ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በቀድሞ ስማቸው አባ ንዋየ ሥላሴ አካሉ የይቅርታ ደብዳቤ በአስገቡ ሰዓት "የተሾሙበትን" አስኬማና አልባሳትም አስረክበዋል።

"እውነትን ተረድተው ስለመጡ ቤተ ክርስቲያን ደስተኛ ናት። ሌሎች በማወቅም ባለማወቅም የሄዳችሁ አሁንም ለመምጣት የተቸገራችሁ ቤተ ክርስቲያን በሯ ክፍት ነው::" ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በዛሬው ዕለት ምእመናን ወደ መንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን /ግቢ ገብርኤል/ እንዳይገቡ ተከለከሉ።

የጸጥታና የደኅንነት ግብረ ኃይል ትናንት ምሽት ከንጋቱ 11:00 እስከ ረፋድ 4:00 ሰዓት ድረስ የተለያዩ የከተማዋ መንገዶች ዝግ እንደሚሆኑ ተናግሮ ነበር።

የአጥቢያው ምእመናን ይህንን በማክበር ከሌሊት 10:00 ጀምሮ ወደ ደብሩ ቢሄዱም ከላይ የመጣ ትእዛዝ ነው በማለት ፖሊሶች እንዳይገቡ ከልክለዋቸዋል።

የደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት ባጋራው መረጃም ምእመናን በሌሉበት ሥርዓተ ቅዳሴ እንደተከናወነ ገልጿል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

https://youtu.be/T3hs_Jxwee0

ሞገሳቸው እግዚአብሔር ነው።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በሕገ ወጡ ሹመት ላይ የተሳተፉ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳትና ግለሰቦች ከዛሬ የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት እንዳይገቡ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አግዷል።

ዛሬ በነበረው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀጠሮ የሕግ አማካሪዎች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም ሹመት የሰጡት በቀድሞ ስማቸው “አባ ኤዎስጣቴዎስ”፣ “አባ ዜና ማርቆስ”፣ “አባ ሳዊሮስ” እና እነርሱ በሕገ ወጥ መልኩ ሾመናችኋል ብለው ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ውጪ አስኬማ ያቀዳጇቸው 25 ግለሰቦች እንዲሁም አቶ ኃይለ ሚካኤል ታደሰ የተባሉ ግለሰብ በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 156 መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግቢ እንዳይገኙ በጊዜያዊነት አግዷቸዋል። ይህንን እግድ የተላለፈ ማንኛውም አካል የወንጀል ተጠያቂነት ይኖርበታል። በሀገሪቱ የሚገኙ የሕግ አስፈጻሚ አካላት እግዱን እንዲያስፈጽሙ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። ቤተ ክርስቲያኗ በቀጣይ በሰብአዊ መብት፣ በአስተዳደር፣ በወንጀልና በፍትሐ ብሔር ለደረሰው ኪሣራ ተጠያቂዎችን በመለየት በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት በሕግ ትጠይቃለች።

በዚህም በሕገ ወጡ ሹመት ላይ የተሳተፉ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳትና ግለሰቦች ከዛሬ የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት እንዳይገቡ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አግዷል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ሰበር_መረጃ

ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ ብፁዓን አባቶች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት እያካሔዱ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕዝብ ግንኙነት አስቸኳይ ሰበር መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫው ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በየካቲት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መሠረት ቤተ ክርስቲያኒቱ መግለጫውን ባወጣች 72 ሰዓታት ውስጥ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሃይማኖት ፤ ቀኖናና አስተዳደራዊ ሕግጋትን ባልጣሰ መልኩ ከመንግሥት ጋር በጉዳዩ ላይ ለመወያየት መንፈሳዊ በሯ ክፍት መሆኑን በመግለጽ ይፋዊ ጥሪ ማስተላለፏን አስታውሷል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የኢፌዳሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ይህንን የቤተ ክርስቲያን ጥሪ መሠረት በማድረግ ለውይይት ጥሪ ማቅረባቸውን ገልጿል።

ውይይቱ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ሊሆን የሚገባ ነው በሚል በተነሳው ሐሳብ በጉዳዩ ላይ ከሽማግሌዎች ጋር ጥልቅ ውይይት በማድረግ የደህንነት ተሽከርካሪዎች እና የጸጥታ አካላት ብዛት ሲታይ ምእመናንን ስጋት ላይ እንዳይወድቁ እና ላልተጋባ ጉዳት እንዳይዳረጉ በማሰብ የሰላም ጥሪውን መንግሥት ከተቀበለ እና በቤተ መንግሥት መገኘቱ ለሕዝቡ የሚያመጣው መፍትሔ የሚኖር እንደሆነ በማሰብ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርካችንን ጨምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተተ ልኡክ በቤተ መንግሥት የሚገኝ መሆኑን ጠቅላይ ቤተ ክህነት አሳውቋል።

ሕዝበ ክርስቲያኑም አባቶች የደረሱበትን ውጤት እስኪያሳውቁ ድረስ በትእግስት እንዲጠባበቁ መልእክት አስተላልፏል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የእሥር ዜና!

የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት ዋና ሰብሳቢ ወ/ሪት ፌቨን ዘሪሁን እንዲሁም ዋና ፀሐፊዋ ወጣት ብሩክታዊት ታሥረዋል።

ምንጭ፡ ተሚማ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደርና የከተማው የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጎን መሆናቸውን አሳወቁ።

የጋሞ ዞንና የአርባ ምንጭ ከተማ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በወቅታዊ ጉዳዮችና የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን  የሚደግፍ ምክክር አካሒደዋል።

የጋሞ ዞንና የአርባ ምንጭ ከተማ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በወቅታዊ ጉዳዮችና የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን አስመልክቶ በትናንትናው ዕለት ባደረጉት ምክክር  በከተማው የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮችና  የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የሃይማኖት ተወካዮች በኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ በደረሰው ክስተት ማዘናቸውን ገልጸዋል።

ቤተ ክርስቲያን ወደ ቀድሞው ሰላም እስክትመለስ ድረስ ሁሉም ቤተ እምነቶችና ምእመናን  በጾምና በጸሎት ከኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጎን እንደሚሆኑ  አሳውቀዋል።

ከተማ አስተዳደሩም ቅዱስ ሲኖዶሱ በሚያስቀምጠው አቅጣጫ መሠረት የሚጠይቁት ጥያቄ  እስኪመለስ ድረስ በማንኛውም ነገር  ከኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጎን መሆኑን አሳውቋል።

በመሆኑም ኅብረተሰቡ እንደ ከዚህ ቀደሙ የሰላም ማስከበር ሥራውን አጠናክሮ በማስቀጠል  እንግዳ እና አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት ጥቆማ በመስጠት ከጸጥታ አካላት ጎን በመሆን የተለመደ ተግባሩን ሊያከናውን እንደሚገባም ተገልጿል። ዘገባው የአርባ ምንጭ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

"አንተ ግን ወገብህን ታጠቅ፥ ተነሥም! . . . ከአንተ ጋር ይዋጋሉ፥ ነገር ግን አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና ድል አይነሡህም፥ ይላል እግዚአብሔር። " (ኤር. ፩:፲፯)

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሁላችሁም ኦርቶዶክሳውያን VPN ጫኑ ኢንተርኔት እየተቋረጠ ነው?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ይህ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እየደረሰ ያለው መከራና በደል በዚህ ዘመን በጉልህ የሚጠቀስ የቤተ ክርስቲያን የስደትና የመከራ ጊዜ ነው፡፡ ይህ የቤተ ክርስቲያን የስደትና የመከራ ጊዜ በቤተ ክርስቲያኒቱ የታሪክ መዝገብ እና በመጽሐፈ ስንክሳር ተመዝግቦ ይቀመጣል፡፡ ለትውልድም ይተላለፋል፡፡ ይህ የፈተና ዘመን ያልፋል፤ ነገር ግን በዚህ ታሪክ ውስጥ ከእውነት ጎን የቆማችሁ ስማችሁ በታሪክ እና በወርቅ ቀለም ሲፃፍ በቤተክርስቲያን ላይ መከራ ያበዛችሁ ክፉ ታሪካችሁን ዛሬ በእጃችሁ ጽፋችሁ አልፋችኋል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውጭ ሌሎች የክልል ርዕሳን መስተዳድሮችና ከተሞች በተለይም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፤ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት፤ የሲዳማ ክልላዊ መንግስት፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት፤ የሱማሌ ክልላዊ መንግሥት፤ የቤንሻንጉል ክልላዊ መንግሥት፣ የሐረሪ ክልላዊ መንግሥት፣ የአፋርና ጋምቤላ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት፤ በጎፋ ዞን የሳውላ ከተማ እና ሌሎች ስማቸውን ያልጠቀስናቸው መንግሥታዊ ተቋማት የቤተ ክርስቲያናችንን ጥሪ በመከተል በአግባቡ ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር የወሰዳችሁ ፍትሐዊ እና ሕጋዊ መፍትሔዎችን እናደንቃለን፣ በቤተ ክርስቲያንም ስም እናመሰግናለን፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🚨 በሃይማኖታችን ላይ ወቅታዊ መረጃ እየሰጡ የሚገኙትን ኦርቶዶክሳውያን ላይ መንግስት የአደና ስራውን ጀምሯል!

የምታውቁትን ኦርቶዶክሳዊ ሚድያ በሙሉ በመቀላቀል ለሌሎቹም በመላክ መረጃ የምንለዋወጥበትን አድማስ እናስፋ!

ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊ በሙሉ Share አድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መንግስት ከአጉል እልከኝነቱ ወጥቶ ከሕገ ወጦቹ ግለሰቦች ጋር በመተባበር በአደባባይ እየፈጸመ ያለውን የሕግ ጥሰት ዛሬን ጨምሮ በቀጣዮቹ ፪/ሁለት/ ቀናት ውስጥ እንዲያቆም እና ሕግ እና ሥርዓትን እንዲያስከብር፣ በኃይል የወረራቸውን መንበረ ጵጵስና እና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ለቆ ለቤተክርስቲያኒቱ ሕጋዊ መዋቅር እንዲያስረክብ፣ ያለአግባብ ያሠራቸውን ካህናት እና ምእመናን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ለፈፀመው በደል በአደባባይ ይቅርታ እንዲጠይቅ፤ በካህናት እና ምእመናን ላይ ለደረሰው ሞት እና የአካል ጉዳት ተገቢውን ካሳ እንዲክስ እና የወደሙ ንብረቶቿን እንዲጠግን በጥብቅ እንጠይቃለን ፡፡

መንግሥት በዚሁ አካሄድ ሕግ እየጣሰ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር እና ልእልና እያዋረደ የሚቀጥል ከሆነ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት የጣሰውን ሕግ መሠረት በማድረግ መብቷን ለማስከበር እስከአሁን ድረስ ፍጹም ሰላማዊ የሆነውን እንቅስቃሴዋን አድማሱን በማስፋት በየካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለማድረግ ያቀደችውንና ያሳወቀችውን ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ያለማንም ከልካይነት በራሷ አደባባይ የምታከናውን መሆኑን እያሳወቅን መንግሥትም ድርሻው ሰልፉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት ብቻ መሆኑን እያሳሰብን ዛሬም ቢሆን መንግሥት ቆም ብሎ በማሰብ ከእኛ ከአባቶች ጋር ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና መንፈሳዊ የአስተዳደር ሥርዓታችንን ባልጣሰ መልኩ ለመነጋገር እና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ጥረት ካደረገ በውይይት ለመፍታት መንፈሳዊ በራችን ክፍት መሆኑንም እናሳውቃለን፡፡

ከዚህ ውጭ ግን በሁለቱ አባቶች መካከል የተፈጠረ ችግር እየተባለ የሚነገረው ፖለቲካዊ ጨዋታ የመንግሥት እንጂ በሀገሪቱ ሕጋዊ ሰውነት የሌላቸውና ከቤተ ክርስቲያን የተለዩ ግለሰቦች ጋር ማነጻጸር ሕገ መንግሥታዊም ሆነ ሞራላዊ የሕግ መሠረት የለውም፡፡

ስለዚህ ቤተ ክርስቲያናችን የጠራችውን ሰላማዊ እና ሕጋዊ የሆነ የመብት ጥያቄ የማፈን ሂደትን በጥብቅ እንቃወማለን፡፡  

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን እስከአሁን ባደረጋችሁት ጽናትና ተጋድሎ ሃይማኖታችሁንና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንችሁን እንዳላሳፈራችሁ ሁሉ አሁንም ከስሜታዊነት በወጣ ሁኔታ በከፍተኛ ጽናት እና ጥንካሬ የአባቶቻችሁን ድምጽ ብቻ እንድትሰሙ፣ ቤተ ክርስቲያንን በየአጥቢያችሁ ተደራጅታችሁ እንድትጠብቁ፤ ለአባቶቻችሁ መንፈሳዊ ጥሪ ፈጣን ምላሽ እንድትሰጡ፣ እየመጣው ላለ መከራና ስደት ለመንፈሳዊ ተጋድሎ እንድትዘጋጁና በፍፁም መንፈሳዊ ጨዋነት በአንድነት የመጣብንን ፈተና እንድትወጡ አደራ እያልን አባታዊ መልእክታችንን እያስተላለፍን ሰላማዊ ሰልፉን በተመለከተም በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝርዝር መግለጫ የምንሰጥ መሆኑን እያሳውቅን በዚህ ጥቃት መስዋእትነት የከፈሉ እና ያረፉ ልጆቻችንን ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት በክብር ያሳርፍልን እያልን ጸሎተ ፍትሐትም በየደረጃው የሚከናወን መሆኑን እያሳወቅን በተለያዬ ጊዜ ዛሬን ጨምሮ በወለቴ እና በሰበታ ከተሞች የደረሰውን የአካል ጉዳት እና ሞት እግዚአብሔር ምህረት እና መጽናናቱን ያድልልን፡፡ እግዚአብሔርም ገድላችሁን፣ ጽናታችሁንና ጸሎታችሁን ይቀበል፤ የቅዱሳን አምላክ ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ 

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

“እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክ”
የካቲት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከጥር ፳፱ እስከ የካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለ ፫ ተከታታይ ቀናት በመላው ዓለም የታወጀው የነነዌ ፆም እና ምሕላ መጠናቀቅን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ::


በትንቢተ ዮናስ በሰፊው እንደተጠቀሰው የነነዌ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ላይ ስለአመጹ እና ግብራቸውም በእግዚአብሔር ፊት አጸያፊ በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ዮናስን “ተነስተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ ክፋታቸውም ወደ ፊቴ ወጥቷልና በእርስዋ ላይ ስበክ” በማለት አዘዘው፡፡ ትንቢተ ዮናስ ምዕ ፩ ቁጥር ፪ ዮናስም ድምፁን ከፍ አድርጎ ለነነዌ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ሲሰብክ “የነነዌ ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም አዋጅ ነገሩ፤ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ፡፡ ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነስቶ መጎናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፤ በአመድም ላይ ተቀመጠ፡፡ አዋጅም አስነገረ፤ በነነዌ ውስጥ የንጉሡንና የመኳንንቱን ትእዛዝ አሳወጀ፤ እንዲህም አለ ሰዎችና እንስሶች፤ ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ፣ አይሰማሩ፣ ውኃንም አይጠጡ፤ ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ፣ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ጩኸት ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ፡፡ እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደሆነ ማን ያውቃል፡፡ እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውንም አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም” ትንቢተ ዮናስ ፫፡ ፭-፲

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ይህን የነነዌ ሰዎች ፆም መነሻ በማድረግ የነነዌ ሰዎችን በምሕረቱ የጎበኘ አምላክ እኛንም በምሕረቱ ይቅር ይለን ዘንድ በየዓመቱ በአዋጅ በመፆም አምላካችንን ስንማጸንበት ኖረናል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባዔ በጥር ፳፮ ቀን ፳፻፲፭ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በወሰነው መሠረት የካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የተጠናቀቀው የነነዌ ፆምና ምሕላ ልዩ በሆነ በመንፈሳዊ የንስሐ ጸሎት በሰላም ተጠናቋል፡፡

በምሕላውም ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ጀምሮ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ ካህናት፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ አገልጋዮች እና ምእመናን እንደነነዌ ሰዎች ጥቁር ለብሰን ጠዋትና ማታ በጸሎት ፤ በምሕላ፤ ቀን በቅዳሴ እንዲሁም በሰባቱ የጸሎት ጊዜያት ፈጣሪያችንን ስንለምን እና ስንማጸን የቆየንበት ምክንያት በቤተክርስቲያናችን ላይ የመጣው ፈተና እጅግ በጣም ከባድ በመሆኑ ነው፡፡

በዚህ የጾምና የንስሐ ወቅት ምእመናን ልጆቻችን የአባቶቻችሁን ጥሪ ሰምታችሁ፤ የሹመኞችን ማዋክብና እስር ሳትፈሩ ጥቁር ለብሳችሁ ጠዋትና ማታ በጾምና በምሕላ፣ ቀን በቅዳሴ በቤተክርስቲያን ቅጥር እየተገኛችሁ ለአምላካችን ያቀረባችሁትን ጸሎት እና ምሕላ እግዚአብሔር ሰምቶ ለችግራችን መፍትሄ፣ ለሀገራችን ሰላምን እንደሚሰጠን እምነታችን ጽኑ ነው፡፡ እናንተም ምእመናን የቤተ ክርስቲያንን ጥሪ ሰምታችሁ ለሃይማኖታችሁ፣ ለሀገራችሁ አንድነትና ሰላም ያላችሁን ጥልቅ ፍቅር ስለገለፃችሁም ያገኘነው መንፈሳዊ ብርታት ሳንገልፅላችሁ አናልፍም፡፡

በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቅዱሳን አማላጅነት፣ በመላእክት ተራዳኢነት በፍፁም ፍቅርና አንድነት የያዝነውን ጸሎት እና ምሕላ አጠናቀናል፡፡ ችግራችንን ለአምላካችን በለቅሶ እና በጩኸት ነግረናል፡፡ ከዚህ በኋላ መከራው ቢጸና፣ የመከራው ጊዜ እንኳን ቢረዝም እግዚአብሔር በመከራ ውስጥ ሊያፀናን እና ሊያበረታታን አስቦ በመሆኑ በፍፁም አንናወጽም፡፡ ከእነኚህ መከራዎች በኃላም ታሪክን ጽፈን ሃይማኖታችንን ጠብቀን እና አስጠብቀን በመንፈሳዊ ጽናት እና ተጋድሎ እንሻገራለን፡፡

ጥቃቱ የቤተ ክርስቲያንን እውነት በካዱና በእውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን መካከል ነው፡፡ ይህም የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖት፤ ቀኖና እና አስተዳደራዊ ሕግጋትን ጥሰው ሕገወጥ የጳጳሳት ሢመት በመደረጉ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ቅዱስ ሲኖዶስ በሕገ ቤተ ክርስቲያንና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት በጥር ፲፰ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ይህን ጥሰት የፈፀሙትን ግለሰቦች አውግዛ ከቤተ ክርስቲያን ኅብረት የለየቻቸው ቢሆንም ጉዳዩ ከግለሰቦቹ በላይ በመንግሥት ስልጣን ላይ ባሉና ጽንፈኛ በሆኑ ፖለቲከኞች እንዲሁም የሌላ እምነት ተከታዮች ጭምር የሚደገፍ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያንን ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈላት ይገኛል፡፡

እየተፈጸመ ያለው ድርጊት በሰማያዊ መንፈሳዊ ዓለምና በምድራዊ ሥጋዊ ዓለም መካከል ስለሆነ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥም የቤተ ክርስቲያን ክብርና ተቋማዊ ልዕልና ተደፍሯል፡፡ የቤተክርስቲያን ቅጥሮች መሣሪያ በያዙ አካላትና በመንግሥት የጸጥታ መዋቅር በኃይልና በጉልበት ተወሯል፡፡ ሊቃነ ጳጳሳት አባቶች ለብዙ ዓመታት ከኖሩበት አህጉረ ስብከት ያለአንዳች የሕግ መሠረት በጸጥታ መዋቅሮች ተባረዋል፡፡ በነጻነት የመንቀሳቀስ መብቶቻቸው ተገድቦም በግዞት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡ ወደ አህጉረ ስብከታቸውም ተመልሰው መግባት እንዳይችሉ እቀባ ተደርጎባቸዋል፡፡ ካህናት አባቶች እና ምእመናንም ያለአንዳች የሕግ መሠረት በየእስር ቤቱ ያለበቂ ምክንያት በሕገወጥ መንገድ ታጉረዋል፡፡ በጸጥታ ኃይል ከመጠን በላይ ከመደብደባቸው የተነሳ የሞት፣ የከባድ እና ቀላል አካል ጉዳት እንዲደርስባቸው ምክንያት ሆኗል፡፡ በአጠቃላይም በመንግሥት ኃይሎች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተፈፅሞባቸዋል፡፡

ቤተ ክርስቲያን ይህ ሁሉ በደል ቢፈጸምባትም ናዛዜ ሕዙናን የሆነው አምላካችን ለቤተ ክርስቲያናችን እና ለሀገራችን መፍትሔ እንዲያመጣልን፣ መንግሥትም ወደ ልቡ ተመልሶ ቤተክርስቲያንን እንዲያከብርና እንዲጠብቅ በሚል ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ይህን ጾም የነነዌ ሰዎች እንዳደረጉት ጥቁር ለብሰን በፍፁም ኃዘን ወደ አምላካችን እንድንጮህ ቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዝ ባስተላለፈበት ማግስት በሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሕገወጡን ቡድን በኃይል ለማስገባት በመንግሥት የጸጥታ መዋቅሮች በተወሰደ አሰቃቂ እርምጃ እስከ አሁን በደረሰን መረጃ ቁጥራቸው ከ፴ በላይ የሚሆኑ ካህናትን እና አገልጋዮችን ጨምሮ የቤተ ክርስቲያናችን ልጆች ቅጥሯ አይደፈርም፣ ቤተክርስቲያን በተወገዙ ግለሰቦች አትረክስም በሚል ለሃይማኖታቸው ሰማእትነትን ተቀብለዋል፡፡ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ልጆቿም በደረሰባቸው ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ምክንያት በሕክምና ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ ሁሉ በደል በኋላም እስከ አሁን ድረስ የሞቱትን በአግባቡ መቅበርና የተጎዱትን በበቂ ሁኔታ ማሳከም ሳንችል ቀርተናል፡፡ እነዚህ ሰማዕታት በዚህ ኃጢያት በበዛበት ዘመን ለቤተክርስቲያን እስከሞት ድረስ በመታመን ለቤተ ክርስቲያንና ለምእመናን የጽናት ተምሳሌት በመሆናቸው ቤተክርስቲያን ስትዘክራቸው ትኖራለች፡፡ እንዲሁም ቤተ ክርስቲያን በልጆቿ ላይ እየደረሰ ባለው ሞት፤ እርዛት፤ እስራት እና መልከ ብዙ በሆነው መከራ ብታዝንም ለክርስትና እውነተኛነት ምስክሮች የሆኑ አዳዲስ ቅዱሳን ሰማእታትን በማግኘቷም እጅግ ደስ ትሰኛለች፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🛑 ቅዱስ ሲኖዶስ በአሁን ሰዓት በቀጥታ ሥርጭት መግለጫ እየሰጠ ይገኛል።

መግለጫውን በቀጥታ ይከታተሉ
https://www.youtube.com/live/13MBP4QrczY?feature=share

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✝ሰበር የሀዘን ዜና✝

እዚህ ቪድዮ ላይ ተተኩሶበት መሬት ላይ ወድቆ ያያችሁት ወንድማችን ነፍሱ አርፋለች።

በረከቱ ይድረሰን። በሰማዕታት ጎን ያቁምልን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሰበር ዜና

ጥር 14 በሕገ ወጥ መንገድ በመሾማቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ከተወገዙት መካከል አንደኛው ዛሬ የካቲት 5/2015 ዓ.ም የይቅርታ ደብዳቤ ለማስገባት ጠቅላይ ቤተ ክህነት እንደሚገኙ ሰምተናል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ሰልፉ_ተራዝሟል "

ቅዱስ ሲኖዶስ ምንም እንኳን የአቋም ለውጥ ባያደርግም ትላንት በነበረው ውይይት መንግሥት የቤተክርስቲያናችንን ጥሪ በመቀበል የቤተክርስቲያናችንን ችግር ለመፍታት #በመስማማቱ ነገ ሊደረግ የታሰበው ሰላማዊ ሰልፍ መራዘሙን አሳውቋል።

በትናትናው ዕለት ከመንግሥት ጋር ባደረግነው ውይይት መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም ሙሉ በሙሉ የተቀበለ ቢሆንም ይህንን ለማስፈጸም የሚያስችል የአፈጻጸም የድርጊት ጊዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ እሁድ የካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም እንዲካሔድ የተወሰነው ሀገር ዓቀፍ እና ዓለም አቀፍ የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እግድ ተሰጠ ማለትም ክስ ቆመ ማለት እንዳልሆነ ያስታወሰው ኮሚቴው የምንጠይቃቸው የወንጀልና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ይቀጥላሉ ብሏል።

የፌደራል ፖሊስ ፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ የኦሮሚያ ፖሊስና ሰላም ሚኒስቴር እግዱን እንዲያስፈጽሙ ኃላፊነት የተጣለባቸው ተቋማት ናቸው።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

"በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት በፍፁም መንፈሳዊ መሪነትና ክብር ሄደናል፤ እግዚአብሔር ሰምቶናል፤ ከጠቅላይ ሚኒስትሩም ለጥያቄዎቻችን መልስ ተሰጥቶናል::" ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ

ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የነበረውን ውይይት አስመልክቶ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

በመግለጫውም ብፁዕነታቸው እንደገለጹት ትናንት በሰጠነው መግለጫ “በአስቀመጥነው ቅድመ ሁኔታ መሠረት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠርተን ጥያቄያችንን አቅርበናል፡፡ ጥያቄያችንም አንድ ነው ሕገ ቤተ ክርስቲያን ይከበር፤ በሀገሪቱ ያለው ኦርቶዶክሳውያን መብት ይጠበቅ፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሀብትና ንብረት በሀገሪቱ ሕግ መሠረት ንብረቷ ይጠበቅ፤ እነዚህ ካልሆኑ ወደ ሰላማዊ ሰልፍ እንሄዳለን ማለታችን ይታወሳል፡፡ በዚህም በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት በፍፁም መንፈሳዊ መሪነትና ክብር ሄደናል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በነበረን ቆይታ በደንብ ተወያይተንበት ለጥያቄዎቻችንም መልስ ተሰጥቶናል ብለዋል ብፁዕነታቸው፡፡ እንዲሁም ዝርዝር መግለጫውን ነገ የምንሰጥ ይሆናል ብለዋል፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

"የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕመም ሕመማችን ክብሯ ክብራችን ነው::" የሮም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን

የሮም ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የአጋርነት ደብዳቤ በፖፑ የክርስቲያን አንድነት ፕሬዝደንት በኩል ላከች::

ብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮህ የፖፕ ፍራንሲስ የክርስቲያኖች አንድነት ፕሬዝዳንት (President Pontifical Council for Prompting Christian Unity) እንደገለጹት "በተፈጠረው ችግር እና ሁኔታ ጥልቅ ሐዘን የተሰማን ሲሆን ለቅዱስ ሲኖዶስ ያለንን አጋርነት በመግለጽ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለመጠበቅ የሚደረግ ጥረትን በሙሉ እንደግፋለን" ብለዋል::

በመልእክታቸው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ በላከው የመጀመሪያ መልእክት “አንድም ብልት ቢሰቃይ ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሣቀያሉ፤ አንድ ብልትም ቢከበር ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።” 1ኛ ቆሮንጦስ 12፥26 ያለውን ጠቅሰው ሕመሟ ሕመማችን ክብሯ ክብራችን ነው ሲሉ በአጽንዖት ገልጸዋል።

በመጨረሻም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ እና የቤተ ክርስቲያን አንድነት እናት በምልጃዋ እጅግ የተከበረች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነቷና ደህንነቷ እንዲጠበቅ ታድርግልን ብለዋል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዛሬ ጠዋት የማኅበረ ቅዱሳን ደቡብ ማእከላት ማስተባበሪያ አስተባባሪ የሆነውን ዲ/ን መልካሙ ጸጋዬ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት ታፍነው ተወስደዋል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የተወደዳችሁ የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች።

👉የእሑዱ ሠላማዊ ሰልፍ የማይቀርበት ነው ስለዚህ ሁላችሁም ሀሞታችሁን ዋጥ አድርጋችሁ አንድ ላይ እንውጣ እና ለቤተክርስቲያን የከበርን ሙሽሪቶች እንሁን።

ግን ጥልቅ ማሳሰቢያ ንስሐ ያልገባን ካለን እባካችሁ ዛሬ እና ነገ ወደ ንስሐ አባቶቻችን በመሄድ ንስሐ እንግባ።

👉 የንስሐ አባትም ያልያዝን ወደ ቤተክርስቲያን ሄደን አባት እንያዝ እና ንስሐ እንግባ።


ሰማዕትም ብንሆን ንስሐ ገብተን ነው መሆን ያለበት። የሰማይ ቤታችንን በክብር እንድንገባበት

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በአሁኑ ሰአት ቴሌግራም ያለ PROXY እና ያለ VPN እየሰራ አይደለም!!!

አልሰራ ላላችሁ: /channel/proxy?server=195.154.42.206&port=443&secret=ee0000006b742e6d6f62696c652e69722e6d6f62696c652e6972

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንዲሁም ሀዘናችሁ ሀዘናችን ነው ብላችሁ ከጎናችን የተሰለፋችሁ አኃት አብያተ ክርስቲያናት፤ የሃይማኖት ተቋማት፣ ድርጅቶች እና ጉባኤያት፤ የእስልምና እምነት ተከታዮች፤ በእምነት የማትመስሉን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ስላደረጋችሁልንና ስለምታደርጉልን እርዳታና ትብብር በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እናመሰግናለን፡፡

የካቲት 2 ቀን 2015 ዓ.ም ከተሰጠው የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ የተወሰደ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጅማን ይባርክሽ ተብሎ ተመደበላት ወጠጤ ይህ ነው እንግዲ!❌

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#Update

ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ " የሰልፍ ክልከላ " መግለጫ ትላንት ምሽት የመንግስት የጋራ ግብረኃይል የሰጠውን መግለጫ እንደማይቀበለው አስገንዝቧል።

ቅዱስ ሲኖዶስ የትላንቱ የመንግስት መግለጫ " መንግሥት አሁንም ችግሩን ለመፍታት ሳይሆን ቤተክርስቲያኒቱን ለአንዴና ለመጨረሻ ለማውደምና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት የታወጀ አዋጅ መሆኑን በጽኑ እንድናምን አድርጎናል " ብሏል።

(ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጾሙ ከተጀመረም በኋላ ሕዝቡ ወደ አምላኩ እንዳይጮህ እና እንዳይጸልይ ለማወክ የሕዝብ አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙ የመንግሥት ሹማምንት ሊያገለግሉት ኃላፊነት የተቀበሉበትን የሀገሪቱን ሕግ ጥሰው ምእመናን ልጆቻችን ጥቁር ለብሰው ወደ መሥሪያ ቤት እንዳይገቡና በመንግሥት ቢሮዎችም አገልግሎት እንዳያገኙ በተለይም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እና አንዳንድ በፌዴራል እና በከተማ መስተዳድር ቢሮዎች ጥቁር የለበሱ እና በሀዘን ላይ ያሉ ልጆቻችንን በማሠር ሲያንገላቱ በዓይናቸው ያዩ ምስክሮች አረጋግጠውልናል፡፡ በዚህም ሹማምንት ስልጣናቸውን ቤተ ክርስቲያንን ለማጥቃት እየተጠቀሙበት መሆኑን እና ለቤተ ክርስቲያናችንም ሆነ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ከፍተኛ ንቀት እና ጥላቻ ያላቸው መሆኑን ተረድተናል፡፡

ይህ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እየደረሰ ያለው መከራና በደል በዚህ ዘመን በጉልህ የሚጠቀስ የቤተ ክርስቲያን የስደትና የመከራ ጊዜ ነው፡፡ ይህ የቤተ ክርስቲያን የስደትና የመከራ ጊዜ በቤተ ክርስቲያኒቱ የታሪክ መዝገብ እና በመጽሐፈ ስንክሳር ተመዝግቦ ይቀመጣል፡፡ ለትውልድም ይተላለፋል፡፡ ይህ የፈተና ዘመን ያልፋል፤ ነገር ግን በዚህ ታሪክ ውስጥ ከእውነት ጎን የቆማችሁ ስማችሁ በታሪክ እና በወርቅ ቀለም ሲፃፍ በቤተክርስቲያን ላይ መከራ ያበዛችሁ ክፉ ታሪካችሁን ዛሬ በእጃችሁ ጽፋችሁ አልፋችኋል፡፡

በዚህ አጋጣሚ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውጭ ሌሎች የክልል ርዕሳን መስተዳድሮችና ከተሞች በተለይም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፤ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት፤ የሲዳማ ክልላዊ መንግስት፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት፤ የሱማሌ ክልላዊ መንግሥት፤ የቤንሻንጉል ክልላዊ መንግሥት፣ የሐረሪ ክልላዊ መንግሥት፣ የአፋርና ጋምቤላ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት፤ በጎፋ ዞን የሳውላ ከተማ እና ሌሎች ስማቸውን ያልጠቀስናቸው መንግሥታዊ ተቋማት የቤተ ክርስቲያናችንን ጥሪ በመከተል በአግባቡ ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር የወሰዳችሁ ፍትሐዊ እና ሕጋዊ መፍትሔዎችን እናደንቃለን፣ በቤተ ክርስቲያንም ስም እናመሰግናለን፡፡ እንዲሁም ሀዘናችሁ ሀዘናችን ነው ብላችሁ ከጎናችን የተሰለፋችሁ አኃት አብያተ ክርስቲያናት፤ የሃይማኖት ተቋማት፣ ድርጅቶች እና ጉባኤያት፤ የእስልምና እምነት ተከታዮች፤ በእምነት የማትመስሉን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ስላደረጋችሁልንና ስለምታደርጉልን እርዳታና ትብብር በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እናመሰግናለን፡፡
ጸሎተ ምሕላውን ስናውጅ መንግሥት ሕግ አክብሮ እንዲያስከብር፣ የቤተክርስቲያኒቱን ክብር እና ልዕልና እንዲያከብር፣ በሃይማኖታችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆምና ወደ ውስጡ ማየት እንዲችል ነበር:: ይህ ድርጊት እስከ አሁን ድረስ ግን መንግሥት ለዘመናት ሕጋዊ ተቋም እና የሀገር ባለውለታ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያንን ከመስማት እና ችግሯን ከመቅረፍ ይልቅ የማዋከቡን ሥራ አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ በዚህም መንግሥት ችግሮችን ኃላፊነት ተሰምቶት እንዲፈታ ያደርገዋል የሚል እምነት ቢኖረንም አገዛዙ ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ልቡ መደንደኑን መመልከታችን በእጅጉ ልባችንን ሰብሮታል፡፡

በተለይም ቤተ ክርስቲያናችን ያወጀችው የ፫ ቀናት ጸሎትና ምህላ በአግባቡ እንኳን ሳይጠናቀቅ ከመንግሥት ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይን አስመልክቶ በየካቲት ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የተሰጠው የሰልፍ ክልከላ መግለጫ መንግሥት አሁንም ችግሩን ለመፍታት ሳይሆን ቤተክርስቲያኒቱን ለአንዴና ለመጨረሻ ለማውደምና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት የታወጀ አዋጅ መሆኑን በጽኑ እንድናምን አድርጎናል፡፡

በመግለጫውም፡-
፩ኛ. በእምነቱ አባቶች በተመሳሳይ መልኩ ሰልፍ ተጠርቷል በማለት መጥቀሱ የቤተክርስቲያን የመጨረሻው አካል የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ የለያቸውን አካላት የእምነቱ ተከታይ ማድረግ ብቻ ሳይሆን መብት ያላቸው ሕጋዊ አካላትና የቤተ ክርስቲያን አባቶች አድርጎ መጥራቱ አሁንም ላይ ማብራርያ ለመስጠት መሞከሩ የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር የሚነካ እና የሚያጠለሽ እንዲሁም ሕግና ሥርዓትን ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጦች ጠበቃ ሆኖ የሚከራከረው መንግሥት መሆኑን ጭምር ለመረዳት ችለናል፡፡ በመሆኑም ቤተክርስቲያን በመንግሥት የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ተሰጠ የተባለው መግለጫ የቤተ ክርስቲያናችንን ሕጋዊ መብት የገፈፈ እና ሕገ ወጥ መግለጫ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያን አትቀበለውም፡፡

፪ኛ. ጉዳዩን የውጪ እና የውስጥ ጠላቶች የፈጠሩት ነው በማለት የተለመደውን ፖለቲካዊ ቅርፅ ለማስያዝ መሞከርም ቤተክርስቲንያንም ሆነ ሕዝብን መናቅ በመሆኑ የምንቀበለው አይሆንም፡፡ ቤተ ክርስቲያን በተለይ ላለፉት ፬ ዓመታት በሀሰተኛ ትርክት ልጆቿ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል መከራን ሲቀበሉ ችግሮችን በሆደ ሰፊነት ችላ ያለፈችው የሀገር መሠረት እንዳይናጋ፣ ቅጥሯ እንዳይደፈር በማሰብና በሀገር አንድነት ላይ ባላት የማይናወጽ ጽኑ አቋም ምክንያት መሆኑን መንገር ለቀባሪው ማርዳት ነው፡፡ ጉዳዩ ግልፅ የሆነ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ሆኖ እያለና መፍትሄውም በመንግሥት እጅ የሚገኝ ብቻ መሆኑ እየታወቀ የፖለቲካ ቅርፅ ለማስያዝ መሞከር ችግሩን ያባብሰው እንደሆን እንጂ አይፈታውም፡፡

በሰሞኑም ቤተ ክርስቲያናችን በመዋቅር የምትመራ እና ልጆቿም ድምጽዋን አውቀው በአግባቡ የሚሰሟት መሆኑ እየታወቀ ሆነ ተብሎ ቃላት አጠቃቀሙ እንኳን ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ የሀሰት እና ጸብ አጫሪ የሆኑ መልእክቶችን በአደባባይ የተለጠፉ መሆናቸውን ሲታይ ምን ያህል ጉዳዩን ላልተገባ ፖለቲካዊ ጥቅም እንደተፈለገ ለመረዳት ችለናል፡፡ ይህ ተለጠፈ የተባለውም ሕገ ወጥ ጽሑፍ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ያልሆነና ፈጽሞም ሊሆን የማይችል መሆኑን ጭምር ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

፫ኛ. የትኛውም ሰልፍ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ማድረግ አይቻልም በማለት የተደረገው ክልከላን በተመለከተም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ውስጥ መሠረታዊ መብት ሆኖ የተጠቀሰ እና በሕገ መንግሥቱም አንቀፅ ፴ ላይ በግልጽ የተደነገገ በመሆኑ መንግሥት ራሱ የሚመራበትን ሕገ መንግሥት ማክበርና ማስከበር ይኖርበታል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከላይ የተጠቀሰው ከፍተኛ መከራና በደል ምክንያት ከብዙ ሺህ ዓመታት በላይ ጸንታ የመጣችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በእኛ በልጆቿ ዘመን ስትፈርስ ዝም ብሎ መመልከት በጭራሽ የሚታሰብ አይሆንም፡፡

   ይህን በደላችንን ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ለማሳወቅ እና መንግሥትም ከሚያደርገው ጣልቃ ገብነትና አፈና ወጥቶ ሕግ እንዲያከብር እና እንዲያስከብር የጠራነው የየካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍም መንግሥት ተገቢውን ጥበቃ በማድረግ እንድናከናውን መፍቀድ አሊያም የጠየቅናቸውን ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄዎቻችንን በአግባቡ እና አንድ በአንድ መመለስ አማራጭ የሌለው መፍትሔ መሆኑን ደግመን ደጋግመን ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

   በዚህ ሂደት ውስጥም የሚደርስብንን ሞት፣ መከራና ስደት እኛ አባቶች ከመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ጋር ደስ ብሎን የምንቀበለው እንጂ ቤተ ክርስቲያናችን እና ሀገራችን ስትፈርስ ቆመን የምንመለከት፣ ዝም የሚል አንደበትና የሚሸከም ኀሊና የማይኖረን መሆኑን በአጽንዖት እናሳስባለን፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አባቶቻችን አንድና አንድ የሌለው ቁርጥ መግለጫ ለመንግስት ሰተዋል።

እኛንም የአባቶቻችሁን ትዕዛዝ ጠብቁ በየአካባቢያችሁም ያሉትን አድባራት ተደራጅታችሁ ጠብቁ ተብለናል። እኛም ተቀብለናል!

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በወለቴ ያለችው ቤተክርስቲያን ትጣራለች!
በሻሸመኔ የብዙ ንፁሀንን ደም ያፈሰሰው ሕገ ወጡ ቡድን በመንግስት በታጠቁ ኃይሎችን ወደ ቤተክርስቲያኗ እየተኮሰ ይገኛል !

በወለቴ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን በከባድ መሳሪያ የታገዘ ድብደባ እየተፈፀመ ይገኛል እስከ አሁን ሁለት ሰዎች እንደተመቱ መረጃዎች ቢያሳዩም ከፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ግን የታየ ምላሽ የለም!

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ለሁሉም share አድርጉ
ይህ መረጃ እውነት ሆነም ውሸት መዘጋጀቱ አይከፋም። ለሁሉም ሙስሊም ወንድም እህቶቻችን አድርሱ።

ለግዜው እኛ ኦርቶዶክሳዊያን አባት እንጂ መንግስት የለንም የምንጠብቀውም የአባቶቻችንን ጥሪ ነው።

Читать полностью…
Подписаться на канал