ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ሥርዓተ ቅዳሴ

ቅዳሴ ማለት ቀደሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን አመሰገነ፣ ባረከ፣ አከበረ፣ ለየ፣ ለእግዚአብሔር መርጦ ሰጠ ማለት ነው። ሥርዓት ማለት ደግሞ ሠርዐ፡ ሠራ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው። ትርጉሙ ሕግ: ደንብ አሠራር ማለት ነው። በአንድ ላይ አድርገን ስናነበው የምሥጋና ሥርዓት ማለት ነው የሚመሰገነው  ደግሞ እግዚአብሔር ነው።

ቅዳሴ በሥርዓተ ቤተክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት በኅብረት የሚጸለይ የኅብረት ጸሎት ነው፡፡ ከፀሎቶች ሁሉ የላቀ የፀሎት ክፍል ነው፡፡

ቅዳሴ፡-
• በሰማይ የሚገኘውን ሥርዓት በምድር መተግበር ነው።
• ቅዱስ ቁርባን የሚቀርብበት እግዚአብሔርን የምናመልክበት ሥርዓት ነው።
• በደስታ የምናከናውነው እግዚአብሔርን የምናመልክበት ጸሎት ነው።
• ቅዳሴ አባቶች ካህናት እና ምእመናን ያሳተፈ የምሥጋና ሥርዓት ነው። ስለዚህ ዘወትር ለቅዳሴና ለመንፈሳዊ ትምህርት ትኩረት ልትሰጡ ይገባል።

ጳጳሳት፣ ቀሳውስት፣ ዲቆናት በመቀደስ ምእመናን ደግሞ በማስቀደስ  ይሳተፋሉ ከሁሉ በላይ አምላካችን የሚገኝበት እመቤታችን ቅድስት ማርያም የምትገኝበት መላእክት የሚገኙበት ሁሉም ቅዱሳን እንደተሰጣቸው ክብር የሚገኙበት ጸሎት ነው ስለዚህ ስናስቀድስ ብዙ በረከት እናገኝበታለን።

በቅዳሴ ጊዜ 5ቱ መሥዋዕቶች ምን ምን ናቸው?

አምስቱ የስሜት ሕዋሳት በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ያስቀድሳሉ፤ በቅዳሴ ጊዜ 5ቱ ምሥዋዕቶች ተሟልተው ይገኙበታል። እዚህንም 5ቱን መሥዋዕቶች ማንኛውም ክርስተያን ለፈጣሪው የሚያቀርበው ነው፡፡

1. የቁርባን መስዋዕት፡-
በጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት የሚሆነው በቅዳሴው ጸሎት ነው። ሳናስቀድስ አንቆርብምና የቁርባን መስዋዕት የሚፈጸመው በሥርዓተ ቅዳሴ ብቻ ነው፡፡ መስዋዕቱም በቤተልሔም ይዘጋጃል፤ በቤተክርስቲያን ውስጥ በቤተ-መቅደስ ውስጥ ደግሞ ይቀርባል ወይም ይታደላል፡፡ ጌታችን ሲወለደ በቤተልሔም ተወልዶ ቀራንዮ ለዓለም ሁሉ መስዋዕት ሆኗልና ቀራንዮ በተባለች በቤተክርስቲያን ቅዱሱ መስዋዕት ለሕዝብ ይታደላል።

2. የከንፈር መስዋዕት፡-
ካህኑ፣ ዲያቆኑና ሕዝቡ በመቀባበል በአንድነት ምስጋና ለፈጣሪያቸው የሚያቀርቡበት የከንፈራችን ፍሬ የሚሰዋበት የፀሎት ክፍል ፀሎተ ቅዳሴ ነው፡፡

3. የመብራት መስዋዕት፡-
በቅዳሴ ጊዜ የሚበራው ጧፍ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የሚሠጥ የመብራት መስዋዕት ነው፡፡ ምሳሌነቱም የጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው። ይህውም ጌታችን ጨለማ ለሆነ ዓለም ብርሃን ሆኖ ብርሃንን ሊያበራ ወደ ዓለም መቷልና ነው፡፡

4. የዕጣን መስዋዕት፡-
የዕጣን ጸሎት ካህኑ ብቻ የሚያጥነው ሲሆን ይህውም በማዕጠንቱ አማካኝነት ቅዱሱን እጣን በመንበሩ፣ በቅዱሳን ስዕላቱ፣ በሕዝቡ መካከል ያጥናል። ይህውም የሕዝቡን ፀሎት ወደላይ ወደ ሥላሴ መንበር ይዞ ይወጣል።

በሰማይም ያሉ ቅዱሳን መላእክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሥላሴን መንበር እንደሚያጥኑ ሁሉ በምድርም ያለው ካህን የሰማያዊው ምሳሌ ነውና በምድር ያለውን መንበር በማጠን ለእግዚአብሔር የዕጣን መስዋዕት ያቀርባል፡፡

5. የሰውነት መስዋዕትነት፡-
በቅዳሴ ጊዜ አብዛኛውን ሰዓት ሙሉውን ማለት ይቻላል በመቆም የሚፀለይ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በመሐል 2 ጊዜያት ብቻ የስገዱ ትዕዛዝ ሲተላለፍ ሕዝቡ ሁሉ ፊቱን ወደ ፈጣሪው አዞሮ እራሱን አዋርዶ ይሰግዳል። በእግዚአብሔር ፊት መቆምም ሆነ መስገድ ለእግዚአብሔር የሚሰጥ የሰውነት መሥዋዕት ነው፡፡

ይህ የጸሎት ክፍል (ቅዳሴ) በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፦
1. የዝግጅት ክፍል
2. የንባብና የትምህርት ክፍል
3. ፍሬ ቅዳሴ፦ ፍሬ ቅዳሴያት እንደየበዓሉ ይለዋወጣተሉ ብዛታቸውም ፲፬ (14) ናቸው። እነዚህም፡-
3.1. ቅዳሴ ዘሐዋርያት
3.2. ቅዳሴ እግዚእ
3.3. ቅዳሴ ማርያም
3.4. ቅዳሴ ዘዮሐንስ ወልደ ነጓድጓድ
3.5. ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምዕት
3.6. ቅዳሴ ዘአትናቴዎስ
3.7. ቅዳሴ ባስልዮስ
3.8. ቅዳሴ ጎርጎርዮስ
3.9. ጎርጎርዮስ ካልእ
3.10. ቅዳሴ ዘኤጲፋንዮስ
3.11. ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ
3.12. ቅዳሴ ዘቄርሎስ
3.13. ቅዳሴ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ
3.14. ቅዳሴ ዘዲዮስቆሮስ

- የጌታችን በዓል ከሆነ (ቅዳሴ እግዚእ)
-የጌታችን ምጽአት፣ ጳጉሜ እሑድ ቀን ከዋለች ሰንበት (ቅዳሴ አትናቴዎስ)
-የእመቤታችን በዓል ከሆነ ቅዳሴ ማርያም (ጎሳ ልብየ ቃለ ሰናየ)
-የመላእክትና የሐዋርያት በዓል ከሆነ (ቅዳሴ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ)
-ከዘመነ ልደት እስከ ዘመነ ግዝረት (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ካልዕ)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፲፰ /18/


በዚህች ቀን የከበረ ቅዱስ ሮማኖስ በሰማዕትነት አረፈ።

ይህም ቅዱስ የክርስቲያን ወገኖችን መኰንኑ እንዳሳደዳቸው በሰማ ጊዜ ከቀሳውስትና ከዲያቆናት ጋር የክርስቲያን ወገኖችን ሁሉ በአንድነት ሰበሰባቸው ስለ ክርስቶስ ሃይማኖትም መክሮ አጸናቸው።

አስቅልጵያኖስም ይህን ሰምቶ እንዲአመጡት አዘዘ በፊቱም በቆመ ጊዜ በወገን የከበርክ ሮማኖስ አንተ ነህን? አለው ቅዱሱም የወገን ክብር ምን ይጠቅመኛል ክብሬ ግን ክርስቶስ ነው ብሎ መለሰለት። መኰንኑም ሰምቶ እንዲሰቅሉትና ጉንጮቹን ይሰነጣጥቁ ዘንድ አዘዘ።

በዚያንም ጊዜ ሮማኖስ መኰንኑን እንዲህ አለው "እነሆ ስንፍናህን እዘልፍ ዘንድ ፈጣሪዬ አፌን ከፈተ፤እውነት ነገርን ብታውቅ ለእግዚአብሔር እንሰግድ ዘንድ ይገባ እንደሆነ ወይም ለአማልክት እንዲነግረን ሕፃን ልጅ እንዲአመጡ እዘዝ" መኰንኑም ታናሽ ሕፃንን እንዲአመጡ አዘዘ መኰንኑም ሕፃኑን ስግደት ለማን እንዲገባ ዕውነቱን ንገረን አለው። ሕፃኑም በአንዲት ቃል ዓለሙን ሁሉ ለፈጠረ ለሕያው እግዚአብሔር ስግደትና አምልኮ እንዲገባ አታውቅምን አለው።  በዚያንም ጊዜ የቅዱስ ሮማኖስንም ምላሱን ከግንዱ እንዲቆርጡ መኰንኑ አዘዘ።

ያን ጊዜ መኰንኑን ይዘልፍ ዘንድ ለአባ ሮማኖስ ረቂቅ አንደበት ተሰጠው ሲዘልፈውም መኰንኑ ሰምቶ ምላሱ እንዳልተቆረጠ ተጠራጠረ፤ ወታደሩንም ጠርቶ ምላሱን ያልቆረጥክ ለምንድን ነው አለው ወታደሩም የምላሱን ቁራጭ ያመጡ ዘንድ እዘዝ አለው አምጥተውለትም አየ መኰንኑም ወደ ወህኒ ቤት አስገብተው በዚያ አንቀው እንዲገድሉት አዘዘ የምስክርነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ኑ በእግዚአብሔር

ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን /2/
ለታላቁ ክብር ለዚህ ያበቃን
ከሞት ወደ ሕይወት ለአሸጋገረን
ኑ በእግዚአብሔር ኑ በድንግል ደስ ይበለን/2/

አዝ

የሰማዩን መንግሥት እርስቱን ለሰጠን
ከጨለማ አውጥቶ ብርሃንን ላሳየን
ለዚህ ድንቅ ውለታው ምሥጋና ያንሰዋል
በእርሱ ደስ ይበለን ክብር ይገባዋል
አዝ

ከዓለት የፈለቀ ውሃ ጠጥተናል
ሰማያዊ መና አምላክ መግቦናል
ፍቅርህ የበዛልኝ ምን ልክፈልህ ጌታ
ስምህን ላመስግን ከጧት እስከ ማታ
አዝ

በቃዴስ በረሃ ምንም በሌለበት
በኤርትራ ባሕር ወጀብ በበዛበት
ለእርሱ መንገድ አለው ከቶ ምን ተስኖት
ልባችሁ አይፍራ በፍጹም እምኑት
አዝ

በባርነት ሳለን በድቅድቅ ዓለም
ብርሃንን አገኘን በድንግል ማርያም
ያጣነውን ሰላም ዛሬ አገኘን
እጅግ ደስ ይበለን በእመቤታችን
አዝ

የሐና የእያቄም የእምነታቸው ፍሬ
በእግዚአብሔር ፈቃድ ተወለደች ዛሬ
የእያቄም ስእለት የሐና እምነት
ለምኝልን ለእኛ ኪዳነ ምሕረት

ዘማሪት አዜብ ከበደ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በርጠሚዮስ ነኝ

በርጠሚዬስ ነኝ አይነ ስውር ምስኪን
ከሩቅ የሰማሁት የጌታዬ ድምፁን
ከብዙ ሁካታ ጉርምርምታ መሃል
የክርስቶስ ድምፁ በግልፅ ይሰማኛል/2/

አዝ

የልቦናዬ አይን ፈፅሞ ታውሯል
አይኔን ፈውስልኝ በርጠሚዮስ ይላል
አብዝቼ እጮሀለው ጌታ ማረኝ ብዬ
በውስጤ እየታየኝ ሲምረኝ ጌታዬ/2/
አዝ

አንተን አይሰማህም ይሉኛል ብዙዎች
በኅጥያት ሰንሰለት ታስረሃል አቅተዎች
ስለዚህ አትልፋ ሲኦልን ጠብቃት
እንደዚህ ቢሉኝም እጮሀለው ሳልታክት/2/
አዝ

የከበበውን ሰው ገለል በሉ እያለ
በደሌን በደሙ ዋጋ እየከፈለ
ስለእኔ የሞተው ኢየሱስ ይመጣል
የልቦናዬን አይን ገልጦ ያሳየኛል/2/
አዝ

አብዝቼ እጮሀለው ጌታ ማረኝ ብዬ
በግልፅ እየታየኝ ሲምረኝ ጌታዬ
በውስጤ በደልስ ህይወቴ ዝላለች
በአምላኬ ቸርነት ህይወት ካላገኘች/2/

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፲፮ /16/

በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ ዘጠነኛ የሆነ፤ ቅዱስ አባት የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ያቃቱ አረፈ።

ከርሱ በፊት የነበረ አባ ብንያሚን በአረፈ ጊዜ ይህን አባት መርጠው በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት በዘመኑም ብዙ ችግር ደርሶበታል ስሙ ቴዎዶስዮስ የሚባል አንድ መለካዊ ሰው ነበረ እርሱም ወደ ደማስቆ ንጉሥ ወደ ዘይድ ሒዶ ብዙ እጅ መንሻ ሰጥቶ ለእስክንድርያ አገረ ገዥ ሁኖ ተሾመ ። ይህንንም አባት አባ ያቃቱን ያስጨንቀው ጀመረ በየዓመቱ ግብር ሰባት ሺህ የወርቅ ዲናር ከእርሱ እስከተቀበለ ድረስ እግዚአብሔርም እስከ አጠፋው ድረስ ይህን አባት እንዲህ አሠቃየው ።

በአንዲት ሌሊትም ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ለዚህ አባት ተገለጸለት ፍዩም በሚባል አገር በአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግል ዮሐንስ የሚባል ጻድቅ ሰው መነኰስ እንዳለ ነገረው ። ሕዝብን በማስተማርና በመምከርም ይረዳው ዘንድ መልእክተኞችን ልኮ እንዲአስመጣውም አዘዘው ሁለተኛም ከእርሱ በኋላ ሊቀ ጳጳሳት እንደሚሆን ገለጠለት ።

በዚያንም ጊዜ መልእክተኞችን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሥራውንም ሁሉ አስረከበው ይህንንም አባት ከብዙ ድካም የሚያሳርፈው ሆነ በሹመቱ ወንበር ዐሥራ ዘጠኝ ዓመት ኑሮ ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ ።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​አጋንንት

ርኩሳንና ረቂቅ መናፍስት የሚጠሩበት መጠሪያ ሲሆን በብዙ ቁጥር አጋንንት ሲባሉ ጋኔን የተናጠል ስያሜያቸው ነው:: የአለቃቸው መጠሪያ ሰይጣን ሲሆን እርሱን የሚከተሉ ሠራዊቱ አጋንንት ተብለው ይጠራሉ፡፡

አጋንንት እነማን ናቸው?

በዕለተ እሁድ እግዚአብሔር መላእክትን ፈጠረ ሲፈጥራቸውም በብሩህ አእምሮ በረቂቅ ተፈጥሮ ፈጥሯቸው ነበርና በእምነት ይፈልጉኝ በአምልኮ ያቅርቡኝ በምስጋና ያክብሩኝ ተመራምረው ያግኙኝ እገለጽላቸዋለሁ ብሎ ተሰወረ፡፡ በዚህን ጊዜ ማን ፈጠረን? ከየት ተገኘን? የሚል ጥያቄ በመላእክት መካከል ተነስቶ ዓለመ መላእክት ተሸበረ፡፡

በመጀመሪያ ማዕረግ /በከፍታ ስፍራ/ ከዘጠና ዘጠኙ ነገድ በላይ የተቀመጠው ሳጥናኤል የተባለው አለቃ ከነሰራዊቱ ነበር ወደ እርሱ የሚደርሰውን ማን ፈጠረን? ከየት ተገኘን? የሚለውን ከታች ከዘጠና ዘጠኙ ነገድ የሚነሳውን ድምጽ በሰማ ጊዜ ከእርሱ በላይ በማዕረግ የተቀመጠ እንደሌለ አይቶ እኔ ፈጠርኋችሁ ልበላቸው ብሎ እሰበ አሰቦም አልቀረ እኔ ፈጠ ርኋችሁ አላቸው ኃጢአትን አደረገ ሐሰትንም ወለደ። /2ጴጥ2÷4/ ዮሐን 8፥44/ በዚህን ጊዜ የእርሱ ነገድ  ሰራዊቱ ከሦስት ተከፋፈሉ፡፡

1ኛው - ከሰራዊቱ አንዱ እጅ አዎ ፈጠርከን ብሎ ተቀበለ ወድቆ ሰገደ
2ኛው -ከሰራዊቱ አንዱ እጅ ፈጥሮን ይሆን ሲለ ተጠራጠረ
3ኛው -ከሰራዊቱ አንዱ እጅ ምን አንተ ትፈጥረናለህ ስለምንበዛ እኛ ብንፈጥርህ እንጂ አሉ።

ከዚህ በኋላ  እግዚአብሔር አምላክ ጨርሶ ሳያስክዳቸው ልገለጽላቸው አለ፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የተባለውም አለቃ «ንቁም በበህላዊነ እስከ ንረክቦ ለአምላክነ» /የፈጠረንን እስክናውቅ ባለንበት እንጽና/ ብሎ በማወጅ የመላእክትን ዓለም አረጋጋ እግዚአብሔርም ከወደ ምስራቅ ብርሃን ገለፀላቸው /በብርሃን ጐርፍ ተገለፀላቸው/ ያን ጊዜ አንዱም ለአንዱ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሰራዊት ጌታ እግዚአበሔር እያሉ ጮኹ ከድምጽም የተነሳ መድረኩ ተንቀጠቀጠ የክብሩንም መቅደስ የጣኑ ጢስ ሞላው /ት.ኢሳ 6፥3/ የመላእክትም አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ያመፀውን መልአክ ከነሰራዊቱ ሊዋጋ ለሰልፍ ወጣ በሰማይ ሰልፍ ሆነ / ራእ ዮሐ 12፥7/ የካዱትን መላእክት ተዋጋቸው ዲያብሎስም  ድልን ተነስቶ ከነሰራዊቱ ወደ ምድር ተጣለ /ራእ ዮሐ 12፥9/

መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው የቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮት ግን አጋንንት በብዙ ልዩ ልዩ መጠሪያ የሚጠሩ የወደቀው መልአክና ሠራዊቶቹ መሆናቸውን ያረጋግጥልናል፡፡ /ራእ 12፥9፣ ሕዝ. 28፥14፣ ኢሳ. 14፥12/ መልአካዊ ክብራቸውንና ሥልጣናቸውን ተገፈው የወደቁት መላእክት ስለመሆናቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ከምናገኛቸው ብዙ ማስረጃዎች በስፋት የሚገልጹት ሁለቱን

1.አጋንንት በኃጢአት ምክንያት የወደቁት መላአክት ስስመሆናቸው
«እግዚአብሔር ኃጢአትን ላደረጉት መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሀነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ ከሰጣቸው. . .» /2ጴጥ. 2፥4/ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይመሰክራል :: /ሉቃ 10÷8  ማቴ 13:29/

2.አጋንንት በትዕቢት ምክንያት የወደቁት መሳአክት ስስመሆናቸው
«አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ አሕዛብን ያዋረድህ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቆረጥህ፡፡ አንተም በልብህ ወደ ሰማይ አርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፡፡ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ ከደመ ናዎች ከፍታ በላይ አርጋለሁ:: በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጉድጓዱም ጥልቅ ትወርዳለህ፡፡» /ኢሳ. 14፥12/ ይላል::

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :-የአጋንንታዊ በሽታዎች ምስጢራዊነት እና በጠበል መፈወስ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፲፭ /15/


በዚህች ቀን ከኒቆምድያ አገር ቅዱስ ቢላሞን በሰማዕትነት አረፈ።

የዚህም ቅዱስ አባቱ ጣዖት አምላኪ ነው እናቱ ግን ክርስቲያን ናት ጥበብንም አስተማሩት ከዚህም በኋላ ስሙ አርማላስ ከሚባል ቄስ ጋር ተገናኘ። ዠ እርሱም ስለቀናች ሃይማኖት አስተምሮ አጠመቀው።

በትንሽ ጊዜም ከጸጋ ደርሶ ድውያንን ይፈውስ ገባ። ብዙ አህዛብንም እያስተማረ ከደዌአቸው እየፈወሰ ወደ ክርስትና መለሳቸው። አንድ ቀንም ዓይነ ስውር አብርተሃል በሚል ተከሶ ከንጉሱ ፊት ቀረበ።

ንጉሱም ስለ ሃይማኖቱ በጠየቀው ጊዜ እርሱም ክርስቲያን ነኝ ብሎ በፊቱ ታመነ ንጉሡም ብዙ ሽንገላን በመሸንገል አባበለው። ብዙ ቃል ኪዳንም ገባለት ባልሰማውም ጊዜ በእርሱ ላይ ተቆጥቶ  ካልሰማኸኝ እኔ ጽኑ ሥቃይን አሠቃይሃለሁ አለው። ቅዱስ ቢላሞንም እኔ ከሥቃይህ የተነሣ ፈርቼ ሃይማኖቴን ለውጬ ፈጣሪዬን አልክድም አለው።

ከዚያችም ቀን ጀምሮ በብዙ አይነት ሥቃይ አሰቃየው። ከመገደሉ በፊትም ጌታችን ከሰማይ ወርዶ ወዳጄ ቢለው ወታደሮቹ ሰሙ። በዚህም ምክንያት አምነው በዚህች ቀን ቁጥራቸው መቶ ኀምሣ ስምንት ወታደሮች አብረውት ተሰይፈዋል::

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ቅዱስ አቡነ አረጋዊ ለተራራው ፍቅር አደረባቸው፤ አለቀሱም፡፡ በዚህም ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ዳግመኛ መጥቶ ‹‹አረጋዊ ሆይ አይዞህ! አትፍራ ስልጣን ተሰጥቶሃልና፡፡ በሐረጓ በስተቀኝ በኩል ባለችው ቦታ ተቀመጥ፤ ወደ ተራራው ጫፍ ያወጣህ ዘንድ በገመድ ፋንታ ቁመቱ ስድሳ ክንድ የሆነ ታላቅ ዘንዶ እግዚአብሔር ይልክልሃል›› አለው፡፡ ከዚያም በጾም በጸሎት ሁለት ሱባኤ ይዘው ፲፬ ቀን  በዚያ ተቀመጡ፡፡ የታዘዘውም ዘንዶ በሦስት ሰዓት መጣ፤ በዘንዶው ጅራት ላይ ወጥቶ በቅጽበት ከተቀደሰው ተራራ ጫፍ ላይ ደረሰ፤ እንደደረሰም ሦስት ጊዜ ሰገደ። ወዲያው ‹‹ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ›› እያለ አመሰገነ፡፡

ስለዚህም ቦታው ደብረ ሃሌ ሉያ ተብሎ ተሠየመ፡፡ በመሸም ጊዜ አነስተኛ ዳቦ አንስቶ ባርኮ መብላት ጀመረ፡፡ ዳቦዋ ግማሽ ስትሆን ስለጠገበ የዳቦውን ግማሽ አምሳል ለኋለኛው ትውልድ ምልክት ትሆን ዘንድ እንጨት ጠርቦ/ቀርጾ/ አስቀመጠ፤ ይህች ምልክት እስከዛሬ ድረስ አለች፡፡

ደቀ መዛሙርቱም ከታች ወደ ላይ የሚወጡበትን መሰላል በሠሩ አባታችን አቡነ አረጋዊ ደግሞ መጠነኛ ቤት ሠራና ይዞት የመጣውን ታቦት በውስጡ አስገባ፡፡ እግዚአብሔርንም ስለቁርባኑ ወይም ስለመሥዋዕቱ ለመኑ፡፡ እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ መላእክት ከሰማይ ይዘውላቸው ወረዱ፡፡ ለመኖሪያቸውም ትንሽ በአት አገኙ፡፡ ያለምንም መኝታ በጸሎትና በስግደት በመትጋት ተቀመጡ፡፡ በዚያም ብዙ ተአምራትን አደረጉ፤ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ተይዘው የሚሠቃዩትን በጸሎታቸው ኃይል ፈወሷቸው፤ ያላመኑትን ደግሞ እያስተማሩ አሳመኗቸው፤ ለዚያችም ሀገር ብርሃን አበሩላት።

አፄ ካሌብም ‹‹አባቴ ሆይ! በጸሎትህ አስበኝ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት ግዳጅ ትፈጽማለች፤ ኃይልም ታሰጣለች፤ በጠላት ላይም ድልን ታቀዳጃለች›› ብሎ አቡነ አረጋዊን ለመኗቸው፤ ወደ ደቡብ በሄደም ጊዜ የመን ከሠራዊቱ ጋር ዘምተው አሸንፈው ተመለሱ። የአፄ ካሌብ ልጅ ገብረ መስቀል ቤተ ክርስቲያን ሠራላቸው። በውስጡም በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች በእመቤታችን በድንግል ማርያም ስም የተሰየመች በወርቅና በብር ያጌጠች ታቦት አስገባ፡፡ ንጉሥ አፄ ገብረ መስቀል ከተራራው ላይ ሲወርድ ለቤተክርስቲያኑ ማሠሪያ የሆነውን መወጣጫ መሰላል ‹ላፍርሰው› ብሎ አባታችንን ጠየቀ፤ አባታችንም ‹‹አዎ! አፍርሰው፤ አትትወው፤ ነገር ግን ስለዘንዶው ጅራት ፈንታ ሰዎች ይወጡበት ዘንድ ገመድ አብጅ›› አለው፡፡ ንጉሡም አባታችን አቡነ አረጋዊ እንዳዘዘው አደረገ፤ያም ቦታ ደብረ ደኃምሞ ተብሎ ተሰየመ።

ከዚህ በኋላም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈቀ ሌሊት ተገልጾ ‹‹ከድካም ወደ ዕረፍት፣ ከኃዘን ደስታ ወዳለበት፣ ከኀሣር ወደ ክብር ቦታ በታላቅ ደስታ እወስድህ ዘንድ ወደ አንተ መጣሁ፡፡ የሞት ጥላ አያርፍብህም፤ መልአከ ሞትም ሊያስደነግጥህ አይችልም፤ እንደ ነቢያት ኤልያስና ሄኖክ ትሰወራለህ›› ብሎ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ አረገ፡፡

አባታችን አቡነ አረጋዊ ማትያስ ለተባለው ደቀ መዛሙር ጌታችን ተገልጦ የሰጣቸውን ቃል ኪዳንና ይህ መጽሐፍ ተጽፎ ለልጅ ልጅ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ነገሩት፤ (መዝ ፻፲፩/፻፲፪፥፮) ወንድሞቹ ደቀ መዛሙርቶቹ በተሰበስቡበትም ሁሉንም ከአስተማሩ በኋላ ‹‹ከዛሬ ጀምሮ በሥጋ አታዩኝም›› አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም በመሪር ኃዘን እግራቸው ሥር ወድቀው አለቀሱ፤  አባታችን አቡነ አረጋዊም አጽኗኗቸው፡፡ ጥቅምት ፲፬ ቀን ቅዱስ አባታችን አቡነ አረጋዊ በ፺፱ ዓመታቸው ተሰወሩ፤ በዚያም ከመቋሚያና ከመስቀል በስተቀር ምንም የተገኘ የለም፡፡

የአባታችን አብነ አረጋዊ ረድኤት በረከት በሁላችንም ላይ ይደር! አሜን
መምህር ሸዋገኘሁ ከበደ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንዲህ በአራት ነጥብ

እንዲህ በአራት ነጥብ ሊዘጋ ምዕራፉ
እግዚአብሔር ሊያሸንፍ የእርሱ ሆኖ ሰልፉ
መልካም ለመናገር አፉ ባይታደል
ይህን እስኪያይ ጠላት ምን አለ ዝም ቢል/2/

አዝ

መልካሙን ደብቆ ክፉን እያሳየ
ይለኝ ነበር ጠላት እግዚአብሔር ዘገየ
ግን ሁሉን በጊዜው ውብ አግድጎ ሲሰራ
አፍሮአል ለዘላላም ደንቆት የእርሱ ሥራ/2/
አዝ

በቃ ልጅ የለህም አትወልድም ሣራ
ላይሰማህ እግዚአብሔር ጮኸ ብትጣራ
እያለ ጠላቴ መስሎት ያሸነፈ
ይስሃቅ ተወለደ ያ ቀንም አለፈ /2/
አዝ

ፍፃሜዬን ሳያይ ገና ከጅምሩ
ጠላት በእሱ ግምት ብዙ መናገሩ
አስብሎታል ቴቄል ተቀይሮ ስሙ
የዘገየ መስሎ ጌታ በመቅደሙ/2/
አዝ

ድንጋይ ያሸከመን ውሃ ተሸከመ
ለእኛ ቀን ወጣልን ለእርሱ ግን ጨለመ
ገዳይ ቢዘገይም ሟች በመገስገሱ
ፈረሰኛው ሞተ እስከነ ፈረሱ/2/
አዝ

ቢመስለንም ሌሊቱ ፍፁም የማይነጋ
ተቆልፎ የሚቀር በሩ እንደተዘጋ
እርሱን ተስፋ አድርገው ባመንክበት ፅና
ቀን አለው እግዚአብሔር ያደርግሃል ቀና/2/

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ፍቅርህ ማረከኝ

ፍቅርህ ማረከኝ በሕይወቴ በዘመኔ/2/
እግዚአብሔር ለእኔ መድሃኒቴ
ፍቅርህ ማረከኝ በህይወቴ በዘመኔ/2/

አዝ

ተገዝቻለሁ በወርቅ ደምህ
ዓለምን ትቼ ላገለግልህ
ሞትህ ህይወቴ ለእኔ ሆኖኛል
በአንተ መከራ ሸክሜ እርቋል
ለክብርህ ቆሜ እዘምራለሁ
እንደ አቅሜ አገንሃለሁ/2/
አዝ

ምድርና ሰማይ እልል ይበሉ
ምስጋና ለአንተ ይድረስ እያሉ
መሳይ የለህም ለቅድስናህ
አቀርባለሁኝ ለአንተ ምስጋና
ጣቴ በገና ይደረድራል
በቀን በሌሊት ያመስግናል/2/
አዝ

ክብርህን አይተው ጠላቶች ፈሩ
ለጌትነትህ ወድቀው ተገዙ
እንዲህ ነህ አምላክ እንዲህ ነህ ጌታ
ሁሉን በፍቅር የምትረታ
በአንተ ተመካሁ በፈጣሪያችን
አዳኝ በሆንከው በንጉሳችን/2/

ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በዋጋ ገዝተኸኛልና

በዋጋ ገዝተኸኛልና
ስለ እኔ ደም ከፍለሀልና/2/
ልሳኔ ያውጃል ክብርህን
አልረሳም ጌታ ውለታህን/2/

አዝ

ህይወት ሠላምን ትቼ
የማይታይ አይቼ
ላንተ ብሰጥ ጀርባዬን
ልተዋወቅ ጠላቴን
የጠበቀኝ ውጊያ ነው
የተረፈኝ ፀፀት ነው
የሻረልኝ ቁስለቴ
ተሰቅለህ ነው አባቴ
አዝ

እጓዛለሁ በምናብ
ወደ ሠላሜ ወደብ
እጄን በአፌ እጭናለሁ
ዛሬም እፁብ እላለሁ
ለክብርህ መሠለፌ
በለምለሙ ማረፌ
ዋጋ ከፍለህ ነው ጌታ
ያኖርከኝ በፀጥታ
አዝ

ከወሃ ከመንፈስ
ተወልጄ በመቅደስ
ልጅህ ሆንኩኝ ዳግመኛ
የመስቀልህ ምርኮኛ
በአንተ ስለመዳኔ
ምስክርህ ነኝ እኔ
ላይታጠፍ ምላሴ
እቀኛለሁ በነፍሴ

ዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረፃዲቅ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ስድቤን አርቀሽ

ስድቤን አርቀሽ ነውሬን ሸፈንሽው
እመ አምላክ በአንቺ መቼም አላፍር
ስምሽን ጠርቼ እጽናናለሁኝ
ሀዘኔን በአንቺ እረሳለሁኝ

አዝ

ነውር አለብኝ ብዙ ስድብ
አንጀት የሚልጥ ልብ የሚያቆስል
ስሜን ለውጠው ቢያንቋሽሹኝ
በሀዘን በለቅሶ ድንግል መጣሁኝ
እንደ ሃና ሆኜ ከቤተ መቅደስ
በመረረ ሐዘን ነው የማለቅስ
ፍረጅልኝና ልመለስ ከቤቴ
ሐዘኔን በደስታ ለውጪው እናቴ
በግራም በቀኝም ጠላት ቢከበኝ
አብዝቼ እጮሃለው እናቴ ስሚኝ
አዝ

መከራው በዝቶ ግራ ገብቶኛል 
ድምፅሽን ልስማ ያረጋጋኛል 
የሰው ህይወቱ ብርቱ ሰልፍ ነው      
ደስታና ሐዘን የማይለየው
በእጃችን ወድቋል ሲሉ ጠላቶቼ
አመለጥኳቸው ስምሽን ጠርቼ
ሰው የዘራውን ያንኑ ያጭዳል
በቆፈረው ጉድጓድ ራሱ ይገባል
እናቴ እመቤቴ ብዬ ስጠራሽ
ከመከራ ሁሉ ታወጪኛለሽ
አዝ

በምርኮ ሳለሁ በሰው ሀገር     
ግፍ ውለውብኝ ስኖር በእስር      
ምልጃሽ ደርሶልኝ ተፈትቻለሁ      
በታምራትሽ እኔ ድኛለሁ
ቃልሽን ሰምቶ ጽንሱ ሰገደ
ብላለች ኤልሳቤጥ ነውሬ ተወገደ
የጌታዬ እናት እኔን አሰበችኝ
ታሪኬን ቀይራ ይኽው ባረከችኝ
የእመቤቴ ከሆንኩ ማን ይቃወመኛል
ወጀቡም ማእበሉም ይታዘዝልኛል
አዝ

ወይን እኮ አልቋል የዶኪማስ ቤት      
ድንግል አማልጅው ነይ የእኛ እመቤት      
ስምሽ ሲጠራ በየቦታው      
ይሞላልና የጎደለው           
ግራ የገባው የቸገረው            
ድንግልን ይጥራት እንድትረዳው            
ሳዝን ስተክዝ የምታጽናና            
እናት አለችኝ እርህርህይተ ልቦና
እናቴ እመቤቴ ብዬ ስጠራሽ
ከመከራ ሁሉ ታወጪኛለሽ

ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፲፪ /12/


በዚች ዕለት የመላእክት አለቃ የከበረ መልአክ የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።

በዚችም ቀን ወደ ነቢይ ሳሙኤል እግዚአብሔር ልኮታልና ለእስራኤል ልጆች ዳዊትን እንዲያነግስላቸው ይቀባው ዘንድ አዘዘው። ሳሙኤልም ወደ እሴይ ቤት ሔዶ ልጆችህን ሁሉንም አቅርብልኝ ብለው እሴይም ከዳዊት በቀር ሁሉንም አቀረባቸው እርሱ በእርሻ ውስጥ በጎችን ይጠብቅ ነበርና ።

ሳሙኤልም የመንግሥት ቅባት ያለበትን ብልቃጥ በራሳቸው ላይ ከፍ ከፍ በአደረገ ጊዜ እግዚአብሔር አልመረጣቸውም። ሳሙኤልም እሴይን ልጆችህ እነዚህ ብቻ ናቸውን አለው ዕሴይም በጎች የሚጠብቅ አንድ ትንሽ ልጅ አለ አለው።

ሳሙኤልም ደግሞ ዕሴይን እሱ ሳይመጣ ምሳ አልበላምና ልከህ አስመጣው አለው። እርሱም ልኮ አስመጣው መልኩም ቀይ ዐይኖቹም የተዋቡ አርአያውም ያማረ ነው እግዚአብሔርም ሳሙኤልን ይህ ይበልጣቸዋልና ተነሥተህ ቀባው አለው። በዚያንም ጊዜ ሳሙኤል የመንግሥት ቅባት ያለበትን ቀንድ አምጥቶ በወንድሞቹ መካከል ቀባው ከዚያችም ቀን ጀምሮ ለሁል ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በዳዊት ላይ አደረበት በእስራኤል ልጆችም ላይ ነገሠ።

ደግሞ ሁለተኛ በዚች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ሚካኤልን ወደ ዳዊት ላከው ረዓይታይ ጎልያድን እስኪገድለውና የእስራኤልን ልጆች እስከሚያድናቸው ረድቶ ኃይልን ሰጠው።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጻድቃን በበግ ኃጥአን በፍየል የተመሰሉት ለምንድን ነው?

የበጎች ተፈጥሮ ከጻድቃን፤ የፍየሎች ተፈጥሮ ከኃጥአን ጋር ይመሳሰላሉ፤

ከበጎች መካከል አንዲቱን ተኩላ ቢነጥቃቸው በረው ወደ ዱር ይገባሉ ወደዚያ ቦታ ተመልሰው አይሄዱም። ጻድቃንም ከሰው መካከል አንዱ በሞት ቢነጠቅ ይሄ እጣ ነገ ለእኔም ይደርሳል ብለው ከኃጢአት ርቀው እግዚአብሔርን በንጽሕና ያገለግሉታል እንጂ ዳግም ወደዚያ የኃጢአት ሥራቸው አይመለሱም።

ፍየሎች ግን ከመካከላቸው አንዲቱን ተኩላ ቢነጥቅባቸው ለጊዜው ከዚያ ቦታ ይሸሹና ተመልሰው እዚያው ይገኛሉ፡ ኃጥአንም ከመካከላቸው አንዱ ቢሞት ለጊዜው ደንግጠው ከኃጢአት ቢርቁም ኋላ ወደ ጥፋታቸው ይመለሳለና በፍየል መሰላቸው።

በግ ኃፍረቷን አታሳይም፡ በላቷ ትሸፍነዋለች። ጻድቃንም ኃጢአት ቢሠሩ እንኳ ኃጢአታቸውን በንስሐ ይሸፍናሉ።

ፍየል ኃፍረቷ የተገለጠ ነው፤ ላቷም የተሰቀለ ነው ኃጥአንም ኃጢአት በሠሩ ጊዜ በንስሐ እናጥፋው አይሉም፣ እንዲያውም ኃጢአታቸው በሰው ሁሉ ፊት የተገለጠ ነው።

በግ ያለችበት፤ የዋለችበት ቦታ አይታወቅም ጻድቃንም በትሕትናቸው፣ በዝምታቸው ያሉበት ቦታ አይታወቅም።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :-ትምህርተ ሃይማኖት
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፲፩ /11/

በዚችም ቀን ገድለኛዋ ቅድስት ጲላግያ አረፈች።

ይቺም ከአንጾኪያ አገር የሆነች ናት፤ ወላጆቿም ከሀድያን ናቸው እርሷም አስቀድማ ከረከሰ ሃይማኖቷ ጋር በረከሰ ሥራ ጸንታ መኖርን ገንዘብ አደረገች። እርሷም በመሸታ በጨዋታ ቤት በመዋል ስትሣለቅና ስታመነዝር ስትዘፍንም ትኖራለች ።

በአንዲት ቀንም የገሀነም እሳትና የዘላለም ሥቃይ እንደሚጠብቃቸው እያሳሰበ ዝንጉዎችንና አመንዝራዎችን ሲገሥጻቸው ኤጲስቆጶስ ጳውሎስን ሰማችው ምክሩም በልቧ አደረ። ከዚህም በኋላ ወደርሱ ሒዳ የሠራችውን ሁሉ ተናዘዘች እርሱም አጽናንቶ የቀናች ሃይማኖትን አስተማራትና አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃት።

በቀደመው ሥራዋም እየተጸጸተች በጾም በጸሎት በስግደት ሰውነቷን ማድከም ጀመረች ከዚህም በኋላ የወንድ ልብስ ለብሳ ወደ ኢየሩሳሌም ሒዳ በከበሩ ቦታዎች ሁሉ ሰግዳ ሁሉንም ቦታዎች ተሳለመች ወደ ኢየሩሳሌሙ ሊቀ ጳጳሳትም ተመለሰች። እርሱም ከኢየሩሳሌም ከተማ ውጭ ከደናግል ገዳማት ወደ አንዱ ላካት የምንኵስናንም ልብስ ለብሳ በጽኑዕ ገድልም ተጠምዳ ሠላሳ ዓመት ያህል ኖረች እግዚአብሔርንም አገልግላ በሰላም አረፈች።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ያዳነኝን አውቀዋለው

ያዳነኝን አውቀዋለው
የሞተልኝ ኢየሱስ ነው
ስለሌለኝ የምከፍለው
ስጦታዬ ምስጋና ነው

ጨለማዬን አስወግዶ
ያበራልኝን አውቃለሁ
ሙሉ ሰው ነኝ ከእንግዲህስ
ስከተለው እኖራለሁ
የብርሃንን ልዩ ውበት
ፊት ለፊቴ ቆሞ አየሁት
ፍቅሩ ማርኮኝ
በመቅደሱ ሰገድኩለት አመለኩት
ላመስግነው ላመስግነው ላመስግነው
ፍቅሩ ማያልቅ ነው /2/

አዝ

አሳደረኝ በእቅፉ
መጠውለጌን አለምልሞ
በመስቀል ላይ ተሰቀለ
ዳንኩኝ እኔ እርሱ ታሞ
በማይዝለው ክንዶቹ ላይ
እኔን በክብር እያኖረ
እንዲመቸኝ ዝቅ ብሎ
በበረት ውስጥ እርሱ አደረ
ላመስግነው ላመስግነው ላመስግነው
ፍቅሩ ማያልቅ ነው /2/
አዝ

ቅኔ ባፈስ ምን ይደንቃል
ደሙን በመስቀል አፍስሶ
ስለ ልጁ መዳን ብሎ
ነፍሱን ሳይቀር ለኔ ክሶ
ፍቅሬ ይዞት ከጸባኦት
በትትና መቶ ወርዶ
ተቀደስኩኝ በነጩ በግ
ቀራንዮ ጌታ ታርዶ
ላመስግነው ላመስግነው ላመስግነው
ፍቅሩ ማያልቅ ነው /2/
አዝ

አክሊለ ሶክ አጠለቀ
ግርማ ክብሩን ሁሉ ትቶ
አሻገረኝ ወደ ክብሬ
በቅዱስ ደም እኔን ዋጅቶ
አጎንብሶ ቀና አረገኝ
ፊቴን በጽድቅ እያበራ
እኖራለሁ ለዘለአለም
ካከበረኝ ጌታ ጋራ
ላመስግነው ላመስግነው ላመስግነው
ፍቅሩ ማያልቅ ነው /2/

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እሰይ ነጋ

እሰይ ነጋ እሰይ ነጋ ላመሰግንህ ነው
አይኔን የከደንኩት አንተን አምኜ ነው /2/

በበደሌ ሳትፈርድ ትጠብቀኛለህ
ከእኔ በላይ ለእኔ ታስብልኛለህ
የማታንቀላፋው ትጉህ እረኛዬ
ብርሃኑን ያየሁት ባንተ ነው ጌታዬ

አዝ

ቀናቶቼን ሰጠሁ ላንተው አሳልፌ
በሰላም እተኛለሁ በክንድህ አርፌ
ተመስገን ማለትን በብርሃን ጨለማ
ታስተምረኛለህ በወፎቹ ዜማ
አዝ

ትናንትናን ታልፎ ስላየሁ አዲስ ቀን
ከእንቅልፌ ስነቃ እላለሁ ተመስገን
አንተ ባታነጋው የጨለመውን
አልኖርም ነበረ ዛሬ ባልኩት ቀን
አዝ

ሁሉም የሚሆነው እንደየ ስርዐቱ
በአንተ ብቻ እኮ ነው መጨለም መንጋቱ
ስለ አደረክልኝ ምኔን ልክፈልህ
ተመስገን ብቻ ነው ሥላሴ ዋጋህ
አዝ

በብርሃን ተተካ አስፈሪው ጨለማ
እንደኔማ ሳይሆን ምህረትህ ቀድማ
የእኔ ያልኳት ዛሬ ነግታ የምትመሸው
በጥበቤ አይደለም በበጎነትህ ነው

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፲፯ /17/


በዚችም ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳ አንደኛ የሆነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ዲዮስቆሮስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።

ይህም አባት በዘመኑ ካሉ ትውልድ እርሱን የሚመስል ያልተገኘ በጠባዩ ቅን የዋህ በእውቀቱ አስተዋይ በበጎ ሥራው ፍጹም የሆነ ነው። በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ ስለ ምስጢረ ሥላሴ እና ስለ ምስጢረ ሥጋዌ አርቅቆ መልእክትን ጽፎ ወደ አንጾኪያ ሊቀ ጳጰሳት ቅዱስ ሳዊሮስ ላካት። መልእክቱም ወደ ቅዱስ አባት ሳዊሮስ በደረሰች ጊዜ አነበባትና ፈጽሞ ደስ ተሰኘባት ለአንጾኪያም ሕዝብ አስተማረባት ሁሉም ደስ አለቸው።

ከዚህም በኋላ አባ ሳዊሮስ ለአባ ዲዮስቆሮስ የመልእክቱን መልስ እንዲህ ብሎ ጻፈ። ቤተ ክርስቲያንን እንድትጠብቅ ለዚች ለከበረች አገልግሎት የመረጠህ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ። ዳግመኛም ሕዝቡ እንዲጸኑ ሁል ጊዜ ስለቀናች ሃይማኖት አስተምራቸው አለው።

የአባ ሳዊሮስም መልእክት ወደ አባ ዲዮስቆሮስ በደረሰች ጊዜ ደስ ተሰኘባት በሁሉ ቦታም እንዲአስተምሩባት አዘዘ። ይህም አባት ሁል ጊዜም ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ያስተምራቸዋል ኤጲስቆጶሳቱንና ካህናቱንም መንጋዎቻቸውን ስለ መጠበቅ ያዛቸዋል፤ መልካም አገልግሎቱንም አድርሶ እግዚአብሔርንም ደስ አሰኝቶ አረፈ።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ኪዳነ ምህረት እናቴ

ኪዳነምህረት እናቴ ምስጢረኛዬ ጓዳዬ
የጎደለኝን ታውቂያለሽ
ከአፌ ሳይወጣ ሳልነግርሽ /2/

አዝ

አልፏል መናኛው ኑሮ
ምልጃሽ ውኃውን ቀይሮ
መልካሙ ወይን ደረሰ
እንባዬ ባንቺ ታበሰ /2/
አዝ

ልዘምር ልቁም ከፊትሽ
ልምጣ ልንበርከክ ለክብርሽ
ብርቅ ከሀገር ከቤቴ
ከቶ አልረሳሽም እናቴ /2/
አዝ

አልልም መቼ ነው ቀኑ
የእኔ መጎብኛ ዘመኑ
እንደሚፈፀም አምናለሁ
ሁሉን በጊዜው አያለው /2/
አዝ

የልቤን ችግር ላዋይሽ
ከስዕልሽ ፊት ቆሜ
እንባዬ ቀድሞ ዝም አልኩኝ
ሳልነግርሽ ስለምታውቂ /2/

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ምስጢረኛዬ ነሽ

አውቀዋለሁ ደጅሽን የእረፍት ቦታዬን
ጽኑ ስላም ጸጥታ ማግኛዬን
የት እሄዳለሁ አልልም ሲከፋኝ
ኪዳነምሕረት አንቺ እያለሽልኝ/2/

አዝ

ከአጸደ መቅደስሽ ከስዕልሽ ስር
እረፍቴ በዚያ ነው በቅዱሱ ደብር
ከተራራው አናት ከደጅሽ መጥቼ
ሰምሮልኛል ስምሽን ጠርቼ
ምሥጢረኛዬ ነሽ ምሥጢረኛዬ
ኪዳነምሕረት መጽናኛዬ/2/
አዝ

የሮማን አበባ መዓዛሽ ተወዳጅ
በረከትን ልቅሰም ሳልለይ ካንቺ ደጅ
አስራትሽ አድርጊኝ ጠቅልይኝ እናቴ
ታብብልኝ ትፍካልኝ ሕይወቴ
ምሥጢረኛዬ ነሽ ምሥጢረኛዬ
ኪዳነምሕረት መጽናኛዬ/2/
አዝ

አጠገቤ ጎኔ በዙሪያዬ እንዳለሽ
እንደርሱ ነው ልቤ እማ የሚያወራሽ
አልቅሼ ሲቀለኝ ነግሬሽ የውስጤን
አትዘገይም ስትሠሪልኝ ቤቴን
ምሥጢረኛዬ ነሽ ምሥጢረኛዬ
ኪዳነምሕረት መጽናኛዬ/2/
አዝ

የእንጦጦዋ እናቴ እምዬ የምልሽ
ኪዳንኪ ደጓ የልብን ሰሚ ነሽ
በሄድኩበት አለሽ ተከትለሽኛል
ስላለሽኝ ሰላም ይሰማኛል
ምሥጢረኛዬ ነሽ ምሥጢረኛዬ
ኪዳነምሕረት መጽናኛዬ/2/

ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አዝላው ወረደች

አዝላው ወረደች ወደ ግብፅ /2/
ስደተኛዋ የአምላክ እናት
ይህ ዓለም ለእርሷ መች ተገባት

አዝ

ዓለም በምኗ ታስተናግዳት
የፍቅር ምንጯ ተሟጦባት
እነ ኮቲባን እየላከች
የአምላክን እናት ተሳደበች
እነ ሄሮድስን እየላከች
ህፃኑን ልትገድል አሳደደች
አዝ

የክብርን ጌታ ተሸክማ
ውርደት ለበሰች እንደ ሸማ
የሀብቱን ጌታ በጀርባ አዝላ
ሰው ተዘከራት ተቸግራ
አዝ

በቃሉ ትዕዛዝ ምድርን ሠርቶ
ተንከራተተ ማደሪያ አጥቶ
ጌታ ሲወለድ የምሥራች
በረት ሰጠችው ዓለም ታካች
አዝ

ግና መላእክት በሰማያት
ሃሌ ሉያ አሉ በፍርሃት
ወልድን በአብ ቀኝ ከላይ አይተው
ደግሞም በምድር ከድንግል ክንድ
ከላይም ሳይጎድል ተመልክተው /2/
አዝ

ዓለም በምኗ ታስተናግዳት
የፍቅር ምንጯ ተሟጦባት
እነ ኮቲባን እየላከች
የአምላክን እናት ተሳደበች
እነ ሄሮድስን እየላከች
ህፃኑን ልትገድል አሳደደች
አዝ

የክብርን ጌታ ተሸክማ
ውርደት ለበሰች እንደ ሸማ
የሀብቱን ጌታ በጀርባ አዝላ
ሰው ተዘከራት ተቸግራ
አዝ

በቃሉ ትዕዛዝ ምድርን ሠርቶ
ተንከራተተ ማደሪያ እጥቶ
ጌታ ሲወለድ የምሥራች
በረት ሰጠችው ዓለም ታካች

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የሚጠብቀኝ አይተኛም

የሚጠብቀኝ አይተኛም/2/
አያንቀላፋም/2/

አዝ

ቤት ባይኖረኝም እደጅ ባድርም
ቀን እና ሌሊት ከእኔ አይርቅም
ድምጸ አራዊት የሌሊት ግርማ
ወደ እኔ አይቀርብም ድምጽህ ሲሰማ
አዝ

መሰናክልን ለእግሮቼ አይሰጥም
ይሰውረኛል በቀኙ ሰላም
ፀሐይም በቀን አይተኩሰኝም
የአጋንንትም ኃይል አያስፈራኝም
አዝ

ነፍሴን ጠበቃት ከጠላት ወጥመድ
ጌታዬ መራኝ በጽድቅ መንገድ
መውጣት መግባቴን እየጠበቀ
ለዚህ አበቃኝ እርሱ ባወቀ
አዝ

የሰማዩን ጠል እታገሳለው
ሰው ከጨከነ ምን እሆናለው
ሌሊት በድብቅ ለሚጎበኙኝ
ለጻድቃኑ ክብር አምላክ ይስጥልኝ
አዝ

እንቅልፌን ባርኮ የሰጠኝ የጌታ
በአለም ሀሳብ ሳልንገላታ
የእለት ምግቤንም ላልነሳኝ ፍጹም
ምስጋና ላቅርብ እስከ ዘለዓለም

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ጥቅምት ፲፬ /14/

​​እንኳን ለአባታችን አቡነ አረጋዊ አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን!

አባታችን አቡነ አረጋዊ ከዘጠኙ ቅዱሳን አባቶች አንዱ ናቸው። ትውልዳቸውም ከሮም ነገሥታት ወገን ሲሆን አባታቸው ይስሐቅ የሮም ንጉሥ ነበር፤ እናታቸው እድና ትባላለች፡፡ ሁለቱም እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያከብሩ ነበሩ፡፡ የተባረከ ልጅም ወለዱ፤ በሕገ እግዚአብሔርና ቅዱሳት መጻሕፍትን እያነበበ አደጉ፡፡ ለአቅመ አዳም ሲደርሱ ሚስት ቢታጭላቸውም ከነበራቸው የክርስቶስ ፍቅር የተነሳ ትዳር መመሥረትን ትተው  ደውናስ ወደ ምትባል ገዳም ሔዱ፤ በዚያም አባ ጳኩሚስ ይኖሩ ነበር።

አበምኔቱ አባ ጳኩሚስን ልብሰ ምንኩስናን እንዲያለብሳቸው ጠየቁት። አባ ጳኩሚስም ‹ልጄ ሆይ አንተ የንጉሥ ልጅ እንደ መሆንህ መጠን የመንግሥቱ ወራሽ ነህና መንኩሰህ ለመኖር ይቻልሃልን?› አለው፡፡ ቅዱስ አባታችንም ‹‹አባቴ ሆይ የምድር መንግሥት ኃላፊ ጠፊ ነው፤ ነገር ግን የማታልፈውንና የማትጠፋውን ዘለዓለማዊት መንግሥት እወርስ ዘንድ እፈልጋለሁ›› አለው፡፡ በ፲፬ /14/ ዓመታቸው በአባ ጳኩሚስ እጅ የምንኩስናውን ልብስ ለበሱ፤ በገዳሙም እየተጉ ኖሩ፡፡

ከዚህ በኋላ የጻድቁ ዜና በሀገራቸው ሮም ውስጥ እንዲሁም በመላው ቦታ ተሰማ፡፡ በዚህም  የተማረኩት ሰባት ቅዱሳን፤ አባ ሊቃኖስ ከቁስጥንጥንያ፣ አባ ይምአታ ከቆስያ፣ አባ ጽሕማ ከአንጾኪያ፣ አባ ጉባ ከቂልቅያ፣ አባ አፍፄ ከእስያ፣ አባ ጰንጠሌዎን ከሮም፣ አባ አሌፍ ከቂሳርያ እርሱ ወዳለበት ገዳም መጡ። አባ ጳኩሚስ ለብዙ ዓመታት ምንኩስናን ሥርዓተ ማኅበርን አስተማራቸው። እናቱ ንግሥት እድና የልጅዋን ዜና ሰምታ እርሱ ወዳለበት መጥታ መነኮሰች፡፡ በሴቶችም ገዳም ገብታ መኖር ጀመረች፡፡

መነኮሳቱም አባ ዘሚካኤልን መሪያቸው አደረጉት፤ በአካለ ሥጋ ሕፃን ሆኖ ሳለ የአእምሮውን ብስለት ዐይተው የሕይወት መንገድ ስለመራህን አቡነ አረጋዊ መባል ይገባሃል አሉት፤ በዚህም አቡነ አረጋዊ ተብለው ተጠሩ፤ ብልህ አዋቂ ማለትም ነው፡፡

በገዳመ ዳውናስ ሰባት ዓመት ከቆዩ በኋላ ይስሐቅን (በኋላ አባ ገሪማን) ለመጠየቅ እና የሀገሩን ሰዎች ለማስተማር በአንድነት ሆነው ወደ ሮም ተመልሰው ሲያስተምሩ በዘመናቸው የካቶሊክ ሃይማኖት እንዲቀበሉ ጫና ቢደረግባቸውም… ‹‹እውነቱን እውነት፣ ሐሰቱን ሐሰት ማለት ተገቢ ነውና ክርስቶስ ከተዋሕዶ በኋላ ሁለት ባሕርይ ነው ብሎ ማስተማር ክሕደት ነው››…. ብለው በድፍረት መቃወም ጀመሩ፡፡ ይሁን እንጂ በኃይል እና በገንዘብ ብዛት የምትመካው የሮማ ቫቲካን ቤተክርስቲያን ቅዱሱን ማሳደድ ጀመረች::

ቅዱሱ አባታችን አቡነ አረጋዊም ‹‹በአንዱ ቦታ መከራ ቢያጸኑባቸው ወደ ሌላው ሽሹ…›› የሚለውን የወንጌል ቃል አብነት በማድረግ እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኢትዮጵያን ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም የዐስራት ሀገር እንዲሆናት በቃል ኪዳን እንደሰጣት ከቅዱሳት መጻሕፍት በማንበቡ በኢትዮጵያ ፍቅር ተያዘ፤ ወደዚያውም መሄድ ፈለገ፡፡ ይህንንም ሁለት ደቀ መዛሙርቱን ይዞ ለማንም ሳያሳውቅ ቅዱስ ሚካኤል እየመራው ንጉሡና ጳጳሱ ካሉበት አክሱም ከተማ ደረሰ፡፡

እዚያም ጥቂት ቀን ተቀምጦ ወደ ሮም ተመለሰ፡፡ ስለኢትዮጵያ በዐይኑ የተመለከተውን በጆሮ የሰማውን ሁሉ ለወንድሞቹ ነገራቸው፡፡ እነርሱም ‹‹እኛም ወደዚህች ሀገር መሄድ አለብን›› ተባባሉ፡፡ ያላቸውን የመገልገያ ዕቃ ይዘው ከታቦቶቻቸውና ከካህናቶቻቸው ጋር ንዋየ ቅድሳትና መጻሕፍችን ይዘው ከመሰል ወገኖቻቸው ጋር አባታችን ዘሚካኤል (በአቡነ አረጋዊ) እየመራቸው በአልዓሜዳ አምስተኛ የንግሥና ዓመት በ፬፻፹ ዓ.ም ንጉሡና ጳጳሱ ካሉበት አክሱም ከተማ ደረሱ፤ ስምንቱ ቅዱሳንም መጡ፡፡ ጥቂት ቆይቶ ዘጠነኛው አቡነ ይስሓቅ (አቡነ ገሪማ) በሮም ከነገሠ ከሰባት ዓመት በኋላ መንግሥቱን ትቶ ወደ አክሱም መጣ፤ በዚያን ጊዜ እንደነሱ አመነኮሱት፤ ቍጥራቸውም ዘጠኝ ሆነ።

ለሁሉም አንድ የተለየ ማረፊያ ቦታ ቤተ ቀጢን የተባለው ተሰጥቷቸው በጸሎት ተጠምደው ይኖሩ ነበር፤ በአንዲት የጸሎት ቤት በአንድነት ሆነው ለጸሎት ፈጣሪያቸውን እየለመኑ፤ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረጉም ቆዩ፡፡ መላእክት ዘወትር ባለመለየት ያጽኗኗቸው፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዘወትር ይገለጽላቸው ነበር፡፡ በእያንዳንዳቸውም ብዙ ተአምራት ተደረጉ፡፡ ከእነርሱ መካከልም ተራራ ያፈለሱ፣ ባሕሩን ከፍለው ደረቅ መንገድ ያደረጉ፣ ስንዴ ዘርተው በቅጽበት ለዘጠኝ ሰዓት መሥዋዕተ ቁርባን ያደረሱ አሉ፡፡ የኢትዮጵያ ምድር በእነዚህ የቅዱሳን ኪደተ እግር ተቀደሰች፡፡

በኋላም ንጉሥ አልዓሜዳ ከሞተ በኋላ በነገሠው በታዜና ስድስተኛ ‹‹የንግሥና ዓመት ላይ ተለያይተን እናስተምር›› ብለው ወስነው ተለያዩ። አቡነ ሊቃኖስ ደብረ ቆናጽል፣ አባ ጰንጠሌዎን ከእዚሁ ሁለት ምዕራፍ እልፍ ብሎ ከሚገኝ ኮረብታ፣ አቡነ ይስሐቅ መደራ፣ አቡነ ጉባ በእዚሁ በመደራ ትይዩ ሦስት ምዕራፍ እልፍ ብሎ፣ አባ ጽሕማ፣ አባ ይምዓታ ገርዓልታ፣ አባ አሌፍ አሕስዓ ብሕዛ በተባለችው፣ አባ አፍጼ ይሐ ተሠማሩ።

አባታችንም እናታቸው እና ማትያስ የተባለ ደቀ መዝሙራቸውን ይዘው ከሁሉም ርቀው ወደ መረጡት ቦታ ሲሄዱ ከዛፍ ጥላ ሥር አረፉ፤ እርስዋም እስከ ዛሬ ድረስ የቅዱሳን ማረፊያ ሆና ትገኛለች፡፡ አባታችንም ቅድስት ቦታ ዳሞን ባያት ጊዜ ሦስት ጊዜ ሰገደ፡፡ በተራራዋ ሥር ለመኖርም ወደደ፡፡ ነገር ግን ወደ ተራራዋ መውጫ አላገኘም፡፡ ተመልሶ ወደ ሌላ ተራራ ሄዶ አማረጠ፤ ሆኖም እንደ ደብረ ዳሞ የበረከት ቦታ ባላገኘ ጊዜ ተመልሰ፡፡ በዚያም የምንጭ ውኃ አገኘ፡፡ ውኃውን እየተንከባከበች የሴት መነኮሳቶችን ታስተዳድር ዘንድ እናቱ ቅድስት እድናን አስቀመጣት፤ ይህችንም ደብረ በአተልሞ አላት፤ ትርጓሜውም የእናቴ ማረፊያ ቤት ማለት ነው፡፡

ከዚያም ሲሄድ ጠፍጣፋ ድንጋይ አገኘና ከዚያ ላይ ትንሽ ምንጣፍ አነጠፈና ተቀመጠ፡፡ በትሩንም በድንጋይዋ ላይ አቆመ፡፡ በተነሳም ጊዜ ደቀ መዝሙሩ ማትያስ በትሩንና ምንጣፉን ሲያነሳው ያች ድንጋይ ቁመቷም ጎኗም ልክ በዚያች ምንጣፍ አይነት ቅርጽ አወጣች፡፡ የቀድሞ መልኳ ነጭ ሲሆን አሁን ግን የማይፋቅና የማይላጥ ቀይ ቀለም ሆኗል፡ ስለአባታችን አቡነ አረጋዊ ታላቅነቱና ስለክብሩ ከዚያ የደረሱ ሁሉ ይሳለሟታል፡፡

ከዕለታት በአንደኛው ቀን መንገድ ሲሄድ ውሎ ከተራራ አጠገብ ወደ ታች የተንዠረገገች ሐረግ/ገመድ/ አገኘና በሥሯ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ሲጸልይ ከቆየ በኋላ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ ‹‹እግዚአብሔር ያከበረህ ቅዱስ ሆይ ምን ያስጨንቅሃል?›› አለው፡፡ አባታችንም ‹‹ከዚህ ተራራ ላይ ወጥቼ ስለኃጢአቴ ይቅርታን እጠይቅህ ዘንድ እወዳለሁ›› አለው፡፡ መልአኩም ‹‹ወደ ተራራው የምትወጣበትን እግዚአብሔር እስኪልክልህ ድረስ ጥቂት ጊዜ ታገስ›› አለው፡፡

ከ1 ሰዓት በኋላ ይቀጥላል!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፲፬ /14/


በዚህች ቀን ከሰባ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የሆነ ቅዱስ ሐዋርያ ፊልጶስ አረፈ።

ከመድኃኔታችንም ዕርገት በኋላ ሐዋርያት ከሾሟቸው ከሰባቱ ዲያቆናት ውስጥ የተቆጠረ ነው። እርሱም ወደ ሰማርያ ወርዶ አስተማረ ብዙዎችንም አሳምኖ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው።
ከዚህም በኋላ ወደ ጋዛ በሚወስደው መንገድ ይሔድ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ፊልጶስን አዘዘው በሔደም ጊዜ ለኢትዮጵያ ንግሥት ለህንደኬ በጅሮንዷ የሆነ ጃንደረባውን አገኘው እርሱም እንደ በግ ሊታረድ መጣ የሚለውን የነቢይ ኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር።

ፊልጶስም ጃንደረባውን የምታነበውን ታስታውለዋለህን አለው። ጃንደረባውም ያስተማረኝ ሳይኖር እንዴት አውቃለሁ አለ። ፊልጶስም ስለ ጌታችን ስለ መከራው ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት ስለሆነው ሞቱ እንደተነገረ ተረጐመለት።

ጃንደረባውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አመነ ያን ጊዜም በፊልጶስ እጅ ከወንዝ ውኃ ውስጥ ተጠመቀ ከውኃውም በወጡ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ፊልጶስን ነጥቆ ወሰደው ጃንደረባውም ሁለተኛ አላየውም። ሐዋርያው ፊልጶስም እግዚአብሔርን አገልግሎ በዚህች ዕለት ፈጽሞ በሰላም አረፈ።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ሕልመ ሌሊት (Nocturnal Emission)

ሕልመ ሌሊት (Nocturnal Emission) በሌላ አጠራር ርጥብ ሕልም (wet dream) እየተባለ የሚጠራ ሲኾን በእንቅልፍ ጊዜ ከወንዶች አባለ ዘር የሚወጣን የዘር ፈሳሽን የሚያመለክት ነው፡፡ በመጀመሪያ ማወቅ ያለብን መሠረታዊ ነገር ይህ ሁኔታ በራሱ ተፈጥሯዊ ወደ መሆን ስለ መጣ በቀጥታ ኃጢአት ነው ሊባል የማይችል መሆኑን ነው፡፡

ይህን በተመለከተ ቅዱስ አትናቴዎስ "ምን ዓይነት ኃጢአት ወይም ክፋት ነው ከተፈጥሮ የሚመነጨው? ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሔር ከኾነ፥ እንዴት መልካም የኾነው ፈጣሪ ርኵስ የኾነ ነገር ሊያመጣ ይችላል? ኾኖም ኃጢአትን ስናደርግ ያንጊዜ እንረሳለን ይላል። ይህ ማለት ከወንድ በሕልም ምክንያትነት የሚወጣው ዘር በራሱ በተፈጥሯዊ ሂደቱ ብቻ ከታየ ርኵስ ሊባል የማይችል መኾኑን ነው፡፡ ይህን ሰውየው ፈቅዶ ያመጣው ሳይኾን በተፈጥሮ እንዲያይ ስለ ኾነ እንጂ።

አንድ ሰው በንቁ ልቡና ሳለ ወደ ኃጢዓት የሚያመሩትን ነገሮች ተግቶ እየተቃወመ ነገር ግን በተኛበት ባንቀላፋ ጊዜ ዝንየት (ሕልመ ሌሊት) ቢያገኘው በተራክቦ፣ ዘር በማፍሰስ ያያት ሕልሙ ዕዳ ኾና አትቆጠርበትም፡፡ መሐሪ የኾነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውየው ተቃወማት እንጂ ወዶ ወደ እርሷ እንዳልተሳበ ያውቃልና፡፡ አንቀላፍቶ ሳለ ዘሩ ቢወርድ ፈልጎ አላመጣውምና ዕዳ አይኾንበትም።

ሕልመ ሌሊት ኃጢአት አይደለም ማለት ግን በተፈጥሯዊ ኹኔታው ብቻ እንጂ በእኛ ችግር ወይም ድክመት ምክንያት የሚከሰተው ኹሉ ችግር የለውም ማለት አለመኾኑን ልብ ይሏል፡፡ ሕልመ ሌሊት በተደጋጋሚ እንዲከሰት የሚያደርግ፣ በሕልመ ሌሊት በሚመታበት ጊዜ ለዚያ ምላሽ (Reaction) የሚያደርግ ከሆነ፣ ደስ የሚለውና ነገም ቢመጣ እያለ የሚመኝ ከሆነ እንቅልፍን ሰበብ አድርጎ ዝሙትን ሽቷል ማለት ነው፡፡ ያኔም ሕልመ ሌሊት ወደ ኃጢአት እንዲቀየር ይሆናል፡፡ ክፉ እያደረጎ ወደ እውናዊ የዝሙት ትግበራ ሊያመጣን ይችላል። ስለሆነም የሕልመ ሌሊት መፍትሔው ከመተኛታችን በፊት በምንተኛበትን አልጋ ላይ መጸለይ፤ የመስቀል ምልክት እያደረግን እግዚአብሔር ከክፉ ሕልም እንዲጠብቀን መማጸን፤ እንቅልፍ እስኪወስደን ድረስ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ያለ ማቋረጥ መጥራት ያስፈልጋል።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :-መጽሔተ ወራዙት ዘኦርቶዶክስ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥቅምት ፲፫/13/


በዚችም ቀን ደግሞ የመነኰስ ዘካርያስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ። የዚህም መስተጋድል የአባቱ ስም አቃርዮስ ነው። ይህም አቃርዮስ ምንኩስናን ሽቶ ሚስቱን አስፈቅዶ ሁለት ልጆቹን ትቶ በገዳመ አስቄጥስ መነኰሰ።

ከጥቂት ወራትም በኋላ በሀገር ውስጥ ረኃብ ሆነ ሚስቱም ልጆቿን ይዛ ወደ አስቄጥስ ገዳም ወደባሏ መጣች የሆነውን ችግር ነገረችው አቃርዮስም እነሆ እግዚአብሔር በመካከላችን ፍርድን አድርጎ ልጆቻችንን አካፈለን እኔም ወንዱን ልጄን እወስዳለሁ አንቺም ሴት ልጅሽን ውሰጂ አላት ይህንንም ብሎ ልጁን ዘካርያስን ወሰደ። ዘካርያስም በበጎ ሥራ በገዳም ውስጥ አደገ። መነኰሳትም ከመልኩ ማማር የተነሳ በመነኰሳት መካከል እንዴት ይኖራል ተባባሉ።

ዘካርያስም መነኰሳት ስለእርሱ እንዳንጐራጐሩ በሰማ ጊዜ ናጥራን ወደሚባል ተራራ ስር ወደአለች ዐዘቅት ሔደ ልብሱንም አውልቆ በረግረግ ውስጥ ተኛ ሥጋውም ተነፋፍቶ ጠቆረ ተመላልጦም ቆሰለ ብዙ ዘመንም በደዌ እንደኖረ ሆነ ከዚህም በኋላ ወደ ገዳም መጣ ያወቀውም የለም። ከብዙ ቀኖችም በኋላ አባቱ አስተውሎ ልጁ ዘካርያስ እንደ ሆነ አወቀውና መልክህን የለወጠው ምንድን ነው ብሎ ጠየቀው እርሱም ያደረገውን ሁሉ ነገረው።

አንድ ቀንም እግዚአብሔር ሥራውን ለአባ ኤስድሮስ ገለጸለት እርሱም ለመነኰሳት ነገራቸው። እነርሱም አስቀድሞ እንደ ሰው ሁነህ መጣህ ዛሬ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ሁነህ መጣህ አሉት። አባቱም ስለእርሱ እኔ በገድል ብዙ ደክሜአለሁ ነገር ግን ከልጄ ሥርዓተ ገድል አልደረስኩም ብሎ ተናገረ። በዚህ ተጋድሎውም ፵፭ (45) ዓመት እግዚአብሔርን አገልግሎ በ፶፪ (52) ዓመቱ አረፈ።

የቅዱሳን በረከታቸው ይደርብን አሜን !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የእግዚአብሔር መልአክ

የእግዚአብሔር መልአክ ስሙ ድንቅ ነው
ለጶርዓ ሰው ለማኑሄ እንደነገረው
በመሰዊያው ነበልባል ውስጥ ዐረገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ(2)

አዝ

ከዳን ወገን የሆነ
በእግዚአብሔር ያመነ
ማኑሄ የሚባል ሰው
የጌታ መልአክ ታየው
ሚስቱ መካን ነበረች
ልጅንም ያልወለደች
ሚካኤል ተገልጦላት
በዘር ፍሬ ባረካት
የእግዚአብሔር መልአክ ስሙ ድንቅ ነው
በኦፍራ አድባር ለጌድዮን የተገለጠው
እስራኤልን ከመድያም እጅ ታደገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ(2)

አንተ ጵኑ ኃያል ሰው
እግዚአብሄር ከአንተ ጋር ነው
ክንድህን ላበረታ
ተልኬያለሁ ከጌታ
ዓይዞህ ጌዴዎን ያለው
ቁርባኑን ያሻተተው
ከእኛ ጋር ነው ሚካኤል
ሰልፋችንን ይመራል
የእግዚአብሔር መልአክ ስሙ ድንቅ ነው
በኦርን አውድማ ሰይፍን ቆሞ የታየው
ዳዊት በመንቀጥቀጥ ፊቱን ፈለገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ(2)

በሶስት ቀን ችነፈር
እንዳትጠፋ ምድር
ሰባ ሺህ ሰዎች ወድቀው
መልአኩን በቃህ አለው
ለምህረት ይመጣሉ
ለመአት ይላካሉ
ሰይፉን በአፎቱ ከቷል
ሚካኤል ለህዝቡ ቆሟል
የእግዚአብሔር መልአክ ስሙ ድንቅ ነው
ስምዖን ጴጥሮስን ከወህይኒ ቤት ገብቶ ያወጣው
የእጆቹን ሰንሰለት ፈቶ አረገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ(2)

በጠባቂዎች መሃል
ኬፋን ከእንቅልፍ አንቅቷል
የተዘጋውን ደጃፍ
አልተሳነውም ማለፍ
ሚካኤል እየመራው
ጴጥሮስ እግሩ የቀናው
አውቆታል ልቡ በርቶ
ዘለለ ስሙን ጠርቶ

ዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረፃዲቅ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ቅዱስ ሚካኤል

ቅዱስ ሚካኤል ወዳጅ ነህ ለሁሉ
ዛሬም ቆመሀል በኪዳንህ ላሉ

አዝ

ክንፍህን ዘርጋ ሚካኤል ቅደም ከፊቴ
ምራኝ መንገዱን እንዳይመሽ ልድረስ ከአባቴ
እንዴት ይገፋል ጎዳናው ያላንተ እርዳታ
ጥሜን ቁረጠው በትርህ ጭንጫውን ምታ
አዝ

ተጠመጠመ ጠላቴ በእሳት ሰንሰለት
የጌታ መልአክ ሚካኤል በሰይፍ ወድቆበት
የለም በቦታው ስመለስ አጥቼዋለሁ
የሚረዳኝን ተሹሞ አይቼዋለሁ
አዝ

ከመቃብሩ ድንጋዩን አንከባለሃል
ስለረዳኸው ዳንኤል እጅግ ወዶሃል
ይነዋወጻል ባሕሩም አንተ ስትመጣ
እግዚአብሔር ይንገስ ዲያብሎስ መድረሻ ይጣ
አዝ

አለኝ ትዝታ በቤትህ ከልጅነቴ
ስትሳሳልኝ እያየሁ ፀንቷል ጉልበቴ
ልዘምር እንጂ ላመስግን ታላቁን ጌታ
አንተን የሰጠኝ ጠባቂ በቀን በማታ

ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አንደበቴም ያውጣ

አንደበቴም ያውጣ የምስጋና ቅኔ
የአምላኬን ማዳን አይቻለሁ በዓይኔ
በገባዖን ሰማይ ፀሐይን ያቆመ
ዛሬም ጎብኝቶኛል እየደጋገመ

አዝ

ወጥመድ ተሰበረ እኔም አመለጥኩኝ
ከኃጢያት ፍላፃ ከሞት አተረፈኝ
የአናብስቱን አፍ በኃይሉ  የዘጋ  
የዳንኤል አምላክ ይኖራል ከእኛጋ
አዝ

በዳዊት ምስጋና በያሬድ ዝማሬ
ከቅዱሳን ጋር ስዘምር አብሬ
እርሱን ሳመሰግን ሜልኮል ብትስቅብኝ
ለጌታዬ ክብር እዘምራለሁኝ
አዝ

አስፈሪው ነበልባል እሳቱ ቢነድም
ለጣኦት እንድሰግድ ነገስታት ቢያውጁም
ሁሉም ቢተወኝም ቢጠላኝም ዓለም
ፅናት ይሆነኛል ጌታ መድሃኔዓለም
አዝ

ወጥመድ ተሰበረ እኔም አመለጥኩኝ
ከኃጢያት ፍላፃ ከሞት አተረፈኝ
የአናብስቱን አፍ በኃይሉ  የዘጋ  
የዳንኤል አምላክ ይኖራል ከእኛጋ

ዘማሪት ፋንቱ ውልዴ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እውነት ነው አዎ እውነት ነው

እውነት ነው አዎ እውነት ነው
መንገድ ነው አዎ መንገድ ነው
ህይወት ነው በእርግጥ ህይወት ነው
ኢየሱስ የጌቶች ጌታ ነው

አዝ

ወደ እግዚአብሔር አብ የምንደርስበት
አንድያ ልጁን የምናምንበት
የህይወት መንገድ እርሱ ብቻ ነው
የባሕርይ አምላክ ብለን ስናምነው
አዝ

በማርያም ስጋ የተገለጠው
ወልድን ስናውቅ ነው አብን ያወቅነው
አብ በእርሱ እንዳለ እርሱም በአብ አለ
በኃይል በሥልጣን የተካከለ
አዝ

ሥጋዉን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ
ህይወት የሰጠን በደልን ክሶ
እኛም ዳሰስነው በላን ጠጣነው
በዝግ ቤት ሳለን ገብቶ ያየነው
አዝ

ፈቅዶ ቢወሰን በአጭር ቁመት
ረቂቁ ቢገዝፍ በጠባብ ደረት
መንሹ በእጁ ነው ሁሉን ያጠራል
በዓለም ሊፈርድ ዳግም ይመጣል

ዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረፃዲቅ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…
Подписаться на канал