ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የተወደድከው ወንድሜ👱‍♂
የተወደድሽው እህቴ👱‍♀
ዛሬ የእግዚአብሔርን ቃል የምታገኝበትን ኦርቶዶክሳዊ ቻናል እንድትከታተል ልጋብዝህ ነው
የመጣሁት።

በእዚህ ቻናል 👉ዝማሬዎች
👉ቃለ እግዚአብሔር
👉የቅዳሴ ትምህርት በቀላሉ ለመማር
👉የተለያዩ መንፈሳዊ መጽሐፍት ማግኘት ከፈለጋችሁ እና
👉 የተለያዩ ጽሑፍ እና ፎቶዎች ከፈለጋችሁ እዚህ ታገኛላችሁ።

🌹ይሄንን ቻናል ከተቀላቀልኩ ጀምሮ መንፈሳዊ ሕይወቴን እንዲያድግ ረድቶኛል አንተም/ቺም አሁን በመቀላቀል ትጠቀሙበት ዘንድ እለምናለሁ።

እንደተቀላቀላችሁ ቻናሉን። ተቀላቅለናል ብላችሁ ንገሩኝ።


/channel/ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​አዘነች ድንግል አለቀሰች

አዘነች ድንግል አለቀሰች ፍጹም አምርራ
በአንድ ልጇ ምክንያት ደርሶባት መከራ
በአንድ ልጇ ምክንያት ደርሶባት መከራ/፪/
#አዝ
በመንጻቱ ወር በዓርባኛው ቀን
ሥምዖን አረጋዊ ታቀፈ እና ጌታን
ትንቢት ተናገረ ተገልጾለት ሞቱ
በነፍስሽ ሠይፍ ያልፋል አንቺም እናቲቱ
ይኽንን መከራ ሲሠማ ጆሮዋ
አምርራ አለቀሰች አልቆም አለ ዕንባዋ
#አዝ
በአሥራ ሁለት ዓመቱ ለማክበር በዓል
በኢየሩሳሌም ቢገኝ አማኑኤል
ሲጠይቅ ሲሠማ በቤተ መቅደሱ
የኦሪት ካኅናት ሲደነቁ በእርሱ
እስከ ሦስት ቀን ድረስ ብትልጣው ፈልጋ
ልቧ ተሠበረ በሐዘን አለንጋ
#አዝ
ጠዋት በማለዳ በጲላጦስ ደጅ
ሲጸናበት አይታ የጨካኞች እጅ
ርቃኑን አድርገው ያለ አንዳች ጥፋት
ከግንድ ጋር አስረው ጀርባውን ሲገርፉት
እንዴትስ አታለቅስ እንዴት አታነባ
ሲገርፉት ሲያዳፉት ልጇን እንደ ሌባ
#አዝ
የዓለሙን ፈጣሪ የዓለሙን ዳኛ
ንጹሑን ጌታ መሥሏቸው ቀማኛ
እጁን እና እግሮቹን በችንካር ወጥረው
በወንበዴ መሐል ሠቅለውን ብታየው
ድንግል አለቀሰች አልቻለች መጽናናት
ዕንባዋ ወረደ እንደ ክረምት ጅረት
#አዝ
ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በአንድ ሲማከሩ
ቅዱሥ ሐያል ብለድ ገንዘው ሊቀብሩ
በአዲስ መቃብር በአሥራ አንደኛው ሠዓት
ሥጋውን አኑረው በድንጋይ ቢዘጉት
እያለች ዐነባች አንድ ልጄ እኮ ነው
ከእርሱ የሚቀድም ተከታይ የሌለው።

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ አሜን✞✞✞

#ቅዱስ_ማርቆስ_ዘአንበሳ

✞✞✞ በዚሕች ዕለት ከ72ቱ አርድእት አንዱ የሆነ: ወንጌላዊ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ዘአንበሳና ርዕሰ ሊቃነ ዻዻሳት የተባለ ቅዱስ ማርቆስ ተወልዷል ::

ቅዱስ ማርቆስ እናቱ ማርያም: አባቱ አርስጥቦሎስ ይባላሉ:: በልጅነቱ ኦሪትንና የዘመኑን ጥበብ ሥጋዊ በሚገባ ተምሮ ክርስቶስን ከቤተሰቦቹ ጋር ተከትሏል:: የመጀመሪያ ስሙ ዮሐንስ ሲሆን ከ120ው ቤተሰብ በእድሜ በጣም ትንሹ /20 ዓመት/ እርሱ ነበር::

ለ3 ዓመታት ከጌታ እግር ሥር ተምሮ: በበዓለ ሃምሳ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ብዙ ደክሟል:: በተለይ የግብፅና የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን አባት ነው:: ክህነትን ያገኘን ከርሱ ነውና::

ቅዱስ ማርቆስ 16 ምዕራፍ ያለውን ወንጌሉን ሲጽፍ ኪሩብ ገጸ አንበሳ በቀኙ: ሊቀ ሐዋርያት በግራው ሆነው ይራዱት ነበር:: ቅዱሱ ክቅዱስ ዻውሎስ: ከበርናባስና ዼጥሮስ ጋር ተጉዟል:: ከብዙ ስቃይና መከራ በኋላ ሰሜን አፍሪካ አካባቢ አረማውያን ገድለውታል:: ይህቺ ዕለት የልደቱ መታሠቢያ ናት::

ዳግመኛ በዚህ ቀን የቅዱስ ማርቆስን ወላጆችን እናስባቸው ዘንድ ይገባል:: ቅዱስ አርስጥቦሎስ (አባቱ) የጌታ ቅን አገልጋይ የነበረ: ቅድስት ማርያም (እናቱ) ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ: ጌታችንን ያገለገለች ቤቷን ለሐዋርያትና ለጌታ በስጦታ ያበረከተች ቅድስት ናት::

ቤቷም (ጽርሐ ጽዮን) የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ስትሆን ይህች ቤት መንፈስ ቅዱስ ወርዶባታል:: የእመቤታችን ግንዘትም ተከናውኖባታል::

እግዚአብሔር ከሐዋርያዊው ቅዱስ ቤተሰብ በረከትን ያድለን::

#ቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ

ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)

የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል!
እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር::

ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::

ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::

የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በኋላ በዚህች ቀን (ሰኔ 30) ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::

ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ 2 ዓመት ከ6 ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ::

እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 (5) ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ 5 (7) ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው ቀበሯት::

ሕጻኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ ድንግል ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ::

ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በኋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ25 (23) ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም::

ከዚህ በኋላ 30 ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጀን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" (ሉቃ. 1:76) ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና::

ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና::

ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሃ ሰበከ: ለንስሃም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ6 ወራት ቆይቶ ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነልብሱ የያዘ ፈጣሪ 'አጥምቀኝ' ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው::

"እንቢ ጌታየ! አንተ አጥምቀኝ" አለው:: ጌታ ግን "ፈቅጄልሃለሁ" አለው: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ ዛሬም "መጥምቀ መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ ለ7 ቀናት አሠረው::

በዚህች ቀንም ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: (ማቴ. 3:1, ማር. 6:14, ሉቃ. 3:1, ዮሐ. 1:6)

ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በኋላ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት ጌታችን ወዳለበት ደብረ ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች:: ቅዱሳን ሐዋርያት በአዩት ነገር ተገርመው ራሱን እጅ ነሷት::

ከዚሕ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት:: በመላው ዓለም ለ15 ዓመታት ስትሰብክ ኑራ ዓረቢያ ውስጥ ዓርፋለች::

👉 ይህች ዕለት ለቅዱሱ 'አስተርዕዮተ ርዕሱ' ወይም ቅድስት ራሱ ከተወረችበት የተገለጠችበት ነው::

ጥቅምት 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1. ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ
2. ቅዱስ አርስጥቦሎስ (አባቱ)
3. ቅድስት ማርያም (እናቱ)
4. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
5. አባ አብርሃም ገዳማዊ
6. ቅዱስ ይስሐቅ ንጉሥ

ዝክረ ቅዱሳን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የሉቃስ ወንጌል የመጨረሻው ክፍል

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን፡፡ ✞✞✞

ጥቅምት ፳፯ (27)

✞✞✞ እንኳን ለፈጣሪያችን "መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ" እና ለቅዱሳኑ "አባ መቃርስ": "አቡነ መብዓ ጽዮን" "ወአባ ጽጌ ድንግል" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ

ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት:: ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል::

ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት:: ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት:: ራሱንም በዘንግ መቱት:: እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ:: በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት::

በሠለስት (3:00 ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6,666 ገረፉት:: ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት:: 6:00 ላይ በረዣዥም ብረቶች 5 ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት::

7 ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ:: ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ 7 ቃላትን ተናገረ:: ከቀኑ 9:00 አካባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ::

+በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ:: 11:00 ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት:: በዚአች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ::

ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት 27 ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት አበው ሊቃውንት ናቸው:: ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት 27 የሚውለው ዓቢይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ በዓላት በዓቢይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው::

ምንም እንኩዋ በቅርብ ጊዜ በዓቢይ ጾም የሚያነግሡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን እንዲህ ያለውን ሥርዓት አላቆዩልንም:: ከበሮና የቸብቸቦ ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም::

በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት 27 ሲመጣ: የመጋቢት 5 ገብረ መንፈስ ቅዱስ ንግሥ ወደ ጥቅምት 5: የመጋቢት 10 መስቀል ወደ መስከረም 17 መጥቶ እንዲከበር ሆኗል::

© ዝክረ ቅዱሳን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ምሥጢረ ጥምቀት ክፍል ፬
የጥምቀት ምሳሌ በብሉይ ኪዳን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ምሥጢረ ጥምቀት መግቢያ
👉ለምን ምሥጢር ተባለ
👉ወንዶች በ40 ሴቶች በ80 ቀን ለምን ይጠመቃሉ? መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ስለ ምሥጢረ ሥላሴ በእዚህ አይነት መልኩ አጠናቀናል።

ጥያቄ ካላችሁ ያልገባችሁ ነገር ካለ

@zmaredawit_messengerbot

በዚህ ውስጥ በመግባት ጥያቄያችሁን ልትልኩልን ትችላላችሁ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን✝

የተወደዳችሁ የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች ዛሬ ተከታታይ ትምህርታችንን ክፍል ሁለት እንጀምራለን።

👉 ዛሬ ለማየት የምንሞክረው ርዕስ ምሥጢረ ሥላሴ ይሆናል።

ስለዚህ ባለፈው በላክንላችሁ ትምህርተ ተዋሕዶ በሚባለው አፕሊኬሽን በመክፈት አእማደ ምሥጢራት የሚለውን አምድ በመክፈት ምሥጢረ ሥላሴን ታነቡ ዘንድ እንጠይቃለን።

አሁን ስለ ምሥጢረ ሥላሴ ማጠቃለያ ትምህርት በድምጽ የምንልክ ይሆናል ተከታተሉ።

ይህንን መልእክት ያያችሁ እና ለመማር እና ለማዳመጥ ዝግጁ የሆናችሁ

👍 ይህንን ምልክት ላኩልን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🌼አዲሱን አመት በገና ክራር እና መሰንቆ መማር ይፈልጋሉ?🌼

👉እንኳን ደስ አለዎት ማኅበራችን ማኅበረ ኀዳፌ ነፍስ የ2016 የትምህርት መርኃ-ግብሮችን አዘጋጅቶ እየጠበቃችሁ ነው።

👉በአዲስ አመት የሚጀመር
⏱የስድስት ወር
⏱የሦስት ወር የትምህርት መርኃ-ግብር ያዘጋጀን ሲሆን

የመመዝገቢያ ቀን ከጷግሜ 6-መስከረም 4 ሲሆን ትምህርት የሚጀመረው መስከረም 5 ቅዳሜ ዕለት ይሆናል። ይደውሉ ይመዝገቡ


   📒 ለመመዝገብ ከታች ባሉት ስልክ ቁጥሮች ወይም በቴሌግራም አካውንታችን በውስጥ መስመር ልታወሩን ትችላላችሁ።

☎️ 0965083251
0956861468
    0912085085

ወይም በቴሌግራም
   @Orthodoxtewahed0
ልታዋሩን ትችላላችሁ ቶሎ በመመዝገብ በመንፈሳዊ መሳሪያ ጊዜዎትን ይጠቀሙ።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አዲስ መጽሐፍ በገበያላይ

#ኦርታዶክሳዊ_ወጣት_እና_ፈተናዎቹ

#ዮጋ በስፊው ተዳሰዋል
ዲን ዳግማዊ ሰሎሞን አዘጋጅቶታል።ወንድሜ ዲን ዳግማዊ
#ኦርቶዶክስ_መልስ_ናት የሚል መጽሐፍ አስነብቦን ነበር።

የጀርባ ዋጋ
#320ብር
ዋና አከፋፋይ
አርጋኖን መጻሕፍት መደብር Areganon Book Store
በCBE 1365 ለሚያስገቡ 250ብር ብቻ።

#አንዱን_ርዕስ_እንጋብዛችሁ
#ዘፈን_ለማቆም_ምን_ላድርግ? (የብዝዎቻችን_ጥያቄ_ነው አይደል?)
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://www.facebook.com/groups/271884238121590/permalink/647188570591153/?mibextid=Nif5oz

#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ዋናው_በር_ፊትለፊት_ሽዋ_ዳቦ_መነጽር_ቤቶቹ_ውስጥ_ወይም_በ0912044752_0925421700_ይደውሉ!
/channel/BetMetsahfte

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

3. ቤተ ክርስቲያናችን የመንፈሳዊ ኮሌጆቿን ቁጥር ከፍ በማድረግ የአገልጋይ መምህራንን ቁጥር ለማሳደግ ባላት እቅድ መሠረት ተጠንተው ከቀረቡት መካከል በ2016 ዓ.ም. የበጀት ዓመት በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ደብረ ብርሃን ከተማ ላይ፣ በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ደብረ ታቦር ከተማ ላይ ሁለት መንፈሳዊ ኮሌጆች እንዲቋቋሙ፣ በማዕከላዊ ጐንደር ሀገረ ስብከት ርእሰ ከተማ ውስጥ ለሚገኙት የምስክር ጉባኤ ቤቶች በኮሌጅ ደረጃ በጀት እንዲመደብላቸው እና በከንባታ ሐድያ ስልጤ ሀገረ ስብከት ሆሣዕና ከተማ ላይ አንድ የካህናት ማሠልጠኛ እንዲከፈት ጉባኤው ወስኗል፡፡

4. ቤተ ክርስቲያናችን ከውስጥና ከውጭ እየደረሱባት ያሉት ከፍተኛ የሆኑ ፈተናዎችን ተቋቁማ ሕልውናዋን አስከብራ መቀጠል ትችል ዘንድ ፡-

ሀ. ውስጣዊ ችግሮቻችን ቀኖና ቤተ ክርስቲያን በጠበቀ በውይይት እንዲፈቱ፣

ለ. ውጫዊ ችግሮችንና የመብት ጥሰቶችን በተመለከተ በችግሮቹ ዙሪያ ከሚመለከታቸው መንግስታዊ ተቋማት ጋር በመነጋገር ችግሮቹ እንዲፈቱ እና የቤተ ክርስቲያናችን መብትና ሕልውና ተጠብቆ እንዲቀጥል እንዲደረግ፣

ሐ. ለቤተ ክርስቲያናችን ሕልውና አደጋ የሆኑና ሊሆኑ የሚችሉ ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎችን አስመልክቶ በአግባቡ ተጠንተውናበማስረጃ ተተንትነው ከመፍትሔ ሐሳብ ጋር እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

5. ትላንት በሰሜኑ ኢትዮጵያ የሀገራችን ክፍል በተካሄደው ጦርነት በጠፋው የሰው ሕይወትና በወደመው ንብረት ከደረሰብን ሐዘን እኛ ኢትዮጵያውያን ገና ሳንጽናና ዛሬም በሀገራችን ኢትዮጵያ በበርካታ አካባቢዎች የተከሰቱት ጦርነቶች፣ ግጭቶችና አለመግባባቶች እያስከተሉት ያለው የንጹሐን የሰው ሕይወት መጥፍትና የንብረት ውድመት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤን በእጅጉ አሳዝኖታል፡፡ በመሆኑም ችግሩ በውይይትና በስምምነት እንዲፈታ የፌዴራልን የክልል መንግሥታት፣ እንዲሁም በግጭቱ ተሳትፎና ድርሻ ያላችሁ በሁሉም አካባቢ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በሙሉ የበኩላችሁን ሚና በመወጣት እናት አገራችን ኢትዮጵያ ሰላሟና አንድነቷ ተጠብቆ ይቀጥል ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶስ ከአደራ ጭምር በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

6. በሀገራችንና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየተከሠተ ያለው ችግርና ፈተና የሚወገደው ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በአንድነትና በሕብረት ለችግሮቹ መፈታት ድርሻ እንዳለን አውቀን እንደየእምነታችን አስተምህሮ በጸሎትና በምሕላ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር በንስሓ መመለስ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ በጽኑ ያምናል፡፡ በመሆኑም ስለ ሀገራችን ሰላምና ስለ ቤተ ክርስቲያናችን አንድነት በመላው ዓለም በሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ከህዳር 15 ቀን 2016 እስከ ታህሣሥ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ጸሎትና ምሕላ እንዲፈጸምና መላው ሕዝበ ክርስቲያንም በአንድነትን በሕብረት ከላይ በተጠቀሱት ዕለታት በቤተ ክርስቲያን በመገኘት የበረከቱና የሥርዓተ ጸሎቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኖ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

7. የቤተ ክርስቲያናችንን ታሪክና ለሀገረ መንግስት ምሥረታና እድገት ያበረከተችውን አስተዋጽኦ በማዕከል ደረጃ በማስረጃ አስደግፎ በመጻፍና በማደራጀት ትውልዱ እንዲረዳው በማድረግ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን የሕልውና አደጋ የሆነውን የሐሰት ትርክት መከላከል ይቻል ዘንድ የዝግጅት ሥራው በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል በሊቃውንት ጉባኤ የበላይ ተቆጣጣሪነት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንንና የታሪክ ተመራማሪዎችን በማሳተፍ ተግባራዊ እንዲሆን ጉባኤው ወስኗል፡፡

8. ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ላይ ስለሚኖራት ተሳትፎና ሚና በተመለከተ ጉባኤው በስፋት የተወያየ ሲሆን ሀገራዊ ምክክሩ ሀገራዊ ችግራችንን እንደሚፈታና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚነገሩትን የሐሰት ትርክቶች ሁሉ የሚታረሙበት እንደሚሆን ጉባኤው በጽኑ ያምናል፡፡ በመሆኑም በምክክር ሂደቱ ላይ ስለሚኖረን ተሳትፎና ሚና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል እየተጠና አስፈላጊው ሁሉ እንዲፈጸም ሆኖ የምክክር ኮሚሽኑም ይህን የቤተ ክርስቲያናችን እቅድ በመርሐግብሩ በማካተት ቤተ ክርስቲያናችን የድርሻዋን እንድትወጣ እድሉን እንዲያመቻችልን ጉባኤው ጥሪውን ያቀርባል፡፡

9. የመረጃ ቋት መዋቅራዊ አደረጃጀትን በሁሉም ክልል አህጉረ ስብከት ደረጃ በማቋቋም እና እለት እለት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚከሰቱትን ችግሮችና የመብት ጥሰቶች በመረጃና ማስረጃ አስደግፎ ለዋናው ማዕከል የመረጃ ቋት በፍጥነት ተደራሽ በማድረግ በአንዱ ቦታ ችግር ሲደርስ በመላ ሀገሪቱ እና በውጭው ክፍለ ዓለማት ባሉት አህጉረ ስብከት በአንድነት ድምፅ መሆን ይቻል ዘንድ ተጠሪነታቸው ለዋናው ማዕከል የሆኑ የመረጃ ቋት ማዕከላት በሁሉም አህጉረ ስብከት ተቋቁመው ወደሥራ እንዲገቡ ጉባኤው ወስኗል፡፡

10. የቤተ ክርስቲያናችን ሀብትና ንብረት የሆኑት ቅዱሳት መጻሕፍትን፣ የሚዳሰሱና እና የማይዳሰሱ ቅርሶችንና በአጠቃላይ ንዋየ ቅድሳቶቻችን ግለሰቦች እና ተቋማት በሕገወጥ መንገድ አትመውና አሳትመው በማሠራጨትና ትክክለኛ ቅጅውን አዛብቶ በማተም ቤተ ክርስቲያናችን ለሐሰተኛ ትርክት እንድትዳረግ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ በደል እየተፈጸመባት መሆኑን ጉባኤው በጽኑ ያምናል፡፡ በመሆኑም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ በኩል የተጀመረው የአዕምሯዊ ንብረት ምዝገባ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና የቤተ ክርስቲያኒቱ መብትና ጥቅም እንዲከበር ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

11. በውጭው ክፍለ ዓለማት በሚገኙት አህጉረ ስብከት ሥር የተቋቋሙት አብያተ ክርስቲያናት የሚተዳደሩበት እራሱን የቻለ ሕግና ደንብ ባለመኖሩ በመዋቅራዊ አስተዳደራችን ላይ ከፍተኛ ክፍተት ሲፈጥር የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ቅዱስ ሲኖዶስ ለውጭው ክፍለ ዓለማት አህጉረ ስብከት እና አብያተ ክርስቲያናት እራሱን የቻለ መተዳደሪያ ደንብ ተዘጋጅቶ የፀደቀ በመሆኑ በውጭው ክፍለ ዓለማት በሚገኙት ሁሉም አህጉረ ስብከትና አብያተ ክርስቲያናት በጸደቀው መተዳደሪያ ደንብ ብቻ ሥራቸውንና አገልግሎታቸውን እንዲያከናውኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

12. የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ኮሌጆች ወጥ የሆነ የጋራ መተዳደሪያ ደንብ እንዲኖራቸው በማሰብ ጉባኤው አስቀድሞ ተዘጋጅ እንዲቀርብ ባዘዘው መሠረት ተዘጋጅቶ የቀረበውን ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብ መርምሮ በማጽደቅ በሁሉም በተቋቋሙትም ሆነ ወደፊት በሚቋቋሙት ኮሌጆች ሥራ ላይ እንዲውል ጉባኤው ወስኗል፡፡

13. ገዳማትና ገዳማዊ ሕይወት፣ የአብነት መምህራን እና ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በአጠቃላይ ክብረ ክህነት እና ትምህርተ ኖሎት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል እየተጠና አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍና ክትትል እንዲደረግ ጉባኤው ወስኗል፡፡

14. የቤተ ክርስቲያናችን ሕጋዊ፣ ተቋማዊ፣ ሃይማኖታዊና ማህበራዊ መብቶች መከበርና የእምነት ነጻነታችንን እና የምእመናንን ደኅንነት በሕግ አግባብ ማስከበር ይቻል ዘንድ ልክ እንደ ዋናው መሥሪያ ቤት በሁሉም ክልሎች ውስጥ ባሉት አህጉረ ስብከት የሕግ ባለሙያዎች ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ እንዲገባ ጉባኤው ወስኗል፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የ2016 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ተጠናቀቀ።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለኢኦተቤ ቴቪ በሰጡት ዕለታዊ መግለጫ ጥቅምት 17 ቀን 2016 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አስተዳደራዊ ጉዳይን የያዘ የመሪ እቅድ ተጨማሪ ግብዓት ተጨምሮበት ለግንቦት ርክበ ካህናት እንዲቀርብ መወሰኑን ገለጹ፡፡ በጸደቁ አጀንዳዎች ላይ ላለፈው አንድ ሳምንት ሲወያይ የቆየው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መንፈስ ቅዱስን አጋዥ በማድረግ መግባባት በሰፈነበት ሁኔታ ጉባኤውን ማጠናቀቁን የገለጹት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) በማጠናቀቂያው በሕግ በመሪ እቅድ ትግበራ እና በልዩ ልዩ ጉዳዮች ጥናት ላቀረቡ እና ማብራሪያ ለሰጡ ባለሙያዎች በብፁዕ ወቅዱስ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ምስጋና ማቅረባቸውን ገልጸዋል። በአጠቃላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎችንአስመልክቶ ቅዱስነታቸው ሰኞ ጥቅምት 19 ቀን 2016 ዓ.ም መግለጫ እንደሚሰጡ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለኢኦተቤ ቴቪ በሰጡት ዕለታዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ የኢኦተቤክ ቴቪ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

እንደምን አመሻችሁ የተወደዳችሁ ኦርቶዶክሳዊያን
ዛሬም የቅዳሴ ትምህርታችንን እንቀጥላለን።

በደንብ እየተለማመዳችሁ እየቻላችሁት እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ። የከበዳችሁ ክፍል ካለ አሳውቁን በደንብ እንዲከለስ።

✝የቅዳሴ ትምህርቱን በደንብ እየተለማመዳችሁ ከሆነ "እየተለማመድን" ነው ብላችሀለ ቴክስት ላኩ አሁን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ለሰ/ት/ቤቶች መማሪያነት የተዘጋጀውን ሥርዓተ ትምህርት ተግባራዊ ለማድረግ የሁሉም ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ በኩል ተዘጋጅቶ ወደ እንቅሰቃሴ እየገባ በሚገኘው የሰ/ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት ዙሪያ ለ አጠቃላይ ዓለም አቀፍ  ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ተሳታፊዎች ማብራሪያ ቀርቧል።

ማብራሪያውን የሰጡት የአገር አቀፍ ሰ/ት/ቤት አንድነት ም/ሰብሳቢ ዲ/ን ስንታየሁ ምስጋናው እንደተናገሩት የሰ/ት/ቤች ሥርዓተ ትምህርትን ለመቅረጽ እጅግ በርካታ ሥራዎች ተሠርተዋል።

አሁን ተቀርጾ ወደ ተግባር እንዲገባ የሚጠበቀው ሥርዓተ ትምህርት 6 ዋና ርእሶች እና አንድ ደጋፊ ርእስ ያለው ሲሆን ለዘንድሮው ዓመት ትግበራ እንዲሆን 42 መጽሐፍት ታትመው እና በሊቃውንት ጉባኤ ተገምግሞ ዝግጁ ሆኗል።

አቅራቢው በተጨማሪ እንደገለጹት ሥርዓተ ትምህርቱ አሁን ያለው ትውልድ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ተረድቶ መንፈሳዊ ወጣት እንዲሆን የሚያስችል ዕውቀትን የያዘ በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለተግባራዊነቱ እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቃ ጳጳስ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዳሉት አሁን ያለውን ትውልድ ለማዳን ሰ/ት/ቤትን ማጠናከር የግድ ይለናል ብለዋል።

በተጨማሪም ሁሉም አኅጉረ ስብከቶች ሥርዓተ ትምህርቱ ተግባራዊ እንዲሆን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ መልእክት አስተላልፈዋል።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

🙏ሰላም የተወደዳችሁ ኦርቶዶክሳዊያን🙏

እኔ ዲያቆን ዳግማዊ ሰለሞን እባላለሁ ከዝማሬ ዳዊት ቻናል አስተባባሪዎች መካከል አንዱ ስሆን እኔ እና አገልጋይ ወንድሞቼ ይሄንን ቻናል ለብዙዎች
ኦርቶዶክሳዊያን የሚጠቅም እና መንፈሳዊ ትምህርት የሚገኝበት እንዲሆን ከቀን ከሌሊት
እየሰራን እንገኛለን። ነገር ግን ባለፉት 4 ወራት
ከ140,000 ወደ 135,800 የቻናላችን ተከታዮች ቀንሰዋል😔።

በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደ ቻናል ማስተካከል ያለብን ነገር ካለ እንድትጠቁሙን ስንጠይቅ ነበር።
ነገር ግን ይሄ ቻናል እስከ አሁንም ድረስ የቆመው
በእናንተ ድጋፍ እና ብርታት ነውና። አሁንም ይሄንን
ቻናል ወደ ቀደመ ቦታው መመለስ የእናንተም ድርሻ ይሆናል።


🌹ስለዚህ ኦርቶዶክሳዊያን የዝማሬ ዳዊት አባላት
የቅዳሴው ትምህርት፣ሌሎችም ዝማሬዎች እና መንፈሳዊ ሕይወትን ያተኮሩ ትምህርቶች እንዲቀጥሉ ከእዚህ በኋላ ከእናንተ የሚጠበቀው።

👉 ለምታውቋቸው ስልካችሁ ላይ፣ቴሌግራማችሁ ላይ ላሉ 100 ኦርቶዶክሳዊያን ይሄንን ከታች የምንልክላችሁ የቻናሉን ሊንክ እና መልእክት ትልኩላቸው ዘንድ በታላቅ ፍቅር እና አክብሮት እንጠይቃለን።

✝እስከ አሁን እኛ በእግዚአብሔር ቸርነት ደከምን
እናንተ ኦርቶዶክሳዊያን እህት ወንድሞቻችን ደግሞ
የእኛን ድካም የምታግዙን ከሆነ አሁን እኛን ደግፋችሁ የሳምራዊቷን ሴት አገልግሎት በሚመስል መልኩ ለብዙዎች የሚደርሰውን ይህንን የወንጌል ቃል በመላክ ከምናዘጋጀው መንፈሳዊ ማዕድ እንዲካፈሉ ታደርጉ ዘንድ እንጠይቃለን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

#ሰላም_አርጊው_ማርያም

ሰላም አርጊው ማርያም ስጭን የእጅሽን(፪)
አንድ መንጋ ሆነን በዛ ቋንቋችን
ናፍቀናል ልጆችሽ ፍቅር አንድነትን

በስንዴው መሃል እንክርዳዱን
ጠላት ዘራና ክፍፍሉን
የፍቅር ቋንቋ ቀዘቀዘ
አንድነታችን ደበዘዘ
እንወድሻለን ማርያም

#አዝ

ያስጎነበሰን ሸክም ይቅለል
በልጅሽ ምህረት ቀና እንበል
ሰላም እንዲሰንፍ በምሕረቱ
ንጉሡን ማልጅው ንግስቲቱ
እንወድሻለን ማርያም

#አዝ

የሽንገላ ቃል ከኛ ይውጣ
ያ ክፉ ዘመን እንዳይመጣ
በመለያየት ተመስርቶ
የፀና መንግስት የለም ከቶ
እንወድሻለን ማርያም

#አዝ

በረከት አዟል አምላካችን
ህብረት ባለበት መኖሪያችን
ክፍፍል ይቅር አሳስቢልን
በቃል ኪዳንሽ አስጠልይን
እንወድሻለን ማርያም

#አዝ

ክፋትን ተክለን በልባችን
መልክ ብቻ ነው አምልኳችን
ወድቀን እንዳንቀር እንዳንጠፋ
ፍቅርን ሳይብን የአዳም ተስፋ
እንወድሻለን ማርያም

ሊቀ_መዘምራን
ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

በይስሐቅ ፈንታ
የበገና መዝሙር

በይስሐቅ ፈንታ ኢየሱስ ታረደ/2/
ደሙን ከፈለና አዳምን ታደገ/2/

ተጨነቀ ጌታ ተሰቃየ ጌታ
የኔ መድኃኔዓለም የአዳም ልጅ አለኝታ
እንደሚታረድ በግ ተነዳ ወደ ሞት
ንፁህ ኢየሱስ በደል የሌለበት

በማመን ሲሸከም የአዳምን መከራ
ስቃይ ተቀበለ ደሙ እየተዘራ
ለሚገርፋት ሁሉ ምህረትን ሲቸር
እርሱ ግን ሲገረፍ ብዙ ተቸገረ

የሰማነውን ድምፅ ማን ሰው እኮ አምኗል
የእግዚአብሔርስ ክንድ ለነማን ተገልጿል
ባየነው ጊዜ ህመም ተሸክሞ
ስለበደላችን ተገርፎና ታሞ

እጁ የታሰረው ይስሀቅ ተፈቶ
ኢየሱስ ቀረበ በሰው ልጆች ፈንታ
ንፁህ በግ ቀረበ በደል የሌለበት በደለኛ ሆኖ
ሊሰቀል ሊገደል መስቀሉን ተጭኖ

በእውነት ደዌያችንን እርሱ ተሰቀለ
በሰው ልጆች ፈንታ በእንጨት ተሰቀለ
እኛ ግን ከሰስነው እንደ ወንጀለኛ
ስለ እኛ ቢሰቀል ሰማያዊው ዳኛ

ለሰው ልጆች ህይወት የታሰበውን ሰይፍ
አይተናል ሰምተናል በኢየሱስ አንገት ሲያልፍ
የመስቀሉ ስዕል ኧረ እንዴት ይገርማል
እዩት ንፁህ በግ በአርምሞይነዳል

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

​​ጥቅምት ፳፯ በዚህች ዕለት የታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አባ መባዓጽዮን መታሰቢያ ነው።

አቡነ መብዓጽዮን ለቸሩ አምላካችን ለመድኃኔ ዓለም ባላቸው ጽኑዕ ፍቅር የሚታወቁ ግሩም አባት ናቸው። ገና ልጅ እያሉ ሥዕለ አድኅኖ ተለይቷቸው አያውቅም። የመድኃኒታችንን ጽኑዕ መከራ በማሰብ በራሳቸው ላይ ያላደረጉት ምን አለ? ችንጋሮችን ራሳቸው ላይ ይቸነክሩ ነበር፣ ድንጋይ ተሸክመው ብዙ ይሰግዱና ከልቅሶ ጋር ይጸልዩ ነበር፣ ሥጋቸውንም በጽኑዕ ቅጣት ይቀጡት ነበር።

ጌታችንን ይወዱትም ስለነበር በቅዱስ ስሙ ዝክር ይዘክሩ ነበር። ዝክራቸውም በንጽሕና የኾነ ነበርና ከዚያ ዝክራቸው የቀመሰ ኹሉ ካለበት ደዌ ይፈወሳል።
ጌታችንም የሚያስደንቁ ቃልኪዳናትን የገባላቸውና በዚህች እለት ብዙ ነፍሳትን ከሲዖል ያወጡበትም እለት ነው።

ዕረፍታቸውም ከጌታችን ዕረፍት ጋራ አንድ እምደሚኾንላቸው ተነግሯቸው ነበር። ከጽኑዕ ገድልም በኋላ በዚህች ቡርክት ቀን ዐርፈዋል።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፣ እኛንም በአባታችን በአባ መባዓ ጽዮን ጸሎት ይማረን !

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ምሥጢረ ጥምቀት የመጨረሻው ክፍል

አፕሊኬሽኑ ላይ ከታች የተጠቀሱትን ተጨማሪ ጥቅሶች አይታችሁ። ጥያቄ ካላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ምሥጢረ ጥምቀት ክፍል ፪
👉ጥምቀት ለምን ያስፈልጋል

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።✝

ሠላም የተወደዳችሁ የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች?
እስከ አሁን ድረስ ምሥጢረ ሥላሴ እና ምሥጢረ ሥጋዌን ያየን ሲሆን በእነዚህ ርዕሶች ላይ ጥያቄዎች ካላችሁ አሁን መጠየቅ ትችላላችሁ። ሰብስበን መልስ እንሰጣለን።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

አምስቱ አእማደ ምሥጢራት መግቢያ ፩

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የሉቃስ ወንጌል ሲነበብ የምንለው ይህንን ይሆናል

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የቅዳሴ ትምህርታችን ከክፍል 40-49
ተለማመዱት የከበዳችሁ ካለ በጥያቄ መጠየቂያው በኩል ላኩልን።

ለምትወዷቸው ጓደኞቻችሁ ቅዳሴ ይማሩ ዘንድ ላኩላቸው

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

15. ወጣቱ ትውልድ በእምነቱ ጸንቶና በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ በእውቀትና በሥነምግባር ይታነጽ ዘንድ በሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ተዘጋጅቶ የቀረበው ሥርዓተ ትምህርት በሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር እና አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ተግባራዊ እንዲሆን ጉባኤው ወስኗል፡፡

16. የ2016 ዓ.ም. ዓመታዊ በጀትን አስመልክቶ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል ተዘጋጅቶ የቀረበውን የበጀት ድልድል ጉባኤው መርምሮ በማጽደቅ ሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

17. የቤተ ክርስቲያናችን የመልካም አስተዳደር ችግሮች የሚፈቱት እና የልማት ተቋማት የሚጠናከሩት ዘመኑን የዋጀ መዋቅራዊ አደረጃጀት በመፍጠር እና በእቅድ ተደግፎ በእውቀት ላይ የተመሠረተ የሀብትና የንብረት አስተዳደር ማስፈን ሲችል መሆኑን ጉባኤው በጽኑ ያምናል፡፡

በመሆኑም በባለፈው ጉባኤ የጸደቀው የ10 ዓመት የመሪ እቅድ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እየተደረገለት የመሪ ዕቅዱ አፈጻጸም እንዲቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን


አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ጥቅምት ፲፱ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም.
ኢትዮጵያ አዲስ አበባ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ በዓመት ሁለት ጊዜ እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 ላይ በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የመክፈቻውን ሥርዓተ ጸሎት ከፈጸመበት ከጥቅምት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡
በመሆኑም ምልዓተ ጉባኤው ስለ ቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ እየተከሰቱ ስላሉት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች እንዲሁም ስለ ሀገር ሰላምና አንድነት በስፋት በመወያየት ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-
1. የ2016 ዓ.ም. የመንበረ ፓትርያርክ ዓለም አቀፍ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ያሳለፈውን የጋራ የአቋም መግለጫ በመመርመርና አስፈላጊውን ማሻሻያዎች በማድረግ የበጀት ዓመቱ የቤተ ክርስቲያናችን የሥራ መመሪያ እንዲሆን ጉባኤው አጽድቆታል፡፡

2. ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን መዋቅራዊ አደረጃጀቱን የበለጠ ተደራሽ በማድረግ ሐዋርያዊ ተልዕኮዋን መወጣት ትችል ዘንድ በአዲስ እንዲደራጁ ተጠንተው የቀረቡትን የአህጉረ ስብከት ይደራጅልን ጥያቄዎችን በመመርመር፡-
ሀ. የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት፣
ለ. የሰሜን ጎጃም ዞን ሀገረ ስብከት
ሐ. የጎፋና ባስኬቶ ዞን ሀገረ ስብከት
መ. የምሥራቅ ጉራጌ ዞን ሀገረ ስብከት እራሳቸውን ችለው ሀገረ ስብከት ሆነው ተደራጅተው እንዲቀጥሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የቅዳሴ ቀጣዩ ክፍል እነሆ👇👇👇

የከበዳችሁ ካለ ንገሩን። በደንብ ተለማመዱት

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

ሰላም የተወደዳችሁ ኦርቶዶክሳዊያን የዝማሬ ዳዊት ቤተሰቦች።
የቅዳሴ ትምህርታችንን በደንብ እየተከታተላችሁ እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን።

🙏ለሌሎች ኦርቶዶክሳዊያን ለምታውቋቸው ቶሎ ከእኛ ጋር ሆነው የቅዳሴውን ትምህርት ተምረው እኩል ከእኛ ጋር ቤተክርስቲያን ሲሄዱ የሚባለው ሳይገባቸው ተሰላችተው ወደ 🏠 ከሚመለሱ።

አሁን እናንተ ይሄንን ቻናላችንን ለምታውቁት ሰው ሁሉ ስልካችሁ ላይ ላለው ሰው ሁሉ እንዲቀላቀሉን ሊንኩን ልካቸውላቸው ከእኛ ጋር በፍቅር ይማሩ ዘንድ በትኅትና እንጠይቃለን። ወደ ቻናላችን እንዲቀላቀሉ ይህንን ሊንክ ላኩላቸው

/channel/ortodoxmezmur
/channel/ortodoxmezmur
/channel/ortodoxmezmur
/channel/ortodoxmezmur
/channel/ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zemare Dawit

የመጀመሪያው ጸልዩ የሚለውን ዲያቆኑ ሲል ምዕመናን ምን እንላለን የሚለውን አዳምጡ

Читать полностью…
Подписаться на канал