ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ለመሆኑ በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ መዝሙር ቻናል ተቀላቅለዋል ? የሰርግ ፣ የሀዘን ፣ የንግስ መዝሙራት ፣ የተለያዩ ወረባት ፣ የመዝሙር ግጥሞችን ያገኛሉ ። አብረውንም መዝሙራትን ያጠናሉ ። # ይቀላቀሉን https://t.me/joinchat/AAAAAE5K_dyT2-AYoTAW5A

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሰሙነ ትንሳኤ /በዓለ ኀምሳ/

#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🎬 የኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሰርግ መዝሙሮች ስብስብ
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ

⚠️ ዝማሬውን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/Xyc7R1Gk2Fs
https://youtu.be/Xyc7R1Gk2Fs

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🎬 "በምግብ ሰዓት የሚጸለይ ጸሎት" - |ቀሲስ ሳሙኤን እሸቱ እንዳዘጋጀው ዮሴፍ በሪሁን እንዳነበበው|
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ

⚠️ ጸሎቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/pjBReIJQ-Q4
https://youtu.be/pjBReIJQ-Q4

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​👉 ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ

⚡⚡⚡ሰኞ⚡⚡⚡

👉ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

⚡⚡⚡ማክሰኞ⚡⚡⚡

👉ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

⚡⚡⚡ረቡዕ⚡⚡⚡

👉አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

⚡⚡⚡ሐሙስ⚡⚡⚡

👉አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

⚡⚡⚡ዓርብ⚡⚡⚡

👉ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

⚡⚡⚡ቅዳሜ⚡⚡⚡

👉ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

⚡⚡⚡እሁድ⚡⚡⚡

👉ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡

#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 ትንሳኤ ክርስቶስ
🎤 በሊቃውንት አንደበት

#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ክርስቶስ ሕያው ነው

ክርስቶስ ሕያው ነው
ሞት ይዞ ያላስቀረው
የለም ከመቃብር ተነሰቷል በክብር /2/

በገዛ ፈቃዱ ነፍሱን ስለሰጠ
የጨለመው ዓለም በብርሃን ተዋጠ
ሲኦል ድል መንሳቱ መውጊያውም ታጠፈ
የሞት ስልጣን በሞት ስለተሸነፈ

የጥሉ ግድግዳ በሞቱ ፈረሰ
የነፍሳችን ቁስል በእርሱ ተፈወሰ
ከቶ አላስቀረውም የመቃብር ድንጋይ
ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና ኤልሻዳይ

ዓለሙን እንዲሁ እግዚአብሔር ወዶ
የሰው ልጅ ከበረ ዲያብሎስ ተዋርዶ
ይገዛን ይነዳን ያስጨንቀን ነበር
በሞት ላይ ተራመድን አምላካችን ይክበር

ሕይወት ይሰጠን ዘንድ ስለኛ የሞተው
ቤዛችን ክርስቶስ ሞትን ድል አረገው
የሞተው ተነስቷል በመቃብር የለም
ዳግመኛም ይመጣል ሊፈርድ በዓለም

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ወምድርኒ

ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ/2/ 
ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ /4/ 

ምደር ጸዳች ሐሴት አደረገች /2/ 
በክርስቶስ ደም በእውነት ታጠበች/4/ 

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ትንሳኤ
ለእናንተ Profile ካዘጋጀናቸው ፎቶዎች
ሼር
👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ትንሳኤ
ለእናንተ Profile ካዘጋጀናቸው ፎቶዎች
ሼር
👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እዩና እመኑ ሰዎች

እዩና እመኑ ሰዎች
ድንጋዩ ተፈነቃቅሏል
ኢየሱስ በኩለ ሌሊት
በሀይሉ ሞትን ድል ነስቷል/2/

እልልታ ለዚህ ይገባል
ግርግርታ ለዚህ ይገባል
የሞት ሀይል ተዋርዷል ዛሬ
ሲኦልም ተመሰቃቅሏል/2/

መላዕክቱ ነጭ ለብሰዉ
ምስራቹን አበሰሩ
ተነስቷል ኢየሱስ ብለው
ለዓለም እዲናገሩ/2/

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

08/08/15 ዓ.ም
ዕለተ ትንሣኤሁ ለክርስቶስ

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበ
መልዕክታት ወንጌልና ምስባክ፡፡

ዲ/ን - ቆሮ15÷20-41
ን/ዲ - 1ጴጥ 1÷1-13
ን/ካ - ግብ፡ሐዋ 2÷22-37

የዕለቱ_ምስባክ:- መዝ 117÷24
ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር ።
ንትፈሣሕ ወንትሐሠይ ባቲ።
ኦ እግዚኦ አድኅንሶ።

ትርጒም
እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት።
ሐሴትን እናድርግ በእርሷም ደስ ይበለን።
አቤቱ እባክህ አሁን አድን።

የዕለቱ ወንጌል፦ ዮሐ፥20 ÷1- 19
ቅዳሴ፦ ዘዲዮስቆሮስ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​​​የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 5ቱ ታላላቅ ሀዘናት

ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በእኔ ምክንያት ካገኙሽ ኅዘናት የትኛው ይበልጣል ብሎ በጠየቃት ጊዜ እመቤታችንም ልጄ ወዳጄ ሆይ ባንተ ምክንያት ካገኙኝ ኅዘናት እነዚህን አምስቱ ይበልጣሉ ብላ እመቤታችን የጠቀሰቻቸው ታላላቅ ኅዘናት የሚከተሉት ሲሆኑ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እነዚህን ያንችን ኅዘናት እያሰበ የጸለየ ኃጢአቱን ይቅር እለዋለሁ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጥቷታል።

፩ኛ - ስምዖን በቤተ መቅደስ ትንቢት በተናገረ ጊዜ።

=> ስምዖን የተባለው ፦ አረጋዊው ስምኦን ነው የእመቤታችን ሐዘን የሚጀምረው ገና አንድዬ ልጇን ከመውለዷ በስምተኛው ቀን ነው ቤተመቅደስ ይዛው በሄደች ጊዜ አረጋዊው ስምዖን “በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል (ልጅሽ በቀራንዮ ይሞታል)” ሉቃስ 2፥34-35 ብሎ በነገራት ጊዜ ድንግል ማርያም አምርራ አዘነች አለቀሰች።

እነሆ፥ የብዙዎች ልብ አሳብ ይገለጥ ዘንድ፥ ይህ በእስራኤል ላሉት ለብዙዎቹ ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ለሚቃወሙትም ምልክት ተሾሞአል፥ በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል አላት። ሉቃ (2፡34-35)

፪ኛ - ከቤተ መቅደስ ፈልጌህ ባጣሁህ ጊዜ።

ወላጆቹም በያመቱ በፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ነበር። የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ በሆነ ጊዜ፥ እንደ በዓሉ ሥርዓት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ፤ ቀኖቹንም ከፈጸሙ በኋላ፥ ሲመለሱ ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፥ ዮሴፍም እናቱም አላወቁም ነበር።

ከመንገደኞች ጋር የነበረ ስለመሰላቸው የአንድ ቀን መንገድ ሄዱ፥ ከዘመዶቻቸውም ከሚያውቋቸውም ዘንድ ፈለጉት፤ ባጡትም ጊዜ እየፈለጉት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

ከሦስት ቀንም በኋላ በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸውም ሲጠይቃቸውም በመቅደስ አገኙት፤ የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ተገረሙ። ባዩትም ጊዜ ተገረሙ እናቱም። ልጄ ሆይ፥ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ፥ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን አለችው። ሉቃ (2፡41-48)

፫ኛ - በጲላጦስ አደባባይ በገረፉህ ጊዜ።

በዚያን ጊዜም ጲላጦስ ኢየሱስን ይዞ ገረፈው። ወታደሮችም ከእሾህ አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ አኖሩ ቀይ ልብስም አለበሱት፤ እየቀረቡም።

የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን ይሉት ነበር፤ በጥፊም ይመቱት ነበር። ጲላጦስም ደግሞ ወደ ውጭ ወጥቶ። እነሆ፥ አንዲት በደል ስንኳ እንዳላገኘሁበት ታውቁ ዘንድ እርሱን ወደ ውጭ አወጣላችኋለሁ አላቸው። ኢየሱስም የእሾህ አክሊል ደፍቶ ቀይ ልብስም ለብሶ ወደ ውጭ ወጣ። ዮሐ (19፡1-5)

፬ኛ - በዕለተ ዓርብ በሰቀሉህ ጊዜ።

ኢየሱስንም ይዘው ወሰዱት፤ መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሉት ወጣ። በዚያም ሰቀሉት፥ ከእርሱም ጋር ሌሎች ሁለት፥ አንዱን በዚህ አንዱን በዚያ ኢየሱስንም በመካከላቸው ሰቀሉ።

ጲላጦስም ደግሞ ጽሕፈት ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረው፤ ጽሕፈቱም። የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ የሚል ነበረ። ኢየሱስም የተሰቀለበት ስፍራ ለከተማ ቅርብ ነበረና ከአይሁድ ብዙዎች ይህን ጽሕፈት አነበቡት፤ በዕብራይስጥና በሮማይስጥ በግሪክም ተጽፎ ነበር።

ስለዚህ የአይሁድ ካህናት አለቆች ጲላጦስን እርሱ። የአይሁድ ንጉስ ነኝ እንዳለ እንጂ የአይሁድ ንጉሥ ብለህ አትጻፍ አሉት። ጲላጦስም። የጻፍሁትን ጽፌአለሁ ብሎ መለሰ። ዮሐ. (19፡17-2

፭ኛ- ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ገንዘው ወደ አዲስ መቃብር ባወረዱህ ጊዜ።

ከዚህም በኋላ አይሁድን ስለ ፈራ በስውር የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረ የአርማትያስ ዮሴፍ የኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ ጲላጦስን ለመነ፤ ጲላጦስም ፈቀደለት። ስለዚህም መጥቶ የኢየሱስን ሥጋ ወሰደ።

ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረ ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ። የኢየሱስንም ሥጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት።

በተሰቀለበትም ስፍራ አትክልት ነበረ፥ በአትክልቱም ማንም ገና ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበረ።ስለዚህ መቃብሩ ቅርብ ነበረና ስለ አይሁድ ማዘጋጀት ቀን ኢየሱስን በዚያ አኖሩት። ዮሐ (19፡38-42)

እንዚህን አምስቱን የእመቤታችን ሐዘናት እያሰበ ያዘነ ዝክሯን የዘከረ በአማላጅነቷ የታመነ ዋጋው ከቶ አይጠፋበትም፡፡

ቅድስት ሆይ ለምኝልን
ቅድስት ሆይ ለምኝልን
ቅድስት ሆይ ለምኝልን
አሜን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​በዝማሬ ዳዊት Tube የተላለፉ ትምህርቶች

1⃣ ኦርቶዶክስ እና የዓለም እምነቶች
https://youtu.be/HXh1IUuBOrE
2⃣ እግዚአብሔርን እንዴት መውደድ እንዳለብን
https://youtu.be/Asx80GdsDDE
3⃣ 666 እና የውጭ ዘፋኞች
https://youtu.be/3iFggkALrws
4⃣ ዘፈን እንዴት ተፈጠረ? ማንስ አስተማረን?
https://youtu.be/1P421kYHutU
5⃣ ስለ ቶ መስቀል ክፍል 1
https://youtu.be/qevNJ5hYQ90
6⃣ ስለ ቶ መስቀል ክፍል 2
https://youtu.be/3H0FkrKbg9A
7⃣ ስለ ቶ መስቀል የመጨረሻው ክፍል
https://youtu.be/2QB2Ra7FHf8
8⃣ ሴጋ የፈጸመ የተክሊል ጋብቻ ይገባዋልን?
https://youtu.be/hnt5Y1F4TDY
9⃣ በጸሎት መሀል ወሬ ማውራት
https://youtu.be/2VsM6cVwgcU
1⃣0⃣ ቅዠት ምንድን ነው?
https://youtu.be/m6eD1pzyIWM
1⃣1⃣ የምግብ ሰዓት ጸሎት
https://youtu.be/pjBReIJQ-Q4
1⃣2⃣ የምእመናን አለባበስ ምን ይመስላል
https://youtu.be/fKuDfxWKUyY
1⃣3⃣ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና ፕሮቴስታንት ክፍል አንድ
https://youtu.be/HBb3vZBZqzs
1⃣4⃣ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና ፕሮቴስታንት ክፍል ሁለት
https://youtu.be/PbmNFCYro4I
1⃣5⃣ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና ፕሮቴስታንት የመጨረሻው ክፍል
https://youtu.be/1NKzUoqtucs
1⃣6⃣ ስለ ቅዱስ ቁርባን ክፍል አንድ
https://youtu.be/Oji7daT4obw
1⃣7⃣ ንስሐ መግባት ለምን እንፈራለን?
https://youtu.be/kIkhOnUJm_A
1⃣8⃣ ሕማማት
https://youtu.be/NMHnlH0YLEE
1⃣9⃣ ስለ ዓቢይ ጾም
https://youtu.be/uErRRCkMsU0
2⃣0⃣ ዘጠኙ አጾማት
https://youtu.be/ZV7iwQS8mEk
2⃣1⃣ ለፓስተር ዳዊት የተሰጠ ምላሽ
https://youtu.be/hK473EGk0qs
2⃣2⃣ ለዮናታን አክሊሉ የተሰጠ ምላሽ
https://youtu.be/m8sFeVaja4I
2⃣3⃣ ጸሎት ምንድን ነው?
https://youtu.be/ZFYd4X-eGBo
2⃣4⃣ ክርስቲያናዊ የሆነ ጾም እንዴት እንጹም
https://youtu.be/ZV7iwQS8mEk
2⃣5⃣ ከፍቅረኛዬ ጋር ወደፊት ስለምንጋባ አሁን ግንኙነት ብንፈጽምስ?
https://youtu.be/ZV7iwQS8mEk
2⃣6⃣ ግብረ አውናን ምንድነው?
https://youtu.be/1XgZf6hq8bs
2⃣7⃣ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ማድረግ ያለብን ዝግጅት?
https://youtu.be/TQeWVmN47PY
2⃣8⃣ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ? 81 ወይስ 66
https://youtu.be/Iggo8ws7quM


በዝማሬ ዳዊት የተላለፉ አጭር ታሪኮች

1⃣ የሰይጣን ጥያቄ
https://youtu.be/mHGEluQCJNY
2⃣ ባላገሩ
https://youtu.be/Kcftb4CReyg

👉 የልደት (ገና) መዝሙሮች
https://youtu.be/iSWmxwIJAac
👉 የጥምቀት መዝሙሮች
https://youtu.be/ESAE29ZvF3o
👉 አጫብር ወረብ
https://youtu.be/phssFP3KCRg
👉 መጾሙን ይጾማል - የበገና መዝሙር
https://youtu.be/q0TcGVnRGb4
👉 ማን ይመራመር - የበገና መዝሙር
https://youtu.be/dHqXNw_27R8
👉 የሰርግ መዝሙሮች
https://youtu.be/Xyc7R1Gk2Fs
👉 ዓለምን ዞሬ አየሁት? - የበገና
https://youtu.be/YP5ugEAYQRg
👉 ስለ ቸርነትህ - የበገና
https://youtu.be/KGBhL_7pA1c

ለሁሉም ሼር ያድርጉ ላላወቁት እናሳውቅ!
Subscribe ማድረግዎን እንዳይዘነጉ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​​​👉 ቅዳሜ

ቀዳም ስዑር ትባላለች ፦
ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል።

ለምለም ቅዳሜ ይባላል፡-
ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል።

ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡-
ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል።
ዝርዝሩን - https://youtu.be/NMHnlH0YLEE

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🇪🇹 የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ የትኞቹን መዝሙራት ማግኝት ይፈልጋሉ❓

👏 የቸብቸቦ መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🎻 የበገና መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
👑 የቅዱሳን መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
⛪️ የንግስ መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🤲 የምስጋና መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🙏 የንስሐ መዝሙራት
📖▓⇨→Audio ⇨ግጥም
💍 የሠርግ መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🌦 ወቅታዊ መዝሙራት
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም
🇪🇹 ለአገር የተዘመሩ
📖▓⇨→audio ⇨ግጥም

👇👇👇👇

✝▓⇨→ሌሎችንም ለማግኘት...

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 በቅዳሴ የሚገኝ በረከት

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🎬 ግብረ አውናን/ሴጋ/ የፈጸመ ኦርቶዶክሳዊ/ት ጋብቻውን/ዋን በተክሊል መፈጸም ይችላሉን?
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ

⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/hnt5Y1F4TDY
https://youtu.be/hnt5Y1F4TDY

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን

#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ትንሳኤከ

ትንሳኤከ ለእለ አመነ /2/
ብርሃነ ከፈኑ ዲቤነ/2/

ትንሣኤህን ለምናምን ለኛ /2/
ብርሃንህን ላክልን ወደኛ /2/

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ክርስቶስ በኲር

ክርስቶስ በኲር ቀደመ ተንሥዖ
እምኲሎሙ ኲሎሙ ሙታን /2/
ወያርእዩ ብርሃነ ወያጸድቆ ለዘይትቀነይ
ለጽድቅ ወለሰናይ ወለብዙኃን
ኃጢአቶሙ ውእቱ ይደመስስ /2/

ትርጉም፡-
በኩር ክርስቶስ የብዙዎችን
ኀጢአት ይደመስስ ዘንድ
ለእውነትና ለመልካም ነገር የሚገዙትንም
ብርሃንን ያሳይ ዘንድ ከሙታን
ሁሉ ቀድሞ ተነሣ፡፡

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የምስራች እንበል

የምስራች እንበል (፪) እናመስግን ጌታን
በመስቀል ላይ ውሎ ከኃጢአት ላነጻን
ሞትን ድል አድርጎ ለሰጠን ትንሳኤን

ታላቁ ጌታችን የዓለም መድኃኒት
አደረ በመቃብር ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት
#አዝ
ፈጣሪ ሆኖ ሳለ የፍጥረታት ጌታ
በሰው ፊት ተዋረደ በሰዎች ተንገላታ
#አዝ
አሳልፎ ሰጠ ስለኛ ራሱን
በመስቀል ተቸንክሮ መረጠ መሞትን
#አዝ
አይሁዶች ተሞኙ ትንሳኤን ሳያምኑ
ሳያምኑ መቃብሩን ወታደር አስጠበቁ
#አዝ
ዘቦችም ወደቁ ሞትም ተሸነፈ
ሰይጣንም ተዋረደ ስልጣኑ ተገፈፈ
#አዝ
በማለዳ ሄዳ ማርያም መግደላዊት
የጌታዋን ትንሳኤ መላዕክት አበሰሯት

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ትንሳኤ
ለእናንተ Profile ካዘጋጀናቸው ፎቶዎች
ሼር
👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ትንሳኤ
ለእናንተ Profile ካዘጋጀናቸው ፎቶዎች
ሼር
👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ትንሳኤ
ለእናንተ Profile ካዘጋጀናቸው ፎቶዎች
ሼር
👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

''ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም''

''ክርስቶስ በታላቅ በኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ''

ውድ የዝማሬ ዳዊት ቻናል ቤተሰቦች በሙሉ ፥ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የአንድነት በዓል ይሁንልን አሜን።

ዝማሬ ዳዊት On Telegram
ሚያዚያ 08|2015 ዓ.ም

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ምስባክ ዘትንሣኤ (ዘማሕሌት)

መዝ 77÷65
ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃህ እምንዋም።
ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን።
ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ።

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የማርያም ለቅሶ

ልጄ ወዳጄ ሆይ ለእኔ ወዮታ አለብኝ ... በጦር ሲወጉህና ሲገድሉህ ዓይኖቼ ከምያዩ ይልቅ ልጄ ወዳጄ ሆይ ነፍሴን ከስጋዬ ትለያት ዘንድ እማልድሃለሁ።

ልጄ ወዳጄ ሆይ ይህ በራስህ የተቀዳጀኸው የእሾህ አክሊል ምነው እኔ በተቀዳጀሁትና የመከራህ ተሳታፊ በሆንኩ።

ልጄ ወዳጄ ሆይ አንተን በእሱ ላይ በሰቀሉበት መስቀልህ በሰላም እሰናበትሃለሁ።
ልጄ ወዳጄ ሆይ አይሁድ መራቃቸውን በተፉበት ብርሃንንም በተሞላ ፊትህ እሰናበትሃለሁ: ንጉስ ሆይ በሁለት ወንበዴዎች መካከል እርቃኑን ለቆመው አካልህ እጅ እየነሳሁ እሰናበትሃለሁ።

ልጄ ወዳጄ ሆይ እጣ በተጣጣሉበት ክብር ልብስህ እጅ እየነሳሁ እሰናበትሃለሁ።
ልጄ ወዳጄ ሆይ አክሊለ ሶክክን ለተቀዳጀ እራስህ ሰላም እያልኩና እጅ እየነሳሁ እሰናበትሃለሁ።

ምንጭ ግብረ ሕማማት
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 ድርሳነ ማሕየዊ ዘቀዳሚት

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በይስሐቅ ፈንታ
የበገና መዝሙር

በይስሐቅ ፈንታ ኢየሱስ ታረደ/2/
ደሙን ከፈለና አዳምን ታደገ/2/

ተጨነቀ ጌታ ተሰቃየ ጌታ
የኔ መድኃኔዓለም የአዳም ልጅ አለኝታ
እንደሚታረድ በግ ተነዳ ወደ ሞት
ንፁህ ኢየሱስ በደል የሌለበት

በማመን ሲሸከም የአዳምን መከራ
ስቃይ ተቀበለ ደሙ እየተዘራ
ለሚገርፋት ሁሉ ምህረትን ሲቸር
እርሱ ግን ሲገረፍ ብዙ ተቸገረ

የሰማነውን ድምፅ ማን ሰው እኮ አምኗል
የእግዚአብሔርስ ክንድ ለነማን ተገልጿል
ባየነው ጊዜ ህመም ተሸክሞ
ስለበደላችን ተገርፎና ታሞ

እጁ የታሰረው ይስሀቅ ተፈቶ
ኢየሱስ ቀረበ በሰው ልጆች ፈንታ
ንፁህ በግ ቀረበ በደል የሌለበት በደለኛ ሆኖ
ሊሰቀል ሊገደል መስቀሉን ተጭኖ

በእውነት ደዌያችንን እርሱ ተሰቀለ
በሰው ልጆች ፈንታ በእንጨት ተሰቀለ
እኛ ግን ከሰስነው እንደ ወንጀለኛ
ስለ እኛ ቢሰቀል ሰማያዊው ዳኛ

ለሰው ልጆች ህይወት የታሰበውን ሰይፍ
አይተናል ሰምተናል በኢየሱስ አንገት ሲያልፍ
የመስቀሉ ስዕል ኧረ እንዴት ይገርማል
እዩት ንፁህ በግ በአርምሞይነዳል

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…
Подписаться на канал