እንኳን ለቅዱስ ቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሰን አደረሳችሁ።
#ቅዱስ_ያሬድ_ማነው?
የቅዳስ ያሬድ አባቱ አብድዩ / ይስሐቅ/ እናቱ ክርስቲና /ታውክልያ / ይባላሉ። በሌላም በኩል አባቱ እንበረም እናቱ ትውልያ ይባላሉ የሚል ታሪክም አለ፡፡ የትውልድ ሥፍራው አክሱም ነው፡፡
የተወለደው በ505 ዓ.ም/ ሚያዝያ 5 ቀን ሲሆን በተወለደ በ7 ዓመቱ ወላጅ አባቱ ስለሞተ እናቱ የአክሱም ጽዮን መምህር ለነበረው ለአጎቱ ለጌዴዎን እያስተማረ እንዲያሳድገው ሰጠችው፡፡ ከአባ ጌዴዎንም ዘንድ እየተማረ ለ25 ዓመት ተቀመጠ፡፡
ሆኖም ቃለ እግዚአብሔር የመቀበል ችሎታው ደካማ ስለሆነ በጣም ያዝን ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ከትምህርት ድክመቱ የተነሣ አጎቱ በጨንገር ቢገርፈው በዚህ ተበሳጭቶ ትምህርቱን ትቶ ሄደ፡፡ በመንገድም ሲጓዝ ውሎ በቀትር ደክሞት ከዛፍ ሥር ዐረፈ፡፡
በዚያ ጊዜ አንድ ትል ከዛፉ ላይ ያለውን ፍሬ ለመብላት ስድስት ጊዜ በመውደቅና በመነሣት ዛፉ ላይ ለመውጣት ሞክሮ በሰባተኛው ሰተት ብሎ ወጥቶ ሲበላ ተመለከተ፡፡ እርሱም በፈጸመው የብስጭት ተግባር በመጸጸት ተመልሶና አጎቱን ይቅርታ ጠይቆ ትምህርቱን ቀጠለ፡፡
አጎቱም ተደስቶ ዓይነ ልቡናውን ያበራለት ዘንድ እያለቀሰ ፈጣሪውን ለመነለት፡፡ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰምቶ ለቅዱስ ያሬድ ዕውቀትን ገልጾለት መጻሕፍተ ብሉያትንና ሐዲሳትን ዐወቀ፡፡
ከዚያም በኋላ ወደ መምህሩ ተመልሶ ትምህርቱን ቀጠለና ቅዱሳት መጻሕፍትን በሚገባ አጠና፡፡ ሢመተ ዲቁናን ቀጥሎም ሢመተ ቅስናን ተቀበለ፡፡ ቅዱስ ያሬድ ግእዝ፣ እዝልና አራራይን ከሦስት ወፎች/መላእክት በወፎች ተመስለው/ መማሩን ሊቃውንት ይገልጣሉ፡፡
እነዚህ በወፍ የተመሰሉ መላእክት እየመሩት ወደ አርአያም አርጎ የ24ቱን ካህናተ ሰማይ ዜማ ከተማረ በኋላ ጠዋት በ3 ሰዓት በአክሱም ቤተ ክርስቲያን «ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሣረረ ወበዳግመ አረአዮ ለሙሴ ዘከመ ይግበር ግብራ ለደብተራ» ብሎ አዜመ፡፡
ይህን ዜማ የደረሰበት ወሩ ታኅሳስ ቀኑም ዕለተ ሰኞ ነው ይባላል፡፡ የቅዱስ ያሬድ የመጀመሪያ ዜማው «አርያም» በመባል ይታወቃል፡፡ ይህም ከመላእክት ወይም ከሰማይ የተገኘ መሆኑን ለማጠየቅ የተሰጠው ስም ነው፡፡
ቅዱስ ያሬድ ይህንን ዜማ በተመስጦ ሲያዜም ንጉሡ ፣ ንግሥቲቱ ፣ ጳጳሱ መኳንንቱና ካህናቱ ወደ አኩስም ቤተ ክርስቲያን ተሰባስበው መጥተው በአድናቆት ያዳምጡት ነበር፡፡ ምክንያቱም ገድለ ቅዱስ ያሬድ እንደሚገልጥልን ከዚያ በፊት በውርድ ንባብ ከሚደረግ ጸሎትና መንፈሳዊ አገልገሎት በቀር ይህን የመሰለ ዜማ አልነበረምና፡፡
የቅዱስ ያሬድ ድርሰት ብሉይን ከሐዲስ ያስማማ ፣ የሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን ትምህርት በሚገባ የያዘ ፣ እንዲሁም ለልዑል እግዚአብሔር ፣ ለእመቤታችን ፣ ለቅዱሳን መላእክት ፣ ለሰማዕታት ተገቢ የሆነውን ምስጋና የያዘ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ለአራቱ የዓመቱ ወቅቶች እንዲስማማ አድርጎ ለበጋ፣ ለክረምት ፣ ለመጸውና ለጸደይ እንደሚሆን አድርጎ ከፋፍሏቸዋል፡፡
ለየበዓላቱም ተስማሚ ድርሰት መድቦላቸዋል፡፡ ይህንን ድርሰቱን በግእዝ ፣ በእዝልና በአራራይ ዜማ ያዘጋጀው ሲሆን ለነዚህም ስምንት የዜማ ምልክቶች ሠርቶላቸዋል፡፡
የቅዱስ ያሬድ ዜማ አንዴት ሁሉንም ይመስጥና ወደ አርያም በመንፈስ ይወስድ እንደ ነበር ለማስረዳት በገድሉም በሌሎችም መጻሕፍት የተመዘገቡ ታሪኮች አሉ፡፡ አንድ ቀን ንጉሥ ገብረመስቀል ፣ ንግሥቲቱ ፣ ጳጳሱ ፣ ካህናቱና ምእመናኑ በተሰባሰቡበት ቅዱስ ያሬድ ዜማውን ሲያዜም ንጉሡ በመመሰጡ የተነሣ በመሰቀል ተሰላጢኑ ጫፍ የቅዱስ ያሬድን እግር ወጋው፡፡
ነገር ግን ማንም አላወቀም ነበር፡፡ ቅዱስ ያሬድ መዝሙሩን ሲፈጽም ንጉሡ መስቀል ተሰላጢኑን ቢያነሳው የቅዱስ ያሬድ ደሙ ፈሰሰ፡፡ ንጉሡ በዚህ ደንግጦ ለዚህ ካሣ ይሆን ዘንድ የፈለግከውን ጠይቀኝ እሰጥሃለሁ ብሎ ቃል ገባለት፡፡ ቅዱስ ያሬድ ግን ከዚህ ዓለም ተለይቶ በምናኔ መኖርና መዝሙሩንም በሚገባ ማዘጋጀት እንደሚፈልግ ገለጠ፡፡
ምንም እንኳን አክሱምን ለቅቆ መውጣቱ ንጉሡን ቅር ቢያሰኘውም ቃሉን አንድ ጊዜ በመስጠቱ ምንም ሊያደርገው አልቻለም፡፡ ቅዱስ ያሬድም ከዚህ በኋላ አኩስምን ለቅቆ ወደ ስሜን ተራራ ጸለምት መጓዙ ይነገራል፡፡
#ይቀጥላል
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሠላም የተወደዳችሁ የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች።
ዛሬ ከአምስቱ አእማደ ምሥጢር 4ተኛ የሆነውን ምሥጢረ ቁርባንን እናያለን።
ማታ ስለ ቅዱስ ቁርባን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቱን እናያለን። እስከዛ ግን ወደ ቁርባን መቅረብ ለምትፈልጉ ይህንን አዳምጡት👇👇👇
ጉባኤ አቅሌስያ
የእግዚአብሔር ፍቅር የበዛላችሁ የሊቀ መላእክቱ የቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች ሆይ እነሆ በጎ ስራ በመስራት እግዚአብሔርን ደስ የምናሰኝበት ጊዜ ደረሰ።
በማዕከላዊ ጎንደር በለሳ ወረዳ ቤተክህነት የሚገኘው የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ከፍተኛ የሆነ የህልውና ችግር አጋጥሞታል።
ስለክርስቶስ ስም ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ ገዳማውያን አበው መነኮሳት እና መነኮሳይት ከማይታየው ፣ ከማይዳሰሰውና ከማይጨበጠው ጠላታችን ጋር በፆም በፀሎት ሲዋጉልን በአለም ከሚገጥማቸው ችግር ደግሞ ልናግዛቸው የመንፈስ ልጆቻችሁ አለን ልንላቸው ይገባናል።
ስለሆነም ገዳሙ ከቁስቋም ቅድስት ማርያም መንፈሳዊ ማህበር ጋር በመተባበር ግንቦት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ታላቅ የሆነ ጉባኤ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዮኒቨርስቲ አራተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው አዳራሽ አዘጋጅቷል።
በዕለቱም ትምህርተ ወንጌል
1- መምህር ጳውሎስ መልከዐ-ሥላሴ
2- መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየዉ
3-መምህር አንተነ አበበ እና ሌሎች መምህራን
እንዲሁም በዝማሬ
1- ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
2- ዘማሪት ሲስተር ሊድያ ታደሰ እና ሌሎችም የሚቀርብ ሲሆን
የተለያዩ የኪነጥበብ ስራዎችም በተለያዩ አርቲስቶች
1-አርቲስት ቸርነት ፍቃዱ እና ሌሎችም ይቀርባል
ኑ የወንጌል ማዕድ እየተቋደስን ስለኛ የተራቡ ገዳማውያንን አለን እንበላቸው።
ለበለጠ መረጃ:-0986348964 ወይም 0912779749
ገዳሙን ድጋፍ ማረግ ለምትፈልጉ በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ሙት አንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል ገዳም
ወዳጄ ሆይ የቅዱሳን ገዳማውያን ገድልና የህወታቸው ኑሮ ለሁሉም መልካም ምሳሌና አርአያ ሊሆን ይችላል ።
በዝማሬ ዳዊት Tube የተላለፉ ትምህርቶች
1⃣ ኦርቶዶክስ እና የዓለም እምነቶች
https://youtu.be/HXh1IUuBOrE
2⃣ እግዚአብሔርን እንዴት መውደድ እንዳለብን
https://youtu.be/Asx80GdsDDE
3⃣ 666 እና የውጭ ዘፋኞች
https://youtu.be/3iFggkALrws
4⃣ ዘፈን እንዴት ተፈጠረ? ማንስ አስተማረን?
https://youtu.be/1P421kYHutU
5⃣ ስለ ቶ መስቀል ክፍል 1
https://youtu.be/qevNJ5hYQ90
6⃣ ስለ ቶ መስቀል ክፍል 2
https://youtu.be/3H0FkrKbg9A
7⃣ ስለ ቶ መስቀል የመጨረሻው ክፍል
https://youtu.be/2QB2Ra7FHf8
8⃣ ሴጋ የፈጸመ የተክሊል ጋብቻ ይገባዋልን?
https://youtu.be/hnt5Y1F4TDY
9⃣ በጸሎት መሀል ወሬ ማውራት
https://youtu.be/2VsM6cVwgcU
1⃣0⃣ ቅዠት ምንድን ነው?
https://youtu.be/m6eD1pzyIWM
1⃣1⃣ የምግብ ሰዓት ጸሎት
https://youtu.be/pjBReIJQ-Q4
1⃣2⃣ የምእመናን አለባበስ ምን ይመስላል
https://youtu.be/fKuDfxWKUyY
1⃣3⃣ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና ፕሮቴስታንት ክፍል አንድ
https://youtu.be/HBb3vZBZqzs
1⃣4⃣ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና ፕሮቴስታንት ክፍል ሁለት
https://youtu.be/PbmNFCYro4I
1⃣5⃣ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና ፕሮቴስታንት የመጨረሻው ክፍል
https://youtu.be/1NKzUoqtucs
1⃣6⃣ ስለ ቅዱስ ቁርባን ክፍል አንድ
https://youtu.be/Oji7daT4obw
1⃣7⃣ ንስሐ መግባት ለምን እንፈራለን?
https://youtu.be/kIkhOnUJm_A
1⃣8⃣ ሕማማት
https://youtu.be/NMHnlH0YLEE
1⃣9⃣ ስለ ዓቢይ ጾም
https://youtu.be/uErRRCkMsU0
2⃣0⃣ ዘጠኙ አጾማት
https://youtu.be/ZV7iwQS8mEk
2⃣1⃣ ለፓስተር ዳዊት የተሰጠ ምላሽ
https://youtu.be/hK473EGk0qs
2⃣2⃣ ለዮናታን አክሊሉ የተሰጠ ምላሽ
https://youtu.be/m8sFeVaja4I
2⃣3⃣ ጸሎት ምንድን ነው?
https://youtu.be/ZFYd4X-eGBo
2⃣4⃣ ክርስቲያናዊ የሆነ ጾም እንዴት እንጹም
https://youtu.be/ZV7iwQS8mEk
2⃣5⃣ ከፍቅረኛዬ ጋር ወደፊት ስለምንጋባ አሁን ግንኙነት ብንፈጽምስ?
https://youtu.be/ZV7iwQS8mEk
2⃣6⃣ ግብረ አውናን ምንድነው?
https://youtu.be/1XgZf6hq8bs
2⃣7⃣ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ማድረግ ያለብን ዝግጅት?
https://youtu.be/TQeWVmN47PY
2⃣8⃣ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ? 81 ወይስ 66
https://youtu.be/Iggo8ws7quM
በዝማሬ ዳዊት የተላለፉ አጭር ታሪኮች
1⃣ የሰይጣን ጥያቄ
https://youtu.be/mHGEluQCJNY
2⃣ ባላገሩ
https://youtu.be/Kcftb4CReyg
👉 የልደት (ገና) መዝሙሮች
https://youtu.be/iSWmxwIJAac
👉 የጥምቀት መዝሙሮች
https://youtu.be/ESAE29ZvF3o
👉 አጫብር ወረብ
https://youtu.be/phssFP3KCRg
👉 መጾሙን ይጾማል - የበገና መዝሙር
https://youtu.be/q0TcGVnRGb4
👉 ማን ይመራመር - የበገና መዝሙር
https://youtu.be/dHqXNw_27R8
👉 የሰርግ መዝሙሮች
https://youtu.be/Xyc7R1Gk2Fs
👉 ዓለምን ዞሬ አየሁት? - የበገና
https://youtu.be/YP5ugEAYQRg
👉 ስለ ቸርነትህ - የበገና
https://youtu.be/KGBhL_7pA1c
ለሁሉም ሼር ያድርጉ ላላወቁት እናሳውቅ!
Subscribe ማድረግዎን እንዳይዘነጉ
የመዝሙር ስብስብ
👉 የድንግል ማርያም መዝሙሮች
💵 በpackage 0.59 ብር
💵 በካርድ 0.98 ብር
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
❖ ሚያዝያ ፴ ❖
❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖
እንዲህ ኃጢአታችን ጽዋዑን ሞልቶ በተረፈበት በዚህ ዘመን አንዲት ሰዓትም ውድ የሆነች የንስሃ ዕድሜ ናት:: እግዚአብሔር ግን ደግ ነውና ይሔው ሚያዝያን አስፈጸመን::
+ ባይገባን ነው እንጂ በዚሕች ወር ውስጥ:-
- ሚሊየኖች በደዌ የአልጋ ቁራኛ ሁነዋል::
- ሚሊየኖችም ለንስሃ ሳይበቁ እንዲሁ አንቀላፍተዋል (ሙተዋል)::
+ እስኪ እርሱ አምላካችን ቀሪዋን ዘመን ደግሞ ለንስሃና ለመልካም ሥራ ባርኮ ይስጠን::
" ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ "
በዚሕች ዕለት ከ72ቱ አርድእት አንዱ የሆነ: ወንጌላዊ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ዘአንበሳና ርዕሰ ሊቃነ ዻዻሳት የተባለ ቅዱስ ማርቆስ በሰማዕትነት ግብፅ ውስጥ ዐርፏል::
+ ቅዱስ ማርቆስ እናቱ ማርያም: አባቱ አርስጥቦሎስ ይባላሉ:: በልጅነቱ ኦሪትንና የዘመኑን ጥበብ ሥጋዊ በሚገባ ተምሮ ክርስቶስን ከቤተሰቦቹ ጋር ተከትሏል::
+ የመጀመሪያ ስሙ ዮሐንስ ሲሆን ከ120ው ቤተሰብ በእድሜ በጣም ትንሹ (20 ዓመት) እርሱ ነበር:: ለ3 ዓመታት ከጌታ እግር ሥር ተምሮ: በበዓለ ሃምሳ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ብዙ ደክሟል::
በተለይ የግብፅና የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን አባት ነው:: ክህነትን ያገኘን ከርሱ ነውና:: ቅዱስ ማርቆስ 16 ምዕራፍ ያለውን ወንጌሉን ሲጽፍ ኪሩብ ገጸ አንበሳ በቀኙ: ሊቀ ሐዋርያት በግራው ሆነው ይራዱት ነበር::
ቅዱሱ ክቅዱስ ዻውሎስ: ከበርናባስና ዼጥሮስ ጋር ተጉዟል:: ከብዙ ስቃይና መከራ በኋላ ሰሜን አፍሪካ አካባቢ በዚህ ቀን በ60 ዓ/ም አካባቢ አረማውያን ገድለውታል::
ዳግመኛ በዚህ ቀን የቅዱስ ማርቆስን ወላጆችን እናስባቸው ዘንድ ይገባል::
❖ ቅዱስ አርስጥቦሎስ (አባቱ) የጌታ ቅን አገልጋይ የነበረ፡፡
❖ ቅድስት ማርያም (እናቱ)
- ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ:
- ጌታችንን ያገለገለች:
- ቤቷን ለሐዋርያትና ለጌታ በስጦታ ያበረከተች ቅድስት ናት::
+ ቤቷም (ጽርሐ ጽዮን) የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ስትሆን ይህች ቤት መንፈስ ቅዱስ ወርዶባታል:: የእመቤታችን ግንዘትም ተከናውኖባታል::
❖ እግዚአብሔር ከሐዋርያዊው ቅዱስ ቤተሰብ በረከትን ያድለን::
ሚያዝያ 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ አርስጥቦሎስ (አባቱ)
3.ቅድስት ማርያም (እናቱ)
ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
2.አባ ሣሉሲ ክቡር
3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
4.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
"+ . . . እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ:: ዼጥሮስም የደጁን መዝጊያ ባንኩዋኩዋ ጊዜ ሮዴ የሚሏት አንዲት አገልጋይ ትሰማ ዘንድ ቀረበች:: የዼጥሮስ ድምጽ መሆኑንም ባወቀች ጊዜ ከደስታዋ የተነሳ ደጁን አልከፈተችም:: ነገር ግን ወደ ውስጥ ሮጣ ዼጥሮስ በደጅ ፊት ቆሞ እንዳለ አወራች::
+" (ሐዋ. 12:12-15)
ዝክረ ቅዱሳን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ለመሆኑ በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ መዝሙር ቻናል ተቀላቅለዋል ? የሰርግ ፣ የሀዘን ፣ የንግስ መዝሙራት ፣ የተለያዩ ወረባት ፣ የመዝሙር ግጥሞችን ያገኛሉ ። አብረውንም መዝሙራትን ያጠናሉ ። # ይቀላቀሉን https://t.me/joinchat/AAAAAE5K_dyT2-AYoTAW5A
Читать полностью…🌺 ሰላም፡ለኵልክሙ የግእዝ ወዳጆች በሙሉ
እነሆ በአዲስ መልኩ ተመልሰን የ"ግእዝን በአንድ ወር" ኮርሳችንን በ፯ኛው ዙር የኦንላይን ትምህርት ለመስጠት ምዝገባ ጀምረናል።
📜 በመሆኑም የግእዝ ቋንቋን መሠረታዊ ትምህርት ለጀማሪዎች ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅታችንን በመጨረሳችን ከታች በተቀመጠው መሠረት በመመዝገብ ጥንታዊ ቋንቋችንን እናጥና ዕንወቅ።
📖 የሚሰጠው ትምህርት፦ የግእዝ ቋንቋ መሠረት (መሠረተ ግእዝ)
⏳ የሚጀምርበት ቀን፦ ግንቦት 2
🌐 የሚሰጥበት ቦታ ፦ በቴሌግራም
...........................
✅ የመመዝገቢያና የበለጠ ማብራሪያ ቦታ በዚህ ገብተው ያግኙ👇
👉 [https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdugh4KZ5HpGX5Xh1jbX1LbAvgN5E6kGOkx7hD7nytXu5eLbA/viewform?usp=sf_link] 🤏
..........................................................
🆔 ሞልተው እንደጨረሱ @Geez202 በዚህ ገብተው ID በመቀበል ምዝገባውን ያጠናቅቁ + ለበለጠ መረጃ ደውለው ያግኙን። ሠናይ፡ጊዜ።
🈸 መሠረተ፡ግእዝ
@MesereteGeez◦0977682046
#ቸሩ_መድኃኔዓለም
ቸሩ መድኃኔዓለም አንተው
ቅረበን ተለመነን /2/
በምሕረትሕ እና በቸርነትህ
እንዳትለየን /4/
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
🌺 ሰላም፡ለኵልክሙ የግእዝ ወዳጆች በሙሉ
እነሆ በአዲስ መልኩ ተመልሰን የ"ግእዝን በአንድ ወር" ኮርሳችንን በ፯ኛው ዙር የኦንላይን ትምህርት ለመስጠት ምዝገባ ጀምረናል።
📜 በመሆኑም የግእዝ ቋንቋን መሠረታዊ ትምህርት ለጀማሪዎች ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅታችንን በመጨረሳችን ከታች በተቀመጠው መሠረት በመመዝገብ ጥንታዊ ቋንቋችንን እናጥና ዕንወቅ።
📖 የሚሰጠው ትምህርት፦ የግእዝ ቋንቋ መሠረት (መሠረተ ግእዝ)
⏳ የሚጀምርበት ቀን፦ ግንቦት 2
🌐 የሚሰጥበት ቦታ ፦ በቴሌግራም
...........................
✅ የመመዝገቢያና የበለጠ ማብራሪያ ቦታ በዚህ ገብተው ያግኙ👇
👉 [https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdugh4KZ5HpGX5Xh1jbX1LbAvgN5E6kGOkx7hD7nytXu5eLbA/viewform?usp=sf_link] 🤏
..........................................................
🆔 ሞልተው እንደጨረሱ @Geez202 በዚህ ገብተው ID በመቀበል ምዝገባውን ያጠናቅቁ + ለበለጠ መረጃ ደውለው ያግኙን። ሠናይ፡ጊዜ።
🈸 መሠረተ፡ግእዝ
@MesereteGeez◦0977682046
✝️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::✝️
እንደምን አመሻችሁ የተወደዳችሁ ኦርቶዶክሳውያን እህቶቼ እና ወንድሞቼ?
በእዚህ ድምጽ ውስጥ የሚዳሰሱት ነጥብ
🌹ቅዱስ ቁርባን ምንድነው? ምን ማለት ነው?
🌹ቅዱስ ቁርባን መቀበል እፈልጋለሁ ግን በእዚህ እድሜዬ እችላለሁ?
🌹ቅዱስ ቁርባን በሐዲስ ኪዳን እና በብሉይ ኪዳን
🌹ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ምን አይነት ዝግጅት ማድረግ አለብን?(ወደ ሥጋ ወ ደሙ ከመቅረባችን በፊት; በቀረብን ጊዜ; ከተቀበልን በኃላ ምን ማድረግ አለብን?)
🌹የአምላካችንን ቅዱስ ሥጋ ና ደም በመቀበላችን ምንደነው በህይወታችን የምናገኘው ጥቅም?
🗣በይሳኮር🙏
‹‹ከሰው ጋር በከንቱ አትጣላ›› መጽሐፈ ምሳሌ ፫፥፴
ክርስትና ዕለት ዕለት የምንኖረው ሕይወት ነው፡፡ በማኅበራዊ ኑሮአችን ውስጥ ደግሞ ብዙውን ጊዜ የምናሳልፈው ከሰዎች ጋር በሚኖረን ግንኙነት ነው፡፡ በእነዚህ ግንኙነቶች ውስጥ ደግሞ ዘወትር በሐሳብ ተግባብቶ አንድ ዓይነት አመለካከት ይዞ መኖር አይቻልም፡፡ ከእኛ ጋር በሐሳብ የማይግባቡና አንድ ዓይነት አመለካከት የሌላቸው፣ በእምነት የሚመስሉንም ሆነ የማይመስሉን ሰዎች ያጋጥሙናል፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር በንጉሥ ሰሎሞን ላይ አድሮ በተናገረው ቃል መሠረት የሚፈጠሩትን አለመግባባቶች በጥበብ ማለፍ እንደሚገባን ማስተዋል የምንጀምረው በዚህ ጊዜ ነው፡፡ ‹‹ከሰው ጋር በከንቱ አትጣላ›› እንዲል፤ (ምሳ.፫፥፴)
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ደግሞ ለዚህ አብነት የሚሆኑ ብዙ ቅዱሳን አሉ፡፡ ከሰው ጋር በከንቱ ሊጣሉ ቀርቶ “ሰውን የሚያሳዝን ነገር ተናግሬ ወይም ፈጽሜ ይሆናል” ብለው ሲያስቡ እንኳን የሰውን ንብረት ሆነ ሌላ ቁስ ሊነኩ ቀርቶ የራሳቸውንም ሰጥተውና ይህችን ዓለም ንቀው በሰላም መኖርን ይመርጣሉ፡፡
ከሰው ጋር በከንቱ ሳይጣሉ በሰላም ስለመኖር ቅዱሳት መጽሐፍትም ገልጸዋል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ማርቆስ ወንጌል ‹‹ጼወ ርከቡ በበይናቲክሙ ወተሰነአው፤ እናንተ በእናንተው ጼው (ጨው) አግኙ፤ ተስማሙ›› በማለት አስተምሮናል፡፡ (ማር.፱፥፵፱) ጨው የተባለ ሥራ ሁሉ የሚሠራበት፣ ከሰው ሁሉ ጋር በጥበብ የሚያኖር ፍቅር ነውና ከሰው ሁሉ ጋር በፍቅር ልንኖር ይገባል፡፡
ቅዱስ ጳውሎስም ለዕብራውያን ሰዎች በላከው መልእክቱ ‹‹ወሩጹ ኀበ ሰላም ምስለ ኲሉ፤ ከሁሉ ጋር ፍቅርን፣ አንድነትን ወደ መያዝ ገሥግሡ›› ብሎ መክሮናል፡፡ (ዕብ.፲፪፥፲፬) ምንም እንኳን ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን በዚህ ሐሰት እና መተላለፍ በበዛበት ዓለም ከሰዎች ጋር በሚኖረን ግንኙነቶች ከባድ ችግር ሊገጥመን እንደማይችል የሚታወቅ ቢሆንም አምላካችን መድኃኒታችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱሳን ሐዋርያቱ አድሮ እንዳስተማረን ከሰው ሁሉ ጋር በፍቅር እና በአንድነት መኖር ያስፈልጋል፡፡
በፍቅርና በሰላም እንድንኖር የአምላካችን ቸርነት፣ የድንግል ማርያም አማላጅነት እና የቅዱሳን ተራዳኢነት አይለየን!
የመዝሙር ስብስብ 2
👉 የድንግል ማርያም መዝሙሮች
💵 በpackage 0.62 ብር
💵 በካርድ 1.04 ብር
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ልደታ ለማርያም
👉 የማርያም ልደት ምን ይመስላል?
💵 በpackage 0.32 ብር
💵 በካርድ 0.54 ብር
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
#መዝ. 86፥1
“መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፡- መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮችናቸው”
ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም በእመቤታችን ልደት ምክንያትዛሬ ደስ ሆነ፡፡
በግንቦት 1 ቀን 5ሺ ከ5መቶ የመከራው ዘመን ሊያልቅ 15 ዓመታት ሲቀሩት/ ሊባኖስ በሚባል ተራራ ከፀሐይ የምታበራ ሴት ልጅ ተወለደች፡፡
ይህቺውም ፍጥረት ሁሉ ደቂቀ አዳም ሁላቸው ተስፋ ሲያደርጓትና ሲጠባበቋት የነበረች የድኅነታቸው ምልክት እመቤታችን ናት፡፡
ሶሪያዊው ሊቅ ቅዱስ ኤፍሬምም
“አክሊለ ምክሕነ ወቀዳሚተ መድኀኒትነ፡፡ወመሠረተ ንጽሕነ ኮነ በማርያም ድንግል:- የመመኪያችን ዘውድ የደኅንነታችን መጀመሪያ የንጽሕናችንም መሠረት በድንግል ማርያም ሆነልን” በማለት መናገሩ ስለዚህ ነው፡፡
አክሊል ምክሐነ አላት ይህም አክሊል የወዲህኛው፣ ምክሕ የወዲያኛው ነው። ከነገሥታት መካከል እንደ ዳዊት የከበረ የለም።
ምንም እንኳን ቅዱስ ዳዊት የከበረ ቢሆን የመመኪያችንን ዘውድ ማምጣት አልተቻለውም፡፡
ወቀዳሚተ መድኀኒትነ አላት፡- ቀዳሚተ የወዲህኛው መድኀኒት የወዲያኛው ነው፡፡ከመሳፍንት ወገን የሚሆን ኢያሱ ምንም የስሙ ትርጓሜ መድኃኒት ቢሆን የደኅንነታ መሆን አልተቻለውም፡፡
ወመሠረተ ንጽሕነ አላት:- መሠረት የወዲህኛው፤ ንጽሕ የወዲያኛው ከነቢያተ እግዚአብሔር ወገን የሚሆን ኤልያስ በድንግልና በንጽሕና መኖሩ የሚታወቅ ነው፡፡
ነገር ግን ምንም ንጹሕ ድንግል ቢባል የንጽሕናችንመሠረት መሆን አልተቻለው።
የመመኪያችን ዘውድ፣ የደኅንነታችን መጀመሪያ፤ የንጽሕናችን መሠረት ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፤” በማለት ተናግሯል።
በእርሷ ምክንያትነት መድኀኒዓለም የሚፈጽምልንን ካሳነቢያትና የቀደሙ አበው ሁሉ
የእርሷን መወለድ በናፍቆት ሲጠባበቁ ነበር።
ከነቢያት አንዱ የሆነ ኢሳይያስም
“የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርዘርን ባያስቀርልን
ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ጎሞራም በመሰልነ ነበር፡፡” በማለት መናገሩ በእርሷ መገኘት ከጥፋት መዳናችንን ሲገልጽ ነው፡፡
#ኢሳ 1፥9
#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
🌺 ሰላም፡ለኵልክሙ የግእዝ ወዳጆች በሙሉ
እነሆ በአዲስ መልኩ ተመልሰን የ"ግእዝን በአንድ ወር" ኮርሳችንን በ፯ኛው ዙር የኦንላይን ትምህርት ለመስጠት ምዝገባ ጀምረናል።
📜 በመሆኑም የግእዝ ቋንቋን መሠረታዊ ትምህርት ለጀማሪዎች ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅታችንን በመጨረሳችን ከታች በተቀመጠው መሠረት በመመዝገብ ጥንታዊ ቋንቋችንን እናጥና ዕንወቅ።
📖 የሚሰጠው ትምህርት፦ የግእዝ ቋንቋ መሠረት (መሠረተ ግእዝ)
⏳ የሚጀምርበት ቀን፦ ግንቦት 2
🌐 የሚሰጥበት ቦታ ፦ በቴሌግራም
...........................
✅ የመመዝገቢያና የበለጠ ማብራሪያ ቦታ በዚህ ገብተው ያግኙ👇
👉 [https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdugh4KZ5HpGX5Xh1jbX1LbAvgN5E6kGOkx7hD7nytXu5eLbA/viewform?usp=sf_link] 🤏
..........................................................
🆔 ሞልተው እንደጨረሱ @Geez202 በዚህ ገብተው ID በመቀበል ምዝገባውን ያጠናቅቁ + ለበለጠ መረጃ ደውለው ያግኙን። ሠናይ፡ጊዜ።
🈸 መሠረተ፡ግእዝ
@MesereteGeez◦0977682046
🇪🇹 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ የትኞቹን መዝሙራት ማግኝት ይፈልጋሉ❓
👏 የቸብቸቦ መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🎻 የበገና መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
👑 የቅዱሳን መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
⛪️ የንግስ መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🤲 የምስጋና መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🙏 የንስሐ መዝሙራት
📖▓⇨→Audio ⇨ግጥም
💍 የሠርግ መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🌦 ወቅታዊ መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🇪🇹 ለአገር የተዘመሩ
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
👇👇👇👇
✝▓⇨→ሌሎችንም ለማግኘት...
#ለመላው_ዓለም
ለመላው ዓለም መድህን የሆነው
በእጸ መስቀል ላይ የዋለው
እናመስግነው /2/ እንመነው መድኃኔዓለም ነው
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን
ሚያዝያ ፳፯
እንኳን ለታላቁ ሰማዕት "ቅዱስ ፊቅጦር" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ማር ፊቅጦር
ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በደማቸውና በገድላቸው ያስጌጡ ብዙ ሰማዕታት አሉ:: ነገር ግን ከኮከብም ኮከብ ይበልጣልና ማን እንደ ጊዮርጊስና እስጢፋኖስ!
ከእነርሱ ቀጥለው ከሚጠሩ ሰማዕታት ደግሞ አንዱና ዋነኛው ቤተ ክርስቲያን "ማር" የምትለው ቅዱስ ፊቅጦር ነው:: እስኪ ከበዛው መዓዛ-ገድሉ ጥቂት እንካፈል::
ቅዱስ ፊቅጦር አባቱ ኅርማኖስ ይባላል:: አረማዊና ጨካኝ ነው:: እናቱ ግን የተመሰገች ቅድስት ማርታ ትባላለች:: ልጇን እንደሚገባ አሳድጋው 20 ዓመት ሲሞላው የአንጾኪያ ንጉሥ የሠራዊት አለቃና በመንግሥቱ 3ኛ አድርጐ ሾመው::
የድሮዋ አንጾኪያ (ሮም) እንደ ዛሬዋ አሜሪካ ዓለምን የተቆጣጠረች ሃገር ነበረች:: ቅዱስ ፊቅጦር ደም ግባቱ ያማረ: በጦርነትም ኃይለኛ ስለ ነበር ሁሉ ያከብሩት: ይወዱትም ነበር:: እርሱ ግን ቀን ቀን ሲጾም: ነዳያንን ሲያበላ ይውል ነበር::
ሌሊት ደግሞ እኩሉን ሲጸልይና ሲሰግድ: እኩሉን የእስረኞችን እግር ሲያጥብ ያድር ነበር:: ይህ ሁሉ ሲሆንኮ እርሱ የንጉሡ 3ኛ: የሠራዊትም አለቃ ነው:: በዘመኑ የሚያገድፍ ምግብና የወይን ጠጅ በአፉ ዙሮ አያውቅም::
ከነገር ሁሉ በሁዋላ ንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ ካደ:: ዘመነ ሰማዕታትም ጀመረ:: አብያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ:: ከ47 ሚሊየን በላይ ክርስቲያኖች በመንኮራኩር ተፈጩ: በመጋዝ ተተረተሩ: ለአራዊት ተሰጡ: በግፍም ተጨፈጨፉ:: ቀባሪ አጥተውም ወደቁ::
በዚሕ ጊዜ ማር ፊቅጦር እናቱን ቅድስት ማርታን በዕንባ ተሰናብቶ ወደ ንጉሡ ቀርቦ በክርስቶስ ስም ታመነ:: ክፉ አባትም በልጁ ላይ ሞትን መከረ::
ከዚያም ቅዱሱን አፉን በብረት ለጉመው ወደ ምድረ ግብፅ አወረዱት:: መሪያቸው እንዳልነበረ ወታደሮቹ መኳንንቱ ሁሉ ተዘባበቱበት:: እርሱ ከምድራዊ ንግሥና ሰማያዊ መንግስትን: በሰዎች ፊት ከመክበር ስለ ክርስቶስ ሲል መናቅን መርጧልና::
ለቀናት: ለወራትና ለዓመታት መኳንንቱ እየተፈራረቁ አሰቃዩት:: በርሱ ላይ ያልሞከሩት የስቃይ ዓይነት አልነበረም:: አካሉን ቆራርጠዋል: ዓይኖቹን አውጥተዋል: ምላሱንም ቆርጠዋል::
በዚሕች ዕለት ግን በሰይፍ አንገቱን ቆርጠውታል:: ስለዚህም እናት ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ማክበር ታከብረዋለች:: እግዚአብሔርም ለቅዱስ ፊቅጦር እንዲህ አለው:-
"እንደ አቅሙ ስምህን የጠራ: መታሠቢያህን ያደረገ: ስምህን ያከበረ: የብርሃን ልብስ አጐናጽፌ ወደ መንግስተ ሰማያት አስገባዋለሁ::"
❖ ቸሩ አምላከ ፊቅጦር ሁላችንም ይማረን:: ከቃል ኪዳኑ አሳትፎ ለርስቱ ያብቃን::
❖ ሚያዝያ 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ጽኑዕና ኃያል ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
2.ቅድስት ማርታ (የፊቅጦር እናት)
3.ብጽዕት እስጢፋና (በክርስቶስ ስላመነች ከ2
ሰንጥቀው የገደሏት የ15 ዓመት ወጣት)
4.ቅዱሳን ሳሲማና አባ ኖባ (ሰማዕታት)
ወርኀዊ በዓላት
1.የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት
2.አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ
3.ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ) 4.ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
5.ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
6.ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
" እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ: ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን::" (ዕብ.
6:10-13)
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💍💍 የጋብቻ ወቅት እንደመሆኑ የሠርግ መዝሙራትን ከግጥምና ከ ዜማቸው ጋር ማግኘት ከፈለጉ ይቀላቀሉን
/channel/+0nmdk7ixreBhZDc0