natnaelmekonnen21 | Неотсортированное

Telegram-канал natnaelmekonnen21 - Natnael Mekonnen

169400

በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7 Facebook.com/natnaelmekonnen.et Instagram.com/natnaelmekonnen21

Подписаться на канал

Natnael Mekonnen

ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች

ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተ‍እ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበ‍ኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።

ሚለየን ምንድነው?

የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ

🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።

🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።

🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።

🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።

🪄We Care

አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ

📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69

www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ስንት አማራ መሞት አለበት?

አንተ በዲያስፓራ ላይ አንዲት ኑሮህ ዘነፍ ሳይልብህ እንቅልፍህን በሰላም ለጥጠህ ከተነሳህ በኋላ ፍሪጅህን አተራምሰህ ሆድህ እስኪወጠር ከበላህ በኋላ ፌስቡክ ላይ ተጥደህ ምንም ትርጉም በሌለው ጦርነት ያለቁትን የድሀ ገበሬ ልጆች "የጀግና ሞት ነው የሞተው" "ታጋይ ይሞታል እንጂ ትግል አይሞትም" እና ዝባዝንኬ ተረቶችን እየቸከቸኩ ከፎቶ ጋር አድርጎ እየለጠፉ ማቅራራት እና የአዞ እንባ እያነቡ ያዘኑ መምሰል ለአማራው ማሰብ ሳይሆን በደሀ ነፍስ ማላገጥ ነው፡፡

ይልቅስ የአማራው ህዝብ ጉዳይ ይቆረቁረኛል ስለዚህ ጦርነት መፍትሄ ነው ብለህ ከልብህ ካመንክ ዲያስፓራ ላይ ተጎልተህ እያቅራራህ እና እየፎከረክ የደሀ ገበሬ ልጆች አንተ ለምትመኘው ስልጣን ወይንም ለውጥ ህይወታቸውን እየገበሩ እንዲያመጡልህ በየሶሻል ሚዲያው መቀስቀስ ሳይሆን፤ ወያኔ ካለህና የምር ለህዝብ ተቆርቋሪ ነኝ ብለህ የምታስብ ከሆነ ኑሮህን እርግፍ አድርገህ ጥለህ ተነስተህ ጫካ ገብተህ ዲሞትፎር እና ክላሽህን ተሽከምህ እየተዋጋህ በተግባር አሳየኝ እንጂ ፌስቡክ ላይ ጀግና ለመምሰል አታቅራራብኝ፡፡

አለበለዚያ አንተ ቅልጥጥ ያለ የተደላደለ ኑሮህን እየኖርክ ደሀው ገበሬ ህይወቱን እየገበረ፤ እየደማና እየቆሰለ፤ አካሉ እየጎደለ፤ ልጆቼን ዛሬ ደግሞ የት ልደብቅ እያለ እየተጨነቀ፤ ቤት ንብረቱ እየወደመበት፤ ከቀየው ሳይወድ በግዱ እየተሰደደ፤ በረሀብ እና በቸነፈር እየተጠበሰ እና በጦርነት ነበልባል በየቀኑ እየተለበለበ እስካሁን ያሳላፈቻው አሰቃቂ ህይወቶች ምንም ሳያሳዝኑህ ዛሬም ሶፋ ላይ ተጎልተህ ቦርጭህን እያሻሸህ ለዳግም ጦርነት ስትቀሰቅሰው እያዘንክለት እና እያሰብክለት ሳይሆን ዘላለማዊ ሲኦል ህይወቱን እንዲገፋ እየተመኘህለት እንደሆነ እውቀው፡፡

ለመሆኑ የአንተ የስልጣን ጥማት፤ አሊያም የንዋይ ፍቅር፤ አሊያም አብይ አህመድ ላይ ያለህ ጥላቻ ከውስጥህ እስኪወጣ ድረስ ስንት አማራ መሞት አለበት?

ለማንኛውም በድጋሚ በቅርቡ ህይወቱ ላለፈው ሻለቃ ውብአንተ እና በዚህ ጦርነት ውስጥ ህይወታቸውን ላጡ በሙሉ አላህ ፈጣሪ በገነት ያኑረው፡፡

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንትና የጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ ክቡር ሳልቫ ኬር ማያርዲት የሀገሪቱን ታላቁን ኒሻን ለኢፌዴሪ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አበረከቱ ።

በደቡብ ሱዳን ብሄራዊ ቤተ-መንግስት በተካሄደው ታላቅ ስነ-ስርዓት የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት እንዲሁም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለደቡብ ሱዳን ህዝብ ነፃነትና ሉአላዊነት መከበር ለከፈሉት ታላቅ የደም መስዋዕትነትና ድጋፍ ክብር ይገባቸዋል በማለት የሀገሪቱን ታላቅ ኒሻን ማበርከታቸው በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል ።

ክቡር ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኬር ይህንን ታላቅ ኒሻን በቤተ-መንግስታቸው ሲያበረክቱ እንደገለፁት ኢትዮጵያ በቸገረን ጊዜ ሁሉ መጠጊያችን መጠለያችን ከመሆኗም በላይ ለዚህ ሀገራዊ ነፃነታችን ክብር የሆኑ በሺህዎች የሚቆጠሩ ልጆቿን ህይወት ጭምር በመክፈል እንደሀገር እንድንቆም ያደረጉ ውለታቸውንም መቼም ከፍለን የማንጨርሰው ባለውለታችን ናቸው ብለዋል።

ዛሬም ድረስ የሠራዊታችንን አቅም በመገንባት የውሰጥ ችግር ሲያጋጥመን ሮጠው በመምጣት ችግራችንን የሚጋሩ ኢትዮጵያዊያን ናቸው ሲሉም ተናግረዋል ።

ክቡር ፕሬዝዳንት ሳልቫኬር ዛሬም ከጎናችን ያልተለዩና የቁርጥ ቀን ወንድሞቻችን ከመሆናቸውም በላይ በደም የተሳሰርን ማንም ሊፈታው የማይችል የአንድ ቤተሰብ ልጆች መሆናችንን የሚያረጋግጥ ሽልማታችን እንደሆነ መላው የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን ህዝብ እንዲያውቅልን እንፈልጋለን ብለዋል።

በተጨማሪም ይህንን ታላቅ ሽልማት ለጀግናው የኢፌዴሪ የመከላከያ ሠራዊት የበላይ ሃላፊና የምስራቅ አፍሪካ ፊልድ ማርሻል ለሆኑት ለክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በደቡብ ሱዳን ህዝብ ስም ሳበረክት ታላቅ ኩራት ይሰማኛል በማለት ተናግረዋል።

በስነ- ስርዓቱ ላይ የሀገሪቱ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፣ የሀገሪቱ የደህንነት ከፍተኛ ሃላፊዎች ፣ ጄኔራል መኮንኖችና የኢፌዴሪ መከላከያ ጄኔራል መኮንኖች መገኘታቸውን የጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፅህፈት ቤት ያደረሠን መረጃ ያመላክታል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ቢቢሲ ትግርኛ በጠዋቱ ያጋራን ዜና በትግራይ ክልል የወንድ ዘር ፍሬ ልገሳ ተጀመረ ይለናል:: ምድነው ነገሩ ይህን ጉዳይ የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር ያውቃል ወይ ካወቀስ እንዴት ያየዋል?

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በጎጃም ኮማንድፖስት የተሰማራው ኮር የተሰጠውን ግዳጅ ውጤታማ በሆነ መንገድ በመፈፀም ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል ።

የኮሩ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሎኔል ሰጥዬ አራጌ እንደተናገሩት ፣ ኮሩ በሰከላ ፣ ፈረስ ቤት ፣  ቋሪት ፣  ቁጭ ፣ ቡሬ ፣ ደንበጫ ባደረገው ስምሪት የጽንፈኛውን አከርካሪ መስበር ችሏል ።

በአማኑኤል ፣ ፍኖተ ሰላም ፣ ማንኩሳ ፣ ጅጋ ፣ ኦዳንሽ ፣ ጅጋ ፣ ዋድ ፣ ገንደ ባቦ ፣ አንጆሌ ፣ ድንጋይ በር ፣ ጥያሜ ፣ ዳማ ማርቆስ ፣ ድኩል ቃና ፣ ወገብ ጊዮርጊስ እና ሌሎች አካባቢዎች የህዝብን ሰላም ሲነሳ የነበረውን ዘራፊ ቡድን በደንብ ቀጥቅጦ ሰላም አስፍኗል።

ኮሎኔል ሰጥዬ አራጌ እንዳሉት በነዚህ ስምሪቶች የጽንፈኛው ሀይል በሚገባ ተመቷል ፤ ሲጠቀምባቸው የነበሩ ሰባት ፒ ኬ ኤም መትረየስ ፣ አንድ ድሽቃ ተማርኳል ፣ በርካታ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች ፣ ቦምቦች እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎች ተማርከዋል ። ከህዝብ ተዘርፈው በየጥሻው ተደብቀው ገንዘብ ሲጠይቅባቸው የነበሩ በርካታ ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አረጋግጠዋል።

ኮሩ ከአማራ ክልል የፀጥታ ሀይሎች ጋር በመጣመር በተገኘው ሰላም አሁን ላይ በመቶ ሺህ የሚቆጠር የአፈር ማዳበሪያ እየተከፋፈለ ይገኛል ፤ ዜጎች ወደ ፈለጉበት ቦታ በትራንስፖርት በነፃነት መንቀሳቀስ ችለዋል ፤ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ፣ ትምህርት ቤቶች ፣ ባንኮች ስራቸውን ጀምረዋል ብለዋል ኮሎኔል ሰጥዬ ።

የጎጃም ህዝብ ለሠራዊቱ 24 በሬ እና 10 ፍየል በመስጠት ለሠራዊቱ በተሰማራበት ሁሉ እያደረገ ያለው ድጋፍ የሚያበረታታ ነው ያሉት ኮሎኔል ሰጥዬ ፣ ሠራዊቱም ለቤተክርስቲያን ማሰሪያ 60 ሺህ ብር ከመስጠት ጀምሮ ሠራዊቱ ካለው ሬሽን በማካፈል እና ሰብል በመሠብሰብ ህዝባዊ ወገንተኝነቱን በተግባር ማስመስከሩን አስረድተዋል ።

ኮሩ በተሰማራባቸው ቀጠናዎች ከህዝቡ ጋር የተደረጉት ስብሰባዎች ላይ ህብረተሰቡ ሰላም ፈላጊ መሆኑን በግልፅ ተናግሯል ብለዋል ። ህዝቡ ሀብቱ ፣ ንብረቱ በጽንፈኛው ሲዘረፍበት እንደነበረና አሁን ሠራዊቱና የክልሉ ሀይል ባደረጉት ኦፕሬሽን እፎይ ማለቱን በውይይት ገልጿል ሲሉ ተናግረዋል ።

ኮሎኔል ሰጥዬ ፣ አብሯቸው የተሰለፈው የአማራ ክልል ፀጥታ ሀይል እየፈጸመ ያለውን ጀግንነት አድንቀዋል ። ለአብነት ባለፈው ሳምንት በፈረስ ቤት ፣ በቋሪት ፣ በገሊላ ፣ ድንጋይ በር ፣ በሰከላ እና ሌሎች ቦታዎች ያደረጓቸውን ስምሪቶች ውጤታማ በሆነ መንገድ መፈፀማቸውን አረጋግጠዋል ።

ኮሩ ተልዕኮውን በብቃት በመወጣቱ በመጣው ሰላም መላው ጎጃም አዝመራውን ሲሰበስብ ሠራዊቱ ደስተኛ ሆኗል ያሉት ኮሎኔል ሰጥዬ ፣ አሁንም የህግ ማስከበሩን ግዳጅ በተጠናከረ መልኩ በመፈፀም ጽንፈኛውን ከየተደበቀበት ጫካ አድነን በማውጣት የህዝባችንን ሰላም እናረጋግጣለን ብለዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

Egypt, mired in economic crisis, sells off its land and infrastructure to Gulf countries For the past decade, the heavily indebted country has been selling off tourism, agricultural and port assets to the United Arab Emirates and Saudi Arabia. https://www.lemonde.fr/en/economy/article/2024/03/18/egypt-mired-in-economic-crisis-sells-off-its-land-and-infrastructure-to-gulf-countries_6629364_19.html

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ከ5 ወራት በላይ በተደረገ ክትትል በአዲስ አበባ እና አዋሳኝ አካባቢዎች በትጥቅ የታገዘ ሁከት እና ብጥብጥ ለመፈፀም በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 50 ተጠርጠሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል አስታወቀ፡፡

ከስር መምስሉ ላይ የምታይዋቸው ናቸው ዛሬ በቁጥጥር ስር የዋሉት

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ሕወሐት ስብሰባ ላይ ነው።

ከአፍሪካ ኅብረት የታዛቢዎች ቡድን ስብሰባ የሚጠብቀውን ያላገኘው ሕወሐት አስቸኳይ ስብሰባ ገብቷል።

በቀደም ዕለት ጠቅላይ ሚር ዐቢይ አሕመድ ለትግራይ ተወካዮች የተናገሩትንና አወዛጋቢ አካባቢዎችን እንዲፈታ የተቋቋመው ኮሚቴ የ።ረሰበትን ከገመገመ በኋላ ሕወሐት አጀንዳውን ቀይሯል።
የስብሰባው ዋና አጀንዳ የትግራይን ግዛት ማስመለስ የሚል ሆኗል። ጊዜያዊ አስተዳደሩንም በተንበርካኪነት ከስሷል። ከአውሮፓ ሕክምና አቋርጦ የመጣው ጌታቸው ረዳ " ብልጽግና ሆኗል" ተብሎ ሲወቀስ ሰንብቷል።

ከክረምቱ በፊት ወልቃይትን መያዝ እንደሚቻልና ከአንዳንድ የአማራ ታጣቂዎች ጋር በጉዳዩ ላይ መግባባት መኖሩ በስብሰባው ተነሥቷል። ወርረን ከያዝን በኋላ ስለ ሕዝበ ውሳኔ መነጋገር ይሻላል የሚል አቅጣጫም ተቀምጧል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

Good news : በትግራይ ክልል በጦርነት ሳቢያ የተቋረጠው የጡረታ ክፍያ “በፖለቲካዊ ውሳኔ” እንዲከፈል ተባለ

ለሁለት ዓመታት በትግራይ ክልል በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት የጡረታ ገንዘብ ያልተከፈላቸው ጡረተኞች፤ “በፖለቲካዊ ውሳኔ” መሰረት ደመወዝ እንዲከፈላቸው መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታና የጡረታ ፈንድ የቦርድ አባል እዮብ ተካልኝ ገለጹ።

እንደ ሚኒስቴር ዴኤታው ገለጻ የጡረታ መዋጮ ባልተሰበሰበበት ሁኔታ ጡረታ እንዲከፈል የሚፈቅድ አሰራር አለመኖሩ ችግሩ በፖለቲካዊ ውሳኔ እንዲፈታ አድርጓል።

በዚህም ከፕሪቶሪያው ስምምነት በፊት ክፍያ ተቋረጦባቸው የነበሩ ጡረተኞች፤ በሚቀጥሉት ሳምንታት ክፍያ ይፈፀምላቸዋል ማለታቸውን የአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣቢያ ዘግቧል።

ከቀናት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከትግራይ ክልል ከመጡ የህዝብ ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት፤ የጡረተኞች የደመወዝ ክፍያ አልተፈጸመም የሚል ቅሬታ ማቅረባቸው አይዘነጋም።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይታቸው “ከሚመለከታቸው የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተነጋግሬ በአጭር ጊዜ ምላሽ ይሰጣል” ብለው ነበር።

በትግራይ ክልል የሚኖሩ ጡረተኞች ላለፉት 17 ወራት ያልተከፈላቸውን የጡረታ ደመወዝ እንዲከፈላቸው በሰላማዊ ሰልፍና በተለያየ መንገድ ሲጠይቁ መቆየታቸውን አዲስ ማለዳ መዘገቧ ይታወሳል።

የካቲት 21 ቀን 2016 “ከመሞታችን በፊት ድረሱልን” በማለት የጡረታ ደመወዛቸው እንዲከፈላቸው በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀው ነበር።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች

ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተ‍እ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበ‍ኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።

ሚለየን ምንድነው?

የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ

🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።

🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።

🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።

🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።

🪄We Care

አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ

📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69

www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የሰራናቸው ስራዎች ተመልሶ አጠፋን:: አንዳርጋቸው ጽጌን ያሰርኩት እኔ ነበርኩኝ:: አንዳርጋቸውን ሳላገኘው ቁጭ ብዬ ሳላወራው ቁጭቱን እይታውን መረዳት ነበረብኝ:: ላጠፋው ሞክሬ አልቻልኩም:: ኮረኔል ቢንያም ተወልደ

እስከዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ታስረው ከተፈቱ በኃላ የተረጋጉና በእስር ወቅት ግዜ አግኝተው ብዙ ነገሮችን እንዲያጤኑና እንዲያስቡ አድርጎ እስር ወደ እውነታ ካመጣቸውና ካስተማራቸው ሰዎች ውስጥ አንዱ የቀድሞ የኢንሳ ጀነራል ዳሬክተር ኮረኔል ቢንያም ተወልደ ይመስለኛል::

ቢንያም ከእስር ከተፈታ በኃላ ያደረጋቸውን ሁለት ኢንተርቪዎች ደጋግሜ አድምጫቸዋለሁ ፍጹም የተረጋጋና በስልጣን ዘመኑ ሲያደርጋቸው ስለነበሩት ነገሮች በቁጭት መልኩ ለምን እያለ ያወራል:: ቢንያም ውስጥ እርጋታን ብቻ ሳይሆን ፍጽም ይቅርታንና ይቅር ባይነትን እያዛመደ ነበር በቁጭት ኢንተርቪውን የሰጠው የሰው ልጅ ያጠፋል ይሳሳታል ከስህተቱ ተምሮ በዚህ ደረጃ እውነትን ይዞ ሌላ ጥፋት እንዳይጠፋ በቁጭት ሚዲያ ላይ በመውጣት መናገር ማስተማር መመስከር መቻል መቼም መታደል ነው:: የቢንያም ኢንተርቪዎች ለሁላችንም መማሪያ ይሆን ዘንድ ክፍል 1 https://youtu.be/Ip3mEQwAlGY?si=wPpUVJ2uJxSXnxXM

ክፍል 2 https://youtu.be/xWLMPlacmes?si=4JiwcxKuMKgnWLq4

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ፕሬዝዳንት ፑቲን ሶስተኛው የዓለም ጦርነት ሊነሳ ጫፍ ላይ መድረሱን ተናገሩ

የኔቶ ወታደሮች በዩክሬን መግባታቸውን እንደሚያውቁም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል

ሩሲያ ደህንነቷን ለማስከበር ስትል ተጨማሪ ግዛቶችን ከዩክሬን ልትወስድ ትችላለች ተብሏል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/49Ye30I

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

#ፑቲን

ቭላድሚር ፑቲን ለቀጣይ 6 ዓመታት ሩስያን መምራት የሚያስችላቸውን የምርጫ ውጤት ማስመዝገባቸው ተነገረ።

ሩስያን በፕሬዜዳንትነት እየመሩ የሚገኙት የቀድሞው የKGB ሰላይ ቭላድሚር ፑቲን በሀገራቸው የተካሄደውን የፕሬዜዳንታዊ ምርጫ በከፍተኛ ብልጫ ማሸነፋቸውን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ባለፉት 3 ቀናት በመላ ሩስያ ህዝቡ ድምፅ ሲሰጥ ቆይቷል።

የ71 ዓመቱ ፑቲን " ጠንካራ ተቀናቃኝ አልገጠማቸውም " በተባለው በዚህ ምርጫ ከ87% በላይ ድምፅ በማግኘት ሀገሪቱን በፕሬዜዳንትነት መምራት እንዲቀጥሉ የሚያስችላቸውን ውጤት እንዳገኙ ተገልጿል።

ፑቲን ለቀጣይ 6 ዓመታት ሩስያን ይመራሉ።

በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲሁም በፕሬዜዳንትነት ረጅም ዓመታትን የሀገሪቱን ዋነኛ ስልጣን በመያዝ እየመሩ የሚገኙት ቭላድሚር ፑቲን ይኸኛው የ2024ቱ ምርጫ ለ5ኛ የስልጣን ዘመን ያሸነፉት ምርጫ ነው።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

70 ሺህ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ሊመለሱ ነው

በሳዑዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን የመመለስ ስራ በ2 ሳምንት ውስጥ ይጀመራል ተብሏል። መንግስት ከዚህ ቀደም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሃገር መመለሱ ይታወቃል።

ዝርዝሩን በተከታዩ ሊንክ ይመለከቱ፤ https://bit.ly/4aiszAV

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

አቶ ነብዩ ተድላ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ሆነው ተሾሙ

አቶ ነብዩ በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ለ22 ዓመታት በዋናው መስሪያ ቤት እና ሚሲዮን ጽህፈት ቤቶች ሲሰሩ ቆይተዋል። በተጨማሪም በምክትል ቃል አቀባይነት መስራታቸውም ተገልጿል።

አቶ ነብዩ በኒዮርክ፣ ሪያድ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሌሎችም ሀገራት እና ከተሞች በዲፕሎማትነት ማገልገላቸውን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። አቶ ነብዩ በዛሬው ዕለት ከውጭ ጉዳይ ቋሚ ዘጋቢዎች ጋር ተዋውቀዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በህገ-ወጥ መንገድ 400 የክላሽ ጥይት ወደ ሽንፋ በማስገባት ለፅንፈኛው ቡድን ሊያቀብል የነበረ ግለሰብና ግብረ አበሮቹ  በቁጥጥር ስር ውለዋል።

መነሻውን ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ቋርድባ ቀበሌ አድርጎ  ወደ ምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ቁጥር አንድ ቀበሌ 400 ጥይት በህገ-ወጥ መንገድ ተገዝቶ ከቁጥር አንድ ወደ ሽንፋ በሞተር ሳይክል ሊገባ ሲል በመከላከያ ሠራዊት አባላት ጥብቅ ክትትል በቁጥጥር ሊውል መቻሉን በስፍራው የሚገኝ የአንድ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ዘውዱ ተሾመ ተናግረዋል።

አስቻለው አያናው የተባለው የ37 ዓመት ጎልማሳና
ተባባሪው እያቸው ፈጠነ ወርቁ የተባለ የ32 ዓመት ወጣት በህገ-ወጥ መንገድ የገዙትን አራት መቶ ጥይት እንዲሁም በፀሃይ ብርሃን የሚሰራ ሶላር በሞተር ሳይክል ጭነው ለማለፍ ሲሞክሩ በስፍራው በሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ምክትል አዛዡ ገልፀዋል።

የክፍለጦሩ ሠራዊት ፅንፈኛውን ፈልጎ የመምታትና የፅንፈኛውን ተላላኪዎች ሴራና እንቅስቃሴ በትኩረት የመከታተል፣ ጥብቅ ቁጥጥር የማድረግና ሲገኙም ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ለሜድረግ ሌት ተቀን እየሠራ መሆኑንም ሌተናል ኮሎኔል ዘዉዱ ተሾመ ተናግረዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች

ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተ‍እ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበ‍ኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።

ሚለየን ምንድነው?

የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ

🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።

🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።

🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።

🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።

🪄We Care

አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ

📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69

www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

Must Watch https://youtu.be/uWUR_AgII_k?si=pwfXlmpOZgzz5m5O

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

የህዳሴ ግድብ 5 ተርባይኖች በመጪው ሳምንታት ሀይል ማመንጨት ይጀምራሉ  ተባለ፡፡

ግንባታው ባይጠናቀቅም በ2 ተርባይኖች ሀይል ማመንጨት ጀምሯል የተባለው ታላቁ የህዳሴ ግድብ፤ ተጨማሪ የሀይል አመንጪ ተርባይኖች ስራ እንዲጀምር እየተሰራ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

5 ተርባይኖችም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ሀይል ማመንጭ ይጀምራሉ  ተብሏል፡፡

ይህንን ለሸገር የተናገሩት የግድቡ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ናቸው፡፡

በአሁኑ ሰዓትም ለጅቡቲ፣ ለሱዳን እና ለኬንያ የኤሌክትሪክ ሀይል እየተሸጠ መሆኑን ያስታወሱት ዶ/ር አረጋዊ፤  ለታንዛኒያ እና ለደቡብ አፍሪካ ለመሸጥ ታቅዶ ንግግር ተጀምሯል ብለዋል፡፡

ለተገባደደው የግድቡ ስራ አሁን የሚቀሩት በአብዛኛውም ከውጭ የሚገቡ የመካኒካል እና ኤሌክትሪካል ግብአቶች ናቸው፤ አጠቃላይ ግንባታውም በ1 ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ መገመቱንም ዋና ዳይሬክተሩ አውርተውናል፡፡

የህዳሴ ግድቡ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት እስካሁን 18.9 ቢሊዮን ብር እንደሰበሰበም ተነግሯል፡፡

የህዝቡ ተሳትፎ በጎ የሚባል ቢሆንም አሁንም ድጋፍ እንዳይቀዘቅዝ የጽ/ቤቱ ዳይሬክተር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ አሳስበዋል፡፡

ከተጀመረ 13ኛ ዓመቱን የያዘው የህዳሴ ግድብ 95 ከመቶው ተጠናቋል የተባለ ሲሆን ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ለማጠናቀቅ 300,000,000  ዶላር እንደሚፈጅ መገመቱም ሰምተናል፡፡

የግድቡ ስራ በ2015 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ እንደነበርም አይዘነጋም፡፡

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ELEGAS ENGINEERING PLC
የእርስዎ አሳንሰር መፍትሄ ባለሙያዎች

ለ Elevator እና ለEscalator ከፍተኛ ደረጃ የምህንድስና መፍትሄዎች ያስፈልጎዎታል? በኢንዱስትሪው ውስጥ ግንባር ቀደም ኩባንያ ከሆነው ELEGAS ኢንጂነሪንግ አለሎት። ባለን ሰፊ ልምድ እና እውቀት ላለፉት 17 አመታት በአስራ በአምስት ሀገራት በልዩ ጥራተ‍እ አገልግሎት ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት የአገር ውስጥ ገበያን እያገለገለ አዲሱን የግንባር መስሪያ ቤታችን በኢትዮጵያ መከፈቱን በደስታእንገልፃለን።
በ ELEGAS ምህንድስና፣ ልዩ ፍላጎቶችዎን ለማሟላት የተዘጋጁ ምርጥ የምህንድስና መፍትሄዎችን በማቅረበ‍ኣችን እንኮራለን። የድርጅታችን ባለ ሞያዎች በምንሰራው እያንዳንዱ ፕሮጀክት የላቀ ጥራት ለማቅረብ ቁርጠኛ ናቸው።

ሚለየን ምንድነው?

የገጠማ ስራን ጨምሮ በአራት ወራት ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን አሳንሰሮች ከቱርክ የማድረስ ችሎታችን። ጊዜ ወሳኝ ነዋ

🖊️ በተጨማሪም ከእያንዳንዱ ሊፍት ግዢ ጋር ጥቅል እናቀርባለን። በምርቶቻችን ላይ ለጋስ የሁለት ዓመት ዋስትና ያገኛሉ። በተጨማሪም የአሳንሰርህን ረጅም ዕድሜ እና ጥሩ አፈጻጸም ለማረጋገጥ የአንድ አመት ነጻ ጥገና እናቀርባለን።

🖊️ የዋጋ አወጣጥን በተመለከተ፣ የፕሮጀክትዎን ፍላጎት የሚያሟላ ተለዋዋጭነት እናቀርባለን።

🖊️ FOB፣ CIF፣ ወይም DDP፣ የዋጋ አወጣጥ አማራጮቻችንን ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር በማዛመድ እናዘጋጃለን።

🖊️ ገጠማ የሚደርጉላችሁ የበርካታ
አመታት ከቱርክ የመጡ ልምድ ያላቸው crewዎች ናቸው።

🪄We Care

አድራሻ:- ቡልጋሪያ ማዞሪያ የትራፊክ መብራት አጠገብ አዌባነ ህንፃ 1ኛ ፎቅ

📞
+251 971 71 71 71
+251 994 69 69 69

www.elegas.com.tr

Email:- ethiopia@elegas.com.tr

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በአዲስ አበባ ሁከት እና ብጥብጥ ለመፈፀም በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 50 ተጠርጠሪዎች ለጥፋት ተልዕኮ ሲንቀሳቀሱ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በአዲስ አበባ እና አዋሳኝ አካባቢዎች በትጥቅ የታገዘ ሁከት እና ብጥብጥ ለመፈፀም በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 50 ተጠርጠሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል አስታወቀ፡፡

ይህንን የተመለከተው የጋራ ግብረ- ኃይል ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

በአዲስ አበባ እና አዋሳኝ አካባቢዎች በትጥቅ የታገዘ ሁከት እና ብጥብጥ ለመፈፀም በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 50 ተጠርጠሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል አስታወቀ

የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ይህ የጥፋት ቡድን ቀደም ሲል አማራ ክልልን የነውጥ እና የብጥብጥ ማዕከል ለማድረግ የነበረው የጥፋት ሴራ በክልሉ የፅጥታ ሀይል፡ በሀገር መከላከያ ሰራዊት እና በፌደራል መንግስት የተቀናጀ ኦፕሬሽን ስለከሸፈበት፤ይሄንኑ እኩይ ዓላማውን ወደ ማዕከል በተለይም ደግሞ በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በማምጣት የሁከትና የሽብር ተልዕኮው መፈፀሚያ የማድረግ እኩይ ሴራ መሆኑን ግብረ ሀይሉ ጠቅሷል፡፡

መግለጫው አክሎም፤በቁጥጥር ስር የዋለው የተደራጀው የህቡዕ ቡድን ዋና ማዕከሉን አዲስ አበባ እንዲሁም በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ በማድረግ በልዩ ሁኔታ ያዘጋጀውን የታጠቀ ኃይል ከህቡዕ ቡድኑ ጋር በማስተሳሰር በተናበበ እና በተቀናጀ መንገድ አዲስ አበባንና የኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎችን የሁከት፡የብጥብጥ እና የሽብር ሴራው ኢላማ የማድረግ እኩይ ተልዕኮ አንግቦ ሲሰራ ቆይተዋል፡፡

ቡድኑ ለአደረጃጀቱ ምቹ ሁኔታ ይፈጥሩልኛል የሚላቸውን አንዳንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተከታዮችን በመጠቀም ተቋማትን መሰብሰቢያ እና ማደራጃ በማድረግ በህቡዕ ሲንቀሳቀስ እንደነበር መረጋገጡን መግለጫው አመልክቷል፡፡

በህቡዕ ተደራጅቶ ሲንቀሳቀስ የነበረው ቡድኑ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች አባላትን የመመልመልና እና ሎጀስቲክስ የማደራጀት ሥራዎችን ሲያከናውን እንደቆየ የጠቆመው መግለጫው፤ ቡድኑ በአማራ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች የጥፋት መረብ ዘርግቶ ከሚንቀሳቀሰው ፀረ ሰላም ሀይል ጋር የህቡዕ ትስስር በመፍጠር እና ተልዕኮ በመቀበል አዲስ አበባ እና የኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎችንም ጭምር የድብቅ ሴራው አካል አድርጎ ሲንቀሳቀስ በዋናነት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባለፉት አምስት ወራት ባካሄደው ጥብቅና ሚስጥራዊ ክትትል እንደተደረሰበትና የክትትል ግኝቱም ለጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ቀረቦ ከተገመገመ በኋላ ወደ ተቀናጀ ኦፕሬሽን በመግባት በተጠርጠሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን መግለጫው አመልክቷል፡፡

ለቡድኑ በአዲስ አበባና በአወሳኝ አካባቢዎች እኩይ ተግባር እንዲፈፅም የጥፋት ተልዕኮ የሰጡት በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ፀረ ሰላም ሀይሎች በክልሉ በትጥቅ የታገዘ ጥቃት በንፁሃን፣በመንግስት አካላትና በፀጥታ ሀይሎች ላይም ጭምር በመፈፀም መንግስትን በኃይል ከስልጣን ለማስወገድ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም ያለው የጋራ ግብረ ሀይሉ መግለጫ፤ ይህ እኩይ ሴራቸው በመንግስት ፀጥታ ሀይሎች በመክሸፉ እና በዚህም የቁም ቅዥት ውስጥ በመግባታቸው የተሰጣቸውን ተደጋጋሚ የሰላም አማራጭ ከመጠቀም ይልቅ አሁንም በህግወጥ ተግባራቸው በመቀጠላቸው በመንግስት ፀጥታ ሀይሎች የማያዳግም እርምጃ እየተወሰደባቸው መሆኑ በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

የህቡዕ አደረጃጀት ፈጥሮ የነበረው ይህ ቡድንና ተባባሪዎቹም፤ በትጥቅ የታገዘ ሁከት እና ብጥብጥ በአዲስ አበባና በአዋሳኝ አካባቢዎች ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ ከተለያዩ የጦር መሳሪያዎች፣ ተተኳሾች፣ቦንቦች፣ ተቀጣጣይ ቁሶች እንዲሁም የተከማቹ ለቡድኑ የቀለብ አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ ግብአቶች፣ የተለያዩ ሀገራት የገንዘብ ኖቶች፣ የባንክ ደብተሮች እና የተለያዩ ሰነዶች ጋር መያዛቸውን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል አስታውቋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት 50 ተጠርጣሪዎች ውስጥም የቡድኑ መሪ ስንታየሁ ንጋቱ ገብረ እየሱስ በቅፅል ስሙ አብርሃም እንዲሁም ለቡድኑ ፋይናንስ፡ ሎጀስቲክስና ሃብት አፈላላጊ አመራር ሆነው ሲሰሩ የነበሩት ፋሲል ጌታቸው እና ተወልደ ብርሀን የተባሉ ተጠርጣሪዎችም እንደሚገኙበት የጋራ ግብረ ሀይሉ መግለጫ አመልክቷል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሴራው ዋነኛ ጠንሳሾች በተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚገኙ የቡድኑ አስተባባሪዎች በዋናነትም ሺ አለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ፡ ሀብታሙ አያሌው እና መሳይ መኮንን እንዲሁም በሀገር ውስጥ በእስክንድር ነጋ የሚመራው የጥፋት ሃይል እና ቀደም ሲል ቡድኑን በበላይነት ሲመሩ የነበሩት በአሁኑ ሰዓት በህግ ቁጥጥር ሥር በማረሚያ ቤት የሚገኙ የእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ፡ ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው እና ዮርዳኖስ ዓለሜ የሚመራ መሆኑን መግለጫው ጠቁሟል።

ህቡዕ ቡድኑ አደረጃጀቱን ከህዳር 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሰነድ በማዘጋጀትና የጋራ መግባባት በመፍጠር የራሱ ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ፣ የመረጃ እና ፋይናንስ እንዲሁም የሚዲያ እና የፕሮፖጋንዳ ክንፍ የሚል መዋቅር በመፍጠር ሲንቀሳቀስ መቆየቱንም ግብረ-ኃይሉ በመግለጫው ጠቁሟል፡፡

የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል፤ የእምነት ተቋማት አማኙ በቅንነት ሄዶ የእምነት ስራውን የሚፈፅምባቸው መሆኑን በመረዳት እኩይ ዓላማ ያላቸው የጥፋት ሀይሎች የእምነት ቦታዎችን ለጥፋት ተልዕኮ እየተጠቀሙበት በመሆኑ፤ህብረተሰቡም ሆነ የሚመለከታቸው አካላት ከእምነቱ ስርዓት ውጭ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ላይ ጥብቁ ቁጥጥርና እና የእርምት እርምጃዎች እንዲወሰድባቸው ግብረ ሀይሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡ህዝቡም ከፀጥታና ደኅንነት አካላት ጎን በመቆም የጥፋት ሀይሎችን ለማጋለጥ የጠለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ግብረ ሀይሉ ጠይቋል፡፡

ፀረ ሰላም ሀይሎች በተደጋጋሚ የሚያደርጓቸው የጥፋት ሴራዎች ከፀጥታና ደኅንነት አካላት አይንና ጆሮ የማያመልጡ መሆኑን አውቀው፤ ከጥፋት መንገዳቸው ተመልሰው መንግስት ያዘጋጀውን የሰላም አማራጭ እንዲጠቀሙበት የጋራ ግብረ ሀይሉ ያሳስባል፡፡ለዚህና መሰል የጥፋት ተልዕኮዎች መሳሪያ እየሆኑ ያሉ ንፁሃን ዜጎችም ራሳቸውን ከእንደዚህ ዓይነቱ ድርጊት እንዲቆጠቡ ይመክራል፡፡

ለጥፋት ሀይሎች የፋይናንስና የሎጅስቲክስ ድጋፎችን በማድረግ ሀገሪቱን የትርምስ ቀጠና ለማድረግ እየሰሩ ያሉ ሀይሎች ከእኩይ ዓላማቸው እንዲቆጠቡ በዚህ አጋጣሚ ግብረ ሀይሉ ያሳስባል፡፡

በመጨረሻም ለኦፕሬሽኑ መሳካት ማህበረሰቡ ለፀጥታና ደኅንነት ግብረ -ኃይሉ ላሳየው ጠንካራ ድጋፍ እና የዘወትር ትብብር የጋራ ግብረሃይሉ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

በቀጣይም የእነዚህን ፀረ ሰላም ኃይሎች እኩይ የጥፋት ዓላማ በማክሸፍ በኩል እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን በመደገፍና ወንጀለኞችን በማጋለጥ ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የጋራ ግብረ ኃይሉ ጥሪውን እያቀረበ ሕጋዊ እርምጃው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ አረጋግጧል፡፡

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል

መጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ.ም

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች እና ከተለያዩ ክልሎች ከተወጣጡ አባቶች ጋር ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል።ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በዳባት ወረዳ በአጅሬ ጃኖራ አካባቢ የህዝቡን ሰላማዊ ኑሮ ሲያውኩ የነበሩ የፅንፈኛ ሃይሎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ።

በሰሜን ጎንደር ዞን በዳባት ወረዳና አካባቢው፣በህዝብ ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ሲያደርስ የነበረውን የፅንፈኛ ሃይል በመቆጣጠር አሁን ላይ በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን በማድረግ ላይ የሚገኙ የክፍለ ጦሩ  የሠራዊት አባላት፣ ግዳጃቸውን በከፍተኛ ህዝባዊነትና በቁርጠኝነት እየተወጡ መሆኑ ተገልጿል።

የሻለቃው አዛዥ ሻለቃ ተስፋሁን ኮኬ፤ የአካባቢውን የፀጥታ ስጋት ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ እየሰራን ነው ብለዋል።

ሻለቃው ግዳጁን እየተወጣ ያለው የየአካባቢውን ነዋሪዎች በማወያየት ከፀረ ሰላም ሃይሉ ጋር በጋራ ሲሰሩ የነበሩ ሃይሎችን የመለየት ተግባር በማከናወን እንዲሁም በየቀጣናዎቹ የሚሹለከለኩ የጥፋት ሃይሎችን በአስተማማኝ ሁኔታ በመምታት መሆኑንም አስረድተዋል።

በየጊዜው በርካታ የፀረ-ሰላም ሃይሎችን በመቆጣጠርና በመደምሰስ በአካባቢው ሠላም እንዲሠፍን እያደረግን ነው ያሉት ሻለቃ አዛዡ፤ በዚህ ሳምንት ውስጥ በርካታ የፅንፈኛ ሃይሉን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ በርካታ ተተኳሾችን በመማረክና ከህብረተሰቡ ጋር በተደረጉ የማጥራት ስራዎች በመለየት በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ ስራ መሰራቱን ጨምረው ገልፀዋል።

መቶ አለቃ ተስፋየ ጫሌ በበኩላቸው የፅንፈኛ ሃይሉን ኑሮ በማወክና ህብረተሰቡን ለማሰቃየት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የተረዳው ሠራዊታችን በፅንፈኛ ሃይሉ ላይ መጠነ ሰፊ እርምጃዎችን በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየወሰደ ይገኛል ብለዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

በባህር ዳር- ጎንደር ኮማንድ ፖስት በደቡብ ጎንደር ወረታ ልዩ ቦታው  ሸለቆ  መድሃኒያለም በተባለ ስፍራ   በተደረገ  ድንገተኛ ኦፕሬሽን ፅንፈኛው የሚገባውን ቅጣት ማግኘቱን የክፍለጦሩ አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ዘሪሁን ተፈሪ ተናግረዋል።

በወረታና አካባቢው እየተሹለከለከ የህዝቡን ሰላም ሲያውክ በነበረው የፅንፈኛውና ዘራፊው ቡድን ላይ  በስፍራው ተልዕኮ በመፈፀም ላይ የሚገኘው የክፍለጦሯ ሬጅመንት ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ስናይፐር ፣ክላሽ፣ ኤፍ ዋን ቦንብ፣ የወገብ ትጥቅ፣ የጀርባ ትጥቅ በቁጥጥር ስር ውሏል።

አበረ የተባለው የፅንፈኛው ቡድን መሪና ሁለት ወንድሞቹ  እየተዋጉ መያዛቸውንና አጠቃላይ ደግሞ 06 መማረካቸውን እንዲሁም 04 መገደላቸውን የክፍለ ጦሩ አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ዘሪሁን ተፈሪ ተናግረዋል።

የህዝቡን ሠላም ወደ ነበረበት ለመመለስ የሚደረጉ ዘመቻዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የተናገሩት አዛዡ ሠራዊቱ የፅንፈኛውን ግብዓተ መሬት ለማፋጠንና አካባቢውን ወደ ተረጋጋ ሠላም ለመመለስ ዝግጁነቱን ከመቼውም ጊዜ በላይ የላቀ ማድረጉን አዛዡ ገልፀዋል።

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ወርቅና ብር ይዘው መውጣት አይችሉም ሲሉ የነበሩ ሰራተኞች በካሜራ እገዛ በቁጥጥር ስር ውለዋል - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ወርቅና ብር ይዘው መውጣት አይችሉም ሲሉ የነበሩት አካላት የጉምሩክ ክፍልን የሚመለከት እንደነበርና አሁን በካሜራ እገዛ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰሞኑን በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ከመንገደኞች አገልግሎት አሠጣጥ ጋር በተያያዘ ቅሬታ መቅረቡን ተከትሎ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው በመግለጫቸው እንዳሉት እየተሰሙ ያሉ ቅሬታዎችን መርምሮ መፍትሄ ለመስጠት አየር መንገዱ በአዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ አገልግሎት ከሚሰጡ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ቅሬታዎችን የማጣራትና የእርምት እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፡፡

በዚህም ወርቅና ብር ይዘው መውጣት አይችሉም የተባሉት ደንበኛ ጉዳይ ዋነኛው ቅሬታ እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡

ድርጊቱን የፈፀሙት የከስተም ወይም የጉምሩክ ክፍልን የሚመለከት እንደነበር ገልጸው በመሆኑም ግለሰቦቹን በካሜራ እገዛ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርገዋል ብለዋል።

በቀጣይም አየር መንገዱ እንዲህ አይነት ድርጊቶችን የማይታገስ መሆኑንና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እርምጃ እንደሚወስድ አሳስቧል፡፡

የደንበኞች አገልግሎት ለተቋማችን የህልውናችን ዋነኛው ጉዳይ ነው የሚሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው በመሆኑም የደንበኞቻችንን ፍላጎት ለማሟላትና በታማኝነት ለማገልገል በትጋት መስራታችንን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም አሁን ያለው ኤርፖት በአመት እስከ 25 ሚሊየን የሚደርሱ ደንበኞችን እያስተናገደ የሚገኝ ሲሆን ነገር ግን የቢሾፍቱ ማስፋፊያ ኤርፖርት ሲጠናቀቅ ይህን አሃዝ ወደ 100 ሚሊየን ከፍ ያደርገዋል፡፡

ይህም ለደንበኞች የተሻለና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት እገዛ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡

Читать полностью…

Natnael Mekonnen

ናሽ ልዩ የጥርስ ህክምና ክሊኒክ ዘመኑ ባፈራቸው መሳሪያዎ ች በመታገዝ ሙሉ የጥርስ ህክምናን በመስጠት ላይ ይገኛል::  ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል በከፊል
➢ መጥፎ የአፍ ጠረንን ማከም
➢ የቆሸሹ ጥርሶችን በማሽን እናፀዳለን
➢ በህክምና መዳን የማይችሉትን ጥርሶች መንቀል
➢ ወጣ ገባ ያሉ ጥርሶችን በ ኦርቶዶንቲክ አፕላይንስ እና በብሬስ ማስተካከል
➢ የጥርስ ስር ህክምናን መስጠት
➢ የተቦረቦሩ ጥርሶችን እንሞላለን
➢ የተነቀሉ ጥርሶችን በሰው ሰራሽ አርተፊሻል መተካት
➢ የጥርስ ራጅ አገልግሎት መስጠት

አድራሻ: ሜክሲኮ ቡልጋሪያ ጫፍ ትራፊክ ማብራቱ አጠገብ
  Tel: 0913858561

Читать полностью…
Подписаться на канал