ጳጉሜን
ጳጉሜን የሚለው ስያሜዋ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ጭማሪ ማለት ነው፡፡ በግእዝ ተውሳክ ማለት ሲሆን ተውሳክ ማለት ተጨማሪ ማለት ነው፡፡ “ወሰከ - ጨመረ” ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ ሌሎች ሀገሮች ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ያደርጓታል፡፡ ይኸውም ይታወቅ ዘንድ እኛ የወርን ቁጠር 30 ስናደርግ እነርሱ 31 ብለው የሚቆጥሩት ወር አላቸው፡፡ ይኹን እንጂ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ሳያደርጉ የዓመት ተጨማሪ አድርገዋታል፡፡
ጳጉሜን በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን ትመጣለች፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ሉቃስ መጨረሻ በዘመነ ዮሐንስ መግቢያ ጳጉሜን ስድስት ቀን ትሆናለች፡፡ በዚህም ሀገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ /Thirty months of sunshine/ በመባል ትታወቃለች፡፡ ጳጉሜን ስድስት በምትሆንበትም ጊዜ ጾመ ነቢያት /የገና ጾም/ ህዳር 14 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈትቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡
በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜን ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው። ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዎች ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡
የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲ 2፥2-7፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋት በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡
ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ ዮዲ 8፥2፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡
ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡
የጳጉሜን ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብባትም ወር ነች፡፡ ይህም ጳጉሜን የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
አምላከ ተክለሃይማኖት ማረን
አምላከ ተክለሐይማኖት ማረን 2×
አምላከ ቅዱሳን ታረቀን 2×
ስለቃልኪዳንህ በቁጣ አታጥፋን
አዝ
ሐዋርያው ቅዱስ ተክለሃይማኖት
የኢቲሳ አንበሳ የኔ አባት
ቁጣውን አብርደው ተክለሐይማኖት
ለምልጃ ተነሳ የኔ አባት
ከሰማይ ካህናት ተክለሐይማኖት
ቤተሰብ ሆነሃል የኔ አባት
የሥላሴን መንበር ተክለሐይማኖት
ለማጠን በቅተሀል የኔ አባት
አዝ
ከከርቤ ከሚያ ተክለሃይማኖት
ከሰሊክም በልጧል የኔ አባት
የፃድቁ ፀሎት ተክለሐይማኖት
በእግዚአብሔር ፊት ሸቷል የኔ አባት
ስለቃልኪዳንህ ተክለሐይማኖት
አምላክ ይለመናል የኔ አባት
ፀሎትህ ሲደርስ ተክለሐይማኖት
እኛን ይታረቃል የኔ አባት
አዝ
ተማፅነንብሃል ተክለሃይማኖት
ጌታ ሆይ በስሙ የኔ አባት
በፃዲቁ ፀሎት ተክለሐይማኖት
በሰባረ አፅሙ የኔ አባት
ኢትዮጲያን በሙሉ ተክለሐይማኖት
አስተምሮ ሲመለስ የኔ አባት
አፅመ ርስቱ ሆነች ተክለሐይማኖት
ደብረ ሊባኖስ የኔ አባት
አዝ
የፃዲቁ መንፈስ ተክለሃይማኖት
ከቅዱሳን ጋራ የኔ አባት
ከልባችን ገብተህ ተክለሐይማኖት
ብርሃንን አብራ የኔ አባት
በፀሎት ስቆም ተክለሐይማኖት
ስምህን ስጠራ የኔ አባት
ነፍሴ ተደሰተች ተክለሐይማኖት
ሲርቀኝ መከራ የኔ አባት
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ታህሳስ 24
በዚህች ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክልሃይማኖት የተወለዱበት ቀን ነው። የትውልድ ቦታቸው ሸዋ ጽላልሽ አወራጃ ዞረሬ ነው፤ የአባታቸው ስም ጸጋ ዘአብ የእናታቸው ስም እግዚ ሐርያ ይባላል መካን ነበሩ ልጅ እንዲሰጣቸው ወደ እግዚያብሔር ዘወትር ይጸልዩ ነበር፤ መጋቢት 12 ቀን እንዲህ ሆነ።
ሞተሎሜ የተባለ ጣኦት አምላኪ ንጉስ አገራቸውን ወረረ መንደሩንም አጠፋ ጸጋ ዘአብ ወንዝ ውስጥ ገብቶ አመለጠ እግዚ ሐርያ ግን ተማርካ ሄደች፤ በጣም መልከ መልካም ስለነበረች ሞቶሎሜ ሊያገባት አሰበ ታላቅ ድግስም ደገሰ አገር ምድሩ ተሰብስቦ ሲዘፍን ሲጨፍር ሳለ ቅዱስ ሚካኤል ታላቅ መብረቅ ነጎድጓድ አሰማ ብዙዎች ሞቱ እግዚሐርያን በክንፎ ተሸክሞ ዞረሬ ከቤተክርስቲያን ውስጥ አስቀመጣት ከባለቤቷ ጸጋ ዘአብ ጋር ተገናኙ ተቃቅፈው ተላቀሱ፤ከሁለት ቀን በኃላ መጋቢት 24 ቀን ተክለሃይማኖት ተጸነሱ።
በዛሬዋ ቀን 1167 ዓ/ም ተወለዱ ቀኑ አርብ ነበር፤ በተወለዱ በ3ኛ ቀናቸው እሁድ በ 3 ሰዓት “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” ብለው ሥላሴን አመሰገኑ፤ ሁለተኛ ተአምር ከዚህ በታች ያለው ስዕል ተክልዬ የአንድ ዓመት ከመንፈቅ ህጻን እያሉ ነው፤ በድፍን ሸዋ ርሃብ ተከስቶ ነበር በተለይም በዞረሬ እግዚሐርያ አዘነች አለቀሰች ምነው እርቧት ነው ጠምቷት ነው ቢሉ የለም እርቧትስ ጠምቷትስ አይደለም የቅዱስ ሚካኤል ዝክሩ ታጎለቢኝ ብላ እንጂ።
ህጻኑ ተክለሃይማኖት ከእናቱ ጭን ወርዶ እየዳኸ ወደ ጓዳ ሄደ አንስታ አቀፈችው እርሱ ግን አለቀሰ ዱቄት የተቀመጠበትን እንቅብ እንድትሰጠው በእጁ ጠቆማት ሊጫወትበት መስሏት ሰጠችው በትንንሽ እጆቹ እንቅቡ ላይ አማተበ ዱቄቱ ሞልቱ ፈሰሰ ዳግመኛ የቅቤ የዘይት ማስቀመጫ ማድጋዎች ላይ በተመሳሳይ አማተበ ሞልቶ ፈሰሰ ቤቱ በበረከት ተትረፈረፈ፤ የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን አዘከረች አገሬውን ጠርታ መገበች፤ ለተቸገሩትም አብዝታ ሰጠች፤ ይህ በረከት ሁለቱም እስኪሞቱ ድረስ አላለቀም ይላል ገድላቸው።
ተክለ ሃይማኖት በ 99 ዓመት ከ8 ወር ከ5 ቀን በዚህ ምድር ኖረው ነሐሴ 24 ቀን አርፈዋል። በደብረሊባኖስ ገዳማቸው የንፍሮ ውኃ አይነስውር ያበራል ድውይ ይፈውሳል ገድላቸው ሊነበብ ሲወጣ አጋንንት ተቃጠልን ይላሉ ሲገርም ምን ያህል ባለጸጎች ነን። ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
እናት ልጇን ወልዳ ለ5 ደቂቃ እንኳን ሳታቅፈው በጥቁር ፌስታል ጠቅልላ የጣለችበት እና ክቡሩ የእግዚአብሔር ፍጡር የውሾች ራት የሆነበት የቆየ ታሪክ አይደለም በእኛው ዘመን ነው😭😭
ይሄ ልጅ ግን እኛስ ብንሆን ኖሮ?🤔
እግዚአብሔርን ስላደረግልን ነገር ሁሉ እናመስግነው።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
የእግዚአብሔር ሠላምታ እያቀረብን።
በእዚህ ትምህርት ላይ ለእናንተ ለተወደዳችሁ
ኦርቶዶክሳዊያን ያካተትነው ርዕስ
👉አመስጋኝ ልብ ለምን ያስፈልጋል?
👉አሁን ያለን ህይወት ምን አይነት ነው?
👉ባለን ነገር እግዚአብሔር እንዴት ማመስገን እንችላለን?
👉ስላልተደረገልን ነገር ማመስገን ከእግዚአብሔር ምን አይነት በረከት አለው?
🙏እንዴት አመስጋኝ ልብ ይኑረን።
የሚል ይሆናል ከልብ ተመስጣችሁ ሳታቋርጡ
እንድትከታተሉት እንጠይቃለን
✞ እግዚአብሔር የወደቁትን ያነሳል
እግዚአብሔር የወደቁትን
ያነሳል የተረሱት ያስታውሳል
የተናቁት ያከብራል
አንተ በክብር ላይ ክብር ስጨምር
እረኛው ይሻማል በንጉስ ወንበር
ጌታ ትውዳለ የተናቁትን አንተ
ልብን እንጂ አታይም ፊትን
#አዝ
ሳሙኤል ልከ ጠርተ ትቀባለክ
ያንበሶቹን አፍ አንተ ትዘጋለክ
በጌርጌሲኖር በመቃብር ስፍራ
አየሁ አምላኬ ለሰው ልጅ ስትራራ
#አዝ
ጠላታችን ደርሳ ቢያስጨንቀንም
ትሞታለ ብሎ ቢዝትብንም
በሃሰት ቢጥለን ከመከራ ቤት
በእግዚአብሔር ቸርነት ወጣን ከስራት
#አዝ
ይደግፋል ክንድህ የተጋቁትን
ከሰው በታች ሆኑ የሚኖሩትን
ደስታ ትሰጣል ሃዘን አርቀህ
አይቀርም አልቅሶ አንተን ያመነህ
#አዝ
ጠላታችን ደርሳ ቢያስጨንቀንም
ትሞታለ ብሎ ቢዝትብንም
በሃሰት ቢጥለን ከመከራ ቤት
በእግዚአብሔር ቸርነት ወጣን ከስራት
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
አረገች በስብሐት
አረገች በስብሐት አረገች በእልልታ በስብሐት በእልልታ አረገች በስብሐት በእልልታ/2/
እየዘመሩላት መላዕክት በደስታ አረገች በስብሐት በእልልታ/2/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#ማርያም_አርጋለች ✞
ማርያም አርጋለች ወደ ገነት(፪)
የሰማይ መላእክት እያረጋጓት
እርሷም እንደ ልጇ ተነስታለች
የአባቷን ዳዊት ትንቢት ልትፈፅም
ወርቁን ተጎናፅፋ በቀኙ ልትቆም
ወደ አምላክ ማደሪያ ወደ ሰማያት
አረገለች በእልልታ ድንግል የእኛ እናት
አርጋለች ማርያም ተነስታለች
#አዝ
ሰማያት ይከፈት ደመናም ይዘርጋ
ዝምታም አይኖርም እመ አምላክ አርጋ
አንደበት ይከፈት ማርያምን ያመስግን
ከዘላለም ጥፋት በምልጃዋ እንድንድን
አርጋለች ማርያም ተነስታለች
#አዝ
የአምላክ ማደሪያ ቅዱስ ስጋሽ
አምላክን ያቀፉት እነዚያ እጆችሽ
ሙስና መቃብር ይዞ አላስቀራቸው
ተነስተዋል በክብር በእምነት አየናቸው
አርጋለች ማርያም ተነስታለች
#አዝ
ሐዋርያት አበው እንኳን ደስ አላችሁ
በክብር አረገች ማርያም ሞገሳችሁ
ወደ ዓለምም ውጡ ሰበኑዋን ይዛችሁ
የድንግል እርገቷን ንገሩ ተግታችሁ
አርጋለች ማርያም ተነስታለች
"በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና
ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።"
መዝ ፵፬፥፱
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
ነሐሴ 16/12/2015 ዓ.ም
ፍልሰተ ሥጋሃ ለእግዝእትነ
✝ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።
ዲያቆን፦ ሮሜ 8÷31-ፍ.ም
ንፍቅ ዲያቆን፦ ዮሐ 2÷1-7
ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 1÷12-15
ምስባክ ፦ መዝ 45፥4-6
ቀደሰ ማኅድሮ ልዑል
እግዚአብሔር ውስተ ማዕከላ ኢትትሀወክ
ወይረድኣ እግዚያብሔር ፍጹመ
ትርጉም ፦
ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ
እግዚያብሔር በመካከሏ ነው አትናወጥም
እግዚያብሔርም ፈጥኖ ይረዳታል
ወንጌል ፦ ማቴ 16÷13-20
ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ(የጌታ ቅዳሴ)
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ነሐሴ 14/12/2015 ዓ.ም
✝ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።
ዲያቆን፦ 1 ቆሮ 1÷10-19
ንፍቅ ዲያቆን፦ ያዕ 1÷12-22
ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 1÷30-34
#ምስባክ ፦ መዝ 43፥4-6
ዘአዘዝከ መድኀኒቶ ለያዕቆብ
ብከ ንወግኦሙ ለኩሎሙ ፀርነ
ወበስምከ ናኀስሮሙ ለእለ ቆሙ ላዕሌነ
#ትርጉም ፦
ለያዕቆብ መድኀኒትን እዘዝ
ባንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን
በስምክም በላያችን የቆሙትን እናዋርዳቸዋለን
#ወንጌል ፦ ማቴ 17÷14-24
#ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
የቀጠለ
ኤልያስና ሙሴን ለምን አመጣቸው?
ሀ- በአንድ ወቅት ነቢዩ ሙሴ እግዚአብሔርን ‹‹ወለእመሰ ረከብኩ ሞገሰ በኀቤከ አስተርእየኒ ገሐደ ሊተ ወአእምር ወእርአይከ ከመ ይኩነኒ ርኪበ ሞገሰ በቅድሜከ ዮም›› ፣ በአንተ ዘንድ ባለሟልነትን ማግኘቴ እውነት ከሆነስ ፊት ለፊት ተገልጸህልኝ ልይህና በአንተ ዘንድ ባለሟልነትን ማግኘቴን ልወቀው› ሲል ጠይቆት ነበር፡፡ እግዚአብሔርም ‹… ትሬኢ ድኅሬየ ወገጽየሰ ኢያስተርኢ ለከ፣ ጀርባዬን ታያለህ ፊቴን ግን አታይም› ብሎት ነበር፡፡ /ዘጸ. 33.13 እና 23/
የዚህ ኃይለ ቃል ትርጓሜና ሐተታ በደብረ ታቦር ተፈጸመ፡፡ እንዲህ ማለቱ በአምስት ሺሕ አምስት መቶ ዘመን ሰው ሆኜ ሥጋ ለብሼ ኋላ በደብረ ታቦር እስክገለጽልህ ድረስ አንተ በመቃብር ተወስነህ ትኖራለህ ማለቱ ነበር፡፡ ይህን ማለቱ እንደሆነ የታወቀው ግን በደብረ ታቦር ሙሴን ከብሔረ ሙታን አምጥቶ ባቆመው ጊዜ ነበር፡፡
ለ- ልዑል እግዚአብሔር ነቢዩ ኤልያስን ‹አንተሰ ትከውነኒ ስምዓ በደኃሪ መዋዕል፣ አንተ በኋለኛው ዘመን ምስክር ትሆነኛለህ› ብሎት ነበርና ይኸውም ኃይለ ቃል ኤልያስ ከብሔረ ሕያዋን መጥቶ ‹የእኔን የኤልያስን ጌታ ማን ኤልያስ ነው ይልሃል እግዚአ ኤልያስ፤ አምላከ ኤልያስ ይበሉህ እንጂ› ሲል በደብረ ታቦር ተፈጸመ፡፡ ታያለህ የተባለው ሙሴም አየ፣ ትመሰክራለህ የተባለው ኤልያስም መሰከረ፡፡
ሐ- በፊልጶስ ቂሳርያ ጌታ ሐዋርያትን ‹ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደሆነ ይሉታል?› ብሎ በጠየቃቸው ጥያቄ ሲመልሱ ሙሴ ነው ይሉሃል ፤ እንዲሁም የኃይል ስራህን ተመልክተው ኤልያስ ነህ ይሉሃል ብለው ነበርና ሙሴን ከመቃብር ፤ ኤልያስን ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ እግዚአ ሙሴ ፤ አምላከ ሙሴ ፤ እግዚአ ኤልያስ ፤ አምላከ ኤልያስ መሆኑን ለማስመስከር፡፡
ታቦር ተራራ የዛሬ ገጽታው ከሩቅ ዕይታ
ታቦር ተራራ የወንጌል ምሳሌ
1. ተራራ ሲወጡት ያደክማል፣ ከወጡት በኋላ ግን ጭንጫውን፣ ግጫውን ሲያሳይ ደስ ያሰኛል፡፡ ወንጌልም ሲማሯት ትከብዳለች በኋላ ግን ጽድቅን እና ኃጢአትን ለይታ ስታሳውቅ ደስ ታሰኛለች፡፡
ታቦር ተራራ የቤተክርስቲያን ምሳሌ
1. በታቦር ተራራ ከብሉይ ኪዳን ነቢያት ኤልያስና ሙሴን፣ ከሐዲስ ኪዳን ሦስቱን ሐዋርያት እንደተገኙ በቤተክርስቲያን ብሉይ ከሐዲስ እንዲነገር ለማጠየቅ ፤ ሐዋርያት የሰበኩት ወንጌል አስቀድመው ነቢያት በምሳሌና በትንቢት የተናገሩት እንደሆነ ሲያስረዳ ነው ፡፡ ነቢያት በቀየሱ ሐዋርያት ገሰገሱ እንዲል ‹በሐዋርያት በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል›ኤፌ 2፣20
2. በታቦር ተራራ ከመዓስባን (ባለትዳር) ሙሴን ከደናግል ደግሞ ኤልያስ እንደተገኙ በቤተክርስቲያን በድንግልና የሚኖሩ መናንያን መነኮሳትም፣ በሕግ በሥርዓት የሚኖሩ ባለትዳሮችም ይገኛሉና፡፡
ታቦር ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ
1. ተራራውን ችግር እንዲወጡት መንግሥተ ሰማያትንም በብዙ መከራ የምትገኝ ናትና ‹እስመ በብዙኅ ጻማ ወድካም ኀለወነ ንባአ ለመንግሥተ እግዚአብሔር› ‹ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል› ሐዋ 14፡22
2. በታቦር ተራራ የብሉይ ኪዳን ነቢያት፣ ከሐዲስ ኪዳን ሐዋርያት እንደተገኙ መንግሥተ ሰማያትን ነቢያትም፣ ሐዋርያትም አንድ ሆነው እንደሚወርሷት ያጠይቃል፡፡
3. በታቦር ተራራ ከመዓስባን ሙሴ፣ ከደናግል ደግሞ ኤልያስ እንደተገኙ መንግሥተ ሰማያትን ደናግልም መዓስባንም በአንድ ላይ እንዲወርሷት ያጠይቃል፡፡
4. በታቦር ተራራ ሞተው ከተቀበሩት መካከል ሙሴን አመጣ፣ በብሔረ ሕያዋን ካሉት ደግሞ ኤልያስን አመጣ መንግሥተ ሰማያትንም ሞተው የተቀበሩትም በብሔረ ሕያዋን ያሉትም በአንድነት እንደሚወርሷት ያጠይቃል፡፡
በአጠቃላይ ታቦር ተራራ፡-
1. የክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት የተመሠከረበት፣
2. የምስጢረ ሥላሴ ትምህርት የተሰጠበት
3. ፈጣሪ ከቅዱሳን ሰዎቹ ጋር የተገኘበት
4. በልበ ሐዋርያት የነበረ ሰይጣን ድል የተደረገበት
5. የሐዋርያት በተለይም የሦስቱ ባለሟልነት የተገለጠበት፣
6. አሉባልታና ተራ ወሬ የከሸፈበት፣
7. የቅዱሳንን ክብር ለሚያናንቁ ተራራም እንኳን ‹ቅዱስ› እንደሚባል የተማሩበት፣
8. የብሔረ ሕያዋን መኖር የተመሰከበረበት
9. የትንሣኤ ሙታን ዋስትና የተገለጠበት የክብር ሰገነት፣ የምስጢረ መቅደስ፣ ታላቅ ትምህርት ቤትም ጭምር ነው፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታ ሆይ በዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው ማለቱ
1. የኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት በሚታመንበት፣ ዋልድ ዋሕድ በምትለው ሃይማኖት መኖር ለእኛ መልካም ነው፡፡
2. መድኃኔዓለም ከቅዱሳን ወዳጆቹ ጋር በምትገኝበት አንተ እያበላኸን እየፈወስከን፣ ሙሴ ደመና እየጋረደ መና እያወረደ ባሕር እየከፈለ፣ ኤልያስ ሰማይ እየለጐመ እሳት እያዘነመ ዝናም እያቆመ በዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው፡፡
3. በልበ ሐዋርያት ያደረ ሰይጣን ድል በተደረገበት በታቦር ተራራ ምሳሌ አንድም በወንጌል ሕይወት፣ አንድም በቤተ ክርስቲያን መኖር ለእኛ መልካም ነው፡፡
ፈጣሪያችን እግዚአብሔር እስከመጨረሻዋ ሕቅታ (እስትንፋስ) በታቦር ተራራ በተመሰለች ቤተክርስቲያን በሃይማኖታችን ጸንተን የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች የስሙ ቀዳሾች እንድንሆን የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፡፡
የደብረ ታቦር መዝሙር
#አሐደ_ለከ
አሐደ ለከ ወአሐደ ለሙሴ /2/
ወአሐደ ለኤልያስ ንግበር ማይደረ /4/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ነሐሴ 13/12/2015 ዓ.ም
ደብረ ታቦር
✝ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።
ዲያቆን፦ ዕብ 11÷23-30
ንፍቅ ዲያቆን፦ 2 ጴጥ 1÷15-ፍ.ም
ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 7÷44-51
ምስባክ ፦ መዝ 88፥12-14
ታቦር ወአርሞንዔም በስመ ዚአከ ይትፌስሁ ወይሴብሑ ለስምከ
መዝራዕትከ ምስለ ኀይል
ትርጉም ፦
ታቦር እና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል
ስምህንም ይመሰግናሉ
ክንድክ ከኃይልክ ጋር ነው
ወንጌል ፦ ሉቃ 9÷28-38
ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#አማን_በአማን
አማን በአማን /2/ ተሰብሐ
አማን በአማን /2/ ተሰብሐ
በደብረ ታቦር /2/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
👉 ጳጉሜ ለምን እንጠመቃለን?
🎤 ቀሲስ ሄኖክ ወልደ ማርያም
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
#ጾመ_ዮዲት
በናቡከደነጾር ዘመነ መንግሥት ንጉሡ ሥልጣኑን መከታ በማድረግ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በግድ እያስገደደ እጅ መንሻ ይቀበል ነበር፡፡
የመንግሥቱን ትእዛዝ ያልተቀበለውንም እየገደለ፣ ጭፍሮቹ ኃያልነቱንና ገናናነቱን በዓዋጅ በጦር አዛዦች ጭምር እያሳወጀ፣ በርካታ የጦር ሠራዊቶችን አሰልፎ ከአይሁድ ከተማ ገባ፡፡
በዚያም ነዋሪዎችን በማስፈራራት የመንግሥቱን ትእዛዝ ያልተቀበሉትን ሁሉ እያሳደደ ስላስጨነቃቸው ማቅ ለብሰው፣ አመድ ነስንሰውና ድንጋይ ተንተርሰው ወደ ፈጣሪያቸው በመጮህ መለመን ጀመሩ። በጭካኔ የተሞላው የጦር አበጋዙ ሆሎፎርኒስም ይበልጥ እጅግ እንዲሰቃዩ ውኃ የሚቀዱበትን ስፍራ ተቆጣጠረው፤ በግዴታ ማርኮም እጅ እንዲሰጡ እንዳደረጋቸው በመጽሐፈ ዮዲት ፪፥፪ ላይ ተጽፏል፡፡
በአካባቢው ይኖር የነበረ ዖዝያን የተባለ አንድ ሰው የአባቶቻቸው አምላክ ጸሎታቸውን እንዲሰማቸው ለአምስት ቀናት በትዕግሥት ይጾሙና ይጸልዩ ዘንድ ሕዝቡን መከራቸው፤ እነርሱም በትዕግሥት ሊጠብቁ ተስማሙ፡፡
የእስራኤል ልጆች የናቡከደነጾርን ጦር ብንችል ተዋግተን እንረታለን፤ ካልሆነም እጅ እንሰጣለን በማለት ይመካከሩ ጀመር። በዚያን ጊዜ ባሏ የሞተባትና በንጽሕና ተጠብቃ፣ በጸሎትና በሕገ እግዚአብሔር የምትኖር ዮዲት የተባለች ሴት ነበረች። (ዮዲት ፯፥፲)
እግዚአብሔርን የምትፈራ ብቸኛዋ ሴት እርሷ ነበረችና ምክክራቸውን ስትሰማ ለምን «እግዚአብሔር ያድነናል አትሉም» ብላ ገሠጸቻቸው፡፡
ማቅ በመልበስ፣ አመድ በመነስነስና ድንጋይ በመንተራስም ሱባኤ ገባች። በሦስተኛው ቀንም እግዚአብሔር አምላክ ሕዝቧን የምታድንበትን ጥበብ ገለጸላት፤ ዮዲትም እግዚአብሔር የሰጣትን ውበት ተጠቅማ ሕዝቧን ከጥፋት የምትታደግበትን ጥበብ ተረዳች።
የክት ልብሷን ለብሳ፣ ሽቱ ተቀብታና ተውባ የጠላት ሠራዊት ወዳሉበት የጦር ሰፈር በድፍረት አመራች፡፡ ሠራዊቱም ውበቷን አይተው እጅግ በመደነቅ «ይህችስ ለአለቃችን ትገባለች» ተባብለው ከጦር መሪያቸው ዘንድ ወሰዷት።
እርሷም ቀድማ ማምለጫ መንገድ አዘጋጅታ ነበርና ወደ አዛዡ ከገባች በኋላ «ክቡር ጌታዬ ሆይ ርስት ተወስዶብኛል፤ እንድትመልስልኝ አስቀድሜ ደጅ ልጠና መጥቻለውና ርዳኝ፤ ትብብርህ አይለየኝ» አለችው፡፡ በስሜት ፈረስ ታውሮ የነበረው የሠራዊቶቹ አዛዥም የጠየቀችውን እንደሚፈጽምላት ቃል ገባላት።
ባማረ ድንካን እንዲያስቀምጧት ሎሌዎቹን አዘዘ። ዮዲትም የተሰጣትን ጥበብ ተጠቅማ፣ መውጣት ስትፈልግ የምትወጣበትን እና የምትገባበትን ዕድል በእግዚአብሔር አጋዥነት ዐወቀች፡፡ ከቀናት በኃላ የጦር አበጋዙ ለሠራዊቱ የምሳ ግብዣ አዘጋጅቶ ዮዲትን ከጎኑ አስቀመጣት፤ ከበሉና ከጠጡ በኋላም ሁሉን ሰው አስወጣ፤ እልፍኙን በመዝጋት ከእርሷ ጋር ብቻውን ሆነ፤ ነገር ግን እንቅልፍ ጣለው፡፡ (ዮዲት ፰፥፪)
እርሷም ወደ አምላኳ ጸለየች፤ ፈጣሪዋ እንዲረዳትም አጥብቃ ለመነች። በኋላም ከራስጌው ሰይፍ አንስታ አንገቱን ቀላችው፤ በድኑንም ከመሬት ጣለችው። የሆሎፎርኒስን ሞት ሠራዊቱ ሲሰሙ አውራ እንደሌለው ንብ ተበተኑ፤ ከፊሎቹ ሞቱ።
እስራኤላውያንም ከሞት ተርፈው በእግዚአብሔር ኃይል ድል አደረጉ፤ በደስታም ፈጣሪያቸውን አመሰገኑ።
ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪክ የሚያስረዳን ዮዲት ጠላቶቿን ድል ያደረገችው በጾምና በጸሎት እንደሆነ ነው፡፡
ለእኛም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ምንም እንኳ ወርኃ ጳጉሜን የፈቃድ ጾም ቢሆንም በሀገራችን የተጋረጠውን ችግር እናልፍ ዘንድ በፈቃደኝነት እንጾማለን። እግዚአብሔር አምላካችን ለሁላችንም ጥበብ ሰጥቶናል።
ይህም ችግሮችን ሁሉ የምንፈታበት መንገድ ነው። በዚህም የዓመተ መሸጋገሪያና የክረምቱ ወር ማብቂያ በመሆኑ ዕለተ ምጽአት ስለሚታሰብበት በየዓመቱ በጳጉሜ ወር ከሌሊት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያን ተገኝተን ጠበል በመጠመቅ፣ በማስቀደስና በመጸለይ እንዲሁም ሥጋ ወደሙን በመቀበል ልናሳልፍ ይገባል።
ዕለተ ምጽአትም ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው ዓለም መሸጋገሪያችን ነውና በቀኙ እንቆም ዘንድ እንጾማለን፡፡
የሚመጣውን አዲስ ዘመንም በንጽሕና ለመቀበል ስላለፈው ዓመት ኃጢአታችን ንስሓ የምንገባበት ጾምም ነው።
ከተጋረጠብን ችግር «እግዚአብሔር ያድነናል» በማለት ልክ እንደ ዮዲት ሱባኤ ገብተን፣ ማቅ ለብሰን፣ አመድ ነስንሰንና ድንጋይ ተንተርሰን አብዝተን ልንጾምና ልንጸልይ ይገባል፡፡ ሊለያየን፣ ሊነጣጥለን፣ ሊበታትነን እና ሊገድለን ካሰበው እንዲሁም ፍቅርን፣ መተሳሰብንና አንድነትን ሊነፍገን ከቃጣው ጠላትና ሃይማኖታችንን ሊያስተወን ከሚመጣ ፀረ ሃይማኖት እንድናለን።
ስለዚህ ከፊታችን ያለችውን ስድስቱን የጳጉሜን ቀን በፍቅር፣ በአንድነትና በሃይማኖት ጸንተን፣ ጾመን፣ ጸልየን ለዘመነ ማቴዎስ እንድንደርስ እግዚአብሔር አምላካችን ይርዳን፤ አሜን።
ምንጭ፦ ከማኅበረ ቅዱሳን
በዲያቆን ዮሴፍ በቀለ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይህ በሺዎች የሚቆጠሩ ባለማሕተቦች የተቀላቀሉት የዝማሬ ዳዊት ቻናል ዩቲዩብ ነው ሊንኩን ተጭነው subscribe በማድረግ አገልግሎቱን ይደግፉ!
https://www.youtube.com/channel/UC8iS8VUpEphoIVnfhsC2WdQ
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ኢትዮጵያዊው ጻድቅ
ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ማነው ብዬ ጠየቅሁ
በረከት ፈልጌ ልሳለመው ናፈቅሁ
ክብሩን ልመሰክር ተፈታ ምላሴ
በደጁ ደርሼ ፍቅሩን በመቅመሴ/፪/
አዝ
በኢቲሳ ምድር ዘር ሆነህ በቅለህ
ተለየህ ለአምላክ ዓለምን ጥለህ
ደብረ ሊባኖስ ህያው ምስክር
ስለ አንተ ዝና ስለ አንተ ክብር
ተክለሃይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ
አዝ
አክባሪው አምላክ ስላከበረህ
ዛሬም ከኛ ጋር በመንፈስ አለህ
ደጅ እንጠናለን በትህትና
የጻድቅ ጸሎት ኃይል አላትና
ተክለሃይማኖት ጸሐይ
ጸጋህ ይውጣልኝ በሠማይ
አዝ
ወደ ለምለም መስክ ሰብከህ መራኸን
የቃሉን ወተት አጠጥተኽን
ያቀጣጠልከው የወንጌል ችቦ
የአምላክ አድርጓል ትውልዱን ስቦ
ተክለሃይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ቤቴ ደጄ
አዝ
ሠላሳ ሥድሳ መቶ ያፈራህ
በደብረ አስሶ ቆመህ በአንድ እግርህ
የሞተለሚ መሻት ቀረና
የጌታ መንገድ ጥርጊያውም ቀና
ተክለሃይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
📣📣📣📣የምሥራች📣📣📣📣
እንደ እግዚአብሔር አምላክ መልካም ፈቃድ በእዚህ በዝማሬ ዳዊት የተለያዩ ትምህርቶችን እያዘጋጀ ሲያስተምረን እንዲሁም ጥያቄዎቻችንን ሲመልስ የቆየው ወንድማችን ዲያቆን ዳግማዊ ሰለሞን።
በአይነቱ ለየት ያለ የሕይወት መጽሐፍ "ኦርቶዶክሳዊ ወጣት እና ፈተናዎቹ" በሚል ርዕስ አዘጋጅቶ ለአንባቢያን አቅርቧል።
🙏እናም የዝማሬ ዳዊት ቻናል ተከታታዮቻችን የአሁኑ ቅዳሜ ነሐሴ 27 ከቀኑ 7:00 በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሚገኘው አዳራሽ የመጽሐፍ ምርቃቱን ወንድማችን ስላዘጋጀ። በእዚህ መርኀ ግብር ላይ በመገኘት ወንድማችንን እንድናበረታታው በትኅትና እንጠይቃለን።
ቦታ 4 ኪሎ ሥላሴ ቤተክርስቲያን ውስጥ ባለው መንፈሳዊ አዳራሽ።
ብጹዓን አባቶች፣ መምህራን እና ዘማሪያን የሚገኙበት ጉባኤ በመሆኑ ማንም ሰው እንዳይቀር። ለምታውቋቸው ጓደኞቻችሁ ይሄንን መልእክት በመንገር የአሁኑ ቅዳሜ በቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን እንገናኝ።
እናት ከልጇ ጋር የታረደችበት ታሪክ ሩቅ አይደለም በዚህ ዓመት ያየነው ነው። ለዛውም ኦርቶዶክስ ስለሆኑ።
እግዚአብሔርን የሚያመሰግን ልብ ሊኖረን ይገባል
ስለ ዘፈን ለጠየቃችሁት ጥያቄዎች
በእዚህ ድምጽ ላይ ለመዳሰስ የተሞከረው
👉🏽ዘፈን ማን እንዳስጀመረ ለመጀመርያ ጊዜ(ታሪካዊ አመጣጡ
👉🏽 ዘፈን በመጽሐፍ ቅዱስ
👉🏽ዘፈን ያመጣው ጣጣ
👉🏽ዘፈን ለማቆም ምን እናድርግ
👉🏽የውጪው ሀገር በዘፈን ምን ላይ ደርሰዋ እስከ ታዋቂ ሰዎች ጭምር
መልካም ጊዜ
#ስምሽን_ስጠራው
ስምሽን ስጠራው ድንግል
ስምሽን ስጠራው ማርያም
ላንደበቴ ማር ነው ለልቤ ሰላም
ስምሽን ስጠራው ማርያም
#አዝ
ትውልድ ነኝና ልጅሽ የፈጠረኝ
ድንግል እመቤቴ ላንቺ ምስጋና አለኝ
በፈቃደ እግዚአብሔር ባባቶቼ ፀጋ
ሳዓሊ ለነ እላለው ሲመሽም ሲነጋ
#አዝ
በጠየቅሽው ጊዜ ወይኑን እንዲመላ
አክብሮሻልና በቃና ገሊላ
የሰላም እናት ሆይ ሰላም ልበልሽ
ዘመኔ ይፈፀም ሳመሰግንሽ
#አዝ
በሰላምታ ድምፅሽ መንፈስ ተመልቼ
አደግድጌ ልቁም እጆቼን ዘርግቼ
በአብይ ቃል ጮሄ ልመስክር በብርቱ
ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር እናቱ
#አዝ
ከሰማይ ሲገኝ ነው አንችን ማወደስ
ሲገለጥ ሲፈቀድ ከመንፈስ ቅዱስ
ማርያም ህይወቴ ነሽ ምክንያት ለመዳኔ
ብዙ ነው ምስጢሩ አንችን ማመስገኔ
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
#ማርያም_አረገች
ማርያም አረገች /2/ ወደ ገነት
የሠማይ መላዕክት በደስታ እያጀቧት
አረገች ወደ ገነት /2/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ ፍቺ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ! በየትም ዓለም የምትኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች ሰላምታችን ይድረሳችሁ፡፡
የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር የኖረችው ስልሳ አራት ዓመት ነው፡፡ እነዚህ ዓመታት ሲተነተኑ ሦስት ዓመት በወላጆቿ ሐናና ኢያቄም ቤት፣ ዐሥራ ሁለት ዓመት በቤተ መቅደስ፣ ሠላሣ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አሥራ አምስት ዓመት ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር ነው፡፡
ያረፈችውም ጥር 21 ቀን በ50 ዓ.ም ነው፡፡ ባረፈችበት ወቅት ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡር ሥጋዋን ለማሳረፍ ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲሔዱ አይሁድ "ቀድሞ ልጇ በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፤ በአርባኛውም ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ተመልሶም ይህን ዓለምን ለማሳለፍ ይመጣል እያሉ በማስተማር ሕዝባችንን ወስደውብናል፡፡ አሁን ደግሞ ዝም ብለን ብንተዋት እርሷም እንደ ልጇ ተነሳች እያሉ በማስተማር ሊያውኩን አይደለምን? ኑ! ተሰብስበን በእሳት እናቃጥላት" ብለው ክፉ ምክር ተማከሩ፡፡
ከመካከላቸውም ብርቱ ሰው የሆነው #ታውፋንያ የተባለ ቅድስት ሥጋዋን ከሐዋርያት ነጥቆ ለማስቀረት ክቡር ሥጋዋ ያለበትን የአልጋ ሸንኮር ሲይዝ በመልአከ እግዚአብሔር እጁ ተቆርጣ ከአልጋው ላይ ተንጠልጥላ ቀረች፤ ከዚህ የጥፋቱ ሥራው ተምሮ እመቤታችንን በመለመኑ እመቤታችን የተቆረጠች እጁን መልሳለታለች፡፡
ከዚህ በኋላ መልአከ እግዚአብሔር የእመቤታችንን የተቀደሰ ሥጋዋን ጌታችን ይወደው የነበረ ተብሎ የተነገረለት ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስን ይዞ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጠው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም የሆነውን ሁሉ ለወንድሞቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ነገራቸው፡፡ እነሱም የእመቤታችን ሥጋ በክብር ለማሳረፍ ካላቸው ጉጉት የተነሣ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምሮ ሱባኤ ገቡ፡፡
ከሁለተኛ ሱባኤ ቆይታቸው በኋላ በአሥራ አራተኛ ቀናቸው ጌታችን የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ ሰጣቸው፡፡ ሐዋርያትም በዝማሬና በታላቅ ምስጋና በጌቴ ሴማኔ ቀበሯት፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት› › ተብሎ ትንቢት የተናገረውን ሲተረጉሙት ‹‹ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት የምታሳርፈው የመቅደስህ ታቦት የሆነችውን ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ›› ብለው ያመሰጥሩታል፡፡ /መዝ. 131፥8/፡፡
የእመቤታችንን ቅድስት ሥጋዋን ሐዋርያት ሲቀብሯት በሀገረ ስብከቱ ሕንድ የነበረው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ ሲመለስ እመቤታችን ስታርግ ያገኛታል ለምልክት እንዲሆነው ሰበኗን (የመግነዟን ጨርቅ) ተቀብሏት ይለያያሉ፡፡ ለወንድሞቹ ሐዋርያት ያየውን ይነግራቸዋል፡፡
ለበረከት የሰጠችውንም ሰበን ያካፍላቸዋል፤ ሐዋርያት ‹ ‹ዕርገቷን እንዴት እሱ ብቻ ተመልክቶ ለምን እኛ ይቀርብናል› › ብለው በዓመቱ ነሐሴ አንድ ቀን ሱባኤ ገቡ፡፡ ነሐሴ 16 ቀን የልባቸው መሻት ተፈጸመላቸው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቀ (ረዳት) ቄስ፣ ቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን ገባሬ ሰናይ (ዋና ዲያቆን) አድርጎ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው፡፡
በትኅትና የያዙት ሱባኤም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገቷን ለማየት አበቃቸው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህን መሠረት አድርጋ ከነሐሴ 1-16 ጾመ ፍልሰታ በማለት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ አድርገን እንድንጠቀምበት ሥርዐት ሠራችልን፡፡
በነቢያና በሐዋርያት መሠረት ላይ የታነጽን ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች በየዓመቱ ይህን ጾም በሱባኤ በማሳለፍ ከእመቤታችን ጸጋና በረከት ተሳታፊዎች እንሆናለን፤ ሆነናልም፡፡ የዓመት ሰዎች ይበለን፡፡
ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ተቋዳሾች ያድርገን፡፡
አሜን!
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
#ሥርዓተ_ማኅሌት_ዘነሐሴ_ኪዳነ_ምሕረት
፩/ ነግሥ ( ለኲልያቲክሙ )
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤
ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤
እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤
ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኀኒት መስቀል፡፡
ዚቅ፦
ወታስተሥርዪ ኃጢአተ ሕዝብኪ ተበውሐ ለኪ ፨ እም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፨ ከመ ትኵኒ ተንከተመ ለዉሉደ ሰብእ፨ ለሕይወት ዘለዓለም ፨ ለኪ ይደሉ ከመ ትኵኒ መድኀኒቶሙ ለመሐይምናን ሕዝብኪ ፨ ኦ መድኀኒተ ኵሉ ዓለም ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡
፪/ ነግሥ ( እምጌቴሴማኒ ፈለሰት )
እምጌቴሴማኒ ፈለሰት ኀበ ዘሉዓሌ መካን፤
ውስተ ቤተ መቅደስ ረባቢ ዘመሳክዊሁ ብርሃን፤
አንቀጸ አድኅኖ ማርያም ጽላተ ኪዳን፤
ኵሉ ይብልዋ በአኅብሮ ዘበዕብራይስጢ ልሳን፤
ዕፀ ጳጦስ ይእቲ እንተ በአማን ቅድስተ ቅዱሳን፤
እመቅድሀ ከርሣ ተቀድሐ አስራባተ ወይን፤
ወበውስቴታ ተሠርዓ ቊርባን፡፡
ዚቅ፦
ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን መዝገቡ ለቃል ፨ ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን አንቀጸ ብርሃን፨ ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን ጽጌ ደንጐላት ፨ ሐረገ ወይን ዘእምነገደ ይሁዳ፨ እንተ ሠረፀት ለሕይወት፡፡
፫/ ለፍልሰተ ሥጋኪ ( መልክአ ኪዳነ ምሕረት )
ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ኀበ ሕንጻ ሕይወት ተሐደሰ፤
እምቅድመ ዝኒ ኀቤሁ ሥጋ ወልድኪ ፈለሰ፤
ቤዛዊተ ዓለም ማርያም አስተበቊዓኪ አንሰ፤
ትቤዝዊ በኪዳንኪ ዘዚአየ ነፍሰ፤
እስመ በሥራይኪ ለቊስልየ ቀባዕክኒ ፈውሰ፡፡
ዚቅ፦
ደብተራ ፍጽምት ዘጳውሊ፨ ወማኅደሩ በጽድቅ ዘገብራ ከሃሊ፨
ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ ፨ በመሰንቆሁ እንዘ የኃሊ፨ ዳዊት አቡሃ ዘወልዳ ወዓሊ።
ወረብ፦
ደብተራ ፍጽምት ዘጳውሊ ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ፤
በመሰንቆሁ እንዘ የሐሊ ዳዊት አቡሃ ዘወልዳ
ወዓሊ።
፬/ ለዝክረ ስምኪ ( መልክአ ማርያም )
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፤
እምነ ከልበኒ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ
ማርያም ድንግል ለባሲተ ዐቢይ ትእዛዝ፤
ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤
ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ፡፡
ዚቅ፦
ሰላም ለኪ ማርያም እመ አምላክ፨ ወልድኪ ይጼውዓኪ፨
ውስተ ሕይወት ወመንግሥተ ክብር፡፡
ወረብ፦
ሰላም ለኪ ማርያም እመ አምላክ ማኅደረ መለኮት፤
ወልድኪ ወልድኪ ይጼውዓኪ ውስተ ሕይወት ወምንግሥተ ክብር።
፭/ ለእስትንፋስኪ ( መልክአ ማርያም )
ሰላም እስትንፋስኪ ዘመዐዛሁ ሕይወት፤
ከመ መዐዛ ዕፅ ኅሩይ ዘውስተ ገነት፤
ማርያም ድንግል ቤተ ቅድሳት፥
ጽንሕኒ ውስተ ሠናይ ወሰውርኒ እሞት፤
በአክናፍኪ ርግብየ ኅሪት፡፡
ዚቅ፦
ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ፨ መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል፨ ወኵሉ ነገራ በሰላም፡፡
ወረብ፦
ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ ፤
መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል መዓዛ አፉሃ ታንሶሱ፡፡
፮/ ለፍልሰተ ሥጋኪ ( መልክአ ፍልሰታ )
ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ዘኢይቀብል ሞገሱ፤
ወዘኢይነጽፍ ባሕርየ ተውዳሱ፤
ማርያም ታዕካ ለእግዚአብሔር ጽርሐ መቅደሱ፤
ተበሃሉ በሰማያት እለ ኪያኪ አፍለሱ፤
ማርያምሰ እንተ በምድር ታንሶሱ ፡፡
ዚቅ፦
ማርያም ጽርሕ ንጽሕት ማኅደረ መለኮት ፨እኅቶሙ ለመላእክት ሰመያ ሰማያዊት ፨ እንተ በምድር ታንሶሱ፡፡
ወረብ፦
ማርያም ጽርሕ ንጽሕት ፤
ማኅደረ መለኮት ጽርሕ ንጽሕት።
+++++ አንገርጋሪ +++++
ትርሢተ ወልድ መለኮት ወፍቅር ኀደረ ላዕሌሃ፤
ይቤላ ርግብየ ወይቤላ ሠናይትየ፥
ፀቃውዕ ይውኅዝ እምከናፍሪሃ ፡፡
ወረብ ዘአመላለስ፦
ትርሢተ ወልድ መለኮት ወፍቅር ኀደረ ላዕሌሃ፤
ይቤላ ርግብየ ወይቤላ ወይቤላ ሠዓለም፡፡
+++++ ዘሰንበት +++++
የማነ ብርሃን ኀደረ ኀበ ማርያም ድንግል፨ጥዕምት በቃላ ወሠናይት በምግባራ፨ እሞሙ ለሰማዕት ፨ ወእኅቶሙ ለመላእክት ፨ እንተ ተሰምየት ሰንበተ ክርስቲያን ተስፋ ቅቡፃን ፨ መድኃኒተ ኮነት ለኵሉ ዓለም፡፡
አመላለስ፦
እንተ ተሰምየት ሰንበተ ክርስቲያን ተስፋ ቅቡፃን ፤
መድኃኒተ ኮነት ለኲሉ ዓለም።
+++++ መዝሙር ++++++
ሃሌ በ፰ እኅትነ ይብልዋ ወይኬልልዋ፨ ነያ ሐዳስዩ ጣዕዋ፨
ጸቃውዕ ይውኅዝ እምከናፍሪሃ ፨ ከመ ቅርፍተ ሮማን መላትሒሃ ፨ ልዑል ሠምራ ዳዊት ዘመራ በቤተ መቅደስ ተወክፍዋ።
መልካም በዓል
#ሆያ_ሆዬ
እንኳን ለደብረታቦር በዓል በሰላም
አደረሳችሁ አደረሰን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
#ሆያ_ሆዬ
ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ
እንኳን ለደብረታቦር በዓል በሰላም
አደረሳችሁ አደረሰን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ምሥጢረ ደብረታቦር
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
እንኳን ለደብረታቦር በዓል በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ
ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ ፤ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ ›
ቅዱስ ጴጥሮስ
ታቦር ተራራ የዛሬ ገጽታው
ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ቅዱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው።በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤሌያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን። ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ከኤልያስ እንሥራ አለ።
እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር። ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና። ተነሡ አትፍሩም አላቸው።ዓይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም። የማቴዎስ ወንጌል 17፡1-8
በቂሳርያ ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ ለሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል ብሎ ጠይቋቸው አንዳንዶች ከነቢያት አንዱ ነህ ይሉሃል፣ አንዳንዶች ሙሴ ነህ ይሉሃል፣ ሌሎች ደግሞ ኤልያስ ነህ ይሉሃል እያሉ መለሱለት ጌታችንም መልሶ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ብሎ ሲጠይቃቸው የሐዋርያት አፈጉባዔ ሊቀ ሐዋርያት ቅ/ጴጥሮስ ‹አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ ነህ› ብሎ በመመስከሩ ጌታም ‹የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ በሰማይ ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ…› ተብሏል፡፡
ይህ በሆነ በሰባተኛው ቀን ሦስቱን ደቀ መዛሙርት ጴጥሮስ፣ ዮሐንስና ያዕቆብን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ወጣ፡፡ በዚያም እንደ ዮርዳኖስ ወንዝ መድኃኔዓለም ክብረ መንግስቱን ፤ ብርሃነ መለኮቱን ገልጧል ፡፡ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ የሆነው በዓለ ደብረታቦር የዚህ ታሪክ መታሰቢያ ነው ፡፡
ታቦር ተራራ ከገሊላ ባሕር በስተምዕራብ 17 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ፤ ከናዝሬት ከተማ በስተምስራቅ ፤ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምዕራብ አቅጣጫ ሲገኝ ከባሕር ጠለል በላይ 572 ሜትር ነው ፡፡ከላይ ወደታች ሲታይ ታቦር ተራራ ቅርጹ የተገለበጠ የሻይ ስኒ ይመስላል ይላሉ ፡፡
እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።
ምሥጢረ መንግሥቱን ለምን በታቦር ተራራ ገለጸው ?
መድኃኔዓለም ሌሎች ተራሮች እያሉ ክብሩን ለመግለጥ ስለምን ደብረ ታቦርን መረጠ ቢሉ ትንቢቱንና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡
ትንቢት
“ ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ ወይሰብሑ በስምከ ”
ታቦርና አርሞንኤም በስምህ አምነው በተደረገላቸው ነገር ደስ ይላቸዋል፣ ስምህን ያመሰግናሉ፣ ለስምህም ምስጋና ያቀርባሉ፡፡ “ መዝ 88፡12
ምሳሌ
ባርቅ ሲሳራን ድል አድርጎበታል መሳፍንት 4፡6 ይኸውም ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡‹… የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደገና ክፉ ሥራ ሠሩ፡፡ እግዚአብሔርም በአሶር በነገሠው በከነዓን ንጉሥ በኢያቡስ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው የሠራዊቱም አለቃ በአሕዛብ አሪሶት የተመረጠው ሲሣራ ነበር… ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች ነበሩትና የእስራኤልንም ልጆች ሃያ ዓመት ያስጨንቃቸው ነበር›/መሳ 4.1-3/
ሁሌም ቢሆን የሰውን በደል ዐይቶ እንደወጣችሁ ግቡት፣ እንደገባችኋት ውጧት የማይልና ‹… ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል› የተባለለት እግዚአብሔር ከዚህ ቀንበር የሚላቀቁበትን መላ ራሱ አመለከታቸው፡፡ /1ቆሮ. 10-13/፡፡
እስራኤላውያን ወደ ፈጣሪያቸው በጮኹ ጊዜ የለፊዶት ሚስት የሆነችውንና እስራኤልን በነቢይነትና ዳኝነት ታገለግል የነበረችው ነቢይቱን ዲቦራን ተጠቅሞ የማሸነፊያ መላውን አመለከታቸው፡፡ ነቢይቱ ዲቦራ ትንቢት ከመናገር አልፋ የእስራኤልን ንጉሥ ባርቅ ከእኔ ጋር ወደ ጦርነቱ ውጪ ብሎ ባስጨነቃት ጊዜ በጦር አዝማችነትም ተሳተፈች፡፡
እግዚአብሔር በነቢይቱ በዲቦራ በኩል ለእስራኤል ንጉሥ ‹ሔደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጡ…› ብሎ አዞት ነበርና ንጉሡ ዐሥር ሺሕ ብረት ለበስ ያልሆነ እግረኛ ሠራዊት ይዞ ደብረ ታቦርን ተማምኖ በተራራው ላይ መሸገ ጦርነቱ ሳይጀመር አለቀ፡፡ ምክንያቱም ‹እግዚአብሔርም ሲሣራን ሰረገሎቹንም ሁሉ ሠራዊቱንም ሁሉ ከባርቅ ፊት በሰይፍ ስለት አስደነገጣቸው፡፡ ሲሣራም ከሰረገላው ወርዶ በእግሩ ሸሸ…› /መሳ. 4.15/
እስራኤል በእግዚአብሔር አጋዥነት በታቦር ተራራ ላይ የሃያ ዓመት የግፍና የሰቀቀን አገዛዝ ቀንበራቸውን ከትከሻቸው አሽቀንጥረው በምትኩ የድል ካባን ደረቡ ‹… በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ የባዕድ ጭፍሮችንም አባረሩ› ተብሎም ጀግንነታቸው ተጻፈላቸው፡፡ የታቦር ተራራ ያኔ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ባለውለታቸው ነበር፡፡ /ዕብ. 11.32-34/
ጌታም በልበ ሐዋርያት ያለ ሰይጣንን ድል ያደርግበታልና ማለትም በልባቸው ጥርጥርን እና ፍቅረ ሢመትን( የሥልጣን ፍቅር) ያሳደረ ዲያብሎስን ድል ነስቶላቸዋል ፡፡ከዚህም በመነሳት ነው በዓለ ደብረታቦር የደቀመዛሙርት ተማሪዎች በዓል ነው የሚባለው ፡፡
ለምን 3ቱን ሐዋርያት ( ጴጥሮስ ፤ዮሐንስ እና ያዕቆብን) ብቻ ይዞ ወደ ተራራ ወጣ፡-
ለፍቅሩ ስለሚሳሱ ነው፡፡ ይህም በዕብራይስጡ ኬፋ ፤ በግሪኩ ጴጥሮስ ፤በግዕዙ ኰኲሕ( ዐለት) የተባለው የዮና ልጅ ስምዖን ጌታ እሞታለሁ እያለ ጌታችን ሲናገር አይሁንብህ በማለቱ ከባሕርይ አባቱ ከአብ እርሱን ስሙት የሚል መለኮታዊ ድምጽ ሰምቷል፡፡ዮሐንስና ያዕቆብ ጌታን ምድራዊ መሲህ አድርጎ በማሰብ ቀኝ ጌትነትን እና ግራ ጌትነትን በእናታቸው በኩል የማይገባ ልመና አቀረቡ ዮሐንስና ያዕቆብ እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ? ሲባሉ አዎ ብለው መለሱ በዚህም ከባሕርይ አባቱ እርሱን ስሙት የሚል ድምጽ ሰሙ፡፡
በይሁዳ ምክንያት ነው ኢሳ 26.13 ‹ኃጥእ ሰው የእግዚአብሔርን ክብር እንዳያይ ያርቁታል› እንዲል እርሱን ጥሎ አስራ አንዱን ወደ ተራራ ይዞ ቢወጣ ከምሥጢር ቢለየኝ በሞቱ ገባሁበት እንዳይል፡፡ ያም ባይሆን ስምንቱ ደቀ መዛሙርት ለምን ይከለከላሉ ቢሉ አልተከለከሉም በርዕሰ ደብር (በተራራው አናት) ለሦስቱ ደቀ መዛሙርት የተገለጸው ምስጢር በእግረ ደብር (በተራራው ግርጌ) ለነበሩት ስምንቱ ደቀ መዛሙርት ተገልጦላቸዋል፡፡ ይህም በደብረሲና ለሰባው ሊቃናት የተገለጠ ምሥጢር በከተማ ለነበሩት ለኤልዳድና ሙዳድ እንደተገለጠ ማለት ነው፡፡ ዘኁልቊ 11፡26
#ቡሄ
ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡
#ጅራፍ
በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡
የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡
የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን #በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል፡፡
#ችቦ
ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡
የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዘዞ ችቦ በ13 ምሽት ይበራል ፣ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና ፡፡
#ሙልሙል
በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም፡፡
ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ….” ይላሉ፡፡
በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡
ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡
አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡
አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው፡፡ ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል።
ከዚም ጋር ተያይዞ ሰንበት ት/ት ቤታችን ለበረካታ ዓመታት ሲወርድ የመጣውን የዝማሬ ሥርዓት ለአጥብያው ምእምን በየቤቱ በመሄድ የብሄን ዝማሬ ከነሥርዓቱ በመዘመር አገልግሎት ይሰጣል ፤የደብር ታቦርን በዓል በተመለከትም የወረቀት ጽሑፎችን ይበትናል በዝማሬ መኃል ያድላል፡፡
ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው፡፡ በተለይ ወጣቱ ክፍል ይህንን አውቀን ተረድተን ለቀሪው ትውልድ ማስተላለፋ እንችል ዘንድ ከክፉ ጠላት ከሰይጣን ፈተና፣ በሽታ ከመሳሰሉት ችግሮች ለመዳን ወደ ተራራዋ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመሸሽ ከክፉ ነገሮች ሁሉ ማምለጥ ይቻላል፡፡
በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር የሚጠለሉ ሁሉ ዕድሜያቸው ይረዝማል፡፡ አስተዋዮችም ይሆናሉ ሁሉን ማየትና የሚጠቅማቸውን መምረጥ ይችላሉ በሥነ-ምግባር የታነፁ አገርንና ወገንን የሚጠቅሙ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በመጠጋት ከክፉ ሁሉ የሚያመልጡ ይሆናሉ ለዚህም የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤
#በስመ_ዚአከ
በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ ዮም /2/
ታቦር ወአርሞንዔም /2/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️