natnaelmekonnen21 | Неотсортированное

Telegram-канал natnaelmekonnen21 - Natnael Mekonnen

169400

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7 Facebook.com/natnaelmekonnen.et Instagram.com/natnaelmekonnen21

Подписаться на канал

Natnael Mekonnen

ጦርነቱን ማን አሸነፈ ተሸነፈ የሚለውን ለግዜው እንተወው:: አቶ ጌታቸው ግን እውነቱን ይናገራል:: ህወሓት እጇን ተጠምዝዛ ህይወቷን ለማዳን ስትል ፕሪቶሪያን እንደፈረመች ግልፅ መሆኑን አቶ ጌታቸው ይመሰከራል:: ህወሓት የፕሪቶሪያን ስምምነት የተፈራረመው ለትግራይ ህዝብ አዝኖ ሳይሆን የራሱን ህይወት ለማትረፍ ነው::

እውነታው ይሄ ነው! በሞት አፋፍ ላይ እያለ አድኑኝ ብሎ የፈረመውን የፕሪቶሪያ ስምምነት ዛሬ እንጥፍጣፊ ህይወት ሲያገኝ ህወህት አሁን የራያን ህዝብ እያሰቃየ ይገኛል። ይሄ የተሠጠ እድል ዳግም ላይገኝ ይችላልና ሰከን ብሎ ማሰብ ጥሩ ነው ህዝብን ማሰቃየት ሊቆም ይገባል!!!

በዚ ንግግር መንግስት ራያና ወልቃይትን ለህውሀት መልሷል ልዩ ሀይሉም ይፍታ የተባለው እነዚን ቦታዎች ሊያስረክብ ስለሆነ ነው ብለው ሲያሶሩ የነበሩት የዛኛው ሠፈር ሠዎች ነበሩ በዚህም ወሬ የተነሳ የአማራ ክልል ያልተፈለገ ግጭት ውስጥ ተገባ ብዙ ሂወት አለፈ ብዙ ንብረትም ወደመ ዛሬ ጌታቸው እውነቱን ነገረን እነ አጎዛውና አናሎግ ግን እውነቱን እያወቁ ለሽቀላቸው ብለው የስንት ደሀ ልጅ አስጨረሱ

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ዛሬ ከሰዓት በሆላ የዘይትና ስኳር አቅርቦትን ለማሳለጥ ከፍራንኮ ቫሉታ እና አጠቃላይ አስመጪዎች ማህበር ተወካዮች ጋር ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል:: ብዙ መጠን ያለው የዘይት እና ስኳር ምርት በትራንስፖርት ሂደት እና በጉምሩክ ጣቢያዎች ላይ እንደሚገኝ እንዲሁም አዲስ የቫት ክፊያ አሰራር በመንግስት ተውእስኖ በመተግበሩ ምክንያት የተወሰነ መዘግየቶች እንዳጋጠማቸው የገመገምን ሲሆን በአጭር ጊዜ ያለምንም የዋጋ ጭማሪ ለገበያው እና ለህብረተሰቡ እንዲያቀርቡ ተስማምተናል::

የንግድ ትስስርና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዶር ካሳሁን ጎፌ

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ጀነራል ታደሰ ወረዳ በትግራይ የጸጥታ ሁኔታ ላይ በትግራይ ብሔራዊ የፖለቲካ አስተዳደር ጉባኤ ያስተላለፉት መልእክት

★ በትግራይ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ከምንጊዜውም በላይ የከፋ ነው።

★ ህገ-ወጥ የማዕድን ቁፋሮ ጨምሯል በዚህም ምክንያት ህገ-ወጥ ማዕድን የህዝቡን ህይወትን እና አካባቢን እየጎዳ ነው።

★ ትግራይ ኮረብታ ፣ታራሚ መሬት ፣እፅዋት እየተበላሹ ነው።

★ ቻይናውያን፣ ሱዳናውያን እና ሴኔጋልን ጨምሮ በርካታ የውጭ ሀገር ዜጎች በህገወጥ ማዕድን ማውጣት ላይ ተሰማርተዋል።

★ የትግራይ ህዝብ ከማዕድን የተፈጥሮ ሃብት ማግኘት የሚገባውን ህጋዊ ጥቅም እያገኘ አይደለም።

★ የሚመረተው ወርቅ ወዴት እንደሚሄድ አይታወቅም እና በጥቁር ገበያ ይሸጣል።

★ የመሬት ዘረፋ፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ዘረፋ፣ አስገድዶ መድፈር እና ሌሎችም ወንጀሎች ጨምረዋል።

★የትግራይ ፀጥታ የሚረጋገጠው ህገ ወጥ ተግባር ላይ የተሰማሩትን በቁጥጥር ስር በማዋል ህግን በማስከበር ነው።

★ ይህንን የሚያስፈጽም የጸጥታ ሃይል አለን።

★ ተያያዥ ተግባራት ከህግ አስከባሪ አካላት ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም።

★ በማንኛውም ህገወጥ ተግባር የተሳተፈ ሁሉ ለፍርድ ይቅረቡ።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የኢትዮጵያ መንግስት 1,500 ብር የሚከፈላቸው ሰራተኞችን ደመወዝ በ300 ፐርሰንት ሊጨምር ነው

የኢትዮጵያ መንግስት ለደመወዝ ጭማሪ ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ እንደመደበ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። በቅርቡ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚቀርበው ተጨማሪ በጀት የሚካተተው የደመወዝ ጭማሪ በዋናነት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የመንግስት ሰራተኞችን የሚመለከት እንደሆነ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ተሿሚዎች ብዙ ላያገኙ ይችላሉ” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የደመወዝ ጭማሪን ጉዳይ ያነሱት፤ ከክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ከፌደራል መንግስት ባለስልጣናት እና ከግል ባንኮች ፕሬዝዳንቶች ጋር በተደረገ ውይይት ነው። ከሁለት ሰዓት በላይ የፈጀው ውይይት፤ የኢትዮጵያ መንግስት የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያተኮረ ቢሆንም በገበያ ላይ ወደ ተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓት የተደረገው ሽግግር ዋነኛ ትኩረት አግኝቷል።

አብይ በትላንቱ ገለጻቸው መንግስታቸው በተገበረው የኢኮኖሚ ማሻሻያ “የሚጎዱ ሰዎች” መኖራቸውን አምነዋል። የኢኮኖሚ ማሻሻያው “በትሩን የሚያሳርፍባቸው” ካሏቸው መካከል የመንግስት ሰራተኞች እና ገበሬዎች ይገኙበታል። ተጽዕኖውን ለመቋቋም መንግስታቸው ለሚያደርገው የደመወዝ ጭማሪ 90 ቢሊዮን ብር እንዳስፈለገውም ጠቅሰዋል።

በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የመንግስት ሰራተኞች የሚደረገው የደመወዝ ጭማሪ “በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ አይታወቅም” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አጽንኦት ሰጥተዋል። በወር 1,500 ብር የሚከፈላቸው የመንግስት ሰራተኞች 300 ፐርሰንት የደመወዝ ጭማሪ እንደሚደረግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ከ25 ሺህ ብር በላይ ወርሃዊ ደመወዝ የሚከፈላቸውን የመንግስት ሰራተኞች “ለጊዜው ታገሰን አልነው” ሲሉም ተደምጠዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች

ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተ‍እ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበ‍ኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።

ሚለየን ምንድነው?

የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ

🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።

🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።

🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።

🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።

🪄We Care

አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ

📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69

www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

📱በፍልስጤም ሕዝባዊ ነፃነት ግንባር መስራችነቱ የሚታወቀው ዋዲ ሀዳድ ስማቸው በሞሳድ የግድያ ዝርዝር ውስጥ ከተካተቱ ግለሰቦች ዋነኛው ነበር። የግድያ ትዕዛዙ ከወጣ ስድስት ክረምቶች በኋላም ግን የእስራኤሉ የስለላ ተቋም ሀዳድን መግደል ሳይቻለው ቆየ። ሆኖም ወርሃ ጥር 1978 የሀዳድን የቅርብ የግንኙነት መረብ ሰብሮ የገባ አንድ የሞሳድ ወኪል በጄምስ ቦንድ ልብ አንጠልጣይ ፊልም ላይ የሚታይ አይነት ነገር በተፈላጊው ግለሰብ ላይ ፈጸመ። ቀጣዩን የዩትዩብ ሊንክ ስትከፍቱ የሀዳድን መጨረሻ ጨምሮ ሞሳድ ከቤይሩት እስከ ፓሪስ የፈፀማቸውን ስድስት ልዩ የግድያ ግዳጆች በተመለከተ ሚስጥራዊ መረጃዎችን ታደምጣላችሁ፡፡ እግረ መንገዳችሁን ቪዲዮውን ላይክ፣ ቻናሉን ሰብስክራይብ እንድታደርጉም በማክበር ተጋብዛችኋል፡፡
https://youtu.be/xWnEnoPtTP4?si=mF-PRiFxdyXjtszt

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት፣ ለጎፋ ዞን የተጎጂ ቤተሰቦች የገንዘብና የአይነት ድጋፍ አደረገ

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለደረሰባቸው ቤተሰቦች ድጋፍ የሚሆን የአንድ ሚሊዮን ብር አልባሳትና የአንድ ሚሊዮን ብር ጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ለግሷል። ድጋፉን የተቋሙ የስራ ሃላፊዎች ጉዳቱ በደረሰበት አከባቢ በመሄድ ለጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጅነር ዳግማዊ አየለ ያስረከቡ ሲሆን የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ተቋም ሐላፊዎችና ሰራተኞች ላደረጉት ድጋፍ በዞኑ ህዝብ ስም አመስግነው፣ የተደረገው ድጋፍም በአደጋው ለተጎዱ የቤተሰብ አባላት እንደሚከፋፈል ገልፀዋል።የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች በቀጣይም ለተጎዱ ወገኖች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ከተቋሙ ድረ-ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል!

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

"ስማችን እውነት ነው,ስራችንም የእውነት ነው"

❇️ከዚህ በፊት የተመረጡ ቦታዎች ላይ ጥንቅቅ አድርገን እንዳስረከብናቸው አሁንም እጅግ ውብ ለኑሮ መቹ በከተማችን የተመረጡ ቦታዎች

❇️በሳርቤት እና በ ቦሌ ቅድመ ክፋያ 770 ( ሰባትመቶ ሰባ ) ሽህ ጀምሮ በመሸጥ እንገኛለን

✅ 65.7 , 86 , 90 ካሬ ባለ 1 መኝታ
✅ 98 , 100 , 114 ካሬ ባለ 2 መኝታ
✅ 140 , 152 , 212 ካሬ ባለ 3 መኝታ

❇️የቤት ባለቤት ከመሆን ባለፈ፣በመሀል አዲስ አበባ የምንገነባቸው ቅነጡ ቤቶቻችን ኢንቨስተር ያደርጉታል !
✅ምስክሮቻችን ከዚህ በፊት ሰርተን ያስርከብናቸው ደንበኞቻችን::

❇️ወለል ውፍረት 25ሲ.ሜ ኮንክሪት አስላብ።
✅ከወለል ወለል እርዝማኔ 3.2 ሜትር
❇️የውጭ በሮቻችን 100ኪሎ የሚመዝኑ፣ከኮንክሪት እና ከብርት የሚስሩ፣ድመፁ የማያስተላልፍ ፣6 የተለያዩ ቦታዎች የሚቆልፍ።


✅Reality real estate✅
🚧 3B+G+17 አፓርታማ
🚘 sufficient parking space
🏋️gymnasium and spa
👉🏻17 th floor club house
👉🏻under ground water and backup generator

💰 10% ቅድመ ክፍያ

What makes Reality real estate different
- Affordable price
- Easy payment schedule
- Prime Location
- Reputed company
- Early Delivery
የድርጅቱ የሽያጭ አማካሪ
☎️0976 20 68 68
0951 69 14 66

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የኢኮኖሚ ባለሙያው ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በርኸ በብዙዎች ዘንድ ውዝግብ ስለፈጠረው አዲሱ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ከአርትስ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በተለይም ከገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ጋር በተገናኘ የሃገር ውስጥ ገበያው ላይ ምን አይነት ተፅዕኖዎች እና ጥቅሞች ሊኖሩት እንደሚችሉ እንዲሁም ተያይዘው ሊመጡ የሚችሉ ነጥቦችን አንስተዋል።

ሙሉውን ለማድመጥ 👉 https://youtu.be/BsP-uC0sP7Q

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ38ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 38ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

38ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 38ኛ መደበኛ ስብሰባው ዓለም ዐቀፍ የልማት ማህበር ጋር የተደረገውን የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት ለማፅደቅ በተዘጋጀው አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ከዓለም ዐቀፍ የልማት ማህበር ጋር የተደረገው የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት የ1.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚያስገኝ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በእርዳታ፣ 500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደግሞ በብድር መልክ የተገኘ ነው፡፡

የፋይናንስ ድጋፉ የኢትዮጵያ መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት የጀመራቸውን የሪፎርም ሥራዎች ለማስፈጸም በተለይም ለሥራ ፈጠራ፣ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለመቅረፍ፣ የመዋቅር ማስተካከያ ለማድረግ እንዲሁም የፌደራል መንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትን በቀጥታ ለመደገፍ የሚውል ነው፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሰነዱ ላይ ከተወያየ በኋላ ብድሩ ከወለድ ነፃ ፣ የ6 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ38 ዓመታት ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ እንዲሁም ከአገራችን የብድር አስተዳደር ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣም መሆኑን በማረጋገጥ ስምምነቱን አጽድቆ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ብሔራዊ ባንክ የወርቅ ግዢ ክፍያን የሚፈጽመው ራሱ በሚያወጣው የውጭ ምንዛሬ ተመን መሆኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከአምራቾች እና አቅራቢዎች ወርቅ የሚገዛው፤ ራሱ በሚያወጣው የውጭ ምንዛሬ ተመን ተሰልቶ መሆኑን አስታወቀ። ብሔራዊ ባንክ በወርቅ መግዣ ላይ አዲሱን አሰራር ተግባራዊ ያደረገው፤ የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያ የሚመራ መደረጉን ተከትሎ ነው።

የውጭ ምንዛሬ ተመን “በባንኮች እና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወሰንበት የገበያ ስርአት” መሸጋገሩ ይፋ የተደረገው ከትላንት በስቲያ ሰኞ ሐምሌ 22፤ 2016 ነበር። እንደ ወርቅ እና ብር ያሉትን የከበሩ ማዕድናት የመግዛት እና የመሸጥ ስልጣን በአዋጅ የተሰጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፤ በዓለም የወርቅ ዋጋ ላይ ማበረታቻዎችን በማከል ወርቅን ከአምራቾች እና ከአቅራቢዎች ሲገዛ ቆይቷል።

ባንኩ ባለፈው ሰኔ ወር ይፋ ባደረገው መመሪያ፤ በዓለም ገበያ ዋጋ ላይ ከ60 እስከ 72 በመቶ ማበረታቻ ጭማሪ በማድረግ የወርቅ ግዢ እንደሚፈጸም ገልጾ ነበር። ብሔራዊው ባንክ ዛሬ ሐምሌ 24፤ 2016 ባወጣው መግለጫ፤ “ለማንኛውም ወርቅ አቅራቢ ክፍያ የሚፈጸመው፤ የእለቱን ዓለም ዓቀፍ የወርቅ ዋጋ በእለቱ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣዉ የውጭ ምንዛሪ ተመን ተባዝቶ” እንደሆነ አስታውቋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

“በህወሓት አመራር መካከል የተፈጠረው ክፍፍል፣ ሙስና እና ብልሹ አሰራር የትግራይን ቀውስ እያባባሰው ነው” - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ በፓርቲያቸው አመራር ላይ የሰላ ትችት የሰነዘሩበት ገለጻ አድርገዋል፤ ለጊዜያዊ አስተዳደሩን ዕቅድ መበላሸት እና ለክልሉ ጸጥታ መደፍረስ የህወሓት አመራር ተጠያቂ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ከድምጽ ወያነ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባካሄዱት የትግርኛ ቃለምልልስ ክልሉ እየተጋፈጠ ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግር አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ክልሉ በቀውስ ውስጥ እየታመሰ ይገኛል ያሉት አቶ ጌታቸው ለዚህም ዋነኛ ምክንያቱ የህወሓት አመራር ከህዝቡ ሰላም እና ደህንነት ይልቅ ለግላዊ ፍላጎቱ ቅድሚያ መስጠቱ ነው ሲሉ ተችተዋል።

በክልሉ እየተባባሰ ላለው የጸጥታ ችግር ዋነኛ ምክንያቶቹ “በተዋረድ ያለው አስተዳደር አለመናበብ፣ በጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ በጸጥታ ሀይሉ እና በፍትህ ተቋማት መካከል አለመናበብ” መሆኑን አመላክተዋል።

“በህወሓት አመራር ላይ እየተስተዋለ ያለው ክፍፍል ሁኔታው እንዲባባስ አድርጓል” ብለዋል።

በወርቅ ዘረፋው ላይ ከሴኔጋል፣ ናይጀሪያ እና ቻይና ዜጎች የተሳተፉበት፣ ወርቁን ለማውጣት መርዛማ ኬሚካልም ጭምር ጥቅም ላይ የዋለበት ነው ሲሉ ገልጸው በክልሉ በስፋት እየተካናወነ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

„የኤርትራ ክስ የኢትዮጵያን አየር መንገድ ስም የማጥፋት ሥራ በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለውም“ - አቶ መስፍን ጣሰው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ ከኤርትራ ሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን የቀረበበትን ክስ “የአየር መንገዱን ስም የማጥፋት ሥራ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም” ሲል ውድቅ አደረገ።የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ፤ የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን በላከው ደብዳቤ ይህንን አጥፍታችኋል የሚል ምንም ዓይነት ማብራሪያ አልነበረውም ብለዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በደቡብ ጎንደር ዞን ታች ጋይንት ወረዳ አርብ ገበያ ከተማ እና በላይ ጋይንት ነፋስ መውጫ ከተማ ከተለያዩ የሰሜን ወሎ፣ ዋግኽምራ በደቡብ ጎንደር ወረዳዎች በመሰባሰብ ትንኮሳ ለማድረግ የሞከረው የጽንፈኛ ኃይሎች ስብስብ በጀግናው የመከላከያ ኃይልና በአካባቢው የፀጥታ መዋቅር ተመቷል፡፡

የሰላምን አማራጭ ወደ ጎን በመተው የንጹሃን ዜጎችን ሰላም ለማወክ፣ ወቅታዊ የልማት ሥራዎችን ለመግታት እና በህይወትና በንብረት ላይ ውድመት ለማስከተል ወደ አርብ ገበያ እና ነፋስ መውጫ ከተማ ሰርጎ ለመግባት ሲንቀሳቀስ የነበረው የፅንፈኛ ኃይሎች ስብስብ አፈ ቀላጤ የሆነው ስመኘው መብራቱ፣ የጉና ቀጠና የፅንፈኛው መሪ ካስየ ሞገስ እና ጀሌዎቻቸው በጀግናው የመከላከያ ኃይላችንና በአካባቢው የፀጥታ ኃይል ተደምስሰዋል፡፡

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የአሁኑ ትውልድ የመትከልም የማጽናትም ኃላፊነትም አለበት፣ ለነገዋ ኢትዮጵያ እንተክላለን የምናልመውን ብልጽግና እውን እናደርጋለን ፦ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል

የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ሠራተኞች ዘንድሮም ለአምስተኛ ጊዜ በእንጦጦ የእጽዋት ማዕከል ሀገር በቀል ችግኞችን ተክለዋል፡፡

ከዚህ በፊት በየዓመቱ የተተከሉት አብዛኞቹ ሀገር በቀል ችግኞች  ተገቢውን  እንክብካቤ በኮርፖሬሽኑ በማግኘታቸው መጽደቃቸውም ታውቋል፡፡

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል ለ አምስተኛ ጊዜ በጉለሌ እጽዋት ማዕከል በመገኘት  አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

የአሁኑ ትውልድ የመትከልም የማጽናትም ኃላፊነትም አለበት፣ ለነገዋ ኢትዮጵያ እንተክላለን የምናልመውን ብልጽግና እውን እናደርጋለን ብለዋል ክቡር ዋና ስራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል፡፡ አለበት፣ ለነገዋ ኢትዮጵያ እንተክላለን የምናልመውን ብልጽግና እውን እናደርጋለን ብለዋል ክቡር ዋና ስራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል፡፡

አገር በትውልድ በቅብብሎሽ ይቀጥላል ፣ ነገን በማሳብ ጎዳናዎቿ  ንጹህና አረንጓዴ ፣  ተራራዎቿ ለምለም የሆነች አገር ለመፍጠር እንደ መንግስት እየተደረገ ያለውን ውጤታማ  ሥራ ኮርፖሬሽኑ የድርሻውን እንደሚወጣ , ክቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ሕንጻዎች በሚገኙባቸው ሀሉ ሀገር በቀል ችግኞች እንዲተከሉ በማድረግና ንዋሪች በግቢያቸው  ዛፎችንና ችግኞችን እንዲከባከቡ የማድረግ  ሥራም እየተሰራ መሆኑን ክቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚው አንስተዋል፡፡

በቀጣይ በኮርፖሬሽኑ የሚሰሩ ሕንጻዎችና መንደሮች አገራዊ የአረንጓዴ ልማት ፖሊሲን ግምት ውስጥ ያስገቡ እንዲሆንም ይደረጋል ነው ያሉት ክቡር አቶ ረሻድ ከማል፡፡ የተተከሉት ሀገር በቀል ችግኞች እንዲጸድቁ አሁንም ኮርፖሬሽኑ አስፈላጊውን በጀት መድቦ እቅክብካቤ እንደሚያደርግም ተገልጿል፡፡

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በአማራ ክልል ጽንፈኛው ላይ የሚወሰደው ኦፕሬሽን ቀጥሏል

በተለያዩ አካባቢወች በቀን 25/11/2016 ሰራዊቱ በወሰደው እርምጃ በርካታ የጸረ ሰላም ሃይሉ አመራሮች መደምሰሳቸው ታወቀ። በጉራንባ ፣ አዲስጌ ፣ ወይና ጣና ፣ አረቢያ እንዲሁም ደብር ዙርያ ቀበሌዎች በተወሰደው ዕርምጃ ደመቀ አለሙ የተባለ ሻለቃ አዛዥ ፣ ሀብቴ አበጀ የተባለ ም/ሻ ፣ እንዳለው ቢያድግልኝ ፣ አወቀ ይልማ ፣ ደጀን ሽበሽ ፣ ሠጠኝ ባየህ ፣ ገብሬ ታረቀኝ ፣ በሪሁን ገብሬ ፣ ጋሻው እምቢያለ ፣ ገብሬ እምቢያለ የተባሉ አመራሮች ሲገደሉ ፣ ቆስለው ለማምለጥ ሙከራ ያደረጉ 5 አባላት በመገጭ ወንዝ መወሰዳቸውም ታውቋል::

በተጨማሪም በስም ያልተለዩ 7 የሠለሞን አጠናና የባሻ ስጦታው ቡድን እንዲሁም 8 በስም ያልተለዩ ዳብሎ ማርያም ህዝብ ያስቀበራቸው አባላት መሞታቸው ተረጋግጧል ፤ በአጠቃላይ ከ ቀን 24- 25/11/2016 ዓ.ም በሁለት ቀናት ብቻ የወገን ሃይል በጸረ ሰላም ቡድኑ ላይ በወሰደው ኦፕሬሽን 65 አባላትን ሲገል ፣ 51 አቁስሎ 41 መማረኩን ለማወቅ ችለናል ።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

"ስማችን እውነት ነው,ስራችንም የእውነት ነው"

❇️ከዚህ በፊት የተመረጡ ቦታዎች ላይ ጥንቅቅ አድርገን እንዳስረከብናቸው አሁንም እጅግ ውብ ለኑሮ መቹ በከተማችን የተመረጡ ቦታዎች

❇️በሳርቤት እና በ ቦሌ ቅድመ ክፋያ 770 ( ሰባትመቶ ሰባ ) ሽህ ጀምሮ በመሸጥ እንገኛለን

✅ 65.7 , 86 , 90 ካሬ ባለ 1 መኝታ
✅ 98 , 100 , 114 ካሬ ባለ 2 መኝታ
✅ 140 , 152 , 212 ካሬ ባለ 3 መኝታ

❇️የቤት ባለቤት ከመሆን ባለፈ፣በመሀል አዲስ አበባ የምንገነባቸው ቅነጡ ቤቶቻችን ኢንቨስተር ያደርጉታል !
✅ምስክሮቻችን ከዚህ በፊት ሰርተን ያስርከብናቸው ደንበኞቻችን::

❇️ወለል ውፍረት 25ሲ.ሜ ኮንክሪት አስላብ።
✅ከወለል ወለል እርዝማኔ 3.2 ሜትር
❇️የውጭ በሮቻችን 100ኪሎ የሚመዝኑ፣ከኮንክሪት እና ከብርት የሚስሩ፣ድመፁ የማያስተላልፍ ፣6 የተለያዩ ቦታዎች የሚቆልፍ።


✅Reality real estate✅
🚧 3B+G+17 አፓርታማ
🚘 sufficient parking space
🏋️gymnasium and spa
👉🏻17 th floor club house
👉🏻under ground water and backup generator

💰 10% ቅድመ ክፍያ

What makes Reality real estate different
- Affordable price
- Easy payment schedule
- Prime Location
- Reputed company
- Early Delivery
የድርጅቱ የሽያጭ አማካሪ
☎️0976 20 68 68
0951 69 14 66

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በአዲስ አበባ ከተማ 18 ኮሌጆች ታገዱ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ባደረገው ድንገተኛ ኢንስፔክሽን 44 ኮሌጆች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡

በትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬክቶሬት በ2016 ዓ.ም ለ59 ኮሌጆች በተከናወነ ድንገተኛ ኢንስፔክሽን የተገኙ ግኝቶችን መሰረት በማድረግ ርምጃ መውሰዱን አስታውቃል።

የከፍተኛ የስርዓተ ስልጠና ፖሊሲ ጥሰት እና የስትራቴጂ ጥሰት የታየባቸው 18 ኮሌጆች መታገዳቸውን ያስታወቀው ባለስልጣኑ ኮሌጆቹንም ይፍ አድርጋል።

1. ብራይት ኮሌጅ ልደታ ካምፓስ
2. ብራይት ኮሌጅ ጀሞ ካምፓስ
3. ሸገር ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ
4. ልቀት ኮሌጅ አራት ኪሎ ካምፓስ
5. ልቀት ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ
6. ላየን ኮሌጅ መገናኛ ካምፓስ
7. ሀርመኒ ኮሌጅ ቂሊንጦ ካምፓስ
8. አልፋ ኮሌጅ ላንቻ ካምፓስ
9. አፍሪካ ቤዛ ኮሌጅ
10. አረና መልቲ ሚዲያ ኮሌጅ
11. ጌጅ ኮሌጅ ሾላ ካምፓስ
12. ሳትኮም ኮሌጅ
13. ኩዊንስ ኮሌጅ አምስት ኪሎ ካምፓስ
14. ሀርመኒ ኮሌጅ ሀና ማርያም ካምፓስ
15. ኩዊንስ ኮሌጅ መድሀኒዓለም ካምፓስ
16. ሀጌ ኮሌጅ
17. ኪያሜድ ኮሌጅ እንቁላል ፋብሪካ ካምፓስ
18. ኩዊንስ ኮሌጅ ዩሀንስ ካምፓስ

በሌላ በኩልም የስርዓተ ስልጠና ፖሊሲ ጥሰት የታየባቸው 18 ኮሌጆች የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሲሆን ኮሌጆቹም ከታች ተዘርዝረዋል።

1. ግሬት ቡልቡላ ኮሌጅ
2. ቢኤስቲ ኮሌጅ
3. ክቡር ኮሌጅ
4. ፋርማ ኮሌጅ
5. ቅድስት ልደታ ኮሌጅ
6. ኤግል ኮሌጅ
7. አፍሪካ ጤና ኮሌጅ
8. ናሽናል ኮሌጅ
9. ሀርቫርድ ኮሌጅ
10. ሰቨን ስታር ኮሌጅ
11. ራዳ ኮሌጅ
12. ሬፍትቫሊይ ኮሌጅ ካራሎ ካምፓስ
13. ኬቢ ኮሌጅ
14. ያጨ ኮሌጅ
15. ኪያሜድ ኮሌጅ 22 ካምፓስ
16. ናይል ሳይድ ኮሌጅ
17. ኪያሜድ ኮሌጅ አየርጤና ካምፓስ
18. ዊልነስ ኮሌጅ

መለስተኛ የስርዓተ ስልጠና ፖሊሲ ጥሰት የታየባቸው 8 ኮሌጆች የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ኮሌጆች
1. ያኔት ኮሌጅ 6 ኪሎ ካምፓስ
2. ዳማት ኮሌጅ ጊወርጊስ ካምፓስ
3. ያኔት ኮሌጅ ሰፈረ ሰላም ካምፓስ
4. ኤክስፕረስ ኮሌጅ
5. ቅድስት ሃና ኮሌጅ
6. ግራንድ ማርክ ኮሌጅ
7. ኩዊንስ ኮሌጅ ሃና ማሪያም ካምፓስ
8. ሀራምቤ ኮሌጅ ሜክሲኮ ካምፓስ

በዚህም አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን ባለስልጣኑ ያሳወቀ ሲሆን ፤ ተቋማቱ እንደደረሳቸው አስተዳደራዊ እርምጃ መሰረት በአስር ቀናት ውስጥ እርምትና ማስተካከያ በማድረግ በጽሁፍና በአካል ሪፖርት በማድረግ ለባለስልጣኑ የማያሳውቁ ከሆነ እንደየደረጃው ቀጣይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ አሳውቋል፡፡

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

“ እኔ ሳላውቀው ያለፈው ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ/ም ጉባኤ ለማካሄድ በድብቅ ሲሰራ ነበር። ይህ እንዲሆን ለምን አስፈለገ ?  “  - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ ጉዳዮች አስመልክተው ለድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ቃለመጠይቅ ሰጥተው ነበር።

አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?

- የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት የትግራይ ህዝብ እና ህልውና ያዳነና ያስቀጠለ ነው።

- ሁሉም የትግራይ ችግሮች ከውጭ ተፅእኖ ነፃ ናቸው ባይባልም በአመዛኝ ውስጣዊ ፓለቲካዊ ችግሮች ናቸው ያሉት። ውስጣዊ ችግሮቻችን ባይጠልፉን የፕሪቶሪያው ስምምነት በፈጠረው እድል በርካታ ለውጦች ይታዩ ነበር።

- ውስጣዊ ፓለቲካዊ ድክመታችን ሰከን ብለን መመርመር አለብን፤ ከጥፋት ለጥቂት ያመለጠ ህዝብ መልሰን ወደ ጦርነት እንዳናስገባው በሃላፊነት መንፈስ መንቀሳቀስ አለብን።

- ጉባኤ መካሄድ የለበትም ያለ የለም ፤ አሁን ያለው ሩጫ ግን ስልጣን ለመቆጣጠርና ከተጠያቂነት ለማምለጥ ያለመ ነው።

- ህወሓት መዳን የሚችለው በጭቅጭቅ ሳይሆን በሳልና ተራማጅ ሃሳብ በማመንጨት ነው።

- እኔ ሳላውቀው ያለፈው ሰኔ 30/2016 ዓ/ም ጉባኤ ለማካሄድ በድብቅ ሲሰራ ነበር ቢሆንም ፍትህ ሚንስቴር በደብዳቤ አስቀርቶታል። ይህ እንዲሆን ለምን አስፈለገ ?

- “ ከፌደራል መንግስት ጥሩ መግባባት ደርሰናል ተስማምተናል “ ይባላል እንጂ መሬት ላይ ጠብ የሚል ነገር የለም። አዲስ አበባ በመሄድ የሚስማሙትና እዚህ የሚነገረን የተለያየ ነው፤ ይህ ካድሬው ሊያውቀው ይገባል።

- የተጀመረው ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው የመመለስ ተግባር ከተጨማሪ ግጭት ቂምና ቁርሾ በፀዳ መልኩ እንዲፈፀም እየሰራን ነው።

- በእርስ በርስ ሽኩቻ ባሳለፍናቸው ጊዚያቶች ፀፀት ተስምቶን ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ለመመለስና የፕሪቶሪያው ስምምነት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈፀም በተቀናጀ የአመራር ጥበብ መስራት ይጠበቅብናል።

ሙሉውን ኢንተርቪው ለመስማት 👉 https://youtu.be/i3xGXImiSyE

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች

ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተ‍እ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበ‍ኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።

ሚለየን ምንድነው?

የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ

🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።

🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።

🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።

🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።

🪄We Care

አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ

📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69

www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

"ተአምረ ማርያም " በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ተተረጎመ

በብፁዕ አቡነ ናትናኤል በአሜሪካ የሚኒሶታና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና በዲ/ን እንዳለው መሰለ ተርጓሚነት የተዘጋጀው RAAJII MAARIYAAM / ተአምረ ማርያም / መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ተተርጉሞ ለንባብ ቀረበ።

በአፋን ኦሮሞ ፣ በግእዝና በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀው ተዓምረ ማርያም መጽሐፍ ተዘጋጅቶ ለማጠናቀቅ ሁለት አመት የፈጀ እንደሆነ የመጽሐፍ ምርቃት አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በአሜሪካ የሚኒሶታና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በዛሬው እለት በማኀበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።

ብፁዕነታቸው ስለመጽሐፉ ቤተክርስቲያኗ በተደጋጋሚ የሚነሳውን የቋንቋ አገልግሎትን አስመልዕክቶ ዜጎች በቋንቋቸው ወንጌልን ለምዕመናቱ እንዲያዳርሱ ለማገዝ እንደሚረዳ ገልጸው በቀጣይም ሌሎች መፅሐፎችን በጋራ ለማዘጋጀትም በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ጨምረው ገልጸዋል።

የመጽሐፍ መርሐ ግብር ያዘጋጀው ሎዛ የኦርቶዶክስ ኢቨንት ኦርጋናይዘር ነው።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች

ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተ‍እ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበ‍ኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።

ሚለየን ምንድነው?

የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ

🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።

🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።

🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።

🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።

🪄We Care

አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ

📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69

www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

"ስማችን እውነት ነው,ስራችንም የእውነት ነው"

❇️ከዚህ በፊት የተመረጡ ቦታዎች ላይ ጥንቅቅ አድርገን እንዳስረከብናቸው አሁንም እጅግ ውብ ለኑሮ መቹ በከተማችን የተመረጡ ቦታዎች

❇️በሳርቤት እና በ ቦሌ ቅድመ ክፋያ 770 ( ሰባትመቶ ሰባ ) ሽህ ጀምሮ በመሸጥ እንገኛለን

✅ 65.7 , 86 , 90 ካሬ ባለ 1 መኝታ
✅ 98 , 100 , 114 ካሬ ባለ 2 መኝታ
✅ 140 , 152 , 212 ካሬ ባለ 3 መኝታ

❇️የቤት ባለቤት ከመሆን ባለፈ፣በመሀል አዲስ አበባ የምንገነባቸው ቅነጡ ቤቶቻችን ኢንቨስተር ያደርጉታል !
✅ምስክሮቻችን ከዚህ በፊት ሰርተን ያስርከብናቸው ደንበኞቻችን::

❇️ወለል ውፍረት 25ሲ.ሜ ኮንክሪት አስላብ።
✅ከወለል ወለል እርዝማኔ 3.2 ሜትር
❇️የውጭ በሮቻችን 100ኪሎ የሚመዝኑ፣ከኮንክሪት እና ከብርት የሚስሩ፣ድመፁ የማያስተላልፍ ፣6 የተለያዩ ቦታዎች የሚቆልፍ።


✅Reality real estate✅
🚧 3B+G+17 አፓርታማ
🚘 sufficient parking space
🏋️gymnasium and spa
👉🏻17 th floor club house
👉🏻under ground water and backup generator

💰 10% ቅድመ ክፍያ

What makes Reality real estate different
- Affordable price
- Easy payment schedule
- Prime Location
- Reputed company
- Early Delivery
የድርጅቱ የሽያጭ አማካሪ
☎️0976 20 68 68
0951 69 14 66

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ሰበር ዜና ‼️

የተደረገው ድርድር ያስገኘው ውጤት ይፋ ሆኗል።
የዓለም ባንክ በዛሬው እለት the Ethiopia First Sustainable and Inclusive Growth Development Policy Operation በሚል ባወጣው መግላጫ ኢትዮጵያ እያከናወነች ላለችው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ለመደገፍ በርካታ የድጋፍ ማዕቀፎችን ይፋ አድርጓል። በዚህ መሰረት ዓለም ባንክ አሁን በቀጥታ ከሚሰጠው 7 ቢሊዮን ዶላር በተጨማሪ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት 8.5 ቢሊዮን ዶላር በመጨመር ኢትዮጵያ በጠቅላላው 15.5 ቢሊዮን ዶላር ከዓለም ባንክ ብቻ ታገኛለች። ከዚህ በተጨማሪ
• 1 ቢሊዮን ዶላር ቀጥተኛ ስጦታ (grant)
• 500 ሚሊዮን ዶላር የእዳ ክፍያ እንዲራዘም፤
• 320 ሚሊዮን ዶላር ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ትብብር (IFC)
• 1.15 ቢሊዮን ዶላር የባለብዙ ወገን ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ
• 6 ቢሊዮን ዶላር በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ለበጀት ድጎማ
• 2.1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ትብብር ለኢንቨስትመንት የምታገኘውን ሲጨምር ኢትዮጵያ አሁን ከምታገኘው 7 ቢሊዮን ዶላር በተጨማሪ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት በጠቅላላው 16̂.6 ቢሊዮን ዶላር ታገኛለች

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ስንቅ ሬስቶራንት በዱባይ https://vm.tiktok.com/ZGe71ay4C/

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኮኖሚው ማሻሻያ ተግባራዊ ከመደረጉ ጋር በተያያዘ ችግር ለመፍጠር የሞሞክሩትን የማረም ሥራ እየተሠራ ነው፡፡


በከተማ ደረጃ ፋይናንስ ቢሮ፣ ንግድ ቢሮ እና ገቢዎች ቢሮን ያካተተ አደረጃጀት እንዲዋቀር ተደርጎ ቁጥጥርና ክትትል እያደረገ የሚገኝ ሲሆን አደረጃጀቱ ከተማና በክፍለ ከተማ ደረጃ እንዲዋቀር ተደርጓል፡፡ በተደረገው ክትትልም በአትክልት እና ፍራፍሬ እንዲሁም በሰብል ምርቶች ላይ ከባለፉት ቀናት አንጻር የጎላ የዋጋ ልዩነት በዛሬው ዕለት በተሰበሰበ የገበያ መረጃ ላይ ያልታየና የተረጋጋ መሆኑ ታውቋል፡፡ የሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ የሚገባው የሩዝ ምርት ገባያው ላይ በሚፈለገው አግባብ እየቀረበ አለመሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይሄንንም ለማስተካከል በቀጣይ ቀናት አስፈላጊው ሁሉ ይከናወናል፡፡

የጅምላ እህል አቅራቢዎች በተለይም በመሳለሚያ ገበያ አካባቢ ምርት የመያዝ አዝማማያ የነበረ ቢሆንም በተወሰደው አስተዳደራዊ ርምጃ ወደ መደበኛ ግብይት እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ ከውጭ የሚገባው ዘይት ትናንት በነበረው ገበያ በሚፈለገው መልኩ በመርካቶ ገበያ ላይ አልቀረበም፡፡ በዚህ ላይ ክትትል እንዲደረግ ተወስኗል፡፡ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃ ሻጮች በተለይም ከሊፋ ህንጻ አካባቢ የዋጋ ጭማሪ እየተስተዋለ መሆኑ የታየ ሲሆን ወደ ትክክለኛ መሥመር እንዲገቡ እርማት እተሰጠ ነው፡፡

በቀጣይም አጋጣሚውን በመጠቀም ሕገ ወጥ ተግባር በሚያከናውኑት ላይ አስፈላጊ ክትትልና ቁጥጥር እንዲደረግ አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሠራ ነው፡፡

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ሰሞኑ በዶክተር ደብረፅዮን እና በጌታቸው መካከል የነበረው የሚድያ ጦርነት አንኳር አንኳር ነጥቦች
ዶክተር ደብፅዮን፡-
* አሁን ጉባኤ ማካሄድ የማይፈልግ፣ ከተጠያቂነት ለማምለጥ እና የፓርቲው ችግሮች እንዲፈቱም የማይፈልግም ነው።

ጌታቸው፡-
* ጉባኤ አታካሂዱ የሚል ማንም የለም፡ አሁን ያለው ጥድፊያ ግን ስልጣንን ለመቆጣጠር እና ከስልጣን ከለቀቁ ከተጠያቂነት ለማምለጥ ነው።
###

ዶ/ር ደብረጽዮን:
* የባለፈው መድረክ ግልፅ፣ አሳታፊ እና ዲሞክራሲያዊ ነበር። ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተገኝተዋል። ለመገምገምም ጊዜ ወስደናል።

ጌታቸው፡-
እስካሁን ድረስ እኛ የሚድን ምንም ስራ አልተሰራም. በእኔ እምነት፡- የድብብቆሽ ሃሳብ የሌለበት ጉባኤ፡ እና ብዙ ክፍተት ያሉት ሂደት ነበር።
###

ዶ/ር ደብረጽዮን:
በውጭ መግለጫ እየሰጡ ያሉት፡ ዴሞክራሲያዊ አደረጃጀት ስተዋል፡ በተቃውሞ ወጥተው በድምፅ ተሸንፈዋል፡ የሚናገሩት መግለጫና ስም ማጥፋት ነው።

ጌታቸው፡-
በባለፈው የከፍተኛ ካድሬዎች መድረክ ላይን በፓርቲው ሊቀ መንበር ሲጠቃለል “ህዝብ የመረጠውን መንግስት የመበተን ስልጣን አልነበራችሁም” ሲሉ ተደምጠዋል።በዚህ ላይ የሃሳብ ልዩነት እንዳለኝ ስናገር ልስተናግድ አልቻልኩም።ስለዚህ ሃሳቤ ወደ ሚዲያ መውጣት ነበረበት።

ዶ/ር ደብረጽዮን:
የፕሪቶሪያ ስምምነት ጦርነቱን አቁሞ አንፃራዊ ሰላም አምጥቶልናል።

ጌታቸው፡-
በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የተፈጠረው እድል ባክኗል; ተአምር የሰራ የትግራይ ህዝብ እና ጀግናው ሰራዊት ድሉን ተበልቷል።ይህ የህወሓት የፖለቲካ ድክመት ውጤት ነው።

ዶ/ር ደብረጽዮን:
ችግሮቹን ለመፍታት ከፌዴራል መንግስት ጋር እየተነጋገርን ነው።

ጌታቸው፡-
አዲስ አበባ ላይ የተስማሙት እና እዚህ የምንነገረው እውነት የተለያየ ነው።
ዶ/ር ደብረጽዮን:
በአዲሱ አዋጅ አንመዘገብም; አይመለከተንም ጥያቄያችንን ለምርጫ ቦርድ አቅርበናል።

ጌታቸው፡-
ህወሓት ያስገባው ደብዳቤ በአዲሱ አዋጅ ላይ የተመሰረተ ነው። ይህንን ካድሬው ማወቅ አለበት።

Читать полностью…
Подписаться на канал