ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ክፋትን ጥሉ

እግዚአብሔርን የምትወዱ
አምላኬ ነው የምትሉ
ክፋትን ጥሉ
....አዝ...
የታተማችሁ በቅዱስ ደሙ
የተጠራችሁ በሕያው ስሙ
ከፀብ እራቁ ሽሹ ከክፋት
ፍቅንር ልበሱ ቁሙ በእውነት
.... አዝ....
በቀልን ገንዘብ የምታደርጉ
ከወንድማችሁ የምትዋጉ
የጠራን በዚህ ስለማይከብር
እያመለክነው አንከራከር
.... አዝ.....
መገፋት እንጂ የኛ ግብራችን
እንደተማርነው ለአምላካችን
አትታወቁ ሰውን በመክሰስ
በእግረ ስጋ በመመላለስ
..... አዝ....
ማህተብ ያሰረ ከአንገቱ ላይ
የፍቅር ሰው ነው በምድሪቱ ላይ
መስቀልን እንጂ ሾተል አይዝም
የሚያጣፍጥ ነው አልጫን አለም

ዘማሪ ሊቀ መዘምራን
ቴዎድሮስ ዮሴፍ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ኪዳነ ምህረት ልዩ ነሽ ለኔ

ኪዳነ ምህረት ልዩ ነሽ ለኔ
ሳዝን ስጨነቅ አትራቂኝ ከጎኔ
የችግሬ ደራሽ እመ እግዚአብሔር
ቃል ኪዳንሽ ይርዳኝ ካንቺ ጋር ልኑር(፪)
#አዝ
የአዳም ተስፋው ነሽ የሴት ቸርነቱ
ኪዳነምህረት ነሽ የኖህ ምልክቱ
አዳም ደጅ የጠናሽ ሲገባ ንስሀ
ኖህም ድኖብሻል ከጥፋቱ ውሃ
#አዝ
የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ
ማርያም አንቺ ነሽ የፈጣሪ እናቱ
የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ
እመብርሃን ስሚኝ ልመናየን ሁሉ
#አዝ
የሰሎሞን አክሊል የዳዊት ዝማሬ
ድንግል መሆንሽን ትመስክር ከንፈሬ
ለተጠማው ውሻ የሚራራው ልብሽ
ለኔም እራርቶልኝ አስታርቂኝ ከልጅሽ
#አዝ
የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ
ማርያም አንች ነሽ የፈጣሪ እናቱ
የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ
እመብርሃን ስሚኝ ልመናዬን ሁሉ

ዘማሪት ሲስተር ፋሲካ መኮንን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ማርያም_አርጋለች ✞

ማርያም አርጋለች ወደ ገነት(፪)
የሰማይ መላእክት እያረጋጓት
እርሷም እንደ ልጇ ተነስታለች

የአባቷን ዳዊት ትንቢት ልትፈፅም
ወርቁን ተጎናፅፋ በቀኙ ልትቆም
ወደ አምላክ ማደሪያ ወደ ሰማያት
አረገለች በእልልታ ድንግል የእኛ እናት
አርጋለች ማርያም ተነስታለች
#አዝ
ሰማያት ይከፈት ደመናም ይዘርጋ
ዝምታም አይኖርም እመ አምላክ አርጋ
አንደበት ይከፈት ማርያምን ያመስግን
ከዘላለም ጥፋት በምልጃዋ እንድንድን
አርጋለች ማርያም ተነስታለች
#አዝ
የአምላክ ማደሪያ ቅዱስ ስጋሽ
አምላክን ያቀፉት እነዚያ እጆችሽ
ሙስና መቃብር ይዞ አላስቀራቸው
ተነስተዋል በክብር በእምነት አየናቸው
አርጋለች ማርያም ተነስታለች
#አዝ
ሐዋርያት አበው እንኳን ደስ አላችሁ
በክብር አረገች ማርያም ሞገሳችሁ
ወደ ዓለምም ውጡ ሰበኑዋን ይዛችሁ
የድንግል እርገቷን ንገሩ ተግታችሁ
አርጋለች ማርያም ተነስታለች

"በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና
ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።"
መዝ ፵፬፥፱

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​​​እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ ፍቺ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ! በየትም ዓለም የምትኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች ሰላምታችን ይድረሳችሁ፡፡

የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር የኖረችው ስልሳ አራት ዓመት ነው፡፡ እነዚህ ዓመታት ሲተነተኑ ሦስት ዓመት በወላጆቿ ሐናና ኢያቄም ቤት፣ ዐሥራ ሁለት ዓመት በቤተ መቅደስ፣ ሠላሣ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አሥራ አምስት ዓመት ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር ነው፡፡

ያረፈችውም ጥር 21 ቀን በ50 ዓ.ም ነው፡፡ ባረፈችበት ወቅት ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡር ሥጋዋን ለማሳረፍ ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲሔዱ አይሁድ "ቀድሞ ልጇ በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፤ በአርባኛውም ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ተመልሶም ይህን ዓለምን ለማሳለፍ ይመጣል እያሉ በማስተማር ሕዝባችንን ወስደውብናል፡፡ አሁን ደግሞ ዝም ብለን ብንተዋት እርሷም እንደ ልጇ ተነሳች እያሉ በማስተማር ሊያውኩን አይደለምን? ኑ! ተሰብስበን በእሳት እናቃጥላት" ብለው ክፉ ምክር ተማከሩ፡፡

ከመካከላቸውም ብርቱ ሰው የሆነው #ታውፋንያ የተባለ ቅድስት ሥጋዋን ከሐዋርያት ነጥቆ ለማስቀረት ክቡር ሥጋዋ ያለበትን የአልጋ ሸንኮር ሲይዝ በመልአከ እግዚአብሔር እጁ ተቆርጣ ከአልጋው ላይ ተንጠልጥላ ቀረች፤ ከዚህ የጥፋቱ ሥራው ተምሮ እመቤታችንን በመለመኑ እመቤታችን የተቆረጠች እጁን መልሳለታለች፡፡

ከዚህ በኋላ መልአከ እግዚአብሔር የእመቤታችንን የተቀደሰ ሥጋዋን ጌታችን ይወደው የነበረ ተብሎ የተነገረለት ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስን ይዞ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጠው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም የሆነውን ሁሉ ለወንድሞቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ነገራቸው፡፡ እነሱም የእመቤታችን ሥጋ በክብር ለማሳረፍ ካላቸው ጉጉት የተነሣ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምሮ ሱባኤ ገቡ፡፡

ከሁለተኛ ሱባኤ ቆይታቸው በኋላ በአሥራ አራተኛ ቀናቸው ጌታችን የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ ሰጣቸው፡፡ ሐዋርያትም በዝማሬና በታላቅ ምስጋና በጌቴ ሴማኔ ቀበሯት፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት› › ተብሎ ትንቢት የተናገረውን ሲተረጉሙት ‹‹ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት የምታሳርፈው የመቅደስህ ታቦት የሆነችውን ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ›› ብለው ያመሰጥሩታል፡፡ /መዝ. 131፥8/፡፡

የእመቤታችንን ቅድስት ሥጋዋን ሐዋርያት ሲቀብሯት በሀገረ ስብከቱ ሕንድ የነበረው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ ሲመለስ እመቤታችን ስታርግ ያገኛታል ለምልክት እንዲሆነው ሰበኗን (የመግነዟን ጨርቅ) ተቀብሏት ይለያያሉ፡፡ ለወንድሞቹ ሐዋርያት ያየውን ይነግራቸዋል፡፡

ለበረከት የሰጠችውንም ሰበን ያካፍላቸዋል፤ ሐዋርያት ‹ ‹ዕርገቷን እንዴት እሱ ብቻ ተመልክቶ ለምን እኛ ይቀርብናል› › ብለው በዓመቱ ነሐሴ አንድ ቀን ሱባኤ ገቡ፡፡ ነሐሴ 16 ቀን የልባቸው መሻት ተፈጸመላቸው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቀ (ረዳት) ቄስ፣ ቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን ገባሬ ሰናይ (ዋና ዲያቆን) አድርጎ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው፡፡

በትኅትና የያዙት ሱባኤም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገቷን ለማየት አበቃቸው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህን መሠረት አድርጋ ከነሐሴ 1-16 ጾመ ፍልሰታ በማለት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ አድርገን እንድንጠቀምበት ሥርዐት ሠራችልን፡፡

በነቢያና በሐዋርያት መሠረት ላይ የታነጽን ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች በየዓመቱ ይህን ጾም በሱባኤ በማሳለፍ ከእመቤታችን ጸጋና በረከት ተሳታፊዎች እንሆናለን፤ ሆነናልም፡፡ የዓመት ሰዎች ይበለን፡፡

ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ተቋዳሾች ያድርገን፡፡
አሜን!

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​በወር አበባ ግዜ የሚከለከል ጸሎትስ አለ?

ወዳጆቼ ቤተ-ክርስትያናችን ከሠራችልንና ከደነገገችልን የግል ጸሎቶች ውስጥ በወር አበባ ጊዜ ይሄ አይጸለይም ይህ የተከለከለ ብላ አላስተማረችንም። ስለዚህ ያስለመድናቸውን ጸሎቶች ሁሉ መጸለይ እንችላለን፡፡ እራሳችሁን ከኃጢአት እንጂ ከጸሎት አታርቁ፡፡ አንደበታችሁን ከሐሜት እንጂ ከጸሎት አታርቁ፡፡

ሥራችሁን ከወር አበባ አንጽታችሁ፣ በልባችሁ ማህደር ቂም እና ክፋት ቋጥራችሁ ብትጸልዩ ምን ዋጋ አለው? ከአንድ ሳምንት ከመርገም ጨርቅ ይልቅ በኃጢአት፣ በሐሜት ፣በክፋት ከሚጨማለቅ ሰውነት የሚቀርብ ጸሎት ከደመና በታች ነው፡፡

የወር አበባ በአንድ ሳምንት ይነጻል፡፡ ግን ከሰውነታችን አልነጻ ያሉን ስንት ኃጢአቶች አሉ፡፡ ስለዚህ ንጹህም ሆንን አልሆንን በርትተን ተግተን ልንጸልይ ይገባል፡፡

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በአርጋኖን ምስጋናው ‹‹የምድር ኃጥአን ሁላችሁ ወደ ቅድስት ድንግል ኑ በእርሷ ስጦታ ጻድቃን ትሆኑ ዘንድ ልብሳችሁ ያደፈ ሁላችሁ ወደዚህች ቅድስት ምንጭ ኑ፣ የይቅርታ ውኃ ወደምታፈስ ልብሳችሁንም በልጇ ደም እጠቡ ለሰማያዊ ሙሽርነት ዝግጁ ትሆኑ ዘንድ›› ብሏል፡፡

ወዳጆቼ መርገመ ሥጋ፣ መርገመ ነፍስን ያራቀችልን እመቤታችንን ስለሆች ጸሎታችንን በእሷ ንጽህና እንድትቀበለን ንጹህ ባንሆንም እንማጸናት እንጸልይ፡፡

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች?
ክፍል 2


ተወዳጆች ሆይ ጌታችን ደመኛን እንጂ ደምን አይጠየፍም አይጠላም፡፡ ቢጠየፍማ ለአሥራ ሁለት ዓመት ሰውነቷ በደም ሲጨቀይባት የነበረችውን ምስኪን ሴት መለኮት ጋ ጠጋ ብላ ልብሱን ነክታ ልትድን ቀርቶ መርገምንና ሌላ በሽታን ሸምታ በተቀሰፈች ነበር፡፡

ጌታችን ግን መልካም አመጣጧን ፣ የዓመታት ጭንቀቷን ተመልክቶ ከነደሟ ተቀብሎ በልቧ የነበረውን አውቆ ፣ የደሟን ምንጭ አድርቆ፣ እምነቷን አድንቆ፣ ከጤናዋ ጋር በሰላም ወደ ቤቷ መልሷታል፡፡ /ማቴ. 9፣18-26, ማር. 5፣21-43, ሉቃ. 8፤41 ይመልከቱ/

ወለላይቱ የእመብርሃን ልጆች የእመቤታችንን ባህርይ አላወቅንም እንጂ፤ እርሷ ጥዩፍነት ከቶ በባህሪዋ የለም፡፡ የዛሬውን አያድርገውና ሁላችንም ስንወለድ እናቶቻችን በምጥ ሰዓት ከነደማቸው በጸሎትና በጭንቀት ጠርተዋት አወዋልዳቸዋለች፤ አሁንም ታዋልዳቸዋለች፡፡ በአራስራቸው ጊዜ ከእነሱ አትለይም፣ እስከ ስሙም ‹የማርያም አራስ› ተብለው በስም ይጠራሉ፡፡

አንዳንዶቹ እንኳን ሊጸለይ ቀርቶ የጸሎት መፅሐፍ አይነካም እያሉ እህቶቻችንን የሚያሳቅቁ አሉ፡፡ እባካችሁ ሰው ከምታሳቅቁ እወቁ፣ ጠይቁ፣ ጠንቅቁ፣ ያለበለዚያ ለእህቶቻችን ፈተና አትሁኑ፡፡

ባይሆን ጥሩ ስሜትና መንፈስ ካልተሰማችሁ ሰውነታችሁን መታጠብ፣ አንቀጸ ሥጋችሁን/የከበረውን ቦታ/ ብቻ በመታጠብ ጸሎታችሁን መቀጠል ትችላላችሁ፡፡ ምናልባት የስንፍና ምክር ሰምታችሁ ካልሆነ በስተቀር ከወር ወር ጸሎት የምናስተጓጉልበት፣የምትተዉበት ምክንያት የለም፡፡

ይቀጥላል
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​👉 በሱባኤ ወቅት የወር አበባ/ደመ ፅጌ/ ቢታየን ምን እናድርግ?
👉 ሴት በወር አበባ ጊዜ መጸለይ ትችላለች?
👉 በወር አበባ ጊዜ የሚከለከልስ ጸሎት አለ?


ሼር በማድረግ ለእህቶቻችን አድርሱ

ተወዳጆች ሆይ ሴት ልጅ በሱባኤ ወቅት የወር አበባ/ደመ ፅጌ/ ቢታያት ከሱባኤ የመውጣትና የመቆየቷ ነገር እንደ ገዳሙ ሥርዓት ይወሰናል፡፡ ከሱባኤ ትወጣለች ማለት ሱባኤን (አርምሞን) ትፈታለች፣ ተአቅቦዋን ትተዋለች ማለት ሳይሆን እስከምትነፃ ድረስ ገዳሙ ባዘጋጀው ቦታ ቆይታ መጨረስ ትችላለች፡፡

በሱባኤው አጋማሽ ላይ ወይንም መውጫው ሲቃረብ የወር አበባ ቢታያት ሱባኤውን ማቋረጥ ሳይሆን በጊዜያዊ ቦታ መጨረስ ይገባታል፡፡

ብዙዎች እህቶቻችን ሱባኤ የምንይዙት በድንገት ነው፡፡ ይህ ችግር እንዳይገጥማችሁ ሱባኤ ከመግባታችሁ በፊት ቀናችሁን ቆጥራችሁ አስተካክላችሁ ብትይዙ የበለጠ ትጠቀማላችሁ፡፡ ሰይጣን ያለጊዜው በወር አበባ ሊፈትናችሁ ስለሚችል ቀናችሁን እንደጨረሳችሁ ሱባኤ ብትይዙ ይመረጣል፡፡

በተለይ ዓይነ ጥላ ከዓይነ ጥላም ገርግር ዓይነ ጥላ ያለባቸውና መተት እና ድግምት የተደገመባቸው እህቶቻችን ያለ ጊዜና ያለ ቀኑ በሚመጣ የወረር አበባ በሱባኤ ወቅት ይፈተናሉ፡፡ ምስጋና ለእመቤታችን ይሁንና እመቤታችን ንፁህ አይደላችሁም በማለት ጸሎታችሁን ቸል ስለመትል የያዛችሁትን ሱባኤ ቀጥሉ፡፡ ምክንያቱም የእኛ ርኩሰት የእመቤታችንን ንፅህና ስለማያሳድፍ ጸሎታችንን ትሰማናለች፡፡

በቀጣይ 👉 ሴት በወር አበባ ጊዜ መጸለይ ትችላለች?

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​​​​​ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል ?

3ኛ/ ስንታበይ

አንዳንድ ጊዜ ምናልባት የዝሙት ሐሳብ ሲጠፋልን እራሳችንን እንደ ንፁህ በምንቆጥርበት ጊዜ ወይም ወደ ብቃት ደረጃ የደረስን አድርገን ስናስብ፤ ይህ መታበይ ነውና በትንሹ ጽድቃችን እራሳችንን ከፍ እንዳናደርግና ለራሳችን ልዩ የጽድቅ ቦታ እንዳንሰጥ እግዚአብሔር ሊገስጽን እንዲህ አይነት ፈተና ይመጣብናል፡፡

በመታበይ ውስጥ ያለን ሰዎች ሕልመ ሌሊት (ዝንየት) በሚመታን ሰዓት የኃጢአተኝነትና የመርከስ ስሜት ስለሚሰማን ራሳችንን ዝቅ በማድረግ ስለምንወቅስ እግዚአብሔር እንዲህ ዓይነት መንፈስ እንዲኖረን ስለሚሻ በዚህ መልኩ ሊያስተምረን ይችላል፡፡

በአንድ ወቅት ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችን በሰውነቱ ያደርገው የነበረውን ቅንዋት እንዲሰጠው ጠየቀው፡፡ ጌታም እጅግ ይወደው ስለነበረ ሰጠው፡፡ ዮሐንስም የጌታን ቅንዋት በሰውነቱ ቢያደርገው ፍፁም ድንግልና እንደ መላእክት ንፁህነት ተሰማው፡፡ ጌታም የተሰማውንና ያሰበውን ስላወቀ ወዳጄ ዮሐንስ ሆይ ‹‹ንጹህ ማነው?›› አለው፡፡

ዮሐንስም ‹‹ጌታ ሆይ! አንተ እና እኔ›› አለ፡፡ ጌታም ወዳጁ ዮሐንስ በመታበይ እንዳይወድቅበት ስላሰበ ሌሊት በሕልመ ሌሊት ፈተነው፡፡ ጠዋት ሲያገኘው ‹‹አሁንስ ንፁህ ማነው?›› አለው፡፡ ዮሐንስም ‹‹ጌታ ሆይ ንፁህ አንተ ብቻ ነህ’’ አለው፡፡ ዮሐንስም ሰው ምንም ቢመረጥ ንፅህና የባህሪ ገንዘቡ ለጌታችን ብቻ እንደሆነ በመመስከር እራሱን ዝቅ በማድረግ ተምሮበታል፡፡

በቀጣይ 👉 ሕልመ ሌሊት መፍትሔ ?

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​የቀጠለ

ኤልያስና ሙሴን ለምን አመጣቸው?
- በአንድ ወቅት ነቢዩ ሙሴ እግዚአብሔርን ‹‹ወለእመሰ ረከብኩ ሞገሰ በኀቤከ አስተርእየኒ ገሐደ ሊተ ወአእምር ወእርአይከ ከመ ይኩነኒ ርኪበ ሞገሰ በቅድሜከ ዮም›› ፣ በአንተ ዘንድ ባለሟልነትን ማግኘቴ እውነት ከሆነስ ፊት ለፊት ተገልጸህልኝ ልይህና በአንተ ዘንድ ባለሟልነትን ማግኘቴን ልወቀው› ሲል ጠይቆት ነበር፡፡

እግዚአብሔርም ‹… ትሬኢ ድኅሬየ ወገጽየሰ ኢያስተርኢ ለከ፣ ጀርባዬን ታያለህ ፊቴን ግን አታይም› ብሎት ነበር፡፡ /ዘጸ. 33.13 እና 23/ የዚህ ኃይለ ቃል ትርጓሜና ሐተታ በደብረ ታቦር ተፈጸመ፡፡ እንዲህ ማለቱ በአምስት ሺሕ አምስት መቶ ዘመን ሰው ሆኜ ሥጋ ለብሼ ኋላ በደብረ ታቦር እስክገለጽልህ ድረስ አንተ በመቃብር ተወስነህ ትኖራለህ ማለቱ ነበር፡፡ ይህን ማለቱ እንደሆነ የታወቀው ግን በደብረ ታቦር ሙሴን ከብሔረ ሙታን አምጥቶ ባቆመው ጊዜ ነበር፡፡

- ልዑል እግዚአብሔር ነቢዩ ኤልያስን ‹አንተሰ ትከውነኒ ስምዓ በደኃሪ መዋዕል፣ አንተ በኋለኛው ዘመን ምስክር ትሆነኛለህ› ብሎት ነበርና ይኸውም ኃይለ ቃል ኤልያስ ከብሔረ ሕያዋን መጥቶ ‹የእኔን የኤልያስን ጌታ ማን ኤልያስ ነው ይልሃል እግዚአ ኤልያስ፤ አምላከ ኤልያስ ይበሉህ እንጂ› ሲል በደብረ ታቦር ተፈጸመ፡፡ ታያለህ የተባለው ሙሴም አየ፣ ትመሰክራለህ የተባለው ኤልያስም መሰከረ፡፡

- በፊልጶስ ቂሳርያ ጌታ ሐዋርያትን ‹ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደሆነ ይሉታል?› ብሎ በጠየቃቸው ጥያቄ ሲመልሱ ሙሴ ነው ይሉሃል ፤ እንዲሁም የኃይል ስራህን ተመልክተው ኤልያስ ነህ ይሉሃል ብለው ነበርና ሙሴን ከመቃብር ፤ ኤልያስን ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ እግዚአ ሙሴ ፤ አምላከ ሙሴ ፤ እግዚአ ኤልያስ ፤ አምላከ ኤልያስ መሆኑን ለማስመስከር፡፡

ታቦር ተራራ የዛሬ ገጽታው ከሩቅ ዕይታ

ታቦር ተራራ የወንጌል ምሳሌ
1. ተራራ ሲወጡት ያደክማል፣ ከወጡት በኋላ ግን ጭንጫውን፣ ግጫውን ሲያሳይ ደስ ያሰኛል፡፡ ወንጌልም ሲማሯት ትከብዳለች በኋላ ግን ጽድቅን እና ኃጢአትን ለይታ ስታሳውቅ ደስ ታሰኛለች፡፡

ታቦር ተራራ የቤተክርስቲያን ምሳሌ
1. በታቦር ተራራ ከብሉይ ኪዳን ነቢያት ኤልያስና ሙሴን፣ ከሐዲስ ኪዳን ሦስቱን ሐዋርያት እንደተገኙ በቤተክርስቲያን ብሉይ ከሐዲስ እንዲነገር ለማጠየቅ ፤ ሐዋርያት የሰበኩት ወንጌል አስቀድመው ነቢያት በምሳሌና በትንቢት የተናገሩት እንደሆነ ሲያስረዳ ነው ፡፡ ነቢያት በቀየሱ ሐዋርያት ገሰገሱ እንዲል ‹በሐዋርያት በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል›ኤፌ 2፣20

2. በታቦር ተራራ ከመዓስባን (ባለትዳር) ሙሴን ከደናግል ደግሞ ኤልያስ እንደተገኙ በቤተክርስቲያን በድንግልና የሚኖሩ መናንያን መነኮሳትም፣ በሕግ በሥርዓት የሚኖሩ ባለትዳሮችም ይገኛሉና፡፡

ታቦር ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ
1. ተራራውን ችግር እንዲወጡት መንግሥተ ሰማያትንም በብዙ መከራ የምትገኝ ናትና ‹እስመ በብዙኅ ጻማ ወድካም ኀለወነ ንባአ ለመንግሥተ እግዚአብሔር› ‹ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል› ሐዋ 14፡22

2. በታቦር ተራራ የብሉይ ኪዳን ነቢያት፣ ከሐዲስ ኪዳን ሐዋርያት እንደተገኙ መንግሥተ ሰማያትን ነቢያትም፣ ሐዋርያትም አንድ ሆነው እንደሚወርሷት ያጠይቃል፡፡

3. በታቦር ተራራ ከመዓስባን ሙሴ፣ ከደናግል ደግሞ ኤልያስ እንደተገኙ መንግሥተ ሰማያትን ደናግልም መዓስባንም በአንድ ላይ እንዲወርሷት ያጠይቃል፡፡

4. በታቦር ተራራ ሞተው ከተቀበሩት መካከል ሙሴን አመጣ፣ በብሔረ ሕያዋን ካሉት ደግሞ ኤልያስን አመጣ መንግሥተ ሰማያትንም ሞተው የተቀበሩትም በብሔረ ሕያዋን ያሉትም በአንድነት እንደሚወርሷት ያጠይቃል፡፡

በአጠቃላይ ታቦር ተራራ፡-
1. የክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት የተመሠከረበት፣
2. የምስጢረ ሥላሴ ትምህርት የተሰጠበት
3. ፈጣሪ ከቅዱሳን ሰዎቹ ጋር የተገኘበት
4. በልበ ሐዋርያት የነበረ ሰይጣን ድል የተደረገበት
5. የሐዋርያት በተለይም የሦስቱ ባለሟልነት የተገለጠበት፣
6. አሉባልታና ተራ ወሬ የከሸፈበት፣
7. የቅዱሳንን ክብር ለሚያናንቁ ተራራም እንኳን ‹ቅዱስ› እንደሚባል የተማሩበት፣
8. የብሔረ ሕያዋን መኖር የተመሰከበረበት
9. የትንሣኤ ሙታን ዋስትና የተገለጠበት የክብር ሰገነት፣ የምስጢረ መቅደስ፣ ታላቅ ትምህርት ቤትም ጭምር ነው፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታ ሆይ በዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው ማለቱ
1. የኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት በሚታመንበት፣ ዋልድ ዋሕድ በምትለው ሃይማኖት መኖር ለእኛ መልካም ነው፡፡
2. መድኃኔዓለም ከቅዱሳን ወዳጆቹ ጋር በምትገኝበት አንተ እያበላኸን እየፈወስከን፣ ሙሴ ደመና እየጋረደ መና እያወረደ ባሕር እየከፈለ፣ ኤልያስ ሰማይ እየለጐመ እሳት እያዘነመ ዝናም እያቆመ በዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው፡፡
3. በልበ ሐዋርያት ያደረ ሰይጣን ድል በተደረገበት በታቦር ተራራ ምሳሌ አንድም በወንጌል ሕይወት፣ አንድም በቤተ ክርስቲያን መኖር ለእኛ መልካም ነው፡፡

ፈጣሪያችን እግዚአብሔር እስከመጨረሻዋ ሕቅታ (እስትንፋስ) በታቦር ተራራ በተመሰለች ቤተክርስቲያን በሃይማኖታችን ጸንተን የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች የስሙ ቀዳሾች እንድንሆን የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፡፡

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 የሰኞ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​​​#ቡሄ

ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡

#ጅራፍ

በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡

የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡

የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን #በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል፡፡

#ችቦ

ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡

የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዘዞ ችቦ በ13 ምሽት ይበራል ፣ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና ፡፡

#ሙልሙል

በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም፡፡

ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ….” ይላሉ፡፡

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡

ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡

አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡

አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው፡፡ ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል።

ከዚም ጋር ተያይዞ ሰንበት ት/ት ቤታችን ለበረካታ ዓመታት ሲወርድ የመጣውን የዝማሬ ሥርዓት ለአጥብያው ምእምን በየቤቱ በመሄድ የብሄን ዝማሬ ከነሥርዓቱ በመዘመር አገልግሎት ይሰጣል ፤የደብር ታቦርን በዓል በተመለከትም የወረቀት ጽሑፎችን ይበትናል በዝማሬ መኃል ያድላል፡፡

ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው፡፡ በተለይ ወጣቱ ክፍል ይህንን አውቀን ተረድተን ለቀሪው ትውልድ ማስተላለፋ እንችል ዘንድ ከክፉ ጠላት ከሰይጣን ፈተና፣ በሽታ ከመሳሰሉት ችግሮች ለመዳን ወደ ተራራዋ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመሸሽ ከክፉ ነገሮች ሁሉ ማምለጥ ይቻላል፡፡

በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር የሚጠለሉ ሁሉ ዕድሜያቸው ይረዝማል፡፡ አስተዋዮችም ይሆናሉ ሁሉን ማየትና የሚጠቅማቸውን መምረጥ ይችላሉ በሥነ-ምግባር የታነፁ አገርንና ወገንን የሚጠቅሙ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በመጠጋት ከክፉ ሁሉ የሚያመልጡ ይሆናሉ ለዚህም የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#በስመ_ዚአከ

በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ ዮም /2/
ታቦር ወአርሞንዔም /2/

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ሃሌ_ሉያ

ሃሌ ሉያ አንተ ሰው ሆይ
ቡሄ መድረሱን ሰምተሀል ወይ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ቡሄ_በሉ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 የቅዳሜ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሰላም አርጊው ማርያም

ሰላም አርጊው ማርያም ስጭን የእጅሽን(፪)
አንድ መንጋ ሆነን በዛ ቋንቋችን
ናፍቀናል ልጆችሽ ፍቅር አንድነትን

በስንዴው መሃል እንክርዳዱን
ጠላት ዘራና ክፍፍሉን
የፍቅር ቋንቋ ቀዘቀዘ
አንድነታችን ደበዘዘ
እንወድሻለን ማርያም
አዝ
ያስጎነበሰን ሸክም ይቅለል
በልጅሽ ምህረት ቀና እንበል
ሰላም እንዲሰንፍ በምሕረቱ
ንጉሡን ማልጅው ንግስቲቱ
እንወድሻለን ማርያም
አዝ
የሽንገላ ቃል ከኛ ይውጣ
ያ ክፉ ዘመን እንዳይመጣ
በመለያየት ተመስርቶ
የፀና መንግስት የለም ከቶ
እንወድሻለን ማርያም
አዝ
በረከት አዟል አምላካችን
ህብረት ባለበት መኖሪያችን
ክፍፍል ይቅር አሳስቢልን
በቃል ኪዳንሽ አስጠልይን
እንወድሻለን ማርያም
አዝ
ክፋትን ተክለን በልባችን
መልክ ብቻ ነው አምልኳችን
ወድቀን እንዳንቀር እንዳንጠፋ
ፍቅርን ሳይብን የአዳም ተስፋ
እንወድሻለን ማርያም

ሊቀ_መዘምራን
ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ተአብዮ ነፍስየ

ተአብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር (3)
ሰአሊለነ ማርያም (2)
ኀበወልድኪ ኄር መድኃኔዓለም

የአብ ሙሽራ ነሽ የወልድም እናቱ
ለመንፈስ ቅዱስ ነሽ ጽራሃዊቱ
በፊትሽ ሰገዱ ቅዱሳን መላእክት

ለምኝልን ማርያም (2)
ከቸሩ ልጅሽ ከመድኃኔዓለም

ከዋክብት ብርሃናት ሳይታይ ደመና
ታስበሽ ኖረሻል በአምላክ ህሊና
ገብርኤል ነገረሽ የክብርሽን ዜና

ለምኝልን ማርያም (2)
ከቸሩ ልጅሽ ከመድኃኔዓለም

የወርቅ ታቦት ነሽ በሰማይ ያለሽ
የፅድቅ ንግስት ነሽ የተመሰገንሽ
በእናትነትሽ ተመካ ልብሽ

ለምኝልን ማርያም (2)
ከቸሩ ልጅሽ ከመድኃኔዓለም

የአለሙን ጌታ በእቅፍሽ አየነው
በመሀፀንሽ አድሮ ቃል ስጋ የሆነው
እግዚአብሔር ስላንቺ ምስጋናው ብዙ ነው

ለምኝልን ማርያም (2)
ከቸሩ ልጅሽ ከመድኃኔዓለም

የዳዊት ልጅ ማርያም ትምክህታችን
የአማኑኤል እናት መሰብሰቢያችን
የእግዚአብሔር ከተማ መማፀኛችን

ለምኝልን ማርያም (2)
ከቸሩ ልጅሽ ከመድኃኔዓለም

ድንግል በክሊሄም በነፍስም በስጋ
ጎዶሎ ይምላል አንቺን የተጠጋ
ክርስቶስ ወልደሽ ክሳችን ተዘጋ

ለምኝልን ማርያም (2)
ከቸሩ ልጅሽ ከመድኃኔዓለም

በፊትሽ ልማፀን ቆምኩኝ ከደጅሽ
ልመናዬ ሁሉ ይግባ ከጆሮሽ
ለሚጠራሽማ ማርያም ቅርብ ነሽ

ለምኝልን ማርያም (2)
ከቸሩ ልጅሽ ከመድሐኒአለም
ሰአሊለነ ማርያም (2)
ሀበወልድክሂር መድኃኔዓለም

ዘማሪ ገ/ዮሐነስ ገ/ጻድቅ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​ነሐሴ 16/12/2016 ዓ.ም
ፍልሰተ ሥጋሃ ለእግዝእትነ

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።

ዲያቆን፦ ሮሜ 8÷31-ፍ.ም
ንፍቅ ዲያቆን፦ ዮሐ 2÷1-7
ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 1÷12-15

ምስባክ ፦ መዝ 45፥4-6
ቀደሰ ማኅድሮ ልዑል
እግዚአብሔር ውስተ ማዕከላ ኢትትሀወክ
ወይረድኣ እግዚያብሔር ፍጹመ

ትርጉም
ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ
እግዚያብሔር በመካከሏ ነው አትናወጥም
እግዚያብሔርም ፈጥኖ ይረዳታል

ወንጌል ፦ ማቴ 16÷13-20
ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ(የጌታ ቅዳሴ)

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ሥርዓተ_ማኅሌት_ዘነሐሴ_ኪዳነ_ምሕረት

፩/ ነግሥ ( ለኲልያቲክሙ )

ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤
ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤
እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤
ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኀኒት መስቀል፡፡

ዚቅ፦

ወታስተሥርዪ ኃጢአተ ሕዝብኪ ተበውሐ ለኪ ፨ እም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፨ ከመ ትኵኒ ተንከተመ ለዉሉደ ሰብእ፨ ለሕይወት ዘለዓለም ፨ ለኪ ይደሉ ከመ ትኵኒ መድኀኒቶሙ ለመሐይምናን ሕዝብኪ ፨ ኦ መድኀኒተ ኵሉ ዓለም ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

፪/ ነግሥ ( እምጌቴሴማኒ ፈለሰት )

እምጌቴሴማኒ ፈለሰት ኀበ ዘሉዓሌ መካን፤
ውስተ ቤተ መቅደስ ረባቢ ዘመሳክዊሁ ብርሃን፤
አንቀጸ አድኅኖ ማርያም ጽላተ ኪዳን፤
ኵሉ ይብልዋ በአኅብሮ ዘበዕብራይስጢ ልሳን፤
ዕፀ ጳጦስ ይእቲ እንተ በአማን ቅድስተ ቅዱሳን፤
እመቅድሀ ከርሣ ተቀድሐ አስራባተ ወይን፤
ወበውስቴታ ተሠርዓ ቊርባን፡፡

ዚቅ፦

ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን መዝገቡ ለቃል ፨ ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን አንቀጸ ብርሃን፨ ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን ጽጌ ደንጐላት ፨ ሐረገ ወይን ዘእምነገደ ይሁዳ፨ እንተ ሠረፀት ለሕይወት፡፡

፫/ ለፍልሰተ ሥጋኪ ( መልክአ ኪዳነ ምሕረት )

ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ኀበ ሕንጻ ሕይወት ተሐደሰ፤
እምቅድመ ዝኒ ኀቤሁ ሥጋ ወልድኪ ፈለሰ፤
ቤዛዊተ ዓለም ማርያም አስተበቊዓኪ አንሰ፤
ትቤዝዊ በኪዳንኪ ዘዚአየ ነፍሰ፤
እስመ በሥራይኪ ለቊስልየ ቀባዕክኒ ፈውሰ፡፡

ዚቅ፦

ደብተራ ፍጽምት ዘጳውሊ፨ ወማኅደሩ በጽድቅ ዘገብራ ከሃሊ፨
ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ ፨ በመሰንቆሁ እንዘ የኃሊ፨ ዳዊት አቡሃ ዘወልዳ ወዓሊ።

ወረብ፦

ደብተራ ፍጽምት ዘጳውሊ ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ፤
በመሰንቆሁ እንዘ የሐሊ ዳዊት አቡሃ ዘወልዳ
ወዓሊ።

፬/ ለዝክረ ስምኪ ( መልክአ ማርያም )

ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፤
እምነ ከልበኒ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ
ማርያም ድንግል ለባሲተ ዐቢይ ትእዛዝ፤
ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤
ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ፡፡

ዚቅ፦

ሰላም ለኪ ማርያም እመ አምላክ፨ ወልድኪ ይጼውዓኪ፨
ውስተ ሕይወት ወመንግሥተ ክብር፡፡

ወረብ፦

ሰላም ለኪ ማርያም እመ አምላክ ማኅደረ መለኮት፤

ወልድኪ ወልድኪ ይጼውዓኪ ውስተ ሕይወት ወምንግሥተ ክብር።

፭/ ለእስትንፋስኪ ( መልክአ ማርያም )

ሰላም እስትንፋስኪ ዘመዐዛሁ ሕይወት፤
ከመ መዐዛ ዕፅ ኅሩይ ዘውስተ ገነት፤
ማርያም ድንግል ቤተ ቅድሳት፥
ጽንሕኒ ውስተ ሠናይ ወሰውርኒ እሞት፤
በአክናፍኪ ርግብየ ኅሪት፡፡

ዚቅ፦
ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ፨ መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል፨ ወኵሉ ነገራ በሰላም፡፡

ወረብ፦

ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ ፤
መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል መዓዛ አፉሃ ታንሶሱ፡፡

፮/ ለፍልሰተ ሥጋኪ ( መልክአ ፍልሰታ )

ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ዘኢይቀብል ሞገሱ፤
ወዘኢይነጽፍ ባሕርየ ተውዳሱ፤
ማርያም ታዕካ ለእግዚአብሔር ጽርሐ መቅደሱ፤
ተበሃሉ በሰማያት እለ ኪያኪ አፍለሱ፤
ማርያምሰ እንተ በምድር ታንሶሱ ፡፡

ዚቅ፦

ማርያም ጽርሕ ንጽሕት ማኅደረ መለኮት ፨እኅቶሙ ለመላእክት ሰመያ ሰማያዊት ፨ እንተ በምድር ታንሶሱ፡፡

ወረብ፦

ማርያም ጽርሕ ንጽሕት ፤
ማኅደረ መለኮት ጽርሕ ንጽሕት።

+++++ አንገርጋሪ +++++

ትርሢተ ወልድ መለኮት ወፍቅር ኀደረ ላዕሌሃ፤
ይቤላ ርግብየ ወይቤላ ሠናይትየ፥
ፀቃውዕ ይውኅዝ እምከናፍሪሃ ፡፡

ወረብ ዘአመላለስ፦

ትርሢተ ወልድ መለኮት ወፍቅር ኀደረ ላዕሌሃ፤

ይቤላ ርግብየ ወይቤላ ወይቤላ ሠዓለም፡፡

+++++ ዘሰንበት +++++

የማነ ብርሃን ኀደረ ኀበ ማርያም ድንግል፨ጥዕምት በቃላ ወሠናይት በምግባራ፨ እሞሙ ለሰማዕት ፨ ወእኅቶሙ ለመላእክት ፨ እንተ ተሰምየት ሰንበተ ክርስቲያን ተስፋ ቅቡፃን ፨ መድኃኒተ ኮነት ለኵሉ ዓለም፡፡

አመላለስ፦

እንተ ተሰምየት ሰንበተ ክርስቲያን ተስፋ ቅቡፃን ፤
መድኃኒተ ኮነት ለኲሉ ዓለም።

+++++ መዝሙር ++++++

ሃሌ በ፰ እኅትነ ይብልዋ ወይኬልልዋ፨ ነያ ሐዳስዩ ጣዕዋ፨
ጸቃውዕ ይውኅዝ እምከናፍሪሃ ፨ ከመ ቅርፍተ ሮማን መላትሒሃ ፨ ልዑል ሠምራ ዳዊት ዘመራ በቤተ መቅደስ ተወክፍዋ።

መልካም በዓል

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች?
ክፍል 3


ሌሎች በወር አበባ ጊዜ አይጾምም ይላሉ፣ ከየት እንዳገኙት ባይገባኝም ይህች በወር አበባ አመካኝቶ፣ አንኩቶ ለመብላት ይመስለኛል፡፡ በወር አበባ ጊዜ አንዳንድ እህቶቻችን ከፍተኛ የሕመምና የስቃይ ስሜት የሚሰማቸው ብሎም እስከ ሕክምና የሚያደርሳቸው ከሆነ ምናልባት መድሃኒት ሊወስዱ ስለሚችሉ እነርሱን አይመለከትም፡፡

እኛ የምንረክሰው በወር አበባ ጊዜ ሳይሆን ኃጢአት በመሥራት ሥጋችንንም ነፍሳችንንም ስናደማ ነው፡፡ ያኔ በሁሉም እንረክሳለን፡፡ ጸሎታችን በእግዚአብሔር እና በእመቤታችን ፊት ስለማረጉ መመዘኛው የወር አበባ ሳይሆን የልባችን ንጽህና፣ መልካምነታችን፣ ቅንነታችን፣ ታማኝነታችን፣ እምነታችን፣ መታዘዛችን ነው፡፡

በተለይ አዲስ መንፈሳዊ ሕይወት ጀማሪዎች፣ ቤተክርስትያን ሳሚዎችና አስቀዳሾች ፣ ገዳማት ተመላላሾች ስንሆን የቤተክርስትያን ሥርዓት ያወቅን፣ ያስጠበቅን እየመሰለን በወር አበባ ጊዜ እንደማይጸለይ እንደማስተማር እያደረገን ለመንፈሳዊ እህቶቻችን ማሰናከያ በመሆን የጸሎት ሥርዓት እናፋልሳለን፡፡ በዚህም የሰይጣን ስፓንሰር እንሆናለን፡፡

ተወዳጆች ሆይ ለአብነት በአዲስ አበባ ያሉትን እንጦጦ ማርያምና አራዳ ጊዮርጊስን ብንመለከት ሁለት ግቢ አላቸው፡፡ ለምን እንደዚያ የተሠሩ ይመስላችኋል? ባለ ሁለት ግቢ የሆነበት ምክንያት ሴተችና ወንዶች ንፁህ በማይሆኑበት ፣ የሥጋ ድቀት በሚያገኛቸው ጊዜና በጋብቻ ተወስነው ሕጋዊ ሩካቤ ሲገጽሙ በእነዚህ ምክንያት ከቤተ-ክርስትያን ደጅ እንዳይርቁና ኪዳን፣ ቅዳሴ ጸሎት እንዲያደርሱበት ነው፡፡ ይህም የሚከናወነው በመጀመሪያው (በአንደኛው) ግቢ በመሆን ነው፡፡

አንደኛው ጊቢ የመንጻት ጊዜያቸው እስከሚያልፍ ድረስ እንዲጸልዮበትና እንዲያስቀድሱበት፣ እንዲማሩባቸው ከዚያም ግዳጃቸውን ሰጨርሱ ወደ ሁለተኛው ወይም ወደ ቤተክርስትያኑ ግቢ መግባት እንዲችሉ እንጂ ለሌላ የተሠሩ አይደሉም፡፡ አባቶቻችን ለተፈጥሮ ግዳጅ እንደዚህ ተጨንቀው ምዕመናን ከቤተክርስትያን ሳይርቁ እንዲገለግሉ ሥርዓት ሲሠሩ እኛ አዋቂዎች (አዋኪዎች) ትልቅ እንቅፋት እንሆናለን፡፡

በቀጣይ 👉 በወር አበባ ግዜ የሚከለከል ጸሎትስ አለ?

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች?

ጸሎት ከፈጣሪ የምንገናኝበት መንገድ ስለሆነ እግዚአብሔር ጊዜን እየጠበቀ በዚህ ጊዜ እሰማችኋለሁ በዚህን ጊዜ አልሰማችሁም አይልም፡፡ በወር አበባ ጊዜ አይጸልይም ማለት የቤተ-ክርስትያን አስተምህሮ ሳይሆን የሰነፉ ሰይጣን የተንኮል እና የእንቅፋት ስብከት ነው፡፡

የሰይጣንን እንኳን ጸሎት ትተን ቀርቶ እየጸለይን ፈተናችንን እኛና እግዚአብሔር ነው የምናውቀው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በዘመኑ እንደ እኛ ግራ ለተጋቡት የተሰሎንቄ ምእመናን "ሳታቋርጡ ፀልዩ" በማለት ፀሎት በየትኛውም ሁኔታ እና አጋጣሚ ማቋረጥ እንደሌለባቸው ፅፎላቸዋል። (1ኛ ተሰሎ 5÷18)

ወዳጆቼ ፀሎትን የለመደች ሴት በወር አበባዋ ምክንያት ለሰባት ቀን ፀሎትዋን ብታቋርጥ ስንፍናን ትለምዳለች፡ትዘናጋለች አጋንንቱም በዚህ አጋጣሚ ፈተናዋን ያበዛል።

ሴት በወር አበባዋ ጊዜ እስከ መንጻቷ ቤተክርስትያን ነው መግባት የማትችለው እንጂ፣ ጸሎት ማቋረጥ የለባትም፡፡ ጊዜን ተብቆ አለመጸለይ ለሰይጣን በር መክፈት ነውና ትንሿን ጸሎታችንን ማቋረጥ የለብንም፡፡

እኛ በወር አበበ ጊዜ ንፁህ አይደለንም ብለን ሥጋዊ ምግብ እንደማንተው ሁሉ ጸሎት የነፍስ ምግብ ነውና ነፍሳችን ለ7 /ሰባት/ ቀን ከውዳሴ ማርያም ፣ ከሰኔ ጎለጎታ ፣ከአርጋኖን፣ከሰይፈ ሥላሴ፣ከሰይፈ መለኮት እና ከተለያዩ የጸሎት ማዕድ እየከለከልን ሕያዊት ነፍሳችንን ማስራብ የለብንም፡፡ ይልቁንም ዘወትር በመጸለይ ነፍሳችንን መመገብ ይገባናል፡፡

ይቀጥላል
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው?

1ኛ/ ጸሎት

ሕልመ ሌሊት የሚያስቸግረን ከሆነ ማታ የእለት ውዳሴ ማርያም ከበረታን ከመዝሙር ዘጠና ጋር ጸልየን መተኛት፡፡ እመቤታችንን የዝንየት አጋንንቱን እንድታስርልን እንድታርቅልን መማጸን፡፡ ያኔ በሌሊት በተቃራኒ ጾታ እየተመሰለ የሚፈትነን የሕልመ ሌሊት አጋንንት (ዝንየት) ሲርቀን በሰላም መኖር እንጀምራለን፡፡

ወዳጆቼ ብርቱ ጸሎት እንኳን ከሕልመ ሌሊት ከገሃነመ እሳት ይታደገናልና በርትተን እንጸልይ፡፡ ማታ ማታ ውዳሴ ማርያም፣ አርጋኖን የቻልነውን ያህል ብንጸልይ የእመቤታችን ጥበቃ እናገኛለን፡፡

2ኛ/ ሕልመ ሌሊት እንደመታን ተመልሶ አለመተኛት

ብዙዎቻችን ሕልመ ሌሊት ሲመታን ተስፋ በመቁረጥ ተመልሰን በዛው እንተኛለን፡፡ ይሄ ድርጊታችን አጋንንቱን ከማስደሰቱም በላይ ለነገ የልብ ልብ ይሰጠዋል፡፡ እኛ በሕልመ ሌሊት ምክንያት ጸሎቱን ትተን ‹‹ጠዋት ታጥቤ እጸልያለሁ›› በሚል ስንፍና ከተኛን አጋንንቱ እየደጋገመ እየመታን ሕልመ ሌሊቱን ጸሎት ለማስታጎያ ያደርግብናል፡፡

ስለዚህ ሕልመ ሌሊት እንደ መታን ፈጥነን በመነሳት ከቻልን ሰውነታችንን መታጠብ ካልቻልን አንቀጸ ሥጋችንን በመታጣብ ጸሎታችንን መጸለይ፡፡ ወዳጆቼ ሕልመ ሌሊት እንደ መታን ተነስተን ታጥበን በመጸለያችን የነገ የአጋንንቱን ውጊያ በር እንዘጋበታለን፡፡ አጋንንቱ በሕልመ ሌሊት የሚመታን አንድም እንዳንጸልይ ስለሆነ እኛ ደግሞ በተቃራኒ ከጸለይን አጋንንቱ ይርቀናል፡፡

3ኛ/ ማታ ውኃ አብዝቶ አለመጠጣት

ሕልመ ሌሊትን ለማስታገስ አንዱ መፍትሔ ማታ ውኃ አብዝቶ አለመጠጣት ነው፡፡ ይህንን ከመጻሕፍተ መነኮሳት ሁለተኛው የሆነው ፊልክስዮስ ‹‹አካልን የሚያደርቅ፤ ከሕልመ ሌሊት፣ ከዘር መፍሰስ የሚከለክል፤ በመዓልት ኃልዮ ኃጢአትን የሚያጠፋ እንደ ውኃ ጥም የለም፡፡

ምንም ቢጾሙ፣ ምንም ከምግብ ቢያከፍሉ አብዝቶ ውኃ ከጠጣ አይጠቅምም፡፡ ምነዋ ትለኝ እንደ ሆነ ሆዱ ቂብ ትላለች›› /ፊልክ.ክፍል 3 ተስእ 38/

ውኃ ማታ አብዝቶ መጠጣት ዘር በቀላሉ እንዲፈስ ያደርጋል፡፡ አባቶቻችን በሕጋዊ ጋብቻ ያሉትን ባለ ትዳሮች ‹‹ሩካቤ ሥጋ ከመፈጸማቸው ከ30 ደቂቃ በፊት ንጹህ ውኃ ጠጡ›› የሚሉት በግንኙነት ጊዜ በሰውነት በቂ ውኃ ካላ የወንድ ዘር በቀላሉ ወደ ሴቷ ማህፀን ስለሚደርስ ነው፡፡

ውኃ ለወንድ ዘር ተሸካሚ ነው፡፡ ውኃው ነው የወንድን ዘር እንደ መርከብ በመሸከም ከማህፀን የሚያደርሰው፡፡ ስለዚህ ማታ ማታ ውኃ አብዝቶ አለመጠጣት ትኩስ ነገርም አለማዘውተር ይመረጣል፡፡

4ኛ መስገድ

ሕልመ ሌሊት አዘውትሮ የሚፈታተነን ከሆነ ስግድት ላይ መበርታት፡፡ በተለይ ማታ ከመተኛታችን በፊት እራሳችንን በስግደት ቀጥቅጠን መተኛት፡፡ በስግደት የደከመ ሰውነት ላይ አጋንንት የበላይነት አይኖረውም፡፡ ስግደት ከእነዚህ ዓይነት አጋንንታዊ ጾር የምንርቅበት እና መፍትሔ የምናገኝበት ስለሆነ መቼም ስግደት ባይሆንልንም መስገድ መልመድ ይገባናል፡፡

5ኛ/ መጠንቀቅ እና ማማከር

ተወዳጆች ሆይ እራሳችንን ለፍትወት እና ለዝሙት ከሚያጋልጡን ነገሮች የምንርቅ ከሆነ አጋንንቱ በእኛው ስህተት ለሕልመ ሌሊት አይዳርገንም፡፡ እንዲሁም ፈተናው ሲደጋገምብን ሲበረታብን አባቶችን በግል በመፍትሔው ዙርያ ማመከርና የሚሉንን መስማት እና መተግበር፡፡

ወዳጆቼ አጋንንት ወንድ ሴት ሳይል በሕልመ ሌሊት መፈተኑን አይተውም፡፡ ስለዚህ እኛ በጾም፣ በጸሎት በስግደት መዋጋቱን ልንተው አይገባም፡፡

‹‹ከእመቤታችን በጸሎት መልስ የምናገኝባቸው ጠቃሚ መንገዶች›› ከሚለው መጽሐፌ ተወስዶ ብዙ አዳዲስ ሐሳቦች ተጨምሮበት ተጻፈ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​ነሐሴ 14/12/2016 ዓ.ም

✝ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።

ዲያቆን፦ 1 ቆሮ 1÷10-19
ንፍቅ ዲያቆን፦ ያዕ 1÷12-22
ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 1÷30-34

ምስባክ ፦ መዝ 43፥4-6
ዘአዘዝከ መድኀኒቶ ለያዕቆብ
ብከ ንወግኦሙ ለኩሎሙ ፀርነ
ወበስምከ ናኀስሮሙ ለእለ ቆሙ ላዕሌነ

ትርጉም
ለያዕቆብ መድኀኒትን እዘዝ
ባንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን
በስምክም በላያችን የቆሙትን እናዋርዳቸዋለን

ወንጌል ፦ ማቴ 17÷14-24
ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ምሥጢረ ደብረታቦር

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

እንኳን ለደብረታቦር በዓል በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ

"ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ ፤ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ"

ቅዱስ ጴጥሮስ

ታቦር ተራራ የዛሬ ገጽታው ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ቅዱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤሌያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን። ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ከኤልያስ እንሥራ አለ።

እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር። ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና። ተነሡ አትፍሩም አላቸው። ዓይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም። የማቴዎስ ወንጌል 17፡1-8

በቂሳርያ ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ ለሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል ብሎ ጠይቋቸው አንዳንዶች ከነቢያት አንዱ ነህ ይሉሃል፣ አንዳንዶች ሙሴ ነህ ይሉሃል፣ ሌሎች ደግሞ ኤልያስ ነህ ይሉሃል እያሉ መለሱለት ጌታችንም መልሶ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ብሎ ሲጠይቃቸው የሐዋርያት አፈጉባዔ ሊቀ ሐዋርያት ቅ/ጴጥሮስ ‹አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ ነህ› ብሎ በመመስከሩ ጌታም ‹የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ በሰማይ ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ…› ተብሏል፡፡

ይህ በሆነ በሰባተኛው ቀን ሦስቱን ደቀ መዛሙርት ጴጥሮስ፣ ዮሐንስና ያዕቆብን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ወጣ፡፡ በዚያም እንደ ዮርዳኖስ ወንዝ መድኃኔዓለም ክብረ መንግስቱን ፤ ብርሃነ መለኮቱን ገልጧል ፡፡ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ የሆነው በዓለ ደብረታቦር የዚህ ታሪክ መታሰቢያ ነው ፡፡

ታቦር ተራራ ከገሊላ ባሕር በስተምዕራብ 17 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ፤ ከናዝሬት ከተማ በስተምስራቅ ፤ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምዕራብ አቅጣጫ ሲገኝ ከባሕር ጠለል በላይ 572 ሜትር ነው ፡፡ከላይ ወደታች ሲታይ ታቦር ተራራ ቅርጹ የተገለበጠ የሻይ ስኒ ይመስላል ይላሉ ፡፡
እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።

ምሥጢረ መንግሥቱን ለምን በታቦር ተራራ ገለጸው ?

መድኃኔዓለም ሌሎች ተራሮች እያሉ ክብሩን ለመግለጥ ስለምን ደብረ ታቦርን መረጠ ቢሉ ትንቢቱንና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡

ትንቢት
“ ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ ወይሰብሑ በስምከ ”

ታቦርና አርሞንኤም በስምህ አምነው በተደረገላቸው ነገር ደስ ይላቸዋል፣ ስምህን ያመሰግናሉ፣ ለስምህም ምስጋና ያቀርባሉ፡፡ “ መዝ 88፡12

ምሳሌ
ባርቅ ሲሳራን ድል አድርጎበታል መሳፍንት 4፡6 ይኸውም ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡ ‹… የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደገና ክፉ ሥራ ሠሩ፡፡ እግዚአብሔርም በአሶር በነገሠው በከነዓን ንጉሥ በኢያቡስ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው የሠራዊቱም አለቃ በአሕዛብ አሪሶት የተመረጠው ሲሣራ ነበር… ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች ነበሩትና የእስራኤልንም ልጆች ሃያ ዓመት ያስጨንቃቸው ነበር› /መሳ 4.1-3/

ሁሌም ቢሆን የሰውን በደል ዐይቶ እንደወጣችሁ ግቡት፣ እንደገባችኋት ውጧት የማይልና ‹… ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል› የተባለለት እግዚአብሔር ከዚህ ቀንበር የሚላቀቁበትን መላ ራሱ አመለከታቸው፡፡ /1ቆሮ. 10-13/፡፡

እስራኤላውያን ወደ ፈጣሪያቸው በጮኹ ጊዜ የለፊዶት ሚስት የሆነችውንና እስራኤልን በነቢይነትና ዳኝነት ታገለግል የነበረችው ነቢይቱን ዲቦራን ተጠቅሞ የማሸነፊያ መላውን አመለከታቸው ነቢይቱ ዲቦራ ትንቢት ከመናገር አልፋ የእስራኤልን ንጉሥ ባርቅ ከእኔ ጋር ወደ ጦርነቱ ውጪ ብሎ ባስጨነቃት ጊዜ በጦር አዝማችነትም ተሳተፈች፡፡

እግዚአብሔር በነቢይቱ በዲቦራ በኩል ለእስራኤል ንጉሥ ‹ሔደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጡ…› ብሎ አዞት ነበርና ንጉሡ ዐሥር ሺሕ ብረት ለበስ ያልሆነ እግረኛ ሠራዊት ይዞ ደብረ ታቦርን ተማምኖ በተራራው ላይ መሸገ ጦርነቱ ሳይጀመር አለቀ፡፡ ምክንያቱም ‹እግዚአብሔርም ሲሣራን ሰረገሎቹንም ሁሉ ሠራዊቱንም ሁሉ ከባርቅ ፊት በሰይፍ ስለት አስደነገጣቸው፡፡ ሲሣራም ከሰረገላው ወርዶ በእግሩ ሸሸ…› /መሳ. 4.15/

እስራኤል በእግዚአብሔር አጋዥነት በታቦር ተራራ ላይ የሃያ ዓመት የግፍና የሰቀቀን አገዛዝ ቀንበራቸውን ከትከሻቸው አሽቀንጥረው በምትኩ የድል ካባን ደረቡ ‹… በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ የባዕድ ጭፍሮችንም አባረሩ› ተብሎም ጀግንነታቸው ተጻፈላቸው፡፡ የታቦር ተራራ ያኔ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ባለውለታቸው ነበር፡፡ /ዕብ. 11.32-34/

ጌታም በልበ ሐዋርያት ያለ ሰይጣንን ድል ያደርግበታልና ማለትም በልባቸው ጥርጥርን እና ፍቅረ ሢመትን( የሥልጣን ፍቅር) ያሳደረ ዲያብሎስን ድል ነስቶላቸዋል ፡፡ከዚህም በመነሳት ነው በዓለ ደብረታቦር የደቀመዛሙርት ተማሪዎች በዓል ነው የሚባለው ፡፡ ለምን 3ቱን ሐዋርያት ( ጴጥሮስ ፤ዮሐንስ እና ያዕቆብን) ብቻ ይዞ ወደ ተራራ ወጣ፡-

ለፍቅሩ ስለሚሳሱ ነው፡፡ ይህም በዕብራይስጡ ኬፋ ፤ በግሪኩ ጴጥሮስ ፤በግዕዙ ኰኲሕ( ዐለት) የተባለው የዮና ልጅ ስምዖን ጌታ እሞታለሁ እያለ ጌታችን ሲናገር አይሁንብህ በማለቱ ከባሕርይ አባቱ ከአብ እርሱን ስሙት የሚል መለኮታዊ ድምጽ ሰምቷል፡፡ዮሐንስና ያዕቆብ ጌታን ምድራዊ መሲህ አድርጎ በማሰብ ቀኝ ጌትነትን እና ግራ ጌትነትን በእናታቸው በኩል የማይገባ ልመና አቀረቡ ዮሐንስና ያዕቆብ እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ? ሲባሉ አዎ ብለው መለሱ በዚህም ከባሕርይ አባቱ እርሱን ስሙት የሚል ድምጽ ሰሙ፡፡

በይሁዳ ምክንያት ነው ኢሳ 26.13 ‹ኃጥእ ሰው የእግዚአብሔርን ክብር እንዳያይ ያርቁታል› እንዲል እርሱን ጥሎ አስራ አንዱን ወደ ተራራ ይዞ ቢወጣ ከምሥጢር ቢለየኝ በሞቱ ገባሁበት እንዳይል፡፡ ያም ባይሆን ስምንቱ ደቀ መዛሙርት ለምን ይከለከላሉ ቢሉ አልተከለከሉም በርዕሰ ደብር (በተራራው አናት) ለሦስቱ ደቀ መዛሙርት የተገለጸው ምስጢር በእግረ ደብር (በተራራው ግርጌ) ለነበሩት ስምንቱ ደቀ መዛሙርት ተገልጦላቸዋል፡፡ ይህም በደብረሲና ለሰባው ሊቃናት የተገለጠ ምሥጢር በከተማ ለነበሩት ለኤልዳድና ሙዳድ እንደተገለጠ ማለት ነው፡፡ ዘኁልቊ 11፡26

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​ነሐሴ 13/12/2016 ዓ.ም
ደብረ ታቦር
✝ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።

ዲያቆን፦ ዕብ 11÷23-30
ንፍቅ ዲያቆን፦ 2 ጴጥ 1÷15-ፍ.ም
ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 7÷44-51

ምስባክ ፦ መዝ 88፥12-14
ታቦር ወአርሞንዔም በስመ ዚአከ ይትፌስሁ ወይሴብሑ ለስምከ
መዝራዕትከ ምስለ ኀይል

ትርጉም
ታቦር እና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል
ስምህንም ይመሰግናሉ
ክንድክ ከኃይልክ ጋር ነው

ወንጌል ፦ ሉቃ 9÷28-38
ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#አማን_በአማን

አማን በአማን /2/ ተሰብሐ
አማን በአማን /2/ ተሰብሐ
በደብረ ታቦር /2/

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#አምላካችን_ናና

አምላካችን ናና በአምደ ደመና
አማኑኤል ናና ብርሀን ነህ እና

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ሆያ_ሆዬ
ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ

እንኳን ለደብረታቦር በዓል በሰላም
አደረሳችሁ አደረሰን

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ቡሄ_በሉ

ቡሄ በሉ (2) ልጆች ሁሉ የኛማ ጌታ
የዓለም ፈጣሪ የሰላም አምላክ
ትሁት መሀሪ በደብረ ታቦር የተገለጠው
ፊቱ እንደ ፀሐይ በርቶ የታየው
ልብሱ እንደብርሃን ያንፀባረቀው

ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን(2)

ያዕቆብ ዮሐንስ እንዲሁም ጴጥሮስ
አምላክን አዩት ሙሴ ኤልያስ
አባቱም አለ ልጄን ስሙት
ቃሌ ነውና የወለድኩት

ታቦር አርሞንኤም ብርሃን ታየባቸው
ከቅዱስ ተራራ ስምህ ደስ አላቸው
ሰላም ሰላም የታቦር ተራራ
ብርሀነ መለኮት ባንቺ ላይ አበራ

በተዋህዶ ወልድ የከበረው
የእግዚአብሔር አብ ልጅ
ወልደማርያም ነው
ቡሄ በሉ/2/ የአዳም ልጆች
ብርሃንን ተቀበሉ

አባቴ ቤት አለኝ ለከት
እናቴ ቤት አለኝ ለከት
አጎቴም ቤት አለኝ ለከት
ተከምሯል እንደ ኩበት

የዓመት ልምዳችን ከጥንት የመጣው
ከተከመረው ከመሶቡ ይውጣ
ከደብረ ታቦር ጌታ ሰለመጣ
የተጋገረው ሙልሙሉ ይምጣ

ኢትዮጵያውያን ታሪክ ያላችሁ
ባህላችሁን ያዙ አጥብቃችሁ
ችቦውን አብሩት እንዳባቶቻችሁ
ምስጢር ስላለው ደስ ይበላችሁ

አባቶቻችን ያወረሱን
የቡሄን ትርጉም ያሳወቁን
እንድንጠብቀው ለእኛ የሰጡን
ይህን ነውና ያስረከቡን

ለድንግል ማርያም አሥራት የሆንሽ
ቅዱሳን ጻድቃን የሞሉብሽ
በረከታቸው ያደረብሽ
ሁሌም እንግዶች የሚያርፉብሽ
ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ነሽ

ለሐዋርያት የላከ መንፈስ
ዛሬም ለኢትዮጵያ ጸጋውን ያፍስስ
በበጎ ምግባር እንድንታነጽ
በቅን ልቦና በጥሩ መንፈስ
በረከተ ቡሄ ለሁላችን ይድረስ

ዓመት ዓውዳመት ድገም እና ዓመት ድገም እና
በጋሽዬ ቤ ድገም እና ዓመት ድገም እና
ያውርድ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ወርቅ ይፍሰስበት ድገም እና ዓመት ድገም እና

በእማምዬ ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይግባ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ማርና ወተት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይትረፍረፍ በእውነት ድገም እና ዓመት ድገም እና


እንዲሁ እንዳላችሁ በፍቅር አይለያችሁ
ላመቱ በሰላም በፍቅር ያድርሳችሁ
ክርስቶስ በቀኙ በፍቅር ያቁማችሁ
የመንግስቱ ወራሽ በፍቅር ያድርጋችሁ
እንዲሁ እንዳለን በፍቅር አይለየን
ለዓመቱ በሰላም በፍቅር ያድርሰን
አማኑኤል በቀኙ በፍቅር ያቁመን
የመንግስቱ ወራሽ በፍቅር ያድርገን


የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት
ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት
በሁሉም ቤት(2) ይግባ በረከት(2)

እንቁም በሃይማኖት ፀንተን በትጋት
የአስራት አገር የአበው ቀደምት
የቅዱሳን አባቶች ትውፊት
ይገባልና ልንጠብቅ በእውነት
ባህላችንን የአባቶች ትውፊት (3)

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ኧረ ምን ዘመን ደረስን 😭😭😭

Читать полностью…
Подписаться на канал