natnaelmekonnen21 | Неотсортированное

Telegram-канал natnaelmekonnen21 - Natnael Mekonnen

169400

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7 Facebook.com/natnaelmekonnen.et Instagram.com/natnaelmekonnen21

Подписаться на канал

Natnael Mekonnen

የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የመሠረቱት ፋውንዴሽን ይፋ ሆነ

የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የመሠረቱት “የአዳም ፋውንዴሽን” የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ምሥረታውን ይፋ አድርጓል።

አቶ ደመቀ መኮንን በቦርድ ሊቀመንበርነት የሚመሩት “የአዳም ፋውንዴሽን”፤የመንግስት ባለስልጣናት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት በተገኙበት ይፋዊ የማብሰሪያ ሥነ ሥርዓቱን በዛሬው ዕለት ተከናውኗል።

ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ ልማትና እድገት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ የገለፁት የፋውንዴሽኑ መስራች አቶ ደመቀ መኮንን፤ በተለይ ህፃናትና እናቶች ላይ በመስራት ብሎም መቀንጨርን በመዋጋት ደህንነቱ የተጠበቀ ትውልድ ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

“በአፍሪካ መቀንጨርን መግታት” የሚል መሪ ሀሳብ ያለው ፋውንዴሽኑ፤ ከኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያገኘው ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ እንደነበር ተገልጿል።

“የአዳም ፋውንዴሽን” በሥነ ምግብ ላይ መስራት ዋና ዓላማው ያደረገ ሲሆን መቀንጨርን ለመግታት የሚያስችሉ ባለብዙ ዘርፍ ፕሮግራሞችን በመቅረፅ ይሰራል ተብሏል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኡጋንዳ ህዝብ መከላከያ ኃይል ጠቅላይ አዛዥ ጀነራል ሙሆዚ ካይኔሩጋባ ጋር ተወያዩ

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

🔶️ ውሳኔዎን የሚያደንቁበት ትርፋማ ኢንቨስትመንት  ከአሚባራ ፕሮፐርቲ ! 🔶️

➣ ለ50 ቤቶች ብቻ የተዘጋጀ
ታላቅ ቅናሽ!

➣ ሸራተን ሆቴል አጠገብ
ወዳጅነት ፓርክ ፊትለፊት
ቅንጡ አፓርትመንቶች
ከ852,000 ብር ቅድመ ክፍያ
ጀምሮ

➣ ሁለት የመዋኛ ገንዳ,
የልጆች የእግር ኳስ ሜዳ,
የቅርጫት ኳስ ሜዳ
እንዲሁም የቤት ውስጥ
የበረዶ መንሸራተቻ

➣ ከባለ አንድ እስከ ባለ አራት
የመኝታ ቤት አማራጮች

➣ በ10% ቅድመ ክፍያ
በኢትዮጵያ ብር የሚዋዋሉት

➣ እስከ 25% የሚደርስ
ታላቅ ቅናሽ

ለበለጠ መረጃ
0979804444
በቀጥታ ወይንም በዋትሳፕ
ይደውሉ

አሚባራ ፕሮፐርቲ
ለዘመናዊ ኑሮ ታስቦ የተገነባ

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

#attention #ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ #ከቴምር ሪልስቴት ላመለጣችሁ በድጋሜ አዲስ ሱቅ ሽያጭ አውጥተናል
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ በኩል
0939770177/0996856273
/channel/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

አዲስ አበባ እራሷን እንዴት ለሳይበር ደህንነት ታብቃ? https://m.youtube.com/watch?v=CK7Kpg74TE0

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የህውሀት አምልኮተ ቤተመቅደስ ውስጥ የመጨረሻው ኩራዝ ያዥ ይሆናሉ ብዬ ከማስባቸው ሰዎች አንዱ አሉላ ሰለሞን (ጦርንት ባህላዊ ጫዎታችን ነው) ነበር። እሱም የህውሀት ነገር አንገፈገፈው።

እንግዲህ ከነአሉላ በላይ በህውሀት ፍቅር የተነደፈ አለነበረም። ዛሬ ህውሀት ኋላቀርና የትግራይን ህዝብ የማይመጥን ድርጅት ነው እያለን ነው። “አሜን” ከማለት ውጪ ምን እንላለን? አበው ሲተርቱ “ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው” ይላሉ።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

#TemerRealEstate በቴምር ሪልስቴት ለሽያጭ የወጡ 3 ሳይቶች
👉7ሳይቶችን ሰርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ካወጣናቸው 3 ሳይቶች
🎯1,ፒያሳ (ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት) ጀርባ
    👉1መኝታ 46ካሬ =Soldout
    👉2መኝታ 71ካሬ=
      10%ቅድመ ክፍያ 745,000ብር
      ሙሉ ክፍያ 7,455,000ብር
    👉2መኝታ 93ካሬ=
     10% ቅድመ ክፍያ 1,044,000ብር
     ሙሉ ክፍያ 10,044,000ብር
    👉3መኝታ 130ካሬ
    10%ቅድመ ክፍያ 1,365,000ብር
    ሙሉ ክፍያ 13,650,000ብር
    👉3መኝታ 142ካሬ
   10%ቅድመ ክፍያ 1,533,600ብር
   ሙሉ ክፍያ 15,336,000ብር
    👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው       የሚጨርሱት
💥30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
   0939770177/0996856273
/channel/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

🔶️ ውሳኔዎን የሚያደንቁበት ትርፋማ ኢንቨስትመንት  ከአሚባራ ፕሮፐርቲ ! 🔶️

➣ ለ50 ቤቶች ብቻ የተዘጋጀ
ታላቅ ቅናሽ!

➣ ሸራተን ሆቴል አጠገብ
ወዳጅነት ፓርክ ፊትለፊት
ቅንጡ አፓርትመንቶች
ከ852,000 ብር ቅድመ ክፍያ
ጀምሮ

➣ ሁለት የመዋኛ ገንዳ,
የልጆች የእግር ኳስ ሜዳ,
የቅርጫት ኳስ ሜዳ
እንዲሁም የቤት ውስጥ
የበረዶ መንሸራተቻ

➣ ከባለ አንድ እስከ ባለ አራት
የመኝታ ቤት አማራጮች

➣ በ10% ቅድመ ክፍያ
በኢትዮጵያ ብር የሚዋዋሉት

➣ እስከ 25% የሚደርስ
ታላቅ ቅናሽ

ለበለጠ መረጃ
0979804444
በቀጥታ ወይንም በዋትሳፕ
ይደውሉ

አሚባራ ፕሮፐርቲ
ለዘመናዊ ኑሮ ታስቦ የተገነባ

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

አንካራ ላይ ምን ተፈፀመ?

ይሄ በየመንገዱ የሚያንቀላፋው ሠውዬ “አብይ አንካራ ድረስ ሄዶ ሽንፈቱን ተጎነጨ” እያለን ነው። መሀይም መሆን ችግር ሊሆን ይችላል ግን ሀጢአት አይደለም። ሀጢአቱ መሀይም ሆነህ እንደአዋቂ act ስታደርግ ነው። ካኮረፈ መሀይም ሶስት ክንድ እራቁ ወገኖቼ።

አንካራ የተሰራው ስራ የሚገባህ ትምህርት ቤት ደርሰህ የመጣህ እንደሆነ ነው። ከሶማሌላንድ ጋር የተደረገው ስምምነት አላማ ምን ነበር? ለእናት ሐገር የባህር በር ማምጣት! የትናንቱ ስምምነት ላይ ሶማሊያ ለኢትዮጵያ የባህር አክሰስ ትሰጣለች። አለቀ። ስለሶማሌ ላንድ MOU የተባለ ነገር የለም። ከሶማሌላንድ ጋር የተደረገው ስምምነት ይፈርሳል አልተባለም።

እንቅልፋሙ ሰውዬ “አብይ የሶማሊያን ሉአላዊነት አከብራለሁ ስላለ ተሸነፈ” ብሎናል። አብይ ድሮስ የሶማሊያን ሉአላዊነት አላከብርም ብሏል ወይ? አንዲት ሐገር የአንዲት ሐገርን ሉአላዊነት አላከብርም ማለትስ ትችላለች ወይ?
የሶማሊያ ድንበር ሶማሊያ ላይ ያበቃል። ሶማሌላንድ ራሷን የቻለች ሐገር ነች። የራሷ ድንበር፥ የራሷ መንግስት፥ የራሷ ፓስፖርት፥ ያላት። በተደጋጋሚ ጤነኛ የሚባል ምርጫ ያሳካች፥ ከሐገራት ጋር ግንኙነት ስታደርግ የቆየች፥ አንድ ሐገር ሐገር ለመሆን ማሟላት ያለበትን መስፈርት በሙሉ አሟልታ የጨረሰች ሐገር ነች። UN በር ላይ ባንዲራዋ ስላልተውለበለበ ሐገር አይደለችም ልትለኝ አትችልም። እንደውም አንዳንድ ጎረቤቶቻችን ሶማሌላንድ ያላት ህገመንግስት እንኳን የላቸውም።

ስለዚህ የአንካራው ስምምነት አንድም ኢትዮጵያ ልታሳካው ከተነሳችለት ግብ አንፃር፥ ሁለተኛው ሶማሊያን እንደጦር ካምፕ ተመልክተው ጠላቶቻችን ሊሰሩት የሞከሩትን ድራማ ከማፈራረስ አንፃር፥ ሶስት ኢትዮጵያ ከሳምንት በፊት የአረብ ሊግ አባል ሐገር ለመሆን ያቀረበችውን ጥያቄ ቅቡል ከማድረግ አንፃር፥ የመጨረሻውና ዋናው ደግሞ ኢትዮጵያ የማይናወጥ የባህር በር የማግኘት ፍላጎቷን ከማስጠበቅ አንፃር የተሳካ ፖለቲካዊ ድል ነው።

በየመንገዱ የሚተኛው ሰውዬና ጓደኞቹ ሁሉን ነገር ፈልገው ሁሉን ነገር ስላጡ አብይ የባህር በሩን አሳክቶ ባንዲራችን ቀይ ባህር ላይ ቢውለበለብ እንኳን ለሀያ አመት ተሸክመው የሚዞሩትን ድንኳን ተክለው መነፋረቃቸው አይቀርም።

ድል ለኢትዮጵያ።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የከሸፈው ቲያትረኛ

እንደ ሐገርፍቅር ቲያትር ቤት አርቲስትና እስክስታ መቺ ብቻ እየዘለለ የሚገባበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ አሁን ደግሞ ሽመልስ አበራ ጆሮ የተባለን የከሸፈ ቲያትረኛ ይዞብን መጥቷል።

ሙስሊም ጠሉ ሽሜ አፉን ሞልቶ “አብይ አህመድ የእስላም መንግስት ሊያመጣብን ነው” ብሎ ሲናገር በሀፍረት ጥፍሬ ውስጥ መደበቅ አቃተኝ። እንደዚህ ያሉ ተመልካች ያጡ አርቲስቶች ወደፖለቲካ ሲገቡ ከልማታቸው ጥፋታቸው ይበልጣል። በሚሊዮን የሚቆጠር ሙስሊም ባለባት ኢትዮጵያ እንዲህ አይነት ድንቁርናን መስበክ ለህዝበ ሙስሊሙ ብቻ ሳይሆን ለክርስቲያኑም ስድብ ነው።

ሽመልስ አበራ ጆሮ ቲያትር ተመልካች ጠፍቶ ልጆቹን ማሳደግ አቅቶት እንደሰላቢ ሚዛን የተንሻፈፈ ጫማ አድርጎ ከሐገር እንደወጣ እናውቃለን። በስደት ላይ ደግሞ ሊርብህና ሊጠማህ ይችላል። የፈለገ ረሀብ ቢጠናብህ ግን አንጥፈህ ትለምናለህ እንጂ እንዲህ አይነት መርዘኛና አዳፋ ንግግር እየተናገርክ ከርስህን አትሞላም።

ሽመልስ አበራ ጆሮ በዘመነ ኢህአዴግ የኢህአዴግ አባል ሆኖ አምቡላውን እየላፈ ስንቱን አርቲስት ሲያሳስርና ሲያስፈራራ የከረመ እንደስሙ ጆሮ ጠቢ እንደነበር የማያውቅ የለም። ዛሬ ወደሙሉ ግዜ ትወና ገብቶ “የአማራ ታጋይ” ሆኛለሁ ሲል የሚያውቁት ሁሉ ተገርመው ነበር። ይሄ አማራ መቼስ ፈረደበት። ልጆቹን እንደቆሎ የትም ሲዘራ የኖረ ደንቆሮ ሁሉ ባንዲራ ለብሶ እንደተውሳክ ይጣበቅበታል። እነአስራት ወልደየስንና እነአክሊሉ ሀብተወልድን ያፈራ አማራ በሽመልስ አይነት ለሀጩን እንኳን መቆጣጠር በማይችል መሀይም አፍ ሲጠራ ማየት ያመኛል።

የኢትዮጵያ ሙስሊም መብቱ የተጓደለ ሲመስለው ለመብቱ ከመታገልና ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ከማቅረብ ውጪ ሐገሪቷ በሸሪአ ትመራልኝ ብሎ ጠይቆ የሚያውቅበት ዘመን የለም። ኢትዮጵያም የብዙ ብሔሮችና ሀይማኖቶች ሐገር ከመሆኗም ባለፈ አንዱ የሌላውን እምነት አክብሮ የሚኖርባት ምድር መሆኗ ልዩ ያደርጋታል። የሚናገሩት ንግግር ምን አይነት ውጤት እንዳለው ለመገመት እውቀታቸው የማይፈቅድላቸው እንደአበራ ጆሮ አይነት የሶስት ወር ታጋዮች ይህንን ማህበራዊ ትስስር ለመናድ ድራማ ማነብነብ በለመደ አፋቸው ደፋ ቀና ሲሉ ሌላው ይቅርና ዘመድ አዝማድ ለማስቆም አለመሞከሩ ያስገርማል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

🔶️ ውሳኔዎን የሚያደንቁበት ትርፋማ ኢንቨስትመንት  ከአሚባራ ፕሮፐርቲ ! 🔶️

➣ ለ50 ቤቶች ብቻ የተዘጋጀ
ታላቅ ቅናሽ!

➣ ሸራተን ሆቴል አጠገብ
ወዳጅነት ፓርክ ፊትለፊት
ቅንጡ አፓርትመንቶች
ከ852,000 ብር ቅድመ ክፍያ
ጀምሮ

➣ ሁለት የመዋኛ ገንዳ,
የልጆች የእግር ኳስ ሜዳ,
የቅርጫት ኳስ ሜዳ
እንዲሁም የቤት ውስጥ
የበረዶ መንሸራተቻ

➣ ከባለ አንድ እስከ ባለ አራት
የመኝታ ቤት አማራጮች

➣ በ10% ቅድመ ክፍያ
በኢትዮጵያ ብር የሚዋዋሉት

➣ እስከ 25% የሚደርስ
ታላቅ ቅናሽ

ለበለጠ መረጃ
0979804444
በቀጥታ ወይንም በዋትሳፕ
ይደውሉ

አሚባራ ፕሮፐርቲ
ለዘመናዊ ኑሮ ታስቦ የተገነባ

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ከሶማሊያ ወታደሮች ጋር የተካሄደውን ውጊያ ተከትሎ ጁባላንድ ራስካምቦኒን ተቆጣጠረች

በሶማሊያ ፌደራል መንግስት ወታደሮች እና ጁባላንድ ኃይሎች መካከል ትናንት ውጊያ መካሄዱን ተከትሎ የጁባላንድ ኃይሎች ራስካምቦኒ ከተማን ተቆጣጠሩ።

ውጊያው በሁለቱ አካላት መካከል ትናንት ታህሳስ 2 ቀን ጠዋት የተጀመረ ሲሆን የጁባላንድ የፌዴራል ኃይሎች ግጭት አስጀምረዋል ሲል ከሷል። የሟቾች ቁጥር ግልጽ ባይሆንም የመሠረተ ልማት ላይ ጉዳት እንደተከሰተ ሪፖርት ተደርጓል።

የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የጁባላንድ መሪ የሆኑትን አህመድ ኢስላም ሞሀመድ ማዶቤ ከአልሸባብ ጋር ተባብረዋል ሲል በመክሰስ በተሳታፊዎች ላይ "ህጋዊ እርምጃ" ሊወሰድ እንደሚችል አስጠንቅቋል ሲል ሶና ዘግቧል።

የጁባላንድ ባለስልጣናት ኃይላቸው ስትራቴጂካዊ አየርማረፊያን ጨምሮ በራስካምቦኒ ቁልፍ ቦታዎችን መቆጣጠሩን ገልጸዋል። ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት ከ300 በላይ የፌደራል ወታደሮች ወደ ኬንያ ተሻግረው በኬንያ ኃይሎች ትጥቅ እንዲፈቱ ተደርገዋል። በተጨማሪም 240 የፌደራል ወታደሮች በጁባላንድ ወታደሮች እጅ መግባታቸው ተነግሯል።


    

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

#TemerRealEstate በቴምር ሪልስቴት ለሽያጭ የወጡ 3 ሳይቶች
👉7ሳይቶችን ሰርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ካወጣናቸው 3 ሳይቶች
🎯1,ፒያሳ (ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት) ጀርባ
    👉1መኝታ 46ካሬ =Soldout
    👉2መኝታ 71ካሬ=
      10%ቅድመ ክፍያ 745,000ብር
      ሙሉ ክፍያ 7,455,000ብር
    👉2መኝታ 93ካሬ=
     10% ቅድመ ክፍያ 1,044,000ብር
     ሙሉ ክፍያ 10,044,000ብር
    👉3መኝታ 130ካሬ
    10%ቅድመ ክፍያ 1,365,000ብር
    ሙሉ ክፍያ 13,650,000ብር
    👉3መኝታ 142ካሬ
   10%ቅድመ ክፍያ 1,533,600ብር
   ሙሉ ክፍያ 15,336,000ብር
    👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው       የሚጨርሱት
💥30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
   0939770177/0996856273
/channel/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

🔶️ ውሳኔዎን የሚያደንቁበት ትርፋማ ኢንቨስትመንት  ከአሚባራ ፕሮፐርቲ ! 🔶️

➣ ለ50 ቤቶች ብቻ የተዘጋጀ
ታላቅ ቅናሽ!

➣ ሸራተን ሆቴል አጠገብ
ወዳጅነት ፓርክ ፊትለፊት
ቅንጡ አፓርትመንቶች
ከ852,000 ብር ቅድመ ክፍያ
ጀምሮ

➣ ሁለት የመዋኛ ገንዳ,
የልጆች የእግር ኳስ ሜዳ,
የቅርጫት ኳስ ሜዳ
እንዲሁም የቤት ውስጥ
የበረዶ መንሸራተቻ

➣ ከባለ አንድ እስከ ባለ አራት
የመኝታ ቤት አማራጮች

➣ በ10% ቅድመ ክፍያ
በኢትዮጵያ ብር የሚዋዋሉት

➣ እስከ 25% የሚደርስ
ታላቅ ቅናሽ

ለበለጠ መረጃ
0979804444
በቀጥታ ወይንም በዋትሳፕ
ይደውሉ

አሚባራ ፕሮፐርቲ
ለዘመናዊ ኑሮ ታስቦ የተገነባ

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ኢትዮጵያየዬ ስብራትሽ በጀግኖች ልጆሽ ይጠገናል ቀይ ባህር ቀይ ናት @AbiyAhmedAli እንቁ የኢትዮጵያ ልጅ አባ መላ 🫡 እንግዲህ ባንዳ አይንህ ይቅላ ቀይ ባህር ገብተናል የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ዳግም በቀይ ባህር

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

#TemerRealEstate በቴምር ሪልስቴት ለሽያጭ የወጡ 3 ሳይቶች
👉7ሳይቶችን ሰርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ካወጣናቸው 3 ሳይቶች
🎯1,ፒያሳ (ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት) ጀርባ
    👉1መኝታ 46ካሬ =Soldout
    👉2መኝታ 71ካሬ=
      10%ቅድመ ክፍያ 745,000ብር
      ሙሉ ክፍያ 7,455,000ብር
    👉2መኝታ 93ካሬ=
     10% ቅድመ ክፍያ 1,044,000ብር
     ሙሉ ክፍያ 10,044,000ብር
    👉3መኝታ 130ካሬ
    10%ቅድመ ክፍያ 1,365,000ብር
    ሙሉ ክፍያ 13,650,000ብር
    👉3መኝታ 142ካሬ
   10%ቅድመ ክፍያ 1,533,600ብር
   ሙሉ ክፍያ 15,336,000ብር
    👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው       የሚጨርሱት
💥30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
   0939770177/0996856273
/channel/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የሱለይማን አብደላ ጉዳይ

ሱለይማን አብደላ የ 18 ወር የሳውዲ እስሩን ጨርሶ ሐገሩ መግባቱ ይታወቃል። ልጁ እስር ቤት ከመግባቱ ቀደም ብሎ “በል በል” ይሉት የነበሩት ሁሉ ሰው ሐገር ላይ ሲታሰር ላለፉት 18 ወራት አቶ ዳኛቸው ከሚባል ሰው ውጪ ዞሮ ያየውና ቤተሰቡ የት ወደቀ? ብሎ የጠየቀው አንድም ሰው አልነበረም። ሱለይማንን ከመንገዱ ለማስወጣት የተረባረቡ ሁሉ ወደወህኒ ሲወርድ ሱለይማን የሚባል ሰው እንዳልነበረ ያክል እረሱት።

የሳውዲ መንግስት ሱለይማንን እስሩ ይበቃዋል ብሎ ወደሐገሩ ሲመልሰው እነዚህ በሰው መነገድ የለመዱ የውሸት ሊቃውንት አመዳቸውን አራግፈው ለሱ ሲያስቡ እንደከረሙ በመሆን የዩቲዩብ መሸቀያ ርእሰ ዜና አደረጉት። “ሱለይማን ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፎ ተሰጠ፥ ሱለይማንን ኢትዮጵያ እንደገባ በጥቁር ጨርቅ አፍነው ወሰዱት” እያሉም ተቀደዱ። ሀሰተኞች ነገ ስለሚጋለጠው ውሸታቸው ሳይሆን ነገ አዲስ ስለሚፈጥሩት ውሸት ነው የሚያስቡት። ሚዲያን የሚያህል ነገር ከፍተው ሰው ምን ይለኛል እንኳን ሳይሉ በ120 ሚሊየን ህዝብ ፊት ሲቀደዱ ለነገ ተአማኝነታቸውን ጥያቄ ምልክት ውስጥ እያስገቡ እንደሆነ አይገባቸውም።

ለማንኛውም ወጣት ሱለይማን የጥፋቱን ያህል ለሀገሩ የሰራቸውም ብዙ በጎ ነገሮች አሉ። ወደሐገሩ እንደገባ ቀጥታ ከቤተሰቡ ጋር ተቀላቅሏል። እንኳን መታፈንና መታሰር አንድም ሰው አልገላመጠውም። የመጣው ወደሐገሩ ነው። የሚያስጠይቀውን ወንጀል ሰርቶ ከሆነ እንደማንኛውም ሰው እንደነፃ ሰው የመቆጠር መብቱና ሰብአዊ መብቱ ተጠብቆለት ይጠየቃል። ወንጀል ካልሰራ ደግሞ እንኳን ሳውዲ ሐገሩ ላይ ቁጭ ብሎም በነፃነት ሃሳቡን እየገለፀ የመኖር መብት አለው። ገና ለገና የሀሳብ ልዩነት አሳየ ብሎ ሲያሻው ከየመን እየጠለፈ ሲያሻው ደግሞ የተቃወመውን ሁሉ ከየቤቱ እያነቀ እስር ቤት መጣል በወያኔ ግዜ ቀርቷል።

ለማንኛውም ሀሰት ዘርተው፥ ሀሰት ቆልተው፥ ሀሰት ቸርችረው፥ በሀሰት አንጀራ ከርሳቸውን ሞልተው ለሚኖሩ ሰዎች ባለንበት የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት እናድርግላቸው። ሱለይማን አብደላ ሰላም ነው። ሰላምም ይሆናል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ አዲስ አበባ ገቡ
*****************

የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ሚኒስትሩ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች የሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

" እነ ድብረፅዮን በአዲስ አበባው ውይይት ' ጌታቸውን ከፕሬዜዳንት እንሱልን ብቻ እንጂ ጊዚያዊ አስተዳደሩ መልሰን በማደራጀት አብረናችሁ ለመስራት ዝግጁ ነን ' ብለዋል " - ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ከድምጺ ወያነ ጋር በነበራቸው ቆይታ ምን አሉ ?

ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ፤ የትግራይ አመራሮች በአዲስ አበባ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐበይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በወቅታዊ ጉዳይ በነበራቸው ቆይታ በክልሉ ጉዳይ የሃሳብ ልዩነት አልነበራቸውም ብለዋል፡፡

ነገር ግን " የትግራይ ፓለቲካ ከድጡ ወደ ማጡ እያመራ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" የፀጥታ ሃይሎች ከማንኛውም ጫና ነፃ ሆነው የህዝቡ ብሄራዊ ጥቅም ማረጋገጥ ይገባቸዋል " ሲሉ አክለዋል፡፡

በአዲስ አበባው ውይይት በደብረፅዮን (ዶ/ር) ይሁን በአቶ ጌታቸው የሚመሩት የህወሓት ልኡካን እንዲሁም የጊዚያዊ አስተዳደሩ ተወካዮች መካከል በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታና ችግሮች ዙሪካ ያለልዩነት መስማማታቸውን ገልጸዋል።

በወቅቱ " የፌደራል መንግሰት የትግራይ ችግሮች እንዲፈቱ አላገዝክም " በማለት ወቀሳ ማቅረባቸውን ጠቁመዋል።

" የፌደራል መንግስት ' ጉባኤ እንድናካሂድ ፤ የትግራይ ፓለቲካ እንድናስተካክል ጊዜ ስጠን በማለት ዕድል እና ጊዚያችሁን አባክናቹሃል ' በማለት መልሶልናል " ሲሉ አብራርተዋል።

ሌተናል ጄነራሉ ፥ " በመሃከላችን እየታየ ያለው ክፉኛ መሳሳብ የትግራይ ሉአላዊ ግዛት እንዳይረጋገጥ ፣ ተፈናቃዮች ወደ ቁያቸው እንዳይመለሱ አደገኛ መሰናክል ሆኗል " ብለዋል።

የፕሪቶሪያ ውል በይፋ የተቃወመ የለም ፤ በተግባር ግን ውሉን የሚያደናቅፍ አሉታዊ ተግባር የሚፈፀሙ አካላት አሉ ብለዋል።

" የፕሪቶሪያ ውል በተሟላ መልኩ በመተግበር ብቻ ነው አቃፊ መንግስት ማቋቋም የሚቻለው " በማለትም አስረግጠዋል።

" እነ ድብረፅዮን በአዲስ አበባው ውይይት ' ጌታቸውን ከፕሬዜዳንት እንሱልን ብቻ እንጂ ጊዚያዊ አስተዳደሩ መልሰን በማደራጀት አብረናችሁ ለመስራት ዝግጁ ነን ' ብለዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" እኛም በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት የፌደራል መንግስት ዓለምአቀፋዊ ወሰኖች የመጠበቅ እና የማስከበር ስልጣን አለው፤ ይህንኑ ስልጣኑ ተጠቅሞ በቦታው የሚገኙ የውጭ ሃይሎች አውጥቶ የግዛት አንድነት እንዲያረጋግጥ በአፅንኦት ጠይቀናል " ብለዋል።

በዚህ ምክንያት " ' ከሃዲዎች ' በሚል ስማችንን ማጠልሸት ተገቢ አይደለም " ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፤ በፌደራል መ/ቤቶች የትግራይ ውክልና ባለመኖሩ ምክንያት የህዝቡ ድምፅ በተገቢው መንገድ ሊሰማ ባለመቻሉ ምክንያት ከጦርነቱ በፊት የነበረው የክልሉ ውክልና እንዲመለስ ለፌደራል መንግስት ጥያቄ መቅረቡን  ሌተናል ጀነራሉ አሳውቀዋል።

በተጨማሪ ፤ " የፕሪቶሪያ ውል አንቀፅ 8 ዓለምቀፍ ወሰኖች በፌደራል መንግስት እንዲጠበቁ ስለሚያዝ ኢትዮጵያ በትግራይ በኩል ከኤርትራ እና ከሱዳን የሚያገናኙ ወሰኖች ጠባቂ ስለሌላቸው የውጭ ሃይሎች እየገቡ ግፎች እየፈፀሙ ፣ ወርቅ ዝውውርን ጨምሮ ሌሎች ህገ-ወጥ ወንጀሎች እየተፈፀመባቸው በመሆኑ ወሰኖቹ በፌደራል መንግስት እንዲጠበቁ " ሲሉ መጠየቃቸውን አሳውቀዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

🔶️ ውሳኔዎን የሚያደንቁበት ትርፋማ ኢንቨስትመንት  ከአሚባራ ፕሮፐርቲ ! 🔶️

➣ ለ50 ቤቶች ብቻ የተዘጋጀ
ታላቅ ቅናሽ!

➣ ሸራተን ሆቴል አጠገብ
ወዳጅነት ፓርክ ፊትለፊት
ቅንጡ አፓርትመንቶች
ከ852,000 ብር ቅድመ ክፍያ
ጀምሮ

➣ ሁለት የመዋኛ ገንዳ,
የልጆች የእግር ኳስ ሜዳ,
የቅርጫት ኳስ ሜዳ
እንዲሁም የቤት ውስጥ
የበረዶ መንሸራተቻ

➣ ከባለ አንድ እስከ ባለ አራት
የመኝታ ቤት አማራጮች

➣ በ10% ቅድመ ክፍያ
በኢትዮጵያ ብር የሚዋዋሉት

➣ እስከ 25% የሚደርስ
ታላቅ ቅናሽ

ለበለጠ መረጃ
0979804444
በቀጥታ ወይንም በዋትሳፕ
ይደውሉ

አሚባራ ፕሮፐርቲ
ለዘመናዊ ኑሮ ታስቦ የተገነባ

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የሚስማሙት በጥቅም፥ የሚባሉት ለጥቅም

ዛሬ “መስቀልህን ፍታ፥ መስቀልህን ፍታ” የሚባባለውና ለመገዳደል የሚፈላለገው፥ ከዛም ባለፈ በየሚዲያው ቡድን ሰርቶ የሚሰዳደበው ከዲሲ እስከአማራ ክልል የተዘረጋው የዘረፋ chain የተበጣጠሰው “በጥቅም” ነው። ዛሬ ምስኪኑ የአማራ ጫንቃ ላይ ተጣብቆ ህዝቡን እየዘረፈና እየገደለ ያለው የሽፍታ ስብስብም ትናንት የተደራጀው “ለጥቅም” ነው።

ዛሬ በአማራ ክልል ተማሪዎች ወደትምህርት ገበታቸው እንዳይሄዱ በሽፍታ ይከለከላሉ። ሾፌሮች “ፋኖ ይዘርፈናል” በሚል ወደክልሉ ለገበሬው የሚያስፈልገውን ሸቀጣ ሸቀጥ ይዘው መሄድ አይፈልጉም። ለገበሬው የሚከፋፈል ምርጥ ዘር በተደጋጋሚ ተዘርፏል ስራ አጡ ሁሉ ዝርፊያን እንደአማራጭ እያየ ከገበሬ ቀምቶና ነጥቆ መብላት ለምዷል

ዛሬ አማራ ክልል ላይ ሰው በቁሙ አስገምቶ በማገት ጥንድ በሬ እንኳን ከሌለው ገበሬ በመቶ ሺዎች መጠየቅ ኖርማል ሆኗል። ዛሬ በክልሉ ህፃናት ተጠልፈው ከፍተኛ ገንዘብ ተተምኖባቸው እሱን ካላገኙ በየመንገዱ ተገድለው ይጣላሉ። ዛሬ በተስኪያን የሽፍታ መደበቂያ ሆና እናቶቻችን በሰላም አስቀድሰው መግባት ተሳቀዋል። ዛሬ ክልሉ ሽምግልና ተዋርዶ አዛውንቶች በዳዴ የሚሄዱበት ቀጠና ሆኗል። ዛሬ በአንድ ቀን ሰላሳ አራት ንፁሀንን በተርታ የሚረሽን የወመኔ ስብስብ እንደባክቴሪያ በክልሉ ፈልቷል።

የአማራው ህዝብ ዛሬ በራሱ ልጆች ታግቷል። ነፃ እናወጣሀለን በሚሉ ነፍሰገዳይና እርስ በርስ እንኳን በማይስማሙ አውሬዎች ህዝቡ ማህበራዊ ሰላም አጥቶ የሚያድነው ፍለጋ እየተጣራ ነው። ዛሬ ውሉ የማይታወቅን የሽፍታ ስብስብ በወንዜ ልጅነት ስም የምትረዳ አማራ ካለህ የገዛ ህዝብህን ሰቆቃ እያራዘምክ እንደሆነ እነግርሀለሁ።

ፅንፈኛው ቡድን የአማራን ክልል ለማፈራረስና የአማራን ህዝብ በማሰቃየት ማህበራዊ ሰላም ለማሳጣት በጠላት የተደራጀ የጥፋት ተልኮ አስፈፃሚ ነው። ከዚህ ውሉና መጨበጫው ከማይታወቅ አንድ መሪ፥ አንድ ማኒፌስቶና አንድ ግብ ከሌለው የጨለማ ስብስብ ጋር የተሰለፍክ ሁሉ ዛሬ የአማራ እናት ለምታነባው እያንዳንዷ እምባ እጅህ አለበት። ዛሬ ኪሱን ለማደለብ በየቀበሌው ለሚዞር የዱርዬ ቡድን ቅንጣት ነገር የምታዋጣ ሁሉ በየመንደሩ ለሚደፈሩ እህቶች፥ በየዞኑ ለሚታገቱ ህፃናት እጅህ እንዳለበት እወቀው።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

*ድርጅታችን ህወሓት ጊዜያዊ ምክር ቤት አቋቋመ*

የትግራይ ህዝብ ጥቅም የሚረጋገጠው በሰላማዊ ትግልና ውይይት እንጂ በጦርነትና የጦርነት ጉሰማ አይደለም ብሎ የሚያምነው በጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ማ/ኮ እስከ ቀጣዩ 14ኛው መደበኛ ጉባኤ ድረስ አመራር የሚሰጥ ጊዜያዊ ምክር ቤት አቋቋመ። የምክር ቤቱ አባላት ሁሉም ከኃላቀሩና ወንጀለኛው ቡድን ጎን አንሰለፍም ያሉት የህወሓት ማ/ኮሚቴ አባላትና የሁሉም ዞኖች አስተባባሪዎች፣ የክልል ስታፍ፣ የትእምትና የትግራይ ዩኒቨርስቲዎችን ያካተተ ነው። ምክር ቤቱ በጊዜያዊነት እንዲመሩት ሊቀ መንበርና ምክትሉን የሰየመ ሲሆን ከአባላቱም መካከል 7 አባላት የያዘ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አቋቁሟል። አስተባባሪ ኮሚቴው ሊቀ መንበርና ም/ሊቀ መንበር የተሰየመለት ሲሆን የአባላቶቻችን ክትትል ስራ የሚከውኑ ዘርፎችም በግልፅ ተቀምጠዋል። በተጨማሪም በዞን ሊቃነመናብርት የሚመሩ የዞን ኮሚቴዎችና የወቅቱ ትግላችንን ለማሳለጥ የሚያስችሉ ልዩ አደረጃጀቶችም እንዲቋቋሙ ተወስኗል። በወረዳዎችና ቀበሌዎችም በተመሳሳይ መልኩ እንዲፈፀም አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን የ3 ወራት ዕቅድም አፅድቋል።

ምክር ቤቱ ባካሄደው የመጀመሪያ ስብሰባም ኃላቀሩና ወንጀለኛው ቡድን ከተባባሪዎቹ ጋር ሆኖ እያካሄደ ያለውን ህገወጥና አውዳሚ የማዕድን ቁፋሮ ዘረፋ በፅናት ሊታገለውና ስርዓት ሊያስይዘው የወሰነ ሲሆን፤ ይህ ከስልጣን ውጪ መኖር የተሳነው ኃላቀሩ ወንጀለኛ ቡድን የትግራይን ህዝብ ዳግም ወደ ጦርነትና ፍጅት ለማስገባት ከአንዳንድ የፍጅት ኃይሎች ጋር በመተባበር እያካሄደ ያለውን የጦርነት ዝግጅቱን በአጭሩ የማያስቆም ከሆነ በሁሉም ዓይነት አማራጮች የሚታገለው መሆኑን ምክር ቤቱ ወስኗል። ከዚህ በተጨማሪም የህዝባችንን አንድነት ለማደፍረስ በመንደርና ጎጥ እንዲከፋፈል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ከህዝባችን ጋር በጋራ በመሆን ለማስቆም፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውሩ እንዲቆምና በመላው ትግራይ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ለመታገል፣ ተፈናቃይ ወገኖቻችን በአጭር ጊዜ ለመመለስና ሉዓላዊ ግዛታችን ለማስመለስ የፕሪቶሪያ ስምምነት ፈራሚ ከሆነው የፌደራል መንግስትና ተባባሪ አካላት ጋር ያላሰለሰ ሰላማዊ ትግል ለማካሄድ ምክር ቤቱ ወስኗል።

በመጨረሻም መላው ህዝባችን፣ የህወሓት አባላት፣ የትግራይ ፀጥታ ኃይሎች፣ የአገር ሽማግሌዎችና ሁሉም የህ/ሰብ ክፍሎች፤ በተለይ ደግሞ ወጣቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ዲያስፖራው በምናካሂደው ሰላማዊ ፖለቲካዊ ትግል ከጎናችን አሰልፈን የትግራይን ህዝብ ጥቅምና ፍላጎት እንደምናሳካ መግለፅ እንወዳለን።

ክብርና ሞገስ ለሰማእቶቻችን!
ድል ለትግራይ ህዝብ!

04 ታህሳስ 2017 ዓ.ም

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

እያመመው መጣ‼️

Good news : በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች፣ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮች መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ወደተዘጋጀላቸው ስፍራ እየገቡ መሆኑን ታውቋል::

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

#attention #ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ #ከቴምር ሪልስቴት ላመለጣችሁ በድጋሜ አዲስ ሱቅ ሽያጭ አውጥተናል
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ በኩል
0939770177/0996856273
/channel/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በአዲስ አበባ ከተማ የፅንፈኛው የሽብር ቡድን ተልዕኮ ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

በአዲስ አበባ ከተማ የፅንፈኛው የሽብር ቡድን ተልዕኮ ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አራት ተጠርጣሪዎች በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በተደረገባቸው ጠንካራ ክትትል በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

በሽብር ወንጀል የተጠራጠሩት አራቱ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ሊውሉ የቻሉት በአዲስ አበባ ከተማ የሽብር ተግባር ለመፈፀም ከፅንፈኛውን የሽብር ቡድን የወሰዱትን ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ 120 የክላሽንኮቭ ጥይት እና ኤፍ ዋን ቦንብ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አባላት ባደረጉት ጠንካራ ክትትል ታህሳስ 4 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ እጅ ከፍጅ ተይዘው ምርመራ እየተጠራባቸው እንደሚገኝ የምርመራ ቡድኑ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሕብረተሰቡ እስከአሁን እያደረገ ላለው ተሳትፎ ምስጋና እያቀረበ ተመሳሳይ የወንጀል ተግባር ሲመለከት የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (EFPApp) በመጠቀም ወይም በነፃ የስልክ መስመር 991 በመደወል በፍጥነት ጥቆማ በመስጠት ወይም መረጃውን በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታና ደኅንነት አካላት በአካል በማድረስ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና በሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሃስን ሼክ መሃመድ ቱርክ አንካራ ላይ የተደርገውን ሥምምነት የአፍሪካ ሕብረት እና ኢጋድ አደነቁ፥የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መሃማ ባወጡት መግለጫ ሥምምነቱ በፍጥነት ተግባራዊ እንዲሆንም ጥሪ አቅርበዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ኢትዮጵያ በዚህ ስምምነት 3 ነገር አሳክታለች

1. የባሕር በር የማግኘት መብቷን

2. ከሶማሌ ላንድ ጋር የተፈረመውን ስምምነት ካልተሻረ የሚለውን ባለበት ማጽናቷ

3. በሶማልያ ሰላም ያላትን ሚና (ኢትዮጵያ ወረረችን የሚለውን ፕሮፖጋንዳ በማስጣል የኢትዮጵያ ዋናው ግብ አስተማማኝ ዘላቂና ደኅንነቱ የተረጋገጠ የባሕር በር ማግኘት ነው። እንዴት የሚለው ታክቲክ?! መንገዱ እንደየ አመቺነቱ ይቀያየራል። ግቡ ግን ያው ነው።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ኢትዮጵያ እና ሶማልያ ግንኙነታቸውን ለማደስ ተስማሙ

በዚህ ስምምነት በሁለቱ ሀገሮች መካከል የተፈጠሩ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት ግንኙነታቸውን ወደ አዲስ የትብብር ምእራፍ ለመውሰድ ተስማምተዋል።

በሶማልያ በኩል ኢትዮጵያ አስተማማኝ ደህንነቱ የተረጋገጠ እና ዘላቂነት ያለው የባሕር በር የማግኘት መብትን ዕውቅና ለመስጠት እና በዚህ ጉዳይ ላይ አብሮ ለመስራት የተስማማች ሲሆን ኢትዮጵያም የሶማልያን የግዛት አንድነት ለማክበር የነበራትን የቆየ አቋም አጽንታለች። ሁለቱ ሃገራት የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት እውን ለማድረግ በቀጣይ አራት ወራት በቱርክዬ አስተባባሪነት ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር እና መሰል አሰራሮች ላይ ለምግባባት ተስማምተዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድንና የሶማልያን ጸጥታና ደኅንነት ለማስጠበቅ ያደረገችውን አስተዋጽዖ ዕውቅና ለመስጠት ተስማምታለች።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

“ኢትዮጵያ ከባህር ጋር ያላት ጉዳይን ከወንድሜ ሀሰን ሼክ ጋር ተነጋግረን ኢትዮጵያ ድጋፍ ትፈልጋለች ብለን ነው ያመነው:: ኢትዮጵያ ቀይ ባህርን የመጠቀም ጥያቄዋን ሶማሊያ እንደምትደግፍ እርግጠኛ ነኝ፤ ሁኔታውንም በዚህ መልኩ ነው የማየው።

የቱርኪዬ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋ

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ኢትዮጵያ እና ሶማልያ ግንኙነታቸውን ለማደስ ተስማሙ

🚨Breaking : በዚህ ስምምነት በሁለቱ ሀገሮች መካከል የተፈጠሩ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት ግንኙነታቸውን ወደ አዲስ የትብብር ምእራፍ ለመውሰድ ተስማምተዋል።

በሶማልያ በኩል ኢትዮጵያ አስተማማኝ ደህንነቱ የተረጋገጠ እና ዘላቂነት ያለው የባሕር በር የማግኘት መብትን ዕውቅና ለመስጠት እና በዚህ ጉዳይ ላይ አብሮ ለመስራት የተስማማች ሲሆን ኢትዮጵያም የሶማልያን የግዛት አንድነት ለማክበር የነበራትን የቆየ አቋም አጽንታለች። ሁለቱ ሃገራት የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት እውን ለማድረግ በቀጣይ አራት ወራት በቱርክዬ አስተባባሪነት ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር እና መሰል አሰራሮች ላይ ለምግባባት ተስማምተዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድንና የሶማልያን ጸጥታና ደኅንነት ለማስጠበቅ ያደረገችውን አስተዋጽዖ ዕውቅና ለመስጠት ተስማምታለች።

Читать полностью…
Подписаться на канал