ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ጌታ ሆይ

ጌታ ሆይ አይሁድ አማጽያን
ሰቀሉህ ወይ 
የዓለም መድኃኒት የዓለም ሲሳይ
ሰቀሉህ ወይ /2/ 

የአዳም በደል አደረሰህ
አንተን ለመሰቀል 
የሔዋን ስህተት አበቃህ ለሞት
ቸሩ አባት/2/
አዝ
ንጹሕ ክርስቶስ ሆንክ ወንጀለኛ
ብለህ ስለእኛ 
መሰቀል አሸክመው
አስረው ገፈፉህ እያዳፉህ/2/ 
አዝ
እጅና እግርህን በብረት ተመታ
የዓለም ጌታ 
የሾህ አክሊል ደፍተህ
ጎንህን ተወጋህ አልፋ ኦሜጋ/2/
አዝ
ግብዞች እንደራሳቸው መስሏቸው 
ምራቅ እየተፉ በፊትህ ቀለዱ
አንተን ሊጎዱ/2/
አዝ 
በመሰቀል ላይ ተጠማሁ ስትል
ታላቅ በደል 
ሀሞትና ከርቤ ሰጡህ ቀላቅለው
ጠጣ ብለው/2/
አዝ
ይቅር ባይ ግልጽ በደላችንን ሁሉ ሳታይ 
አንተ ይቅር በለን
በእኛ ሳትከፋ እንዳንጠፋ /2/ 

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ንሴብሖ

ንሴብሖ /2/ ለእግዚአብሔር /2/ 
ስቡሐ ዘተሰብሐ /4 
እናመስግነው /2/ እግዚአብሔርን /2/ 
ምስጉን ነው የተመሰገነ /4/ 

ባህሩን ተሻግረን ወንዙ ደረቅ ሆነ
በጠላታችን ላይ ድሉ የኛ ሆነ
ከባርነት ቀንበር ፍፁም ነፃ ወጣን
ህይወት የሚሰጠን መና ነው ምግባችን

አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል መከራም ቢበዛ
ሃይላችን ጌታ ነው የዓለም ቤዛ

ከአለት ላይ ውሃ ፈልቆ እንደጠጣነው
ይህን ታላቅ አምላክ ኑ እናመስግነው
ሰዎች ደስ ይበለን ሕይወታችን ድኗል
ሰይጣን ጠላታችን አፍሮ ተመልሷል

አስፈሪ ነው ያልነው ብዙ ነገር ነበር
ሁሉንም አለፍነው አምላካችን ይክበር
ጉልበታችን ቢዝል ፈተናው ቢበዛ
ሃይላችን ጌታ ነው የዓለሙ ቤዛ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ክርስቲያኖች ሁላችሁ ኑ እናፅናናት

"ክርስቲያን ሁላችሁ ኑ ድንግል ማርያምን እናፅናናት፤ በልጇ ስቃይ ሆድ ብሷታልና፥ እንባን ከመጠጧ ጋር አመድንም ከምግቧ ጋር ቀላቅላለችና። የተወደደ ልጇ በመስቀል ተሰቅሎ ስታየው አንድ ጊዜ ከእሾህ አንድ ጊዜ ከድንጋይ ላይ እየወደቀች አለቀሰች። ወንድም የሌለው አንድ ልጇ እንዲህ ሲሰቃይ የወለደ አንጀቷ እንደምን ይቻል? ምንስ ብላ ትፅናና? ያፅናኗት ዘንድ ሊቃነ መልአክት በዙሪያዋ መጡ ግን አልተፅናናችም፤ ልጄ እያለ የሚጠራት አባቷ ዳዊትም መጣ ድንግል ግን እርቃኑን የተሰቀለው ልጇን እያየች መሪር እንባን አፈሰሰች። ስለ ልጇ ብዙ መከራ አሳልፋለች፥ ያሁኑ የልጇ መከራ ግን ከሀዘኖች ሁሉ የከፋ ሆነባት። አንድ ልጇ እየሞተ ምን ብላ ትፅናና ? የእናቱን አለመፅናናት ያየ ጌታ ኢየሱስ ከሃዘን ብዛት እንዳትሞት ያፅናናት ዘንድ ቁጽረ ገፅ ለተባለው ለዮሐንስ እነኋት እናትህ አለው። በእውነት እነኋት እናታችን በልጇ ስቃይ ሆድ ብሷታልና ክርስቲያን ሁላችሁ ኑ እናፅናናት።"

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

"ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ። አባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ አለ። ይህንም ብሎ ነፍሱን ሰጠ።"
(የሉቃስ ወንጌል 23:46)

"ኢየሱስም ሁለተኛ በታላቅ ድምፅ ጮኾ ነፍሱን ተወ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 27:50)

"ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኸ ነፍሱንም ሰጠ።"
(የማርቆስ ወንጌል 15:37)

"ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ። ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።"
(የዮሐንስ ወንጌል 19:30)

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዓርብ ዘጠኝ ሰዓት

በዚህች ዕለት በዚህች ሰዓት የዓለም መድኃኒት ጌታችን ኢየሱስ ለአዳም ልጆች ድኅነት በመስቀል ላይ ሆኖ በታላቅ ድምፅ ጮሆ “ኤሎሄ ኤሎሄ” ብሎ “ሁሉ ተፈጸመ” በማለት በባሕርይው ሞት የሌለበት አምላክ ነፍሱን በፈቃዱ ለሞት አሳልፎ ሰጠ።

“ቀትር በሆነ ጊዜም በስድስት ሰዓት ፀሐይ ጨለመ፤ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስም ዓለም ሁሉ ጨለማ ሆነ። ፀሐዩም በጨለመ ጊዜ የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከመካከሉ ተቀደደ። ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ድምፁን ከፍ አድርጎ፥ “አባት ሆይ፥ ነፍሴን በአንተ እጅ አደራ እሰጣለሁ”’ ብሎ ጮኸ፤ ይህንም ብሎ ነፍሱን ሰጠ።” (ሉቃ.፳፫÷፵፬-፵፮)

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

•✞ #አልፋና_ኦሜጋ ✞•

አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ (2)
በከሃዲዎች እጅ ተይዘክ ቀረብክ (2)

ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ
እየደበደቡ ክርስቶስ ሆይ አሉህ
ጽድቅን ስለሰራህ በወንጀል ከሰሱህ
ለአዳም ቤዛ ብለህ ብዙ ተንገላታህ
#አዝ•••
ቅዱሳን እጆችህ የፍጥኝ ታስርው
እንደ በግ ተጎትተህ ልትመራቸው
የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ
ፊትህን ሸፈኑት ለመመጻደቅ
#አዝ•••
በአውደ ምኩና ከጲላጦስ ዘንድ
አሳልፈው ሰጡ አጋልጠው ለፍርድ
ከሃና ቀያፋ ከመሳፍንቱ ደጅ
ከነሄሮድስ ዘንድ አቀረቡ በአዋጅ
#አዝ•••
ግርፋት ሕማሙ አልበቃ ብሎህ
በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ
ሳዶርና አላዶር ዳናትና አዴራ
ተፈልገው መጡ ለችንካር በተራ
#አዝ•••
የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ
ሊያያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ
ግፈኞች አይሁዶች ባንተ ላይ ቀለዱ
ምራቅን ተፉብህ እራስህን ሊጎዱ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዓርብ ስድስት ሰዓት

በዚህች ዕለት በዚህች ሰዓት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አይሁድ መስቀል አሸክመው፣ ከለሜዳ አልብሰው፣ ምራቅ እየተፉ ከተዘባበቱበት በኋላ ከለሜዳውን ገፍፈው፣ ልብሱን አልብሰው፣ እየገፉ፣ እያዳፉ ቀራንዮ አደባባይ አደረሱት፤ ልብሱንም ገፍፈው ራቁቱን በሁለት ወንበዴዎች መካከል በመስቀል ላይ ሰቀሉት።

“ከዚህም በኋላ የመስፍኑ ጭፍሮች ጌታችን ኢየሱስን ተቀብለው ወደ ፍርድ ሸንጎ ወሰዱት፤ ጭፍራውንም ሁሉ ወደ እርሱ ሰበሰቡ። ልብሱንም ገፈው ቀይ ልብስ አለበሱት። የእሾህም አክሊል ጎንጉነው በራሱ ላይ አቀዳጁት፤ በቀኝ እጁም ዘንግ አሲያዙት፤ በፊቱም ተንበርክከው፥ “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን” እያሉ ተዘባበቱበት፤ በላዩም ተፉበት፤  ዘንጉንም ነጥቀው ራሱን መቱት። ከተዘባበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፍፈው ልብሱንም አለበሱት፤ ሊሰቅሉትም ወሰዱት።” (ማቴ ፳፯÷፳፯-፴)
“በወሰዱትም ጊዜ የቀሬና ሰው ስምዖንን ከዱር ሲመለስ ያዙት ከጌታችን ከኢየሱስ በስተኋላ መስቀሉን አሸከሙት።” (ሉቃ.፳፫÷፳፮)

“ከዚህ በኋላ ሊሰቅሉት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ጌታችን ኢየሱስንም ተቀብለው ወሰዱት። መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው ቀራንዮ ወደሚባል ቦታ ወጣ። በዚያም ሰቀሉት፥ ከእርሱም ጋር አንዱን በቀኝ፥ አንዱንም በግራ አድርገው ሌሎች ሁለት ወንበዴዎችን ሰቀሉ፤ ኢየሱስንም በመካከላቸው ሰቀሉ። ጲላጦስም ጽሕፈት ጽፎ በመስቀሉ ላይ አኖረ፤ ጽሕፈቱም። ‘የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ’ የሚል ነበር።” (ዮሐ.፲፱÷፲፮-፲፱)

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

(የሉቃስ ወንጌል ምዕ. 23)

24፤ ጲላጦስም ልመናቸው እንዲሆንላቸው ፈረደበት።
25፤ ያንን የለመኑትንም፥ ስለ ሁከት ሰውንም ስለ መግደል በወኅኒ ታስሮ የነበረውን አስፈታላቸው፥ ኢየሱስን ግን ለፈቃዳቸው አሳልፎ ሰጠው።
26፤ በወሰዱትም ጊዜ ስምዖን የተባለ የቀሬናን ሰው ከገጠር ሲመጣ ይዘው ከኢየሱስ በኋላ መስቀሉን እንዲሸከም ጫኑበት።
27፤ ዋይ ዋይ ከሚሉና ሙሾ ከሚያወጡ ሴቶችና ከሕዝቡ እጅግ ብዙዎች ተከተሉት።
28-29፤ ኢየሱስ ግን ወደ እነርሱ ዘወር ብሎ እንዲህ አለ። እናንተ የኢየሩሳሌም ልጆች፥ ለእኔስ አታልቅሱልኝ፤ ዳሩ ግን። መካኖችና ያልወለዱ ማኅፀኖች ያላጠቡ ጡቶችም ብፁዓን ናቸው የሚሉበት ጊዜ እነሆ ይመጣልና ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ።
30፤ በዚያን ጊዜ ተራራዎችን። በላያችን ውደቁ፥ ኮረብቶችንም። ሰውሩን ይሉ ዘንድ ይጀምራሉ፤
31፤ በእርጥብ እንጨት እንዲህ የሚያደርጉ ከሆኑ፥ በደረቀውስ እንዴት ይሆን?
32፤ ሌሎችንም ሁለት ክፉ አድራጊዎች ደግሞ ከእርሱ ጋር ይገድሉ ዘንድ ወሰዱ።
33፤ ቀራንዮም ወደሚባል ስፍራ በደረሱ ጊዜ፥ በዚያ እርሱን ክፉ አድራጊዎቹንም አንዱን በቀኝ ሁለተኛውንም በግራ ሰቀሉ።

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

(የማርቆስ ወንጌል ምዕ. 15)

17፤ ቀይ ልብስም አለበሱት፥ የእሾህ አክሊልም ጎንጉነው ደፉበት፤
18፤ የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን እያሉ እጅ ይነሱት ጀመር፤
19፤ ራሱንም በመቃ መቱት ተፉበትም፥ ተንበርክከውም ሰገዱለት።
20፤ ከተዘባበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፥ ልብሱንም አለበሱት፥ ሊሰቅሉትም ወሰዱት።
21፤ አንድ መንገድ አላፊም የአሌክስንድሮስና የሩፎስ አባት ስምዖን የተባለ የቀሬና ሰው ከገጠር ሲመጣ መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት።
22፤ ትርጓሜውም የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሆን ጎልጎታ ወደተባለ ስፍራ ወሰዱት።
23፤ ከርቤም የተቀላቀለበትን የወይን ጠጅ እንዲጠጣ ሰጡት፤ እርሱ ግን አልተቀበለም።
24፤ ሰቀሉትም፥ ልብሱንም ማን ማን እንዲወስድ ዕጣ ተጣጥለው ተካፈሉ።
25፤ በሰቀሉትም ጊዜ ሦስት ሰዓት ነበረ።

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በወይራ ዝንጣፊ መጠብጠብ

በሰሙነ ሕማማት ዕለተ ዓርብ የስቅለቱ መታሰቢያ ነው፡፡ ምእመናን በሰሙነ ሕማማት የሠሩትን ኃጢአት ይናዘዛሉ፡፡ ካህናቱም በወይራ ቅጠል ትከሻቸወን እየጠበጠቡ ቀን ከሰገዱት በተጨማሪ ሌላ ስግደት ያዟቸዋል፡፡ ጥብጠባው የተግሣጽ ምሳሌ ነው፡፡
••
ጥብጣብ የሚደረግለት ሰው በሕማማቱ ወቅት የፈጸመው በደል ወይንም ኃጢአት ካለ ይህንኑ በመናገር የስግደቱ ቍጥር ከፍ እንዲል ይደረጋል፡፡ ይህ በስቅለት ቀን የሚፈጸም ሥርዓት ሲሆን፣ ጠብጣቤ ማለት ቸብ ቸብ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ሕዝበ ክርስቲያኑ በዕለተ ስቅለት ሲሰግድ ፣ ሲጸልይ ፣ መጻሕፍትን ሲያነብ ከዋለ በኋላ ሰርሆተ ሕዝብ / የሕዝብ መሰነባበቻ / ከመሆኑ በፊት በወይራ ቅጠል የእያንዳንዱ ምእመን ጀርባ ቸብ ቸብ መደረጉ ፣ የጌታን ግርፋት ያስታውሳል፡፡


💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዮሐንስን ይዛ ወደ ቀራንዮ

ዮሐንስን ይዛ ወደ ቀራንዮ
ድንግል ማርያም ሄደች እያለች ወዮ
ሥለ ልጇ ሐዘን ሥለ መከራዋ
ያስገርም ነበረ የፈሰሰው ዕንባዋ /፪/

ዮሐንስ ቢደንቀው የሐዘኗ ጽናት
አነሳት ደግፎ በብርቱ ሊያጽናናት
ድንግልም አለችው ልጄ አሳዘነኝ
እሕት ወንድም የለው ላልቅስለት ተወኝ

ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን

መቅደላዊት ማርያም ሶሎሜ ዮሐና
ማርያምን አይዋት ጸንቶባት ሐዘኗ
በልቅሶዋ ጣዕም ተነክቶ ልባቸው
ዕንባን አፈሰሱ ውለታው ገብቷቸው

ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን

ራሔል አልቅሳለች ላላቀፈቻቸው
ድንግል ግን ብታለቅስ አዝላው ተሰዳ ነው
ያዕቆብም አልቅሷል በሌላ የሠው ደም
ማርያም ግን ብታለቅስ ፈሷል የልጇ ደም

ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን

ጠብቶ ስለአደገ የድንግልና ጡቷን
መቆም አልቻለችም ስታይ መጠማቱን
በደም ተሸፍኖ ብታየው ውበቱን
ለይልኝ አለችው ከሥጋዋ ነፍሷን

ከሁሉም ይበልጣል ያስደፋል አንገትን የማርያም ሐዘን

ዮሐንስን ይዛ ወደ ቀራንዮ
ድንግል ማርያም ሔደች እያለች ወዮ
ሥለ ልጇ ሐዘን ሥለ መከራዋ
ያስገርም ነበረ የፈሰሰው ዕንባዋ

በእንተ ማርያም መሐርነ ክርስቶስ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዓርብ ሦስት ሰዓት

በዚህች ሰዓት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ጲላጦስ ፍርድ ወስደው አቁመውታል፤ ጲላጦስም በርባንን ፈትቶ ጌታችንን ገርፎት እንዲሰቅሉት አሳልፎ ሰጥቷቸዋል፣ ጌታችንንም ይዘውት ሊሰቅሉት ወስደውታል። “በየበዓሉም ከእስረኞች የመረጡትን አንዱን ይፈታላቸው ነበር። ከክፉ አድራጊዎችና ከነፍሰ ገዳዮች ጋር የታሰረ በርባን የሚባል አንድ ሰው ነበረ። ሕዝቡም ወጥተው እንደ አስለመደ ያደርግላቸው ዘንድ እየጮኹ ለመኑ። ጲላጦስም መልሶ፥ “የአይሁድን ንጉሥ እፈታላችሁ ዘንድ ትወዳላችሁን?” አላቸው። የካህናት አለቆች በቅንዓት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና። የካህናት አለቆች ግን በርባንን እንዲፈታላቸው ይለምኑት ዘንድ ሕዝቡን አነሣሡአቸው። ጲላጦስም መልሶ፥ “እንግዲህ የአይሁድ ንጉሥ የተባለውን ምን ላደርገው ትወዳላችሁ?” አላቸው። እነርሱም እንደገና ‘ስቀለው’ እያሉ ጮኹ።” (ማር.፲፭÷፮-፲፫)

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

📺 የስቅለት ሙሉ ፊልም

💰package ከገዙ ወደ 48.61 ብር
💵 package ከሌለዎት ወደ 81 ብር ይፈጃል
📍WiFi ብትጠቀሙ ይመረጣል

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ስቅለት
ለእናንተ Profile ካዘጋጀናቸው ፎቶዎች
ሼር
👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ስቅለት
ለእናንተ Profile ካዘጋጀናቸው ፎቶዎች
ሼር
👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#በዕጸ_መስቀል_ላይ

በዕጸ መስቀል ላይ በዚያ አደባባይ 
አምላክ ሆይ ጌታ ሆይ ተንገላታህ ወይ 
አምላክ ሆይ ጌታ ሆይ መከራ አየህ ወይ 
#አዝ
መስቀል አስይዘው ኪራያላይሶን 
ወደ ጎልጎታ   " "
ሲገራፉ ሲዳፉ  " "
ስትንገላታ  " "
#አዝ
ያንን አቀበት ኪርያላይሶን 
ያንን ዳገት  " "
ጀርባህ ተገርፎ  " "
ስትቃትት  " "
#አዝ
አንተን እያዩ ኪርያላይሶን 
ሴቶች ሲያለቅሱ  " "
እናቶች ቀርበው  " "
ላብህን ዳበሱ  " "
#አዝ
መስቀል አስይዘው ኪያላይሶን 
እንዲያ ሲያዳፉህ  " "
የቀሬናው ሰው  " "
ስምኦን አገዘው  " "

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም እና የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ መ/ር ዋሲሁን በላይ በትናንትናው ዕለት ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም በመንግሥት የጸጥታ አካላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደሚገኙ አሳውቀን ነበር።

በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን እየገለጽን፣ በሂደቱ ጉዳዩን በመረዳት አፋጣኝ ምላሽ የሰጡንን የመንግሥት የጸጥታ አካላት እናመሰግናለን።

በተጨማሪም በትዕግሥት ስትከታተሉና በጸሎት ስታስቡ ለነበራችሁ አባቶች፣ ምእመናን እና የማኅበረ ቅዱሳን አባላት እያመሰገንን፣ በዓሉ የሰላምና የበረከት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

ማኅበረ ቅዱሳን!

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​#አዘነች_ድንግል_አለቀሰች

አዘነች ድንግል አለቀሰች ፍጹም አምርራ
በአንድ ልጇ ምክንያት ደርሶባት መከራ
በአንድ ልጇ ምክንያት ደርሶባት መከራ/፪/
#አዝ
በመንጻቱ ወር በዓርባኛው ቀን
ሥምዖን አረጋዊ ታቀፈ እና ጌታን
ትንቢት ተናገረ ተገልጾለት ሞቱ
በነፍስሽ ሠይፍ ያልፋል አንቺም እናቲቱ
ይኽንን መከራ ሲሠማ ጆሮዋ
አምርራ አለቀሰች አልቆም አለ ዕንባዋ
#አዝ
በአሥራ ሁለት ዓመቱ ለማክበር በዓል
በኢየሩሳሌም ቢገኝ አማኑኤል
ሲጠይቅ ሲሠማ በቤተ መቅደሱ
የኦሪት ካኅናት ሲደነቁ በእርሱ
እስከ ሦስት ቀን ድረስ ብትልጣው ፈልጋ
ልቧ ተሠበረ በሐዘን አለንጋ
#አዝ
ጠዋት በማለዳ በጲላጦስ ደጅ
ሲጸናበት አይታ የጨካኞች እጅ
ርቃኑን አድርገው ያለ አንዳች ጥፋት
ከግንድ ጋር አስረው ጀርባውን ሲገርፉት
እንዴትስ አታለቅስ እንዴት አታነባ
ሲገርፉት ሲያዳፉት ልጇን እንደ ሌባ
#አዝ
የዓለሙን ፈጣሪ የዓለሙን ዳኛ
ንጹሑን ጌታ መሥሏቸው ቀማኛ
እጁን እና እግሮቹን በችንካር ወጥረው
በወንበዴ መሐል ሠቅለውን ብታየው
ድንግል አለቀሰች አልቻለች መጽናናት
ዕንባዋ ወረደ እንደ ክረምት ጅረት
#አዝ
ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በአንድ ሲማከሩ
ቅዱሥ ሐያል ብለድ ገንዘው ሊቀብሩ
በአዲስ መቃብር በአሥራ አንደኛው ሠዓት
ሥጋውን አኑረው በድንጋይ ቢዘጉት
እያለች ዐነባች አንድ ልጄ እኮ ነው
ከእርሱ የሚቀድም ተከታይ የሌለው።

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን

ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን አባት ሆይ
በመስቀል ሆነህ አባት ሆይ
ድምጽህን በማሰማት አባት ሆይ
ነፍስህን ሰጠህ አባት ሆይ

ከዋክብተ ሰማይ በሙሉ ረገፉ
ጨረቃና ፀሐይ ደምን አጎረፉ
ብርሃናት ጨለሙ ጠፍተው ተለያዩ
ሥጋህን በመስቀል ተገልጦ ስላዩ
#አዝ
ጌታችን ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ
አሰምቶ ጮኸ ተጠማሁ እያለ
ማርና ወተትን ለሚመግበው
ሐሞት አመጡለት ይቅመሰው ብለው
#አዝ
አካሉ ሲወጋ ውኃ ደም ፈሰሰ
በምድር ተረጭቶ ዓለምን ቀደሰ
የእሥራኤል ሴቶች ዋይ ዋይ ሲሉልህ
ለእነርሱ አዘንክ እንጂ ለአንተስ አላሰብክም
#አዝ
እናትህ ስታለቅስ በመስቃል ሥር ሆና
ዮሐንስን ሰጠህ ጠብቆ እንዲያፅናና
መላእክትም ታዩ አጋንንትም ሸሹ
የአይሁድ ሠራዊት ፈርተው ተረበሹ

ሊቀ-መዘምራን
ኪነ-ጥበብ ወልደ-ቂርቆስ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር

መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር (2)
ይቀሰቅሰኛል ለስሙ እንድዘምር (2)

ፊቱን እየፀፉት/ እየተንገላታ (2)
በጦር እየወጉት /ይሰጣል ይቅርታ (2)
እነርሱ እየጠሉት/ እርሱ ይወዳቸዋል (2)
አስረው ሲጎትቱት/ ይከተላቸዋል (2)
#አዝ
ፃድቁን ሃጥእ ነው/ እውነትን ሃሰት (2)
እያሉ ሲጮሁ /ይሰቀል ይሙት (2)
እየመረመረው/ ፍጡር ፈጣሪን (2)
ክርስቶስን አስሮ/ ፈታው በርባንን (2)
#አዝ
ጀርባውን ሲገርፉት በሚያቃጥል ጅራፍ
በምህረት ያዛቸው በይቅርታው እቅፍ (2)
ጨክነው ሲያጠጡት መራራ ሃሞት (2)
ደሙን አፈሰሰ ጎኑን ሲወጉት (2)
#አዝ
ግምጃን አለበሱት/ ቀሚሱን ገፈው (2)
በራሱም አኖሩ/ እሾህ ጎንጉነው (2)
የአይሁድ ንጉስ ሆይ/ እያሉ ዘበቱ (2)
ለህይወት ሆናቸው/ የክርስቶስ ሞቱ (2)

ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​​​👉 ሰባቱ የመስቀሉ ቃላት

1. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ (ማቴ 27፡46)
2. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው (ሉቃ 23፡34)
3. ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር እንድትኖር በእውነት እነግርሃለሁ (ሉቃ 23፡43)
4. እነሆ ልጅሽ አነኋት እናትህ (ዮሐ 19፡26-27)
5. ተጠማሁ (ዮሐ 19፡28)
6. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ (ሉቃ 23፡46)
7. የተጻፈው ሁሉ ደረሰ ተፈጸመ አለ (ዮሐ 19፡30)

👉 ሰባቱ ተዐምራት

ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈጸሙ ተዐምራት

1. ፀሐይ ጨልሟል
2. ጨረቃ ደም ሆነ
3. ከዋክብት ረገፉ
4. ዐለቶች ተሠነጠቁ
5. መቃብራት ተከፈቱ
6. ሙታን ተነሡ
7. የቤተ መቅደስም መጋረጃ ለሁለት ተቀደደ

👉 አምስቱ ችንካሮች

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸው አምስቱ ችንካሮች

1. ሳዶር ፦ በሚባል ችንካር ቀኝ እጁን ቸነከሩት
2. አላዶር ፦ በሚባል ችንካር ግራ እጁን ቸነከሩት
3. ዳናት ፦ በሚባል ችንካር ሁለት እግሩን ቸነከሩት
4. አዴራ ፦ በሚባል ችንካር ማሀል ልቡን ቸነከሩት
5. ሮዳስ ፦ በሚባል ችንካር ደረቱን ቸነከሩት

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

(የሉቃስ ወንጌል ምዕ. 23)

25፤ ያንን የለመኑትንም፥ ስለ ሁከት ሰውንም ስለ መግደል በወኅኒ ታስሮ የነበረውን አስፈታላቸው፥ ኢየሱስን ግን ለፈቃዳቸው አሳልፎ ሰጠው።
26፤ በወሰዱትም ጊዜ ስምዖን የተባለ የቀሬናን ሰው ከገጠር ሲመጣ ይዘው ከኢየሱስ በኋላ መስቀሉን እንዲሸከም ጫኑበት።
27፤ ዋይ ዋይ ከሚሉና ሙሾ ከሚያወጡ ሴቶችና ከሕዝቡ እጅግ ብዙዎች ተከተሉት።
28-29፤ ኢየሱስ ግን ወደ እነርሱ ዘወር ብሎ እንዲህ አለ። እናንተ የኢየሩሳሌም ልጆች፥ ለእኔስ አታልቅሱልኝ፤ ዳሩ ግን። መካኖችና ያልወለዱ ማኅፀኖች ያላጠቡ ጡቶችም ብፁዓን ናቸው የሚሉበት ጊዜ እነሆ ይመጣልና ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ።
30፤ በዚያን ጊዜ ተራራዎችን። በላያችን ውደቁ፥ ኮረብቶችንም። ሰውሩን ይሉ ዘንድ ይጀምራሉ፤
31፤ በእርጥብ እንጨት እንዲህ የሚያደርጉ ከሆኑ፥ በደረቀውስ እንዴት ይሆን?
32፤ ሌሎችንም ሁለት ክፉ አድራጊዎች ደግሞ ከእርሱ ጋር ይገድሉ ዘንድ ወሰዱ።
33፤ ቀራንዮም ወደሚባል ስፍራ በደረሱ ጊዜ፥ በዚያ እርሱን ክፉ አድራጊዎቹንም አንዱን በቀኝ ሁለተኛውንም በግራ ሰቀሉ።

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 27)

28፤ ልብሱንም ገፈው ቀይ ልብስ አለበሱት፥
29፤ ከእሾህም አክሊል ጎንጉነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፥ በፊቱም ተንበርክከው። የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን እያሉ ዘበቱበት፤
30፤ ተፉበትም መቃውንም ይዘው ራሱን መቱት።
31፤ ከዘበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፥ ልብሱንም አለበሱት ሊሰቅሉትም ወሰዱት።
32፤ ሲወጡም ስምዖን የተባለው የቀሬናን ሰው አገኙ፤ እርሱንም መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት።
33፤ ትርጓሜው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሆን ጎልጎታ ወደሚባለው ስፍራ በደረሱ ጊዜም፥
34፤ በሐሞት የተደባለቀ የወይን ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት፤ ቀምሶም ሊጠጣው አልወደደም።
35፤ ከሰቀሉትም በኋላ ልብሱን ዕጣ ጥለው ተካፈሉ፥
36፤ በዚያም ተቀምጠው ይጠብቁት ነበር።
37፤ ይህ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ ነው የሚል የክሱን ጽሕፈት ከራሱ በላይ አኖሩ።
38፤ በዚያን ጊዜ ሁለት ወንበዶች አንዱ በቀኝ አንዱም በግራ ከእርሱ ጋር ተሰቀሉ።

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

"ጊዜ ስድስቱ ሰዓት ሰቀልዎ ለኢየሱስ ማዕከለ ክልኤ ፈያት።"
ዮሐ ፲፱፥፲፫-፳፯
@ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የምትወዱት ሰዎች አልቅሱለት

ብክይዎ ወላሕውዎ
እለ ታፈቅርዎ
ወይቤ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ ኤልማስ
ዘበ እደ አይሁድ ተአስረ
አመ ጸምአ ማይ ይሰቲ
ሀሞተ ወከርቤ መሪረ
ወይቤ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ

ጌታዬ አምላኬ በደል ሳይኖርበት ተገፋ
የአዳምን መርገም ሊያጠፋ
በአይሁድ እጅ ታሰረ
እንደ ወንጀለኛ ተቆጠረ
ጌታዬ አምላኬ ሞተልኝ ስለኔ
አልቅሱለት ስለ መከራው የምትወዱት

አዕንቃዕደ ወሰማየ
ኀበ አቡሁ ነጸረ
ሶበመንፈሱ ትወጽዕ
በላዕለ መስቀሉ ገአረ
ወይቤ ወይቤ ተፈጸመ ኲሉ

ውሃን የፈጠረ ተጠማ
ሀሞትን አጠጡት እየደማ
የሾህ አክሊል ደፍቶ ቀና አለ
መራራውን ጽዋ ተቀበለ
ጌታዬ አምላኬ ሞተልኝ ስለኔ
አልቅሱለት ስለ መከራው የምትወዱት

በእናቱ ፊት ሰቀሉት
በጥፊ እየመቱ ዘበቱበት
ሐዘኑንስ እንዴት ትቻለው
መተኪያ የሌለው ልጇ እኮ ነው

እውነት ወደ ምድር ቢመጣ
በሀሰት ዳኝነት ተመታ
በጀርባው ላይ ጅራፍ አረፈ
ደሙ እንደ ውሃ ጎረፈ
ጌታዬ አምላኬ ሞተልኝ ሰለኔ
ወይቤ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ
ወይቤ ኤሎሄ ተፈጸመ ኲሉ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

👉 ድርሳነ ማሕየዊ ዘዓርብ

#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

(የማርቆስ ወንጌል ምዕ. 14)

29፤ ጴጥሮስም። ሁሉም ቢሰናከሉ እኔ ግን ከቶ አልሰናከልም አለው።

30፤ ኢየሱስም። እውነት እልሃለሁ፥ ዛሬ በዚች ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ አለው።

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ስቅለት
ለእናንተ Profile ካዘጋጀናቸው ፎቶዎች
ሼር
👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ስቅለት
ለእናንተ Profile ካዘጋጀናቸው ፎቶዎች
ሼር
👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​​​ምን ሰጡህ ይሁዳ

ሙትን ልታስነሳ ድውይን ልትፈውስ
ሥልጣን ሰጥቶህ ነበር ኢየሱስ ክርስቶስ
ልታስር ልትፈታ በነፍስም በሥጋ
ሥልጣን ሰጥቶህ ነበር አልፋና ኦሜጋ

ምን ሰጡህ ይሁዳ አይሁድ ወገኖችህ
ለነርሱ አሳልፈህ ጌታህን የሰጠህ
ከሁሉ የሚበልጥ ሥልጣን ሰጥቶህ ሳለ
ብርን ለመቀበል ልብህ ተታለለ

ሰማይና ምድርን በቃሉ የፈጠረ
እንዴት በመቃብር ሶሥት ቀን አደረ
አንተ የሰጠኸው አሳልፈህ ለሞት
ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ በሰንበት

#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…
Подписаться на канал