ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች?

ጸሎት ከፈጣሪ የምንገናኝበት መንገድ ስለሆነ እግዚአብሔር ጊዜን እየጠበቀ በዚህ ጊዜ እሰማችኋለሁ በዚህን ጊዜ አልሰማችሁም አይልም፡፡ በወር አበባ ጊዜ አይጸልይም ማለት የቤተ-ክርስትያን አስተምህሮ ሳይሆን የሰነፉ ሰይጣን የተንኮል እና የእንቅፋት ስብከት ነው፡፡

የሰይጣንን እንኳን ጸሎት ትተን ቀርቶ እየጸለይን ፈተናችንን እኛና እግዚአብሔር ነው የምናውቀው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በዘመኑ እንደ እኛ ግራ ለተጋቡት የተሰሎንቄ ምእመናን "ሳታቋርጡ ፀልዩ" በማለት ፀሎት በየትኛውም ሁኔታ እና አጋጣሚ ማቋረጥ እንደሌለባቸው ፅፎላቸዋል። (1ኛ ተሰሎ 5÷18)

ወዳጆቼ ፀሎትን የለመደች ሴት በወር አበባዋ ምክንያት ለሰባት ቀን ፀሎትዋን ብታቋርጥ ስንፍናን ትለምዳለች፡ትዘናጋለች አጋንንቱም በዚህ አጋጣሚ ፈተናዋን ያበዛል።

ሴት በወር አበባዋ ጊዜ እስከ መንጻቷ ቤተክርስትያን ነው መግባት የማትችለው እንጂ፣ ጸሎት ማቋረጥ የለባትም፡፡ ጊዜን ተብቆ አለመጸለይ ለሰይጣን በር መክፈት ነውና ትንሿን ጸሎታችንን ማቋረጥ የለብንም፡፡

እኛ በወር አበበ ጊዜ ንፁህ አይደለንም ብለን ሥጋዊ ምግብ እንደማንተው ሁሉ ጸሎት የነፍስ ምግብ ነውና ነፍሳችን ለ7 /ሰባት/ ቀን ከውዳሴ ማርያም ፣ ከሰኔ ጎለጎታ ፣ከአርጋኖን፣ከሰይፈ ሥላሴ፣ከሰይፈ መለኮት እና ከተለያዩ የጸሎት ማዕድ እየከለከልን ሕያዊት ነፍሳችንን ማስራብ የለብንም፡፡ ይልቁንም ዘወትር በመጸለይ ነፍሳችንን መመገብ ይገባናል፡፡

ይቀጥላል
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው?

1ኛ/ ጸሎት

ሕልመ ሌሊት የሚያስቸግረን ከሆነ ማታ የእለት ውዳሴ ማርያም ከበረታን ከመዝሙር ዘጠና ጋር ጸልየን መተኛት፡፡ እመቤታችንን የዝንየት አጋንንቱን እንድታስርልን እንድታርቅልን መማጸን፡፡ ያኔ በሌሊት በተቃራኒ ጾታ እየተመሰለ የሚፈትነን የሕልመ ሌሊት አጋንንት (ዝንየት) ሲርቀን በሰላም መኖር እንጀምራለን፡፡

ወዳጆቼ ብርቱ ጸሎት እንኳን ከሕልመ ሌሊት ከገሃነመ እሳት ይታደገናልና በርትተን እንጸልይ፡፡ ማታ ማታ ውዳሴ ማርያም፣ አርጋኖን የቻልነውን ያህል ብንጸልይ የእመቤታችን ጥበቃ እናገኛለን፡፡

2ኛ/ ሕልመ ሌሊት እንደመታን ተመልሶ አለመተኛት

ብዙዎቻችን ሕልመ ሌሊት ሲመታን ተስፋ በመቁረጥ ተመልሰን በዛው እንተኛለን፡፡ ይሄ ድርጊታችን አጋንንቱን ከማስደሰቱም በላይ ለነገ የልብ ልብ ይሰጠዋል፡፡ እኛ በሕልመ ሌሊት ምክንያት ጸሎቱን ትተን ‹‹ጠዋት ታጥቤ እጸልያለሁ›› በሚል ስንፍና ከተኛን አጋንንቱ እየደጋገመ እየመታን ሕልመ ሌሊቱን ጸሎት ለማስታጎያ ያደርግብናል፡፡

ስለዚህ ሕልመ ሌሊት እንደ መታን ፈጥነን በመነሳት ከቻልን ሰውነታችንን መታጠብ ካልቻልን አንቀጸ ሥጋችንን በመታጣብ ጸሎታችንን መጸለይ፡፡ ወዳጆቼ ሕልመ ሌሊት እንደ መታን ተነስተን ታጥበን በመጸለያችን የነገ የአጋንንቱን ውጊያ በር እንዘጋበታለን፡፡ አጋንንቱ በሕልመ ሌሊት የሚመታን አንድም እንዳንጸልይ ስለሆነ እኛ ደግሞ በተቃራኒ ከጸለይን አጋንንቱ ይርቀናል፡፡

3ኛ/ ማታ ውኃ አብዝቶ አለመጠጣት

ሕልመ ሌሊትን ለማስታገስ አንዱ መፍትሔ ማታ ውኃ አብዝቶ አለመጠጣት ነው፡፡ ይህንን ከመጻሕፍተ መነኮሳት ሁለተኛው የሆነው ፊልክስዮስ ‹‹አካልን የሚያደርቅ፤ ከሕልመ ሌሊት፣ ከዘር መፍሰስ የሚከለክል፤ በመዓልት ኃልዮ ኃጢአትን የሚያጠፋ እንደ ውኃ ጥም የለም፡፡

ምንም ቢጾሙ፣ ምንም ከምግብ ቢያከፍሉ አብዝቶ ውኃ ከጠጣ አይጠቅምም፡፡ ምነዋ ትለኝ እንደ ሆነ ሆዱ ቂብ ትላለች›› /ፊልክ.ክፍል 3 ተስእ 38/

ውኃ ማታ አብዝቶ መጠጣት ዘር በቀላሉ እንዲፈስ ያደርጋል፡፡ አባቶቻችን በሕጋዊ ጋብቻ ያሉትን ባለ ትዳሮች ‹‹ሩካቤ ሥጋ ከመፈጸማቸው ከ30 ደቂቃ በፊት ንጹህ ውኃ ጠጡ›› የሚሉት በግንኙነት ጊዜ በሰውነት በቂ ውኃ ካላ የወንድ ዘር በቀላሉ ወደ ሴቷ ማህፀን ስለሚደርስ ነው፡፡

ውኃ ለወንድ ዘር ተሸካሚ ነው፡፡ ውኃው ነው የወንድን ዘር እንደ መርከብ በመሸከም ከማህፀን የሚያደርሰው፡፡ ስለዚህ ማታ ማታ ውኃ አብዝቶ አለመጠጣት ትኩስ ነገርም አለማዘውተር ይመረጣል፡፡

4ኛ መስገድ

ሕልመ ሌሊት አዘውትሮ የሚፈታተነን ከሆነ ስግድት ላይ መበርታት፡፡ በተለይ ማታ ከመተኛታችን በፊት እራሳችንን በስግደት ቀጥቅጠን መተኛት፡፡ በስግደት የደከመ ሰውነት ላይ አጋንንት የበላይነት አይኖረውም፡፡ ስግደት ከእነዚህ ዓይነት አጋንንታዊ ጾር የምንርቅበት እና መፍትሔ የምናገኝበት ስለሆነ መቼም ስግደት ባይሆንልንም መስገድ መልመድ ይገባናል፡፡

5ኛ/ መጠንቀቅ እና ማማከር

ተወዳጆች ሆይ እራሳችንን ለፍትወት እና ለዝሙት ከሚያጋልጡን ነገሮች የምንርቅ ከሆነ አጋንንቱ በእኛው ስህተት ለሕልመ ሌሊት አይዳርገንም፡፡ እንዲሁም ፈተናው ሲደጋገምብን ሲበረታብን አባቶችን በግል በመፍትሔው ዙርያ ማመከርና የሚሉንን መስማት እና መተግበር፡፡

ወዳጆቼ አጋንንት ወንድ ሴት ሳይል በሕልመ ሌሊት መፈተኑን አይተውም፡፡ ስለዚህ እኛ በጾም፣ በጸሎት በስግደት መዋጋቱን ልንተው አይገባም፡፡

‹‹ከእመቤታችን በጸሎት መልስ የምናገኝባቸው ጠቃሚ መንገዶች›› ከሚለው መጽሐፌ ተወስዶ ብዙ አዳዲስ ሐሳቦች ተጨምሮበት ተጻፈ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​ነሐሴ 14/12/2016 ዓ.ም

✝ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።

ዲያቆን፦ 1 ቆሮ 1÷10-19
ንፍቅ ዲያቆን፦ ያዕ 1÷12-22
ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 1÷30-34

ምስባክ ፦ መዝ 43፥4-6
ዘአዘዝከ መድኀኒቶ ለያዕቆብ
ብከ ንወግኦሙ ለኩሎሙ ፀርነ
ወበስምከ ናኀስሮሙ ለእለ ቆሙ ላዕሌነ

ትርጉም
ለያዕቆብ መድኀኒትን እዘዝ
ባንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን
በስምክም በላያችን የቆሙትን እናዋርዳቸዋለን

ወንጌል ፦ ማቴ 17÷14-24
ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ምሥጢረ ደብረታቦር

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

እንኳን ለደብረታቦር በዓል በሰላም በጤና አደረሰን አደረሳችሁ

"ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ ፤ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ"

ቅዱስ ጴጥሮስ

ታቦር ተራራ የዛሬ ገጽታው ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ቅዱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤሌያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን። ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ከኤልያስ እንሥራ አለ።

እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር። ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና። ተነሡ አትፍሩም አላቸው። ዓይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም። የማቴዎስ ወንጌል 17፡1-8

በቂሳርያ ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ ለሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል ብሎ ጠይቋቸው አንዳንዶች ከነቢያት አንዱ ነህ ይሉሃል፣ አንዳንዶች ሙሴ ነህ ይሉሃል፣ ሌሎች ደግሞ ኤልያስ ነህ ይሉሃል እያሉ መለሱለት ጌታችንም መልሶ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ብሎ ሲጠይቃቸው የሐዋርያት አፈጉባዔ ሊቀ ሐዋርያት ቅ/ጴጥሮስ ‹አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጅ ነህ› ብሎ በመመስከሩ ጌታም ‹የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ በሰማይ ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ…› ተብሏል፡፡

ይህ በሆነ በሰባተኛው ቀን ሦስቱን ደቀ መዛሙርት ጴጥሮስ፣ ዮሐንስና ያዕቆብን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ወጣ፡፡ በዚያም እንደ ዮርዳኖስ ወንዝ መድኃኔዓለም ክብረ መንግስቱን ፤ ብርሃነ መለኮቱን ገልጧል ፡፡ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንዱ የሆነው በዓለ ደብረታቦር የዚህ ታሪክ መታሰቢያ ነው ፡፡

ታቦር ተራራ ከገሊላ ባሕር በስተምዕራብ 17 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ፤ ከናዝሬት ከተማ በስተምስራቅ ፤ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምዕራብ አቅጣጫ ሲገኝ ከባሕር ጠለል በላይ 572 ሜትር ነው ፡፡ከላይ ወደታች ሲታይ ታቦር ተራራ ቅርጹ የተገለበጠ የሻይ ስኒ ይመስላል ይላሉ ፡፡
እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።

ምሥጢረ መንግሥቱን ለምን በታቦር ተራራ ገለጸው ?

መድኃኔዓለም ሌሎች ተራሮች እያሉ ክብሩን ለመግለጥ ስለምን ደብረ ታቦርን መረጠ ቢሉ ትንቢቱንና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡

ትንቢት
“ ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ ወይሰብሑ በስምከ ”

ታቦርና አርሞንኤም በስምህ አምነው በተደረገላቸው ነገር ደስ ይላቸዋል፣ ስምህን ያመሰግናሉ፣ ለስምህም ምስጋና ያቀርባሉ፡፡ “ መዝ 88፡12

ምሳሌ
ባርቅ ሲሳራን ድል አድርጎበታል መሳፍንት 4፡6 ይኸውም ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡ ‹… የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደገና ክፉ ሥራ ሠሩ፡፡ እግዚአብሔርም በአሶር በነገሠው በከነዓን ንጉሥ በኢያቡስ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው የሠራዊቱም አለቃ በአሕዛብ አሪሶት የተመረጠው ሲሣራ ነበር… ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች ነበሩትና የእስራኤልንም ልጆች ሃያ ዓመት ያስጨንቃቸው ነበር› /መሳ 4.1-3/

ሁሌም ቢሆን የሰውን በደል ዐይቶ እንደወጣችሁ ግቡት፣ እንደገባችኋት ውጧት የማይልና ‹… ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል› የተባለለት እግዚአብሔር ከዚህ ቀንበር የሚላቀቁበትን መላ ራሱ አመለከታቸው፡፡ /1ቆሮ. 10-13/፡፡

እስራኤላውያን ወደ ፈጣሪያቸው በጮኹ ጊዜ የለፊዶት ሚስት የሆነችውንና እስራኤልን በነቢይነትና ዳኝነት ታገለግል የነበረችው ነቢይቱን ዲቦራን ተጠቅሞ የማሸነፊያ መላውን አመለከታቸው ነቢይቱ ዲቦራ ትንቢት ከመናገር አልፋ የእስራኤልን ንጉሥ ባርቅ ከእኔ ጋር ወደ ጦርነቱ ውጪ ብሎ ባስጨነቃት ጊዜ በጦር አዝማችነትም ተሳተፈች፡፡

እግዚአብሔር በነቢይቱ በዲቦራ በኩል ለእስራኤል ንጉሥ ‹ሔደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጡ…› ብሎ አዞት ነበርና ንጉሡ ዐሥር ሺሕ ብረት ለበስ ያልሆነ እግረኛ ሠራዊት ይዞ ደብረ ታቦርን ተማምኖ በተራራው ላይ መሸገ ጦርነቱ ሳይጀመር አለቀ፡፡ ምክንያቱም ‹እግዚአብሔርም ሲሣራን ሰረገሎቹንም ሁሉ ሠራዊቱንም ሁሉ ከባርቅ ፊት በሰይፍ ስለት አስደነገጣቸው፡፡ ሲሣራም ከሰረገላው ወርዶ በእግሩ ሸሸ…› /መሳ. 4.15/

እስራኤል በእግዚአብሔር አጋዥነት በታቦር ተራራ ላይ የሃያ ዓመት የግፍና የሰቀቀን አገዛዝ ቀንበራቸውን ከትከሻቸው አሽቀንጥረው በምትኩ የድል ካባን ደረቡ ‹… በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ የባዕድ ጭፍሮችንም አባረሩ› ተብሎም ጀግንነታቸው ተጻፈላቸው፡፡ የታቦር ተራራ ያኔ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ባለውለታቸው ነበር፡፡ /ዕብ. 11.32-34/

ጌታም በልበ ሐዋርያት ያለ ሰይጣንን ድል ያደርግበታልና ማለትም በልባቸው ጥርጥርን እና ፍቅረ ሢመትን( የሥልጣን ፍቅር) ያሳደረ ዲያብሎስን ድል ነስቶላቸዋል ፡፡ከዚህም በመነሳት ነው በዓለ ደብረታቦር የደቀመዛሙርት ተማሪዎች በዓል ነው የሚባለው ፡፡ ለምን 3ቱን ሐዋርያት ( ጴጥሮስ ፤ዮሐንስ እና ያዕቆብን) ብቻ ይዞ ወደ ተራራ ወጣ፡-

ለፍቅሩ ስለሚሳሱ ነው፡፡ ይህም በዕብራይስጡ ኬፋ ፤ በግሪኩ ጴጥሮስ ፤በግዕዙ ኰኲሕ( ዐለት) የተባለው የዮና ልጅ ስምዖን ጌታ እሞታለሁ እያለ ጌታችን ሲናገር አይሁንብህ በማለቱ ከባሕርይ አባቱ ከአብ እርሱን ስሙት የሚል መለኮታዊ ድምጽ ሰምቷል፡፡ዮሐንስና ያዕቆብ ጌታን ምድራዊ መሲህ አድርጎ በማሰብ ቀኝ ጌትነትን እና ግራ ጌትነትን በእናታቸው በኩል የማይገባ ልመና አቀረቡ ዮሐንስና ያዕቆብ እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ? ሲባሉ አዎ ብለው መለሱ በዚህም ከባሕርይ አባቱ እርሱን ስሙት የሚል ድምጽ ሰሙ፡፡

በይሁዳ ምክንያት ነው ኢሳ 26.13 ‹ኃጥእ ሰው የእግዚአብሔርን ክብር እንዳያይ ያርቁታል› እንዲል እርሱን ጥሎ አስራ አንዱን ወደ ተራራ ይዞ ቢወጣ ከምሥጢር ቢለየኝ በሞቱ ገባሁበት እንዳይል፡፡ ያም ባይሆን ስምንቱ ደቀ መዛሙርት ለምን ይከለከላሉ ቢሉ አልተከለከሉም በርዕሰ ደብር (በተራራው አናት) ለሦስቱ ደቀ መዛሙርት የተገለጸው ምስጢር በእግረ ደብር (በተራራው ግርጌ) ለነበሩት ስምንቱ ደቀ መዛሙርት ተገልጦላቸዋል፡፡ ይህም በደብረሲና ለሰባው ሊቃናት የተገለጠ ምሥጢር በከተማ ለነበሩት ለኤልዳድና ሙዳድ እንደተገለጠ ማለት ነው፡፡ ዘኁልቊ 11፡26

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​ነሐሴ 13/12/2016 ዓ.ም
ደብረ ታቦር
✝ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።

ዲያቆን፦ ዕብ 11÷23-30
ንፍቅ ዲያቆን፦ 2 ጴጥ 1÷15-ፍ.ም
ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 7÷44-51

ምስባክ ፦ መዝ 88፥12-14
ታቦር ወአርሞንዔም በስመ ዚአከ ይትፌስሁ ወይሴብሑ ለስምከ
መዝራዕትከ ምስለ ኀይል

ትርጉም
ታቦር እና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል
ስምህንም ይመሰግናሉ
ክንድክ ከኃይልክ ጋር ነው

ወንጌል ፦ ሉቃ 9÷28-38
ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

#አማን_በአማን

አማን በአማን /2/ ተሰብሐ
አማን በአማን /2/ ተሰብሐ
በደብረ ታቦር /2/

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

#አምላካችን_ናና

አምላካችን ናና በአምደ ደመና
አማኑኤል ናና ብርሀን ነህ እና

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

#ሆያ_ሆዬ
ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ

እንኳን ለደብረታቦር በዓል በሰላም
አደረሳችሁ አደረሰን

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

#ቡሄ_በሉ

ቡሄ በሉ (2) ልጆች ሁሉ የኛማ ጌታ
የዓለም ፈጣሪ የሰላም አምላክ
ትሁት መሀሪ በደብረ ታቦር የተገለጠው
ፊቱ እንደ ፀሐይ በርቶ የታየው
ልብሱ እንደብርሃን ያንፀባረቀው

ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና(2)
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን(2)

ያዕቆብ ዮሐንስ እንዲሁም ጴጥሮስ
አምላክን አዩት ሙሴ ኤልያስ
አባቱም አለ ልጄን ስሙት
ቃሌ ነውና የወለድኩት

ታቦር አርሞንኤም ብርሃን ታየባቸው
ከቅዱስ ተራራ ስምህ ደስ አላቸው
ሰላም ሰላም የታቦር ተራራ
ብርሀነ መለኮት ባንቺ ላይ አበራ

በተዋህዶ ወልድ የከበረው
የእግዚአብሔር አብ ልጅ
ወልደማርያም ነው
ቡሄ በሉ/2/ የአዳም ልጆች
ብርሃንን ተቀበሉ

አባቴ ቤት አለኝ ለከት
እናቴ ቤት አለኝ ለከት
አጎቴም ቤት አለኝ ለከት
ተከምሯል እንደ ኩበት

የዓመት ልምዳችን ከጥንት የመጣው
ከተከመረው ከመሶቡ ይውጣ
ከደብረ ታቦር ጌታ ሰለመጣ
የተጋገረው ሙልሙሉ ይምጣ

ኢትዮጵያውያን ታሪክ ያላችሁ
ባህላችሁን ያዙ አጥብቃችሁ
ችቦውን አብሩት እንዳባቶቻችሁ
ምስጢር ስላለው ደስ ይበላችሁ

አባቶቻችን ያወረሱን
የቡሄን ትርጉም ያሳወቁን
እንድንጠብቀው ለእኛ የሰጡን
ይህን ነውና ያስረከቡን

ለድንግል ማርያም አሥራት የሆንሽ
ቅዱሳን ጻድቃን የሞሉብሽ
በረከታቸው ያደረብሽ
ሁሌም እንግዶች የሚያርፉብሽ
ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ነሽ

ለሐዋርያት የላከ መንፈስ
ዛሬም ለኢትዮጵያ ጸጋውን ያፍስስ
በበጎ ምግባር እንድንታነጽ
በቅን ልቦና በጥሩ መንፈስ
በረከተ ቡሄ ለሁላችን ይድረስ

ዓመት ዓውዳመት ድገም እና ዓመት ድገም እና
በጋሽዬ ቤ ድገም እና ዓመት ድገም እና
ያውርድ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ወርቅ ይፍሰስበት ድገም እና ዓመት ድገም እና

በእማምዬ ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይግባ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ማርና ወተት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይትረፍረፍ በእውነት ድገም እና ዓመት ድገም እና


እንዲሁ እንዳላችሁ በፍቅር አይለያችሁ
ላመቱ በሰላም በፍቅር ያድርሳችሁ
ክርስቶስ በቀኙ በፍቅር ያቁማችሁ
የመንግስቱ ወራሽ በፍቅር ያድርጋችሁ
እንዲሁ እንዳለን በፍቅር አይለየን
ለዓመቱ በሰላም በፍቅር ያድርሰን
አማኑኤል በቀኙ በፍቅር ያቁመን
የመንግስቱ ወራሽ በፍቅር ያድርገን


የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት
ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት
በሁሉም ቤት(2) ይግባ በረከት(2)

እንቁም በሃይማኖት ፀንተን በትጋት
የአስራት አገር የአበው ቀደምት
የቅዱሳን አባቶች ትውፊት
ይገባልና ልንጠብቅ በእውነት
ባህላችንን የአባቶች ትውፊት (3)

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ኧረ ምን ዘመን ደረስን 😭😭😭

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​ነሐሴ 12/12/2016 ዓ.ም

✝ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።

ዲያቆን፦ 1 ቆሮ 9÷17-ፍ.ም
ንፍቅ ዲያቆን፦ ይሁዳ 1÷8-14
ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋ፦ 24÷1-22

#ምስባክ ፦ መዝ 71፥1-3
እግዚኦ ኩነኔከ ሀቦ ለንጉስ
ወጽድቀከኒ ለወልደ ንጉሥ
ከመ ይኮንኖሙ ለሕዝብከ በጽድቅ

#ትርጉም ፦
አቤቱ ፍርድህን ለንጉስ ስጥ
ጽድቅክንም ለንጉስ ልጅ
ሕዝብክን በጽድቅ ችግረኛዎችክንም
በፍርድ ይዳኝ ዘንድ

#ወንጌል ፦ ማቴ 22÷1-15
#ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 የአርብ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን?

ወዳጆቼ ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት አይደለም፡፡ ግን ኃጢአት የሚሆንበት ሂደት አለው፡፡ አንድ ሰው በሕልሙ ሕልመ ሌሊት ቢመታው በዚህም ከሰውነቱ አባለ ዘር ይፈሳል፡፡ የአባለ ዘር መፍሰስ ኃጢአት የሚሆነው በራስ ፍቃድ ሲሆን ነው፡፡ ለምሳሌ ወዶ እና ፈቅዶ ግለ ወሲብ ሲፈጽም፣ የወሲብ ፊልም በማየት ከሚመጣ የሰውነት ሙቀት ጋር ዘር ሲፈስ፣ ከተቃራኒ ጾና ጋር በሚደረግ አልባል ንክኪና መሳሳም ነው፡፡

ሕልመ ሌሊት እላፊ በልቶ እና ጠጥቶ ከሚመጣ የሥጋ ፈተና ከሆነ ኃጢአት ይሆንበታል፡፡ ቅድስናን የሚያጎድል በመሆኑ የኃጢአተኝነት ስሜት እንዲጫነን ያደርገናል፡፡ ግን አንድ ሰውን ሕልመ ሌሊት ቢመታው ኃጢአት የሚሆንበት ሂደት አለ፡፡ ይህም አንድን ሰው ሕልመ ሌሊት ሲመታው ማለትም አጋንንቱ በሚያውቃት ሴት ተመስሎ በተኛበት ተገናኝቶት ዘሩን ቢያስፈስሰው የዚህ ችግር ሰለባ የሆነው ሰው በተፈጠረው ነገር ለምሳሌ ሴቷን እያሰበ፣ በሕልሙ ያየውን እያሰበ የሚደሰት፣ በሕልሙ የተፈጠረውን ግንኙነት በምልሰት እያየ ደስታን ካጣጣመ ኃጢአት ነው፡፡

ምክንያቱም ይሁዳ በመልእክቱ ‹‹እያለሙ ሥጋቸውን ያስደስታሉ›› ብሏልና፡፡ /ይሁ 1÷8/ በሕልማችን የተፈጠረውን ሕልመ ሌሊት በምልሰት በማየት እና በማሰብ መደሰት ሳይሆን መጸጸት መቆጨት ካልተሰማን ኃጢአት ነው የሚሆንብን፡፡

ወዳጆቼ የአጋንንት የረከሰ ሐሳብ በሕልማችን እየተከሰተ ሕልመ ሌሊት ሲያጋጥመን የተፈጠረውን ክስተት በጸጸት አጋንንቱን ልናሳፍረው ይገባል እንጂ የሆነውን እንደ በጎ ነገር ልንቀበለው አይገባም፡፡ ይህ እሳቤያችን ከፈጣሪ መለኮታዊ እርዳታ እንድናገኝ ይረዳናል፡፡ የማንቆጭ፣የማንጸጸት ከሆነ የዝንየት አጋንንት ይለምድና የሌሊት ደንበኛው ያደርገናል፡፡

እዚህ ላይ አንድ መረሳት የሌለበት ነገር አለ፡፡ አንዳንዴ ሕልመ ሌሊት (ዝንየት) በሰይጣን ፈተና ብቻ ላይከሰት ይችላል፡፡ ምናልባት ከምንጠቀማቸው ምግብና መጠጥ እንዲሁም ከሥጋ ባህርያችን ሊከሰት ይችላል፡፡ ምክንያቱም ሰውነታችን ሲስማማው በራሱ ጊዜ ፈሳሽ ሊወጣ ይችላል፡፡

ይህ ደግሞ ተፈጥሮ ነው፤ ምንም ማድረግ አይቻልም በጸጋ መቀበል ነው፡፡ ለምሳሌ ማታ ትኩስ ነገር ሙቅ፣ ሻይ አብዝተን የምንጠጣ ከሆነ በዘር ከረጢጣችን ያለው አባለ ዘር በራሱ ጊዜ ሊፈስ ይችላል፡፡

ተወዳጆች ሆይ በተአምረ ማርያም ላይ እንደሰማችሁት በሕልመ ሌሊት የተፈተነው ወጣት መነኩሴ ሕልመ ሌሊት ሳይሆን በሥጋው ምክንያት ሞት የመጣበት ስለመሰለው ‹‹የፍትወትን ጣዕም ዛሬ ቀምሰሻልና ወዮልሽ›› በማለት አምርሮ እራሱን ጠልቶ ወደ እመቤታችን አንብቶ ቢማጸናት እመቤታችን ተገልጣ ፈተናውን አርቃለት፣ በእጆችዋም ምልክት አድርጋለት ከሕልመ ሌሊት ተላቆ በሰጠችው ሐብተ ፈውስ ብዙ ድንቆችን አድርጎ ነበር፡፡

እኛም ወለላይቱ እመ ብርሃን በሕልመ ሌሊት የሚፈትነንን አጋንንት በጸሎቷ እንድታስርልን፣ እንድታርቅልን ከተማጸናት በእውነትም ይህን ፈተና፣ይህን መናጢ ታርቅልናለች፡፡

በቀጣይ 👉 ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል?

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​ነሐሴ 9/12/2016 ዓ.ም
 
✝ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።

ዲያቆን፦ ፊል 1÷12-24
ንፍቅ ደያቆን፦2 ዮሐ 1፥6-ፍ.ም
ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 15÷19-ፍ.ም
   
#የዕለቱ ምስባክ፦ መዝ 44 ÷ 10
ወትቀውም ንግስት በየማንከ።
በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወሁብርት።
ስምኢ ወለትየ ወርእዩ- ወአጽምኢ እዝነኪ።
                         
ወንጌል ፦ ዮሐ 10÷1-12
ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ(የእመቤታችን ቅዳሴ)

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​👉 በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን?
👉 ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን?
👉 ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል?
👉 ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው?
👉 የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው?


ተወዳጆች ሆይ መቼም ሱባኤ አይደል! በድካም ውስጥ ሆኜ ስለጻፍኩ የሐሳብ መደጋገም ካለ እያረማችሁ አንብቡት፡፡ በዚህ በሱባኤ የአጋንንት ውጊያ የሚበረታበት፣ ሕልመ ሌሊት ደግሞ በተደጋጋሚ የሚከሰትበት ነው፡፡ የበጎ ነገር ጠላት አጋንንት እኛን ከመንፈሳዊ አገልግሎት እና ተገልጎሎት ለማሰናከል እኛ ላይ ዓይኑን ፈጠጥ፣ ጥርሱን ገጠጥ የሚያደርግበት ጊዜ በአጽዋማት ወቅት ነው፡፡

ሕልመ ሌሊት (ዝንየት) የሚባለው አንድ ሰው ተኝቶ በሕልሙ ወንድን በሴት፣ ሴትን በወንድ አምሳል እንደ ገሐዱ በሚመስል ሩካቤ ሥጋ የሚታየንና ከሰውነታችን ፈሳሽ የሚወጣበት ሂደት ነው፡፡ ዝንየት የሚባለው ደግሞ በሕልመ ሌሊት የሚፈታተነን አጋንንት ነው፡፡ ሕልመ ሌሊት (ዝንየት) ወንድና ሴት ሳይል በማንኛውም ሰው ላይ በተለያየ ምክንያት ሊከሰት ይችላል፡፡

በሱባኤ ጊዜ ሕልመ ሌሊት ከመታን እለቱን ቤተ-ክርስትያን በተለይም ቤተ-መቅደስ መግባት፣ ቅዱስ ቁርባን መቀበል፣ ጸበል መጠመቅና መጠጣት፣ አንችልም፡፡ በማግስቱ ግን ሰውነታችንን ታጥበን፣ልብሳችንን ቀይረን ቤተ-ክርስትያን መግባት፣ ቅዱስ ቁርባን መቀበል፣ ጸበል መጠመቅና መጠጣት እንችላለ፡፡

እንደዚህ የምናደርገው አንደኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትእዛዝ ስለሆነ ነው፡፡ ሁለተኛ ቅድስት ለሆነችው እናት ቤተ-ክርስትያን ክብር ከመስጠት አንጻር ነው፡፡ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን በዘሌዋውያን ምዕራፍ 15÷2 ላይ ‹‹ማንም ሰው ከሥጋው ፈሳሽ ነገር ቢወጣ፣ስለሚወጣው ነገር ርኩስ ነው›› ይልና እዛው ቁጥር 16 ላይ ‹‹ማንም ሰው ዘር ከእርሱ ቢወጣ፣ገላውን ሁሉ በውኃ ይታጠባል፣እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው›› ይላል፡፡ /ዘሌ 15÷16/

ተወዳጆች ሆይ ልብ በሉ ‹‹ማንም ሰው›› ነው እንጂ ወንድ ሴት፣ወጣት አዛውንት አይልም፡፡ ይህ የሚያሳየው ኦርቶዶክስ የሆነ በየትኛው ጾታ እና የእድሜ ክልል ያለ ሁሉ ሕልመ ሌሊት ከመታው እለቱን ሳይሆን ማግስቱን ነው ቤተ-ክርስትያን መግባት የሚችለው፡፡ ‹‹እስከ ማታ›› የሚለው ሕልመ ሌሊት ሲመታን ለአንድ ቀን ብቻ የተከለከልን መሆናችን ያስረዳል፡፡ መቼም ሕልመ ሌሊት የሚመታን ማታ ወይም ሌሊት ነው፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው ማታ ወይም ሌሊት ሕልመ ሌሊት ከመታው ቀኑን ውሎ እስከ ማታ ነው የሚረክሰው፡፡ ከማታ በኃላ ንፁህ ይሆናል፡፡

ወዳጆቼ አንዳንዶች ‹‹ሕልመ ሌሊት ከተመታችሁ እስከ ሦስት ቀን ቤተ-ክርስትያን መግባት አይቻልም›› ይላሉ፡፡ ይህንም ‹‹ማነው ያለው›› ስትሉ የፈረደባቸው ‹‹አባቶች›› ናቸው ይላሉ፡፡ ቅዱስ መጽሐፍም አባቶቻችንም የሚነግሩን እስከ ሦስት ቀን ድረስ ቤተ-ክርስትያን የማንገበው ሩካቤ ሥጋ ስንፈጽም ብቻ ነው፡፡

ሕልመ ሌሊት መታን ማለት በቤት እና በቅጽረ ቤተ-ክርስትያን ሆኖ መጸለይ አይቻልም ማለት አይደለም፡፡ በሱባኤም ሆነን ሕልመ ሌሊት ቢመታን ሰውነታችን ታጥበት ሱባኤው መቀጠል እንጂ ማፍረስ የለብንም፡፡

በቀጣይ👉 ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን?
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​👉 በሱባኤ ወቅት የወር አበባ/ደመ ፅጌ/ ቢታየን ምን እናድርግ?
👉 ሴት በወር አበባ ጊዜ መጸለይ ትችላለች?
👉 በወር አበባ ጊዜ የሚከለከልስ ጸሎት አለ?


ሼር በማድረግ ለእህቶቻችን አድርሱ

ተወዳጆች ሆይ ሴት ልጅ በሱባኤ ወቅት የወር አበባ/ደመ ፅጌ/ ቢታያት ከሱባኤ የመውጣትና የመቆየቷ ነገር እንደ ገዳሙ ሥርዓት ይወሰናል፡፡ ከሱባኤ ትወጣለች ማለት ሱባኤን (አርምሞን) ትፈታለች፣ ተአቅቦዋን ትተዋለች ማለት ሳይሆን እስከምትነፃ ድረስ ገዳሙ ባዘጋጀው ቦታ ቆይታ መጨረስ ትችላለች፡፡

በሱባኤው አጋማሽ ላይ ወይንም መውጫው ሲቃረብ የወር አበባ ቢታያት ሱባኤውን ማቋረጥ ሳይሆን በጊዜያዊ ቦታ መጨረስ ይገባታል፡፡

ብዙዎች እህቶቻችን ሱባኤ የምንይዙት በድንገት ነው፡፡ ይህ ችግር እንዳይገጥማችሁ ሱባኤ ከመግባታችሁ በፊት ቀናችሁን ቆጥራችሁ አስተካክላችሁ ብትይዙ የበለጠ ትጠቀማላችሁ፡፡ ሰይጣን ያለጊዜው በወር አበባ ሊፈትናችሁ ስለሚችል ቀናችሁን እንደጨረሳችሁ ሱባኤ ብትይዙ ይመረጣል፡፡

በተለይ ዓይነ ጥላ ከዓይነ ጥላም ገርግር ዓይነ ጥላ ያለባቸውና መተት እና ድግምት የተደገመባቸው እህቶቻችን ያለ ጊዜና ያለ ቀኑ በሚመጣ የወረር አበባ በሱባኤ ወቅት ይፈተናሉ፡፡ ምስጋና ለእመቤታችን ይሁንና እመቤታችን ንፁህ አይደላችሁም በማለት ጸሎታችሁን ቸል ስለመትል የያዛችሁትን ሱባኤ ቀጥሉ፡፡ ምክንያቱም የእኛ ርኩሰት የእመቤታችንን ንፅህና ስለማያሳድፍ ጸሎታችንን ትሰማናለች፡፡

በቀጣይ 👉 ሴት በወር አበባ ጊዜ መጸለይ ትችላለች?

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​​​​​ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል ?

3ኛ/ ስንታበይ

አንዳንድ ጊዜ ምናልባት የዝሙት ሐሳብ ሲጠፋልን እራሳችንን እንደ ንፁህ በምንቆጥርበት ጊዜ ወይም ወደ ብቃት ደረጃ የደረስን አድርገን ስናስብ፤ ይህ መታበይ ነውና በትንሹ ጽድቃችን እራሳችንን ከፍ እንዳናደርግና ለራሳችን ልዩ የጽድቅ ቦታ እንዳንሰጥ እግዚአብሔር ሊገስጽን እንዲህ አይነት ፈተና ይመጣብናል፡፡

በመታበይ ውስጥ ያለን ሰዎች ሕልመ ሌሊት (ዝንየት) በሚመታን ሰዓት የኃጢአተኝነትና የመርከስ ስሜት ስለሚሰማን ራሳችንን ዝቅ በማድረግ ስለምንወቅስ እግዚአብሔር እንዲህ ዓይነት መንፈስ እንዲኖረን ስለሚሻ በዚህ መልኩ ሊያስተምረን ይችላል፡፡

በአንድ ወቅት ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችን በሰውነቱ ያደርገው የነበረውን ቅንዋት እንዲሰጠው ጠየቀው፡፡ ጌታም እጅግ ይወደው ስለነበረ ሰጠው፡፡ ዮሐንስም የጌታን ቅንዋት በሰውነቱ ቢያደርገው ፍፁም ድንግልና እንደ መላእክት ንፁህነት ተሰማው፡፡ ጌታም የተሰማውንና ያሰበውን ስላወቀ ወዳጄ ዮሐንስ ሆይ ‹‹ንጹህ ማነው?›› አለው፡፡

ዮሐንስም ‹‹ጌታ ሆይ! አንተ እና እኔ›› አለ፡፡ ጌታም ወዳጁ ዮሐንስ በመታበይ እንዳይወድቅበት ስላሰበ ሌሊት በሕልመ ሌሊት ፈተነው፡፡ ጠዋት ሲያገኘው ‹‹አሁንስ ንፁህ ማነው?›› አለው፡፡ ዮሐንስም ‹‹ጌታ ሆይ ንፁህ አንተ ብቻ ነህ’’ አለው፡፡ ዮሐንስም ሰው ምንም ቢመረጥ ንፅህና የባህሪ ገንዘቡ ለጌታችን ብቻ እንደሆነ በመመስከር እራሱን ዝቅ በማድረግ ተምሮበታል፡፡

በቀጣይ 👉 ሕልመ ሌሊት መፍትሔ ?

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​የቀጠለ

ኤልያስና ሙሴን ለምን አመጣቸው?
- በአንድ ወቅት ነቢዩ ሙሴ እግዚአብሔርን ‹‹ወለእመሰ ረከብኩ ሞገሰ በኀቤከ አስተርእየኒ ገሐደ ሊተ ወአእምር ወእርአይከ ከመ ይኩነኒ ርኪበ ሞገሰ በቅድሜከ ዮም›› ፣ በአንተ ዘንድ ባለሟልነትን ማግኘቴ እውነት ከሆነስ ፊት ለፊት ተገልጸህልኝ ልይህና በአንተ ዘንድ ባለሟልነትን ማግኘቴን ልወቀው› ሲል ጠይቆት ነበር፡፡

እግዚአብሔርም ‹… ትሬኢ ድኅሬየ ወገጽየሰ ኢያስተርኢ ለከ፣ ጀርባዬን ታያለህ ፊቴን ግን አታይም› ብሎት ነበር፡፡ /ዘጸ. 33.13 እና 23/ የዚህ ኃይለ ቃል ትርጓሜና ሐተታ በደብረ ታቦር ተፈጸመ፡፡ እንዲህ ማለቱ በአምስት ሺሕ አምስት መቶ ዘመን ሰው ሆኜ ሥጋ ለብሼ ኋላ በደብረ ታቦር እስክገለጽልህ ድረስ አንተ በመቃብር ተወስነህ ትኖራለህ ማለቱ ነበር፡፡ ይህን ማለቱ እንደሆነ የታወቀው ግን በደብረ ታቦር ሙሴን ከብሔረ ሙታን አምጥቶ ባቆመው ጊዜ ነበር፡፡

- ልዑል እግዚአብሔር ነቢዩ ኤልያስን ‹አንተሰ ትከውነኒ ስምዓ በደኃሪ መዋዕል፣ አንተ በኋለኛው ዘመን ምስክር ትሆነኛለህ› ብሎት ነበርና ይኸውም ኃይለ ቃል ኤልያስ ከብሔረ ሕያዋን መጥቶ ‹የእኔን የኤልያስን ጌታ ማን ኤልያስ ነው ይልሃል እግዚአ ኤልያስ፤ አምላከ ኤልያስ ይበሉህ እንጂ› ሲል በደብረ ታቦር ተፈጸመ፡፡ ታያለህ የተባለው ሙሴም አየ፣ ትመሰክራለህ የተባለው ኤልያስም መሰከረ፡፡

- በፊልጶስ ቂሳርያ ጌታ ሐዋርያትን ‹ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደሆነ ይሉታል?› ብሎ በጠየቃቸው ጥያቄ ሲመልሱ ሙሴ ነው ይሉሃል ፤ እንዲሁም የኃይል ስራህን ተመልክተው ኤልያስ ነህ ይሉሃል ብለው ነበርና ሙሴን ከመቃብር ፤ ኤልያስን ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ እግዚአ ሙሴ ፤ አምላከ ሙሴ ፤ እግዚአ ኤልያስ ፤ አምላከ ኤልያስ መሆኑን ለማስመስከር፡፡

ታቦር ተራራ የዛሬ ገጽታው ከሩቅ ዕይታ

ታቦር ተራራ የወንጌል ምሳሌ
1. ተራራ ሲወጡት ያደክማል፣ ከወጡት በኋላ ግን ጭንጫውን፣ ግጫውን ሲያሳይ ደስ ያሰኛል፡፡ ወንጌልም ሲማሯት ትከብዳለች በኋላ ግን ጽድቅን እና ኃጢአትን ለይታ ስታሳውቅ ደስ ታሰኛለች፡፡

ታቦር ተራራ የቤተክርስቲያን ምሳሌ
1. በታቦር ተራራ ከብሉይ ኪዳን ነቢያት ኤልያስና ሙሴን፣ ከሐዲስ ኪዳን ሦስቱን ሐዋርያት እንደተገኙ በቤተክርስቲያን ብሉይ ከሐዲስ እንዲነገር ለማጠየቅ ፤ ሐዋርያት የሰበኩት ወንጌል አስቀድመው ነቢያት በምሳሌና በትንቢት የተናገሩት እንደሆነ ሲያስረዳ ነው ፡፡ ነቢያት በቀየሱ ሐዋርያት ገሰገሱ እንዲል ‹በሐዋርያት በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል›ኤፌ 2፣20

2. በታቦር ተራራ ከመዓስባን (ባለትዳር) ሙሴን ከደናግል ደግሞ ኤልያስ እንደተገኙ በቤተክርስቲያን በድንግልና የሚኖሩ መናንያን መነኮሳትም፣ በሕግ በሥርዓት የሚኖሩ ባለትዳሮችም ይገኛሉና፡፡

ታቦር ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ
1. ተራራውን ችግር እንዲወጡት መንግሥተ ሰማያትንም በብዙ መከራ የምትገኝ ናትና ‹እስመ በብዙኅ ጻማ ወድካም ኀለወነ ንባአ ለመንግሥተ እግዚአብሔር› ‹ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል› ሐዋ 14፡22

2. በታቦር ተራራ የብሉይ ኪዳን ነቢያት፣ ከሐዲስ ኪዳን ሐዋርያት እንደተገኙ መንግሥተ ሰማያትን ነቢያትም፣ ሐዋርያትም አንድ ሆነው እንደሚወርሷት ያጠይቃል፡፡

3. በታቦር ተራራ ከመዓስባን ሙሴ፣ ከደናግል ደግሞ ኤልያስ እንደተገኙ መንግሥተ ሰማያትን ደናግልም መዓስባንም በአንድ ላይ እንዲወርሷት ያጠይቃል፡፡

4. በታቦር ተራራ ሞተው ከተቀበሩት መካከል ሙሴን አመጣ፣ በብሔረ ሕያዋን ካሉት ደግሞ ኤልያስን አመጣ መንግሥተ ሰማያትንም ሞተው የተቀበሩትም በብሔረ ሕያዋን ያሉትም በአንድነት እንደሚወርሷት ያጠይቃል፡፡

በአጠቃላይ ታቦር ተራራ፡-
1. የክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት የተመሠከረበት፣
2. የምስጢረ ሥላሴ ትምህርት የተሰጠበት
3. ፈጣሪ ከቅዱሳን ሰዎቹ ጋር የተገኘበት
4. በልበ ሐዋርያት የነበረ ሰይጣን ድል የተደረገበት
5. የሐዋርያት በተለይም የሦስቱ ባለሟልነት የተገለጠበት፣
6. አሉባልታና ተራ ወሬ የከሸፈበት፣
7. የቅዱሳንን ክብር ለሚያናንቁ ተራራም እንኳን ‹ቅዱስ› እንደሚባል የተማሩበት፣
8. የብሔረ ሕያዋን መኖር የተመሰከበረበት
9. የትንሣኤ ሙታን ዋስትና የተገለጠበት የክብር ሰገነት፣ የምስጢረ መቅደስ፣ ታላቅ ትምህርት ቤትም ጭምር ነው፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታ ሆይ በዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው ማለቱ
1. የኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት በሚታመንበት፣ ዋልድ ዋሕድ በምትለው ሃይማኖት መኖር ለእኛ መልካም ነው፡፡
2. መድኃኔዓለም ከቅዱሳን ወዳጆቹ ጋር በምትገኝበት አንተ እያበላኸን እየፈወስከን፣ ሙሴ ደመና እየጋረደ መና እያወረደ ባሕር እየከፈለ፣ ኤልያስ ሰማይ እየለጐመ እሳት እያዘነመ ዝናም እያቆመ በዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው፡፡
3. በልበ ሐዋርያት ያደረ ሰይጣን ድል በተደረገበት በታቦር ተራራ ምሳሌ አንድም በወንጌል ሕይወት፣ አንድም በቤተ ክርስቲያን መኖር ለእኛ መልካም ነው፡፡

ፈጣሪያችን እግዚአብሔር እስከመጨረሻዋ ሕቅታ (እስትንፋስ) በታቦር ተራራ በተመሰለች ቤተክርስቲያን በሃይማኖታችን ጸንተን የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች የስሙ ቀዳሾች እንድንሆን የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፡፡

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 የሰኞ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​​​#ቡሄ

ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡

#ጅራፍ

በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡

የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡

የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን #በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል፡፡

#ችቦ

ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡

የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዘዞ ችቦ በ13 ምሽት ይበራል ፣ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና ፡፡

#ሙልሙል

በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም፡፡

ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ….” ይላሉ፡፡

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡

ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡

አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡

አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው፡፡ ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል።

ከዚም ጋር ተያይዞ ሰንበት ት/ት ቤታችን ለበረካታ ዓመታት ሲወርድ የመጣውን የዝማሬ ሥርዓት ለአጥብያው ምእምን በየቤቱ በመሄድ የብሄን ዝማሬ ከነሥርዓቱ በመዘመር አገልግሎት ይሰጣል ፤የደብር ታቦርን በዓል በተመለከትም የወረቀት ጽሑፎችን ይበትናል በዝማሬ መኃል ያድላል፡፡

ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው፡፡ በተለይ ወጣቱ ክፍል ይህንን አውቀን ተረድተን ለቀሪው ትውልድ ማስተላለፋ እንችል ዘንድ ከክፉ ጠላት ከሰይጣን ፈተና፣ በሽታ ከመሳሰሉት ችግሮች ለመዳን ወደ ተራራዋ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመሸሽ ከክፉ ነገሮች ሁሉ ማምለጥ ይቻላል፡፡

በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር የሚጠለሉ ሁሉ ዕድሜያቸው ይረዝማል፡፡ አስተዋዮችም ይሆናሉ ሁሉን ማየትና የሚጠቅማቸውን መምረጥ ይችላሉ በሥነ-ምግባር የታነፁ አገርንና ወገንን የሚጠቅሙ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በመጠጋት ከክፉ ሁሉ የሚያመልጡ ይሆናሉ ለዚህም የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

#በስመ_ዚአከ

በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ ዮም /2/
ታቦር ወአርሞንዔም /2/

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

#ሃሌ_ሉያ

ሃሌ ሉያ አንተ ሰው ሆይ
ቡሄ መድረሱን ሰምተሀል ወይ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

#ቡሄ_በሉ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 የቅዳሜ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል

2ኛ/ የዝሙት መንፈስ ካለብን

ተወዳጆች ሆይ የዝሙት አጋንንት ያው አጋንንት ቢሆንም ከሌሎቹ አጋንንት የሚለው በተልዕኮው ነው፡፡ የዝሙት አጋንንት ሰዎችን በዝሙት ማጥመድና መጣል፣ከቅድስና ሕይወት ሰዎችን ማግለል ነው፡፡ የዝሙት መንፈስ ካለብን ይበልጥ ሕልመ ሌሊት (ዝንየት) ሊፈትነን ይችላል፡፡

የዝሙት መንፈስ ማለት በልቦናችንና በአእምሮአችን ዝሙትን በማሰብና ሲከፋም ወደ መፈጸም የሚያደርሰንና ከፈጣሪ የሚያጣላን እርኩስ መንፈስ ነው፡፡ የዝሙት መንፈስ በተለይ ባላገቡ ወጣቶች ላይ ይጸናል፡፡ አሁን አሁን ግን ያገቡትም የዚህ መንፈስ ተጠቂ እየሆኑ ነው፡፡

ወዳጆቼ ወጣቱ በዝሙት መንፈስ በተለያየ መንገድ ሊጠቃ ይችላል፡፡ አንዱ ተፈጥሮአችንን በመጠቀም ነው፡፡ ይህ ማለት ወደ እሳትነት ዕድሜ ክልል በምንገባበት ጊዜ የሥጋ ባህሪያችንን በመጠቀም የዝሙት መንፈስ ሊጠናወተን ይችላል፡፡

ይህም የሚሆነው ወንዶች ዓይናችን ወደ ሴቶች፣ ሴቶችም አይናችን ወደ ወንዶች ማማተር፣ በልዩ ፈቃድ መመኘትና ልባችንም ፈቃደ ሥጋን ለመፈጸም በሚከጅልበት ሰዓት ውሻ በቀደደው አንዲሉ የዝሙት መንፈስ ወደ ውስጣችን ይገባል፡፡

በዚህ መልኩ ውስጣችን ገብቶ ለዓመታት ከተቀመጠ በኋላ በተደጋጋሚ ቤተ-ክርስትያን ለመሄድ በተዘጋጀንበት ጊዜና በሱባኤ ላይ ፈተናውን በግልፅ ይጀምራል፡፡ ሳናውቅ በድብቅ ገየባው የዝሙት መንፈስ በግልጽ ይፈትነናል፡፡

ሌላው በዓለማዊ ሕይወት በምንኖርበት ጊዜ የተለያዩ ዝሙት ተስቃሽ ፊልሞችን በምንመለከትበትና መጽሐፍቶችን በምናነብበት ጊዜ መንፈሱ ሳናውቀው ወደ ውስጣችን ይገባና፤ በኋላ ሁሉን ትተን በመንፈሳዊነት ወደ ቤተ-ክርስትያን መገስገስ ስንጀምር በሕልመ ሌሊት (በዝንየት) በመፈተን ከቤተ-ክርስትያን ያስቀረናል፣ በፈተናም ያስመርረናል፡፡

ውድ አንባቢያን ፊልም ማየትና መጽሐፍት ማንበብ ኃጢኃት ባይሆንም የምናየውን ፊልምና የምናነበውን መጽሐፍ መምረጥ ይገባል፡፡ ጸያፍ እና ሥጋና ነፍስን የሚያሳድፍ ፊልም/ቨዲዮ/ ከሆነ ድብን ያለ ኃጢአት ነው፡፡

3ኛ/ ስንታበይ
ይቀጥላል

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል?

ተወዳጆች ሆይ ሕልመ ሌሊት ከሚከሰትብን ምክንያቶች ዋና ዋናዎችን ከዚህ በታች እናያለን፡፡

1ኛ/ በአጋንንት ይከሰታል

በጣም የሚገርመው በሕልመ ሌሊት (ዝንየት) የተፈተናችሁ እስቲ ልብ በሉ፡፡ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ሳትገቡ በዓለም ሳላችሁ ብዙም አይከሰትም፡፡ ቢከሰትም ለአቅመ-አዳምና ለአቅመ ሔዋን በደረስንበት ወቅት በሥጋ ባህሪያችን ይከሰታል፡፡ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ገብተን በተግባር መኖር ስንጀምር ሕልመ ሌሊት (ዝንየት) በተደጋጋሚ ይመታናል፡፡ በተለይ ወንዶችን ቋሚ ደንበኞች ያደርገናል፡፡

ወዳጆቼ አጋንንት ጸበል እንዳንጠመቅ፣ ቤተ ክርስትያን ገብተን ጸሎት እንዳናደርስ፣ ከመለኮታዊው ማዕድ እንዳንቋደስ /ቅዱስ ቁርባን እንዳንቀበል/ ከሱባኤ ዋሻ ለማስወጣት ከሚጠቀምበት ዋንኛ ማሰናከያ መፈተኛው ሕልመ ሌሊት (ዝንየት) ነው፡፡ አባቶቻችን ‹‹ተጻቦዖ›› ይሉታል ‹‹ተጻብዖ›› ማለት ቃሉ የግዕዝ ሲሆን መጣላትን ያመለክታል፡፡

እኛ ሀገር ሰላም ብለን በተኛንበት ሰይጣን በማናየው መልኩ በሕልመ ሌሊት ስለሚጣባንና እኛ የማንፈልገውን ፈቃደ ሥጋ በማሳየት ፈትኖን ከሰውነታችን ፈሳሽ እንዲወጣ ስለሚያደርግ ‹‹ተጻብዖ›› ብለውታል፡፡ በእውነት ከዚህ በላይ ምን ጸብ አለ? ሰው የማይገላግለን፣ሰው የማይደርስልን ፣ጮኸን የማናመልጠው ጠብ፡፡

ተወዳጆች ሆይ በሱባኤ ላይ ሆነን አጋንንት በሕልመ ሌሊት ቢፈትነን ሱባኤያችን አይፋረስም፡፡ ሕልመ ሌሊት ስለመታን ሱባኤያችን አይቋረጥም፡፡ ምናልባት በዋሻ ውስጥ ሱባኤውን የያዝን ከሆንን ለአንድ ቀን ከደጅ እንሆናለን አልያም ሰውነታችንን ታጥበን ተመልሰን ልንገባ እንችላለን፡፡ ይህን የሚወስነው የገዳሙ የአባቶች ሥርዓት ነው፡፡

ስለዚህ በሱባኤ ጊዜ በሕልመ ሌሊት በተደጋጋሚ ብንፈተን ሊደንቀን አይገባም፡፡ ይልቁንም ከአጋንንቱ ጋር በስውርና በገሃድ እየተዋጋን ስለሆነ ደስ ሊለንና በጸሎት ልንዋጋው ይገባል፡፡

ሰይጣን ሕልመ ሌሊትን (ዝንየትን) ለጸሎት ማስታጎያነት ይጠቀምበታል፡፡ ሌሊት ጸሎት ካስለመድን ከመነሳታችን በፊት ሕልመ ሌሊት ይመታናል፡፡ ከዛ በኋላ ተነስተን መጸለይ ይከብደናል፡፡ ከሰውነታችን ፈሳሽ ስለወጣ፤ ጥሩ ስሜት ስለማይሰማን ‹‹ጠዋት ታጥቤ እጸልያለሁ›› በማለት ጸሎታችንን እናስተጓጉላለን፡፡

ለዚህ መፍትሄው በፍፁም ጸሎታችንን አለመተው ነው፡፡ በዚያ በሌሊት ሙሉ ሰውነትን መታጠብ ስለሚከብድ ከቻልን ፈሳሽ የወጣበትን እርጥበት የተሰማንን ቦታ ታጥቦ መጸለይ፡፡ ሴቶችም አንቀጸ ሥጋችሁን አሊያም እጃችሁን በመታጠብ ጸሎታችሁን መቀጠል፡፡

ሰይጣን የራሳችንን ሰውነት እየተጠየፍን ጸሎት እንድንተው ነውና የሚሻው በምንም ምክንያት ጸሎት መተው የለብንም፡፡ እንኳን በሕልመ ሌሊት (ዝንየት) ተመትተን ቀርቶ በጥሩ ሰዓት ማናችውንም ንፁሆች አይደለንም፡፡ የሚገርመው የማያፍረው ሰይጣን በሕልመ ሌሊት (ዝንየት) ቤተክርስትያን ገብቶ ይፈትነናል ማለት ሳይሆን፤ እኛ ላይ ያለው አጋንንት በስውር ለዚህ ፈተና ሊዳርገን ይችላል፡፡

ቤተ ክርስትያን ለንግሥ አዳር ስንሄድ አባቶች አትተኙ የሚሉን አንድም ሕልመ ሌሊት (ዝንየት) ሊመታንና ሊፈትነን ስለሚችል ነው፡፡ ለአንድ ቀን ሌሊት ቤተ-ክርስትያን ጊዜያችንን በጸሎት ብናሳልፍ ካልሆነ ማህሌቱንና ሰዓታቱን ብንሰማ ይበልጥ ጥቅም ስላለው አለመተኛቱ ይመረጣል፡፡

2ኛ/ የዝሙት መንፈስ ካለብን
ይቀጥላል

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ነገረ ማርያም ክፍል ፪
እነሆ🤲🤲🤲


ክፍል ፩ ያላዳመጣችሁ ካላችሁ በኮመንት አሳውቁን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​ነሐሴ 10/12/2016 ዓ.ም

✝ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።

ዲያቆን፦ ዕብ 12÷22-ፍ.ም
ንፍቅ ዲያቆን፦1 ጴጥ 1፥6-13
ንፍቅ ካህን፦ ግብረ ሐዋርያት፦ 4÷31-ፍ.ም
ምስባክ ፦ መዝ 73፥2-4
ተዘከር ማኅበረከ ዘአቅድምከ ፈጢረ
ወአድኀንከ በትረ ርስትከ
ደብረ ጽዮን ዘኀደርከ ውስቴታ

ትርጉም
አስቀድመህ የፈጠርካትን ማኅበርህን
የተቤዤሃትንም የርስትህን በትር
በርስዋ ያደርህባትን የጽዮንን ተኣኣ አስብ፡፡

ወንጌል ፦ ሉቃ 16÷9-19
ቅዳሴ ፦ ዘእግዝእትነ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 የሐሙስ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 የረቡዕ ውዳሴ ማርያም አንድምታ
🎙 ሊቀ ጉባኤ ጌታሁን

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…
Подписаться на канал