ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንኳን ለአባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

#ለሀገር_ኢትነ

ለሀገር ኢትነ ሰላማ ኪያከ ተአቅብ
አባ ኦ አባ(2) ገብረ መንፈስ ቅዱስ

በዘማሪት #ገነት

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የመፃጉዕ - አልጋ

ጸሐፊ - ትዕግስት
አንባቢ- ዓ.ማርያም
ለእህታችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#የአንተ_ሥራ

የአንተ ሥራ የአንተ ሥራ
የአንተ ሥራ ለዓለም ይወራ (፪)

በዮሐንስ ወንጌል በምዕራፍ አምስት
መጻጉዕ ተብሎ ተኝቶ ባዐራት
ዘመን ያስቆጠረ ሠላሳ ስምንት
ተነሳ ተባለ አገኘ ምህረት
#አዝ
ሰውነቱ ደቆ እጅግ የታመመ (፪)
በሱ ድንቅ ስራ አልጋ ተሸከመ (፪)
#አዝ
ወገን ያልነበረው ወድቆ የተረሳ (፪)
ምሕረት አገኘና በድንገት ተነሳ (፪)
#አዝ
ያዳነው ኢየሱስ መሆኑን ሲናገር
ያልተፈቀደውን ይሄው ሰንበት ሲሽር
አየነው ሰማነው አያሻም ምስክር
ብለው ተነሱበት በጠማማ ምክር

መዝሙር ሊቀ መዘምራን
ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ

"ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ"
ዮሐ፭፥፰

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የቤተክርስቲያን ችግሮች እና ዘለቄታዊ መፍትሔ ጥናትና ትግበራ ኮሚቴ በሚል ስያሜ የተቋቋመው እና ከሁሉም የሞያ ዘርፎች የተውጣጡ የቤተክርስቲያን ልጆችን ያቀፈው ቡድን ወደ ትግበራ ሊገባ ነው።

ኮሚቴው የጥናታዊ ጽሑፍ በማቅረብ አላማውን እና የአሰራር ሂደቱን ያብራራ ሲሆን ሰፊ ውይይት አካሂዷል።

በቅድስት ቤተክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ከዶግማ በስተቀር ከላይ ጀምሮ እስከ ታች ድረስ ያሉችግሮችን ለማስተካከል እንደሠራም ተገልጿል ።

ውጤቱን በተመለከተ ቤተክርስቲያን የራሷ መንፈሳዊ ፍርድ ቤት እንዲኖራት ማድረግን ጨምሮ 25 ዝርዝር ነጥቦች ላይ አተኩሯል። ከ90በላይ አባላትን በጥናት ያሳተፈው ኮሚቴ በ14ቡድኖች ተዋቅሮ ስራውን በቅርቡ ይጀምራል ።

ምንጭ: EOTC TV

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በዚህም መሠረት ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በክልል ትግራይ ደቡባዊ ዞን ማይጨው፣ የደቡባዊ ምሥራቅ ትግራይ አህጉረ ስብከት፣ የቅርስ ጥበቃና ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያና የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ሔኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ም/ዋና ሥራ አስኪያጅና ሊቀ ትጉሃን እስክንድር ገብረ ክርስቶስ የጠቅላይ ቤተክህነት ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ የድጋፍ ማሰባሰቡን ሥራ እንዲያስተባብሩ በቋሚ ሲኖዶስ መመረጣቸውን በመጥቀስ ለተቋቋመው ዐቢይ ኮሚቴ በጻፈው ደብዳቤ ድርቁ በተከሰተበት ቦታ በመገኘትና በድርቁ የደረሰውን ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት ዕርዳታውን እንዲያሰባስቡና ለተጎጂዎች እንዲያደርሱ አሳስቧል።

ይህንን ተከትሎ ዐቢይ ኮሚቴው በቅርቡ ስብሰባ በማድረግ የተጣለበትን ከባድ ኃላፊነት ለማስፈጸም የሚያስችለውን እቅድ በማውጣት ወደ ተግባር የሚገባ መሆኑ ታውቋል።

ምንጭ፡ የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ይህንንም ተከትሎ መንግሥት ራሱ ለገባው ቃል ተገዢ እየሆነ አይደለም ያሉት ጠበቃው በዚህም ምክንያት ካህናትና ምዕመናን ለበርካታ ችግሮች ተጋልጠዋል ቤተ ክርስትያኗም ጉዳት እየደረሰባት ይገኛል ብለዋል፡፡

ጠበቃው አክለውም ቤተ ክርስቲያኗ ከመንግሥት ጋር የደረሰችው ስምምነት በመንግሥት በኩል ሊደረግ ታስቦ የነበረውን ሰልፍ የማስቀረት ጉዳይ ብቻ ተደርጎ መታየት የለበትም ያሉ ሲሆን አሁን ባለው ሁኔታ ችግሩ እየከፋ መሄዱን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕገ ወጥ የኤጲስ ቆጶሳት ሹመትን አከናውነዋል ካለቻቸውና ከተሾሙ አባቶች መካከል ይቅርታ ጠይቀው ወደ ቤተ ክርስትያኗ የተመለሱ መኖራቸው የሚታወስ ቢሆንም ይቅርታ ያልጠየቁ ግለሰቦች ግን በፍርድ ቤት የተጣለባቸውን እግድ በመጣስ ከመንግሥት በተለይም በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የጸጥታ ኃይሎች በመታገዝ ተዳጋጋሚ የሕግ ጥሰቶችን እየፈጸሙ ይገኛል፡፡

“ምዕመናኑ ምንም እንኳን በሚፈጸሙ ድርጊቶች ያዘኑ ቢሆንም የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ትዕዛዝ እየተጠባበቁ ይገኛሉ።” ያሉት ጠበቃ አያሌው “መንግሥት የገባውን ቃል አለመፈጸሙ፣ በሕግ እንዲያስፈጽም የተሰጠውን ኃላፊነት አለመወጣቱ እና የያዘው አካሄድ ሕዝብና ሀገርን ዋጋ የሚያስከፍል ነው” ብለዋል፡፡

ለዚህም እስከ ዛሬ ማክሰኞ ድረስ ሁሉንም ጉዳዮችና የሕግ ጥሰቶች ለማስተካከል በኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት ሽመልስ አብዲሳ የተገባው ቃል እንዲፈጸም የጠየቁት ጠበቃ አያሌው የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ወደ ከፋ ነገር ሳያመራ መንግሥት ኃላፊነቱን በአግባቡ እዲወጣ ጠይቀዋል፡፡

በተያያዘ ዜና በአዋሽ ሰባት ከታሰሩ ወጣቶች መካከል ከ300 በላይ የሚሆኑት መለቀቃቸው የተሰማ ሲሆን ወጣቶቹ ብፁዓን አባቶች በቦታው ሊያደርጉት የታሰበው ጉብኝት መሰማቱን ተከትሎ መፈታታቸው ተነግሯል፡፡

ይሁንና አሁንም ድረስ በቦታው ታስረው የሚገኙ ወጣቶች እንዳሉ ይታወቃል በዚህም ታሳሪዎች እንዲፈቱ ጊዜያዊ የሕግ ኮሚቴው እየሠራ እንደሚገኝ ታውቋል ሲል አዲስ ማለዳ በፌስ ቡክ ገጹ አስነብቧል፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​አዲስ አበባ ፈረንሳይ ጉራራ ምሥራቀ ፀሀይ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቶስ ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት

''የጻድቃን መታሰቢያ ለበረከት ነው''
ምሳ 10÷7

ጉዞ ወደ ምድረ ከብድ አቦ
መነሻ :- መጋቢት 4
መመለሻ :- መጋቢት 5

ዋጋ 500 ብር

መመዝገቢያ ቦታ
- በሰንበት ትምህርት ቤት ጽህፈት ቤት ቢሮ
- በኪዳነ ምሕረት መዝሙር ቤት
- በደብሩ የእለት ገንዘብ መቀበያ ቢሮ

ለበለጠ መረጃ
📞 09 09 26 96 97
📞 09 34 46 94 82

አዘጋጅ
ጉራራ ምሥራቀ ፀሀይ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት እና ቅዱስ ገብርኤል ጽርሐ ጽዮን ሰ/ት/ቤ/ት

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ስለ_ዳግም_ምፅዓት
(አቶ አለሙ አጋ በገና)
ቅኝት - ሰላምታ

እንዲህ አርገን ሥራውን ሁሉ አምነን
እናምናለን ዳግም ይመጣል ብለን
ነገር ግን ዳግም ይመጣል ስላልን
ከፃድቃን ከመላእክትም ቢሆን
የሚያውቅ የለም የሚመጣበት ቀኑን
ባላወቅነው ባልመረመርነው ሰዓት
ግሩም ሆኖ ይመጣል እንጂ ድንገት
መጀመሪያ የአዋጅ ነጋሪት ሲመታ
ከያለበት ይሰበሰባል በአንድ አፍታ
አጥንታችን ትቢያ የሆነው አፈር
ጅብ የበላው የተበተነው ከዱር
የራስ ፀጉር የእግር ጥፍራችን ሳይቀር
ተሳስቶ የአንዱ ወደ አንዱ ሳይዞር
በየራሱ ይሰበሰባል ሁሉም
ይመታል የአዋጅ ነጋሪት ዳግም
ነፍስ የሌለው በድን ይሆናል ፍፁም
በሶስተኛው የአዋጅ ነጋሪት ሲመታ
ይነሳሉ መልካም የሠሩ በእልልታ
የብርሃን ልብስ የብርሃን ቀሚስ ለብሰው
እንደ ፀሐይ እንደ ጨረቃ ደምቀው
እግዚአብሔርን ፈጣሪያቸውን መስለው
ይሰሙና በቀኙ ቆመው ፍርዱን
ከማያልፈው ተድላ ደስታ በቀር
ጠግቦ ቁንጣን ተርቦ ስስት ሳይኖር
ገብቶ መውጣት አግኝቶ ማጣት ችጋር
የሌለባት ደገኛይቱን ሀገር
ይወርሳሉ መልካም የሠሩ በምድር
ኃጥአንም እጅግ ከጭራ ቀጥነው
መልካቸውም እጅግ ከቁራ ጠቁረው
ከላይ ከታች የጨለማ ልብስ ለብሰው
ዲያብሎስን አለቃቸውን መስለው
ይሰሙና በግራ በኩል ቆመው
በመንቀጥቀጥ የሚፈርደውን ሰምተው
ከልቅሶና ጥርስ ማፋጨት በቀር
ተድላ ደስታ የሌለባትን ሀገር
ይወርሳሉ ክፉ የሠሩ በምድር
እንዲህ አርገው መጻሕፍት ሁሉ እንዳሉ
በየሥራው ይከፈለዋል ለሁሉ
ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ
ለዓለም ወለዓለመ ዓለም አሜን

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በጾም

በጾም ትትፌውስ ቁስለ ነፍስ
ወበጸሎት ትትሐሠይ መንፈስ /2/

መአልትና ሌሊት በጾም ጸሎት ተግቶ
አሳይቷል ጌታ ስርዓትን ሰርቶ
አይቀርም ፈተናው ትጋት ከሌለበት
ስጋ ካልደከመች በጾምና ጸሎት
አዝ
ሙሴ የተባለው ያ የእግዚአብሔር ሰው
ፊቱን የበራለት አርባ ቀን ጾሞ ነው
በሲና ተራራ ተቀብሎ ህግን
እርሙን እንድንተው አሳየን መንገድን
አዝ
የጸሎት እናቷ ስለሆነች ጾም
ትህትናን ይዘን ደግሞም አንድ ሆነን
ብንተጋ በጸሎት ከንስሐ ጋራ
ጾም ታደርሰናለች ከጽዮን ተራራ
አዝ
አንድበትም ይጹም ዓይንም ይረጋጋ
ጆሮም ክፉ ሰምቶ ነፍሱን እንዳይወጋ
ድሀን ከመበደል ልብም ተመልሶ
መጾምስ እንዲህ ነው የበደለን ክሶ

ዘማሪ መምህር አቤል ተስፋዬ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በምእራብ ሐረርጌ ጭሮ ከተማ በሚገኘው በደብረ ሲና ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ ዝርፊያ መፈጸሙ ተገለጸ፡፡

በምእራብ ሐረርጌ ጭሮ ከተማ በሚገኘው በደብረ ሲና ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ዛሬ የካቲት 25 ቀን 2015 ዓ.ም ኪዳን እናደርሳለን ባሉ ከሕገ ወጡ ተሿሚ ወገን በሆኑ 4 ግለሰቦች አማካኝነት ከቤተ ክርስቲያኑ ሽቶ፣ ዕጣንና መብዓት ይዘው ሲወጡ መያዛቸውን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሁኔታውን የተመለከተው የቤተ ክርስቲያኑ ጠባቂ ጥይት በመተኮስ ምእመናን ተሰብስበው ሁለቱ ግለሰቦች ሊያዙ ችለዋል፡፡ ዝርፊያ የፈጸሙት ግለሰቦችን ምእመኑ ለከተማው ፖሊስ ያስረከበ ቢሆንም የከተማው ፖሊስ ግን ግለሰቦቹ ይህንን አያደርጉም አውቃችሁ ነው በሚል ያለምንም ማጣራት ግለሰቦቹን መልቀቁ ተገልጿል፡፡

በአንጻሩ የቤተ ክርስቲያኑን ጠባቂ ለምን ወደ ሰማይ ተኮስክ በሚል ማሰራቸውን ለመረዳት ችለናል፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ቅዱስ ላሊበላ ቤተ ገብርኤል ቤተ መቅደስ መግቢያ ድልድይ እየተሠራ እንደሆነ ተገለጸ።

የቤተ ገብርኤል ቤተ መቅደስ በቅዱስ ላሊበላ ከታነጹት 11 ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዱ ሲሆን የቤተ መቅደሱ መግቢያ ከቤተልሔሙ የጸሎት ቤት ፊት ለፊት በምሥራቅ በኩል ይገኛል። በሌላ በኩል ከቤተ አማኑኤል ቤተ መቅደስ በሚመጣ ተሻጋሪ ድልድይም መግባት የሚቻል ሲሆን ድልድዮቹ ከዛፍ ግንዶች ርብርብ እንደተሠሩ ርዝመታቸውም 10 ሜትር መሆኑ ይነገራል።

በዛሬው ዕለት ወደ ቤተ ገብርኤል ቤተ መቅደስ መግቢያ ድልድይ በፈረንሣይ ላሊበላ ዲቨሎፕመንት ፕሮጀክት አማካኝነት እየተሠራ እንደሚገኝ የቅዱስ ላሊበላ ገዳም ጽ/ቤት በፌስቡክ ገጹ አስነብቧል፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#የአድዋ_ድል_ቤተ_ክርስቲያን_በገነባችው_የሥነ_ልቡና_ልዕልና_የተገኘ_ነው::

ክፍል ሦስት
አፈ ሊቅ አክሊሉ ገብረ ኪሮስ የተባሉ ሊቅ ‹‹ለኢትዮጵያ ታሪኳ-ነው መልኳ›› በተሰኘው መጽሐፋቸው የአድዋውን ድል መሠረት እንደሚከተለው ገልጠዋል።
‹‹… ምኒልክን ለአድዋው ድል ያበቃቸው
አንዱም ፣ ኦርቶዶክሳዊ እምነታቸውና የልብ ጸሎታቸው ነው።›› (ገጽ፣፷፭)
ዳንኤል ሮኘስ የተባለ ታዋቂ የፈረንሳይ ጋዜጠኛ ‹‹የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ታውቋታላችሁን?›› በሚል ርእስ ባዘጋጀው መጣጥፍ ላይ የሚከተለውን አስፍሯል።
“ወራሪዎች ምድርዋን የያዙባት መሆኑን ታሪክ ያወሳል፤
ነገር ግን ሃይማኖት የእንቅስቃሴ መሣሪያዋ ሆኖ በመገኘቱ በነፃነት ተመልሳ ተገኝታለች››
የአድዋን ድል በቀጥታ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ጋር ያያያዙት ሌሎችም ኢትዮጵያን በአፍሪካ እንደምትገኝ ኢየሩሳሌም አድርገው መቍጠር ጀምረው ነበር። ፕሮፌሰር ሬይሞንድ ጆናስ ‹‹ THE BATTLE OF ADWA:-African victory in the age of Empire›› በተሰኘው ታሪካዊ መጽሐፋችው ‹‹የዓድዋን ድል ተከትሎ በመላው ዓለም ተበትነው ያሉ ዝርዋን አፍሪካውያን የዓድዋን፣ የምኒልክንና የነጻይቱን አገር ኢትዮጵያን ስም በልዩ ሁኔታ ማንሣት ጀመሩ፤ ጥቁር ሕዝቦች እንደ ታላቂቷ ጽዮናዊት ኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጵያ ሃይማኖታዊ ጉዞ ማድረግ ጀመሩ።›› ሲሉ መግለጻቸው ለዚህ ምስክር ነው።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የኢትዮጵያ ገበዝ
የኢትዮጵያ ጠባቂ
የቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦት ላይ መንግስት ተኩስ ከፍቷል! ምዕመኑ በዓሉን ማክበር ታቦቱን ማንገስ አልቻሉም።

ተዋግቶ ኢትዮጵያን ላስከበራት ለቅዱስ ጊዮርጊስ መሳርያ ይገባዋል???‼️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት መቐለ አሉላ ኣባነጋ ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ በሰላም ገብተዋል።

በአየር ማረፊያው ሲደርሱ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የቤተ ክህነት ሠራተኞች እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እና ምእመናን አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መች ይረሳል
የበገና መዝሙር

መች ይረሳል የዋለልን ውለታ
ቸርነቱ እፁብ ፍቅር የጌታ
የታተመው በልባችን ፅላት
ሞትን ገድሎ የሠጠንን ህይወት

በጥፋቱ ቢወጣ አዳም ከገነት
ቃል ገባለት ዳግም ሊሰጠው ህይወት
ህያው ጌታ አምላክ ፈጣሪ ሳለ
ስለ ቃሉ በእፀ መስቀል ላይ ዋለ
አዝ
በአይሁድ እጅ በፅኑ ተንገላታ
የፍቅር አባት ክርስቶስ የእኛ ጌታ
ሥጋው ደክሞ ቅዱስ ደሙ ፈሰሰ
እዳችንን በሞቱ ደመሠሠ
አዝ
ስንጠላው እርሱ አብዝቶ ወደደን
ስለ ፍቅሩ ሞትን ገድሎ አዳነን
ባርነትን ኃጢአትን ከኛ ጥሎ
ነፃ አወጣን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ
አዝ
ሰላማችን የድንግል ማርያም ፍሬ
ይገባዋል ምስጋና ዝማሬ
ስለ ፍቅሩ ስላረገልን ሁሉ
ተቀኙለት ፍጥረታት ዝም አትበሉ

መምህር አቤል ተስፋዬ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​​​✝ እንኳን ለአባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓለ እረፍታቸው በሰላም አደረሰን!

🕕 ቀኑ መጋቢት 5 ዕለቱ ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ሰዓቱ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ሆኗል፤ አሁንም ህማሙን እየታገለ እያላበው በድካም ለፍጥረቱ ሁሉ ይለምናል፤

“አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህን ኢትዮጰያንም ባርክ” ይላል።

ህመም የጀመረው መጋቢት 3 ዓርብ ቀን ነው፤ መታመሙን የሰሙ እንደርሱ ቅዱሳን የሆኑት ዘርአቡሩክ፤ ፍሬ ቅዱስ፤ ያዕቆብ፤ ብንያምና ዮሴፍ እንዲሁም በወቅቱ የኢትዮጰያ ንጉስ የነበረው እንድርያስ ሊጠይቁት ተሰብስበዋል ወደ አጠገቡ መድረስ ግን አልተቻላቸውም አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ የሚጋርደው እንጨት ዛፍ በሌለበት በርሃ እንደ አንበሳ ተኝቶ አዩት በላዩ ያረፈው የእግዚአብሔር ጸጋ ከፊቱ የሚወጣው ብርሃን ቀይ መልኩ ረዥም የራስ ጠጉሩ እንደ ነጭ ሐር የሚሆን ጽሕሙ አስደነቃቸው።

ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ሲሆን ከሰማይ ታላቅ ነጎድጓድ ድምጽ ተሰማ ጌታችን መላአክትን አስከትሎ ወደ አባታችን ወረደ፤ ከሰማይ ወደ ምድር ህብሩ አምሳያው ልዩ ልዩ የሆነ እንደ ጸሐይና እንደ ጨረቃ የሚያበራ እንደ ወንጪፍ ድንጋይ ይወረወር ነበር ከዚያ የነበሩ ሁሉ ፈሩ ወደ ኋላም ሸሹ ምድር ራደች ተራሮች ኮረብቶች ተናወጡ ብርቱ ጩኸት ንውጽውጽታ ሆነ።

“ወዳጄ ገብረመንፈስ ቅዱስ ሰላም ላንተ ይሁን” እነሆ የማይታበል ቃል ኪዳን እገባልሃለው ስምህን የጠራ መታሰቢያህን ያደረገውን እጣን ቋጥሮ ግብር ሰፍሮ መባ ይዞ ቤትህ የመጣውን እምርልሃለው አንተ ከገባህበት ገነት መንግስተ ሰማያት አገባዋለሁ አለው፤

አባታችንም “አቤቱ ጌታ ሆይ የኢትዮጰያን ህዝብ ማርልኝ” አለው፤ እነሆ ምሬልሃለው አስራት በኩራት አድርጌም ሰጥቼሃለው፤ ከመጋቢት አምስት ቀን ጀምሮ ዝክርህን ያድርጉ በአማላጅነትህም ይማጸኑ አለው።

ከዚህ በኃላ ሰባቱ ሊቃነ መላክት የአባታችንን ነፍስ ሊቀበሉ ወረዱ በታላቅ ምስጋናም ወደ ሰማይ አሳረጉት ስጋውንም ይዘውት ሄዱ የት እንደተቀበረ ግን እስካሁን አይታወቅም አንዳንዱ በእየሩሳሌም ነው ይላሉ፤ ሌላው በምድረ ከብድ ነው ይላል ግን እስካሁን ልክ እንደ ሊቀ ነብያት ሙሴ ስጋ የት እንደ ተቀበረ አይታወቅም።

ገድሉ ትሩፋቱ ከሰማይ ከዋክብት ከምድር አሸዋ ይበዛል ኢትዮጰያን አብዝቶ ይወዳታል፤ ምድራዊ ምግብ አልተመገበም የእናቱን ጡት እንኳን አልጠባም፤ ልብስ፤ መጠለል አልፈለገም፤ የክረምት ቁር የበጋ ሐሩር እየተፈራረቀበት በተጋድሎ 562 ዓመት ኖረ፤ በዛሬዋ ቀን #መጋቢት_5 ሩጫውን ጨረሰ።

ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን እኛንም ከአባታችን በረከት ያሳትፈን፤ ከመጣብን ክፉ መቅሰፍት ይሰውረን! አሜን።

👉 መጽሐፈ ስንክሳር ዘመጋቢት

#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✞ መፃጕዕ

ሰው የለኝም ያለ በሠው የተረሳ
የዳነው መፃጕዕ ያዳነውን ረሳ

በአምስቱ እርከኖች በአእማደ ምስጢራት
ቤተ ሣይዳ ላለች ከመቅደስ ላኖርካት
በበደል ለምናዝን ምህረትን ፍለጋ
በንስሐ ማረን ከዓራተ ዝንጋኤ ከኃጥያት አልጋ
አዝ
በጠበሉ ደጃፍ ለፀኑት የሚላክ
ለቀድሶተ ማይ የሚወርደው መልዐክ
በመንገድ ጠብቆ ሞትን የሚያሳልፍ
ዛሬም ይድረስልን ቀድመው ከገቡት ጋር ነፍሳችን እንድታርፍ
አዝ
አልጋው ተሸክሞት ደክሞ ለሚጨነቅ
አልጋን አሸክመህ ህመም የምታርቅ
ደዌያችንን ነስተህ ቆስለህ የምትፈውስ
የመፃጕዕ ረዳት የነፍሳት መጠጊያ መድኃኒት ክርስቶስ
አዝ
የባሰ እንዳያየው ቃሉን ያልጠበቀ
እጁን ሰዶ ፀፍቶ ከደዌው ታረቀ
ሰንበትን የሻረ ከሚሉት እንዳንውል
ለትንሳኤው ደስታ የሰንበትን ጌታ ዓርብን እንከተል

ዘማሪ ዲ/ን ቀዳሜፀጋ ዮሐንስ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​​​የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት #መጻጒዕ

እንኳን አደረሳቹ የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት መጻጒዕ ለ 38 ዓመት በአልጋ ላይ ተኝቶ የሚኖር አንደ ሰው ነበረ እርሱም #መጾጒዕ ይባላል።

((ዮሐ5፥1-11)) ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነበረ ኢየሱስም ወደ አየሩሳሌም ወጣ በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ "ቤተ ሳይዳ" የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች አምስትም መመላለሻ ነበረባት

በእነዚህ ውስጥ የወኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞችና፣ ዕዉሮች፣ አንካሶችም ሰውነታቸውም የሰለለ በዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር አንደንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጥ ነበርና እንግዲህ ከወኃውን መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ የገባ ከማናቸውም ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር።

በዚያም "ሠላሳ ስምንት" ዓመት ያህል ይታመም የነበረ አንድ ሰው ነበረ ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ነበረ አውቆ ልትደን ትወዳላህን? አለው

ድውዮም፦ አዎ ጌታ ሆይ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያው ወስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም! ነባር ግን እኔ ስመጣ ሳላሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለስለት፣

ኢየሱስም ፦ ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው፣ ወዲያውም ሰውየው ዳነ አልጋውንም ተሸክሞ ሄደ።

ያም ቀን "ሰንበት" ቀን ነበረ ስለዚህ አይሁድ የተፈወሰውን ሰው "ሰንበት" ነው አልጋውን ልትሸከም አልተፈቀደልህም አሉት እርሱ ግን ያዳነኝ ያ ሰው "አልጋውን ተሸክመህ ሂድ" አለኝ ብሎ
መለሰላቸው።

((ማቴ9÷1)) በታንኳም ገብቶ ተሻገረና ወደ ገዛ ከተማው መጣ እነሆም በአልጋ የተኛ ሽባ ወደ እርሱ አመጡ ኢየሱስ እምነታቸውን አይቶ ሽባውን አንተ ልጅ አይዞህ ኃጢአትህ ተሰረየችልህ አለው

((መዝ 40፥3)) እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳላ ይረዳዋል መኝታውንም ሁሉ ከበሽታው የተነሣ ይለውጥለታል።

አቤቱ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ በየጸበሉ በሆስፒታሉ የታመሙትን ምህረትህን ለሚናፍቁ የምህረት እጅህን ዘርጋላቸው እኛንም የመጣብንን መቅሰፍት በቸርነትህ ያዝልን!

የሐዋሪያት የነብያት የቅዱሳን አበው ጸሎት ልመና የተቀበልክ አምላክ የእኛንም ተቀበል! አሜን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን

#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ለምን_ጠላኸኝ_ወንድሜ

ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ
የአንድ አባት ልጆችኮ ነን
ለምን ጠላኸኝ ወንድሜ
የአንድ የእናት ልጆችኮ ነን
ብዙ ነዉ መንግስቱ አብረን እንወርሳለን
ሰፊ ነው ግዛቱ አብረን እንወርሳለን

የተካፈልኩትን ንብረት
አጥፍቼ ብመለስ ዛሬ
አባቴ ናፍቆኝ ብመጣ
ልቤን አንገቴን ሰብሬ
ለሁላችንም ይበቃል
ብዙ ነው የርሱ መንግስት
አይክፋህ እባክህ ወንድሜ
ፍቅር ይበልጣል ከሃብት
#አዝ
ፊትህ በሐዘን አይጥቆር
ድንጋዩን ጣለው ወንድሜ
ተቅበዝባዥ እንዳያደርግህ
እጅህ ቆሽሾ በደሜ
ልብህን መልካም ብታደርግ
ያንተም መስዋዕት ያርጋል
ጌታ ለሁሉም እኩል ነው
መታዘዝ ንጉሥ ያደርጋል
#አዝ
ብልጥ ስለሆንኩ አይደለም
የተባረኩት በጌታ
ጽኑ መሻቴን አይቶ ነው
በኩር ያደረገኝ ስመታ
የበቀል ጦርክን ሸሽቼ
በባዕድ አገር ብኖርም
በልጅ በትዳር ባርኮኛል
አብረን እንኑር በሰላም
#አዝ
ብልጥ ስለሆንኩ አይደለም
የተባረኩት በጌታ
ጽኑ መሻቴን አይቶ ነዉ
በኩር ያደረገኝ ስመታ
የበቀል ጦርክን ሸሽቼ
በባዕድ ሀገር ብኖርም
በልጅ በትዳር ባርኮኛል
አብረን እንኑር በሰላም

ሊቀ መዘምራን
ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በቦረና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ የማሰባሰብ እንቅስቃሴውን የሚያስተባብሩ በብፁዓን አባቶች የሚመራ አምስት አባላት ያሉት ዐቢይ ኮሚቴ ተመደበ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በቦረና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ የማሰባሰብ እንቅስቃሴን የሚያስተባብር በብፁዕ አቡነ አቡነ ማርቆስ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ሰብሳቢነትና በሊቀ ትጉሃን እስክንድር ገብረ ክርስቶስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ጸሐፊነት የሚመራ ዐቢይ ኮሚት አቋቁሟል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የካቲት ፳ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ስብሰባ በሦስት ብፁዓን አባቶች እና በሁለት የጠቅላይ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች የሚመራ ዐቢይ ኮሚቴ እንዲዋቀርና ወደ ሥራ እንዲገባ ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ውሳኔውን እንዲያስፈጽም ኃላፊነት ሰጥቷል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከብፁዓን አባቶች ጋር ስምምነት ላይ ቢደርሱም አሁንም ችግሮች እንዳልተፈቱ ተገለጸ

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ከሰሞኑ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን አባቶች ጋር በወቅታዊ የቤተ ክርስትያን ጉዳዮች ላይ ተወያይተው ችግሮችን ለመፍታት ቃል የገቡ ቢሆንም አሁንም ችግሮች እንዳልተፈቱ ተነግሯል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ያቋቋመችው የሕግ ኮሚቴ አባል የሆኑት የሕግ ባለሙያና ጠበቃ አያሌው ቢታኔ እንደተናገሩት ፕሬዝዳንቱ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የታሰሩ ሰዎች እስከ ዛሬ ማክሰኞ ድረስ ይፈታሉ ብለው ቃል የገቡ ቢሆንም ሽንገላ የሚመስል ነገር እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል መንግሥትና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ሕግን የማስፈጸም ግዴታ እያለባቸው ኃላፊነት ባለመወጣታቸው ምክንያት አሁንም በርካታ የሕግ ጥሰቶችና የንብረት ውድመቶች እየደረሱ እንደሆነ ጠበቃው ተናግረዋል፡፡

ትናንት ሰኞ በፍርድ ቤት እግድ የተጣለባቸውና ከቤተ ክርስትያኗ ቀኖና ውጭ የተሾሙ ግለሰቦች በአሰላ የአቡነ ያሬድ መንበረ ጵጵስናን ሰብረው የገቡ ሲሆን ይህም በኦሮሚያ ፖሊስ አባላት ድጋፍ የሚደረግ ሕገወጥ ድርጊት መሆኑ ተነግሯል፡፡

ሻሸመኔና አርሲ ነገሌን ጨምሮ በበርካታ የኦሮሚያ አካባቢዎች አሁንም በርካታ ካህናትና ምዕመናን ያለምንም ጥፋት ታስረው ይገኛሉ ያሉት ጠበቃው ከዚህ በፊትም በመንግሥት በኹለት ቀን ውስጥ ይፈታሉ ተብለው የነበሩ ታሳሪዎች ሳይፈቱ በርካታ ቀናት መቆጠራቸውን ተናግረዋል፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ዙሪያ የካህናት ሥልጠና መስጠት ጀመረ።

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አባታዊ መመሪያ ሰጪነት ከ31 ወረዳ ቤተ ክህነት ከተውጣጡ የአድባራት እና ገዳማት ካህናት ለ3 ወራት የሚቆይ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል።

የሥልጠናው ዋና ዓላማ አንዱ ያለውን እውቀት ለሌላው በማጋራት፣ በአንድነት ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል፣ ለምእመናን አርአያ በመሆን የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለማስቀጠል እንዲሁም ራስን ለማየት ያስችል ዘንድ የተዘጋጀ እንደሆነ ተገልጿል።

የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ሐዲስ ነቅዐ ጥበብ አባቡ በሥልጠናው ላይ በአስተላለፉት መልእክት ካህናት በአላቸው እውቀት ላይ ተጨማሪ እውቀት በመስጠት የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት በይበልጥ ለማስኬድ የተዘጋጀ ነው ብለዋል። መረጃው አቡቀለምሲስ ሚዲያ ነው፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ቅዱስ

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ
ኃያል ኃያል ኃያል አማኑኤል

አስቀድሞ የነበረ አሳልፎ የሚኖር
በሥልጣኑ ያጠፋልን ሙስና መቃብር
ከአባቱ ጋር ትክክል ነው በኃይል በጌትነት
በዓለም ሊፈርድ የሚመጣው በክብር በትስብእት

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
ኃያል ኃያል ኃያል አማኑኤል

የሰው ፍቅር አገብሮት ወደ ምድር የመጣ
ከሰማያት የወረደው ወደ ሰማይ የወጣ
ከምስጉኖች ይልቅ ምስጉን ከግሩማን ግሩም
የጠቢባን ጠቢብ ጌታ የሚመስልህ የለም

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አማኑኤል

ብንዳስሰው ብንበላው ደግሞም ብንጠጣው
ረቂቁ የገዘፈው ሥጋን ተዋሕዶ ነው
በደመናት መጋረጃ የተሰወረ እሳት
በግርግም ውስጥ አገኘነው በግዕዘ ሕፃናት

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ
ኃያል ኃያል ኃያል አማኑኤል

ሰማያትን የዘረጋ ውኆችን የፈጠረ
የማይታይ የሚታየው በእርሱ ተፈጠረ
ሁሉን በእጁ የጨበጠ አሸናፊው ልዑል
በቤተልሔም ተወለደ ከማርያም ድንግል

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
ኃያል ኃያል ኃያል አማኑኤል

ዘማሪ መምህር አቤል ተስፋዬ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ምኵራብ
 
እንኳን ለዐቢይ ጾም ሦስትኛ ሳምንት አደረሰን!
 
የዐቢይ ጾም ሦስተኛው ሳምንት ‹ምኵራብ› ይባላል፡፡ አይሁድ በሰቀላማ መሰሉ አዳራሽ በምኵራብ ጸሎት ያደረጉ ነበር፤ ስለዚህም “የጸሎት ቤት” ተባለ፡፡ የቃሉ ስያሜም የተገኘው ‹‹በመቅደስም በሬዎችን፣ ላሞችን፣ በጎችን፣ ርግቦችን፣ የሚሸጡትን አገኘ›› ተብሎ ከተገለጸው ቃል ነው፡፡ ‹ምኵራብ› የሚለው ቃልም በአማርኛ ‹መቅደስ› ተብሎ ተተርጕሟል፡፡ (ዮሐ.፪፥፲፬) 
 
ምኵራብ አምልኮተ እግዚአብሔር የሚፈጸምበት እንዲሁም ሕገ ኦሪት የሚነበብበት በአይሁድ የሚሠራ መካነ ጸሎት ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀዳሚት ሰንበት በምኵራብ በርካታ ሕዝብ ይሰበሰብበት ስለነበር ሊያስተምራቸው ተገኝቶ ነበር፡፡ እርሱም ከዚያ እንደደረሰ  “በመቅደስም በሬዎችና በጎችን ርግቦችን የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ። የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፤ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ፤ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ። ርግብ ሻጮችንም ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው፤ ቤቴስ የጸሎት ቤት ይባላል” አላቸው። (ዮሐ.፪፥፲፪-፲፮)
 
ስለዚህም ምኵራብ በተባለው የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምኵራብ የገባበትንና ማስተማሩን የሚነገርበት፣ በምኵራብ ይሸጡና ይለውጡ የነበሩትን ሻጮችንና ለዋጮችን የገሠፀበትና ከቤተ መቅደስም ከነሸቀጣቸው ያስወጣበት፣ ቤተ መቅደስ የእግዚአብሔር ማደሪያ፣ የስሙ መጠሪያ እንዲሁም የጸሎት ሥፍራ መሆኗን ያስረዳበትና ያወጀበትና በቤተ መቅደስ የንግድ ሥራ ማከናወን እንደማይገባ ያረጋገጠበት ዕለት ነው፡፡
 
አምላካችን እግዚአብሔር በቸርነቱ ይጎብኘን!
 

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መቄዶንያ የ1 ሚሊየን ዶላር ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ማዘጋጀቱን ገለጸ።

መቄዶንያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል በኮሜዲያን እሸቱ መለሰ አስተባባሪነት የካቲት 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ የ1 ሚሊየን ዶላር የማሰባሰብ መርሐ ግብር እንደሚካሔድ ተገልጿል፡፡

የገቢ ማሰባሰቢያው ዋና ዓላማ ማዕከሉ በመገንባት ላይ ለሚገኘው ባለ 12 ወለል ሕንጻ የ1ሚሊየን ዶላር በመሰብሰብና በርና መስኮቱ በመግጠም ሕንጻው እስኪጠናቀቅ ድረስ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ታስቦ የተዘጋጀ መርሐ ግብር መሆኑ ተነግሯል፡፡

መቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል ምንም ዓይነት የውጪ ድጋፍ የሌለው በመሆኑ እስከ አሁን እያገዙ ያሉ ግለሰቦች ወደፊትም እንዲያግዙ ለማድረግ እንዲሁም የሚሠራቸውን ሥራዎች ቁጥር ለመጨመር በማሰብ የተጀመረው ሕንጻ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከ2.3 ቢሊየን ብር በላይ የሚፈጀው ዘመናዊ ሆስፒታልና የአረጋውያን መኖሪያ ሕንጻ በተጀመረ በ3 ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ግንባታው 70% ተጠናቋል።

ማእከሉ በአሁኑ ሰዓት ከ10 በላይ ከተሞች ከ7ሺ በላይ አረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማንን እየረዳ የሚገኝ ሲሆን በተጨማሪም አገልግሎቱን በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ከተሞች ለማድረግና ከ20ሺ በላይ አረጋውያንን እና አእምሮ ሕሙማንን ለመርዳት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሩ በዶንኪ ትዩብና በማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን የካቲት 26 እሑድ ከ9 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ የሚተላለፍ ሲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ተጠይቋል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አንድ ጣልያናዊ ተዋጊም ‹‹በነጭ ፈረስ ተቀምጦ ወደ ቀኝና ወደ ግራ እየተመላለሰ ወደ ጦርነቱ ግቡ ኢጣሊያኖችን ማርኩ እያለ ትእዛዝ ሲሰጥና ሲዋጋን የዋለ ማነው?›› ብሎ መጠየቁ እየተገለጸ የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ አጋዥነት መገለጹም እዚህ ላይ መነሣት የሚገባው ነው። (በአድዋ ጦርነትና ድል...፣፶፫)። ይህንንም በአንድ ባለ ቅኔ፡-
‹‹ኃይል ውእቱ ዘጊዮርጊስ፣
አኮኑ ኵዕናት
በላዔ ሮማዊት ነፍስ፣
ዘጌዴዎን ምኒልክ
ዘአውረደ በዐውደ ሮምያ
ጠለ ደም እምርእስ። (በአድዋ ጦርነትና ድል...፣ ፶፪)።
(የሮማዊትን ነፍስ (ሰውነት) የበላ (ድል ያደረገ) የጊዮርጊስ ኃይል እንጂ ጦር አይደለም፣የጌዴዎን ምሳሌ ምኒልክ በሮምያ አደባባይ ከራስ ላይ እስካወረደ ጠብታ ደም።) ተብሎ የተነገረ ነው።
የአድዋ ድል ብሔራዊና ዓለም ዐቀፋዊ ትሩፋቱ ባሻገር ሃይማኖታዊ ትሩፋቱም መነገር የሚገባው ነው። ‹ኢትዮጵያውያንን እንደ እስራኤል ዘነፍስ መቍጠርና ሀገሪቱንም ጸጋ እግዚአብሔርን የታደለችና ሀገረ እግዚአብሔር እንደ ሆነች አድርጎ ማየት፣ ሀገረ እግዚአብሔር ከሆነች ዘንድም መደፈር የለባትም በሚል እሳቤ ድንበሯን መጠበቅና በዚህም ሂደት መሠዋት የዜግነት ክብር ብቻ ሳይሆን ጽድቅም ነው ብሎ ማመን› ለኢትዮጵያውያን አዲስ እሳቤ ባይሆንም በአድዋ ድል ግን ይበልጥ ጠንክሯል፤ ከዓለም ሕዝብ መካከልም ይህንን ያመኑ እጅግ ብዙ ነበሩ። ከነጮች ተፅዕኖ ነፃ የሆነ  የጥቁሮች የሃይማኖት እንቅስቃሴ በተለይ በአሜሪካና በደቡብ አፍሪካ ‹ኢትዮጵያኒዝም› በሚል ስያሜ እንዲጀመር መሆኑ ለዚህ ምስክር ነው።
ለማጠቃለል ያህል የአድዋ ድል ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በገነባችው የመንፈሳዊ ሥነ ልቡና ብርታትና ለሀገርና ለሃይማኖት እስከ ሞት የመጋደል ወኔ የተገኘ መሆኑ ከድሉ እኩል መነገር ያለበት ነው። ኢትዮጵያውያን የኢጣሊያን ወረራ በሀገረ እግዚአብሔር ላይ እንደ ተደረገ ሰይጣናዊ ጥቃት ነበር የቈጠሩት። ለዚህም ነው ድሉን እንኳን ሰይጣን ድል ከተነሣበት ከክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ጋር በማመሳሰል
‹‹ሞዖ ለሞት
ሠዐሮ ለጣዖት
ገብረ ትንሣኤ በሰንበት›› እያሉ ዳግመኛም
‹‹ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ
ተሐፂባ በደመ ሰማዕታት››
ብለው እየዘመሩ ያከበሩት። (በአድዋ ጦረነትና ድል…፣ ፷)።
የአድዋ ጦርነት ሊጀመር ሰዓታት በቀሩበት ጊዜ እንደ ተዋጊ ሳይጨነቁ፣ ሁሉን ትቶ በተጠንቀቅ ከመቆምና የነደፉትን የውጊያ ስልት ከማሰላሰል ይልቅ ‹እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቅ ይበልጣል› በሚል ታላቅ የሥነ ልቡና ዐቅም ዐፄ ምኒልክ፣ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት፣ ራስ መኮንን፣ ራስ መንገሻ፣ ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ …ወዘተ በአድዋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን እያስቀደሱ ነበር። በርግጥ ከዚህም በኋላም ንጉሡ በእርጋታቸው ጸንተው ዕለቱ ጊዮርጊስ በመሆኑ አሁንም ወደማይጕዓጕዓ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሄደው ልባዊ ጸሎትን አቅርበው ነበር። በጦርነት መጀመሪያ የመጨረሻው ሰዓት ለዚያውም ዐቅሙ እጅግ የሚገዝፍ ጠላት ከፊት ተደግኖ እንዲህ ዓይነት መረጋጋትን ያሳዩ ሌሎች ተዋጊዎች መኖራቸው እጅጉን አስገራሚ ነው። ይህ በርግጥም መንፈሳዊ ጥብዐት እንጂ ምን ይባላል?
በአድዋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን፡ ተሰብስበው ሲያስቀድሱ ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስ ቀዳሽ ነበሩ። እርሳቸውም ከቅዳሴ በኋላ ሲያስተምሩ እንዲህ አሉ፡-
‹‹ልጆቼ ሆይ… ዛሬ የእግዚአብሔር ፍርድ የሚፈጸምበት ቀን ነው። ኺዱ ለሃይማኖታችሁ፣ ለሀገራችሁ ሙቱ፤ እግዚአብሔር ይፍታህ››። (ጳውሎስ ኞኞ፣ ፪፻፫)።
በእውነት የእግዚአብሔር ፍርድ በዕለቱ ተፈጸመ፤ ለሀገርና ለሃይማኖት የተሠዉትን ሁሉ ነፍሳቸውን ይማርልን።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አባቶቻችን ይህንን የበዛ የ"መንግስት" ንቀት በዝምታ ማለፍ የለባቸውም! መግለጫ እንጠብቃለን!

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዓድዋ የኢትዮጵያ ከፍታ

🎇 ለፌስቡክ, ለቴሌግራም እንዲሁም ለተለያዩ ሶሻል ሚድያ እንደ ፕሮፋይል መጠቀም ይችላሉ

ሼር
👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት ወደ መቐለ አቀኑ።

ቅዱስነታቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትንና ሊቃውንትን አስከትለው በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት ወደ መቐለ ሲጓዙ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የኒውዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው  ከቅዱስነታቸው ቡራኬ ተቀብለዋል ።

ምንጭ: ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የዜና ሽፋን ጥቆማ

የብፁዕ ወቅት አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖትን ፲ኛ ዓመት በዐለ ሢመት ምክንያት በማድረግ የተዘጋጁት "ዜና መዋል ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ" እና "ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ " የተሰኙት መጽሐፍት የካቲት ፳፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ይመረቃሉ።

ስለሆነም በደብዳቤው ላይ የተጠቀሳችሁ የሚዲያ ተቋማት በዕለቱና በቦታው በመገኘትና ዘገባውን በመስራት ለሕዝብ ይፋ እንድታደርጉ ጥሪአችንን እናስተላልፋለን ።

Читать полностью…
Подписаться на канал