ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

1. በሰንበት ልብስ ማጠብ ይፈቀዳል ወይ?
2. ዲቁና በስንት አመት ነው መቀበል የሚቻለው።

የሚሉት ጥያቄዎች ተመልሰዋል። ለዛሬ የጥያቄና መልስ ሰዓታችን አብቅቷል ነገ በተመሳሳይ ሰዓት ይጠብቁን።

ሠናይ አዳር

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ስለ ምሥጢረ ሥላሴ መውለድ እና መስረጽ የተመለሰ መልስ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ስለ ምሥጢረ ሥላሴ እና አምስቱን አእማደ ምሥጢር መማር የምትፈልጉ እዚህ ድምጽ ላይ ታገኙታላችሁ ተከታተሉ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

dekunena eske sent amet dres yesetal?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የሰው ልጅ የተወለደበትን የልደት ቀን ብያከብር ጣዋትነው

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የማማተብ ትርጉም ቢነገረኝ ደስ ይለኛል

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✝ሠላም የተወደዳችሁ የዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች✝

👉ዛሬ ምሽት ላይ ባለፈው የተጠየቁትን ጥያቄዎች መልስ የምንሰጥ ስለሆነ ሁላችሁም ከምሽቱ 3:0ዐ ጀምሮ ትጠብቁን ዘንድ በትኅትና እንጠይቃለን።

መልሱ ሌሎች እህት ወንድሞቻችን ይሰሙት እና ይማሩበት ዘንድ ይገባልና ለምታውቁት ኦርቶዶክሳዊ በሙሉ ይሄንን የቻናል ሊንክ ላኩላቸው
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ኦ_ሚካኤል

ኦ ሚካኤል መላዕከ ሃይል/2/
ስንጠራህ ድረስልን ኦ ሚካኤል መላዕከ ሃይል

ዘንዶው ጠላታችን ከፊታችን ቆሟል
ከባህር ሊጥለን አድፍጦ ያደባል
የመላዕክት አለቃ እርዳን በፀሎትህ
ጥበቃህ አይራቀን በቀን በሌሊት/2/

ክርስትና ኑሮ እጅጉን ከብዶናል
የጌታን ውለታ ፍቅሩን ዘንግተናል
አፅናኙ መልዐክ ከፊታችን ቅደም
በመንገድህ ምራን እንድንሆን ሰላም/2/

የጌታ ባለሟል የህዝብ እረኛ
ባህሩን አሻግረን ቅረበን ወደ እኛ
ከጌታህ አማልደን መልዐከ ራማ
የልጆችህን ቃል ድምፃችንን ስማ

በሚያስፈራው ዘመን ሰላም በሌለበት
ባስጨናቂው ጊዜ ፍቅር በጠፋበት
የፍቅርን ወንጌል ቃሉንም ስበከን
ሚካኤል ተራዳን ድረስም አፅናናን

ዘ/ዲ ሱራፌል ስዩም
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሥርዓተ ማኅሌት ዘሰኔ ሚካኤል
"ሰኔ ፲፪"

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ለጒርኤክሙ ስቴ አንብአ ሰብእ ዘኀሠሠ: ብኡላነ ሞገስ ሥላሴ ኢታንድዩኒ ሞገሰ: እመትትኃየዩኒሰ ኢትኅድጉኒ ጽኑሰ: ሚካኤልኑ ለአውጽኦ ስጋየ ጌሠ: ወእመ አኮ ገብርኤል ወሀበኒ ነፍሰ።

ዚቅ
ኢይጽሕቅ ዘይመክሮ ወኢየኀሥሥ ዘይመክሮ: አልቦቱ ጥንት ወኢተፍጻሜት: ኢየኀልቅ መንግሥቱ ወአልቦ ዘይክል መዊዓ ኀይሉ: ወአልቦ ኁልቊ ለሠራዊተ መላእክት እለ ይትለአክዎ: አንተ ውእቱ አቡሃ ለጥበብ: ገባሬ ኲሉ ፍጥረት ወገባሪሃ ለሕግ።

ነግሥ
ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል: ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል: አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሳሕል: እንበለ ባህቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል።

ዚቅ
አመ ይነፍህ ሚካኤል ቀርነ በደብረ መቅደስየ: አሜሃ ይትነሥኡ ሙታን: ይትፌሥሁ መላእክት በዕርገቱ: በፍሥሃ ወበሰላም አዕኮትዎ ለንጉሠ ስብሐት።

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ: ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ፀሃፈ: ሶበ እጼውእ ስመከ ከሢትየ አፈ: ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል በከመ ታለምድ ዘልፈ: ለረዲኦትየ ነዓ ሠፊሐከ ክንፈ።

ዚቅ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ዓቢተነ በመድኃኒትከ: ጸግወነ ንጸውዕ ስመከ: ኖላዊነ ኄር ትጉሕ ዘኢትነውም ሰላመከ ሀበነ።

ወረብ
ሀበነ ሰላመከ ንጸውዕ ስመከ/፪/
ዘኢትነውም ትጉሕ "ኖላዊነ ኄር"/፪//፪/

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለልሳንከ በነቢበ ጽርፈት ዘኢተኃበለ: በእንተ ስጋሁ ለሙሴ አመ ምስለ ሰይጣን ተበኃለ: ሚካኤል ክብርከ እምክብረ መላእክት ተልዕለ: ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ: በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ።

ወረብ
ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ/፪/
"በብሂለ ኦሆ"/፪/ ፍጡነ አስምአኒ ቃለ/፪/

ዚቅ
አመ ይነፍሕ ሚካኤል ቀርነ በደብረ መቅደስየ: አሜሃ ይትነሥኡ ሙታን: ይትፌሥሁ መላእክት በዕርገቱ: በፍሥሃ ወበሰላም አዕኮትዎ ለንጉሠ ስብሐት።

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ዕብል ለአስናኒከ ዘመንፈስ: ዘኢይረክቦን ጥረስ: ሚካኤል ረዳኢ ለእለ ውስተ ባሕር ወየብስ: እስመ ረሰይከ ካህነ ምሥዋኡ ክርስቶስ: መፍትው ሊተ ትተንብል ቀሲስ።

ዚቅ
ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ ምስሌሁ: ርኢክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቶ: ዮም ሰማያዊ በምድር አስተርአየ።

ወረብ
ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ/፪/
ርኢክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቶ ስዕንኩ/፪/

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለእስትንፋስከ ቁሱላነ ነፍስ ለአጥዕዮ: ዘይነፍሕ ፄና አንህዮ: ሚካኤል ነዓ ኲናተከ በተረስዮ: ለገቢር ከመ ቀዳሚ ለአርዌ አመፃ ደርብዮ: እስመ ኢኃደገ እንከ ዘትካት እከዮ።

ዚቅ
ወከሢቶ ረከበ ኀበ ይብል እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ: ወእከስተ ሎሙ ግዕዛነ ለጼውዋን: ወእፈውስ ሎሙ ለቁሱላነ ልብ: ወእሰምዮ ለባሕራን ኅሩየ: ዝኬ ዘተነግረ በመዋዕለ ትካት: ለ፳ኤል ኅብስተ መና ዘአውረደ በገዳም: ወርእየቱ ከመ ተቅጻ ወከመ አያያተ መዓር ጥዑም ፈድፋደ።

ወረብ
"ወከሢቶ ረከበ"/፪/ ኀበ ይብል እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ/፪/
ወእስብክ ሎሙ ግዕዛነ ለጼውዋን ወእስምዮ ለባሕራን ኅሩየ/፪/

መልክዐ ሚካኤል
ሰላም ለአጻብኢከ መጽሐፈ እለ ለክዑ: ዕጒለ አባግዕ እምኖሎት በጊዜ ተመልዑ: ሚካኤል አንተ ለንጉሠ ነገሥት ካህነ ምሥዋኡ: አሣዕነ መድኃኒት ለእገርየ አጻብኢከ ይቅጽዑ: ከመ በፍናውየ የኀዝ ለሰላም ቅብዑ።

ዚቅ
ቅዱሳት አጻብኢከ ለጽሒፈ መጽሐፍ እለ ተቀንያ: ወብጹዓት አዕይንቲከ ምስጢረ መለኮት ዘርእያ: ሚካኤል መልአክ ወሐዋርያ።

ወረብ
ምስጢረ መለኮት ዘርእያ አዕይንቲከ/፪/
ሚካኤል መልአክ ወሐዋርያ "ሚካኤል መልአክ"/፪//፪/

መልክዐ ሚካኤል
አምኃ ሰላም አቅረብኩ ለመልክዕከ ኲሉ: ለለአሐዱ አሐዱ ዘበበክፍሉ: ሚካኤል ክቡር ለልዑል መልአከ ኃይሉ: ተወኪፈከ አምኃየ እምኑኃ ሰማያት ዘላዕሉ: ዕሴተ ጸሎትየ ፈኑ ወአስብየ ድሉ።

ዚቅ
መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል: ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ: አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ ዓቢይ።

ወረብ
መልአከ ሰላምነ/፬/
ሊቀ መላእክት ሚካኤል ሰአል በእንቲአነ/፪/

ምልጣን
አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ: ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ: ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ: ወሪዶ እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ።

አመላለስ
ወሪዶ እመስቀሉ/፪/
እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ/፬/

ወረብ
አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ/፪/
ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ/፪/

እስመ ለዓለም
እምድኅረ ተንሥአ እሙታን ዓርገ ውስተ ሰማያት በስብሐት አምላከ ምሕረት: ወተቀብልዎ አዕላፋ አዕላፋት: ወሚካኤል ሊቀ መላእክት በንፍሐተ ቀርን እምኀበ እግዚአብሔር: ስብኩ ትንሣኤ ውስተ ኲሉ ምድር።

ዓዲ (ወይም)
እስመ ለዓለም
ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ: አዓርግ ሰማየ አቡየ ወአቡክሙ: ኀበ አምላኪየ ወአምላክክሙ: ዘንተ ይቤሎሙ ዓርገ ውስተ ሰማያት: ካዕበ ይመጽእ በዘዚአሁ ስብሐት: ሠርጎሙ ለሐዋርያት ብርሃኖሙ ለእለ ውስተ ጽልመት: መድኃኔ ነገሥት ክብሮሙ ለመላእክት ኖላዊሆሙ።

አመላለስ
በንፍሐተ ቀርን እምኀበ እግዚአብሔር/፪/
ስብኩ ትንሣኤ ውስተ ኲሉ ምድር/፪/
ኦ አምላከ ቅዱስ ሚካኤል ዕቀብ ሕይወተነ ወሥረይ ኀጢአተነ፤
አድኀነነ ወባልሐነ ከመ ኢይርከብ ኃይለ ላዕሌነ ዝንቱ ደዌ ዘኮነ በመዋዕሊነ፡፡
ክፍለነ እምበረከትከ ቅድስት፡ በጸሎተ ኲሎሙ ቅዱሳን እለ አሥመሩከ እምፍጥረተ ዓለም፡፡

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ስለዘፈን እህታችን ለጠየቀችው ጥያቄም መልስ በእዚሁ እንስጥበት
👇👇👇

ስለዘፈን የተዘጋጀ ትምህርት ስላለ ከርሱ አድምጡት

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👆
👆
👆
👆
👆
👆

እነዚህ ከላይ የተላኩትን ትምህርቶች አዳምጧቸውና ወደ ቀጣይ ጥያቄዎች ዛሬ ማታ ወይም ነገ የምንቀጥል ይሆናል።


መልካም ሰንበት

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

1. ንስሐ ምን ማለት?
2.ንስሐ በመጽሐፍ ቅዱስ?
3.ንስሐ በምሳሌ ስንረዳው
4. ንስሐ ለመግባት ምን ያስፈልገኛል?
5. የንስሐ ጥቅሙ ምንድነው?
6. ንስሐ ለመግባት እፈራለሁ ምን ላድርግ?
7.ለካህናት ለምንድን ነው ንስሐችንን የምንናገረው?ቀጥታ ለእግዚአብሔር ለምንድነው የማንናገረው? የሚሉ ነጥቦች እና ሌሎችም በውስጡ ተካትተዋል እንድታዳምጡት እንጋብዛለን

መልካም ቀን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የተጠየቁትን ርዕሶቹን ስንጠቀልላቸው
1. ስለ ጸሎት
2. ቅዱስ ቁርባን
3. ስለ ንስሐ ናቸው ትምህርቶቹን አዳምጡት

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ፀሎት ሳረግ ብዙ ነገር አስባለው ምን ላርግ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሠላም የተወደዳችሁ የዝማሬ ዳዊት ቻናል ተከታታዮች። እንደሚታወቀው ከትላንት ጀምሮ።

ጥያቄዎቻችሁን በየትኛው ርዕስ ዙሪያ ስንቀበል የነበረ ሲሆን።

ለዛሬው ዕለት #4 ጥያቄዎችን ለመመለስ አስበናል ጥያቄዎቹ ከታች የተጠቀሱት ናቸው።

👉እነዚህን ጥያቄዎች የመረጥናቸው ከእዚህ በፊት በዝማሬ ዳዊት እንደ ትምህርት ተዘጋጅተው ስለነበር። እርሱን በማዳመጥ እንድትጀምሩ በማሰብ ነው።


🙏ተከታተሉ🙏

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የልደትን ቀን ማክበር ኀጢአት ነው?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ኔትወርክ እንደምታውቁት እያስቸገረ ስለሆነ ትንሽ እየታገሳችሁ ትጠብቁን ዘንድ በትኅትና እንጠይቃለን።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስቀል የማማተብ ትርጉም
ምላሽ ተሰጥቶበታል አዳምጡት

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እኔ ሠራተኛ ነኝ እናም ያለችኝ እረፍት እሁድ ናት እናም በእሁድ እለት በጠዋት ተነስቼ ቤተክርስቲያን ሄጄ ከዛ መልስ ልብሴን ባጥብ ምን ችግር አለው ?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በስላሴ Consept መወለድ እና መስረፅ ልዩነታቸው

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንዴት አመሻችሁ የተወደዳችሁ የዝማሬ ዳዊት የቴሌግራም ቻናል ተከታታዮች እንደ አምላካችን መልካም ፈቃድ አብዛኞቹን የጠየቃችኋቸውን ጥያቄዎች አንድ በአንድ መመለስ እንጀምራለን


🫸🫸🫸ተከታተሉን🫷🫷🫷

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ናና_ሚካኤል_ናና

ናና ሚካኤል ናና /2/
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና
ናና ሚካኤል ናና

የረዳህ አፎምያን ሚካኤል ናና
ሰይጣን ሲፈትናት ሚካኤል ናና
አንተነህ ያዳንከው ሚካኤል ናና
ባሕራንን ከሞት ሚካኤል ናና
ለእነርሱ እንደመጣህ ሚካኤል ናና
እኔንም ተራዳኝ ሚካኤል ናና
ሚካኤል ደግፈህ ሚካኤል ናና
ለመንግሥቱ አብቃኝ ሚካኤል ናና
ናና ሚካኤል ናና /2/
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና

አዝ-------------

ናና ገብርኤል ናና /2/
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና
ናና ገብርኤል ናና

ዘመኑ ሲፈፀም ገብርኤል ናና
አምላክ መምጫው ሲደርስ ገብርኤል ናና
ገብርኤል አንተ ነህ ገብርኤል ናና
ያልካት ደስ ይበልሽ ገብርኤል ናና
ድምጽህን አሰማኝ ገብርኤል ናና
ነፍሴ ጽድቅን ትልበስ ገብርኤል ናና
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና
ናና ገብርኤል ናና

አዝ-------------

ናና ዑራኤል ናና /2/
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና
ናና ዑራኤል ናና

ቆመህ ጽዋ ይዘህ ዑራኤል ናና
ለእዝራ ሱቱኤል ዑራኤል ናና
ጥበብ አጠጥተህ ዑራኤል ናና
ዕውቀት ስታድል ዑራኤል ናና
ተገለጠ ክብርህ ዑራኤል ናና
መልአኩ ዑራኤል ዑራኤል ናና
ድኜ በፀበልህ ዑራኤል ናና
በአውደ ምህረትህ ላይ ዑራኤል ናና
እኔም ዘመርኩልህ ዑራኤል ናና
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና
ናና ዑራኤል ናና

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​​​ሰኔ 12 #የቅዱስ_ሚካኤል ዓመታዊ በዓል!

እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለእናታችን ቅድስት አፎሚያ አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። ሰኔ 12 ቅዱስ ሚካኤል እናታችን ቅድስት አፎሚያን ከጠላት ዲያብሎስ እጅ ያዳነበት ፣ እናታችን ቅድስት አፎሚያ እረፍቷ ነው ።እግዚአብሔር ከቅዱሱ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ፣ ከእናታችን ቅድስት አፎሚያ በረከት ተካፋይ ያድርገን ።

👉 በወርኃ ሠኔ መታሰቢያ ከሚደረግላቸው ቅዱሳን መካከል እግዚአብሔርን የሚፈራ የአስተራኒቆስ ሚስት የሆነች የቅድስት አፎምያን ታሪክ በአጭሩ እንዳስሳለን፡፡

ቅድስት አፎምያ በትዳር በነበረችባቸው ዘመናት እግዚአብሔርን ከሚወድ ባለቤቷ ጋር እግዚአብሔርን ስታገለግለው የኖረች ሴት ነበረች፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ እንደነበር ታሪካቸው ይነግረናል፡፡

ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጉል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አኖረችው፡፡

ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፡፡ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ ባያት ጊዜ ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡ በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ፣ ሌላ ባል አግብታ፣ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት፡፡

ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ፤ እነሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡ ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ፤ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ፡፡

በሠኔ ፲፪ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ሞከረ፡፡ ሰይጣን አስቀድሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገዳመ ቆሮንቶስ መጻሕፍትን እየጠቀሰ እንደተፈታተነው ሁሉ ቅድስት አፎምያንም ለማሳመንም አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን፣ ዳዊትን የመሳሰሉ ደጋግ አባቶችን ታሪክ እየጠቀሰ ወደ ትዳር እንድትገባ ደጋግሞ ወተወታት፡፡

ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና “የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?” በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ ጠየቀችው፡፡

ለጊዜው “በኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም” ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን ሊያስቀይራት ሞከረ፡፡ ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት አብራርታ የእሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት፡፡ ከቤቷ ላለው ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ ትክክለኛ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት፡፡ ቅድስት አፎምያም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን “ድረስልኝ” እያለች በጠራችው ጊዜ መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት፡፡

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሠኔ ፲፪ ቀን በሰላም ዐረፈች፡፡

ይህች የታመነች ቅድስት አፎምያ በሰላም እስክታርፍ ጊዜ ድረስ የተጓዘችበትን መንፈሳዊ ጎዳና አስተውለን ይሆን? አስቀድማ ከባሏ ጋር አንድ ሆና በታማኝነት ፈጣሪዋን አገለገለችው፡፡ በኋላም የባሏን ኑዛዜ አክብራ ምንም እንኳን ኃጢአት ባይሆንባትም በሁለተኛ ትዳር ራስዋን ማጠላለፍ አልፈለገችም፡፡ በጎ ሥራ አብልጣ በመሥራት እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ተፋጠነች እንጂ፡፡

ሰይጣን ልጅ አለመውለዷን ተጠቅሞ ያቀረበላትን የጋብቻ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ “መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ መናፍስት ከእግዚአብሔር እንደሆኑ መርምሩ” ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የታዘዘውን መመሪያ ተጠቅማ ሰይጣንን በተወክሎ እግዚአብሔር ተቃውማ አሸነፈችው፡፡ የቅዱስ ሚካኤልን ርዳታ ያገኘችውና በሰላም ዐርፋ ወዳገለገለችው እግዚአብሔር በክብር የሔደችው በጽናት ተጋድላ ነው፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛንም በጸሎቷ ይማረን፤ የቅዱስ ሚካኤል የረድኤቱ ኃይል ሁላችንንም ይጠብቀን፣ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ስለ ዘፈን ለጠየቃችሁት ጥያቄዎች

በእዚህ ድምጽ ላይ ለመዳሰስ የተሞከረው

👉🏽ዘፈን ማን እንዳስጀመረ ለመጀመርያ ጊዜ(ታሪካዊ አመጣጡ
👉🏽 ዘፈን በመጽሐፍ ቅዱስ
👉🏽ዘፈን ያመጣው ጣጣ
👉🏽ዘፈን ለማቆም ምን እናድርግ
👉🏽የውጪው ሀገር በዘፈን ምን ላይ ደርሰዋ እስከ ታዋቂ ሰዎች ጭምር

መልካም ጊዜ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

zefen mesmat or zefen mezfen hatiat new ende🧐

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✝️በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::✝️

እንደምን አመሻችሁ የተወደዳችሁ ኦርቶዶክሳውያን እህቶቼ እና ወንድሞቼ?


በእዚህ ድምጽ ውስጥ የሚዳሰሱት ነጥብ

🌹ቅዱስ ቁርባን ምንድነው? ምን ማለት ነው?

🌹ቅዱስ ቁርባን መቀበል እፈልጋለሁ ግን በእዚህ እድሜዬ እችላለሁ?

🌹ቅዱስ ቁርባን በሐዲስ ኪዳን እና በብሉይ ኪዳን


🌹ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ምን አይነት ዝግጅት ማድረግ አለብን?(ወደ ሥጋ ወ ደሙ ከመቅረባችን በፊት; በቀረብን ጊዜ; ከተቀበልን በኃላ ምን ማድረግ አለብን?)

🌹የአምላካችንን ቅዱስ ሥጋ ና ደም በመቀበላችን ምንደነው በህይወታችን የምናገኘው ጥቅም?



🗣በይሳኮር🙏

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንደምን አደራችሁ እህቶቼ እና ወንድሞቼ?

ክርስቶስ ኢየሱስ ተወልዶላቹህል: እናንተም አባቴ ሆይ ከልደትህ ጀምሮ እስከ ስቅለትህ በልባችን ውስጥ ኑርልን; ፍቅርህን ሳልብን; የአባትነት ፍቅርህ ከአቅማችን በላይ ሆኖ ሁል ጊዜ ስናስብህ እንባችን በፍቅርህ ይፍሰስ😭😭😭

ኑሮዬ;ውሎዬ; ደስታዬ አንተ ሁንልኝ::

ሰዎች የማማርህ/ሽ ምሥጢር ምንድነው? እንደዚህ ሰላምን ማግኘትሽ? እያሉ ሲጠይቁኝ ትላንትናዬን በቁስሉ ያጠፋልኝ: ዛሬዬን በሩህሩህ አይኖቹ የሰራልኝ; ገደሉን በእቅፉ ያሻገረኝ;

በማየት ብቻ ልቤን የሚያውቅብኝ

አባቴ;ጌታዬ;ሠላሜ;ወዳጄ; እግዚአብሔር ነው ብለን የምንመሰክርበትን ዕለት እርሱ ያድለን::

😇😇😇😇😇😇😇😇😇😇😇😇😇😇😇😇በእዚህ ድምጽ ውስጥ😇😇😇😇😇

1.ጸሎት ምን እንደሆነ
2.ጸሎት መጀመርያ ማን እንደ ጀመረ?
3.ጸሎት ስናደርግ ልባችን ሁል ጊዜ ይሰራረቃል አይደል?
ለእርሱ መፍትሔው ምንድነው?
እና ሌሎችም

እንድታዳምጡ እጋብዛለሁ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የንስሀ አባት ስንይዝ ንስሀ አባታችን ለኛ ምን ምንድነው ሚያደርጉልን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንዴት አመሻችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ስለ ንስሃ የንስሃ አባት እንዴት መያዝ እንችላለን መልካም አባት ብዙ ጊዜ ይባላል እንዴት ነው የምናውቀው መልካምነታቸውን ብታስረዱኝ በሰፊው
ክብር ይስጥልኝ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✝✝✝✝ማሳሰቢያ✝✝✝✝

1. ጥያቄ መጠየቅ ነው እንጂ የምትችሉት። መመለስም ሆነ መከራከር፣መውቀስ አትችሉም።

2. የእራሳችሁን ብቻ ጥያቄ አቅርቡ እንጂ በግል አውሩኝ ምናምን የሚል መልእክት የሚልኩ ሰዎች።

ግሩፑን ስለሚያውኩ ከግሩፑ የምናስወጣ ይሆናል።

Читать полностью…
Подписаться на канал