ortodoxmezmur | Неотсортированное

Telegram-канал ortodoxmezmur - ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

134932

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። . ዝማሬ ዳዊት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ። ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @zmaredawit_messengerbot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Подписаться на канал

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​​​ጳጉሜን

ጳጉሜን የሚለው ስያሜዋ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ጭማሪ ማለት ነው፡፡ በግእዝ ተውሳክ ማለት ሲሆን ተውሳክ ማለት ተጨማሪ ማለት ነው፡፡ “ወሰከ - ጨመረ” ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ ሌሎች ሀገሮች ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ያደርጓታል፡፡ ይኸውም ይታወቅ ዘንድ እኛ የወርን ቁጠር 30 ስናደርግ እነርሱ 31 ብለው የሚቆጥሩት ወር አላቸው፡፡ ይኹን እንጂ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ሳያደርጉ የዓመት ተጨማሪ አድርገዋታል፡፡

ጳጉሜን በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን ትመጣለች፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ሉቃስ መጨረሻ በዘመነ ዮሐንስ መግቢያ ጳጉሜን ስድስት ቀን ትሆናለች፡፡ በዚህም ሀገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ /Thirty months of sunshine/ በመባል ትታወቃለች፡፡ ጳጉሜን ስድስት በምትሆንበትም ጊዜ ጾመ ነቢያት /የገና ጾም/ ህዳር 14 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈትቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡

በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜን ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው። ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዎች ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡

የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲ 2፥2-7፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋት በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡

ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ ዮዲ 8፥2፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡

ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡

የጳጉሜን ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብባትም ወር ነች፡፡ ይህም ጳጉሜን የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

🙏🙏ነገረ ማርያም ክፍል ፫🙏🙏
ምልጃ ወይም አማላጅነት ምን ማለት ነው?

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ነገረ ማርያም ክፍል ፪
እነሆ🤲🤲🤲


ክፍል ፩ ያላዳመጣችሁ ካላችሁ በኮመንት አሳውቁን

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

"ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል" ሉቃ 1:48

🤲ክፍል ፭🤲

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

🙏አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ🙏
       

      🤲ትርጓሜ ክፍል ፫🤲

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

🤲ነገረ ማርያም መግቢያ🤲

📣ክፍል ፩📣

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉ስለ ድንግል ማርያም
👉ስለ ፍጹም ድንግልናዋ
👉አምላክን ስለመውለዷ
👉ስለ አማላጅነቷ እና ሌሎችም ጥያቄዎች መልስ ከፈለጋችሁ እነዚህን አዳምጧቸው

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ጳጉሜ 2


ከ72ቱ አርድእት የሆነ የከበረ ቅዱስ ቲቶ በዚች ዕለት አረፈ።

ቅዱሱ ባለፈ ሕይወቱ እግዚአብሔርን ባያመልክም በጠባዩ ግን እጅግ ቅንና ደግ ነበር። እግዚአብሔርም ይህን ቅን ሰው መልካም ስራውን ተመልክቶ በራዕይ ተገለጠለት።
ስለነፍስህ ተጋደል አለው።


ቅዱስ ቲቶም ተነስቶ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ። ጌታችንም በሚያደርጋቸውን አምላከዊ ስራ ተመልክቶ ፍጡር እንዳልሆነ ተረዳ። ሰማያዊና ዘላለማዊ ትምሕርቱን በሰማ ጊዜ  በራዕይ ''ስለ ነፍስህ ተጋደል።'' ያለው ምሥጢር አሁን ተገለፀለት። አምኖም ተከታዩ ሆነ።

ከዚህም በኋላ ከጌታችን እግር ለሦስት ዓመታት ተምሮ በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ በመላው እስያ ለስምንት ዓመታት ወንጌልን ሰብኳል። ዕድሜው በደረሰ ጊዜም በዚህች ዕለት አርፏል።

በረከቱ ይደርብን! አሜን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​ቅዱሱ ጲላጦስ

ብዙዎቻችን መስፍኑን ጲላጦስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጌታችን እንዳይሰቀል ከአይሁድ ጋር ሲከራከር እናውቀዋለን። የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ ነበርና አይሁድ እንቢ ሲሉት የክርስቶስን ንጽሕና መስክሮ: እጁንም ታጥቦ ሰጥቷቸዋል። የጲላጦስ ታሪክ ግን እዚህ ላይ አያበቃም።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሳ በኋላ ትንሳኤውን በራዕይ ገልጦለት አይሁድን ተከራክሯቸዋል። ውሸታም ወታደሮችንም ቀጥቷል።

ጲላጦስም ከሚስቱ አብሮቅላ ስለ እግዚአብሔር ገናንነት እየተጨዋወቱ ኹለቱም ስለ ትንሣኤው ሲነጋገሩ ከደመና ድምፅ ተሰማ።

ከደመናውም ጲላጦስ ሆይ በዚኽ ደመና ላይ በክብር ተቀምጠው ወደ ገነት የሚወስዷቸውን እነዚህን ነፍሳት ታያለህን፡፡ ይኽም የሄሮድስ ወታደሮች ከመቶ አለቃው ጋራ በመንገድ የገደሏቸው ናቸው፡፡ እንደዚሁም አንተንም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ምክንያት በሮም አንገትህን በሰይፍ ይቈርጡሃል፡፡

የአንተንና የሚስትህ አብሮቅላን ነፍስ በዚኹ ዐይነት ክብር በደመና ተሸክመው ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ያሳርጓችኋል፡፡ ጲላጦስ ሆይ ፈጣሪህ ኢየሱስ ክርስቶስ ከዕፀ ሕይወት ሥር ያኖርሃልና አይዞህ ጽና የሚል ድምፅ ተሰማ፡፡

ድምፁም ይኽን ተናግሮ ከእነርሱ ዘንድ ተሠወረ፡፡ ጲላጦስም ስለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ አንገቱን ይቈርጡት ዘንድም እጅግ ተደሰተ፡፡ በመጨረሻም በሮም ቄሳር ተጠርቶ ከእሥራኤል እስከ ሮም ድረስ ሰብኮ በሮም አደባባይ አንገቱ ተሠይፏል።

ቅድስት እናታችን አብሮቅላም የዺላጦስ ሚስት ስትሆን ቁጥሯ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ነው። ጌታችንን ተከትላ ቤቷን ለሐዋርያት አስረክባ ቤተ ክርስቲያንንም በዘመኗ አገልግላ ዐርፏለች።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ ፦ መጽሐፈ ስንክሳር ሰኔ 25 እና ላሐ ማርያም
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

አልረሳውም ያንን ዕለት

አልረሳውም ያንን ዕለት
አልዘነጋው ያን ደግነት
እናቴ ሆይ ምልሽ ኪዳነ ምሕረት
እምዬ ሆይ ምልሽ ኪዳነ ምሕረት
ስላለኝ ነው ምክንያት/፪/

ለሠው ተናግሬ ያልተረዳኝ ሰው
ዕንባዬ በምሬት ከዓይኔ የሚፈሰው
የቤቴን ገመና ሁሉን ስነግርሽ
አዛኝት ነሽና እራራልኝ ልብሽ
አረሳው መቼም የአንቺን ደግነት/፪/
ውለታ አለብኝ ኪዳነ ምሕረት
አዝ
ልቤ በሐዘን ጠቁሮ ውስጤ እየደማ
መቅረዜ ሲጨልም ስዋጥ በጨለማ
በራፌን ዘግቼ ዝም ብዬ አለቅሳለሁ
ግን እኔ አቀርቅሬ እናቴ እልሻለሁ
ዘንበል አልሽልኝ ሠምተሽ ፆሎቴን/፪/
አልተጸየፍሽም ብቸኝነቴን
አዝ
እናት የለኝ ብዬ ከቶም አልከፋ
እኔስ አይቻለሁ ስትሞይኝ በተስፋ
ምድራዊዋ እናቴ ለጊዜው ነው ፍቅሯ
ያንቺስ ግን ልዩ ነው ኧረ ስንቱን ላውራ
ማርያም ማርያም ብል አልሠለችሽ/፪/
በልቤ ጽላት ስለ ታተምሽ
አዝ
ሲረበኝ መጥተሻል ሲጠማኝ ደርሰሻል
ለጎደለው ቤቴ በረከት ሆነሻል
ጭንቄም ቀለለልኝ ሐዘኔም ራቀ
ያስጨነቀኝ ጠላት ራሱ ተጨነቀ
መዳኒት ወልደሽ ዳንኩኝ ከህመሜ/፪/
ይኸው ዘመርኩኝ በምልጃሽ ቆሜ

ዘማሪ ዲ/ን ሙሉቀን ከበደ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

👉 ጳጉሜ ለምን እንጠመቃለን?
🎤 ቀሲስ ሄኖክ ወልደ ማርያም

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​​​በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ጾመ ዮዲት

በናቡከደነጾር ዘመነ መንግሥት ንጉሡ ሥልጣኑን መከታ በማድረግ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በግድ እያስገደደ እጅ መንሻ ይቀበል ነበር፡፡ የመንግሥቱን ትእዛዝ ያልተቀበለውንም እየገደለ፣ ጭፍሮቹ ኃያልነቱንና ገናናነቱን በዓዋጅ በጦር አዛዦች ጭምር እያሳወጀ፣ በርካታ የጦር ሠራዊቶችን አሰልፎ ከአይሁድ ከተማ ገባ፡፡

በዚያም ነዋሪዎችን በማስፈራራት የመንግሥቱን ትእዛዝ ያልተቀበሉትን ሁሉ እያሳደደ ስላስጨነቃቸው ማቅ ለብሰው፣ አመድ ነስንሰውና ድንጋይ ተንተርሰው ወደ ፈጣሪያቸው በመጮህ መለመን ጀመሩ። በጭካኔ የተሞላው የጦር አበጋዙ ሆሎፎርኒስም ይበልጥ እጅግ እንዲሰቃዩ ውኃ የሚቀዱበትን ስፍራ ተቆጣጠረው፤ በግዴታ ማርኮም እጅ እንዲሰጡ እንዳደረጋቸው በመጽሐፈ ዮዲት ፪፥፪ ላይ ተጽፏል፡፡

በአካባቢው ይኖር የነበረ ዖዝያን የተባለ አንድ ሰው የአባቶቻቸው አምላክ ጸሎታቸውን እንዲሰማቸው ለአምስት ቀናት በትዕግሥት ይጾሙና ይጸልዩ ዘንድ ሕዝቡን መከራቸው፤ እነርሱም በትዕግሥት ሊጠብቁ ተስማሙ፡፡

የእስራኤል ልጆች የናቡከደነጾርን ጦር ብንችል ተዋግተን እንረታለን፤ ካልሆነም እጅ እንሰጣለን በማለት ይመካከሩ ጀመር።
በዚያን ጊዜ ባሏ የሞተባትና በንጽሕና ተጠብቃ፣ በጸሎትና በሕገ እግዚአብሔር የምትኖር ዮዲት የተባለች ሴት ነበረች። (ዮዲት ፯፥፲)

እግዚአብሔርን የምትፈራ ብቸኛዋ ሴት እርሷ ነበረችና ምክክራቸውን ስትሰማ

ለምን እግዚአብሔር ያድነናል አትሉም ብላ ገሠጸቻቸው፡፡


ማቅ በመልበስ፣ አመድ በመነስነስና ድንጋይ በመንተራስም ሱባኤ ገባች። በሦስተኛው ቀንም እግዚአብሔር አምላክ ሕዝቧን የምታድንበትን ጥበብ ገለጸላት፤ ዮዲትም እግዚአብሔር የሰጣትን ውበት ተጠቅማ ሕዝቧን ከጥፋት የምትታደግበትን ጥበብ ተረዳች።

የክት ልብሷን ለብሳ፣ ሽቱ ተቀብታና ተውባ የጠላት ሠራዊት ወዳሉበት የጦር ሰፈር በድፍረት አመራች፡፡ ሠራዊቱም ውበቷን አይተው እጅግ በመደነቅ
«ይህችስ ለአለቃችን ትገባለች» ተባብለው ከጦር መሪያቸው ዘንድ ወሰዷት።


እርሷም ቀድማ ማምለጫ መንገድ አዘጋጅታ ነበርና ወደ አዛዡ ከገባች በኋላ
«ክቡር ጌታዬ ሆይ ርስት ተወስዶብኛል፤ እንድትመልስልኝ አስቀድሜ ደጅ ልጠና መጥቻለውና ርዳኝ፤ ትብብርህ አይለየኝ» አለችው፡፡

በስሜት ፈረስ ታውሮ የነበረው የሠራዊቶቹ አዛዥም የጠየቀችውን እንደሚፈጽምላት ቃል ገባላት።

ባማረ ድንካን እንዲያስቀምጧት ሎሌዎቹን አዘዘ። ዮዲትም የተሰጣትን ጥበብ ተጠቅማ፣ መውጣት ስትፈልግ የምትወጣበትን እና የምትገባበትን ዕድል በእግዚአብሔር አጋዥነት ዐወቀች፡፡ ከቀናት በኃላ የጦር አበጋዙ ለሠራዊቱ የምሳ ግብዣ አዘጋጅቶ ዮዲትን ከጎኑ አስቀመጣት፤ ከበሉና ከጠጡ በኋላም ሁሉን ሰው አስወጣ፤ እልፍኙን በመዝጋት ከእርሷ ጋር ብቻውን ሆነ፤ ነገር ግን እንቅልፍ ጣለው፡፡ (ዮዲት ፰፥፪)

እርሷም ወደ አምላኳ ጸለየች፤ ፈጣሪዋ እንዲረዳትም አጥብቃ ለመነች። በኋላም ከራስጌው ሰይፍ አንስታ አንገቱን ቀላችው፤ በድኑንም ከመሬት ጣለችው። የሆሎፎርኒስን ሞት ሠራዊቱ ሲሰሙ አውራ እንደሌለው ንብ ተበተኑ፤ ከፊሎቹ ሞቱ።

እስራኤላውያንም ከሞት ተርፈው በእግዚአብሔር ኃይል ድል አደረጉ፤ በደስታም ፈጣሪያቸውን አመሰገኑ። ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪክ የሚያስረዳን ዮዲት ጠላቶቿን ድል ያደረገችው በጾምና በጸሎት እንደሆነ ነው፡፡

ለእኛም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ምንም እንኳ ወርኃ ጳጉሜን የፈቃድ ጾም ቢሆንም በሀገራችን የተጋረጠውን ችግር እናልፍ ዘንድ በፈቃደኝነት እንጾማለን። እግዚአብሔር አምላካችን ለሁላችንም ጥበብ ሰጥቶናል።

ይህም ችግሮችን ሁሉ የምንፈታበት መንገድ ነው። በዚህም የዓመተ መሸጋገሪያና የክረምቱ ወር ማብቂያ በመሆኑ ዕለተ ምጽአት ስለሚታሰብበት በየዓመቱ በጳጉሜ ወር ከሌሊት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያን ተገኝተን ጠበል በመጠመቅ፣ በማስቀደስና በመጸለይ እንዲሁም ሥጋ ወደሙን በመቀበል ልናሳልፍ ይገባል።

ዕለተ ምጽአትም ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው ዓለም መሸጋገሪያችን ነውና በቀኙ እንቆም ዘንድ እንጾማለን፡፡

የሚመጣውን አዲስ ዘመንም በንጽሕና ለመቀበል ስላለፈው ዓመት ኃጢአታችን ንስሓ የምንገባበት ጾምም ነው።
ከተጋረጠብን ችግር እግዚአብሔር ያድነናል

በማለት ልክ እንደ ዮዲት ሱባኤ ገብተን፣ ማቅ ለብሰን፣ አመድ ነስንሰንና ድንጋይ ተንተርሰን አብዝተን ልንጾምና ልንጸልይ ይገባል፡፡ ሊለያየን፣ ሊነጣጥለን፣ ሊበታትነን እና ሊገድለን ካሰበው እንዲሁም ፍቅርን፣ መተሳሰብንና አንድነትን ሊነፍገን ከቃጣው ጠላትና ሃይማኖታችንን ሊያስተወን ከሚመጣ ፀረ ሃይማኖት እንድናለን።

ስለዚህ ከፊታችን ያለችውን ስድስቱን የጳጉሜን ቀን በፍቅር፣ በአንድነትና በሃይማኖት ጸንተን፣ ጾመን፣ ጸልየን ለዘመነ ማቴዎስ እንድንደርስ እግዚአብሔር አምላካችን ይርዳን፤ አሜን።

ምንጭ፦ ከማኅበረ ቅዱሳን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ምን አለ ያጎደልክብኝ

ምን አለ ያጎደልክብኝ
ሳትነፍገኝ ሁሉን ሰጠኸኝ
ሁነኸኝ እናት እና አባት
አለፈ ብዙ ዘመናት (2)

አዝ

አኖርከኝ ዛሬም በጤና
ወጥቸ ገባሁ በደና
መንገዴን ሰጥቸሀለው
ስትመራኝ እከተላለው
አዝ

ወረት አታውቅም ጌታየ
መች ቀረ ፈሶ እንባየ
ህይወቴ በመድሀፍህ ነው
መፍራቴ ከቶ ለምን ነው
አዝ

አውቀኸኝ ሳሰራኝ ገና
ሞልተኸኝ ቅኔ ምስጋና
ካንተ ነው የተቀበልኩት
በመዝሙር የሰለጠንሁት
አዝ

መዛሌ በውሀ ጥም
በባእድ ሀገር መድከም
በብዙ ስጋት ተጉዤ
ቁሜአለው ስምህን ይዤ
አዝ

በትዳር በልጅ ባርከኸኝ
የልቤን ደስታ ሰጠኸኝ
ስለያዝኩ ጌታ ያንተን እጅ
ተባልኩኝ የንጉሱ ልጅ

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ኑ በብርሃኑ ተመላለሱ

ኑ በብርሐኑ ተመላለሱ ተመላለሱ
ኑ በብርሐኑ በብርሐኑ ተመላለሱ
የፍቅርን ሕይወት እንድትለብሱ
ኑ በብርሐኑ ተመላለሱ/፪/

አዝ

ሁሉን በሚችል በአምላክ ጥላ
በእረፍት ውሃ ሥር አርፈናልና
ሠላም እና ፍቅር ሕይወት በሚሰጥ
ወደ ጌታችን እንሂድ እንሩጥ
አዝ

ምሕረት እና ፍርድ በእጁ የያዘው
የሠላም አባት መድሐኔዓለም ነው
ሕይወት የሆነን በመስቀል ውሎ
ብርሐን ሠጠን ጨለማን ሽሮ
አዝ

የሚያስደነግጥ የሚያስጨንቀን
ይጠፋልና እርሱን ተማጽነን
በቀን ከሚበር ፍላጻ ሁሉ
ይታደገናል በቅዱሥ ቃሉ
አዝ

እግርህ በድንጋይ እንዳይመታ
በፈተና ውስጥ እንድትበረታ
መቅሰፍት ከቤትኽ እንዲከለከል
ይጠብቅሃል ሌሊት እና ቀን
አዝ

ሥሙን ያወቀ ሕይወት መሆኑን
ይመላለሳል ከሐይል ወደ ሐይል
ረጅም ዕድሜ ይጠግባል እርሱ
ብርሐን ይሆናል የጸጋ ልብሱ
አዝ        

አቤቱ አንተ ተሥፋ ነህና
የምትመግብ የፍቅር መና
ማዳንህ እኛን አስደስቶናል
እንዲህ ያለ ክብር ከየት ይገኛል

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የማይጠፋው

የማይጠፋው የዘላለም ህይወት
የመይፈርሰው የፀና መሠረት
የእግዚአብሔር ቃልን በወለደችልን /2/
በድንግል ማርያም ተገኘልን /2/

አዝ

የመውለድ ችሎታዋ የማይመረመር
ድንግል እናት መሆኗን የማይችል ሊነገር
ዘሩያልተዘራባት ሆናለችና እርሻ
ደስታን አስገኝታለች የሀዘንን መርሻ
አዝ

ከእርሷ የሆነውን ከማድነቅ በቀር
ለስሟ ከመሰዋት ምስጋናና ክብር
ከህሊና በላይ ነው ግብረ መንፈስ ቅዱስ
አይኖራትም ምሳሌ እስከ አፅናፍ ድረስ
አዝ

የመላክት ደስታቸው ጌታን የወለድሽ
የነበያተሰ ዜናቸው ነፅህት የሆንሽ
ክብርና ገናናነትሽን እንናገራለን
በማይነጥፍም መስጋና እናገንሻለን
አዝ

በድንግልና ፀንሶ መዉለድ በድግል
ከቶ ለማን ተሰጠ ከሴቶች መሀል
አለማትም ተፈጥረው ዘመን ቢቆጠር
ለማንም አልተቻለም ከማርያም በቀር

ዘማሪ ዲ/ን ሱራፌል ስዩም
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ቀዋምያን

ቀዋምያን ለነፍሳት እሙንቱ ሊቃናት 
ኡራኤል ወሩፋኤል/2/ 
ይትፌነዉ ለሣህል/2/
እምኀበ ልኡል/2/ 

ትርጉም
ለነፍሳት የቆሙ እነዚህ መላእክት 
ኡራኤልና ሩፋኤል/2/ 
ከልኡል ዘንድ ለይቅርታ/2/
ይላካሉ ከልኡል/2/

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ነገረ ማርያም ክፍል ፫
እነሆ🤲🤲🤲

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

📣የዛሬው ምሽት ስለ ነገረ ማርያም የነበረን ትምህርት በእዚህ ላይ እናበቃለን📣


ቅዳሜ ምሽትም በተመሳሳይ ሰዓት 2:00 ላይ ቀጣዩን ክፍል የምንቀጥል ይሆናል። ሁላችሁም ቅዳሜ 2:00 ላይ ጠብቁን።


👉እስከ አሁን የነበረውን ትምህርት ከወደዳችሁት በኮመንት ላይ አሳውቁን።

ከ8,000 ሰው በላይ ይሄንን ቻናል በአንድ ቀን ውስጥ እየተመለከተው ግን ለምትወዷቸው ኦርቶዶክሳዊያን እህት ወንድሞቻችሁ የእኛን ቻናል እንዲቀላቀሉ ለምን እንደማትልኩላቸው አላውቅም።


🤲እባካችሁ ድንግል ማርያምን አትወዷትም? ጓደኞቻችሁስ በደንብ ፍቅሯ እንዲያድርባቸው አትፈልጉም? ለምን አትልኩላቸውም?


አሁን ድንግል ማርያምን ከወደዳችኋት ለ20-30 ጓደኞቻችሁ አሁን በኃላፊነት የቻናላችንን ሊንክ ላኩላቸው አሁን። ከእዛም ከላካችሁ በኋላ ልከናል ብላችሁ ኮመንት አድርጉ🙏🙏🙏

ሊንኩ 👉 /channel/ortodoxmezmur
/channel/ortodoxmezmur
/channel/ortodoxmezmur

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

"እነሆ የጌታ ባርያ" ሉቃ 1:38

       🤲ክፍል ፬🤲

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

የእመቤታችን የድንግል ማርያም ንጽሕና እና ቅድስና እንዴት ነው?🤔

📣ክፍል ፪📣

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

🤲🤲🤲ስለ ነገረ ማርያም🤲🤲🤲


ዛሬ ማታ 2:00 ላይ ትምህርታችንን የምንጀምር ስለሚሆን ሁላችሁም 2:00 ላይ ተሰብስባችሁ እንድትገኙ እናሳስባለን።

መምህር ዲያቆን ዳግማዊ ሰለሞን

ይሄንን ትምህርት ጓደኞቻችሁ እንዲማሩ ይሄንን ማስታወቂያ ላኩላቸው ከታች ያለውን ሊንክ በመግባት ይቀላቀሉን።


🌙 የማታ ሰው ይበለን 🌙

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ድል አለ በስምህ
በስልክ የተቀዳ

ድል አለ በስምህ
ድል አለ በቃልህ /2/
ተራራው ይናዳል አማኑኤል ስልህ
ባህር ይከፈላል መድሀኔዓለም ስልህ

ቃዴስን ታላቁን በርሀ
አለፍነው ሳንጠማ ውሀ
ፈርኦንን ከባህር የጣለው
ጌታዬ የጸና ስምህ ነው
አምላኬ የጸና ስምህ ነው
አዝ
በእልልታ ቢፈርስ እያረኮ
ጠላትም ቢወድቅ ተማርኮ
ቢሰጠን ለእኛ ከተማው
የሆነው ሁሉ ካንተ ነው/2/
አዝ
ከክፋት ሁሉ ብናመልጥ
የማረ ውሀ ቢጣፍጥ
ብንበላ መና ከሰማይ
ስለ ሆንክ ነው አ ዶናይ
ስለ ሆንክ ነው ሁሉን ቻይ
አዝ
የቆምነው ዛሬ በህይወት
ሰምህን አድርገን ነው ጉልበት
ከሜዳ ተጠርተን ብንነግስ
ሆነኸን ነው ክብርና ሞገስ

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

በዝማሬ ዳዊት ቻናል የምትለቋቸው መልዕክቶች እኛ ጋር Not supported ነው የሚለን ብላችሁ መልዕክት ለላካችሁልን ተከታታዮች በሙሉ፤ እባክዎ ከስር ባስቀመጥነው ሊንክ የቴሌግራም መተግበሪያዎን ያዘምኑት /Update/ ያድርጉት።

https://play.google.com/store/apps/details?id=org.telegram.messenger

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ኪዳነ ምህረት ልዩ ነሽ ለኔ

ኪዳነ ምህረት ልዩ ነሽ ለኔ
ሳዝን ስጨነቅ አትራቂኝ ከጎኔ
የችግሬ ደራሽ እመ እግዚአብሔር
ቃል ኪዳንሽ ይርዳኝ ካንቺ ጋር ልኑር(፪)
አዝ
የአዳም ተስፋው ነሽ የሴት ቸርነቱ
ኪዳነምህረት ነሽ የኖህ ምልክቱ
አዳም ደጅ የጠናሽ ሲገባ ንስሀ
ኖህም ድኖብሻል ከጥፋቱ ውሃ
አዝ
የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ
ማርያም አንቺ ነሽ የፈጣሪ እናቱ
የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ
እመብርሃን ስሚኝ ልመናየን ሁሉ
አዝ
የሰሎሞን አክሊል የዳዊት ዝማሬ
ድንግል መሆንሽን ትመስክር ከንፈሬ
ለተጠማው ውሻ የሚራራው ልብሽ
ለኔም እራርቶልኝ አስታርቂኝ ከልጅሽ
አዝ
የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ
ማርያም አንች ነሽ የፈጣሪ እናቱ
የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ
እመብርሃን ስሚኝ ልመናዬን ሁሉ

ዘማሪት ሲስተር ፋሲካ መኮንን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ጳጉሜ 1


በዚች ዕለት ቅዱስ ዮሐንስ ወደ እሥር ቤት ገብቷል

ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

ንጉሡ ሔሮድስ የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሔሮድያዳን በማግባቱና በመሰል ክፋቶቹ ቅዱስ ዮሐንስ ይገስጸው ነበር። ፊት አይቶ የማያዳላ ነውና ገሰጸው።

ሔሮድስ ቅዱሱን ይፈራው: ያከብረውም ነበር። በኋላ ግን ፈቃደ ስጋው ስላየለበት: በተለይ ደግሞ ከሰባት ቀናት በኋላ ልደቱን ሲያከብር እንዳይረብሸው በመስጋት በዚህች ቀን በወታደሮቹ አስይዞ እስር ቤት ውስጥ አስገብቶታል።

ጌታችን ኢየሱስ ለሕዝብ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ ምን ልታዮ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን...እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም...ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ተናገሩ። ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ ነው። (ማቴ 11÷7-15)


ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ

የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ: በማኅጸን ሳለ መንፈስቅዱስ የሞላበት: በበረኀ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ:እሥራኤልን ለንሰሐ ያጠመቀ:ጌታውን ያጠመቀ:የጌታችንን መንገድ የጠረገና ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ቅዱስ ሰው ነው።

በረከቱ ይደርብን! አሜን
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ሰላም ውድ የዝማሬ ዳዊት ተከታታዮች በዝማሬ ዳዊት ገጽ የሚለቀቁትን ለወዳጅዎ ለማጋራት ካሰቡ ከታች ያስቀመጥነውን ቅደም ተከተል ተከተሉ።

1. ማጋራት የፈለጉትን መልዕክት ሲነኩ ከሚዘረዝርልዎ አማራጭ መካከል Copy link የሚለውን ይንኩት።

2. ለሚፈልጉት ሰው ወይም ማጋራት ወደሚፈለጉበት ቻናል ወይም ግሩፕ ላይ Copy ያደረጉትን ወስደው Past ማድረግ።

3. የዝማሬ ዳዊት ገጽን ከፍተው ሲገቡ ከስር UNMUTE የሚል ከሆነ የሚታይዎት ወደ MUTE መቀየርዎን አይዘንጉ።

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን! አሜን።

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ዮሐንስ መጥምቅ

መብልዕ ዜና ፍቅርከ ወነገረ ጽድቅከ ስቴ(፪)
ያስተፌስህ መላዕክተ ወሰብአ መዋቴ(፪)

ዘካርያስ አየ የገብርኤልን እውነት
በእርጅና ዘመንዋ ስትወልድ ኤልሳቤጥ
የልቦና መንገድ ከጥርጥር ጸድቶ
ዓለም ተደሰተ ልደትህን ሰምቶ

ዮሐንስ መልአክ ለእግዚአብሔር ቅሩቡ
ወርቀ ኪዳንከ ለነዳይ መዝገቡ

አዝ
እንደምን ሰገደ በረታ ጉልበትህ
መለኮትን ጸንሳ ድንግል ስትጎበኝህ
ነፍሴ ታመስግንህ ትዘምር ልሳኔ
ውዳሴህን ላንሳ ላቅርብልህ እኔ
ዮሐንስ ዘኮንከ ደመና ሰማይ ኮናኔ
አዝንም መና አእምሮ ወህብስተ ወጥበበ መድኃኒት

አዝ
የራጉኤል ትጋት የኢዮብ መታመን
መች ቻለ ሊዳስስ ነደ ነበልባሉን
በዮርዳኖስ ባሕር አሳየህ መስዋዕቱን
የዓለምን ኃጢአት  የሚያስወግደውን
ዮሐንስ ጠቢብ ሐመረ ክርሰቲያን አዳፊ
ኢይትዔየረከ በዕበይ በሰማይ ሱራፊ

አዝ
ከሴቶች ልጆች መሃል ዮሐንስ በለጠ
ናቡቴን መሠለው ለእውነት የተሰጠ
በመንፈስህ ትጉህ በኤልያስ ኃይል
ሳትፈራ መሰከርክ የእውነትን ቃል
ዮሐንስ አንተ ጽልመተ አበሳ ሰዳዴ
በአየረ ሰማይ ይጸርሕ ቃልከ ዓዋዲ

አዝ
መስክሪ ሄሮድያዳ የዮሐንስ ነገሩን
ታምኖ ቢሞት እንኳን በክንፍ መብረሩን
ምንኛ ታላቅ ነው ዮሐንስ ተጋድሎህ
ፈጥነህ ትደርሳለህ ዛሬም ለሚጠሩህ
ዮሐንስ ልብ መዝገበ ጥበብ ወአእምሮ
ፍጹመ መነንከ አብያተ ዘውቅሮ

      
ነብየ ልዑል ሰማዕት ወጽድቅ ካህን ሐዋርያ
መምህር ወመገስጽ  ባሕታዊ ድንግል መጥምቀ መለኮት
ርዕሰ ዓውደ ዓመት ጸያሔ ፍኖት
አርኩ ለመርአዊ ዮሐንስ መጥምቅ (፫)

💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ነሐሴ 30


በዚህች ዕለት ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ የሆነው ታላቁ ነቢይ ሚልክያስ አረፈ።

እግዚአብሔር አምላክ በነቢዩ አንደበት አድሮ እንዲህ ይለናል።
ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም። የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው። ትንቢተ ሚልክያስ 3:8


እንዴት አድርጌ ነው ከ5ሺህ ብር ደሞዝ በዛ ላይ የኑሮ ውድነቱ ተጨምሮበት አስራት የማወጣው? ብላችሁ ብትጠይቁም እግዚአብሔር በነቢዩ አድሮ እንዲህ ይለናል።
በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፤ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። ትንቢተ ሚልክያስ 3:10


ቅዱስ ሚልክያስም በበጎ ተጋድሎው እግዚአብሔርን ከአገለገለ በኋላ በዛሬዋ ዕለት ከዚህ ዓለም በመፍለስ በሰላም አረፈ። ሚልክያስ ማለት መልዐክ አንድም የተላከ ማለት ነው።

በረከቱ ይደርብን! አሜን
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ዘማሪ ዲ/ን ሱራፌል ስዩም አባክህን ይህን እየተመከትክ ከሆነ ወይም የምታውቁት ካላችሁ ከታሽ ባስቀመጥነው አድራሻ መልዕክት ይላክልን። አድራሻህ ከስልካችን ስለጠፋብን ነው።

📩 @Zimaredawitmessanger

Читать полностью…

ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ነሐሴ 29

በትሕትናው፣ በትዕግስቱ ይበልጡንም ደግሞ በመታዘዙ የሚታወቀው አባት ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር የፍልሰቱ ዕለት ናት። በአንድ ወቅት አባ ባይሞይ ቅዱስ ዮሐንስን ጠራውና ተፈልጦ የወደቀ ደረቅ እንጨት ሠጠው ከዚያም
ትከለውና እንዲያፈራ አድርገው። ከዚያ አምጥተህ አብላኝ

አለው። ይህ ነገር ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪ መሆኑን እያወቀ ቅዱስ ዮሐንስ እሺ ብሎ ወስዶ ተከለው።  ከ10ኪ.ሜ በላይ እየተጓዘ ወሃ እየቀዳ ለ2 ዓመታት ሳይታክት አጠጣው። በሦስተኛው ዓመት ግን ለመለመ ወስዶም ለመምህሩ
አባቴ እንካ ብላ ብሎ ሰጠው። መምህሩም ወዲያው ያን ፍሬ ታቅፎ ወስዶ ለገዳሙ መነኮሳት
ንሱ ብሉ: በረከትንም አግኙ:: ይህ የዛፍ ሳይሆን የመታዘዝ ፍሬ ነው አላቸው።


ቁመቱ እጅግ ያጠረ: ጽድቁ ግን ከሰማይ የደረሰ ቅዱስ ዮሐንስን ሰላም ሰላም እንለዋለን


በረከቱ ይደርብን! አሜን
💚 @ortodoxmezmur 💚
💛 @ortodoxmezmur 💛
❤️ @ortodoxmezmur ❤️

Читать полностью…
Подписаться на канал