ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጸሎተ ፍትሐት
ለሞተ ሰው ጸሎት ማድረግ ለምን አስፈለገ ?

ፍትሐት ማለት ከኃጢአት እስራት መፍታት ወይም መፈታት ማለት ነው፡፡ ስለዚህም ለሞቱ ሰዎች የሚደረገው ጸሎት ጸሎተ ፍትሐት ይባላል። የሙታን ነፍሳት ከሥጋ እንደተለዩ እስከ እለተ ምጽአት ድረስ በማረፊያ ቦታ ይቆያሉ እንጂ በቀጥታ ወደ መንግስተ ሰማይ ወይም ወደ ገሃነመ እሳት እንደማይላኩ ቤተ ክርስቲያን የምታምነውና የምታስተምረው ትምህርት ነው፤ እስከ ፍርድ ቀን ድረስ የሚቆዩበትም ቦታ ለጻድቃን ገነት ሲሆን ለኃጢአተኞች ደግሞ ሲኦል ነው። የጻድቃን ማረፊያ ቦታቸው ገነት መሆኑን ለማመልከት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ በነበረ ጊዜ ንስሐ ለገባው ወንበዴ፡ “በእውነት እልሃለው ዛሬውኑ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ” ብሎታል። ሉቃስ ፳፫፡ ፵፫። የኃጢአተኞች መቆያ ደግሞ ሲኦል መሆኑን ለማመልከት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሀብታሙ ሰውና በድኻው አልዓዛር ምሳሌ ትምህርቱ ሀብታሙ ሰው በሲኦል ውስጥ እንደነበረ ገልጿል። ሉቃስ ፲፮፡ ፳፫፡፡ በሙታን ትንሣኤ ጊዜ የምንነሳው በውርደት ወይም ክብር በሌለው ሁናቴ በመሬት ውስጥ እንደተቀበርነው ሳይሆን፣ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው በክብር፣ በኃይልና በመንፈሳዊነት ነው። ፩ኛ ቆሮንቶስ ፲፭፡ ፵፪-፵፬። ከዚያም በኋላ ወደ ክርስቶስ የፍርድ ፊት እንቀርባለን። ፪ኛ ቆሮንቶስ ፭፡ ፲፤ ራዕይ ፮፡ ፱-፲፩፡፡ ይቅርታ በዚሁ ዓለምና በሚመጣውም ዓለም መኖሩን ቅዱስ መጽሐፍ ያስረዳል። ማቴዎስ ፲፪፡ ፴፪፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቶ ለነበረው ለኦኔሲፎር “በመጨረሻው ቀን ምሕረትን ይስጠው” ብሎ ጸልዮለታል። ፪ኛ ጢሞቴዎስ ፩፡ ፲፰። ቤተ ክርስቲያንም ይህንኑ ጸሎት ለሞቱ ሁሉ ትጸልያለች። ለሞቱ ሰዎች መጸለይ ደግሞ በጥንት በዘመነ ብሉይም ነበረ። ጀግናው ይሁዳ መቃብዮስ በጦርነት ለሞቱ ወታደሮቹ የኃጢአት መሥዋዕት ይደረግላቸው ዘንድ ሁለት ሺህ የብር ድራህም አሰባስቦ ወደ ኢየሩሳሌም ልኳል። ፪ኛ መቃብያን ፲፪፡ ፵፫፤ ዕዝራ ሱቱኤል ፮: ፴፭። አይሁድ ለሙታን ሲጸልዩ ዳዊት ይደግማሉ። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች በተላከው የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ላይ ባደረገው ስብከቱ እንዲህ ብሏል “አንድ ሰው ኃጢአተኛ እንደሆነ ቢሞት የምንችለውን ያኽል ልንረዳው ይገባል። የምንረዳውም በለቅሶና በሐዘን ሳይሆን በጸሎት፣ በምጽዋትና በቁርባን ነው። የዓለምን ኃጢአት ወደ ተሸከመው የእግዚአብሔር በግ ስለ ሙታን የምንጸልየው እነርሱ መጽናናትንና እረፍትን እንዲያገኙ ብለን ነው እንጂ በከንቱ አይደለም። ጻድቁ ኢዮብ ስለልጆቹ ያቀርብ የነበረው ቁርባን ጠቀሜታ ከነበረው ስለ ሙታን የምናቀርበው ቁርባን ምንኛ የበለጠ ጠቀሜታ ይኖረው?

ከሞትም በኋላ ቢሆን በሰዎች መካከል የሚኖረው መንፈሳዊ ግኑኝነት በጸሎት አማካይነት ይቀጥላል። ሉቃ ፲፮፡ ፲፱-፴፩። በእምነት የሚደረግ ጸሎት ኃይል እንዳለው ተራራንም ለማንቀሳቀስ እንደሚያስችል በወንጌል ተገልጾልናል። መጽሐፍ ቅዱስም የአንዱ ሰው ጸሎት ሌላውን እንደሚራዳ ያስተምረናል። ዮሐ ፬፡ ፵፮-፶፫፤ ማቴ ፲፭፡ ፳፩-፵፰፤ ማር ፱፡ ፲፯-፳፯፤ ማር ፪፡ ፪-፲፪፤ ማቴ ፰፡ ፭-፲፫፤ ዮሐ ፲፩፡ ፩። ጌታችን ከላይ ከተጠቀሱት ተአምራት በርካታዎቹን በአካል በቦታው ተገኝቶ ሳይሆን ሳይገኝ በኃይሉ ፈጽሟል። ጸሎት እንደ ብርሃን ነጸብራቅ የሚጓዝና የሚያበራ የፍቅር ውጤት ነው። እግዚአብሔርን አምነው የሚጸልዩትን ከምድር ጫፍ እስከ ምድር ጫፍም ይሁን የእርሱ አገር እስከ ሆነውም አልፎ ያገናኛል። ጸሎት እኛ የምንኖርባትን ዓለም ከመላእክት፤ ከቅዱሳንና በሞት የተለዩን ወገኖቻችን ከሚገኙባት ዓለም ጋር ያገናኛል። ሞት በጌታችን ትንሳኤ የተነሳም የቀደመ ኃይሉን አጥቷል። ትንሳኤውም የአዲስ ሕይወት መጀመሪያ ሆኗል። ሮሜ ፰፡ ፴፰- ፴፱። በዚህም የተነሳ እግዚአብሔርን #ሁሉ ለእርሱ ሕያዋን ስለ ሆኑ፥ የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም; እያልን ሁሉ በሕይወት ይኖሩ ዘንድ እንጸልያለን። ሉቃስ ፳፡ ፴፰። በዚህ ዓለም የነበሩ ክርስቲያኖች በሕይወት በነበሩበት ዘመን ከቤተ ክርስቲያናቸው ጋር የነበረው ግኑንነት ከአረፉም በኋላ አይቋረጥም። በገነት ከሆኑ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት ስለ እኛ ሊጸልዩልን ነጻነት አላቸው። ወደ ሲኦል የወረዱም ከሆኑ በዚያ ሆነው የእኛን ጸሎት ይሻሉ። ቅዱስ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያንን መሠረቶቿ በምድር ሆነው ጫፎቿ ከሰማይ ጋር የተያያዙ አድርጎ መመሰሉም ይህንኑ ለማስረዳት ጭምር ነው። #ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፥ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላዕክት፥ በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፥ የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።; ዕብ ፲፪፡ ፳፪-፳፬። ይህም የሚያመለክተው በሰማይና በምድር ባሉት አብያተ ክርስቲያናት መካከል የማይጠፋ የጠበቀ ግኑኝነት ያለ መሆኑን ነው። በምንጸልየውም ጸሎት የዘመናት ገደብ ሳይኖርብን የሐዋርያት፤ የሰማእታትና የቅዱሳን ሁሉ ጸሎትም እንዲረዳን እንጸልያለን።

ጸሎተ ፍትሐት የሚደረገው ሳይታወቁ ለተፈጸሙ ኃጢአቶች፣ በድብቅ ለተፈጸሙ ኃጢአቶች፣ እንዲሁም ለተረሱ ኃጢአቶችና ኃጢአት ሰሪው ኃጢአት መስራቱ ሳይሰማው የሚሰራቸው ኃጢአቶች ናቸው። እንደነዚህ ያሉት ኃጢአቶች ከሰው ተፈጥሮ ደካማነት የተነሳ የሚፈጸሙ መሆናቸው ቢታመንበትም በእግዚአብሔር ፍትሕ በኩል ግን እንዲህ አይደለም። እግዚአብሔር ለሙሴ የነገረው “አንድ ሰው ባለማወቅ ከእግዚአብሔር ትእዛዝ አንዱን ቢተላለፍ በደለኛ ነው” ብሎ ነው፡፡ ዘሌዋ ፭፡ ፲፯። ሰው አፈር የሆነውን ሥጋ የለበሰ እንደመሆኑ መቼም ቢሆን ሙሉ ለሙሉ ከኃጢአት የነፃ ሊሆን አይችልም። “ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናታልላለን፣ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም” እንዲሉ። ፩ኛ ዮሐንስ ፩፡ ፰። እግዚአብሔር በንስሐ የሚመለሰውን ሰው በማንኛውም ጊዜ ቢሆን ይቀበለዋል።፡ ለምሳሌ በሞት አፋፍ ላይ የነበረውና ከጌታችን ጋር ተሰቅሎ የነበረው ወንበዴ ንስሐው ተቀባይነት ያገኘው በመጨረሻው ደቂቃ ነው። ስለዚህ ንስሐ የገባ ሰውና በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያገኘው ማን እንደሆነ ስለማናውቅ ለሁሉም እንጸልያለን። ለሙታን የሚደረግ ጸሎት ወይም ጸሎተ ፍትሐት ዘወትር ጠቃሚ ነው። ወደ ገነት ለመግባት ላልታደሉት ጸሎቱ ዕድላቸውን ከመቃብር በላይ ያደርግላቸዋል። #በሰማይ ስማ ሰምተህም ይቅር በል።; ፪ኛ ዜና ፮፡ ፳፩። በገነት ላሉትም እንደ ታላቅ ብርሃን እየፈነጠቀ ታላቅ ደስታን ይሰጣቸዋል። በዚህም መሠረት ቤተ ክርስቲያን በፍትሐት ጸሎት አምና ለልጆቿ ምህረትን ትለምናለች፣ ይህንኑም ታስተምራለች።
ከጎናችን ያለ ሰው ሲያዝን እኛስ ማዘናችን ይቀራል? ጌታችን ወዳጁ አልዓዛር ሲሞት አዝኖለት እንባውን አፍስሷል። ይሁን እንጂ በሞት የተነሳ የሚገጥመን ሐዘን ግን በእግዚአብሔር እስከ ማጉረምረም ሊያደርሰን አይገባውም። ሞት ለጊዜው የነፍስ ከሥጋ መለየት እንጂ የሰው ለዘላለም መጥፋት አይደለም። በመጽሐፍ ቅዱስም እንቅልፍ እየተባለ ተጠቅሷል። የሐ.

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እስቲ ስለ ሴት ልጅ አለባበስ ንገሩኝ በክርስትና ሀይማኖት ሴት ልጅ ፀጉር መግለጥ፣ሱሪ መልበስ፣አጫጭር ቀሚስ መልበስ ተፈቅዶላታል ወይስ አልተፈቀደላትም???

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አንድ ሰው ከክርስቲያም ቤተሰብ ተወልዶ ሳይጠመቅ ቢሞት ለምንድን ነው መቃብር ቤት ቤተክርስቲያን እማይቀበረው ?!

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጋብቻን በቤተክርሰቲያን ለመፈፀም ከሙሸሮቹ ወይም ከተጋቢዎቹ ምን ምን ያሰፈልጋ ወይም ይጠበቅባቸዋል

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ለንሰሀ ለመቅረብ  የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታወች ወይም ዝግጂቶች  ምን ምን ናቸው  ?

መልስ👇👇👇👇

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥያቄ
በክርስትና ህይወት ዉስጥ ከፍላጎት ባሻገር ለዉጥ ማምጣት አለመቻል ለምን ይሆን።

መልስ👇👇👇

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥያቄ
እግዚአብሔር ለጥያቄዬ መልስ መስጠቱን እንዴት እናውቃለን ? እና ለዛ ጥያቄ መልሡ ዝምታ ከሆነስ?



መልስ👇👇👇

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መንታ ወንድ እና ሴት ብወለዱ ክርስትና እንደት ነው ማስነሳት የምቻለው?????

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

begena siderder lamendenw ba gera eji yahonew gera eji yalelaw sew kale be kegu me metate yechelal way ??

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በሀሳብ ምንሰራውን ሀጥያት እንዴት ባለ ነው ሀትያቱ ሚሰረየቅ?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እግዚአብሔር ለጥያቄዬ መልስ መስጠቱን እንዴት እናውቃለን ? እና ለዛ ጥያቄ መልሡ ዝምታ ከሆነስ?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

#ሼር_እንድታደርጉ_በቤተክርስቲያን_ስም_እንጠይቃለን

❖ ታላቅ የንግሥ ጉዞ ወደ ተአምረኛው ስእለት ሰሚ

ደርሶ መልስ

ቁልቢ ቅዱስ/ገብርኤል ገዳም

ድሬዳዋ የሚገኙ ገዳማትና አድባራትን ጨምሮ

  → መነሻ ሐምሌ 16
  → መመለሻ ሐምሌ 20

  → የጉዞ ዋጋ፦ ትራንስፖርትን ማረፊያና ቤትን ጨምሮ 2500 ብር

ለበለጠ መረጃ☎️ +251986677077
                     ☎️ +251907748876
                     ☎️ +251941747170

ፈጥነው ትኬት ይቁረጡ ውስን ቦታዎች ብቻ ነው ያሉን

ለጉዞ መረጃ /channel/ENATEZ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

#ሼር_እንድታደርጉ_በቤተክርስቲያን_ስም_እንጠይቃለን

❖ ታላቅ የንግሥ ጉዞ ወደ ተአምረኛው ስእለት ሰሚ

ደርሶ መልስ

ቁልቢ ቅዱስ/ገብርኤል ገዳም

ድሬዳዋ የሚገኙ ገዳማትና አድባራትን ጨምሮ

  → መነሻ ሐምሌ 16
  → መመለሻ ሐምሌ 20

  → የጉዞ ዋጋ፦ ትራንስፖርትን ማረፊያና ቤትን ጨምሮ 2500 ብር

ለበለጠ መረጃ☎️ +251986677077
                     ☎️ +251907748876
                     ☎️ +251941747170

ፈጥነው ትኬት ይቁረጡ ውስን ቦታዎች ብቻ ነው ያሉን

ለጉዞ መረጃ /channel/ENATEZ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ለሥልጣነ ክህነቱ የማይገባ' ካህን ብትመለከት፥ [በደፈናው] ክህነትን አትንቀፍ፡፡ ደገኛ የኾነውን የክህነት ሥልጣን ይዞ ያልተገባ ሥራን ሲሠራ በማየቱ ምክንያት፥ ከዚህ ተነሥቶ ሥልጣነ ክህነትን የሚነቅፍ አንድ ሰውስ እንኳን አይኑር፡፡
የአስቆሮቱ ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ ይሁዳ እንዲህ በማድረጉ ግን ሐዋርያነት የሚነቀፍ ስለ ኾነ አይደለም፤ የይሁዳ የገዛ ነጻ ፈቃድ ችግር ነው እንጂ፡፡ የሚተቸውም ክህነቱ አይደለም፤ ጠማማው ነጻ ፈቃዱ ነው እንጂ፡፡
ስለዚህ አንተም ክህነትን አትንቀፍ፤ ክህነቱን ላልተገባ ሥራ የሚያውለውን ካህኑን እንጂ፡፡ ...

ሐኪም ሳይኾኑ ሐኪም ነን ያሉት ስንት ናቸው? በዚሁ ምክንያት በመድኃኒት ፈንታ መርዝ የሰጡትስ ስንት ናቸው? እየነቀፍኩ ያለሁት ሙያውን አይደለም፤ ሙያውን በአግባቡ የማይተገብሩትን ነው እንጂ፡፡

መርከቦች እንዲሰምጡ ያደረጉ መርከበኞችስ ስንት ናቸው? ነገር ግን ችግሩ የባሕር ላይ ጉዞ አይደለም፤ ሙያውን እንደሚገባ የማይተገብሩት ሰዎች ችግር ነው እንጂ፡፡
ስለዚህ አንተም አንድ ክፉ ክርስቲያን ብትመለከት በደፈናው የክርስትና ትምህርትን ወይም ሥልጣነ ክህነትን አትንቀፍ፤ ደገኛውን ሥልጣን ላልተገባ ሥራ የሚያውለውን ነው እንጂ፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፥ ትንቢተ ኢሳይያስን በተረጎመበት ፬ኛ ድርሳን ላይ ከተናገረው የተወሰደ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

#ሼር_እንድታደርጉ_በቤተክርስቲያን_ስም_እንጠይቃለን

❖ ታላቅ የንግሥ ጉዞ ወደ ተአምረኛው ስእለት ሰሚ

ደርሶ መልስ

ቁልቢ ቅዱስ/ገብርኤል ገዳም

ድሬዳዋ የሚገኙ ገዳማትና አድባራትን ጨምሮ

  → መነሻ ሐምሌ 16
  → መመለሻ ሐምሌ 20

  → የጉዞ ዋጋ፦ ትራንስፖርትን ማረፊያና ቤትን ጨምሮ 2300 ብር

ለበለጠ መረጃ☎️ +251986677077
                     ☎️ +251907748876
                     ☎️ +251941747170

ፈጥነው ትኬት ይቁረጡ ውስን ቦታዎች ብቻ ነው ያሉን

ለጉዞ መረጃ /channel/ENATEZ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጥያቄ

    እግዚአብሔርም የሰውን ልጅ በመፍጠሬ ተፀፀትኩ አለ ።
አንግዲ መፀፀት ማለት ባለፈው ነገር መቆጨት ነው
እግዚአብሔር ደግም ዛሬ ሚሆነውን ወደፊትም እሚሆነውን ያውቃል ታዲያ እኛ እንደምንበድለው እያወቀ
1 ለምን ፈጠረን
2  ለምን ተፀፀተ

ጋብቻን በቤተክርሰቲያን ለመፈፀም ከሙሸሮቹ ወይም ከተጋቢዎቹ ምን ምን ያሰፈልጋ ወይም ይጠበቅባቸዋል

መልስ👇👇👇

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

Setoch lmndnw be bethelem bekul malef mayechelut

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሰው ከሞተ ቡሀላ 40 80 ቁርባን እየተባለ ተደግሶ እሚበላው ለሞተው ሰው ነብስ ምንድነው ጥቅሙ ሌላው ሰው ከሞተ ነብስ ይማር ማለት ወይም ስለሱ ነብስ መፀለይ ከፍርድ ያድነዋል

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እግዚአብሔር ይስጥልኝ የኔ ጥያቄ
እግዚአብሔርም የሰውን ልጅ በመፍጠሬ ተፀፀትኩ አለ ።
አንግዲ መፀፀት ማለት ባለፈው ነገር መቆጨት ነው
እግዚአብሔር ደግም ዛሬ ሚሆነውን ወደፊትም እሚሆነውን ያውቃል ታዲያ እኛ እንደምንበድለው እያወቀ
1 ለምን ፈጠረን
2 ለምን ተፀፀተ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

begena siderder lamendenw ba gera eji yahonew gera eji yalelaw sew kale be kegu me metate yechelal way ??

መልስ👇👇👇

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሰላም የእግዚሃብሔር ቤተሰቦች የኔ ጥያቄ
1.በሌላ እምነት የነበረ ሰው የስላሴን ልጅነት ለማግኘት ምን ማድረግ ይገባዋል
2.አንድ ሴት የወር አበባ ላይ ሆና የቅዳሴ ፀበል መጠጣት ይቻላል ወይ


መልስ👇👇👇

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መልሶቹ እነሆ ያዳምጧቸው
👇👇👇👇👇👇

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ለንሰሀ ለመቅረብ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታወች ወይም ዝግጂቶች ምን ምን ናቸው ?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በክርስትና ህይወት ዉስጥ ከፍላጎት ባሻገር ለዉጥ ማምጣት አለመቻል ለምን ይሆን።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሰላም የእግዚሃብሔር ቤተሰቦች የኔ ጥያቄ
1.በሌላ እምነት የነበረ ሰው የስላሴን ልጅነት ለማግኘት ምን ማድረግ ይገባዋል
2.አንድ ሴት የወር አበባ ላይ ሆና የቅዳሴ ፀበል መጠጣት ይቻላል ወይ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ለእዛሬ ምሽት የሚመለሱ ጥያቄዎች እነሆ👇👇👇

ተከታተሉ መልሱን አሁን የምንልክ ይሆናል

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🎬 🛑 ትክክለኛው የቅዱስ ሚካኤል ስዕል የቱ ነው? ይህኛውስ ስህተቱ ምንድን ነው?
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ

⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/L4RFDc6-W5c
https://youtu.be/L4RFDc6-W5c

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​📯📯📯  ታላቅ የንግስ ጉዞ #ቁልቢ_ገብርኤል  📯📯📯

             #ቁልቢ_ገብርኤል_ገዳም
ቁልቢ ገብርኤል ከአዲስ አበባ በስተምሥራቅ 461
ኪ/ሜ. ርቀት ላይ በምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በጋራ
ሙለታ የሚገኝ ከተመሰረተ ጀምሮ ብዙዎቹን እንቆቅልሸ የፈታ ታላቅ ገዳም ነው።

   በዘጠነኛው መ/ክ/ዘ. ዮዲት ጉዲት ተነሥታ አብያተ
ክርስቲያናትን ስትመዘብር፣ ክርስቲያኖችን ስትገድልና
መጻሕፍትን ስትቆነጻጽል ንጉሥ አንበሣ ውድም በአክሱምና
በአከባቢዋ የነበሩ ታቦታትንና ንዋያተ ቅዱሳትን በመያዝ ወደ
ደቡብ ኢትዮጵያ ወደ ዝዋይ መጣ፡፡
ከ40 ዓመታት ስደት በኋላ አንበሣ ውድም ወደ አኵሱም ሲመለስና የንዋያተ ቅዱሳት ቆጠራ ሲደረግ ታቦተ
ቅዱስ ገብርኤል በዝዋይ መቅረቱ ታወቀ፡፡ ከኤርትራ ደብረ
ሲና ማርያም የመጡና አባ ሌዊ የተባሉ አባት ታቦቱን
ለማምጣት ከንጉሡ አስፈቅደው ወደ ዝዋይ መጡ፡፡
አባ ሌዊ ከሰባት ቀን ሱባኤ በኋላ ታቦተ ቅዱስ
ገብርኤልን ይዘው ወደ አኵሱም ሲጓዙ ቅዱስ ገብርኤል
ተገልጦ “#እኔ_ወደ_ማሳይህ_ቦታ_ታቦቱን_ይዘህ_ሂድ” አላቸው፡፡ታቦቱንም ይዘው ተከተሉት፡፡ በመጨረሻም #ቁልቢ
ደረሱ፡፡
ለአባ ሌዊም የተፈቀደላቸው ቦታ ይሄ መሆኑን
#ታቦቱም_በኋላ_ዘመን_ለሕዝቡ_ድንቅ_ሥራ_እንደሚሠራ ቅዱስ ገብርኤል ነግሯቸው ተሠወረ፡፡ አባ ሌዊ በቦታው ለ130
ዓመታት ያህል አገልግለው በንጉሥ ግርማ ሥዩም ዘመነ
መንግሥት ታኅሳስ 14 ቀን ዐርፈዋል፡፡

ግራኝ አሕመድ ኢትዮጵያን ሲወርር ብዙ ካህናት ከሰሜን ኢትዮጵያ ታቦታትንና ንዋያተ ቅዱሳትን ይዘው ሲጓዙ
ቁልቢ ደረሱ፡፡ 3 ካህናት ከተነጠፈ ድንጋይ ላይ
የተጻፈ ነገር ያገኛሉ፡፡ ጽሑፉም ታቦተ ቅዱስ ገብርኤል ሥዉር መቀመጡን፣ ልዩ ልዩ ተአምራት እንደሚሰራ፣ ወደ ፊትም ታላቅ መቅደስ እንደ ሚሠራበት፣ እንዴት አባ ሌዊ ታቦቱን ወደ ዚህ ቦታ እንዳመጡት የሚገልጽ ነበር፡፡ እነርሱም ይህን ታሪክ ይዘውት በነበረው መጽሐፈቀሌሜንጦስ ሕዳግ ላይ ጻፉት፡፡

  ወደ ዝዋይ ደሴት ሲደርሱም መጽሐፉን በዚያ አኖሩት፡፡
ልዑል ራስ መኰንን ከዝዋይ ደሴት መጽሐፈ
ቀሌሜንጦስን አስመጥተው ሲያነቡ
#የቁልቢ\ገብርኤልን ታሪክ በማግኘታቸው የቅዱስ ገብርኤልን ቤተ ክርስቲያን ለማነጽ ተነሡ፡፡
  ልዑል ራስ መኰንን በአከባቢው የአየር ንብረት ተማርከው በሥፍራው ቤት ሠርተው ነበር፡፡
ልዑል ራስ መኰንን የቁልቢ ገብርኤልን ታቦት በዚሁ ስፍራ አስተከሉ። የካቲት 21 ቀን 1884 ዓ.ም ታቦቱ
ቁልቢ ገባ፡፡

ቅዳሴ ቤቱ የተከበረው ሐምሌ 19 ቀን 1884 ዓ.ም ነው፡፡
በዚሁ ዕለት የዋናው ቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ሥራ የመሠረቱ
ድንጋይ ተጥሎ ታኅሳስ 19 ቀን 1888 ዓ.ም የቤተ ክርስቲያኑ ሥራ ተፈጸመ።
ያኔ ቦታው የተገዛው በአርባ የቁም ከብት ነበር፡፡

ወደዚሕ ታላቅ ገዳም ቅዳሴ ቤቱን እንዲሁም በዓለ ንግሱን ለማክበር ቤተ-ኤጲፋንዮስ ከ16-11-2015 እስከ 20-11-2015ዓ,ም ድረስ ጉዞ ያደርጋል።

    ከአዲስ አበባ 🙏 ፒያሳ ጊዮርጊስ
                           መነሻ ቦታዎቻችን ሲሆ

  #በ_+251986677077

   #በ_0907748876 ላይ በመደወል መመዝገብ የምትችሉ የጉዞውን ሁኔታ ማጣራት ቸምትችሉ ሲሆን።

ለጉዞ የተዘጋጃችሁ ህዝበ ክርስቲያን ግን ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ በባንክ አካውንት ገቢ በማድረግ እና ደረሰኙን እንደትኬት በመያዝ ቦታ ማስያዝ እንደምትችሉ እናሳውቃለን።

           
ትኬቱን መቁረጥ ትችላላችሁ።

   #የጉዞ_ዋጋ_2500ብር_ነው።

      ➛🏦 #በ1000529190167  #CBE_ባንክ ዳንኤል ተስፋ
         🤳  #በ +251986677077

           ገቢ አድርገው በቴሌግራም ቢልኩልን ዲጂታል ትኬት በእጅ ስልክዎ ከነወንበር ቁጥርዎ ይደርስዎታል።

#በጉዞአችን_ድሬዳዋ የምንገባ ሲሆን እና የጉዞው ዋጋ የአንድ ቀን ትራንስፖርትን እና #ማደሪያ_ቦታን እንደሚያጠቃልል ለመግለጽ እንወዳለን።

አድራሻችን:➛ፓያሣ ጊዮርጊስ ሕንፃ ማዕዶት ህትመት ቤት እና ዮቶር ህትመት ቤት

      አዘጋጅ :-#ማዕዶት መንፈሳዊ ጉዞ ማኅበር

የቴሌግራም ቻናላችን :➛
                                   /channel/ENATEZ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🎬 ፀበል ስንጠመቅ እርቃናችንን መሆን አለብን ወይስ በልብስ? ፈጣሪ ምን ሰራህ እንጂ ምን በላህ አይልም ይላሉ?
👤 ዝማሬ ዳዊት ቲዩብ

⚠️ ትምህርቱን ከስር ባስቀመጥነው LINK ያገኙታል!
https://youtu.be/vpcA0p5ScOM
https://youtu.be/vpcA0p5ScOM

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

፮- ቆሞስ አባ ጥላሁን ወርቁ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ተብለው ተሠይመው በቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት

፯-  ቆሞስ አባ ዘተክለሃይማኖት ገብሬ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ተብለው ተሠይመው በሆሮ ጉድሩ ሀገረ ስብከት

፰-  ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ ገብሬ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ተብለው ተሠይመው በምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት

፱-  ቆሞስ አባ ወልደገብርኤል አበበ ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ ተብለው ተሠይመው በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ተመድበዋል።

ምንጭ: ሕዝብ ግንኘነት መምሪያ

Читать полностью…
Подписаться на канал