በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7 Facebook.com/natnaelmekonnen.et Instagram.com/natnaelmekonnen21
Must Listen : “ማንም ያቦካው ጭቃ ሁሉ ቅርስ አይደለም”‼️የትዉስት ነገሮችንም ቅርስ ማለት አይቻልም።
የኢትዮጵያ ቅርስ ላሊበላ ነው። የኢትዮጵያ ቅርስ ሶፍኡመር ዋሻ ነው። የኢትዮጵያ ቅርስ የሀረር ግንብ ነው። ማንም ጭቃ እያቦካ የለጣጠፈው ግርግዳ ሁሉ ቅርስ አይደለም።”
—
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ,
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተሠጠ መግለጫ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም የአማራ ክልል ተማሪዎች መማሪያ መጻህፍትን እንደሰበብ ተመርኩዞ ያወጣውን የዛቻ እና የጠብ አጫሪነት መግለጫ ተመልክተናል፡፡
ጊዚያዊ አስተዳደሩ የአማራ ክልል የትምህርት ስርዓትን በማጣቀስ የተሳሳተ ካርታ ተሰርቷል ሲል ያወጣው መግለጫ በተሳሳተ ካርታ ወደ አማራ ክልል ተካተዋል ያላቸውን አካባቢ ሕዝቦች ታሪካዊ እውነታን፣ ተጨባጭ ማስረጃዎችን እና ነባራዊ ሐቅን የካደ፣ አሳሳችና የጠብ አጫሪነት ፍላጎትን የተሸከመ መግለጫ በመሆኑና በትናንትናው እለት ማለትም በ18/7/2016 ዓ/ም ደግሞ ከነበረበት አካባቢ በመንቀሳቀስ የራያ አላማጣ ወረዳ ቀበሌዎችን በመያዝ ነዋሪዎችን በመግደልና በማሰቃየት ላይ ይገኛል፡፡
ስለሆነም የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ ግልጽ መግለጫ መስጠት ተገቢ ሆኖ አግኝቶታል፡፡ ጊዚያዊ አስተዳደሩ የአማራ ክልል የተማሪዎች የመማሪያ መጻሕፍ ውስጥ የተሳሳተ ካርታ ተሰርቷል ሲል ባወጣው መግለጫ ሊያመላክታቸው የተፈለጉት አካባቢዎች ካለፉት 30 ዓመታት በፊት ጀምሮ የወልቃይት ጠገዴ፤ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች የማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄዎችን ሲያቀርቡባቸው በነበሩ ቦታዎች ላይ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡
አሁን በሥራ ላይ የሚገኘው የሀገሪቱ ሕገ መንግስት ከመጽደቁ በፊት በተስተዋሉት የአስተዳደራዊ መዋቅሮች እና አደረጃጀት ቅመራ ጅማሬ አንስቶ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በሰሜን ዕዝ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ አሰቃቂ ጥቃት በመፈጸሙ ምክንያት ጦርነት እስከተቀሰቀሰበት ግዜ ድረስ የወልቃይት ጠገዴ፤ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች በወቅቱ ለነበረው መንግስት የማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄዎችን በማንሳት መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ሲጠይቁ የነበሩ መሆኑን በበርካታ ታሪካዊ ሁነቶችና ተጨባጭ ማስረጃዎች የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡
ይሁን እንጂ እነዚህ የማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ሲጠይቁ የነበሩ ሕዝቦች እና አካባቢዎችን ለበርካታ ዘመናት በኃይል ሲገዛ የነበው የቀድሞው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የወልቃይት ጠገዴ፤ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች ላነሱት ታሪካዊና ሕጋዊ ጥያቄዎች ሕጋዊ አሰራርን የተከተለ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ የአካባበው ተወላጆችን፣ የሀገር ሽማግሌዎችን፣ የማንነትና የአስተዳደር ጥያቄ አስተባባሪዎችን በማሰር፣ በማሰደድ እና በመግደል የሕዝቡ ጥያቄ ምላሽ ሳያገኝ እስከ ሰሜኑ የህግ ማስከበር ጊዜ ድረስ እንዲገፋ አድርጎታል፡፡
የማንነት እና የአስተዳደር መብት ዙሪያ ላነሳቸው ጥቄዎች የወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች ትግል በተፋፋመበትና ከፍተኛ መስዋዕትነት ጭምር እየከፈለ በሚገኝበት ወቅት ህወሓት የሠሜን ዕዝ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን አሰቃቂ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሁሉንም ኢትዮጵያዊያንን በማቀናጀት ለሁለት ዓመታት የቆየ የሕግ ማስከበር እርምጃ ለመውሰድ የተገደደበት ሁኔታ መፈጠሩ ይታወሳል፡፡
የማንነትና የአስተዳደር ጥያቄዎቹ ለዘመናት የታፈኑበት ሕዝብም ከማዕከላዊው መንግስት ጎን ተሰልፎ በህ.ወ.ሓ.ት የክህደት ተግባር በኢትዮጵያ ሕልውና እና ሉአላዊነትት ላይ የተጋረጠውን ግልጽ አደጋ እንዲቀለበስ የበኩሉን አስተዋጽዖ ከማበርከቱ ባሻገር በሂደቱ ህወሓት በኃይል ተገፍፎባቸው የነበረውን የማንነትና ጥያቄና ራስን በራስ የማስተዳደር ነጻነት የተቀዳጁበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡
በዚህም ምክንያት የወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች ህዝብ እንደማንኛውም የሀገሪቱ ሕዝብ ሁሉ የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚነት መብቱ ሊቀለበስ የማይችል በመሆኑ በቀድሞው የህ.ወ.ኃ.ት እና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት መካከል የፕሪቶሪያው ስምምነት ከመፈረሙ በፊት ጀምሮ የአማራ ክልል እንደሌሎቹ ዞኖችና የልማት ትሩፋቶች ሁሉ የአካባቢው ሕዝብም በትምህርቱም መስክ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡
አካባቢዎቹን በተመለከተ የነበረው፣ ያለው እና የሚኖረው እውነታ ይሄ ሆኖ ሳለ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም ከፕሪቶሪያው ስምምነት ከመፈረሙ በፊት በስራ ላይ የዋሉ የአማራ ክልል ተማሪዎች እንደሌሎቹ አካባቢዎች የነዚህ አካባቢ ህፃናትም የመማራ መብታቸው እንዲከበር የአማራ ክልል መንግስት ግዴታውን መወጣቱን ሰበብ በማድረግ በአማራ ክልል ላይ ጥቃት ከመፈጸም የማይመለስ መሆኑን የሚገልጽ የጠብ አጫሪ መግለጫ ማውጣቱ ካለፉት ድርብርብ ውድቀቶች ትምህርት አለመውሰድን ከማሳየት የዘለለ ፋይዳ አይኖረውም፡፡
የተፈጠሩ ችግሮችን በህግ አግባብ እንዲፈታ እተደረገ ያለውን ጥረት የአማራ ክልል መንግስት የራሱን ድርሻ እየተወጣ ባለበት ሁኔታ በህዝብ መጎሳቆልና በወጣቶች እልቂት ትምህርት አለመወሰዱና የተለመደ ትንኮሳ በማድረግ ላይ መሆኑ እጅጉን አሳዝኖናል፡፡
ስለሆነም የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር ለሀገሪቱ ቋሚ ቀውስ ምንጭ ከሚያደርጉት ተግባራት እንዲታቀብ፣ ሀገራችንንና ሁለቱን ክልሎች ወደ ቀውስ ከሚያስገቡ ተግባራት በመቆጠብ ከለመደው አጓጉል የካርታ ፖለቲካ ጨዋታ እንዲወጣና የህዝብን ፍላጎት ማዕከል ባደረጉ ውይይቶች ላይ እንዲያተኩር እንዲሁም አንድ ሀገር ለመገንባት ለሚፈለገው ዘላቂ ሠላም እና ለሕዝቦች አንድነት መጽናት በሚበጅ ሐሳብና ተግባር ላይ እንዲያተኩር እንመክራለን፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
መጋቢት18-2016 ዓ/ም
ባሕር ዳር
ሚሊተሪ ለብሶ ቪዲዮ መስራት ያስቀጣል‼️
የፌደራል ፖሊስ ፍቃድ ከተሰጣቸው ውጭ በተቋሙ የደንብ ልብስ ቪዲዮ በሚለቁ አባላት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ አለ‼️ የፌደራል ፖሊስ ፍቃድ ከሰጠኋቸው ውጭ በተቋሙ የደንብ ልብስ በማህበራዊ ትሥሥር ገጾች ተንቀሳቃሽ ምስል (ቪዲዮ) በሚለቁ አባላት ላይ እርምጃ እወስዳለሁ አለ።
አሁን ላይ በስፋት በተለይም ቲክቶክ የተሰኘ መተግበሪያን በመጠቀም ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እውቅና እና ፍቃድ ውጭ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን የሚያጋሩ የፖሊስ አባላት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ ተቋሙ ገልጿል።
ተቋሙ ወጣቱን ተደራሽ ለማድረግ በተለይ ቲክቶክን ተጠቅሞ አስተማሪ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን የሚያሰራቸው አባላት እንዳሉት ገልፆ ከእነሱ ውጭ ባሉት ላይ ግን እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል።
ድርጊቱ ከደመወዝ ቅጣት እስከ ሥራ መባረር የደረሰ ቅጣት እንደሚያስከትልና እስከአሁንም ቅጣት የተጣለባቸው እንዳሉ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ጄይላን አብዱ ለአራዳ ኤፍ ኤም ገልፀዋል::
አንዳንድ ተንቀሳቃሽ ምስሎች የተቋሙን እና የአባላቱን ክብር የማይመጥንና በማህበረሰቡም ዘንድ ቅሬታን የፈጠረ በመሆኑ ይህን ለማስተካከል ይሰራልም ነው ያሉት።
የማህበረሰቡን ሞራል የማይነኩ እንዲሁም ሃይማኖትና ፖለቲካ ውስጥ የማይገቡ ቪዲዮዎችን የሰሩና ከተቋሙ የማረጋገጫ ፍቃድ ያገኙት ግን ተንቀሳቃሽ ምስሉን ማጋራት ይችላሉ ብለዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የባሕር ዳር ከተማ የመሐል ሜዳ ተጫዋች የሆነው አለልኝ አዘነ እረፍት ለመውሰድ ወደ ቤተሰቦቹ አርባ ምንጭ ከተማ በሄደበት በድንገት ህይወቱ እንዳለፈ ተነግሯል።
ህይወቱ ያለፈው ለሊት ላይ መሆኑ ተሰምቷል።
ወደ አርባምንጭ የሄደው ያጋጠመውን መጠነኛ ጉዳት ተከትሎ እረፍት ለመውሰድ ነበር።
የህልፈቱ ምክንያት " ድንገተኛ " ተብሎ ከተገለፀው ውጭ በዝርዝር የሚታወቅ ነገር የለም።
ተጫዋቹ ባለትዳር ሲሆን ከሁለት ሳምንታት በፊት ነበር በስርዓተ ቁርባን ጋብቻውን የፈፀመው።
የአለልኝ አዘነ ስርዓተ ቀብር ዛሬ መጋቢት 18 በትውልድ ከተማው አርባ ምንጭ እንደሚፈፀም ታውቋል።
+++++Major Surgery !+++++ በብርሃኑ ፈይሳ
በማይመጥን ሰፈር፣
ከእንድህስ ለመኖር ፣
ተቸክለህ አትቅር ።ማዲያቷ ሰፋፍቶ፣
~~~~~~~~~
ውበቷም ተገቶ፣
እርጅናው በርትቶ፣
ፊቶቿም ገርጥቶ፣
ችግሯ ፈንድቶ ፣
አደባባይ ወጥቶ፣
ላይደበቅ ከቶ፣
መነሳት ይሻላል ......
አንድ ጊዜ ሞቶ ።
Kanaaf ....
ፈራርሶ ይሰራ፣
ይራገፍ አቧራ።
ለመኖር በሕይወት፣
አሻግሮ በማየት፣
መርፌውን መወጋት ።
እስካሁን 78 በመቶ ወይም ከ 622.9 ሚሊዮን ብር በላይ ወደ ባንኩ ተመላሽ ተደርጓል የጊዜ ገደብ ዉስጥ በፍቃደኝነት ገንዘብን ተመላሽ ያላደረጉ ግለሰቦች ስማቸዉን ጨምሮ ማንነታቸውን የሚገልፅ ምስዕል ከዛሬ ጀምሮ በተለያዩ አማራጮች ይፋ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሰሞኑ በተፈጠረው የሲስተም ችግር ሳቢያ ከ 9 ሚሊዮን ብር በላይ የወሰዱትን ወደ 567 የሚጠጉ ግለሰቦችን ማግኘት አለመቻሉን አስታወቀ!
ንግድ ባንክ ባጋጠመው የሲስተም ችግር ምክንያት ከተወሰደዉ ከ 801 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ 622 ሚሊዮን ያህሉን ወደ ባንኩ ተመላሽ ማድረጉን የገለፀዉ እና ቀሪ 567 ግለሰቦች ደግሞ የወሰዱትን 9.8 ሚሊዮን ብር ማግኘት አለመቻሉን አስታዉቋል።መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ምሽት ላይ ከ 3 ሰዓት ጀምሮ እስከ 8: 45 ድረስ ባለዉ 25 ሺህ 761 ደንበኞች ብር 801.4 ሚሊዮን መወሰዳቸውን ገልጿል።
ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በሂደቱ ዉስጥ የተሳተፉ 15 ሺህ ያህል የሂሳብ ቁጥሮችን ማግኘቱን ያስታወቀው ባንኩ 14 ግዜ ግበይት ነበራቸው ብሏል።በዕለቱ 238 ሺህ 293 ግብይት መደረጉን እና አንድ የባንኩ ደንበኛ ከ 9 ጊዜ በላይ ግብይት መፈፀሙን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ለሁለተኛ ጊዜ በሰጡት መግለጫ አስታዉቀዋል።
በሂደቱ ላይ 57 በመቶ ተሳታፊ የነበሩት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መሆናቸው ተነግሯል። አቶ አቤ ሳኖ እንደገለፁት እስከ ትላንት መጋቢት 16 ፤ 2016 ዓ.ም. ድረስ ከተወሰደዉ ገንዘብ 78 በመቶ ወይም ከ 622.9 ሚሊዮን ብር በላይ ወደ ባንኩ ተመላሽ ተደርጓል ብለዋል።በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ዉስጥ በፍቃደኝነት ገንዘብን ተመላሽ ያላደረጉ ግለሰቦች ስማቸዉን ጨምሮ ማንነታቸውን የሚገልፅ ምስዕል ከዛሬ ጀምሮ በተለያዩ አማራጮች ይፋ እንደሚያደርግ አስታዉቋል።
ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል:: ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት
አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
Tel: 0913858561
ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች
ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተእ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።
ሚለየን ምንድነው?
የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ
🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።
🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።
🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።
🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።
🪄We Care
አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ
📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69
www.elegas.com.tr
Email:- ethiopia@elegas.com.tr
የመጀመሪያዎቹ በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሠሩ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች በአዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።
የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶቹ በበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የተገጣጠሙ መሆናቸው ነው የተገለጸው፡፡
አውቶብሶቹን ወደ ሥራ ያስገባው በቅርቡ 20 በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሠሩ ሚኒባሶችን ወደ ሥራ ያስገባው የግሩፑ እህት ድርጂት ቬሎሲቲ ኤክስፕረስ ነው ተብሏል፡፡
ዛሬ ሥራ የጀመሩት አውቶብሶች መነሻቸው ቦሌ ሲሆን መዳረሻቸው ደግሞ በእስጢፋኖስ -4 ኪሎ- 6 ኪሎ ሽሮ ሜዳ መሆኑን የተቋሙ መረጃ ያመላክታል፡
ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች
ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተእ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።
ሚለየን ምንድነው?
የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ
🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።
🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።
🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።
🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።
🪄We Care
አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ
📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69
www.elegas.com.tr
Email:- ethiopia@elegas.com.tr
ዶክተር በሃይሉ ሀይሉ ከከፍታ ቦታ በመውደቅ በአካላቸው ላይ በተከሰተ ጉዳት ህይወታቸው ማለፉን የዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል የአስክሬን የምርመራ ውጤቱ እንዳረጋገጠ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ስራውን የቀጠለ ሲሆን ከከፍታው የወደቁበትን ሁኔታና ሌሎች ተያያዥ የምርመራ ውጤቶች ሲጠቃለሉ ለህዝብ ግልፅ እንደሚደረጉ አስታውቋል፡፡
***
የሰርጀሪ ህክምና ባለሞያ የሆኑት ዶክተር በሀይሉ ሀይሉ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ ም በዕለተ እሁድ ሊነጋጋ ሲል ስፖርት ለመስራት ከቤት ወጥተው እንዳልተመለሱ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሲገለፅ ቆይቷል።
ፖሊስ መረጃው ከደረሰው ሰዓት ጀምሮ ባደረገው ማጣራት የሟች ዶክተር በሀይሉ ሀይሉ አስከሬን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከቦሌ ሚካኤል ወደ ሳሪስ አቦ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኝ ቀጠና 3 በተለምዶ ማሞ ድልድይ ስር ወድቆ በመገኘቱ በወቅቱ አስከሬኑ ተነስቶ የአሟሟታቸውን ምክንያት ለማወቅ ለአስክሬን ምርመራ ወደ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል እዲሄድ ተደርጓል ፡፡ ከሆስፒታሉ የተገኘው የአስክሬን ምርመራ ውጤት እንደሚያስረዳው ከከፍታ ቦታ በመውደቅ በአካላቸው ላይ በተከሰተ ጉዳት ህይወታቸው ማለፉን የአስክሬን የምርመራ ውጤቱ ይገልፃል፡፡ ሟች ዶ/ር በይሉ ሐይሉ ከከፍታው ላይ ቁልቁል ወደ ገደሉ በመውረድ አካላቸው ድንጋይ ላይ ስላረፈ በጭንቅላታቸው፤ በእግራቸው በጀርባ አጥንታቸውና በውስጥ የሰውነታቸው አካላት ላይ በደረሰባቸው ከፍተኛ ጉዳት ምክንያት ህይወታቸው ማለፉን ከሆስፒታሉ የተገኘው የአስክሬን የምርመራ ውጤቱ ያብራራል፡፡ከዚህ ጋር በተያያዘ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ስራውን የቀጠለ ሲሆን ከከፍታው የወደቁበትን ሁኔታና ሌሎች ተያያዥ የምርመራ ውጤቶች ሲጠቃለሉ ለህዝብ ግልፅ የሚደረጉ መሆናቸውን ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ፖሊስ በዶክተር በሃይሉ ሀይሉ አሟሟትን የተሰማውን ሐዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸውና ለሙያ አጋሮቻቸው መፅናናት እንዲሰጣቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡
ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል:: ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት
አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
Tel: 0913858561
በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በአንዲት ደንበኛ ላይ እንግልትና መጉላላት በፈጠሩ አመራርና ባለሙያ ላይ እርምጃ ተወሰደ
በአገልግሎት አሰጣጥ ወቅት ከደንበኞች የሚሰጡ አስተያየቶችንና ሚዛናዊ ትችቶችን ተቀብሎ ፈጣን ምላሽ ለመስጠትና ለማስተካከል ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆኑን የጉምሩክ ኮሚሽን ገለጸ፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽንን ከነበረበት ውስብስብ ችግር ለማውጣት እና የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል በተደረገው እንቅስቃሴ በርካታ ፈተናዎች ማጋጠማቸውን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ አንስተዋል፡፡
በተለይም ከሕገ-ወጦች ጋር በሚደረገው ትንቅንቅ የኮሚሽኑ አመራሮች እና ሰራተኞች ህይወት እንደሚያልፍ እና የአካል ጉዳት እንደሚደርስባቸው ነው የተናገሩት፡፡
“ይህን በርካታ መስዋዕትነት ተከፍሎበት የመጣውን የተቋም ሪፎርም ጥላሸት ለመቀባት የሚጥሩ የውስጥም ሆነ የውጭ አካላትን አንታገስም ” ብለዋል፡፡
በተለይም በአገልግሎት አሰጣጥ ወቅት እንከን በሚፈጥሩ አመራሮች እና ሰራተኞች ላይ ጠንካራ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝም አስረድተዋል፡፡
በቅርቡም በኢትዮጵያ አየር መንገድ በአንዲት ደንበኛ ላይ በደረሰው እንግልት ማዘናቸውን የገለጹት ኮሚሽነሩ÷ ችግሩን በፈጠሩ አንድ አመራር እና ባለሙያ ላይ በወቅቱ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃ የተወሰደ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በወቅቱ ደንበኛዋ የፈጸመችው የህግ ጥሰት እንደሌለ ጠቅሰው፤ ደንበኛዋ ለደረሰባት እንግልት እና መጉላላት በኮሚሽኑ ስም ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡
ደንበኞች እንደዚህ ዓይነት ችግር ሲያጋጥማቸው በአቅራቢያው ለሚገኙ የህግ አካላት እና በየደረጃው ለሚገኙ የኮሚሽኑ አመራሮች ማቅረብ እንደሚችሉ መናገራቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
በግለሰብ ደረጃ ጥፋት የሚፈጽም አመራር እና ሰራተኛ በየትኛውም ተቋም እና ጊዜ እንደሚኖር ጠቁመው÷ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትም የተቋማትን ቅንጅታዊ ስራ ማጎልበት እና የክትትልና ቁጥጥር ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
ክፍለጦሩ በሆሮ ጉድሮ ወለጋ ዞን ዋዩ ወረዳ ለሚኖሩ ሶስት አሳዳጊ ለሌላቸው ህፃናት የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።
ክፍለጦሩ በተሰማራበት የሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ዋዩ ወረዳ የግዳጅ ቀጠና አሸባሪውን የኦነግ ሼኔ ቡድን በገባበት ገብቶ ከመምታትና ለህዝቦች ሰላምን ከማረጋገጥ ባሻገር አቅም ለሌላቸው እና አሳዳጊ ለሌላቸው ህፃናት የ160,255 ,00 /አንድ መቶ ስልሳ ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ አምስት ብር/ ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል።
በዕለቱ የተገኙት የክፍለጦሩ ዋና አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ተካ ተፈራ የክፍለጦሩ ሠራዊት ሰላም ጠል ለሆኑ አሸባሪ ሀይሎች አይቀጡ ቅጣት የሚቀጣ ፤ አቅም ላጡና ጧሪ ደጋፊ ለሌላቸው ወገኖች ደግሞ ካለው ቀንሶ የሚያጎርስ እና የሚደግፍ ህዝባዊ እና ልማታዊ ሰራዊት መሆኑን ተናግረዋል።
በቀጣይም ከግዳጃችን ጎን ለጎን ከማህበረሰቡና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት እና ሰላምን በማረጋገጥ የሰራዊታችንን እገዛ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች ሁሉ ከጎናቸው መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
በተመሳሳይ የክፍለጦሩ ስነ-ልቦና ግንባታ ቡድን መሪ ሻለቃ ቢኒያም አስገዶም እነዚህን መሰል ህዝባዊ ስራዎች እያደረገው የመጣና ቀጣይም የሚያደረገው የሰራዊታችን መገለጫ ከመሆኑም ባሻገር የተገነባበት ባህል እና እሴትም ጭምር መሆኑን አብራርተዋል።
የዋዩ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አቡሜ ኦብሳ በበኩላቸው ሰራዊቱ ከህዝብ አብራክ የወጣ ህዝባዊ ሰራዊት ቢሆንም በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ይህንን መሰል አስደናቂ በጎ ተግባር ያደርጋል ብለው እንዳልጠበቁና እንዳላሰቡ ገልፀው ለሰራዊቱ ትልቅ ክብርና ምስጋና አቅርበዋል።
ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል:: ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት
አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
Tel: 0913858561
ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች
ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተእ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።
ሚለየን ምንድነው?
የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ
🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።
🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።
🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።
🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።
🪄We Care
አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ
📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69
www.elegas.com.tr
Email:- ethiopia@elegas.com.tr
በሸኔ ቡድን ላይ እየተወሠደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ አመያ ወረዳ ዳሌ ዳክን ጨምሮ በተለያዩ ቀበሌዎች ላይ ህብረተሠቡን ሠላም ሲያሳጣ በነበረው የሸኔ ቡድን ላይ በቀጠናው የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት አሥፈላጊውን እርምጃ ወስዷል።
ሠራዊቱ ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር በመሆን በዛሬው ዕለት በሸኔ የሽብር ቡድን ላይ በወሰደው እርምጃ በርካታ የሸኔ ቡድን ታጣቂ ከጥቅም ውጪ እንዲሆን ተደርጓል።
በተለያዬ ከጋጣሚ የሠላም ሃሳብ ሲቀርብለት ለመቀበል ወደ ኋላ የሚለውና ህዝብን እያሥገደደ የሚዘርፈው የሸኔ ቡድን በተለያዩ ቦታዎች በመከላከያ ሠራዊቱ እየተወሠደበት ያለውን እርምጃ መቋቋም ተስኖት እየተበታተነ ይገኛል።
በዛሬው ዕለት ብቻ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ አመያ ወረዳ ዳሌ ዳክንና አካባቢው በቀጠናው የሚገኘው ሠራዊት በሸኔ ቡድን ላይ በወሠደው እርምጃ፦
👉 12 ታጣቂ ተማርኳል
👉 02 ተገድሏል
👉 08 ክላሽ ተማርኳል
👉 02 ብሬይን ተማርኳል
👉 03 ኋላ ቀር መሳሪያ የተማረከ ሲሆን በሽብር ቡድኑ ላይ የሚወሰደው ዘመቻ የቀጠለ መሆኑን ከሥፈራው የሚገኙ የሠራዊቱ አመራር ገልፀዋል።
ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች
ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተእ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።
ሚለየን ምንድነው?
የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ
🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።
🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።
🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።
🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።
🪄We Care
አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ
📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69
www.elegas.com.tr
Email:- ethiopia@elegas.com.tr
ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል:: ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት
አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
Tel: 0913858561
300 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል ያለው የቻይና ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች የማምረት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ
300 ሚሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት ካፒታል ያለው ዌንዡ ኒክሲን ትሬዲንግ ኩባንያ፤ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ወረቀት የማምረት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የኩባንያውን አመራሮች በፅሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
የኩባንያው አመራሮች ስለ ኢንቨስትመንት ዕቅዳቸው ዝርዝር መረጃዎችን ማቅረባቸው ተጠቅሷል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ፤ በኮርፖሬሽኑ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ማዕከሎችን፤ማበረታቻዎችን እንዲሁም የመሰረተ ልማትና የአገልግሎት አሰጣጥን የተመለከቱ መረጃዎችን ለኩባንያው አመራሮች አቅርበዋል።
ኢንቨስትመንቱ እንዲሳካ ኮርፖሬሽኑ ያልተቋረጠ ድጋፍ እንደሚያደርግም አቶ አክሊሉ አረጋግጠውላቸዋል።
https://youtu.be/FT-vw8Mel-U?si=Cp9tVj9n2B4L1Zi7
Читать полностью…ሩስያ
ከዚህ ቀደም ማንኛውም አይነት #የግብረሰዶም እንቀስቃሴን #ሕገወጥ እና #ጽንፈኛ በማለት ፈርጃ የነበረችው ሩስያ አሁን ደግሞ የግብረሰዶም እንቅስቃሴን #የአክራሪነት እና #የሽብር ድርጊት ዝርዝር ውስጥ አካታዋለች።
በዚህም ማንኛውም ዓለም አቀፍ የግብረሰዶም እንቅስቃሴ በሩስያ በአሸባሪነት እና በአክራሪነት ዝርዝር ውስጥ ተካቷል።
ውሳኔው የተደረሰው የሩስያ የፍትህ ሚኒስቴር የቀረበለትን አቤቱታ ተከትሎ የግብረሰዶም ተከራካሪዎች #አክራሪ እና #አሸባሪ ተብለው እንዲጠሩ በህዳር ወር ላይ የሩሲያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከወሰነ በኋላ ነው።
በቅርቡ የሩስያ ፍርድ ቤት በ " አክራሪ ድርጅት " ውስጥ ሚና አላቸው በሚል በመወንጀል ሁለት የመጠጥ ቤት / ባር ሰራተኞችን በእስር ቤት እንዲቆዩ እና እዛው እስር ቤት ሆነው ፍርዳቸውን እንዲከታተሉ ወሷል።
የሩሲያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ከዚህ በፊት ዓለም አቀፍ የግብረሰዶም የአደባባይ እንቅስቃሴን " #ጽንፈኛ " በማለት ማንኛውንም እንቅስቃሴዎችን አግዶ ነበር።
በወቅቱም የሩስያ ፀጥታ ኃይሎች በሞስኮ ከተማ በሚገኙ ፦
የተመሳሳይ ጾታ የምሽት ክበቦች (ክለቦች)
የተመሳሳይ ፆታ ፓርቲዎችን ያዘጋጃሉ በተባሉ ባሮች
የወንዶች ሳውና ቤቶች ላይ ዘመቻ አካሂደው ተጠርጣሪዎችን አስረው እንደነበር ይታወሳል።
በሩሲያ የተመሳሳይ ጾታ ጥምረት እውቅና የለውም።
በሩሲያ ትዳር ማለት የወንድ እና የሴት ጥምረት ማለት ስለመሆኑ ትርጉም ለመስጠት የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ከ3 ዓመታት በፊት ተቀይሮ ነበር።
Good Morning #Ethiopiaዬ የኮሪደር ልማት በአዲስ አበባ
#YouTube $ እና ጫጫታ የማያስቆመው ልማት:: በአዲስ አበባ ከተማ የሚደረጉ የኮሪደር ልማቶችን የትኛውም ምድራዊ ሃይል ሊያስቆመው አይችልም:: አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እንደ ስሟ አዲስ አበባ ይሆናለች::
የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ዞን ቡራ ወረዳ ላይ ለሚገኙ ለክርስትያን ምዕመናኑ ፈጣን ምላሽ ሰጡ።
በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ቡራ ወረዳ በህብረተሰብ ተሳትፎ የፖሊስ ፅህፈት ቤት ለመገንባት የታቀደበት ስፍራ በአከባቢው በምትገኘዉ የህይወት ብርሀን ቤተክርስቲያንን ድንበር ይነካል የሚል ቅሬታ በቤተክርስቲያን መሪዎች እና ምዕመናን ተነስቶ ለክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ የቀረበ ሲሆን በትላንትናው እለት አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ እስከስፍራዉ ድረስ በአካል በመሄድ ለቤተክርስቲያኒቷ አፋጣኝ ምላሽ ሰቷል።
በትላንትናው እለት በተካሄደው ስነስርዓት ላይ የዞኑ እና የወረዳዉ አስተዳዳሪዎች ፣ የኢትዮጵያ ህይወት ብርሀን ቤተክርስቲያን ፕሬዝዳንት ፣ የቤተክርስቲያኗ አገልጋዮች ፣ ምዕመናን በተገኙበት ሙሉ ለሙሉ የቤተክርስቲያኒቱን ችግር የተፈታ ሲሆን በቀጣይነት በመንግሥት እና በቤተክርስቲያኒቱ የሁሉቱን ህጋዊ ማንነት በማይጥስ መልኩ በአከባቢው በጋራ ትብብር በርከት ያሉ ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባ ቅሬታ ለመፍታት በተካሄደው መድረክ ላይ ተመላክቷል።
በዚህም አቶ አለማየሁ የፀጥታውን ዘርፍ እኛ በፖለቲካ ምህዳሮች የምንመራ ሲሆን ቤተክርስቲያኒቱ ደግሞ በፀሎት ታግዘን ዘንድ እንጠይቃለን ያሉ ሲሆን የፀጥታው ዘርፍ መጠናከር ለሁሉም አስፈላጊ ስለሆነ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
በመሆኑም ግንባታው ሊካሄድ የታሰበውን የፖሊሲ ፅ/ቤት ግንባታ ከመንግሥት እኩል የህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ክትትል እና ድጋፍ እንዲያደርግ ሃላፊው ጠይቀዋል።
በመጨረሻም ክብር አቶ አለማየሁ ጢሞቴዎስ የቤተክርስቲያኒቱ ምዕመናን እና አባት የሃይማኖት መሪዎች ጉዳይ በህግ አግባብ በትግስት እንዲፈታ ስላደረጉ አመሰግነዋል።
ኢትዮጵያ ሩሲያ አሸባሪዎችን ለመዋጋት ለምታደርገው ጥረት ሙሉ ድጋፍ እንደምተሰጥ ገለጸች
ኢትዮጵያ በሩሲያ ሞስኮ የተፈፀመውን የሽብር ጥቃት አውግዛለች። በሩሲያ ሞስኮ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ በተፈጸመ ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 115 ደርሷል።
ኢትዮጵያ ስለ ጥቃቱ ምን አለች? በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፤ https://bit.ly/497KpVx
ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች
ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተእ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።
ሚለየን ምንድነው?
የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ
🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።
🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።
🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።
🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።
🪄We Care
አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ
📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69
www.elegas.com.tr
Email:- ethiopia@elegas.com.tr
Fake news Alert ‼️
የአዲስ አበባ ህዝብ ይህን ታዘብ:: በተባለው አካባዊ አንድም ኮሽታ የለም ምንም አይነት ነገር አልተፈጠረም:: ትናት አዲስ አበባ ሳር ቤት አውቶብስ ውስጥ ቦንብ ፈነዳ ብለው የውሸት ዜና መስራታቸውንም የአዲስ አበባ ነዋሪ እነዚህ ሰዎች ምን እንደሚፈልጉ ይታዘብ::
የጎጃም ኮማንድፖስት ትናንት በጎንጂ ቆለላ ፣ በገርገጭ ፣ በአጊታ ፣ በመርዓዊ እና በቲሊሊ ባደረገው ማጽዳት የጽንፈኛው ሀይል ተመቷል ፤ የጦር መሳሪያም ተማርኳል ።
በሰሜን ጎጃም የተሰማራው ኮር በተለያዩ ቀጠናዎች ባደረገው አሰሳና ፍተሻ በድምሩ 41 ጽንፈኛ ሲደመሰስ 11 ተማርኳል ። ስድስት ከሕዝብ የተዘረፉ ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል ።
ሠራዊቱ ከአማራ ክልል የፀጥታ ሀይል ጋር በመቀናጀት በወሰደው ርምጃ ፣ በጎንጅ ቆለላ ዙሪያ 15 ፣ በገርጨጭ አራት ፤ በዜጋንታ ቀበሌ ላይ ዘጠኝ ተመቷል ።
በመርሀዊ አንድ የፅንፈኛ ታጣቂ ከነ ሙሉ ትጥቁ በቁጥጥር ስር ውሏል። በቲሊሊም ሦስት የፅንፈኛው አባላት ቆስለው በቁጥጥር ስር ውለዋል። የአዴት ከተማ ሚሊሺያና ፓሊስ አጊታ ከተማ የነበረውን ፅንፈኛ በማጥቃት 13 በመደምሰስ አራት ኤ ኬ ኤም እና ሌሎች መሳሪያዎች ተማርከዋል።
የ5ኛ ሬጅመንት አዛዥ ሻለቃ ወንድወሰን ጋሻው እንደተናገሩት ፣ የሕዝብን ሰላም ሲነሳ በነበረው ጽንፈኛ ላይ የተወሰደው የህግ ማስከበር እርምጃ ህብረተሰቡን ያስደሰተ ነው ።
ሠራዊቱ የቆመለትን ሕዝባዊ አላማ ከግብ አድርሶ ጎጃም ሰላም እስኪሠፍን ድረስ ጽንፈኛውን ከየተደበቀበት እያወጣን ለህግ ማቅረባችንን እንቀጥላለን ብለዋል።