ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

14፤ ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ለእዚህኛው ጥያቄ መልስ

👉ማንኛውም አይነት የጸሎት መጽሐፍ ሴት ልጅ በወር አበባዋ ጊዜ ማንበብ፣መጸለይ መደባበስ ትችላለች የሚከለክላት ነገር የለም።


የማትችለው ነገር
👉ቤተመቅደስ አለመግባት
👉ቤተክርስቲያን 40 ክንድ መራቅ ወይም ቅጽሩ ጋር መሆን እና ከእዛ አለመዝለቅ
👉ጠበል አለመጠመቅ

እነዚህ ናቸው እንጂ ጠበል እራሱ በወር አበባ ጊዜ መጠጣት ትችላለች።

🙏እባካችሁ ማሳሰቢያ ለሁሉም እንድታስተላልፉ የምንፈልገው የወር አበባ መርገም አይደለም!!!

ከቃሉ እንደምንረዳው በየወሩ የሚመጣ አበባ ፍሬ(ልጅ) የሚገኝበት ነው። እንጂ መርገም አይደለም።

የሔዋን መርገም በክርስቶስ የመስቀል ላይ ዋጋ ተሽሯል። ይህንን ለዓለም ሁሉ ንገሩ ለሁሉም እህቶች ተናገሩ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስም፣ በእንተ እግዝእትነ ማርያምም ሁለቱም የሚጀምሩት ከላይ ወደታች ነው።

👉እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ስንል ከጠቋሚ(ሌባ) ጣት ጀምሮ ወደ ታች ወርደን፣ የመሐል ጣታችን ላይ ከታች ወደ ላይ ወጥተን፣ቀለበት ጣታችን ላይ ወደ ታች ወርደን፣ የማርያም ጣት ላይ በስተመጨረሻ ከታች ወደ ላይ የምንወጣበት ነው።

👉በእንተ እግዝእትነ ማርያም ደግሞ ከማርያም ጣታችን ጀምሮ ወደ ታች ወርደን፣ የቀለበት ጣታችን ላይ ከታች ወደ ላይ ወጥተን፣መሐል ጣታችን ላይ ወደ ታች ወርደን፣ የጠቋሚ(ሌባ) ጣታችን ላይ ወደ ላይ የምንወጣበት ነው።


ይህም በአጭሩ ስንገልጸው እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ የሚለውን ያልነውን ተቃራኒ አቅጣጫ "በእንተ እግዝእትነ ማርያም" ማድረግ ማለት ነው

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጀማሪ መፅሐፍ ቅዱስ አንባቢ ኬትኛው የፀሎት መፅሐፍ መጀመር አለበት?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

Matiwos 7:23 abzagnawn gze endemekerakerya netb slemitekemut "emesekrbachuhalw"milw lay??

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከሌሎች አማኞች ጋር አብሮ መመገብን እንዴት ታየዋለች?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ምድር ለምን ተፈጠረች
ማለት አዳም ገነት እያለ ማለቴ ነው?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሠላም ውድ የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች። ትላንት የጀመርነውን የጥያቄ እና መልስ መርኀ ግብር አሁን እንቀጥላለን ተከታተሉ።👇👇👇

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የልደትን ቀን ማክበር ኀጢአት ነው?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ኔትወርክ እንደምታውቁት እያስቸገረ ስለሆነ ትንሽ እየታገሳችሁ ትጠብቁን ዘንድ በትኅትና እንጠይቃለን።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስቀል የማማተብ ትርጉም
ምላሽ ተሰጥቶበታል አዳምጡት

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እኔ ሠራተኛ ነኝ እናም ያለችኝ እረፍት እሁድ ናት እናም በእሁድ እለት በጠዋት ተነስቼ ቤተክርስቲያን ሄጄ ከዛ መልስ ልብሴን ባጥብ ምን ችግር አለው ?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በስላሴ Consept መወለድ እና መስረፅ ልዩነታቸው

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንዴት አመሻችሁ የተወደዳችሁ የዝማሬ ዳዊት የቴሌግራም ቻናል ተከታታዮች እንደ አምላካችን መልካም ፈቃድ አብዛኞቹን የጠየቃችኋቸውን ጥያቄዎች አንድ በአንድ መመለስ እንጀምራለን


🫸🫸🫸ተከታተሉን🫷🫷🫷

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ናና_ሚካኤል_ናና

ናና ሚካኤል ናና /2/
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና
ናና ሚካኤል ናና

የረዳህ አፎምያን ሚካኤል ናና
ሰይጣን ሲፈትናት ሚካኤል ናና
አንተነህ ያዳንከው ሚካኤል ናና
ባሕራንን ከሞት ሚካኤል ናና
ለእነርሱ እንደመጣህ ሚካኤል ናና
እኔንም ተራዳኝ ሚካኤል ናና
ሚካኤል ደግፈህ ሚካኤል ናና
ለመንግሥቱ አብቃኝ ሚካኤል ናና
ናና ሚካኤል ናና /2/
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና

አዝ-------------

ናና ገብርኤል ናና /2/
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና
ናና ገብርኤል ናና

ዘመኑ ሲፈፀም ገብርኤል ናና
አምላክ መምጫው ሲደርስ ገብርኤል ናና
ገብርኤል አንተ ነህ ገብርኤል ናና
ያልካት ደስ ይበልሽ ገብርኤል ናና
ድምጽህን አሰማኝ ገብርኤል ናና
ነፍሴ ጽድቅን ትልበስ ገብርኤል ናና
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና
ናና ገብርኤል ናና

አዝ-------------

ናና ዑራኤል ናና /2/
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና
ናና ዑራኤል ናና

ቆመህ ጽዋ ይዘህ ዑራኤል ናና
ለእዝራ ሱቱኤል ዑራኤል ናና
ጥበብ አጠጥተህ ዑራኤል ናና
ዕውቀት ስታድል ዑራኤል ናና
ተገለጠ ክብርህ ዑራኤል ናና
መልአኩ ዑራኤል ዑራኤል ናና
ድኜ በፀበልህ ዑራኤል ናና
በአውደ ምህረትህ ላይ ዑራኤል ናና
እኔም ዘመርኩልህ ዑራኤል ናና
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና
ናና ዑራኤል ናና

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

1. እግዚአብሔር ፍጥረትን ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን አረፈ ይላል። ታዲያ የሰው ልጆች መቼ ነው የተፈጠሩት???

2. መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ እና ጸሎትን መጸለይ ለጀመረ ሰው ምን ጸሎትን ትመክሩኛላችሁ?

ለተባለው ጥያቄ የተሰጠ መልስ ነው ተከታተሉት

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

1. ምድር ለምን ተፈጠረች
ማለት አዳም ገነት እያለ ማለቴ ነው?

2. እኛ የምንኖረው የተጻፈልንን ነው ወይስ የምንኖረው ነው የሚጻፍልን

የሚሉት ጥያቄዎች የተመለሱበት ነው አዳምጡት

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የቆረበ ሰው በሰንበት ውሃ ቢያልቅበት ቀድቶ መጠጣት ይችላል ወይ? ሰንበትን ማፍረስ አይሆንም ወይ?

ለሚለው ጥያቄ የተመለሰ መልስ እና ስለ ሰንበት አከባበር የተሰጠ ማብራሪያ አዳምጡት።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እግዚአብሔርም የሠራውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጸመ፤ በሰባተኛውም ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ ዐረፈ።
እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም፤ እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና። ይለናል ዘፍ ፪÷፪ ስለዚህ እግዚአብሔር መፍጠርን በ፮ኛው ቀን ከፈፀመ (ከጨረሰ) እኛ መቼ ነዉ የተፈጠርነው?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

1,ሰኔ ጎልጎታን ሴት መርገሟ በመጣ ጊዜ መፀለይ ትችላለች?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በኢተ እግትነ ማርያም መሀረን ክርስቶስ ወደላይ ነዉ ወይስ ከነ መሣሌዉ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ይቅርታ እየተቆራርጥብኝነው


ስለ ቁርባን በቁርባን ተጋብተን የሰንበት ውሃ ብንቀዳ አጋጣም አልቆብን ሀጥያት ይሆናል አሁን በቁርባን የተጋባ ሰው በሰው ቤት ተቀጥሩ ብስራ የስንበት ውሃ ቀደቶ ብጠጣ ሀጥያት ይሆንብናል

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

1. በሰንበት ልብስ ማጠብ ይፈቀዳል ወይ?
2. ዲቁና በስንት አመት ነው መቀበል የሚቻለው።

የሚሉት ጥያቄዎች ተመልሰዋል። ለዛሬ የጥያቄና መልስ ሰዓታችን አብቅቷል ነገ በተመሳሳይ ሰዓት ይጠብቁን።

ሠናይ አዳር

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ስለ ምሥጢረ ሥላሴ መውለድ እና መስረጽ የተመለሰ መልስ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ስለ ምሥጢረ ሥላሴ እና አምስቱን አእማደ ምሥጢር መማር የምትፈልጉ እዚህ ድምጽ ላይ ታገኙታላችሁ ተከታተሉ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

dekunena eske sent amet dres yesetal?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የሰው ልጅ የተወለደበትን የልደት ቀን ብያከብር ጣዋትነው

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የማማተብ ትርጉም ቢነገረኝ ደስ ይለኛል

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✝ሠላም የተወደዳችሁ የዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች✝

👉ዛሬ ምሽት ላይ ባለፈው የተጠየቁትን ጥያቄዎች መልስ የምንሰጥ ስለሆነ ሁላችሁም ከምሽቱ 3:0ዐ ጀምሮ ትጠብቁን ዘንድ በትኅትና እንጠይቃለን።

መልሱ ሌሎች እህት ወንድሞቻችን ይሰሙት እና ይማሩበት ዘንድ ይገባልና ለምታውቁት ኦርቶዶክሳዊ በሙሉ ይሄንን የቻናል ሊንክ ላኩላቸው
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ኦ_ሚካኤል

ኦ ሚካኤል መላዕከ ሃይል/2/
ስንጠራህ ድረስልን ኦ ሚካኤል መላዕከ ሃይል

ዘንዶው ጠላታችን ከፊታችን ቆሟል
ከባህር ሊጥለን አድፍጦ ያደባል
የመላዕክት አለቃ እርዳን በፀሎትህ
ጥበቃህ አይራቀን በቀን በሌሊት/2/

ክርስትና ኑሮ እጅጉን ከብዶናል
የጌታን ውለታ ፍቅሩን ዘንግተናል
አፅናኙ መልዐክ ከፊታችን ቅደም
በመንገድህ ምራን እንድንሆን ሰላም/2/

የጌታ ባለሟል የህዝብ እረኛ
ባህሩን አሻግረን ቅረበን ወደ እኛ
ከጌታህ አማልደን መልዐከ ራማ
የልጆችህን ቃል ድምፃችንን ስማ

በሚያስፈራው ዘመን ሰላም በሌለበት
ባስጨናቂው ጊዜ ፍቅር በጠፋበት
የፍቅርን ወንጌል ቃሉንም ስበከን
ሚካኤል ተራዳን ድረስም አፅናናን

ዘ/ዲ ሱራፌል ስዩም
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…
Подписаться на канал