ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

1፣5-7 ፍትሕ መን አንቀጽ 4)

- ይህንም ቅዱሳን ሐዋርያት ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳትን በተመለከተ በ3ኛው ቀሌምንጦስ “ኤጲስ ቆጶስ የሀገሩ ሰዎች፣ የሀገሩ ጳጳስ፣ ፈቅደውለት ይሾም፤ ቢገኙ ሦስት፣ ባይገኙ ሁለት፣ ኤጲስ ቆጶሳት ሁነው ይሹሙት” ብለዋል፡፡ ይህም ቅዱስ ሲኖዶስ በሌለበት ሀገር፣ ፓትርያርክ በሌለ ጊዜ ምእመናን እንዳይበተኑ ተብሎ የሚደረግ ነው እንጅ በቅዱስ ፓትርያርኩ ሊቀመንበርነት በመንፈስ ቅዱስ የሚመራውን የቅዱስ ሲኖዶስን ሉዓላዊ ሥልጣን በመጋፋት የሚፈጸም ከሆነ ግን ይህን ቀኖና በሕገወጥ መንገድ ለተፈጸመ ድርጊት መጥቀሱ በቅዱስ ወንጌል ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን በመንፈስ ቅዱስ ላይ የስድብ ቃል እንደመናገር ተቆጥሮ የማይሠረይ ኃጢአት መሆኑ ሊሠመርበት ይገባል፡፡ (ማቴ.12፣30-32 ሉቃስ 12፣10፣ ማርቆስ 3፡28-29 1ኛ ጢሞ 1፣13) የእነዚህ ሰዎች ተግባር በሥራ ላይ ያለውን በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ ሕጋዊ የኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ የመፈንቅል፣ የታላቋን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መዋቅር የመናድ፣ ሕጋዊ ተቋምን የማፍረስ ወይም የመናድ ተግባር በመሆኑ በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዟል፣

- ሠለስቱ ምዕትም ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳትን በተመለከተ በኒቅያ በጻፉት ቀኖና በዘጠነኛው አንቀጽ አንዱም አንዱ ኤጲስ ቆጶስነት ሊሾም ቢሻ፣ የሀገሩ ሰዎች ቢፈቅዱለት፣ የሀገሩ ጳጳስ ካልፈቀደለት ኤጲስ ቆጶስነት መሾም አይገባውም ይህን አፍርሶ ቢገኝ ሲኖዶስ ያወግዘዋል፤ ሹመቱም ይቀራል” ብለዋል፡፡ ይህም በዚህ ወቅት ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጭ የጥንታዊት፣ ሐዋርያዊት፣ ብሔራዊትና ዓለም አቀፋዊት ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲየን ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ ሉዓላዊ ስልጣን በመጋፋት በድፍረት ተፈጸመ የተባለው ሹመት አስቀድሞ በአበው ቅዱሳን የተወገዘ ነው፤

- ከዚህም ጋር ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት በሚፈጸምበት ጊዜ፣ ያለ ቅዱስ ፓትርያርኩ ፈቃድ ማንም ወደ ቤተ መንግሥት እንዲሔድ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን አይፈቅድም፡፡ ይህንንም የተላለፈ ቢኖር ከጳጳሳና ከኤጲስ ቆጶሳት ማንም ማን ሊቀጳጳሳቱ ሳይፈቅድለት ወደ ንጉሥ ቤት አይሒድ ወለኲሉ ዘዐለወ ዘንተ ሲኖዶስ ያወግዞ ይህን ትእዛዝ ያፈረሰውን ሲኖዶስ ያወግዘዋል” ተብሎ ስለተወሰነ ዛሬም ከቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እና ከቅዱስ ፓትርያርኩ ውጭ የሚደረግ ማናቸውም እንቅስቃሴ ሕገወጥ በመሆኑ በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘዋል፤

- በቀኖና ቤተ ክርስቲያን … ሰው ሁሉ ማዕርጉን ጠብቆ ይኑር እንጅ፣ አንዱ ወደ አንዱ ማዕርግ አይተላለፍ፤ ይህን የሠራነውን ሥርዐት ያፈረሰውን ሰው ሲኖዶስ ያወግዘዋል ተብሎ በተጻፈው መሰረት እነዚህ ሕገወጥ አካላት በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘዋል፤

- በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 16 ንዑስ ቁጥር 30 የአጲስ ቀጶሳት መሾም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ፣ በቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት እንዲመረጡና እንዲሾሙ የመወሰን ሥልጣን የቅዱስ ሲኖዶስ መሆኑን የሚደነግገውን ክፍል በግልጽ የጣሰ በመሆኑ፤

- በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 37 ንዑስ ቁ.1 የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ የሚፈጸመው ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ አስፈላጊ መሆኑ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሲታመንበትና ሲወሰን ብቻ እንደሚፈጸምና መደንገጉ፤

- በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 18 ንዑስ ቁጥር 5 የቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖታዊ ሕግጋትንና ቀኖናን የሚያፋልስ ሊቀ ጳጳስ /ኤጲስ ቆጶስ/ ከአባልነት እንደሚሰረዝ በመደንገጉ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዟቸዋል፡፡

በአጠቃላይ የተፈጸመው ሕገ ወጥ ተግባር በሕገ ሰብእም ሆነ በሕገ እግዚአብሔር ሚዛን የተወገዘ ከመሠረተ እምነት የተለየ፣ በአበው ቀኖና፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያን እና በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር በአጠቃላይ ተቀባይት የሌለው ነው፡፡ ስለዚህ

1ኛ. በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 138 መሠረት ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሶዶ ዳጩ ወረዳ ሐሮ ባለወልድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ
1ኛ. አባ ሳዊሮስ
2ኛ. አባ ኤዎስጣቴዎስ
3ኛ. አባ ዜና ማርቆስ የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በመጣስ ባልተሰጣቸው ስልጣን 26 ኤጴስ ቆጰሳትን ሾመናል፤ ሲኖዶስ አቋቁመናል በማለት በማኅህበራዊ እና በብሮድካስት ሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ የተረጋገጠ በመሆኑ በዚሁ ድርጊታቸው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለም የሚኖረውን ሕዝበ ክርስቲያንን በማታለል የክህደት እና የኑፋቄ ተግባር በመፈጸማቸው በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ፤ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸውን ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት በመሻር አውግዞ ለይቷቸዋል፡፡

በመሆኑም፡-
ሀ. ሥልጣነ ክህነታቸውና የማዕረግ ስማቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ውሳኔ የተነሣ ስለሆነ ከዛሬ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በቀድሞ ዓለማዊ ስማቸው እንዲጠሩ፤
ለ. በቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ አገልግሎት ዙርያም በሕይወትም ሆነ በሞት ማናቸውንም መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳያገኙ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ ከቤተ ክርስቲያን ለይቷቸዋል፡፡
ሐ. በነዚህ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ አውግዞ በለያቸው ግለሰቦች ይመሯቸው በነበሩ አህጉረ ስብከት መንፈሳዊ አገልግሎት በማከናወን ሀገረ ስብከቱን የሚመሩ ብፁዐን አባቶችን
• ለደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት
• ለኬንያ፤ኡጋንዳ፤ታንዛኒያ እና ሩዋንዳ ሀገረ ስብከት
• ለኢሉ አባቦራ እና በኖ በደሌ ሀገረ ስብከት
• በሰሜን አሜሪካ ለሜኒሶታ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት
• ለጉጂ፤ ምዕራብ ጉጂ እና ቦረና ሊበን ዞኖች ሀገረ ስብከት
• ለምስካዬ ኅዙናን መድኃኒዓለም ገዳም
በአባትነት የሚመሩ አበው ሊቃነ ጳጳሳት እንዲመደቡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ወስኗል፡፡
ይሁን እንጅ ከላይ በስም ተጠቅሰው የተወገዙት ግለሰቦች በሠሩት የቀኖና ጥሰት ተጸጽው ይቅርታን ቢጠይቁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምህረት ደጆች ሁል ጊዜ ክፈት መሆናቸውና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት የምንቀበላቸው መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳውቃል፤

2. የቅዱስ ሲኖዶሱንና የቤተ ክርስቲያኒቱን ልዕልና በመዳፈር እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ በተነሳሱ ግለሰቦች አማካኝነት የኤጲስ ቆጶስነት ሺመት አግኝተናል፤ ተሸመናል እያሉ የሚገኙ 25 መነኰሳት በሕገ ወጥ መንገድ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንንን ጥሰው የተገኙ በመሆኑ አስቀድሞ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸው ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት ተሽሮ ከዛሬ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ተወግዘው ከቤተ ክርስቲያን ተለይተዋል፡፡

3. ከነዚሁ ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆኑት አባ ጸጋዘአብ አዱኛን ከቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዐተ ጉባኤ ስብሰባ በፊት የቀኖና ጥሰቱንና ሕገ ወጥ አድራጎቱን በመረዳትና በመጸጸት ድርጊቱን በመቃወም ለቤተ ክርስቲያኒቱ ባቀረቡት የይቅርታ አቤቱታ መሠረት ቅዱስ ሲኖዶሱ ይቅርታውን የተቀበላቸው ሲሆን እንደሳቸው ሁሉ ከላይ የተወገዙት 25 ግለሰቦች በሠሩት የቀኖና ጥሰት ተጸጽው ይቅርታን ቢጠይቁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምህረት ደጆች ሁል ጊዜ ክፈት መሆናቸውና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት የምንቀበላቸው መሆኑን እንገልጻለን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ኦ ፍጡነ ረድኤት እምሩጸተ ነፋስ ወዓውሎ
ለዘይጼውዐከ በተወክሎ
ጊዮርጊስ ቅረብ ለምሕረት ወለተሣህሎ
ተወከፍ ወትረ ጸሎትየ ወቃለ ጽራኅየ ኵሎ
እስመ ልበ አምላከ ርኅሩኅ በኀቤከ ሐሎ

ለቤሩታዊት የደረሰ
ሰማቱ ጊወርጊስ ገሰገሰ
ፈጥኖ ሊወጣኝ ከመከራ
ቆሟል ከጎኔ ከእኔ ጋራ/፪/
#አዝ
ሥጋው ሲመተር አልፈራም እርሱ
ሠባት አክሊላት ጭኗል በራሱ
በደብረ ይድራስ በዛ ተራራ
የልዳው ጸሐይ ተብሎ ተጠራ
#አዝ
ዓለምን ስትዞር በነጭ ፈረስ
አንድግዜ እርዳኝ ጊዮርጊስ ድረስ
ሥሙን ለጠራ አምላከ ጊዮርጊስ
ሲደርስ ይፈጥናል ከዓውሎ ንፍስ
#አዝ
ለእሣት ለግለት ሥጋውን ሲሰጥ
ፍርሐት የለበት ወይም መደንገጥ
ኡዲያኖስ አፍሮ ጣዖት ወደቀ
በጊዮርጊስ ጽናት ጌታ ታወቀ
#አዝ
ከሹመት ይልቅ መርጠኽ መከራ
ወንጌሉን ሰበክ አንዳች ሳትፈራ
በጭንቀት ሆነ የአንተ ንግሥና
ብድራትኽን አይተሃልና
#አዝ
መስተጋድል ነኽ ሐያል ገናና
መክብበ ሠማያት የዕምነት ጀግና
ሥምኽን ስጠራ ከቤትኽ ቆሜ
ይቀልልኛል የሐጢዓት ሸክሜ።

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን፡፡ ✞

✞ ጥር 18 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞

#ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ልዳዊ

መጽሐፈ ገድሉ እንደሚለው የሰማዕታት አለቃቸው: አንድም ሞገሳቸው ታላቅና ክቡር ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ7 ዓመታት ስቃይ በኋላ ተሰይፏል:: ይህስ ጥንተ ነገሩ እንደምን ነው ቢሉ:-

+ቅዱሱ የተወለደው ከአባቱ ዘረንቶስ (አንስጣስዮስ) እና ከእናቱ ቴዎብስታ የድሮው ፋርስ ግዛት ፍልስጥኤም (ልዳ) ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቹ ክርስትናን ጠንቅቀው አስተምረውት አባቱ ይሞታል::

+ቅዱስ ጊዮርጊስ 20 ዓመት ሲሞላው የአባቱን ስልጣን እጅ ለማድረግ ሲሔድ የቢሩት (የአሁኗ ቤይሩት-ሊባኖስ) ሰዎች ዘንዶ/ደራጎን ሲያመልኩ አገኛቸው:: እርሱ ግን የከተማውን ሕዝብ አስተምሮ: አሳምኖ: ደራጎኑንም በፈጣሪው ኃይል ገድሎ መንገዱን ቀጥሏል::

+ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ዱድያኖስና 70 ነገሥታት ዘንድ ሲደርስ ክርስቶስ ተክዶ ለጣዖት ይሠገድ ነበር:: በዚያች ሰዓት ድንግል እመቤታችን ወደ ሰማዕቱ መጥታ መከራውንና ክብሩን ነገረችው:: እርሱም በክርስቶስ ስም መሞት ምርጫው ነበርና ከእመቤታችን ተባርኮ ወደ ምስክርነት አደባባይ (ዐውደ ስምዕ) ደረሰ::

+ከዚያም ለተከታታይ 7 ዓመታት ብዙ ጸዋትወ መከራዎችን ተቀበለ:: 3 ጊዜ ሙቶ ተነሳ:: ከሰው ልጅ የተፈጥሮ ትዕግስት በላይ የሆነ ስቃይን ስለ ቀናች ሃይማኖት ሲል በመቀበሉ የሰማዕታት አለቃቸው: ፀሐይና የንጋት ኮከብ በሚል ይጠራል::
"ተውላጠ ጻማሁ ወሕማሙ:
ዘተለዐለ ሞገሰ ስሙ" እንዲል መጽሐፍ::

+ከ7 ዓመታት መከራ በኋላም ከብዙ ተዓምራት ጋር ተሰይፎ ደም: ውሃና ወተት ከአንገቱ ፈሷል:: 7 አክሊላትም ወርደውለታል::

+" #ዝርወተ_ዓጽሙ "+

+ይህቺ ዕለት ለሰማዕቱ 'ዝርወተ አጽሙ' ትባላለች:: በቁሙ 'አጥንቱ የተበተነበት' እንደ ማለት ነው:: ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዘመናት በብዙ ስቃያት ሲያስጨንቁት ኖረው በጽናቱ አሸነፋቸው:: 70 ነገሥታትን ከነ ሠራዊታቸው ከማሳፈሩ
ባሻገርም በርካታ (በመቶ ሺ የሚቆጠሩ) አሕዛብን ማርኮ ለሰማዕትነት አበቃ::

+በዚህ የተበሳጨ ዱድያኖስም ኮከበ ፋርስ ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲቆራርጡት አዘዘ:: ወታደሮቹም ቅዱሱን ቆራርጠው: በብረት ምጣድ ላይ ጠበሱት:: ያለ ርሕራሔም አካሉን አሳረሩት:: ቀጥለውም ፈጭተው አመድ አደረጉት::

+በአካባቢው ወደ ነበረው ትልቅ ተራራ ጫፍ (ደብረ ይድራስ) ወጥተውም በነፋስ በተኑት::
"ሐረድዎ ወገመድዎ: ወዘረዉ ሥጋሁ ከመ ዓመድ" እንዲል:: (ምቅናይ)

+እነርሱ ይህንን ፈጽመው ዘወር ሲሉ ግን የቅዱሱ ዓጽም ባረፈባቸው ዛፎች: ቅጠሎችና ድንጋዮች ሁሉ "ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት" የሚል ጽሑፍ ተገኘ:: ስለዚህም ይህቺ ዕለት ቅዱሱ አለቅነትን የተሾመባት ናት ማለት ነው::

+ወዲያው ግን ኃያል ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተበተነበት ተነስቶ ወታደሮችን አገኛቸውና "በክርስቶስ እመኑ" ብሎ: አስደንቆ ወደ ሕይወት መራቸው:: 70ው ነገሥታት ግን አፈሩ::

#ቅዱስ_ባኮስ_ጃንደረባው

+'ጃንደረባ' የሚለው ቃል በግዕዙ 'ሕጽው' ተብሏል:: ይህ ስም በቤተ ክርስቲያን የተለመደ እንጂ እንግዳ አይደለም:: መድኃኒታችን እንዳለው በተፈጥሮ የሆኑ: ሰዎች እንዲያ ያደረጉዋቸውና ራሳቸውን ስለ ጽድቅ ጃንደረባ ያደረጉ ብዙዎች ናቸውና::

+ኢትዮዽያዊው ጃንደረባ ቅዱስ ባኮስም (አንዳንዴ አቤላክ / አቤሜሌክም ይባላል):-

- በ1ኛው መቶ ክ/ዘመን በሃገራችን ኢትዮዽያ ተወልዶ ያደገ
- ነገሥታቱንና ሃገሩን በሙያው ያገለገለ
በተለይ ከ34 እስከ 46 ዓ/ም ለነገሠችው ንግሥት ሕንደኬ ገርስሞት በገንዘብ ሚንስትርነት ያገለገለ
- በገንዘቧ ላይ ሁሉ አዛዥ (ታማኝ) የነበረ
- ጃንደረባ በመሆኑ ለንግሥቲቱና ቤተሰቧ ቅርብ የነበረ
- መጻሕፍትን የሚያነብና የሚመረምር
- ዘወትር ወደ ኢየሩሳሌም እየሔደ ከቅዱሳት መካናት የሚሳለም በጐ ሰው ነበር::

+በግብረ ሐዋርያት ምዕ. 8:26 ላይ እንደ ተጠቀሰው ቅዱሱ ከኢየሩሳሌም ለፋሲካና ለእሸት በዓል ነበር የሔደው:: ሲመለስ መንፈስ ቅዱስ ከፊልዾስ ጋር በጋዛ አገናኝቶታል:: በዚያም ምሥጢረ ክርስትናን ተምሮ: በክርስቶስ አምላክነትና አዳኝነት አምኖ ተጠምቁዋል::

+ክርስትናን ለኢትዮዽያ በ34 ዓ/ም አምጥቷል:: "ጃንደረባው ለወገኖቹ ሐዋርያ ሆነ" ሲል ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንደ ተናገረው ወደ ሃገራችን ተመልሶ: ስለ ክርስቶስ ሰብኮ በርካቶችን አሳምኗል::

+ቀጥሎም ሃብቱን ንቆ (መንኖ): ከኢትዮዽያ እስከ ሕንድ ወንጌልን ሰብኮ በዚህች ዕለት በሰማዕትነት ዐርፏል። (ተሰውሯል የሚሉም አሉ)

<< በእውነት ለቅዱስ ባኮስ ክብር ይገባል:: >>

ዝክረ ቅዱሳን
ወስብሐት ለእግዚአብሄር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሰበር ዜና

ከቀኖናና ከህግ ውጪ በተደረገው ሲመት ከተሾሙት መካከል አባ ጸጋዘአብ አዱኛ በዚህ ሰዓት ቤተክርስቲያንን ይቅርታ ለመጠየቅ ቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ተገኝተው ለብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር የይቅርታ ደብዳቤ አስገብተዋል።

በደብዳቤአቸውም ያሳደገቻቸውን፣ ያስተማረቻቸውንና ለዚህ ክብር ያበቃቻቸውን ቤተክርስቲያን ማሳዘናቸውን ገልጸው ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።

ምንጭ የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የእስክንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ አባ ቶማስ የቂሊያ ሜትፖሊታን እና የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ።

ምንጭ: EOTC TV

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን መብትና ክብር አስጠባቂ ኅብረት ወቅታዊ መግለጫ

“ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት፤ቅድስት በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን”
ጸሎተ ሃይማኖት

ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተፈጸመውን ከሕገ ቤተ ክርስቲያን የወጣ እና ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ያፈነገጠ "ሲመተ ጵጵስና" በቀጥታ በቤተ ክርስቲያን ህልውና ላይ የተቃጣና ቅዱስ ሲኖዶስንም ሆነ መንበረ ፕትርክናውን በመገዳደር ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ የተሰነዘረ ጥቃት አድርገን እንደምንወስደው ለመግለጽ እንወዳለን፤

ስለሆነም፡
አሁን ላይ የተፈጠረው ችግር ሊፈታ የሚገባው የቤተ ክርስቲያንን ሕግና ሥርዓት በመከተል እንደመሆኑ መጠን ለጉዳዩ ባለቤት ለቤተ ክርስቲያን ብቻ መተው አግባብ መሆኑን እየገለጽን መንግሥት ሰላምና ጸጥታ የማስከበር ኀላፊነቱን እንዲወጣ አበክረን እናሳስባለን። የመንግሥት ኀላፊነቱን በአግባቡ አለመወጣት የችግሩ ፈጣሪና መሪ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሁነኛ ማስረጃ ነው። ይህን ኀላፊነቱን ባልተወጣ መጠን ችግሩ ሀገርን ሊያፈርስና ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመታት ወደ ነበርንበት አገራዊ ቀውስ ውስጥ ሊያስገባን የሚችል መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሰበር ዜና

"
መንግሥት ቤተ ክርስቲያንና አባቶችን የመጠበቅ ኃላፊነቱን ካልተወጣ ልጆቻቸው ለመጠበቅ ተዘጋጅተናል፤ በቂ ዝግጅትም አድርገናል።"

የመንፈሳዊ ማኅበራትና የኅብረቶች የጋራ መግለጫ

ዛሬ ጥር 16 ምሽት ማኅበረ ቅዱሳን፣ አገር አቀፍ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ኅብረት፣ ምእመናን ኅብረት ፣ ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን ክብርና መብት አስጠባቂ ኅብረት፣ የወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት በጋራ በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫውም የማኅበራቱ ተወካዮች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ካጋጠማት ታሪካዊ ክስተት አንጻር  ከመቼውም ጊዜ በላይ የቤተ ክርስቲያንን ክብርና ልዕልና የምናስጠብቅበት እና ከአባቶቻችን ጎን የምንቆምበት ወቅት በመሆኑ በኅብረት መክረን አቅጣጫዎችን አስቀምጠናል ብለዋል።

ማኅበረ ቅዱሳንን ወክለው የተገኙት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ሙሉጌታ ሥዩም በመግለጫው እንደተናገሩት የቅዱስ ሲኖዶስን ልዕልና ያቃለለ የነገ የሐዋርያዊ አገልግሎትን ያሰናከለ በመሆኑ አባቶቻችን ይህንን ያማከለ ውስኔ እንዲወስኑ እንጠይቃለን ሲሉ ገልጸዋል። አክለውም መንግሥት እጁን ከዚህ ሂደት እንዲያነሳ ይልቁንም የእሱ ግዴታ የሆነውን ጥበቃ እንዳያነሳ ይህ ካልሆነ ግን ኦርቶዶክሳውያን ቤተ ክርስቲያን እስከሰማእትነት ለመታደግ የታመኑ ናቸው ብለዋል። ምእመናንም ሳይደናገጡ በጸሎት እንዲተጉ እና ተመሳሳይ ግንዛቤ እንዲኖራቸውም ጥሪ አስተላልፈዋል።

ከመንግሥት ጋርም በቀጣይ ችግሩን እንዲረዳና ቤተ ክርስቲያን የራሷን ችግር በራሷ እንድትፈታ እድል እንዲሰጣት መወያየታቸውን በመግለጽ የዜጎችን ደህንነት ካልጠበቀ ግን ከተጠያቂነት አይድንም ሲሉ ገልጸዋል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የተለያዩ ቦታዎች የመንግስት የፀጥታ ሐይሎች ያደርጉ የነበረውን ጥበቃ ባልታወቀ ሁኔታ አቁመዋል!

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

"የኖላዊነት ኃላፊነታችሁን የዘነጋችሁ ወንድሞቻችን እና ሌሎችም ሰዓቱ ከማለቁ አስቀድሞ ወደ ልባችሁ በመመለስ ወደ ቀድሞው ማንነታችሁ ተመለሱ" ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ አሳሰቡ።

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የበላይ ጠበቂ በትናንትናው ዕለት በተፈፀመው ኢ-ቀኖናዊ "ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳትን" አስመልክቶ በይፋዊ የፌስቡክ ገጻቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

እውነት እውነት እላችኋለሁ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው (ዮሐ.10፥1)በሚል የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መልዕክታቸውን የጀመሩት ብፁዕነታቸው በትናንትናው ዕለት በወሊሶ በተፈጸአው ኢ-ቀኖናዊ "ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት" ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በእጅጉ አዝናለች ብለዋል።

መከራና ፈተና ከቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ተለይተው የማያውቁ ቢሆንም ካለን መከራንና ችግርን የማለፍ ልምድ በመማር ይህንን አስቸጋሪ እና ፈታኝ ወቅት በጥበብ እና ብስለት በተመላበት አኳኋን ልናሳልፈው ይገባል ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ
አሳስበዋል።

ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ብዙ መናገር ቢቻልም ያለንበት ወቅት ይህንን ለመናገር ጊዜው ባለመሆኑ ምዕመናን ልጆቻችን ሁሉ ለቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አፈጻጸም ራሳችሁን ዝግጁ በማድረግ ፤ መንፈስ ቅዱስ እና ቅዱስ ሲኖዶስ የሚወስኑትን ውሳኔ በትዕግስት እንድትጠብቁ እናሳስባለን ብለዋል።

ብፁዕነታቸው በዚህ ስህተት ውስጥ የገባችሁ የኖላዊነት ኃላፊነታችሁን የዘነጋችሁ ወንድሞቻችን እና ሌሎችም ሰዓቱ ከማለቁ አስቀድሞ ወደ ልባችሁ ተመልሳችሁ ወደ ቀድሞው ማንነታችሁ ትመለሱ ዘንድ ጸሎታችን መሆኑን እንገልጻለን ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ሲል የዘገበው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ነው።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በአዲስ አበባ የሚገኘውን የ"አባ" ሳዊሮስ ፣ የ"አባ" ኤዎስጣቴዎስን እና የ"አባ" ዜና ማርቆስን ማረፊያ ቤት አሸገ፡፡

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በአዲስ አበባ የሚገኘውን የ"አባ" ሳዊሮስ፣ የ"አባ" ኤዎስጣቴዎስን እና የ"አባ" ዜና ማርቆስን ማረፊያ ቤት መታሸጉን ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል በፌስቡክ ገጽ አስነብቧል።

በትናንትናው ዕለት 3ቱ አባቶች ሕገ ቤተ ክርስቲያንን እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ለመናድ እና ሲኖዶሳዊ አንድነትን ለመከፋፈል በማቀድ 26 መነኮሳትን ሾመናል በማለት መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ትላንት በተመለከትነው አስነዋሪ እና ሥርዐተቢስነት የተሞላበት ጉባኤ /ጉባኤ ከለባት/ የመንግስት እጅ እንዳለበት ግልጽ ነው። በቅርቡ በሌሎች እምነቶች የሰራውን የመከፋፈል ሴራ በኦርቶዶክስ ላይ ሊሳካ እንደማይችል ማወቅ ይኖርበታል።

ይህ ንግግር ዝግጅቱ በሃይማኖታዊ የመንግሥት ኔትዎረክ ውስጥ መረጃ እንደነበረ ይጠቁማል። ከሳምንት በፊት ቤተክርስቲያንን ለማዘናጋት ይቅርታ እንጠይቃለን ሲሉ የነበሩና አንዲጠይቁ የላኳቸው አካላት ለዚህ ሤራ እየተዘጋጁ ነበር ማለት ነው። የማስመሰል ጭምብል ወልቋል።

ጉዳዩ ከአሁን በኋላ የእውነተኛ ክርስቲያኖችና አባቶች፣ አንዲሁም ዋናው የአግዚአብሔር ነው። ቁማርተኞቹ በእምነትም በኩል እንዲህ ያሉ ጎበዝ ተጫዋቾች ናቸው።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በጉባኤ ከለባት በህገወጡ ቡድን ከተሾሙት የስልጣን ጥመኞች ዝርዝር መካከል 👇👇የሚገኙበት

1. አባ ተክለ ሃይማኖት ።።።።።።። የቀድሞ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ

2. አባ ገብረ እግዚአብሔር ።።።።።። የአየር ጤና ኪዳነ ምሕረት አስተዳዳሪ

3. አባ ሽኖዳ ።።።።።።።።። አለም ገና ኢየሱስ አስተዳዳሪ

4. አባ ወልደ ጊዮርጊስ ።።።።።።። ወለቴ ዮሐንስ አስተዳዳሪ

5. አባ ገብረ ኢየሱስ ።።።።።። አለም ገና ሚካኤል አስተዳዳሪ

6. አባ ገብረማርያም ነጋሳ ።።።።። የኦሮምያ ቤተ ክህነት መስራች

7. አባ ጳውሎስ ከበደ ።።።።። የሐረር ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የነበረና በተሐድሶነት የተባረረ

8. አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ ።።።።።።። የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መጽሐፍ መምህር

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መግለጫ ተሰጠ ።

መግለጫውን ለኢኦተቤ ቴቪ (EOTC TV) የሠጡት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፖትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት; ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ : በመንበረ ፓትርያርክ የተገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው።

ቅዱስነታቸው ዛሬ ማለዳ በተሰማው ሕገ ወጥ "ሢመተ ጳጳሳት" ጉዳይ በሰጡት መግለጫ ጉዳዩ ከቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ውጪ በሕገወጥነት የተከናወነ መሆኑን በመግለጽ :-
1. በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ ሊቃነ ጳጳሳት በአስቸኳይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ እንዲመጡ ጥሪ ቀርቧል።
2. መንግሥት ክስተቱ በሀገር ላይ ጭምር የሚያስከትለውን ጉዳት ተመልክቶ በጉዳዩ ላይ ሕጋዊ ሓላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።
3. ምዕመናን ቤተክርስቲያንን ከመቸውም ጊዜ በላይ በንቃት በሀሣብና በጸሎት እንዲጠብቁ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ: EOTC TV

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እጅግ አሳዛኝ ዜና!

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የምስካየኅዙናን መድኃኒአለም ገዳም የበላይ ጠባቂ በዛሬው ዕለት እራሳቸውን ፓትሪያርክ በማድረግ 25 ኤጲስ ቆጶሳትን ሾመዋል!!!

በዛሬው ዕለት በወሊሶ መድኃኒአለም ቤተክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እራሳቸውን ፓትሪያርክ በማድረግ ለስልጣን ጥማት ያደረባቸውን 25 ኤጲስ ቆጶሳት አድርገው ሾመዋል።

ከአንድ የቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ የማይጠበቅ እና ህገ ቤተክርስቲያንን የሚፃረር ድርጊት ይፈፅማሉ ብለን የማንጠብቃቸው አቡነ ሳዊሮስ ይሄንን አድርገዋል።

ቤተክርስቲያኒቷ በራሷ ስርዓት እና ህግ የምትገዛ ሆኖም ሲኖዶሳዊት የሆነችውን ይቺ ሀገር የሆነችውን ቤተክርስቲያን ብትንትኗን ለማውጣት ይሄን ያህል መንገድ መራመዳቸው እጅግ የሚያሳዝን ተግባር ነው።

በአስቸኳይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለምመናኗ መፍትሔ ሊሰጥ እንደሚገባ በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን ።

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​#ቃና_ዘገሊላ

በዛሬው ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከሐዋርያቱ ጋር የገሊላ ክፍል በሆነችው በቃና በሰርግ ቤት ተገኝቶ ውሃውን ወይን ጠጅ ያደረገበት ነው። ሰርግ ደግሶ የነበረው ዶኪማስ አዘጋጅቶት የነበረው ወይን ጠጅ አልቆ በተጨነቀ ጊዜ ችግሩን ቀርቦ ሳይነግራት ማለቁን አውቃ ልጄ ሆይ ወይን ጠጅ እኮ አልቆባቸዋል በማለት ተናግራ ውሃው ወደ ወይን ጠጅ እንዲለወጥ የማማለድ ተግባር የፈጸመችበት ዕለት ነው።

አምላካችን ጋብቻ ክቡር መሆኑን ዓለም እንዲረዳ ያደረገበት፣ ሰዎች ያዘጋጁት ነገር ተንጠፍጥፎ አልቆ በተጨነቁ ጊዜ እመቤታችን ለልጇ አሳስባ ጎደሏቸው እንዲሞላ ፣ጭንቀታቸው እንዲወገድ የምታደርግበት በዓል ነው።

ጥንቱ ዕለቱ የካቲት 23 ቀን ቢሆንም ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የውሃን በዓል ከውሃ በዓል ጋር ማክበር ይገባል ብለው የሚጠጡት አልቆባቸው ተጨንቀው የነበሩበት ቃና ዘገሊላ የውሃ በዓል በመሆኑ ከውሃ በዓል ከሆነውና የእዳ ደብዳቤያችን ከተደመሰሰበት ከጥምቀት ጋር እንዲከበር በማድረጋቸው በዛሬው ዕለት እናከብረዋለን።

ዛሬ የዶኪማስ ጭንቀት ብቻ ሳይሆን በጋብቻ ምክንያት የሚከሠት የክርስቲያኖች ሁሉ ጭንቀት የተቃለልበት ዕለት ነው። እመቤታችን ዶኪማስ ሳይለምናት ጭንቀቱን እንዳቃለለችለት ለልጅሽ አሳስቢልን ብለን ብንማጸናት የማይፈጸምልን ነገር፣ የማይወገድልን ጭንቀት አለመሆኑን የተረዳበት ዕለት ነው። በዓሉን ማክበር የሚገባንም ይህን እያሰብን ነው። አምላካችን ከበዓሉ በረከት ይክፈለን።

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በፍትሕ መንፈሳዊ እንዲሁም በሕገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ 19 ንዑስ ቁጥር 3 አስቸኳይና ድንገተኛ ጉዳይ ሲያጋጥም ምልዓተ ጉባኤ እንደሚያደርግ በተደነገገው መሠረት ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያኒቷ ላይ በተፈጠረው ወቅታዊ የሃይማኖት፣ የቀኖና እና የአስተዳደራዊ ጥሰቶችን አስመልክቶ ውሳኔዎች አሳልፏል፡፡

ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊትና ዓለም አቀፋዊት የሆነች ቅድስት ቤተክርስቲያን ሕዝብና አሕዛብን፣ ሰውና መላእክትን፣ ፍጡራን እና ፈጣሪን ይልቁንም በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን ልዩነት አጥፍቶ የሰው ልጅ ሁሉ በቋንቋ፣ በቀለምና በጐሣ ሳይከፋፈሉ በአንድነት ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትና አግኝተው ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማህፀነ ዮርዳኖስ የተወለዱ በማየ ገቦ የተጠመቁ የቤተ ክርስቲያን ልጆች እንዲሆኑ ልዩነት የሌለባትን ዘለዓለማዊት መንግሥተ እግዚአብሔር እንዲወርሱ በደመ ክርስቶስ የተመሠረተች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ የተነሣባትን ፈተና ሁሉ አልፋ ከእኛ ዘመን ደርሳለች፤

ምንም እንኳ ከቅዱሳት መጻሕፍትም ሆነ ከኦርቶዶክስ ትምህርተ ሃይማኖት ፈጽሞ በተለየ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያንን በጐሣና በቋንቋ የመለየት ሂደት በዓለም አቀፍ ደረጃ እንግዳ ክስተት ቢሆንም ቤተ ክርስቲየን ከሃይማኖታዊና መንፈሳዊ ጠባይዋ በተለየ፣ ታሪኳንና ሥርዓቷን በማይመጥን፣ ከሕግ መንፈሳዊ፣ ከሕግ ጠባይአዊ እና ከሕገ አእምሮ በወጣ መልኩ የደረሰባት ጥቃት፣ እና የመፈንቅለ ሲኖዶስን ተግባር ቅዱስ ሲኖዶስን እጅግ አሳዝኖታል፤

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ ውስጥ ለሀገር አንድነት፣ ለፍትሕ፣ ለጥበብ፣ ለሕዝብ ትስስር፣ ለማኅበራዊ ዕድገት፣ ለጤና፣ ለሥነ-ምግባር መሠረት እና ዐምድ፤ ምሰሶ እና ማገር ሆና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተፈራች፣ የተከበረች እና የተወደደች፤ ዕሴቷ እና ዕምቅ የዕውቀት ሀብቷ በምሁራን የታወቀ፣ በትምህርተ ዓለም ሳይቀር የተቀረጸ፤ በእውነተኛ ሊቃውንት የተመሠከረ፣ ቅርሶቿ የተመዘገቡላት ስትሆን፤

በቅርቡ ራስዋ በሾመቻቸው በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ከፍተኛውና ሐዋርያዊ ተልእኮ እንዲወጡ አደራ በተሰጣቸው ሊቃነ ጳጳሳት መሠረተ እምነትን፣ ሃይማኖታዊ ቀኖናን፣ የአስተዳደር ሥርዓት ሁሉ በጣሰ፣ መንገድ በማኅበረሰብ ዕድገትና አስተዳደር ውስጥ ከሕዝብ ጋር የቆመች፣ ከፖለቲካ የጸዳች መንፈሳዊና ሕዝባዊት ተቋምነቷን በመካድ ከፍተኛ የሆነ ሕገ ወጥ ድርጊት፣ ተቋምን የመናድና መዋቅሯን የማፍረስ ተግባር ተከናውኗል፡-

በዚሁ መሠረት፡-
ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሶዶ ዳጡ ወረዳ ከወሊሶ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው አሮ ባለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጸመውን እጅግ አሳዛኝ እና ኢ-ሲኖዶሳዊ የሆነ አስነዋሪ፤ ሕገ ወጥ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት አስመልከቶ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት አስቸኳይ የምልዐተ ጉባዔ አድርጓል፤

ቅዱስ ሲኖዶስም በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ያሉ መላው አህጉረ ስብከት፤ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባዔ፣ የሊቃውንተ ጉባኤ፤ የሕግ አገልግሎት መምሪያ፤ በዓለም አቀፍና ሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ የወጣቶች እና የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት፣ መንፈሳውያን ማኅበራት፤ የምእመናን እና አገልጋዮች ኅብረት፣ ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን በደብዳቤ፣ በሚዲያ እና በአካል ከሰጡት ምክረ ሐሳብ እና የአቋም መግለጫ በመነሣት፤

በሀገር ውስጥ እና በውጪው ዓለም የሚገኙ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ወዳጆች፣ በተለይም የግብጽ እስክንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶከስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕጋዊ ፓትርያርክ ውጭ የሚደረግ ሢመትን እንደማይቀበሉና ዕውቅና እንደማይሰጡ በላኩት የአቋም መግለጫ፣ የኤርትራ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶከስ ቤተ ክርስቲያን፣ እና የሌሎች አኀት ኦርቶዶከስ አብያተ ክርስያናት፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት፣ ዓለም አቀፍ መንፈሳዉያን ተቋማት፣ የልማት እና የበጎ አድርጎት አጋር ድርጅቶች፤ ድርጊቱን በማውገዝ የማይቀበሉት መሆኑን የአቋም መግለጫ በመላክ ባሳዩት አጋርነት፤

አስቀድሞ እንደተገለጸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በደመ ክርስቶስ ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ ያለፈተና የኖረችበት ጊዜ እንደሌለ ቅዱሳት መጻሕፍትና የታሪክ መዛግብት ሲመሰክሩ በዘመነ ሐዋርያት ቢጽ ሐሳውያን፣ በዘመነ ሊቃውንት የተለያዩ መናፍቃን፣… በየጊዜው እየተነሡ ሲፈታተኗት ኑረዋል፡፡ አሁንም በግልጽ እንደሚታየው ከውጭም ከውስጥም በተደራጁ ምንደኞች በመፈተን ላይ ትገኛለች፡፡

ለዚህም ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም. በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት፣ በሶዶ ዳጩ ወረዳ፣ ሀሮ በዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአባ ሳዊሮስ መሪነት እጅግ አሳዛኝ ኢ-ሲኖዶሳዊ የሆነ አስነዋሪ፣ ሕገ-ወጥ፣ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት አንዱ ሲሆን፤ በአባ ሳዊሮስ መሪነት የተፈጸመው የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት ፳፮ መነኰሳትን ከቀኖና የወጣ ሢመት በመስጠትና ሊቃነ ጳጳሳት በሚመሯቸው አህጉረ ስብከት በሕገ ወጥ መንገድ በመመደብ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት አልፎ ሃይማኖትን የሚከፋፍል፤ የሀገር አንድነትን የሚሸረሽር እና የሚያፈርስ፣ ምእመናንን ከምእመናን፣ ካህናትን ከካህናት፣ ሊቃውንትን ከሊቃውንት ወጣትን ከወጣት … የሚያጋጭና ደም የሚያፋስስ ፀጥታን የሚያናጋ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ተገንዝሟል፤ በመሆኑም፤

- ከላይ እንደተገለጸው ሐዋርያት በሦስተኛው ቀሌምንጦስ በሃያ አምስተኛው አንቀጽ “በአውራጃው ሁሉ ያሉ ኤጲስ ቆጶሳት አለቃቸው ማንም እንደሆነ ማወቅ ይገባቸዋል፡፡ አለቃ ያድርጉት፤ ያለ ፍቃዱ ጥቃቅኑንም ደጋጉንም ሥራ ምንም ምን አይሥሩ፤ እርሱም ዳግመኛ ኤጲስ ቆጶሳቱ ሳይፈቅዱ ደጋጉን ሥራ አይሥራ ጥቃቅኑን ቢሠራ እዳ የለበትም፡፡ ሁሉም እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ፣ ሁነው በአንድነት ይኑሩ” ብለው ወስነዋል፡፡ እነዚህ ሕገ ወጥ አካላት ይህን የሐዋርያት ቀኖናን በመሻራቸው፡፡

- ሁለተኛም በአርባ አራተኛው አንቀጽ “ሊቀጳጳሳት (ፓትርያርክ) ኤጲስ ቆጶሳት በተሾሙባቸው አገሮች የሚሠሩትን ሥራ፣ የሚያዙትን ትእዛዝ ይመርምር፡፡ የማይገባ ሥራ ሠርተው፣ የማይገባ ትእዛዝ አዝዘው፣ ቢያኝ ለውጦ የተገለጸለትን ትእዛዝ ይዘዝ፡፡ እርሱ ለሁሉ የሹመት አባታቸው ነውና፤ እነሱም ልጆቹ ናቸውና…” ብለዋል፡፡ ይህን ኢ-ቀኖናዊ ሥርዐተ ሲመት የፈጸሙት ግለሰቦች በሕገወጥ መንገድ በአደባባይ የቅዱስ ሲኖዶስን ሉዓላዊ ሥልጣን እና የቅዱስ ፓትርያርኩን መብት በመጣሳቸው፡፡

- ሢመተ ክህነትን በተመለከተ “ወአልቦ ዘይነሥእ ክብረ ለርእሱ ዘእንበለ ዘጸውዖ እግዚአብሔር … እንደ አሮን በእግዚአብሔር ከተጠራ በቀር ማንም ለራሱ ክብርን የሚወስድ የለም” (ዕብ 5፤4) እንደሚለው የእግዚአበሔር ቃል ከዲቁና ጀምሮ እስከ ፓትርያርክ ሹመት ድረስ ያለው ሹመት በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር መጠራቱን የሚጠይቅ ሲሆን እንኳንስ ለተሿሟዎች ለመራጮችና ለአስመራጮች በቀኖና ቤተ ክርስቲያን የተወሰነ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መስፈርት ያለው፣ መሆኑ ለሁሉም ግልጽ ነው፡፡ ይህንም ቅዱስ ጳውሎስ በጻፈው መልእክቱ በሰፊው ገልጾታል፡፡ (ጢሞ.3፣10፣ ቲቶ፣

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ዝርወተ ዓጽሙ ለቅዱስ ጊዮርጊስ

በዛሬው ዕለት የሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ አጥንቱ ተፈጭቶ ከተቃጠለ በኋላ ይድራስ በሚባል ተራራ ላይ የተበተነበት ነው፡፡ ከሐዲውን ንጉሥ ዱድያኖስ ጨምሮ ሰባ ነገሥታት ቅዱስ ጊዮርጊስን በልዩ ልዩ መከራ አሰቃይተውታል።

ሦስት ጊዜ ቢገድሉትም ጌታችን ከሞት እያስነሣው ከሐድያንን አሳፍሯቸዋል፡፡ ቅዱሱን መግደል ያልተቻለው ንጉሥ “አጥንቱን ንፋስ እንዲወስደው በመንኰራኩር ፈጭታችሁ በይድራስ ተራራ ላይ በትኑት” በማለት አዘዘ፡፡

ወታደሮችም ቅዱስ ጊዮርጊስን በመንኰራኩር ፈጭተው በተራራ ላይ ቢበትኑት እራሩ ያረፈበት ሣር ቅጠል ሁሉ “ጊዮርጊስ ቅዱሱ ለእግዚአብሔር፣ ጊዮርጊስ ሰማዕቱ ለእግዚአብሔር” በማለት ቅድስናውን ገልጧል ፡፡
ጌታችን ሰማዕቱን ለሦስተኛ ጊዜ ከሞት አስነሣው። አጥንቱን አድቅቀው በማቃጠል በተራራ ላይ በትነውት ነገሥታቱ ወደ ነበሩበት በመመለስ ላይ የነበሩትን ወታደሮች “ እናንተ ወታደሮች ጠብቁኝ” አላቸው፡፡

ወታደሮቹ ዘወር ብለው ቢመለከቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው። በጣም ደንግጠው እንዴት ከሞት ልትነሣ ቻልክ በማለት ጠየቁት። “አምላኬ ከሞት አስነሣኝ” አላቸው፡፡ ጭፍሮቹም ከእግሩ ሥር ወድቀው በአምላክህ እናምናለን አሉት። ቅዱስ ጊዮርጊስም አምላኩን ቢለምነው ውሃ ፈለቀለት።

አዳዲስ አማንያንንም ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ተገልጦ አጥምቋቸው ተሰወረ፡፡ እነርሱም በነገሠታቱ ፊት ስለጌታችን በመመስከር በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡ አጥንቱ ተፈጭቶ ከተቃጠለ በኋላ በይድራስ ተራራ ላይ ቢበተንም በአምላኩ ቸርነት ተነሥቶ በከሐድያን ፊት በጽናት እየመሰከረ ብዙዎችን ክርስቶስን ወደ ማመን የመለሳቸው የቅዱስ ጊዮርጊስ በረከት ይደርብን፡፡ አሜን!!

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ(ዶ/ር) በሕገ ወጥ እንቅስቃሴው ውስጥ የተሳተፍ ሌሎች አባቶችም እንዲመለሱ ጥሪ አቀረቡ።

ሰው ሆኖ የማይሳሳት የለም ያሉትና የይቅርታ ደብዳቤውን የተቀበሉት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ(ዶ/ር)ቤተ ክርስቲያን ችግር የለም አንልም ነገር ግን ችግሩ የሚፈታው በንስሐ በይቅርታ አንድ ሆነን ስናገለግል ነው ብለዋል።

ጸሎታችንን እንቀጥል ሕያው እግዚአብሔር ይሰማናል ያሉት ብፁዕነታቸው ሌሎች አባቶችም እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።

አባ ጸጋ ዘአብ በበኩላቸው ባለፉት ቀናት አይደለም ኦርቶዶክሳውያን የሌላ ቤተ እምነት ተከታዮች እየደወሉ ራሴን እንድወቅስ አድርገውኛል ብለዋል።

እነሱ ለሰጡኝ "ክብር" የማልገባ በመሆኑ የተሰጠኝን አስኬማና አልባስ አስረክባለሁ ሲሉም ተናግረዋል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለ3 ቀናት የሚቆይ ጸሎት አወጀች፡፡

በዛሬው ዕለት የቅዱስ ሲኖዶስ የመክፈቻ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ቅድስት ማርያም ገዳም ከተጠናቀቀነ በኋላ ሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሦስት ቀናት የጸሎትና የሱባኤ ጊዜ እንዲሆን አዋጅ መታወጁን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ( ዶ/ር ) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ገልጸዋል፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ውጪ የሚደረግን ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት እንደማይቀበል የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በአቋም መግለጫው አስታውቋል።

ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ታዋድሮስ ዳግማዊ የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ
ልዩ ጽሕፈት ቤት፣

ካይሮ፡ 24 ጃንዋሪ 2023 ዓ/ም (ጥር 16 ቀን 2015 ዓ/ም)
የአቋም መግለጫ

የእስክንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ አቡነ ሳዊሮስ በተባሉ ጳጳስ የተፈጠረውን ቤተ ክርስቲያንን የመክፈልና ራሳቸውን በኢትዮጵያ የኦሮሞ ክልል ፓትርያርክ አድርገው የመሠየም ተግባር ሙሉ ለሙሉ የማይቀበለው ፍጹም ሕግን የጣሰ መሆኑና እና በእሳቸው መሪነት ተሾሙ የተባሉ 26 ጳጳሳት የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሕግ የጣሱ እንዲሁም መሠረት ያለውን እና ቋሚ የሆነን ከጥንት ጀምሮ በትውልዱ ሁሉ ሲተላለፍ ከመጣውን ከኦርቶደክስ ቀኖና እና መመሪያ ሕገ ወጥ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የእስክንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ዕውቅና ውጭ የሚደረግን ሢመት ዕውቅና አትሰጥም አትቀበልም።

ከዚህ በተጨማሪ ኮሚቴው (የውጭ ጉዳይ) ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለውን ወዳጅነት እና አጋርነት እየገለጽን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት፤ ሜትሮፖሊታን የሆናቸሁ ሁላችሁ ጥንታዊነት እና በታሪክ የበለጸገች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነት እና ትሥሥር በፍቅርና በሰላም ሁናችሁ እንድትጠብቁ በጥብቅ አደራ እንላለን፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥሪ ለኦርቶዶክሳውያን ከቅዱስነታቸው

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የተለያዩ ቦታዎች የመንግስት የፀጥታ ሐይሎች ያደርጉ የነበረውን ጥበቃ ባልታወቀ ሁኔታ አቁመዋል!

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🎬  🛑 ምስጢረ ሥጋዌ የክርስቶስ ሰው መሆን የመጨረሻው ክፍል | አምስቱ አዕማደ ምስጢራት |
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ

⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/ZwEn8GvaEgM
https://youtu.be/ZwEn8GvaEgM

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱን የሰጠውን የመኖሪያ ቤት ውል አቋረጠ ቤቱንም አሸገ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ በነበሩበት ወቅት ከጠቅላይ ቤተክህነት በተሰጠ ትዕዛዝ የተሰጣቸውን ከድርጅቱ የተሰጣቸውን መኖሪያ ቤት ውል በማቋረጥ ቤቱን ተረክቧል።

ድርጅቱ ውሳኔውን ያስተላለፈው ሕገ ወጥ መንገድ የቤተክርስቲያናችንን ቀኖናና ሕግጋት በመጣስ በትላንትናው እለት የተሰጠውን ሕገ ወጥ ሹመት ተከትሎ ዋነኛ አስተባባሪና ተሿሚ መሆናቸውን ምክንያት በማድረግ ነው።

ምንጭ: የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ከጀርመን ሀገረ ስብከት ጽ/ቤ በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ከማኅበረ ቅዱሳን በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መግለጫ ተሰጠ።

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#አስቸኳይ_የቅዱስ_ሲኖዶስ_ምልዐተ_ጉባኤ_ተጠራ!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሰጥቷል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በአገር ውስጥ እና በውጪ አገር  ያሉ ሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት በአስቸኳይ ከነገ ጀምሮ  ለአስቸኳይ ስብሰባ እንዲመጡ አሳስቧል።

መንግሥትም በተፈጠረው ችግር አስፈላጊውን ጥበቃ እንያደርግ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን እንዲረጋጉ መልእክት አስተላልፏል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🎬  🛑 ምስጢረ ሥጋዌ የክርስቶስ ሰው መሆን | አምስቱ አዕማደ ምስጢራት | ክፍል አንድ!
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ

⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/GhPT-R0G4D0
https://youtu.be/GhPT-R0G4D0

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉ጥምቀት_ምንድን_ነው?

ተወዳጆች የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች እንኳን ለጌታችንና ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሳችሁ እያልን ነገረ ጥምቀቱን እንዲህ መናገር እንጀምራለን

💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

✅ ጥምቀት በጽርዕ ቋንቋ ኤጲፋኒያ በግእዝ አስተርዮ በአማርኛ መገለጥ ይባላል።

✅ ጥምቀት “አጥመቀ” ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ፍቺውም በገቢር መንከር፣ መድፈቅ፣ መዘፈቅ፣ በተገብሮ መነከር፣ መደፈቅ፣ መዘፈቅ፣ መላ አካልን በውኃ ውስጥ ማስገባት ማለት ነው።

✅ በሌላ አገላለጽ ጥምቀት ማለት በተጸለየበት ወይም በተለየና በከበረ ውኃ (ማየ ገቦ ወይም ማየ ሕይወት) ውስጥ በሥላሴ (በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ) ስም ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር መጥለቅ፣ መዘፈቅ፣ መነከር ማለት ነው። በመሆኑም የምንጠመቅበት ውኃ ተራ ውኃ አይደለም።

✅ጥምቀት ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን አንዱ ነው።

💎የጥምቀት በዓል ከዘጠኙ የጌታ ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ ነው

💎በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓተ አክብሮት መሠረት በየዓመቱ ከጥር አሥር እስከ አሥራ አንድ ቀን በደማቅ ሥነ ሥርዓት በካህናት፣ በምዕመናንና በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች አገልግሎት ይከበራል።

💎 በዓሉ የሚከበረው ጌታ በዕደ ዮሐንስ በማየ ዮርዳኖስ የተጠመቀበት ምሥጢረ ጥምቀትና ሥርዓተ ጥምቀትን የመሠረተበት ዕለት በመሆኑ ነው። ጌታ የተጠመቀው በተወለደ በሠላሳኛው ዓመት ሲሆን ያ ወራት ዮሐንስ መጥምቁ ሕዝቡን እየሰበሰበ የንስሐ ጥምቀት የሚያጠምቅበት ጊዜ ነበር:: 📗ማቴ. 3:1📗

ታሪካዊ የጥምቀት በዓል አከባበር በኢትዮጲያ

💧ታላቁ የከተራ እና የጥምቀት በዓል ሲነሳ ኢትዮጵያውያን ሩቅ ዘመንን ተሻግረን የቅዱሳን ሰማዕት አባቶችን፣ የሊቃውንት አባቶችን አስተምሮት እናዘክራለን።

💧በቅዱስ ላልይበላ ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ምድር እየተመላለሱ በብሕትውና እና በስብከተ ወንጌል ያገለግሉ የነበሩት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአክሱም፣ በመቐለና በመርጡለ ማርያም እየተዘዋወሩ ባሕረ ጥምቀቱን ባርከዋል።

💧በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት (1260-1275 ዓ.ም) በጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (1203-1204 ዓ.ም) አሳሳቢነት የተጀመረው ሥርዐተ በዓል ተጠናክሮ እንዲቀጥል በዐዋጅ ትእዛዝ አስተላልፈዋል።

💧ታቦታቱም በሕዝብ ጥበቃና እንክብካቤ ተደርጎላቸው በየጥምቀተ ባሕሩ እንዲያድሩ ወስነዋል።

💧የበዓሉ አከባበር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋና አድማሱ ብሔራዊነትን እየያዘ መጣ።

💧ከዐፄ ገብረ መስቀል ጀምሮ የአደባባይ በዓል የሆነው የጥምቀት በዓል በ15ኛው ክ/ዘመን በደገኛው ኢትዮጵያዊው ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ (1426-1460 ዓ.ም) አማካኝነት ታቦታቱ ወደ ወንዝ ወርደው ዕለቱን እንዳይመለሱ፣ በዚያ ፈንታ በጥምቀት ዋዜማ ጥር 10 ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ወርደው እንዲያድሩ፣ አገሩን በኪደተ እግር ይባርኩም ዘንድ በሄዱበት መንገድ እንዳይመለሱ በዐዋጅ ወሰኑ።

💧ይህን ታሪክ በመከተል ዐፄ ናዖድ (1486-1500) ዓ.ም) ማንኛውም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመን ታቦተ ሕጉ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ በሚወርድበት እና ከባሕረ ጥምቀቱ ወደ ቤተ መቅደሱ በሚመለስበት ጊዜ አጅቦ አውርዶ፣ አጅቦ መመለስ እንዳለበት timqet celebration በዐዋጅ አስነግረው ነበር።

💧ሕዝቡም ታቦታተ ሕጉን በሆታና በእልልታ ከቤተ መቅደስ አጅቦ ካወጣ በኋላ በባሕረ ጥምቀት ከትሞ ማደር ጀመረ ።

💧ኢትዮጵያ ዜና ጥምቀተ ክርስቶስን ከሰማችበት ከመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን አንሥቶ በተለይም ከአጤ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት (6ኛው መ/ክ/ዘ) ወዲህ የጥምቀትን በዓል ዛሬ በሚታየው አኳኋን ስታከበር እንደ ቆየች ይታመናል።

💧በክብረ በዓሉ ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው ወደ ባሕረ ጥምቀት የሚወርዱት ታቦታት በካህናቱ ሃሌታ፣ በምእመናኑ እልልታ እና በየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያኑ በተቋቋሙ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች መዝሙሮች ታጅበው በተመሳሳይ አኳኋን እንደሚመለሱ ይታወቃል።

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን።

መዝሙረ ዳዊት ፻፶፥፮

💎ጌታችን በተጠመቀ ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ የላይኛው ሸሽቶ ወደ ላይ ተመልሶ ሽቅብ ፈሷል። የታቹም ወደ ታች ሸሽቷል። የላይኛው ፈሳሽ ተቋርጦ እንደ ክምር ተቆልሎ ቀርቷል።

💎ቅዱስ ዳዊት የተመለከተውም ይህንኑ ነው።

✅ከአዳም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ቤዛነት ተቋርጦ፤ የታቹም ፈጽሞ መድረቁ ኃጢአተ አዳም የመጥፋቱ ምሳሌ ነው።

✅እስራኤል ፈለገ ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ኢያሪኮ መሔዳቸው ምእመናን በጥምቀት ከኃጢአት ቍራኝነት ተላቀው እግራቸውን ወደ ልምላሜ ገነት ወደ ዕረፍት መንግሥተ ሰማያት አቅንተው ለመሔዳቸው ምሳሌ ነው።

✅ኢያሱ የጌታ፣

✅እስራኤል የምእመናን፣

✅ዮርዳኖስ የጥምቀት፣

✅ምድረ ርስት የገነት መንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው።

✅ታቦቱን አክብሮ የሚሔደው ካህን የቅዱስ ዮሐንስ፣

✅ታቦቱ የጌታችን፣

✅ባሕረ ጥምቀቱ የዮርዳኖስ ወንዝ፣

✅ታቦታቱን አጅበው የሚሔዱትና በዓሉን የሚያከብሩት ምእመናን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ እየመጡ የንስሐ ጥምቀት ሲጠመቁ የነበሩት ሰዎች ምሳሌዎች ናቸው።

✅ታቦታቱ በጥምቀት ዋዜማ ከመንበራቸው ወደ ጥምቀተ ባሕር መውረዳቸውና በዚያ ማደራቸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ ከማታው ጀምሮ መውረዱንና ተሰልፎ ተራውን ሲጠብቅ ማደሩን ያጠይቃል።

✅‹‹ጥምቀት የሞቱና የትንሣኤው ምሳሌ ነው።

👉ከኃጥአን ጋር ተቆጥሮ እንዲጠመቅና እንዲሰቀል የተጻፈውን ቃል ንስሐና ጥምቀት የማያስፈልገው ሲሆን ነገር ግን ፍጹም ኃጥእ መስሎ በዮሐንስ እጅ ጥምቀትን ለመፈጸም በማየ ዮርዳኖስ እግር ተጠመቀ።››።

💎ጌታችን የተጠመቀበት ወርኀ ጥር በእስራኤላውያን ዘንድ የዝናብ፣ የበረዶ ወራት ነው። ከወንዝ ዳር ያለ መጠለ

ያ መዋልና ማደር አይቻልም። በመኾኑም ከዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄዱ ሰዎች ሁሉ በዮርዳኖስ ዙሪያ ድንኳናቸውን ተክለው ያርፉ ነበር። በዚህ አንጻር ዛሬም በባሕረ ጥምቀት ዙሪያ ድንኳኖች ዳሶች ይጣላሉ።

በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በተለይ በአክሱም የንግሥት ሳባ መዋኛን ‹‹ማይ ሹም›› በጎንደር የዐፄ ፋሲል መዋኛን፣ በላስታ የላሊበላ መዋኛን፣ በሸዋ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ፍርድ መስጫ አደባባይን፣ አርባ አራት ታቦታት የሚያድሩበትን የሸንኮራ ሜዳን “ራቡቴ ወንዝ” በአዲስ አበባ ደግሞ ጃንሆይ ሜዳን /ጃንሜዳን/ ወዘተ ለአብሕርተ ምጥማቃት እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። እኒህ ቦታዎች ዛሬም ድረስ ተከብረው ይገኛሉ።

💎እኛ በዚህ ወቅት ታቦት ይዘን፣ ከወንዝ ወርደን፣ ድንኳን ተክለን በማክበራችን ይፈጸማል፡፡


💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
ምንጭ ፦ ሥርዓተ ተዋህዶ ርትዕት
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

Читать полностью…
Подписаться на канал