ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉ኢየሱስ ክርስቶስ ስንት ሰዓት ተሰቀለ ?

ማርቆስ 15÷25"በሰቀለትም ጊዜ 3 ሰዓት ነበር"
ዮሀንስ ወንጌል "የ ፈሲካም ዝግጅት ነበር ጊዜውም 9 ሰአት
ነበር 'ጲላጦስም እንሆ ንጉሳችሁ አላቸው እነሱም ስቀለው አሉት"

የጊዜው አቆጣጠር እነ ዩሐንስ የአይሁዳውያንን ሲጠቀሙ ማርቆስ ግን የሮማውያንን ነው የተጠቀመው ለማስረዳት ያህል

👉 ኢየሱስ ክርስቶስ በአይሁድ ሰዓት አቆጣጠር ሶስት ሰአት በሮማውያን አቆጣጠር በስድስት ሰአት ተሰቀለ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ስድስት ሰዓት ያለው የሮማውያን የሰአት አቆጣጠር ተከትሎ ሲሆን👉 ሌሎቹ ወንጌላውያን ሶስት ሰዓት ያሉት የአይሁድን የሰአት አቆጣጠር
ተከትለው ነው፡፡ በመጀመሪያ ይህንን ለመረዳት በቅደም ተከተል ድርጊቶችን
እንመልከት ፡-
1. ኢየሱስ በፋሲካ ሌሊት ተያዘ ሉቃ 22÷7-8 ፤ዮሐ18፡2-4
2. ሲነጋጋ (ማለዳ) ወደ ሮማዊው ገዥ ወደ ጲላጦስ ግቢ ወሰዱት ዮሐ18:28-30
3. ከብዙ ንትርክ በኋላ ጲላጦስ ኢየሱስን ወደ ውጭ አውጥቶ ለፍርድ ተቀመጠ፡፡ ጊዜው ከቀኑ 6 ሰዓት ያህል ነበር የሚለው ቅዱስ ዮሐንስ በሮማውያኑ አቆጣጠር እንደሆነ ልናስተውል
ይገባል፡፡ በአይሁዳውያኑ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ማለት ነው ዮሐ19፡13-14፡፡ ይህን ሰዓት በተመለከተ ብዙ ጭቅጭቅ ይነሳል/በተለይ መሀመዳውያን የሚያነሱት ሀሳብ ነው/፡፡ ምክንያቱም
ዮሐ 4፡6 ላይ 6 ሰዓት የተባለው ለምን ከዚህኛው ተለየ? በማለት፡፡ ዮሐ 4፡6 የአይሁዳውያን/ሳምራውያንን አውድ የተከተለ ታሪክ ነው፡፡ ዮሐ19፡14 ግን የሮማውያንን የፍርድ ቤት (መሥሪያ ቤት) አውድ የተከተለ ስለሆነ ሁለቱንም እንደ አውዳቸው ነው የፃፈልን፡፡
4. ኢየሱስ አርብ በአይሁዳዊያን ሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ 3 ሰዓት ተሰቀለ ማር15÷25

ስንጠቀልለው ቅዱስ ዮሐንስ የኢየሱስን የመስቀል ፍርድ የፃፈው ሮማውያን ከፈረዱበት ተነስቶ በመሆኑ የሰአት አቆጣጠሩንም እንደታሪኩ ፍሰት በሮማውያን አቆጣጠር አድርጎ ፅፎልናል፡፡ ሌሎቹ ወንጌላውያን ግን የጌታን ፍርድ ከአይሁድ ጋር አያይዘው እንደታሪኩ ፍሰት በአይሁዳውያን የሰዓት አቆጣጠር መሰረት በሶስት ሰዓት እንደተሰቀለ ፅፈውልናል ፡፡ እንደውም ከአራቱ ወንጌሎች
የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ታሪኩን ሙሉ ወንጌሉን ስናጠና ይህ የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ሶስቱ ወንጌላት ያላካተቱትን በመጀመሪያ ቃል ነበር ብሎ ቀዳማዊ ልደቱን ጀምሮ በጌታ መለኮታዊ እና አስደናቂ ታምራት ጌትነት ቀጥሎ ከትንሳኤው በኋላ ያደረገውን ፅፎ ጌታ ያደረገው ብዙ ነገር እንዳለ ግን አለም ራሱ መፅሐፍ ቢሆን ተጽፎ እንደማያልቅ ተናግሮ ፈፅሟል ፡፡ስለዚህም ዮሐንስን ወንጌል ከሌሎቹ ሶስቱ ወንጌላት በታሪኩ እና በአውዱ የተለየ ሌሎቹ ያላካተቱትን ታሪክ ይዟል

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በቅዱስ ሲኖዶስ የጸደቀው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ውጤት ይፋ ተደረገ

ምንጭ: EOTC public relation

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥያቄ
ቁርባን የተቀበልን እለት ብቻችንን መሆን የለብንም ሚባለው እውነት ነው? ምክንያቱስ?

መልስ በድምጹ ተልኳል አዳምጡት

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እኔ ምጠይቀው 1,ያመነ የተጠመቀ ነው የሚድነው 40እና 80ቀን ያልሞላው ህፃን ህይወቱ ቢያልፍ እንዴት ነው ሚሆነው
2,የአብርሀምና የሣራ ሙሉ ታሪካቸውን ማወቅ በጣም እፈልጋለሁ
3,ቅዳሴ ሳስቀድስ በሀሳብ እንዳልሔድና እየገባኝ እንዳስቀድስ ምን ላድርግ እግዚአብሔር ይስጥልኝ አመሰግናለሁ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሰላም ቤተሰቦች እንዴት አረፈዳችሁ የኔ ጥያቄ የነበረው
1 እግዚአብሔር ከእኔ በሰተቀር ቅርስ ቀርሳችሁ ወይም ስላችሁ(ምሰለ አዕድኖ) አተስገዱ የሚል የመጻፍ ቅዱስ ቃል አለ??? ካለስ
2 የሰማዕታትን እና ... የሌሎች ፃድቃን ምስል ሰዕል አንስቶ መስገድ በመፃፍ ቅዱስ ላይ አለ(ስገዱ የሚል) ወይስ በልማድ ነው?? ። 🙏🙏

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ከ4ቱ ወንጌላውያን 3ቱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ6ሰዓት እንደተሰቀለ ሲፅፉ ወንጌላዊው ማርቆስ ግን በ3ሰዓት ተሰቀለ ብሎ ፅፏል ይህ እዴት ነው መፅሐፍ ቅዱስ እርስ በእርሱ ይጋጫል ማለት ነው?የምታውቁ ብታሳውቁኝ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ቁርባን የተቀበልን እለት ብቻችንን መሆን የለብንም ሚባለው እውነት ነው? ምክንያቱስ?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✝የጥያቄ እና መልስ መርኀ ግብራችን ተጀምሯል ተከታተሉት✝

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🎬 እግዚአብሔር አምላክ ሰዎችን የሚያሳስተዉን ሴጣንን ለምን አላጠፋውም? የቤተክርስቲያን አስተምሮ በዚህ ላይ ምን ይመስላል?
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ

⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/gtbwgAce1MQ
https://youtu.be/gtbwgAce1MQ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አዲስ መጽሐፍ በገበያላይ

#ኦርታዶክሳዊ_ወጣት_እና_ፈተናዎቹ

#ዮጋ በስፊው ተዳሰዋል
ዲን ዳግማዊ ሰሎሞን አዘጋጅቶታል።ወንድሜ ዲን ዳግማዊ
#ኦርቶዶክስ_መልስ_ናት የሚል መጽሐፍ አስነብቦን ነበር።

የጀርባ ዋጋ
#320ብር
ዋና አከፋፋይ
አርጋኖን መጻሕፍት መደብር Areganon Book Store
በCBE 1365 ለሚያስገቡ 250ብር ብቻ።

#አንዱን_ርዕስ_እንጋብዛችሁ
#ዘፈን_ለማቆም_ምን_ላድርግ? (የብዝዎቻችን_ጥያቄ_ነው አይደል?)
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://www.facebook.com/groups/271884238121590/permalink/647188570591153/?mibextid=Nif5oz

#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ዋናው_በር_ፊትለፊት_ሽዋ_ዳቦ_መነጽር_ቤቶቹ_ውስጥ_ወይም_በ0912044752_0925421700_ይደውሉ!
/channel/BetMetsahfte

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✝ የትኛውን የመዝሙሮችን ግጥምና ዜማቸውን ፈልገው አተዋል?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#የያረድ_ዉብ_ዜማ

የያረድ ዉብ ዜማ ድንግል እመቤቴ
ስጦታዬ ነሺ /2/ በምን አንደበቴ
እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ/2/

ምድርና ሰማዩ ተአምርሺን ይንገሩ 
ፍጥረታት በሙሉ ስለ አንቺ ይመስክሩ 
ተነግሮ የማያልቅ ድንቅ ነው ስራሽ 
ድንግል ሆይ እናቴ አምሳያም የለሺ 
ማርያም ድንግል እረዳቴ
የምትደርሺልኝ ነይ ስልሽ በጭንቀተ 
ታምርሺንም በአይነ አይቻለሁ 
ጽዮን ሆይ ስልሽ ድንግል ሆይ እጠግባለሁ 
#አዝ
የእግዚአብሄር ጥበቡ በአንቺ ተገለጠ 
የአዳም ዘር በሙሉ ከሞት አመለጠ 
የመዳን ምክንያት ማርያም አንቺ ነሽ
ለፍጥረቱ ሁሉ መሰላል የሆንሺ
ነገን ባላውቅ እኔን ቢያስፈራኚ 
አንቺ ካለሺኝ በፍጹም አልወድቅም 
በፊትሺም እንድቆም ለምስጋና 
ማርያም ልበልሽ በትህትና 
#አዝ
ትውልዱ በሙሉ ለምስጋና ይቁም 
ባንቺ ስለሆነ የቀረለት መርገም 
አዳም ከነልጁ በሰማይ በምድር 
ማርያም ማርያም ይበል ተአምርሺን ይናገር 
ጨለማው ከፊቴ ተገፈፈ 
ማርያም በምልጃሽ ልቤ አረፈ 
ከጎኔ ነይ ስልሺ እጽናናለሁ 
እሳት ገደሉን ሁሉንም አልፈዋለሁ 

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​ሰኔ 21/10/2015 ዓ.ም

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌልና ምስባክ።

ምስባክ ፦ መዝ 45፥4-6
ቀደሰ ማኅድሮ ልዑል
እግዚአብሔር ውስተ ማዕከላ ኢትትሀወክ
ወይረድኣ እግዚያብሔር ፍጹመ

ትርጉም
ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ
እግዚያብሔር በመካከሏ ነው አትናወጥም
እግዚያብሔርም ፈጥኖ ይረዳታል

ወንጌል ፦ ማቴ 16÷13-20
ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ(የጌታ ቅዳሴ)

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 የሰኔ ማርያም ዚቅ

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 የሰኔ ማርያም ዋዜማ

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥያቄ 2
ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ሰይጣንን እረግጦ ባቶቹ እና ጡንቻዎቹ እየታዩ የተሳሉ አሉ። ሁለተኛው በተለይ በሁሉም እጅ ላይ አለ። ዝማሬ ዳዊት በዚህ ላይ የናንተ አስተምሮት ምንድን ነው?

መልሱ በድምጽ ተቀምጧል

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ስለ ስዕል አድኖ በቂ ትምህርት ብትሰጡን ለምሳሌ
1, እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አንዳንድ ቦታ ላይ ፀጉሯ እየታየ የተሳለ አለ

መልስ በድምጹ ተልኳል አዳምጡት

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥያቄ
ቅዱስ እግዝአብሔር ፍጥረታትን ፈጥሮ ቅዳሜ ቀን ነው ያረፈው  ታድያ እኛ ለምን ሰንበታችን እሁድ ሆነ???

መልስ በእዚህ ድምጽ ውስጥ ተካትቷል አዳምጡት

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ኢየሱስ የግዚአብሄር ልጅ ይባላል እራሱ እግዚአብሄር ከሆነ እንዴት ልጅ ይባላል???

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

1,አንዲት ሴት ከወለደች በኋላ ልጇን ክርስትና ሳታስነሳ ብትሞት ፍታት ይደረግላታል ወይ?
1ኛጢሞ 3፥1 ኤጲስ ቆጶስ አንድ ሚስት እንድትኖረው ይናገራል፤በቤተ ክርስቲያናችን ስርዓት ደግሞ ጳጳስ(ኤጲስ ቆጶስ) የሚሆነው ድንግል ነው ይህ እንዴት ነው?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ስለ ስዕል አድኖ በቂ ትምህርት ብትሰጡን ለምሳሌ
1, እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አንዳንድ ቦታ ላይ ፀጉሯ እየታየ የተሳለ አለ
2, ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ሰይጣንን እረግጦ ባቶቹ እና ጡንቻዎቹ እየታዩ የተሳሉ አሉ። ሁለተኛው በተለይ በሁሉም እጅ ላይ አለ። ዝማሬ ዳዊት በዚህ ላይ የናንተ አስተምሮት ምንድን ነው?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ቅዱስ እግዝአብሔር ፍጥረታትን ፈጥሮ ቅዳሜ ቀን ነው ያረፈው
ታድያ እኛ ለምን ሰንበታችን እሁድ ሆነ???

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🌺 ሰላም፡ለኵልክሙ። እነሆ የምስራች ግእዝን በአንድ ወር ኮርሳችን ልዩ በሆነ የክረምት ዝግጅት በ፱ኛው ዙር ትምህርት ተመልሷል።

📜 በመሆኑም የግእዝ ቋንቋን ለጀማሪዎች ቀለል ባለና ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅታችንን ጨርሰናልና ከታች በተቀመጠው ፎርም ተመዝግበው ጥንታዊና ውዱ ቋንቋችንን እናጥና ፥ ዕንወቅ።

📖 ትምህርቱን ከ14 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው፤ ስልክ ወይም ላፕቶፕ በመጠቀም መማር ይቻላል።

ለመመዝገብ በዚህ ይጠቀሙhttps://forms.gle/Hh3ivcARauXyd5A58
👆

🗣 ለሌሎችም ሼር በማድረግ እንድናዳርስ በትሕትና እንጠይቃለን። ለበለጠ መረጃ በ @Geez202 ወይም ደውለው ያግኙን። ሠናይ፡ጊዜ።

🈸 መሠረተ፡ግእዝ
@MesereteGeez - 0977682046

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

📣📣📣የምስራች ለወጣቶች አዲስ ዜና📣📣📣


✝ይህ መጽሐፍ ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ወጣት እጅግ የሚጠቅም አዲስ የወጣ መጽሐፍ ሲሆን።

👉ዘፈን ለማቆም
👉ክርስቲያናዊ አለባበስ እንዲኖረን
👉ጸሎት ሐሳባችንን ሰብስበን እንድንጸልይ
👉የእግዚአብሔርን ትክክለኛ ፍቅር እንድናጣጥም
👉ንስሐ እንዴት መግባት እንዳለብን
👉እንዴት መቁረብ እንዳለብን
👉 ቶ መስቀል የቤተክርስቲያናችን ነው አይደለም?
👉ማንነታችንን እንዴት ማግኘት እንችላለን? እንዴትስ አዲስ ማንነት ሊኖረን ይችላል...
እና ሌሎች ርዕሶች የተካተቱበት መጽሐፍ ነው።


እያለቀ ስለሆነ መጽሐፉ ቶሎ ገዝታችሁ ታነቡ ዘንድ ዝማሬ ዳዊት ይጋብዛችኋል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🎬 ፀበል ስንጠመቅ እርቃናችንን መሆን አለብን ወይስ በልብስ? ፈጣሪ ምን ሰራህ እንጂ ምን በላህ አይልም ይላሉ?
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ

⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/vpcA0p5ScOM
https://youtu.be/vpcA0p5ScOM

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ድንግል_ማርያም_ብዬ

ድንግል ማርያም ብዬ
ስማጸን በስምሽ (፪)
በቅድመ እግዚአብሔር
ልመናዬን አድርሽ (፪)

እኔ ደካማ ነኝ ኃጢአቴ የበዛ
እኔ ጎስቋላ ነኝ በደሌ የበዛ
ጊዜዬን ያባከንኩ በዋዛ ፈዛዛ
ጊዜዬን ያሳለፍኩ በከንቱ በዋዛ

እመብርሃን ስልሽ ፈጥነሽ ድረሽልኝ(፪)
ልመናዬን ሰምተሽ ቆመሽ ለምኝልኝ
ኃጢአቴ ቢበዛም ይዣለሁ አንቺን(፪)
አስምረሻልና በላዒ ሰብን
#አዝ
አንገት የሚያስደፋ በዝቶብኝ ኃጢአቴ
ምልጃሽን ፈለኩኝ ድንግል ሆይ እናቴ
ያን ክፉ ጨለማ እንዳላይ አደራ(፪)
ድንግል ሆይ ከልይኝ ከዲያብሎስ ጭፍራ
#አዝ
እመብርሃን እያልኩ ቆሜ ከደጅሽ
በብርሃን እጆችሽ እንባዬን አብሽ
ዓለም አታላይ ነች ወደሷ ተሳብኩኝ
ታማልጂኝ ብዬ አንቺኑ ተራብኩኝ

ሊቀ መዘምራን
ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ

"ጻድቃን እኔን ይጠብቃሉ"
መዝ፻፵፩፥፯

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#አመ_ትትሐነፅ

አመ ትትሐነፅ ኢየሩሳሌም በዕንቈ ሰንፔር ወበከርከዴን በዕንቁ ሴንፔር
ዓረፋቲሃኒ ለኢየሩሳሌም ወማኅፈዲሃኒ በወርቅ ንጹሕ ወመርኅባሰ ለኢየሩሳሌም

#ትርጉም
ኢየሩሳሌም በታነጸች ጊዜ በእንቔ ሰፔር በከርከዴን ነው ጎኖቿም ልባሷም ክዳኗም በንጹህ ወርቅ ነው ፡፡

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 የሰኔ ማርያም ወረብ

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 የሰኔ ማርያም እስመለ ዓለምና
ምልጣን

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​​​ሰኔ 21 ለሚከበረው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

#ሰኔ_20_እና_21

👉 ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ ህንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል።

የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የታነጸው በዛሬዋ ቀን ነው አናጺውም እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው።

ጴጥሮስ፤ ዮሐንስ በርናባስና ሌሎችም ሐዋርያት በፊልጰስዩስ ተሰብስበው ሳለ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፤ 3 ድንጋዮችን አንስቶ ጎተታቸው እንደ ሰም ተለጠጡ እንደ ግድግዳም ሆኑ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ እየሩሳሌም አምሳያ አድረጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፤ ዳግመኛ በበነጋው ሰኔ 21 ቀን እመቤታችንን እና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል ቅዳሴ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቆረባቸው ፍጹም ደስታም ሆነ።

ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታ እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተክርስቲያን አንጸዋል። ከዚያ በፊት የነበረው የነሶሎሞን ቤተ መቅደስ የአይሁድ ምኩራብ የአይሁድ ስርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ስርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፤ ታዲያ ሐዋርያት የት ነበር ህዝቡን የሚያጠምቁት የሚያቆርቡት ካሉ በየሰው ቤት ነበር።

ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን ታላቁ ነብይ ኤልሳዕ አረፈ። ይህ ነብይ በ 12 ጥማድ በሬ ሲያርስ ቴስቢያዊው ነብዩ ኤልያስ ተከተለኝ አለው ምንም ሳያቅማማ ሀብት ንብረቱን ትቶ ተከተለው፤ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ከማረጉ በፊት ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ ይለዋል ባንተ ላይ ያደረ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርቢኝ ይለዋል፤ እንደ ቃሉ ሆነለት ተደረገለት፤ ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል።

የእምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች፤ የዚህ ነብይ ድንቅ ታሪኩ 2ኛ ነገስት ላይ በስፋት ተጽፏል ሰኔ 20 ቀን እረፍቱ ነው ቤተክርስቲያን የዛሬውን ቀን እመቤታችንን እና ነብዩን አስባ ትውላለች።

ከበዓሉ ያሳትፈን የእመቤታችን ምልጃና ረዳትነት አይለየን!

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…
Подписаться на канал