keneyalew | Неотсортированное

Telegram-канал keneyalew - ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

-

ሃሳብ በሃሳብ …………! የግሩፑ አላማ/ህግ፦ https://t.me/keneyalew/34269

Подписаться на канал

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

ባህሪ ማለት አንድ የተፈጥሮ አካል ከሌላው የተፈጥሮ አካል የሚለው uniqueness ማለት ነው ወይም አፍላጦን form የሚለው እንደማለት ነው...ፈረስነት ሰውነት ቅማልነት ወዘተ እንደማለት ይህ እንግዲህ ከ physiological እስከ psychological መሰረት ያለው ነገር ነው

ጠባይ ግን የተፈጥሮ አካላት በአከባቢያዊ ተፅእኖ እና በጊዜ ሂደት የሚያዳብሩት ለውጫዊ ሁነቶች የሚሰጡት action ተብሎ ሊገለፅ ይችላል ይህ ነገር የባህል፣ የማህበራዊ አስተሳሰብ፣ የሞራል እና የአምልኮ መሰረት ነው....ዝቅ ዝቅ ብለን ነገሩን ስቃኘው ደሞ ጠባይ በቤተሰባዊ እና በማህበራዊ መስተጋብር የሚፈጠር የግለሰባዊ ሁነት ብለን መደስኮርም እንችላለን

ወደ ዋናው ጉዳይ ስመጣ ምናልባት nihilistic approach ስለሚባል ነገር ሰምታቹ ይሆናል...ያው በአጭሩ ህይወትም ተፈጥሮም ፍትህ አልባ ጨካኝ እንዲሁም ትርጉም አልባ ናቸው ይላል ይሄ school of thought.... መልካም ጠባይ የሚባል ነገር የለም ምክንያቱም መልካም ተብሎ ሁሉንም ሊያስማማ የሚችል የሞራል ህግ በሌለበት ሰዎች ይሄን ነገር ቢያደረጉ መልካም ያስብላቸዋል ብለን ለመበየን የእውነት መሰረት እናጣለን....መልካምነት አንፃራዊ ነው ስለዚህ አንድ ግለሰብ ለኔ መልካምነት ማለት ባልየውን ገሎ ሚስትዬውን መድፈር ነው ካል ካላስ ለሱ መልካምነት ተግባር ነው ቀጥልበት ግፋበት እንለዋል

ሻሎም🙏😁
🔯שלום

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

የተለያዩ መጽሐፍቶችን ለማግኘት ከታች ባለው ሊንክ ቻናላችን ይቀላቀላሉ።👉 /channel/Amharic_books_30

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

እዩት እስኪ(በሆነ ነገር ላይ Review መስጠት ግን ቀላል አይደለም)

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

Wow, I found your photo. Maybe you can become a model? https://cutt.ly/zwThQQpZ

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

' አብረናቸው ቁጭ እንዳልንም ካ'ባቴ ጋር ስለነበራቸው ወዳጅነት
ወጎች፥ዐብረው ያሳለፉትን የጉብዝና ወራት በማስታወስ ያለፉትን ዓመታት'ና በጊዜ ባሕር ውስጥ የተደበቁትን፥የተዳፈኑትን፥በጊዜ ከርሥ ውስጥ የተቀበሩትን ታሪኮች በማውሳት አስደሰቱን። እያንዳንዱ ጎምቱ ሰው በትዝታው ወደወጣትነት ዘመን ቀናቱ መመለስ ይሻል -ባይተዋር ሰው 'ትብቱ ወደተቀበረችበት ምድር ወደወንዙ ለመመለስ እንደሚጓጓው ኹሉ። አዛውንት ሰው የውርዝው'ና ጊዜውን ወጎች ዘርዝሮ ማውጋት ያስደስተዋል -ልክ ባለቅኔ ከኹሉ ይበልጥ የተዋጣለትን ግጥሙን በቃሉ ፉት ብሎ የተወጣው ጊዜ ደስ -ደስ እንደሚለው-(ባለቅኔዎች የተዋጣላቸውን ግጥሞች ጮኽ ብለው ማንበብ እንደሚያስደስታቸው)-። አረጋውያን በመንፈስ የሚኖሩት ባ'ቧራማው ያለፈ ጊዜ ስርቻ ውስጥ ነው - የዛሬው ዘመን ኻጃዬ -ነገሬ ሳይላቸው በጥድፊያ ጥሏቸው ይነጉዳል'ና። መጻኢውም ጊዜ ወደመረሳት ዐፈና'ና፥ ወደከረሠ-መቃብር ድምንምን ማቆልቆል መስሎ ይታያቸዋል።
     በቀድሞ ትዝታዎች ጭውውት የተሞላች አንዲት ሰዓት፥በመስክ ላይ እንደሚያልፉ የዛፍ ጥላዎች ዐለፈች። ፋሪስ ኤፋንዲ ለመኼድ ሲነሱ ለመሰናበት ቀረብ ስል ቀኝ እጄን ጨበጡ'ና የግራ እጃቸውን በትከሻዬ ላይ አሳርፈው 'አባትህን ለኻያ ዓመታት አላየሁትም ፤ ነገር ግን ቤቴን አዘውትረህ በመጎብኘት አባትህን እንደምትተካ ተስፋ አደርጋለሁ! አሉኝ።
     ራሴን በአዎንታ ነቀነቀሁ'ና ግዴታዬን ለመወጣት ላ'ባቴ የልብ ወዳጅ ከምስጋና ጋር ቃል ገብቼ ቸሩን በመመኘት ተሰናበትኋቸው።
     ፋሪስ ካራሚ ቤቱን ለቀው እንደኼዱ ጓደኛዬን ስለሰውዬው በይበልጥ እንዲነግረኝ ፍትር አደረገኹት። እሱም በተቆጠበ አንደበት  "በቤይሩት ከተማ ውስጥ ሀብቱ ብፁዕ ያደረገው'ና ፥ብፅዕናው ያጌተየው ሰው ከ'ሳቸው ሌላ ማንንም አላውቅም። ወደዚህች ዓለም ከሚመጡት'ና ማንንም ምንንም ሳያሳዝኑ፥ ሳይጎዱ ከሚያልፉት ጥቂት ሰዎች አንዱ ናቸው ። ነገር ግን እንዲያ  ዐይነቱ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ራሳቸውን አሳዛኝ መከረኞች'ና ግፉአን ጭቁኖች ናቸው ፤ለምነው ቢሉ ከሌሎች ምግባረ-እኩያን ተንኮል'ና ሴራ ራሳቸውን ለማዳን ያን ያኽል ብልኀ ጥንቁቅ አይዶሉማ። ፋሪስ ኤፋንዲ በባሕርይዋ እሳቸውን የመሰለች ከከተማው ዳር ባለው ዕፁብ-ድንቅ መኖርያ ቤታቸው ዐብራቸው የምትኖር አንዲት ሴት ልጅ አለቻቸው፤ ወዘንደናዋ'ና ዠርጋዳነቷ ይኽ ነው አይባልም፤ መሰል የላትም። እሷም መከረኛ ምስኪን መኾና ሳይታለም የተፈታ ነው፤ ምክንያቱም ገና ድሮውኑ ያ'ባቷ ቅልጥጥ ያለ ሀብት ህው-ዥው ካለ የገደል አፋፍ ላይ አስቀምጧታል" አለ።
    ወዳጄ እነዚህን የመጨረሻዎቹን ቃላት እንደተናገረ ፊቱ ላይ ከፍያለ የጭንቀት'ና የቁጭት ሐዘን ሲዳምንበት አስተዋለሁት። ወዲያውኑ ቀጠለና "ፋሪስ ኤፋንዲ ልበ-ቀን፥ ልጨኛ'ና የተከበሩ አዛውንት ናቸው፤ ነገር ግን ቆራጥነት ይጎድላቸዋል። እንዳይነስውር-እንደቦይ ውሃ በሰዎች አስተያየት በጭፍን ይመራሉ-ይነዳሉ። የሰዎች ምኞት ፍላጎት ልጉም አንደበተ-ዲዳ አድርጓቸዋል። ሴት ልጃቸውም የኾነች እንደኾነ በጨዋነት'ና በለባዊነቷ ፈንታ ትታዘዛቸዋለች።
ባ'ባት'ና በልጅ ሒወት ዠርባ ያደፈጠው የተደበቀው ምስጢርም ይኸው ነው።
     'ይኸው ምስጢር በባሕርዩ ዝነኛ ለመኾን ባለው ምኞት'ና ተንኮልን ያዘለ ብልጠት በቀላቀለ ኤጲስቆጶስ በኾነ ጭቦኛ ከይሲ ሰው ታወቀ። እኩይነቱን በወንጌሉ ጥላ ሥር ከልሎ ለሕዝቡ ምግባር-ሠናይ መስሎ ይታያል ። በይህች የሃይማኖትና የእምነት በኾች ምድር ላይ የሃይማኖት አባት ነው። በሥጋም በነፍሱም ይፈራል፥ኹሉም ይነሸቀሸቁለታል፤ በጋማች ቆልምሞ እንደሚያደርዳቸው በጎች አንገታቸውን ያንጋልሉታል። ይኸው ኤጲስቆጶስ በውስጡ የ'ምነት-ቢስነት'ና ክፋት ባሕርያት፥ በየዋሻው'ና በ'ያረንቋው ስርቻ ውስጥ ርስበ'ርሳቸው እንደሚሻኮቱት ጊንጦች'ና እባቦች፥ የሚታገሉበት አንድ የወንድም ልጅ አለው።
       ኤጲስቆጶሱ በልብስ-ተክህኖው አጊጦ የወንድሙን ልጅ በቀኙ፤ የፋሪስ እፋንዲን ሴት ልጅ በግራው የሚያደርግበት'ና የጋብቻን የዘውድ አክሊል በ'ርኩስ እጁ ይዞ በ'ራሳቸው  ላይ የሚደፋበት ቀን፤ ይዋል ይደር እንጅ ሩቅ አይዶለም፤ በደብተራዊ መነባነብ ትብትብ'ና የጥንቆላ ሟርት ንጵሒቱን ድንግላይ አካል ከጭቅቂታም የገማ በድን ጋር ያስተሳስራል፤ በጎደፈ-ባደፈ የሃይማኖት ሕግ አንቆ ይዞ ሰማያዊቱን ነፍስ ካንድ ምድራዊ ፍጡር ጋር ያጣምዳል፤ ያቆራኛል - ፍትፍት ውስጥ ምርቅ። ስለ ፋሪስ ኤፋንዲ'ና ሴት ልጃቸው አኹን ልነግርህ የምችለው ይኸው ብቻ ነው፥ ስለዚህ ስለ'ነሱ ሌላ ተጨማሪ ምንም ዓይነት ጥያቄዎች እንዳትጠይቀኝ። የፈሩት ይደርሳል የጠሉት ይወርሳል እንዲሉ።
    ወዳጄ ይኽንን አለ'ና ፊቱን ወደመስኮቱ አዞረ  - በምልኣተ ዓለም ውበት ላይ በማተኮር የሰውን ልጅ የሒወት እንቆቅልሾች ለመፍታት እንደሚሞክር ዓይነት ኹሉ።
      ለመኼድ ብድግ አልኹና ለመሰናበት እጁን እየጨበጠኹት " በቅርብ ቀናት ውስጥ ቃል-ኪዳኔን ለመጠበቅ'ና አባቴን'ና እሳቸውን ስላጎዳኛቸው -ስላቆራኛቸው ወዳጅነት ስል ፋሪስ ኤፋንዲን ኼጄ እጠይቃቸዋለሁ አለኹት።
     ይኽ ጎበዝ ላንዲት አፍታ ባ'ግራሞት ተኩር ብሎ አየኝ፤ የእኔ ጥቂት ተራ ቃላት ዐዳ'ዲስ ጥልቅ ዕሳቤዎች እንዳነቁበት-እንደከሠቱለት ዓይነት የፊቱ ገጥ በቅፅበት ልውጥውጥ ሲል ልብ'ለሁ። ወዲያውኑ በቀጥታ ዐይኖቼ ውስጥ በትክታ በተለየ ኹኔታ አየኝ- የፍቅር ፥ የሐዘኔታ'ና የፍራቻ እይታ- እሱ ብቻ እንጅ ቀደም ብሎ የሚታየው ሌላ ማንም ሊተነባው በማይችለው  የነቢይ እይታ።  ከናፍሩ ትንሽ ተንቀጠቀጡ፥ ግን ምንም ትንፍሽ አላለ። ትቼው በተመሰቃቀለ ሐሳብ ወደበሩ አመራሁ። ወዲያው ፊቱን ከማዞሩ በፊት ዐይኖቹ በዚያ ልዩ እይታ እየተከተሉኝ እንደኾነ አየሁ። ከዚህ ምጥን'ና የቅጥብ ውስን ዓለም ነፍሴን ነጻ አድርጌና አላቅቄ ቀልቦች በመተያየት በሚግባቡት'ና ነፍሶች ርስበ'ርስ በ'ውቀት በሚበቁበት በሰማየ ሰማያቱ የብሔረ-ብፁዐን መገናኛ ክልል እስክሰፍ ድረስ ፍቺው በቁሙ-በውርዱ አካቶ አልገባኝም ነበር።

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

“I've had a lot of ups and downs in my life. I'm still working through it personally, but the best thing about me is that if an alcoholic or drug addict comes up to me and says, 'Will you help me?' I will always say, 'Yes, I know how to do that. I will do that for you, even if I can't always do it for myself! So I do that, whenever I can. In groups, or one on one.
And I created the Perry House in Malibu, a sober-living facility for men. I also wrote my play The End of Longing, which is a personal message to the world, an exaggerated form of me as a drunk. I had something important to say to people like me, and to people who love people like me.
When I die, I know people will talk about Friends, Friends, Friends. And I'm glad of that, happy l've done some solid work as an actor, as well as given people multiple chances to make fun of my struggles on the world wide web...
but when I die, as far as my so-called accomplishments go, it would be nice if Friends were listed far behind the things I did to try to help other people.
I know it won't happen, but it would be nice."

~Matthew Langford Perry
(August 19, 1969 - October 28, 2023)
#RIP

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

ብዙ ለመግባት ስላላመቻትም ይሆናል ብቻ እንጠይቃታለን እስኪ አይሻልም አሁን ባለው ሀሳብ ነው ሀሳብ ስጡ በልልኝ😍

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

በመጀመሪያ እኚህ ሁለት factors ፍፁም በሆነ ቀይ መስመር ተለያይተው ሲጓዙ ማየት rare ነው። ስለዚህ ለጥያቄው የኔ መልስ የሚሆነው የሰው ልጅ ባህሪ በተፈጥሮ ጀምሮ በተፅእኖ(ሰው ጋር በሚኖረው መስተጋብር) የሚመራ ነው ይሆናል።

(ግን ግን.........ተፈጥሯዊ ስንል ከማህበረሱ ጋር በሚደረግ መስተጋብር የራሱን ቀለም የማይለቅ ማለት ከሆነ ከጅምሩም ተፈጥሯዊ ነገር መኖሩ ጥያቄ ውስጥ ይከተኛል። ነገር ግን ተፈጥሯዊነት ከውጫዊ መስተጋብር ከሚመጣበት መበረዝ ይልቅ የራሱ ውስጣዊ ተፈጥሮ የሚያፈልቀው ከለር ሞቅ ብሎ ሲታይ ከሆነ ተፈጥሯዊ ነገሮች ብዙ ይሆናሉ።)

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

የአካባቢ ተጽዕኖ የሚጎላ ይመስለኛል

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

ተፈጥሮ መቀየር የማንችለው ከሆነ አከባቢ ደሞ ልምድም አይደል የቱ የትኛውን የሚቀይር ወይም በአንድ ግለሰብ ጎልቶ የሚታይ ይመስልሃል ?

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

የተፈጥሮና የአካባቢ ድምር ውጤት ነው

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

እሺ ወዳጄ ለሀሳብህ ደሞ አመሰግናለሁ
(ልጆቹንም ለመመለስ እንሞክራለን)(አዲስም ሚሳተፍ ሰው ይኖራል)(ትዙ አለቃነቴን ትመልስልኝ የት አለች?)

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

ባህሪ(character) ማለት በአዕምሮህ ያሰብከውን አሳብ(feeling) manifest ስታደርገው ሲሆን
ለምሳሌ፦ መበሳጨት፡ መደሰት ወዘተ

ጠባይ(behavior) ደግሞ በአዕምሮህ ሳታስብ የምታሳየው ነገር ነው።
ለምሳሌ፦ ዝምተኛነት
...
so እኔን እንደሚመስለኝ ባህሪም ሆነ ጠባይ የተፈጥሮና የአስተዳደግ ድምር ውጤት ናቸው። በብዛት ግን የአስተዳደግ ኹኔታ shape ያደርጋቸዋል። ይኸን ለመረዳት የአስተዳደግን psychoanalysis መረዳት የሚገባ ይመስለኛል።
...
ስለዚህ የተፈጥሮን effect መቀየር ስለማንችል የአስተዳደግ ዘይቤን በማሻሻል የሰውን ሰብዓዊ ጠባይና ባህሪ መልካም በጎ እንዲሆን guide ማድረግ እንችላለን።
የልጆች አስተዳደግ matters!

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

አዲስ አመት
አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

ይሄን ቤተስኪያን በር ላይ እየለመነች ነው ማን ያውቃል😂😂😂

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

User 1109550786 changed name from ፩ 𝑭𝒆𝒓𝒔𝒕 ፩ to 𝕞𝕦𝕝𝕖 𝕟

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

What would you like to tell young people?

"I don't know... I think I'd like to say only that they should learn to be alone and try to spend as much time as possible by themselves. I think one of the faults of young people today is that they try to come together around events that are noisy, almost aggressive at times. This desire to be together in order to not feel alone is an unfortunate symptom, in my opinion. Every person needs to learn from childhood how to spend time with oneself. That doesn't mean he should be lonely, but that he shouldn't grow bored with himself because people who grow bored in their own company seem to me in danger, from a self-esteem point of view."

- Andrei Tarkovsky, an excerpt from the documentary Andrei Tarkovsky - A Poet in Cinema (1983), dir. by Donatella Baglivo
[cinema speaks)

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

1948_Creation_Catastrophe_Full_documentary_Bwy_Rf15UIs_247.mkv

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

Linked below is a Google Drive folder that contains 1,700+ books on Palestine and Israel. They are mostly in English.
https://drive.google.com/drive/folders/18u9KYo3MvRpyI0SDqD2AzseTvuSn3S8T

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

የ'ጣ ፋንታ እጅ

  'በዚያ በሚያስደምም ዓመት በወርሃ-ጽጌ በቤይሩት ነበርሁ።
የከተማዋ ዐጸዶች በኒሳን(ማዚያ)አበቦች ተሸልመዋል፤ምድርም የጨሌ ሣር ሥጋጃ ተነጥፎባታል ኹሉም አንዳች ምድራዊ ምስጢር ለጽርሓ-አርያም እንደሚያሳዩ ዓይነት። የብርትካኑ'ና የቱፋህ ዛፎች ሽቷማ አበቦች ጻዐዳዊ ልብስ ለብሰው የባለቅኔዎችን ስሜት ለማስነሸጥ'ና ምናብንም ለማጫር በተፈጥሮ የተላኩ ኹረል-ዐይን(እንደፀሐይ የሚበሩ ሰማያዊ ሙሽሮች)ወይ ሙሽራዎችን ይመስላሉ።
  ዐደይ የትም ውብ ነው፤ ነገር ግን በሊባኖስ እጅግ ይቆነዣል። ጸደይ በምድር ዙርያ የሚንከራተት የሚንቀዋለል፥ በሊባኖስ ላይ ሲደርስ ግን ፍጥነቱን ዝግ ገታ አድርጎ ወደኋላው እያየ በኒያ ሰማያት ከሚያንዣብቡት ነገሥታቱ'ና ከነቢያቱ መንፈሶች ጋር የሚነጋገር ያ'ንዳች ያልታወቀ አምላክ መንፈስ ነው፤  ከምድረ ይሁዳ ወንዞች ጋር መቼም መች አይረሴውን መሓልይ ዘሰሎሞንን ይዘምራል፤ ከቅዱስ አርዘ-ሊባኖስ ጋርም የጥንቱን ዝና ትውስታ ይዘክራል።
   ቤይሩት በጸደይ ወቅት ከሌሎቹ ወራት ይልቅ በይበልጥ ትዋባለች። ቤይሩት ከክረምቱ ጭቃና ከበጋው አዋራ የጸዳች የተናጻች የጸደይ ጊዜ ሙሽራን ትመስላለች። ወይ በዥረት ዳር ቁጭ ብላ ለስላሳ ቆዳዋን በፀሐይ ጨረር የምታደርቅ ሜርሜይድን ትመስላለች።
    የኒሳንን መንፈስ ልውጥ ንውጥ የሚያደርገውን የንፋስ ሽውታና የእንኳን ደኽና መጣችሁን ፈገግታ ባዘለው ከለታቱ ባንዱ ቀን፥ ከውቢቱ ከተማ ከሰው ትንቅንቅ ጭቅጭቅ ጥቂት ራቅ ባለ ቤቱ የሚኖረውን ወዳጄን ልጠይቀው ኼደሁ። ምኞቶቻችንና ተስፋዎቻችንን በቃላት እየበገርን'ና እየነደፍን ወጋችንን በማረቅ ላይ እንዳለን፥ ዕድሜያቸው ወደ ስድሳ-ዐምስት ዓመት የሚጠጋ፤ያዘቦቱ ቀን አለባበሳቸው'ና  የፊታቸው ሽብሽባቶች፥ ግርማ ሞገሳቸውን'ና የበቁ መኾናቸውን የሚነገርላቸው ፥ ለምድር-ለሰማዩ የከበዱ አዛውንት ወደ ክፍሉ ሰተት አሉ። እጅ ልነሳቸው ባ'ክብሮት ተነስቼ እጃቸውን ጨብጨ ሰላምታ ከማቅረቤ በፊት ባልንዠሬ ወደፊት ራመድ ብሎ ወጣ አለ'ና  "ፋሪስ ኤፋንዲ ካራሚ ይሉሃል እሳቸው ናቸው!" ብሎ ለጥቆም እኔን አሞካሽቶ አወዳድሶ አስተዋወቀኝ።
    አዛውንቱም ለአንዲት አፍታ ያኽል አስተውለው አዩኝ፤ የቆየ'ና የት እንዳኖሩት ያላወቁትን ምስል ለማግኘት ትዝታቸውን ለማስታወስ እንደሚሞክሩ ሁሉ፤ ሙሉ በሙሉ የሽበት ፀጉር ዘውድ የጫነውን ፈጠጥ ያለ ግንባራቸውን በጣቶቻቸው ጫፎች እየነካኩ። ወዲያውኑ በመፍለቅለቅ'ና በፍቅር ፈገግ አሉና ቀረብ ብለው "አንተ ያ'ፍላነት ዘመኔን  አብሬው በባልዠርነት ያሳለፍኩት ያ'ንድ የድሮ ያንዠት ወዳጄ-ምስጢር ባልንዠሬ ልጅ ነህ፥ አንተን በማየቴ ምንኛ ደስ አለኝ!
አባትህንስ ባልንዠሬን ባ'ንተነትህ ውስጥ ለማየት ምንኛ ያጓጓል! አሉኝ።
    በቃላቶቻቸው በጣም ተነካሁ፤ ያ'ንዳች ተፈጥሮኣዊ አመኔታ ኹኔታ ወደ'ሳቸው በስውር ሲያቀርበኝ ታወቀኝ ልክ ወዠቡ ከመተገቡ በፊት የደመ ነፍሱዊ ጥሪ ወደጎጆዋ እንደሚያበራት ድምቢጥ ዓይነት ።

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

'ብዙ አለማወቅ - አለመራቀቅ ሰውን ባዶ ያደርገዋል ያም ባዶነት አባግድየለሽ ያደርገዋል ይባላል'( ድንቁርና የነጻነት ምንጭ ነው፤ ነጻነትም የደስታ መደብ ነው ይላሉ(ኮል)። በ'ኒያ ምውት ኾነው በሚወለዱቱ'ና በገረረ በድን ሬሳ ኾነው በሚኖሩቱ መኻል ይህ እውን ሊኾን ይችላል፤ ነገር ግን ጭፍን ድንቁርና በፍልቅልቅ ሒወት አቅራቢያ የሚኖሮ ከኾነ ከገሃነም በጣሙን የከፋ'ና ከሞትም እጅጉን የመረረ ነው። ብዙ የሚሰማው ግን ትንሽ የሚያውቅ ሕዙን ወትኩዝ ስሱ ልጅ ¯ ከፀሐይ በታች በጣሙን ያልታደለ ፍጡር ነው! ለምን ቢሉ ነፍስያው በኹለት ተቃራኒ'ና አስፈሪ ሀይሎች መኻል ትቦጫጨቃለች'ና። የመዠመሪያው ህቡእ ወክቡት ሀይል ወደላይ ከፍ -ከፍ ያደርገውና የሒወትን ውበት በሕልሞች ዳመና ውስጥ ያሳየዋል ፤ኹለተኛው ክሡት ወግሁድ ሀይልም በመሬት ላይ ጥፍንግ አድርጎ ዓይኖቹን ባ'ዋራ ይሞላቸው'ና ድል መትቶ'ና ፈሪ አድርጎ ጨለማማ የኮነ ደብዛዛ ብርሃን ውስጥ ይጥለዋል።
ሐዘን ሲነኩት የሚለሰልስ ግና ጅማታም'ና ጠንካራ የኾነ- ጥንድ እጆች ማለት ነው - ልቦችን ጨብጦ ይዞ ያጣምር'ና ያሠቃያል ፤ ዋሕድነት-ብቸኝነት የሐዘን እንደራሴ ምስለኔ ነው፤ የማናቸውም መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ቅሩብ የልብ ወዳጅ እንደ ኾነው ኹሉ። በዋሕድና - በባታይነት ሀይል ስሜት'ና በሐዘን ተጽ'ኖ መኻል የተወጠረች የልጅ ነፍስ እየፈካች ያለችን ጽጌ ደንጎላት ትመስላለች '( ብሕትውና ልፍና ልስልስ እጆች አሉት፤ ግና ጠንካራ በኾኑ ጣቶቹም ልብን ጨብጦ ይይዝና እንድትሠቃይ ያደርጋታል -በሐዘን። ብቸኝነት የሐዘን አጋር ነው - የመንፈሳዊ ልቀት ቅሩብ ወዳጅ እንደኾነው ኹሉ። በሐዘን ብትር ተደጋግሞ ሽንቆጣ የደረሰባት የልጅ ነፍስ - ልክ እንደምትፈካ ነጭ ጽጌ ደንጎለት ናት...(ኮል)! ነፋሱ ሽው ሲል ትንቀጠቀጥ'ና ለወገግታ ጮራ መኻልዋን ትዘረጋለች፤ የምሽቱ ጥላ ሲመጣም ቅጠሎችዋን መልሳ ታጣጥፋለች። ያ ልጅ ሐሳቡን የመከፍሉለት የጊዜ ማሳለፊያዎች ወይ ስሜቶቹን የሚጋሩ ወዳጆች ከሌሉት መጻኢው የወደፊት ሒወቱ የሸረሪቶች ድር እንጅ ሌላ የማያይባት፤ የነፍሳቱን የመንፏቀቅ ድምፅን እንጅ ሌላ የማይሰማባት እንደጠባብ 'ስር ቤት ትኾናለች።
በወጣትነት ዘመኔ የጠናወተኝ ያ ሐዘን ፥ በኔ በኩል የመደሰቻ ጫዎታዎች በማጣት የተፈጠረ አልነበረም፤ ብዙ-ብዙ ነበረኛ! አልያም ወዳጆች በማጣትም አልነበረም፤ ምክንያቱም በየኼድኹበት ኹሉ አገኛቸው ነበር'ና። ይልቁንስ የዚህ ሐዘን መነሾ ያለው ብሕትው እንድኾን'ና ዋሕድነትን-ብቸታን እንድሻ ባስገደደኝ፥ ለጫዎቻዎች'ና ለጊዜ ማሳለፊዎች የነበረኝን የቀድሞ ፍላጎቴን ያጠፋብኝ'ና የወጣትነትን አክናፍ ከትከሻዬ ላይ በነጠቀኝ የተለየ ባሕሪዬ'ና በራሴው የነፍሴ ሥነ-ተፈጥሮ ነው(...ይልቁንስ የዛ ሐዘን መነሾ የመፍቀሬ ጽማዌ ወጽሙ'ና ውስጣዊ ደዌ ነው...ለመጫዎት'ና ለመደሰት ያለኝን ውስጣዊ ዝንባሌዬን ኹሉ የገደለብኝ!(ኮል)!። ሐዘን በድፍን ዓለሙ ፊት በተራሮች ቁንጮዎች መኻል ኾኖ 'ርግት ባለው ገጹ ላለው የምስላቸውን ጥላ፤ የዳመናቱን መልክ'ና የዛፎቹን ውዝዋዜ እንደሚያንጸባርቅ ኾኖም እያንጎራጎረ ወደ ባሕሩ ይገሰግስ ዘንድ እንዳይችል መውጫ እንዳጣ የኩሬ ውሃ አደረገኝ።
ይህ ነበር እንግዲህ ወሥራስምንት ዓመት ከመሙላቴ በፊት የነበረው የሰርክ ሒወቴ ። ያ ዐመት በሒወቴ ውስጥ እንደ ተራሬ ቁንጮ ብቅታ ልቆ-ዘልቆ ይታያል ፤ ይህችን ዓለም በተመሥጦ ነፍስ ሳወጣ'ና ሳወርድ ፤ በሒወት ጉዞዬ ላይ አስቁሞ የሰውን ልጅ ጎዳናዎች፥ የፍላጎቶቹን ሜዳዎች፥ የድካሙን አቀበታማ ስርጓጉጥ ሰርጦች ፥ የሕጎቹን'ና የልማዶቹን ዋሻዎች አሳይቶኛል'ና '(...በውስጤ ዑቀትን ስላሠረዐብኝና የሰው ልጅ ዕድል ተለዋዋጭ ተፈራራቂ መኾኑን አስረድቶኛል'ና )።
በዚያ ዓመት ዳግመኛ ተወለድሁ፤ አንድን ሰው አሳዛኝ መከራ ካልገራው፥ ሥቃይ ካላስነሸጠው ፥ ፍቅር በራእያት መደብ ላይ ካላስተኛው ኑሮው በመጣፍ ሒወት ውስጥ ልክ እንደ ነጣ ገጽ ኾኖ ይቀራል።
በዚያ ዓመት የሰማይ መላ'ክት ባ'ንዲት ውብ ሴት ዐይኖች ውስጥ ሲመለከቱኝ አየሁ። በዛውም ዓመት የገሃነም ሰይጣኖችም ባ'ንድ 'ርኩስ ሰው(ወንጀለኛ ) ልቡና ውስጥ ሲበግኑ ሱተከነከኑ'ና ሲጣደፉ አየሁ ። በሒወት ሠናይና እኩይ ነገሮች ውስጥ መላክትንና ሴጣኖችን ማየት የተሳነው ማነኛውም ሰው ቢኾን ልቡናው ካስተውሎት ከባይኖት በጣምር ይርቃል፥ ነፍስያውም ፍቅርን የማታውቅ ባዶ ገዋ ትኾናለች።

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

የግል ዩዘራቸው ስለጠፋብኝ ነውኮ ከቻልን ልንመልሳቸው እንሞክራለን ካልሆነ ባለው እንደፊቱ መቀጠልም እንችላለን

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

ታውቃላችሁ ብዙ ሰዎች ናቸው ከዚህ ግሩኦግሩፕ የጠፉት በተለይ ዋና ዋና ተሳታፊዎች የሚባሉት ብዙም የሉም

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

መኖር እንኳ አለች ትግባ አትግባ እንጂ(እናስመልሳል 😂)

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

ለኔም አለቃነቴን ትመልስ😑

ሲጀመር ግን ትዙ ግሩፑን left ሳትል አልቀረችም😂

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

ሰለዚህ ባህሪ ተፈጥሮአዊ ነው ማለት እንችላለን ሁሉም ሰው ተመሳሳይ ተፈጥሮአዊ ጠባይ አለው ማለት ነው

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

ብዙ ልጆች በአንድም በሌላም ምክንያት ጠፍተዋል። ብቻ በሰላማቸው ይሁንልን💜

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

የሰው ልጅ ባህሪ ተፈጥሯዊ ?
ወይስ የአስተዳደግ ውጤ?
ባህሪና ጠባይ አንድ ናቸው ወይስ
መሰረታዊ ልዩነት አላቸው መልካም ሰብአዊ ጠባይ እንዲኖር ምን ላይ መስራት አለብን?
(ሰው ጠይቆኝ ነው ሀሳባችሁን እፈልጋለሁ ወገን)

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

እኮ አንተን ስጠኝ ብላ መሆኑ ነው?😂

Читать полностью…

ቅኔ ያለው የመወያያ ገፅ

😂አማኝ አለመሆን ጠቀመህ እንጂ የተፈጠረችልህን ገለሀላ

Читать полностью…
Подписаться на канал