መስከረም 19/2017 ዓ.ም በመላው ኦሮሚያ ሰባት ዞኖች በተወሰደው ኦፕሬሽንና ፍተሻ 49 ታጣቂ የተደመሰሰ ሲሆን ወደ 15 የሚሆኑ አባላት ቆሰለዋል። 20 የተማረከ፣ 41 ሴል እና ሎጀስቲክስ አቀባይ በአምስት ዞኖች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የተያዙ ንብረቶች ክላሻ 13፣ ሽጉጥ 2 የኃላ ቀር 1 ፣ የወገብ ትጥቅ 3፣ ቦምብ 2፣ የተለያዩ ተተኳሾች 432 እንዲሁም ጥሬ ገንዘብ 32,200፣ ባለቤታቸው ያልታወቁ 32 የቀንድ ከብቶች እና 30 ፍሎች ተይዘዋል።
ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል:: ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት
አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
Tel: 0913858561
በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 79ኛው የተመድ ጉባዔ ጎን ለጎን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከዴንማርክ አቻቸው ላርስ ሎክ ራስምሰን ጋር ተወያይተዋል።
አምባሳደር ታዬ በውይይቱ ላይ ዴንማርክ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት አባል ሆና በመመረጧ የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ በወቅታዊ የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮችና ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድ ባላት ቁርጠኝነት ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል።
አምባሳደር ታዬ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሼህ ሻክቡት ናህያን አል ናህያን ጋር በሁለትዮሽ እና በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ደኀንነት ዙሪያ መክረዋል።
ሶማሊያን በተመለከተ ባደረጉት ውይይት አምባሳደር ታዬ የቀጣናው አገራት ዋጋ የከፈሉበት እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከፍተኛ ወጪ ያወጣበት የሶማሊያ ደህንነት እንዲቀጥል ማድረግ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።
“የከበበንም ለመክበብም አቅም ያለው ሃይልም የለም፤ ተከበናል ወይም ተከበዋል ብሎ የሚያስብ የመረጃ እጥረት ያለበት ብቻ ነው”
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፣ የኢፌድሪ ጦር ኃይሎች
ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም
https://youtu.be/fx_5ZEgAFKI
እንኳን ለ2017 የመስቀል በዓል አደረሳችሁ!
Baga ayyaana Masqalaa bara 2017tiin isin gahe!
ርሑስ በዓል መስቀል 2017!
በነቀምቴ ከተማ በተደረገ ዘመቻ በርካታ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ውሏል።
በነቀምቴ ከተማ በተደረገ ድንገተኛ ዘመቻ በርካታ የአሸባሪው የሼኔ ቡድን ሎጀስቲክስ እና የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን በማዕከላዊ ዕዝ የህዳሴ ኮር ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ ኮሎኔል እያሱ ሀብቱ ገልፀዋል።
ዘመቻው የኮሩ ሰራዊት ከከተማው ፓሊስ እና ሚሊሺያ ጋር በመቀናጀት የተደረገ ሲሆን ለጠላት መረጃ የሚያቀብሉ አባ ቶርቤ ፣የቡድኑን አባላት ጨምሮ 117 የተለያዬ ዓይነት ሽጉጥ ፣646 የሽጉጥ ጥይት፣ 30 ክላሽ፣ 34 ኋላቀር መሳሪያ ፣ 563 የክላሽ ጥይት እና 50 የእጅ ቦምብ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ተናግረዋል።
የነቀምቴ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ሻሎም በዳሳ በበኩላቸው በተደረገው ኦፕሬሽን እና በተገኘው ውጤት
ለኮሩ የሰራዊት አባላትና ለፀጥታ ሃይሎች ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።
የተገኙ ድሎችን በሚመለከት በነቀምቴ ከተማ ውይይት የተደረገ ሲሆን የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ በማስቀጠል የዞኑን ሰላም ማስጠበቅ እንደሚገባ ተገልጿል።
ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ከኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር በወቅታዊ የሃገራችን ጉዳይና በመከላክያ ሰራዊት እንዲሁም በቀጠናው ዙሪያ ልዩ ቃለመጠይቅ አድርጏል ሰሞኑን ይጠብቁን!
Читать полностью…Vote for Naomi Melketsadek to be Baby of the Year while supporting a great cause! Cast your daily vote below, or make even more of an impact with a tax-deductible donation supporting Baby2Baby. https://babyoftheyear.org/2024/naomi-melketsadek
Читать полностью…ካስሽ ጋዜጠኝነት ውጥንቅጥ ወጥቶ በጥቅምና በጎጥ በተጨማለቀበት ወቅት በእንዲህ አይነት ህዝብን/ወጣቶችን ሊያስተምሩ በሚችሉ ስራዎች ይዘህ ዳግም ወደ ሚዲያው በመምጣትህ ልትመሰገን ይገባል::
ጋዜጠኛ ካሳሁን ይልማ (ካስሽ) ግራ ቀኙን አይተህ አስተውለህ ይህ ህዝብ ምን አይነት ነገር ይበጀዋል ወጣቱስ ከጦርነት አባዜ ወጥቶ ምን ያስተምረዋል ብለህ አስበህ አስተውለህ እንዲህ አይነት ፕሮግራሞችን ይዘህ ወደ ሚዲያ ብቅ ማለትህ ብቻ ሳይሆን ወደፊት በስፋት በርትተህ እንዲህ ያሉ አስተማሪ ፕሮግራሞችን እንደምታቀርብ ተስፋ አደርጋለሁ:: ጤናማ የሆነ የፖለቲካውን ትንተናውን ጨሮም:: ካስሽ በርታ‼️ https://youtu.be/7mPfdW9fMbo?si=epTDuiFJCpY45-Dk
የመስቀል ደመራ በዓል ሃይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ ያለምንም የፀጥታ ሥጋት በሰላም እንዲከበር በቴክኖሎጂ የታገዘ ዝግጅት ማድረጉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገለፀ
የመስቀል ደመራ በዓል ሃይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ ያለምንም የፀጥታ ሥጋት በሰላም እንዲከበር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት አካላት ጋር ውይይት በማድረግ በቴክኖሎጂ የታገዘ ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ተግባር መገባቱን ገልጿል።
ክቡር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በውይይቱ ላይ ሀገራዊ ሰላምና የፀጥታ ሁኔታን ከግምት ውስጥ ያስገባ የኦፕሬሽን፣ የምርመራ፣ የመረጃ፣ የህዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ቲሞችን በማዋቀር የሽብር ቡድን አባላትን እና የተደራጁ ወንጀለኞች እንዲሁም የኢኮኖሚ አሻጥሮችን የመቆጣጠር ተግባርም አጠናክሮ በማስቀጠል ያለ አግባብ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን አንስተው የተጀመረው ኦፕሬሽን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል አያይዘው የመስቀል በዓል በሰላም እንዲከበር ሁሉም በተሰማራበት የፀጥታ ስራ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበው ለመላው የእምነቱ ተከታዮች የእንኳን አደረሳቹ መልዕክትም አስተላልፈዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ በበኩላቸው የሀገራችን የፀጥታ ሁኔታ አሁን ላይ በአስተማማኝ ሰላምና ደኅንነት ላይ እንደሚገኝ አመላክተው በቀጣይም በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች በአደባባይ በከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር የሚከበረው የመስቀል በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት እንደተደረገና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ በርካታ የፀጥታ ኃይልም እንደተሰማራ ተናግረዋል።
ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታው ኃይሉ ከሀይማኖት አባቶችና ከሰላም ወዳዱ ህብረተሰብ ጋር በመተባበር መስራት እንዳለበት አሳስበው ማንኛውንም ለበዓሉ ማድመቂያ ተተኳሽ ነገሮችና ርችቶችን ሆነ በዓሉ ከሚፈቅደው ስርዓት ውጪ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ መልዕክቶችን የያዙ አልባሳትና ፅሁፎችን ይዞ ወደ በዓሉ ቦታ መሄድ የተከለከለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ሀሰን ነጋሽ እና የክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ረዳት ኮሚሽነሮች በዓሉን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ በዓሉን በሰላምና በደስታ ለማሳለፍ የሚፈልግ በርካታ ሕዝብ እንዳለ ሁሉ የበዓሉን ድባብ ለማጠልሸት የተንቀሳቀሱ የሸኔ እና የፅንፈኛ የሽብር ቡድን አባላት እንዲሁም የአይኤስና የአልሸባብ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ሥር አውለው ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
ኅብረተሰቡ ከፖሊስ የሚተላለፉ ክልከላዎችን በማክበር ፀጥታን የሚያደፈርሱ አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲመለከት የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (EFPApp) ወይም በነፃ የስልክ መስመር 991 በመጠቀም ጥቆማዎችን በፍጥነት በመስጠት ወይም መረጃውን በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ ኃይሎች በአካል በማድረስ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል፡፡
ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል:: ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት
አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
Tel: 0913858561
በሶማሊያ “ከድህረ አትሚስ በኋላ የሚኖረው የሀይል ስምሪት ተግባራዊ ከመደረጉ አስቀድሞ የስምሪቱ ማዕቀፍ በጥንቃቄ መሠራት አለበት” - አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ
በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 79ኛው የተ.መ.ድ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ጋር በጋራ ጉዳዮች መወያየታቸው ተገለጸ።
በውይይታቸው ወቅት በአፍሪካ ቀን የአሜሪካ መንግስት ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር መገኘታቸውም ታውቋል።አምባሳደር ታዬ ለረዳት ሚኒስትሯ በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ ባደረጉበት ወቅት በተለይ ኢትዮጵያ በቀጣናው ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን እያደረገች ያለውን ጥረት ትኩረት ሰጥተው ማንሳታቸው ተጠቁሟል።
ሚኒስትሩ ሶማሊያን በተመለከተ ከሞሊ ፊ ጋር በነበራቸው ውይይት ኢትዮጵያ ሽብርተኞችን በመዋጋት ረገድ በምታደርገውን የተጠናከረ ጥረት ዙሪያ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ከድህረ አትሚስ በኋላ የሚኖረው የኃይል ሥምሪት ተግባራዊ ከመደረጉ አስቀድሞ የስምሪቱ ማዕቀፍ በጥንቃቄ መሠራት እንዳለበት ተናግረዋል።
የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ክብርት ሞሊ ፊ በበኩላቸው አሜሪካ ሽብርተኝነትን በመዋጋት እና አጠቃላይ በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ እና አሜሪካ መካከል ጠንካራ ግንኙነት መኖሩን በመግለጽ በቀጣይ የጋራ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ቀጣይነት ያለው ውይይት አስፈላጊ መሆኑን ማንሳታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የአሸባሪዎች ስፖንሰሯ በአለም አደባባይ እንዲህ ተነግሯታል። አንዳንድ ተከፋይ ባንዳዎች ካልሰሙ ሼር እናድርጋቸው ፦ ምናልባት ድስት እያጠቡ ነው ፣ በኑሮ ውድነት ስም ግጭት እየጠነሰሱ ወይም የትም የማያደርሰውን መስመር ሀይሊና እየዘመሩ ከሆነ።
Читать полностью…የቀዩ መኪና ህግና ባለሰባራ ካልኩሌተሩ
የሆነ በላይነህ ሲርጋጋ የሚባል ዘፋኝ ነበር። አንድ ነጠላ ዜማ ለቆ እውቅና ባተረፈ ማግስት ምን እንደነካው እንጃ ዳያስፖራ አግብቶ ከአርቱም ከሐገሪቱም ርቆ ለአመታት ጠፋና ከሃያ አመት በኋላ በጉልምስና መባቻው አንድ ነጠላ ዜማ ለቀቀ። «ምነው?» ቢሉት «እንዳልረሳ ብዬ» አለ አሉ። በኢትዮጵያ ፖለቲካም ከተረሱ ወዲያ «እንዳልረሳ ብዬ» የሚሉ ሰዎችን አይተን ገርሞናል።
አንዳንዶቹ እነሱ የፈጠሩት ሀገራዊ ቁስልና ህመም እንኳን በአግባቡ ሳይሽርልን እንደሰጎን አሸዋ ውስጥ ጭንቅላታውን ቀብረው ይከርሙና ህዝብን የበለጠ አንድ ሊያደርግ ይችላል የሚሉት የተስፋ ፣ የሰላም ፣የመለወጥ ዝማሬ አየሩን ሲሞላው ወይም እንደዘንድሮው ኢሬቻ አይነት ህዝባዊ አንድነት የሚያመጣ ክብረ በአል ሲመጣ ብቅ ብለው «አትርሱኝ» ይላሉ። ኢትዮጵያም ሆነች ህዝቧ በሻኬሽን እየመጡ እንደሚጎበኙት የእንስሳት ዙ/Zoo ነው የሚመስላቸው። ሊዝናኑብን ይመጡና ዛፉ ደርቋል ፣ አንበሳው ከስቷል ይሉናል። እስከዛሬ ያልታያቸው ችግር ድንገት ይገለጥላቸዋል። ሰው ፊት ላይ የተፃፈን ጉስቁልና ድንገት "እንደመዳፍ ማንበብ ጀምረናል" ይሉሃል። በተግባራቸው፤ በንግግራቸው የፈጠሩትን ቀውስ ቢያንስ ፀፀታቸዉን በዝምታቸው እያካካሱት ነው ብለን ሳንጨርስ የለቅሶ መዝገባቸውን ገልጠው ሙሾ ያወርዳሉ። ለምን? አይባልም እነዚህ ሰዎች በለቅሷቸው ልክ ነው ኮሮጇቸው የሚሞላው። አለቀ።
በሐገር ሳቅ ላይ የሀዘን ቅመም መበተን የማይሰለቸው ባለ ሰባራ ካልኩሌተሩ ሰውዬ ድንገት እንደ ወልይ የህዝቡ ችግር ወለል ብሎ ታየኝ እያለን ነው። የከተማው ብርሀን የጠወለገ ፊት አሳየኝ ይለናል።
ሃሃ
እኛ ችግርና ሃዘን የለም የምንል ደንቆሮዎች አይደለንም። ነገር ግን እድሚያችንን ችግር ፈጥረን የራሳችንን ችግር እራሳችን ስንተነትን አንኖርም። ችግሩን ለመቅረፍ ቀን ከሌት የምንሰራና እንደንስር ከጭጋጋማው ደመና በላይ እየተንሳፈፍን የችግሩን ውል በመለየት ሐገራችንን ለማሸገር ሳንተኛ የምናድር እንጂ የሃዘንና የጉስቁልና ልሂቃን አይደለንም። መፍትሄ እንድናመጣ እንጂ ችግር እየተነተንን የአስለቃሽነት ሚና እንድንወጣ አልተነሳንም።
በሳይኮሎጂ the red car theory የምንላት ቀላል ምሳሌ አለች። አንድ ሰው ቀይ መኪና ለመግዛት ካሰበ በተለየ ሁኔታ ቀይ መኪኖችን notice ማድረግ ይጀምራል። ሰውየው አይኑ ቀዩንም ጥቁሩንም መኪና ቢያሳየውም ጭንቅላቱ ግን filter አድርጎ የበለጠ notice የሚያደርገው ቀድሞ ሲያብሰለስለው የከረመውን ቀይ መኪና ነው።
ኦቦሌሳ በሐገሪቱ ላይ ከዚህ ሁሉ በጎ ነገር የታየህ የጠወለገ ፊትና የጠቆረ ገፅታ ብቻ ከሆነ according to the red car theory የፈለግከውን ነው መርጠህ ያየኸው ለማለት እንገደዳለን።
ሰው መነፅሩ ከቆሸሸ የሚታየው ሁሉ ቆሻሻ ይመስለዋል። ሚዛናዊ ሆነህ ሁሉንም እንድትመለከት መጀመሪያ መነፅርህን አውልቀህ አፅዳና መልሰህ አጥልቀው። ላንተ ስንፍና ሌላው የሚከሰስበት አንዳችም ምክኒያት የለም።
ኢትዮጵያ አሸንፋለች። መልካም የኢሬቻ በአል ይሁንልን።
From Ethiopia Prevail Team «ሰኚ ተሾመ»
“የከበበንም ለመክበብም አቅም ያለው ሃይልም የለም፤ ተከበናል ወይም ተከበዋል ብሎ የሚያስብ የመረጃ እጥረት ያለበት ብቻ ነው”
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፣ የኢፌድሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም
https://youtu.be/fx_5ZEgAFKI
በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 79ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን የብሪክስ አባል አገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ተካሂዷል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር፥ በዓለም አቀፍ ተቋማት አስተዳደር እና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ፍትሀዊ ውክልና እና ተሰሚነት እንዲሰፍን በሚደረገው የማሻሻያ ጥረት የብሪክስ ማዕቀፍ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል የሚል ተስፋ እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል።
አምባሳደር ታዬ የባለብዙወገን ዓለም አቀፍ ተቋማቱ አሳታፊ እና ጠንካራ እንዲሆኑ የተጀመሩ የማሻሻያ ጥረቶች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አንስተዋል።
ሚኒስትሩ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ማሻሻያን በተመለከተ ባደረጉት ንግግር፥ ማሻሻያው ቅድሚያ ለአፍሪካ ውክልና መስጠት እንደሚገባው እና ታማኝ እና ፍትሃዊ ሆኖ መቀጠል እንዳለበት ጠቁመዋል።
አምባሳደር ታዬ በጸጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ ላይ ኢትዮጵያ የምታራምደው አቋም የአፍሪካን አቋም ነው፤ ለአፍሪካ ሕጋዊ ጥያቄ እና ታሪካዊ ኢ-ፍትሀዊነት ግማሻ ምላሽ ሊሰጠው አይገባም ብለዋል።
ሚኒስትሩ ውክልናው መልከዓ ምድርን፣ የብሪክስን የጋራ ዕሴቶችን እና በብሪክስ ማዕቀፍ አባል አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት እንዲሁም የተመድን ቻርተር ባማከለ መልኩ መከናወን እንዳለበትም ጠቁመዋል። እነዚህ መርሆዎች ብሪክስ በዓለም አቀፍ ተቋማት ማሻሻያ እና ፍትሀዊ ውክልና እንዲኖር የሚጫወተውን ሚና የበለጠ ያጠናክሩለታል ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
መስቀል (ደመራ )በመስቀል አደባባይ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
Meskel (Demera) at Meskle square
Addis Abeba Ethiopia
መስከረም 16 2017
September 26 2024
©️ Mikias Kassahun
ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል:: ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት
አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
Tel: 0913858561
ለ2017 ዓመት የመስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ
የመስቀል በዓል የሕልም ጉልበት የታየበት በዓል ነው፡፡
ንግሥት ዕሌኒ መስቀሉን ለማውጣት ያለመችው ምንም አመቺ ነገር ባልነበረበት ጊዜ ነው፡፡ ዙሪያዋ ጨለማ ነበር፡፡ መንገዶች ሁሉ ዝግ ነበሩ፡፡ ነገሮች ሁሉ አስቸጋሪ ነበሩ፡፡ ማንም በማያስበው ጊዜ፤ አይቻልም አይሞከርም በሚባልበት ወቅት፤ አንድ ቀን፤ ፈጣሪዋ ሲፈቅድ፤ መስቀሉን ከተቀበረበት ሥፍራ ለማውጣት ሕልም ነበራት፡፡
ሕልሟ እንዲሳካ ሠራች፤ ታገለች፡፡ ጨለማውን እየገፈፈች፤ አስቸጋሪውን ጎዳና እየጠረገች፤ ከውስብስብ ችግሮች ጋር እየተጋፈጠች ወደ ፊት ተጓዘች፡፡ በመጨረሻም ኢየሩሳሌም ተሻግራ፣ መስቀሉን ከተቀበረበት ሥፍራ ለማውጣት በቃች፡፡ ሕልሟ እውን ሆነ፡፡ ታሪክን ቀየረች፡፡ ልዕልናን ዐወጀች፡፡ ደመራ ለሚታገል፤ ተስፋ ለማይቆርጥና እስከ መጨረሻው ለሚጸና ሰው ሕልሙ አንድ ቀን እውን እንደሚሆን የሚያሳይ ትእምርት ነው፡፡
እዮሃ፤ ማለት “ይሄዋ” ማለት ነው ይባላል፡፡
ይሄው ተገኘ፤ ይሄው ተሳካ፤ ይሄው እውን ሆነ ማለት ነው፡፡ ከበረቱ፤ ከታገሉና ከጸኑ የማይሳካ ምን ነገር አለ? ሕልሙን ለሚያውቅ፤ ሕልሙ እንዲሳካ በነገሮች ተስፋ ሳይቆርጥ ለሚለፋ፤ እንደ ንግሥት እሌኒ ሕልሙ እውን ሆኖ አንድ ቀን ማየቱ አይቀርም፡፡ የሕልሙን ደመራ መደመሩ አይቀርም፡፡ “እዮሃ”፤ “ይሄዋ!” ማለቱ አይቀርም፡፡
መስቀል ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በሁለት መንገድ የሚያሳይ በዓል ነው፡፡ ደመራው ከእንጨት ወደ ችቦ፤ ከችቦ ወደ ደመራ የሚያድግበት መንገድ መደመር ምን ያህል ኃይልና ጉልበት እንዳለው ያሳያል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ መስቀል በተለያየ መንገድ፣ በተለያየ ባህልና አከባበር በብዙ ብሔረሰቦች ይከበራል፡፡ ይሄ ደግሞ በኅብረ ብሔራዊነታችን ውስጥ ያለውን ነባር ትሥሥር፣ የወል ትርክትና አንድነት የሚሳይ ነው፡፡
እንዲህ ዓይነት በዓላት ሃይማኖታውያን ብቻ አይደሉም፡፡ የኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን መገለጫዎች ጭምር ናቸው፡፡ በመደመር ውስጥ ያለውን ጥንካሬና ጉልበት የሚሳዩ ትውልድ ለእኛ ትምህርት ያቆማቸው ምልክቶች ናቸው፡፡
ደመራውን በደመርን ጊዜ፤ ደመራውን በለኮስን ጊዜ፤ እንደየባህላችን የመስቀልን በዓል ለማክበር በቤተሰብና በማኅበረሰብ ደረጃ በተሰባሰብን ጊዜ ኢትዮጵያን እናስባት፡፡
የሁላችንም ዕሴቶች፣ ባህሎች፣ ወጎች፣ ዐቅሞች፣ ጸጋዎች፣ ሀብቶች፣ ቋንቋዎች፣ ታሪኮች፣ ወዘተ. ተደምረው ኢትዮጵያን ታላቅ፣ የበለጸገችና የተከበረች ሊያደርጓት እንደሚችሉ እናስብ፡፡ ኢትዮጵያ የእነዚህ ሁሉ ድምር መሆኗን እናስብ፡፡ ከድምሩም በላይ መሆኗንም እናስብ፡፡ ደመራውን እያሳየን ለልጆቻችን ከሃይማኖታዊና ባህላዊ ትርጉሙ በተጨማሪ “እኛ ኢትዮጵያውያን ከተደመርን እንደ ደመራው ብርቱ እንሆናለን፤ እንደደመራው ከፍ ብለን እናበራለን” በሏቸው፡፡
መልካም የመስቀል በዓል ይሁን፡፡
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
መስከረም 16፣ 2017 ዓ.ም
ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል:: ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት
አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
Tel: 0913858561
ልዩ መረጃ‼️
እየሰነበተ ሳይሆን እየተሰናበተ ነው
ራሱን የአማራ ፋኖ በወሎ አሳምነው ኮር እሸት ክፍለጦር ዋና አዛዥ ብሎ የሚጠራው የጽንፈኛው ቀንደኛ ሠማኝ አማረ እስከወዲያኛው በጀግናዉ የመከላከያ ሰራዊት እስከነ 8 አጃቢዎቹ ተሸኝቷል። ከሞት የተረፈዉ በአካባቢዉ የሚገኘዉ ጽንፈኛ ቡድንም ሞት ቀርቦት መዉጫና መግቢያዉ ጠፍቶበት እየተቅበዘበዘ እንደሆነ ከአካባቢው ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል።
መስከረም 16/2017 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የ2017 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በሠላም እንዲከበር የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባቸው የሚታወቅ ሲሆን መስከረም 16 ቀን 2017 ዓ/ም ከረፋዱ 5:00 ሰአት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
በዚህም መሠረት ፦
• ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ላይ
• ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና
• ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ
• ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ አጠገብ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር ላይ)
• ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት ላይ
• ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ
• ከራስ ሆቴል ወደ ስታድዮም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል ላይ
• ከሃራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ
• ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ
• ከዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሼል አጠገብ እንዲሁም
• ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወሰደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ ከመስከረም 16 ቀን 2017 ዓ/ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ መንገድ የሚዘጋ ሲሆን በተጨማሪም በተገለፁት መስመሮች ላይ ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ይሁን ለረዥም ጊዜ ማቆም የተከለከለ መሆኑን አሽከርካሪዎች ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን በመጠቀምና የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚያሳይዋቸው መንገድ በመጓዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን ያቀርባል።
በአሉ ያለ አንዳች የፀጥታ ስጋት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጎ ወደ ስራ መግባቱን ያስታወሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በዓሉ ኃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር እና የበዓሉ ታዳሚዎች ሠላምና ደህንነት እንዲጠበቅ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጿል።
ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በ011-1-11-01-11 እንዲሁም በ991 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፥ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራውን የህወሓት ቡድን አስጠነቀቁ።
ፕሬዜዳንቱ በማስጠንቀቂያቸው „ ቡድን „ ሲሉ የጠሩት ሃይል የወረዳና የከተማ የህዝብ ምክር ቤቶች ለመረበሽ እየሄደበት ያለው ርቀትና በማድረግ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ ማቆም አለበት ብለዋል።
መስከረም 14/2017 ዓ.ም በፕሬዜዳንቱ ፊርማ ተፈርሞ ለሁሉም የወረዳና የከተማ ም/ቤቶች የተፃፈው የማስጠንቀቅያ ደብዳቤ „ የህዝብ ምክር ቤቶች የትግራይ ጊዚያዊ መንግስትና የህዝቡ አካል እንጂ የህወሓት መዋቅር አለመሆናቸው አውቆ ‚ ቡድኑ ‚ የራሱ መሳሪያ ለማድረግ እያካሄደ ያለውን መሯሯጥና ውንብድና ማቆም አለበት „ ይላል።
ስለሆነም ምክር ቤቶቹ የመንግስትና የህዝብ መዋቅር መሆናቸው በማመን ‚ ቡድኑ‘ ምክር ቤቶቹ በመጠቀም ያልደገፉትንና ሃሳቡ ያልተቀበሉት የመንግስት ሹመኞች ጥላሸት ለመቀባትና ከሃላፊነት ለማውረድ የሚያደርገው ጥረት መቆም አለበት ሲል አስጠንቅቋል።
ምክር ቤቶቹም ይህንን የመንግሰትና የፓለቲካ ድርጅት የሚቀላቅል ህገ-ወጥ ጣልቃ ገብነት ማውገዝ አለባቸው ብሏል።
„ ይህ ሳይሆን ከቀረ ግን ህግና ስርዓት ለማስከበር ሲባል ወደ ህጋዊ ተጠያቂነት መሸጋገር የግድ ይሆናል „ በማለት አክለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት ከቀናት በፊት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ያወጣውን የአቋም መግለጫ የሚቃወም መግለጫ አውጥቷል።
በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው ህወሓት መስከረም 14/2017 ዓ.ም ያወጣው ባለ 4 ነጥብ የተቋውሞ መግለጫ ፤ „ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ጊዚያዊ ስራዎች ለመስራት መቋቋሙ ተዘንግቶ ከተቀመጠለት የቆይታ የጊዜ ሰሌዳ በላይ እንዲቆይና ራሱን ወደ ተሟላ የመንግስት ሃላፊነት ለመለወጥ የሚያደርገው ጥረት ፀረ ዴሞክራሲና ኢ-ህገመንግስታዊ ነው „ ብሏል።
ምንም እንኳን „ ኢ-ህገመንግስታዊ „ ብሎ ቢገልጽም የአገር ወይም የክልሉ ህገ-መንግስት አንቀፆችን አላጣቀሰም።
የእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ቡድን „ ጊዚያዊ አስተዳደሩ የተሰጠው ተልእኮ ወደ ጎን በመተው ህወሓት ለማፍረስ ፣ ሰራዊት ለማዘዝና የመንግስትና ህዝብ ሃብት በመጠቀም የትግራይ ህዝብ አንድነት ለመበተን እየሄደበት ያለውን የተሳሳተ መንገድ ሊያቆም ይገባል „ ሲል አሳስቧል።
የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት ለማስጀመር የቅድመ ምዝገባና ማረጋገጫ ሂደት ተጀመረ
ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመት ተግባራዊ ለማድረግ ያቀደችውን የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት አለማቀፍ ተቀባይነት እንዲኖረው ለማስቻል ያለመ ምክክር ከአለማቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተካሂዷል።በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የተመራ ልዑክ በካናዳ ሞንትሪያል ከአለማቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጁዋን ካርሎስ ሳላዛር ጋር በመገናኘት ምክክር አድርገዋል። በዚህ ወቅትም ዋና ዳይሬክተሯ ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ዘርፍ የዳበረ ልምድ ያላትና አለምን በአገልግሎት እያስተሳሰረ ያለ ግዙፍ የአየርመንገድ ባለቤት መሆኗን አስታውሰዋል።አለማቀፉ የአቪዬሽን ድርጅት ከጉዞ ሰነድ የደህንነት ስራዎች ጋር በተያያዘ እያደረገ ላለው ድጋፍ ዋና ዳይሬክተሯ ምስጋና አቅርበዋል።ድርጅቱ በቀጣይም ኢትዮጵያ ወደ ኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት ስርዓት በምታደርገው የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠናን ጨምሮ ልዩ ልዩ ድጋፎች እንዲያደርግ ወ/ሮ ሰላማዊት ጠይቀዋል።
ዋና ዳይሬክተር ጁዋን ካርሎስ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ወደ ኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት ስርዓት ለመግባት ያሳለፈችውን ውሳኔ በማድነቅ በቀጣይ ተቋማቸው የማይቋረጥ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
ልዑኩ ከዚህ በተጨማሪ በየብስ የድንበር ቁጥጥር ላይ ተግባራዊ የሚደረገው ቴክኖሎጂ ከአለማቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ደረጃ ጋር የተጣጣመ መሆኑን የማረጋገጥ ምክክር ከሚመለከታቸው የተቋሙ ሃላፊዎች ጋር ያካሄደ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም ተመሳሳይ ምክክሮች እንደሚካሄዱ ተጠቁሟል።
ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመት የኤሌክትሪክ ፓስፖርት ስርዓት እንድትገባ ለማድረግ የዝግጅት ስራ እየተጠናቀቀ ይገኛል።
ደብረጺዮን ገብረሚካኤል፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጀነራል ጻድቃን ገብረተንሳይን “ሥልጣን ለመጠቅለል” እና “የቆየ ቂማቸውን ለመወጣት” ይፈልጋሉ በማለት ቅዳሜ’ለት መቀሌ ውስጥ በተካሄደ ሕዝናዊ ስብሰባ ላይ ወቅሰዋል።
ደብረጺዮን፣ በጦርነቱ ወቅት የትግራይ ተዋጊዎች አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በደረሱ ጊዜ “እኔ ድርድር ያስፈልጋል” ስል፣ ጻድቃን “ከማን ጋር ነው የምንደራደረው? ውጊያው አልቋል” በማለት ይናገር ነበር ብለዋል። የጊዜያዊ አስተዳደሩ ባለሥልጣናት ሕወሓት ሰላም እንደማይፈልግ አድርገው ያቀርባሉ ያሉት ደብረጺዮን፣ ይህ ግን የተሳሳተ ፍረጃ ነው በማለት ተናግረዋል። በደቡባዊ ዞን በተካሄደ አንድ መድረክ ላይ ጀነራል ጻድቃን እሱ እና እነ ጌታቸው ሰላም ፈላጊ፤ ባንጻሩ እኛ የጦርነት አቀንቃኞች እንደኾንን አድርገው ተናግረዋል በማለትም ደብረጺዮን ወቅሰዋል። ደብረጺዮን አያይዘውም፣ እነ ጌታቸው ተኩስ አቁም እንዲፈራረሙ ፕሪቶሪያ ሲላኩ፣ ከተሠጣቸው ሥልጣን ውጭ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የሚያቋቁም ስምምነት ተፈራርመዋል በማለት ከሰዋል።
የመስቀል ስር ቁማርተኞች መስቀሉን አውልቁት!!
በአማራ ክልል እራሱን ፋኖ በማለት የሚጠራው የጽንፈኛና የመሃይም ስብስብ ትምህርት ቤቶችን አዘግተው ጭፈራ ቤት አድርገውታል ፊደል ጠል የሆነው የጽንፈኛው ስብስብ ሁለት መምህራንን ገድለዋል 😓
ይህ የብልጽግና ቢሮ አልያም የአመራሮች ቤት አይደለም ትምህርት ቤት ነው ። የቀጣይ ትውልድ እድል ላይ ቆመው የሚጨፍሩ በቁም የሞቱ ናቸው ። ለዕውቀት ያልታደለ ጭንቅላት ለተንኮል ተወዳዳሪ የለውምና የመሃይሞች ስብስብ መጨረሻው ትውልድን በሚቀርጽ ትምህርት ቤት አዘግቶ አስተማሪ ገሎ ዳንኪራ መምታት ነው::