ዮሐንስን ይዛ ወደ ቀራንዮ
ዮሐንስን ይዛ ወደ ቀራንዮ
ድንግል ማርያም ሄደች እያለች ወዮ
ሥለ ልጇ ሐዘን ሥለ መከራዋ
ያስገርም ነበረ የፈሰሰው ዕንባዋ /፪/
ዮሐንስ ቢደንቀው የሐዘኗ ጽናት
አነሳት ደግፎ በብርቱ ሊያጽናናት
ድንግልም አለችው ልጄ አሳዘነኝ
እሕት ወንድም የለው ላልቅስለት ተወኝ
ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን
መቅደላዊት ማርያም ሶሎሜ ዮሐና
ማርያምን አይዋት ጸንቶባት ሐዘኗ
በልቅሶዋ ጣዕም ተነክቶ ልባቸው
ዕንባን አፈሰሱ ውለታው ገብቷቸው
ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን
ራሔል አልቅሳለች ላላቀፈቻቸው
ድንግል ግን ብታለቅስ አዝላው ተሰዳ ነው
ያዕቆብም አልቅሷል በሌላ የሠው ደም
ማርያም ግን ብታለቅስ ፈሷል የልጇ ደም
ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን
ጠብቶ ስለአደገ የድንግልና ጡቷን
መቆም አልቻለችም ስታይ መጠማቱን
በደም ተሸፍኖ ብታየው ውበቱን
ለይልኝ አለችው ከሥጋዋ ነፍሷን
ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን
ዮሐንስን ይዛ ወደ ቀራንዮ
ድንግል ማርያም ሔደች እያለች ወዮ
ሥለ ልጇ ሐዘን ሥለ መከራዋ
ያስገርም ነበረ የፈሰሰው ዕንባዋ
በእንተ ማርያም መሐርነ ክርስቶስ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
"ሲነጋም የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሎች ሁሉ ሊገድሉት ፣ ላይ ተማከሩ፤ አስረውም ወሰዱት፥ ለገዢው ለጴንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት።" ማቴ፳፯፥፩-፪
@ortodoxmezmur
ሕማማት ክፍል 32
👉 የኢየሱስን ልብስ ገፈፉት
✍ ጸሐፊ ፦ ዲ/ሄኖክ ኃይሌ
🎤 ተራኩ ፦ ኢዮብ ዮናስ
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሕማማት ክፍል 31
👉 አለቅነትም በጫንቃው ላይ ነው
✍ ጸሐፊ ፦ ዲ/ሄኖክ ኃይሌ
🎤 ተራኩ ፦ ኢዮብ ዮናስ
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሕማማት ክፍል 29
👉 ደምን የሚያወርሱ ወላጆች
✍ ጸሐፊ ፦ ዲ/ሄኖክ ኃይሌ
🎤 ተራኩ ፦ ኢዮብ ዮናስ
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ምን ሰጡህ ይሁዳ
ሙትን ልታስነሳ ድውይን ልትፈውስ
ሥልጣን ሰጥቶህ ነበር ኢየሱስ ክርስቶስ
ልታስር ልትፈታ በነፍስም በሥጋ
ሥልጣን ሰጥቶህ ነበር አልፋና ኦሜጋ
ምን ሰጡህ ይሁዳ አይሁድ ወገኖችህ
ለነርሱ አሳልፈህ ጌታህን የሰጠህ
ከሁሉ የሚበልጥ ሥልጣን ሰጥቶህ ሳለ
ብርን ለመቀበል ልብህ ተታለለ
ሰማይና ምድርን በቃሉ የፈጠረ
እንዴት በመቃብር ሶሥት ቀን አደረ
አንተ የሰጠኸው አሳልፈህ ለሞት
ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ በሰንበት
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ጉልባን
ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡
በጸሎተ ሐሙስ በቤት ውስጥ ከሚፈጸሙ ተግባራት አንዱ ጉልባን ማዘጋጀት ነው፡፡ ጉልባን እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ሲወጡ በችኮላ መጓዛቸውን የምናስታውስበት ከእስራኤላውያን የመጣ ትውፊታዊ ሥርዓት ነው፡፡
በአገራችን ኢትዮጵያ አብዛኞቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ይህ ሥርዓት ዛሬም በኢትዮጵያውያን ምእመናን ዘንድ ይከበራል፡፡
ጉልባን እስራኤላውያን ከባርነት በወጡ ጊዜ አቡክተው፣ ጋግረው መብላት አለመቻላቸውን ያስታውሰናል፡፡ በወቅቱ ያልቦካውን ሊጥ እየጋገሩ ቂጣ መመገብ ፤ ንፍሮ ቀቅለው ስንቅ መያዝ የመንገድ ተግባራቸው ነበርና፡፡
ይህን ታሪክ ለማሰብም በሰሙነ ሕማማት በተለይም በጸሎተ ሐሙስ ቂጣና ጉልባን ይዘጋጃል፡፡ በጸሎተ ሐሙስ የሚዘጋጀው ጉልባንና ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ይኸውም ጨው ውኃ እንደሚያስጠማ ዅሉ፣ ጌታችንም በመከራው ወቅት ውኃ መጠማቱን ለማስታወስ ነው፡፡
ምንጭ፡- ስምዐ ተዋሕዶ (ልዩ ዕትም ዘሰሙነ ሕማማት)
እንበለ ደዌ ወሕማም፥
እንበለ ጻማ ወድካም፥
ያብፀሓነ አመ ከመ ዮም።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
መዝ 68÷21
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ።
ወአስተዩኒ ብሒዐ ለጽምዕየ።
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ።
06/08/15 ዓ.ም
✝ በዕለቱ በ9 ሰዓት የሚሰበክ
ምስባክ።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
መዝ 27÷17
ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን።
ወአኀዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን።
ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን።
06/08/15 ዓ.ም
✝ በዕለቱ በ3 ሰዓት የሚሰበክ
ምስባክ።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሕማማት ክፍል 27
👉 ቀሚስህ ስለምን ቀላ
✍ ጸሐፊ ፦ ዲ/ሄኖክ ኃይሌ
🎤 ተራኩ ፦ ኢዮብ ዮናስ
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሕማማት ክፍል 25
👉 የእግዚአብሔር በግ በቀበሮ ፊት
✍ ጸሐፊ ፦ ዲ/ሄኖክ ኃይሌ
🎤 ተራኩ ፦ ኢዮብ ዮናስ
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሰሙነ ሕማማት
👉 ዓርብ
የስቅለት ዓርብ ይባላል፦
ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል።
ዝርዝሩን - https://youtu.be/NMHnlH0YLEE
መልካሙ ዓርብ ይባላል፡-
ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።
ዝርዝሩን - https://youtu.be/NMHnlH0YLEE
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሕማማት ክፍል 32
👉 የምትወዱት አልቅሱለት
✍ ጸሐፊ ፦ ዲ/ሄኖክ ኃይሌ
🎤 ተራኩ ፦ ኢዮብ ዮናስ
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሕማማት ክፍል 30
👉 የመከራ ጉዞ ወደ መከራ
✍ ጸሐፊ ፦ ዲ/ሄኖክ ኃይሌ
🎤 ተራኩ ፦ ኢዮብ ዮናስ
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
•✞ #አልፋና_ኦሜጋ ✞•
አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ (2)
በከሃዲዎች እጅ ተይዘክ ቀረብክ (2)
ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ
እየደበደቡ ክርስቶስ ሆይ አሉህ
ጽድቅን ስለሰራህ በወንጀል ከሰሱህ
ለአዳም ቤዛ ብለህ ብዙ ተንገላታህ
#አዝ•••
ቅዱሳን እጆችህ የፍጥኝ ታስርው
እንደ በግ ተጎትተህ ልትመራቸው
የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ
ፊትህን ሸፈኑት ለመመጻደቅ
#አዝ•••
በአውደ ምኩና ከጲላጦስ ዘንድ
አሳልፈው ሰጡ አጋልጠው ለፍርድ
ከሃና ቀያፋ ከመሳፍንቱ ደጅ
ከነሄሮድስ ዘንድ አቀረቡ በአዋጅ
#አዝ•••
ግርፋት ሕማሙ አልበቃ ብሎህ
በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ
ሳዶርና አላዶር ዳናትና አዴራ
ተፈልገው መጡ ለችንካር በተራ
#አዝ•••
የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ
ሊያያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ
ግፈኞች አይሁዶች ባንተ ላይ ቀለዱ
ምራቅን ተፉብህ እራስህን ሊጎዱ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
አክፍሎት
በሰሙነ ሕማማት ዕለተ አርብ ከስግደት በሗላ ምዕመናን በየቤታቸው ጥቂት ነገር ለቁመተ ሥጋ ቀምሰው እስከ እሁድ /የትንሳኤ ሰዓት/ ይሰነብታሉ፡፡ ይህ አክፍሎት ይባላል፡፡
ከአርብ እስከ ቅዳሜ ሌሊት ለእሁድ አጥቢያ ማክፈል የብዙዎች ነው። አንዳንዶች ግን ከሐሙስ ጀምረው ያከፍላሉ፡፡ ይህም እመቤታችን፣ ያዕቆብ እና ዮሐንስ የጌታን ትንሳኤ ሳናይ እህል ውሃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤ መቆየታቸውን ተከትሎ የመጣ ትውፊት ነው፡፡
ይህንን ትውፊት አስመልክቶ ሄሬ ኔዎስ፣ አውሳብዮስ የተባሉ ጸሐፍት፣ ሐዋሪያት በሰሙነ ሕማማት ከደረቅ ዳቦ እና ከትንሽ ውሃ በቀር እንደማይመገቡ እና ከሐሙስ ጀምረው እንደሚያከፍሉ ጽፈዋል፡፡
ይህም ብቻ ሳይሆን ሐዋሪያት ሌሎቹንም እንድያከፍሉ እንዲያሳስቡና ከሐሙስ ጀምሮ ያልተቻላቸው ቢያንስ ከአርብ ጀምሮ እንዲያከፍል ማዘዛቸውን ጽፈዋል፡፡ የኛ ቤተክርስቲያን ትምህርትም ይሄው ነው፡፡
ምንጭ፦ ስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
አምንስቲቲ ሙኪርያ አንቲ ፋሲልያሱ።
አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ።
አምንስቲቲ ሙዐግያ አንቲ ፋሲልያሱ።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
መዝ 21÷16
ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ።
ወኋለቁ ኵሎ አዕፅምትየ።
ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ።
06/08/15 ዓ.ም
✝ በዕለቱ በ6 ሰዓት የሚሰበክ
ምስባክ።
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
መዝ 34÷11
ተንሥኡ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ።
ወዘኢየአምር ነበቡ ላዕሌየ።
ተንሥኡ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ።
06/08/15 ዓ.ም
✝ በዕለቱ በ1 ሰዓት የሚሰበክ
ምስባክ።፥
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሕማማት ክፍል 28
👉 በርባን
✍ ጸሐፊ ፦ ዲ/ሄኖክ ኃይሌ
🎤 ተራኩ ፦ ኢዮብ ዮናስ
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሕማማት ክፍል 26
👉 በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን
✍ ጸሐፊ ፦ ዲ/ሄኖክ ኃይሌ
🎤 ተራኩ ፦ ኢዮብ ዮናስ
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሕማማት ክፍል 24
👉 ከንግግር የሚበልጥ ዝምታ
✍ ጸሐፊ ፦ ዲ/ሄኖክ ኃይሌ
🎤 ተራኩ ፦ ኢዮብ ዮናስ
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️