#Update
#GOAL ጃደን ሳንቾ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ የቡድን ልምምድ ተመልሷል በማለት ለቆት የነበረው ፎቶ ሳንቾ በልምምድ ላይ እያለ የተነሳው የድሮ ምስል ነው ።
ሆኖም ምንም እንኳን ይሄንን ምስል ተጠቀሙ እንጂ መረጃው ትክክለኛም ሊሆን የሚችልበት እድል አለ። እስካሁን ከክለቡም ሆነ ከታማኝ ምንጮች የተሰጠ መግለጫ የለም !
ቴንሀግም ቢሆን ዛሬ በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት ስለ ሳንቾ ምንም የተናገረው ነገር የለም። አዲስ ነገር ካለ እየተከታተልን እናደርሳችኋለን ።
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
ከጋክፖ ወደ ዌጎረስት?
ዩናይትድ ስለ ኮዲ ጋክፖ እየተወያየ ነበር። ነገር ግን ጆኤል ግሌዘር ከገና በፊት ፤ ለጋክፖ ምንም ገንዘብ እንደማይኖር በአጭሩ ተናግሯል ።
በዚህ የተነሳ ኤሪክ ቴንሀግ ዩናይትዶቹ ተጫዋቹን በውሰት መውሰድ እንደሚችሉ ስለተረዳ ፊቱን ወደ ውት ዌጎረስት አዙሯል ።
የዩናይትድ አመራሮችም በታህሳስ 21 ፤ በካራባኦ ካፕ ከበርንሌይ ጋር ከተደረገው ጨዋታ በኋላ ስለ አጥቂው ዝውውር ከአቻወቻቸው ጋር ተነጋግረው ነበር ።
ቴንሀግ ተጫዋቹ ኮንትራቱን ይፈርም ዘንድ በንግግሩ ውስጥ አብሮ የነበረ ቢሆንም በዝውውሩ ውስጥ 3 ክለቦች መገኘታቸውን ተከትሎ ሂደቱ እጅጉን አዝጋሚ የሆነ ነበር ።
[The Athletic]
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
አሁን ላይ እየወጡ እንደሚገኙ መረጃዎች ከሆነ ጀደን ሳንቾ በእዚህ ሳምንት የዩናይትድ ቡድንን በመቀላቀል ከቡድኑ ጋር ልምምድ ማድረግ የሚጀምር ይሆናል።
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
ክሪስታል ፓላስን ለመግጠም ወደ ለንደን የተጓዙ ተጫዋቾቻችን !
ተከላካዮች
ቪክተር ሊንድሎፍ ፣ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ፣ ራፋኤል ቫራን እና ሀሪ ማጓየር
አማካዮች
ካሴሚሮ ፣ ስኮት ማክቶሚናይ ፣ ፍሬድሪኮ ሮድሪጌዝ እና ክርስቲያን ኤሪክሰን
አጥቂዎች
አንቶኒ ዶ ሳንቶስ ፣ ማርከስ ራሽፎርድ እና ዌግሆረስት
ይሄ ገና የተሟላው ስብስብ አይደለም ከዚህም በኋላ ወደ ለንደን የሚያቀኑ ተጫዋቾች አሉ ።
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
ስለ ራትክሊፍ አንዳንድ ነገር ልበላቹ!
💰 ራትክሊፍ በ2023 ብቻ በግሉ ያለው ንብረቶች ዋጋ ፡ 15 ቢሊዮን ዶላር
💰ራትክሊፍ የሚያስተዳድረው INEOS ኩባንያ በ2023 ያለው ንብረቶች ዋጋ ፡ 61 ቢሊዮን ዶላር
እንደ እኔ ሀሳብ ይህ ሰው ከአረቦች ይልቅ ማንችስተር ዩናይትድን ቢጠቀልል እመርጣለሁ። ምክንያቱም ይህ እንግሊዛዊ ባለጸጋ ከምንም በላይ የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊ እና በእግርኳስ ስፖርት ዙሪያ የበለጠ እውቀት አለው!
እናንተስ ምን ትላላችሁ?
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
የሰር ጂም ራትክሊፍ ድርጅት INEOS ማንቸስተር ዩናይትድን ለመግዛት በይፋ ወደ ጨረታ ገብቷል።
ሰር ጂም ራትክሊፍ ክለቡን ከግላዘርስ ለመግዛት በይፋ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን አረጋግጠዋል።
የ INEOS ቃል አቀባይም እንዲህ ሲል ተደምጧል፡- "ማንቸስተር ዩናይትድን ለመግዛት በሂደት ላይ ነን!"
[Times]
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
በጥሩ ሁኔታ እየሄዱ ነው !
የአሌሃንድሮ ጋርናቾን ኮንትራት ለማራዘም የሚደረጉት ድርድሮች በጥሩ ሁኔታ ላይ እየሄዱ ነው ።
ማንችስተር ዩናይትዶችም ቢሆኑ ተጫዋቹ አሁን ላይ እየሄደበት በሚገኘው መንገድ እድገቱን እንዲቀጥል ፍላጎት አላቸው ።
[The Guardian]
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
ጣልያናዊው እውቁ የዝውውር ኤክስፐርት ፋብሪዚዮ ሮማኖ በ YouTube ገፁ ስለ ስኮት ማክቶሚናይ እየተወራ ስላለው ወሬ...
🗣"በአሁኑ ጊዜ በስኮት ማክቶሚናይ እና በኒውካስትል ዩናይትዶች መካከል ምንም አይነት ግንኙነት የለም። ኒውካስትል እና ተጨዋቹ ንግግር አድርገዋል እየተባለ የሚወራውም ወሬ ከእውነት የራቀ ነው።"
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
ከነዚ ከሶስቱ አንዱን ወደ ክለባችን መመለስ ብትችሉ ማንን መልሳችሁ ታመጣላችሁ?
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
#የቀጠለ
ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከመሀል ሜዳ ይልቅ በክንፍ በኩል ሲጫወት ምን እያየህ ነው? በማንችስተር ሲቲ ጨዋታ በዛ ቦታ ላይ የስካይ ስፖርት የጨዋታው ኮከብ ተብሎ ተመርጦ ነበር!
''ሃሳባችን በቀኝ ክንፍ በኩል ከብሩኖ ፈርናንዴዝ ጋር በተለይም ደግሞ በመከላከል ላይ እንዲሳተፍ ነበር። እናም እኔ እንደማስበው ከሆነ እርሱ እንደተለመደው ተከላክሏል።"
"ነገር ግን በኳስ ቅብብል ወቅት በመስመሮች መሀል እንዲመጣ ሚና ተሰጥቶት ነበር። በዚያ ቦታ ላይ ተጨማሪ ተጫዋች ለማግኘት እንዲረዳን ማለት ነው። ተጋጣሚዎቻችን ላይ ችግሮችን እና ግራ መጋባቶችን ለመፍጠር።"
"እኔ እንደማስበው ያንን ሚና በቀኝ እና በግራ በኩልም በብቃት የተጫወተው ይመስለኛል! የተቀረውም ቡድን ከሁኔታው ጋር ጥሩ በሆነ ሁኔታ የተላመደ ይመስለኛል ነፃ የሆነ ሰው በማግኘታችንም ጥሩ እረፍት አግኝተናል ብዬ አስባለሁ።"
"በዚህ ሚና ውስጥም ብሩኖ ወሳኝ ሚና ነበረው እናም ለፕረሲንጋችንም አስፈላጊ ነበር። እርሱ የስካይ ስፖርት የጨዋታው ኮከብ መሆኑን አላውቅም ነበር። ነገር ግን የእኔ የጨዋታው ኮከብ በርግጠኝነት ብሩኖ ፈርናንዴዝ ነው።''
የአለቃን ጋዜጣዊ መግለጫ ያሰናዳውላችሁ #ኢዘዲን ነበርኩ መልካም ምሽት! ❤
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
የስካይ ስፖርቱ ተንታኝ የሆነው የማንችስተር ዩናይትዱ ሌጀንድ ጋሪ ኔቪል ኤሪክ ቴን ሀግን እንዲህ ሲል አሞካሽቶታል...
🗣"ማንቸስተር ዩናይትድ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ይህን ያህል እድገት ያደርጋል ብዬ በጭራሽ አልጠበኩም ነበር። እና ኤሪክ ቴን ሀግ ለዚህ ስራው ልናደንቀው ይገባል።"
🗣"መጀመሪያ ላይ ማንችስተር ዩናይትዶች ለካሴሚሮ እና ለአንቶኒ የማይገባቸውን ገንዘብ አውጥተዋል የሚል አመለካከት ነበረኝ። ይህ ቡድን በዚህ ደረጃ ማደግ የሚችል ጭራሽ አልመሰለኝም ነበር።"
🗣"ነገርግን አሁን አሰልጣኙ ቡድናቸው ከሚያቀርበው ውብ እግር ኳስን ምክንያት አድርገው ተጨዋቾቹን እንዳስፈረሙ ተረድቻለሁ።"
🗣"አሁን ላይ ያለው የማንችስተር ዩናይትድ የአሰልጣኞች ቡድን ብዙ እቅድ እንዳላቸው እና ቡድኑም ትልቅ ተስፋ እንዳለው ያሳየናል።"
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
"Not for sale!"
ማንችስተር ዩናይትዶች አርጀንቲናዊውን ተስፈኛ አጥቂ አሌሃንድሮ ጋርናቾን በየትኛውም ዋጋ ለየትኛውም ክለብ አሳልፈው እንደማይሰጡት ጃኩ ታልቦት የተሰኘ የ ዘ ታይምስ ጋዜጣ ዘጋቢ ተናግሯል።
ዩናይትዶች ምንም እንኳ የጣሊያኑ ክለብ ጁቬንቱስ እና የስፔኑ ሪያል ማደሪድ ተጨዋቹን እንደሚፈልጉት መረጃው ያላቸው ቢሆንም
የተጨዋቹን ውል ግን እንደሚያራዝሙ ሙሉ የራስ መተማመን አላቸው ሲል ዘጋቢው አክሎ ገልጿል።
@Man_united_ethio_fans
@Man_united_ethio_fans
ቴንሀግ ከሲቲው ድል በፊት ስለ ዌጎርስት ተጠይቀው የተናገሩት 🗣
" ዌጎርስት በእርግጠኝነት ጎል አስቆጣሪ ነው ነገር ግን ለቡድኑ የሚሰራ ዓይነትም ተጨዋች ነው " አስምሩበት ይሄንን አስተያየት !
" በመልሶ ማጥቃት መጫወት የሚችል የሳጥን ክልል ውስጥ ተጫዋች ነው "
" እኔ አንድን ተጨዋች ቴክኒካል ተስጥኦ ብቻ አልመለከትም አጠቃላይ ነገሩን ነው የምመለከተው "
" እናም ለዚያ የአሸናፊነት አመለካከት (በክለባችን ውስጥ ላለው) ተጨማሪ አስተዋፅዖ ያደርጋል ብዬ አስባለሁ " ሲሉ ነው የገለፁት ።
ይሄን አስተያየት ልብ ብላቹ ተረዱት !
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
ክለባችን ከዴፓይ ጋር ያልተስማሙበት ጉዳይ !
ክለባችን ዌጎርስትን ከማስፈረሙ በፊት ከዴፓይ ጋር ተነጋግሮ ነበር ዳግም ወደ ክለቡ ለመመለስ ነገር ግን በአንድ ሁኔታ አልተስማሙም ነበር ።
እሱም በኮንትራት ዙሪያ ዴፓይ የረጅም ጊዜ ውል ነበር የፈለገው ነገር ግን ክለባችን በፋይናንስ ሁኔታ ምክንያት ጥያቄውን እንዳልተቀበሉት ነው ዘ አትሌቲክ የገለፀው ።
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
ቴንሀግ ዌጎርስትን ከበፊት ጀምሮ ነው የሚያቀው !
እንደ ዘአትሌቲክ ገለፃ ቴን ሃግ ዌጎርስትን በግላቸው ባያቁትም ከ16 ዓመቱ ጀምሮ ግን ስራውን ይከታተሉት እንደነበር ገልጿል ።
አክሎም ቴንሀግ እና ዌጎርስት ትውልዳቸው አንድ አካባቢ ነው ቴንሀግ የተወለደው በሃክስበርገን ሲሆን ዌጎርስት ደሞ በቦርን ነው የተወለደው ።
ከአንዱ ሰፈር ወደ ሌላኛው ሰፈር ለመሄድ የ20 ደቂቃ የመኪና ጉዞ እንደሆነ ገልጿል ።
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
በነገራችን ላይ ጀደን ሳንቾ በኦልድትራፎርድ የነበረውን የማንቹኒያን ደርቢ በኦልድትራፎርድ በመታደም መከታተል ችሎ ነበር።
በወቅቱም ከደጋፊዎች ጋር ፎቶችን ሲነሳ ታይቶ ነበር።አሁን ላይ ወደ ጨዋታ ለመመለስ በይፋ ከቡድኑ ጋር ልምምድ ማድረግ ጀምሯል።
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
He is back 😳
ጀደን ሚሊክ ሳንቾ ከ ማንችስተር ዩናይትድ ቡድን ጋር ልምምድ ማድረግ ጀምሯል።
በይፋም ወደ ቡድኑ ተመልሷል ሲል Goal መረጃ ይዞ ወጥቷል።
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
ግሌዘሮች ልክ የመጋቢት ወር ሲጠናቀቅ ማንችስተር ዩናይትድን ለመሸጥ ከአንድ ወገን ጋር ስምምነት ላይ እንደሚደርሱ ተስፋ ሰንቀዋል ።
[Alex Crook]
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
ትውስታ ከ ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ ጋር !
የታላቁ አብዮት ጅማሬ 1902...
ክለባችን ማንቸስተር ዩናይትድ ይህን አሁን እየተገለገለበት የሚገኘውን 'ማንቸስተር ዩናይትድ' የሚለውን ስያሜ ያገኘው በ 1902 ነበር ሲል የታሪክ ማህደር ያጋራናል ።
ኒውተን ኸልዝ የሚለውን ስያሜ ለመጨረሻ ጊዜ በ 1902 እ.ኤ.አ መጀመሪያ ከተጠቀመ በኋላ የክለቡ አመራሮች ስሙን ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ሊቀይሩት ችለዋል ።
በዛ ወቅት በቁመታቸው መለሎ እንደነበሩ የሚነገርላቸው ጆን ሄነሪ ዲቬስ የክለባችን ዋና ባለሀብት እንደነበሩም ታሪክ ይነግረናል ።
ጄምስ ዌስት የተሰኙት ጎልማሳ ደግሞ ቡድናችን ማንቸስተር ዩናይትድ ተብሎ በተሰየመበት ወቅት ዋና አሰልጣኝ ሆነው ለክለባችን ያገለግሉ ነበር ።
በ 1902/03 የውድድር ዘመን ቡድናችን በ 2ተኛ ዲቪዚየኑ 5ተኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀ ሲሆን በ ኤፍኤ ካፕ ውድድር ላይ ደግሞ ገና በ2ተኛው ዙር ከውድድሩ መሰናበት ችሎ ነበር ።
ክለባችን በአዲስ ስያሜ የውድድር አመቱን ከጀመረበት 1902-03 ሲዝን ጃክ ፔድዬ የተሰኘው አጥቂ በፕሪሚየር ሊጉ እና በሌሎች ውድድሮች 15 ግቦችን በማስቆጠር የቡድናችን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን አመቱን ማጠናቀቅ ችሎ ነበር ።
በ 1902-03 የውድድር አመትም ከፍተኛ ተመልካች የተገኘበት ጨዋታ ደግሞ በ መስከረም ወር 25ኛው ቀን ላይ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር የተጫወትንበት ጨዋታ ሲሆን 40,000 ያክል ተመልካቾች ጨዋታውን ካምቦሎጆ ድረስ በመገኘት ተመልክተውት ነበር ።
ዝቅተኛ ተመልካች የተገኘበት ጨዋታ ደግሞ በ ስቶክፖርት ሜዳ ከስቶክፖርት ጋር በመጋቢት 26 1903 ላይ የተፋለምንበት ጨዋታ ሲሆን 2000 ያክል ብቻ ተመልካቾች ጨዋታውን ታድመው ነበር ።
....
በአጠቃላይ 1902 ከአብዮቶች ሁላ የላቀ እና የበለጠ አብዮት የተቀሰቀሰበት ዘመን ይመስለኛል...ማንቸስተር ዩናይትድ...የ ማንቸስተር ህብረት አንድ የሆነበት አመት ነበር !
አዲሱ ፕሮግራማችን ቀጣይ በምን ጉዳይ እንዲመጣ ትፈልጋላችሁ...መልሳችሁን ኮሜንት ላይ አስፍሩልን ።
#ሚካኤል ነበርኩ ሰላም ያቆየን!❤
@Man_united_ethio_fans
@Man_united_ethio_fans
አዲሱ ፈራሚ ውት ዌጎረስትና ክርስቲያን ኤሪክሰን አንድ ላይ በመኪና ሲሄዱ! 📸
አንዱ ክሮስ ያደርጋል አንዱ ከመረብ ይደባልቃል 😁
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
ኤሪክ ቴን ሀግ የክለባችን አሰልጣኝ ሁኖ ባደረጋቸው አጠቃላይ 28 ጨዋታዎች 28 ተጫዋቾች ዩናይትድን ወክለው ተጫውተዋል ።
ቀጣይም ከክሪስታል ፓላስ ጋር በምናደርገው ጨዋታ አዲሱ ፈራሚያ ውት ዌጎረስት ተሰልፎ እንደሚጫወት የሚጠበቅ ሲሆን..
በ 29ኛው የቴንሀግ ጨዋታ 29ኛው ክለባችንን ወክሎ መጫወት የሚችል ተጫዋች ይሆናል ።
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
ቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ይካተታል ተብሎ ይጠበቃል !
ዌግሆረስት የማርሲያል መግባት አጠራጣሪ መሆኑን ተከትሎ ነገ ከክሪስታል ፓላስ ጋር በምናረገው ጨዋታ ላይ የመጀመሪያ ጨዋታውን ለማንችስተር ዩናይትድ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል ።
[Samuel Luckhurst]
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
#just_in
እንደ ዳረን ሌዊስ ዘገባ ከሆነ የለንደኑ ክለብ ዌስትሃም የክለባችንን አምበል እና የመሃል ስፍራ ተከላካይ ሃሪ ማጓየር በውሰት ውል ለማስፈረም ነገሮችን እያጤነ ነው።
@Man_united_ethio_fans
@Man_united_ethio_fans
ብሩኖ ፈርናንዴዝ ስለ ማርከስ ራሽፎርድ !
“እርሱ ሁልጊዜም ቢሆን መቆም የማይችል ነው ነገር ግን ባለፉት አመታት ውስጥ ግቦችን እና ሽልማቶቹች እያገኘ አልነበረም።
" ነገር ግን እርሱ አሁን ላይ ግቦቹን በሚገባ እያስቆጠረ ነው፣ ለቡድኑ እያደረገ ላለው ጥረትም ሽልማቶችን እያገኘ ነው።"
@Man_united_ethio_fans
@Man_united_ethio_fans
ነገ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ከምናከናውነው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ መርሀ ግብር በፊት የኤሪክ ቴንሀግ ጋዜጣዊ መግለጫ።
ማርሲያልን በሲቲው ጨዋታ ቀይራችሁ ስታስወጡት ተጎድቶ ነበር?
''እንዳይጎዳ ለማድረግ አስቤ ነበር። ነገር ግን እሱ ቅር እያለው ነበር። ስለዚህ በሳምንቱ ልምምድ ያላደረገው እና ጥያቄ ምልክት ውስጥ ገብቶ የነበረው ለዚህ ነው! እኛ ወሰንን እሱም እንዲሁ ወስኗል።"
"በዚህ ጨዋታ ቢጀምር በጣም አስፈላጊ እንደሚሆን ስለማውቅ እንዲጀምር ሲለምነኝ ነበር። በተለይም እሱ መጫዎቱ በጣም ጥሩ ስለሆነና በእኛ ፕረሲንግ ውስጥ ትልቅ አካል ስለሆነ። ይህንንም ከእረፍት በፊት በጥሩ ሁኔታ ተግብሯል።"
"ግን ደሞ 100% መጫወት እንደማይችል አይታችኋል እና ያንን መሰለኝ የምትፈልገው እሱ እንዳይጎዳ ብለን ቀይረነዋል። ነገር ግን መቀየሩ በጨዋታችን ላይም ተፅዕኖ አሳድሯል። ከእረፍት በኋላም አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሮብናል።''
እሱ [ማርሲያል] የማይገኝ ከሆነ ውት ዌጎርስት ከፓላስ ጋር በአሰላለፍ ውስጥ ታካትተዋለህ?
"ያንን ደግሜ ማሰብ ይኖርብኛል። በመጀመሪያ ይህንን ጨዋታ ማስተካከል እና በትክክለኛው መደምደሚያ ላይ መድረስ ይኖርብሀል። ከዚያም ግልጽ የሆነ እቅድ እናዘጋጃለን።"
"ፓላሶችን መመልከት አለብኝ። በርግጥ ስለ እነሱ ብዙ ነገሮችን አውቃለሁ። በቅድመ ውድድር አመት ዝግጅት ወቅት እንዲሁ ገጥመናቸው ነበር። ቡድኑ ምን አይነት እንደሆነም አውቃለሁ።"
"አሁን ላይ ገና የጨዋታው ሙሉ እቅዶች የሉኝም። እኔ እስካሁን አሰላለፍ አልሰራሁም። ስለዚህ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ መስራት እንችላለን እናም ቡድኑን በትክክለኛው መንገድ ማዘጋጀት እንችላለን።"
ከሲቲው ጨዋታ መልስ ተጫዋቾችህን በምን አይነት ሁኔታ አዘጋጅተሀቸዋል? እነሱ ድላቸውን እንዲያከብሩ ትፈቅዳለህ ወይስ ያን ረስተው ቀጥታ ወደ እንቅስቃሴ መግባት አለባቸው?
"እኔ እንደማስበው ከእያንዳንዱ ድል በኋላ ማክበር አለብህ። ለእንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች በጣም ጠንክረህ ትሰራለህ። በከፍተኛ እግር ኳስ ማንኛውም ድል ትልቅ ነገር ነው። እናም እያንዳንዱን ድል ማክበር ካልቻልክ ጉልበትህንም የምትገድል ይመስለኛል።"
"ስለዚህ ልናከብረው ይገባል። ነገር ግን ከእሱ በኋላ መረጋጋት እና ከ 24 ሰአት በኋላ ወደሚቀጥለው ጨዋታ መሄድ አለብን። ከዚያም በትክክለኛው ሪትም ውስጥ ትገባለህ።"
"በየሶስት ቀኑ ተጫዋቾቹ ከአካላዊ እይታ አንፃር ወደ ትክክለኛው ሪትም መግባት አለባቸው ብዬ አስባለሁ። ነገር ግን በአእምሮም ረገድ እንዲሁ ለቀጣዩ ጨዋታ ዝግጁ መሆን መቻል አለብህ። ይህም ደግሞ እሮብ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ነው።"
#ይቀጥላል
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
ቦስ በአሁኑ ሰአት ለነገው ጨዋታ ጋዜጣዊ መግለጫቸውን እየሰጡ የሚገኙ ሲሆን እኛም መግለጫው ሲጠናቀቅ ጠቅለል አድርገን የመግለጫውን ይዘት ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!
@Man_united_ethio_fans
@Man_united_ethio_fans
ዘ አትሌቲክ በገለፀው መረጃ የክለባችን አስተዳደሮች ለቴንሀግ በጥሩ የዝውውር መስኮት የሚያወጡት በቂ
ገንዘብ ስለሌላቸው የውሰት ዝውውሮችን እንዲመለከት ነግረውታል በዛም ምክንያት ነው ቴንሀግ ዌጎርስትን በውሰት ውል ሊያመጣው የቻለው ።
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans
ሳታነቡት እንዳታልፉት በጣም ነው ሚጠቅማቹ
ውድ ቤተሰቦቼ ዛሬ አሪፍ ቻናል ልጦቁማቹ
በጣም አሪፍ ቻናል ነው እና join ብላቹ ትርፋማ ሁኑ ችላ ብላቹት join ሳትሉ እንዳታልፉት ሂወታቹን ነው ምቀይርበት join ካላላቹ እራሳቹ ነው ምትጓዱት አሁኑኑ join በሉ
/channel/+6BfcYokU5WIyYjk0
/channel/+6BfcYokU5WIyYjk0
/channel/+6BfcYokU5WIyYjk0
/channel/+6BfcYokU5WIyYjk0
/channel/+6BfcYokU5WIyYjk0
Join በሉት አሁኑኑ
ዌግሆረስት ፦
🗣"ወደ ኦልድትራፎርድ ለመጀመሪያ ጊዜ መምጣቴ ነው። ሁልጊዜም ሄጄ መጫወት ከምፈልጋቸው ስቴድየሞች ውስጥ ኦልድትራፎርድ አንዱ ነው።"
ዊጎ በዩናይትድ ቤት ማሳካት ስለሚፈልገው ነገር ፦
🗣"ቀላል ነው ዋንጫዎችን ማሳካት ነው ምፈልገው አሰልጣኜም ስለዚህ እና ቡድኑ ውስጥ ስለሚኖረኝ ሚና ነው የነገረኝ።"
@man_united_ethio_fans
@man_united_ethio_fans