ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የሥላሴን መንበር

የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት
ኪሩቤል በደመና ዙፋኑን ይዘውት
ድንግልን ከመሃል ሚካኤልን ከፊት
አእላፍ መላዕክት ሲሰግዱ በፍራት
እዩት ተመልከቱት የሰማዩን ድምቀት
እዩት ተመልከቱት የሰማዩን አባት

አዝ

የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት
እያሸበሸቡ የሰማይ መላዕክት
ካህናተ ሰማይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ
ይህን ልዩ ተ0ምር ሊያዩ የታደሉ
በጽድቅ ስራቸው በምድር ይታያሉ/ 2/
አዝ

የቅዱሳን ህብረት የቅዱሳን ሀገር
ሲያወድስ ይኖራል የሥላሴን ክብር
ጽድቅና ርህራሄ የተሞላ ሰማይ
እግዚአብሔር ያድለን በትንሳኤ እንድናይ/2/
አዝ

የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት
እያሸበሸቡ በሰማይ መላዕክት
ካህናተ ሰማይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ
ይህን ልዩ ተዐምር ሊያዩ የታደሉ
በጽድቅ ስራቸው በምድር ይታያሉ/ 2/

ሊቀ መዘምራን ይልማ ሀይሉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የተወደደ ቀን

የተወደደ ቀን የተወደደ ዓመት
ወደ አባቴ መቅደስ የተመለስኩበት
አንባር ቀለበትን የተሸለምኩበት
የተወደደ ዓመት

አዝ

አምሽቶ የመጣ አይገባም አትበሉ(2)
አባክኖ የመጣ አይገባም አትበሉ(2)
ፍቅር ስለሆነ እግዚአብሔር ለሁሉ(2)
ልጅ ቤቱን ይወርሳል እንደተስፋ ቃሉ(2)
አዝ

ከናዝሬት መልካም ሰው አይወጣም እያሉ(2)
ፊልጶስ ናትናኤል ይነጋገራሉ(2)
አድርጎታልና ውሀውን ወይን(2)
ዛሬም ለውጦኛል ወስዶታል ልቤን(2)
አዝ

እኔ ነኝ አላማው እኔ ነኝ ሀሳቡ(2)
አባቴ ደግ ነው የሚራራ ልቡ(2)
ዘጠና ዘጠኙ ታምነውት እያለ(2)
አንዱን ይፈልጋል ወዴት ነህ እያለ(2)
አዝ

ሁሉን አይቻለሁ ሁሉን መርምሬአለሁ(2)
አለም ካንተ ሌላ እንደሌለ አውቃለሁ(2)
እንደማይለወጥ አባትነትህ ወዳጅነትህ
ጠፍቼ ስመጣ አየሁት ልጅህ(2)

ዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስከረም ፮

በዚህች ዕለት ታላቅ ነቢይ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ አረፈ። ታላቁ ነቢይ ኢሳይያስ ከተናገራቸው ትንቢቶችም አንዱ በትንቢተ ኢሳይያስ 7፥14

"ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች"

የሚል ነበር ።በወቅቱ የነበሩ አንዳንድ ክፉ ሰዎች ግን ለንጉስ ሕዝቅያስ "ይህ ትንቢት ላንተ ነው ድንግል የተባለችዋ ኢየሩሳሌም ስትሆን ወንድ ልጅ የተባለው ደግሞ አንተ ነህ" አሉት።

ንጉሱም ይህን ሰምቶ አልገሰጻቸውምና። እግዚአብሔርም በንጉሱ ተቆጥቶ ኢሳይያስን ላከው። እንዲህም አለው
ትሞታለህ እንጂ አትተርፍምና ቤትህን ሥራ። መጽ ነገ ካልዕ 20:1

ይህ እንደሆነ ንጉሱ በጽኑ ታመመ ደከመ። ንጉሡም በልቡ ተጸጽቶ ጌታ ሆይ ይቅር በለኝ ሲል ተማጸነ። እግዚአብሔርም ንስሐውን እንደተቀበለው እና በዘመኑም ላይ 15 ዓመታትን እንደጨመረለት ነቢዩ ነገረው።

በኋላ ዘመንም ንጉስ ምናሴ ጣዖትን ያመልክ ነበር። ነቢዩም በአደባባይ ገሰጸው። ምናሴም በዚህ ተበሳጭቶ ነቢዩ ኢሳያስን በዚህች ዕለት በእንጨት መጋዝ ለሁለት አሰነጠቀው። ቅዱሱም ተጋድሎውን ፈጸመ።

በረከቱ ይደርብን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የዕለቱን ስንክሳር በአጭሩ ማንበብ ይፈልጋሉ፤ ጠዋት እና ማታ የምንለቃቸውንም ዝማሬዎች ማዳመጥ ይፈልጋሉ፤ በተጨማሪም የምንለቃቸውን ትምህርቶች ማግኘት እና ማንበብ ይፈልጋሉ። ነገር ግን ዝንጉ አይምሮ ነውና ያለን ማስታወስ አቅቶን የዝማሬ ዳዊት ቻናልን ከፍተን ሳናይ ከቴሌግራም እንወጣለን። ይህም የሚሆንበት አንዱ ምክንያት ቴሌግራም ላይ ካሉ ብዙ ቻናሎች መሀከል ስለሚደበቅ ነው።

በመሆኑም ቻናላችንን ከላይ Pin በማድረግ ወደ ቴሌግራም በሚገብ ግዜ ሁሉ ከፊት ለፊት ስለሚያገኙት የምንለቃቸው ነገሮች በሙሉ አያመልጧችሁም።

Pin ለማድረግ ይህን ቅደም ተከተል ይከተሉ።

1. የዝማሬ ዳዊት ገጽን ለትንሽ ግዜ ጫን ብለው ይቆዩ።
2. ከላይ ምስሉ ላይ እንደሚታየው ቻናሉን Mark ካደረገላችሁ በኃላ Pin የሚል ጽሁፍ ካያችሁ እርሱን መንካት ወይም በቀይ ሰንጠረዥ የጠቆምናትን ምልክት መንካት።

በዚህ መልኩ ቻናላችንን PIN ማድረግ ትችላላችሁ።
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስከረም ፭


በዚህች ቀን የከበረች ሶፊያ ከሁለት ልጆቿ አክሶስ እና በርናባ ጋር በሰማዕትነት አረፈች።

ቅድስት ሶፍያ አስቀድማ አረማዊት ነበረች ወላጆቿም ጣዖታትን የሚያመልኩ ነበሩ። እርሷም በልቧ የወላጇቿ ሃይማኖት ከንቱ እንደሆነ ከመረመረች በኋላ ወደ መኖፌ ኤጲስቆጶስም ሄዳ ክብር ይግባውና በጌታችን በክርስቶስ ታመነች። እርሱም ሃይማኖትን የቤተክርስቲያንን ሕግ አስተማራት።

ከዚሕም በኋላ ከልጆቿ ጋር በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ ስም አጠመቃት። የሀገሩ ገዢ ለጣዖት መስገድን ትታ ክርስቲያን እንደሆነች በሰማ ጊዜ ከልጇቿ ጋር ብዙ ስቃይን አሰቃያት። ገዢውም ልጇቿ አይተው ይፈሩ ዘንድ በጅራፍ ይገርፏት ዘንድ አዘዘ። ያን ጊዜም የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ ወርዶ እናታቸውን ከግርፋት ሲሰውራት አዩ።

ከዚህም በኋላ ወደ እስር ቤት ወስደው አሰሯት እራሷንም በሰይፍ ይቆርጡት ዘንድ አዘዘ የድል አክሊልንም ተቀበለች። ከዚህም በኋላ ልጆቿን ወደርሱ ይመለሱ ዘንድ አስፈራራቸው እንቢ ባሉት ጊዜም እያከታተለ አንገታቸውን አስቆረጠ።

ምስክርነታቸውንና ተጋድሏቸውን ፈጸሙ። ከመቃብራቸውም፤ በሽታውንና ደዌውን ሁሉ የሚፈውሱ ብዙ የሆኑ ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ።


የጻድቅ መታሰቢያው ለዘለዓለም
ይኖራል።
                   መዝ ፻፲፩፡ ቁ ፮


በረከታቸው ይደርብን
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ለውዳሴሽ ልትጋ

ለውዳሴሽ ልትጋ ስምሽ ግርማ አለው 2
እመቤተ ኧኸ እመቤተ ስልሽ እውላለው

ከልቤ አቀርባለው ምስጋናን ለስምሽ
ተመስክሮልሻል ብፅዕት ተብለሽ
የሰላምታ ድምፅሽ ያልነካው ማን አለ
ጽንሱ በማህፀን በደስታ ዘለለ

አዝ

ማርና ወተት ነው የስምሽ ስያሜ
እመቤተ ስልሽ ይቀላል ሸክሜ
ቅኔ ማህሌቱ ሰአታት መዝሙሩ
ያመሰግኑሻል ምድርና ጠፈሩ
አዝ

እናቱ ነሽና አንቺ ለኢየሱስ
አድሮብሽ ይኖራል እግዚአብሔር መንፈስ
ሰዓሊ ለነ ብዬ ቀኑን ጀምራለው
ልጅሽን አምኜ ነገም እኖራለው
አዝ

ነይ ነይ እልሻለው እንደት ካህናቱ
በሰዓታት ጸሎት ቆሜ በሌሊቱ
ዝም አልልም እኔ አወድስሻለው
ያለምን መከራ እረሳብሻለው

ዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አጥቷል ጎሎበታል

አጥቷል ጎሎበታል ብለህ ሳትንቀኝ
ለዚህ ያደረስከኝ ጌታዬ እኔ ማነኝ
ይሞላል አይቀርም ባንተ ሸለቆዬ
ጠብቃለሁና ቀንህን ጌታዬ

አዝ

ሀዘን ፅልመት ክፉ ዘመን
ቢገጥመኝም እንኴን
ያልፋል ሁሉም ታሪክ ሆኖ
በፊትህ ሲለካ
ማን ጎደለ ማን አፈረ አንተን የጠበቀ
ፀና ልቤ በእግዚአብሔር ይሄን እያወቀ
አዝ

ባለም ስፍራ ባይኖረኝም
ብሆንም ጎስቇላ
አምላኬ ሆይ ካንተ በቀር
አልሄድ ወደ ሌላ
ጌታዬ ሆይ በፍለጋ ወጣሁ ከመቃብር
ስመሰክር እኖራለሁ ስራህን ስናገር
አዝ

ቀን ለክተህ ጊዜን አይተህ
ሰውን የማትከዳ
ያለ ወረት ትመጣለህ እኔን ልትረዳ
ከእነ ኤልያስ ወንድሞቼ ባልስተካከልም
ማማ ሆነህ ከፍአረከኝ አንተ ሰው አጥልም
አዝ

እንደ እናት ልጅ እንዳልቆጥርህ
ከዚህም ትበልጣለህ
ካንተ በቀር ያፈቀረኝ
በምድር ስለሌለ ስለ
ስምህ መነቀፌ ክብሬ ነው ማረጌ
በምን መንገድ ላስደስትህ እንደምን አድርጌ

ዘማሪ ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የያሬድ ውብ ዜማ

የያሬድ ውብ ዜማ ድንግል እመቤቴ
ስጦታዬ ነሽ 2
በምን አንደበቴ እንዴትስ ባለ ቃል
ማርያም ልበልሽ 2

ምድርና ሰማዩ ተዓምርሽን ይንገሩ
ፍጥረታት በሙሉ ስላንቺ ይመስከሩ
ተነግሮ የማያልቅ ድንቅ ነው ስራሽ
ድንግል ሆይ እናቴ አምሳያም የለሽ
ማርያም ድንግል እረዳቴ
የምትደርሺልኝ ነይ ስልሽ በጭንቀቴ
ተአምርሽንም በአይኔ አይቻለሁ
ፅዮን ሆይ ስልሽ ድንግል ሆይ እጠግባለ

አዝ

የእግዚብሔር ጥበቡ በአንቺ ተገለጠ
የአዳም ዘር በሙሉ ከሞት አመለጠ
የመዳን ምክንያት ማርያም አንቺ ነሽ
ለፍጥረቱ ሁሉ መሠላል የሆንሽ
ነገን ባላውቅ እኔንም ቢያስፈራኝ
አንቺ ካለሽኝ በፍፁም አልወድቅም
በፊትሽ እንድቆም ለምስጋን
ማርያም ልበልሽ በትህትና
አዝ

ትውልዱ በሙሉ ለምስጋና ይቁም
በአንቺ ስለሆነ የቀረለት መርገም
አዳም ከነ ልጁ በሰማይ በምድር
ማርያም ማርያም ይበል ተዓምርሽን ይናገር
ጨለማውም ከፊቴ ተገፈ
ማርያም በምልጃሽ ልቤ አረፈ
ከጎኔ ነሽ ስልሽ እፅናናለሁ
እሳት ገደሉን ሁሉንም አልፈዋለሁ

ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በቸርነት በይቅርታው አሰበን

በቸርነት በይቅርታው አሰበን
በፍቅሩና በምሕረቱ ጎበኘን
አምላካችን በሞቱ ወደደን
አምላካችን በሞቱ ወደደን

ተነጥቆ ሰላም እረፍታችን
ላያድን ላይፈውስ ጽድቃችን
ተጥለን ስንኖር በሞት
በደምህ ወጣን አርነት
በደምህ ወጣን ነጻነት

አዝ

የጭንቀት የመከራ ዓመት
ተረሳ በኢየሱስ ሞት
በፍጹም ፍቅሩ ወደደን
በሞቱ ከሞት አዳነን
በሞቱ ከሞት አዳነን
አዝ

ህዝቡን ሲያስጨንቅ የነበረ
የጠላት ቅጥሩ ተሰበረ
ማልቀስ ቀረልን መቅበዝበዝ
ገነት ገብተናል በእርሱ ወዝ
ገነትን ወረስን በእርሱ ወዝ
አዝ

ሰማይና ምድር ተስማሙ
ታጥበዋልና በደሙ
ነፃነት አዋጅ ተሰማ
አዜምን የጽድቅን ዜማ
ዘመርን የጽድቅ ዜማ
አዝ

ህዝቡን ሲያስጨንቅ የነበረ
የጠላት ቅጥሩ ተሰበረ
ማልቀስ ቀረልን መቅበዝበዝ
ገነት ገብተናል በእርሱ ወዝ
ገነትን ወረስን በእርሱ ወዝ

ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በዝማሬ ዳዊት ቻናል የምትለቋቸው መልዕክቶች እኛ ጋር Not supported ነው የሚለን ብላችሁ መልዕክት ለላካችሁልን ተከታታዮች በሙሉ፤ እባክዎ ከስር ባስቀመጥነው ሊንክ የቴሌግራም መተግበሪያዎን ያዘምኑት /Update/ ያድርጉት።

https://play.google.com/store/apps/details?id=org.telegram.messenger

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🌼ተሰጥቶናል አዲስ አመት🌼

የአህዛብን  ፈቃድ ያረጋችሁበት
ጣዖትን በማምለክ ይኖራችሁበት
በምኞት በስካር በዘፈን
ያሳለፋችሁት ይብቃ ያለፈው ዘመነ

ያለ ልክ በመብላት በመጠጣት
በመስረቅ በመግደል በመዋሸት
የተመላለስ ነው በቂም በበቀል
የተተከለ አረም ከኛ ይነቀል
ተሰቶናል አዲስ ዘመን
ተሰቶናል አዲስ አመት
ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንኑርበት

አዝ

በከንቱ አንድከም በብዙ አንልፋ
ይህ የዓለም ጤዛ ነው ታይቶ የሚጠፋ 
በመንፈስ ቅዱስ ሃይል እንድንታደስ
በፍጹም ንስሐ አሁን እንመለስ
ተሰቶናል አዲስ ዘመን
ተሰቶናል አዲስ አመት
ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንኑርበት
አዝ

በድካም አይለቅ ዘመናችን
ቸርነቱ በዝቶ የተሰጠን
ብርሃናችንም በሰው ፊት ይብራ
ቅጠል ብቻ እንሁን ፍሬንም እናፍራ
ተሰቶናል አዲስ ዘመን
ተሰቶናል አዲስ አመት
ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንኑርበት
አዝ

ያለ ልክ በመብላት በመጠጣት
በመስረቅ በመግደል በመዋሸት
የተመላለስ ነው በቂም በበቀል
የተተከለ አረም ከኛ ይነቀል
ተሰቶናል አዲስ ዘመን
ተሰቶናል አዲስ አመት
ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንኑርበት

ዘማሪ በአቤል በገና ተማሪዎች
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስከረም ፪


በዚህች ዕለት የካህኑ የዘካርያስ ልጅ መጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዕረፍቱ ሆነ።

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ንጉሥ ሄሮድስን የወንድምህን ሚስት ልታገባ አልተፈቀደልህም እያለ ይዘልፈው ነበር። ዳግመኛም ሌላ ያደርገው ስለነበረው ክፉ ነገር ይገሥጸው ነበር። ቅዱስ ዮሐንስም በተግሣጽ ላይ ተግሣጽን በጨመረ ጊዜ ንጉሡ ቅዱስ ዮሐንስን ተቀየመውና በግዞት ቤት አኖረው።

በመጨረሻም ንጉሱ በዚህች ቀን ልደቱን ባከበረ ግዜ የሄሮድያዳ ልጅ በዘፈን አጥምዳ ቃል አስገባችው እርሱም የከበረች የቅዱስ ዮሐንስን አንገት ቆርጦ ሰጣት። አንገቱ ግን ክንፍ አውጥታ ትሰብክ ነበረ።

አበውም እንዲህ አሉ ;-
እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር።


ደቀ መዛሙርቱም ይህን በሰሙ ጊዜ
መጥተው በድኑን ወስደው ቀበሩት።

በረከቱ ይደርብን! አሜን
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ይህን ማድረግ ቀናችሁን ቀና ያደርጋል።


በ2017 ዓ.ም ሕይወታችሁን የሚለውጥ አንድ ልማድ ላጋራችሁ! ሁልግዜ ጠዋት ስራም ሆነ ትምህርት ከመጀመራችሁ በፊት በዕለቱ የሚታሰበውን የአንድ ቅዱስ ታሪክ ከስንክሳር አንብባችሁ ጀምሩ።

እንደው ግዜ አጥሮአችሁ ስንክሳር ማየት ካልቻላችሁ ወይም ስንክሳር ከሌላችሁ ግን ሁልግዜ ጠዋት ጠዋት አንድ ሰዓት ላይ በዝማሬ ዳዊት የቴሌግራም እና የፌስቡክ ገጽ የአንድ ቅዱስ ታሪክ ከስንክሳር በአጭሩ ስለምንለቅ እርሱን ሳያነቡ በፍጹም እንዳይውሉ። እንዲሁም ጠዋት የምንለቃቸውን ዝማሬዎችም በማድመጥ ቀናችሁን በመንፈሳዊነት ጀምሩ።

መልካም አዲስ አመት

የዝማሬ ዳዊት ገጽ አስተዳዳሪዎች
👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እግዚአብሔር የሚወዳችሁ እናንተም የምትወዱት ልጆቼ!

አዲሱ ዓመት የእውነት አዲስ ዓመት እንዲኾንላችሁ ካሻችሁ ነፍሳችሁን ከኀጢአት ቀንበር አላቋት እንጂ ድጋሜ በኀጢአት ሸክም አትጫኗት፡፡ አሮጌው ዓመት እንዳለቀ ስታዩ እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡

ወደሌላ ዘመን አሸጋግሯቸዋልና እግዚአብሔርን አመስግኑት፡፡ ልቡናችሁንም ውቀሱት፡፡ በዕሜአችሁ ስንት ጊዜ እያለፈ እንደ ኾነ እያሰባችሁም ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁት፡-

ቀናት እየሮጡ ነው፡፡ ዓመታቱም እየነጐዱ ነው፡፡ የዕድሜዬ መንገድም እየተጋመሰ ነው፡፡ ታዲያ ምን በጐ ምግባር ያዝኩ? ከዚህ ምድር የማልፍበት ቀን እየቀረበ ነው፡፡ ታዲያ ምን የጽድቅ ሥራ ሠራሁ? በዚህ ዕድሜዬ መሥራት የነበረብኝ ምግባር ትሩፋት ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ አልችልም፡፡ ታዲያ ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ የማልችላቸውም የጽድቅ ሥራዎች (ፆም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ አገልግሎት፣… ዕድሜ ሲገፋ ይከብዳሉና) እንዳቅሜ እያደረግኩ ነውን? በማለት ልቡናችሁን ጠይቁት፡፡


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🌼አምላክ ሆይ ባርክልን🌼

ውድ የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎስ በሰላም አሸጋገራችሁ።

የዝማሬ ዳዊት ቻናል ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን መልካም አዲስ ዓመትን ይመኛል። መልካም በዓል🌼🌼🌼

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አሥራት


ሰው እግዚአብሔር ከሰጠው ላይ አሥራትን ካልከፈለ እግዚአብሔር አምላክ ሰርቃችሁኛል ይላል።

አሥራት የሚለው ቃል ዐሠረ (ዓሥር)
አደረገ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ፍቺውም ከአሥር (10) አንድ ማለት ሲሆን ይህንንም ለእግዚአብሔር መስጠት ማለት ነው።አሥራት ሰው ጥሮ ግሮ ሠርቶ ከሚያገኘው ከላቡ ገቢ ለእግዚአብሔር ከአሥር አንድ እጁን ወይንም ከመቶ አሥር ክፍሉን ለእግዚአብሔር መሥጠት ማለት ነው።

አሥራት በሕገ ልቦናና በሕገ ኦሪትም ይሠጥ ነበረ።ለምሳሌ በሕገ ልቦና አብርሃም አባታችን ለካሕኑ ለመልከጼዲቅ አሥራትን እንደከፈለ በቅዱስ መጽሐፍ  ተገልጧል። አብርሃምም ከሁሉ አሥራት ሠጠው።ዘፍ ፲፬÷፳

አባታችን ያዕቆብም ቤቴል ብሎ በሰየማት በሎዛ ምድር እግዚአብሔር ቢገለጥለት በሥፍራው የእግዚአብሔር ቤት እንደሚታነጽና እርሱም አሥራት እንደሚያደርግ ቃልኪዳን አደረገ።
ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከአሥር እጅ አንዱን እሰጥሃለሁ። ዘፍ፳፰÷፳፪

እግዚአብሔር አምላካችን ሙሴን በሲና ተራራ ካዘዘው ትእዛዝ አንዱ አሥራትን ስለመክፈል ነው።ይሕም በዘሌ ፳፯÷፴፡፴፫ ተጽፎ ያለው ነው።ስለዚህ አሥራትን ማውጣት የአምላክን ሕግ መጠበቅና መፈጸም ነው።

ሰው እግዚአብሔር ከሰጠው ላይ አሥራትን ካልከፈለ እግዚአብሔር አምላክ ሰርቃችሁኛል ይላል።
ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም። የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው። ትን ሚል 3:8
አሥራት የሚከፈለው ለካሕናት መገልገያ በአጠቃላይ ለእግዚአብሔር መንግስት ማስፋፊያ ነው። ካሕናት ሙሉ በሙሉ ጊዜያቸውን ሁሉ አምላካቸውን እንዲያገለግሉ ሕዝቡንም እንዲጠብቁ ነው።

አሥራትን በዘመነ ወንጌልም በዘመነ ክርስትናም እንደሚፈጸም ክብር ይግባውና ጌታችን እንዲህ ብሎ አዟል።
የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ስጡ የማቴ ፳፪÷፳፩

እግዚአብሔር አምላክ ዘጠኙን ሊባርክልን አንዷን ብቻ ለኔ ሥጡኝ ሲለን ገንዘብ አምላኪዎች እንዳንሆን ከእርሱም ይልቅ ገንዘብን እንዳንወድ ወይም ለእርሱ ያለንን ፍቅር ያይበት ዘንድ ስለሚፈልግ  አሥራትን በኩራትን ምፅዋትንና ለጋስነትን አስተማረን አንድም ቸር ለጋስ መሆን እርሱን መምሰል ነውና። ስለዚህ እኛም ይህን በመረዳት ከምናገኛት ገቢያችን ላይ አነሰም በዛም ሳንል አስራታችንን በስርአቱና በጊዜው እናውጣ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ:- መጽሐፈ አሚን ወሥርዓት
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንደ ዝማሬ ዳዊት ገጽ ከሁለት አመት በፊት በቅዱስ ጊዮርጊስ ስዕል እና ቢራ ዙሪያ ትልቅ የሆነ የሚድያ ንቅናቄ ቢያደርግም ግቡን ሳይመታ ቀርቶ ነበር።

አሁንም የተጀመረው የግዜ ጩኸት ብቻ ሆኖ እንዳይቀር ነገሩን ከኛ በዘለለ ከላይ ባሉ አባቶቻችን ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። በሕግ ዕውቀት ያላችሁ የተዋህዶ ልጆችም ቤተ ክርስቲያናችሁ ትፈልጋቹሀለች። የኛን ክብር ማስጠበቅ እምንችለው እኛው ነን።

እንደ ማሳሰብያ ማስተላለፍ የምንፈልገው መልዕክት ግን በተለያዩ ሶሺያል ሚድያ ይህን ድርጊት በመቃወም የተለያየ ቪድዮ በምትሰሩ ግዜ የቅዱስ ጊዮርጊስን ስዕለ አድኅኖ ክብር በማያወርድ እና ኦርቶዶክሳዊ ሥነምግባርን በተላበሰ መልኩ ሊሆን ይገባል። በአንዳንድ ቦታ ያልተገባ ድርጊት ስላስተዋልን ነው።

/channel/ortodoxmezmur/12787

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ታላቅ በሆነው
  
ታላቅ በሆነው እምነትሽ ታመንኩኝ    
ካለሽበት ገስግሼ መጣሁኝ    
እናቴ ክብርሽን አንግሼ    
ቆምኩኝ እንደ ህፃን ታድሼ    
እናቴ ቅድስት አርሴማ    
ዝናሽ ለአለም ተሰማ  

አዝ

ስመጣ ባልጋ ነበረ    
ተስፋዬም የተሰበረ    
በእምነትሽ በጠበልሽ    
ሰው ሆኜ ቆምኩኝ ደጅሽ   
ልናገር ዝናሽን ላውራ    
ይደነቅ የአምላክሽ ስራ    
ተጋድሎሽ የእምነትሽ ፅናት    
ሆኖኛል የእምነቴ መብራት    
አዝ

ደምግባት ከንቱ ብለሽ    
ለሰማይ ክብር የታጨሽ    
የእምነቴ ሐሰረ ፍኖት    
በምልጃሽ አለሁኝ በህይወት 
የልቡን ለነገረሽ    
ፈጥኖ ይደርሳል መልስሽ    
ዘንባባሽ ህይወት ይዘራል    
የጠራሽ ማን አፍሮ ያውቃል    
አዝ

እርዳታሽ የደረሰለት    
ያመጣል የልቡን ስለት    
ላመኑሽ ፈውስሽ ቅርብ ነው    
ባንቺ አፍሮ የሄደ ማነው
የልቡን ለነገረሽ    
ፈጥኖ ይደርሳል መልስሽ    
ዘንባባሽ ህይወት ይዘራል    
የጠራሽ ማን አፍሮ ያውቃል      
አዝ

ስመጣ ባልጋ ነበረ    
ተስፋዬም የተሰበረ    
በእምነትሽ በፀበልሽ    
ሰው ሆኜ ቆምኩኝ ደጅሽ    
ልናገር ዝናሽን ላውራ    
ይደነቅ የአምላክሽ ስራ    
ተጋድሎሽ የእምነትሽ ፅናት    
ሆኖኛል የእምነቴ መብራት።    
 
ዘማሪት ሲስተር ሊድያ ታደሠ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በዘባነ ኪሩብ

በዘባነ ኪሩብ ለሚቀመጠው
በእሳት ድንጋዮች ቅጥሩን ላጠረው
ዘምሩ ለእግዚአብሔር ለጌታ ዘምሩ
የተከበረ ነው በሰማይ በምድሩ 2

አዝ

ኢሳይያስ ሲያየው እጅግ አፈረ
የተፈራ ነው የተከበረ
የሰማይ ደጆች ተንቀጠቀጡ
ለቅዱስ ስሙ ክብርን ሲሰጡ
አዝ

ያልተቀደሰ ለምጽ ያነደደው
እንዴት ይችላል ሊያመሰግነው
በል ፍቀድልኝ ፍቅር ነህና
ልግባ መቅደስህ ላቅርብ ምስጋና
አዝ

ዙፋንህ ታየኝ ትምክህቴ ሆይ
ስትመሰገን በሰማይ ላይ
ሲያመሰግንህ ያልተደሰተ 
ባይተዋር አልሁን አልውጣ ካንተ
አዝ

ቅኔ የሞላበት ያን ሰገነት
ልቀላቀለው ተመኘው በእውነት
ልዘምርልህ ባይገባኝም
ዝም የሚል ልሳን አልሰጠኸኝም

ሊቀ መዘምራን ቴድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አምላኬ መቅደስህን እወደዋለሁ

አምላኬ መቅደስህን እወደዋለሁ
በውስጡ ለመኖር እናፍቃለሁ
ሰላም እንድሆን በቤት በደጄ
ወደ ማደርያህ ልምጣ ማልጄ

እንድሰለጥን በመላእክት ዜማ
የሕወትን ቃል ከአፍህ ልስማ
እንዲቀል ሸክሜ ከትክሻዬ
ወደ ዙፋንህ ልቅረብ ጌታዬ
መልካም በሚልዋት በመቅደስህ
ሳመልክህ ልኑር ስማጸንህ

አዝ

ተመለሰልኝ ደስታ ሰላሜ
ቤትህ መጥቼ በመሳለሜ
ስጋዬም ዳነ ታደሰች ነፍሴ
ወደ ማደርያህ በመግስገሴ
መልካም በሚልዋት በመቅደስህ
ሳመልክህ ልኑር ስማጸንህ
አዝ

የተማርኩባት የሰላም ቅኔ
የተባረከው እድሜ ዘመኔ
የተለወጠው ሞቴ በሕይወት
እኔ እናፍቃለሁ የእግዚያብሔርን ቤት
መልካም በሚልዋት በመቅደስህ
ሳመልክህ ልኑር ስማጸንህ
አዝ

የሰማይ ዜማ የሚሰማባት
ሰዎች ከሀዘን የሚጽናኑባት
የጸሎት ስፍራ የአምልኮት ቦታ
ቤተክርስትያን ውድዋ ስጦታ

ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ማርያም
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስከረም ፬


በዚህች ዕለት የእስክንድርያ ሊቀጳጳሳት አባ መቃርስ አረፈ።

አባ መቃርስ ከታናሽነቱ ጀምሮ በገድል የተጠመደ ነበር የምንኩስናንም ልብስ ሊለብስ ወዶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ወጣ።በዚያም መነኮሰ በምንኩስናም ያለውን ታላቅ ተጋድሎ ተጋደለ።

ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀጳጳስ አባ ሚካኤል በአረፈ ጊዜም ኤጲስቆጶሳቱ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሂደው አባ መቃርስን ሊሾሙት ተስማሙ። አባታችን ግን ለዚች ሹመት የተገባው አይደለሁም ብሎ ሹመቱን እንቢ አለ ቢሆንም ግን በገመድ አስረው ሾሙት

በሹመቱ ወራትም ከራሱ ከሚገባውን ግብር ለቤተክርስቲያን ይሰጣል ለድኖችና ለችግረኞችም ይመጸውታል እንጅ ከቤተክርስቲያን ገንዘብ ምንም ምን አልወሰደም። በሹመቱም ሃያ ሰባት ዓመት ኖረ እግዚአብሔርንም በአገልግሎት ደስ አሰኝቶ በዚህች ዕለት አረፈ።

በረከቱ ይደርብን! አሜን
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​​​የከበሮ ክፍል ምሳሌያዊ ትርጉም

የከበሮ ክፍል ምሳሌያዊ ትርጉም አለው። ምሳሌውን ግልጽ ለማድረግ ከታች ያለውን ስዕላዊ  መግለጫ እንመለከት እና ወደ ትንታኔው እንሂድ።

ከበሮ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው። ግራና ቀኝ ሲመታ ስንመለከልት  ጌታችን በአይሁድ እጅ በጥፊ መመታቱን ያስታዉሰናል።

፩. ሰፊው የከበሮው አፍ


የመለኮት ምሳሌ ነው። ይህ  የከበሮ አፍ የጌታችንን የባህሪ  አምላክነት  ምሉዕ በኵለሄ መሆኑን ስልጣኑ ወሰን ድንበር  እንደሌለው የሚያስታውሰን ነው። የአፉን መስፋት ስንመለከት በአጭር  ቁመት  በጠባብ ደረት ተወስኖ  የተገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ  በህልውና በመለኮት  ባሕርይ አባቱ ከአ ባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተስተካከለ ሁሉን የያዘ ሁሉን የሚገዛ መሆኑን እናስባለን።

፪. ጠባቡ የከበሮው አፍ


የትስብእት ምሳሌ ነው በመዝሙር ጊዜ 
እየተቆረቆረ ድምጽ የሚሰጠው ጠባቡ 
የከበሮ አፍ የወልድ እግዚአብሔርን በጠባብ ደረት በአጭር ቁመት ተወስኖ መገለጥ የሚያመለክተን ነው። ፍጥረታትን ሁሉ የሚገዛ እሱ በስልጣኑ ሽረት በመለኮቱ ኅልፈት የሌለበት ቢሆንም ስጋን ተዋህዶ ተገልጧል። ይህንን ጠባብ የከበሮ  አፍ  ስንመለከት ሁሉን የሚገዛ እሱ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት መወሰኑን እናስባለን። ዩሐ፤፩፡፩-፩፬

፫. ከበሮው የሚለብሰው ጨርቅ

  
ከበሮ የጌታችን ምሳሌ እንደሆነ ከላይ 
አይተናል። ከዚህ አንጻር የለበሰው ጨርቅደግሞ በዕለተ ዓርብ አይሁድ ጌታችንን ያለበሱት ጨርቅ (ቀይ ከለሜዳ) ምሳሌ ነው። 
''ልብሱንም ገፈው ቀይ ልብስ አለበሱት'' ማቴ 26:28


፬. በከበሮው ላይ የተለጠፈው ጠፍር

 
በጌታችን ጀርባ ላይ የታየው የግርፋት ሰንበር ምሳሌ ነው። ጠፍሩን በከበሮው ላይስንመለከት በጌታችን ጀርባ ላይ የታየውን ሰንበር እናስታውሳለን።
''እጆቼን እና እግሮቼን ቸነከሩኝ አጥንቶቼ ሁሉ ተቆጠሩ'' መዝ 21(22):16

እንዲል ጌታችን አጥንቱ እስኪቆጠር ጀርባው እስኪቆስል ተገርፏልና የዚያ
ምሳሌ ነው።

፭. የከበሮው ማንገቻ


የከበሮውን መምታት ስናስብ በአንገታችን የምናስገባው ማንገቻ ጌታችንን አስረው  የጎተቱበት ገመድ ምሳሌነው። አይሁድ ጌታችንን ወደ ቀራኒዮ ሲወስዱት የእጁ መጋፊያና መጋፊያ እስኪገጥም ድረስ በገመድ የእንግርግሪት አስረው ጎትተውታል ማንገቻውን ከበሮው ላይ ስናይ ይኽንን ጌታችን የታሰረበትን
ገመድ እናስታውሳለን።

በተጨማሪም በከበሮ ውስጥ የሚገኙት አምስት ጠጠሮች የአምስቱ አእማደ ሚስጥራት ምሳሌዎች ናቸው።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሰላም ውድ የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች

ትላንት ምሽት በጠየቅነው ጥያቄ መሰረት አጠቃላይ እስከ አሁን ድረስ 2,060 የሚሆኑ የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች የተሳተፉ ሲሆን ትክክለኛውን መልስ ያገኙት ግን 1,526 ሰዎች ብቻ ናቸው።

ይህም የሚያሳየው ከ500 በላይ የሚሆኑት ጥያቄውን በግምት ወይም ጠዋት የተለቀቀውን አጭር የስንክሳር ታሪክ ሳያነቡ ነው። ስለዚህ እባካችሁ የሚለቀቁት ለእናንተ ስለሆነ በሚገባ አንብቡት ከቀናችሁ ላይ ከ5 ደቂቃ በላይ አይወስድም ጥቅሙ ግን በቁጥር የሚለካ አይደለም።

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን! አሜን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስከረም ፫


አባ ዲዮናስዮስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ይኸውም የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት ሲሆን እርሱም የትንሣኤ ሙታንን ድርሳን የደረሰው ነው፡፡ ይኸውም
ነፍስ ከሥጋ ጋር ትሞታለች፣ በትንሣኤም ከሥጋ ጋር  አብራ ትነሣለች

የሚሉ መናፍቃን ከዐረቢያ አገር በመነሳታቸው ቅዱስ ዲዮናስዮስ በግብጽ የአንድነት ገባዔ አድርጎ ቢያስተምራቸው እምቢ ቢሉት ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ስለ ትንሣኤ ሙታን የሚነገረውንና የነፍስን ረቂቅነት፣ ዘላለማዊና ሕያዊት መሆኗን የሚናገር ድርሳን ደረሰ፡፡

ከደረሳቸው ድርሰቶች መካከልም፦

በዚህ በቸርነቱ ስጦታ ውስጥ የእግዚአብሔር ፍቅር የጎላ የተረዳ ሆነ ነፍስ ረቂቅ ስለሆነች እንደ መላእክት በሕይወት እንድትኖር እንጂ እንዳትሞት እንዳትጠፋም ማድረጉ ነው።

ከሥጋዋ በምትወጣ ጊዜ ስለ በጎ ሥራዋ እንደሚገባት መጠን ወደ ሕይወት ቦታዋ ይወስዷታል ወይም እንደ ሥራዋ ክፉነት ወደ ሥቃይ ይወስዷታል።

በትንሣኤ ቀንም ንቃሕ መዋቲ ተብሎ አዋጅ ሲነገር በፈጣሪያቸው ትዕዛዝ የሙታን በድኖች ሲነሡ ነፍሳት እንዲህ ይሆናሉ እያንዳንዲቱ ነፍስ ከሥጋዋ ተዋሕዳ አብራ ትነሳለች።

እግዚአብሔርንም ሲያገለግል ኖሮ በዛሬዋ ዕለት በሰላም አርፎ ወደ ሚወደው አምላክ ሄደ።

በረከቱ ይደርብን! አሜን
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🌼አዲስ አመት አዲስ ዘመን🌼

አዲስ አመት አዲስ ዘመን 
የሰጠኸን ጌታ ክበር ተመስገን

ምድርን በአበባ አጊጠህ አሳምረህ
ክረምትና በጋን ታፈራርቃለህ
የማታንቀላፋ ሳተፍ እንኳ ለአፍታ
ተመስገን አዲስ ቀን በሰጠኸን ጌታ 2
እንኳን ለዚህ ቀን አደረሳችሁ
እንኳን እግዚአብሔር አብሮ አደረሰን 2

አዝ

የመከራ ዘመን ታለፈና ዛሬ
ለአዲስ አመት በቃን ይኸውና ዛሬ
ዘመን ለፍስሃ ሰተኸናልና
የዘመናት ጌታ ይድረስህ ምስጋና 2
እንኳን ለዚህ ቀን አደረሳችሁ
እንኳን እግዚአብሔር አብሮ አደረሰን 2

አዝ

በአመቱ ያድርሰን ብለን ተመራርቀን
የዓመታት ባለቤት ይኸው አደረሰን
እድሜ ጤና ሰጥተህ ለዚህ ቀን ደርሰናል
የጊዜ ባለቤት በብዙ ረድቶናል 2
እንኳን ለዚህ ቀን አደረሳችሁ
እንኳን እግዚአብሔር አብሮ አደረሰን 2

አዝ

ከሩቅ ሀገር ያለው ላገሩ አብቃውና
የአባቶች ምርቃት ያግኝ እንደገና
ውዳሴ ምስጋና ለአንተ እናቀረባለን 2
እንኳን ለዚህ ቀን አደረሳችሁ
እንኳን እግዚአብሔር አብሮ አደረሰን 2

አዝ

የመከራ ዘመን ታለፈና ዛሬ
ለአዲስ አመት በቃን ይኸውና ዛሬ
ዘመን ለፍስሃ ሰተኸናልና
የዘመናት ጌታ ይድረስህ ምስጋና 2
እንኳን ለዚህ ቀን አደረሳችሁ
እንኳን እግዚአብሔር አብሮ አደረሰን 2


ዘማሪ ዳግማዊ ደርቤ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🌼ያለፈው ዘመኔ ይበቃኛል🌼

ያለፈው ዘመኔ ይበቃኛል 2
በአምላክ መታመኔ ይሻለኛል 2

እውነት በሌለበት በውሸቱ ኑሮ
ነፍሴ እየባዘነች በኃጢአት ቀጠሮ
አሁን ግን ተረዳሁ ይበቃኛል
እግዚአብሔር አምላኬ ይሻለኛል

አዝ

ካራን ተሰሎንቄ ባቢሎንና ግብፅ
አይኔን ቢጋርዱኝ በእግዚአብሔር እንዳምፅ
ዛሬ ግን ማዳኑን አየሁት
ያዳነኝን አምላክ ወደድኩት
አዝ

ጌታን ባለማወቅ የተጓዝኩትጉዞ
በሀጢያት በእርኩሰት ህሊናዬ ናውዞ
ሰማሁት አወኩት ቃልህን
በእርሱ ላይ አቀናሁ መንገዴን
አዝ

እረፍት ያጣሁበት ያለፈው ዘመኔ
ዛሬ ጠፍቶልኛል ተወግዷ ከአይኔ
ህግህ ለመንገዴ ብርሀን ነው
አዲስ ሰው የሆንኩት በአንተው ነው

ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🌼የአዋጅ ነጋሪ ቃል🌼

የአዋጅ ነጋሪው ቃል በበረሃ አየለ
የእግዚአብሔርን መንገድ አስተካክሉ እያለ
ምስክርነቱን ዮሐንስ ካስረዳ
ልባችን ለጌታ መልካም መንገድ ይሁን

የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
አውደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
ሀገራችንን ባርኪልን ድንግል ማርያም

ተራራው ዝቅ ይበል ጠማማውም ይቅና
ካልተስተካከለ መንገድ የለምና
የእግዚአብሔርን መንግስት እንመስርት ሁላችን
ማረፊያ እንዲሆነን ለመጪው ሃብታችን

የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
አውደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
ቤተክርስቲያን ጠብቂ ድንግል ማርያም

ክፋትና ተንኮል ከልባችን ይጥፋ
ጽድቅና ርህራሄ በኛ ላይ ይስፋፋ
ሥጋና ደምህን በክብር አግኝተናል
ህይወት እንዲሆነን አምላክ ተማጽነናል

የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
አውደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
ሀገራችንን ጠብቂ ድንግል ማርያም

ሁለት ልብሶች ያሉት ከማብዛት ልብስን
ለሌለው ያድለው  ሁለተኛውን
ከበደላችንም አንጻን አደራህን
በክፉ እንዳንጠፋ እኛ ባህሮችህ

የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
አውደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
ሀገራችንን ጠብቂ ድንግል ማርያም

ክፋትና ተንኮል ከልባችን ይጥፋ
ጽድቅና ርህራሄ በኛ ላይ ይስፋፋ
ሥጋና ደምህን በክብር አግኝተናል
ህይወት እንዲሆነን አምላክ ተማጽነናል

የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
ቤተክርስቲያንን ጠብቂ ድንግል ማርያም
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
አውደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም

ዘማሪት ፀዳለ ጎበዜ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🌼 እንደምን በረታች 🌼

እንደምን በረታች ዳነች ሰውነቴ
ብትወደኝ እኮ ነው አቤት መድኃኒቴ
ይቺን ዓመት ደግሞ አንተ ብትተወኝ
ወዳጄ  መውደድህ ፍቅርህ አስለቀሰኝ ×2

የአህዛብን ፈቃድ ያደረኩበት ቀን
እንደምን ይቆጠር ገብቶ በእኔ ዘመን
ካየሁ ጀምሮ ይቆጠር እድሜ
ሳላውቀህ የኖርኩት እኔ አይደል ጌታዬ
×2

አዝ

የትግስት መጠን ስፋቱ ጥልቅ ነው
ሁሌም እያጠፋሁ ቃልህ የፍቅር ነው
ረቡኒ ተናገር ላድመጥ በዝምታ
እስራቴ ይውለቅ ስትናገር ጌታ
×2
አዝ

በእኔ ውስጥ ምሰሶ እያለ ተጋርዶ
አይኔ ያያል የሰው የበደልን ነዶ
አልታዘዝ ብዬ ልቤን ሳትታዘብ
ሰው እየከሰስኩም አደረከኝ ገንዘብ
×2
አዝ

ሰው ፊትን እያየ ሞገስን ሲያበዛ
ሚዛንህ ልብ ነው የዓለሙ ቤዛ
ከአገር የሰፋውን የእኔን እዳ ምህረ
ለትንሽ ስጨክን ይቅር አለኝ ፍቅር
ከአገር የሰፋውን የእኔን እዳ ምህረ
ለትንሽ ስጨክን ይቅር አለኝ ልብህ

ስላልተውከኝ ክበር ስላልተውኝ ንገስ
የልቤ መድኃኒት ተስፋዬ ኢየሱስ
×2


ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🌼 አዲስ ዘመን አየን🌼

ኧኸ በጽድቃችን አይደል
ኧኸ በመልካም ስራችን
ኧኸ በቸርነቱ ነው
ኧኸ ለዚህ የደረስን
መውጣት መግባታችን እርሱ ሲፈቅድ ነው
አዲስ አመት አየን ከሞት የተረፍነው

ሜዳው ምድረ በዳው ደምቆ በአበባ
አዲስ ቀን ተሰጠን ይሄው ዘመን ጠባ
የሰማይ ጠል ወርዶ ምድር ረሰረሰ
ዝማሬን ይሰዋ ለዚህ የደረሰ

አ/ዝ


ዘመን አክሊል ሆነ የክብር ሽልማት
ባርኮ ሲለግሰን የምሕረትን ዓመት
የሚያስፈልገንን ስለሚያውቅ ቀድሞ
ለንስሐ ሰጠን ዛሬን እንደከርሞ

አ/ዝ


መልካሞች ቀኖችን ማየት የሚፈልግ
ከክፋ እርቆ መልካም ነገር ያድርግ
ዘመን የሚከፋው መልካም የሚያደርገው
የሰው ልጅ ሕይወት ነው ሁሉን የሚያበጀው

አ/ዝ


ጆሮ ስንቱን ሰማ ስንቱን አየ አይናችን
ባሳለፍነው አመት ባሳለፍነው ዘመን
ዳግመኛ ከቸርከን ፈቅደህ እንድንኖር
የእርቅ አድርግልን የሰላም የፍቅር

አ/ዝ


ሰዓታትን በቀን ቀንን በሳምንታት
እያፈራረቀ ወራትን በአመታት
በበዛው ምህረቱ ጨመረልን እድሜ
ለመንግስቱ ግዛት የለውም ፍጻሜ

ዘማሪ ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🌼 አምላክ ሆይ ባርክልን በዓሉን 🌼
                                           

አምላክ ሆይ ባርክልን በዓሉን /2/      

ባርክልን ኧኸ በዓሉን
ለዛሬ ዓመት ኧኸ አድርሰን
ሠላም ፍቅር ኧኸ አድለን
በዕምነታችን ኧኸ አበርታን
በአንድነት ኧኸ አቁመን                             
አምላክ ሆይ ባርክልን በዓሉን /2/                 

ጽኑ ሠላም ኧኸ ለሐገሪቱ
እንዲጦሩ ኧኸ አዛውንቱ
ወጣቱ እና ኧኸ ሕጻናቱ
ያለ ጊዜ ኧኸ እንዳይሞቱ
አንድም ሳይጎድል ኧኸ በመሃላችን
ለዓመት ያብቃን ኧኸ አምላካችን                                  
አምላክ ሆይ ባርክልን በዓሉን /2/               

አገልጋዩን ኧኸ ከመቅደሱ
እንዲኖሩ ኧኸ ሲያወድሱ
ታቦቱንም ኧኸ ከመንበሩ
አታናውጠው ኧኸ ከደብሩ
ወታደሩን ኧኸ በድንበሩ
ጠብቅልን ኧኸ በበረከት
ቸሩ ጌታ ኧኸ የፍቅር አባት       
ድንግል ሆይ ባርኪልን በዓሉን /2/                  

ለባርኮ ኧኸ አውደ ዓመት
ንዒ ማርያም ኧኸ በምሕረት
ያዘነው ኧኸ እንዲጽናና
የተከዘው ኧኸ እንዲል ቀና
በሐገር ውስጥ ኧኸ ውጭም ላለው
በበረከት ኧኸ አትለይው                             
ድንግል ሆይ ባርኪልን በዓሉን                   

የናቁሽም ኧኸ ጽዮን ብለው
ይሠግዳሉ ኧኸ ፊትሽ ወድቀው
ካኅናቱ ኧኸ በማሕሌቱ
በቅዳሴው ኧኸ በሠዓታቱ
ከልጅሽ ጋር ኧኸ ከዓለም ጌታ
ዘመሩልሽ ኧኸ በዕልልታ
                           
ድንግል ሆይ ባርኪልን በዓሉን               
ባርኪልን  ኧኸ /4/

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…
Подписаться на канал