ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

#ልደተ_ክርስቶስ
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​ወላጆች ለልጆቻችሁ የልደትን በዓል አስተምሩ የማይጠቅም የዓለም ስጦታ ከምትሰጧቸው በነፃ የተሰጠንን ክርስቶስ ስጧቸው!

#ልደተ_ክርስቶስ /የገና በዐል/
በአዜብ ገብሩ

እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች? ደህና ናችሁ? ዛሬ ስለጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት /ገና በዓል/ እንነግራችኋለን፡፡ በደንብ ተከታተሉን፡፡ እሺ?

ልጆች በአንድ ወቅት እንዲህ ሆነ፡፡ አውግስጦስ ቄሳር የተባለ ንጉሥ ሰው ሁሉ ይቆጠር ዘንድ አዘዘ፡፡ በትእዛዙ መሠረትም ሰው ሁሉ ሊቆጠር ወደየትውልድ ከተማው ሄደ፡፡

ዮሴፍና እመቤታችንም ሊቆጠሩ ከናዝሬት ወደ ትውልድ ሥፍራቸው ወደ ቤተልሔም ሄዱ፡፡ በቤተልሔም ሳሉም እመቤታችን የምትወልድበት ቀን ደረሰ፡፡ በዚያ ሥፍራም ብዙ እንግዳ ስለነበር እነ ዮሴፍ የሚያርፉበት ቦታ አላገኙም ነበር፡፡ ማደርያም ስላልነበራቸው በከብቶች ማደርያ በበረት ውስጥ እመቤታችን ልጅዋን ወለደችው፡፡

በጨርቅ ጠቅልላ እዛው በበረት ውስጥ አስተኛችው፤ በዚያ ሀገር ይኖሩ የነበሩ እረኞችም ሌሊት ከብቶቻቸውን ይጠብቁ ነበር፤ የእግዚአብሔር መልአክም በእረኞቹ አጠገብ ቆመ፤ የእግዚአብሔርም ብርሃን በዙሪያቸው በራ፤ በጣምም ፈሩ፡፡ መልአኩም እንዲህ አላቸው ‹‹እነሆ ለእናንተና ለሕዝቡ ሁሉ ደስታ የሚሆን ታላቅ የምስራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ‹‹እነሆ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት የሆነ ተወልዶላችኋል፡፡

ይኸውም ጌታ እና እግዚአብሔር የሆነ መድኃኒታችን ኢያሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ እናንተም ባገኛችሁት ጊዜ ምልክቱ እንዲህ ነው፡፡ ሕፃን በጨርቅ ተጠቅልሎ በበረት ውስጥ ተኝቶ ታገኙታላችሁ ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ የሰማይ መላእክት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ እነዚህ እረኞች እርስ በርሳቸው ‹እስከ ቤተልሔም እንሂድ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን ነገር እንወቅ አሉ፡፡

ፈጥነውም ሄዱ፡፡ ማርያምንና ዮሴፍን አገኙአቸው፡፡ ሕፃኑንም በበረት ውስጥ አገኙት፡፡ በአዩትም ጊዜ የነገሩአቸውን ሰምተው በጣም ተደነቁ፡፡ እረኞቹም እንደነገሩአቸው ባዩትና በሰሙት ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ‹‹በሰማይ ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን በምድርም ለሰው ልጆች በጎፈቃድ ሆነ›› ብለው እያመሰገኑና እያከበሩ ወደመጡበት ተመለሱ፡፡

አያችሁ ልጆች እነዚህ ክርስቶስን ሊያዩ የመጡ ሰዎች ደስተኞች ነበሩ፤ ስለዚህ ልጆች እኛም በቤተ ክርስቲያን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት በደስታ ልናከብር ይገባናል፡፡ ከመላእክት ጋር ሆነንም ‹‹በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን›› እያልን እንዘምር፡፡ እንግዲህ ልጆች መልካም የገና በዓል ይሁንላችሁ እሺ፡፡

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ታኅሣሥ 27 በቦሌ መድኃኔዓለም ከቀኑ 09:30 ለአእላፋት ዝማሬ እንገናኝ::

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

Code 8:- ይህንን ይመስላል
ለማዘዝ እና ለበለጠ መረጃ
📩 @kalSandy

📞 0965875219
📞 0922501999
📞 0913655116

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

code 1 :- ሲታተም ይህንን ይመስላል።
ለማዘዝ እና ለበለጠ መረጃ
📩 @kalSandy

📞 0965875219
📞 0922501999
📞 0913655116

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

አምላከ ተክለሃይማኖት ማረን

አምላከ ተክለሐይማኖት ማረን 2×
አምላከ ቅዱሳን ታረቀን 2×
ስለቃልኪዳንህ በቁጣ አታጥፋን
አዝ
ሐዋርያው ቅዱስ ተክለሃይማኖት
የኢቲሳ አንበሳ የኔ አባት
ቁጣውን አብርደው ተክለሐይማኖት
ለምልጃ ተነሳ የኔ አባት
ከሰማይ ካህናት ተክለሐይማኖት
ቤተሰብ ሆነሃል የኔ አባት
የሥላሴን መንበር ተክለሐይማኖት
ለማጠን በቅተሀል የኔ አባት
አዝ
ከከርቤ ከሚያ ተክለሃይማኖት
ከሰሊክም በልጧል የኔ አባት
የፃድቁ ፀሎት ተክለሐይማኖት
በእግዚአብሔር ፊት ሸቷል የኔ አባት
ስለቃልኪዳንህ ተክለሐይማኖት
አምላክ ይለመናል የኔ አባት
ፀሎትህ ሲደርስ ተክለሐይማኖት
እኛን ይታረቃል የኔ አባት
አዝ
ተማፅነንብሃል ተክለሃይማኖት
ጌታ ሆይ በስሙ የኔ አባት
በፃዲቁ ፀሎት ተክለሐይማኖት
በሰባረ አፅሙ የኔ አባት
ኢትዮጲያን በሙሉ ተክለሐይማኖት
አስተምሮ ሲመለስ የኔ አባት
አፅመ ርስቱ ሆነች ተክለሐይማኖት
ደብረ ሊባኖስ የኔ አባት
አዝ
የፃዲቁ መንፈስ ተክለሃይማኖት
ከቅዱሳን ጋራ የኔ አባት
ከልባችን ገብተህ ተክለሐይማኖት
ብርሃንን አብራ የኔ አባት
በፀሎት ስቆም ተክለሐይማኖት
ስምህን ስጠራ የኔ አባት
ነፍሴ ተደሰተች ተክለሐይማኖት
ሲርቀኝ መከራ የኔ አባት

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​​​ታህሳስ 24

በዚህች ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክልሃይማኖት የተወለዱበት ቀን ነው። የትውልድ ቦታቸው ሸዋ ጽላልሽ አወራጃ ዞረሬ ነው፤ የአባታቸው ስም ጸጋ ዘአብ የእናታቸው ስም እግዚ ሐርያ ይባላል መካን ነበሩ ልጅ እንዲሰጣቸው ወደ እግዚያብሔር ዘወትር ይጸልዩ ነበር፤ መጋቢት 12 ቀን እንዲህ ሆነ።

ሞተሎሜ የተባለ ጣኦት አምላኪ ንጉስ አገራቸውን ወረረ መንደሩንም አጠፋ ጸጋ ዘአብ ወንዝ ውስጥ ገብቶ አመለጠ እግዚ ሐርያ ግን ተማርካ ሄደች፤ በጣም መልከ መልካም ስለነበረች ሞቶሎሜ ሊያገባት አሰበ ታላቅ ድግስም ደገሰ አገር ምድሩ ተሰብስቦ ሲዘፍን ሲጨፍር ሳለ ቅዱስ ሚካኤል ታላቅ መብረቅ ነጎድጓድ አሰማ ብዙዎች ሞቱ እግዚሐርያን በክንፎ ተሸክሞ ዞረሬ ከቤተክርስቲያን ውስጥ አስቀመጣት ከባለቤቷ ጸጋ ዘአብ ጋር ተገናኙ ተቃቅፈው ተላቀሱ፤ከሁለት ቀን በኃላ መጋቢት 24 ቀን ተክለሃይማኖት ተጸነሱ።

በዛሬዋ ቀን 1167 ዓ/ም ተወለዱ ቀኑ አርብ ነበር፤ በተወለዱ በ3ኛ ቀናቸው እሁድ በ 3 ሰዓት “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” ብለው ሥላሴን አመሰገኑ፤ ሁለተኛ ተአምር ከዚህ በታች ያለው ስዕል ተክልዬ የአንድ ዓመት ከመንፈቅ ህጻን እያሉ ነው፤ በድፍን ሸዋ ርሃብ ተከስቶ ነበር በተለይም በዞረሬ እግዚሐርያ አዘነች አለቀሰች ምነው እርቧት ነው ጠምቷት ነው ቢሉ የለም እርቧትስ ጠምቷትስ አይደለም የቅዱስ ሚካኤል ዝክሩ ታጎለቢኝ ብላ እንጂ።

ህጻኑ ተክለሃይማኖት ከእናቱ ጭን ወርዶ እየዳኸ ወደ ጓዳ ሄደ አንስታ አቀፈችው እርሱ ግን አለቀሰ ዱቄት የተቀመጠበትን እንቅብ እንድትሰጠው በእጁ ጠቆማት ሊጫወትበት መስሏት ሰጠችው በትንንሽ እጆቹ እንቅቡ ላይ አማተበ ዱቄቱ ሞልቱ ፈሰሰ ዳግመኛ የቅቤ የዘይት ማስቀመጫ ማድጋዎች ላይ በተመሳሳይ አማተበ ሞልቶ ፈሰሰ ቤቱ በበረከት ተትረፈረፈ፤ የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን አዘከረች አገሬውን ጠርታ መገበች፤ ለተቸገሩትም አብዝታ ሰጠች፤ ይህ በረከት ሁለቱም እስኪሞቱ ድረስ አላለቀም ይላል ገድላቸው።

ተክለ ሃይማኖት በ 99 ዓመት ከ8 ወር ከ5 ቀን በዚህ ምድር ኖረው ነሐሴ 24 ቀን አርፈዋል። በደብረሊባኖስ ገዳማቸው የንፍሮ ውኃ አይነስውር ያበራል ድውይ ይፈውሳል ገድላቸው ሊነበብ ሲወጣ አጋንንት ተቃጠልን ይላሉ ሲገርም ምን ያህል ባለጸጎች ነን። ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።

#ሼር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - ድንግል በድንግልና

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - የምሥራች ደስ ይበለን

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - ተወልደ ኢየሱስ

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - እም ሰማያት ወረደ

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - ዝም አትበሉ

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - መድኃኒነ

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የጃን ሜዳው መርሐግብር ወደ ቦሌ መድኃኔዓለም ተዘዋውሯል። 😡

👉 @ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - በብርሃኑ ተመላለሱ

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

🔴 ቀጥታ ስርጭት | ከቦሌ መድኃኔዓለም የአእላፋት ዝማሬ ታኅሣሥ 27/2016 ዓ.ም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ለመከታተል ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ

ይህንን ይጫኑ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

፨የጌታን ልደት በዝማሬ፨
ታኅሣሥ 27 በቦሌ መድኃኔዓለም ከቀኑ 9:30 ለአእላፋት ዝማሬ እንገናኝ::

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

code 6 :- ይህንን ይመስላል
ለማዘዝ እና ለበለጠ መረጃ
📩 @kalSandy

📞 0965875219
📞 0922501999
📞 0913655116

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

code 3 :- ይህንን ይመስላል 🙏
ለማዘዝ እና ለበለጠ መረጃ
📩 @kalSandy

📞 0965875219
📞 0922501999
📞 0913655116

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ተመልከቱ ሕትመቱ ላይ ውበቱን!!!

ጥራት እና ውበት መገለጫችን ነው። እንደምታዩት በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ በጣም የተዋቡ ቲሸርቶችን ለማህበራት፣ ለግለሰብ፣ ከኛ ተረክበው ለሚያከፋፍሉ፣ ለሰፈር ወጣቶች፣ ለቤተክርስቲያን ከአዲስአበባ ጀምሮ ወደ ተለያየ ቦታ እያከፋፈልን እንገኛለን።

በተለይም በብዛት ተረክባችሁ ለምታከፋፍሉለምትሸጡ በሙሉ በጣም አስገራሚ ቅናሽ አቅርበንላቹኀል።

እንደምትመለከቱት ዲዛይናችን እና ሕትመታችን ልዩነት የለውም። በዓይናቹ ምታዩትን በእጃቹ ትወስዳላቹ።

"ትዕዛዝ በጣም ስለሚበዛብን ቀኑ ደርሶ ከመዋከብ ቀደም ብለው ቢያዙን መልካም ነው።"

ተጨማሪ ዲዛይኖችን ለመመልከት
👉 /channel/KABAPrint
👉 /channel/KABAPrint

ለማዘዝ እና ለበለጠ መረጃ
📩 @kalSandy

📞 0965875219
📞 0922501999
📞 0913655116

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ኢትዮጵያዊው ጻድቅ

ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ማነው ብዬ ጠየቅሁ
በረከት ፈልጌ ልሳለመው ናፈቅሁ
ክብሩን ልመሰክር ተፈታ ምላሴ
በደጁ ደርሼ ፍቅሩን በመቅመሴ/፪/

አዝ
በኢቲሳ ምድር ዘር ሆነህ በቅለህ
ተለየህ ለአምላክ ዓለምን ጥለህ
ደብረ ሊባኖስ ህያው ምስክር
ስለ አንተ ዝና ስለ አንተ ክብር

ተክለሃይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ
አዝ
አክባሪው አምላክ ስላከበረህ
ዛሬም ከኛ ጋር በመንፈስ አለህ
ደጅ እንጠናለን በትህትና
የጻድቅ ጸሎት ኃይል አላትና

ተክለሃይማኖት ጸሐይ
ጸጋህ ይውጣልኝ በሠማይ
አዝ
ወደ ለምለም መስክ ሰብከህ መራኸን
የቃሉን ወተት አጠጥተኽን
ያቀጣጠልከው የወንጌል ችቦ
የአምላክ አድርጓል ትውልዱን ስቦ

ተክለሃይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ቤቴ ደጄ
አዝ
ሠላሳ ሥድሳ መቶ ያፈራህ
በደብረ አስሶ ቆመህ በአንድ እግርህ
የሞተለሚ መሻት ቀረና
የጌታ መንገድ ጥርጊያውም ቀና

ተክለሃይማኖት ወዳጄ
ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - ድንግል በድንግልና

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - የምሥራች ደስ ይበለን

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - ተወልደ ኢየሱስ

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - እም ሰማያት ወረደ

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - ዝም አትበሉ

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - መድኃኒነ

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​"በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው" ሉቃ. 2:7

| ጃንደረባው ሚድያ | ታኅሣሥ 2016 ዓ.ም.|
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

የመድኃኔዓለም ክርስቶስን በዓለ ልደት ዋዜማ ምእመናን በዝማሬ እንዲያከብሩ በማሰብ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ (ኢጃት)  "የአእላፋት ዝማሬ"ን  ከመስከረም 2 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል::

"የአእላፋት ዝማሬን" ለማካሔድ የታሰበበት የመጀመሪያው ቦታ መስቀል አደባባይ የነበረ ሲሆን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ጽሕፈት ቤት ኅዳር 15 2016 ዓ.ም. ለመንግሥት አካል ደብዳቤ በማስገባት እና በግንባር ተገኝቶ ለሚመለከተው አካል "የአእላፋት ዝማሬን" ምንነት በማስረዳት መንግሥት ለዝማሬው ተገቢውን ትብብር እንዲያደርግ ጥያቄ ቀርቦ ነበር:: በመንግሥት አካላትም ሀገሪቱ ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ አንጻር በመስቀል አደባባይ ሁነቱን ለማካሔድ እንደሚያስቸግር ምላሽ የተሠጠ በመሆኑና አዘጋጅ ኮሚቴውም በኤግዚቢሽን ማእከል ባለው የንግድ ትርዒት ምክንያት ቀድሞ የተያዙ ነገሮች እንቅፋት ሊሆኑ እንደሚችሉ በዘርፉ ልምድ ካላቸው የቤተ ክርስቲያን ልጆች መረጃ በማግኘቱ በጥያቄው ላይ ብዙም ሳይገፋበት ቀርቶአል::

ሁለተኛው "የአእላፋት ዝማሬ"ን ለማካሔድ የተመረጠው ሥፍራ የጃን ሜዳ ጥምቀተ ባሕር ሥፍራ ነበረ:: በሥፍራው ዝግጅቱን ለማድረግም በሀገረ ስብከቱ በኩል ከሚመለከተው የመንግሥት ቢሮ ሓላፊዎች ጋር ደብዳቤ ገብቶ ምላሽ በመጠባበቅ ሒደት ላይ ቆይቶአል::

ይህ በሒደት ላይ እንዳለ ደግሞ "የአእላፋት ዝማሬን" ወደ ጃን ሜዳ ለማድረግ ከመታሰቡ አስቀድሞ  በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል እና ከሚመለከተው አካል ተገቢው ፈቃድ ተጠይቆበት ሊካሔድ በነበረው በ"ተዋሕዶ ኤክስፖ" ላይ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድም ተሳታፊ ከነበሩ የቤተ ክርስቲያን ማኅበራት አንዱ ነበረ:: በመሆኑም በሥፍራው ኢጃት በተሠጠው ቦታ ላይ ከዲዛይን ጀምሮ ብዙ ወጪ በማውጣት የማሳያ ቦታ ግንባታ ካደረገ በኋላ ባልተጠበቀ መልኩ ዝግጅቱ በመቋረጡ እና ዕቃዎቻችሁን አንሱ በመባሉ ከአቻ ማኅበራት ጋር የሥነ ልቡና ፣ የገንዘብ እና የጊዜ ኪሳራን አስተናግደናል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ "የአእላፋት ዝማሬ"ን በጃን ሜዳ ለማካሔድ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ደብዳቤ የተጻፈ ሲሆን ብፁዕነታቸው ከሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅና ከአእላፋት ዝማሬ ተወካዮች ጋር በመሆን ከከተማው የጸጥታ ሓላፊዎች ጋር ስብሰባ በመቀመጥ የአእላፋት ዝማሬን ዓላማና ለሀገር ገጽታም ሆነ ለወጣቶች ሕይወት ያለውን ማኅበራዊ ፋይዳ በማስረዳት መንግሥት ተገቢውን ትብብር እንዲያደርግ ጠይቀዋል:: በመንግሥት ሓላፊዎች በኩል ለመሠረታዊ ሃሳቡ ያላቸውን በጎ ሃሳብ በመግለጽ "ፈቃድ ለመሥጠትና ጥበቃ ለማድረግ ግን ከጸጥታ አካላት ጋር ተነጋግረን እናሳውቃለን" የሚል ተስፋ ተሠጥቶ እስከ አሁን በመጠባበቅ ላይ ነበረ::

በመጨረሻም ለሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት የተሠጠው ምላሽ "ከፍተኛ የጸጥታ ሥጋት ስላለ እና መንግሥት ባለው መረጃ መሠረት በመንፈሳዊ መድረክ ሰበብ ሊፈጸሙ የሚችሉ የሽብር ድርጊቶችም ሊኖሩ ስለሚችሉ ታኅሣሥ 27 የታሰበውን ዝግጅት በጃንሜዳ ማከናወን አይቻልም" የሚል ነው::

በዚህ ምክንያት የታኅሣሥ 27 2016 ዓ.ም. የመጀመሪያው የገና "የአእላፋት ዝማሬ" በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን  እንዲካሔድ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ መመሪያ ሠጥተዋል:: በዕለቱም ቅዱስ ፓትርያርኩ ተገኝተው ሕዝቡን እንዲባርኩ ለማድረግና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትም ተገኝተው ስብሐተ ልደቱን ለሚካፈሉ ምእመናን ቡራኬ  እንዲሠጡ ሀገረ ስብከቱ ጥሪ እንደሚያደርግና የአእላፋት ዝማሬው ባማረ ሁኔታ እንደሚካሔድ ገልጸዋል::

ብፁዕነታቸው አያይዘውም  "ይህ የአእላፋት ዝማሬ በሀገረ ስብከታችን የተፈቀደበት ዓላማ ምእመናን ጾሙን በመንፈስ ሲጾሙ ቆይተው ፍጻሜውን በሥጋ እንዳይጨርሱና ከቅዱሳን መላእክት ጋር በዝማሬ እንዲያከብሩ ለማድረግ በመሆኑ ለአእላፋት ዝማሬ ስትዘጋጁ የነበራችሁ ልጆቻችን ከቦታ ለውጥ በስተቀር የታሰበውን ዝማሬ ከመሆን የሚያስቀረው ምንም ነገር ስለሌለ የጀመራችሁትን የዝማሬ ዝግጅት እንድትቀጥሉና በዕለቱ እንድትገኙ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች" ብለዋል::

የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ  ላለፉት ሦስት ወራት የአእላፋት ዝማሬን ለማካሔድና ልደቱን ለባለልደቱ በሚገባ ምስጋና ለማክበር ብዙ ሥራዎችን ሲያከናውን መሰንበቱ ይታወቃል:: በዐሥር አድባራት የመሐረነ አብ የጸሎተ ምሕላ ጉዞ በማድረግም ወጣቶች ወደ ተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ሰብአ ሰገላዊ የጸሎት ጉዞ ሲያደርጉ ሰንብተዋል:: ከሃምሳ ስምንት ሺህ ሰዎች በላይ ዝማሬውን ሲለማመዱና በሥራ ቦታቸውና በየሥፍራው በመዝሙር ሕሊናቸውን ሲቀድሱ ከርመዋል:: በሚያስደንቅ ሁኔታ የሙዚቃ ኮንሰርት በማዘጋጀት የሚተዳደሩ አካላት ሳይቀር "የትርፋቸው ተስፋ" ስለተነካባቸው በመቆጣት ፈንታ "እስከዛሬ ለሠራነው ንስሓ እንዲሆነን ምን እናግዛችሁ?" ብለው እስከመጠየቅ ደርሰው አስገርመውናል::

ምንም እንኳን የመጀመሪያውን ዙር የአእላፋት ዝማሬ ለማካሔድ ባሰብንበት ቦታ ላይ ማድረግ ባለመቻላችን እጅግ ብናዝንም ክርስቶስም ሊወለድ በጠየቀበት ሥፍራ እንዳልተወለደ እናውቃለን::
"በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው" የሚለው ቃልም በሕሊናችን የተጻፈ ነው:: ለተወለደው ንጉሥ ለመዘመርም እንኳንስ ወደ ቤተ ክርስቲያን በዘመኑ ቢያኖረን ወደ ከብቶች በረትም በሔድን ነበር:: 

ስለዚህ ምእመናን የልደቱን ምስጋና "በአእላፋት ዝማሬ" ከማክበር በምንም ምክንያት ሳትረበሹና ሳትዘናጉ እንደ ሰብአ ሰገል የተወለደውን ንጉሥ አድራሻ መፈለጋችሁን እንዳትተዉ እና የከንፈራችሁን ፍሬ ይኸውም የምስጋና ሥጦታችሁን "ለተወለደው አምላክ" እንድታቀርቡ በትሕትና እንጋብዛለን:: የአእላፋት ዝማሬ ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፎ እዚህ የደረሰው አንዳች መንፈሳዊ በረከትን ስላዘለ ነውና በቀሩት ቀናት ለዝማሬው በትጋት እንድትዘጋጁና ኦርቶዶክሳውያን ሁላችሁ ከመላእክትና ከእረኞች ጋር ለመዘመር በሥፍራው እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን::

"በእግዚአብሔር ቤት በመቅደሱ እንገናኝ" ነህ. 6:10

#አእላፋት_ዝማሬ
#የኢትዮጵያዊው_ጃንደረባ_ትውልድ
#ወደ_ሠረገላው_ቅረብ

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - በብርሃኑ ተመላለሱ

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - ስምህ በሁሉ ተመሰገነ

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…
Подписаться на канал