በነቀምቴ ከተማ በተደረገ ዘመቻ በርካታ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ውሏል።
በነቀምቴ ከተማ በተደረገ ድንገተኛ ዘመቻ በርካታ የአሸባሪው የሼኔ ቡድን ሎጀስቲክስ እና የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን በማዕከላዊ ዕዝ የህዳሴ ኮር ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ ኮሎኔል እያሱ ሀብቱ ገልፀዋል።
ዘመቻው የኮሩ ሰራዊት ከከተማው ፓሊስ እና ሚሊሺያ ጋር በመቀናጀት የተደረገ ሲሆን ለጠላት መረጃ የሚያቀብሉ አባ ቶርቤ ፣የቡድኑን አባላት ጨምሮ 117 የተለያዬ ዓይነት ሽጉጥ ፣646 የሽጉጥ ጥይት፣ 30 ክላሽ፣ 34 ኋላቀር መሳሪያ ፣ 563 የክላሽ ጥይት እና 50 የእጅ ቦምብ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ተናግረዋል።
የነቀምቴ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ሻሎም በዳሳ በበኩላቸው በተደረገው ኦፕሬሽን እና በተገኘው ውጤት
ለኮሩ የሰራዊት አባላትና ለፀጥታ ሃይሎች ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።
የተገኙ ድሎችን በሚመለከት በነቀምቴ ከተማ ውይይት የተደረገ ሲሆን የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ በማስቀጠል የዞኑን ሰላም ማስጠበቅ እንደሚገባ ተገልጿል።
ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ከኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር በወቅታዊ የሃገራችን ጉዳይና በመከላክያ ሰራዊት እንዲሁም በቀጠናው ዙሪያ ልዩ ቃለመጠይቅ አድርጏል ሰሞኑን ይጠብቁን!
Читать полностью…Vote for Naomi Melketsadek to be Baby of the Year while supporting a great cause! Cast your daily vote below, or make even more of an impact with a tax-deductible donation supporting Baby2Baby. https://babyoftheyear.org/2024/naomi-melketsadek
Читать полностью…ካስሽ ጋዜጠኝነት ውጥንቅጥ ወጥቶ በጥቅምና በጎጥ በተጨማለቀበት ወቅት በእንዲህ አይነት ህዝብን/ወጣቶችን ሊያስተምሩ በሚችሉ ስራዎች ይዘህ ዳግም ወደ ሚዲያው በመምጣትህ ልትመሰገን ይገባል::
ጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ (ካስሽ) ግራ ቀኙን አይተህ አስተውለህ ይህ ህዝብ ምን አይነት ነገር ይበጀዋል ወጣቱስ ከጦርነት አባዜ ወጥቶ ምን ያስተምረዋል ብለህ አስበህ አስተውለህ እንዲህ አይነት ፕሮግራሞችን ይዘህ ወደ ሚዲያ ብቅ ማለትህ ብቻ ሳይሆን ወደፊት በስፋት በርትተህ እንዲህ ያሉ አስተማሪ ፕሮግራሞችን እንደምታቀርብ ተስፋ አደርጋለሁ:: ጤናማ የሆነ የፖለቲካውን ትንተናውን ጨሮም:: ካስሽ በርታ‼️ https://youtu.be/7mPfdW9fMbo?si=epTDuiFJCpY45-Dk
የመስቀል ደመራ በዓል ሃይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ ያለምንም የፀጥታ ሥጋት በሰላም እንዲከበር በቴክኖሎጂ የታገዘ ዝግጅት ማድረጉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገለፀ
የመስቀል ደመራ በዓል ሃይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ ያለምንም የፀጥታ ሥጋት በሰላም እንዲከበር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት አካላት ጋር ውይይት በማድረግ በቴክኖሎጂ የታገዘ ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ተግባር መገባቱን ገልጿል።
ክቡር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በውይይቱ ላይ ሀገራዊ ሰላምና የፀጥታ ሁኔታን ከግምት ውስጥ ያስገባ የኦፕሬሽን፣ የምርመራ፣ የመረጃ፣ የህዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ቲሞችን በማዋቀር የሽብር ቡድን አባላትን እና የተደራጁ ወንጀለኞች እንዲሁም የኢኮኖሚ አሻጥሮችን የመቆጣጠር ተግባርም አጠናክሮ በማስቀጠል ያለ አግባብ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን አንስተው የተጀመረው ኦፕሬሽን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል አያይዘው የመስቀል በዓል በሰላም እንዲከበር ሁሉም በተሰማራበት የፀጥታ ስራ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበው ለመላው የእምነቱ ተከታዮች የእንኳን አደረሳቹ መልዕክትም አስተላልፈዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ በበኩላቸው የሀገራችን የፀጥታ ሁኔታ አሁን ላይ በአስተማማኝ ሰላምና ደኅንነት ላይ እንደሚገኝ አመላክተው በቀጣይም በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች በአደባባይ በከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር የሚከበረው የመስቀል በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት እንደተደረገና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ በርካታ የፀጥታ ኃይልም እንደተሰማራ ተናግረዋል።
ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታው ኃይሉ ከሀይማኖት አባቶችና ከሰላም ወዳዱ ህብረተሰብ ጋር በመተባበር መስራት እንዳለበት አሳስበው ማንኛውንም ለበዓሉ ማድመቂያ ተተኳሽ ነገሮችና ርችቶችን ሆነ በዓሉ ከሚፈቅደው ስርዓት ውጪ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ መልዕክቶችን የያዙ አልባሳትና ፅሁፎችን ይዞ ወደ በዓሉ ቦታ መሄድ የተከለከለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ሀሰን ነጋሽ እና የክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ረዳት ኮሚሽነሮች በዓሉን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ በዓሉን በሰላምና በደስታ ለማሳለፍ የሚፈልግ በርካታ ሕዝብ እንዳለ ሁሉ የበዓሉን ድባብ ለማጠልሸት የተንቀሳቀሱ የሸኔ እና የፅንፈኛ የሽብር ቡድን አባላት እንዲሁም የአይኤስና የአልሸባብ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ሥር አውለው ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
ኅብረተሰቡ ከፖሊስ የሚተላለፉ ክልከላዎችን በማክበር ፀጥታን የሚያደፈርሱ አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲመለከት የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (EFPApp) ወይም በነፃ የስልክ መስመር 991 በመጠቀም ጥቆማዎችን በፍጥነት በመስጠት ወይም መረጃውን በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች በአካል በማድረስ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል፡፡
ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል:: ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት
አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
Tel: 0913858561
በሶማሊያ “ከድህረ አትሚስ በኋላ የሚኖረው የሀይል ስምሪት ተግባራዊ ከመደረጉ አስቀድሞ የስምሪቱ ማዕቀፍ በጥንቃቄ መሠራት አለበት” - አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ
በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 79ኛው የተ.መ.ድ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ጋር በጋራ ጉዳዮች መወያየታቸው ተገለጸ።
በውይይታቸው ወቅት በአፍሪካ ቀን የአሜሪካ መንግስት ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር መገኘታቸውም ታውቋል።አምባሳደር ታዬ ለረዳት ሚኒስትሯ በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ ባደረጉበት ወቅት በተለይ ኢትዮጵያ በቀጣናው ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን እያደረገች ያለውን ጥረት ትኩረት ሰጥተው ማንሳታቸው ተጠቁሟል።
ሚኒስትሩ ሶማሊያን በተመለከተ ከሞሊ ፊ ጋር በነበራቸው ውይይት ኢትዮጵያ ሽብርተኞችን በመዋጋት ረገድ በምታደርገውን የተጠናከረ ጥረት ዙሪያ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ከድህረ አትሚስ በኋላ የሚኖረው የኃይል ሥምሪት ተግባራዊ ከመደረጉ አስቀድሞ የስምሪቱ ማዕቀፍ በጥንቃቄ መሠራት እንዳለበት ተናግረዋል።
የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ክብርት ሞሊ ፊ በበኩላቸው አሜሪካ ሽብርተኝነትን በመዋጋት እና አጠቃላይ በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ እና አሜሪካ መካከል ጠንካራ ግንኙነት መኖሩን በመግለጽ በቀጣይ የጋራ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ቀጣይነት ያለው ውይይት አስፈላጊ መሆኑን ማንሳታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ፖለቲካ ከሌሎች ሳይንሶች ለየት የሚያደርገው ቀመር አለመኖሩና በሁኔታወች የሚገዛና የሚለዋወጥ ሳይንስ ስለሆነ ነው፤ ለዛም ነው አስተዋይ አርቆ አሳቢና መጭውን መተንበይ የሚችሉ ጥሩ ፖለቲካኞች የሚሆኑት፤
ጊዜውና ሁኔታወች በደንብ ያልተገነዘበ የፖለቲካ አካሄድ ዋጋ የሌለውና ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚያመዝን ነው፤
የአማራ ትግል ማንም እየገባ የሚደንስበት ቡና ቤት በመሆኑ መቼ ምን መደረግ መቼ ምን አለማድረግ እንደሚገባ መለየት አልተቻለም፤ለምን ማንን እንደሚታገልና ማንን መደገፍና ምን አላማና ግብ አለን የሚለውም የተዘበራረቀ ነው፤
የተደበላለቀውንና የተሳሳተውን የመነሻና የመዳረሻን አካሄድ ለማስተካከል ችግሩን አምኖ ለመፍትሄው አማራው ካልሰራ በቀጣይ ትግሉ ከተራዘመ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት መገባቱ አይቀርም፤ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ሕዝቡ ፋኖን አንፈልግም መንግሥት ሕግ ያስከብርልን የሚልና የፋኖ ጠላት ሊሆን የሚችል ሁኔታ እየተፈጠረ እየመጣ መሆኑን ምልክቶቹን ማጤን ለትግሉ ጠቃሚ ይሆናል፤
ስለሆነም የተሳሳተ ከተጨባጭ ሁኔታ ይልቅ ስሜትና አጉል ምኞትን ጥገኛ ያደረገ አካሄድ መጨረሻው ሽንፈትና ውድቀት መሆኑን የሚገነዘቡ ነገርን በስክነት መመርመርና ሁኔታዎችን እያስተካከሉ ነገን ማየት የሚችሉ አርቆ አሳቢወች ወደፊት መጥተው አማራውን ከራሱ ልጆች ሰይፍና ከጠላት ሰይፍ ሊታደጉ ይገባል፤ መጨነቅ ያለብን ስላለፈው ሳይሆን ስለ ቀጣዩ ሁኔታ መሆን አለበት።
ከሀሰተኛ መረጃው ጀርባ….!
የሶማሊ ማህበረሰብ ኃይማኖቱን አክባሪ፣ ለሀገር ሽማግሌ፤ ለጋራድ፣ ሱልጣን እና ኡጋዝ እሺ ብሎ መታዘዝን የሚያውቅ፣ከባህላዊ ጎሳ መሪ የሚሰጥ ትዕዛዝን በመቀበል በጋራ እና በአንድነት መኖር ትልቅ ዕሴቱ ነው፡፡
በመሬት ወሰን የተጋጨም ሆነ በድንገተኛ ጸብ የተጣላ ፣ በጎሳ የመሬት አከላለም ሆነ በግጦሽ መሬት ነፍስ የተጣፋ፣ በድንገተኛ ጸብም ይሁን ሆን ብሎ አደጋ ያደረሰ፣ እንዲሁም ለኒካህ (ጋብቻ) የሚሰጥ ጥሎሽን በተመለከተ በጎሳ መሪ፣ በሀገር ሽማግሌ የተወሰነን የሚያከብር ለቃላቸውም የሚገዛ ማህበረሰብ እንደሆነም ይታወቃል፡፡
በትላንትናው ዕለትም የሀገር ሽማግሌዎች፣ ገራዶች፣ ሱልጣኖች በጋራ ስብሰባ በማካሄድ በሶስት ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ የውይይታቸው ሶስት ዋና ነጥቦች፡-
1.የኒካህ (ጋብቻ) ጥሎሽ መቀነስን በተመለከተ፤ ልጆቻችን ለጥሎሽ የሚጠየቁት ዋጋ ከፍተኛ መሆን ወዳልተገባና አላህ ወደ ማይወደው የዝሙት ሊያመራ ስለሚችል ለኒካህ(ጋብቻ) የሚሰጥ ክፍያን መወሰን፤
2.የሰው ህይወት በድንገተኛ ሁኔታ ( በመኪና አደጋና በመሳሰሉት) ያጠፋ ሰው ለቀብር ተብሎ የሚጠየቀው ክፍያን በተመለከተ ገደብ ማስቀመጥ፤
3.በጎሳዎች መካካል በሚፈጠሩ ግጭቶች የሚከሰቱ ጉዳቶች የካሳ አከፋፋል ምን መሆን አለበት በሚሉ ነጥቦች ላይ በመምከር ውሳኔዎችን አሳልፈዋል፡፡
ነገር ግን ይህን እውነታ ሽምጥጥ አድርጎ በመካድ ጦርነት፣ እልቂት፣ ድርቅና ችግር መርዶ እንጂ የሰላም ዜና የሚያሳምማቸው አንዳንድ ትላንትን ናፋቂ የሆኑ የማህበራዊ ሚዲያዎች “በሶማሊ ክልል አንድ ዞን በሼሪአ እንዲተዳደር ተደረገ” በሚል በማህበራዊ ሚዲያ ሀሰተኛ መረጃ ሲያሰራጩ ለመመልከት ተችሏል፡፡
ከለውጡ በኋላ ባሉ ዓመታት እስካሁን ድረስ በክልሉ ላይ ሆን ተብሎ የህዝቡን አንድነትና እድገቱን ለማሰናከል ያልተፈነቀለ ድንጋይ፣ ያልተሞከረ ሴራ፣ ያልታቀደ ተንኮል ባይኖርም ዛሬም በከፍታ እንደምትታይና ለአካባቢ ሁሉ ብርሃን እንደምትሰጥ ኮከብ ይበልጥ ማንጸባረቅና ማብራቱን የቀጠለው የሶማሌ ህዝብ ይህንንም እንደሌሎቹ ታዝቧል፡፡
በዛሬው ዕለትም “ሼሪዓ መንግስት ተመሰረተ” በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛና በሬ ወለደ ብቻ ሳይሆን ኢስላም ጠል አላማ ያነገበ ለዘመናት በሶማሊ ማህበረሰብ ላይ ሲሰራጭ የነበረው ትርክት አንድ ማሳያ ብቻ ሳይሆን ከሀሰተኛ መረጃው ጀርባ ያለውን ግብም ያመላከተ ነው፡፡
ትላንት የሶማሊ ህዝብ ሲገድልና ሲጨፈጭፍ ከነበረ ሃይል ጎን ተሰልፈው የነበሩ እነኚህ አካላት በህዝቡ ሞትና እልቂት ከማዘን ይልቅ ለፍርፋሪ ብለው ህዝቡን ‘አሸባሪና ተገንጣይ’ ሲሉ ስም እንደሰጡት ሁሉ ዛሬ ባይሳካላቸውም በተደጋጋሚ ከሚነዙት ሽብር በተጨማሪ ‘ሸሪዓ ተመሰረተ’ የሚል ካባ ለብሰው መምጣታቸው ዓላማቸውን ይበልጥ ግልፅ ያደረገ ነው፡፡
የሶማሊ ክልል ህዝብን ከሌላው ክልል ህዝብ ጋር የመነጠል ግብን በመያዝ በተከታታይ የሀሰት መረጃዎችን ከሚያሰራጩ ጭር ሲል አልወድም የሆኑ የማህበራዊ ሚዲያዎች መካከል ይህ ዓይነቱን አጀንዳ ተቀብለው የሶማሌ ክልል ማህበረሰብ ትልቅ እሴት የሆነውን የሀገር ሽማግሌና የጎሳ መሪዎችን በመንካትና ያልተባለ በማራገብ መርዛቸውን ሲረጩ ተስተውሏል፡፡
በዚህ አጋጣሚ የሀገር ሽማግሌዎቹና የጎሳ መሪዎቹ የውይይት ዓለማ ህዝብን በሚጠቅሙ ከላይ በተነሱ ባህላዊ የእርቅ መፍቻ መንገዶች ላይ ያተኮሩ ሲሆን ይህን በካደ መልኩ ያልተባለ ተባለ በሚል በሀሰት የሚነዛው ፍጹም ሀሰት ብቻም ሳይሆን ይህ አይነቱ ሴራ ያገኘውንና ያተረፈውን ጠንቅቆ የሚያውቀው የሶማሊ ህዝብን፣የሚከበሩ የጎሳ መሪዎቹንም ሆነ የሀገር ሽማግሌዎቹን የማይወከል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የሶማሊ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ
የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች መጋዣ ሁኖ የሚያገለግለዉ ጽንፈኛ ቡድን መጨረሻዉ የደረሰ ይመስላል፤
በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው ፅንፈኛ፣ ዘራፊና የውጭ ታሪካዊ ጠላቶቻችን መጋዣ በመሆን የሚያገለግለዉ ቅጥረኛ ቡድን እስከዛሬ ድረስ ወደ ሠላማዊ መንገድ ይመለሳል ተብሎ በሠላም ጥሪና በሽምግልናም ሆነ በድርድር ጥረት ቢደረግም ውስጣዊና ውጫዊ ጠላቶቻችንን በመተማመን ወደ ሠላም መንገድ መምጣት አልቻለም።
የሠላም በሮችን ዘግቶ ህዝባችን እያሰቃየ ህሙማን ወደ ሆስፒታል እንዳይሄዱ፣ ነጋዴው ተንቀሳቅሶና ነግዶ እንዳያተርፍ በማድረግ ነዋሪዎች በኑሮ ውድነት እንዲሰቃዩ፣ ተማሪዎች ትምህርት ቤት እንዳይገቡ፣ ማዳበሪያ ለአርሶአደር እንዳይደርስ በማድረግ የአማራ ህዝብ ላይ ጥቁር መጋረጃ ከልሎበት አንድ አመት አሳልፏል። በዚህ እኩይ ተግባር የተሰቃየዉ ህዝብም የመንግስትን እርምጃ እየተጠባበቀ እና እየጠየቀ ይገኛል።
መንግስትም ለሰላም ካለዉ ቁርጨኝነት የመነጨ ከዛሬ ነገ በሠላማዊ መንገድ ይፈታል ብሎ በአነስተኛ ቁጥር ባለው የሠራዊት ኃይል በማጥቃት በሙሉ አቅሙ ወደ ኦፕሬሽን ሳይገባ ቆይቷል።
ፅንፈኛ፣ ዘራፊውና የታሪካዊ ጠላታችን ተላላኪው ቡድን ግን በባንዳነቱ ቀጥሎ ክልሉን እየጎዳ በመሆኑ የማያዳግም እርምጃ በጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን ሊወሰድበት እንደሆነ መረጃዎች ደርሰውናል።
አንበሳው የመከላከያ ሠራዊታችን በተለመደው ባንዳንና ተላላኪን የመጥረግ ልምዱ እርምጃ ሲወስድ ተባባሪ የሚሆኑ፣ መረጃ የሚያሾልኩ፣ ግብአትና ቁሳቁስ የሚሠጡ ወዘተ. ኃይሎች ከፅንፈኛውና ዘራፊ ቡድኑ ተለይተው እንደማይታዩና እርምጃ እንደሚወሰድባቸው መረጃው ደርሶናል። መጠንቀቅ ይበጃል ለባንዳና ተላላኪ መወገን እርምጃው ከባድ ነው።
በትግራይ #ሽሬ የነበረው ስብሰባ ተቋረጠ‼️
ለዛሬ ቀጠሮ ተይዞ የነበረው የሽሬ መድረክ ተበተነ‼️ ጄኔራል ፃድቃን ወደ አዳራሹ ከገቡ በኋላ የአዳራሹ ድባብ ጥሩ መስሎ ያልታያቸቸው ጀጀራል ፃድቃን አዳራሹን ለቀው የወጡት ከሌሎቹ ግዚያዊ አስተዳደሮች ቀደም ብሎ እንደሆነ ተነግሯል።
ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር አዳራሹ ውስጥ የቆዩት ሹማምንት ስብሰባውን መቀጠል እንደማይችሉ ተረድተው ለሌላ ቀን ቀጠሮ በመያዝ አዳራሹን ለቀው እንዲወጡ የተገደዱት ከተሰብሳቢዎቹ መካከል አንዲት ሴትዎ ወንበር አንስታ እነሱ ወደ ተቀመጡበት አቅጣጫ ለመወርወር ስትገለገል ታይታለች::
ዶ/ር አሸብርን ጨምሮ የ #ኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮች በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ክስ ተመሰረተባቸው
የ #ኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ አራት አመራሮች በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ሌሎች ተያያዝ ጉዳዮች ክስ ተመሰረተባቸው።
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፤ ዐቃቤ ነዋይዋ ዶ/ር ኤደን አሸናፊ፣ ዋና ፀሐፊ አቶ ዳዊት አስፋው እና ምክትል ፀሐፊ አቶ ገዛኸኝ ወልዴም ከተከሳሾቹ መካከል ነው።
ክሱን የመሰረቱት ሻለቃ አትሌት #ኃይሌ_ገብረሥላሴ፣ አትሌት #ገዛኸኝ_አበራ፣ የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ ቴኒስ ፌዴሬሽን ናቸው።
በከሳሾቹ ጠበቆች በኩል ክሱ የቀረበለት የፌደራል አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት አራድ ምድብ ችሎት ኮሚቴው፤ ግንቦት 5 እና ሰኔ 4፤ 2016 ዓ.ም. ያካሄዳቸው ጠቅላላ ጉባኤዎች እና ውሳኔዎች እንዲታገዱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
የከሳሽ ጠበቃ የሆኑት አቶ አያሌው ቢታኔ “ከፓሪስ ኦሊምፒክ ጋር በተያያዘ [ተከሳሾቹ] ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ ተሰማርተዋል ብለን እንጠረጥራለን። የወንጀል ተጠያቂነቱ እንዳለ ሆኖ ሥልጣናቸውን ያለ አግባብ በመጠቀም ኦሊምፒክ ኮሚቴውን [በዝብዘዋል]” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ጠበቃው አክለው “ደብዳቤ ስለተጻፈ ብቻ የማይመለከተው ሰው [ወደ ፓሪስ] ይሄድ ነበር” ብለዋል።
ለ2017 ዓመት የመስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ
የመስቀል በዓል የሕልም ጉልበት የታየበት በዓል ነው፡፡
ንግሥት ዕሌኒ መስቀሉን ለማውጣት ያለመችው ምንም አመቺ ነገር ባልነበረበት ጊዜ ነው፡፡ ዙሪያዋ ጨለማ ነበር፡፡ መንገዶች ሁሉ ዝግ ነበሩ፡፡ ነገሮች ሁሉ አስቸጋሪ ነበሩ፡፡ ማንም በማያስበው ጊዜ፤ አይቻልም አይሞከርም በሚባልበት ወቅት፤ አንድ ቀን፤ ፈጣሪዋ ሲፈቅድ፤ መስቀሉን ከተቀበረበት ሥፍራ ለማውጣት ሕልም ነበራት፡፡
ሕልሟ እንዲሳካ ሠራች፤ ታገለች፡፡ ጨለማውን እየገፈፈች፤ አስቸጋሪውን ጎዳና እየጠረገች፤ ከውስብስብ ችግሮች ጋር እየተጋፈጠች ወደ ፊት ተጓዘች፡፡ በመጨረሻም ኢየሩሳሌም ተሻግራ፣ መስቀሉን ከተቀበረበት ሥፍራ ለማውጣት በቃች፡፡ ሕልሟ እውን ሆነ፡፡ ታሪክን ቀየረች፡፡ ልዕልናን ዐወጀች፡፡ ደመራ ለሚታገል፤ ተስፋ ለማይቆርጥና እስከ መጨረሻው ለሚጸና ሰው ሕልሙ አንድ ቀን እውን እንደሚሆን የሚያሳይ ትእምርት ነው፡፡
እዮሃ፤ ማለት “ይሄዋ” ማለት ነው ይባላል፡፡
ይሄው ተገኘ፤ ይሄው ተሳካ፤ ይሄው እውን ሆነ ማለት ነው፡፡ ከበረቱ፤ ከታገሉና ከጸኑ የማይሳካ ምን ነገር አለ? ሕልሙን ለሚያውቅ፤ ሕልሙ እንዲሳካ በነገሮች ተስፋ ሳይቆርጥ ለሚለፋ፤ እንደ ንግሥት እሌኒ ሕልሙ እውን ሆኖ አንድ ቀን ማየቱ አይቀርም፡፡ የሕልሙን ደመራ መደመሩ አይቀርም፡፡ “እዮሃ”፤ “ይሄዋ!” ማለቱ አይቀርም፡፡
መስቀል ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በሁለት መንገድ የሚያሳይ በዓል ነው፡፡ ደመራው ከእንጨት ወደ ችቦ፤ ከችቦ ወደ ደመራ የሚያድግበት መንገድ መደመር ምን ያህል ኃይልና ጉልበት እንዳለው ያሳያል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ መስቀል በተለያየ መንገድ፣ በተለያየ ባህልና አከባበር በብዙ ብሔረሰቦች ይከበራል፡፡ ይሄ ደግሞ በኅብረ ብሔራዊነታችን ውስጥ ያለውን ነባር ትሥሥር፣ የወል ትርክትና አንድነት የሚሳይ ነው፡፡
እንዲህ ዓይነት በዓላት ሃይማኖታውያን ብቻ አይደሉም፡፡ የኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን መገለጫዎች ጭምር ናቸው፡፡ በመደመር ውስጥ ያለውን ጥንካሬና ጉልበት የሚሳዩ ትውልድ ለእኛ ትምህርት ያቆማቸው ምልክቶች ናቸው፡፡
ደመራውን በደመርን ጊዜ፤ ደመራውን በለኮስን ጊዜ፤ እንደየባህላችን የመስቀልን በዓል ለማክበር በቤተሰብና በማኅበረሰብ ደረጃ በተሰባሰብን ጊዜ ኢትዮጵያን እናስባት፡፡
የሁላችንም ዕሴቶች፣ ባህሎች፣ ወጎች፣ ዐቅሞች፣ ጸጋዎች፣ ሀብቶች፣ ቋንቋዎች፣ ታሪኮች፣ ወዘተ. ተደምረው ኢትዮጵያን ታላቅ፣ የበለጸገችና የተከበረች ሊያደርጓት እንደሚችሉ እናስብ፡፡ ኢትዮጵያ የእነዚህ ሁሉ ድምር መሆኗን እናስብ፡፡ ከድምሩም በላይ መሆኗንም እናስብ፡፡ ደመራውን እያሳየን ለልጆቻችን ከሃይማኖታዊና ባህላዊ ትርጉሙ በተጨማሪ “እኛ ኢትዮጵያውያን ከተደመርን እንደ ደመራው ብርቱ እንሆናለን፤ እንደደመራው ከፍ ብለን እናበራለን” በሏቸው፡፡
መልካም የመስቀል በዓል ይሁን፡፡
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
መስከረም 16፣ 2017 ዓ.ም
ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል:: ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት
አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
Tel: 0913858561
ልዩ መረጃ‼️
እየሰነበተ ሳይሆን እየተሰናበተ ነው
ራሱን የአማራ ፋኖ በወሎ አሳምነው ኮር እሸት ክፍለጦር ዋና አዛዥ ብሎ የሚጠራው የጽንፈኛው ቀንደኛ ሠማኝ አማረ እስከወዲያኛው በጀግናዉ የመከላከያ ሰራዊት እስከነ 8 አጃቢዎቹ ተሸኝቷል። ከሞት የተረፈዉ በአካባቢዉ የሚገኘዉ ጽንፈኛ ቡድንም ሞት ቀርቦት መዉጫና መግቢያዉ ጠፍቶበት እየተቅበዘበዘ እንደሆነ ከአካባቢው ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል።
መስከረም 16/2017 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የ2017 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በሠላም እንዲከበር የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባቸው የሚታወቅ ሲሆን መስከረም 16 ቀን 2017 ዓ/ም ከረፋዱ 5:00 ሰአት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
በዚህም መሠረት ፦
• ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ላይ
• ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና
• ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ
• ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ አጠገብ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር ላይ)
• ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት ላይ
• ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ
• ከራስ ሆቴል ወደ ስታድዮም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል ላይ
• ከሃራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ
• ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ
• ከዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሼል አጠገብ እንዲሁም
• ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወሰደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ ከመስከረም 16 ቀን 2017 ዓ/ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ መንገድ የሚዘጋ ሲሆን በተጨማሪም በተገለፁት መስመሮች ላይ ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ይሁን ለረዥም ጊዜ ማቆም የተከለከለ መሆኑን አሽከርካሪዎች ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን በመጠቀምና የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚያሳይዋቸው መንገድ በመጓዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን ያቀርባል።
በአሉ ያለ አንዳች የፀጥታ ስጋት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጎ ወደ ስራ መግባቱን ያስታወሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በዓሉ ኃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር እና የበዓሉ ታዳሚዎች ሠላምና ደህንነት እንዲጠበቅ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጿል።
ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በ011-1-11-01-11 እንዲሁም በ991 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፥ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራውን የህወሓት ቡድን አስጠነቀቁ።
ፕሬዜዳንቱ በማስጠንቀቂያቸው „ ቡድን „ ሲሉ የጠሩት ሃይል የወረዳና የከተማ የህዝብ ምክር ቤቶች ለመረበሽ እየሄደበት ያለው ርቀትና በማድረግ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ ማቆም አለበት ብለዋል።
መስከረም 14/2017 ዓ.ም በፕሬዜዳንቱ ፊርማ ተፈርሞ ለሁሉም የወረዳና የከተማ ም/ቤቶች የተፃፈው የማስጠንቀቅያ ደብዳቤ „ የህዝብ ምክር ቤቶች የትግራይ ጊዚያዊ መንግስትና የህዝቡ አካል እንጂ የህወሓት መዋቅር አለመሆናቸው አውቆ ‚ ቡድኑ ‚ የራሱ መሳሪያ ለማድረግ እያካሄደ ያለውን መሯሯጥና ውንብድና ማቆም አለበት „ ይላል።
ስለሆነም ምክር ቤቶቹ የመንግስትና የህዝብ መዋቅር መሆናቸው በማመን ‚ ቡድኑ‘ ምክር ቤቶቹ በመጠቀም ያልደገፉትንና ሃሳቡ ያልተቀበሉት የመንግስት ሹመኞች ጥላሸት ለመቀባትና ከሃላፊነት ለማውረድ የሚያደርገው ጥረት መቆም አለበት ሲል አስጠንቅቋል።
ምክር ቤቶቹም ይህንን የመንግሰትና የፓለቲካ ድርጅት የሚቀላቅል ህገ-ወጥ ጣልቃ ገብነት ማውገዝ አለባቸው ብሏል።
„ ይህ ሳይሆን ከቀረ ግን ህግና ስርዓት ለማስከበር ሲባል ወደ ህጋዊ ተጠያቂነት መሸጋገር የግድ ይሆናል „ በማለት አክለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ከቀናት በፊት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ያወጣውን የአቋም መግለጫ የሚቃወም መግለጫ አውጥቷል።
በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው ህወሓት መስከረም 14/2017 ዓ.ም ያወጣው ባለ 4 ነጥብ የተቋውሞ መግለጫ ፤ „ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ጊዚያዊ ስራዎች ለመስራት መቋቋሙ ተዘንግቶ ከተቀመጠለት የቆይታ የጊዜ ሰሌዳ በላይ እንዲቆይና ራሱን ወደ ተሟላ የመንግስት ሃላፊነት ለመለወጥ የሚያደርገው ጥረት ፀረ ዴሞክራሲና ኢ-ህገመንግስታዊ ነው „ ብሏል።
ምንም እንኳን „ ኢ-ህገመንግስታዊ „ ብሎ ቢገልጽም የአገር ወይም የክልሉ ህገ-መንግስት አንቀፆችን አላጣቀሰም።
የእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ቡድን „ ጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሰጠው ተልእኮ ወደ ጎን በመተው ህወሓት ለማፍረስ ፣ ሰራዊት ለማዘዝና የመንግስትና ህዝብ ሃብት በመጠቀም የትግራይ ህዝብ አንድነት ለመበተን እየሄደበት ያለውን የተሳሳተ መንገድ ሊያቆም ይገባል „ ሲል አሳስቧል።
የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት ለማስጀመር የቅድመ ምዝገባና ማረጋገጫ ሂደት ተጀመረ
ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመት ተግባራዊ ለማድረግ ያቀደችውን የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት አለማቀፍ ተቀባይነት እንዲኖረው ለማስቻል ያለመ ምክክር ከአለማቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተካሂዷል።በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የተመራ ልዑክ በካናዳ ሞንትሪያል ከአለማቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጁዋን ካርሎስ ሳላዛር ጋር በመገናኘት ምክክር አድርገዋል። በዚህ ወቅትም ዋና ዳይሬክተሯ ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ዘርፍ የዳበረ ልምድ ያላትና አለምን በአገልግሎት እያስተሳሰረ ያለ ግዙፍ የአየርመንገድ ባለቤት መሆኗን አስታውሰዋል።አለማቀፉ የአቪዬሽን ድርጅት ከጉዞ ሰነድ የደህንነት ስራዎች ጋር በተያያዘ እያደረገ ላለው ድጋፍ ዋና ዳይሬክተሯ ምስጋና አቅርበዋል።ድርጅቱ በቀጣይም ኢትዮጵያ ወደ ኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት ስርዓት በምታደርገው የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠናን ጨምሮ ልዩ ልዩ ድጋፎች እንዲያደርግ ወ/ሮ ሰላማዊት ጠይቀዋል።
ዋና ዳይሬክተር ጁዋን ካርሎስ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ወደ ኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት ስርዓት ለመግባት ያሳለፈችውን ውሳኔ በማድነቅ በቀጣይ ተቋማቸው የማይቋረጥ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
ልዑኩ ከዚህ በተጨማሪ በየብስ የድንበር ቁጥጥር ላይ ተግባራዊ የሚደረገው ቴክኖሎጂ ከአለማቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ደረጃ ጋር የተጣጣመ መሆኑን የማረጋገጥ ምክክር ከሚመለከታቸው የተቋሙ ሃላፊዎች ጋር ያካሄደ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም ተመሳሳይ ምክክሮች እንደሚካሄዱ ተጠቁሟል።
ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመት የኤሌክትሪክ ፓስፖርት ስርዓት እንድትገባ ለማድረግ የዝግጅት ስራ እየተጠናቀቀ ይገኛል።
ደብረጺዮን ገብረሚካኤል፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጀነራል ጻድቃን ገብረተንሳይን “ሥልጣን ለመጠቅለል” እና “የቆየ ቂማቸውን ለመወጣት” ይፈልጋሉ በማለት ቅዳሜ’ለት መቀሌ ውስጥ በተካሄደ ሕዝናዊ ስብሰባ ላይ ወቅሰዋል።
ደብረጺዮን፣ በጦርነቱ ወቅት የትግራይ ተዋጊዎች አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በደረሱ ጊዜ “እኔ ድርድር ያስፈልጋል” ስል፣ ጻድቃን “ከማን ጋር ነው የምንደራደረው? ውጊያው አልቋል” በማለት ይናገር ነበር ብለዋል። የጊዜያዊ አስተዳደሩ ባለሥልጣናት ሕወሓት ሰላም እንደማይፈልግ አድርገው ያቀርባሉ ያሉት ደብረጺዮን፣ ይህ ግን የተሳሳተ ፍረጃ ነው በማለት ተናግረዋል። በደቡባዊ ዞን በተካሄደ አንድ መድረክ ላይ ጀነራል ጻድቃን እሱ እና እነ ጌታቸው ሰላም ፈላጊ፤ ባንጻሩ እኛ የጦርነት አቀንቃኞች እንደኾንን አድርገው ተናግረዋል በማለትም ደብረጺዮን ወቅሰዋል። ደብረጺዮን አያይዘውም፣ እነ ጌታቸው ተኩስ አቁም እንዲፈራረሙ ፕሪቶሪያ ሲላኩ፣ ከተሠጣቸው ሥልጣን ውጭ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የሚያቋቁም ስምምነት ተፈራርመዋል በማለት ከሰዋል።
የመስቀል ስር ቁማርተኞች መስቀሉን አውልቁት!!
በአማራ ክልል እራሱን ፋኖ በማለት የሚጠራው የጽንፈኛና የመሃይም ስብስብ ትምህርት ቤቶችን አዘግተው ጭፈራ ቤት አድርገውታል ፊደል ጠል የሆነው የጽንፈኛው ስብስብ ሁለት መምህራንን ገድለዋል 😓
ይህ የብልጽግና ቢሮ አልያም የአመራሮች ቤት አይደለም ትምህርት ቤት ነው ። የቀጣይ ትውልድ እድል ላይ ቆመው የሚጨፍሩ በቁም የሞቱ ናቸው ። ለዕውቀት ያልታደለ ጭንቅላት ለተንኮል ተወዳዳሪ የለውምና የመሃይሞች ስብስብ መጨረሻው ትውልድን በሚቀርጽ ትምህርት ቤት አዘግቶ አስተማሪ ገሎ ዳንኪራ መምታት ነው::
እነ እማዋጉሽ የማይነግሯችሁ እውንታ!
ከሰሞኑ በጎንደር አካባቢ በነበረው ግጭት የጽንፈኛው ቡድን ምነው በቀረብኝ እስኪል ተወቅጧል።
መከላከያ ለታክቲክ ወደኋላ ሲል ድል የቀናው መስሎት የመጣው ጽንፈኛ የአንበሳ አፍ መግባቱን ያወቀው በኋላ ነው።
በነበረው ውጊያ
1. ጎንደር ከተማ 36 ጽንፈኛ የተደመሰሰ ሲሆን 25 ቆስሏል። ከዚህ በላይ በከፍተኛ ሁኔታ ቁጥሩ እንደሚጨምር ይገመታል።
2. ትናንት ደባርቅ በነበረው ግጭት 31 ጽንፈኛ የተደመሰሰ ሲሆን፣ 52 ቆስሏል። ከተደመሰሱት ውስጥ 18ቱ ቀንደኛ የጠላት መሪዎች ናቸው።
3. ዛሬ አምባጊዮርጊስ ራዳር ላይ በነበረው ግጭት 14 ጠላት ተደምሷል።
4. ከትናንት በፊት ሳንኪሳ ላይ የቆሰለው የአካባቢው የጽንፈኛው አለቃ የደረጀ በላይ ልጅ ዋሲሁን ደረጀ በላይ በደረሰበት ጉዳት ዘግይቶ ሞቷል።
መከላከያ የኢትዮጵያ መከታ
መከላከያ በሮቹን ከፍቶ ሲያስገባቸው፦ ለምን በሩ ተከፈተ ብለዉ የማያስቡ ከፉከራ ዉጪ ቅንጣት የወታደራዊ ጥበብ የሌላቸው የጫካ ታጣቂዎች ናቸው ያሉት። ወታደሩ ወደኋላ የተሳበው መከላከያን በግንባር ሰለማይገጥሙት ወደፊት ለፊት እንዲመጡ የተጠቀመባቸዉ ወታደራዊ ጥበብ ነው። Finally፦ ድል አብሳሪዎቹ ወደ መርዶ ነጋሪነት ተቀይረዋል። ;)
Читать полностью…ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) በአደረባቸው ህመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) ጳጉሜን 4 ቀን 2012 ዓ.ም የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሹመው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡
በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት በፖለቲካ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ከቆዩ አንጋፋ ሰዎች መካከል አንዱ መሆናቸው የሚነገርላቸው በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር)÷ የተፎካካሪ ፓርቲው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀ-መንበር ሆነው ማገልገላቸው ይታወቃል፡፡
የተለያዩ ፓርቲዎችን በአባልነት የያዘውን የመድረክ ፓርቲንም በሊቀ-መንበርነት የመሩ ሲሆን÷ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም በመምህርነት እንዲሁም በትምህርት ሚኒስትር ዴዔታነት ማገልገላቸው የሚታወስ ነው፡፡
“ከጦርነቱ በኃላ የህወሓት ደጋፊነቴን ትቻለሁ “ አሉላ ሰለሞን
“ጦርነት ባህላዊ ጨዋታችን ነው” አሉላ ሰለሞን ከጦርነቱ በፊት
እርግጥ ነው በትግራይ ጆኖሳይድ አለመጸሙን እኛ ከተናገርነው በላይ የህወሓቱ ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል ከማራማዊት ጋር ባደረገው ቆይታ ግልጽ አድርጎልናል:: እንደው በትግራይ ጆኖሳይድ ተፈጽሟል እንኳን ቢባል ፈጻሚውና ሃላፊነቱን የሚወስደው እንደነ አሉላ ሰለሞን የመሰሉ በሎም እያሉ ውጪ ተቀምጠው ወጣቱን ያስፈጁት ስለመሆናቸው መናገር ተመራማሪና ፖለቲካ አዋቂ መሆን አያስፈልግም::
በ5 ሺህ የዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት በቤልጂየም ብራሰልስ በተካሄደው የ2024 ዳያመንድ ሊግ 5 ሺህ የወንዶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ በመያዝ ተከታትለው ገብተዋል።
በውድድሩ አትሌት በሪሁ አረጋዊ 12:43.66 በሆነ ሰዓት በመግባት በውድድሩ ቀዳሚ ሆኖ አጠናቋል።
አትሌት በሪሁ አረጋዊን በመከተል ሀጎስ ገብረህይወት 12:44.25 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ እንዲሁም ጥላሁን በቀለ 12:45.63 በሆነ ሰዓት በመግባት ሶስተኛ ደረጃ ይዘው በመግባት ውድድሩ ላይ ደምቀው ታይተዋል።
ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች
ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተእ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።
ሚለየን ምንድነው?
የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ
🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።
🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።
🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።
🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።
🪄We Care
አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ
📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69
www.elegas.com.tr
Email:- ethiopia@elegas.com.tr