natnaelmekonnen21 | Неотсортированное

Telegram-канал natnaelmekonnen21 - Natnael Mekonnen

181663

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7 Facebook.com/natnaelmekonnen.et Instagram.com/natnaelmekonnen21

Подписаться на канал

Natnael Mekonnen

ስንቅ ሬስቶራንት በዱባይ https://vm.tiktok.com/ZGe71ay4C/

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኮኖሚው ማሻሻያ ተግባራዊ ከመደረጉ ጋር በተያያዘ ችግር ለመፍጠር የሞሞክሩትን የማረም ሥራ እየተሠራ ነው፡፡


በከተማ ደረጃ ፋይናንስ ቢሮ፣ ንግድ ቢሮ እና ገቢዎች ቢሮን ያካተተ አደረጃጀት እንዲዋቀር ተደርጎ ቁጥጥርና ክትትል እያደረገ የሚገኝ ሲሆን አደረጃጀቱ ከተማና በክፍለ ከተማ ደረጃ እንዲዋቀር ተደርጓል፡፡ በተደረገው ክትትልም በአትክልት እና ፍራፍሬ እንዲሁም በሰብል ምርቶች ላይ ከባለፉት ቀናት አንጻር የጎላ የዋጋ ልዩነት በዛሬው ዕለት በተሰበሰበ የገበያ መረጃ ላይ ያልታየና የተረጋጋ መሆኑ ታውቋል፡፡ የሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ የሚገባው የሩዝ ምርት ገባያው ላይ በሚፈለገው አግባብ እየቀረበ አለመሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይሄንንም ለማስተካከል በቀጣይ ቀናት አስፈላጊው ሁሉ ይከናወናል፡፡

የጅምላ እህል አቅራቢዎች በተለይም በመሳለሚያ ገበያ አካባቢ ምርት የመያዝ አዝማማያ የነበረ ቢሆንም በተወሰደው አስተዳደራዊ ርምጃ ወደ መደበኛ ግብይት እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ ከውጭ የሚገባው ዘይት ትናንት በነበረው ገበያ በሚፈለገው መልኩ በመርካቶ ገበያ ላይ አልቀረበም፡፡ በዚህ ላይ ክትትል እንዲደረግ ተወስኗል፡፡ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃ ሻጮች በተለይም ከሊፋ ህንጻ አካባቢ የዋጋ ጭማሪ እየተስተዋለ መሆኑ የታየ ሲሆን ወደ ትክክለኛ መሥመር እንዲገቡ እርማት እተሰጠ ነው፡፡

በቀጣይም አጋጣሚውን በመጠቀም ሕገ ወጥ ተግባር በሚያከናውኑት ላይ አስፈላጊ ክትትልና ቁጥጥር እንዲደረግ አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሠራ ነው፡፡

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ሰሞኑ በዶክተር ደብረፅዮን እና በጌታቸው መካከል የነበረው የሚድያ ጦርነት አንኳር አንኳር ነጥቦች
ዶክተር ደብፅዮን፡-
* አሁን ጉባኤ ማካሄድ የማይፈልግ፣ ከተጠያቂነት ለማምለጥ እና የፓርቲው ችግሮች እንዲፈቱም የማይፈልግም ነው።

ጌታቸው፡-
* ጉባኤ አታካሂዱ የሚል ማንም የለም፡ አሁን ያለው ጥድፊያ ግን ስልጣንን ለመቆጣጠር እና ከስልጣን ከለቀቁ ከተጠያቂነት ለማምለጥ ነው።
###

ዶ/ር ደብረጽዮን:
* የባለፈው መድረክ ግልፅ፣ አሳታፊ እና ዲሞክራሲያዊ ነበር። ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተገኝተዋል። ለመገምገምም ጊዜ ወስደናል።

ጌታቸው፡-
እስካሁን ድረስ እኛ የሚድን ምንም ስራ አልተሰራም. በእኔ እምነት፡- የድብብቆሽ ሃሳብ የሌለበት ጉባኤ፡ እና ብዙ ክፍተት ያሉት ሂደት ነበር።
###

ዶ/ር ደብረጽዮን:
በውጭ መግለጫ እየሰጡ ያሉት፡ ዴሞክራሲያዊ አደረጃጀት ስተዋል፡ በተቃውሞ ወጥተው በድምፅ ተሸንፈዋል፡ የሚናገሩት መግለጫና ስም ማጥፋት ነው።

ጌታቸው፡-
በባለፈው የከፍተኛ ካድሬዎች መድረክ ላይን በፓርቲው ሊቀ መንበር ሲጠቃለል “ህዝብ የመረጠውን መንግስት የመበተን ስልጣን አልነበራችሁም” ሲሉ ተደምጠዋል።በዚህ ላይ የሃሳብ ልዩነት እንዳለኝ ስናገር ልስተናግድ አልቻልኩም።ስለዚህ ሃሳቤ ወደ ሚዲያ መውጣት ነበረበት።

ዶ/ር ደብረጽዮን:
የፕሪቶሪያ ስምምነት ጦርነቱን አቁሞ አንፃራዊ ሰላም አምጥቶልናል።

ጌታቸው፡-
በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የተፈጠረው እድል ባክኗል; ተአምር የሰራ የትግራይ ህዝብ እና ጀግናው ሰራዊት ድሉን ተበልቷል።ይህ የህወሓት የፖለቲካ ድክመት ውጤት ነው።

ዶ/ር ደብረጽዮን:
ችግሮቹን ለመፍታት ከፌዴራል መንግስት ጋር እየተነጋገርን ነው።

ጌታቸው፡-
አዲስ አበባ ላይ የተስማሙት እና እዚህ የምንነገረው እውነት የተለያየ ነው።
ዶ/ር ደብረጽዮን:
በአዲሱ አዋጅ አንመዘገብም; አይመለከተንም ጥያቄያችንን ለምርጫ ቦርድ አቅርበናል።

ጌታቸው፡-
ህወሓት ያስገባው ደብዳቤ በአዲሱ አዋጅ ላይ የተመሰረተ ነው። ይህንን ካድሬው ማወቅ አለበት።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

"ስማችን እውነት ነው,ስራችንም የእውነት ነው"

❇️ከዚህ በፊት የተመረጡ ቦታዎች ላይ ጥንቅቅ አድርገን እንዳስረከብናቸው አሁንም እጅግ ውብ ለኑሮ መቹ በከተማችን የተመረጡ ቦታዎች

❇️በሳርቤት እና በ ቦሌ ቅድመ ክፋያ 770 ( ሰባትመቶ ሰባ ) ሽህ ጀምሮ በመሸጥ እንገኛለን

✅ 65.7 , 86 , 90 ካሬ ባለ 1 መኝታ
✅ 98 , 100 , 114 ካሬ ባለ 2 መኝታ
✅ 140 , 152 , 212 ካሬ ባለ 3 መኝታ

❇️የቤት ባለቤት ከመሆን ባለፈ፣በመሀል አዲስ አበባ የምንገነባቸው ቅነጡ ቤቶቻችን ኢንቨስተር ያደርጉታል !
✅ምስክሮቻችን ከዚህ በፊት ሰርተን ያስርከብናቸው ደንበኞቻችን::

❇️ወለል ውፍረት 25ሲ.ሜ ኮንክሪት አስላብ።
✅ከወለል ወለል እርዝማኔ 3.2 ሜትር
❇️የውጭ በሮቻችን 100ኪሎ የሚመዝኑ፣ከኮንክሪት እና ከብርት የሚስሩ፣ድመፁ የማያስተላልፍ ፣6 የተለያዩ ቦታዎች የሚቆልፍ።


✅Reality real estate✅
🚧 3B+G+17 አፓርታማ
🚘 sufficient parking space
🏋️gymnasium and spa
👉🏻17 th floor club house
👉🏻under ground water and backup generator

💰 10% ቅድመ ክፍያ

What makes Reality real estate different
- Affordable price
- Easy payment schedule
- Prime Location
- Reputed company
- Early Delivery
የድርጅቱ የሽያጭ አማካሪ
☎️0976 20 68 68
0951 69 14 66

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የውጭ ምንዛሪ የማግኘት መብት ያላቸውና የሚሟሉ ልዩ ልዩ መስፈርቶች‼️

1👉 የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት የተፈቀደላቸው የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ከኢትዮጵያ ውጭ የሚጓዙ ኢትዮጵያዊውያን ወይም በአገሪቱ ውስጥ የሚኖር የውጭ ዜጎች ናቸው።

2👉 ምንዛሪ ለማግኘት የሚፈልጉ ግለሰቦች ለበዓል ፣ ለትምህርት ፣ ለህክምና ጉዞዎች እና ሌሎች የግል ጉዳዮች እንደሚጓዙ የሚያሳይ ፓስፖርት፣ ሕጋዊ የመግቢያ ቪዛ እና የአየር ትኬት የማቅረብ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

3👉 ተጓዦች ከምንዛሪ ቢሮዎች እስከ 5 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወይም የዚህ አቻ የሆነ የሌላ አገር ገንዘብ በጥሬ ወይም በክፍያ መፈጸሚያ ካርድ (debit card) አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ።

4👉 የውጭ ምንዛሪ የባንክ ሂሳብ ያላቸው ተጓዦች እስከ 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ድረስ ማግኘት ተፈቅዶላቸዋል።

5👉 በብሔራዊ ባንክ ካልተፈቀደ በስተቀር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነዋሪ በአንድ ጉዞ ላይ ከ10,000 የአሜሪካን ዶላር ወይም ተመጣጣኝ ገንዘብ በካሽ መያዝ አይችልም።

6👉 ለንግድ የሚጓዙ ግለሰቦችም የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ይችላሉ።

7👉 የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ ፓስፖርት እና የአየር ትኬት ለሚያቀርቡ ለንግድ ድርጅት ተወካዮች የውጭ ምንዛሪ መሸጥ እንዲችሉ ተፈቅዷል። እነዚሁ ቢሮዎች ፦
- ለንግድ ድርጅቶች፣
- ለበጎ አድራጎት ተቋማት
- ለሃይማኖት ማኅበራት፣
- ለንግድ ትርኢቶች፣
- ለቱሪዝም
- ለባህል እና ለስፖርቶች አዘጋጆች የውጭ ምንዛሪ መሸጥ ይችላሉ።

8👉 የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ለመንግሥት ተጓዦች ለምግብ፣ ለማረፊያ እና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎች ከ10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወይም ተመጣጣኝ ገንዘብ የማይበልጥ የውጭ ምንዛሬ ሊሸጡ ይችላሉ።

9👉 ነዋሪ ላልሆኑ የውጭ አገር ዜጎች እና ቱሪስቶች ብርን ወደ ውጭ ምንዛሬ ሊለውጡ የሚችሉበት አሠራርም አለ። ፓስፖርት፣ ትክክለኛ ቪዛ እና የአየር ትኬት የሚያቀርቡ ሰዎች ያለማስረጃ እስከ 500 የአሜሪካን ዶላር መለወጥ ይችላሉ። ከ500 ዶላር በላይ መለወጥ የሚፈልጉ ከሆነ ፓስፖርት፣ ሕጋዊ ቪዛ፣ የአየር ትኬት እና ተመጣጣኝ የሆነው የውጭ ምንዛሪ በሕጋዊ መንገድ ወደ አገር ውስጥ ገንዘብ መቀየሩን የሚያሳይ የተረጋገጠ የባንክ ማስረጃ ማቅርብ ይጠበቅባቸዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የሲዳማ ክልል ውሃ ማዕድን ኢነርጂ ቢሮ በ2016 ብጀት አመት በክልሉ በአጠቃላይ ከ269 በላይ የውሃ ተቋማት መገንባቱን ተገለጸ።

በዚህ ምክንያት የክልሉን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን  60.4% ማድረሱ ተችሏል። በአማራጭ እኔርጅ ዘርፍም ከ115ሺ በላይ ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ እቅድ ተይዘው  96ሺ ለሚሆን የማህበረሰብ ክፍል ተደራሽ ተደርጓል።

ባለፉት 3 ዓመት ውስጥ ከ22 በላይ የመስኖ አውታሮች የተገነቡ ሲሆን ይህም በወቅት ሳይገደብ በክልሉ ጠንካራ የሆነ የግብርና ምርታማነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው ተብሏል።

ለዚህም ዓመቱን ሙሉ ምርታማነት ለሚያረጋግጠው የመስኖ ፕሮጀክቶች በዓመት ከ340 ሚሊዮን በላይ ገንዘብ የሚበጀት ሲሆን እያንዳንዱ ፕሮጀክት ከ150 እስከ 200 ሄክታር ማልማት የሚያስችል ነው።

በአጠቃልይ በክልሉ ከ4500 ሄ/ር በላይ የሚያለማ የዘመናዊ መስኖ ፕሮጀክቶች የተገነቡ ሲሆን በቀጣይ አመታትም ከፍተኛ ምርታማነት በክልሉ የሚያረጋግጥ ይሆናል ተብሎም ይጠበቃል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በሲዳማ ክልል ባጋጠመው የመሬት መንሸራተትና ደራሽ ውኃ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 11 ደረሰ

በሲዳማ ክልል ባጋጠመው የመሬት መንሸራተትና ደራሽ ውኃ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 11 መድረሱን የክልሉ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

በክልሉ ወንሾ ወረዳ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 9 መድረሱንና 6 ተጨማሪ ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በይርጋለም ሆስፒታል በሕክምና ላይ መሆናቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል።

በተመሳሳይ በክልሉ ቡራ ወረዳ በደራሽ ውኃ የ2 ህጻናት ሕይወት ማለፉን ኮሚሽኑ ገልጾ፤ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክት አስተላልፏል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸው፤ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን ተመኝተዋል።

የክልሉ መንግሥት በዜጎች ላይ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ እንዲሁም ተጎጂዎች ሕክምና እና ድጋፍ እንዲያገኙ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ ነው ብለዋል።

በሌሎች አካባቢዎችም መሰል ችግሮች ሊፈጠሩ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ርዕሰ መስተዳድሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የክረምት ልዩ ስልጠና!
**************

የክረምት ልዩ የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና የመክፈቻ ስነ-ስርዓት በበይነመረብ ተካሄዷል፡፡

ስልጠናውን 1743 ሰልጣኞት በበይነ መረብ የተሰጠውን ማብራሪያ መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው የመክፈቻ መርሐግብሩን ተከታትሏል፡፡

ስልጠናው ለትምህርት ቤት አመራሮች ለአስር ቀናት እንዲሁም ለመምህራን ለሃያ ቀናት ይሰጣል፡፡

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 405 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2016 የበጀት ዓመት 405 ቢሊዮን ብር (7 ነጥብ 02 ቢሊዮን ዶላር) ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።

የአየር መንገዱ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው የአየር መንገዱን የ2016 አፈጻጸም የተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

እንደ ዋና ስራ አስፈጻሚው ገለጻ ከተገኘው 7 ነጥብ 02 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ውስጥ ከመንገደኞች ማጓጓዝ 5 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም ከጭነት ደግሞ 1 ነጥብ 65 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል።

በ2016 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ አየር መንገድ 17 ነጥብ 1 ሚሊዮን መንገደኞችን ያጓጓዘ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 13 ነጥብ 4 ሚሊዮን የሚሆኑት አለማቀፍ እንዲሁም 3 ነጥብ 7 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ የሀገር ውጥ ተጓዦች መሆናቸውን ዋና ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።

577 ሺሕ 746 የበረራ ሰዓትን የበረረ ሲሆን ባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው የበረራ ሰዓት የ19 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የደንበኞቹን ፍላጎት ለሟሟላት በበጀት ዓመቱ የበረራ መዳረሻዎችን አስፍቶ በአለም አቀፍ ደረጃ 5 መዳረሻዎች እንዲሁም በሀገር ውስጥ ወደ 3 ከተሞች በረራ መጀመሩን አቶ መስፍን ጠቁመዋል።

በአጠቃላይ የአየር መንገዱን መዳረሻ ወደ 139 ከፍ ሲያደርግ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎችን 22 ማድረሱን አስታውቀዋል።

አየር መንገዱ 754 ሺሕ 681 ቶን ካርጎ ሲያጓጉዝ ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ6 በመቶ ብልጫ ማሳዬቱን በመግጫው ተጠቅሷል።

አገልግሎትን በማስፋፋትና በማዘመን በኩልም የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸው የተገለፀ ሲሆን የጥገና፣ የአየር ማረፊያ ማስፋፊያ፣ የአውሮፕላን ግዥና ሌሎች ስራዎች መሰራታቸውን ዋና ስራ አስፈጻሚው አንስተዋል።

አየር መንዱድ በቀጣይ 125 አውሮፕላኖችን ማዘዙን የጠቀሱት አቶ መስፍን የቦሌ አለማቀፍ አየር ማረፊያም እየተጨናነቀ በመሆኑ በቢሾፍቱ አዲስ አየር ማረፊያ በ18 ወራት ውስጥ ገንብቶ ለማጠናቀቅ ስራ ተጀምሯል ብለዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

Exchange Rate Applicable for, Monday, 29 July 2024.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻያ አስመልክቶ የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ : https://youtu.be/Sa0gYs0KVRg?si=odwfVznBSsrBIHTB

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

"ስማችን እውነት ነው,ስራችንም የእውነት ነው"

❇️ከዚህ በፊት የተመረጡ ቦታዎች ላይ ጥንቅቅ አድርገን እንዳስረከብናቸው አሁንም እጅግ ውብ ለኑሮ መቹ በከተማችን የተመረጡ ቦታዎች

❇️በሳርቤት እና በ ቦሌ ቅድመ ክፋያ 770 ( ሰባትመቶ ሰባ ) ሽህ ጀምሮ በመሸጥ እንገኛለን

✅ 65.7 , 86 , 90 ካሬ ባለ 1 መኝታ
✅ 98 , 100 , 114 ካሬ ባለ 2 መኝታ
✅ 140 , 152 , 212 ካሬ ባለ 3 መኝታ

❇️የቤት ባለቤት ከመሆን ባለፈ፣በመሀል አዲስ አበባ የምንገነባቸው ቅነጡ ቤቶቻችን ኢንቨስተር ያደርጉታል !
✅ምስክሮቻችን ከዚህ በፊት ሰርተን ያስርከብናቸው ደንበኞቻችን::

❇️ወለል ውፍረት 25ሲ.ሜ ኮንክሪት አስላብ።
✅ከወለል ወለል እርዝማኔ 3.2 ሜትር
❇️የውጭ በሮቻችን 100ኪሎ የሚመዝኑ፣ከኮንክሪት እና ከብርት የሚስሩ፣ድመፁ የማያስተላልፍ ፣6 የተለያዩ ቦታዎች የሚቆልፍ።


✅Reality real estate✅
🚧 3B+G+17 አፓርታማ
🚘 sufficient parking space
🏋️gymnasium and spa
👉🏻17 th floor club house
👉🏻under ground water and backup generator

💰 10% ቅድመ ክፍያ

What makes Reality real estate different
- Affordable price
- Easy payment schedule
- Prime Location
- Reputed company
- Early Delivery
የድርጅቱ የሽያጭ አማካሪ
☎️0976 20 68 68
0951 69 14 66

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ኢትዮጵያዊነት ሰውነት ሲሆን እንዲህ ነው!!! @yarednegu 🙌

አርቲስት ያሬድ ነጉ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ ምክኒያት የደረሰውን አደጋ ለማቋቋም እየተደረገ ያለውን ጥረት ለመደገፍ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ጎፋ ደርሷል።

ያሬድ ጓደኞቹን በማስተባበርም የተለያዪ ለድጋፍ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን እና ለምግብነት የሚውሉ ግብአቶችን በአይሱዙ አስጭኖ የአደጋው ስፍራ ድረስ በመገኘት በአስክሬን ፍለጋ ስራ ላይም እንደተሰማራ በስፍራው የተገኙ ምንጮች ገልጸውልናል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

„የኤርትራ ክስ የኢትዮጵያን አየር መንገድ ስም የማጥፋት ሥራ በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለውም“ - አቶ መስፍን ጣሰው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ ከኤርትራ ሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን የቀረበበትን ክስ “የአየር መንገዱን ስም የማጥፋት ሥራ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም” ሲል ውድቅ አደረገ።የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ፤ የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን በላከው ደብዳቤ ይህንን አጥፍታችኋል የሚል ምንም ዓይነት ማብራሪያ አልነበረውም ብለዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም ምንድነው? ጥቅም እና ጉዳቶቹስ?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መንግሥት የአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ተመን በገበያ ሥርዓት እንዲመራ መወሰኑን ተከትሎ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ከዛሬ ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም. ጀምሮ መሻሻሉን አስታውቋል።

ብሔራዊ ባንክ በመግለጫው የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ማሻሻያው በአዲሱ የውጭ ምንዛሪ መመሪያ መሠረት የሚተገበር ይሆናል ብሏል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን በባንኮች እና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወስንበት የገበያ ሥርዓት ይሸጋገራል ያለ ሲሆን፤ በዚህ ውስጥ የባንኩ ሚና ገበያውን ማረጋጋት ላይ ያተኮረ እንደሚሆንም ተገልጿል።

ውሳኔው የብርን የመግዛት አቅም የሚያዳክም ነው።

ይህንን ውሳኔ ተከትሎ መንግሥታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአሜሪካ ዶላር መግዣ እና መሸጫ ዋጋ ላይ የ17 ብር ጭማሪ አደርጓል።

ባለፈው ሳምንት አርብ ባንኩ አንዱን የአሜሪካ ዶላር ሲሸጥ የነበረው 58.63 ብር የነበረ ሲሆን ዛሬ ወደ 76.23 ብር ከፍ ብሏል።

📌 ለመሆኑ የገንዘብ መግዛት አቅም መዳከም ምንድን ነው?

አንድ አገር መገበያያ ገንዘብ ከዋና ዋና የውጭ አገራት ገንዘቦች በተለይም ከአሜሪካን ዶላር አንጻር የነበረው ዋጋ ሲቀንስ የመግዛት አቅሙ ቀንሷል ይባላል።

ለምሳሌ ያህል አንድ ዶላር ይመነዘርበት ከነበረበት 57 ብር ወደ በ76 ብር መመንዘር ከጀመረ የብር መግዛት አቅም ተዳክሟል ይባላል።

በርካታ አገራት ፍላጎት እና አቅርቦትን ለመቆጣጠር የመገበያያ ገንዘባቸውን ያዳክማሉ።

📌 የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም ጥቅሞች

የገንዘብ የመግዛት አቅም ሦስት ዋና ዋና ጥቅሞች አሉት።

የወጪ ንግድን ያሳድጋል

በወጪ ንግድ እና ገቢ ንግድ መካከል ያለውን ልዩነት ያጠባል

አገራት የገንዘብ የመግዛት አቅምን የሚቀንሱበት ዋነኛው ምክንያት የወጪ እና ገቢ ንግዳቸውን መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ በሚል ነው።

የገንዘብ የመግዛት አቅምን በመቀነስ ለወጪ ንግድ ሚቀርቡ ምርቶችን ዋጋ መቀነስ የሚቻል ሲሆን፣ ይህም በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪነትን ያሳድጋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ዋጋ ይጨምራል። ይህም ተጠቃሚዎች ከውጭ ከሚገቡ ምርቶች ይልቅ የአገር ውስጥ ምርቶችን እንዲገዙ እንደሚገፋፋ ይታመናል።

በአገር ውስጥ ያለው የገንዘብ ፍሰት መጨመር ደግሞ የአንድን አገር ኢኮኖሚ የሚያነቃቃ እንደሚሆን የምጣኔ ሐብት ባለሙያዎች ይስማማሉ።

በዋጋ መዳከም ምንያት በሚፈጠር የዋጋ መርከስ ምክንያት የወጪ ንግድ ሲጨመር ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች ደግሞ በተቃራኒው ዋጋቸው ስለሚጨምር፤ ለገቢ ምርቶች ያለው ፍላጎት ይቀንሳል።

የዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ደግሞ በገቢ እና በወጪ ንግድ መካከል ያለውን ልዩነት ያጠባል።

አገራት ያለባቸው ውጭ ዕዳ ከፍተኛ ከሆነ እና እድገታቸውን ከተፈታተነ የገንዘብ የመግዛት አቅም ማዳከምን ሊተገብሩ ይችላሉ። የገንዘብ የመግዛት አቅምን መቀነስ በረዥም ጊዜ ዕዳቸውን የመክፈል አቅማቸውን ያሳድግላቸዋል።

ለምሳሌ ያህል አንድ አገር ባለባት የውጭ ዕዳ ምክንያት በየወሩ ሁለት ሚሊዮን ዶላር ወለድ የምትከፍል ከሆነ የአገሪቱን ገንዘብ የመግዛት አቅምን በመቀነስ የወለድ መጠኑን መቀነስ ይቻላል።

በዚህ አካሄድ ግን ከቦንድ ጋር ከተያያዙ ብድሮች ጋር ውጤታማ አይሆንም። ምክንያቱም የገንዘብ የመግዛት አቅም መቀነስ ይህን መሰሉን ብድር የመመለስ ዋጋን ይጨምረዋል።

📌 የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም ጎጂ ጎኖች

የገንዘብ የመግዛት አቅምን በጊዜ ሂደት የምርቶችን እና የአገልግሎቶችን ዋጋ ሊጨምር ይችላል። ዋጋ ጭማሪው ግን በገቢ ምርቶች ውድድር እና በፍላጎት መጠን ላይ ይወሰናል።

የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም የወጪ ንግድን በማሳደግ የአገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት (ጂዲፒ) እና ዋጋ ንረትን ይጨምራል። አምራቾች ከውጭ የሚያሰግቡት ጥሬ ዕቃ ዋጋው ስለሚጨምር የምርቶቻቸውን ዋጋ ለመጨመር ይገደዳሉ።

ዋናው ከገንዘብ የመግዛት አቅም ጋር መዳከም ጋር የሚያያዘው ጉዳይ የገበያ አለመረጋጋት ነው። የኢኮኖሚው አቅጣጫ በግልጽ ስለማይታወቅ በፍላጎት እና በአቅርቦት ላይ አለመረጋጋጥ ይፈጥራል። ይህም ኢኮኖሚያዊ ወድቀትን ሊያስከትል እንደሚችል ይታመናል።

📌 የገንዘብ የመግዛት አቅምን በማዳከም የሚታወቁ አገራት

ቻይና የአገር ውስጥ ጠቅላላ ምርትቷን ለማሳደግ የገንዘብ የመግዛት አቅምን አዳክማለች። ከዚያወዲህ በዓለም ንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጠሪ ለመሆን በቅታለች።

እአአ በ2016 የተደረገውን የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተከትሎ ገንዘቧን በተመለከተ ውሳኔ እንደምታስተላልፍ አስታውቃ ነበር።

ከአሜሪካ ዶላር አንጻር የቻይናው ዩዋን ያለውን አቅም ለማሳደግ የተያዘውን ዕቅድ ከግምት በማስገባት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቻይና ምርቶች ላይ ከፍተኛ ታሪፍ ጫኑ።

ግብፅ በ2016 (እአአ) መገበያያ ገንዘቧ ከዶላር አንጻር በ14 በመቶ እንዲዳከም አደረገች። ይህም የትይዩ ገበያውን እንቅስቃሴ ለመግታት ያለመ ነበር።

ጥቁር ገበያው ግን በግብፅ ፓውንድ እና በአሜሪካ ዶላር መካከል ያለውን የመግዛት አቅም ይበልጥ በማስፋት ምላሽ ሰጥቷል። በዚህም አገሪቱ ያሰበችውን ያህል ውጤት አግኝታለች ለማለት አይቻልም።

ከኢትዮጵያ አንጻርም ውሳኔው ምን ውጤት እንደሚያመጣ በሂደት የሚታይ ቢሆንም፣ በርካቶች አሁን ያለውን የሸቀጦች የዋጋ ውድነት ሊያባብሰው ይችላል የሚል ስጋት አላቸው።

ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት አገሪቱን ይህንን እርምጃ እንድትወስድ ለዓመታት ግፊት ሲያደርጉ ቢቆዩም ተቀባይነት ሳያገኝ ቆይቶ ነበር።

በጦርነት እና በዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ምክንያት በአገሪቱ ተፈጠረውን ውጭ ምንዛሪ እጥረት ችግር እንዲሁም ታይቶ በማይታወቅ የዋጋ ንረት የተዳከመውን ምጣኔ ሀብት ለመደገፍ መንግሥት የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ ነው።

ይህ የውጭ ምንዛሪ ግብይት በገበያ ሥርዓት እንዲተመን የሚያደርገው ውሳኔም የተከታታይ ማሻሻያዎቹ አንድ አካል ነው።

BBC

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች

ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተ‍እ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበ‍ኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።

ሚለየን ምንድነው?

የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ

🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።

🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።

🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።

🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።

🪄We Care

አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ

📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69

www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የዐለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት አስፍጻሚ ቦርድ ለኢትዮጵያ የአራት ዓመት የ3.4 ቢሊዮን ዶላር የተራዘመ ብድር አገልግሎት አቅርቦትን አጸደቀ

• የዐለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ቦርድ ለኢትዮጵያ የ2.556 ቢሊዮን SDR ወይም ወደ 3.4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚጠጋ የተራዘመ የብድር አገልግሎት አቅርቦትን አጽድቋል። ይህም ውሳኔ 766.75 ሚሊዮን SDR ወይም 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር አካባቢ የሚሆን ገንዘብ ክፍያ ወዲያውኑ እንዲለቀቅ የሚያስችል ይሆናል።

• ይህ የአራት ዓመት የፋይናንስ ፓኬጅ የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን መፋለሶችን ለመፍታት፣ የውጪ እዳ [አከፋፈል] ዘላቂነትን በመመለስ እንዲሁም ለላቀ አካታች ለሆነ እና በግል ዘርፉ ለሚመራ እድገት መሠረትን በመጣል የመንግሥትን ‘ሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ’ አጀንዳ የሚደግፍ ይሆናል።

• ይህ የተራዘመ የብድር አገልግሎት አቅርቦት ከልማት አጋሮች እና አበዳሪዎች የሚገኝ ተጨማሪ የውጪ የገንዘብ አቅርቦትን እንደሚያፋጥን ይጠበቃል።

ዋሺንግተን ዲሲ፤ ሐምሌ 22/2016፡ የዐለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት አስፈጻሚ ቦርድ ለኢትዮጵያ የሚሆንና መጠኑም 2.556 ቢሊዮን SDR (የኮታው 850% ወይም ወደ 3.4 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ) የሆነ፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን መፋለስን መፍታትን እና በግል ዘርፉ ለሚመራ እድገት መሠረት መጣልን አላማው ያደረገውን የመንግሥትን የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ አፈጻጸም የሚደግፍ የአራት ዓመት የተራዘመ የብድር አገልግሎት አቅርቦት (ECF)1 አጽድቋል።

የአስፈጻሚ ቦርዱ ውሳኔም ኢትዮጵያ ከባላንስ ኦፍ ፓይመንት ጋር የተያያዙ ፍላጎቶቿን እንድታሟላ የሚረዳትን እንዲሁም በጀቷን የሚደግፈውን የ766.75 ሚሊዮን SDR ወይም 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር አካባቢ የሚሆን ገንዘብ ክፍያ ወዲያውኑ እንዲለቀቅ የሚያስችል ይሆናል።
በአራት ዐመቱ የተራዘመ የብድር አገልግሎት አቅርቦት የሚደገፈው የመንግሥት የኢኮኖሚ ፕሮግራም የግል ዘርፉን እንቅስቃሴ የሚያነቃቃ ሁለገብ የፖሊሲ ፓኬጅን እንዲሁም የላቀ እና በይበልጥ አካታች የሆነ እድገትን ማምጣት ይቻል ዘንድ ኢኮኖሚውን ክፍት ማድረግን ኢላማው ያደረገ ነው። ማሻሻያው ተጋላጭ በሆኑ ቤተሰቦች/አባዎራዎች ላይ የሚኖረውን ተጽእኖ ለማለዘብ ይቻል ዘንድ የማህበራዊ ሴፍቲ ኔቶችን ማጠናከርም የመንግሥት የማሻሻያ ፕሮግራም አንድ ወሳኝ ክፍለአካል ነው።

ቁልፍ የሚባሉት ፖሊሲዎችም የሚከተሉትን ያካትታሉ፡ 1) ውጫዊ ኢሚዛናዊንትን ለመፍታት እና የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለማስታገስ በገበያ ወደሚወሰን የምንዛሪ ዋጋ መሄድ፤ 2) የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍን በማዘመን የዋጋ ግሽበትን መዋጋት፤ 3) የሀገር ውስጥ የገንዘብ ምንጮችን በማሰባብሰብ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ሕዝባዊ ወጪዎች ማዋል፤ 4) ከውጪ አበዳሪዎች ጋር የሚደረጉ ወቅታዊ የእዳ ሪስትረክቸሪንግ ስምምነቶችን በመፈጸም ጭምር የእዳ አከፋፈል ዘላቂነትን መመለስ እንዲሁም 5) ወሳኝ የሆኑ የማክሮ ፋይናንሺያል ተጋላጭነቶችን ለመቀነስ የመንግሥት ኢንተርፕራይዞችን የገንዘብ አቋም ማጠናከር። ፕሮግራሙ ከልማት አጋሮች የሚገኝ ተጨማሪ የገንዘብ አቅርቦትን በማፋጠን እንዲሁም በመካሄድ ላይ ያለው የእዳ ሪስትረክቸሪንግ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የሚያደርግ ማዕቀፍ በመስጠት ረገድ እንደሚያግዝ ይጠበቃል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ለበርካታ ዐሥርት ዓመታት ፈጣን እድገት እና የኑሮ መሻሻል ከተመዘገበ በኋላ የተከሰቱት ተከታታይ ችግሮች ከባድ የኢኮኖሚ ጫናዎችን በመፍጠራቸው በመንግሥት ኢንቨስትመንት የሚመራው የእድገት ሞዴል ለውጥ የማያመጣበት ወሰን ላይ ደርሷል። የሀገሪቱ መንግሥትም ማሻሻያ የማድረግን አስቸኳይነት በመገንዘብ፤ የሀገሪቱን የባላንስ ኦፍ ፔይመንት ፍላጎቶች ለማሟላት፣ በጀቱን ለመደገፍ እንዲሁም የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳን ለማስፈጸም ይቻል ዘንድ የገንዘብ ድርጅቱ የአራት ዓመት የተራዘመ የብድር አገልግሎት አቅርቦት እንዲያደርግለት ጠይቋል።

የፕሮግራም አጭር መግለጫ

የኢኮኖሚ ፕሮግራሙ የግል ዘርፍ እንቅስቃሴን ለማነቃቃት የሚሆን ሁለገብ የፖሊሲ ፓኬጅ ማዘጋጀትን እንዲሁም የላቀ እና ይበልጥ አካታች የሆነ እድገት ለማምጣት ሲባል ኢኮኖሚውን በይበልጥ ክፍት ማድረግን ኢላማው ያደረገ ነው። ማሻሻያው ተጋላጭ በሆኑ ቤተሰቦች/አባዎራዎች ላይ የሚኖረውን ተጽእኖ ለማለዘብ ይቻል ዘንድ የማህበራዊ ሴፍቲ ኔቶችን ማጠናከርም የመንግሥት የማሻሻያ ፕሮግራም አንድ ወሳኝ ክፍለአካል ነው። ቁልፍ ፖሊሲዎችም የሚከተሉትን ያካትታሉ፡

1 ውጫዊ ኢሚዛናዊንትን ለመፍታት እና የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለማስታገስ በገበያ ወደሚወሰን የምንዛሪ ዋጋ መሄድ፤
2የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍን በማዘመን የዋጋ ግሽበትን መዋጋት፤
3 የሀገር ውስጥ የገንዘብ ምንጮችን በማሰባብሰብ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ሕዝባዊ ወጪዎች ማዋል፤
4 ከውጪ አበዳሪዎች ጋር የሚደረጉ ወቅታዊ የእዳ ሪስትረክቸሪንግ ስምምነቶችን በመፈጸም ጭምር የእዳ
አከፋፈል ዘላቂነትን መመለስ እንዲሁም
5 ወሳኝ የሆኑ የማክሮ ፋይናንሺያል ተጋላጭነቶችን ለመቀነስ የመንግሥት ኢንተርፕራይዞችን የገንዘብ አቋም
ማጠናከር።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) መንግሥት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ማወጁን “በደስታ እቀበለዋለሁ አለች።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከዓለምዓቀፉ የንግድና የፋይንናስ ተቋም ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የበርካታ አገራት ባለሀብቶች ጥምረት ከሆነው ከዓለም ዓቀፉ የንግድና የፋይንናስ ተቋም (Global Trade & Finance) ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል የዓለም ዓቀፉ የንግድና የፋይንናስ ተቋም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስስ ኬጀ ሊ ፈርመዋል፡፡

በፕሮጀክት ፋይናንስ ፣ በቤት ግንባታና አስተዳደር ቴክኖሎጂ አቅርቦት ላይ እና በቬንቸር ካፒታል ኢንቨስትመንት ዙሪያ ኮርፖሬሽኑ ከዓለም ዓቀፉ የንግድና የፋይናንስ ተቋም ድጋፍ የሚያገኝበትን እድል የሚፈጥር ነው፡፡

በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ወቅትም የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የከተማና መሰረተ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ኢ/ር እሽቱ ተሾመ ተገኝተዋል፡፡

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል ኮርፖሬሽኑ የመኖሪያ ቤት እጥረትን ለመቅረፍና የፋይናንስ አቅሙን ለማጠናከር በርካታ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን አንስተው ከጠንካራ ዓለም ዓቀፍ የፋይናንስ ምንጮች ጋር በጋራ ለመስራት ጥረት እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከዓለም ዓቀፉ የንግድና የፋይናንስ ተቋም ጋርም በተለይ በፕሮጀክት ፋይናንስ ዙሪያ በጋራ ለመስራት ኮርፖሬሽኑ ፍላጎት እንዳለው ክቡር አቶ ረሻድ ከማል ተናግረዋል፡፡ ለስምምነቱ ተግባራዊነት ኮርፖሬሽኑ እንደሚሰራም ክቡር አቶ ረሻድ ከማል አክለው ተናግረዋል፡፡

የዓለም ዓቀፉ የንግድና የፋይንናስ ተቋም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስስ ኬጀ ሊ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ኮርፖሬሽኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ሊለማ የሚችል ግዙፍ ሀብት ባለቤት በመሆኑ በቂ የፋይናንስ አቅርቦት እንዲኖረው ተቋማቸው እንደሚሰራም ተናረዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪም ተቋማቸው ከበርካታ ስመ ጥር ዓለም ዓቀፍ ኩባንያዎች ጋር በጥምረት የሚሰራ በመሆኑ የኮርፖሬሽኑን ትራፋማነት በሚጨምሩ ሌሎች ተግባራትም በጋራ ለመስራት ተቋማቸው ቁርጠኛ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስስ ኬጀ ሊ ተናግረዋል፡፡

አጠቃላይ በኮርፖሬሽኑ የሥራ እንቅስቃሴም ደስተኛ መሆናቸውን ሚስስ ኬጀ ሊ ገልጸው ለስምምነቱ ተግባራዊነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

https://vm.tiktok.com/ZMr9xqcXB/

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች

ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተ‍እ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበ‍ኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።

ሚለየን ምንድነው?

የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ

🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።

🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።

🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።

🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።

🪄We Care

አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ

📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69

www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የአሜሪካ መንግስት የማሻሻያ ውሳኔውን በመደገፍ መግለጫ አወጣ!

የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ምንዛሪ ተመን ገበያ መር እንዲሆን መወሰኑ አስቸጋሪ ቢሆንም ነጻ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ማድርጉ አስፈላጊ ነው” ሲል የአሜሪካ መንግስት ውሳኔውን በመደገፍ መግለጫ አውቷል።

በዚህም የአሜሪካ መንግሥት ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመሆን መንግሥት የወሰደውን የነፃ ኢኮኖሚ ማሻሻያን ያበረታታል፣ይደግፋል ብሏል።

በተያያዘ ዜና ብሔራዊ ባንክ ፥ 10.7 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ከውጭ አጋሮች መገኘቱን አሳውቋል።

ባንኩ “የሽግግር ወቅት ወጪዎችንና የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያ የሚያስከትላቸውን ጫናዎችን ለመቀነስ የሚረዳ 10.7 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ትልቅ የገንዘብ ድጋፍ ከውጭ አጋሮች ተገኝቷል “ ብሏል። የገንዘብ ድጋፉ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት (#IMF) ፣ ከዓለም ባንክ (WB) እና ከአበዳሪዎች የሚገኘውን እንደሚጨምር አመልክቷል።

ነገር ግን፣ በሁለትዮሽ የማዕከላዊ ባንክ ተቀማጭ (central bank deposits) እና በከረንሲ ልውውጥ (currency swap) መልክ የሚመጣውን 2.8 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንዲሁም ከዓለም ባንክ፣ ከዓለም አቀፍ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) እና ከሌሎች ባለብዙ ወገኖች (multilaterals) ይገኛል ተብሎ የሚጠበቀውንና በሃደት ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት ይፋ የሚደረገውን ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ አያካትትም ብሏል።

ብሔራዊ ባንክ “ በዓለም የገንዘብ ድርጅት እና የዓለም ባንክ የሚለገሰው ልዩ የገንዘብ እርዳታ የመንግሥትን የሪፎርም ሥራዎችን ጥንካሬ ያገናዘበና በአፍሪካ አህጉር ትልቁ ከሚባሉት የገንዘብ እርዳታዎች አንዱ ነው “ ብሎታል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

"ስማችን እውነት ነው,ስራችንም የእውነት ነው"

❇️ከዚህ በፊት የተመረጡ ቦታዎች ላይ ጥንቅቅ አድርገን እንዳስረከብናቸው አሁንም እጅግ ውብ ለኑሮ መቹ በከተማችን የተመረጡ ቦታዎች

❇️በሳርቤት እና በ ቦሌ ቅድመ ክፋያ 770 ( ሰባትመቶ ሰባ ) ሽህ ጀምሮ በመሸጥ እንገኛለን

✅ 65.7 , 86 , 90 ካሬ ባለ 1 መኝታ
✅ 98 , 100 , 114 ካሬ ባለ 2 መኝታ
✅ 140 , 152 , 212 ካሬ ባለ 3 መኝታ

❇️የቤት ባለቤት ከመሆን ባለፈ፣በመሀል አዲስ አበባ የምንገነባቸው ቅነጡ ቤቶቻችን ኢንቨስተር ያደርጉታል !
✅ምስክሮቻችን ከዚህ በፊት ሰርተን ያስርከብናቸው ደንበኞቻችን::

❇️ወለል ውፍረት 25ሲ.ሜ ኮንክሪት አስላብ።
✅ከወለል ወለል እርዝማኔ 3.2 ሜትር
❇️የውጭ በሮቻችን 100ኪሎ የሚመዝኑ፣ከኮንክሪት እና ከብርት የሚስሩ፣ድመፁ የማያስተላልፍ ፣6 የተለያዩ ቦታዎች የሚቆልፍ።


✅Reality real estate✅
🚧 3B+G+17 አፓርታማ
🚘 sufficient parking space
🏋️gymnasium and spa
👉🏻17 th floor club house
👉🏻under ground water and backup generator

💰 10% ቅድመ ክፍያ

What makes Reality real estate different
- Affordable price
- Easy payment schedule
- Prime Location
- Reputed company
- Early Delivery
የድርጅቱ የሽያጭ አማካሪ
☎️0976 20 68 68
0951 69 14 66

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

#IMF : የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ኢትዮጵያ በጠየቀችው ብድር ላይ ለመወያየት ነገ ሰኞ ሐምሌ 22 / 2016 ይሰበሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ብሎምበርግ ድረገጽ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የመረጃ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ከዓለም ባንክ ጋር የምታደርገው ድርድር ከተሳካ በቀጣይ አመታት 10.5 ቢሊዮን ዶላር ልታገኝ እንደምትችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በፓርላማ ቀርበው በነበረበት ወቅት መናገራቸው ይታወሳል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

#ETHIOPIA

መንግስት “ በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓት “ ተግባራዊ ሊያደርግ እንደሆነ አስታውቋል።

ውሳኔው በመንግስት ቁጥጥር ሲከናወን የቆየውን የውጭ ምንዛሬ ግብይት “ በገበያው አማካኝነት እንዲበየን “ የሚያደርግ ነው።

ውሳኔው ተግባራዊ ሲሆን ብር፤ ዶላር እና ፓውንድን ከመሳሰሉ ዋና ዋና የመገበያያ ገንዘቦች አኳያ ያለው የምንዛሬ ተመን ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል።

አሁን በስራ ላይ በሚገኘው የውጭ ምንዛሪ ተመን ስርዓት፤ ባንኮች አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ54 ብር ከ50 ሳንቲም ገደማ ገዝተው በ58 ብር ከ64 ሳንቲም ገደማ ይሸጣሉ።

በተለምዶ “ ጥቁር “ እየተባለ በሚጠራው ትይዩ ገበያ በአንጻሩ፤ ይህ የምንዛሪ ተመን ከእጥፍ በላይ ልዩነት አለው።

የውጭ ምንዛሬ ግብይት ስርዓትን ጨምሮ የኢትዮጵያ መንግስት ተግባራዊ በሚያደርጋቸው የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያዎች እና እርምጃዎች “ ተጋላጭ “ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ የሚያስችሉ ተግባራት እንደሚከናወኑ መንግስት ገልጿል።

ለዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኞች የማክሮ ኤኮኖሚ ማሻሻያዎቹ ሊያስከትሉ ከሚችሉት የአጭር ጊዜ አሉታዊ ተጽዕኖዎች ለመጠበቅ አስፈላጊ የደመወዝ ድጎማ እና ማሻሻያዎች ለተወሰኑ ጊዜያት ይደረጋሉ ተብሏል።

በነዳጅ ዋጋ ላይ የሚከተለውን ጭማሪም መንግስት በከፊል #እንደሚደጉም አሳውቋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች

ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተ‍እ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበ‍ኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።

ሚለየን ምንድነው?

የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ

🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።

🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።

🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።

🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።

🪄We Care

አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ

📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69

www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በፓሪስ የሚገኘው የኦሎምፒክ ቡድናችን የምድረቀደምት መለያን እና የኢትዮጵያን ቱሪዝም በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል::

መልካም እድል ለአትሌቶቻችን ቱሪዝም ሚኒስትር

Читать полностью…
Подписаться на канал