬዬን
ሚካኤል አሳምረው ፍፃሜዬን
አዝ
ውድቅ አረገው የጠላቴ ክፉ እቅድ
አራመደኝ በከፍታዬ መንገድ
ሊያስቀረኝ አልቻለም ሊጎትተኝ ባላጋራ
ተጥሎ ስላለ በእግዚአብሔር ድንቅ ስራ
ሚካኤል እሳታዊ ነው ነበልባል
ሚካኤል ጠላቴ ፊትህ ይቀልጣል
ሚካኤል ለኔ ኃይሌ ነው መከታዬ
ሚካኤል የዘለዓለም ጠባቂዬ
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
21 сентября 2024 12:17
ይላል አንደበቴ
ይላል አንደበቴ እግዚአብሔር ቅዱስ ነው
አይተወኝምና ወላጅ እንደሌለው
ትናንት የጠበቀኝ የነገም ተስፋዬ
ትልሃለች ነፍሴ ፍቅር ነህ ጌታዬ
አዝ
የትናንት ሕይወቴን ዞር ብዬ ሳየው
ማምለጫ የሌለው አጥሩም እሾህ ነው
ወደ እረፍቴ ወጣሁ ይድረስ ምስጋናዬ
ደጆች ቢዘጉብኝ በር ሆኖኝ ጌታዬ (2)
አዝ
በጥልቁ በረሃ ምግብ መጠጥ ሆኖኝ
መንገዴን አቀናው እጄን በአፌ አስጫነኝ
በእሳትና ውሃ መካከል አልፌ
ተመስገን እላለሁ ቅኔ ሞልቶት አፌ (2)
አዝ
የብቸኝነቴን ማዕበል ገስጿል
ለእኔ ብርሃን ሆኖ ለከሳሽ ጨልሟል
ቀስቱን እያጠፈ ታደገኝ ከስቃይ
የጌታዬ ሃሳብ ፍቅር ነው በእኔ ላይ (2)
አዝ
ትናንት ዛሬ ነገ ዘላለም ጠባቂ
የልቤን ፍላጎት ሳልነግረው አዋቂ
በባሕርይው ቅዱስ የሌለው አምሳያ
ስሙ ወደቤ ነው መልህቄን መጣያ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
21 сентября 2024 05:00
በብርሃን ፀዳል
በብርሃን ፀዳል ተከባ እመቤቴ
በደመና ዙፋን ተቀምጣ ከፊቴ
የፅጌውን ዜማ ስንዘምር በደስታ
በምስጋናሽ መጠጥ ሲሰማኝ እርካታ/2/
አዝ
እንባዬ ሲቀዳ ናፍቆትሽ መስጦኝ
ከደስታ በላይ አንቺን ስላየሁኝ
ምኞቴ ተሳክቶ ፊትሽን አይቼው
የሌሊቱ ሕልሜ
የቀን ምኞቴ ነው/2/
አዝ
እሩሩህ ነሽና ይህ ህልሜ ተሳክቶ
አመስግኜሽ ድንግል ህሊናዬ እረክቶ
ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ
አንቺን በማመስገን
ሕሊናዬ ይትጋ/2/
አዝ
ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ
አንቺን በማመስገን ህሊናዬ ይርካ
የምስጋናሽ ብዕር ብራናሽ ልሁን
ስምሽ ይጻፍብኝ
በልዩ ሕብር/2/
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
20 сентября 2024 12:28
ሰባቱ መንጦላይት
ሰባቱ መንጦላይት ወዴት ተጋረዱ
ሰባቱ መብራቶች ወዴት ተሰናዱ
ታናሽ ሙሽራ ነሽ የአሥራ አምስት ዓመት
በአንቺ ላይ ሲፈጸም እንግዳ ሥርዓት
አዝ
አንዴ እየታጠቀ አንዴም እየፈታ
ገብርኤል ሲያበስርሽ በፍጹም ሰላምታ
ይኩነኒ ብለሽ ስትቀበይው
መለኮት እንዴት ነው የተዋሐደው
ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል
አዝ
ሁሉን የሚወስን ባንቺ ተወሰነ
ከሦስቱ አካል አንዱ ቃልም ሥጋ ሆነ
ስፋት እና ጥበት ሰማይ እና ምድር
ባንቺ ተገናኙ ገባሪና ግብር
ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል
አዝ
እንዴት ቢመርጥሽ ነው እንዴት ቢያከብርሽ
ትናንት እና ዛሬን ያገናኘብሽ
ምልዐትና ወሰን ግዝፈትና ርቀት
ባንቺ ተዋሐዱ ፈጣሪና ፍጥረት
ይህን ባሰብኩ ቁጥር ልቤ ይመሰጣል
ከዚህ በላይ ፍቅርስ እንዴት ይገለጣል
አዝ
ምስጢር ሊመረምር ይወጣል ኀሊና
ያልፋል ይሻገራል ከሰማይ ደመና
ነገር ግን አይችልም ምንም ቢገሠግሥ
ከመሰወሪያው ዘንድ ከልጅሽም ሊደርስ
ስለዚህ አቅቶት ደክሞት ይመለሳል
መልክዐ ውዳሴሽን በአድናቆት ያደርሳል
ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
20 сентября 2024 04:59
እግዚአብሔርን አመስግኑት
እግዚአብሔርን አመስግኑት
ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት/2/
አዝ
ሰማይን ያለምሰሶ
ምድርንም ያለ መሠረት
ያጸናው እርሱ ነው
ሥራህ ድንቅ ነው በሉት
አዝ
የባሕርን ጥልቀት የመጠነ
ዳርቻዋን የወሰነ
እግዚአብሔርን አመስግኑት
ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው በሉት
አዝ
ማዕበል ነፋስ የሚገስጽ
ፍጥረቱ ለስሙ የሚታዘዝ
ትጉህ እረኛ ድካም የሌለበት
እግዚአብሔርን ሥራህ ድንቅ ነው በሉት
አዝ
ንጹሀ ባሕርይ ነው ሁሉን የሚገዛ
የነገስታት ንጉሥ አልፋና ኦሜጋ
ዘላለም እርሱ የማይለወጥ
እግዚአብሔርን ሥራህ ድንቅ ነው በሉት
አዝ
ጥበብን የሚገልጥ ጥበበኛ
ፍርድን የሚያደርግ እውነተኛ ዳኛ
እንደ እርሱ ያለ ከቶ አይገኝም
እግዚአብሔር ግሩም ነው ዘለዓለም
ዘማሪት ፀዳለ ጎበዜ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
19 сентября 2024 06:07
መስከረም ፱
በዚህች ቀን መጺል በምትባል አገር ኤጲስ ቆጶስ የነበረ፤ ቅዱስ አባት አባ ቢሶራ በሰማዕትነት አረፈ።
በወቅቱ ዲዮቅልጥያኖስ የተባለ ክፉ ሰው በንግስና ላይ የነበረበት ግዜ ነበር። በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሰይጣን ቀጥሎ እንደዚህ የከፋ ስም የለም። የዓለም ክርስቲያኖችን የጨፈጨፈ ሰው ነው። መከራውም እየገፋ ሲመጣ ቅዱሱ በመፍራት ፈንታ የሰማዕትነት ፍቅር አደረበት። በክርስቶስ ስም ደሙን ያፈስ ዘንድ ወደደ።
ሕዝቡንም ሰብስቦ አቆማቸው፤ ሊጠብቁት የሚገባውን ለጽድቅ የሚያበቃቸውን ትዕዛዝ ሁሉ አዘዛቸው። ከዚህም በኋላ ለሰማዕትነት እንደተዘጋጀ ነገራቸው። ይህንንም በሰሙ ግዜ ሁሉም አለቀሱ። የሙት ልጆች እንሆን ዘንድ ለምን ትተወናለህ፤ እንድትሄድ አንለቅህም አሉት ሊይዙትም ቃጡ። ቅዱሱም ሰላምታ ሰጥቷቸው ከእነርሱ ዘንድ ወጥቶ ተጓዘ። አንዳንድ አባቶችም አብረን እንሞታለን ብለው አብረውት ሄዱ።
በኋላም መኰንኑ ጽኑ የሆነ መከራ አደረሰባቸው ፤አባቶች ግን በታላቅ ትዕግስት ጸኑ። ከዚህም በኋላ ራሶቻቸውንም በሰይፍ ይቆርጧቸው ዘንድ አዘዘ። በዚህች ዕለትም የሕይወት አክሊልን በመንግስተ ሰማያት ተቀበሉ።
በረከታቸው ይደርብን
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
18 сентября 2024 19:37
ስግደት
ስግደት ማለት መዋረድ፣ ማጎንበስ፣ መንበርከክ፣ በግንባር መውደቅ፣ ግንባርን ምድርን አስንክቶ መሬት ስሞ መመለስ ማለት ነው።
ስግደት ለምን ይጠቅማል?ስግደት ከአምላካችን ፀጋ እና በረከትን እንድናገኝ እንዲሁም ክፉ መንፈስ ከእኛ እንዲርቅ ይረዳል። በቤተ ክርስቲያን ሁለት አይነት ስግደቶች አሉ፦እነሱም
፩.የአምልኮ (የባህሪይ) ስግደት
ይህ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ብቻ አንተ አምላኬ ነህ በማለት የምንሠግደው ስግደት ነው። ማቴ 4፥10
፪.የአክብሮት (ጸጋ) ስግደት
ለመላእክት ለቅዱሳን ለፃድቃን ለሰማዕታት የሚሰገድ ስግደት ነው። በፀሎት ጊዜ በተለይም ስግደትን የሚያነሳ አንቀፅ ሲገኝ ህሊና ተሰብስቦ የአንክሮ፣ የተደሞ፣ የትህትና ስግደት ይሰገዳል። ስግደት በቤተክርስቲያን እንዲሰገድ መጽሐፍ ቅዱስ ያዝዛል። ቤተክርስቲያን በሌለበት ቦታ ደግሞ በስተምስራቅ አቅጣጫ እንሰግዳለን።
ስርዓተ ቤተክርስቲያን በወር ውስጥ አምስት ቀናት ስግደት እንዳይሰገዱባቸው ያዛል፦1. የበዓለ ወልድ እለት (በየወሩ በ29) እና በጌታችን አበይት በአላት
2. የእመቤታችን ወርሃዊ መታስቢያ (በየወሩ በ21) እና በእመቤታችን በዓላት
3. የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል መታሰቢያ (በየወሩ በ12)
4. ቀዳሚት ሰንበት (ቅዳሜ)
5. ሰንበተ ክርስቲያን (እሁድ) እና በዓለ ሀምሳ።
በእነዚህ ቀናት የማይሰገድበት ምክንያት
📌 ዕለተ
ቅዳሜ ጌታችን ፍጥረታትን ሁሉ ፈጥሮ ከስራው ያረፈበት ቀን ስለሆነ።
📌 ዕለተ
እሁድ ጌታ ከሙታን መካከል ተለይቶ የተነሳበት ቀን ስለሆነ።
📌
በ12 በዓለ ቅዱስ ሚካኤል ራዕ᎐፲፪ኀ ሰይጣን የወደቀበት ቀን ስለሆነ።
📌
በ21 በዓለ ማርያም የነፍሳችን ዕረፍት ነጻ የወጣንባት ስለሆነ።
📌
በ29 በዓለ እግዚአብሔር የነጻነት ቀን ጌታ የተወለደበት ቀን ስለሆነ።
የአምልኮት ስግደት ሦስት ደረጃዎች አሉት እነርሱም;-
፩᎐ ሰው አድርገህ ከመሬት ፈጥረኸኛልና ስንል ወደ ምድር ጉልበትና ግንባራችንን እናስነካለን።
፪᎐ በኃጢአት ወድቄ በንስሐ እነሳለሁ ስንል ከሰገድንበት ብድግ እንላለን።
፫᎐ ብሞት በትንሣኤ እነሳለሁ ስንል ከሰገድንበት ቦታ በሁለት እግሮቻችን እንቆማለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
18 сентября 2024 06:01
መስከረም ፰
በዚህች ቀን ደግሞ የእግዚአብሔር ሰው የሆነ፤ ቅን፤ የዋህ፤ ጻድቅ፤ የነቢያት አለቃ የቅዱስ ሙሴ ዕረፍቱ ነው።
ከኮከብም ኮከብ እንደሚበልጥ ከነቢያት ሁሉ ደግሞ ቅዱስ ሙሴ ይበልጣል። የቅዱስ ሙሴ አባት
እንበረም እናቱ ደግሞ
ዮካብድ ይባላሉ። ቅዱስ ሙሴ በተወለደ ወቅትም የእስራኤል ወንድ ልጆች ይገደሉ ነበር። ወላጆቹም እርሱን ለማሸሽ ሲሉ ገና በ3ወሩ በግብጽ /ዓባይ/ ወንዝ ውስጥ ጣሉት።
የፈርዖን ልጅም ከወንዝ ላይ ባገኘችው ግዜ ለእርሷ ልጅ ይሆናት ዘንድ ወስዳ በመልካም አስተዳደግ አሳደገችው። ስሙንም
ሙሴ ያለችው እርሷ ናት፤ ትርጉሙም ከውሃ የተገኘ ማለት ነው። ወላጆቹ ግን በተወለደ ወቅት ፊቱ ያበራ ነበርና
ምልክአም ብለው ስም አውጥተውለት ነበር። እናቱ ዮካብድም በሞግዚትነት ገብታ ልጇን ማንም ሳያውቅ አሳድጋዋለች።
በቅዱስ መጽሐፍ እንደምናነበው ቅዱስ ሙሴ ኮልታፋ ነው፤ ይህም ገና በ5 አመቱ ፈርኦንን በጥፊ በመምታቱ እሳት አበሉት በዚህም ኮልታፋ ሆኖ ቀርቷል። 40 አመት በሞላው ግዜም አንድ የግብጽ ሰው አንዱን ዕብራዊ ሲያጠቃው ተመልክቶ ለዕብራዊው ተበቅሎ ግብጻዊውን ገደለው ከዚያም ወደ ምድያም ሸሽቷል።
ቅዱስ ሙሴ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ግብጻውያን ላይ ዘጠኝ መቅሰፍት በአስረኛውም ሞተ በኩር መታ። እሥራኤልንም ነጻ አወጣ። መልካም ተጋድሎንም ፈጽሞ በዚህች ዕለት ዐረፈ።
በረከቱ ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
17 сентября 2024 12:27
ድንቅ አድርጎልኛል
ድንቅ አድርጎልኛል የሠራዊት ጌታ 2
አልረሳኝም አምላክ አነሳኝ ከትቢያ 2
አዝ
ድንቅ አድርጎልኛል በደሌን ሳይቆጥር
ድንቅ አድርጎልኛል ወደቤቱ ጠራኝ
ድንቅ አድርጎልኛል እረክሼ ሳለሁ
ድንቅ አድርጎልኛል ልጄ ሆይ ና አለኝ
ድንቅ አድርጎልኛል በዳግም ምጻቱ
ድንቅ አድርጎልኛል መንግስቱን ሊያወርሰኝ
አዝ
ድንቅ አድርጎልኛል ከአንበሳ መንጋጋ
ድንቅ አድርጎልኛል ከጉድጓድ አወጣኝ
ድንቅ አድርጎልኛል በጠላቶቼ ፊት
ድንቅ አድርጎልኛል ግርማ ሞገስ ሰጠኝ
ድንቅ አድርጎልኛል ምን እመልሳለሁ
ድንቅ አድርጎልኛል እንዲህ ለወደደኝ
አዝ
ድንቅ አድርጎልኛል ጠላቶቼ ሁሉ
ድንቅ አድርጎልኛል ሲጓደዱብኝ
ድንቅ አድርጎልኛል ማን ይደርስለታል
ድንቅ አድርጎልኛል እያሉ ሲሉኝ
ድንቅ አድርጎልኛል ፈጥነህ ደረስክልኝ
ድንቅ አድርጎልኛል ከሞት አዳንከኝ
ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
24 сентября 2024 06:00
መስከረም ፲፬
በዚህች ዕለት ቅዱስ አባ አጋቶን ዘዓምድ አረፈ።
እኚህ አባት
ዘዓምድ ይባላሉ። ምክንያቱም ለ50 ዓመታት አንድ ምሰሶ ላይ ያለ ዕረፍት ጸልየዋልና ነው። ገና ከልጅነታቸው መጻሕፍትን የተማሩ ሲሆኑ ምናኔን አጥብቀው ይፈልጓት ነበር። በዚህም ራሳቸውን በትሕርምት እየገዙ በዲቁና ማዕርጋቸውም እያገለገሉ እስከ 35ዓመታቸው ቆዩ። በዚህ ጊዜ ደግሞ
ይገባሃል ብለው ቅስናን ሾሟቸው።
እኚህ አባት አብዝተው ምንኩስናን ይፈልጉ ነበርና አስፈላጊውን የምንኩስና ፈተና ካለፉ በኋላም ምንኩስናን ከአባቶች ተቀበሉ። በዚያው በገዳመ አስቄጥስ በጽኑ ገድል ተጠምደው ለ15 ዓመታት አገለገሉ። እድሜአቸውም 50 በሞላ ጊዜ በልቡናቸው እንደ አባ ስምዖን ዘዓምድ ለመጋደል ወሰኑ።
አባ አጋቶን የዳዊትን መዝሙር እየዘመሩ ከገዳሙ ወጡ። ወደ ዓለም ሳይገቡ ከዓለምም በጣም ሳይርቁ አንድ ረዥም ምሰሶ አገኙና ከላዩ ላይ ወጡ። ለ50 ዓመታትም ከዚያች ዓምድ (ምሰሶ) ወርደው ለሥጋቸውም ዕረፍትን ሰጥተውት አያውቁም። ለአካባቢውም የብርሃን ምሰሶ ሆኑ። የታመመ ቢኖር ይፈውሱታል። የበደለውን በንስሃ ይመልሱታል። ሰይጣን የቋጠረውን ይፈቱታል።
ጻድቁ አባ አጋቶን ዘዓምድ ከእነዚህ የቅድስና ዘመናት በኋላ በተወለዱ በ100 ዓመታቸው በዚህች ቀን ዐረፉ።
በረከታቸው ይደርብን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
23 сентября 2024 20:11
ምሥጢረ ቁርባን
ቁርባን ፤ ማለት፣ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ አምኃ፣ መስዋዕት፣ መንፈሳዊ ነገር ሁሉ ማለት ነው።
በብሉይ ኪዳን ለሐዲስ ኪዳን ቁርባን (መስዋዕት) ምሳሌዎች
1. የመልከ ጼዴቅ መስዋዕት ዘፍ 14፥ 18። ዕብ 5 ፥6። ዕብ 6 ፥1። ህብስቱ የሥጋው፤ ወይኑ የደሙ ምሳሌ፤ መልከ ጼዴቅ የክርስቶስ፤ አብርሐም የምዕመናን።
2. የእስራኤል ፋሲካ። ዘፀ 12፥ 1። ሞት የዲያብሎስ፤ እስራኤል የምዕመናን፤ በጉ ደግሞ የክርስቶስ ምሳሌ።
3. የእስራኤል መና። ዘፀ 16፥ 13። መና የጌታችን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም፤ እስራኤል የምዕመናን፤ ደመና የእመቤታችን
በብሉይ ኪዳን መስዋዕት ቁርባን ያቀረቡና በረከት ያገኙ አባቶች
1. አዳም አባታችን አዳም ባቀረበው መስዋዕት ከአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን በኋላ ሰው ሆኖ እንደሚያድነው ቃል ገባለት። ዘፍ 3፥ 22። ገላ 4፥ 4።
2. ኖኅ ባቀረበው መስዋዕት ለኖኅና ለልጆቹ ምድርን ዳግም በመቅሰፍት እንደማያጠፋት በቀስተ ደመና ምልክት ቃል ገባላቸው። ዘፍ 9፥ 1። ዘፍ 9፥ 8።
3. አብርሐም ዘፍ 18፥ 3። አባታችን አብርሐም ባቀረበው መስዋዕት በዘርህ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ የሚለውን የተስፋ ቃል ሰማ፤ ያም ዘር የተባለው ለጊዜው ይስሐቅ ሲሆን፤ ፍጻሜው ግን ለጌታ ነበር።
4. መልከ ጼዴቅ ዘፍ 14 ፥ 17። መዝ 109፥ 4። ዕብ 5፥ 6። በእግዚአብሔር ፊት ባቀረበው መስዋዕት ክህነቱ ለዘለዓለም ተብሎለት የክርስቶስ ምሳሌ ሆነ። ዕብ 7፥ 1።
5. ዳዊት መዝ 131፥ 11። መስዋዕት ባቀረበበት ሠዓት ከአብራክህ የተገኘው ልጅህ በዙፋንህ ይነግሣል ተባለለት፤ ይህም ለጊዜው የተነገረው ለሰሎሞን ሲሆን ፍጻሜው ለክርስቶስ ነበር። መዝ 71 ፡1። ሌሎችም በእግዚአብሔር ፊት ንጹህ መስዋዕታቸውን እያቀረቡ በረከት ተቀብለዋል።
ምሥጢረ ቁርባን በሐዲስ ኪዳን
በብሉይ ኪዳን ዘመን ይቀርብ የነበረው የመስዋዕት ቁርባን፤ ከበግ፤ ከላምና፤ ከተለያዩ እንስሳት ነበር። በሐዲስ ኪዳን ግን እንስሳት በቤተ መቅደስ ውስጥ መስዋዕት (ቁርባን) ሆነው አይቀርቡም መስዋዕት ሁሉ በክስቶስ ሥጋና ደም ተጠቃሏል። ይህንም የአዲስ ኪዳን መስዋዕት የመሠረተው ራሱ ጌታችን ሲሆን ፤ በጸሎተ ሐሙስ ማታ አስራ ሁለቱ ሐዋርያት እንዳሉ በመጀመሪያ መስዋዕተ ኦሪትን ሰርቶ ካሳለፈ በኋላ ኅብስቱና ወይኑን ባርኮ “ነገ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬና የሚፈሰው ደሜ ይህ ነው ብሉ ጠጡ ብሎ ሰጣቸው”። ማቴ 26፥ 26።
ዛሬ ካህኑ ኅብስቱን በጻህል ወይኑን በጽዋ አድርጎ ጸሎተ ቅዳሴውን እየጸለየ ሲባርከው እንደዚያ ጊዜው ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑም ተለውጦ ደመ መለኮት ይሆናል። ይህንም ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም በምንቀበልበት ጊዜ ለእኛ ሲል የተቀበለውን መከራና ስቃይ እያሰብን ራሳችንን በንስሓ ከኃጢአት ንጹህ አድርገን ከንስሓ የቀረውን በደላችንን እንደሚደመስስልን ፤ ከበደል እንደሚያነጻንና የዘለዓለም ሕይወት እንደሚሰጠን አምነን መሆን አለበት። በ1ቆሮ 11 ፥ 23 “ይህንም ለመታሰቢያዬ አድርጉት ”የሚለው ቃል ሥጋውንና ደሙን በምንቀበልበት ጊዜ ስለሰው ልጆች ሲል በቀራንዮ አደባባይ የተቀበለውን መከራና በልባችን ውስጥ የተሳለውን አምላካዊ ፍቅሩን እያስታወስን እንድንኖር ነው መታሰቢያ የሚለው ቃል የሚያመለክተው የማይረሳ ነገርን ነውና። ገላ 3፥1
ጌታችን ይህን ምሥጢር ከማሳየቱ (ከመመስረቱ) በፊት በዮሐ 6 ፥ 25-8። “ሥጋዬን ካልበላችሁ ደሜንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም ሥጋዬን የበላ ደሜንም የጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው። ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ (ሕይወትን የሚሰጥ) ነው ”በማለት ስለምሥጢረ ቁርባን በስፋት አስተምሯል። ክፍል ፪ ይቀጥላል
እግዚአብሔር አምላክ ከቅዱስ ስጋው ከክቡር ደሙ እንድንሳተፍ መልካም ፍቃዱ ይሁንልን። አሜን!
ምንጭ:- የጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ሰንበት ት/ቤት የተልኮ ትምህርት የመማሪያ መጽሐፍ
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
23 сентября 2024 14:00
መስቀል ብርሃን ነው
መስቀል ብርሃን ነው ለመላው ዓለም
ፍቅርን የሚያድል የሚሰጥ ሰላም
መድኅን ክርስቶስ በደሙ ያከበረው
ለክርስቲያን መስቀል ትምክህት ነው
አዝ
መስቀል ብርሃን ነው ኢየሱስ ክርስቶስ
መስቀል ብርሃን ነው የነገሰበት
መስቀል ብርሃን ነው ከሳሹ ዲያብሎስ
መስቀል ብርሃን ነው የተጣለበት
መስቀል ብርሃን ነው ስሙን ለሚፈሩ
መስቀል ብርሃን ነው ምልክት የሆነ
መስቀል ብርሃን ነው የእኛ ምርኩዛችን
መስቀል ብርሃን ነው ቅዱስ መስቀሉ ነው
አዝ
መስቀል ብርሃን ነው ከቀስት እንድናመልጥ
መስቀል ብርሃን ነው የሆነን መከታ
መስቀል ብርሃን ነው ለቅዱስ መስቀሉ
መስቀል ብርሃን ነው ይገባል ሰላምታ
መስቀል ብርሃን ነው እንሰግድለታለን
መስቀል ብርሃን ነው እግሩ ለቆመበት
መስቀል ብርሃን ነው ለጌታችን ዙፋን
መስቀል ብርሃን ነው ሞት ለተረታበት
አዝ
መስቀል ብርሃን ነው ሥጋው ተቆርሶበት
መስቀል ብርሃን ነው ፈሶበታል ደሙ
መስቀል ብርሃን ነው በዛልን ይቅርታው
መስቀል ብርሃን ነው በዛልን ሰላሙ
መስቀል ብርሃን ነው በትምህርተ መስቀል
መስቀል ብርሃን ነው እናማትባለን
መስቀል ብርሃን ነው ሞትን አሸንፈን
መስቀል ብርሃን ነው ክፉን እናልፋለን
አዝ
መስቀል ብርሃን ነው የቤተክርስቲያን
መስቀል ብርሃን ነው መሰረቷ እርሱ ነው
መስቀል ብርሃን ነው ክብር እና ውበቷ
መስቀል ብርሃን ነው ጌጥ ጉልበቷ ነው
መስቀል ብርሃን ነው ተዐምርን የሚያደርግ
መስቀል ብርሃን ነው ድንቅን የሚሰራ
መስቀል ብርሃን ነው የሚገለጥበት
መስቀል ብርሃን ነው የአምላካችን ስራ
ዘማሪት ኢየሩሳሌም አለሙ 💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
23 сентября 2024 06:01
መስከረም ፲፫
በዚች ቀን ታላቅና ቅዱስ የሆነ የቂሣርያ ሊቀ ጳጳሳት ባስልዮስ ላደረገው ተአምር መታሰቢያ ሆነ።
በአንድ ወቅት አንድ ጐልማሳ አገልጋይ የጌታውን ልጅ ስለወደዳት ወደ አንድ ከሀዲ ሥራየኛ ሔደ። ሥራየኛውም የክህደት ደብዳቤ ጽፎ ሰጠው። ወደ አረሚ መቃብርም ሒዶ በመንፈቀ ሌሊት ደብዳቤዋን ይዞ ወደላይ እጁን አንሥቶ በዚያ እንዲቆም አዘዘው። አንድ ሰይጣንም መጥቶ ያቺንም የክህደት ደብዳቤ ከእጁ ወሰደ። ዲያብሎስም ክርስቶስን ክጃለሁ ብለህ ፃፍ እና የምትፈልገውን አደርግልሀለው አለው። እርሱም የክህደቱን ቃል ጻፈለት።
በማግስቱ ጠዋት በሃገረ ገዥው ቤት ታላቅ ግርግር ሆነ። ልጃቸው "ያን አገልጋይ ካላጋባችሁኝ ራሴን አጠፋለሁ" አለች። ቢለምኗትም ልትሰማ አልቻለችም። ወላጆቿ ግራ ስለተጋቡ ከምትሞት ብለው እያዘኑ ልጃቸውን ከአጋንንት ጋር ለተዛመደ ሰው ሰጡ። እነርሱ ተጋብተው ኑሯቸውን ቀጠሉ። ወላጆች ግን ስለአንድ ልጃቸውን ይጾሙ ይጸልዩ ነበር። አንድ ቀንም ባሏን ጠርታ "ቤተ ክርስቲያን ተሳልመህ፤ ቆርበህ፤ ስመ እግዚአብሔር ጠርተህ፤ ታውቃለህ?" አለችው። እርሱም "በጭራሽ አላውቅም" አላት። "ለምን?" ብትለው የሆነውን ነገር ሁሉ ነገራት። ለረዥም ሰዓት አለቀሰች። ፈጥናም ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ዘንድ ሒዳ ከእግሩ ሥር ወድቃ አለቀሰች።
ቅዱሱም ያን ሰው "መዳን ትፈልጋለህ?" አለው። ሰውየው መልሶ "ያቺን ደብዳቤ መመለስ የሚቻል ቢሆንማ እፈልግ ነበር" አለው። ወደ ራሱ በዓት ወስዶ አስገባውና በ4 አቅጣጫ በመስቀል አተመው። "ከ3 ቀን በሁዋላ እመጣለሁ" ብሎት ሔደ። ቅዱሱ ያለ ዕረፍት ይጋደልም ጀመር። በ3ኛው ቀን መጥቶ "እንዴት ነህ?" አለው "አባቴ! አጋንንት አሰቃዩኝ" አለው፤ "አይዞህ!" ብሎት ወጣ። በ6ኛው ቀን መጥቶ "አሁንስ?" አለው:: "አባ! ስቃዩ ቀረልኝ: ግን ደብዳቤዋን እያሳዩ ያስፈራሩኛል" አለው:: "በርታ" ብሎት ሔደ።
እንዲህ በ3 በ3 ቀናት እየተመላለሰ ለ13 ጊዜ ጠየቀው። በ39ኛው ቀን መጥቶ "ዛሬ ምን አየህ" ቢለው "አባ! አጋንንትን ከእግርህ በታች ስትረግጣቸው አየሁ" አለው። ቅዱስ ባስልዮስ በ40ኛው ቀን ደወል ደውሎ መነኮሳት ካህናትና ምዕመናንን ሰብስቦ ያን ሰው ከመሃል አቁሞ "እግዚኦ በሉ" አላቸው። ሲጨርሱም ለሰይጣን የሰጠው የክህደት ደብዳቤ ከሰይጣን እጅ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ወደቀ ሁሉም ደስ ብሏቸው ምስጉን እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ይህንን ቅዱስ አባት ባስልዮስን እያከበሩ ወደ ቤታቸው ገቡ።
በረከቱ ይደርብን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
22 сентября 2024 12:00
ብዙ ልጆች አሉት
ብዙ ልጆች አሉት ለስሙ ምስክር
በዙሪያው ያሉትን አብቅቷል ለክብር
ስለፍፁም ምልጃው ለኔግን ይለያል
መላአኩ ሚካኤል ስለው ደስ ይለኛል
አዝ
ከመላእክት ክብሩ ከፍ ከፍ ብሎ
በአምላክ የተሾመ ዘንዶውንም ጥሎ
አሳዳጊዬነው ሆኖ እናት አባቴ
ሚካኤል ባለበት ይሸሻል ጠላቴ
አዝ
ከሚታየው ሁሉ ልቤ ከሚፈራው
ካላየሁት ነገር ጠላት ከሰወረው
ያድነኛል ፈጥኖ በመንገዴ ወቶ
ሚካኤል ሀያሉ ክንፎቹን ዘርግቶ
አዝ
በባህራን ታሪክ በነተላፊኖስ
በአፎምያ መትረፍ በነ ዱራታኦስ
በነብዩ ዳንኤል መች ይፈጸምና
የሚካኤል ስራ ይቀጥላል ገና
አዝ
በጉዞ የረዳችሁ በባህር በየብሱ
ፈጥኖ ደርሶላችሁ እንባን ስታፈሱ
ስለታችሁ ሰምሯል ቁሙ ለዝማሬ
በሚካኤል ምልጃ የቆማችሁ ዛሬ
አዝ
ክብር ለሚገባው ክብርን እንሰጣለን
ንጉሥ ለወደደው እንሰግድለታለን
እንኳን ለሚካኤል ለሚቆም ጌታ ፊት
ክብርን እንሰጥ የለ ለምድር ሹማምንት
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
22 сентября 2024 06:26
መስከረም ፲፪
በዚህችም ቀን ደግሞ በኤፌሶን ከተማ የቅዱሳን፤ የሁለት መቶ ኤጲስቆጶሳት ስብሰባ ሆነ ይህም ለታላላቆች ጉባኤያት ሦስተኛ ነው።
በወቅቱ ክፉ መናፍቅ ንስጥሮስ ተነስቶ የእስያ አብያተ ክርስቲያናትን አወካቸው። ትምሕርቱም ክርስቶስን 2 አካል: ባሕርይ ነው (ሎቱ ስብሐት!) ማለትም እመቤታችንም የወለደችው ሰውን ነው ስለዚህ እመአምላክ አትባልም (ላቲ ስብሐት) ብሎ ነበር። ነገሩን ቅዱስ ቄርሎስ በሰማ ጊዜ ወዳለበት ሒዶ ቢመክረውም ንስጥሮስ ሊሰማ አልፈለገም:: በዚህ ምክንያት በቁስጥንጥንያ ንጉሥ ትዕዛዝ በኤፌሶን ታላቅ ጉባኤ እንዲሰበሰብ ተደረገ።
አፈ ጉባዔው ቅዱስ ቄርሎስ ነበርና በጉባዔ ፊት ንስጥሮስን ተከራክሮ ረታው። ምላሽም አሳጣው። የሰይጣን ማደሪያ ንስጥሮስ ግን አላምንም በማለቱ ተወግዞ ተለየ። ቅዱሳን ሊቃውንቱም በቅዱስ ቄርሎስ አርቃቂነት 12 አንቀጾችን አዘጋጅተው ወደ ዓለም ሁሉ ላኩ።
በኋላም ቅዱስ ቄርሎስ ንስጥሮስን ጠርቶ
በድንግል ማርያም እመን። እርሷ ከልጇ ታስታርቅሃለች
ቢለው በድጋሚ "እንቢ" አለው። ያን ጊዜ ሊቁ ለአምላክ እናት ያልታዘዘ ምላስህ ላንተም አይታዘዝህ ብሎ ረገመው። ወዲያው ምላሱ ተጐልጉሎ ወጥቶ ደረቱ ላይ ወደቀ። እንደ ውሻ እየተዝረከረከ ሂዶ ከወዳጆቹ ጋር ቁሞ ሳለ መሬት ተከፍታ ውጣዋለች።
በረከታቸው ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
21 сентября 2024 19:41
ሰላም ውድ የዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች እንደምን ዋላችሁ? እግዚአብሔር ይመስገን።
መንፈሳዊ የዜማ ስቱዲዮ ያላችሁ ወንድም እህቶች በውስጥ በኩል መልዕክት ይላኩልን። የምታውቁም ካላችሁ ጠቁሙልን @ 📩
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
21 сентября 2024 06:05
መስከረም ፲፩
በዚህችም ቀን በእስክንድርያ አገር ትህትናን ገንዘብ ያደረገች ቅድስት ታዖድራ አረፈች።
ቅድስት ታዖድራ እድሜዋ በደረሰ ግዜ ወላጆቿ ያመጡላትን ባል እሺ ብላ አገባች። በሥጋ ወደሙም ተወስነው ኖሩ። አንድ ቀን ግን ከቤተክርስቲያን ስትመለስ፤ በመልኳ ምክንያት ለኃጢአት ይፈልጋት የነበር አንድ ጎረምሳ ያዛት። በአቅምም አልቻለችውም፤ የሚፈልገውንም አድርጎ ከክብር አሳነሳት።
ታላቅ ኀዘን አዘነች፤ መሪር የሆነ ልቅሶንም አለቀሰች። የወንዶችንም ልብስ ለብሳ ወንድ መስላ ስሟንም ቴዎድሮስ በማለት በወቅቱ የሴቶች ገዳም አልነበረምና የወንዶች ገዳም ገባች። የምንኩስና ልብስንም ለበሰች። ሰይጣን ግን ፈተናውን አጸናባት።
በአንድ ወቅትም አንድ ወንድ ከአንዲት ብላቴና ጋር አመነዘረ፤ እርሷም ወንድ ልጅ ወለደች። ወላጆቿም ድንግልናሽን ያጠፋው ማነው ብለው ጠየቋት። ሰይጣንም በእርሷ አድሮ፤ በገዳም ውስጥ የሚኖር አባ ቴዎድሮስ የሚባል ነው አለች። ወላጆቿም የተወለደውን ልጅ ወስደው ለገዳሙ አበምኔት የአባ ቴዎድሮስ ልጅ ነው ብለው ሰጡት።
አበምኔቱም ቅድስት ታዖድራን ልጁን አስይዘው ከገዳም አባረሯት። በበረሀም በብዙ ፈተና ሰባት አመት ኖረች። በኋላም ዳግመኛ ተቀብለው ወደ ገዳም አስገቧት። ጥቂት ቀንም ኖረች፤ መልካም ተጋድሎዋንም ፈጽማ በዚህች እለት አረፈች።
በረከቷ ይደርብን! አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
20 сентября 2024 19:55
ንስሐ
ንስሐ ማለት ሐዘን፣ፀፀት፣ ቁጭት፣ ቀኖና፣ የኃጢአት ካሣ ማለት ነው፡፡ ንስሐ አንድ ሰው በሠራው ጥፋት፣ ባደረገው ስህተት፣ በፈጸመው ኃጢአት ማዘኑና መፀፀቱን ዳግመኛም ያንን የመሰለ ኃጢአት ላለማድረግ የሚወስነው ውሳኔ ነው፡ ንስሐ የመንግሥተ ሰማያት መግቢያ በር ነው፡፡ በሌላ አገላለፅ ደግሞ ንስሐ ማለት ወደ እግዚአብሔር መመለስ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ፣ ከኃጢአት መራቅ፣ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት መመለስ ነው።
ንስሐ ለመግባት ስናሳብ ከታች የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ማሟላት አለብን፦1. በአጥቢያችን ከሚገኝ ቤ/ክ ክህነት ያላቸው በአገልግሎት ላይ ያሉ መልካም መንፈሳዊ ምግባር ያለቸውን አባቶች የንስሐ አባት መያዝ፤
2. የሰራነውን ኃጢአት ማመንእና በሰራነው ኃጢአት ከልብ አብዝተን መፀፀት፣ማዘንና ማልቀስ፤
3. እግዚአብሔር ይቅር እንዲለን በፍጹም ትህትና ራስን በማዋረድ መጠየቅ፤
4. ከእኛ ኃጢአት ይልቅ የእግዚአብሔር ቸርነትና ይቅር ባይነት እንደሚበልጥ እና ይቅር እንደሚለን ያለጥርጥር ፍጹም ማመን፤
5. ወደ ንስሐ አባታችን ሄደን ንስሐ ለመግባት እና ቀኖናችንን ለመቀበል ማሰብ እና መወሰን፤
6. ከልጅነት እስከ ዕውቀት የሰራናቸውን ኃጢአቶች ለማስታወስ መሞከር ከተቻለም ለማስታወስ ይረዳን ዘንድ በጽሑፍ መያዝ፤
7. ዳግም ወደ ሰራነው ኃጢአት እንደማንመለስ ለራሳችን ቃል መግባትና መወሰን፣ኃጢአትን መጸየፍ፤
8. ወደ ንስሐ አባታችን ሄደን የሰራነውን ኃጢአት ሳንደብቅ በግልፅ መናዘዝ።
9.የሚሰጠንን ቀኖና በትክክል መተግበር፤
10. ዳግም ወደ ኃጢአት እንዳንመለስ ራሳችንን በቃለ እግዚአብሔር ማነጽ፤
11. ዳግመኛ ለንስሐ መዘጋጀት።
ንስሐ ከሚደገሙ ምስጢራት መካከል አንዱ ነው። ሰዎች እንደመሆናችን በተደጋጋሚ በኃጢአት እንወድቃለን ስለዚህ በተደጋጋሚ ንስሐ ልንገባ ይገባናል ማለት ነው። ኃጢአት ለንስሐ አባት መናዘዝ ለምን አስፈለገ? ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያዘዘው ትዕዛዝ ስለሆነ ነው።
ሄደህ ራስህን ለካህን አሳይ፡ ለእነርሱም ምስክር እንዲሆን ስለመንጻትህ ሙሴ እንዳዘዘ መሥዋዕት አቅርብ አለው። ሉቃ.፭፥፲፬
ንስሐ ከገባን ቀኖናችንን በስርዓቱ ከፈፀምን በኋላ ንስሐችንን ፍፁም የሚያደርገው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል ነው። ዮሐ 6፥33
ብዙዎቻችን መቁረብን እንደ ትርፍ ነገርና በዕድሜ የተገደበ ለአዛውንቶች ብቻ አድርገን ስለምንቆጥር ለመቀበል ዝግጁ አይደለንም። ነገር ግን ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ቅዱስ ቁርባን የግድ ያስፈልገዋል። ቀኖና የተቀበልንበት በደላችን የሚሰረየው ሥጋውን ስንበላ፣ ደሙንም ስንጠጣ ነውና። ንስሐ ገብተን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ለመቀበል ያብቃን። አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
20 сентября 2024 06:04
መስከረም ፲
በዚህች ዕለት ጼዴንያ በምትባል አገር ሥጋ የለበሰች ከምትመስል፤ ከሠሌዳዋም ቅባት የሚንጠፈጠፍባት የእመቤታችን የድንግል ማርያም ሥዕል ተዐምር ተገለጠ።
ይህችን ሥዕል የሳላት ቅዱስ ሉቃስ ነው። ወደ ጸዴንያ እንዴት መጣች ቢሉ፤ አንዲት ማርታ የምትባል ሴት ነበረች በቤቷም እንግዳ ትቀበል ነበር። ድንግል ማርያምንም አብዝታ ትወዳት ነበር። በአንዲት ቀንም ስሙ ቴዎድሮስ የሚባል መነኩሴ በእንግድነት መጣ። በማግስቱ ስትሸኘው ወዴት ነህ ብላ ጠየቀችው። እርሱም ወደ ኢየሩሳሌም እንደሆነ ነገራት። እርሷም ሲመለስ የእመቤታችንን ሥዕል አምጣልኝ አለችው።
ከዚህም በኋላ ከቦታው ደርሶ ሥዕሏን ሳይገዛ ተመለሰ፤
በመንገድም ሥዕሏን ለምን አልገዛህም? የሚል ድምጽ ሰምቶ ተመልሶ ገዛ። በጎዳናው እየተመለሰ ሳለም የሚያስፈሩ ወንበዴዎች፤ ኋላም አንበሳ ገጠመው፤ የያዛት ሥዕልም ቃል አውጥታ አዳነችው።
አባ ቴዎድሮስም ይህን ድንቅ ተአምር ባየ ግዜ ሥዕሏን ወደ ሀገሩ ሊወስዳት ወደደ። በሌላ ከተማም አድርጎ ሊሄድ መርከብ ተሳፈረ።
በመርከቧ ሳለም ታላቅ ነፋስ ተነስቶ አቅጣጫውን አስቀይሮ ወደ ጸዴንያ ወሰደው። ኋላም ቢመሽበት ማርታ ቤት ሄደ እራሱን ግን አልገለጠም። በማግስቱም ተሰውሮ ከከተማው ሊወጣ ቢሞክር መውጫው ጠፍቶት ሲዞር ውሎ ተመለሰ። እንዲህም እያለ ሶስት ቀን ሆነው። ማርታም ይህን ተመልክታ ምን እንደሆነ ጠየቀችው። እርሱም ሁሉንም ነገራት።
በኋላም የመነኩሴውን እጅና እግር ስማ ሥዕሏን ተቀበለች። በታላቅ ክብርም አስቀመጠቻት። ያም መነኩሴ እስከሚሞትበት ቀን ድረስ የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ሥዕል እያገለገለ ኖረ።
የእመቤታችን በረከት ይደርብን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔርምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
19 сентября 2024 12:03
ምክንያት ስላለኝ ነው
ምክንያት ስላለኝ ነው የምዘምርልሽ
ምክንያት ስላለኝ ነው ቅኔ እምቀኝልሽ
አሁንም ይብዛልኝ ፍቅርሽ/2/
ከዚህ በላይ እንዳመሰግንሽ
አዝ
አውቃለሁ ከደጅሽ ምን እንዳገኘሁኝ
አስታውሰዋለሁ ሸክሜን እንደጣልኩኝ
የለመንኩሽ ሁሉ መቼ ከንቱ ቀረ
ሰይጣን ተመለሰ እያቀረቀረ
ጠላት ቢከፋውም ለአንቺ በመቆሜ
አደገድጋለው ደግሜ ደግሜ/2/
አዝ
ልቤ አርፏል በአንቺ በእናቴ አማላጄ
እንቅፋት እሾሁ አይበቅልም በደጄ
በሚጣፍጥ ዜማ በኤፍሬም ውዳሴ
ሳሸበሽብልሽ ትረካለች ነፍሴ
ጠላት ቢከፋውም ለአንቺ በመቆሜ
አደገድጋለው ደግሜ ደግሜ/2/
አዝ
ውለታ ያለበት የማይከፈል
ሲመሽም ሲነጋ ያመሰግናል
ማርያም ማርያም ይላል ምድርና ሰማዩ
በልጅሽ መከራ ሞቶለት ገዳዩ
ጠላት ቢከፋውም ለአንቺ በመቆሜ
አደገድጋለው ደግሜ ደግሜ/2/
ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
19 сентября 2024 05:00
በበጎ ፍቃዱ
በበጎ ፍቃዱ ሁሉ በእርሱ ሆነ (2)
ነገር ሁሉ በርሱ ተከናወነ (2)
አዝ
ሰማይና ምድር ግብሩን ተናገሩ
ፈጥሯቸዋልና እንዲገለጥ ክብሩ
በፈጠረው ፍጥረት የሚታወቅ እሱ
እግዚአብሔር ይመስገን ስሙን አወድሱ
አዝ
አልሆነም ያለእርሱ ፍፁም አንዳች ነገር
ብንመረምረው በሰማይ በምድር
ፍቃዱ ነውና መልካምና በጎ
ሰርቶ አሳይቶናል ሁሉን ውብ አድርጎ
አዝ
ክረምትና በጋ ሌሊትና ቀን
ሁሉን አሳይቶ ጌታ አስተማረን
ያደረገው ሁሉ እንከን የሌለው
ለዚህ ቅዱስ አምላክ ምሳሌም የለው
አዝ
ያዘነውን ያውቃል ደስም ያለውን
ሁሉ በእርሱ ፍቃድ ስለ ሚከወን
ችግርና ደስታም ለበጎ ነውና
ይህን ያስተማረን ይድረሰው ምሥጋና
ዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
18 сентября 2024 12:00
ቸሪቱ አማላጅቱ ሆይ
ቸሪቱ አማላጅቱ ሆይ
እናቱ ነሽና ለአዶናይ
በሥላሴ ፊት ስልጣን ያለሽ
የባህሪያችን መመኪያ ነሽ (2)
አዝ
ተጥሎ አዝኖ የኖረው
በልጅሽ ነው ቀናቀና ያለው
ንጉሱን ስትወልጂ በበረት
ተፈታ አዳም ከእስራት
ዘጸውዓ ስምኪ
ወዘገብረ ተስካርኪ
ብሎ ቃልኪዳን ሰጠሽ
ፍጥረትን እንዲምርብሽ
አዝ
ከሚያስብ ከማይዘነጋ
ፍጥረቱን ከሚያረጋጋ
ስላለሽ በእግዚአብሔር ቀኝ
ለኃጥአን ድንግል ለምኝ
ዘጸውዓ ስምኪ
ወዘገብረ ተስካርኪ
ብሎ ቃልኪዳን ሰጠሽ
ፍጥረትን እንዲምርብሽ
አዝ
ከሰማይ ሰማያት ወርዶ
መለኮት ሥጋን ተዋህዶ
አየነው በጠባብ ደረት
ወሰንሽው በአጭር ቁመት
ዘጸውዓ ስምኪ
ወዘገብረ ተስካርኪ
ብሎ ቃልኪዳን ሰጠሽ
ፍጥረትን እንዲምርብሽ
አዝ
ሰነድ ነሽ መታረቂያችን
ከተማም መማፀኛችን
በሰማይ በምድርም ያሉ
ለክብርሽ ቅኔ ይቀኛሉ
ዘጸውዓ ስምኪ
ወዘገብረ ተስካርኪ
ብሎ ቃልኪዳን ሰጠሽ
ፍጥረትን እንዲምርብሽ
ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ማርያም💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
18 сентября 2024 05:01
ኦ እንዳንተ ያለ ወዳጅ
ኦ እንዳንተ ያለ ወዳጅ አላገኘሁም እኔ
ኦ ውለታህን ሳስበው በእንባ ይመላል አይኔ/2/
አዝ
ከእናቴም ልጆች በላይ አንተ ውድ ነህ ለኔ
ወዳጅ እና ዘመዴ ጌታ የክፉ ቀኔ
ምን አለኝ እና ልስጥህ የሚነገር የሚወራ
እኔስ ተሸንፌያለሁ በእንባ ስምህን ልጥራ
አዝ
ተሰድጄ ብወጣ ወተሃል ከኔ ጋራ
ትናንትናን አለፍኩት ጠላቴን እያራራ
ደግሞ የነገውን ቀን አንተ ታውቃለህ ጌታ
ወጥመዴን ስበር እና አፌን ሙላው በእልልታ
አዝ
በእስረኞች መሃል ሆኜ ሰንሰለት ለብሻለሁ
አለም እውነት የላትም ፍትህ ካንተ እሻለሁ
መቼ ታጽናናኛለህ ወዳጅ እና ዘመዴ
አውጣኝ አውጣኝ ለሚልህ አንተ አታጣም ዘዴ
አዝ
መመላለስ አይደክምህ እኔን ማስታመም አንተ
ደክመህ አልፈህልኛል እጆቼን አበርትተህ
ሁሌ በሬ ላይ ቆመህ ደጃፌን የምትመታ
ግባ የክብር ንጉስ ብያለሁ ማራናታ
ብያለሁ ማራናታ/4/
ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…
ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit
17 сентября 2024 06:02
መስከረም ፯
በዚህች ቀን የመጥምቁ ዮሐንስ እናት፤ የከበረች ኤልሳቤጥ አረፈች።
ቅድስት ኤልሳቤጥ እድሜዋ በደረሰ ግዜ ካህን ለሆነው ለቅዱስ ዘካርያስ አጋቧት። ነገር ግን እስከ እርጅና ዘመናቸው ልጅ መውለድ አልቻሉም ነበር። የኤልሳቤጥ እድሜ 90 የዘካርያስም 100 ደርሶ ነበር። እግዚአብሔርም ትዕግስታቸውን እና ጽድቃቸውን ተመልክቶ በመልዐኩ ገብርኤል አብሳሪነት ታላቅ የሆነ ነቢይን ሰጣቸው።
የኤልሳቤጥ የስድስት ወር ጽንስም የድንግል ማርያምን ድምጽ በሰማ ግዜ በደስታ ዘሏል። ቅዱስ ዮሐንስም 2 ዓመት ከ6 ወር በሞላው ግዜም ንጉስ ሔሮድስ የተወለደውን ንጉስ /ኢየሱስ ክርስቶስን/ ለማጥፋት ተነሳ። አይሁዶችም ለንጉስ ሔሮድስ
ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ ሲወለድ ደግሞ የከፈተ ዮሐንስ የሚባል አለና እርሱን ግደል አሉት።
ቅድስት ኤልሳቤጥም ቅዱስ ዮሐንስን ይዛው ሸሸች። አባቱ ካህኑ ዘካርያስን ግን በቤተመቅደስ ውስጥ ገደሉት። ቅድስት ኤልሳቤጥም ዮሐንስን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 ዓመታት ቆየች። ቅዱስ ዮሐንስም 5 ዓመት በሞላው ግዜ በዚህች ዕለት ቅድስት ኤልሳቤጥ በዚያው በበርሃ አረፈች።
በረከቷ ይደርብን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር💚 @ 💚
💛 @ 💛
❤️ @ ❤️
Читать полностью…