nejashipp | Unsorted

Telegram-канал nejashipp - Nejashi Printing Press

4356

ይህ የነጃሺ ማተሚያ ቤት ኦፊሻል የቴሌግራም ቻናል ነው። የተለያዩ ጠቃሚ መልዕክቶችን፣ አዳዲስ የህትመት ውጤቶቻችንና አገልግሎቶቻችንን ተከታተሉን፣ ለሌላውም ሼር አድርጉ።

Subscribe to a channel

Nejashi Printing Press

በዚያ ዕለትም ‘ሠንየተል ወዳዕ’ በተባለው ሥፍራ በርካታ የመዲና ሕዝብ ተሰብስቦ ምስጋናና ውዳሴ እያሰማ ተቀበላቸው፡፡ መዲና በታሪኳ እንደዚያ ቀን የደስታ እልልታ ገጥሟት አያውቅም፡፡
ዕለቱ በእርግጥም ኢስላም ጠባብ ከሆነው የመካ አስጨናቂ ሕይወት ወደ ሠፊውና አስደሳች ወደ ሆነው የመዲና ሕይወት ሽግግር ያደረገበት ታሪካዊ ቀን ነበር፡፡ የመዲና ሕዝቦች የአላህን ታላቅ በረከትና ጸጋ በደስታ ተቀብለው ምስጋናና ውዳሴ ያሰሙበት ድንቅ ዕለት፡፡ ለምን አመስጋኝ አይሆኑ!! ምድራቸው ታሪካዊውን የኢስላም ብርሃን ለዓለም እንድታደርስ ተመርጣለች፡፡ የመጨረሻውንና የነብያት ሁሉ መደምደሚያ የሆኑትን ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) ተቀብላ ለማስተናገድ ከመታደል የበለጠ ምን ልቅና ትሻለች! ዕድለኛ ከተማ፡፡ በጊዜው ሁሉም “የአላህ መልዕክተኛ! የአላህ መልዕክተኛ! ሙሐመድ!” እያለ ደስታውን ሲገልጽ ይታይ ነበር።

ዝነኛው የጠለዐል በድሩ ዐለይና ነሺዳም በዚያ ቀን ተነሸደ።

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በታሪክ ገጾች የሚስተካከለው በሌለ የደመቀ አቀባበል መዲና ከገቡ በኋላ የሚያርፉበትን ሥፍራ ራሳቸው መወሰን አልፈለጉም ነበር፡፡ ከዚያ ይልቅ “ግመላቸው መለኮታዊ ምሪት” እንዳላትና እርሷ የምታርፍበትን ቦታ ትክክለኛው ማረፊያቸው እንደሆነ በማሳወቅ ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡ በመጨረሻም የአቡ አዩብ አል-አንሷሪ (ረ.ዐ) ቤት ሲደርሱ አቡ አዩብ (ረ.ዐ) ተሸቀዳድመው ጓዛቸውን በመያዝ እቤታቸው አስገቡት፡፡

ከ" ለዓለማት እዝነት" መጽሐፍ
ትርጉም : አቡ ቢላል

/channel/Nejashipp

nejashibooks" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@nejashibooks

https://nejashibooks.com/

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ነጃሺ ማተሚያ ቤት ከዚህ በታች በተዘረዘረው ክፍት የስራ መደብ ዝርዝር መሰረት አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
*የስራ መደቡ መጠሪያ:- የማርኬቲንግ ባለሙያ
*ብዛት:-1
*የት/ት ደረጃ:- በማርኬቲንግ ወይንም ተዛማጅ የት/ት ዘርፍ የተመረቀች/ቀ
*የስራ ልምድ:-2 አመትና ከዚያ በላይ
*ፆታ:-ሴ/ወ
*ደሞዝ:-በስምምነት

አመልካቾች የትምህርት ማስረጃችሁንና የስራ ልምዳችሁን 09_45_85_85_85 በቴሌግራም ወይንም
nejashipress@gmail.com ላይ መላክ ትችላላችሁ
ነጃሺ ማተሚያ ቤት

/channel/MuhammedSeidAbx

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

በአያመ ተሽሪቅ ውስጥ የሚፈፀሙ ሥርዓቶች
*
ከዒድ ቀን በኋላ ያሉ ሦስቱ የዚል-ሒጃ 11ኛ፣ 12ኛ እና 13ኛ ቀናት ቀናት “አያመ ተሸሪቅ” በመባል ይታወቃሉ፡፡ የዒድ ቀናቶች ናቸው፡፡ በነኚህ ቀናት ውስጥ ይበላል፣ ይጠጣል፣ የጠጠር ውርወራ ሥርዓት ይከናወናል፡፡


ውርወራው ሰባት ሰባት ጠጠሮች በሦስት ቦታዎች ላይ በመወርወር ይከናወናል።
ቦታዎቹና ቅደም ተከተላቸውም "ጀምረቱል-ኡላ" (የመጀመሪያው ጠጠር መወርወሪያ) "ጀምረቱል ውስጧ" (የመሃለኛው) ጠጠር መወርወሪያ እና "ጀምረቱል ዐቀበህ" የመጨረሻው የጠጠር መወርወሪያ ቦታዎች ናቸው።
የመወርወሪያ ጊዜም ፀሐይ ከእኩለ-ሰማይ ወደ ምእራብ ከወረደች በኋላ ጀምሮ እስከምትጠልቅ ድረስ ባለው ወቅት ነው።

በ "ጀምረቱል ኡላ እና በ ጀምረቱል ውስጧ የጠጠር መወርወሪያ ሥፍራ ላይ ጠጠሮችን ወርውሮረው እንደጨረሱ ወደ ቂባላ ዙሮ ዱዓእ ማድረግ ይመረጣል።
በ "ጀምረቱል_ዐቀበህ" (በመጨረሻው) የጠጠር መወርወሪያ ስፍራ ላይ ግን ጠጠሮችን ወርዉሮ መመለስ እንጂ ዱዓእ አይደረግም።

ትንሹን፣ መካከለኛውንና ትልቁን (የመጨረሻውን) የጠጠር ውርወራ ሥርዓት መፈፀም ተገቢ ነው፡፡ ለእያንዳንዳቸው ሰባት ሰባት ጠጠሮች ይወረወራል፡፡
እያንዳንዱን ጠጠር ሲወረወር ተክቢራ በማድረግ ይወደዳል፡፡ ሰባቱንም ጠጠሮች አከታትሎ መወርወር ሱንና ነው፡፡

የውርወራውን ሥርዓት በቅደም ተከተል መፈፀሙ መስፈርት ነው፡፡ በትንሹ ይጀምራል፡፡ መካከለኛውን ያስከትላል፡፡ በትልቁ ያጠናቅቃል፡፡

ጠጠሮች በሚወረውሩበት ገንዳ እና በሰውዬው መካከል ሦስት ክንድ እና ከዚያ በላይ ርቀት መኖሩ ሱንና ነው፡፡ ርቀቱ ከዚያ ያነሰ ከሆነ መጣል እንጅ መወርወር አይባልምና፡፡

የጠጠር ውርወራ ሥርዓት የሚጀመርበትን ወቅት በሚመለከት ታላቁ የውርወራ ሥርዓት ከዒድ ሌሊት አጋማሽ በኋላ የሚጀመር ሲሆን ሦስቱም ከዒድ ቀን አጋማሽ በኋላ ይጀመራሉ፡፡ በአያመ ተሸሪቅ የመጀመሪያው ቀን ተጀምረው በመጨረሻው (ዒድ በዋለ በአራተኛው ቀን) ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ይጠናቀቃሉ፡፡

ሐጅ አድራጊ ጠጠር መወርወር ሲጀምር ‹ለበይክ…› ማለቱን ማቆም ይኖርበታል፡

ከሐጅና ዑምራ መጽሐፍ

/channel/Nejashipp

nejashibooks" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@nejashibooks

https://nejashibooks.com/

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

https://vt.tiktok.com/ZSxjUouJ9/

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

እጅግ በርካታ የኢስላም ሊቃውንት አርባ ምርጥ ሐዲሦችን ለመሰብሰብ ጥረት አድርገዋል፡፡ ከሁሉም ግን በዓለም አቀፍ ደረጃ የተሳካላቸውና ኪታባቸው በያንዳንዱ ሙስሊም ቤት ገብቷል የሚባልላቸው ታላቁ ሸይኽ ኢማም ነወዊ ናቸው፡፡ ስብስባቸውም አርበዒን አን-ነወዊ “የነወዊ አርባ ሐዲሥ” በመባል ይታወቃል፡፡ ከስብስብ ሐዲሣቸው መካከል አንዱን እንጋብዛችሁ፡-

ሀያ ሦስተኛ ሐዲሥ
አቡ ማሊክ አልሓሪሥ ኢብኑ ዓሲም አል-ዐሸዐሪይ (ረ.ዐ) እንዳወሩት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
“ንፅህና የእምነት ግማሽ ነው፡፡ አልሐምዱሊላህ ማለት ሚዛንን ትሞላለች፡፡ ሱብሓነሏህ ወልሐምዱሊላህ በሰማይና በምድር መካከል ያለውን ክፍተት ይሞላሉ፡፡ ሶላት ብርሃን ናት፡፡ ምፅዋት የእምነት ማረጋገጫ ነው፡፡ ትዕግስት ወገግታ ነው፡፡ ቁርአን ይመስክርልሃል ወይም ይመሰክርብሃል፡፡ እያንዳንዱ ሰው (ባለበት ቦታ) ይማለዳል ሕይወቱን (ለአላህ) በመሸጥ ነፃ ያወጣታል፤ ወይም ወንጀልን በመስራት ያጠፋታል፡፡”
(ሙስሊም ዘግበውታል፡፡)

/channel/Nejashipp

nejashibooks" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@nejashibooks

https://nejashibooks.com/

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

ከጠቢባን አንደበት
****
ዑመር ኢብኑ ዐብዱልዐዚዝ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹አላህን የሚፈራ ሰው አላህ ሁሉም ነገር እሱን እንዲፈራው ያደርጋል፡፡ አላህን የማይፈራ ሰው ደግሞ ሁሉንም ነገር ይፈራል፡፡›

ሰልማን አልፋሪሲ (ረ.ዐ.) እንዲህ ብለዋል፡-
‹የምትመኛቸውን ነገሮች ማግኘት የምትችለው ስሜትህ የሚፈልገውን ነገር በመተው ብቻ ነው፡፡ ተስፋ የምታደርገውንና የምታልመውን ነገር የምትጨብጠው በምትጠላው ነገር ላይ ስትታገስ ነው፡፡ ንግግርህ አላህን ማውሳት ይሁን፡፡ ዝምታህ ማስተንተን፣ እይታህ ማስተዋል የተሞላበት ይሁን፡፡ ዱንያ ትቀየራለች፡፡ ድሎቷም ሆነ ደስታዋ ይለወጣል፡፡ በሷ አትታለል፡፡ ቤትህ መስጅድ ይሁን!›

ዐብዱላህ ኢብኑ አልሙባረክ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹አስተዋይና ብልህ ሰዎች ስድስት ነገሮችን አያምኑም፡፡ ያለፈ ወንጀላቸውን በተመለከተ አላህ ምን ሊያደርጋቸው እንደሚችል፣ ከእድሜያቸው የቀረው ክፍል ስንት ጥፋቶችን ይዞባቸው ሊመጣ እንደሚችል፣ የተሰጣቸው ችሮታና ጸጋ ለፈተና ይሁን ለማዘናጋት ስለመሆኑ፣ መልካምና ቆንጆ ነገር መስሎ የሚታያቸው ነገር በርግጥም መልካም ስለመሆኑ፣ አሁንም አሁንም ሊመጣባቸው ከሚችል የቀልብ መንሸራተት፣ ሳያውቁና ሳያስቡ ድንገት በዐይን ብልጭታ ሊነጠቁ ከሚችሉት እምነታቸው፡፡›

ፉደይል ኢብኑ ዒያድ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹አላህን የሚፈራ ሰው፤ ለሱ ያለው ፍራቻ መልካም ወደተባለ ነገር ሁሉ ያመላክተዋል፤ ይመራዋል፡›

ፉደይል ኢብኑ ዒያድ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹አላህን የሚፈራን ሰው ማንም ሊጎዳው አይችልም፡፡ ከአላህ ውጭ የሚፈራን ሰው ማንም ሊጠቅመው አይችልም፡፡›

ኢማም አሕመድ ኢብኑ ሐንበል ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹የአላህ ፍራቻ አንዳንድ ጊዜ ከምግብና መጠጥ ይከለክለኛል፡፡ ሞትን ሳስታውስ የዚህች ዓለም ጉዳይ ምንም ሆኖ ይታየኛል፡፡ እንበላለን፣ እንጠጣለን፣ እንለብሳን፡፡ ያለችን ቀን ጥቂት ናት፡፡ ከድህነት የሚስተካክል ምንም የለም፡፡ መንገድ ባገኝ ምንም መታወስ በማልችልበት መልኩ ከዚህች ዓለም በወጣሁ ነበር፡፡›

ሓቲም አልአሶም ረሒመሁላህ እንዲህ ይላል፡-
‹ለሁሉም ነገር መዋቢያ ጌጥ አለው፡፡ የአምልኮ ተግባራት (ዒባዳ) ጌጡ የአላህ ፍራቻ ነው፡፡ የአላህ ፍራቻ ምልክቱ ደግሞ ምኞትን ማሳጠር ነው፡፡›

ሉቅማን ልጃቸውን ሲመክሩ እንዲህ ይላሉ፡-
‹ልጄ ሆይ! በሱ ላይ ተስፋ ማድረግህ ወንጀልን እንድትዳፈር በማያደርግህ መልኩ በአላህ ላይ ተስፋ አድርግ፡፡ ከሱ እዝነት ተስፋ በማያስቆርጥህ መልኩ ፍራቻ አላህን ፍራ፡፡›


/channel/Nejashipp

nejashibooks" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@nejashibooks

https://nejashibooks.com/

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

https://vt.tiktok.com/ZS92ABtW8/

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

ልዩነቱ ሰፍቷል
የሸይኽ ኻሊድ አር ራሺድ መጽሐፍ
ትርጉም - ጀማል ሙሐመድ
ነጃሺ ማተሚያ ቤት

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

ከ “አርዓያ ቁጥር አንድ” መጽሐፍ የተወሰደ
****
ይህ መጽሐፍ የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ.) የተግባቦት መንገዶች ይዳስሳል፡፡ መጽሐፉ ቀጥር አንድ እና ሁለት አለው፡፡

አዘጋጁ ፡ ኡስታዝ ሙሐመድ ዑመር ነው፡፡
አንብቡት ትጠቀሙበታላችሁ፡፡
***
ከመጽሐፉ ፡-

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ከሁሉም በላይ በዱዓ ላይ ትኩረት ያደርጋሉ። እንደሰው ማድረግ ያለባቸውን ሁሉ ያደርጋሉ። ከዚያም ነገረ ጉዳያቸውን በአላህ ላይ ይተዋሉ። በሁሉም ነገር ላይ የመጨረሻውን ስኬት አላህን አጥብቀው ይለምናሉ። ከርሱ ፍቃድ ውጭ የሕይወትን ሚዛን መጠበቅና ለስኬት መብቃት እንደማይቻል ያስተምራሉ። ትልቁን የሕይወት ስዕል በሚይዙና አጠቃላይነት ባላቸው የዱዓ ቃላት ላይ ያተኩራሉ። ለአብነት የሚከተሉትን እንመልከት፤-

* ‹‹አላህ ሆይ! ፍቅርህን አንተን የሚወዱ ሰዎችንም ፍቅር ወደ ፍቅርህ የሚያደርሰኝንም በጎ ተግባር እለምነሃለሁ። አላህ ሆይ! ፍቅርህን ከነፍሴ ከቤተሰቤና ከቀዝቃዛ ውሃ ይበልጥ ለእኔ ተወዳጅ አድርግልኝ።›› (ቲርሚዚ የዘገቡት)

* ‹‹አላህ ሆይ! ከማይጠቅም ዕውቀት አንተን፣ አንተን ከማይፈራ ልቦና ከማትጠግብ ነፍስ፣ ተቀባይነት ከሌለው ዱዓ በአንተ እጠበቃለሁ።›› (ሙስሊም የዘገቡት)

*‹‹ዱዓ (ማድረግ) አምልኮት ነው።›› (አቡ ዳዉድና ቲርሚዚ)

* ‹‹አላህ ያልለመነውን ሰው በርሱ ላይ ይቆጣበታል።›› (ቲርሚዚ የዘገቡት)

ሰው የቱንም ያህል ቢያውቅ፣ የቱንም ያህል ቢጥር፣ የቱንም ዓይነት ደረጃ ላይ ቢደርስ፣ሁሌም ቢሆን የሚቀሩት ነገሮች አሉት። የሚያንሰው ዕውቀት፣ ያላገኘው አጋጣሚ፣ ያላሸነፋቸውና የሚታገሉት ስሜቶች ያሉበት ነው። በሌላ አባባል ሰው ውስን ነው። የሚሆነውን ለመሆን የፈጣሪውን እርዳታ ዘወትር መጠየቅ አለበት። በዱዓ ወደ ተመዛዘነ ሕይወት መቅረብ ይችላል።

ከአባባሎች
***
* ‹‹ጥልቅ የልብ ምኞት በዱዓ መልስ ያገኛል።›› (የሰዕድ ጥበቦች ገ/157)

* ‹‹ዱዓ በድርጊት ሊደገፍ ይገባል። አለዚያ ባዶውን ይቀራል።›› (የሰዕድ ጥበቦች /ገ/157)

* ‹‹ጭንቀትና ግራ መጋባት ወደ ዱዓ መሩኝ። ዱዓ ግራ መጋባትንና ጭንቀትን አስወግድልኝ።›› (የሰዕድ ጥበቦች /ገ/157)

/channel/Nejashipp

nejashibooks" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@nejashibooks

https://nejashibooks.com/

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

https://vt.tiktok.com/ZSHbthTN3/

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

አዲስ አበባ ውስጥ በሞተረኛ
ወደተለያዩ የአገሪቱ ከተሞችና የውጭ አገራት በፖስታ ቤት በኩል እንልካለን።

ይዘዙን

ስልክ

+251945858585

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

https://vt.tiktok.com/ZSHf2Tm2N/

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

ፈተናዎች፣ እኛን ከኀጢአት ለማጽዳት የሚከሰቱበት ጊዜ አለ።
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ፦
“አንድን ሙስሊም ድካም፣ ህመም፣ ትካዜ፣ ሐዘን፣ ወይም ጉዳት -የእሾህ መውጋት ቢሆንም እንኳን- አይደርስበትም፤ አላህ የተወሰነውን ኀጢአቱን የሚያብስለት ቢሆን እንጂ።” (ቅጽ 7፣ ምዕራፍ 70፣ ቁጥር 545)

አንድ ታላቅ ገጣሚ እንዳለውም፦
“አንድ ሰው ምንጣፍ ሲደበድብ ውጥኑ ምንጣፉ አይደለም። ምንጣፉ ውስጥ ያለው አቧራ እንጂ።”

አንጥረኛ ወርቅን የሚቀጠቅጠው ሊያጠፋው አይደለም። ሊያፀዳው ነው።
አላህም ምእመናንን ለማጽዳት ልክ ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን በፈተና እንደሚያፀዳቸው በቁርኣን ነግሮናል።
ወርቅ በእሳት ሲለበለብ ጉድፎቹ ይወገዱለታል።
የአማኝ ልብ በፈተና እንዲያልፍ ሲደረግም የቀልብ ላይ እድፎች ይወገዳሉ።

የባዶነት ስሜት መንስኤው እና ፈውስ
በያስሚን ሙጃሂድ
ትርጉም - ሱለይማን ጠይብ።


/channel/Nejashipp

nejashibooks" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@nejashibooks

https://nejashibooks.com/

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

መላው ሙስሊም ማኅበረሰብ እንኳን ለዒድ አል-ፊጥር በሰላም አደረሣችሁ።
ዒዱኩም ሙባረክ!
ወኩሉ ዓሚን ወአንቱም ቢኸይር ።

ነጃሺ ማተሚያ ቤት
ነጃሺ መፃሕፍት መደብር


https://nejashibooks.com/

nejashibooks" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@nejashibooks

/channel/Nejashipp

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

አዲስ መጽሐፍ ከነጃሺ
***
የመጽሐፉ ሥም ፡ ነፍሲያን ማረቅ
አዘጋጅ ፡ ኢብን አል-ጀውዚ
ትርጉም ፡ ሱለይማን ጠይብ ሐምዛ
የገጽ ብዛት፡ 84

ስለ መጽሐፉ ፡ መጽሐፉ ነፍሲያን በማረቅ እና አጉል ፍላጎቶቿን በማገድብ ወደ ትልቅ ደረጃ ማድረስ ስለሚቻልበት ሁኔታ ይዳስሳል፡፡

ከመጽሐፉ ፡ አላህ ለሰው ልጆች የሚወስነውም ሆነ የሚያመላክተው ነገር ሁሉ ፋይዳው ለእነሱ ነው። አንድም እንደ የምግብ ፍላጎት ዓይነት ጠቃሚ ስሜቶች እንዲኖሯቸው አለዚያም እንደ ቁጣ ኃይል የመሣሠሉትን ክፋቶችን ለመቆጣጠር ነው። የምግብ ፍላጎት ወሰን ሲያልፍ ወደ ስግብግብነት ያመራል። በዚህ ምክንያትም ጎጂ ይሆናል። በተመሳሳይም የሰው ቁጣ ሚዛን ሲስት ጥፋት ማስከተሉ አይቀርም።
የዚህ መጽሐፍ ዋና ዓላማ የምጣኔን እና ትክክለኛነትን ሕግ በአእምሮ እና በልብ አውታሮች ውስጥ ማስረፅ፣ ማንበር እና ‹ሀዋእ›  (ሥጋዊ ዝንባሌ) ጉዳት እንዳያስከትል መድፈቅ የሚቻልበትን መንገድ መጠቆም ነው። አለፍ ሲልም የምጣኔን እና ትክክለኛነትን ሕግ የሚቃወምን ሥጋዊ ዝንባሌ ፈውሶችን ያመላክታል።
መጽሐፉ በአጫጭር ሰላሳ ምዕራፎች የተከፋፈለ ነው።

https://nejashibooks.com/

nejashibooks" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@nejashibooks

/channel/Nejashipp

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

https://vt.tiktok.com/ZSHbthTN3/

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

ያ ጉድጓድ ውስጥ የተጣለው፣
በባልዲ ተንጠልጥሎ ከጉድጓዱ የወጣው እና
በርካሽ ዋጋ የተሸጠው፤

ኋላ ላይም ሚኒስቴር ሆኖ፣
ቀጥሎም የግብፅ ዋና ገዥ ሊሆን ጥቂት ቀርቶት የነበረው ነቢዩ ዩሱፍ (ዐ.ሰ.) ታሪኩ ምን ያስተምረናል መሰለህ…

በዘመንህ ውስጥ የሚያጋጥሙህ ከባባድ የሕይወት ገፆች ሁሉ፣
በሕይወት ውስጥ ወደፊት የሚመጣውን እጅግ ውቡን ሕይወትህን መንገድ ለመጥረግ የተላኩ መቅድሞች ሊሆኑ ይችላሉና ታገስ!
በአላህ ላይ መልካምን ብቻ ጠርጥር!፡፡

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

ስምንተኛው ቀን አመሻሽ ላይ
የውም አት-ተርዊየህ
*****

የሐጅ ተግባራት ዛሬ ዚል-ሒጃ ስምንተኛው ቀን ላይ ጀምረዋል። በሐጅ ወቅት የኢሕራም ልብስ ከለበሱ በኋላ ሐጅ ይነየታል።
የኢሕራምን ሁለት ረከዓዎችን ከሰገዱ በኋላ እንዲህ ይላሉ፡- “አላህ ሆይ! ሐጅ አስቤያለሁና አግራልኝ፤ ተቀበለኝ። አንተ ሰሚም፣ ዐዋቂም ነህና።”

ከዚያም “ተልቢያ” ለብበይከ-ልላሁምመ ለብበይክ… ይባላል።

በዚሁ ቀን ጸሐይ ከወጣች በኋላ ወደ ሚና ጉዞ ይጀመራል። ይህ ቀን የተርዊየህ (ውሃ የማጠጣት ቀን) ተብሎ ይታወቃል። በጥንት ጊዜ የሐጅ እንግዶችን የሚቀበሉ ሰዎች ለሐጃጆች ውሃ በማቀበል የሚያሳልፉት ቀን ነው።

በዚሁ ቀን ተልቢያን /ለብበይከ-ልላሁምመ ለብበይከ… ማለትን ማብዛት ይወደዳል። ዚክር ማድረግ፣ ለአላህ መተናነስና ለሱ ያለንን ፍራቻ መግለጽ አስፈላጊ ነው።

ወደ ሚና መሄድና እዚያው ማደር በነጋታው ለሚደረገው የዐረፋ ላይ የመቆም ሁኔታ ያዘጋጃል።

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

አሥሩ የዚል-ሒጃ ቀናት፡፡
ከዱንያ ቀናት ሁሉ ምርጦቹ፡፡
*
* ዛሬ ዚል-ቂዕዳ 30ኛ ቀን ላይ ነው ያለነው፡፡

* በኢስላማዊው አቆጣጠር ነገ ሰኞ 1 ብሎ የሚገባው ወር የዚል-ሒጃ ወር ይባላል፡፡

* ዚል-ሒጃ እጅግ የተከበረ ወር ነው፡፡

* ጦርነት በውስጡ ከተከለከለባቸው ከአራቱ የተከበሩ ወራት ውስጥም አንዱ ናት፡፡

* ከወሩም የመጀመርያዎቹ አሥር ቀናት እጅግ የተከበሩ ናቸው፡፡

* ቀናቶቹ የዚል-ሒጃ ወር ሲጀምር ይጀምራሉ፡፡ የዒድ አል-አድሓ ቀን ያበቃሉ፡፡

*ፆም ምርጥ የአምልኮ ተግባር እንደመሆኑ በነኚህ የመጀመርያዎቹ ዘጠኝ ቀናት ውስጥ መፆም ይወደዳል ።

* ከነኚህ ቀናት ውስጥ ከ8ኛው ቀን ጀምሮ የሐጅ ሥራዎች ይከናወናሉ፡፡

* እነኚህ ቀናት እጅግ ክቡር መሆናቸው የታወቀ ቢሆንም ብዙዎች በነኚህ ቀናት ዉስጥ ሲዘናጉ ይታያሉ፡፡

* በነኚህ ቀናት ዉስጥ የሚሠሩ መልካም ሥራዎች በየትኛዉም የዱንያ ቀናት ዉስጥ ከሚሠሩት በላይ አላህ ዘንድ ተወዳጅ ናቸው፡፡

* የዐረፋ ቀን ፆም (ዘጠነኛው ቀን) የሁለት ዓመት ኃጢኣት ያስምራል፡፡ ያለፈን አንድ ዓመት እና የሚቀጥለዉን አንድ ዓመት፡፡

* የዐረፋ ቀን ፆም የሐጅ ሥራ ላይ ለሌለ ሰው ነው። ዐረፋ ላይ የሚቆም ሰው ይህን ቀን አይፆምም።

* ሐጅ አድራጊ በዚህ ቀን ውስጥ በዱዓና ኢስቲግፋር መበርታት ይኖርበታል ።

* አሥረኛው ቀን ዒድ ነው።

* የዒድ ቀን መፆም የተከለከለ ነው።

* ቀንም ሆነ ሌሊት በነኚህ ቀናት ዉስጥ በዒባዳ መበርታት ይገባል፡፡

* ለዒዱ ኡድሒያ ማረድ ሀሳቡ ያለው ሰው ቀነኚህ ቀናት ውስጥ ፀጉሩንም ሆነ ጥፍሩን መቆረጥ የለበትም።

* በነኚህ አሥር ሌሊቶች አላህ (ሱ.ወ.) ምሎባቸዋል፡፡ ይህም የቀናቱን ታላቅነት ያሳያል፡፡

* በነኚህ ቀናት ውስጥ የሚሠሩ መልካም ሥራዎች ተወዳጅ የመሆናቸውን ያህል በውስጣቸው የሚሠራ ኃጢኣትም ጥፋቱ ክቡድ ነው፡፡

* እነ ኢብኑ ዐመር እና አቢ ሁረይራ (ረ.ዐ.) በነኚህ ቀናት ዉስጥ ተክቢራ እያደረጉ ወደ ገበያ ይወጡ ነበር፡፡ ሰዎችም አብረዋቸው ተክቢራ (አሏሁ አክበር) ይላሉ፡፡

* በነኚህ ቀናት ዉስጥ ዚክር ማብዛት፣ አላህን ማላቅ ይወደዳል፡፡

* በነኚህ ቀናት ውስጥ ሱብሐነላህ፣ አልሐምዱ ሊላህ፣ ላ ኢላሀ ኢልለላሀ አላሁ አክበር ማለት ይወደዳል፡፡

* በዐረፋ ቀን ዱዓ መብዛት ይመረጣል፡፡ በተለይ ላ ኢላህ ኢልለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፤ ለሁልሙልኩ፣ ወለሁል ሐምዱ፣ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር … የሚለዉን፡፡

* በነኚህ ቀናት ዉስጥ የሚሠሩ የዒባዳ ዓይነቶች ቀናቶቹን ልዩ ያደርጋቸዋል፡፡ ሶላት፣ ፆም፣ ሶደቃ፣ ሐጅ … ሁሉም የተሰባሰቡባቸው ናቸው፡፡

* ደጋጎች እነኚህን አሥርቶች ልዩ ትኩረት ይሠጧቸው ነበር፡፡
- የረመዷን ወር የመጨረሻዎቹ አሥር ቀናት፣
- የዚል ሒጃ ወር የመጀመርያዎቹ አሥር ቀናት፣
- የሙሐረም ወር የመጀመርያዎቹ አሥር ቀናት፡፡

አሥርቱ ዚል ሒጃ ቀናት፤ ከዱንያ ቀናት ሁሉ ምርጦቹ በመባል ይታወቃሉ፡፡

ያስታውሱ ቀናቱ ነገ ይጀምራሉ፡፡

መልካም የዒባዳ ጊዜ
ነጃሺ ማተሚያ ቤት
ነጃሺ መፃሕፍት መደብር

/channel/Nejashipp

nejashibooks" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@nejashibooks

https://nejashibooks.com/

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

የአላህ ነቢይ (ሰ.ዐ.ወ) ይህችን ዓለም ሲሰናበቱ መዲና የሙስሊሙ ዓለም ዋና ከተማ ሆና ነበር። ከዚያም መንበሩን የተረከቡ ኸሊፋዎች የሚቀመጡባት እንዲሁም ኢስላማዊ ሕግጋትን ለማርቀቅ የዕውቀት ባቤቶች የሚሰበሰቡባት ከተማ ሆና ቀጥላለች።
ከዚያ በኋላ ግን የሙስሊሙ ኢምፓየር ድንበሮች እየተለጠጡ ሄደው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብና ሰፊ መሬት እንዲሁም በርካታ ክ/ሀገራትና ከተሞች ተጨመሩ።

በዑመር (ረ.ዐ0) የአመራር ዘመናት በርካታ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረቦች ተቀማጭነታቸው መዲና ነበር። ይህ በአጋጣሚ የሆነ አልነበረም። ብዙ ሙስሊሞች ሀገር በመክፈትና ኢስላምን ከአጥቂዎች በመከላከሉ ተግባር ተሰማርተው በግንባር ይገኛሉ።
ዑመር (ረ.ዐ) በርካታ ቁጥር ያላቸው ዋና ዋና የሚባሉ የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባልደረቦች ከጎናቸው እንዳይለዩ በማድረግ መዲና እንዲቀመጡ ይፈልጉ ነበር። ይህን በማድረግም ካላቸው እምቅ ዕውቀት እና ከምክራቸው ተጠቅመዋል።
በዚህ የዑመር ፖሊሲ ምክንያት 130 የሚሆኑ በሙፍቲ ደረጃ የተቀመጡ ሰሓባዎች (አላህ የሁሉንም ሥራ ይውደድላቸውና) መዲና ይገኙ ነበር።

ከነዚህ ሙፍቲዎች መካከል ራሳቸው ዑመር (ረ.ዐ)፣ ዐሊ (ረ.ዐ)፣ ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረ.ዐ)፣ ዓኢሻ (ረ.ዐ)፣ ዘይድ ኢብኑ ሣቢት (ረ.ዐ) ዐብደላህ ኢብን ዐባስ (ረ.ዐ) እና ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ) ዋነኞቹ ናቸው። እነዚህን ሰባት ታላቅ የዕውቀት ባለቤቶች አስመልክተው ሙሐመድ ኢብን ሐዝም እንዲህ ብለዋል፡- “እያንዳንዳቸው የሰጧቸው ፈትዋዎች (በመጽሐፍት መልክ ቢዘጋጁ) ትልልቅ ጥራዝ ያላቸው መጽሐፍት በወጣቸው ነበር።


ከአል-ፋሩቅ ዑመር መጽሐፍ የተወሰደ
አዘጋጅ ፡ ሸይኽ ዶ/ር ሙሐመድ ዐሊ አሶላቢ
ትርጉም ፡ አሕመድ ሑሴን (አቡ ቢላል)

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

https://vt.tiktok.com/ZS9DtmyE8/

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

ከእነዚህ ሰዎች አንፃር እኛ የት ላይ እንገኛለን?
፨፨፨፨

1- ራፊዕ “ዐብደላህ ኢብን ዑመር (ረ.ዐ) ቤቱ ውስጥ ሲሆን የሚሠራው ምንድን ነበር?” ተበሎ ተጠየቀ፡፡
እርሱም “አትችሉትም! ለሁሉም ሰላቶች ዉዱእ ማድረግ፣ በሁሉም ሰላቶች መካከል ቁርኣን ማንበብ” ሲል መለሱ፡፡

2- ሙሐመድ ኢብን ዋሲዕ “ተቀመጥ፤ ለምን አትደገፍም” ተበሎ ተጠየቀ፡፡
እርሱም “የሚደገፈው ከቀጣዩ ዓለም ጭንቀት ነፃ የሆነ ሰው ነው፡፡ እኔ እስካሁን እንደፈራሁኝ ነኝ” ሲል መለሰ፡፡

3- ሣቢት አል-ቢናኒይ ለቅሶ ከማብዛቱ የተነሳ ዓይኖቹ ለመጥፋት ተቃረቡ፡፡ ወደ እርሱም አንድ ሐኪም መጣና “ለዓይኖችህ ህክምና አደርግልሃለሁ፤ ግን አንተ ከዛሬ ጀምሮ ላለማልቀስ ቃል ግባልኝ” አለው፡፡ እርሱም “አላህን ፈርተው ካላለቀሱ የዓይኖቼ በላጭነት የት ላይ ነው? ” ሲል መለሰለት፡፡

4- ለኢማም ሐሰን አል-በሰሪ ለማፍጠሪያ የሚሆን ውሃ በኩባያ መጣላቸው፡፡ ለመጠጣት ወደ አፋቸው ካስጠጉት በኋላ አለቀሱ፡፡ ከዙሪያቸው ያሉ ሰዎችም ለምን ታለቅሳለህ? ብለው ጠየቋቸው፡፡ እርሣቸውም “የጀሀነም ሰዎች ከጀነት ሰዎች የሚያደርጉትን የውሃ ልመና አስታወስኩ፡-
የሚሰጣቸውንም መልስ አስታወስኩኝ፡-
( አል-አእራፍ፡ 50)
እነዚያ ሃይማኖታቸው መሳለቂያና መጫወቻ አድርገው የያዙ፣ የቅርቢቱ ሕይወት ያታለለቻቸው፣ ይህንን ቀናቸውን (የፍርዱን ቀን) መገናኘትን እንደርሱ፣ በተአምራታችንም ይክዱ እንደነበሩ ዛሬ እንረሳቸዋለን፡፡

5- ዐጣእ ኢብን ሳኢብ የሚከተለውን ዘግቧል፤ “ወደ አባ ዐብዱረሕማን አስ-ሱለሚይ ሄድን፡፡ መስጂድ ውስጥ ሆኖ ጣዕረ-ሞት ውስጥ ገብቷል፡፡
እኛም “ወደ ቤትህ ወስደንህ ከፍራሽህ ላይ ብትተኛ የተሻለ ነው” አልነው፡፡ እሱም “ከእናንተ ውስጥ አንድ ሰው አንድ ሰላት መስጂድ ውስጥ ሰግዶ ሌላ ሰላት ለመስገድ መስጂድ ውስጥ አይጠባበቅም፤ የተጠባበቀውን ጊዜ ያህል ሰላት እየሰገደ እንደሆን አላህ ዘንድ የተጻፈለት፣ እንዲሁም መላእክት ለርሱ አላህን ምህረት የጠየቁለት ቢሆን እንጂ፡፡ የሚለውን የነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲስ ሰምቻለሁ፡፡ ስለዚህ መስጂድ ውስጥ ነው መሞት የምፈልገው” አለን፡፡


6- ሰዒድ ኢብን ሙሰየብ “ለ50 ዓመታት ያህል በመስጂድ ውስጥ የጀማዓ ሰላት አልፎኝ አያውቅም፣ ለ40 ዓመታት በመስጂድ ውስጥ የኢማሙ የመጀመሪያው ተክቢራ (ተክቢረተል-ኢሕራም) አልፎኝ አያውቅም፣ለ30 ዓመታት የመጀመሪያው ሶፍ ላይ ሆኜ እንዲሁም ሙአዚኑ እኔ ቀድሜ መስጂድ ውስጥ ሆኜ እንጂ አዛን ብሎ አያውቅም” ብሏል፡፡


7- ኢማም ቡኻሪ “ለአቅመ - አዳም ከደርስኩ ጀምሮ ሙስሊም ወንድሜን አምቼ አላውቅም” ብለዋል፡፡

8- ኢማሙ ሻፊዒይ “በእውነትም ሆነ ውሸት ጉዳይ በአላህ ስም ምዬ አላውቅም፣ ንጹህ ውሃ እንኳን መጠጣት ከአላህ ጋር ያለኝን ግንኙነት እንደሚያበላሽብኝ ባውቅ አልጠጣም ነበር” ብለዋል፡፡

9- ወደ ኢማም አውዛዒይ ቤት አንዲት ሴት ገባች፡፡ ኢማም አውዛዒይ በሚሰግዱበት ቦታ (ሚሕራብ) ላይ ርጥብ ነገር አገኘች፡፡
ለባለቤታቸውም “አላህ ይዘንልሽ! የህፃናት ሽንት ከሼኹ መስገጃ ላይ ይገኛል” አለቻት፡፡
የአውዛዒይ ባለቤትም “ወዮልሽ! ይህ የምትመለከችው ርጥበት ሼይኹ የሌሊት ሰላት ሲሰግዱ የሚያነቡት እንባ ነው” አለቻት፡፡

10- ኢማም ኢብኑል ቀዪም ስለ ኡስታዛቸው ኢብን ተይሚያ የሚከተለውን ጽፈዋል፡- “በአላህ ይሁንብኝ ከኢብኑ ተይሚያ የተሻለ ያማረ ሕይወት የሚኖር አልተመለከትኩም፡፡ ከቅርቢቱ ዓለም የተሰጠው ፀጋ አናሣ፣ዛቻ እና እስር የበዛበት የሆነ ሕይወት ከመምራቱ ጋር ሁሌም ደስተኛና ልቦናውም ሰፊና ጠንካራ ነበር፡፡ የደስተኝነት ፀጋ በፊቱ ላይ ይስተዋላል፡፡ የሰዎች ማስፈራራት እንዲሁም ምድር ሰፊ ከመሆኗ ጋር ስትጠብበን ወደ እርሱ ዘንድ እንመጣ ነበር፡፡ ከንግግሮቹም ስንሰማ ያስጨነቁን ነገሮች በሙሉ ይወገዳሉ፡፡ ነፍሳችንም የተረጋጋች ሆና እንመለሣለን”፡፡

https://nejashibooks.com/

nejashibooks" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@nejashibooks

/channel/Nejashipp

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

ከኢሕያእ ዑሉሚዲን ገፆች
አዘጋጅ ፡ ኢማም አል-ገዛሊ
ትርጉም ፡ ሙሐመድ ሰዒድ ABX (PhD)
ነጃሺ መፃሕፍት መደብር ያገኙታል ።

በትዕዛዝ አዲስ አበባ ውስጥ በሞተረኛ
ክልሎች እና ውጭ አገር በፖስታ ቤት በኩል እንልካለን ።

ስልክ - +251945858585

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

https://vt.tiktok.com/ZSHbthTN3/

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

የሐጅ ግዴታነት በቁርኣን እና በነቢያዊ መልእክት (ሐዲሥ) የጸና ነው። ስለዚህ ማንኛውም አካላዊም ሆነ ቁሳዊ አቅሙ የተሟላለት ወንድ ይሁን ሴት ሙስሊም፣ በሕይወት ዘመኑ ቢያንስ አንድ ጊዜ ሐጅ ማድረግ ይኖርበታል።

ሐጅ እየደረሠ ነው።

ውድ አንባቢያን! ይህ መጽሐፍ በሐጅ እና ዑምራ ዙርያ የተዘጋጀ ድንቅ መጽሐፍ ነው።
የመጽሐፉ ዋና ዓላማ በተለይ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሐጅ እና ዑምራ ለሚጓዙ ምእመናን በሥርዓቱ ዙርያ የእስልምናን አስተምህሮ በትክክል አውቀው መተግበር ይችሉ ዘንድ መረጃ መስጠት ነው።

መጽሐፉ ምንም እንኳ አጠር ያለ ቢሆንም በጉዳዩ ዙርያ ጠቃሚ መረጃዎችን ይዟል።

ግለሰቦች፣
በሐጅና ዑምራ ዙርያ የሚሠሩ ተቋማትና ኤጀንሲዎች መጽሐፉን ይጠቀሙበት ዘንድ እንመክራለን።

/channel/Nejashipp

nejashibooks" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@nejashibooks

https://nejashibooks.com/

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

በየዕለቱ እንድንሰግድ የታዘዝናቸው የአምስት ጊዜያት ሰላቶች፣ የልባችን ኦክሲጅን (እስትንፋስ) ናቸው።

ሰላት የተውን ጊዜ መተንፈስም ያቅተናል። አካላዊው ልባችን ያለ ኦክሲጅን መኖር እንደማይችለው ሁሉ፣ መንፈሳዊው ልባችንም ያለ ዚክር (በተለይም ያለ ሰላት) ሕያው ሊሆን አይችልም።

የሰላት መድኃኒት በታወቁ (ተለይተው በተወሰኑ) ሰዓቶች እንዲወሰድ በአላህ የታዘዘው ያለ ምክንያት አይደለም። ልክ አንድ ሐኪም እንደሚያዘው መድኃኒት፣ የሰላትን ክፍለ ጊዜ ጠብቀን መስገድ አለብን። ምክንያቱም ሐኪሙ (አላህ) ያን ያደረገበት እርሱ ብቻ የሚያውቀው ምክንያት አለው።
ለአላህ ከዶክተር ጋር የማይነፃፀር እጅግ የላቀ መገለጫ እንዳለው ሳይዘነጋ።

የፈጅር ሰላት፣ ፀሐይ ከመውጣቷ ጥቂት ቀደም ብሎ እንዲሰገድ ሲወስን ያን ያደረገበትን ምክንያት ያውቃል። ሐኪም ያዘዘልንን ሕይወት አድን መድኃኒት በየዕለቱ የተወሰነውን እየተውን ብንወስድ ምን ይከሰታል? በቀን አምስቴ እንድንወስድ የታዘዝነውን መድኃኒት፣ ማታ ከመኝታ በፊት አምስቱንም ብንወስድ ምን ይፈጠራል? መቼም መድኃኒቱ በታዘዘው ሰዓት መወሰድ የሚኖርበት እኛን በሕይወት እና በጤና ለማቆየት እንደሆነ አይጠፋንም።

የባዶነት ስሜት
ያስሚን ሙጃሂድ

ትርጉም ፡ ሱለይማን ጠይብ

/channel/Nejashipp
nejashibooks" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@nejashibooks

/channel/NejashiPP/1575

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

የሚያጎለብቱ ፈተናዎች
*,
ፍጥረትን ስናጠና የአላህን ሱንና (መንገድ) የተመለከቱ በርካታ እውነታዎችን እናገኛለን። ለምሳሌ፣ አጥንታችን ሲሰበርና መልሶ ሲድን፣ አጥንቱ ተሰብሮ የዳነበት ጥግን ቦታ ላይ የበለጠ ጠንካራ ይሆናል። ዓለማዊ ፈተናዎቻችንም ተመሳሳይ ባህሪ አላቸው። ከታላላቅ የሱና ምሁራን አንዱ የሆኑት አል-ዒዝ ኢብን ዐብዱሰላም “ፈተናዎችና 17 ፋይዳዎቻቸው” የሚሰኝ ዕውቅ ድርሰት አላቸው።

በዚህ ሥራቸው ሸይኹ፣ ፈተናዎች የአላህን የኃያልነት (ሁሉን ቻይነት) ልክ እንድንረዳ እንደሚያደርጉ አብራርተዋል። ብዙውን ጊዜ የሕይወታችን መሪዎች ራሳችን እንደሆንን እናስባለን። ሕይወታችንን ራሳችን የምንሾፍር ይመስለናል። ሁሉን ነገር የማበጀት እና ሰባራን ሁሉ የመጠገንን ከባድ ኃላፊነት ለመወጣት እንጥራለን። ይህ ደግሞ መከራ ውስጥ ይከተናል። ዘና ማለት አንችልም። እንቅልፍ ካይናችን ይሸሻል።

ብዙዎች፣ ሁኔታዎች ላይ ሥልጣን አለን ብለው በማሰባቸው ምክንያት ውስጣዊ ሰላምን አያገኙም። በሕይወታችን ላይ የተለገሥነውን ውሳኔ የማሳለፍ ክህሎት ትክክለኛ ሥልጣን አድርገን እንቆጥረዋለን። ፈተናዎችና መከራዎች ደግሞ አላህ በእኛ ላይ የማይገሠሥ ሥልጣን ያለው መሆኑን እንድናስታውስ ያስገድዱናል። አላህ አል-ቀሃር (አስገዳጅ) እና አል-ዐዚዝ (አሸናፊ) ነው።

እናም ይህ ዕውቀት ወደሚያድነንንና ድህነታችንን በማስታወስ አላህን እንድንከጅል ወደሚያደርገን ግንዛቤ ይመራናል። ከአላህ ፊት መልካም የማርገድ ስሜት ውስጣችን ያሰርፃል። “በአላህ ቢሆን እንጂ ኃይልም ሆነ ብልሃት የለም፣” የሚለውን ወርቃማ መርህ በገቢር ያስተምረናል። ሰዎችን ሁሉ ወይም ሁሉንም ነገር የምናድን እኛ አለመሆናችንን ይዘክረናል።
የምናስተካክለው እኛ እንዳልሆንን፣ ኃላፊነትም እንዳልተጣለብን ያስገነዝበናል። ይህ ኃላፊነት የአላህ መሆኑን ጭምር።

ይህ ግንዛቤ ሕይወታችንን መታደግ የሚችል ነው። ከሰዎች ጋር ያሉንን ግንኙነቶች ማረቅ ይችላል። የሰው ልጅ ልቦና የዓለምን ክብደት እንዲሸከም አልተበጀም። ይህን ክብደት መሸከም የሚችል አላህ ብቻ ነው። ይህን ጭነት ለሰማይና ለምድር ባለቤት እስካላስረከብን ድረስም ይህን ከንቱ ክህሎታችንን በሚያፈርስ ጫና ሥር ስንሰቃይ መኖራችን አይቀርም።

/channel/Nejashipp

nejashibooks" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@nejashibooks

https://nejashibooks.com/

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

የህሊና ዕረፍቶች (ከቁጥር 1- ቁጥር 4)
***

መጽሐፎቹ ውስጥ

* የተለያዩ መሳጭ ጥበባዊ ንግግርች፣
* የታላላቅ ሰዎች አባባሎች፣
* አጫጭርና ውብ የሆኑ ግጥሞች፣
* መረጃዎችና ቆንጆ ሀሳቦች ፣
* ቀልብን የሚያለሰልሱ ምክሮች፣
* አዝናኝ እና አስተማሪ መልእክቶች እና ሌሎችንም
* የማይሰለቹ መጣጥፎችን ያገኙባቸዋል፡፡

ነጃሺ መፃሕፍት መደብር ያገኟቸዋል።

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

አስደሣች ዜና ለመጽሐፍ ወዳጆች
****

የሦስተኛውን የሙስሊሞች ኸሊፋ የታላቁን ሰሐባ ዑሥማን ኢብኑ ዐፋን (ዙን-ኑረይን) ታሪክ የያዘ መጽሐፍ በነጃሺ ማተሚያ ቤት ታትሞ በዛሬው ዕለት በገበያ ላይ ውሏል።

መጽሐፉ 414 ገፆች አሉት።

አዘጋጁ ሸይኽ ዶ/ር ዐሊ ሙሐመድ ሶላቢ ናቸው።
ኡስታዝ አሕመድ ሑሴን ተርጉሞታል ።


መርካቶ ታላቁ አንዋር መስጊድ መግቢያ በር ላይ ነጃሺ መፃሕፍት መደብር ያገኙታል።

ነጃሺ የዕውቀት ማዕድ!!

https://nejashibooks.com/

nejashibooks" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@nejashibooks

/channel/Nejashipp

Читать полностью…

Nejashi Printing Press

ውድ ደንበኞቻችን
ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ መርካቶ አንዋር መስጊድ መግቢያ በር ላይ የሚገኘው መክተባችን ወሩን ሙሉ ክፍት ነው።

https://nejashibooks.com/

nejashibooks" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@nejashibooks


/channel/Nejashipp

Читать полностью…
Subscribe to a channel