natnaelmekonnen21 | Неотсортированное

Telegram-канал natnaelmekonnen21 - Natnael Mekonnen

181663

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7 Facebook.com/natnaelmekonnen.et Instagram.com/natnaelmekonnen21

Подписаться на канал

Natnael Mekonnen

አንድ ወስላታ በሚዲያ ቀርቦ እኔን “የቀድሞው ፕሬዚዳንት” እያለ ሲጠራኝ ነበር አሉ።እሱ ችግር የለውም።ፖሊስ ጋ ቀርቦ መልስ ይሰጥበታል።የእነዚህ ሰዎች ችግር ስራ አለመስራታቸው ብቻ አይደለም።ከበፊት ጀምሮ የወንጀልና የሌብነት ኔትወርካቸው እንደሚጋለጥና እንደሚጠይቁ ስለሚያውቁ የትግራይ ፖለቲካ እንዲስተካከል አለመፈለጋቸው ነው።በዘረፋ የተሰማሩባቸው የወርቅና የመዳብ ማዕድናቱ ከእጃቸው እንዲወጣ አይፈልጉም።የትግራይ ፖለቲካ ተበላሽቶ የቀረው በነዚህ ሰዎች ምክንያት ነው

ጌታቸው ረዳ

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በቡሄ ግዜ የደነቆረው ስታሊን

ስታሊን ገብረስላሴ "ጃል ሰኚ የወቦን ትግል ከዳ" ብሎ በሀዘን ስሜት የፃፈውን አየሁትና አሳቀኝ። የኦሮሞ ልጆች "መገዳደል ይብቃ" ብለው እርቀሰላም ስለፈፀሙ የአንደኛው የህውሀት ክንፍ ደጋፊዎች ድንኳን ጥለው ለቅሶ ሲቀመጡ እንደማየት የሚገርም ነገር ነው 😁

የነ ስታሊን ካምፕ ህውሀት ፕሪቶሪያ ላይ እርቅ ስትፈራረም አጨብጭበው ሰላም ከሰፈነ በኋላ፥ አማራና ኦሮሚያ ክልል ግን በጦርነት ውስጥ እንዲከርሙ ሲቀሰቅሱ ይውላሉ። ምክኒያቱም ለትግራይ ማህበራዊ እረፍት የሰጠ የሰላም አየር በኦሮሚያና በአማራ ክልል ውስጥ እንዲነፍስ አይፈልጉም። በዚህ ሰአት እንደዚህ አይነት ተራ ብልጣብልጥነት የማይገባው ኢትዮጵያዊ አለመኖሩን የተረዱት አይመስሉም።

"በቡሄ ግዜ የደነቆረ ሁልጊዜ ሆሆሆ ይላል" አሉ። ወንድሜ በድሮ በሬ ያረሰ የለም። እራስህ በጀመርከው ቁማር ጆከር ተጥሎብህ ከተሸነፍክ በኋላ "እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል" እንዳለችው አህያ በሰገሌ ግዜ የቀረ ተንኮል አራምዳለሁ ካልክ የአዲሱ ትውልድ መሳለቂያ ትሆናለህ እንጂ የምታገኘው አንዳች የፖለቲካ ትርፍ የለም።

ቢያንስ ግዜውም ትውልዱም መለወጡትን አይተህ እውቀትህን ባታሳድግና ከትናንት ስህተትህ መማር ባትችል እንኳን የተሻለ ተንኮል ይዘህ ገበያ እንዳጣ ግሮሰሪ የቀዘቀዘ ዩቲዩብህን ብትሸቅል የሚል ወንድማዊ ምክር አለኝ። move on my brother.

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ወታደራዊ የቴክኖሎጅ አቅም ማሳደግ በሚያስችል የምርምር ስራ ላይ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የሠራዊታችንን ወታደራዊ የቴክኖሎጅ አቅም ማሳደግ በሚያስችል ጠንካራ የምርምር ስራ ላይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር ዐቢይ አህመድ አረጋግጠዋል።

ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሠ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ እየሰራቸው የሚገኙ የትምህርትና የምርምር ውጤቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል ።

ዩኒቨርሲቲው የሠራዊታችንን ወታደራዊ የቴክኖሎጅ አጠቃቀም ሳይንሳዊ በሚያደርግ አግባብ እየሰራቸው የሚገኙ ተሰፋ ሰጪ የምርምር ስራዎች ወደፊት የመከላከያን ወታደራዊ አቅም የበለጠ ማሳደግ የሚችል እንደሆነ የሃገሪቱ ከፍተኛ አመራሮች በምልከታቸው አረጋግጠዋል ።

በኢንጅነሪግ ፣ በጤና እና በሪሶርስ ማኔጅመንት ዘርፈ ብዙ የትምህርት ፕሮግራሞችን አጣምሮ እየሰጠ የሚገኘው የሃገሪቱ ብቸኛው ወታደራዊ ዩኒቨርሲቲ የሠራዊታችንን ክፍተቶች መሙላት የሚችል በርካታ የሰው ሃይል በእውቀትና በክህሎት ብቁ አድርጎ ከማፍራት ባሻገር እየሰራቸው የሚገኙ የተለያዩ ችግር ፈቺ ወታደራዊ የምርምር ስራዎች የሠራዊታችንን ተጠቃሚነት በብዙ ዘርፍ ማረጋገጥ የሚችሉ እንደሆነም አመራሮቹ ተገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የተሰጠውን የመማር ማስተማር ተልዕኮ መሠረት አድርጎ በመስራት በትምህርት ጥራት ፣በጥናት ተመራጭነት እና በምርምር ውጤታማነት የላቀ ሆኖ የሃገሪቱን ዘመኑን የዋጀ ወታደራዊ የቴክኖሎጅ ተጠቃሚነት በብዙ ዘርፍ በማረጋገጥ ተደራሽ ማድረግ እንዲችልም በአመራሮች ምልከታ ላይ ተጠቁሟል ።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ለአንድ ከተማ ሁለት ከንቲባ ተሾመ

ትግራይ ክልል ዓዲግራት ከተማ ሁለት ከንቲባዎች ተሾሙባት

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከትላንት በስቲያ አቶ ዓለም አረጋዊ ለዓዲግራት ከተማ “ከንቲባ” አድርጎ የሾመ ሲሆን፣

በዶ.ር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ደግሞ ዛሬ ባካሄደው የምክር ቤት ጉባኤ አቶ ረዳኢ ገብረእግዚኣብሄር ለዓዲግራት ከተማ “ከንቲባ” አድርጎ መሾሙን የአሜሪካ ድምፅ ዘግቧል:: ሁለቱንም ተሿሚዎች VOA አነጋግሯል።

በጊዜያዊ አስተዳደሩ የተሾሙት አቶ ዓለም <<ጊዜያዊ አስታዳደሩ በተቋቋመበት ህግ እና አሰራር መሰረት ወደ ስራ ገብቻለሁ አሁን ላይ በፅ/ቤት ስራ ርክክብ እያደረኩ ነው>> ብለዋል።

የእነ ዶ/ር ደብረፂዮን ተሿሚ አቶ ረዳኢ ሹመቱን አረጋግጠው <<TPLF ተወዳድሮ በተመረጠበት ትግራይ እስካሁን ያለው የTPLF ም/ቤት አባላት ናቸው ፤ እኔም እንደ TPLF አንድ አካል ተወካይ ሆኜ ነው የቀረብኩት>> ሲሉ ሹመቱ በም/ቤት እንደፀደቀላቸው ለጣቢያው ተናግረዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

THE SKY IS OURS : በኢትዮጵያ አየር ኃይል ተሰርታ ለበረራ ብቁ የሆነችው ‘’ጸሐይ 2’’ አውሮፕላን በጠሚ ዶር አቢይ አንደበት ስትገለፅ::

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ታፍራና ተከብራ ትኖራለች ያኔ ትልቅ ነበርን አሁን ደግሞ ይበልጥ ትልቅ እንሆናለን።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ‘’ጸሐይ 2’’ የተሰኘች አውሮፕላን ሰራ

የኢትዮጵያ አየር ኃይል 89ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ባለበት በዚህ ወቅት ‘’ጸሐይ 2’’ የተሰኘችና በአየር ኃይሉ የተሰራች አውሮፕላን ለበረራ ብቁ ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ በጸጥታና ደህንነት ተቋማት ያከናወነው የሪፎርም ስራ ኢትዮጵያን የሚመጥንና ዘመን ተሻጋሪ ተቋማትን ለመገንባት ጠንካራ መሰረት የጣለ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ደግሞ በዚህ ረገድ ተጠቃሽ መሆኑን ጠቅሰዋል።

አየር ኃይሉ 89ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ባለበት በዚህ ወቅት ‘’ጸሐይ 2’’ የተሰኘችና በአየር ኃይሉ የተሰራች አውሮፕላን ለበረራ ብቁ ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡

አውሮፕላኗ ግዳጅን በብቃት መፈጸም የሚያስችል ቴክኖሎጂ የታጠቀች መሆኗንም አክለዋል።

ይህም አየር ኃይሉ በ2030 በአፍሪካ ስመጥር አየር ኃይል ለመሆን የያዘውን ራዕይ እውን ለማድረግ በትክክለኛ ጎዳና ላይ መሆኑን የሚያመላክት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

“ በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ቡድን ህወሓትን በአመፅ ለመበተን ወጣቶችን እያሰለጠነ ነው” አማኑኤል አሰፋ

በደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ባካሄደው ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አቶ አማኑኤል አሰፋ  መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህ መግለጫቸው ላይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በባለፈው ጉባኤ ከሥልጣን የተነሱ በመሆናቸው “ፕሬዝደንትነታቸውን አንቀበልም” ብለዋል።

አቶ አማኑኤል “የጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮች ህወሓትን በአመፅ ለመበተን ወጣቶች እያሰለጠኑ ናቸው” ሲሉ ወንጅለዋል።

“ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ለሁለት ዓመት ያለ እቅድ እየተመራ ይገኛል “  በማለትም ገልፀዋል ።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

#USA

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጾታቸውን የቀየሩ የሀገሪቱ ጦር አባላት ወታደሮችን እንደሚያግዱ ተነገረ።

ትራምፕ ሰዎች ተፈጥሯዊ ጾታዎችን መቀየር የለባቸውም ብለው ያምናሉ።

ይህን ተከትሎም ጾታቸውን የቀየሩ እና የሀገሪቱ ጦር አባላት የሆኑ ወታደሮችን ከስራ እንደሚያግዱ ዘ ታየምስ ዘግቧል።

እንደዘገባው ከሆነ 15 ሺህ ጾታቸውን የቀየሩ ወታደሮችን የማባረር እቅድ አላቸው።

ከዚህ በተጨማሪም ተፈጥሯዊ ጾታቸውን የቀየሩ አሜሪካዊያን የሀገሪቱን ጦር መቀላቀል እንዳይችሉ እገዳ እንደሚጥሉም ተገልጿል።

ዶኔልድ ትራምፕ በከ2016-2020 ድረስ በስልጣን ላይ በነበሩባቸው ዓመታት ውስጥ ተፈጥሯዊ ጾታቸውን የቀየሩ ዜጎች የአሜሪካ ጦርን እንዳይቀላቀሉ እገዳ ጥለው የነበረ ቢሆንም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ይህንን እገዳ አንስተውታል።

ይህን መረጃ ዘ ታይምስን ዋቢ በማድረግ ያጋራው አል አይን ኒውስ ነው።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

#ትግራይ

“ ‘ ተቀምተናል ‘ የሚሉትን ስልጣን ለማስመለስ ስም ከማጥፋት ባለፈ እስከ ፕሬዜዳንት መቀየር ያለመ አደገኛ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው “  - ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ 

ዛሬ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ የፀጥታ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት አቶ ጌታቸው ፥ “ የህዝብ ጥቅም ማእከል አድርጎ በሚንቀሳቀስ የፓለቲካ ፓርቲ ውስጥ ለግሉ ጥቅም ብቻ የሚያስብ አመራር ከተፈጠረ ረጅም ጊዜ ሆኗል “ ብለዋል።

“ ‘ ስልጣን ለኛ ነው የሚገባው ‘ የሚሉ የህዝብ አጀንዳ በማፈን ፍላጎታቸው ለማሳካት የግጭትና የግርግር መልእክቶች በማስተላለፍ ላይ ይገኛሉ “ ሲሉም ገልጸዋል።

እነዚህን አካላት በስም አልጠቀሷቸውም።

ፕሬዜዳንቱ በስም ያልገለፁዋቸው አካላት “ ተቀምተናል “ የሚሉት ስልጣን ለማስመለስ ስም ከማጥፋት ባለፈ እስከ ፕሬዜዳንት መቀየር ያለመ አደገኛ እንቅስቃሴ እያካሄዱ እንደሆነ አመላክተዋል። 

“ ትኩረታችን የትግራይ ህዝብ መሆን ይገባ ነበር “ ያሉት ፕሬዜዳንቱ “ ለወንበር ሲባል የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራዎች የማደናቅፍ ስራዎች ተባብሰው ቀጥለዋል “ ሲሉ ገልፀዋል። 

“ ‘ ሰራዊት ከኛ ጎን ነው ‘ በማለት የግለሰቦችን ስልጣን ለማርካት ታስቦ የፀጥታ ሃይል ለመከፋፈል አልሞ እየተሰራ ነው “ ሲሉም አክለዋል። 

አቶ ጌታቸው ፥ “ በትግራይ ሁሉንም ነገር በብቸኝነት ተቆጣጥሮ የቆየ ሃይል አሁንም የፀጥታ ሃይል ፤ ሚድያ ተቆጣጥሮ በለመደው መንገድ በመሄድ የግል ጥቅሙን ለማረጋገጥ ጠላት ከሚለው እየተደራደረ ይገኛል “ ብለዋብ።

“ ጠላት “ ያሉትን ሃይል በስም አልገለፁም። 

የም/ ቤት አባላት በማንሳት የአስተዳዳሪዎች ስልጣን እንዲለወጥ መስራት መፈንቅለ መንግስት ነው ያሉት አቶ ጌታቸው “ መንግስትን ለማፍረስ የሚደረጉ መድረኮች በመንግስት በጀት ነው የሚካሄዱት “ ሲሉ ተግባሩን ኮንነዋል።

“ ‘ የፀጥታ ሃይል ከኛ ነው ‘ የሚለው አነጋገር የፀጥታ ሃይሉን በመጠቀም ‘ ከስልጣን እናስወግዳችኋለን ‘ የሚል መልእክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ የሚሰራ ነው “ ሲሉም ተናግረዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ሩሲያ ወደ ዩክሬን የተኮሰችው “ኦሬሽኒክ” የተሰኘው ሚሳኤል በርካታ የአውሮፓ ሀገራትን በ20 ደቂቃ ውስጥ መምታት የሚችል ነው ተባለ

በሰዓት ከ12 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ይጓዛል የተባለው ይህ አዲስ ሚሳኤል ለመምታት አስቸጋሪ እንደሆነም ተገልጿል ሩሲያ ወደ ዩክሬን የተኮሰችው “ኦሬሽኒክ” የተሰኘው ሚሳኤል በርካታ የአውሮፓ ሀገራትን በ20 ደቂቃ ውስጥ መምታት የሚችል ነው ተባለ፡፡

አሜሪካ እና ሌሎች የኔቶ አባል ሀገራት ለዩክሬን የረጅም ርቀት የጦር መሳሪያዎችን መስጠታቸውን ተከትሎ ኪቭ ሞስኮን ከሰሞኑ አጥቅታለች፡፡ ይህን ተከትሎ ሩሲያ “ኦሬሽኒክ” በተሰኘ አዲስ አህጉር አቋራጭ ሚሳኤል ዩክሬንን መታለች፡፡

እንደ ሩሲያ መከላከያ መግለጫ ከሆነ ወደ ዩክሬን የተተኮሰው “ኦሬሽኒክ” ሚሳኤል በዲንፒሮ የሚገኘውን የሚሳኤል ማምረቻ እና የጦር መሳሪያ መጋዝንን አጥቅቷል፡፡ የአሜሪካ ጦር በዚህ ሚሳኤል ዙሪያ እንደገለጸው ሚሳኤሉ አዲስ እና አህጉር አቋራጭ፣ የኑክሌር አረር መሸከም የሚችል ነው ብሏል፡፡

ሩሲያ ሚሳኤሉን የተኮሰችው ለሙከራ ጭምር እንደሆነ ያሳወቀው የአሜሪካ ጦር ሚሳኤሉ በቀጣይ የመሻሻል አቅም እንዳለው እና ሞስኮ ይህንን ሚሳኤል በብዛት ሊኖራት እንደሚችልም ገልጿል ሩሲያ ወደ ዩክሬን አህጉር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳኤል መተኮሷ ተነገረ የብሪታንያ ጦር በበኩሉ የሩሲያ አዲሱ ሚሳኤል አውሮፓን ኢላማ ለማድረግ ተብሎ የተሰራ እንደሆነ ገልጿል፡፡

ከደቡባዊ ሩሲያ ወደ ዩክሬን የተተኮሰው ይህ ሚሳኤል ብሪታንያ ለመድረስ 19 ደቂቃ፣ ጀርመን ለመድረስ 14 እንዲሁም ፖላንድ ለመድረስ ስምንት ደቂቃዎች በቂ መሆናቸውን አርቲ ዘግቧል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በ40 ደቂቃዎች ውስጥ በአሜሪካ ያሉ ኢላማዎችን መምታት እንደሚችልም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

Good Morning #Ethiopiaዬ : ያራዳ ልጅ አንድ ሰው አእምሮውን ሳተ ለማለት “ጨለለ” ይላል። ራሳቸውን ገግመው ጋዜጠኛ ያደረጉት ወዳጆቻችን አንድ በአንድ እየጨለሉ ነው። ፋሲል የኔአለምም A group of idiots የተባለውን ግሩፕ በይፋ ተቀላቅሏል 😁 ፋሲል የደበዘዘ ጋዜጠኛ ነው። መኖሩንም አለመኖሩንም የማታውቁት አይነት ሠው አለ አይደል? ቢኖር የማይሞላ ባይኖር የማያጎድል አይነት።

ከሶስት ቀን በፊት “ፋኖ ኢሊኮፍተር ጥሏል እመኑኝ” ብሎ እየማለ እየተገዘተ ተናገረና ቆይቶ ደግሞ የሆነች ቀይ የሞተር ሳይክል ስብርባሪ የሚመስል ቆርቆሮ ለጠፈ። ይህን መለጠፉ አይደለም የሚገርመው ተቃውሞ ሲበዛበት እዛው ኮመንት ላይ “የለጠፍኩት ፎቶ የቆየ እንደሆነ ይታወቅልኝ” ብሎን አረፈው 😂 በሶሻል ሚዲያ ታሪክ ራሱን በራሱ ያጋለጠ ቀጣፊ ጋዜጠኛ ተብሎ በቅሌት መዝገብ ላይ ተመዝግቧል 😂🫣

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የፌደራል እና የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች ጎንደር ከተማ ገቡ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ጎንደር ከተማ ገብተዋል።

ከፍተኛ መሪዎቹ ጎንደር አጼ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው፣ የሰሜን ምዕራብ እዝ አዛዥ ሌትናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ፣ የጎንደር ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና አባት አርበኞች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎቹ በጎንደር ከተማ በሚኖራቸው ቆይታ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በጎንደር ከተማ አስተዳደር የጎንደርን ከተማ የውኃ ችግር ይፈታል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የመገጭ ግድብ፣ የአዘዞ አርበኞች አደባባይ የመንገድ ፕሮጀክት፣ የጎንደር አብያተ መንግሥታት እድሳት እና ጥገና ሥራ፣ የጎንደር ከተማ የኮሪደር ልማትን የመሳሰሉ በከተማዋ እየተገገበሩ የሚገኙ ታላላቅ ፕሮጀክቶች ይገኛሉ።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ክብር ኢትዮጵያን ለሚገነቡ እጆች።

የፌደራል ፖሊስ በክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል አመራር እየሰራ ያለው ነገር አስደናቂ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ የሐገሪቱ ፖሊስ የሚመራበትን doctrine ለመጀመሪያ ግዜ አዘጋጅተዋል። የፖሊስ ኮሌጅን ወደዩኒቨርስቲ አሳድገዋል። አጠቃላይ የኢትዮጵያ ፖሊስ ኢትዮጵያን እንዲመጥን አድርገው Reform ሰርተዋል። ለአባላቱ ከፍተኛ የሚባል ስልጠና በመስጠት ምናልባትም አንዳንድ ያደጉ ሐገራትን በሚስተካከል ደረጃ ተቋሙን በተማረ የሰው ሃይልም ሆነ በቴክኖሎጂ አዘምነዋል።

አሁን ደግሞ በአስራስምንት ወር የተሰራው የፎረንሲክ ምርመራና የምርምር ልህቀት መአከል ተአምር የሚባል ነው። ይህ ማእከል በአፍሪካ ትልቁ ከመሆኑ ባሻገር ለፍትህ ስርአቱ ምሉእ መሆን የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ቀላል የሚባል አይደለምና ለዚህ ታላቅ ስራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይንና ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤልን እና ቡድናቸውን አለማድነቅ ንፉግነት ይሆናል።

የሐገሪቱ ተቋማት ያለምንም ጣልቃ ገብነት ራሳቸውን በዚህ ደረጃ ሲያሳድጉና በዘመኑ ቴክኖሎጂ ሲያስታጥቁ እንደማየት የሚያኮራ ነገር የለም። ኢትዮጵያ ከዚህም በላይ ይገባታል።

ክብር ኢትዮጵያን ለሚገነቡ እጆች።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የሀዋሳ ከተማ 85% በካሜራ መሸፈኑን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር መልካሙ አየለ ገለፀ!!!

የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር መልካሙ አየለ በሃዋሳ ከተማ በቴክኖሎጂ የታገዘ የፀጥታ እና የሰላም ማስከበር ሂደት በማከናወን ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

ኮማንደር መልካሙ በሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በተያዘው የፀጥታ ዘርፍ ሪፎርምን አቅጣጫ መሰረት እንደ መምሪያ በርካታ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን ያሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ የሆነው የሀዋሳ ከተማን በቴክኖሎጂ የበለፀገ ከተማ ለማድረግ ብሎም በቴክኖሎጂ የታገዘ የፀጥታ ማስከበር ሂደት ያላት ከተማ ለማድረግ በተሰራው ስራ የከተማዋን 85% በካሜራ እንዲሸፈን ማድረግ ችለናል ሲሉ ኮማንደር መልካሙ ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በሀዋሳ ከተማ ውስጥ በዚህ የሪፎርም እቅድ አንድ አካል የሆነውን በህብረተሰብ ተሳትፎ ግንባታዎች ሲሆኑ በዚህም እንደ መምሪያ በሀዋሳ ከተማ ውስጥ 3 ትላልቅ የፖሊስ ፅ/ቤት እና 40 የመረጃ መቀበያ ማዕከሎች ግንባታዎች ተጠናቅቀው በከፊል ስራ እየሰሩ መሆኑን የገለፁ ሲሆን በዚህም ሰዓት 40 ዘመናዊ የመረጃ መቀበያ ማዕከሎች በሀዋሳ ከተማ ላይ ለ24 ሰዓት ለማህበረሰቡ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አስታውቀዋል።

በአሁኑ ሰዓት በከተማችንን ላይ የሚገኙ የወንጀል ምርመራ እና የቃል አሰጣጥ ሂደት በቴክኖሎጂ የታገዘ እና በካሜራ የተደገፉ ሲሆን ይህም የሆነው የተመማሪውን ደህንነት እና መብት መረጋገጥ ለማረጋገጥ ከዛም በተጨማሪም የፋይል መረጃዎችን በማስቀመጥ ቀላል አሰራር እንዲዘረጋ ለማስቻል ሲሆን ይህ አግልግሎት በመላው ከተማችን ፖሊስ ጣቢያ የሚተገበር ነው።

በተጨማሪም 7614 ነፃ የፖሊስ መምሪያው የስልክ መስመር ሲሆን በማንኛውም ቀን እና ሰዓት በዚህ የነፃ መስመር በመደወል መረጃ ለመምሪያው የመረጃ ማዕከል ማድረስ ይችላል ተብላል። የስልክ መስመሩም በአንድ ላይ 5 ደዋዬችን በእኩል ሰዓት ማስተናገድ ስለሚችል ያለ ችግር ለማዕከሉ መረጃ ማድረስ ስለሚቻል ህብረተሰቡ ይህንን የነፃ የስልክ መስመር እንዲጠቀም ኮማንደር መልካሙ የገለፁት።

(Hawassa Engeda) በሚል በከተማችንን አልጋ ቤቶች ጋር በጀመርነው አዲስ Software መሰረት ማንኛውም የአልጋ አግልግሎት የሚጠቀም አካል ሙሉ መረጃ በSoftware አማካኝነት ወደ ተቋማችንን ይመጣል በዚህም በአልጋ ቤቶች የሚፈፀሙ ወንጀሎች ለመቀነስ ያቀደ የቴክኖሎጂ ትግበራ በከተማች ላይ በሚገኙ አልጋ ቤቶች ላይ ተግባራዊ አድርገናል።

በአሁኑ ሰዓት በከተማችንን የሚገኙ ሁሉም የንግድ ተቋማት የድህንነት ካሜራ አግልግሎት እንዲጠቀሙ ባስቀመጥነው አስገዳጅ እቅድ መሰረት 583 ተቋምት የድህንነት ካሜራ በጊዜያዊነት የተከሉ ሲሆን በቀጣይም ሁሉም ተቋማት የድህንነት ካሜራ አግልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ኮማንደሩ ገልፀዋል።

ኮማንደር መልካሙ አየለ አክለውም የማህበረሰብ አቀፍ ስራዎች በከተማችን ላይ በብዛት እየተሰሩ ሲሆን ፖሊስም ከማህበረሰቡ ጋር በህብረት በመስራት ሰላሙን ያረጋገጠ ከተማ የተገነባ ሲሆን በተጨማሪም 24 ሰዓት ያልተጎደለ የመረጃ መቀበያ ማዕከሎች አግልግሎት የፖትሮል ቅኝት የአባላት ስምሪት በመንደሮች ላይ በማድረግ ሰላማዊ ከተማ ቀጠና መፍጠር መቻሉን ተገልፆል።

ማህበረሰቡ እና ወጣቱ ከፖሊስ ሃይሉ ጋር በቅንጅት በመስራቱ በተገኘው ድል መሰረት የከተማችንን ነዋሪዎች እና ወጣቶች ከልብ አመሰግናለሁ ሲል የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር መልካሙ አየለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ፒያሳ ሊሴ ገ/ማርያም!

ከስቱዲዮ እስከ ባለ ሶስት መኝታ አፓርታማ

በ10% ቅድመ ክፍያ

ከ480,000 ብር ጀምሮ አፓርታማዎችን እየሸጥን ነው

ጥቂት አፓርታማዎች ይቀሩናል!

ይፍጠኑ!

ለበለጠ መረጃ (Direct/ Whatsapp) :- 0940407294 ወይም 0913935081

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

"ባለፉት የለውጥ አመታት በሶማሌ ክልል የተረጋገጠው ሰላም እና ልማት የየበኩላችንን በመውሰድ እናስቀጥላለን"፦ በአውሮፓ የሚኖሩ የዲያስፖራው ማህበረሰብ

ባለፉት የለውጥ አመታት በሶማሌ ክልል የተረጋገጠው ሰላም እና ልማት የበኩላችንን ወስደን ለማስቀጠል ቃል እንገባለን ሲሉ ኑሮዋቸውን በአውሮፓ በተለይ በስካንዴኔቭያን ሀገራት ያደረጉ የሶማሌ ክልል ተወላጆችና የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላት ገለፁ።

የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ከአውሮፓ ሀገራት የተውጣጡ የክልሉ ተወላጆች እና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ጋር በስዊድን ስቶኾልም ከተማ ተወያዩ።

በውይይቱም ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል አመስግነው፣ በኢትዮጵያ በተለይ በሶማሌ ክልል የሰፈነው ለውጥ ያስገኛቸው ፍሬዎች እና ድሎል እንዲሁም ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ገለፃ አድርገዋል።

ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ በገለፃቸው፤ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ መሪነት በፖለቲካው ዘርፍ በተደረገው ሪፎርም ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሆና ዜጎች በሀገራቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተረጋግጧል ብለው፣ ለዚህም ላለፉት ስድስት አመታት በሶማሌ ክልል የሰፈነው ሰላም፣ ልማትና የክልሉ ህዝብ በሀገር ጉዳይ ላይ ከተመልካችነት ወደ ውሳኔ ሰጪነት የመጣበት ሁኔታ ማሳያ ነው ብለዋል።

በተለይም ባለፉት ስድስት አመታት በኢትዮጵያ በተፈጠረው ለውጥ አማካኝነት በሶማሌ ክልል የሀይማኖት ነፃነት፣ ሰበዓዊ መብት መጠበቅ፣ ፖለቲካ ምህዳር መስፋትና ማንም በፖለቲካ አመለካከቱ በሀሳቡ እንደማይታሰር እና የህዝቡን ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ መልስ መስጠት መቻሉን ገልጸዋል።

አቶ ሙስጠፋ ባለፉት አመታት እንደ ጤና፣ መንገድ፣ ትምህርት፣ ከተማ ልማት፣ ግብርና፣ የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ ሃይልና የስራ እድል ፈጠራ፣ የኢኮኖሚ ሪፎርም፣ያሉ አንኳር የልማት ሥራዎችን መሰራታቸውን አንስተዋል።

በሶማሌ ክልል የፌዴራል እና የክልሉ መንግሥት ከሰላሙ ባሻገር ለ50 አመታት ያልተሰሩ የልማት ሥራዎች ባለፉት ስድስት አመታት ብቻ መሰራታቸውን ጠቁመው፣ በተለይ በጤናው መስክ ከስድስት አመታት በፊት በክልሉ 9 ሆስፒታሎች ብቻ እንደነበሩና፣ ለውጡ ማግስት 9 አዳዲስ ሆስፒታሎች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ እንሆነና በአሁኑ ወቅትም 15 ሆስፒታሎች በግንባታ ሂደት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል በክልሉ የመንገድ አውታሮች ማስፋፋት መቻሉንና የፌደራሉ መንግሥት ከ2 ሺህኪ.ሜ በላይ የአስፓልት መንገድ በክልሉ መገንባቱንና ሌሎች በርካታ መነረገዶችም በግንባታ ላይ ናቸው ብለው፣ ከኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ጋር በተያያዘም ባለፉት ስድስት አመታት በክልሉ 80 የሚሆኑ ከተሞች ወረዳዎች እና በቀበሌ ደረጃ ያሉ የ24 ሰዓት ኤሌክትሪክ ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን በውይይት መድረኩ ላይ ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም መንግሥት ለዲያስፖራው ምቹ ሁኔታዎችን ማመቻነቱንና፣ በውጭ ሀገራት የቀሰሙትን እውቀትና ያፈሩትን ሀብት ወደ ሀገራቸው ተመልሰው ኢንቨስት በማድረግ እራሳቸውንም ሆነ ዜጎችን እንዲጠቅሙ ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ጥሪ አቅርበዋል።

በበኩላቸው በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላት በተወካዮቻቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክት፤ በተደረገላቸው ገለፃ በኢትዮጵያ በተለይ በሶማሌ ክልል ያለውን ሁኔታ ጥሩ ግንዛቤ ማግኘት መቻላቸውን ገልፀው፣ የተረጋገጠው ሰላም እና ልማት ለማስቀጠል የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም ዲያስፖራው ሀገር ቤት ከተለያዩ ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት በሚሄዱበት ጊዜ መጉላላት እንዳለ ጠቁመው፣ ይህም እንዲስተካከል ጠይቀዋል።

በመጨረሻም የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ዲያስፖራው ለክልሉ ልማትና ለዜጎች ኑሮ መሻሻል እያደረገ ያለውን የተያየ ድጋፍና እገዛ አመስግነው፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የተነሱት ጥያቄዎች እንደሚታረሙ ተናግረዋል።

በመድረኩ ላይ በስካንዲናቪያን ሀገራት ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ምህረተአብ ሙሉጌታን ጨምሮ የሶማሌ ክልል አመራሮች እንዲሁም የስቶኾልም ከተማ ምክትል ከንቲባ ተገኝተዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

Good news : የኦሮሚያ ክልል መንግስት በኦሮሚያ ክልልና አካባቢው ይንቀሳቀስ ከነበረው ቡድን መሪ ጃል ሠኚ ነጋሳና እሱ ከሚመራው ሀይል ጋር የሰላም ስምምነት በአዲስ አበባ ተፈራርሟል። ይህ ውሳኔ ለኦሮሞ ህዝብም ሆነ አጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ መልካም ዜና ነው። ሌሎቹም ሀይሎች የህዝባቸውን ድምፅ ሰምተው ባስቸኳይ ወደሰላም መድረክ ሊመጡ ይገባል።

በቦታው የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ተገኝተው የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለመጡት ሃይሎችም ሆነ የሰላም ጥሪ ላቀረበው አካል ምስጋናቸውን አቅርበው ይህ አይነቱ ተግባር በሌሎቹም አካባቢዎችም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልፀዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የሠራዊታችንን የማድረግ አቅም ከፍ የሚያደርጉ ዘመናዊ ወታደራዊ ትጥቆች ለዕይታ ቀርበዋል።

“የተከበረች ሀገር የማይደፈር አየር ኃይል” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘውን 89ኛውን የአየር ኃይል ቀን የምስረታ በዓልን በማስመልከት የኢፌዴሪ አየር ኃይል ያዘጋጀው የአቭዬሽንና የተለያዩ ወታደራዊ ትጥቆች ኤግዚቪሽን በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በይፋ ተመርቆ ተከፍቷል።

በኢፌዴሪ አየር ኃይል ፣በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን በመከላከያ ዩኒቨርሲቲ የተመረቱ እንዲሁም ደግሞ አፕግሬዲንግና ኦቨርሆል ተደርጎላቸው የሠራዊታችንን የማድረግ አቅም ከፍ የሚያደርጉ ልዩ ልዩ ዘመናዊ ወታደራዊ ትጥቆች በኤግዚቢሽኑ ላይ ለዕይታ ቀርበዋል።

ትጥቆቹ የኢትዮጵያን አየር ኃይል እና የመከላከያ የኢንዱስትሪ ተቋማትን የፈጠራ አቅም ያሳዩ ከመሆኑም ባሻገር በራስ አቅም ጠንካራ ተቋም ለመገንባት የተያዘውን ዕቅድ በአጭር ጊዜ ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው መሆኑ ተገልጿል።

በኤግዚቪሽኑ ላይ የአፍሪካ አየር ኃይል አዛዦች፣ ወታደራዊ አታሼዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ ጀኔራል መኮንኖችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ለአመታት ስቃወመው የነበረው ነገር ህወሓት እራሱ ላይ አፍጥጦ መጥቶበታል:: የዘር ፖለቲካ መጨረሻው ከሃገር አልፎ ቀበሌና ሰፈር ውስጥ ይገባል:: ወያኔ የዘራችው አሜኬላ አድጎ እራሷን ወያኔን መቀርጠፍ ይዟል። መማር ለፈለገ ከወያኔ በላይ ጥሩ ‘ት/ቤት’ አያገኝም‼️

//እኔ እንደርታዊ ነኝ ትግራዋይነትን በግድ ልትጭኑብኝ አትችሉም//

የመቀሌው ሰው ህወሓት በጠራው ህዝባዊ ውይይት ላይ የተናገረው

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

"Impressive progress by the Ethiopian Air Force on their 89th anniversary! The successful flight readiness of Sun 2 is a major milestone in their journey towards becoming the largest air force in Africa by 2030. Proud to see such innovation and growth! #Ethiopia #AirForce

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

“ችግሩ ካልተፈታ የፌደራል መንግሥት ክልሉን ይረከባል”አቶ ጌታቸው

የህወሓት አመራሮች በውስጣቸው ያለውን በመፍታት ያዋጣል የሚሉትን መንገድ የማያቀርቡ ከኾነ፣ ብልጽግና የክልሉን አስተዳደር ራሱ ሊይዘው እንደሚችል ማሳሰቢያ መስጠቱን፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ተናገሩ።

አቶ ጌታቸው ብዙኅን መገናኛ በሰጡት መግለጫ፣ በክልሉ ባለፉት ሦስት ወራት ተኩል ከ28 ኩንታል በላይ ወርቅ መዘረፉን እና ወደ ፌዳራል መንግሥትም ሆነ “የክልሉ መንግሥት ከዚህ ውስጥ ያገኘው ገቢ የለም” ብለዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ሠውዬውን ለምን እደግፈዋለሁ?

የአብይ ፈተና የጀመረው በመጣ በጥቂት ቀን ውስጥ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ቦንብ በመወርወር ነበር። ይህ በሆነ በጥቂት ወራት ውስጥ ደግሞ በተቀናጀ ሁኔታ በሚዲያ ከባድ ስሙን የመበከል ተግባር ይፈፀምበት ጀመር።

በአንድ ቡድን Monopoly ተይዞ የነበረውን የደህንነትና የመከላከያ chain of command እንደገና ለማዋቀር ሲሞክር Power vacuum መፈጠሩን ያዩ ጠላቶች ከገዛ ድርጅቱ ባንዳዎች ጋር በፉጨት ተጠራርተው ከ 120 በላይ መፈናቀሎች በሐገሪቱ ላይ በጭካኔ በመፈፀም ሐገሪቱን በአጭር ግዜ ውስጥ በሐገር ውስጥ መፈናቀል ከአለም አንደኛ አድርገው ኢትዮጵያ እየደማች እነሱ ዳር ቆመው ማላገጥ ጀመሩ። ሠውየው ግን ጥርሱን ነክሶ ጉዞውን ቀጠለ። ህዝብ ከባድ ድንጋጤ ውስጥ ገባ።

ያፈሰሱት ደም ያላረካቸው የጥፋት ኔቶርኮች ሚሊየኖችን ለሚዲያ በመመደብ specifically አብይን ሰይጣናዊ መልክ በመስጠት ከህዝቡ ሊነጥሉት ሠሩ። አነስተኛ መፈንቅለ መንግስት ከመሞከር ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የግድያ ሙከራ እከማቀነባበር እቅድ ነደፉ። ሠውየውን ግን ማቆም የሚችል እቅድና ሴራ ፈፅሞ ሊፈጠር አልቻለም። ጉዞውን ቀጠለ።

አንዱ የኦሮሞ ጠላት አረገው። ሌላው የአማራ ጠላት ነው ብሎ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ከፈተበት። የገዛ የሚመራትን ሐገር ህዝብ አፈናቀለ የሚል የሞኝ ዘመቻ ተከፈተበት። እኔ በዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ የሚፈጠሩትን ነገሮች ከቅርብ ሆኜ ታዝቢያለሁ። የሰውዬውን ልፋትና በሱ ላይ የተከፈተውን የማያቋርጥ ዘመቻና የጠላትን ክፋትም አይቻለሁ።

ሁሉ እንዳልተሳካ ያዩ ጠላቶች የመጨረሻ አማራጭ ያሉትን ጦርነት ከፈቱ። የጦርነቱ አስከፊ ጎን መከላከያ ሠራዊታችን የተመታው ውስጡ ባሉ ከሃዲዎች መሆኑ ነበር። ባመነው ተከዳ። ከጀርባ ተወጋ። ግዜ ጠብቀው ጦርነት ከፈቱበት። ነገር ግን ይህ ሁሉ እልቂትና የሚዲያ ዘመቻ ያላሸነፈው የኢትዮጵያ ህዝብ ከአብይና ከመከላከያ ጎን ተሰለፈ ሠውየው የአለም አቀፍ ጫናና የዲስኩር ጋጋታ አድርገው ወደአዲስ አበባ ተጠጋን ሲሉ ጭራሽ ወደጦር ሜዳ ሄዶ ፊት ለፊት እንደወንድ ገጠማቸው። ግዙፍ የሚመስለውንና በአውሮፕላን ሳይቀር ከካይሮ መሳሪያ ይላክለት የነበረውን ጎልያድ በፈጣሪ ድጋፍ ድል አደረገ። የሚገርመው ድል ማድረጉ አይደለም። ይህን ሁሉ ያደረገውን አካል ሊያጠፋ ሲችል በድሉ አፋፍ ላይ ቆሞ የይቅርታ እጁን ዘረጋ።

ፈተናው ቀጠለ። የኢትዮጵያ ጠላቶች አልተኙም። የብሔራቸውን ካባ ለብሰው በነፃ አውጪ ስም እዚያም እዚም ተደራጁ። ሐገራቸው ላይ ከግብፅ እስከሶማሊያ ከሐገር ቤት እስከአንታርቲካ የሚዘረጋ የጥፋት ሴራ ይሸርባሉ። ሐገሪቱን እረፍት መንሳትና ሠውየውን የማቆም ዘመቻው ቀጠለ። የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ይታዘባል።

ሠውየውን ማከብረው በፈተኑት ቁጥር ህልሙ ስለሚጨምር ነው። ጦርነት መሀል አባይን ይገነባል። እሳት መሀል ቆሞ ወደብ ያልማል። የትኛውንም አይነት ፈተና ብትደቅንበት ከመርሀግብሩ ፈቀቅ አታደርገውም። ሊያጠፉት የሚያሴሩትን ሳይቀር አሸንፏቸው ሊያጠፋቸው ሲችል ለይቅርታ እጁን ሲዘረጋ ደጋግሜ አይቸዋለሁ።

ባጭሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ታሪክ የትኛውም መሪ ያልገጠመውን ፈተና በስድስት አመት ውስጥ ተፈትኖ ያለፈ። እንደወርቅ በእሳት የነጠረና ኢትዮጵያን ከመፍረስ የታደገ መሪ መሆኑን እኔ ሁሉን ነገር ከቅርብ ሆኜ የተመለከትኩት ናትናኤል መኮንን ህያው ምስክር ነኝ።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ደጃች ዉቤ ሰፈር በቻይና ጃንጉዜ የኮንስትራክሽን ድርጅት ላይ የእሳት አደጋ ደረሰ

አራዳ ክፍለ ከተማ ደጃች ዉቤ ሰፈር
በቻይና ጃንጉዜ የኮንስትራክሽን ድርጅት ላይ ያጋጠመዉን የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ለማዋል የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሰራ አመራር ኮሚሽን  የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ርብርብ እያደረጉ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጋምቤላ ክልል የተገነባውን ኢትኖ ማይኒንግ የወርቅ ፋብሪካ በዛሬው ዕለት መርቀው ከፍተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ኢትኖ ማይኒንግ የአኮቦ ሚኒራልስ ኩባንያ መጋቢ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኩባንያው በስካንዲኔቪያን ሀገራት መሠረቱን ያደረገ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በኩል ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ወርቅ ፍለጋ እና ማውጫ ላይ የተሰማራ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

በጋምቤላ ክልል አኮቦ ወረዳ በተከናወነው ትርጉም ባለው የኢንቨስትመንት ሥራም ለሁሉም አካላት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በአኮቦ የምትገኘው ዲማ ከተማ በአነስተኛ ባሕላዊ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ሒደት ለብዙ ጊዜ ብክነት የተሞላበት አሠራር መቆየቱን አስታውሰዋል።

ይህ አዲስ ኢንቨስትመንት በአጭር ጊዜ ውስጥ አመርቂ እና ደረጃውን የጠበቀ የወርቅ ምርት ከማስገኘቱም በላይ በሕገ-ወጥ የማዕድን ሥራ ለተጋረጠው ፈተና ምላሽ ይሰጣል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ለጋምቤላ ክልል ዘላቂ ልማት በክልሉ ያለውን እምቅ ሃብት ለሕዝቡ እና ለክልሉ ጠቀሜታ ለማዋል ያለውን ተነሳሽነት እንደሚያሳይም ነው ያስረዱት፡፡

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በሱሉልታ ክፍለ ከተማ ወሰርቢ ወረዳ ቢሎ ዞን ልዬ ቦታው ኮንቦልቻ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አዱኛ ጭኮ ሆርዶፋ የተባለ ግለሰብ ከውጭ ሀገር ለሸኔ ሽብር ቡድን አመራር ለሆነው ቦሬ ለተባለው የተላከ ብዛቱ 29,985 ዶላር አቡ ወይም ሮብሰን ከተባለ የቡድኑ ሴል በመቀበል በመኖሪያ ቤቱ በመደበቅ ዶላሩን በህዳር 12/2017 ወደ ቦሬ ለመላክ ዝግጅት ላይ እያለ በተገኘው መረጃ መሰረት ዛሬ ከቀኑ 6:30 በቁጥጥር ስር ውሏል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በዳንሻ፣ በሶሮቃና አካባቢው የፅንፈኛው ቡድን አባላት እጅ ሰጥተዋል።

የፅንፈኛው ቡድን አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው በዳንሻ፣ በሶሮቃና አካባቢው በስምሪት ላይ ለሚገኘው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ኮር የሠራዊት አባላት እጅ እየሰጡ ነው።

የኮሩ የሠራዊት አባላት በአካባቢው የፀጥታ መዋቅር በማደራጀት እና በመቀናጀት ባደረጉት ህግ የማስከበር ኦፕሬሽን የፅንፈኛው ቡድን ተበታትኖ እጁን እንዲሰጥ አድርጓል ያሉት የኮሩ ምክትል አዛዥ ለውጊያ አገልግሎት ድጋፍ ኮሎኔል መዝገቡ ዘሩ አሁን ላይ በቡድኑ ተፅዕኖ ስር የነበረውን አካባቢ በማፅዳትና አንፃራዊ ሰላም እንዲመዘገብ በማድረግ ህዝቡ የተለመደ ተግባሩን እያከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

የተሰጠውን የሰላም አማራጭ እድል በመጠቀም በርካቶች በሰላም እጃቸውን እየሰጡ እንደሆነ የገለፁት ኮሎኔል መዝገቡ ይህን ሳይጠቀም ወደ ለመደው ዘረፋ፣ ግድያ፣ ውድመት ድርጊቱ የገባው ፀረ-ህዝብ ቡድን ላይ ሠራዊቱ እርምጃ መውሠዱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ህዝቡን በመዝረፍና ሰላም በማሳጣት ለከፋ ችግር መዳረጋቸውን የተናገሩት እጅ የሰጡት የቡድኑ አባላት አሁን በተሰጣቸው የሰላም ምህረት በመጠቀም የበደሉትን ህዝብ ለመካስ ከመንግስት ጎን ተሰልፈው በሰላም ማስከበር እና በልማት ስራዎች ተሰማርተው ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ጥሪ ማስታወቂያ
 
የአፍሪካ መዲና እና የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ቀንዲል የሆነችው አገራችን ኢትዮጵያ በቀጣይ የካቲት ወር በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የሚሳተፉ እንግዶችን በላቀ መስተንግዶ ለመቀበል ልዩ ዝግጅት እያደረገች ትገኛለች።
 
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአገራችንን በጎ ገፅታ አጉልቶ ለማሳየት መልካም አጋጣሚን በሚፈጥረው በዚህ መርሃግብር ላይ ከአቀባበል እስከ አሸኛኘት ባለው የመስተንግዶ መርሃግብር  በጎ ፍቃደኛ ፕሮቶኮል ካዴቶችን በመቀበል አሰልጥኖ በተለያዩ የፕሮቶኮል ሥራዎች ላይ ማሰማራት ይፈልጋል።
 
በመሆኑም የእንግሊዘኛ፣ፈረንሳይኛና ዓረብኛ ቋንቋዎችን መናገርና መጻፍ የምትችሉ እና ዕድሚያችሁ ከ18-30 የሆነ ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋናው መ/ቤት በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ እያሳወቅን ለምዝገባ ስትመጡ የትምህርት ማስረጃችሁን እና ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እንገልፃለን።
 
የአገራት መሪዎች፣የዓለምአቀፍና ቀጠናዊ ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በሚሳተፉበት የአህጉራችን ትልቁ ጉባዔ ላይ በጎ ፍቃደኛ ፕሮቶኮል በመሆን የዚህ ታሪክ አካል ሆናችሁ አገራችሁን ያለ ክፍያ በኩራት እንድታገለግሉ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ.ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጥሪውን ያስተላልፋል።
 
ለተጨማሪ መረጃ፡-
 
+251911411045
+251912663737
 
ኑ! ሁሉም ዜጋ ለአገሩ ዲፕሎማት ነው!
 
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ሉዓላዊ-የጎጃም ፋኖ የትግሉ ግምገማ ሰነድ ሲዳሰስ/በሕወሐት ውዝግብ ውስጥ የኤፈርት ሐብት ሚና/ማንነታችንን ለጨረታ አናቀርብም-ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ https://youtu.be/X50rDJNuLks

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሽመልስ ቶማስ በሀዋሳ ከተማ በተካሄደው የሃገራዊ የሰላም ኮንፍራስ ላይ የሙሉ ኮምሽነር ማዕረግ ሹመት ተሰጣቸው!!!

የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ባለፉት ሁለት አመታት ውስጥ በርካታ ሪፎርሞችን ሰርቻለሁ ያለ ሲሆን ከተቋሙ ላይ ፍፁም ወገንተኝነት እና ብልሹ የሌቤነት አሰራርን ያለ ርራሄ በመታገል ፍትሃዊ ገለልተኛ መስመር ያለውን ጠንካራ ተቋም እንዲፈጠር አስችለናል ተብሏል።

በሲዳማ ክልል ብቻ ሳይሆን በአጎራባች ክልሎች ያለውን የሰላም ሁኔታ ለማስጠበቅ ቀን ሳይል ማታ ሳይል በብቃት ተልዕኮችን እየፈፀመ በብቃት እያከወነ ያለ ጠንካራ የፖሊስ ተቋም አቅም ያለው ሃይል ገንብተናል ብለዋል።

ከተቋሙ የሲዳማ ፖሊስ ኮሚሽን ግቢ የጀመርነው የግንባታ ሪፎርም እንደ ክልል አድጎ መሰረታዊ ቅርፅ ይዞ በመዋቅሩ ላይ አሻራ ጥሎ የሲዳማ ክልል ፖሊስ እስከ መጨረሻ ከክራይ ቤት ያዳነ ፕሮጀክት ይዘን በማጠናቀቅ ላይ እንገኛለን ብለዋል።

በህብረተሰብ ተሳትፎ የፖሊስ ተቋሙን ለመገንባት እና ለማዘመን በተያዘው እቅድ መሰረት ከህብረተሰብ ክፍሉ 1.1 ቢሊዮን ብር በላይ በመሰበብ 42 የፖሊስ ፅ/ቤት 640 የመረጃ መቀበያ መሰረተ ግንባታዎችን በ90 ቀን ገንብተን ለማጠናቀቅ እየሰራን ሲሆን ያጠናቀቅነውም አለ።

በሲዳማ ፖሊስ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለፖሊስ ሃይሉ እና ለቤተሰባቸው ነፃ የህክምና አገልግሎት የሚያገኙበት የፖሊስ ጤና ጣቢያ ከሟቋቋም ባለፈ ለፖሊስ ኮሚሽኑ ገራጅ እና ነዳጅ ማደያ ግንባታዎችን ከትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ አስገብተን ሪፎርሙን እያከናወንን እንገኛለን ብለዋል።

የዚህ የትራንስፎርሜሽ እቅድ አውራ አካል የሆኑት የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ቶማስ በክልሉ የመጀመሪያው የሆነውን የሙሉ ኮምሽነር ማዕረግን አግኝተዋል።

በኮንፍራንሱ ላይ የሁሉም ክልል የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊዎች, ኮሚሽነሮች, የመከላከያ ሰራዊቱ አመራሮች, የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አመራሮች, እና ሚኒስተሮች ተገኝተዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561

Читать полностью…
Подписаться на канал