ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ሕማማት ክፍል 3

👉 የይሁዳ እግሮች
ጸሐፊ ፦ ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
🎤 ተራኩ ፦ ኢዮብ ዮናስ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ሕማማት ክፍል 1

👉 የመጀመሪያው ቁስል! አሳልፎ የሚሰጥህ ማነው?
ጸሐፊ ፦ ዲ/ሄኖክ ኃይሌ
🎤 ተራኩ ፦ ኢዮብ ዮናስ

#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 ሆሣዕና
👉 የዐብይ ጾም ስምንተኛ ሳምንት
🎤 በመ/ር ዶ/ር ዘበነ ለማ

#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

20/08/16 ዓ.ም
መዝሙር ዘሆሳዕና
"ወእንዘ ሰሙን"

✝ በዕለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚሰበክ ምስባክ።

ዲ/ን - ዕብ 9÷11- ፍ ም
ን/ዲ - 1ጴጥ 4÷1-12
ን/ካ - ግብ፡ሐዋ 28÷11-ፍ ም

የዕለቱ_ምስባክ - መዝ 8÷2
እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ
በእንተ ጸላኢ
ከመ ትንሥቶ ለጸላኢ ወለገፋዒ

ትርጒም
ጠላትን ለማሳፈር ቂመኛንና ግፈኛንም ለማጥፋት ከህፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ::

ወንጌል፦ ዮሐ 5÷11-31
ቅዳሴ: ዘጎርጎርዮስ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

#መዝ 49÷1
እምሥራቀ ፀሐይ እስከነዓረብ
ወእምጽዮን ሥነ ስብሐቲሁ
እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

#መዝ 80÷3
ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሠርቅ
በዕምርት ዕለት በዓልነ
እስመ ሥርዓቱ ለእስራኤል ውእቱ

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ሆሳዕና በምዕዋድ በዑደት ጊዜ በቤተ መቅደስ ውስጥ አየተዞረ (በመቅደስ; በምስራቅ;በምዕራብ; በሰሜን; በደቡብ)የሚሰበኩ ምስባኮች

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ሆሣዕና

ሆሣዕና /6/
ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት

በዘማሪት ቤዛ እና ቤቴል
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

እያለፈ ነው ዘመኔ

እያለፈ ነው ዘመኔ ትእዛዙን ሳልፈጽም
ወየው ለእኔ/2/ 
በጠራኝ ጊዜ ምን እላለሁ
ና ብሎ ወደእኔ/2/ 

በወጣትነቴ ሳልሠራ እያየሁ አለፈኝ
ብዙ አዝመራ/2/ 
ከእንግዲህ በመሥራት ጌታ ሆይ
ልኑር ከአንተ ጋራ/2/ 

የማስብበት በየለእቱ ንጹሕ ልብን
ስጠኝ አቤቱ /2/ 
ከትእዛዝህ ውጪ በመሆን
እዳልቀር በከንቱ /2/ 

እንደየሥራው ለመስጠት
በግርማ መንግሥቱ ሲመጣ/2/ 
ማን ይሆን የሚቆም ከፊቱ
ፊተናን የወጣ/2/ 

እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ
እየተማራችሁ ከቃሉ/2/ 
ይመጣሉና በእርሱ ስም
አምላክ ነን የሚሉ/2/ 

ትእግሥትን በመያዝ ሁላችሁ
እስከመጨረሻው ጠንክሩ/2/ 
ያን ጊዜ ይሆናል በእርሱ ዘንድ
የማዳን ተግባሩ/2/ 

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

መች ይረሳል
የበገና መዝሙር

መች ይረሳል የዋለልን ውለታ
ቸርነቱ እፁብ ፍቅር የጌታ
የታተመው በልባችን ፅላት
ሞትን ገድሎ የሠጠንን ህይወት

በጥፋቱ ቢወጣ አዳም ከገነት
ቃል ገባለት ዳግም ሊሰጠው ህይወት
ህያው ጌታ አምላክ ፈጣሪ ሳለ
ስለ ቃሉ በእፀ መስቀል ላይ ዋለ
አዝ
በአይሁድ እጅ በፅኑ ተንገላታ
የፍቅር አባት ክርስቶስ የእኛ ጌታ
ሥጋው ደክሞ ቅዱስ ደሙ ፈሰሰ
እዳችንን በሞቱ ደመሠሠ
አዝ
ስንጠላው እርሱ አብዝቶ ወደደን
ስለ ፍቅሩ ሞትን ገድሎ አዳነን
ባርነትን ኃጢአትን ከኛ ጥሎ
ነፃ አወጣን በመስቀል ላይ ተሰቅሎ
አዝ
ሰላማችን የድንግል ማርያም ፍሬ
ይገባዋል ምስጋና ዝማሬ
ስለ ፍቅሩ ስላረገልን ሁሉ
ተቀኙለት ፍጥረታት ዝም አትበሉ

መምህር አቤል ተስፋዬ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​​​ኒቆዲሞስ

👉 የዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት
🎤 በመምህር ቀሲስ ዶ/ር ዘበነ ለማ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​​​​​ኒቆዲሞስ - የዐብይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት።

''እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው። (ዮሐ 3:3-6)

ጌታችን ወደዚህ ምድር መጥቶ የምስራቹን ቃል ሲያውጅ እስራኤላውያን የተቀበሉት በተደበላለቀ ስሜት ነበር። በአንድ በኩል ሕዝቡ ለብዙ ዘመናት በባርነት ሲገዛ ስለነበር ከሮማውያን ቅኝ ግዛት ነጻ የሚያወጣቸው መሲህ ይፈልጋሉ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ሕዝቡ ለብዙ ዘመናት በባርነት ቀንበር ስለደከመ ተስፋ በመቁረጥ ተዳክሞ ነበር፡፡ መሲህ ቢመጣ እንኳ ይመጣል ብለው የሚጠብቁት ጦር ይዞ ሰራዊት አስከትሎ ነው ብለው ያምኑ ነበር፡፡ ስለዚህም ነው ክርስቶስን መሲህ ነኝ ብሎ ሲመጣ ለመቀበል ፈቃደኞች አልነበሩም፡፡

ምክንያቱ ደግሞ ጦር ሳይዝ ሰራዊት ሳያስከትል እንዲሁ ባዶ እጁን አርነት ላወጣችሁ መጥቻለሁ እያለ ደጋግሞ ተናግሯልና ነው፡፡ ምንም እንኳ አብዛኛው እስራኤላዊ የክርስቶስን መሲህነት ቢጠራጠርና ባይቀበለውም፣ በፍጹም እምነት እስከ መጨረሻው የተከተሉትም ነበሩ፡፡

ለዚህም ትልቅ ማሳያ የሚሆነን ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አይሁዳዊ ነው፡፡

ቅድስት ቤተክርስቲያንም ይህን ታላቅ ሰው ለማዘከር የዐቢይን ጾም ሰባተኛ እሁድ በእርሱ ስም ሰይማ ታከብረዋለች። ተከታዮቿ ምዕመናንም የእርሱን አሰረ ፍኖት እንዲከተሉ ትመክራለች ታስተምራለችም፡፡

=> ኒቆዲሞስ ማነው?

፩. ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ ነው 《ዮሐ 3-1》
፪. ኒቆዲሞስ የአይሁድ አለቃ ነው《ዮሐ 3-1》
፫. ኒቆዲሞስ መምህረ እስራኤል ነው《ዮሐ 3-10》
፬. ኒቆዲሞስ ምሁረ ኦሪት ነው 《ዮሐ 7-51》

=> ኒቆዲሞስ ምን አደረገ?

ለምስጢረ ጥምቀት መገለጥ ምክንያት ሆነ 《ዮሐ 3:1-21)
አዋቂ ነን የሚሉትን አሳፈራቸው 《ዮሐ 7-51》
ጌታን ለመገነዝ በቃ 《ዮሐ 19-38》

=> ከኒቆዲሞስ ምን እንማር?
አትኅቶ ርእስ ጎደሎን ማወቅ የእውነት ምስክር《ስምዐ ጽድቅ》መሆን ትግሃ ሌሊት እስከ መጨረሻ መጽናት በአጠቃላይ ከኒቆዲሞስ ህይወት ብዙ ቁምነገሮችን እንማራለን፡፡

የኒቆዲሞስ በሌሊት ገስግሶ መምጣት ለምስጢረ ጥምቀት ትምህርት መገለጥ ምክንያት እንደሆነ ሁሉ በቅዳሴው በኪዳኑ በሰዓታቱ በማኅሌቱ መገኘትና መሳተፍ ረቂቅ የሆነው ሰማያዊ ምሥጢር ፍንትው ብሎ አንዲገለጥልን ምክንያት ነውና በምሥጢራት በመሳተፍ ራስን ዝቅ በማድረግ ለታላቅ ክብር እንድንበቃ የእርሱ መልካም ፈቃድ ይሁንልን፡፡

የዕለቱ ምስባክ፦ "ሐወጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ። አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመፃ በላዕልየ። ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመ ሕያው"። መዝ17፥3-4። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ3፥1-12። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።


ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

🔰የዘማሪት የትምወርቅ ሙላት የበገና መዝሙሮች

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

✞ ቸር አገልጋይ ማነው? ✞

ቸር አገልጋይ ማነው ለንጉሥ የታመነ
መክሊቱን ያልቀበረ አትርፎ የከበረ (፪)

ባለ አምስቱ መክሊት መልካም ያደረገው
በመውጣት በመውረድ አትርፎ መጥቶ ነው
በጥቂቱ ታምኖ በብዙ የተሾመው
ባለ አምስቱ መክሊት ሊቀ ጳጳሱ ነው
አዝ
ሳይሰለች የተጋ ባለሁለት መክሊት
የታመነ እረኛ በፍቅርና በእምነት
ግባ የተባለው ወደ ጌታው ደስታ
አጥምቆ ያቆርባል ካህኑ የጌታ
አዝ
ለሚበልጠው ጸጋ ተጠርቶ የነበረ
መክሊቱን ደብቆ ቆፍሮ የቀበረ
ሰነፍ ባርያ ተብሎ ወደ ፍርድ ተጣለ
ማኔ ቴቄል ፋሬስ በአምላክ ፊት ቀለለ
አዝ
ፈቃድህን ማድረግ ነፍሱ ለምትወደው
ወንጌልህን መግለፅ የየዕለት ግብሩ ነው
ህግህ ለዘለላም ተጽፎ ይኖራል
በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህ ይነገራል

ዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​​​​​የዐብይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት ገብርኄር ይባላል፡፡

ገብርኄር ማለት ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ስለ ታማኝ አገልጋይ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ስንኖር ለፈጣሪያችን ያለንን ታማኝነትና የምናገኘውን ዋጋ በመዋዕለ ሥጋዌው
አስተምሯል፡፡

ቅዱስ ያሬድ ለዜማ መክፈያነት የዐብይ ጾምን ሳምንታትን ሲከፍል ገብርኄርን ተጠቅሟልና እኛም ስለ ገብር ሄር ጥቂት እንበል፡፡ ልዑል እግዚአብሔር አምላካችን በነቢዩ አንደበት አድሮ፤ “እከሥት በምሳሌ አፉየ፤ ወእነግር አምሳለ ዘእምትካት፤ አንደበቴን /ነገሬን/ በምሳሌ እገልጣለሁ፤ ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ
ታሪክና ምሳሌ እናገራለሁ” አለ፡፡

ይህም ማለት ወንጌልን በምሳሌ አስተምራለሁ፤ በመልከ ጼዴቅ ዘመን አስቀድማ የተሠራችና ታይታ የጠፋችውን ወንጌልን እናገራለሁ፡፡ ይህን ታላቅ ምሥጢር ሐዋርያው ሲያብራራ “ከመ በአሚን ያጸድቆሙ እግዚአብሔር ለአሕዛብ አቅደመ አሰፍዎቶ ለአብርሃም ከመ ቦቱ ይትባረኩ ኲሎሙ አሕዛብ ፤ በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ” ብሏል፡፡ /ገላ. ፫፥፰፣ መዝ. ፸፯፥፪

በዚሁ መሠረት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያትን ለልዩ ልዩ ወገኖች በልዩ ልዩ ምሳሌ አስተምሯል፤ ከላይ በተገለጠው ኃይለ ቃል መነሻነት ሁለት ምሳሌያትና አንድ ቃለ ትንቢት ቀርበዋል፡፡ ከምሳሌያቱ
የመጀመሪያው በዐሥሩ ደናግል አንጻር የቀረበው ምሥጢር ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ ወጥተው ወርደው ነግደው ያተርፉበት ዘንድ ገንዘቡን ስለሰጠ አንድ ነጋዴ የሚናገረው ነው፡፡

የትንቢቱ ምሥጢራዊ ይዘት የሚያስረዳውም ስለ ኅልቀተ ዓለም አይቀሬነት ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ ዕትማችን ወጥተው ወርደው ነግደው እንዲያተርፉበት ከጌታቸው የተሰጣቸውን መክሊት ስለተቀበሉት አገልጋዮች ሕይወት እንመለከታለን፡፡ ፈጣሪያችን አእምሮውን ለብዎውን /ማስተዋሉን/ ያድለን፡፡

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማራቸው ምሳሌያዊ ትምህርቶች በቅዱስ መጽሐፋችን በሰፊው ተጽፈው እናገኛለን፡፡ የእነዚህ ትምህርታዊ ምሳሌዎች መሠረታዊ ሀሳብና ዓላማም የእግዚአብሔርን መንግሥት የምናገኝበትን የታማኝነትን ሥራ እንዴት መሥራት እንደሚገባንና መሥራትም እንደምንችል ማስተማር ነው፡፡

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለመንግሥተ ሰማያት ምሥጢር ያስተማራቸው ብዙ ምሳሌዎች ያሉ ሲሆን ከእነዚህ ብዙ ምሳሌያዊ ትምህርቶች መካከልም እንዲያተርፉበት መክሊት ስለተሰጣቸውና ስለተመሰገኑት መልካም አገልጋዮች፣ እንዲሁም መክሊቱን በመቅበሩ ምክንያት በጌታው ስለተወቀሰውና ፍርድን ስለተቀበለው ሰነፍ ሰው ታሪክ፣ የታሪኩም ምሥጢር ምን እንደሚመስል የተጻፈው ትምህርት ነው።

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን ምሳሌ የተናገረው /ያስተማረው/ በሚከተለው መልኩ ነበር፤ ‹‹ወደ ሌላ ሀገር የሚሔድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ እንደሰጣቸው እንዲሁ ይሆናልና ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ ሀገር ወዲያውኑ ሔደ፡፡

አምስት መክሊትም የተቀበለው ሔዶ ነገደበት ሌላም አምስት አተረፈ፣ እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ፣ አንድ የተቀበለው ግን ሔዶ ምድርን ቆፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ፡፡

ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቆጣጠራቸው፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና ሌላ አምስት መክሊት አስረክቦ፡- ጌታ ሆይ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ ሌላ አምስት መክሊት አተረፍሁበት አለ፡፡
ጌታውም፡- መልካም አንተ በጎ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡

ሁለት መክሊት የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፡- ጌታ ሆይ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፡፡ እነሆ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍሁበት አለ፡፡
ጌታውም፡- መልካም አንተ በጎ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው።

አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፡- ጌታ ሆይ ካልዘራህበት የምታጭድ ካልበተንህበትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ፈራሁም ሔጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት ፤ እነሆ መክሊትህ አለልህ አለው፡፡
ጌታውም መልሶ እንዲህ አለው፡- አንተ ክፉና ሐሰተኛ ባሪያ ካልዘራሁበት እንዳጭድ ካልበተንሁበትም እንድሰበስብ ታውቃለህን? ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር።

እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር፡፡ ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት ዐሥር መክሊትም ላለው ስጡት። ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል። ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል፡፡

የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል የሚል ነው፡፡

መክሊት ጥንት የክብደት መለኪያ ነበር:: አንድ መክሊት 30 ኪሎ ግራም ያህል ነው፡፡ በዚህ ምሳሌ ላይ እንደተገለጸውም መክሊት የሚለው ቃል ገንዘብን ያመለክታል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምሳሌ ውስጥ እርሱን የምናገለግል ሁላችን እንደየዓቅማችን ማድረግ የሚገባንን መንፈሳዊ የአገልግሎት ሥራንና በአገልግሎታችን ውጤታማ በመሆናችንም ከእርሱ የምናገኘውን ዘለዓለማዊ ክብርና ዋጋን እንዲሁም መሥራት የሚገባንን ባለማድረጋችንም ምክንያት የሚገጥመንን መለኮታዊ ቅጣትን አመልክቶናል፡፡

በዚህ ምሳሌ ውስጥ ባለ አምስት የተባለው በቂና ፍጹም ትምህርት ተምሮ ሌላውን መክሮ አስተምሮ ራሱን አስመስሎ የተካ ያወጣ ነው፡፡

በተመሳሳይም ባለ ሁለት የተባለው እንደ መጀመሪያው ሁሉ ተምሮ ሌላውን መክሮ አስተምሮ ራሱን አስመስሎ ያወጣ ሲሆን ባለ አንድ የተባለው ደግሞ ተምሮ ሳያስተምር የቀረ በስንፍና በቸልተኝነት በማን አለብኝነት ሕይወት ተገድቦ የቀረ ሰው ነው፡፡

ይቀጥላል
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ሕማማት ክፍል 2

👉 ይሁዳ የመረጠው ጌታ
ጸሐፊ ፦ ዲ/ሄኖክ ኃይሌ
🎤 ተራኩ ፦ ኢዮብ ዮናስ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​​​​​በሰሞነ ሕማማት የሚጸለዩት እና የማይጸለዩት ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው?

ሼር በማድረግ ለወዳጆቻችሁ አድርሱ አሳውቁ!

ከነገ ጀምሮ የጌታችንን ሕማም የምናስብበት ሰሞን ነው። እንደ ቅድስት ቤተ-ክርስትያናችን ሥርዓት በዚህ በሰሞነ ሕማማት የምንጸልያቸውና ለጊዜው የምንታቀባቸው ጸሎቶች አሉ።

👉 በሰሞነ ሕማማት የምንጸልያቸው ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው?

በሰሞነ ሕማማት አጥብቀን የምንጸልያቸው ጸሎቶች ውዳሴ ማርያም:ዳዊት: ሰይፈ ሥላሴ:ሰይፈ መለኮት:ድርሳነ ማሕየዊ ውዳሴ አምላክ ናቸው።

እመቤታችን ድንግል ማርያም በዚህ በሰሞነ ሕማም በልጅዋ ምክንያት ብዙ እንግልት ስለደረሰባት የእሷን ምስጋና የሆነውን ውዳሴ ማርያም አናስታጉልም። ውዳሴ ማርያም ማመስገኛ መማጸኛ ስለሆነ እንጸልያለን። ምክንያቱም በዚህ በሰሞነ ሕማማት መከራ ተቀብሎ ሞቶ ሕይወቱን የሰጠንን ጌታ በሥጋ ወልዳለችን በውዳሴዋ እናስባታለን።

የቅዱስ ዳዊት ድርሰት የሆነው ታላቁ መዝሙረ ዳዊት በትንቢት ክፍሉ ስለ ጌታችን ሕማም ስቃይ እና ሞት የሚናገርና በዳዊት ምስጋና በምድር የሰው ልጆች በሰማይ ቅዱሳን መላእክት ስለሚያመሰግኑ እንጸልየዋለን።

ሰይፈ ሥላሴ ከሦስቱ አካላት እግዚአብሔር ወልድን የሚያመሰግን አምላክነቱን የሚመሰክር እና የሚመሰጥር በመሆኑ እንጸልየዋለን።

ሰይፈ መለኮት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ስለ ምስጢረ መለኮት እና ስለ ጌታችን አምላክነት ስለሚናገር እንጸልየዋለን።

ድርሳነ ማሕየዊ በቅዱስ ዮሐንስ ወልደ-ነጎድጓድ የዓይን እማኝነት እና የቃል ምስክርነት የተጻፈና የጌታችንን መከራ ስቃይ እንግልት እና ሞት በልዩ ሁኔታ የሚናገር በመሆኑ ልክ እንደ ውዳሴ ማርየም የየእለት/የየቀን ስላለው ብንጸልየው በዓይነ ሕሊና ቀራንዮ ወሰዶ በነፍሳችን የጌታችንን ሰማያዊ ውለታ የሚስልብንና በመጸለያችን ልዩ ጸጋና ክብር የሚያሰጥ የቃል-ኪዳን ጸሎት በመሆኑ በዚህ በሰሞነ ሕማማት ብንጸልየው እጅጉን እንጠቀምበታለን። ውዳሴ አምላክም የጌታችን ምስጋና በመሆኑ መጸለይ እንችላለን።

👉 በሰሞነ ሕማማት የማይጸለዩት ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው?

በሰሞነ ሕማማት የማይጸለዩትን ጸሎቶች ጠቅለል አድርገን ስናያቸው ድርሳናት ገድላት እና መልካ መልኮች ናቸው። ይህም የሆነው በሰሞነ ሕማማት ጌታችን ለእኛ ለሰው ልጆች ብሎ የተቀበላቸውን ስቃይ እና መከራ ሞት የምናስብበት እና የምናለቅስበት እንጂ ሌሎቹን በድርሳናቸው በገድላቸው በመልካቸው የምናመሰግንበት ጊዜ ስላልሆነ ነው።

በተረፈ በዚህ በሰሞነ ሕማማት ለራሳችሁ ለሀገራችሁ ብቻ አትጸልዩ ለዓለም ሕዝብ ለአሕዛብ በሙሉ ጸልዩ። ምክንያቱም ለእነሱ የመጣ ሰማያዊ ቁጣ በቀጥታም በተዘዋዋሪም ለእኛም ይተርፋልና። እነሱ ሲለበለቡ እኛ መቃጠላችን እነሱ ሲሰበሩ እኛ ወለም ማለታችን እነሱ ሲሞቱ ሞት ደጃፋችን መቆምን በማሰብ ለእነሱም እንጸልይ። የእነሱ መከራ ሲርቅ ነው የኛም የሚርቀው።

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ሰላምሽ ዛሬ ነው

ሰላምሽ ዛሬ ነው እየሩሳሌም
ወደአንች መጥቷልና አምላክ ዘላአለም/2/ 
ሆሣእና በአርያም እያሉ ዘመሩ 
ሕፃናት በኢየሩሳሌም 

አንቺ ቤተልሄም የዳዊት ከተማ
የሕዝቦችሽ ብርሃን መጣልሽ በግርማ/2 /
ኪሩቤል መንበሩን የሚሸከሙለት
መስቀል ተሸከመ ሊሆነን መድኃኒት /2 /

የኢየሱስን ሕማም ደናግልም አይተው
እያለቀሱለት ሄዱ ተከትለው /2/ 

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

#መዝ 146÷1
ትሴብሖ ኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር
ወሰብሒዮ ለአምላክኪ ጽዮን
እስመ አጽንዐ መናሥግተ ኆኃትኪ

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

#መዝ 8÷2
እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ
በእንተ ጸላኢ
ከመ ትንሥቶ ለጸላኢ ወለገፋዒ

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

#መዝ 121÷1
ተፈሣሕኩ እስመ ይቤሉኒ ቤተ እግዚአብሔር ነሐውር
ወቆማ እገሪነ ውስተ አዕፃድኪ ኢየሩሳሌም
ኢየሩሳሌምሰ ሕንጽት ከመ ሀገር .

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​​​ሆሳዕና

በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15)

የዘንባባ ዝንጣፊ፡-
👉 ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አነተ ደሰታ የምታስገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡

👉 ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው(
👉 ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው
👉 ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው
👉 ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው
👉 ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡

የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ፡-
☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ሂወታችን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።

👉 የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
👉 የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው።
👉 የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው።

የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ፡-
👉 የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡
👉 የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
👉 ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
👉 በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና።

በዓሉን በዓለ ክብር በዓለ ፍስሐ ያድርግልን፡፡ ከመጣብን መቅሰፍት መከራ እሱ በሀይል በስልጣኑ ይሰውረን ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን።

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

#ሆሳዕና ✞

ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና
ብለን እናቅርብ ምስጋና

ሆሳዕና በሉ - - - ሆሳዕና
ለወልደ አምላክ - - - ሆሳዕና
ትህትናን አሳየን - - - ሆሳዕና
ስሙ ይባረክ - - - ሆሳዕና
#አዝ
ሆሳዕና በሉ - - - ሆሳዕና
ለሰማይ ንጉስ - - - ሆሳዕና
ግርማ ለብሶ መጣ - - - ሆሳዕና
እኛን ሊቀድስ - - - ሆሳዕና
#አዝ
ሆሳዕና በሉ - - - ሆሳዕና
ለወልደ ዳዊት - - - ሆሳዕና
ነብያት በትንቢት - - - ሆሳዕና
ለተናገሩለት - - - ሆሳዕና
ሐዋርያት በወንጌል - - - ሆሳዕና
ለሰበኩለት - - - ሆሳዕና
#አዝ
ሆሳዕና በሉ - - - ሆሳዕና
ለአምላከ ምህረት - - - ሆሳዕና
ተወልዶ ከድንግል - - - ሆሳዕና
እንደ ህጻናት - - - ሆሳዕና
እረኞች በዋሻ - - - ሆሳዕና
የሰገዱለት - - - ሆሳዕና
የአዳም ልጆች ሁሉ - - - ሆሳዕና
ደግሞም መላእክት - - - ሆሳዕና

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

እስመለአለም ምህረቱ

እስመለአለም ምህረቱ/4/
አያልቅም ብዙነው የአምላክ ቸርነቱ/2/

ከማርያም የነሳው ያቅዱስ ስጋው/2/
ቀራንዮ ሲውል የሚያሳዝን ነው/2/

በፈጠረው ፍጥረት እጅግ ተሰቃይቶ/2/
ነፍሳትን አወጣ ከሲኦል ጎትቶ/2/

የማይሞተው ሞቶ የተቀበረው/2/
ከገሀነም እሳት እኛን ሊያድን ነው/2/

አመስግኑት ጌታን ሁላችሁ በአንድነት/2/
መሀሪ ነውና ለሰው ልጆች ህይወት/2/

ሊቀ መዘምራን
ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

በእጅ የያዙት ......... ።

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ኒቆዲሞስ

ኒቆዲሞስ ኒቆዲሞስ ክቡር
ሌቱን በብርሃን የሚማር መምህር

በጨለማው ግርማ ኮከብ የደመቀ
በመከራው ፅናት ይህን ዓለም ናቀ
መምህር ሆኖ ሳለ ከመማር ያልራቀ
የትዕቢትን ጅረት በትህትና ተዋርዶ አደረቀ

ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አዝ
ፍርሃትን በሚጥል ፍፁም ፍቅር ያደረ
ከመስቀል አውርዶ ጌታውን ቀበረ
የመግነዙን በፍታ በሽቶ አከበረ
ከመቅደሱ አንቀፅ ላይረሳ አምድ ሆኖ ታጠረ

ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አዝ
ለሊትም ለሊት ዕውቀትን ነገረች
ህጉን ለሚያስበው ምክር አለኝ እያለች
ከጨለማ ሀጢያት ነግታ ብርሃን ከአየች
እንደ ኒቆዲሞስ ነፍስህም ተምራ ተመለሰች

ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አፅባይት እምነ አፅባይት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ

ዲያቆን ዘማሪ ቀዳሚፀጋ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

13/08/2016 ዓ.ም

በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ።

ሮሜ. ፯፥፩ - ፲፪፤
፩ ዮሐ. ፬፥፲፰ - ፍ፤
ግብ ሐዋ. ፭፥፴፬ - ፍ፤

የዕለቱ ምስባክመዝ ፲፮፥፫
ሐወፅከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ፤
አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመፃ በላዕሌየ፤
ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመሕያው።

ትርጉም
በሌሊት ጎበኘኸኝ ልቤንም ፈተንኸው፤
ፈተንኸኝ ዓመፅ አልተገኘብኝም፤
የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር።

የዕለቱ ወንጌል፦ ዮሐ ፫፥፩ - ፲፪
ቅዳሴ፦ ዘእግዝእትነ ማርያም

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

በገና ክራር እና ከበሮ መማር የምትፈልጉ ኦርቶዶክሳዊያን ምዝገባ ስለጀመርን።

ሁላችሁም ደውላችሁ ትመዘገቡ እና በመንፈሳዊ ዝማሬ ልባችንን እናሳርፍ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ማኅበረ ኀዳፌ ነፍስ
ለበለጠ መረጃ ☎️0912085085
ወይም በቴሌግራም @Orthodoxtewahed0 ያነጋግሩን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​የቀጠለ 👆

በመሆኑም የባለ አምስትና የባለ ሁለት መክሊት ባለቤቶች የሆኑት ወጥተው ወርደው ደክመው፣ መከራ መስቀልን ሳይሳቀቁና ሳይፈሩ፤ ወድደው ፈቅደው የጀመሩትን አገልግሎት በማክበር ሕይወታቸውን ለታመነው አምላክ አደራ በመስጠት የተማሩትን ፍጹም ትምህርት ለሌላው አስተምረው፣ ሠርተው ያገኙትን ለሌላው አካፍለው ወገናቸውን እንደራሳቸው አድርገው ሲመለከቱ

ባለ አንድ መክሊት የተባለው ግን ዓላውያን እሳት ስለት አሳይተው ሃይማኖቴን ሲያስክዱኝ መናፍቃን ተከራክረው ምላሽ ቢያሳጡኝ ብሎ ፈርቶ ሃይማኖቱን በልቡ ከመደበቅና ከመሠወር በቀር የተማረውን ትምህርት ሠርቶ ያገኘውን ሀብት ንብረት ለሌላው ሊያካፍልና የተሰጠውን አደራም ሊወጣ አልወደደም፡፡

ይህ የመክሊቱ ባለቤት የተባለው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን የተሰጣቸውን ሓላፊነት በአግባቡና በጽንአት ለተወጡት ሁሉ እርሱ ፍጹም ዋጋን የሚሰጣቸው መሆኑን ያመለክታል፡፡

ይህም ሁኔታ “አንተ በጎ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ። ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” በሚል ታላቅ የምስጋና ቃል ተገልጧል፡፡ ይህ ቃል በሃይማኖትና በበጎ ምግባር ለእግዚአብሔር የታመኑ ሁሉ ዘለዓለማዊና ፍጹም ደስታ ወደሚገኝበት መንግሥተ ሰማያት ለመግባት ለሚያደርጉት የእምነት ጉዞ እጅግ ተስፋ የሆነ ቃል ነው፡፡

በዚህ ምንባብ ላይ እንደተገለጸው እግዚአብሔር አምላክ ለሁላችንም እርሱን የምናገለግልበትንና ለእርሱ በመታመን ዘለዓለማዊ ክብርን የምናገኝበትን ዕውቀትን፣ ማስተዋልን፣ እምነትን፣ ተስፋን፣ የሥነ ምግባር ሀብትን፣ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን እንጠቀምባቸው ዘንድ ለእኛ ለሰው ልጆች እንደየዓቅማችን መጠን ሰጥቶናል፡፡

እነዚህ ሁሉ ነገሮች የሥጋችንን ምኞት
ለማስፈጸም የተሰጡ ሳይሆኑ ነፍሳችን የምትከብርበትን መልካም ሥራን የምንሠራባቸው መሣሪያዎቻችን ናቸው። በመሆኑም እርሱ በሰጠን የአገልግሎት በር ጸጋ በታማኝነት በማገልገል በሕይወት ዘመናችን ሁሉ መንፈሳዊውን ሀብት የምናተርፍ እንሆን ዘንድ የተላለፈልን አምላካዊ ምክር ነው፡፡

ምክንያቱም እኛ የተጠራነው ፍሬ ልናፈራና ሌላውንም ልናተርፍ መልካም ሥራን ልንሠራ እንጂ የሥጋችንን ፈቃድ በመከተል የኃጢአት ባሮች ልንሆን አይደለም፡፡ መጽሐፍ እንዲህ አለ “ወኲሉ ዘከመ ተጸውአ ከማሁ ለየሀሉ፤ ሁሉ እንደተጠራ እንዲሁ ይኑር” /፩ኛ ቆሮ. ፯፥፳/

ከላይ እንደተመለከትነው በልዑል አምላክ በእግዚአብሔር አንደበት አንተ በጎ ታማኝ አገልጋይ በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ መባልን የመሰለ አስደሳችና አስደናቂ ነገር የለም፡፡

ይህ ደግሞ የሚገኘው ሃይማኖትን በሥራ በመግለጥ እንጂ ሃይማኖትን በልቡና በመያዝ ብቻ /ሙያ በልብ ነው/ በማለት ብቻ የሚገኝ አይደለም፡፡ ከእነዚህ እንደ አቅማቸው መጠን መክሊት ተሰጥቷቸው በትጋታቸውና በቅንነታቸው ሌላ መክሊት ካተረፉት በጎና ታማኝ አገልጋዮች የምንማረው እውነታም ይህ ነው፡፡

በብዙ ለመሾም ለማደግ ለመጽደቅ በጥቂቱ መታመን መፈተን መጋደል ግድ ነው፡፡ አንድ መክሊት የተሰጠውን ሰው ስንመለከተው ጌታውን ጨካኝና ፈራጅ አድርጎ ከመቁጠር ውጪ በተሰጠው መክሊት ወጥቶ ወርዶ ሊያተርፍ አልወደደም፡፡

መክሊቱንም ባስረከበ ጊዜ በጌታው ላይ የተናገራቸው ቃላት የእርሱን አለመታዘዝና አመጸኝነት ይገልጡ ነበር፡፡ በመሆኑም ይህ ሰው በጥቂቱ መታመን ያቃተውና በአስተሳሰቡ ደካማነት እጅግ የተጎሳቆለ ሰው ነው፡፡

በዚህ ምሳሌ መሠረት ይህ ባለ አንድ መክሊት የተባለው ሰው ዓላውያን ነገሥታት እሳት ስለት አሳይተው ቢያስክዱኝ መናፍቃን ተከራክረው መልስ ቢያሳጡኝ በማለት ሃይማኖቱን በልቡ ሸሽጎና ቀብሮ በተቀደሰ ተግባር ሳይገልጠው ከመያዙ ባሻገር በጌታ ፊት በድፍረት ቆሞ አንተ ሕግ ሳትሠራ በአእምሮ ጠባይዕ አውቃችሁ፤ መምህራንንም ሳትመድብ በሥነ ፍጥረት ተመራምራችሁ በሠራችሁ ብለህ የምትፈርድ ጽኑ ጨካኝ መሆንክን አውቃለሁና ፈርቼ ሃይማኖቴን በልቡናዬ ይዠዋለው በአዕምሮዬ ጠብቄዋለሁ የሚል ሃይማኖቱን ግን በሥራ የማይገልጥ ሰነፍ ሰውን ያመለክታል፡፡

ለዚህ ዓይነት ሰው የጌታ መልስ ደግሞ በምሳሌው መሠረት የሚከተለው ነው። እኔ ሕግ ሳልሠራ በአእምሮ ጠባይዕ አውቃችሁ ፤ መምህር ሳልሰጥ በሥነ ፍጥረት ተመራምራችሁ አውቃችሁ በሠራችሁት ብዬ የምፈርድ ጽኑ ጨካኝ መሆኔን ታውቃለህን? እንዲህስ ካወቅህ ሹመትክን ልትመልስልኝ ይገባኝ ነበር፡፡

ወጥቶ ወርዶ ለሚያስተምር በሰጠሁት ነበር፡፡ አሁንም የእርሱን መምህርነት ሹመት ነሥታችሁ (ወስዳችሁ) ለዚያ ለባለ ዐራቱና ለባለ ዐሥሩ ደርቡለት!

እርሱን ግን አውጡት የሚል ነው። ምክንያቱም ከበጎ ምግባር የተለየች እምነት የሞተች እንደሆነ ተጽፏልና። ዛሬም እያንዳንዳችን በዓቅማችን መጠን መክሊት ተሰጥቶናል፡፡ ነገር ግን መክሊቱን እንደቀበረው እንደዚያ ሰው የተሰጠንን ቀብረን ለወቀሳና ለፍርድ እንዳንሰጥ በአገልግሎታችን ልንተጋ ይገባናል፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ይህንኑ ሲገልጥ “ወዘሂ ይትለአክ በመልእክቱ፤ ወዘሂ ይሜህር በትምህርቱ. . .፤ አገልግሎት ቢሆን በአገልግሎታችን እንትጋ የሚያስተምርም በማስተማሩ ይትጋ የሚሰጥም በልግሥና ይስጥ›› (ሮሜ. ፲፪፥፯) በማለት ተናግሯል፡፡

ለመሆኑ አሁን ባለንበት የስግብግብነት ወቅት ዛሬ ‹‹አንተ በጎ ታማኝ አገልጋይ…›› ተብሎ በእግዚአብሔር ሊመሰገን የሚችል ሰው ማን ይሆን? በእውነት እንዲህ ተብሎ የሚመሰገን በጎና ታማኝ ካህን በጎና ታማኝ መምህር በጎና ታማኝ ምእመን ታማኝ ሰባኪና ታማኝ ዘማሪ ማግኘት ይቻል ይሆንን?

ነገር ግን መቼም አምላካችን ቸር ነውና በየዘመናቱ አንዳንድ ታማኝ አባቶችን እንደማያሳጣን ተስፋ አለን። ምክንያቱም ዛሬም ቢሆን እንደአባቶቻችን እንደቅዱሳን ሐዋርያት በእምነት፣ በትዕግሥት በፍቅር በተጋድሎ በየውሐት በትሕርምት በጸሊዓ ንዋይ በትሕትናና በትጋት በማገልገል የተሰጣቸውን መክሊት የሚያበዙ አገልጋዮች አሉ፡፡

የእነዚህ ክብራቸው በምድርም በሰማይም እጅግ የበዛና ራሳቸውን አስመስለው በትምህርት የወለዷቸው ልጆቻቸውም ለቤተ ክርስቲያን የተወደዱ የተከበሩ ልጆች ናቸው፡፡

ለምሳሌ ነቢየ እግዚአብሔር ሙሴ ነቢየ እግዚአብሔር ኢያሱን ፤ ቅዱስ ጴጥሮስ ቀሌምንጦስን፣ ቅዱስ ጳውሎስም ቅዱስ ጢሞቴዎስን ለቤተ ክርስቲያን አበርክተዋል፡፡ ሌሎችም አበው ቅዱሳን በወንጌል ቃል መንፈሳውያንና ትጉሃን የሆኑ ምእመናንን በሚገባ አፍርተዋል፡፡

ያላመኑትንም አሳምነው ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመመለስ ለዘለዓለማዊ ክብር የበቁ እንዲሆኑ አስችለዋቸዋል። በተሰጣቸው ጸጋም አትርፈው አትረፍርፈው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሀብተ መንፈስ ቅዱስ እንድትጎበኝ አድርገዋል፡፡ የእነርሱም በረከታቸው ረድኤታቸው ቃል ኪዳናቸው ለሌሎች እንዲተርፍ ሆኖላቸዋል፡፡

በመሆኑም ክርስቶስ በደሙ የከፈለውን ወደር የሌለውን ዋጋ ዓለም አምኖና ተቀብሎ በክርስትና ሃይማኖት እንዲድንበትና እንዲጠቀምበት በማድረግ እንዲሁም በታማኝነትና በበጎነት አገልግሎታቸው ጥንትም ዛሬም ላለችዋና ወደፊትም ለምትኖረዋ ቅድስት ቤተክርስቲያን ድምቀትም ውበትም የሆኑት ቅዱሳን አበው ሊገኙ የቻሉት ከእግዚአብሔር ይልቅ ሰውን ደስ ለማሰኘት በመድከማቸው ሳይሆን የተጠሩበትን ዓላማና የጠራቸውን እርሱን በሚገባ አውቀውና ከልብ ተረድተው ለዘለዓለማዊ ሕይወት ተግተው በመሥራታቸው ነው።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

08/06/16 ዓ.ም
መዝሙር ዘገብር ኄር መኑ ውእቱ ገብርኄር

የዕለቱ ምስባክ :- መዝ ፴፱(፵)፥፰
ከመ እንግር ፈቃደከ መከርኩ አምላኪየ፡፡
ወሕግከኒ በማዕከለ ከርሥየ፡፡
ዜኖኩ ጽድቀከ በማኅበር ዐቢይ፡፡

ትርጒም
አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ ፤ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው፡፡
በታላቅ ጉባኤ ጽድቅን አወራሁ፡፡

የዕለቱ ወንጌል፦ ማቴ ፳፭ ፥ ፲፬ -፴፩
ቅዳሴ፦ ዘባስልዮስ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…
Подписаться на канал