ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

4. በየደረጃ ያሉ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሥራ ኃላፊዎች እና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ምዕመናን ከአሁን ቀደም በቤተ ክርስቲያናችን ላይ በደረሰው ፈተና በሐዘንና በጸሎት ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን በመቆም ላሳያችሁት ጽናት እያመሰገንን አሁንም በደረሰው ፈተና እንዳሁን ቀደሙ ሁሉ በሐዘንና በጸሎት ከቤተ ክርስቲያናችን ጎን ጸንታችሁ እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

5. በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ ተገቢውን ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ በትግዕስት እንድትጠብቁ እናሳስባለን፡፡

6. ምንም እንኳን ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ ጥሪው በደብዳቤ የተላለፈ ቢሆንም የመልእክቱ በፍጥነት መድረስ ካለው ስጋት አንጻር የችግሩን ተደጋጋሚነትና አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ክፍለ ዓለማት የምትገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ተጠቃላችሁ ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ እንድትመጡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡


7. ሁሉም የቤተ ክርስቲያናችን ሚዲያዎችና ሌሎች መገናኛ ብዙኃን ይህን መልዕክት ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን መልእክቱን በማስተላለፍ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ በቤተ ክርስቲያናችን ስም እንጠይቃለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም.

ምንጭ: ኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

📍 ለመሆኑ በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ መዝሙር ቻናል ተቀላቅለዋል ? የሰርግ ፣ የሀዘን ፣ የንግስ መዝሙራት ፣ የተለያዩ ወረባት ፣ የመዝሙር ግጥሞችን ያገኛሉ ። አብረውንም መዝሙራትን ያጠናሉ ። # ይቀላቀሉን  👇👇

/channel/+_R21gL_5brU5MDRk
/channel/+_R21gL_5brU5MDRk

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

#ሼር_እንድታደርጉ_በቤተክርስቲያን_ስም_እንጠይቃለን

❖ ታላቅ የንግሥ ጉዞ ወደ ተአምረኛው ስእለት ሰሚ

ደርሶ መልስ

ቁልቢ ቅዱስ/ገብርኤል ገዳም

ድሬዳዋ የሚገኙ ገዳማትና አድባራትን ጨምሮ

  → መነሻ ሐምሌ 16
  → መመለሻ ሐምሌ 20

  → የጉዞ ዋጋ፦ ትራንስፖርትን ማረፊያና ቤትን ጨምሮ 2500 ብር

ለበለጠ መረጃ☎️ +251986677077
                     ☎️ +251907748876
                     ☎️ +251941747170

ፈጥነው ትኬት ይቁረጡ ውስን ቦታዎች ብቻ ነው ያሉን

ለጉዞ መረጃ /channel/ENATEZ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የእዚህን ጥያቄ መልስ የተዘጋጀ ትምህርት ስላለ እርሱን እንድትከታተሉ እጠይቃለሁ።👇👇👇

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሥራ ፲፫፡ ፴፮። ይህ በሥጋ የሚገጥም አካላዊ ሞት በምድር ካለ የዘወትር ድካም፤ ሐዘን፤ ሕመም፤ ፍርሐት ይህችን ዓለም ከሞላባት ድካም ሁሉ ማረፊያ መንገድ ነው። ራዕይ ፲፬፡ ፲፫። ሞት የእግዚአብሔር እውነት ብቻ ወደ ነገሰችባት፤ ሰማያዊው ብርሃን ወደ ሚያበራባት፤ የሰው ነፍስ ፍጻሜ የሌለው ደስታ ወደ ምታገኝባት ዓለም መሻገሪያ ድልድይ ነው። ፩ኛ ተሰ ፬፡ ፲፫-፲፭፤ ፪ኛ ቆሮ ፭፡ ፩-፰። የወገኖቻችን ወደ ሌላ ዓለም በሞት መሻገር የኛም መጨረሻ መቃረቡን ያስታውሰናል። ስለዚህ መጨረሻችን ሕመምና ፍርድ የሌለበት ሰላማዊ የሆነ ክርስቲያናዊ ፍጻሜ እንዲሆንና በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት እንዳይፈረድብን ለነርሱ ስንጸልይ ለራሳችንም እንጸልይ። ሉቃ ፲፮፡ ፳፪።

ተዝካር በመፀሐፍ ቅዱስ ጥበበኛው ሲራክ እንዲህ ብሉል ሲራክ 38÷16 ልጄ ለሞተ ሰው አልቅስለት እዘንለትእደአገሩ ተዝካር አውጣለት ይላል ። የሞተሰውስ ዓረፈ ነገር ግን ነፍሱ ታርፍ ዘንድ ተዝካር አውጣለት ከዚህ በሁላ ለቅሶህን ተው በማለት በሐይማኖት ኖረው ለሞቱ ወገኖች ተዝካር ማውጣት ተገቢ መሆኑን ያመለክታል ። ጠቢቡ ሶሎሞንም የፃድቅ መታሰቢያተዝካር ለበረከት ነው በማለት ተናግሩል ።ምሳ 10÷7ይህም በእግዚያብሔር ቤት ኖረው ላረፉ ወገኖች ማውጣት ላውጪው በርድከት ነው ። ተዝካር እዴት ይወጣል ለመሆኑ ተዝካር ለማውጣት ላቅ ያለ ድግስ መደገስ ግዴታ ነውን ? መልሱ አጭር ነው። አይደለም ተዝካር የሚወጣው በምን በምን እደሆነ የቤተክርስቲያን ስረዓት። "በፀሎግ በመሥዋዕት በመብራት በማዕጠንት እና በምፅዋት በማለት ተንትኖታል ።በፀሎተ ፍትሐት ዳዊት መድገም። በመሥዋዕት በመብራት በጡፋ በማዕጠንት በመብራት መስዋት። በገንዘብ በልብስ በእህል ውሀ ወዘተ የሚሰጥ ልገሳ ነው ። በመሆኑም ተዝካር ማውጣት ማለት የሙት ስም በጸሎት እንዲነሳ ቅዳሴ እንዲቀደስ ቁርባን እንዲቆረብ ማድረግ ነው።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥያቄ

    እግዚአብሔርም የሰውን ልጅ በመፍጠሬ ተፀፀትኩ አለ ።
አንግዲ መፀፀት ማለት ባለፈው ነገር መቆጨት ነው
እግዚአብሔር ደግም ዛሬ ሚሆነውን ወደፊትም እሚሆነውን ያውቃል ታዲያ እኛ እንደምንበድለው እያወቀ
1 ለምን ፈጠረን
2  ለምን ተፀፀተ

ጋብቻን በቤተክርሰቲያን ለመፈፀም ከሙሸሮቹ ወይም ከተጋቢዎቹ ምን ምን ያሰፈልጋ ወይም ይጠበቅባቸዋል

መልስ👇👇👇

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

Setoch lmndnw be bethelem bekul malef mayechelut

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሰው ከሞተ ቡሀላ 40 80 ቁርባን እየተባለ ተደግሶ እሚበላው ለሞተው ሰው ነብስ ምንድነው ጥቅሙ ሌላው ሰው ከሞተ ነብስ ይማር ማለት ወይም ስለሱ ነብስ መፀለይ ከፍርድ ያድነዋል

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እግዚአብሔር ይስጥልኝ የኔ ጥያቄ
እግዚአብሔርም የሰውን ልጅ በመፍጠሬ ተፀፀትኩ አለ ።
አንግዲ መፀፀት ማለት ባለፈው ነገር መቆጨት ነው
እግዚአብሔር ደግም ዛሬ ሚሆነውን ወደፊትም እሚሆነውን ያውቃል ታዲያ እኛ እንደምንበድለው እያወቀ
1 ለምን ፈጠረን
2 ለምን ተፀፀተ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

begena siderder lamendenw ba gera eji yahonew gera eji yalelaw sew kale be kegu me metate yechelal way ??

መልስ👇👇👇

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሰላም የእግዚሃብሔር ቤተሰቦች የኔ ጥያቄ
1.በሌላ እምነት የነበረ ሰው የስላሴን ልጅነት ለማግኘት ምን ማድረግ ይገባዋል
2.አንድ ሴት የወር አበባ ላይ ሆና የቅዳሴ ፀበል መጠጣት ይቻላል ወይ


መልስ👇👇👇

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መልሶቹ እነሆ ያዳምጧቸው
👇👇👇👇👇👇

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ለንሰሀ ለመቅረብ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታወች ወይም ዝግጂቶች ምን ምን ናቸው ?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በክርስትና ህይወት ዉስጥ ከፍላጎት ባሻገር ለዉጥ ማምጣት አለመቻል ለምን ይሆን።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሰላም የእግዚሃብሔር ቤተሰቦች የኔ ጥያቄ
1.በሌላ እምነት የነበረ ሰው የስላሴን ልጅነት ለማግኘት ምን ማድረግ ይገባዋል
2.አንድ ሴት የወር አበባ ላይ ሆና የቅዳሴ ፀበል መጠጣት ይቻላል ወይ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በትግራይ በተከናወነው የሕገ ወጥ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ለሐምሌ 25/2015 ዓ.ም ምልዐተ ጉባኤ ጠራ።

1. በክልል ትግራይ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በክልሉ ከሚገኙት አህጉረ ስብከት ጋር ተቋርጦ የነበረውን መዋቅራዊ ግንኙነት ችግር በውይይት እንዲፈታ ቅዱስ ሲኖዶስ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪና ልዑካኑን በአካል ልኮ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ባለበት ወቅት በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አባቶች ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ ቅዱስ ፓትርያርኩ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ተብለው በሚጠሩበት በማዕከላዊ ትግራይ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 15 እና 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በተከናወነ ሕገ ወጥ ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት መፈጸሙን በመገናኛ ብዙኃን ለማወቅ ችለናል፡፡ በመሆኑም በዚህ የዶግማና የቀኖና ጥሰት ተግባር የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በእጅጉ አዝኗል፡፡

2. በመሆኑም የተከሰተው የዶግማ፣ የቀኖና እና አስተዳደራዊ ጥሰት አስመልክቶ ተወያይቶ ተገቢውን ለመወሰን ለሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪ ተላልፏል፡፡

3. የስብሰባው ቀን ሊራዘም የቻለው በውጭው ክፍለ ዓለማት ያሉት ሊቃነ ጳጳሳት መገኘት ስላለባቸው የጉዞ ቀኑ እንዳያጥር እና በሀገር ውስጥ የሚገኙትም ሊቃነ ጳጳሳት ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት ለአገልግሎት ወደ አህጉረ ስብከታቸው የሄዱ በመሆኑ ለመመለሻ የሚያስፈልገውን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ ነው፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✏️ ከ120,000 በላይ ባለ ማህተቦች ምእመናን ያሉበት ከ1500 በላይ አዳዲስ እና የዱሮ መዝሙሮች ከነግጥማቸው የምታገኙበትን ድንቅ ኦርቶዶክሳዊ የሆነውን ቻናል አሁንኑ ተቀላቀሉ📍

👇👇 የመዝሙር ግጥሞች📙

/channel/+_R21gL_5brU5MDRk
/channel/+_R21gL_5brU5MDRk

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🙏በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅድስ አሐዱ አምላክ አሜን 🙏

የእግዚአብሔር ልጆች እንዴት ዋላችሁ?

ዛሬ በዚህ ድምጽ ላይ የምንመለከተው

1 ልብስ ምንድነው ትርጓሜ?

2 ለመጀመሪያ ጊዜ ልብስ የለበሱት እነማን ናቸው በመፅሐፍ ቅዱስ?

3 የአለም ታሪክ ስለ mini skirt ምን ይላል ?👯‍♀️💃🏻💃🏻💃
4 የአለም ታሪክ ስለ crop top ምን ይላል?👗
5 ክርስቲያናዊ የሆነ አለባበስ ምንድነው?

6 ክርስቲያዊ አለባበስ አለመልበስ ምን ችግር ያመጣል ?

7 መፍትሔዎች ምንድን ናቸዉ ?

የሚሉትን እንመለከታለን የምንሰማውን እንድናስተውል አምላከ ቅዱሳን ይርዳን 🙏

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥያቄ
ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit:
አንድ ሰው ከክርስቲያም ቤተሰብ ተወልዶ ሳይጠመቅ ቢሞት ለምንድን ነው መቃብር ቤት ቤተክርስቲያን እማይቀበረው ?!

2.Setoch lmndnw be bethelem bekul malef mayechelut

መልስ👇👇👇👇

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጸሎተ ፍትሐት
ለሞተ ሰው ጸሎት ማድረግ ለምን አስፈለገ ?

ፍትሐት ማለት ከኃጢአት እስራት መፍታት ወይም መፈታት ማለት ነው፡፡ ስለዚህም ለሞቱ ሰዎች የሚደረገው ጸሎት ጸሎተ ፍትሐት ይባላል። የሙታን ነፍሳት ከሥጋ እንደተለዩ እስከ እለተ ምጽአት ድረስ በማረፊያ ቦታ ይቆያሉ እንጂ በቀጥታ ወደ መንግስተ ሰማይ ወይም ወደ ገሃነመ እሳት እንደማይላኩ ቤተ ክርስቲያን የምታምነውና የምታስተምረው ትምህርት ነው፤ እስከ ፍርድ ቀን ድረስ የሚቆዩበትም ቦታ ለጻድቃን ገነት ሲሆን ለኃጢአተኞች ደግሞ ሲኦል ነው። የጻድቃን ማረፊያ ቦታቸው ገነት መሆኑን ለማመልከት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ በነበረ ጊዜ ንስሐ ለገባው ወንበዴ፡ “በእውነት እልሃለው ዛሬውኑ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ” ብሎታል። ሉቃስ ፳፫፡ ፵፫። የኃጢአተኞች መቆያ ደግሞ ሲኦል መሆኑን ለማመልከት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሀብታሙ ሰውና በድኻው አልዓዛር ምሳሌ ትምህርቱ ሀብታሙ ሰው በሲኦል ውስጥ እንደነበረ ገልጿል። ሉቃስ ፲፮፡ ፳፫፡፡ በሙታን ትንሣኤ ጊዜ የምንነሳው በውርደት ወይም ክብር በሌለው ሁናቴ በመሬት ውስጥ እንደተቀበርነው ሳይሆን፣ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው በክብር፣ በኃይልና በመንፈሳዊነት ነው። ፩ኛ ቆሮንቶስ ፲፭፡ ፵፪-፵፬። ከዚያም በኋላ ወደ ክርስቶስ የፍርድ ፊት እንቀርባለን። ፪ኛ ቆሮንቶስ ፭፡ ፲፤ ራዕይ ፮፡ ፱-፲፩፡፡ ይቅርታ በዚሁ ዓለምና በሚመጣውም ዓለም መኖሩን ቅዱስ መጽሐፍ ያስረዳል። ማቴዎስ ፲፪፡ ፴፪፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቶ ለነበረው ለኦኔሲፎር “በመጨረሻው ቀን ምሕረትን ይስጠው” ብሎ ጸልዮለታል። ፪ኛ ጢሞቴዎስ ፩፡ ፲፰። ቤተ ክርስቲያንም ይህንኑ ጸሎት ለሞቱ ሁሉ ትጸልያለች። ለሞቱ ሰዎች መጸለይ ደግሞ በጥንት በዘመነ ብሉይም ነበረ። ጀግናው ይሁዳ መቃብዮስ በጦርነት ለሞቱ ወታደሮቹ የኃጢአት መሥዋዕት ይደረግላቸው ዘንድ ሁለት ሺህ የብር ድራህም አሰባስቦ ወደ ኢየሩሳሌም ልኳል። ፪ኛ መቃብያን ፲፪፡ ፵፫፤ ዕዝራ ሱቱኤል ፮: ፴፭። አይሁድ ለሙታን ሲጸልዩ ዳዊት ይደግማሉ። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች በተላከው የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ላይ ባደረገው ስብከቱ እንዲህ ብሏል “አንድ ሰው ኃጢአተኛ እንደሆነ ቢሞት የምንችለውን ያኽል ልንረዳው ይገባል። የምንረዳውም በለቅሶና በሐዘን ሳይሆን በጸሎት፣ በምጽዋትና በቁርባን ነው። የዓለምን ኃጢአት ወደ ተሸከመው የእግዚአብሔር በግ ስለ ሙታን የምንጸልየው እነርሱ መጽናናትንና እረፍትን እንዲያገኙ ብለን ነው እንጂ በከንቱ አይደለም። ጻድቁ ኢዮብ ስለልጆቹ ያቀርብ የነበረው ቁርባን ጠቀሜታ ከነበረው ስለ ሙታን የምናቀርበው ቁርባን ምንኛ የበለጠ ጠቀሜታ ይኖረው?

ከሞትም በኋላ ቢሆን በሰዎች መካከል የሚኖረው መንፈሳዊ ግኑኝነት በጸሎት አማካይነት ይቀጥላል። ሉቃ ፲፮፡ ፲፱-፴፩። በእምነት የሚደረግ ጸሎት ኃይል እንዳለው ተራራንም ለማንቀሳቀስ እንደሚያስችል በወንጌል ተገልጾልናል። መጽሐፍ ቅዱስም የአንዱ ሰው ጸሎት ሌላውን እንደሚራዳ ያስተምረናል። ዮሐ ፬፡ ፵፮-፶፫፤ ማቴ ፲፭፡ ፳፩-፵፰፤ ማር ፱፡ ፲፯-፳፯፤ ማር ፪፡ ፪-፲፪፤ ማቴ ፰፡ ፭-፲፫፤ ዮሐ ፲፩፡ ፩። ጌታችን ከላይ ከተጠቀሱት ተአምራት በርካታዎቹን በአካል በቦታው ተገኝቶ ሳይሆን ሳይገኝ በኃይሉ ፈጽሟል። ጸሎት እንደ ብርሃን ነጸብራቅ የሚጓዝና የሚያበራ የፍቅር ውጤት ነው። እግዚአብሔርን አምነው የሚጸልዩትን ከምድር ጫፍ እስከ ምድር ጫፍም ይሁን የእርሱ አገር እስከ ሆነውም አልፎ ያገናኛል። ጸሎት እኛ የምንኖርባትን ዓለም ከመላእክት፤ ከቅዱሳንና በሞት የተለዩን ወገኖቻችን ከሚገኙባት ዓለም ጋር ያገናኛል። ሞት በጌታችን ትንሳኤ የተነሳም የቀደመ ኃይሉን አጥቷል። ትንሳኤውም የአዲስ ሕይወት መጀመሪያ ሆኗል። ሮሜ ፰፡ ፴፰- ፴፱። በዚህም የተነሳ እግዚአብሔርን #ሁሉ ለእርሱ ሕያዋን ስለ ሆኑ፥ የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም; እያልን ሁሉ በሕይወት ይኖሩ ዘንድ እንጸልያለን። ሉቃስ ፳፡ ፴፰። በዚህ ዓለም የነበሩ ክርስቲያኖች በሕይወት በነበሩበት ዘመን ከቤተ ክርስቲያናቸው ጋር የነበረው ግኑንነት ከአረፉም በኋላ አይቋረጥም። በገነት ከሆኑ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ስለ እኛ ሊጸልዩልን ነጻነት አላቸው። ወደ ሲኦል የወረዱም ከሆኑ በዚያ ሆነው የእኛን ጸሎት ይሻሉ። ቅዱስ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያንን መሠረቶቿ በምድር ሆነው ጫፎቿ ከሰማይ ጋር የተያያዙ አድርጎ መመሰሉም ይህንኑ ለማስረዳት ጭምር ነው። #ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፥ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላዕክት፥ በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፥ የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።; ዕብ ፲፪፡ ፳፪-፳፬። ይህም የሚያመለክተው በሰማይና በምድር ባሉት አብያተ ክርስቲያናት መካከል የማይጠፋ የጠበቀ ግኑኝነት ያለ መሆኑን ነው። በምንጸልየውም ጸሎት የዘመናት ገደብ ሳይኖርብን የሐዋርያት፤ የሰማእታትና የቅዱሳን ሁሉ ጸሎትም እንዲረዳን እንጸልያለን።

ጸሎተ ፍትሐት የሚደረገው ሳይታወቁ ለተፈጸሙ ኃጢአቶች፣ በድብቅ ለተፈጸሙ ኃጢአቶች፣ እንዲሁም ለተረሱ ኃጢአቶችና ኃጢአት ሰሪው ኃጢአት መስራቱ ሳይሰማው የሚሰራቸው ኃጢአቶች ናቸው። እንደነዚህ ያሉት ኃጢአቶች ከሰው ተፈጥሮ ደካማነት የተነሳ የሚፈጸሙ መሆናቸው ቢታመንበትም በእግዚአብሔር ፍትሕ በኩል ግን እንዲህ አይደለም። እግዚአብሔር ለሙሴ የነገረው “አንድ ሰው ባለማወቅ ከእግዚአብሔር ትእዛዝ አንዱን ቢተላለፍ በደለኛ ነው” ብሎ ነው፡፡ ዘሌዋ ፭፡ ፲፯። ሰው አፈር የሆነውን ሥጋ የለበሰ እንደመሆኑ መቼም ቢሆን ሙሉ ለሙሉ ከኃጢአት የነፃ ሊሆን አይችልም። “ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናታልላለን፣ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም” እንዲሉ። ፩ኛ ዮሐንስ ፩፡ ፰። እግዚአብሔር በንስሐ የሚመለሰውን ሰው በማንኛውም ጊዜ ቢሆን ይቀበለዋል።፡ ለምሳሌ በሞት አፋፍ ላይ የነበረውና ከጌታችን ጋር ተሰቅሎ የነበረው ወንበዴ ንስሐው ተቀባይነት ያገኘው በመጨረሻው ደቂቃ ነው። ስለዚህ ንስሐ የገባ ሰውና በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያገኘው ማን እንደሆነ ስለማናውቅ ለሁሉም እንጸልያለን። ለሙታን የሚደረግ ጸሎት ወይም ጸሎተ ፍትሐት ዘወትር ጠቃሚ ነው። ወደ ገነት ለመግባት ላልታደሉት ጸሎቱ ዕድላቸውን ከመቃብር በላይ ያደርግላቸዋል። #በሰማይ ስማ ሰምተህም ይቅር በል።; ፪ኛ ዜና ፮፡ ፳፩። በገነት ላሉትም እንደ ታላቅ ብርሃን እየፈነጠቀ ታላቅ ደስታን ይሰጣቸዋል። በዚህም መሠረት ቤተ ክርስቲያን በፍትሐት ጸሎት አምና ለልጆቿ ምህረትን ትለምናለች፣ ይህንኑም ታስተምራለች።
ከጎናችን ያለ ሰው ሲያዝን እኛስ ማዘናችን ይቀራል? ጌታችን ወዳጁ አልዓዛር ሲሞት አዝኖለት እንባውን አፍስሷል። ይሁን እንጂ በሞት የተነሳ የሚገጥመን ሐዘን ግን በእግዚአብሔር እስከ ማጉረምረም ሊያደርሰን አይገባውም። ሞት ለጊዜው የነፍስ ከሥጋ መለየት እንጂ የሰው ለዘላለም መጥፋት አይደለም። በመጽሐፍ ቅዱስም እንቅልፍ እየተባለ ተጠቅሷል። የሐ.

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እስቲ ስለ ሴት ልጅ አለባበስ ንገሩኝ በክርስትና ሀይማኖት ሴት ልጅ ፀጉር መግለጥ፣ሱሪ መልበስ፣አጫጭር ቀሚስ መልበስ ተፈቅዶላታል ወይስ አልተፈቀደላትም???

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አንድ ሰው ከክርስቲያም ቤተሰብ ተወልዶ ሳይጠመቅ ቢሞት ለምንድን ነው መቃብር ቤት ቤተክርስቲያን እማይቀበረው ?!

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጋብቻን በቤተክርሰቲያን ለመፈፀም ከሙሸሮቹ ወይም ከተጋቢዎቹ ምን ምን ያሰፈልጋ ወይም ይጠበቅባቸዋል

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ለንሰሀ ለመቅረብ  የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታወች ወይም ዝግጂቶች  ምን ምን ናቸው  ?

መልስ👇👇👇👇

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥያቄ
በክርስትና ህይወት ዉስጥ ከፍላጎት ባሻገር ለዉጥ ማምጣት አለመቻል ለምን ይሆን።

መልስ👇👇👇

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥያቄ
እግዚአብሔር ለጥያቄዬ መልስ መስጠቱን እንዴት እናውቃለን ? እና ለዛ ጥያቄ መልሡ ዝምታ ከሆነስ?



መልስ👇👇👇

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መንታ ወንድ እና ሴት ብወለዱ ክርስትና እንደት ነው ማስነሳት የምቻለው?????

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

begena siderder lamendenw ba gera eji yahonew gera eji yalelaw sew kale be kegu me metate yechelal way ??

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በሀሳብ ምንሰራውን ሀጥያት እንዴት ባለ ነው ሀትያቱ ሚሰረየቅ?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እግዚአብሔር ለጥያቄዬ መልስ መስጠቱን እንዴት እናውቃለን ? እና ለዛ ጥያቄ መልሡ ዝምታ ከሆነስ?

Читать полностью…
Подписаться на канал