12246
✍ ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..! ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤ የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡ 🎖For any comment T.me/Aisuu_bot 💠Another channal @IslamisUniverstiy_public_group
......, #ፍቅር ...,
✍አሚር ሰይድ
🔰አንዲት እህቴ ፍቅር ይዞኛል ግን ፍቅር ምንድን ነዉ ብላ ጠይቃኝ የዛሬ 2አመት በፊት የመለስኩላት ነዉ እናንተ ስለፍቅር ምን ትላላችሁ⁉️❓
☞ፍቅር ህልም ነዉ ስትነሺ የማታገኚዉ
☞ፍቅር ንፋስ ነዉ ከየት በኩል እንደመጣ የማታየዉ
☞ፍቅር ዉሀ ነዉ ጨብጠሽ ይዘሽ የማታስቀምጪዉ
☞ፍቅር የእሳት እረመጥ ነዉ አንዴ የእሳት ረመጥ በእግርሽ ከረገጥሽዉ እግርሽ እንደመግል ሁኖ ያመረቅዛል በዛ እግርሽ መሬት መንካት አትችይም ሳታነክሽ ብዙ ወር ትቆያለሽ ከዛ በስንት ድካም ይሻልሻል
☞ፍቅር የማያገኙትን ሰዉ በዉንም በህልምም አብሮ እሱ ጋር እየኖሩ አብረዉ ልጅ ሲወልዱ ተከባብረዉ ሲኖሩ የሚያሳይ የህይወት ስዕል ነዉ ...ስዕል ደግሞ እዉነት አይደለም ያዉ ስዕል ነዉ...,ፍቅር የማያገኙትን ሰዉ ልብሽ ላይ ስለሽ ያንን ስዕል እንዳይጠፋብኝ እያሉ የመጨነቅ የመጠበብ ኑሮ ነዉ..ስዕሉ እንዳይጠፋ የመታገል ህይወት ነዉ
☞ፍቅር ተራራ ነዉ ይላሉ ግን ፍቅር ተራራ አይደለም ሜዳ ነዉ ..ግን የሜዳ ላይ ተራራ ነዉ ...ተራራ ስትወጪ ይደክምሻል ግን በግድም ቢሆን ወጥተሽ ትጨርሻለሽ ከተራራዉ ጫፍ ላይ ደርሻለሁ በስንት ድካም ብለሽ ራስሽን ታደንቂያለሽ ደክመሽም ቢሆንከተራራዉ ጫፍ በመድረስሽ
...ፍቅር ግን የሜዳ ላይ ተራራ ነዉ ሂደሽ ሂደሽ አጨርሽዉም ጫፉ ላይ የማይደረስ ነዉ...ለምን ብትይ ተራራ ወጥተሽ ከጫፍ ትሆኛለሽ...የወጣሽዉን ተራራ ደግሞ መዉረድ አያቅትም ተራራ የሚከብደዉ መዉጣቱ ነዉና
ሜዳ ግን ብትሄጅ ብትሄጅ ብትሄጅ አያልቅም....ለምሳሌ ከደሴ አዲስ አበባ 401 km ነዉ ያንን በእግርሽ ሂደሽ ትጨርሽዋለሽ?በጭራሽ አጨርሺዉም ግን ጠንካራ ነኝ ብለሽ ካሰብሽ አያቶቻችን መኪና በሌለበት ዘመን ሂደዋል እኔም በእግሬ እሄዳለሁ ብለሽ ከተሳካልሽ ☺️ አአ ከሄድሽ😉 ከአአ አሶሳ ሱዳን ድንበር 660 km አለ እሱን በእግርሽ ሂደሽ ትጨርሺዋለሽ?በጭራሽ አሞክሪዉም ...አይታወቅም የሰዉ አቅሙ☺️ ጠንካራ ከሆንሽ ሄድሽ እንበል አሶሳ ደረሽ ምድር ታበቃለች?ምድር ተሂዶ አያልቅም ከሱዳን ጀምሮ ስንት ሀገር አለ...በእግርሽ በመኪና በአየር ሂደሽ የማጨርሺዉ....በእግርሽ ሱዳንን አልፈሽ ብትሄጅ ስትሄጅ ስትሄጅ ዉቅያኖስ ወይ ባህር ታገኛለሽ በእግርሽ ከሞከርሽ ሰምጠሽ ትቀሪያለሽ ...ወደ ጀመርሽበት አትመለሽ ሩቅ ነዉ ባለሽበት ቀባሪ ሳትገኝ ትሞቻለሽ ማለት ነዉ☺️ ፍቅርም ሂደዉ ሂደዉ የማይመለሱበት የቁም ሞት መሞቿ ህይወት ነዉ
ፍቅር ተራራ ሳይሆን ሂደሽ ሂደሽ የማጨርሺዉ የሜዳ ላይ ተራራ ነዉ ...
እናም ይሄን ረጅም መንገድ ሂደሽ የማጨርሽዉ አለም ...በእግሬ እሄዳለሁ ብለሽ ማሳመን ነዉ ፍቅርም እወጠዋለሁ ብለሽ ሂደሽ የማጨርሽዉን ጉዞ መጀመር ነዉ...ከጀመርሽም ይሄን የማይጨረስ አለም አንድ እርምጃ ሳትረመጅ ሀሳብሽ ተበታትኖ እግርሽ ተሳስሮ ሳትሄጅ ትመለሻለሽ ..,ፍቅር አሰቡበት ሳይደርሱ ወደ ፊት የሆዱ መስሎ በማያቁት መንገድ ወደ ሆላ መመለስ ነዉ.. ግን ወደ ሆላ መመለስሽ የሚገባሽ ቡሀላ ሳትሄጅ ከተመለሽ ቡሀላ ነዉ
☞ፍቅር ካልተሳካ ከህይወት ተስፋ መቁረጥ ነዉ ...ደግሞም ሴት ነሽ ይከብዳል ወንዱ ሌላ ሊኖረዉ ይችላልና ....እሱ ካልተረዳሽ ስቃይ ነዉ
☞ፍቅር ያለዉ አማረኛ ፊልም እና ዘፈን ላይ ነዉ...አማረኛ ፊልም ስናይ ዘፈን ስናዳምጥ ያንን ያየነዉ ያዳመጥነዉ ሙዚቃ ወደ ዉስጣችን ገብቶ ያንን ለማዋሀድ እኔስ የለኝም ወይ? ብለን በአየነዉ ፊልም ሙዚቃ ፍቅርን እየሳልን የምንረበሽበት የሙዚቃዉ የፊልሙ አይነት አፍቃሪ ሳናገኝበት የምንኖርበት የፊልምና የሙዚቃ ኑሮ ነዉ
☞ፍቅር ጥልቀት ያለዉ ክብ ዲንጋይ ነዉ...ያንን ዲንጋይ ለማዉጣት ብቻሽን ብትቆፍሪም ሰዉ ቢረባረብ የማይወጣ ነዉ...ፍቅርም ጥልቀት ያለዉ ከልብ የማይወጣ ክብ ዲንጋይ ነዉ
☞እኔ የምልሽ ፍቅር ከሚይዝሽ ኮረንቲ ያዝ አርጎ ቢለቅሽ ይሻላል...ለምን ኮረንቲ አስደንግጦ ይተዉሻል ፍቅር ግን ያፈቀርሺዉ የኔ ይሆን በሚል እልክ ....እራስሽን በራስሽ አሳምነሽ የምትኖሪበት ህይወት ነዉ፡፡
☞ፍቅር ያፈቀሩትን ሰዉ የማያገኙበት ህይወት ነዉ...ትዋጀሻለሽ ግን አብሮ ለመሆን የምትሰቃይበት ኑሮ ነዉ.
የማይረዳሽ ለትዳር የማይሆን ከሆነ የወደድሽዉ አደራ አደራ ፍቅርሽን አፍነሽ አላህ እንዲያነሳልሽ ዱአ አርጊ ካልሆነ እሱ በፍቅር ልብሽ ላይ ይጫወትብሻል ሀራም ያሰራሻል...የሴት ልጅ ፍቅር ከባድ ነዉ ፡እኔ ይሻላል የምለዉ ወንድ ቢያፈቅር ነዉ ወንድ ከወደደ ይታገሳል ተስፋ ቆርጦም ይነሳል...ሴትግን ብታፈቅር ትጎዳለች በተለይ
የማይረዳ ለትዳር የማይሆንሽ ከሆነ
✅ ደግሞ ማወቅ ያለብሽ በፍቅር መለየት አለ ምክንያቱን ሳታቂ የኔ ነዉ ያልሽዉ ሊከዳሽ ይችላል.....ወይም በቤተሰብ ወይ በእትህት ወንድም ወይ በተሳሳተ መረጃ ልብ ላይ ያርፍና የሆነ ጊዜ ይቆረፍዳል የዛን ጊዜ ከወዳጅ ከምወጂዉ ትለያለሽ የዛን ጊዜ ማፍቀርሽን ትጠያለሽ ፍቅር ልብሽ ላይ ተቀምጦ ትሰቃያለሽ ከሰዉ በታች ልትሆኝ ትችያለሽ....ከሚወዱት መለየት ከባድ ነዉ እምባስ ይወጣል የልብ እምባ ግን እዛዉ አልቅሶ ይቀራል😔...የማይወጣ ነገር የቀረ ደግሞ ለዉስጥ በሽታ ነዉ መቼም ጤነኛ አትሆኝም....
አሏህ በተከበረ ቁርአኑ እንኳን ከወዳጅ መለያየት
ሀዘኑ በጣም ጥልቅ እንደሆነ ይናገራል
የአይን ብርሃን እስከማጣት
( وتَوَلَّىٰ عَنْهُمْ وَقَالَ يَٰٓأَسَفَىٰ عَلَىٰ يُوسُفَ وَٱبْيَضَّتْ عَيْنَاهُ مِنَ ٱلْحُزْنِ فَهُوَ كَظِيمٌۭ )
" ከእነሱም ዘወር አለና ኣ«በዩሱፍ ላይ ዋ ሐዘኔ!» አለ ፡፡ ዓይኖቹም ከሐዘን (ለቅሶ) የተነሳ ነጡ ፡፡ እርሱም በትካዜ የተሞላ ነው ፡፡"
_....የየሱፍ አባት ወደዉ አልቅሰዉ አይናቸዉን ያጡት ነብይን ነዉ..እኛ ግን አላህ ለፈጠረዉ ተራ ሰዉ አልቅሰን አይናችንን ታመን ልባችንን ማድማት የለብንም
ሆነም ቀረ...የሰዉ ልጅ ለራሱ ሳያቅ የራሴ ህይወት ሳይገባኝ በሰዉ እፈርዳለሁ ...
✔በጥላቻ ድልድይ መረማመድ ቁልቁለት ነው።
✔ፍቅርን በተግባር ማረጋገጥ ዳገት ነው።
✔ስለ በደል ማውራት ተራ ነው።
✔ የተበዳይን እንባ ማበስ ከባድ ነዉ😔።
✔መፍረድ ቀላል ነው።
✔ፍትሀዊ መሆን ምጥ ነው።
✔መለያየት ቀላል ነው። አንድ መሆን ፈተና ነው።
✔ትልልቅ ነገሮችን ማሰብ ቀላል ነው። ትንንሽ ነገሮችን ማድረግ ከባድ ነዉ።
✔በምኞት መኖር ቀላል ነው። እውነትን መቀበል መራር ነው።
✔ተስፋ ማድረግ ቀላል ነው። አማኝ መሆን ፅናት ነው።
ብቻ አሏህ ከሁላችንም ጋር ይሁን ከፍቅር የዉሸት ኑሮ ይሰዉረን
እናም እኔ የምለዉ ልብን አትዉደድ አይባልም ግን መጀመሪያ ለይል ተነስተሽ አልቅሰሽ ዱአ አርጊበት
ይቅርታ ግን እኔ ለፍቅር ጥሩ አመለካከት የለኝም😊 እኔ ለአንቺ የምረዳሽ ቢኖር ከፍቅር ተስፋ ማስቆሮጥ....የምወጂዉን እንደማታገቢ ተስፋ ማስቆረጥ ...ፍቅር በሌለበት አለም አፍቃሪ እንዳትሆኝ አእምሮሽን እንድትጠርጥሪ ማድረግ...የፍቅር ህይወትሽ እንዲጨልም ማረግ ብቻ ነዉ😂
💛 ጧኢፍ ነዋሪዎቿን በነቂስ አውጥታ የስድብ እና የድንጋይ ናዳ እንዲወርድበት ፈቀደች። ምድር ከሰውነቱ የሚፈሰውን ደም መጠጠች።
❤️በመርዝ የተለወሰ ምግብ ሲሱጠት፣ ከሚናፍቅው የትውልድ ቀዬ ሲባረር ይቅር ባይነት የዘወትር ስንቁ ነበር። ስቃይ በተሸከመው አካልና መንፈሱ ታግዞ እግሮቹ አስከሚያብጡ ድረስ ለሊቱን በመቆም አመስጋኝ ባሪያ ለመሆን ከአምላኩ ጋር ያወጋል ሰዎችን ይቅር ይሉ ነበር ሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ
እናም ፈተና መብዛት ችግር መደራረብ ባይኖር ዱንያ የደስታ ሀገር ብትሆን ሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ ባልተፈተኑ ነበር እናም አንተም አንቺም እሱም እሷም እናንተም ፈተና ላይ ናቸሁ ፈተና ጨርሳችሁ ትንሽ ከተደሰታችሁ ቡሀላ ሌላ የከበደ ፈተና እንደሚጠብቀን እርግጠኛ ሁን የዛን ጊዜ ነዉ ኢማንህ የሚለካዉ፡፡
ኢማናችን መለካት እንጂ መነካት የለብንም ወገን
📌 እጅግ አምልኮ በማብዛት የሚታወቀው ታላቁ ታቢዒይ አልፉደይል ኢብኑ ዒያድ ረሒመሁላህ ፈገግታ አያበዙም ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ግን ልጅ ሲሞትባቸው ፈገግ አሉ፡፡ ለምን ፈገግ እንዳሉ በተጠየቁ ጊዜ “አላህ የወደደው ነገር ነውና እኔም ወድጄ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) የወደደውን እንድትወድ ነፍሴ ፈገግ እንድትል አስገደድኳት” አሉ፡፡
ዑለማዎች ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያለቀሱበትንና አልፉደይል ግን ፈገግ ያሉበትን ሁኔታ በማንሳት ለመተንተን ሞክረዋል፡፡ በመታገስ ደረጃ አፉደይል ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይበልጣሉ ማለት ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ትርጉሙም፡- ሞት በሚመጣበት ቅፅበት ቀልብን በሁለት ሰሜት ውስጥ ይከታል፡፡ እዝነትና ውዴታ፡፡ ማንም ሰው ሁለቱን ስሜቶች በአንድ ጊዜ ማስተናገድ አይችልም፡፡ አልፉደይል ሁለቱን ማሳካት አልቻሉምና በውዴታ ስሜት አንድም ፈገግ ማለት አለባቸው አሊያም አብዝተው ማልቀስ ነበረባቸው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ግን ሁለቱን ማሳካት ችለዋል፡፡ አላህ የወደደውን ወደዋል በሌላ በኩል ደግሞ አልቅሰው እዝነት ስሜት አሳይተዋል
📌 የነቢያችን አክስት የሆነችው : እመት ሶፊያ በኡሑድ ጦርነት ወቅት ቁስለኞችን ውሃ ታጠጣ ነበር፡፡ ታላቁ ጀግና ሐምዛ (ረ.ዐ) ተገደሉና አካላቸውም እንዲቆራረጥ ሆዳቸው እንዲቀደድ ተደረገ፡፡ ሒንድ በበቀል ስሜት ጉበታቸውን እስከማኘክ ደረሰች። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለልጇ ዙበይር ኢብኑ አልዐዋም ዝበይር ሆይ! ሶፊያን ወደ መዲና ይዘሀት ሂድ ሐምዛን ማየት የለባትም፡፡” አሉት። ልጇም ሄደና “እናቴ ሆይ! ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ መዲና ተመለሽ ብለውሻል፡፡” አላት፡፡
ልጄ ሆይ! ይህን የምታደርጉት ሐምዛን እንዳላይ ብላችሁ ነው አይደል? አለችው፡፡
....“አዎን” አላት፡፡
....እሷም “ልጄ ሆይ! አላህ ከዋለልን ፀጋ አንፃር በሐምዛ ላይ የደረሰው በጣም ቀላል ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) በሐምዛ የፈተነን ሥራውን መውደድ አለመውደዳችንን ለማየት ነው፡፡ ወደ አላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሂድና የአላህ መልዕክተኛ ሆይ አላህ በሐምዛ የፈተነን ሥራውን መውደዳችንን ለመፈተን ነው ብላለች ሶፊያ በላቸው ፡፡ ልጁም ወደ ነብዩ (ሲዐወ) በመመለስ ነገራቸው፡፡
... ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) “እንግዲያውስ ማየት ትችላለች፡፡” አሉ፡፡ ሄደችና አይታው አለቀሰች፡፡ ኢንና ሊላህ ወኢንና ኢለይሂ ራጂኡን የኛዑን እኛ የአላህ ነን ወደ አላህም ተመላሾች ነን፡ በማለትም ዱዓእ አደረገችለት፡፡
እናም አላህ በሚያመጣብን ፈተና የዱንያም ሆነ የጂን የሲህርም አላህ ወዶን እየፈተነን እንደሆነ አንዘንጋ
♦ ጅን ሲህር ሳሂር ደጋሚ ጠንቋይ ደብተራ እንደማይጎዳ አሏህ ብቻ ጎጂ እንደሆነ ማወቅን ከኢማኖች ውስጥ ጠንካራ ኢማን ሁኖ እናገኘዋለን!! በአሏህ ላይ የቂን እጅግ የምንፈልገው መሳርያ ነው!! ሌቦች ቤትን ሊዘርፉ ሲመጡ አለሁ ብሎ ድምፅን ማሰማት ሲቀጥልም የመሳርያን ድምፅ ማሰማት እነርሱን እንደሚያስበረግጋቸው ሁሉ የቂን ልክ እንደዛው ጅኖችን ያስፈራቸዋል እንዳይቀርቡን!! ይሁንና ያለ እውቀት ያለ መጠበቅያ የቁርአን አያዎች እና ዚክሮቸች ማለት ያለ መሳርያ መሳርያ ታጥቀው የመጡ ሌቦችን ማስፈራራት ብቻ ነው፡፡ ለኛ መሳርያችን ለጅኖች ሊያውም ከባለጌዎች ለመጠበቅ የምንታጠቀው መሳርያ ዚክርና ቁርአን እንዲሁም ዱአእ ነው፡፡ ሌላውን አይነት የመሀይማን መሳርያ የሆነውን ጥንቆላ መተት ፀበል እና አንጃ ግራንጃዎች ልክ ሌቦችን እንደመማፀን እንደመደራደር ነው የምንቆጥረው፡፡ ከሌባ ጋር ድርድር የለም ባንተ ንብረት ላይ መጥቷልና ፡፡ ከጅን ጋርም እያጠቃህ መደራደር የለም በቁርአን በዚክር ልኩን አሳይተሀው መከባበር እንጂ፡፡
🖍🖍 እናም ፈጣሪ ይሁን ብሎ ተፅፎብን ከሆነ ትዕግስት ጥንካሬ ፅናት ያስፈልጋል፡፡ በሲህር በጂን የሚፈተን ሰዉ በዛዉም የፀና የጠነከረ አላህ ወዶን ይሆናል ዱአ ላይ መበርታት ግዴታ ነዉ...ከዱአ በጭራሽ ተስፋ ልንቆርጥ አይገባም
{ وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِی عَنِّی فَإِنِّی قَرِیبٌۖ أُجِیبُ دَعۡوَةَ ٱلدَّاعِ إِذَا دَعَانِۖ فَلۡیَسۡتَجِیبُوا۟ لِی وَلۡیُؤۡمِنُوا۟ بِی لَعَلَّهُمۡ یَرۡشُدُونَ }
ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡[አል በቀራህ: 186]
🟢 አንድ ድንቅ የሆነ ሐዲስ አልቁድስይ ላካፍላችሁ፡፡ ነቢዩ ባስተላለፉት ሐዲስ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- “የአደም ልጅ ሆይ! እኔም እፈልጋለሁ አንተም ትፈልጋለህ፡፡ እኔ ለምፈልገው ነገር እጅ የሰጠህ እንደሆነ የምትፈልገውን አመጣልሃለሁ እኔ ለምፈልገው ነገር እጅ የማትሰጥ ከሆነ በምትፈልገው ነገር ላይ እንድትደከም አደርግሃለሁ፡፡ በመጨረሻ እኔ የምፈልገው ነገር ብቻ እንጂ የሚሆን የለም፡፡” ይለናል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) በተከበረ ቃሉ “አላህ ካሻ በስተቀር አናንተ አትሹም (አል-ኢንሳን ፡3) ብሏል፡፡
🟢 ኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ) ዱዓዬ መቼ ተቀባይነት እንደሚያገኝ አውቃለሁ፡፡ አሉ፡፡ “እንዴት ልታውቅ ትችላለህ? ተባሉ፡፡፡ “ቀልቤ በጥልቀት የአላህ ፍራቻ ካደረበት፣ መላ አካላቴ ከተንቀጠቀጠ፣ ዐይኔ ካነባች፣ ይህች ሰዓት ዱዓዬ ምላሽ የሚያገኝበት ነው፡፡ በማለት በዱዓዬ እጠናከራለሁ፡፡ ብለዋል፡፡
ለዱአ መቸኮል አያስፈልግም
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “እስካልቸኮላችሁ ድረስ ምላሽ ይሰጣችኋል፡፡” አሉ፡፡ መቸኮል ሲባል እንዴት ነው? ሲሏቸው አንዳችሁ “ዱዓእ አደረግኩ፤ ዱዓእ አደረግኩ ምላሽ አላገኘሁም፡፡ ይላል፡፡ (ተስፋ መቁረጥ) ዱዓእ ይተውን ይተዉና በዚያው ምላሽ ያጣል፡፡” ብለዋል፡፡
ሲህር ከተደረገብን ወደ አላህ የማይቋረጥ ቀጣይ የሆነ ዱአ ያስፈልጋል፡፡
🟢 ኢብኑ አልቀይም ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡ ብትባረርም እንኳን ከአላህ በር ላይ ከመቆም ተስፋ አትቁረጥ፡፡ ቢመልስህም እንኳን ምክንያት ከማቅረብ አትውረድ፡፡ በሩ ተቀባይነትን ላገኙት የተከፈተ እንደሆነ ቀስ ብለህ በስርአቱ ግባ፡፡ ድሀ ነኝ ምፅዋት እፈልጋለሁ፡፡ በለው፡፡ ምፅዋት የሚሰጠው ለድሆችና ለችግረኞች ነው፡፡ እኔም ምስኪን ደሃ ነኝ፡፡ በለው፡፡👇👇👇
ዛሬ ጁምአ ነዉ የሆነ ችግር ሲበዛ ወይ ነይተን ለሰዉ ነግረን ያልተሳካ ካለ እንደዚህ ልጅ ሁኔታ ለጀሊሉ ነግረዉን ያሳፍረን ይሆን??
እስኪ ለጀሊሉ እንደዚህ ልጅ ሁኔታ አድርገን እንገረዉ
Join👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
✍ አሚር ሰይድ
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
⭐️ #ክፍል👉አስራ አራት 1⃣4⃣
🟢 የሲህር(ድግምት) የቡዳ(አይንናስ ጂን ህክምናዎች
ነብዩ ሰዐወ በሀዲሳቸዉ አላህ እኔን በጠረጠራችሁኝ በኩል ታገኙኛላችሁ ብሏል እናም ሲህር አለብን ብለን ባንጠራጠር ራሳችን ባናሳምን ጥሩ ነዉ ምልክቱ እስካልታየብን ድረስ
...በተጨማሪ በዉዱዕ የምንቀሳበቀስ ..የጠዋት ማታ ዚክር የምናደርግ...
>> አላህ የከከለልንን የምንከለከል ከሆነ
>> ዚናን ሙዚቃን ዉሸትን ስርቆት የየቲም ሀቅ የሰዉ ሀቅ የሚዲያ አጠቃቀማችን ለሀላል ነገር ብቻ ከሆነ ..
>> ከትልቅም ከትንሽም ወንጀል የራቅን ከሆን በአላህ ፍቃድ ወደኛ ማንም መጥፎ ሰዉ ቢያስብ አይነካንም
ከነካንም በዲናችን ጠንካራ ከሆን ዚክር ቁርአን የምናበዛ ከሆነ እንደተያዝን ሳናቀዉ በራሱ ጊዜ ይለቀናል፡፡
🔻🔻 ግን ከላይ የጠቀስኳቸዉ በትልቅ ወይ በችንሽ ወንጀል በከፊልም በሙሉም የተዘፈቅን ከሆነ በተጨማሪ እስኪ ወደ ሆላ 3 ወይ 4አመታት አስታዉሱ የነበራችሁን ጥንካሬ
☞ አሁን ግን የኢማን መንሸራተት ካለባችሁ..
☞ ትዳር ሲመጣ ጭንቅጭ ጭንቅ የሚላችሁ
☞ከማግባት ይልቅ ለማበላሸት የሚቀናችሁ..ከዛ ካበላሻችሁ ቡሀላ የሚቆጫችሁ ከሆነ
☞ አጭቴችሁ ምነዉ አጭቼ ባልነበር ከአጨሁት ይሄኛዉ ይሻለኝ ነበር ወይም ያችኛዋ ትሻለኝ ነበር እያለ ሸይጧን ለማበላሸት የሚወሰዉሳችሁ ከሆነ
☞ ቁርአን ሂፍዝ እስከ መጥፋት..
☞ ቁርአን ስቀሩ ስታዳምጩ የሚጨንቃችሁ የሚያልባችሁ ካለ ሩቃ ቢደረግባችሁ ጥሩ ነዉ፡፡
🌐🌐 ሩቃ ሁለት ጥቅም አለዉ
#የመጀመሪያዉ በኛ ላይ ሲህር ወይ ድግምት ወይ አይነጥላ ጅን ካለ ይለቃል
#ሁለተኛ ጥቅሙ እኛ ሁሉም ከሌለብን ቀልባችን ይጀደዳል በቁርአን ጥንካሬ ያገኛል፡፡
✅ በራስ ሩቃ ማድረግ በጣም በላጩ ነዉ
ሩቃ ሲባል ከባድ አድርገን አንያዘዉ ..ሩቃ በቀላል ቋንቋ ከአላህ ጋር ያለን ግንኙነትን ማስተካከል በዚክር በቁርአን ልብን ማርጠብ ማለት ነዉ
✏️ የጠዋት የማታ ዚክሮችን ማለት
✏️ ሲተኙ ሱረቱል ናስ ፈለቅ አሀድን ሶስት ሶስቴ መቅራት አያተል ኩርሲን መቅራት እነዚህን ስንቀራ ዉሀ በሀይላንድ ይዘን ዉሀዉ ላይ መቅራት ከዛ የሩቃ ዉሀ ሆነ ማለት ነዉ...የሩቃ ዉሀ መጠጣት ከተቻለም የወይራ ዘይት ጥቁር አዝሙድ ዘይት ዉሀዉ ላይ ጠብ ጠብ አድርጎ መጨመር ነዉ
✏️ ቁርአንን በቻልነዉ አጋጣሚ በቁርአን መቅራት..
ዚክሮችን በስራ ቦታ በትምህርት ቤት ታክሲ ላይ ሲንቀሳቀሱ ዚክሮችን ማድረግ አላህን ማስታወስ ነዉ...
🔶 #ነብዩላህ_የኑስ ዐ.ሰ ብዙ መልካም ስራ አልነበራቸዉም ጥፋት ባጠፉ ጊዜ አላህ ሱ.ወ በዓሳ ሆድ ዉስጥ ጣላቸዉ ከዚያ ያወጣቸዉ ያደረጉት ተስቢህ የአላህ ዉዳሴ ነዉ፡፡
አላህ ሱወ እንዲህ ይላል
እርሱ ለጌታዉ ከአወዳሾች ባልሆነ ኑሮ እስከሚቀሰቀስበት ቀን ድረስ በሆዱ ዉስጥ በቆየ ነበር
(አል ሷፋት 143-144)
እናም አላህን ማዉሳት መቶበት ለሁሉም መፍትሄ ነዉ
✏️ በቁርአን ዉስጥ በደረጃ ትልቅ አንቀፅ አያተል ኩርሲይ ነዉ በአንድ አንቀፅ ዉስጥ ስድስት ያህል መልካም የአላህ ስሞች እናገኛለን...አያተል ኩርሲን ባገኝንበት አጋጣሚ መቅራት
✏️ ወንጀል ላይ ካለን ዚና የምንሰራ ሙዚቃ የምናዳምጥ ትንሽም ትልቅም ወንጀል ላይ ካለን ከዛ መታቀብ
✏️ የማይጠቅሙ የማይጎዱ ጓደኞችን መቀነስ
✏️ በtv በስፒከር ቁርአን መክፈት ጆሯችን ጎን አድርገን የተለያዩ የሩቃ አንቀፆችን ቁርአኖችን መቅራት ነዉ...በአላህ ፍቃድ ጂኑ ሳይናገር ሳይለፈልፍ በራሱ ጊዜ እየተወገደ ይሄዳል፡፡
ከበፊቱ ለዉጥ ካለን እንቅልፍ እምቢ የሚለን ከሆነ እንቅልፍ መዉሰድ ከጀመረን መጥፎ ህልሞች እያየን በፊት ከነበረ ከዛ ቡሀላ መጥፎ ህልሞች ከራቁልን ..ሙዚቃ ካስጠላን ከዚና ቱብት ካደረግን ወይም ከዉሸት ከመጥፎ ጓደኛ ከራቅን በራሳችን ሩቃ ተሳክቶልናል ማለት ነዉ ...በዚሁ ኢማንን እያጠነከሩ መሄድ ነዉ
🟢 ጂን መቷቾሁ ከሆነ ወይም በምቀኛ ሰዉ ሲህር ድግምት ተደርጎባችሁ ከሆነ እኔ ራሴን በራሴ ሩቃ ማድረግ አይሆንልኝም ብላችሁ ካሰባችሁ...ሩቃ የሚያደርግላችሁ ፈልጋችሁ በቁርአን ሀይል የዛን ጊዜ መናገር ይጀምራል በአላህ ፍቃድ ይለቃል፡፡
📚📚 ከሁሉም ግራ የሚገባዉ ነገር ማን ጋር ሩቃ እንጀምር❓❓ የሚለዉ የብዙ ሰዉ ጥያቄ ነዉ ለምን ቢባል አንደንድ ሩቃ እናደርጋለን የሚል በሩቃ ስም ሀራም የሚሰሩ ሴቶች ጋር የሚተሻሹ በተጨማሪም ሳይታመሙ ታመምን የሚሉ አሉ እዛ ሂደዉ መተሻሸት የሚፈልጉም ሴቶች እንዳሉ ልናወቅ ይገባል ..እናም ትክክለኞቹ ማን ናቸዉ??ግራ የሚያጋባ ነዉ
♻️♻️ ግን እኔ የምለዉ ቆይ እስኪ እቤት እናት አባት እህት ወንድም ሲታመም ምን የሚያስፈራ አለ?? የአላህ ቃል በስፒከር ከፍቶ በተከታታይ ቀናቶች መቅራት ነዉ ብዙዉ በአንድ ቀን ይለቃል እናም እኔም አንተም አንቺም እሱም እሷም ማላቀቅ እንችላለን መጀመሪያ በአላህ መተማመን አንተን ይዤ በአንተዉ ቃል ቁርአን አድነዋለሁ ብሎ ነይቶ መነሳት ነዉ እናም ሩቃ ቤት ከመዉሰድ መጀመሪያ በራስ መታገል ይበልጣል፡፡
የተለያዩ የሩቃ እወቀቶች መቅሰምና መፅሀፎችን ማንበብ ለቤተሰብህ ለጓደኛህ መሆን ይቻላል
✅ ሴት የዲን እህትሽ ስትታም ለምን ለአጂ ነቢይ ወንድ አሳልፈሽ ትሰጫለሽ?? ሀስቢየሏሁ ወኒዕመል ወኪል ብለሽ አንቺዉ ቁርአን ቂሪባት
✅ እህትህ ስትታመም ለምን ወንድ ሩቃ የሚያደርግ ትፈልጋለህ??
ሀስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል ብለህ ጀምረዉ ...ሀስቡነሏህ ብለህ ከጀመርክ ከጀመርሽ ሰበብ አድርስ አላህ ያግዘሀል ያግዝሻል ግን ያለስበብ ወደፊት ያለርምጃ የሚሆን አይደለም ሰበብ ግዴታ ነዉ
ሀስቡነላህ ወኒዕመል-ወኪል”
✔ ነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ወደ እሳት በተወረወሩ ጊዜ የተናገሯት ቃል ነች፡፡
✔ ነብዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) ፊርአውንን በመሸሽ ላይ እያሉ በሱ ያመኑ ሰዎች “እነ ፊርዐውን ደረሱብን!” ባሏቸው ጊዜ ይህችኑ ቃል ተናግረዋል፡፡
✔ የአላህ መልእክተኛም (ሰዐወ ሰዎች "በኡሀድ ጦርነት ሰዎች እናንተን ለማጥቃት ተሰባስበዋልና ፍሯቸው ባሏቸው ጊዜ ሀስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል ይህችን ቃል ብለዋል፡፡
እናም ሀስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል ብለን ጀምረን ፈጣሪ አያሳፍረንም እርግጠኛ ሁኑ
✔ እናታችን ሀጀር ብቻዋን በዛ በርሀ ለኢስማኢል ዉሀ ጠምቶት ሲያለቅስ ቁማ አልተመለከተችም ሰባት ጊዜ ስትዞር ነዉ ጂብሪል ከሰማይ በመውረድ በክንፉ እግር ስር በመጫር ዘምዘም ዉሀ እንዲፈልቅ ያደረገዉ
✔ መርየም በዛ በምጥ ተሰቃይታ ባለችበት ጊዜ አላህ የሚበላ የሰጣት እኮ በጅብሪል አማካኝነት የተምሩን ዛፍ አወዛዉዢዉ ሲላት ስታወዛዉዘዉ ነዉ የሚበላ ያገኘችዉ...እናም አላህ የሚያግዘን ከኛ ትንሽ ሰበብ ይፈልጋል ሀስቡነሏህ ብለን መጀመር ነዉ 👇👇
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
✍ አሚር ሰይድ
⭐️ #ክፍል👉አስራ ሶስት 1⃣3⃣
🟢 ጊዜዉ ከባድ ነዉ ልንገራችሁ እስኪ ብዙ መንገር ይቻላል
ግን ለመስማት የሚዘገንን ነዉ ግን ይሄ ከሌላዉ አንፃር ይሻላል ብየ ነዉ፡፡
አንዲት እህታችን 7 ልጅ አላት..ባሏ የከባድ መኪና ሹፌር ነዉ እናም ብዙ ቀን እቤት አያድርም፡፡ እቤት ስለማያድር ሚስቲቱን ሌላ ወንድ ጋር እኔ ሳልኖር ብትሄድ ወይ ብትተኛብኝስ??ብሎ ይጠረጥራታል ፡፡
ጊዜ የማያመጣዉ የለም የመጨረሻዉ ልጅ ይታመምና እኛ ሰፈር ያለ ሩቃ የሚያደርግ አንድ ብር የማይቀበል ለአላህ ብሎ የሚሰራ ነበር እሱ ጋር መጣች ልጁን በተወሰነ ደቂቃ በአላህ ፍቃድ በአፉ ብዙ ነገር ወጥቶ ሻረ....እናቲቱም እስኪ እኔም ለሊት ጭንቅ ጭንቅ ይለኛል ስትለዉ በቁርአን ገና ጀመር ሲያደርግ...ለማመን ይከብዳል እርይ ማለት ጀመረች...ጂኑ ተነቃብኝ ተጋለጥኩ ተጋለጥኩ ማለት ጀመረ...
ከዛ ልጁ ጂኑን መጠየቅ ጀመረ...ጂኑ ሲናገር...
ባሏ እሷን አያምናትም ሹፌር ስለሆነ ሌላ ጋር ብትማግጥስ ብሎ ስለሚያስብ ሶስት አይነት ሲህር(ድግምት) ጎጃም ሂዶ 10,000 ብር ከፍሎ አሰራ እሱ እያሰራ ለእሷ ግን የአስቤዛ የለኝም ይላታል፡፡ የተሰራዉ የተላክነዉ 3 ጂኖች ነን የተሰጠን ስራ
➊ ቤተሰብ ጋር እንዳትስማማ ልጆቿ እንዳይወዷት አንቺ ነገረኛ ነሽ አባታችን ነዉ ለኛ የሚያስብልን ብለዉ እሷን
እንዲጠሏት...የእሷም የእሱም ዘመዶች ነገረኛ ከፉ ነች ተብላ እንድትጠላ
➋ ሌላ ወንድ ጋር ከተኛች ቀኝ አይኗን እንድናጠፋ
➌ ሌላ ወንድ ጋር ከተኛች በአደባባይ እንድትጋለጥ በዛ እፍረት እብድ እንድትሆን ነዉ ያስደገመባት ...
ድግምቱን ይዘን መጥተናል የመጀመሪያ ከልጆቿ ከቤተሰቦች እንዳትስማማ አሳክተናል፡፡ ግን ሌላ ወንድ ጋር ከተኛች ቀኝ አይኗን አጥፍተን እብድ ለማድረግ በሰከንድ ከእኛ እይታ ተደብቃ አታቅም በየሰከንዱ እንሰልላታለን እሷ ግን የዋህ ታማኝ ነች እንኳን ከሌላ ወንድ ጋር ልትተኛ ..ልጆቿ እሷን ባይወዷትም በሰገደች ቁጥር ለልጆቿ ለባሏ ዱአ ታደርግላቸዋለች...
ከዛ ትለቃላችሁ ሲባል አዎ እንለቃለን ግን እሱ መጥፎ ሰዉ ነዉ ይቺ ምንም የማታቅ ሚስኪን 7ልጅ ለማሳደግ እየተጨነቀች እሷን በዚና ጠርጥሮ እንደዚህ አድርጓታል አንለቀዉም ብለዉ ከእሷ ሰዉነት ጅኖቹ ወጡ
እናም ጊዜዉ ከብዷል ጎበዝ
ወላሂ እኔ ብዙ የማቀዉ ብነግራችሁ ጓደኞ ዘመድ ቤተሰብ ጋር ያለን ግንኙነት ትንሽ እንዳይሻክር በመፍራት ብዙዉን ከመፃፍ ተቆጥቢያለሁ
☞ እህት በእህት/እህት በወንድም/ወንድም በእህት
☞ሁለተኛ ወይ የመጀመሪያ ሚስት በባሏ
እስኪ አስተዉሉ ሸሪአዉ ፈቅዶ አቅም ኑሮት ሁለተኛ ሲያገባ በጣም ከባድ ፀብ ጭቅጭቅ በአንዷ ቤት ይኖራል ..ከአንዷ ጋር በጣም ፍቅር ከአንዷ ጋር ፀብ ምናምን በቃ ያገባዉ የተለያዩ ባህሪ ፀባይ እስከ ፍች ወይም ለሁለቱም ሚስቶቹ ሳይሆን የሚቀር ከሆነ እንጃ ወንዶች መጠርጠሩ አይጎዳም
☞ የዘመድ የጎረቤት ያለ ጉድ ከባድ ነዉ...ብቻ የሚሻለዉ #ከሰዉ_ጋር_ያለንን_ግንኙነት_በዉዱዕ_መሆን_ነዉ_ያለብን
🟢 በደንብ አዉቀን ልናሳዉቅ ለሌች ትምህርት ልንሰጥ የሚገባዉ አንዳንዴ በዲን እዉቀት ጠለቅ ብለን የማናቅ ሙስሊሞች ላይ ሸክ ጥርጣሬ የሚገባን ጉዳይ አለ እሱም ...ጂንን ሲህር ድግምትን
🔶 ክርስቲያኖቹ በፀበል እያስለቀቁት አይደል እንዴ❓
🔶ጴንጤዎች አሜን እያሉ እያተበተቡ ያስለቅቁ የለ እንዴ❓
🔶 አንዳንድ ሸሆች እየቃሙ ያስለቅቁ የለ እንዴ❓
🔶 ጠንቋዮችም ሲያስለቅቁ እያየን አይደል እንዴ❓
አንዳንዶቹ ሲሞግቱ ከባድ ጂን ወይም ብዙ ሲህር አይነጥላ ከሆነ ቀናቶች ይፈጃሉ በቁርአን ይሄን ያህል ቀን ይፈጃል በፀበል ጠንቋይ ቤት ግን በአንድ ቀን ይለቃል ታዳ ከቁርአን ዉጭ ፀበልም የጴንጤዎች ቦታ የታመዉ መሻሉ እንጂ ለምን አንወስድም?? እያሉ እየወሰዱም ነዉ...ግን ክርስቲያኖችም ጴንጤዎች እንዴት ማስለቀቅ ቻሉ??የብዙ ሰዉ ጥያቄ ነዉ
🌀 #ለምሳሌ በቫቲካኖች (ካቶሊኮች) ህክምና እነርሱ ዘንድ ሊታከም የመጣ ሰው በኮከብ ውስጥ አስረው እና ጥላሸት ቀብተው እነሱ ትልልቅ ጂኖችን እያዘዙ ሰዉየዉን የያዘዉን ትንሽ ጂን ከቦታው ያስወጣሉ። አዎ ይህ ህክምና ይሰራል ምክንያቱም ለደካማ ጅን ሁሌም ቢሆን ጠንካራ ጅን አለ ። ይሁንና ይህ ታካሚ ኢፍሪት የያዘው ወቅት ላለመውጣት ታካሚውን ሙሉ ለሙሉ ገድሎና ሰውነቱን ቀጭቶ ይወጣል። ከ 100% 25%ድንገተኛ ሟቾች ናቸው።
ይህ አይነቱ ህክምናም በተለያዩ እምነቶች ያለ ሲሆን ህክምናቸውም ሲህርን በሲህር በጅን እያደረጉ አስማት ነው በማለት ሰዎችን ይሸነግላሉ ።
አስማትን በአስማት ማከም መታከም ለድንገተኛ ሞት ይጋልጣል።ለምን የሚያዟቸዉ ትልቅ ጅንን ነዉ ሰዉየዉ የያዘዉ ከሚታዘዘዉ ጅን በላይ አቅም ካለዉ ከባድ ነዉ ሰዉየዉን በሂደት እስከመግደል ይደርሳል፡፡
ለምሳሌ እስኪ እሰቡት እስኪ በወንዶች በፊት ስናድግ በሰፈራችን የሰፈር አለቃ አለ እንበል....እሱ የፈለገ ቦታ ይልከናል እምቢ ብንል ይመታናል ያለን አማራጭ መታዘዝ ነዉ፡፡ ወይም መንግስት ግዴታ ይሄን አድርግ ካለን ምን አማራጭ አለን??? ምንም ግዴታ ከማረግ ዉጭ..,,እናም ትልቅ ተፅእኖ ፈጣሪ ተፈሪ የሆኑ ጅንኖች ትናንሽ ደካማን ፈሪን ከሰዉየዉ ገላ የማስወጣት አቅም አላቸዉ
በጠንቋዮች (በደብተራዎች) በቄሶች የሚፈታ ድግምት ለጊዜዉ የተፋታ ይምሰል እንጂ ሙሉ በሙሉ አይድንም፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ዳግም ያንሰራራል፡፡ ምክንያቱም ሰይጣናት በጎሳ የተከፋፈሉ ናቸዉ፡፡
☑️ ድግምቱን የሰራዉን ደብተራ የሚያገለግሉት ሰያጣናት ድግምቱን የሚፈታዉን ደብተራ ከሚያገለግሉት ሰይጣናት በጎሳ የተለዩ ስለሚሆኑ የአንዱ ጎሳ ሰይጣን የሰራዉን መተት የሌላ ጎሳ ሰይጣን መፍታት ወይም በመተት የተወከለዉን ጂኒ ማስወጣት አይችልም፡፡ ምክንያቱም ይህን ማድረግ በጎሳዎች መካከል ጦርነት ይቀሰቅሳል።
ጂኒዎች እንደኛዉ ናቸዉ እነሱ የሚያዩን እኛ የማናያቸዉ ስለሆን ነዉ እንጂ
#ስለሆነም ብዙ ጊዜ ጠንቋይ የሚያገለግሉ ሰይጣናት የሚያደርጉት ነገር ቢኖር በታማሚዉ ዉስጥ ከገባዉ ስይጣን ጋር መስማማት ነዉ፡፡ ይህም ስምምነት ሰይጣኑ ታማሚዉን ለጥቂት ወራት ወይም ሳምንታት ላያንገላታዉ እና ታማሚዉ ደግሞ ሰይጣኑ የሚፈልገዉን ሊያሟላ ይስማማሉ፡፡
ለምሳሌ፡-ጥቁር ዶሮ እንዲታረድለት ፈልጎ ከሆነ ታማሚዉ ይህንኑ ያቀርባል ወይም ለምስሎች እንዲሰግድ ያታዘዛል፡፡ በዚህም ታማሚዉ ለተወሰነ ጊዜያት ወራትም አመታትም ሊሆን ይችላል ጠንቋዩ ጋር ጅኑ እንደስምምነታቸዉ ነዉ ተሸሎት ይከርምና ያ የተስማሙበት የጊዜ ገደብ ሲያበቃ ህመሙ ዳግም ይቀሰቀሳል፡፡ ከዚያም ሌላ ስምምነት ማካሄድ አለባቸዉ መቼም አይለቅም ... ሙሉ ፈዉስ ማግኘት የሚቻለዉ በዓለማት ፈጣሪ በአላህ ቃል በቁርአን ብቻ ነዉ፡፡
🌀 በፀበል ደግሞ ላላችሁት በሚዲያ ላይ ማዉጣት ይከብዳል የሆነ የሚሰማ የማቀዉ ስላለ ነዉ፡፡ወሎ ሲባል ቅልቅል ነን እኔም ብዙ ቤተሰቦቼ ክርስቲያን ናቸዉ👇👇
✍ አንድ የጓደኛየ እህት ታሪክ ላጫዉታችሁ...
ያዉ መቼም አሁን እወድሻለሁ እወድሀለሁ የሚለዉ ቃላት ህፃን ልጅ እናቴ ቁርስ ምሳ እራት እራበኝ የሚበላ ስጭኝ በቀን ብዙ ጊዜ ከምላሱ የማይጠፋ ነዉ አሁንም እወድሀለሁ አፍቅርሀለሁ ቋንቋ እንደዚህ ህፃን ልጅ ምግብ ፍላጎት ጋር የተመሳሰለ ነዉ....
እናም ይዋደዱሉ ግን የሚገርመዉ ሲገናኙ እሱ ሲርየስ ይሆናል ግን ማታ እቤቱ ሲሄድ ምነዉ አዉርቻት በነበር እያለ ያለቅሳል በዚህ አይነት ሲጣሉ ሲታረቁ 8ወር ያህል አሳልፈዉ ፌንት መዉደቅ መጨናነቅ የፀባይ መከረባበት ሲገጥም ወንድሟ በዲኑ የተሻለ ስለሆነ ሌላ ጓደኛዉም በዲኑ ጎበዝ ስለሆነ እሱም ጓደኛዉ ሲቀራ ቢያንስ ሁለት ወር ፈጀ...
የሚገርማችሁ ቁርአን እየቀራባት እንቅልፍ ሸለብ ሲያደርገዉ ቁርአን ሲቀራ ጂኑ ከፊት ስለሚሆን ስልክ አንስቶ ለምወደዉ ልጅ ይደዉልና ናፈከኝ እወድሀለሁ እንቅልፍ እምቢ ብሎኝ ናፈቅከኝ ምናምን እያለ ያወረዋል የሚገርም የሚገርም የፍቅር ወሬ ከዛ ከእንቅልፉ ሲባንን መልሼ እደዉልልሀለሁ ቤተሰብ መጣ ወይ ወንድሜ መጣ ብሎ ስልኩን ይዘጋዉና....ጂኑ ይስቃል ለምትወደዉ ለሚወዳት ፍቅረኛዋ ደዉየ ተጫወትኩበትን እንደምወደዉ ነግሬዋለሁ ዛሬ ሲደሰት ያድራል ነገ ደግሞ አጣላቸዋለሁ ይላል...ከዛ ትምህርት ስትሄድ እንዳለዉም እዛ ይጣላሉ በቃ እሷን የሚያሽከረክራት ጂኑ ነበር...
የሚገርማችሁ ልጁ ስልክ ጋር በmessage በtelegram የሚያወራዉ ጂኑ ነበር እሱ ማታ በtg በmessage እንደዚህ ብለሽኝ አረ አላልኩህም ትለዋለች
ከእሷ የለም ይጠፋል mesage እሱ ጋር ይኖራል በቃ ግራ የሚያጋባ ሁለት የሚዋደዱ ተብየ ግራ የሚያጋባ ፀብ የበዛበት ፍቅር ሆኖ ነበር፡፡
ወንድሟ ቁርአን ቀን ማታ ያለመሰልቸት ሲቀራ ሩቃ ሲያደርግ በስንት ጥረት ጂኒዉ ብዙ ነገሮችን ተናገረ በፍቅር ስም እሱንም እሷንም ሲቆጣጠራቸዉ ሲያስለቅሳቸዉ ከአንተ መኖር አልችልም ካለ አንቺ መኖር አልችልም ሲል የነበረዉ በmesaage አልፎ አልፎ ሲያወራ የነበረዉ ይሄዉ እሷን ተቆጣጥሯት የነበረዉ በሲህር የተላከ ጂን ነበር🙄🙄
ከዛ ከእሷ ላይ ጅኑ ሲለቅ የሚገርመዉ ነገር እሷም እሱም እንደበፊቱ መሆን አልቻሉም... አለ አይደል ያ ፍቅር ሲባል የነበረዉ ነገር ህልም ሁኖ ቀረ .....
ጅኑ(ሲህሩ) ከለቀቀ ከተወሰኑ ቀን ቡሀላ የወንድሟ ጓደኛ ወንድሟን እሷን እንዲድረዉ ይጠይቀዋል ...ወንድሟም ያለዉን ነግር የበፊት ታሪኳን በፊት የነበረዉን በሩቃ እንደተሻላት ይነግረዋል....ከዛ ትዳር የጠየቀዉ ይስማማል....
የሚገርመዉ ነገር እሷም ስትጠየቅ የምወደዉ አለኝ አላለችም መርሀባ በትዳሩ እስማማለሁ አለች...
በፊት የሚወዳትም ከመታጨቱ በፊት ሰምቶ ማሻ አላህ ደስ ይላል ታግቧ ኸይር ነዉ ነበር ያለዉ...እናም ሁለቱም አንድ ላይ ሆኑም አልሆኑም ጂኑ(ሲህሩ) ከለቀቀ ቡሀላ በቃ ሁለቱም ኖርማል ሁነዋል፡፡በጣም ነዉ የገረመኝ..
ከዛም ልጂቱ አገባች ግን በኢማኗ ትንሽ ደከም ያለች ስለሆነች በተወሰኑ ወራት ልዩነት ሲህሩን ያሳድሱባታል መልሳ የተወሰነ ትሰቃያለች ግን ባልየዉ መጀመሪያ ስለሰማ ታጋሽ አስተዋይ ነዉ በሩቃ እሱዉ እየቀራ ይዟታል፡፡የሚገርማችሁ ባሏ ጋር እንድትፋታ ሳሂሩ ያላደረገዉ ጥረት የለም ግን ባልየዉ ታገሽ መሆኑ ትዳሩን እድሜ እንዲረዝሞ አደረገዉ....አሁን ከሁለት ወር በፊት ጂኑ መፍትሄ ሲያጣ አዉቆ የበፊት ፍቅረኛዋን ስም እየጠራ ናፈቀኝ ይላል...አዉቆ ጂኑ ዉሸቱን አንተን ከማግባቴ በፊት እሱ ጋር ይሄን ይሄን አሳልፊያለሁ ላይፍ ቀጭቻለሁ አንተን ያገባሁት እሱ ጋር ላይፌን ቀጭቼ ነዉ እያለ ሲህሩ ሲታደስባት የተላከዉ ጅን በእሷ አስመስሎ ያወራል ...በጣም ከባድ ነዉ ግን ባልየዉ የዲን እዉቀት ስላለዉ በሰከነ መልኩ በሩቃ ይታገል ይዟል....
አስባችሁታል ወንዶች?? ያገባሀት ምስት ጂን ይዟት ወይም ሲህር ተደርግባት ከትዳር በፊት ያለፈ ተብሎ እዉነቱንም ዉሸቱንም ቢነግርህ ለባልየዉ አቅል አይከብድም??? አሁን ደህና ሁናለች ግን ሲህር ያደረገባት ሲያሳድሰዉ በጣም እሷም ባልየዉም ይፈተናሉ፡፡
ምን ለማለት ፈልጌ መሰላችሁ ይሄ ታሪክ የጓደኛየ እህት ታሪክ ነዉ፡፡ ግን እስኪ ሲህር ወይ አይነጥላ ቡዳ ወይ ጂን ይዟችሁ ሩቃ ተደርጎ በአላህ እገዛ ስትሽሩ ከዛ በፊት ፍቅር ተብየ ከነበረባችሁ ፍቅሩ ከሩቃ ቡሀላ ለቋችሆል ወይስ አለቀቃችሁም?? እስኪ ለጠቅላላ እዉቀት ነዉ ገጠመኝ ካለ አሳዉቁኝ...በተጨማሪ እዚህ ቻናል የስነ ልቦና ባለሙያ ካላችሁ እስኪ ሀሳብ ስጡበት ከምር ግራ ነዉ የገባኝ...
4any cmt 🔽
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
🔰🔰 ግን ማወቅ ያለብን አፍቃሪ ጅኖች የሚባል አለን!!
አሺቅ ጅን ማለት በቀጥታ ፍቺው አፍቃሪ ጅን ማለት ነው፡፡
ጅኖች ከሴትም ይሁን ከወንድ ጋር ፍቅር ይይዛቸዋል፡፡ ይህንም እጅግ በጣም በሚዘገንን ሁኔታ ፍቅራቸውን ገላጮች ናቸው እስኪ ምልክታቸውን እንይ!!
ምልክቶቻቸው!!
➊ ህልማችን በሙሉ ወሲባዊ ይሆናል!! በህልም ስትዳሪ አንሶላ ስትጋፈፊ በህልምህ ዚናን ስትሰራ እላይህ ላይ ዘርህን ስታፈስ የምትነቃ ከሆነ ይህ የመጀመርያው ምልክታቸው ነው፡፡
➋ ከእንቅልፋችን ስንነቃ ሰውነታችን ላይ የመበለዝ ምልክቶችን እናያለን፡፡ ልክ ሌላ ሰው እንደደበደበን አይነት ምልክት!! ይህ እጅ ላይ እግር ላይ ይሆናል ምልክቱ!! የሚገርመው ግን ከግማሽ በላይ ታካሚዎቻችን ላይ የሂና ከለር የመሰለ ጥቁር ምልክቶች ይታይባቸዋል
➌ ለሊቱን ተደባድቦ እንዳደረ ሰው ወይም ተደብድቦ እንዳደረ ሰው ሰውነታችን ስብርብር ብሎ ማደር፡፡ ይህ ለየት የሚያደርገው የጅን ምልክት ነው!!
➍ ሰውነትህ ወይም ሰውነትሽ ምንም ብታደርጉበት ይሸታል፡፡ ይህን ሽታ በምንም ነገር ልትቆጣጠረው አትችልም ወይም አትችይም፡፡ ሽታውን ለማጥፋት ታጥበን ተኩል ደቂቃ በሞላ ግዜ ውስጥ የሚያስጠላ ሽታ ይኖረናል፡፡ አሏህም ይጠብቀን!! ይህ በሽቶ በዶድራንት ሊደበቅ አይቻለውም፡፡
➎ ይህ ጥቃት በሴቶችም በወንዶችም ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡ በዚህ ጥቃት ላይ ያሉ ሰዎች ከምንግዜውም በላይ ሊወፍሩ ይችላሉ አልያም ሊከሱ ይችላሉ!! ይህም ሌላው ተመልካች በነርሱ ላይ ፍላጎት እንዳይኖረው የማድረግያ ጥበቡ ነው!! አሏህም ከጅን ተንኮሎች ይጠብቃችሁ!!
➏ በተጠቂው ጆሮ ላይ መጥፎ ነገሮችን በሙሉ በማምጣት መካሪ ነው፡፡ ለምሳሌ
☞ ሴት ከሆነች ‹‹ገና ነሽ ቆንጆ ነሽ ሰው ይፈልግሻል እንዳትሞኚ›› ሲል ይሸነግላል
☞ ኋላ ላይ አስወፍሮ ጉድ ሊሰራ ወይ ደግሚ ‹‹በቃ የሚፈልግሽ የለም ትዳር የለም ላንቺ የሚመጣ ወንድ የለም፡፡
☞ ላንቺ መስዋአትነት የሚከፍል የለም ተፈላጊ አይደለሽም ›› ሲል በጆሮ በመምጣት ይመክራል!!
➐ ሰላትና ኢባዳ ላይ ደካማ ያደርገናል፡፡ በሙሉ ለሙሉ ተስፋ ቆራጮች ብንሆንም በዚህ ግዜ የቀረችን የነበረችውን ሰላታችንን ያጠፋብናል፡፡ በዚያም ላይ እርካታ እንዳይኖረን ይገፋፋናል፡፡ ይህም ብዙውን ግዜ ከሱብሂ ይጀምራል በማዘናጋት አስር ላይ ይጠነክራል ኢሻእ ላይ ይጥላል ወደ እንቅልፍ፡፡ ይህ በጅኑ ሙሉ ለሙሉ ቁጥጥር ላይ ስትሆኑ ነውና፡፡
🔰🔰በሚቀጥለዉ ክፍል
አንዲት እናት 7 ልጅ ያላት ባሏ ሹፌር ነበር ስላላመናት ስላደረገባት ሲህር እዉነተኛ ታሪክ ይዤ እቀርባለሁ
#ክፍል 1⃣3⃣
ይቀጥላል....
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
👇👇
30 አመት ወደ ኋላ የዘመን ቀመሩ ሲፈተል በ1992
በተሞሸረች በ3 ቀኗ የሠርጉ ድባብ በቅጡ ሳይቀዘቅዝ ፍቺው ፀድቆ ወደወላጆቿ ቤት ተመለሰች። ያለምንም ምክንያት ተፋተው ወደ እናቷ ቤት ተሸኘች። ያ አምስት ዓመታትን ያስቆጠረው ውብ የፍቅራቸው ጊዜ በድንገት አከተመ። ሚስት የስቃይ ህይወትን መግፋት ጀመረች። እሱም ከሷ በኋላ ሳያገባ ድፍን ሰላሳ ዓመታት አለፈ። ሲህር ነበር ያለያያቸው የሠርግ ቬሎዋን ጠቅልለው ከሞተ ሰው አስክሬን አፍ ላይ ፎቷቸውን አስረው ቆፍረው ከመቃብር ስፍራው ቀበረው በስቃያቸው ተደሰቱ።
ሲህሩ ተገኝቶ ከተቀበረበት እንደወጣ ሚስቱ ድና ወደመልካም የጤንነት ሁኔታዋ ተመለሰች። ባል ወደ ቤተሰቦቿ አቀና። ሚስቱን በድጋሜ ተንበርክኮ ጠየቀ። አዲስ ፍቅር ቤታቸው ገባ። ጤንነት ከደጃፋቸው ደረሰ። ፍቅራቸውም አገረሸ። በ2022 ዳግም በእልልታ ተሞሸሩ።
የአክስቷ ልጅ ነበረች ሲህሩን ያሰራችባት። ቬሎዋን ቀዳ ለደጋሚው የሰጠች። ሳሂሩ ጥቁር ዶሮ አሽከርክሮ አንገቱን በጠሰና ደሙን ከፎቷቸው ጋር ለውሶ ከጀናዛ አፍ ጋር አስሮ ህይወታቸውን በስቃይ እንዲገፉ አደረጋቸው። አላህ ከሰባት ሰማያት በላይ ሆኖ አዘነላቸው ከድፍን ሰላሳ አመታት በኋላ ከአፊያው ዳብሶ ዳግም አገናኛቸው።
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
✍ አሚር ሰይድ
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
⭐️ #ክፍል👉 #አስራ_አንድ1⃣
🟢 #በምቀኝነትና_በቡዳ_መካከል_ያለ_ልዩነት
➊ ምቀኛ ሲባል ቡዳን ይጨምራል።
>> ቡዳ ማለት ልዩ የሆነ ምቀኛ ማለት ነዉ፡፡
>> ቡዳ ሁሉ ምቀኛ ነዉ፡፡
>> ምቀኛ ሁሉ ግን ቡዳ አይደለም፡፡ ከምቀኛ አላህ እንዲጠብቀን ዱዓ ማድረግ እንዳለብን ከአል ፈለቅ ምዕራፍ እንማራለን፡፡
☑️ አንድ ሙስሊም አላህ ከምቀኛ እንዲጠብቀዉ ዱዓ (ጾለት) ሲያደርግ ከቡዳም ጭምር እንዲጠብቀዉ ዱዓ አድርጓል ማለት ነዉ። ምክንያቱም ምቀኛ የሚለዉ ቃል ቡዳንም ምቀኛንም ሁለቱን ያጣመረ አገላለፅ በመሆኑ፡፡ ይህ እንግዲህ የቁርአን ታዓምራዊነት መገለጫ ነዉ።
➋ ምቀኝነት ከመመቅኘት፣ ከጥላቻ ወይም ሰዉ እንዲያጣ ከመፈለግ የሚመነጭ ሲሆን በተቃራነዉ ደግሞ የቡዳ መንስኤ ማድነቅና መገረም ነዉ፡፡
➌ ምቀኝነትና ቡዳ በሰዉ ላይ ጉዳት በማድረስ በዉጤት ሲመሳሰሉ በመንስኤዎቻቸዉ ደግሞ ይለያያሉ፡፡
>> የምቀኝነት መንስኤ የሰዉን ፀጋ መመቅኘት፣ በሰዉ ነገር መንገብገብ እና መቃጠል፣ እንዲያጣ መፈለግ ሲሆን በተቃራኒዉ
>> የቡዳ መንስኤ ማየት እና መመልከት ነዉ። በዚህም ምክንያት ቡዳ ያልተመቀኘዉን ሰብል፣ ግዑዝ እቃ ወይም ንብረት ሊበላ ይቻላል፡፡ እንዲያዉም ቡዳ እራሱን በራሱ ሊበላ ይችላል፡፡ ቡዳ አንድን ነገር በአድናቆትና በአግርሞት በመመልከቱ ምክንያት ነፍሱ ወደ ዚህ ሁኔታ ትለውጥና በምታየዉ ነገር ላይ ጉዳት ታደርሳለች፡፡
➍ ምቀኛ ያልተከስተንና ገና ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅን ነገር ሊመቀኝ እና ሊጎዳ ይችላል፡፡
>> ቡዳ ግን በተግባር የሌለን ነገር ሊበላ አይችልም፡፡
➎ ሰዉ እራሱን ወይም ንብረቱን አይመቀኝም፡፡ ነገር ግን እራሱን ወይም ንብረቱን በቡዳ ሊበላ ይችላል፡፡
➏ ምቀኝነት ከምቀኛና ተንኮለኛ ብቻ የሚከሰት ሲሆን
>> ቡዳ ግን ከመልካም እና ደጋግ ሰዎች ጭምር ሊከሰት ይችላል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ያስደነቃቸዉ ነገር እንዲጠፋ ባይፈልጉም በመደነቃቸዉ ብቻ ጉዳት ሊደርስ ይችላልና፡፡
➐ አንድ ሰዉ የሚያስደንቀዉ ነገር ሲያይ አላህ በረካ (ረድኤት) እንዲያደርግበት ዱዓ (ፆለት) ማድረግ አለበት፡፡ ያስደነቀዉ ነገር የራሱ ይሁን የሌላ ለዉጥ አያመጣም፡፡ ይህ ዱዓዕ አስደናቂዉን ነገር በቡዳ እንዳይጎዳ ያደርገዋል፡፡
🔴 #ጂኒዎች_ሰዎችን_በቡዳ_ይበላሉ
➊ አቡ ሰዒድ አልኹድሪ እንዲህ ይላሉ>>> ነብዩ ከጂኒ ዓይንና ከሰዉ ዓይን አላህ እንዲጠብቃቸዉ ዱዓዕ ያደርጉ ነበር፡፡ የእል ፈለቅ እና የአል ናስ ምዕራፎች ሲወርዱ በእነዚህ በመጠቀም ሌሎችን (ዱዓዎች) ትተዋል” (ቲርሚዚ ዘግበዉታል፡፡ አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብላዋል)፡፡
📌 የአል ፈለቅ እና የአል ናስ ምዕራፎችን በመቅራት ከጂኒ እና ከሰዉ ቡዳ መከላከል እና መጠበቅ እንደሚቻል ከዚህ ሃዲስ እንማራለን
➋ እናታችን ኡሙ ሰለማ እንዲህ ይላሉ፡ በቤቱ ዉስጥ በፊቷ ላይ ጥቁረት ያለባትን ልጅ ነብዩ ተመለከቱና እንዲህ አሉ የጂኒ ቡዳ ስላለባት ሩቅያ አድርጉላት” (ቡኻሪ ዘግበዉታል)
📌 ቡዳ ከ ከሰዉ ብቻ ሳይሆን ከጂኒዎችም : (ከሰይጣናትም) ሊከስት እንደሚችል ከእነዚህ ሁለት ሀዲሶች እንገነዘባለን፡፡
ስለዚህ ማንኛዉም ሙስሊም
>> ልብሱን ሲያወልቅ፧
>> መስታዎት ሲያይ ማንኛዉንምስራ ሲጀምር ቢስሚላህ (በአላህ ስም) ማለት ይኖርበታል፡፡ ይህም ከጂኒ ቡዳ፣ ከሰዎች ቡዳ እና ከሌሎች ጉዳቶችም ይከላከልለታል፡፡
🟡 #የሰዉ_ዓይን (የቡዳ) #ህክምና
የሰዉ ዓይን (ቡዳን) ለማከም የሚያገለግሉ በርካታ ዘዴዎች አሉ። የተወሰኑትን እንደሚከተለዉ እንመለከታለን፡፡
🔸🔸 #መታጠብ 🔸🔸
በዓይነ ጉዳት ያደረሰዉ ሰዉ _ የሚታወቅ ከሆነ እንዲታጠብ ይደረጋል፡፡ ከዚያም የታጠበበትን ዉሀ በመዉሰድ በታመመዉ ሰዉ ገላ ላይ በጀርባዉ በኩል ማፍሰስ፡፡ በዚህም በአላህ ፈቃድ ይድናል፡፡
የትጥበቱ አፈፃፀም
ኢብን ሺሀብ አል ዙህሪ እንዲህ አሉ "ኡለማዎች ትጥበቱን በሚከተለዉ መልኩ ሲገልጹት አስተዉያለሁ፡፡ ይኸዉም በዓይኑ ጉዳት ላደረሰዉ ሰዉ በሳፋ ዉሃ ይቀርብለታል፤ ይህም ስዉ ከዉሃዉ በመዝገን ተጉመጥምጦ መልሶ ሳፋዉ ዉስጥ ይተፋዋል፡፡ ከዚያም ፊቱን ሳፋዉ ዉስጥ ያጥባል፡፡ ከዚያም ቀኝ እጁን በግራ እጁ ያጥባል። ከዚያም ግራ እጅን በቀኝ እጁ ያጥባል፡፡ ከዚያም የቀኝ እጁን ክርን በግራ እጁ የግራ እጁን ከርን በቀኝ እጁ ያጥባል፡፡ ከዚያም የቀኝ እግሩን በቀኝ እጁ የግራ እግሩን በግራ እጁ ያጥባል፡፡ ከዚያም የቀኝ ጉልበቱን በግራ እጁ የግራ ጉልበቱን በቀኝ እጁ ያጥባል፡፡ ከዚያም በሽርጡ የተሸፈነዉን የአካሉን ክፍል ሳፋዉ ዉስጥ ያጥባል፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ሳፋዉ መሬት ላይ መቀመጥ የለበትም፡፡ ከዚያም ዉሃዉን በታመመዉ ሰዉ ላይ በጀርባዉ በኩል ባንድ ግዜ ማፍሰስ፡፡"
ከዚህ በተረፈ በተማሚዉ ራስ እጅን አኑሮ የተለያዩ የሩቃ ምዕራፎችንና ቁርአንን መቅራት ነዉ፡፡
🔵🔵 🟠🟠🟠 #ከድግሞት_ከሲህር_ከአይንናስ_ከስንፈተ_ወሲብ_መከላከያ_መንገዶች
✏️✏️ #ዉዱዕ_አድርጎ_መንቀሳቀስ
በዉዱዕ የሚንቀሳቀስ ሙስሊምን ድግምት ሊነካዉ አይችልም፡፡ ምክንያቱም በዉዱዕ የሚንቀሳቀስ ሙስሊም ከአላህ በተላኩ መላእክት ስለሚጠበቅ ነዉ፡፡ ይህን በማስመልከት ነብዩ እንዲህ ይላሉ “የአካላችሁን ንጽህና ጠብቁ! አላህ ንፁሀ ያድርጋችሁ፡፡ ማንኛዉም ሰዉ ዉዱዕ አድርጎ ሲያድር መላኢካ ከጎኑ ያድራል፡፡ ይህ ስዉ በመኝታዉ ዉስጥ ሲንቀሳቀስ መላኢካዉ እንዲህ እያለ ጸሎት ያደርግለታል “አላህ ሆይ! ይህን አገልጋይህን ይቅር በለው ዉዱዕ አድርጎ ነዉ ያደረዉና።" (ሳራኒ ዘግበዉታል ኢስናዱ ጀይድ ነዉ ብለዋል)
✏️✏️ ሶላት አል ጀማዓህ (የህብረት ስግደትን) መከታተል
የህብረት ስግደትን መከታተል ለሙስሊም ከሰይጣናት ተንኮል ሰላምን ታመጣለታለች፡፡ አንድ ሰዉ ሶላትን በጀምዓ ከመስገድ ከተዘናጋ የሰይጣናት መፈንጫ ይሆናል፡፡ በልክፍት፣ በድግምት፣ በቡዳ እና በመሳሰሉት ሰይጣናት ይዘባበቱበታል፡፡ በዚህ ዙሪያ ነብዩ እንዲህ ይላሉ፡- ሶስት ሰዎች የጀምዓ ስገደት በማይሰገድባት ከተማ ወይም የገጠር መንደር ዉስጥ ከኖሩ ሰይጣን ይሰለጥንባቸዋል፡፡ ህብረትን (ጀማዓን) አደራ!! ተኩላ የሚያድነዉ እኮ ከመንጋ ያፈነገጠን በግ ነው” (አቡ ዳዉድ በኢስናዲን ሀሰን ዘግበዉታል)
✏️✏️ የሌሊት ሶላት (ስግደት)
እራሱን ከድግምት ለመከላከል የፈለገ የሌሊት ሶላት ይሰገድ፡ ከዚህም ሊዘናጋ አይገባም፤ የሌሊት ሰላትን አለመስገድ ሰይጣን በሰዎች ላይ እንዲሰለጥን በር ይከፍትለታል፤ ሰይጣን ከሰለጠነብህ ደግሞ ለድግምት ምቹ ሆንክ ማለት ነዉ ፡፡ ይህን በተመለከተ አንድ ቀን ነብዩ ዘንድ የሌሊት ሰላት ሳይሰግድ ስላደረ ሰዉ ጥያቄ ተነስቶ ነብዩ እንዲህ አሉ፡
“ይህ ሰዉ በጆሮዎቹ ሰይጣን ሸንተታል" (ኻሪ ዘግበታል)
ኢብን ዑመር እንዲህ ይላሉ - “ማንም ሰዉ የዊትር ሰላት ሳይሰገድ ካደረ ሰባ ክንድ ሰንሰስት ባንገቱ ላይ ታስሮበት ያህል " (አል ሃፈዝ.ፈትሁል ባሪ ዉስጥ ኢስናዱ ጀይድ ነዉ ብለዋል)👇👇👇
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
✍ አሚር ሰይድ
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
⭐️ #ክፍል👉 አስር 🔟
🔰🔰 #የሰዉ_ዓይን (ቡዳ) 🔰🔰
⚡️⚡️#የሰዉ_ዓይን (ቡዳ) ምልክቶችን አስመልክቶ ሸይኽ አብዱ አል ረዛቅ እንዲህ ይላሉ፡- በቡዳ የተበላዉ የሰዉዬዉ ነፍስ ከሆነ በዚህ ሰዉ ላይ ሳኮሎጂያዊ የህመም ምልክቶች ይታዩበታል፡ ለምሳሌ፡-
☞ ወደ ትምህርት ቤት፣ ኮሌጅ ወይም ወደ ስራ ለመሄድ ይደብረዋል፡፡
☞ትምህርት ለመማር እና ለማጥናት ይከብደዋል ይጫጫነዋል፡፡
☞ነገሮችን ለመረዳትና ለማስታወስ የነበረዉ ችሎታ በእጅጉ ይቀንሳል፡፡
☞ ብችኝነትን ምርጫዉ ያደርጋል ከቤተሰቦቹ ይርቃል። የቅርብ ቤተሰቦቹ እንኳን የማይወዱትና የማያስቡለት ይመስለዋል፡፡
☞ሰዎችን ተተናኮል ተተናኮል የሚል ስሜት ያድርበታል፡፡
☞ መቃወም እና መቃረን ባህሪዉ ይሆናል፡
☞ ንፅህናዉን አይጠበቅም፡፡
☞ ከቤተሰቦቹ፤ ከወዳጆቹ እንዲሁም ከጓደኞቹ ጋር መግባባት አይሆንለትም፡፡ በጭንቀት ይወረራል፡፡
☞ በፀባዩ በአመለካከቱ እና በንግገሩ ግራ የሚያጋባና የማይገመት ይሆናል፡፡
☞ መክሳት
☞ በቤተሰብ የሌለ የፊት ቡጉር የራስ ቁስለት
☞ የቆዳ መላላጥ
☞ የፊትና ሰውነት መቁሰል
☞ የትዳር አለመሳካት ። ወንድ ከሆነ ማግባት መፍራት ሴት ከሆነች ትዳር መራቅ ወይም ትዳር ይርቃቸዋል።
☞ ሰው ፊት ማውራትና መናገር መፍራት። ነገሮችን እንደ ከዚህ ቀደም በድፍረት ማድረግ አለመቻል።
☞ በተዋወቁት ሰው ሁሉ መጠላት። ጥሩ ስራ ሰርቶ ምስጋና ቢስ መሆን።
☞ የብብት የ ፊንጢጣ መቁሰል መላላጥ።
☞ ሰውን አለማመን መጠራጠር።
☞ ቁጡና ያለ ምክንያት ተናዳጅ መሆን።
☞ የልብ ምት ድንገት መጨመር።
☞ የሰውነት መጋል።
☞ ቶሎ ተሎሎ ማዛጋት፡፡ ይህም በሰላት ላይ አልያም ቁርአን በሚቀሩበት ወቅት ይፈጠራል፡፡
☞ ከሰዎች መገለልና ሰዎችን ያለምንም ምክንያት መጥላት፡፡
☞ ድንገተኛ የሆኑ በብዙ አይነት በሽታዎች መያዝ መጠቃት፡፡
☞ መስነፍና ቶሎ ቶሎ ተስፋ መቁረጥ፡፡
☞ የሰውነት ልክ አንቀጥቅጥ እንዳለበት ሰው መንቀጥቀጥ መራድ፡፡
☞ ያለ ምንም ምክንያት ማልቀስ ማዘን፡፡
☞ የሰውነት መገርጣት፡፡ ማድያት ማውጣት ፊት መቁሰል ብጉሮች መብዛት ፡፡
☞ የምግብ ፍላጎት ማጣት፡፡ ምግብ ሲበሉ መታመም፡፡ መቃጠል ማስታወክ፡፡
☞ እሞታለው ብሎ ከመጠን በላይ ፍራቻ በተለይም ከመግሪብ ኋላ ፡፡
☞ የማይለቅ ራስ ምታት በአንድ ጎን ብቻ ከፍሎ መታመም(ማይግሬን)
☞ እራስን ማጥፋት መመኘት
☞ ቁርአን በሚሰሙበት ግዜ ማላብ ማስታወክ እና አይን እያዛጉ ማልቀስ፡፡
☞ የከንፈር መንከስ። ደም ቢደማም አለማቆም።
ወዘተ
እነዚህ ምልክቶች አንድ ሰዉ ላይ በሙሉ ባይታዩም የተወሰነት ከታዩበት የሰዉ ዓይን (በቡዳ) ለመለከፉ አመላካች ስለሚሆኑ የቁርዓን ህክምና እንዲከታተል ያስፈልጋል፡፡
🟢 #በቡዳ_የተበላዉ_የሰዉዬዉ ንብረት (ንግዱ፣ ስራዉ …..) ከሆነ ደግሞ
✏️ በገንዘብ ዙሪያ ከሰዎች ጋር ለመስራት ይጨንቀዋል፡፡
✏️የንግድ እቃዎችን ለማቅረብ እና ለማዘጋጀት ሲያስብና ሲንቀሳቀስ ይጫጫነዋል፡፡
✏️ የንግድ እቃዎቹ ለብልሽት የተጋለጡ ይሆናሉ፡፡
✏️ ገዢ ወደ እርሱ ለመደራደር ሲቀርብ የሆነ ነገር ገፍቶ ይመልሰዋል።
🟢 በቡዳ የተበላዉ የሰዉዬዉ አካል ከሆነ ደግሞ
✏️ሰዉነቱ ሙትት ድክምክም ይላል፡፡
✏️ ሰዉነቱ ይዝላል፡፡
✏️ ሲተነፍስ የማለክለክ እና ቶሎ ቶሎ አየር የማስገባት እና የማስወጣት ስሜት ይስተዋልበታል፡፡
✏️ጭንቅ ጭንቅ ይላወል፡፡ አንዳንድ ህመሞችም ይከሰቱበታል፡፡
📚📚 አንዳንድ ሰዎች በሰዉ አይን ቡዳ የለም ብለዉ የሚያምኑ አሉ ስለ ሰዉ ዓይን ማስረጃዎች ከቁርአን
#ልጆቼ_ሆይ በአንድ በር አትግቡ ግን በተለያዩ በሮች ግቡ፣ ከአላህም (ዉሳኔ) በምንም አልጠቅማችሁም (አልመልስላችሁም፡፡) ፍርዱ የአላህ እንጂ የኔ አይደለም፡፡ በእርሱ ላይ ተመካሁ ተመከዎችም ሁሉ በእርሱ ብቻ ይመኩ
አባታቸዉ ካዘዛቸዉ ስፍራ በገቡ ግዜ ከአላህ (ዉሳኔ) ምንም ነገር ከእነርሱ የሚከላከልላቸዉ አልነበረም፡፡ ግን በያዕቆብ ነፍስ ዉስጥ የነበረች ጉዳይ ናት ፈፀማት፡፡ እርሱም ስላሳወቅነዉ የእዉቀት ባለቤት ነዉ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያዉቁም፡ (ዩሱፍ ፡ 67-68)
🔰🔰 ኢብን ከሲር እነዚህን ሁለት የቁርእን እንቀጾች ሲተነትኑ እንዲህ ይላሉ ..አላህ ስለ ያዕቆብ የሚከተለዉን አስተምሮናል ፡- ያዕቆብ ልጆቻቸዉን ከቢንያሚን ጋር ወደ ግብጽ ሲልካቸው ሁላቸዉም በአንድ በር በኩል እንዳይገቡ ይልቁንም በተለያዩ በሮች እንዲገቡ አዘዛቸዉ ይህን ያደረገበት ምክንያት ልጆቻቸዉ በጣም ቆንጆዎችና መልከ መልካም ስለነበሩ የሰዉ ዓይን እንዳያገኛቸዉ በመስጋት ነበር፡፡ የሰዉ ዓይን ደግሞ እዉነት ነዉ። ፈረሰኛን ከፈረሱ ላይ አሽቀንጥራ ትጥላለች፡፡
ከአላህም (ዉሳኔ) በምንም አልጠቅማችሁም አልመልስላችሁም ማለት፡- እንዲህ ዓይነት ጥንቃቄ ማድረግ ከአላህ ዉሳኔ ሊያድን እንደማይችል ያስረዳል፤፤
አላህ ከወሰነ ማንም የእርሱን ዉሳኔ ሊሽር አይቻለዉምና፡፡ አባታቸዉ ካዘዛቸዉ ስፍራ በገቡ ጊዜ ከአላህ ዉሳኔ ምንም ነገር ከእነርሱ የሚከላከልላቸዉ አልነበረም፡፡ ግን በያዕቆብ ነፍስ ዉስጥ የነበረች ጉዳይ ናት ፈፀማት፡፡ ከለዉ ዓይን መጠበቅ ማለት ነዉ ብለዋል፡፡
✅ እነሆ እነዚያ የካዱት ሰዎች ቁርአንን በሰሙ ግዜ በዓይናታቸዉ ሊጥሉህ (ሊያጠፉህ) ይቃረባሉ፤ እርሱም በእርግጥ አብድ ነዉ ይላሉ” (አል ቀለም፡ 5)
🌐🌐 ኢብን ዓባስ፡ ሙጃሂድ እንዲሁም ሌሎች ሊቃዉንት ይህን የቁርአን አንቀፅ በማስመልከት እንዲህ ብለዋል፡- በዓይኖቻቸዉ ሊጥሉህ (ሊያጠፉህ) ይቃረባሉ” ማለት፡- አንተን ከመጥላታቸዉ የተነሳ ይመቀኙሃል የአላህ ጥበቃ ባይኖር ኖሮ (በጎዱህ ነበር)፡፡ ከነዚህ የቁርአን አንቀጾች የሰዉ ዓይን እዉነት መሆኑን እንገነዘባለን፡
🔰 #ስለ_ሰዉ_ዓይን_ማስረጃዎች_ከሃዲስ 🔰
➊ አቡ ሁረይራህ የሚከተለዉን ሃዲስ አስተላልፈዋል፡፡ ነብዩ እንዲህ እሉ የሰዉ ዓይን (ቡዳ) እዉነት ነዉ” (ቡኻሪ እና ሙስሊም)
➋ ዓዒሻ የሚከተለዉን ሃዲስ እስተላልፈዋል፡፡ ነብዩ እንዲህ ይላሉ ...ከሰዉ .አይን በአላህ ተጠበቁ አላህ እንዲጠብቃችሁ ፀልዩ ምክንያቱም የሰዉ አይን እዉነት ነዉ።” (ኢብን ማጀህ ዘግበዉታል። አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብለዋል)
➌ ኢብን ዓባስ የሚከተለዉን ሃዲስ አስተላልፈዋል፡፡ ነብዩ እንዲህ ይላሉ
.... የሰዉ ዓይን እዉነት ነዉ። ቀደርን እጣ ፈንታን የሚሽቀዳደም ቢኖር የሰዉ ዓይን ትቀድመዉ ነበር። እጣቢያችሁን ስትጠየቁ ታጠቡ፡፡ (ሙስሊም ዘግበዉታል) አንድ ሰዉ ወንድሙን በዓይኑ አግኝቶት እጣቢዉን ሲጠየቅ ታጥቦ ይስጥ ማለት ነዉ።
➍ አስማእ ቢንት ዑመይስ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!!! የጃዕፈርን ልጆች የሰዉ ዓይን ታገኛቸዋለች። ህክምና ባደርግላቸዉስ? ስትል ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ጠየቀች፡፡ ነብዩም እንዲህ በማለት መለሱላት አዎን .....ህክምና አድርጊላቸዉ፡፡ ቀደርን እጣ ፈንታን የሚሽቀዳደም ቢኖር ኖሮ የሰዉ ዓይን ትቀድመዉ ነበር (አህመድ ዘግበዉታል። አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብለዋል)👇👇👇
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
✍ አሚር ሰይድ
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
⭐️ #ክፍል👉 ዘጠኝ 9⃣
🟢 #ስንፈተ_ወሲብ(መሰናክለ ወሲብ)
መሰናክለ ወሲብ ማለት፡- ጤነኛ ሰዉ ሚስቱን መገናኘት አለመቻል ማለት ነዉ፡፡
መሰናክለ ወሲብ በወንዶች ላይ እንዴት ሊከሰት ይችላል?
በድግምት የተወከለዉ ጂኒ በወንዱ አእምሮ ዉስጥ ይቀመጣል፡፡
በተለይ ወሲባዊ መነሳሳትን በሚቆጣጠሩ እና ወሲባዊ መነሳሳትን በሚመለከት መልዕክት ወደ ወሲባዊ አካላት በሚልከዉ የአእምሮ ክፍል ዉስጥ ይቀመጣል፡፡
ጂኒዉ ይህ የአዕምሮ ክፍል መደበኛ ስራዉን እንዲያከናዉን ይተወዋል፡፡ ነገር ግን ሰዉዬዉ ሚስቱን ለመገናኘት ሲጠጋ ይህን የአእምሮ ክፍል ያሰናክለዋል። የወንዱን ብልት ዝግጁ ለማድረግ ደም እንዲረጭ የሚያደርጉትን የአእምሮ መልእክቶች አንዳይተላለፉ ያደርጋቸዋል፡፡ በዚህ ሳቢያ / ለግንኙነት ዝግጁ የሚያደርገዉ ደም ወደ ወንዱ ብልት አይደርስም፡፡ በወንዱ ብልት ዉስጥ ያለዉም ደም ይመለሳል፡፡ በዚህም ሳቢያ የወንዱ ብልት ጨርቅ ይሆናል፡፡
ለዚህም ነዉ አንድ ባል ከሚስቱ ጋር ቅድመ ወሲብ ልፍያ በሚያደርግበት ጊዜ ብልቱ ዝግጁ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ብልቱን ወደ ብልቷ ሲያስጠጋ ድንገት ይሟሽሽና ግንኙነቱ ሳይሳካ ይቀራል፡፡
♠ እንዲህም ያጋጥማል፡- ባል ሁለት ሚስቶች ይኖሩትና ከአንደኛዋ ጋር ወሲባዊ ተራክቦ ሲፈጽም ደህና ይሆናል፡፡ ከሁለተኛዋ ጋር ግን መሰናክለ ወሲብ ያጋጥመዋል፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ድግምት የተሰራበት ከሁለተኛዋ ሚስቱ ጋር እንዳይገናኝ ለማድረግ ነዉ ማለት ነዉ፡፡
ባል ሁለተኛ ሚስቱን ለመገናኘት ሲቀርባት የድግምቱ እንደራሴ ሰይጣን ጂን ያሰናክለዋል፡፡ ምክንያቱም ሰይጣኑ የታዘዘዉ ከሁለተኛ ሚስቱ ጋር እንደይገናኝ እንዲያሰናክለዉ በመሆኑ የታዘዘዉን ብቻ ይፈፅማል፡፡
🟢 #የሴቶች_መሰናክለ_ወሲብ
በወንዶች ላይ የሚከሰተዉ የመሰናክለ ወሲብ ዓይነቱ ይለያይ እንጂ በሴቶች ላይም ይከሰታል፡፡ በሴቶች ላይ የሚከሰት መሰናከለ በአምስት ይከፈላል፡፡ እነሱም፡-
➊ #መከልከል
ይህ የሚከሰተዉ ሴቷ ጭኖቿን እርስ በርሳቸዉ በማቆላለፍ እንዲይገናኛት ስታደርግ ነዉ። ይህም በሴቷ ፍላጎት የሚከሰት ሳይሆን ክፍላጎቷ ወጪ በዉጫዊ ሀይል የሚከሰት ነዉ። አንድ ወጣት በዚህ ዓይነት ድግምት መለከፏን ሳያዉቅ ሚስቱን ለምን እንዲህ ታደርጊያለሽ እያለ ሲጨቀጭቃት እንዲህ ትመልስለት ነበር እኔኮ ፈልጌ አይደለም የማደርገዉ ጭኖቼ እንዳይቆላለፉ ከፈለክ ግንኙነት ከማድረጋችን በፊት እግሮቼን በሰንሰለት ለያይተህ እሰራቸዉ" አለችዉ፡፡ እንዳለችዉም አደረገ ነገር ግን ምንም መፍትሄ ሊያመጣ አልቻለም፡፡ ሊገናኛት በሚፈልግበት ወቅት ማደንዘዣ መርፌ እንዲወጋት ጠቁማዉ አደረገዉ፡፡ መፍትሄ ቢገኝም አንደኛዉን ወገን ብቻ ነበር የጠቀመዉ፡፡ ከዚያም የቁርዓን ህክምና በመከታተል ተፈወሰች፡፡
➋ #ወሲባዊ_ስሜት_ማጣት
በድግምት የተወከለዉ ጂኒ የሴቷን የወሲብ ስሜት በሚቆጣጠረዉ የአእምሮ ክፍል ዉስጥ ይቀመጣል፡፤ ባለቤቷ ሊገናኛት ሲቀርብ የወሲብ ስሜት እንድታጣ ያደርጋታል። በዚህም ሳቢያ ወሲባዊ እርካታ አታገኝም ለባሏ ፍቅር ምላሽ መስጠት ይሳናታል፡፡ ባለቤቷ የሻዉን ቢያደርጋት እንኳ የሞተ ገላ ትሆንበታለች፡፡ በተጨማሪም ለግንኙነት ብልት የሚያለሰልሰዉ ፈሳሽ አስፈላጊ የሆነዉ እና የሴቷን ብልት እይመነጭም፡፡ በዚህ ሳቢያ ወሲባዊ ተራክቦዉ ሳይሳካ ይቀራል።
➌ #በወሲባዊ _ግንኙነት_ወቅት_ደም_መፍሰስ
ከተለመደዉ የወር አበባ ቀናት ዉጪ ደም መፍሰስን በተመለከተ በዚህ ቀደም አይተናል፡፡ በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት ደም መፍሰስ ከዚህ አንድ ነገር ይለያል፡፡ ይኸዉም በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት ደም መፍሰስ የሚከሰተዉ በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት ብቻ ሲሆን ከተለመደዉ የወር አበባ ቀናት ዉጪ ደም መፍሰስ ደግሞ ከወሲባዊ ግንኙነት ጋር ተያያዥነት የለዉም እንዲያዉም ለበርካታ ቀናት ያለማቋረጥ የሚዘልቅ ነዉ፡፡
በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት ደም መፍሰስ ማለት አንድ ባል ሚስቱን ሊገናኝ ሲል ሰይጣን ደም እንዲፈሳት ያደርጋታል፡፡ በዚህ የተነሳ ባል ለመገናኘት አይችልም፡፡
አንድ ወታደር እንዲህ ብሏል፡- ለእረፍት ወደ ቤቴ መጥቼ ገና ከቤት ስደርስ ባለቤቴ ደም መፍሰስ ይጀምራታል፡፡ ደሙም ቤት ዉስጥ ባለሁባቸዉ የእረፍት ቀናት ሁሉ ይቆይባታል። የእረፍት ፈቃዴን ጨርሼ ወደ ጦሩ ስቀላቀል ግን ደሙ ይቋረጣል፡፡ እንዲያዉም ገና ቤቴን ሲለቅ ነዉ ደመ የሚቆመዉ፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ነዉ፡፡ ከዚያም ሴትየዋ የቁርአን ህክምና በመከታተል ተፈወሰች።
➍ #የሴቷ_ብልት_በስጋ_መሸፈን
ባል ሚስቱን ለመገናኘት ሲጠጋ በብልቷ አካባቢ የሚያግደዉ እና ሊበጥሰዉ የማይችለዉ ስጋ ያጋጥመዋል። በዚህ ሳቢያ ወሲባዊ ተራክቦዉ ሳይሳካ ይቀራል፡፡
➎ #ድንግልናን_ማድበስበስ
አንድ ባል ድንግል ያገባል፡፡ ነገር ግን በግንኙነት ወቅት ድንግልና የሌላት ሆና ያገኛታል፡፡ በዚህም ጥርጣሬ ላይ ይወድቃል፡፡ ነገር ግን ከቁርዓን ህክምና በኋላ ድግምቱ ሲከሽፍ ድንግልናዋ ይመለሳል።
⚫️ #የመሰናክለ_ወሲብ_ህክምና
መሰናክለ ወሲብን ለማከም በርካታ ዘዴዎች አሉ እነርሱም፡-
🌙 #ዘዴ_አንድ 1⃣
የአል ሩቅያ አንቀፆችን በታማሚዉ ላይ ትቀራበታለህ፡፡ በዚህም ጂኒዉ ከለፈለፈ ድግምቱ ስለሚገኝበት ቦታ ትጠይቀዉና ድግምቱን አዉጥተህ እንዲከሽፍ ታደርገዋለህ፡፡ ከዚያም ጂኒዉ ከሰዉዬዉ አካል እንዲወጣ ትነግረዋለህ። ከወጣ ድግምቱ ከሸፈ ማለት ነዉ፡፡ ነገር ግን የአል ሩቅያ አንቀፆችን ስትቀራበት ጂኒዉ ካልተናገረ ከዚህ በታች ከምናያቸዉ ዘዴዎች ዉስጥ ትጠቀማለህ፡፡
🌙 #ዘዴ_ሁለት 2⃣
ሱረቱል አእራፍ 117-122 የቁርአን አንቀፅን በዉሃ ላይ ሰባት ጊዜ ደጋግመህ ትቀራለህ፡፡ ከዚያም ታካሚዉ ለሰባት ተከታታይ ቀናት ከዚህ ዉሃ ይጠጣለታል ይታጠብበታልም፡፡ በዚህም በአላህ ፈቃድ ድግምቱ ይረክሳል።
🌙 #ዘዴ_ሶስት 3⃣
ሰባት አረንጓዴ የቁርቁራ ቅጠሎችን ታመጣና በሁለት ድንጋይ መሃል ትጨቀጭቃቸዋለህ፡፡ ከዚያም በዉሃ ዉስጥ ትጨምራቸዉና ዉሀዉን ወደ አፍህ አስጠግተህ ቅጠሎቹን በእጅህ እያገላበጥ አያት አል ኩርስይ፤ አል ኢኽላስ አል ፈለቅ እና አል ናስን ሰባት ጊዜ በመደጋገም ትቀራበታለህ፡፡ - ከዚያም ታካሚዉን ለሰባት ቀናት አንዲጠጣና እንዲታጠብበት ታደርጋለህ፡፡ ይህንንም ሲያደርግ በዚህ ዉሀ ላይ ሌላ ዉሃ መጨመርም ሆነ በእሳት ማሞቅ የለበትም... በፀሀይ ማሞቅ ግን ይችላል። ከታጠበ በኋላም አጣቢዉን በቆሻሻ ቦታ ላይ ማፍሰስ የለበትም፡፡ በዚህም በአላህ ፈቃድ ድግምቱ ከሽፎ መሰናክሉ ወሲቡ ይድናል፡፡
🌙 #ዘዴ_አራት 4⃣
የአል ሩቅያ አንቀጾችን በታማሚዉ ጆሮ ላይ ትቀራለህ፡፡ ከዚያም በእጆቹና በእግሮቹ ጫፎች የመደንዘዝ ስሜት እስኪሰማዉ ድረስ ከዚህ በታች የተጠቀሰዉን የቁርአን አንቀጽ መቶና ከዚያ በላይ ደጋግመህ በጆሮዉ ላይ ትቀራበታለህ፡፡ ይህንንም ጤንነት እስኪሰማዉ ድረስ ለበርካታ ቀናት ትደጋግምለታለህ፡፡ ችግሩ ከተወገደለት ድግምቱ በአላህ ፈቃድ መክሸፉን ታረጋግጣለህ፡፡ ይህም አንቀጽ የሚከተለዉ ነዉ።👇👇👇
⚠️⚠️ በዚህ ዙርያ ሷሂሮትን የሚለዩባቸው አጋጣሚዎች እነሆ፡፡ ይህን ሲህር የሰራቦትን ሰው ሲያዩ፡፡
♦️ ልቦ መፍራት መምታት ይጀምራል፡፡
♦️ ጭንቀት ይወሮታል፡፡ አጠገቡ መቀመጥን አይቻሎትም፡፡
♦️ ያ ሰው የፈለገውን ነገር አድርገው መገላገል ምኞቶ ነው፡፡ በተቃራኒ ግን ያ ሰው እጅግ እርጋታ የተሞላበት ሁኖ ያገኙታል፡፡ ምክያቱም ለግዜው አሸናፊ የሆነ ስለሚመስለው ነው፡፡ አሏህም ካርታውን ያጠፋበታል፡፡ አንዴ ሩቅያህ ከጀመሩ ኋላ፡፡
♦️ ከሱ ጋር ላለመገናኘት የማያደርጉት ጥረት አይኖርም ሰውየው ግን ሁሌም እርሶ ባሉበት ስፍራ አይጠፋም፡፡ ይህም ከብዙዎቹ በጥቂቶቹ ላይ የሚታይ ነው፡፡
====== ===== ==== ===== ===== =====
🟢 #ከተለመደዉ_የወር_አበባ_ቀናት_ዉጪ ደም እንዲፈስ የሚያደርግ ድግምት አንዴት ይከሰታል?
>>> ይህ ዓይነት ድግምት በሴቶች ላይ ብቻ የሚከሰት ነዉ፡፡ አንድ ጠንቋይ ድግምት ወደ ሚደረግባት ሴት ደም እንዲፈሳት እንዲያደርጋት ጂኒ ይልካል፡፡ ጂኒዉም በሴትየዋ ዉስጥ በመግባት በደም ስሮቿ ዉስጥ ይዘዋወራል።
.... ይህን በማስመልከት ነብዩ እንዲህ ይላሉ ሰይጣን በሰዉ ሰዉነት ዉስጥ ደም እንደሚዘዋወረዉ ይዘዋወራል” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበዉታል) ጂኒዉ ወደ ሴቷ ማህፀን የደም ጋን በመድረስ ይረግጠዋል በዚህም ደም ይፈሳታል፡፡
✅ ከተለመዱ የወር አበባ ቀናት ዉጪ ስለሚፈስ ደም ተጠይቀዉ ነብዩ እንዲህ አሉ
>>> “ይህ ዓይነት ደም የሰይጣን እርግጫ ዉጤት ነዉ” (ቲርሚዚ ዘግበዉታል ሃስኑን ሶሂህ ነዉ ብለዉታል)
በሌላ ዘገባም ይህንኑ አስመልክተዉ ነብዩ እንዲህ ይላሉ "የሰይጣን እርግጫ ዉጤት ነዉ፣ የወር አበባ ደም አይደለም፡፡" አህመድና ነሳኢ ቢሰነዲን ጀይድ" ዘግበዉታል)
ከነዚህ ሁለት ዘገባዎች የምንገነዘበዉ ከተለመደዉ የወር አበባ ቀናት ዉጪ የሚፈስ ደም በሰይጣን እርግጫ ሳቢያ ከማህፀን የደም ጋን የሚፈስ መሆኑን ነዉ፡፡
#ህክምናዉ
የእል ሩቅያ አንቀፆችን በዉሀ ላይ ትቀራና ታማሚዋ ትጠጣለች ለሶስት ተከታታይ ቀናትም ሰዉነቷን ትታጠብበት፡፡ በዚህም በአላህ ፈቃድ ደሙ ይቆማል፡፡
🟡 #ሰዉ_እንዳያገባ_ለማድረግ_የሚደረግ_ድግምት
አንድን ሰው ከትዳር ለማራቅ ሚደረጉ ሲህሮች እጅግ አስነዋሪዎች ናቸው፡፡ ከእነዛ ምልክቶች ዉስጥ
☑️ የውስጥ አለመረጋጋት እጅግ በጣም ለነገራቶች መጨነቅ
☑️ ቀን ላይ ትዳር ፈልጎ የመጣው ሰው ውሳኔ አጥቶ ወድያው መመለስ! አለመፈለግ፡፡ መጀመርያ ፍላጎት ኑሮ ከዛንም ፍላጎት ማጣት፡፡
☑️ ልብ በየቀኑ ‹‹ቀኔ እያለፈ ነው ሲል መጨነቅ፡፡›› ይህ ሁሉም ሰው ይጨነቃል ግን ደግሞ ያንቺ ይብሳል ልብሽ እስኪፈነዳ ድረስ መጨነቅ፡፡
☑️ ብሩህ የወደፊት ተስፋን ‹‹ትዳርን›› ፈላጊ መሆን ግን ደግሞ ትዳር ሲመጣ እጅግ መጥላት!!
☑️ ዶሮ ከመጮሁዋ እና ከመንጋቱ ፊት በተለይ ሱብሂ ሰላት አካባቢ በህልም ከጥቁር መልኩን ከማታውቂው ሰውነቱ ፈርጣማ ከሆነ ሰው ጋር ወሲብ ማድረግ፡፡
☑️ ክንውንን ወይም በውስጠ ህሊና ሀራም ማሰብ ወይም ማስተርቤሽን ማብዛት፡፡ ሃታ ሰላት ላይ ሳይቀር ማስተርቤሽንን ማሰብ! የመሳሰሉት ናቸዉ
📌📌 ምቀኛና ተንኮለኛ የሆነ ሰዉ ጠንቋይ ዘንድ በመሄድ እገሊት የእገሌ ልጅ እንዳታገባ የሆነ ነገር አድርግ ይለዋል፡፡ ጠንቋዩም የልጅቷንና የእናቷን ስም ይጠይቀዋል፡፡ የላቧ ጠረን ያለበትን ልብስ፤ ፀጉር... እንዲያመጣለት ያደርግና ድግምት መስራት ይጀምራል፡፡ ለዚህ ድግምት አንድና ከአንድ በላይ ጂኒዎችን ይወክላል፡፡ ከዚያም ጂኒዉ ወደ ልጅቷ በመሄድ ለመግባት እድል እስከሚያገኝ ድረስ ይከታተላታል፡፡ ከሚከተሉት አራት ምክንያቶች አንዱ ሲከሰት ጂኒ ወደ ስዉ ልጅ ስነት ሊጋባ ይችላል።
➊ ከፍተኛ ፍርሃት ሲኖር
➋ ከፍተኛ ንዴት (ቁጣ) ሲክስት
➌ ከፍተኛ እንቅልፍ ወይም እራስን አለማወቅ በሚኖርበት ወቅት
➍ በማንኛዉም በትንሽም በትልቅ በሀራም ስራዎች ዉስጥ መዘፈቅ
በዚህ ጊዜ ጂኒዉ ሁለት አማራጮች ይኖሩታል፡፡
1⃣ ልጅቷ ዉስጥ በመግባት ለማጨት የሚመጣ ወንድ ስታይ እንድትጨነቅ እና እንድትተወዉ ማድረግ፡፡ ወይም
2⃣ ልጅቷ ዉስጥ ለመግባት ሳይችል ከቀረ ከልጅቷ ዉጪ በመሆን የማስመሰል አስማት መስራት ይጀምራል፡፡ በዚህም ልጅቷን ለማጨት የሚመጣን ሰዉ መልከ ጥፉ መስላ እንድትታየዉ በማድረግ ይወሰዉሰዋል፡፡ ልጅቷንም እንደዚሁ ይወሰዉሳታል፡፡
በዚህም የተነሳ ሊያጫት የሚመጣ ሁሉ ሲተዋት ይስተዋላል፡፡ በመጀመሪያዉ ቀን ሊያገባት የተስማማ ከቀናት በኋላ ሲያፈገፍግ ታየዋለህ፡፡ ይህ እንግዲህ የሚሆነዉ በሰይጣን ውስወሳ ሳቢያ ነዉ፡፡
🌟 የተሰራዉ ድግምት ጠንካራ በሚሆንባቸዉ ሁኔታዎች ልጅቷን ለማጨት የሚመጣዉ ስዉ ገና ወደ ቤት ሲገባ ከፍተኛ ጭንቀት ይሰማዋል። ልክ እስር ቤት እንዳለ ሰዉ ህይወት ትጨልምበታለች፡፡ በዚያዉ ሳይመለስ ይቀራል፤ የዚህ ዓይነት ድግምት በሚቆይባቸዉ ጊዜያት በልጅቷ ላይ ብቅ እልም የሚል እራስ ምታት ወይም ማይግሬን የሚባለዉ የራስ ህመም
(ግማሽ ራስን ከፍሎ የሚያም) ይስተዋላል።
🌟 #ሰዉ_እንዳያገባ_ለማድረግ_የሚደረግ_ድግምት_ሲህር_ምልክቶች
⚡️ መድሃኒት በመዉሰድ የማይሻል ሄድ መጣ የሚል የራስ ምታት
⚡️ከባድ የራስ ምታት (ማይግሬን)
⚡️ደረት ዉስጥ ጭንቅ የሚል ስሜት በተለይም ከአስር ሰዓት በኋላ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ
⚡️ለማጨት የሚፈልገዉን ሰዉ መልከ ጥፉ አድርጎ መመልከት
⚡️በብዛት በሀሳብ መወጠር (የሀሳብ መብዛት)
⚡️ በመኝታ ወቅት ፍርሃት ፍርሃት ማለት
⚡️ ይህ ዓይነት ድግምት በተደረገባቸዉ አንዳንድ ሰዎች ላይ የሆድ ህመም ይከሰታል
⚡️ የጀርባ የታችኛዉ ክፍል ህመም (የጀርባ ላይ ህመም መሰማት
📌📌 #ሰዉ_አንዳያገባ_ የተደረገበት_ ድግምት_ህክምና
✏️የሩቅያ አንቀፆችን ተቀራባታለህ እራሷን ከሳተች ከዚህ ቀደም በተማርነዉ መንገድ ጂኒዉን ታነጋግረዋለህ፡፡
✏️ እራሷን ሳትስት ነገር ግን በአካሏ ላይ የተለየ ስሜት የሚሰማት ከሆነ የሚከተለዉን እንድትከታተል ታደርጋለህ
➢ ሂጃብ መልበስ
➢ ሶላትን በወቅቱ ሳያቋርጡ መስገድ
ሙዚቃም ሆነ መዝሙር ከመስማት መታቀብ
➢ ከመኝታ በፊት ዉዱዕ ማድረግ እና አያት አል ኩርስይን መቅራት
➢ ለአንድ ሰዓት ያህል አያት አል ኩርሲሰይን በመደጋገም በስልክ ላይ በመጫን በቀን አንድ ጊዜ እንድታዳምጠዉ ማድረግ፡፡
➢ አል ኢኽላስ፤ አል ፈለቅ፤ አል ናስ ለአንድ ሰዓት ያህል በካሴት ደጋግሞ በመቅዳት በቀን አንድ ጊዜ እንድታዳምጥ ማድረግ
➢ በዉሃ ላይ የአል ሩቅያ አንቀጾችን ትቀራለህ፡፡ ከዚያም ከዚህ ዉሃ ልጅቷ ትጠጣለች፣ በየሶስት ቀኑ ልዩነት ሰዉነቷን ትታጠብበት፡፡
➢ ላኢላሀ ኢለ አላህ ወህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልክ ወለሁል ሀምድ ወሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር ከስብሂ ሶላት በኋላ 100 ጊዜ ማለት
እነዚህን ለአንድ ወር ሙሉ መከታተል ይኖርባታል፡፡ ከዚህ በኋላ ከሚከተሉት አንዱ ይሆናል፡፡
➊ የህመሙ ምልክቶች ጠፍተዉ ህመሙ ድኖ ድግምቱ ይረክሳል።
አልሃምዱ ሊላህ ወይም
➋ ህመሙ ጠንቶባት የህመሙ ምልክቶች አይለዉ ሊሆን ይችላል። በዚህ ግዜ የአል ሩቅያ አንቀጾችን ትቀራባታለህ በአላህ ፈቃድ- እራሷን ትስታለች፡፡ ከዚያም ከዚህ ቀደም ባየነዉ መልኩ ጂኑን እንዲናገር እያረክ ታክማታለህ፡፡
#ክፍል 8⃣
ይቀጥላል....
Join👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
የ____ስጦታ❤️🌟🌻🌻⭐️⭐️
#ቢስሚከ_ነህያ_አል_ሙጁብ📚
🌙🌙🌙🌙🌙🌙⚡️⚡️⚡️🌟🌟🌟☀️
አልሙጁብ ማለት ምን ማለት ነው?
💥💥💥💥💥💥💥💥
#ሬድዋን🎤🎤
/channel/+-zHkXQeSZdc4MjY0
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
✍ አሚር ሰይድ
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
⭐️ #ክፍል👉 ስድስት 6⃣
♦♦ አንድ ታካሚ መዳኑን ሲያዉቁ ድግምት የሚያሰሩ ሰዎች ድግምቱን ለማሳደስ ወደ ደብተራ ጠንቋይ ዘንድ ይሄዳሉ፡፡ ስለዚህ ታካሚዉ ስለመፈወሱ ለማንም መንገር የለበትም፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የሚከተሉት መከላከያዎች በድግምት እንዳይያዝና እንዳይታደስበት ይከላከሉለታል፡፡ ስለዚህ አጥብቆ ሊይዛቸዉ ይገባል፡፡ መከላከያዎቹ የሚከተሉት ናቸዉ፡፡
➊ ሶላት በጀመዓ መስገድ
➋ ሙዚቃን መዝሙርን አለመስማት
➌ ከመኝታ በፊት ዉዱዕ አድርጎ እና አያት አል ኩርሲይን ቀርቶ መተኛት
➍ ከማንኛዉም ነገር በፊት ቢስሚ አላህ ብሎ መጀመር
➎ላኢላሀ ኢለ አላህ ወህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁ ሀምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር .... ከሱብህ ሶላት በኋላ እና ከዓስር ሶላት በኋላ 100 ጊዜ ማለት
>>> መቶ ግዜ ያለ አስር ባሮችን ነፃ እንዳወጣ ይቆጠርለታል፤ መቶ መልካም ሥራ ይመዘገብለታል፤ መቶ ሀጢያቶችን ይማራል፣ በዚያ ቀን እስከማምሻ ድረስ ከሰይጣናት መጠበቂያ ትሆነዋለች፡፡ ከመቶ በላይ ያለ ካልሆነ በቀር የሚበልጠዉ የለም፡፡
➏ በየቀኑ ቁርአን መቅራት፣ቁርአን ያልቀራ ከሆነ እቤቱ ቁርአን መክፈት በስልኩ ማዳመጥ
➐ዉሎዉን ሷሊህ (መልካም) ከሆኑ ሰዎች ጋር ማድረግ
➑ጠዋትና ማታ የሚባሉ ዚክሮችን ሳያቋርጥ ማለት
እነዚህ ድግምቱ እንዳይታደስና ለወደፊት ጥንካሬን ይሰጡናል
⚠️⚠️ ማወቅ የሚገባን ነገር አለ፡፡ ይኸዉም አንድ ደብተራ ወይም ጠንቋይ ድግምት ወደ ሚደረግበት ሰዉ ጂኒ (ሰይጣን) ይልካል። ጂኒዉ እንዲሁ ወደ ሰዎች ሰዉነት ዉስጥ መግባት ስለማይችል ለመግባት _ ምቹ ሁኔታ ይጠባበቃል። ጂኒ ወደ ሰዉ ሰዉነት ዉስጥ የሚገባዉ ከሚከተሉት ሁኔታዎች አንዱ ሲከሰት ነዉ፡፡
✅ ከፍተኛ ፍርሃት
✅ ከፍተኛ ንዴት (ቁጣ)
✅ ከፍተኛ እንቅልፍ (እራስን አለማወቅ)
✅ በስሜት (በሀጢያት) ዉስጥ መዘፈቅ
ከነዚህ ሁኔታዎች በአንዱ ተዘፍቆ ካገኘዉ ጂኒዉ ሊገባበት ይችላል። ነገር ግን ዉደዕ አድርጎ ከሆነ ወይም አላህን ካወሳ በምንም ዓይነት ሁኔታ ጂኒዉ ሊገባበት አይችልም፡፡
አንድ ሰዉ ጂኒ ሊገባበት ሲል አላህን ካስታወሰና ካወሳ ጂኒዉ ይቃጠላል። በጂኒዎች ህይወት ዉስጥ አስቸጋሪዉ ህይወት በሰዉ ዉስጥ የሚገቡበት ጊዜ ነዉ፡፡
🔰🔰🔰 #መስተፋቅር 🔰🔰🔰
መስተፋቅር ማለት ባል ሚስቱን እንዲወዳት ወይም እሱ ሚስቱ እንድትወደዉ ለማድረግ ሲባል የሚሰራ ድግምት ወይ ሌላ ነገር ነው
🟢 #በመስተፋቅር_ድግምት_በተለከፈ_ሰዉ_ላይ_የሚታዩ_ምልክቶች
➊ ከተለመደዉ ወጣ ያለ ፍቅር ይታይበታል
➋ ግብረ ስጋ ግንኙነት ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት ያድርበታል
➌ ሚስቱን ለማየት በጣም ይጣደፋል ይቻኮላል
➍ ሚስቱ ስታዘዉ በጭፍን ያለማገናዘብ ይታዘዛታል
➎ ያለ እርሷ ትዕግስት ማጣት
➏ ስለ እርሷ ይተናል
🟡 #መስተፋቅር_እንዴት_ይከሰታል?
በባልና ሚስት መካከል ብዙ ጊዜ አለመግባባቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን እነዚህ አለመግባባቶች ወዲያዉኑ ተወግደዉ ህይወት ወደ ነበረችበት ትመለሳለች፡፡ አንዳንድ ሴቶች በቀላል አለመግባባት ትዕግስት ስለማይኖራቸዉ መስተፋቅር ለማሰራት ሮጠዉ ጠንቋይ (ደብተራ) ቤት ይሄዳሉ፡፡ ይህም የሚሆነዉ እንግዲህ ከሴትየዋ የኢማን ማጣት ወይም እንዲህ ያለ ስራ የተከለከለ ሀራም መሆኑን ካለማወቅ የመነጨ ሊሆን ይችላል፡፡ ሴትየዋ ጠንቋይ ዘንድ መስተፋቅር ለማሰራት ስትሄድ ጠንቋዩ የባሏን የላብ ፋና ማህረቡን፣ ኮፍያዉን፤ የልብሱን ቁራጭ እንድታመጣለት ያደርጋል፡፡ ከዚያም ከልብሶቹ ላይ ክሮችን በመምዘዝ እየደገመ ይቋጥራቸዋል፡፡ ከዚያም ሰዉ በማይደርስበት እንድትቀብረዉ ያዛታል፡፡
>>>> ወይም በሚበላ ወይም በሚጠጣ ነገር ላይ ድግምት ይሰራና እንድታበላዉ ወይም እንድታጠጣዉ ያደርጋል። ድግምቱ በነጃሳ ነገር ላይ የተሰራ ከሆነ በጣም አስከፊ ይሆናል፡፡ በወር አበባ ደም ከሆነ ደግሞ እጅግ በጣም አስከፊ ነው፡፡
☑️ መተትን ድግሞምት ከትዉልድ ወደ ትዉልድ የሚወራረሱ ቤተሰቦች በተለያዩ አካባቢዎች ይገኛሉ፡ ስለሆነም ሁላችንም ብንሆን ለጋብቻ ስናጭ የልጅቷ ቤተሰቦች ምን እንደሆኑ በቅድሚያ ልንመረምር ይገባል፡፡
#ለምሳሌ፡- የልጅቷ እናት በየጠንቋዩ እና በየቃልቻዉ ቤት የምትንጦለጦል ወይም በቤቷ ዉስጥም ቢሆን ለቃልቻ የምታደገድግ ከሆነ ከእንዲህ ያለ ቤተሰብ ጋር በጋብቻ ልትተሳሰር አይገባም፡፡ ምክንያቱም እንዲህ ያሉ ሰዎች ባሎቻቸዉን የመተት የድግምት መሞከሪያ እንደሚያደርጉዋቸዉ እና ለሰይጣን እንደሚገብሯቸዉ ይታወቃል።
🔴 #የመስተፋቅር_ተቃራኒ_ዉጤት
➊ በመስተፋቅር ድግምት ሳቢያ ባል ሊታመም ይችላል፡፡ በዚህ የተነሳ ለብዙ አመታት ባሎች ህመሙ ሳይታወቅ ይታመማል
➋ የመስተፋቅር ድግምት ይቀለበስና ባል ሚስቱን እንዲጠላት ሊያደርግ ይችላል። ይህም የሚሆነዉ በርካታ ጠንቋዮች ስለ ድግምት አሰራር በቂ እዉቀት ስለማይኖራቸዉ ነዉ፡፡
➌ አንድ ሴት ባሏ ሴቶችን በሙሉ ጠልቶ እርሷን ብቻ እንዲወዳት ለማድረግ ሁለት ዓይነት ድግምት ልታሰራ ትችላለች እነርሱም
☞ #አንደኛ፦ ድግምት ከርሷ በቀር ያሉ ሴቶችን እንዲጠላ የሚያደርግ ሲሆን
☞ #ሁለተኛዉ፡ ደግሞ እርሷን ብቻ እንዲወድ የሚያደርግ ይህም ባል እህቶቹን፣ እናቱን፣ አክስቶቹን ባጠቃላይ ሴት ዘመዶቹን በሙሉ እንዲጠላ ያደርገዋል፡፡
➍ እንዲህ ዓይነቱ ሁለት ዓይነት ድግምት ይቀለበስና ባል ሴቶችን በሙሉ ሚስቱን ጨምሮ እንዲጠላ ያደርገዋል፡፡ አንድ ሚስት የዚህ ዓይነት ድግምት ባሏ ላይ ታሰራበታለች፡፡ በዚህ የተነሳ ባል ሚስቱን ይጠላትና ይፈታታል፡፡ ሚስት ድግምቱን ለማስፈታት ወደ አሰራችበት ጠንቋይ ዘንድ ስትሄድ ሞቶ አገኘችዉ፡፡
✅ #የመስተፋቅር_መንስኤዎች
➡️ የባልና የሚስት አለመግባባት
➡️ ሚስት ለባሏ ገንዘብ መቋመጥ በተለይ ሃብታም ከሆነ
➡️ ባለቤቷ ሌላ ሁለተኛ ሚስት ሊያገባ ይችላል ብላ መጠርጠር። ሆኖም ከአንድ በላይ እስከ አራት ሚስት ድረስ ማግባት የተፈቀደ ነዉ፡፡ ነገር ግን የዘመናችን ሴቶች በተለይ ተልዕኳቸዉን ጥፋት ላይ ባደረጉ ሚዲያዎች ተፅዕኖ ያረፈባቸዉ ባል ሁለተኛ ሚስት ለማግባት መፈለጉን የጥላቻ ምልክት አድርገዉ ይወስዱታል፡፡ ይህ ደግሞ ከባድ ስህተት ነዉ፡፡ ምክንያቱም ባል ሚስቴን እየወደዳት ሌላ ተጨማሪ ሚስት እንዲያገባ የሚያደርጉት በርካታ አሳማኝ ምክንያቶች ስለሚኖሩ ነዉ። ከነዚህም ጥቂቶቹ በርካታ
☞ልጆች መፈለግ፤
☞ ሚስት የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም በምታይበት ጊዜ የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎት ሊያድርበት ይችላል፡፡
☞ ከተለየ ቤተሰብ ጋር በጋብቻ አማካኝነት ትስስር ለመመስረት ሊፈልግ ይችላል እና ሌሎችም ምክንያቶች ይኖራሉ።
ብዙ ሴቶች ሁለተኛ ሚስት የሚለዉን ይጠሉታል...ወንድም ሁለተኛ ሚስት የምትለዉን ኪታብ የቀራዉም ያልቀራዉ ጃሂሉም አሊሙም ከምላሱ የማትጠፋ ነች👇👇
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
✍ አሚር ሰይድ
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
⭐️ #ክፍል👉 አምስት 5⃣
🟢 #የሚለያይ_የሚያጣላ_መተት_ሲህር_ምንነት
ባልና ሚስትን ለማለያየት፣ በጓደኞች ወይም በንግድ ሸሪኮች መካከል ጠብ እና ጥላቻ እንዲፈጠር ለማድረግ የሚሠራ መተት ነዉ።
🔶 #የሚለያይ_መተት _ዓይነቶች
➊ እናትና ልጅን የሚያጣላ
➋ አባትና ልጅን የሚያጣላ
➌ ወንድማማቾችን የሚያጣላ
➍ ጓደኛሞችን የሚያጠላ
➎ የንግድ ወይም በሌላ መስክ የተሰማሩ ሽሪኮችን የሚያጣላ
➏ባለትዳሮችን የሚያለያይ (የሚያጣላ) ይህ ዓይነቱ አስከፊዉና እጅግ በጣም ተንሰራፍቶ ይገኛል፡፡
🔷 #የሚለያይ_የሚያጣላ_መተት_ሲህር_በተስከፈ_ሰዉ_ላይ_የሚታዩ _ምልክቶች
☞ከመዉደድ ወደ መጥላት ያልተጠበቀ የፀባይ ለዉጥ
☞መጠራጠር ማብዛት
☞አንዱ ሲያጠፋ ሌላኛዉ ያለማለፍ (ይቅር አለመባባል)
☞ በጣም ቀላልና ትንሽ ብትሆንም የፀባቸዉን መንስኤ ማግዘፍ
☞በትንሽ በትልቁ መጋጨት
☞ሚስት ለባሏ ያላት ባል ለሚስቱ ያለዉ እይታ መለወጥ፡፡ ምንም ዉብ ቆንጆ ብትሆንም እንኳን ባል ሚስቱ መልከ ጥፉ ትመስለዋለች አስቀያሚ መስላ ትታየዋለች። በተመሳሳይ መልኩ ሚስት ባሏ አስፈሪ መስሎ ይታያታል፡ በተጨባጭ ግን በሚስቲቱ ወይም በባል ፊት በአስቀያሚ ምስል የሚመሰለዉ የድግምቱ እንደራሴ ሰይጣን ነዉ።
☞ ድግምት የተደረገበት ወገን ሌላኛዉ የሚሰራዉን ሥራ መጥላት
☞ ድግምት የተደረገበት ወገን ሌላኛዉ የሚቀመጥበትን ቦታ መጥላት (ከፊቱ ዞር እንዲልለት ይፈልጋል)
#ለምሳሌ፡- ድግምት የተደረገበት ሰዉ ከከቤቱ ዉጭ ሲሆን በጥሩ ሁኔታና ፀባይ ይታያል ወደ ቤቱ ሲገባ የጭንቀትና የድብርት ስሜት ይሰማዋል።
☑️ ይህን በማስመልከት አል ሃፊዝ ኢብን ከሲር እንዲህ ይላሉ... ባለትዳሮች በድግምት የተነሳ የሚጣሉትና የሚለያዩት መጥፎ ወይ አስቃያሚ መልክ፣ እና ሌሎች የሚያጣሉ ነገሮችን አንዱ በሌላዉ ላይ ያየ ስለሚመስለዉ ነዉ፡፡
🟡 #የሚያለያይ_ድግምት_ሲህር_አንዴት_ሲከሰት_ይችላል?
አንድ በአላህ የተረገመ ሰው ወደ ጠንቋይ ዘንድ ይሄድና እገሌ እና ሚስቱን እንዲያለያይለት ይጠይቀዋል፡፡ ጠንቋዩም ድግምት የሚደረግበትን ሰዉዬ ስምና የእናቱን ስም ንገረኝ ይለዋል።
ከዚያም የዚህን ሰዉዬ
>> የላብ ፋና
>> የፀጉሩን
>> የልብሱን
>> የኮፍያዉን፣ የካልሲዉን ቁራጭ ይቀበለዋል፣
የላቡን ፋና ማግኘት የማይችል ከሆነ፣ በፈሳሽ ነገር ላይ ድግምት ይሰራና በስዉዬዉ መንገድ ላይ እንዲረጨዉ ያዘዋል፡፡ ሰዉዬዉ በሚረግጠዉ ጊዜ በድግምቱ ይለከፋል (እስላማዊ የድግምት መከላከያዎችን የሚከታተል ከሆነ ግን በድግምቱ አይለክፍም)፡፡
🟣 #የሚለያይ_የሚያጣላ_ድግምት_ህክምና
☑️ ደረጃ አንድ ቅድመ ህክምና ተገባራት
ህክምናዉ ከመጀመሩ በፊት የሚከተሉትን አድርግ-
➊ የኢማን አካባቢ መፍጠር :- ይህም ማለት ህክምናዉ በሚሰጥበት ክፍል ዉስጥ መላኢኮች መግባት እንዲችሉ ፎቶዎች እና ምስሎች ካሉ ማንሳት እና ንጽህናዉ የተጠበቀ ክፍል ሊሆን ይገባል፡፡
➋ ሂርዝ፣ ክታብ የመሳሰሉ ታካሚዉ የያዛቸዉ ነገሮች ካሉ ማስወገድ እና ማቃጠል
➌ ህክምና በሚደረግበት ክፍል ዉስጥ ሙዚቃ እና የመሳሰሉት ነገሮች መኖር የለባቸዉም
➍ በሸሪዓ ከተከለከሉ ነገሮች ቦታዉ የፀዳ መሆን አለበት ፡፡
ለምሳሌ
>> ወርቅ ያደረገ ወንድ
>> ሂጃብ ያልለበሰች ሴት
>> ሲጋራ የሚያጨስ መኖር የለበትም
➎ ለታካሚዉና ለቤተሰቦቹ በእስልምና እምነት (በአቂዳ) ዙሪያ ትምህርት መስጠት፡፡ ይህም በአላህ ላይ ያላቸዉን እምነት ያፀናላቸዋል፡፡
በአላህ ላይ ብቻ ተስፋ እንዲኖራቸዉ ያደርጋል።
ጠንቋዮች የሚያክመት ከስይጣን ጋር በመተባበር መሆኑን አንተ ግን የምታክመዉ በአላህ ቃል በቁርአን ብቻ መሆኑን ለታዳሚዎች በሚገባ ልታባራራላቸዉ ይገባል።
እንዲሁም የቁርአንን ፈዋሽነት ልታረጋግጥላቸዉ ይገባል፡፡
➏ የህመሙን ሁኔታ በመጠየቅ መመርመር
የህመሙ ምልክቶች በሙሉ ወይም በአብዛኛዉ መኖራቸዉን ለማረጋገጥ ታካሚዉን አንዳንድ ጥያቄዎችን መጠየቅ፡- ለምሳሌ
✔አልፎ አልፎ እንኳን ቢሆን ባለቤትህ(ሽ) አስቀያሚ መስላ(ሎ) ትታይሃለች (ይታይሻል)?
✔ ከባለቤትህ (ሽ) ጋር በትንሽ በትልቁ ትጋጫላችሁን
✔ ቤት በደህና ዉለህ (ሽ) - ወደ ቤት ስትገንቢ የመጨናነቅና የድብርት ስሜት ይሰማሃል (ይሰማሻል?)
✔ከባለቤትህ (ሽ) ጋር በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት ጭንቀት ይሰማሀል (ሻል)?
✔ አንተ ወይም ሚስትህ በእንቅልፍ ማጣት ተቸግራችኋልን?
✔አስፈሪ ህልሞች ይታዩሃል?
>>>>እንደዚህ እያልክ ጥያቄህን ትቀጥላለህ፡፡ ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሚሆኑ የድግምት ምልክቶች በታካሚዉ ላይ ከተገኙበት ህክምናን ትቀጥላለህ፡፡
1⃣ ህክምና ከመጀመርህ በፊት ዉዱእ አድርግ፡፡ ታካሚዉ እና አብረዉህ የታደሙት ዉዱዕ እንዲያደርጉ አድርግ
2⃣ ታካሚዋ ሴት ከሆነች በሚገባ ትሸፋፈን በህክምና ወቅት እንዳትገለጥ ልብሶቿ ጠበቅ ተደርገዉ ይታሰሩ
3⃣ ከሸሪዓ ዉጭ የለበሰች (ምሳሌ፡- ፊቷን የገለጠች፣የጥፍር ቀለም የተቀባች ሴት አታክም
4⃣ ሙህሪሟ በሌለበት ሴትን አታከም
5⃣ በህክምና ክፍሉ ዉስጥ ከሙሀሪሟ በስተቀር ማንንም አታስገባ
6⃣ ሃይልም ሆነ ብልሃት የአላህ እንጂ አንተ እንደሌለህ አምነህ በአላህ ብቻ ታገዝ
🟠 #ህክምናዉ_በደንብ_እናስተዉል
እጅህን በታካሚዉ ራስ ላይ ታደርግና የሚከተሉትን የቁርአን አንቀጾች በጥሩ አቀራርና ከፍ ባለ ድምፅ በጆሮዎቹ በኩል ትቀራበታለህ፡፡ እነዚህ የቁርአን አንቀጾች የሩቅያ አንቀጾች በመባል ይታወቃሉ፡፡ እነዚህ የሩቅያ አንቀጾች ጂኒዉ ከሰዉየዉ አካል ወጥቶ እንዲሄድ ወይም ቀርቦ እንዲናገር (እንዲለፈልፍ) ያደርጉታል፡፡
መቅራት የማትችል ከሆነ እነዚህን የሩቃ አንቀፆች በሞባይል ወይም በFLASH አድርጎ በጂፓስ ከፍቶ እንዲያዳምጥ ማድረግ ይቻላል፡፡
🔶 #የቁርአን_አንቀፆቹ
➊ ሱረቱል ፋቲሀ
➋ አል በቀራህ 1-5
➌ አል በቀራህ 101-102
➍ አል በቀራህ 163-164
➎ አል በቀራህ 255
➏ አል በቀራህ 285-286
➐ አል ኢምራን 18-19
➑ አል አዕራፍ 54-56
➒ አል አዕራፍ 117-122
➓ ዩኑስ 81-82
➊➊ አል ሙእሚኑን 115-118
➊➋ አስ ሷፍፋቲ 1-10
➊➌ አል አህቃፍ 29-32
➊➍ አር ረህማን 33-36
➊➎ አል ሃሽር 21-24
➊➏ አል ጂን 1-9
➊➐ አል ኢኸላስ
➊➑ አል ፈለቅ
➊➒ አል ናስ
በነዚህ የቁርአን አንቀፆች በጥሩ አቀራር ከቀራህበት በሆላ ታካሚዉ ከሚከተሉት ሶስት ሁኔታዎች ዉስጥ
በአንዱ ሁኔታ ላይ ይሆናል፡፡
1⃣ #አንደኛዉ_ሁኔታ
ታካሚዉ እራሱን ይስታል የድግምቱ እንደራሴ ጅኒዉ መናገር (መለፍለፍ) ይጀምራል፡፡ በዚህ ግዜ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጂኑን ትጠይቃለህ።
➊ ስምህ ማን ነዉ? ሀይማኖትህ ምንድን ነዉ? ሀይማኖቱን ሲነግርህ እንደ ሀይማኖቱ ሁኔታ ታነጋግረዋለህ፡፡ ይህም ማለት ሙስሊም ካልሆነ እስልምናን እንዲቀበል ጥሪ ታቀርብለታለሁ፡፡ ሙስሊም ከሆነ ደግሞ የሚሰራዉ ሥራ ማለትም ጠንቋይን ማገልገሉና መተባበሩ እስልምናን የሚቃረን እና የተከለከለ መሆኑን አስረዳዉ፡፡👇👇
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
✍ አሚር ሰይድ
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
⭐️ #ክፍል👉 አራት 4⃣
🔰🔰 #ደጋሚዎች_ጂኒ_የሚስቡባቸዉ_የተለያዩ_ዘደዎች
💠 #ዘዴ አንድ፡- እርግማን
ድግምተኛው ጨለማ ክፍል ዉስጥ ገብቶ እሳት ያቀጣጥላል፡፡ ሊሰራዉ ለፈለገዉ የድግምት ዓይነት ተስማሚ የሆነ እጣን ያጨሳል፡፡ ሰዎችን የሚያጣላ፣ የሚያለያይ…….. ድግምት ለመስራት ሲፈልግ መጥፎ ጠረን ያላቸዉን እጣኖች ይጠቀማል።
☞ በተቃራኒዉ መስተፋቅር ለመስራት፤ ድግምት ለመፍታት... ሲፈልግ ጥሩ መዓዛ ያላቸዉን እጣኖች ይጠቀማል፡፡ ከዚያ በኋላ በክህደት የተሞሉ የድግምት ቃላትን ማማተብ ይጀምራል፡፡ እነዚህ የድግምት ቃላት ደግሞ በጂኒዎች አለቃ መማል በአለቃችሁ ይሁንባችሁ ... የሚሉትን የክህደት ቃላት ያዘሉ ናቸዉ፡፡ እነዚህን በማማተብ ጂኒዎችን ይለማመናል ለእነርሱም ይፀልያል እርዳታ ይጠይቃቸዋል ታላላቅ የጂኒ መሪዎችን ያወድሳል። ይህን ሁሉ በሚያደርግበት ጊዜ ሁሉ ድግምተኛው የቆሸሹ እና የተነጀሱ ልብሶችን መልበስ አለበት፡፡
ድግምቱን ተብትቦ ሲጨርስ ሰይጣን በዉሻ ወይም በእባብ ወይም በሌላ ማንኛዉም ቅርፅ ተመስሎ ይገለጥለታል፡፡ ከዚህ በኋላ የሚፈልገዉን እንዲፈፅምለት ይጠይቀዋል፡፡ ወይም ሰይጣኑ ሳይገለጥ ድምፁን ብቻ ያሰማዋል ወይም ድምፅ ላያሰማም ይችላል። በዚህ ጊዜ ድግምተኛው ወይም ደብተራው መተት ሊሰራበት ያሰበዉን ሰዉ ላብ የያዙ ቁራጭ ጨርቆችን ወይም ፀጉሩን በመቋጠር ይህ ሰዉ እንዲሆን የፈለገዉን አድርግ በማለት ሰይጣኑን ያዘዋል።
#ከዚህ_ዘዴ_የሚከተሉትን_እንገነዘባለን
➊ ሰይጣናት ጨለማ ክፍልን ይመርጣሉ
➋ የአላህ ስም ያልተጠራባቸዉን ጭሳጭሶች ይመገባሉ
➌ በዚህ ዘዴ ዉስጥ ያለዉ በጂኒዎች መማልና እርዳታ መለማመን ግልፅ የሆነ ሽርክ ነዉ
➍ ጂኒዎች ቆሻሻን ይመርጣሉ፡፡ ሰይጣናት ወደ ቆሻሻ ይቀርባሉ
💠 #ሁለተኛዉ_ዘዴ፡- እርድ
ድግምተኛው ጂኒዉ በሚፈለገዉ ዓይነት ልዩ የሆነ ወፍ ወይም ዶሮ ወይም እርግብ ወይም ሌላ እንስሳ ያቀርባል፡፡ (አብዛኛዉን ጊዜ ጥቁር ቀለምን ይመርጣሉ፡፡ ምክንያቱም ጂኖዎች ምርጫቸዉ ጥቁር ስለሆነ ከዚያም የአላህን ስም ሳይጠራ ያርደዋል፡፡ አልፎ አልፎ በታረደዉ ደም የታመመዉን ሰዉ አካል ሊቀቡም፣ ላይቀቡም ይችላሉ። የታረደዉ እንሰሳ የጂኒዎች መኖሪያዎች ናቸዉ በሚባሉ በፍርስራሽ ቦታዎች ጉድጓዶች ወይም ሰዉ በማይደርስባቸዉ አካባቢዎች የአላህን (ሱ.ወ) ስም ሳይጠራ ይወረዉረዋል፡፡ ከወረወረ በኋላ ወደ ቤቱ በመመለስ የክህደት ድግምቶችን ያነበንባሉ፡፡ ከዚያም እንዲሆንለት የሚፈልገዉን ጂኒዉ አንዲያደርግለት ይነግረዋል ወይም ያዘዋል፡፡
በዚህ ዘዴ ዉስጥ ሁለት ዓይነት ሽርኮችን እናያለን፡፡ እነርሱም፡-
➊ ለጂኒ ማረድ☞ ከአላህ በቀር ለሌላ ማረድ ሀራም በመሆኑ ከሀራምም አልፎ እንዲያዉም ሽርክ ነዉ፡፡ እንኳንስ ለጂኒ ማረድ ለጂኒ የታረደን መብላት ሀራም (ክልክል) ነዉ፡፡ የሚያሳዝነዉ ነገር በተለያዩ ጊዜያትና ቦታዎች መሀይማን እንዲህ ያለ ፀያፍ ድርጊት መስራታቸዉ ነዉ፡:
➋ እርዱን ከፈፀመ በኋላ ጠንቋዩ ወደ ቤቱ ተመልሶ የሚላቸዉ ድግምቶች ግልፅ ሽርክ እና ክህደት ያዘሉ ናቸዉ፡፡ ይህንንም ኢብን ተይሚያህ ገልፀዉታል፡፡
💠 #ሶስተኛዉ_ዘዴ፡ ወራዳዉ ዘዴ
ይህ ዘዴ ወራዳ ዘዴ በሚል መጠሪያ በድግምተኛው ዘንድ ይታወቃል፡፡ በዚህ ዘዴ የሚጠቀም ድግምተኛ የሚያገለግሉትና ትዕዛዛቱን የሚፈፅሙለት እጅግ ብዙ ሰይጣናት ይኖሩታል፡፡ ምክንያቱም በክህደቱና በሽርኩ ወደር ስለማይገኝለት ነዉ፡፡ ይህ ዘዴ ባጭሩ እንደሚከተለዉ ነዉ፡፡
📌📌📌 ድግምተኛው ወይ ጠንቋዩ (የማያቋርጥ የአላህ እርግማን ይዉረድበትና) ቁርአንን በእግሮቹ በመጫማት ሽንት ቤት ገብቶ የክህደት ድግምቶችን ያነበንባል፡፡ አነብንቦ ሲያበቃ አንድ ክፍል ዉስጥ በመቀመጥ የሚፈልገዉን እንዲያደርጉለት ሰይጣናትን ያዛቸዋል፡ ሰይጣናትም ትዕዛዙን ለመፈፀም ይጣደፋሉ ምክንያቱም በአላህ በመካድ ወደር የለሽ በመሆን ባልእንጀራቸዉ ሆኗልና፡፡ ይህን በማድረጉ ከፍተኛ ክስረት ዉስጥ ወድቋል። ይህን ወራዳ ዘዴ የሚጠቀም ድግምተኛ ወይም ደብተራ ከላይ ካየናቸዉ ድርጊቶች በተጨማሪ
>> ከባለ ትዳሮች ጋር ወሲብ ማድረግ፣
>> ግብረ ሰዶም መፈጸም፤
>> እስልምናን መሳደብ እና የመሳሰሉትን በርካታ ተደራራቢ ሀጢያቶችንና ወንጀሎችን እንዲፈፅም ሰይጣናት ሊተባበሩት ዘንድ እንደ ቅድመ ሁኔታ ያስቀምጡበታል።
💠 #አራተኛዉ_ዘዴ፦ ቆሻሻ
ይህን ዘዴ የሚጠቀም ድግምተኛ የአላህን ቃል በወር አበባ ደም ወይም በማንኛዉም ቆሻሻ ነገር ይፅፋል፡፡ እንደዚህ አድርጎ በመፃፉ ሰይጣን ይገለጥለታል፡፡ ከዚያም የሚፈልገዉን እንዲፈፅምለት ያዘዋል። በዚህ ዘዴ ዉስጥ ያለዉ ክህደት ለማንም ሰዉ የተሸሸገ አይደለም። አንዲትን የአላህን ቃል ማቃለል ክህደት (ኩፍር) ነዉ አይደለም በቆሻሻ መፃፍ፡፡ ከእንዲህ ዓይነቱ እርክስት አላህ እንዲጠብቀን እንማፀናለን፡፡
♦ ጌታችን አላህ ሆይ! ልቦናችንን በኢማን አፅናልን ሞታችንን በእስልምና አድርግለን ከሞትም በኋላ መልካም ከሰሩት ጋር ሰብስበን።
💠 #አምስተኛ_ዘዴ፡- ማዞር
ድግምተኛው ጠንቋዩ (የአላህ እርግማን ይዝነብበት) ከቁርአን አንድ አንቀፅ በመዉሰድ የፊቱን ኋላ የኋላዉን ፊት አድርጎ ገልብጦ እና ፊደላቱን ነጣጥሎ ይፅፋል። በዚህም ምክንያት ሰይጣን ይገለጥለታል፡፡ ከዚያም ሰይጣኑን የሚፈልገዉን እንዲፈፅምለት ያዘዋል፡፡ ይህ ዘዴ እንደሚታወቀዉ ግልፅ ክህደት ነዉ።
💠 #ስድስተኛ_ዘዴ፦ ኮኮብ ቆጠራ
ይህ ዘዴ በሌላ አጠራር መጠባበቅ _ ይባላል፡፡ ምክንያቱም ድግምተኞች አንድ የተለየ ኮኮብ እስኪወጣ ስለሚጠባበቁ : ነጢር የሚጠበቀዉ ኮከብ ሲወጣ ድግምተኛዉ የድግምት ንባባትን እያማተበ ኮከቡን ይማፀናል። በተጨማሪም ልዩ የሆነ በሽርክና በክህደት የተሞላ ድግምት ይደግማል። ከዚያም ልዩ የሆነ እንቅስቃሴ ያደርጋል፡፡ ይህንንም የሚያደርገዉ ድግምተኞች እንዲህ ዓይነት እንቅስቃሴ ስናደርግ የኮከቡ መንፈስ ይወርድልናል ብለዉ ስለሚያምኑ ነዉ፡፡ ነገር ግን ድግምተኛዉ አያዉቅም እንጂ ኮኮቡን እያመለከዉ ነዉ" በዚህ ግዜ ሰይጣናት የድግምተኛውን ጉዳይ ይፈፅማሉ ለድግምተኛው ኮከቡ ያደረገለት ይመስለዋል እንጂ ኮከቡ የሚያዉቀዉ ነገር የለም፡፡
በዚህ ዓይነት ዘዴ የተሰራ ድግምት ኮከቡ ተመልሶ ካልወጣ በቀር ሊፈታ አይችልም ይላሉ ድግምተኞች፤ ነገር ግን በቁርአን ወዲያዉኑ ይፈታል፡፡ አንዳንድ ኮከቦች ደግሞ በአመት አንድ ግዜ ብቻ ስለሚወጡ ድግምተኞች የነዚህን ኮከቦች መዉጣት በመጠባበቅ የተሰራ ድግምት ካለ ለመፍታት ጥረት ያደርጋሉ። 👇👇
እያለቀስክም ቢሆን የበሩ መከፈት ቢዘገይ እንኳን አትዘን፡፡ ዋናው ሳትሰለች በሩ ላይ ቆመህ መገኘትህ ነው፡፡ በሀይልና በተደጋጋሚ የተንኳኳ በር መከፈቱ ግድ ነው፡፡ እስልምናህን የምትወድ ከሆነ አላህ ይከፍትልሀልና ተስፋ አትቁረጥ፡፡ አላህ ይሰጥሀል፡፡ ውስጥህ ያለውንም ተስፋ ያድሳል፡፡ አል-ፈታሕ ብለህ በስሙ ጥራው፡፡ በርግጠኝነት ይከፍትልሀል፡፡
🟡 ነብዩ ሰዐወ በለሊት ተነስቶ ሚስቱንም ቀስቅሶ ሁለት ረከአ ለሰገዱት አላህ ይዘንላቸዉ ብለዋል፡፡
እናም ተኝቶ ድምፃችን ይሰማ እያሉ ከማንኮራፋት ተነስቶ ሚስትህ ጋር መስገድ አብራችሁ ዱአ ማድረግ ለዚህ ቅጥ ላጣ ዘመን መፍትሄ ነዉ፡፡
ዱንያ የደስታ ምንጭ አይደለችም ይሄን ማወቅ አለብን አላህ የትንኝ ክንፍ ለኔ ቦታ የላትም ብሎ እኛ ደስተኛ እንሆናለን ብለን ራሳችንን አናሳምን
አል ኢማም አር ራዚ ቆንጆ ልብስ መልበስ ይወዱ ነበር፡፡ አንድ ቀን ከመስጅድ ወጭ እያሉ አንድ ሙስሊም ያልሆነ ሰው ጋር ተገናኙ፡፡ ሰውዬው የተበጣጠሰ ልብስ ነበር የለበሰው፡፡ ለኢማም አርራዚ እንዲህ አላቸው የናንተ ነብይ ይህች ዓለም ለአማኞች እስር ቤት ለከሐዲዎች ጀነት ናት፡፡› ይላል፡፡ ይህን የመሰለ ፀጋ ውስጥ እያለህ ከየትኛው እስር ቤት ውስጥ ነህ? እኔስ በየትኛው ጀነት ውስጥ ነኝ? አላቸው፡፡ ኢማም እርራዚም እኔ አሁን ያለሁበት ሁኔታ በጀነት ውስጥ ካለው ድሎትና ፀጋ አንፃር እስር ቤት ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) በጀሃነም ውስጥ ለከሐዲያን ካዘጋጀው ቅጣት ደግሞ አንተ አሁን ያለህበት የችግር ኑሮ ጀነት ነው፡፡ አለው፡፡ ሰውዬውም ጥቂት ካስተነተነ በኋላ በርግጥም የናንተ መልእከተኛ የተናገረው እውነት ነው፡፡› አለና ሰለመ፡፡
ይህች ዓለም እስር ቤት መሆኗ፣ አላህ (ሱወ) ጀነትን ለኛ ማዘጋጀቱ፣ አኺራ በላጭና ዘላለማዊ መሆኗ ... ይህ ሁሉ አላህ (ሱ.ወ) እኛን ሊያስደስተን የፈለገ መሆኑ ያመላክተናል፡፡ _ ስለሆነም ጀነት ሊያስገባን ብሎ ይከታተለናል፣ ይጠብቀናል፣ በችግሮችም ይፈትነናል፡፡
🟡 በተጨማሪም ሲህርም ባይሆን ማንኛዉም ህመም ሲያጋጥመን ሀኪም ቤት ልሂድ ከማለት መጀመሪያ አላህ እንዲያሽረን እንማፀን
ዑሥማን ኢብን ጦለሐ የሚባል ሰሐባ ነብዩ (ሰዐወ) ዘንድ መጣና የአላህ መልእተኛ ሆይ!!! ሰውነቴ ውስጥ ህመም ይሰማኛል፡፡ አላቸው፡፡ ነብዩም (ሰዐወ) በአላህ (ሱ.ወ) መካከል ያለው ግንኙነት የጠበቀ እንዲሆን ፈለጉ፡፡ እናም በሚያምህ ቦታ ላይ እጅህን አኑርና ሶስት ጊዜ ቢስሚላህ በል፡፡ ከዚያም ሰባት
ጊዜ አዑዙ ቢላሂ ወቁድረቲሂ ሚን ሸር ማ አጂዱ ወኡሓዚሩ፡፡" በል አሉት፡፡ ሰሐባውም እሳቸው እንዳሉኝ አደረኩኝ፡፡ ህመሙም ለቀቀኝ፡፡ በአላህ እምላለሁ ከዚያ ቀን ጀምሮ ለቤተሰቤና ለማውቀው ሰው ሁሉ ከማስተማር ወደኋላ አላልኩም፡፡› ብሏል፡፡
ታማሚም አስታማሚም አላህ ፅናቱን ጥንካሬዉን ይስጠን...እኛም ለዲናችን ጠቃሚ ለሰዉ የምንተርፍ ያድርገን
ለሰዉ ክፋት መጥፎ የምናስብ ሰዎች እባካችሁ ቶብቱ በሰዉ ደስታ ለምን እንደኛ ይቸገር እንላለን??
ክፉዉን ማዳመጥ ማየት የክፋት መጀመሪያ ነዉ
ክፋት በሰዉ ባህሪ ዉስጥ አብሮ የተፈጠረ ሳይሆን ክፋትን ማስወገድ ባለመቻሉና ዉጫዊ ተፅእኖዉን መቋቋም ስላቃተዉ የመጣበት ነገር ነዉ፡፡
ህይወት ወጪዉን የማትሸፍን ንግድ ነችና በእሷ ስኬትን በሀራም በጠንቋይ በሳሂር እገዛ እጨብጣለሁ ብለህ አትሰብ እናም በሰዉ ስቃይ ሀዘን ለቅሶ መደሰት ምን የሚሉት ህሊና ነዉ ?? አላሁ የስቱርና አላህ ከመጥፎ ባህሪ አመል ይጠብቀን
🔰 አላህ ሆይ ከደጋሚዎች ከሳሂሮች ተንኮል ጠብቀን...ምቀኛን ቀናተኛን ከጎናችን አርቅልን..ስቀዉ ከሚጎዱ የቅርብ ሰዎች ጠብቀን ያረብ...
🔰 ሲህር የተየደረገብን የታመምን ወይ ሲህር ተደርጎብን ሳናቅ ብዙ አመታት ፈጅቶ ከረፈደ ያወቅን አልሀምዱሊላህ ከረፈደም ማወቃቸዉን ...እንደ አጋጣሚ ያለወቅን ካለ አላህ አሳዉቀን ያረብ
🔰 ጠንቋይ ቤት ለሚሄዱትም ሂድያ ስጣቸዉ...
🔰 ኢላሂ ለዲነል ኢስላም የምንጠቅም ባንጠቅም እንኳኝ በኛ እንዳይሰደብ የምንሆን ጀሊሉ ያድረገን
✈ አንዳንዴ በማህበራዊ ሚዲያ ሙስሊሞች አለቅጥ ወንጀል ፈሳድ ላይ ተጥለቅልቀዉ የሌላ ሀይማኖት ወይም አንዳንድ ኢስላም ሲደፈር የሚቆጫቸዉ እህት ወንድሞች ሙስሊም አይደለሽ እንዴ ብለዉ ሰመከሩ
የማምለጫ ዘዴ አለች...እኔ ሙስሊም ነኝ ችግር ካለብኝ እኔን እንጂ እስልምናየን አትናገሩ ብለዉ ኮስተር ሲሉ ይታያሉ ይገርመኛል እነሱ ኢስላምን እያሰደቡ እስላምን አትሳደቡ እያሉ ቀጭን ኢስላምን አትንኩብኝ እያሉ የዉሸት ተስፋ ይዘራሉ...ተስፋ ጥሩ ቁርስ ቢሆንም መጥፎ እራት መሆኑን አንዘንጋ
እናም በሚዲያ ላይ ሙስሊም ሁነን ጅልባብም ጀለብያም ለበስንም አለበስንም በኛ ኢስላም ሊሰደብ ሊመዘን አይገባም እኛ በኢስላም ሀይማኖት ማዕቀፍ ዉስጥ ነን አማኝ ነን ካልን ሙስሊም ተብለናል ...አማኝ ሙስሊም ባንሆን እንኳ ህሊናችን የሚሰራ ሰዉ እንሁን... አረ ሰዉ ሰዉ እንሁን እባካችሁ...ኢስላም በኔም በአንተም በእኛም በእናንተም እየተሰደበ እየተዋረደ ነዉ...አላህ ዲነል ኢስላምን እኔ ነኝ የምጠብቀዉ ስላለ ነዉ እንጂ በእኛ ስራ ቢሆን አፍርሰን ትቢያ አመድ አርገነዉ ነበር
🔰 ኢንሻ አላህ እያሉ ከመሾለክ ዝም ብሎ በምሉላስ አሏሁ አክበር እያሉ ሙስሊምን ከመጉዳት ያለችንን ትንሽየ ኢማን አላህ ያድስልን፡፡አላህ ጠንካራ የማይበገር ኢማን ይስጠን
📚📚📚 #ዉድ የተከበራችሁ አንባባዎች በ➊➎ part ስለሲህር ድግምት አይነጥላ ..ስለትዳር ስለስንፈተ ወሲብ በሁሉም ባሉት ቸግሮች ትኩረት አድርጌ አቅሪቢያሁ
የሰዉ ልጅ ነኝ እሳሳታለሁ ከኔ በላይ እዉቀት ያላችሁ እዚህ ቦታ ተሳስተሀል በሉኝ edit ማድረግ እችላለሁ edit አሁኑ ላድርግ ከወር ቡሀላ edit ማድረግ ስለማይቻል ...ብዙ ሰዉ እያነበበዉ ሼር እያደረገዉ ስለሆነ ...ግን የተዘጋጀዉ ከመፅሀፍ እና ከሀዲስ ከሚያቁ ጠይቄ ስለሆነ እስከ አሁን በአስተያየት መስጫ አስተካክል የተባልኩት የለኝም፡፡ በአስተያየት ስሰጡ ሳነባቸዉ በሲህር ተለክፈዉ የነበሩ እና በይፋ ያደረገባቸዉ ሰዉ እየነገረን ነዉ ያሉኝ አሉ ፡፡
ወደ 5 የሚሆኑ አስተያየቶች እኔን ካላገባሽ መቼም አታገቢ ብለዉ ከወንድየዉ ተነግሯቸዉ እንዳላገቡ በተጨማሪ አንዷ አግብታ ኒካሁ ታስሮ ሳይቆዩ እንደተፋታች የነገረችኝ አለች ...ሌሎቹ ይሄን ፁሁፍ ሲያነቡ ራሳቸዉን ፈትሸዉ ሩቃ ሊጀምሩ እንደሆነ አሳዉቀዉኛል...እናም በተለይ በትዳር ላይ የተተበተበ ጉድ ከባድ ነዉ ራሳችንን ማኔጅ ብናደርግ ጥሩ ነዉ
ለ15 ቀን በ15 ክፍል የቀረበዉን ፁሁፍ ሀምሌ 1 ጀምረን ሀምሌ 15 2015 ጨርሰናል ፡፡ባለመሰልቸት ባለመታከት አንብባችሁ ስለጨረሳችሁ ጀዛችሁን አላህ ይክፈላችሁ ለምን እኔም እናንተ ባነበባችሁበት ራሳችሁን በፈተሻችሁበት አጅር ስለማገኝ እናንተም ባነበበባችሁት እኔም ባዘጋጀሁት ተጠቃሚ ያድርገን፡፡
ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሁ ወበረካትሁ
#ተ.......... #ፈ.......... #ፀ........... #መ
⚡️⚡️⚡️አንብባችሁ ምን ተረዳችሁ?
ምን አስተያየት አላችሁ?
👇👇👇እዚህ ላይ ይፃፉ
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
ከፁሀፉ ያልገባችሁ ያልተዋጠላችሁ ካለ👇👇
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
✍ አሚር ሰይድ
✨✨✨ #የመጨረሻዉ ክፍል✨✨✨
🔰 #ራስን_በራስ_ማከም_ከዛም_ለሌላ_መትረፍ
🌙🌙
ከpart ➊➍ ቀጥታ የቀጠለ.....
ከዛር ዉጭ ያለን ሩቃን ለማድረግ ባንፈራ ጥሩ ነዉ ብቻ መጀመሪያ አላህን ይዘን ነይተን ሀስበነሏህ ብለህ መጀመር ነዉ ፡፡
📚📚 ከተሞክሮ እስኪ ጀባ ልበላችሁ ወላሂ ይሄን የምነግራችሁ ጀሊሉ ያቅብኛል ለጉራ አይደለም ባልፅፈዉ ደስ ይለኛል ግን እንድትደፍሩ እንዳትፈሩ ለመጠቆም ነዉ፡፡ እኔ የዲን እዉቀት የለኝም በማንበብ እና የሰሙትን በመተግበር ላይ አተከለራለሁ ...እና ማንኛዉም ነገር አንድ እርምጃ ያስፈልገዋል የብዙ ሰዉ ችግር ሶስት አራት እርምጃ ይራመዳል ሳያጣራ ከዛ ግብ ሳይመታ ይመለሳል ...እኔ የማምነዉ አንድ እርምጃ ካልሆነ ወደፊት ሳይሄዱ መለስ እርምጃዉ የተሳካ ከሆነ ቀኝን እግርህን ካስቀደሙ ግራህን አስተከትለህ ሁለት እርምጃ ላይ ትቆማለህ ከዛ ነገሮችን እያገናዘቡ መሄድ ነዉ...
#ከተሞክሮ
✍🏼 አንዲት ክርስቲያን ጎረቤታችን የ7 አመት ልጇ አላት ለሊት አይተኛ ቀን ታዝሎ ይዉላል ስራዉ ማልቀስ ምግብ የሚበላዉ ትንሽ ለዛዉም ያስመልሰዋል እንደ እድሜ እኩየቹ አይጫወትም ብቸኛ ነዉ ... ይሄ ህመም የጀመረዉ ገና በ4 አመቱ ነዉ 3 አመት ያህል ተሰቃይቷል ያልሄደችበት ፀበል የለም ሌላም ሀገር ሂዳለች ፡፡በፀበል መፍትሄ ሲያጡ ሌላ ሀገር ጠንቋይ ቤት ሄዱ አረንጓዴ እስስት አምጡ ብሏቸዉ አረንጓዴ እስስት ለማግኘት አራት ወር ፈጀ በግድ ተገኘ ጠንቋዩ በአረንጓዴ እስስት ሌላም ጨምሮ አንገት ላይ የሚንጠለጠል ሰጠው ምንም ለዉጥ የለም...ከ3አመት ስቃይ ቡሀላ ሲጨንቃት ቁርአን ቅሩልኝ አለች...
#አላህ_ሆይ እንዳታስፍረኝ የቁርአንን ሀይልን ለነዚህ ክርስቲያኖች አሳያቸዉ ብየ ዱአ አደረኩ ...ከዛማ በስፒከር ሩቃ ከፈትኩ ሁለት ሁነን በቻልነዉ ቀራን ወላሂ 45 ደቂቃ ባልሞላ እንቅልፍ ወስዶት ላብ በላብ ሆነ ቁርአኑን ስንጨርስ ጩኾ ተነሳ በዛዉ ለቀቀዉ ከዛ ቀን ቡሀላ ታሞ አያቅም ይሄዉ እንቅልፍም ይወስደዋል እናቱም አታዝለዉ ምግብም መመገብ ጀመረ የሚያስመልሰዉ ቀረለት ትምህርትም ተመዘገበ አልሀምዱሊላህ....እናት አባቱ አጥባቂ ክርስቲያን ነበሩ አሁን ግን ከምነግራችሁ በላይ ለሙስሊም ያለቸዉ አመለካከት ደስ የሚል ነዉ አላህ ሂድያ ይስጣቸዉ የቁርአንን ሀይል ቤተሰብ ዘመድ ልጁን ተሽሎ ሲያዩት ይገርማቸዉ ይደንቃቸዉ ይዟል፡፡
✍🏼 አክስቴ ክርስቲያን ነች ታማ ፀበል ብትመላለስ ምን ብትል ያልተሻላትን በ30 ደቂቃ ሩቃ በመቅራት በአላህ ፍቃድ እንዲሻላት አድርጊያለሁ
✍🏼 ከነዚህ ዉጭ 3 ሰዎች ጎረቤት ምናምን ሲታመሙ በአላህ እገዛ ተሳክቶሎኛል እናም እንደዚህ ልላችሁ ያሰብኩት ሩቃ ማድረግ ከባድ አይደለም መጀመሪያ ጀሊሉን አላህየን ከያዙ ምንም የሚያስቸግር የለም እናም እህት ወንድምህን እናት አባትህን ...እናት አባትሽን እህት ወንድምሽን ለሌላ ባዳ አሳልፋችሁ አትስጡ
----- ጂን ሲናገር ሊዋሽም ላይዋሽም ስለሚቾል አንዳንዴ ሲናገር እዉነት ነዉ ብለን ከተናገረዉ ሰዉ ጋር ሂደን መጣላት አያስፈልግም፡፡
🌟 ከዚህ ርዕሱ ጋር ባይሄድም በፊት ክፍል ላይ ዘንግቼ ሳላስገባ የቀሁት ጉዳይ አሁን ያለቦታዉም ቢሆን ስለዚህ ጉዳይ ትንሽ ልበል...
በቅርብ አመታት በተለያየ ማህበራዊ ሚዲያ ወንድና ሴት ዚና ሲሰሩ ወይ በባል ወይ በሚስቱ ላይ ሲማግጥ ተጣብቀዉ እያየን ነዉ፡፡ ይሄ ባልየዉ ሚስቱን ካላመናት ወይም ሚስት ባሏን ካላመነችዉ ጠንቋዮች ጋር ሂደዉ ሌላ ወንድ ጋር ከተኛች ወይም ሌላ ሴት ጋር ከተኛ እዛዉ እንዲጣበቅ ሰዉ እንዲያዋርደዉ ይሁን ብለዉ አስደግመዉ ሊሆን እንደሚችል አንዘንጋ...ካልሆነም ደግሞ ፈጣሪ እኛን ለማስተማር እነሱን ምሳሌም እያረገ ሊሆን ይችላል፡፡እናም ለትዳራቸዉ ታማኝ ያልሆኑ ሰዎች መጀመሪያ ባለመተማመን ይጋባሉ ከዛ ይሄ ይፈጠራል፡፡
እናም ወይ የአላህ ቁጣ ነዉ ካልሆነ ድግምት ነዉ ...
ግን በተለይ በትዳር ላይ የሚሰሩ ሲህሮች በአሁን ዘመን ላይ በሰፊዉ ተንሰራፍቷል፡፡
⚡️⚡️⚡️ #በጂን_የተያዘ_ወይም_ሲህር_ወይ #በአይነጥላ_የተያዘ_ሰዉ_ወይም_አስታማሚዉ
#ምን_ማድረግ_አለበት⁉️⁉️
ኩን ፈየኩን ...አላህ ኩን ብሎት አላህ ሱወ በሲህር በጂን በአይነጥላ ሊፈትነን ይችላል ፡፡ ዱንያ የፈተና አለም ነች ለአላህ የትንኝ ክንፍ ያህል ቦታ የላትም ላለን ዱንያ ደስታን እናጣጥማለን ማለት አይደለም፡፡ ዱንያ በሀዘን ማቅ የተተበተበች ደስታ እንደመብረቅ ብልጭ ብሎ የሚጠፋበት የኑሮ መድረክ የፈተና መሸጋገሪያ ድልድይ ነች የጀነት መግቢያ የኸይር መሸመቻ የፈተና ማለፊያና መዉደቂያ የቁጥጥር ጣቢያ ነች፡፡
በርዚቃችን ትዳር እንዳናገባ ነገሮች እንዳይሳኩ ወዘተ ሲህር ድግምት ከተደረገብን የአላህ ዉሳኔ ነዉ ፅናት ብርታት ጥንካሬ ያስፈልጋል ፡፡
♻️♻️ አላህ (ሱ.ወ) የወሰነውን ነገር መደው የተቀበሉ ነብዩ ሰዐወ ናቸዉ በሲህር ተሰቃይተዋል.....በተጨማሪ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ኢብራሂም የሚባል ልጅ በተወለደላቸው ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የደስታ ስሜት ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ ተሸክመውት ወደተለያዩ ሰሐቦች ቤት ይዘውት ይሄዳሉ፡፡ ለሰዎችም ልጇን ኢብራሂምን ተመልከቱት፡፡› ይሉ ነበር፡፡ ትንሹ ኢብራሂም አባት ለልጅ በእጅጉ በሚጓጓበት የህፃንነት ዕድሜ ጡት መጣያው አካባቢ ሞተ፡፡ ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) አለቀሱ😢፡፡ እንባ የልብ እዝነት ውጤት ነውና የአላህን ውሳኔ ካለመውደድ አይቆጠርም፡፡ እርሳቸውም ዐይን ያለቅሳል፣ ቀልብ ያዝናል፣ ጌታችን የሚወደውን ነገር እንጂ አንልም፡፡
#ኢብራሂም_ሆይ!!!! ከኛ በመለየትህ አዝነናል፡፡” አሉ፡፡ ከዚያም ወደቤታችው በመግባት ለአላህ (ሱወ) እንዲህ አሉ፡- ‹‹ጥሪህ ሰምተን በደስታ ወዳንተ መጣን፡፡ መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ ነው፡፡ መጥፎ ካንተ አይደለም፡፡” ብለዉ የጌታቸዉን ዉሳኔ ተቀበሉ...
መቼም የሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ ታሪክ ታቃላችሁ
💚በእናታቸዉ ሆድ ውስጥ ሳለ ወላጅ አባቱን በሞት ተነጠቁ
💛ዕድሜያቸዉ ስድስት ሲሞላ ወላጅ እናታቸዉን ቀበሩ።
❤️ በስምንት ዓመታቸዉ በፍቅር ተንከባክበው ያሳደጓቸዉ አያቱን አይቀሬው ሞት ነጠቀው።
💚 እንደ አይን ብሌናቸው የሚሳሱለት በማራኪ ስብዕናው ተረታ የትዳር አጋሩ ለመሆን የበቃችው ውድ ሚስቱ በአንድ ዓመት ውስጥ ተከታትለው ተለዩት።
💛 ከሁለት ዓመታት ዕድሜ በላይ ያልቆዩ ሁለት ወንድ ልጆቹን ሞት ቀጠፋቸው። በህፃናቱ ፈገግታ ደምቆ የነበረው ቤት የሀዘን ጥላ አጠላበት።
❤️ከእርሱ ህልፈት በኋላ በስድስተኛው ወር በሞት ከተከተለችው ተናፋቂ ልጁ በስተቀር ሁሉም ሴቶች ልጆቹ ወደ መጪው ዓለም ተጓዙ።
💚 የአባቱ ጥሪት የነበሩት አጎቱ ተገደሉ። መገደል ብቻ አይደለም የሰው ልጅ ያደርገዋል ተብሎ የማይታሰብ ጭራቃዊ ተግባር በአካላቸው ላይ ተፈፀመ። ሂንድ አስክሬኑን አስቀድዳ ጉበቱን በላችው።👇👇👇
ሀስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል ብለህ ጀምር እርግጠኛ ሁን አላህ አያሳፍርህም ፡፡ ችግሩ የኛ ኢማን ጥንካሬ መድከምና ተስፋ መቁረጥ ነዉ....ንብ አንድ ኪሎ ማር ለመስራት 400 km ትንቀሳቀሳለች ተስፋ አትቁርጥም ታሳካለች ታዳ አንቺ አንተ እናንተ ምን የሚያስፈራ አለ???ምን ተስፋ የሚያስቆርጥ አለ??
ለምን እህትህን ለአጂ ነብይ ወንድ አሳልፈህ ትሰጣለህ??? ለምን እኔ አልችልም ትላለህ/ትያለሽ⁉️
ሀስቡነሏህ ብለህ መጀመር አቅቶህ ነዉ ወይስ አላህ በኔ ተማመን እያለህ በአሏህ መተማመን ፈርተህ ነዉ⁉️
የጀአለሁ መኽረጃ የወሙጫ መንገድ አዘጋጃለሁ ያለህ ጀሊሉን እንዴት መተማመን አቃተህ⁉️
ሀስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል አላህን ይዘህ ሁሉም ነገር ቀላል ነዉ....አላህን ይዘን መፍራት አያስፈልግም
♻️♻️ ብዙ ሩቃ ቤቶች ሩቃን ለቢዚነስ አርገዉታል ከ3,000 እስከ 20,000 ከዛም በላይ እየጠየቁ እኔ መጀመሪያ ላይ ብር ላይ ፎከስ የሚያደርጉ ሰዎች ንያቸዉ ብር እንጂ ከአላህ አጅር እናገኛለን ብለዉ ስለማይሆን እንደነዚህ ሩቃ ቦታዎች እንጃ ብቻ ምን እንደምል አላቅም...በሀዲስ ይበቃል አይበቃም ፊርቃ ስላለዉ የሚሻለዉ ወላሁ አዕለም ግን ብዙም አይዋጡልኝ
የሚሻለዉ በራስ ኮንፊደስ ተወከልቱ አለሏህ ብሎ መጀመር ነዉ አሏህ ቁርአኑን መፍትሄዉን ነግሮናል ነብዩ ሰዐወ አስተምረዉናል እናም በራሳችን መታገሉ ኸይር ነዉ፡፡
ማወቅ ያለብን ጂን በደም ስር በመርፌ ቀዳዳ መሹለክ የሚችል ዉሸታም ሰላቢ የማይጨበጥ ነዉ ፡፡ #ግን_ቁርአን_በሚቀራበት_ጊዜ_መላኢካ_ከታማሚዉ_ሰዉነት_እንዳይወጣ_ጠፍሮ_ይይዘዋል፡፡
ከዛ ቁርአን በሚቀራበት ጊዜ ለእሱ ቁርአኑ ሰይፍ ነዉ የሚሆንበት ይቆራርጠዋል ...ወላሂ ቶሎ ብለዉ ነዉ የሚወጡት ለምን ካልወጣም ሊገለዉ ይችላል ፡፡
🔰🔰ቁርአን ለሰዉ ልጅም ለጂንም ካመንበት መድሀኒት እርጋታ ከፈጣሪ ጋር ያለን ግንኙነት መጨመሪያ ነዉ....ጂኖች ያቃሉ ግን ተገደዉ ወደ ሰዉ ገላ ስለሚገቡ ለመዉጣት የላካቸዉ ሸይጧን ወይም ትልቁ ጂን ወይ የጎሳ አለቃ ጂኑ ቅጣቱ ከባድ ስለሚሆንባቸዉ ላለመዉጣት ይታገላሉ ግን የሚያሸንፈዉ ቁርአን ነዉ ተቃጥለዉ ተንገብግበዉ አይናቸዉ ጠፍቶ እግራቸዉ ተቆርጦ ድረስ ይለቃሉ ሲናገሩ ከሰማችሁ አይኔ ጠፋ እግሬ እጄ ተቆረጠ ይላሉ ቁርአን ሀይል ነዉ ...አልሀምዱሊላህ ጀሊሉ ለሰጠን መድሀኒት ሀይል ብርታት ቁርአን
#ቁርአን 77430 ቃላት እና 430740 ፊደላት አለዉ አሏህ ፈጣሪያችን በቁርአን በአንድ ፊደል 10 ሀሰና አለዉ ብሎናል እናም 430740 ብናሰላዉ
🔶 በወር ሶስቴ ብናከትም 12,922,200 ሀሰና ሲኖረዉ
🔶 በወር ሁለቴ ብናከትም 8,614,800 ሀሰና እናገኛለን
🔶 በወር አንዴ ብናከትም 4,307,400 ሀሰና እናገኛለን
ቁርኣን አጠቃላይ ገፁ 604 ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር በመጠኑ በግማሽ ያንሳል። ነገርግን ላለፉት 1,400 ዓመታት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሙፈሲሮች ማብራሪያውን ቢፅፉትም ፈፅሞ ሊጨርሱት አልቻሉም።
ለአብነት
♦️ ቁርጢቢ ➨ 21 ቅፅ 👉 5509 ገፅ
♦️ ኢብን ከሲር ➨ 10 ቅፅ 👉 6608 ገፅ
♦️ ጠበሪይ ➨ 12 ቅፅ 👉 3000 ገፅ
♦️ በገዊ ➨ 4 ቅፅ 👉 1487 ገፅ
♦️ ጀላለይን ➨ 1 ቅፅ 👉 1378 ገፅ
♦️ ሰዕዲ ➨ 10 ቅፅ 👉 6600 ገፅ
♦️ ቁጥብ ➨ 30 ቅፅ 👉 4018 ገፅ
ይህ ሁሉ ተፍሲር ለ604 ገፅ መጽሐፍ የተፃፈ ቢሆንም ሁሉም የሚችሉትን ያህል አብራሩት እንጅ አንዳቸውም አሟልተው ፅፈው አልጨረሱትም።
ከዚህ በተጨማሪ ቁርኣን በታሪክ፣ በህክምና፣ በጂኦግራፊ፣ በጠፈር ምርምርና በተለያዩ ዝርፎች የተጠና ሲሆን የተወሰነውን ቢያረጋግጡትም ገና ብዙ ያልተደረሱባቸው ምርምሮችን ይዟል።
ይህ ለሚያስተነትን ሰው በእርግጥ ተዓምር ነው።
«ይህ ቁርአን አንቀፆቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው። ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ የተወረደ ነው።»
(ሑድ 1)
እናም እኛ እንደ ቀልድ የያዝነዉ የአላህ ቃል ቁርአን ማስተንተን አልቻልንም እንጂ ሀይላችን ቅዋችን ከህመም መሻሪያችን ነዉ እናም ሀስቡነሏህ ወኒዕመል ወኪል ብለን እንጀምር
⚠️⚠️⚠️ ማስጠንቀቂያ
በፊት ለጅን የሚገብሩ በግ ፍየል ዶሮ በሬ ላም ወዘተ የሚያርዱ.... የሚገበረዉ ለብዙ ጃሂል ጂን ስለሆነ መጀመሪያ ማስቶበት ወደ አላህ እንዲመለሱ ማድረግ አለብን፡፡ ማድማቱን ማረዱን ሲያቆሙ ሀይለኛ ህመም ጂኑ ይልካል ሀኪም ቤት ሲሄዱ ጂኑ አዉቆ እንደ ካንሰር ኩላሊት ምናምን ያስብላል
የዛን ጊዜ ካንሰር ኩላሊት ደም ግፊት ምናምን ከተባለ አደራ መድሀኒት አይጀሞሩ የካንሰርም በጨረር የሚሰራ አለ ባይሰሩ ጥሩ ነዉ ለምን ጅኑ ደም ሲቆምበት እንዲሞቱ ይፈልግና ወደ ልጅ ወይ ልጅ ልጅ ይተላለፋል...የዚህ ጊዜ ጥሩ ሩቃ የሚቀራ ተፈልጎ ማስለቀቅ ነዉ መፍትሄው፡፡ግን ይሄን ጂን ለማስለቀቅ ቢያንስ 2ወር ሊፈጅ ይችላል፡፡ ነጬ በላ/ጥቁር በላ/ራሄሎ/አንበሴ/ወንዘኛዉ/ወዘተ ለጂን በሚያርዱበት ጊዜ ያለማካበድ ከ30 በላይ የሚሆኑ ናቸዉ የሚገበርላቸዉ እናም ማረድ ሲያቆሙ ያሁሉ ነዉ ቂም ይዞ እስከ ሞት የሚደርሽ ህመም ካንሰር ደም ግፊት የሚያስብሉት ...ግን ለመሻር እንደ ታማሜዉ ቀልብ ይወሰናል፡፡ ትክክለኛ ተዉበት ከሆነ 3ቀን ለራሱ በቂ ነዉ፡፡
ነገር ግን አደራ አደራ!!! ሳይቶብቱ ሩቃ እንዳይጀምሩ ለምን ዋናዉ ቀልብ ነዉ ቀልባቸዉ ማድማት ለጂን ማረድ ከሆነ ሩቃዉ በጣጣም አድካሚ ነዉ የሚሆነዉ ካልቶበቱ ሰዉነታቸዉን በጣም የሚያስጠላ ሽታ ሊሸቱ ይችላሉ፡፡ እናም ማስቶበቱ ላይ ትኩረት ማድረጉ ነዉ ...
አንዲት ሴትየ ሲታመሙ ካንሰር ተብለዉ ልጆቻቸዉ ቁርአን በተከታታይ ቀን ሲያስቀሩ የዛር ጂኖቹ ይለቃሉ መልሰዉ ከሁለት ከሶስት ቀን ቡሀላ ይመለሳሉ ከዛ ለምን ትመለሳላችሁ⁉️ብሎ ሲጠየቅ
ወላሂ እኛ እንወጣለን መጀመሪያ እሷን አስቶብታት ስንወጣ መልሳ እየጠራችን ተቸገርን ለምን እሷን ሳታስቶብት በቁርአን ታቃጥለናለህ❓❓ብሎ ነበር የመለሰዉ ጂኑ
🟢 አንዷ እናታችን በፊት ለጂን ያርዱ ነበር ሁለት ወር ያህል ታመዉ በአላህ ፍቃድ በሩቃ ጅኖቹ ለቀቁ.,,ሴትየዋ ግን አልሀምዱሊላህ በአላህ ቃል ተሻለኝ አላሉም....እኔን ያመመኝ እኮ ባለማድማቴ ነዉ የሚደማበት ቦታ ልሂድ ብለዉ ሲሄዱ የአሏህ ስራ የሚሄዱበት መኪና ሌላ መኪና ጋር ተጋጭቶ ከተሳፋሪዉ ሌሎቹ ሲተርፉ እሳቸዉ ግን ሞቱ😔😔 ኢናሊላህ ወኢኒ ኢለይሂ ራጂኡን አሟሟታቸዉ አላማረም....አላህ የመቶበቻ ጊዜ ሰጥቷቸዉ አልተጠቀሙበትም
ትክክለኛ ተዉበት አድርገዉ ማድማቱን ሲያቆሙ ህመሙ ቁስለቱና ጂኑ ደማቸዉን ስለሚመጣቸዉ ደማቸዉ ይወርዳል ደም ግፊት ወይም ደም ብዛት ይባላሉ፡፡ በተጨማሪም የማህፀን ካንሰር ነዉ የመባል ቻንሱ ሰፊ ነዉ..ሰዉነታቸዉ ከበፊቱ በበለጠ መወፈር ወይም መክሳት ...ሆዳቸዉ እጃቸዉ አካባቢ ለብቻዉ ማበጥ ምልክት ያሳያል
⚠️ የምናቃቸዉ ደም የሚያደሙ ለጅን የሚገብሩ እናት አባቶች ካሉን በተጨማሪ አያቶቻችን ካሉ ብዙ የዲነል ኢስላም እዉቀት ስለሌላቸዉ በህይወት ካሉ ይሄን ጊዜ እንዲቶቡ ማድረጉ ኸይር ጥሩ ነዉ ካልሆነ አሟሟታቸዉ እንደማያምር እወቁ ካንሰር ምናምን ሆነ ተብሎ ነዉ ህይወታቸዉ የሚያልፈዉ፡፡
ወደ ልጅ ወይ ወደ ልጅ ልጅ ይተላለፋል
#የመጨረሻዉ_ክፍል_ይቀጥላል.....
4any cmt 🔽
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
ከእነሱ አንዳንድ የምሰማዉም አለ....እስኪ በመጀመሪያ የራሳችንን እንወቅ ሙስሊም መስለዉ የሚሸዉዱት ጥንቃቄ እናድርግ የሌላዉ ይደርሳል...ብቻ በፀበል
ይለቀናል ባላችሁ ሂዳችሁ የብስ ህመም ጨምራችሁ እንዳትመጡ ....
🌀 እነሸህ ተብየ ጫት ቅመዉ ወይ በዛር የሚያስለቅቁ ይሄ በቀላል ቋንቋ 90% እርግጠኛ ሁኑ ለጅን ይገብራሉ ትልቁ ጉልበተኛዉ ጂን ለትንሹ ቀላል ነዉ ...ሲያጎራ ሲጮሁ ሰምታችሁ ከሆነ በጣም ለአቅል ይከብዳል ሲለፈልፉ በእነሱ አድርጎ ይወጣል፡፡
አንዳንዴ ዛር ያለበት እያጨበጨበ እየጨፈረ ሲያስለቅቅ ያየሁት አሉ ጅኑ አጨብጭብ ጨፍር ብሎት ወላሂ በአይኔ ያየሁት ነዉ፡፡ ግን ይሄ ለጅን ግብር ነዉ ተመልሶ ይመጣል ወይ ሌላ የቤተሰብ አባል ወይም ልጅን ይይዛል፡፡
የሀሉም መፍትሄ ቁርአን ብቻ
🟢 አይንናስ(ቡዳ) ..ሲህር..ጂን ብዙዎቻችን ላይ ያለ ይመስለኛል ለምን ብዙሀን ሙስሊሞች ከዲናችን የተዘናጋን ስለሆነ ራሳችንን ቆም ብለን ብናይ ጥሩ ነው.....ብዙዎቻችን
✏️ የጠዋት ማታ ዚክር ማድረግ አቁመናል
✏️ ቁርአን ስልክ ከመጣ ቡሀላ የምንቀራ በጣት የምንቆጠር ነን ሁሉም በስልኩ ቁርአን አዝካር አለ ያንን ለመቅራት ነይቶ ስልኩን ሲነካካ ወደ ማህበራዊ ሚዲያላይ ነዉ የሚወስደን፡፡ ግን አስተዉለናል?? በፊት ስልክ ሳይመጣ እኮ ለቁርአን ያለን ፍቅር ዚክር ለማድረግ ያለንን ጉጉት የተለየ ነበር ግን አሁን ማን ነዉ ቁርአንን አክብሮ ገልጦ የሚቀራዉ??የሚሻለዉ በስልክ ቁርአን መቅራት ብናቆም የተሻለ ነዉ እናም
የኛ ከቁርአን መዘናጋት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ማሳለፍ ከዲን የመዘናጋት ስለሆነ ራሳችንን ማኔጅ ብናደርግ ጥሩ ነዉ
✏️ በማህበራዊ ሚዲያ በTG..Whatsap..facebok..instgram ወዘተ የምናደርገዉ profile pictur ፎቶ ለአይን ናስ(ቡዳ) መበላት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡
ለምን ጀሊሉ ሲፈጥር ማስጠሌ ብሎ የፈጠረዉ የለም ግን የሰዉ አይን የፈለገዉን ቆንጆ የፈለገዉን ማስጠሌ አድርጎ ይስላል፡፡ profile ስታደርጉ እራሱን ወይ እራሷን እንደ ማስጠሌ የምታይ ዉይ ሲያምር ወይም ዉይ ስታምር ሊሉ ይችላሉ እናም profile ከማድረግ እንጠንቀቅ
✏️ በtiktok ላይ video የምፓስቱም የሰዉ አይን ሰለባ ስለምትሆኑ መጠንቀቁ አይጎዳም...እስኪ እኔ ብዙም ግንዛቤዉ የለኝም በtiktok የሚታወቁ ሰዎች ትዳር አላቸዉ የላቸዉም? ካላገቡ መቼም የሚታዩት ቆንጆ ናቸዉ እንዴት አላገቡም?
መጀመሪያ በሚዲያን የቀረበ ራሱን ጨረታ ያወጣ በሀራጅ ተከስሮ ነዉ የሚሸጠዉ ጨረታ እቃ ያሸነፈ ነዉ በሀራጅ ይገዛል ኦዲት ሲደረግ ይወድቃል
በመቀጠል ግን የሰዉ አይንም(ቡዳ) ችግር ሊሆን ይችላል
✏️ ያለቅጥ የተካበደ ሰርግ ብራይድ ማድረግ በሰዉ አይን የመበላት አቅሙ ሰፊ ነዉ ለምን በዚህ በኑሮ ዉድነት ባለበት ዘመን የሚበላ የሚጠጣ ቤት ኪራይ መክፈል በአቃቃተበት ዘመን ያለቅጥ ደስታ በደሀ እምባ መቀለድ ነዉ የእናንተን ሰርግ ደሀ ሲያየዉ ወይ የበላችሁበት ወይ የጠጣችሁበት ምግብ ላይ ወይ የለበሳችሁት ልብስ ላይ አይኑ ያርፋል እናም የተቸገረ ሰዉ ቀልብ አይን ከባድ ነዉ ፡፡
በተጨማሪ በዚህ ወንዱ ብር ማስተዳደሪያ ሴት ደግሞ ባል ባጣችበት ዘመን በሚዲያ ሰርጋችሁ ተካብዶ ሲያዩት ወንዱም ወይኔ ትንሽ ኑሮኝ በነበር ሴቷም እድለኛ ነች የሚያምር ባል አግብታለች ባይባል ጥሩ ነዉ የሰዉ አይን ከባድ ነው፡፡
የተወራለት በሚዲያ የታዩ ሰርጎች ብዙዎች ፍች ተፈጥሮ ደብቁኝ ደብቁኝ እያሉ ነዉ እናም ሁሉም በልክ ይሁን
✏️ ልጅ ሲወልዱ በደስታ prpfile pictur ማድረግ ይሄ ደግሞ በጣም ከባድ ነዉ ልጅ ያጣ ያላገባ ባለበት ዘመን ማሻ አላህ ሳይሆን አይኑ አፍንጫዉ መልኩ እናቱን ወይስ አባቱን በሚባልበት ዘመን profile ባይደረግ ባይ ነኝ፡፡
✏️ ከሰዎች የተለየ ልብሶችን መልበስ እና ቀን በቀን መቀያየር ይሄም ልብስ ያጡ አይኖች ላይ ትኩረት መግባት ነዉ ፡፡ ዱንያ ነዉ መብላት መጠጣት መልበስ ነዉ ማለት ቡሀላ ምነዉ ባልበላሁ ባልጠጣሁ ባለበስኩ ከማለት ሁሉን በልክ ማድረግ እና በዚክር በቁርአን መንቀሳቀስ ነዉ
በሰዉ ህይወት ቀንታችሁ በማወቅም ባለማወቅም ያሰራችሁ ካላችሁ ጉዳቱ ለተደረገበትም ለእናንተም ጭምር መሆኑን አትዘንጉ የተዉበት ጊዜዉ ገና ነዉ ወደአላህ እንመለስ ...እኛ የምናምፀዉ በወንጀል ድንበር የምናልፍበት ጌታችን ቅርብ ሁኖ እያየን እንደሆነ አንዘንጋ....
ጌታችን አሏህ ሱወ በተከበረ ቃሉ እንዲህ ይለናል
“ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው) እኔ ቅርብ ነኝ፣ የለማኝን ፀሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፣ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፣ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ለምመሩ፡፡ ይከጀላልና፡፡” (አል-በቀራህ፡ 186)
ታዳ ለምን እኛ የሰዉንም የራሳችንን ህይወት ለማበላሸት ደጋሚዎች ደብተራዎች ጠንቋይ ቤቶች እንሄዳለን??
የምንመቀዉን ሰዉ የሰጠዉ አላህ ለምን ለእኛስ ስጠን ብለን ወደ ጠንቋይ ከመሄድ ወደ ጀሊሉ እጃችንን አንዘረጋም??
በሐዲሥ አልቁድሲይ እንደተዘገበው አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- የሰው ልጅና አጋንት በሚገርም ሁኔታ ውስጥ ነው ያሉት፡፡ እፈጥራለሁ የሚመለከው ሌላ ነው፡፡ ሲሳይ እሰጣቸዋለሁ የሚመሰገነው ሌላ ነው:: መልካም ነገር ሁሉ ከኔ ወደ ባሮቼ ይወርዳል፤ የነሱ መጥፎ ነገር ወደኔ ይወጣል፡፡ ከነርሱ የተብቃቃሁ ሆኜ ሳለ በእዝነቴ ወደነርሱ እወደዳለሁ፡፡ እነርሱ ግን ከኔ ፈላጊ ድሆች ሆነው ሳሉ ወንጀል በመሥራት በኔ ለመጠላት ይሠራሉ፡፡ ለኔ ቅርብ የሆኑት እኔን የሚያወሱት ናቸው፡፡ እኔ የምወዳቸው እኔን የሚታዘቡት ናቸው፡፡ ወንጀል የሚሠሩትን ከእዝነቱ ተስፋ እንዲቆርጡ አላደርጋቸውም፡፡ በተዉባ ወደኔ የሚመለሱትን እኔ ወዳጃቸው ነኝ፡፡ ቢያምፁም አካሚያቸው እኔ ነኝ፡፡ በችግርና መከራ የምፈትናቸው ከነውር ላፀዳቸው ነው፡፡ ተውባ አድርጎ ወደኔ የሚመለስን ሰው ገና ሩቅ እያለ እቀበለዋለሁ፡፡ ከኔ ዞር ብሎ የሄደውን በቅርብ ሆኜ እጠራዋለሁ፡፡ ከኔ ውጭ ሌላ አምላክ አለህ እንዴ ወዴት ነው የምትሄደው?› እለዋለሁ፡፡
በተጨማሪ
አላህ ለነብዩ ዳወድ እንዲህ አለ፡- ዳውድ ሆይ! ለኔ ጀርባቸውን የሰጡ ሰዎች (ወደኔ በመመለሳቸውና ተፀፅተው በመምጣታቸው) ለነርሱ ያለኝን ጉጉት ቢያውቁ ኖሮ ለኔ ከሚኖራቸው ጉጉት የተነሳ በቀለጡ ነበር፡፡ ዳውድ ሆይ! ይህ ለኔ ጀርባቸውን ለሰጡ ሰዎች ያለኝ ፍላጎት ነው፡፡ ፊታቸውን ወደኔ ላዞሩ ሰዎች እንዴት የሚሆን ይመስልሀል?
አላህ እንዲህ እያለ ይወቅሰናል
ለነዚያ ለአመኑት ለአላህ ተግሳፅና ከቁርአንም ለወረደዉ ልቦቻቸዉ ሊፈሩ ጊዜዉ አልቀረበምን??
አላህ እየወደደን ወደኔ ቅረቡ እያለ ይለምናል እኮ
እናም ያለፈዉ ስህተት ከነበርን ቶብተን ወደ አላህ እንመለስ ያስደረግንም ካለን በሰዉ ህይወት አንጫወት ላንጠቀም ነገር ሲህሩ ድግምቱ እንዲፈታ እንዲቆም ማድረግ አለብን፡፡
ህሊና ላለዉ ሰዉ ሲህር አስደርጎ የተደረገበት ሰዉ ሲሰቃይ ሲቸገር ሲታመም እንዴት አቅላችን ይሸከመዋል??
እንዴት ሰዉ እንዳያገባ ተደርገ የእሱ ወይ እሷ አግብቶ መዉለድ እንዴት እኛን ሊያናድደን ይችላል??ብቻ አሁንም የተዉበት በሩ ክፍት ነዉ ወደ አላህ እንመለስ
#ክፍል 1⃣4⃣
ይቀጥላል.....
አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ👇👇
T.me/Aisuu_bot
ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
♥
Join👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
✍ አሚር ሰይድ
⭐️ #ክፍል👉 አስራ ሁለት 1⃣2⃣
🔰🔰በተከታታይ ➊➊ ፓርቶች ድግሞትና ሲህር ከሚለዉ 70% በራሴ ካነበብኳቸዉ ከማቃቸዉ 30% ጨምሬ ከሰዎች ታሪክ በመጨመር በምሳሌ አቅርቢያለሁ ..ከpart ➊➋ ጀምሬ እስኪ ከሰማሁት ከማቀዉና መረጃዎችን በማጣቀስ ለእናንተ አቀርባለሁ፡፡
መጀመሪያ ብዙሀን ሰዉ አናምንም እኛን አይነካንም እንላለን ...ግን በራስ ሲደርስ ነዉ የሚታወቀዉ የኢማን የመጠንከር የመላላት ጉዳይ አይደለም የሆነ የምንዘናጋበት ቀን አለ በዛ ቀን በሰዉ ምቀኛ በተለይ በቅርብ ጓደኛ በቅርብ ዘመዶች ሊያነጣጥሩብን ይችላሉ ....የት ይሰራል ብላችሁ ካሰባችሁ ...ብዙዎች እነሸህ እነ ወልይ የወደፊት ያቃሉ እያሉ እየሄዱ እየሰገዱ ቁርአን እየቀሩ ጀለብያ ጥምጣም ለብሰዉ ሳሂር ደጋሚ የሆኑ እንዳሉ አንዘንጋ በተጨማሪ ደግሞ በጣም ብዙ ሰዉ ከሙስሊሙም ሌላም ሀይማኖት ተከታዮች የሚሄዱት ደብተራዎች ጋር ነዉ፡፡
ደብተራዎች face book እና tg ቻናል አላቸዉ ለምሳሌ ሁለት የማቀዉን ከtg ያገኘሁትን ከታች ተመልከቱ
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
መርጌታ ገብረ መድን በውጭ ሀገር ለሚኖሩም መምጣት ለማይችሉ ባሉበት እንሰራለን የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል ☎️ 09 ... 03 ....☎️ ስልኩን ያጠፋሁት ደግሞ እንዳደዉሉ ብየ ነዉ☺️
ለገበያ>>ለሀብት>>ለስንፈተ ወሲብ (ለቁመት:ለውፍረት: ቶሎ ለሚያበቃ) >> ለመስተፋቅር >>ጥይት ለማያስመታ >> ለማንኛውም ዓይነት በሽታ መፍትሔ >> ለራእይ (በህልም የሚያሳይ)>> ለፀር (ለጠላት)>>ዓቃቤ_ርእስ (ጠላት እንዳይጎዳን የሚጠብቅ)>> ለዘኢያገድፍ (ለትምህርት የማያስጠፋ የማያስጥል)>>ለመክስተ_ምስጢር (ትምህርት የሚያጎብዝ)>>ለመፍትሔ_ሀብት(ሀብቱ በጠላት ድግምት ለተሰወረበት)>> #መስተፋቅር>> ለግርማ_ሞገስ (ሰው እንዲያከብረን እንዲወደን)
>> ለመድፍነ_ፀር (ጠላት እንዳይናገረን እና እንዲፈራ>> ለሌባ(እንዳንሰረቅ እንዳንዘረፍ የሚጠብቅ)>> የትዳር አጋር ላጣ ወይም ላጣች
የሚያስገኝ>>ለምስያጥ ለገበያ (ገበያ እንዲቀናን እንድናገኝ)>> መስተኃድር (ከብት ቢጠፋብን ሳይበሉ በሰላም እቤታቸው
የሚያመጣ)>> መንድግ(በገበያ ገንዘብ ማግኛ)>> ለዓይነ_ጥላ (የፍራቻ መንፈስ ማስለቀቂያ)>>ምስሀበ_ነዋይ(ገንዘብ ማግኛ)>> ለጽሑፍ ለስእል ለከበሮ ለበገና ለክራር በእጂ ለሚሰሩ>> ንባብ ስናነብ ቀልጣፋ የሚያረግ>> ለመፍዝዝ (ጠላት እኛን ለማጥቃት ሲሞክር አጠገባችን ሲደርስ
መጣላቱን አስረስቶ አፍዝዞ የሚያስቀር የማያስመታ)>> ለሙግት>> ለሰላቢ>> ለስንፈት ወሲብ>> ዘኢያወርድ ( ለወንዶች በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፍሬ ቶሎ
እንዳይወርድ የሚያረግ አግዶ የሚያቆይ)>> ለመደንግፅ (የተጣላን ሰው እኛን ሲያይ እንዲደነግጥ እንዲፈራ
የሚያረግ)>> ለጥይት (ጥይት የማያስመታ)>> ለዱላ( ዱላ የማያስመታ)>> መንስኤ_እስኪት (ለወንድ የመራቢያ አካሉ ለደከመ ላነሰ)>> ህገ_ጠብቅ (የትዳር አጋራችን ወደሌላ እንዳይሄድ የሚያስር
እንዳይዘሙት የሚከለክል)>> ለአይነ_ሰብእ (ከሰው አይን የሚጠብቅ)>> በመኝታ ሽንት ለሚያመልጠው >> እንቅልፍ መብዛት>> የእንቅልፍ ማነስ >> የወር አበባ ችግር ካለ
09... 03 ....
ይደውሉልን
✏️✏️በተጨማሪ የሌላዉን በtg የሚፓስተዉን ልላክላችሁ👇👇👇👇
☎️📞09 4............5 የባህል መድህኒት ጥበብ አስማት ይፈልጋሉ:
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
መፍትሄ ሀብት መስተፋቅር = የገበያ ለቀለም= ትምህርት ለአይነ ጥላ= ለመፍትሔ ስራይ= ለህማም = ጋኔን ለያዘው ሰው = ቡዳ ለበላው = የዛር ውላጅ ለተዋረሰው = ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር) = ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ) = ለቀለም(ለትምህርት) = ሰላቢ የማያስጠጋ = ለመፍትሔ ሀብት =ለመስተፋቅር = ለገብያ = ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ) = ለመድፍነ ፀር = ሌባ የማያስነካ = ለበረከት
= ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ) = አፍዝዝ አደንግዝ = ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ) = ለግርማ ሞገስ = ለዓይነ ጥላ
= ለሁሉ መስተፋቅር = ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ = ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ) = ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ = ለድምፅ = ለብልት እንደመቆም = ለኤች አይቪ መድሀኒት
አገልግሎት(ምናልባት ያለ ኮከባቸው
የተጋቡ ካሉ
አስማምቶ የሚያኖር መድሀኒት
ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል
ለጥያቄወ 📞☎️09 4........5 ይደውሉልን በአካል መቅረብ ለማትችሉ በሙሉ ወደ አሉበት ቦታ ድረስ ይደርሶዎታል
ይላል በTelegram በfacebook በጣም ብዙ አሉ ይሄን የላኩላችሁ ሲህር ድግምት ለእናንተ መጥፎ የሚስቡ መጥፎ ሰዎች እነዚህ ቦታ ቢሄዱ አስባችሁታል?? እነዚህ ቦታ ሂደዉ መስተፋቅር ወይ ገበያ እንድንከሰር ወይ ሌላ ነገር ቢያሰሩበን በእኛ ኢማን ድክመት በጣም ከባድ ነዉ ፡፡ እናም ብዙ ሰዉ የለም የሚል ካለ ራስን ማሞኘት ነዉ ደጋሚዎች ደብተራዎች በየሀገሩ በየመንደሩ አሉ፡፡
📌📌ማወቅ ያለብን የደብተራ ብቻ አይደለም ..በጣም በዙ ሙስሊም ተብለዉ በየገጠሩ የሚሰሩ አሉ ዱአ ላስደርግ ምናምን ጫት የሚቃምበት በጣም የሚበዛ ከሆነ ..ወይም በጫት እናስለቅቃለን ካሉ ዛር አለባቸዉ በጫት የሚያስለቅቀዉ ለትልቅ ጅን ይገብራል ማለት ነዉ እንወቅ እባካችሁሁሁሁ ....
ወልዮች ሸሆች ጋር እያልን ጫት የሚቅሙ ጋር እየሄድን ባንዘናጋ ኸይር ነዉ፡፡በነገራችን ላይ እንደዚህ እያለ የሚሄድን ወጣትም ሆነ ትልቅ ሰዉ ሰዉየዉን ባንቀርብ ወይ ሰዉየዉን ከቀረቡ እራቅ ብሎ በዉዲዕ ቢሆን አሪፍ ነዉ፡፡
የሚገርመዉ ነገር አንድ የገጠር ሰዉ የማምነዉ ለጅን ማረድ ከተወ ቡሀላ ሲያወራኝ ለጅን የሚያርድልን ሰዉ የመስጊድ ኢማማችን ነዉ ብሎኛል ...
አሏሁ የስቱርና
--------- ------ ------ ------ -----
📚📚ግን አንዳንድ ፍቅሮች እንዴት ነዉ ???🙄
አሁን ላይ ግራ የገባኝ ነገር አለ ፍቅር እንዴት ነዉ???
ፍቅር አለ ወይስ የለም ማለት ለማለት እየከበደ ነዉ ..ፍቅር አንዳንዴ የሲህር በሽታም ሊሆንም ይችላል ብቻ እኔ አሁን ግራ እየገባኝ ያለ ፍቅርን እንዴት መገለፅ ይቻላል መልስ የሌለዉ ጥያቄ...
ግን እስኪ ከዚህ በታች አይነት ታሪክ የደረሰባችሁ ካለ በአስተያየት መስጫ ላይ አስቀምጡልኝ...ግን በፊት እወደዋለሁ አፈቅረዋለሁ ወይም እወዳታለሁ አፈቅራታለሁ ብለዉ በፍቅር ሲያለቅሱ ሲሰቃዩ የነበሩ..እንደ አጋጣሚ ወይም በሌላ ምክንያትም ቢሆን ታመዉ ሩቃ ሲገባ እወደዋለሁ አፈቅረዋለሁ ያሉትን ሰዎች 80% እሱ ጋር ቢኖሩም ባይኖሩም ምንም አይመስላቸዉም...ከሩቃ ቡሀላ አፍቃሪዉ ሲህር ወይ ጂን ከነበረበት ከለቀቀ አፍቅረዋለሁ የሚለዉ ሰዉ ረጋ ማለት እና መረጋጋት ይታይበታል፡፡👇👇
✏️✏️ ወደ መፀዳጃ ቤት ከመገባት በፊት ከሰይጣናት በአላህ መጠበቅ
ቢስሚላህ አሏሁመ ኢኒ አኡዙቢከ ሚነል ኹቡሲ ወል ኸባኢስ ማለት ..
መፀዳጃ ቤቶች የሰይጣናት መኖሪያዎች ናቸዉ፡ የሙስሊምን እነዚህ ቦታዎች ላይ መገኘት እንደ ጥሩ አጋጣሚ ተጠቅሞ ሰይጣን ሊገባበት ይችላል፤ በሩቃ ጊዜ አንዳንዴ ጂኖቹ ከሰይጣናት ሳይጠበቅ ወደ መፀዳጃ ቤት በመግባቱ ምክንያት ነዉ ልገባበት የቻልኩት" በማለት ይናገራሉ
(ዉዳሴዎች) ናቸዉ” በማለት መለሰልኝ፡ ነብዩ ወደ መጸዳጃ ቤት ሲገቡ የሚከተለዉን ዚክር (ጸሎት) ይሉ ነበር፡-
(بسم الله اللهم إني أَعُوذُ بِكَ مِنَ الْحُبْثِ وَالْخَالِيث ቢስሚ አላህ አላሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚነ አል ኹቡሲ ወ አል ኸባኢስ” (ቡኻሪ ዘግበዉታል) ትርጉም፡- በአላህ ስም፤ አላህ ሆይ! ከወንድና ከሴት ሰይጣናት በአንተ
እጠበቃለሁ፡፡
✏️✏️ የሶላት መከፈቻ ዚክር
የሚከተለዉን ጾለት በሶላት መክፈቻ ወቅት ማለት፡፡ ጁበይር ኢብን አል ሙጥዒም የሚከተለዉን ሃዲስ ሲያስተላልፉ እንዲህ አሉ፡- ነብዩ ሲሰግዱ አየሁዋቸዉ እንዲህም ሲሉ ሰማሁ፡-
“አሏሁ አክበር ከቢራ፤ ወል ሃምዱ ሊላሂ ከሲራ፣ ወሱብሃነ አልሏሂ ቡክረተን ወአሲላ (ሶስት ግዜ)።
☞ አዑዙ ቢላሂ ሚነ ሸይጧን ረጂም ሚን ነፍኺኽ ወነፍሲኺ ወሀምዚሂ
ትርጉም፡- አላህ ታላቅ ነዉ፡፡ አላህ በብዙ የተመሰገነ ይሁን፡፡ በጠዋት በማታ አላህ ፍፁም ነዉ፡፡ ከተረገመዉ ስይጣን ከትምክህቱ፤ ከግጥሙ እና ከእብደቱ በአላህ እጠበቃለሁ፡
✏️✏️ የጋብቻ ህይወትን በሶላት መጀመር
ዓብደላህ ኢብን አል መስዑድ የሚከተለዉን አስተምረዋል። “ከመጀመሪያዉ የጫጉላ ግንኙነታችሁ በፊት ሚስትህ ሁለት ረክዓ ሶላት እንድትሰግድ አድርግ፡፡ አንተም ስገድ፡፡ ከዚያም የሚከተለዉን ፀሎት አድርግ፡-
አሏሁመ ባሪክ ሊ ፊ አኽሊ ወባሪክ ለኁም ፊዬ፣አሏሁመ ኢጅመዕ በይነና ማ ጀመዕተ በኸይሪን.. ወፈሪቅ በይነና ኢዛ ፈረቀተ ኢለ አል ኸይር” (ጦበራኒ ዘግበዉታል፡፡ አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብለዋል)
ትርጉም፡- አላህ ሆይ በረካ ያላት ሚስት አድርግልኝ፣ በእኔ ላይም በረካ አድርግ ለበጎ እስከተስበለብን ድረስ አንድ አድርገን፡፡ ወደ መልካም በምትለያየን ጊዜ ለያየን፡፡
✏️✏️ በግንኙነት ወቅት የሚባል ዱዓዕ
ነብዩ የሚከተለዉን አስተምረዉናል “ማንኛዉም ሰዉ ከባለቤቱ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ሊፈፅም ሲል የሚከተለዉን ዱዓዕ ካለ በዚህ ግንኙነታቸዉ ልጀ ቢፈጠር ልጁን ሰይጣን በፍጹም ሊጎዳዉ አይችልም ::
بِسْمِ اللهِ اللَّهُمَّ جَنِّبْنَا الشَّيْطَانَ፣ وَجَنْبِ الشَّيْطَانَ مَا رَزَقْتَنا ቢስሚላህ። አሏሁመ ጀኒብና አል ሸይጣን፤ ወ ጀኒብ አል ሸይጣን ማ ረዘቅተና
ትርጉም፡- አላህ ሆይ! ከኛ ሰይጣንን አርቅልን፡፡ ከሰጠኸን ሲሳይ ላይም ሰይጣንን አርቅልን፡፡
📌📌 በአንድ ወቅት በጂኒ የተለከፈን ሰዉ ሩቃ ሲቀራበት፡፡ ጂኒዉ እስልምናን ከተቀበለ እና ንስሃ ከገባ በኋላ ታካሚዉ ይህን ፀሎት ሳይል ሚስቱን ይገናኛት ስለነበረ ሚስቱን በወሲብ እጋራዉ ነበር ብሏል፡፡
ሱብሃን አላህ! ስንት እና ስንት እንቁ ስጦታዎች እያሉን ዋጋቸዉን ዘነጋናቸዉ!
✏️✏️ ከመኝታ በፊት ዉዱዕ አድርጎ እና አያት አል ኩርሲይን ቀርቶ መተኛት፡፡
ከዚያም እንቅልፍ እንስከሚያሸንፍህ ድረስ ዚክር ማለት፡፡ ከመተኛቱ በፊት አያት አል ኩርሲይን የቀራ ከአላህ የተላከ ጠባቂ : አይለየዉም፡፡ እስከሚነጋ ድረስም ሰይጣን አይቀርበዉም የሚለዉን ሀዲስ አቡ ሁረይራ አስተላልፈዉልናል፡፡ (ቡኻሪ ዘግበዉታል)
✏️✏️ በየቀኑ ከመገሪብ ሶላት በኋላ የሚከተሱትን የቁርአን አንቀጾች መቅራት።
➊ የአል በቀራ ምዕራፍን ከቁጥር 1 - 5 ያለዉን
➋ አያት አል ኩርስይን እና ቀጥለዉ ያሉትን ሁለት አንቀጾች
➌ አል በቀራ ምዕራፍ የመጨረሻዎችን ሶስት አንቀፆች
እነዚህን አንቀፆች በቀራህባቸዉ ቀናት ሌሊቱንና ቀኑን ከድግምትና ከጂኒ ልክፍት በአላህ ፈቃድ ትጠበቃለህ፡፡
✏️✏️ ላኢላሀ ኢላ አላህ ወህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁ አል ሙልክ ወ ለሁ አል ሀምድ ወ ሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር ከሱቢህ ሶላት በኋላ 100 ጊዜ ማለት፡፡
ይህንን በማስመልከት የሚከተለዉ ሃዲስ ተላልፎልናል። ይህን ፀሎት በቀን መቶ ጊዜ ያለ አስር ባሪያዎችን ነፃ እንዳወጣ ይቆጠርለታል፡፡ መቶ ምንዳ ይፃፍለታል። መቶ ሀጢያቶችን ይማራል። በዚያ ቀን እስከሚመሽ ድረስ ከሰይጣን መከላከያ ይሆነዋል፤ ይህ ሰዉ ከስራዉ ሥራ የሚበልጥ ማንም አያመጣም ከመቶ በላይ ያለ ካልሆነ በስተቀር፡፡ (ቡኻሪ ዘግበዉታል)
✏️✏️ ወደ መስጊድ ስትገባ የሚከተለዉን ዱአ ማለት፡-
አኡዙቢላሂል አዚም፣ ወቢወጂብ አል ከሪም ወ ሱልጣኒሂ አል ቀዲም ሚነ አል ሸይጧን አል ረጅም (አቡ ዳዉድ ዘግበዉታል፡፡ አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብለዋል)
✏️✏️ ከቤትህ ስትወጣ የሚከተለው ዱዓዕ ማለት
بسم الله توكلت عَلى اللهِ፣ وَلا حول ولا قوة إلا بِاللَّهِ
ይህን ዱዓዕ በምትልበት ግዜ ሰይጣን እንዲህ ይላል “ተጠበክ ተመራህ፤ ተብቃቃህ እንግዲህማ ሰይጣን ይሸሽሃል ....ሌላ ሰይጣንም ሲያገኝ እንዲህ ይለዋል የተጠበቀን የተመራን የተብቃቃን ሰዉ ምንስ ልታደርገዉ ትችላለህ? ምንም ልታደርገዉ አትችልም” (አቡ ዳዉድ እና ቲርሚዚ ዘግበዉታል)
#ክፍል 1⃣2⃣
ይቀጥላል....
አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ👇👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
➎ አቡ ዘር የሚከተለዉን ሃዲስ አስተሳልፈዋል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ>>> የሰዉ ዓይን በአላህ ፈቃድ አንድን ሰዉ ከፍታ ላይ ወጥቶ እስኪፈጠፈጥ ድረስ ታጠቃዋለች” (አህመድ ዘግበዉታል፡፡ አልባኒ ሶሂህ ነዉ ብለዋል)
✔ ይህም ማለት የሰዉ ዓይን አንድን ሰዉ ስታገኘዉ ከፍ ያለ ስፍራ ላይ ወጥቶ እንዲፈጠፈጥ ልታደርገዉ ትችላለች።
➏ ኢብን ዓባስ የሚከተለዉን አስተላልፈዋል፡፡ ነብዩ እንዲህ አሉ የሰዉ ዓይን አይነት እዉነት ነው ፡፡ ከፍታ ቦታ (ከተራራ ላይ) ትወረራለች (አህመድ ዘግበዉታል አልባኒ ሃሰን ነዉ ብለዋል)
➐ ጃቢር የሚከተለዉን ሃዲስ አስተላልፈዋል፡፡ ነብዩ እንዲህ አሉ>>> የሰዉ ዓይን ሰዉን ቀብር ዉስጥ፤ ግመልን ድስት ዉስጥ ትከታለች (አቡ ነዒም ዘግበዉታል። አልባኒ ሃሰን ነዉ ብለዋል)
የዚህ ሀዲስ መልዕክት፡- የሰዉ ዓይን አንድን ሰዉ ታገኘዉና እንዲሞት አድርጋ ቀብር ዉስጥ ይገባ፡፡ ግመልንም ታገኝና ሊሞት ሲል ይታረዳል ድስት ዉስጥ ገብቶ ይቀቀላል፡፡
➑ ጃቢር የሚከተለዉን ሀዲስ አስተላልፈዋል። ነብዩ እንዲህ አሉ ፡- ከአላህ ቀዷዕ እና ቀድር በሆላ አብዛኛዉ ኡመቴ(ህዝቦቼ) የሚሞቱት በሰዉ አይን ሳቢያ ነዉ፡፡(ቡኻሪ ዘግበዉታል)
➒ ዐዒሻ እንዲህ አሉ >>ከሰዉ ዓይን በሩቅያ እንድታከም ነብዩ አዘዉኛል(ቡኻሪ ዘግበዉታል)
➓ አነስ አብኑ ማሊክ የሚከተለዉን ብለዋል "ከሰዉ ዓይን፣ ከአል ሁማ (መርዛማ የእባብ ጊንጥ መነደፍ) እና ከአል ነመነህ (በጀርባ ላይ የሚከሰት የቁስል አይነት ነዉ) ህመሞች በ አል ሩቅያ መታከምን ነብዩ ፈቅደዋል (ሙስሊም ዘግበዉታል)
➊➊ ኡሙ ሰለማህ የሚከተለዉን ሀዲስ አስተላልፈዋል፡፡ እኔ ቤት የነበረች ልጅን ፊቷ ላይ ጥቁር ወይም ዳልቻ ነገር ተመልክተዉ ነብዩ "ይህች ልጅ የሰዉ ዓይን አባት፡፡ ስሊዚህ በአል ሩቅያ አክሟት” አሉን፡
(ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበዉታል)
🔰🔰 #ስለ_ስዉ_ዓይን(ቡዳ) የሙስሊም ሊቃዉንት አስተያየት
☑️ አል ሃፊዝ ኢብን ከሲር እንዲህ ይላሉ....የሰዉ ዓይን በአላህ ፈቃድ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። ይህም እዉነት ነዉ፡፡ አልሃፊዝ ኢብን ሃጀር እንዲህ ይላሉ
እርኩስ ባህሪ የተጠናወተዉ ሰዉ ከምቀኝነት ጋር በተቀራኜ አድናቆት ወደ አንድ ሰዉ ሲመለከትና በዚህ ሰዉ ላይ ጉዳት ሲደርስበት ይህ ነዉ እንግዲህ የሰዉ ዓይን ማለት፡:
☑️ ኢብን አሰር እንዲህ ይላሉ “ጠላት ወይም ምቀኛ አንድን ሰዉ ሊያየዉ እና በዚህም ሳቢያ ሰዉዬዉ ከታመመ የሰዉ ዓይን አገኘዉ ይባላል
☑️ አል ሃፊዝ ኢብን ቀዩም እንዲህ ይላሉ “ከፍተኛ የእዉቀት እጥረት ያለባቸዉ አንዳንድ ሰዎች የሰዉ ዓይን ስለመኖሩ ይክዳሉ። የሰዉ ዓይን ተጨባጭነት የሌለዉ ተረት ነዉ በማለት ይከራከራሉ፡፡ እንዲህ ያሉ ሰዎች ከእዉነት እና ከእዉቀት የራቁ ስለ ነፍስ እና መንፈሳዊ ጉዳዮች ስለባህሪያቶቻቸዉ፣ ሊያደርሱት ስለሚችሉት ዉጤት እና ሊያስከትሉት ስለሚችሉት ተፅእኖ አንዳች ግንዛቤ የሌላቸዉ ናቸዉ፡፡
🔸🔸🔸 የተለያዩ ሃይማኖት ተከታይ የሆኑ ጠቢባን የሰዉ ዓይን ስለመኖሩ አይክዱም፡፡ ምንም እንኳን ስለ መንስኤዎቹና ሊያስከትል ስለሚችለዉ ጉዳት የተለያየ አመለካከት ቢኖራቸዉም፡፡
አላህ የሰዉ ልጆችን አካላትና ነፍሶቻቸዉን በዉስጣቸዉ የተለያየ ሀይላት እና ስብዕና አድርጎ እንደፈጠራቸዉ አያከራክርም፡፡ በአንዳንድ በርከት ባሉት ላይ ደግሞ ልዩ ተጽዕኖ ፈጣሪ ባህሪያት አድርጎባቸዋል። ነፍስ በአካል ላይ ልታደርስ የምትችለዉን ተጽዕኖ ማንም አስተዋይ ሰዉ አይክድም፡፡ ምክንያቱም ተጨባጭ ነገር ነዉና፡፡
#ለምሳሌ፡- የሚወደዉና የሚያከበረዉ ሰዉ የአንድን ሰዉ ፊት ሲመለከት ሲፈካ፣ በተቃራኒዉ ደግሞ የሚፈራዉ (በቁጣ) ሲያየዉ ፍም ሲመስል ይስተዋላል፡፡ ሰዉ ስላያቸዉ ብቻ የታመሙ የተዝለፈለፉ ሰዎች ማየታቸዉን ብዙዎች መስክረዋል፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነዉ እንግዲህ በሰዉ ልጆች ነፍስ ተፅዕኖ ሳቢያ ነዉ። በሰዎች ነፍሶች እና በአይኖቻቸዉ መካከል ከፍተኛ ቁርኝት ስላለ ነዉ.... ይህ በነፍሶቻቸዉ የደረሰዉ ጉዳት በዓይን እንደደረሰ ተደርጎ ይቆጠራል። እዉነታዉ ግን ይህን ጉዳት የሚያስከትሉት የሰዉ ልጅ ዓይኖች ሳይሆኑ ነፍሶቻቸዉ ናቸዉ፡፡ ነፍሶች ደግም ባላቸዉ ሃይል፣ ባህሪያት እና በሌሎች ልዩ ልዩ ገጽታዎች ከሰዉ ሰዉ የተለያዩ ናቸዉ።
የምቀኛ ነፍስ ለምትመቀኘዉ ሰዉ ጎጂ ናት። ለዚህም ነዉ ነብዩን ከምቀኛ ተንኮል እንዲጠብቃቸዉ እንዲፀልዩ አላህ ያዘዛቸዉ፡፡ ምቀኛ በሚመቀኘዉ ሰዉ ላይ ስለሚያስከትለዉ ጉዳት ስለ ሰዎች አዉቀት የሌለዉ ካልሆነ በቀር ማንም አይክድም፡፡
🔹🔹🔹 .የሰዉ ዓይን ልክፍት መሰረቱ እንዲህ ነዉ፡፡ እርኩስ የሆነች ነፍስ በእርኩስ ባህሪይ ተገልጣ የምትመቀኘዉን ሰዉ ስታገኘዉ በዚህ ልዩ በሆነዉ እርኩስ ባህሪዋ ጉዳት ታደርስበታለች፡፡
ለዚህ ደግሞ ኮብራ እባብን በንፅፅር መዉሰድ ይቻላል። በኮብራ ዉስጥ መርዝ ከሃይል ጋር ይገኛል፡፡ ኮብራዉ ጠላቶቹን ሲያይ በሃይል እና በቁጣ ይነሳሳል። መጥፎና ጎጂ በሆነዉ ባህሪዉ ይገለጣል፡፡ ይህ መጥፎ የሃይልና የቁጣ ባህሪዉ ሲብስ ጽንስ እስከማስወረድ እና ዓይን እስከ ማጥፋት ይደርሳል፡፡
አብተር እና ዙጡፍየተይን ስለሚባሉ የእባብ ዓይነቶች እነዚህ ዓይን ያጠፋሉ ፅንስ ያስወርዳሉ፡፡ በማለት ነብዩ አስተምረዉናል፡፡ (ቡኻሪ ዘግበዉታል)
🔻በመገናኘት!
🔻ድንገት በማግኘት፣
🔸በማየት፣ በነፍስ በማሰብ፣
🔺ድግምት በማነብነብ፤ በማማተብ፣
🔺 በምናብ በመሳል ቡዳ በሰዉ ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል፡፡
🟡🔴 የቡዳ ነፍስ በማየት ብቻ አይደለም ጉዳት የምታደርሰዉ፡፡ ቡዳዉ ማየት የተሳነዉ ቢሆንም እንኳ ስለ ሆነ ነገር በሚነገረዉ ወይም በሚሰማዉ ብቻ ተመስርቶ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። በርካታ ቡዳዎች ሰዉየዉን ሳያዩት ስለ እርሱ በተነገራቸዉ ላይ ብቻ ተመስርተዉ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ ቡዳ ከቡዳዉ ሰዉ በዓይኑ በኩል ውጥታ እንደ ቀስት ትወረወራለች። ዒላማዋን ልትስት ወይም ልታገኝ ትችላለች። ዒላማዉ
>> የጠዋት የማታ አዝካር የሚል
>> ሶላት የሚሰግድ
>> ቁርአን የሚቀራ ከሆን ቡዳዉ ሊጎዳዉ አይችልም።
# ባጭሩ የቡዳ ጉዳት የተመሰረተዉ እንዲህ ነዉ፡- ቡዳዉን አንድ ነገር ያስደንቀዋል፡፡ በዚህ ግዜ እርኩስ ነፍሱ ወደ አስደነቃት ነገር በዓይን በኩል መርዟን ትረጫለች፡፡ አንዳንዴም ቡዳ እራሱን በራሱ ሊበላ ይችላል። ሌሎችንም ቢሆን ያለፍላጎቱ ይበላል።
ክፍል 1⃣1⃣
ይቀጥላል....
4any cmt 🔽
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
{ وَقَدِمۡنَاۤ إِلَىٰ مَا عَمِلُوا۟ مِنۡ عَمَلࣲ فَجَعَلۡنَـٰهُ هَبَاۤءࣰ مَّنثُورًا }
[Surah Al-Furqân: 23]
🌙 #ዘዴ_አምስት 5⃣
አል ሃፊን እንዲህ ይላሉ - እብዱል ረዛቅ በአል ሻህ በኩል የሚከተለዉን ዘግበዋል : የአረቦችን አል ኑሽራ መጠቀም ክልክል አይደለም፡፡
አል ኑሽራ ማለት እሾሃማ ተክሎች ወዳሉበት ስፍራ ሄዶ ከግራ እና ከቀኙ ቅሎችን እየቆረጠ ይይዝና ይጨቀጭቃቸዋል። ከዚያም በዉሀ አድርጎ ይቀራባቸዉና ሰዉነቱን ይታጠብባቸዋል። የሚቀሪዉም የሚከተሉትን የቁርአን ምእራፎች ነዉ፡፡ አያተ አል ኩርስይ፣ አል-ኢኽላስ፤ አል-ፈለቅ፣ አል-ናስ።
🌙 #ዘዴ_ስድስት 6⃣
ታማሚዉ በፀደይ ወራት ከጫካና ከጓሮ አበቦች የቻለዉን ያህል ሰብስቦ በንፁህ እቃ አድርጎ ከንፁህ ዉሀ ጋር በመጠኑ ያፈላቸዋል፡፡ ዉሃዉ ፈልቶ ሲሰክን አል-ኢኽላስ፤ አል-ፈለቅ እና አል-ናስ ይቀራበታል። ከዚያም ይታጠብበታል። በአላህ ፈቃድ ይድናል፡፡
🌙 #ዘዴ_ሰባት 7⃣
በንጹህ እቃ ዉሃ ታቀርብና፣ አል ኢኽላስ፤ አል ፈለቅ፣ አል ናስ እና የሚከተሉትን ዱዓዎች ሰባት ግዜ በዉሀዉ ላይ ትቀራለህ፡፡ ከዚያም በዚህ ዉሃ ታማሚዉ ለሶስት ቀናት ይታጠብበታል፡፡ በዚህም በአላህ ፈቃድ ድግምቱ ይረክሳል ከመሰናክለ ወሲቡም ይድናል፡፡
🌙 #ዘዴ_ስምንት 8⃣
☞ አል ፋቲሃን ሰባ ጊዜ ወይም ከሰባ በላይ መቅራት
ኢያት አል ኩርሲይን ሰባ ጊዜ ወይም ከሰባ በላይ መቅራት
☞ አል ኢኽላስ፣ አል ፈለቅ እና አል ናስን ሰባ ጊዜ ወይም ከሰባ በላይ ለሶስት ወይም ለሰባት ተከታታይ ቀናት በታማሚው ጆሮ ላይ ትቀራለህ። በዚህም በአላህ ፈቃድ ድግምቱ እና መስናክለ ወሲቡ ይፈታል፡፡
🌙 #ዘዴ_ዘጠኝ 9⃣
ከዚህ በታች የተጠቀሰዉን የቁርአን አንቀፅ በጡሃራ ቀለም በንጹህ እቃ ላይ ትፅፋለህ፡፡ ከዚያም ይህን የቁርአን ጽሁፍ በጥቁር አዝሙድ ዘይት ታጥበዋለህ፡፡ ይህንን ቁርአኑ የታጠበበትን የጥቁር አዝሙድ ዘይት ታማሚዉ ለሶስት ቀናት ይጠጣለታል ደረቱን እና ግንባሩን ያሽበታል። በዚህም በአላህ ፈቃድ ድግምቱ ይፈታል፡፡ መሰናክለ ወሲቡም ይወገዳል፡፡
{ فَلَمَّاۤ أَلۡقَوۡا۟ قَالَ مُوسَىٰ مَا جِئۡتُم بِهِ ٱلسِّحۡرُۖ إِنَّ ٱللَّهَ سَیُبۡطِلُهُۥۤ إِنَّ ٱللَّهَ لَا یُصۡلِحُ عَمَلَ ٱلۡمُفۡسِدِینَ }
{ وَیُحِقُّ ٱللَّهُ ٱلۡحَقَّ بِكَلِمَـٰتِهِۦ وَلَوۡ كَرِهَ ٱلۡمُجۡرِمُونَ }
[Surah Yûnus:81- 82]
ኢብን ተይሚያህ ቁርአን እና አዝካር ጽፎ እና አጥቦ ለታማ ማጠጣት የተፈቀደ ስለመሆኑ ፈትዋ ሰጥተዉበታል፡፡
🔰🔰 #በመሰናክስ_ወሲብ፤ #በስንፈተ_ወሲብ እና #በወሲብ_መሳን #መካከል_ያለ_ልዩነት
📌 #መሰናክለ_ወሲብ፡- በዚህ ድግምት የተያዘ ሰዉ ከሚስቱ ጋር ወሲብ ለመፈጸም ከፍተኛ ፍላጎት እና ስሜት ይኖረዋል። ወደ ሚስቱ እስካልተጠጋ ድረስ ብልቱ ለወሲብ ዝግጁ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ለግንኙነት ወደ ሚስቱ ሲጠጋ ብልቱ ይደክማል በዚህም ሳቢያ መገናኘት ሳይችል ይቀራል፡፡
📌 #የወሲብ_መሳን፡- ወንድ ከሚስቱ ጋር ወሲባዊ ግንኙነት ማድረግ አለመቻል ማለት ነዉ፡፡ በመሰረቱ ከሚስቱ እርቆም ሆነ ቀርቦ ብልቱ ለግንኙነት ዝግጁ አይሆንም፡፡
📌 #ስንፈተ_ወሲብ፡- ባል ከሚስቱ ጋር ግንኙነት ማድረግ የሚችለዉ በተራራቀ ጊዜያት ነዉ፡፡ ይህም ሆኖ እንኳ ወሲባዊ ግንኙነቱ ለአጭር ጊዜ ብቻ ነዉ የሚቆየዉ፡ ብልቱ ከትንሽ ግንኙነት በኋላ ይቀዘቅዛል፡፡
⚡️⚡️ #ህክምናዉ የመሰናክለ ወሲብ ህክምናን በተመለከተ 10 ዓይነት ዘዴዎችን ከላይ ተመልክተናል፡፡ የወሲብ መሳን ደግሞ በዶክተሮች ሊታከም ይችላል፡፡ የስንፈተ ወሲብ ህክምና እንደሚከተለዉ ነዉ፡፡
➊ 1 ኪሎ ንፁህ ማር እና 200 ግራም በንግስት ንብ የተመረተ ማር ማቅረብ
➋ ከዚያም አል ፋቲሃህ፣ አል ሸርህ አል ኢኽላስ፤ አል ፈለቅ፣ አል ናስ የተሰኙትን የቁርአን ምዕራፎች ሰባት ጊዜ ደጋግሞ በማሮቹ ላይ መቅራት
➌ ጠዋት ከምግብ በፊት 1 ማንኪያ፣ በምሳ ሰዓት ምግብ ከመብላቱ አንድ ሰዓት ቀደም ብሎ 1 ማንኪያ አራት ከመብላቱ አንድ ሰዓት ቀደም ብሎ አንድ ማንኪያ ይወስዳል
➍ እንደ ስንፈተ ወሲቡ መጠን ይህን ህክምና ሰወር ወይም ለሁለት
ወራት ያህል መከታተል፡፡ ህመሙ በአላህ ፈቃድ ይድናል፡፡
🌟 #በወንዶች_ላይ_የሚከሰት _ወሲብን_ቶሎ_የመጨረስ_ችግር_ህክምና
ወሲብን ቶሎ የመጨረስ ችግር በወንዶች ላይ አካላዊ (ተፈጥሯዊ) ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን እንግዲህ ዶክተሮች በተለያዩ ዘዴዎች ሊያክሙት ይችላሉ፡፡ ከነዚህም ዘዴዎች፡-
➊ ስሜትን የሚያቀዘቅዙ ቅባቶችን በመጠቀም
➋ በግንኙነት ወቅት ሌሎች ነገሮችን በማሰብ
➌ በግንኙነት ወቅት ከባድ የሂሳብ ስሌቶችን በማስላት
በሌላ በኩል ደግሞ ቶሎ የመጨረስ ችግር በጂኒ ምክንያት ሊከሰት ይችላል፡፡ ይህም የሚሆነዉ ጂኒዉ በወንዱ የብልት ፍሬዎች ዉስጥ ፈጣን የስሜት መነሳሳት በመፍጠር ወንዱ ቶሎ እንዲጨርስ ያደርገዋል፡፡ ይህ እንግዲህ በሚከተሉት ዘዴዎች በአላህ ፈቃድ ይታከማል፡፡
🔶 የአል ሙልክ ምዕራፍን ከመኝታ በፊት መቅራት ወይም ማዳመጥ
🔶 ኢያት አል ኩርሲይን በቀን ስባ ወይም ከሰባ በላይ መቅራት
🔶 የሚከተሉትን ዱዓዎች ጠዋትና ማታ ማለት
"ላኢላሀ ኢላ አላህ ወህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁ አል ሙልክ ወ ለሁ አል ሀምድ ወ ሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር ከሱቢህ ሶላት በኋላ 100 ጊዜ ለአንድ ወር ያህል ማለት
أعُوذُ بِكَلِمَاتِ اللهِ التَّامَّاتِ مِنْ شَرِّ مَا خَلَقَ
اسم الله الذي لا يَضُرُّ مَعَ الشيهِ شَيْءٌ فِي الْأَرْضِ وَلَا في السَّمَاءِ وَهُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ
☞ አ ዑምሩ በከሊማቲላሂ አል ታማህ ሚን ኩሊ ሸይጣንን ወሃማህ ወሚን ኩሊ ዓይኒን ላማህ
እነዚህን ዱዓዎች ጠዋትና ማታ ሶስት ግዜ ለተከታታይ ሶስት ወራት ማለት፡፡
✏️✏️ በሚቀጣለዉ ክፍል ➓ የሰዉ አይን ቡዳ ምን እንደሆነና ህክምናዉ እንዳስሳለን
#ክፍል 🔟
ይቀጥላል......
4any cmt👇👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
✍ አሚር ሰይድ
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
⭐️ #ክፍል👉 ስምንት 8⃣
🟢 #በሜካፕ_ላይ_የሚሰሩ_ሲህሮች
ኡስታዛህ ኡሙ ሩመይሳ ጥናት አድርጋ እንደተናገረችዉ
>>> በስጦታ ለተገኙ ቤት ውስጥ ለተገኙና በሚጠረጥሩት ሰው ለተሰጠ ሜካፖች ብቻ የሚያገለግሉ ናቸው፡፡
እቃው ከሚያመጣው ችግሮች በፊት ይህ ሲህር በቤት ውስጥ ተጥሎ ከተገኘ በሜካፕ ሲህር የተጣለበት ቤት ላይ የሚፈጠሩ ችግሮች፡፡
📌 #ሴቶች_ወይም_እቃውን_ያገኘው_ሰው በብዙ ሰው
አስቀያሚ ተብሎ የሚነገረው ይመስለዋል፡፡ ያገኘው ሰው ሁሉ በያዘው ነገር ላይ መጥፎ አስተያየት መስጠትን ይቀናዋል፡፡
📌 #በቤት_ውስጥ_በረካ_ይነሳል....ብዙውን ግዜ ይህ ሲህር ገላጣ ቦታ ሶፋ ላይ ጠረቤዛ ላይ ተጥሎ የሚሄድ አልያም ስጦታ የሚሰጥ ሲሆን
ያ ቤት አልያም የያዘው ሰው ሙሉ ለሙሉ በረካን የማጣት ችግሮች ይፈጠራሉ፡፡ የሚያገኙት ብር ብትን ብሎ የመጥፋት ለምን እዳዋሉት እስኪጠፋባቸው ድረስ፡፡ ረሀብ ጠኔ ቤት ውስጥ ሊፈጠር ይችላል፡፡
📌 #ቤት_ውስጥ_ተማሪዎች_ካሉ በጥናት ላይ መሳነፍ ሲያነቡ መታመም፡፡ ቤት ውስጥ ቁርአን የሚቀራ ሰው ካለ መሳነፍ ከሚቀራው ነገር መዘናጋትን ይጀምራሉ፡፡
📌 #ብዙውን_ግዜ_በባልና_ሚስት_መሀከል የሚፈጠሩ እርግዝናዎች እንዲጨናገፉ ያደርጋል፡፡ ይህም በሆስፒታል መውለድ ትችላላችሁ ተብለው እንኳ ቢወሰን እነርሱ ግን ልጅ ሊያገኙ አይቻላቸውም፡፡ ይህም የሩቅያህ ኡስታዞችን ተስፋ የሚያስቆርጥ ሲሆን ነገሮችን ሳይንቁ ጠለቅ ብሎ ማየቱ ውጤታማ ያደርጋል፡፡
📙 #ምልክቶቹ!!
➊ በመጀመርያ ሁለት ሳምንታት አስማታዊ የሆነ ለውጥ አለው፡፡ ሰው ሁሉ አማረብሽ/ አማረብህ ይልሀል ይልሻል፡፡
➋ ልክ ከሁለት ሳምንት አልያም ሜካፑን መጠቀም ስታቆሚ/ስታቆም ቡጉር በቡጉር አልያም የፊት መላላጥ ይኖራል፡፡ ይህም በአለርጂነት ወይም በእስቴሮይድ ኢፌክትነት የሚመጣ አይደለም ፡፡ ከዚህ በፊት ብዙ የሜካፕ ፕሮዳክት ተጠቃሚ ብትሆኚም ይህ ግን አደገኛ ነው፡፡
➌ ያለ ሜካፑ ካሳለፍሽ ፊት መቆጥቆጥ ፊት ማቃጠል ይመጣል፡፡ ይህም በቫዝሊን ብሎም በሎሽን አይጠፋም፡፡
➍ ንፋስ ፊት ላይ ይሰማናል፡፡ ሌላ ግዜ ፊታችን ፀሃይ እንኳን የማያቃጥለው አሁን ፊታችን በሙሉ ንፋስ የለ ፀሀይ ይሞክረናል ፡፡ ያሳክከናል ልክ ሲብስም እንደ ጥርስ ህመም ይጠዘጥዘናል፡፡
➎ ብጉር በብጉር ይሆናል ፊታችን...ይህን ልብ በሉት ሜካፑን እንኳን አንዴ ብንቀባው ከዛ ግዜ ጀምሮ ፊታችን ለምን 10 አመት አያልፈውም ቡግሩ የማያልቅ ይሆናል፡፡
➏ ማድያት ይፈጥራል.... ይህ ማድያት ቀን በቀን የሚላጥ የሚጠቁር የሚደማ የሚያቃጥል ነው፡፡ በዚህ ሰአት ብስጭት መናደድ ይከሰታል፡፡
➐ ውስጣችን ሰላም አያገኝም በተለይ ውዱእ ማድረግ ጀሀነም መግባት ይመስለናል፡፡ ውዱእም ስናደርግ ፊታችን በጣም ይታመማል፡፡
➑ ያለርሱ ከመውጣት ወኔ ሞራላችንን ይሰልበዋል፡፡
➒ አይናችን በባዶ ማልቀስ መቆጥቆጥ ይጀምረናል፡፡ ፊታችን የኛ አይመስለንም፡፡
➓ፊት ማበጥ ደባደቦ ከለር የሚያስጠላ የአፍ ሽታ ሳይቀር ይኖራል፡፡
🟡 #በሊፒስቲክ_ላይ_የሚሰሩ_ሲህሮች
እነኚህ ምልክቶች በስጦታ ለተገኙ ቤት ውስጥ ለተገኙና በሚጠረጥሩት ሰው ከተሰጠ ብቻ የሚያገለግሉ ናቸው፡፡
እቃው ከሚያመጣው ችግሮች በፊት ይህ ሲህር በቤት ውስጥ ተጥሎ ከተገኘ ሊፒስቲክ የተጣለበት ቤት ላይ የሚፈጠሩ ችግሮች፡፡
✏️ በቤት ውስጥ ፍቅር አይኖርም ይህም በተለይ ሴት ልጆች ላይ እጅግ ስነልቦናዊ ጫና እና ጭቆና ከዚህ ሰአት ኋላ ይፈጠራል፡፡
✏️ ሚስትም ትሁን የቤቱ ሴት ልጆች መልካቸው ብሎም አቋማቸው እጅግ ከሚስብ ምልከታ ወጥቶ ማስጠላት ያለ እድሜያቸው ማርጀት ይፈጠራል፡፡
✏️ በባልና ሚስት መካከል ያለ ፍቅ ወደ ጥላቻነት ይለወጣል፡፡
✏️ ሴቷ ውስጧ ጭንቀት ይነግሳል፡፡ ባሏን ላለማየት በርሱ ላለመታየት ብዙ ጥረቶችን ታደርጋለች፡፡ ባልም ትኩር ብሎ ሲያያት ህመሙ ይቀሰቀስባታል፡፡
✏️ እጅግ በጣም የሚያስጠላ ከንፈር ያለን ይመስለናል፡፡
✏️ ከንፈራችን በተደጋጋሚ ያብጣል ይሰነጣጠቃል፡፡ ማለስለሻ ነገሮችን ብንቀባ እንኳ፡፡
✏️ አፍ መሽተት ይጀምራል፡፡ ይህ የሲህር መነሻ ነውና፡፡
✏️ የምግብ ቃናዎቻችን ይለወጣሉ፡፡ የምንበላው አይጣፍጠንም ፡፡
✏️ ከንፈራችን መንፈሩ አልያም መቃጠሉን ሰዎች ባይረዱትም በሶፍት እንኳ መንካት ይከብዳል ከህመሙ የተነሳ፡፡
✏️ አፋችን ከተወሰነ ርቀት በላይ አይከፈትልንም፡፡ የበፊቱን የአፋችንን እቅስቃሴ ይገድበዋል፡፡
ለዚህ በሽታ ትኩስ ሽንት የሚያስነኩ አሉ ፡፡ ለግዜው ፍቱን ቢሆንላቸው እንኳ በንጋታው መድማት መላላጥ ይጀምራል፡፡
✏️ ሰው ሁሉ ከንፈራቸውን የሚያይ ይመስላቸዋል፡፡
እንዲያ እየታመሙ እንኳን ሊፒስቲክ ሳይቀቡ ወደ ውጭ መውጣት አይችሉም፡፡
✏️ውዱእ ሲያደርጉ ከንፈራቸውን አያስነኩም የሚሞቱ የሚመስላቸውም አሉ ፡፡
📕📕 #ለህክምናው_የሚረዱ_ቁሳቁሶች፡፡
🔶 ማኡዘምዘም
🔷 ጥቁር አዝሙድ ፍሬ
🔶 ወይራ ዘይት
🔷 ዘይቱን ናቸዉ...
🟢 #ስለ_ድገምት_ሊታወቁ_የሚገባቸዉ_ቁልፍ_ሀቆች
⚡️ የድግምት ምልክቶች ከልክፍት ምልክቶች ጋር ሊመሳሰሉ ይችላሉ
⚡️የማይለቅ የሆድ ህመም መኖሩ ድግምቱ የተበላ ወይም የተጠጣ መሆኑን ይጠቁማል፡፡
⚡️ የቁርአን ህክምና ይሳካ ዘንድ የሚከተሉት ሁለት ሁኔታዎች ሊሟሉ የግድ ይላል።
➊ ሃኪሙ የአላህን ትዕዛዛት የጠበቀ ሊሆን ይገባል።
➋ ታካሚዉ በቁርዓን ህክምና ፈዋሽነትና ዉጤታማነት ሊተማመንና ሊያምን ይገባል።
⚡️ በርካታ የድግምት ዓይነቶች አንድ ተመሳሳይ ምልክት ያሳያሉ፡፡ ይኸዉም ምልክት በደረት ዉስጥ ጭንቅ የሚል ስሜት ሲሆን በተለይም እኩለ ሌሊት ገደማ በጣም ይስተዋላል፡፡
⚡️ በጥቁር አዝሙድ ዘይት _ ላይ የአል ሩቅያ አንቀጾችን ትቀራና ታካሚዉ የሚያመዉን ቦታ ጠዋትና ማታ እንዲቀባዉ ታደርጋለህ። ይህም ለማንኛዉም የድግምት ዓይነት ያገለግላል፡፡ በቡኻሪ እንደተዘገበዉ ነብያችን (ሰ.ዐ.ወ)፡- “ጥቁር አዝሙድ ከሞት በቀር ለሁሉም ህመም መድሃኒት ናት” በማለት ተናግረዋል፡፡
⚡️ድግምቱ ያለበትን ቦታ በሚከተሉት ሁለት መንገዶች ለማወቅ ይቻላል።
➊ የድግምቱ እንደራሴ ጂኒ ድግምቱ ያለበትን ቦታ ሊናገር ይችላል። ነገር ግን በተባለዉ ቦታ ፈልጎ የሚያመጣዉ ሰዉ ልከህ ሳታረጋግጥ አትመነዉ፡፡ የተላከዉ ሰዉ ካገኘዉ ጂኒዉ እዉነቱን ነዉ ማለት ነዉ፡
ካልሆነ ግን ጂኒዎች በጣም ይዋሻሉ፡፡
➋ ሌላኛዉ መንገድ ደግሞ ታካሚዉ ወይም ሃኪሙ በእምነት በእርጋታ፣ አላህን በመፍራት ሁለት ረከዓ ሶላት በሌሊት በመጨረሻዉ ክፍለ ጊዜ ዉስጥ ይሰግዳል፡፡ በዚህ ሶላት ዉስጥ ድግምቱ ያለበትን ቦታ እንዲያሳዉቀዉ አላህን ይለምናል፡፡ ከዚያማ በኋላ ድግምቱ ስላለበት ቦታ ህልም ልታይ ትችላለህ ወይም የድግምቱ ቦታ እዚህ ነዉ የሚል ስሜት በዉስጥህ ሊፈጠር ይችላል ወይም ደግሞ የድግምቱ ቦታ እዚህ ይሆናል ብሎ ዉስጥህ ሊያምን ይችላል፡፡ ከነዚህ አንዱ ሲከሰት አላህን አመስግን፡ ደግምቱንም ለማክሸፍ ተንቀሳቀስ
#ክፍል 9⃣
ይቀጥላል.......
👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
⚡️⚡️#ሲህር_ጂን_አይነጥላን_ራስን_በራስ_ማከም⚡️
✍ አሚር ሰይድ
#ምንጭ ☞ድግምት(ሲህር) ምንነቱና ፈዉሱ ከሚለዉ
መፅሀፍ 70% የተዘጋጀ
☞30%በመጠየቅና ከሌላ ካነበብኩት የተዘጋጀ
⭐️ #ክፍል👉 ሰባት 7⃣
🔰🔰 #ሳይታይ_የሚጮኽ_ድግምት(ሲህር)
#ሳይታይ የሚጮህ ድገምት አንዲት ይከሰታል?
ደጋሚው ድግምት ወደ ተደረገበት ሰዉ ጂኒ ይልካል። ይህን ስጡ በህልሙም በዉኑም እንዲያዋክበዉ ጂኒዉን ያዘዋል፡፡ ጂኒዉም በህልሙ የሚያጠቃዉ አስፈሪ አዉሬ በመምሰል፣ በዉኑም በስሙ እየጠራዉ እንዲያዉም ሰዉዬዉ በሚያዉቃቸዉ እና በማያዉቃቸዉ ሰዎች ድምፆች እየተጣራ ግራ ያጋበዋል፡፡ ዘመዱንም ባእዱንም እንዲጠራጠር ያደርገዋል፡፡
#ምልክቶቹም እንደ ድግምቱ ክብደትና ቅለት ይለያያሉ፡፡ አንዳንዴም የህመሙ ምልክቶች አይለዉ ወደ እብደት ሊያደርሱ ሲችሉ ሌላ ግዜም አንሰዉ ከዉስወሳ ላይዘሉ ይችላሉ፡፡
🟢 #የዚህ_ድግምት_ምልክቶች
☞ አስፈሪ ቀዠቶችን ማየት
☞ የሆነ ነገር ሲጠራዉ በህልሙ ያያል
☞ በዉኑ (በቀን) የሚያናግረዉ ድምፅ ይሰማል ሰዉ ግን አያይም
☞ በብዛት መወሳወስ ይበዛበታል
☞ ዘመዶቹንና ጓደኞቹን በትንሽ በትልቁ ይጠራጠራል
☞ እንስሳት ሲያሳድዱት በህልሙ ያያል
☞ ከከፍተኛ ቦታ ላይ ሲወድቅ በህልሙ ያያል
🟡 #ሳይታይ_የሚጮኽ_ድግምት_ህክምና
1) የአል ሩቅያ አንቀጾችን በታማሚዉ ላይ ትቀራለህ፡፡
2) እራሱን ሲስት ከዚህ ቀደም እንዳየነዉ ታደርጋለህ፡፡
3) እራሱን ካልሳተ ታካሚዉ የሚከተሉትን ያደርጋል፡፡
➢ ዉዱእ አድርጎ እና ኢያት አል ኩርሲይ ቀርቶ መተኛት
➢ ከመኝታ በፊት ሁለት መዳፎቹን ዘርግቶ አል ኢኽላስ፤ አል ፈለቅ እና አሳ ናስን መቅራትና መዳፎቹ ላይ እንትፍ እንትፍ በማለት መላ አካላቱን መዳበስ፡፡ ይህንንም ሶስት ግዜ መደጋገም።
➢ የአል ሳፋት ምዕራፍን ጠዋት ላይ፣ የአል ዱኻን ምዕራፍን በመኝታ ጊዜ መቅራት ወይም መቅራት ካልተቻለ በስልክ ማዳመጥ
➢ በየሶስት ቀኑ የአል በቀራ ምዕራፍን መቅራት ወይም ማዳመጥ
> ጠዋት እና ማታ የሚከተለዉን ዚክር ሰባት ጊዜ ማለት احَسْيَ اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ وَهُوَ رَبُّ الْعَرْشِ العَظِيمِ،
ሀስቢየ ላሁ፡ ላኢላሃ ኢላ ሁወ ዓለይሂ ተወከልቱ፣ ወሁወ ረቡል አርሺያል አዚም
➢ ከመኝታ በፊት የአል በቀራ ምዕራፍ የመጨረሻዉን ሁለት አንቀጾች መቅራት
የሚከተሉት የቁርአን አንቀጾች በስልክ በቀን ሶስት .. ያዳምጣል፡፡ እነሱም፡- ፉሲለት፤ አል ፈትህ አል ጂን
➢ እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን በሙሉ ለአንድ : ወር : በተከታታይ መፈጸም፡፡ ፈዉስ በአላህ ፈቃድ ይመጣል።
🟢 #ሲህር_አል_ሃዋቲፍ (የመጥፎ ህልሞችና ለሰው የማይሰሙ የጥሪ ድምፆች ሲህር)
ዶክተር አቡ ፈርሀን መጣጥፍ ላይ የተወሰደ
#ምልክቶቹ
➊ በሚተኙበት ወቅት ሁሌም ቅዠት መኖር ፡፡ በጣም የሚያስፈሩ የሚያስጠሉና የተቆራረጡ ህልሞችን ማየት፡፡
➋ ታማሚው በሚተኛበት ወቅት በህልሙ ሰው ስሙን ሲጠራው ይሰማል፡፡
➌ ታማሚው ሹክሹክታዎችን (ውስዋሶችን) ያዳምጣል፡፡
➍ ታማሚው ቤተሰቡብን ጓደኞቹን ልጆቹን ሳይቀር መጠራጠር ይጀምራል፡፡
➎ ታማሚው ከእንቅልፉ እየነቃ ሳለ ለሌላ የማይሰማ ነገር ግን ለርሱ የሚሰማ ድምፅ ይኖራል፡፡
➏ ታማሚው በእንቅልፍ ውስጥ ከከፍተኛ ቦታ ሲወድቁ ማየት እና መባነን፡፡
➐ በህልሙ ታማሚው በእንስሳት እየተሳደደ የሚበላ ነገር እያሯሯጠው ይነቃል፡፡
ለዚህም ህክምና
🔻 ሲተኙ በሱና መተኛት
🔻 ከእንቅልፎ ሲባንኑ ዱአ አድርገው መተኛት
🔻 አያተል ኩርሲ መቅራት በተደጋጋሚ መቅራት ነዉ
🟡 #በስራ_ቦታ_ላይ_የሚሰራ_ሲህር
ከዶክተር አቡ ፈርሀን መጣጥፍ ላይ የተወሰደ፡፡
……እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ፡፡ ሷሂሮችኮ አይተኙላችሁም፡፡ ከቤታችሁ አልፎም ስራ ቦታችሁን አጥንተው በዚያ በምትሰሩበት ሲህር ቢደቁሳችሁ እንኳ በምታገግሙበት ስራ ቦታችሁ የሀላልን ገንዘብ የምታመጡበት ቦታ ድረስ አንዴ ታካሚ አንዴ ባለጉዳይ አንዴ ገዢ ሆነው መጥተው ሲህር ጥለውባችሁ ይሄዳሉ፡፡ አሏህም ከእንዲህ አይነቶቹ ጀነት ሀራም ከተደረገባቸው ወራዶች ይጠብቃችሁ፡፡ አጅርን በስቃይ የሚሸምት ሰው ማለት ሲህር ተሰርቶበት ሰብር ያደረገ በሰው ነው……
#ምልክቶቹ
🔶 የስራ ቦታ ገበያ መቀዝቀዝ፡
🔷 አንተጋ ወይም አንቺ ጋ ኳሊቲ የሆነ እቃ ማግኘት እየቻለ ያ ሰው ግን ያንቺን ወይም ያንተን እቃ አይገዛም፡፡ ይልቁንም ያን እቃ ትቶ የማይረቡ እቃዎችን ይገዛል፡፡
🔶 ብዙውን ግዜ በነጋዴዎች ላይ የሚታየው እቃ ይበዳደራሉ፡፡ ሌሎች ካንተ ወይም ካንቺ የሚበደሩት እቃ ተፈልጎ ሲሸጥላቸው አልያም አንተ ጋር ተመሳሳይ እቃ 50 ብር እየተሸጠ ሊያውም ፈላጊ ሳይኖረው ቀርቶ ልክ ሌላው እጅ ላይ ግን ሲገባ እስከ አምስት መቶ ብር ድረስ ሲሸጥ እውነትም እኔ ላይ ሲህር አለ ያስብላል፡፡
🔷 ከውጭ ተፈላጊ እቃ ጭነው አምጥተው ባልሆነ ምክንያት ያ እቃ እነሱ እጅ ውስጥ መግባት አይችልም፡፡ ያም ሲባል እቃው ላይ ችግር ሳይኖር አመጣጡ ስርአቱን ጠብቆ መጥቶ በፍፁም ሲህር የተሰራበት እጅ ውስጥ ከመግባት ይርቃል፡፡ ቆይቶም ከከሰረ እቃው ከተባለሸ ኋላ ይወጣል፡፡ ይህ ሲደጋገም ለነጋዴው ይታወቃል፡፡
🔶 የድርጅት ባለቤት ሆነው ሳለ ድርጅቶ ትርፋማ ሆኖ እየተንቀሳቀሰ አንድ የወጪ ቀዳዳዎች እጅግ ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ ድርጅቱ እራሱን በራሱ የሚበላ ይሆናል፡፡ ወደ ቤትዎ ይዘውት የሚሄዱት ትርፍ የለም፡፡
🔷 የቢሮ ሰራተኛ ከሆኑ፡፡ ወደ መስርያ ቤት መሄድ ሞት መስሎ ነው የሚታየው፡፡ ይህም ተጫዋች ሁነው አካባቢው እጅግ የሚወዱት እንደነበረ ቢገነዘቡም ወደ ቦታው መሄድ ሰላም አይሰጦትም፡፡ ይህ ነጋዴውም ተቀጣሪውም የድርጅት ባለቤቱም ላይ የሚታይ ነው፡፡
🔶 ከአለቃ ጋር ባልሆነ በሆነው መጣላት፡፡ ስራዎትን በአግባቡ ሰርተው ሳለ ሌላው ባልሰራው እንኳ ሲመሰገን እርሶ ግን ማንም መስራት የማይችለውን ሰርተው ምስጋና ቢስ ተወቃሽ ኖት፡፡
🔷 ስለ ስራ ሲያስቡ ፍርሃት ጭንቀት መረበሽ ይህ ዋነኛ ምልቱ ሲሆን ሲህሩ መጀመሩን መጠንከሩንም በዚሁ ማወቅ ይቻላል፡፡
🔶 የሚፈልጉት እረፍት ብቻ ነው፡፡ ንግዱ አትራፊ ሁኖ ደሞዝዎ ጥሩ ሁኖ እርሶ ግን እረፍት ብቻ ይፈልጋሉ፡፡ ስራዎትን ዞር ብለው ባያዩት ይመርጣሉ፡፡ ይበልጡኑ መታመም ይጀምራሉ፡፡ በዚህም ሰአት ከገጠሙን ውስጥ ያለ አቅም የሚወፍሩና ከስተው ከስተው በአጥንት ብቻ የሚቀሩትንም ታዝበናል፡፡
🔷 ካሁን ካሁን ከስራዬ ተባረርኩ ፡፡ ካሁን ካሁን ከሰርኩ ፡፡ ካሁን ካሁን እንዲህ እንዲያ ሆንኩ በሚል ፍርሃት ብቻ ከአላህም እንዲርቁ ያደርጎታል፡፡ ሰላቶ ላይ እስከዚም ይሆናሉ፡፡ ኢባዳዎ ላይ ያዘናጋዎታል👇👇👇
ለሴቶች ጆሮ ሸክም ቃል ቢኖር ሁለተኛ ሚስት ላግባ የምትለዉ ንግግር መችም አትዋጣላቸዉ...ሁለተኛ ያገቡ ወንዶች ብዙዎች ደስታ አጥተዋል ወይ የመጀመሪያ ወይ ሁለተኛዋ ሲህር እያስደረጉባቸዉ
ከአንዷ ጋር ይጣላሉ ቤተሰብ ሲበተን እየተስተዋለ ነዉ፡፡ የሚገርመዉ አንዷ ጋር ሲሆኑ ጤነኛ የሆኑት ሌላ ሚስት ጋር ለመገናኘት አይችሉም ስንፈተ ወሲብ ይገጥማቸዋል፡፡ ብቻ ሁለተኛ ሚስት የሚያገባ አላህ ካዘነለት ከጠበቀዉ በቀር ከባድ ነዉ ፈተናዉ ሙሲባዉ ብዙ ነዉ፡፡
🌐 #መስተፋቅር_በተደረገባት_ሴት_የሚታዩ_ምልክቶች
✏️ ሴቷ ወይም ወንዱ ስለ አንድ ሰው በአንድ ወቅት ስላዩት ይሁን ስለሰሙት ሰው ከምንግዜውም በላይ ማሰብ ማሰላሰል ይጀምራሉ፡፡ ያን ሰው ከዚህ በፊት ሊቀርቡት ይገባል፡፡ ቀርበውትም ከእህትነት ወይም ከወንድምነት የዘለለ ፍላጎት የሌላቸው ሲሆን ይህ ሲህር ከተሰራባቸው ጀምሮ ግን ስለዚያ ሰው ህልም ማየት ማሰብ ፡፡
✏️ ያን ሰው አብዝቶ መናፈቅ ለደቂቃ ከነርሱ ጋር መሆን ከምንም በላይ ለነርሱ ልዩ ስሜትን ይፈጥራል፡፡ ከነርሱ ሲለያዩ እጅግ በጣም መፍራት ይፈጠርባቸዋል፡፡
✏️ ከርሱ ወይም ከርሷ ሲጣሉ እራስን ወደማጥፋት ማምራት ፡፡ ያለ ምንም ጥያቄና ቅድመ ሁኔታ እራስን ወደማጥፋት ሲሄዱ የገዛ ማንነቶ ህሊናዎ እንኳን ሊከላከሎት አይችልም፡፡ ይህን ሲያደርጉ ሰው እንዲያዮት ይፈልጋሉ፡፡ ይህ ሲህር ለየት የሚለው በድብቅ እራስን ማጥፋት የሚያስፈፅም ሳይሆን በምስክር ፊት እራሶን ሊያጠፉ ይቃጣሉ፡፡
✏️ ድንገት ከመሬት ተነስተው ባልሆነና ባልታሰበ ሁኔታ ስለወደዱት ሰው መጥፎነትና አይረቤነት ቢነገራቸው እንኳን አለመስማት፡፡ ብሎም ይህ ከምቀኝነት የመነጨ ወሬ መሆኑን አምኖ ሰውን በሙሉ ለወደዱት ሰው ሲሉ መራቅና መጣላት፡፡
✏️ ያን ሰው እስከማምለክ መሞከር ፡፡ በዚያ ሰው ይምላሉ በዚያ ሰውም እድለኛ ይሆናሉ፡፡ ያ ሲህር ያደረገባቸው ሰው ላይ ሰው የማያየውን ልዩ እና አስደሳች ፀባዮችን እነርሱ ብቻ ይታያቸዋል፡፡
✏️ ልብ ሊባል የሚገባዉ ነጀር ሲህሩን ያደረገው ሰው ለአፍቃሪው የተለየ ስሜት የለውም ፡፡ በአፍቃሪው ላይ መጥፎ ነገሮችን ሲሰራ ነው የሚታየው አፍቃሪውን ሲያሰቃይ ነው የሚታየው፡፡ ይህ ግን ለአፍቃሪው አይታወቀውም፡፡
✏️ አልፎ አልፎ ጥዋትም ይሁን ከሰአት እንቅልፍ ተኝተው ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ወደ ማንነት መመለስና በሰሩት ስራ በሙሉ መፀፀት እራስን በጣም መጥላት፡፡ እነኚህ ሰዎች በዚህ ወቅት ከሰው ደብቀው የሚያስቀምጡት ዲያሪ ነክ ነገሮች ሊኖሩዋቸው ይችላል፡፡ ፍፁምም ከሰው የተደበቁ ደብተሮች ብዙ ምስጢር የያዙ ነገሮችን ይይዛሉ፡፡ ይህን ግን ለማንም ቢሆን አያሳዩም፡፡ ሞትንም ይመርጣሉ፡፡ ይሁንና ወደ ቀድሞው ማንነት በሚገቡበት በዚያች ቅፅበት ቡና በሚጠጡበትና በቃ ሲገፋፋቸዉ ወ ያን ምስጢር የማሳየት ግፊታቸው ሀይለኛ ነው፡፡
✏️ ጥርሷን በጣም ታፋጫለች ይህም በተኛችበት ጥርስ ጥርሶቿን መብላት ትጀምራለች፡፡
✏️ ከኢማን ከሰላት ከቂርአት ትሸሻለች፡፡ ይህ ሰው ቢርቃት እንኳ ካላገባሁት ሙቼ እገኛለሁ ትላለች፡፡
✏️ ይህ ሲህር ሲጀምር ሰውየውን መፍራት የምትጀምር ሲሆን ያም ፍራቻ ወደ ወሲባዊ ፍቅር ተለዋጭ ነው፡፡
✏️ ጅኖችም በዚህች ሴት አናት ላይ ያረፉ ሲሆኑ ይህች ሴት አብዛኛውን ግዜ የራስ ህመም(ማይግሬን) አለባት በመድሀኒት የማይፈታ፡፡
✏️ ብቻን ማልቀስ ብቸኝነት መሰማት ከሰዎች መሀል ውስጥ ሁና ብቸኝነት ይሰማታል፡፡ ይህም ስለርሱ ላታስብ ትችላለች ግና ብቸኝነቱ ከባድ ነው፡፡
🔰🔰 ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች የተወሰነም ቢሆን ምልክቱ ከአንቺ ጋር ካለ
👉 በመጀመርያ ዳእዋዎችን ማዳመጥ ስለ ቀብር ስለ አላህ ውዴታ የሚያስተምሩ ዳእዋዎችን መከታተል፡፡
👉 በቀጣይም አያተል ኩርሲን መቅራት ያም ልጁን ስታስብ መቅራቱ ይረዳታል፡፡
👉 በመቀጠልም ውዱእን መጠበቅ ከውዱእ ውጭ አለመሆንና
👉 የሰሃቦችን ታሪኮች ማንበብ
👉 ስሜት ቀስቃሽ ከሆኑ ነገሮች በሙሉ ልትርቅ ይገባታል፡፡
⚠️⚠️ እንዲህ አይነት ነገር እንዳይገጥማችሁም ምሽት ላይ በአዳበ ነውም መሰረት እንቅልፍን መተኛት ጥዋትም በሚነሱበት ወቅት አያተል ኩርሲን ማንበብ ተገቢ ነው፡፡
🟢 #የመስተፋቅር_ህክምና
➊ የአል ሩቅያ አንቀጾችን በታካሚዉ ላይ ትቀራለህ፡፡ ከአል ሩቅያ አንቀጾች ዉስጥ የአል በቀራ ምዕራፍ አንቀጽ 102 ን በመተዉ በምትኩ ከአል ተጋቡን ምዕራፍ አንቀጽ 14፣ 15 እና 16 መቅራት
➋ በመስተፋቅር ድግምት የተለከፈ ሰዉ ሲቀራበት አብዛኛዉን ጊዜ እራሱን አይስትም፡፡ ሆኖም በእጆቹና በእግሮቹ አካባቢ የመደንዘዝ ስሜት ይሰማዋል።
>> እራስ ምታት፣
>> ደረት አካባቢ የማፈን
>> ከፍተኛ የ የሆድ ህመም ይሰማዋል (በተለይ ሆዱን የሚያመዉ ድግምቱን በልቶት ወይም ጠጥቶት ከሆነ ነዉ)፡፡ ምን አልባትም : ሊያስመልሰዉ ሁሉ ይችላል፡፡ በተለይ የሆድ ህመም የሚሰማዉ ወይም ለማስመለስ የሚቃጣዉ ከሆነ
☞ ሱረቱ ዩኑስ 81-82
☞ ሱረቱ ዩኑስ81
☞ ሱረቱል ጦሀ 69
☞ ሱረቱል በቀራ 255
☞ የቁርአን አንቀጾች
በዉሃ ላይ ትቀራና ፊት ለፊትህ እንዲጠጣዉ አድርግ፡፡
ታካሚዉ እነዚህ የቁርአን አንቀፆች የተቀሩበትን ዉሃ ሲጠጣ ቢጫ ወይም ቀይ ወይም ጥቁር ነገር ካስመለሰዉ ድግምቱ ፈሰደ (ተፈታ) ማለት ነዉና ምስጋና ለአላህ አድርስ፡፡
ይህ ነገር ካልተከሰተ ደግሞ እነዚህ አንቀች የተቀሩበትን ዉሀ ለሶስት ተከታታይ ሳምንታት ወይም እንደ አስፈላጊነቱ ከዚያ በላይ ድግምቱ እስኪፈታ ድረስ ይጠጣ፡፡ ይህን ሲያደርግ ሚስቱ ማወቅ የለባትም፡፡ ምክንያቱም ህክምና እየተከታተለ መሆኑን ካወቀች ዳግመኛ ልታሳድስበት ትችላለችና፡፡
ሴትም ከሆነች የተደረገባት ባልየዉ ማወቅ የለበትም መልሶ ሂዶ ሊያሳድስ ይችላልና...ከትዳር በፊት ከሆነ የተደረገዉ ዝምታ ነዉ የሚሻለዉ ከሰማ ወይ ከሰማች መልሶ ማሳደሱ በጣም ቀላል ስለሆነ ....
#ክፍል 7⃣
ይቀጥላል.....
አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ👇👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
➋ ድግምቱ ያለበትን ቦታ ትጠይቀዋለህ፡፡ ነገር ግን የነገረህን እስከምታረጋግጥ ድረስ አትመነዉ። ድግምቱ እዚህ ቦታ ይገኛል ካለህ የሚያመጣዉ ሰዉ ትልካለህ፡፡ የተላከዉም ሰዉ ድግምቱን በተባለበት ቦታ ካገኘዉ መልካም፡፡ ካላገኘዉ ግን ጅኑ ዋሽቷል ማለት ነዉ፡፡ ጂኒዎች ደግሞ በጣም ዉሸታሞች ናቸዉ፡፡
➌ የድግምቱ እንደራሴ እሱ ብቻ እንደሆነ ወይም ሌላ ጅን ከሱ ጋር አብሮት እንዳለ ጠይቀዉ፡፡ ሌላ ጅን አብሮት ካለ አቅርበዉ በለዉ፡፡
➍ አንዳንዴ ጂኒዎች ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ድግምቱን ያሰራዉ አገሌ ነዉ በማለት ይናገራሉ። እንዲህ ካለህ ጀኒዉን አትመነዉ፡፡ ምክንያቱም ሰዎች መካከል ጠብ እንዲፈጠር ስለሚፈልጉ ነዉ ይህን የሚናገሩት፡፡ ዚህም በላይ ጂኒዉ ጠንቋይ በማገልገሉ ሳቢያ ፋሲቅ ስለሆነ ምስክርነቱ በሸሪዓ ህግ መሠረት ዉድቅ ነዉ፡፡
#እናንተ_ያመናችሁ_ሆይ ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ኾናች ህዝቦችን እንዳትጎዱና በሠራችሁት ነገር ላይ ተፀፃቾች እንዳትሆኑ አረጋግጡ፡፡(አል ሁጁራት፡ 6)
🔶 #ድግምቱን_ካገኘኸዉ_እነዚህን_ሁለት_የቁርአን_አንቀፅ_ትቀራለህ ።
☞ አል አእራፍ 117-122 እና
☞ ዩኑስ 8
እነዚህን የቁርአን አንቀጾች በዉሀ ላይ ስትቀራ ካፍህ የሚወጣዉ ትንፋሽህ በምትቀራበት ዉሀ ላይ እንዲያርፍ አድርገህ ቅራ ፡፡ ከዚያም ድግምቱን በሩቃ ዉሀ ዉስጥ ረዘም ላለ ጊዜያት በመዘፍዘፍ ታማሟዋለህ። ከዚያም ከሰዉ ርቆ በሚገኝ ቦታ ላይ ይደፋል።
⏩ #ድግምቱን_ጠጥቶት_በልቶት_ነዉ ካለህ ታካሚዉን ብዙ ጊዜ የሆድ ህመም ይሰማዉ እንደሆነ ትጠይቀዋለህ፡፡ ህመም የሚሰማዉ ከሆነ ድግምቱን በልቶታል ወይም ጠጥቶታል ማለት ነዉ፡፡ ጂኒዉ የነገረህ እዉነት መሆኑን ስትረዳ እንዲወጣና ዳግመኛ እንዳይመለስ ለስለስ ባለ አነጋገር ትነግረዋለህ፡፡ በዚህም በአላህ ፈቃድ ድግምቱን ትፈታዋለህ፡፡ በመቀጠል ከላይ የተጠቀሱትን የቁርአን አንቀጾች እና የአል በቀራህ ምዕራፍ አንቀፅ 102 በዉሀ ላይ ደግመህ ትቀራለህ ከዚህ ዉሀም ታካሚዉ ለተወሰኑ ቀናት መጠጣትና መታጠብ አለበት፡፡
⏩ #ድግምቱን_ረግጦት ወይም በላቡ ፋና በፀጉሩ፣ በልብሱ ቁራጭ ነዉ ድግምት የተደረገበት ካለህ..... ከላይ የተጠቀሱትን የቁርአን አንቀፆች በዉሀ ላይ ትቀራለህ ከዚያም ታካሚዉ ለተወሰኑ ቀናት እንዲጠጣ እና እንዲታጠብበት ታደርጋለህ፡፡ ታካሚዉ የሚታጠበዉ ከባኞ ቤት ዉጭ መሆን ይኖርበታል፡፡ የታጠበበትን ዉሀ ከመታጠቢያ ቤት ዉጭ በጡሀራ ቦታ ላይ ይድፋዉ፡፡ ይህንንም ህመሙ እስከሚቆም ድረስ መከታተልና መደጋገም አለበት፡፡ ከዚህ በኋላ ጂኒዉ እንዲወጣ እና ዳግመኛ እንዳይመለስ ቃል ኪዳን አስገብተህ እንዲወጣ እዘዘዉ፡፡
ከተወሰነ ቀን ቡሀላ የሩቅያ አንቀፆችን ትቀራበታለህ፡፡ በምትቀራበት ወቅት ምንም ዓይነት ስሜት ካልተሰማዉ ምስጋና ለአላህ ነዉ ድግምቱ አብቅቷል (ተፈትቷል) ማለት ነዉ፡፡ ነገር ግን ስትቀራበት እራሱን ከሳተ ጂኒዉ ዋሽቷል አልወጣም ተመልሶ ሰዉየዉ ጋር መጥቷል ማለት ነዉ፡፡ ስለዚህ ያልወጣበትን ምክንያት ጠይቀዉ ለስለስ ባለ መልኩ አነጋግረዉ። በዚህ ሁኔታ ለመዉጣት ከተስማማ ምስጋና ለአላህ ነዉ፡፡ ለመዉጣት ካልተስማማ ግን ቁርአን መቅራት በቅቶት እስኪጠግብ ድረስ በቁርአን እየቀሩ መልሶ እንዳይመለስ ማድረግ ነዉ
☑️ የሩቅያ አንቀፆችን ስትቀራበት ታካሚዉ እራሱን ላይስት ይችላል. ነገር ግን
🔸መንቀጥቀጥ
🔹መንዘርዘር፤
🔸ጭንቀት
🔹 በሰዉነቱ ዉስጥ ንዝረት ወይም የሚወር ስሜት የሚሰማዉ ከሆነ
አያት አል ኩርሲ ለ አንድ ሰዓት ያህል በመደጋገም ተቀርቶ የተቀመጠ በስልኩ በመጫን በኤርፎን አድርጎ በቀን ሶስት ጊዜ በተከታታይ ለአንድ ወር ያዳምጣል፡፡
#በዚህ_ካልዳነ_ግን
>> አል ሷፋት፤
>> አል ዱኻን፣
>> አል ጂን የተሰኙትን የቁርአን : ምዕራፎች አሁንም በስልኩ በቀን ሶስት ጊዜ ለተከታታይ ሶስት ሳምንታት ያዳምጣል። በዚህም በአላህ ፈቃድ ይድናል፡፡ ምን አልባት ያልዳነ እንደሆነ የሚያዳምጥበትን ቀን ማራዘም አለብት
2⃣ #ሁለተኛ_ዘዴ_ህክምና
የሩቅያ አንቀፆች በሚቀሩበት ጊዜ መንቀጠቀጥ ጭንቀት ከፍተኛ የራስ ምታት እና ሰዉነቱን ሲነዝረዉ ይሰማዋል (ሰዉነቱን እንደ ኤሌክትሪክ ያለ ንዝረት ይነዝረዋል) ነገር ግን እራሱን አይስትም፣ ይህ ከሆነ የሩቅያ አንቀፆችን ሶስት ጊዜ በመደጋገም ትቀራበታለህ፡፡ ይሄኔ እራሱን ከሳተ መጀመሪያ ላይ በተገለፀዉ መልኩ ታነጋግረዋለህ።
ነገር ግን ታካሚዉ እራሱን አልሳተም ብቻ የሚያንቀጠቅጠዉ የሚነዝረዉ ጭንቀቱ እና የራስ ምታቱ ቀለል እያለዉ ከሆነ ለተወሱ ቀናት የሩቅያ አንቀፆችን ቅራበት በአላህ ፈቃድ ይድናል፡፡ ከዚህ ሁሉ በኋላ ካልዳነ የሚከተለዉን ማድረግ ይኖርበታል፡፡
➊ ሙሉዉን የአል ሷፋት ምዕራፍ አንድ ጊዜ እና አያት አል ኩርሲን በመደጋገም የተቀራበትን በስልኩ ይጫን ታካሚዉ በቀን ሶስት ጊዜ ያዳምጣል፡፡
➋ ሶላት በጀመዓ መስገድ አለበት
➌
لا إله إلا اللَّهُ وَحْدَهُ لا شَرِيكَ لَهُ፣ لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قدِي
ከሱብሂ ሶላት ቡሀላ 100 ጊዜ ለአንድ ወር ያህል ማለት
ይህን ህክምና በሚከታተልበት በመጀመሪያዎቹ 10 እና 15 ቀናት ዉስጥ ህመሙ ሊባባስ እንደሚችል እና ቀስ በቀስ እየቀለለ እንደሚሄድ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ በወሩ መጨረሻ በአላህ ፈቃድ ከህመሙ ሙሉ በሙሉ ይድናል፡፡ ከዚያም ሲቀራበት በአላህ ፈቃድ ምንም ዓይነት ህመም አይሰማዉም፡፡
3⃣ #ሶስተኛዉ_ዘዴ_ህክምና
ሩቅያ በሚቀራበት ጊዜ ታካሚዉ ምንም ዓይነት ህመም አይሰማም፡፡ በዚህ ጊዜ ከላይ ያየናቸዉን የድግምት ምልክቶችን ትጠይቀዋለህ፡፡ ምንም ዓይነት ምልክት ካላገኘህበት አልተደረገበትም ማለት ነዉ። ይበልጥ እርግጠኛ ለመሆን ሩቅያ ሶስት ጊዜ ደጋጋመህ ቅራበት፡፡ የድግምት ምልክቶች ታይተዉበት ሩቅያ ተደጋግሞ ተቀርቶበት ምንም ሊሰማዉ ካልቻለ (ይህ ዓይነት ሁኔታ እጅግ በጣም አልፎ አልፎ የሚከሰት ነዉ) የሚከተለዉን እንዲፈጽም ታደርጋለህ፡፡ ድግምት
➊) استغفر الله
“አስተግፊሩላህ” በቀን 100 ጊዜ እና ከዚያ በላይ ማለት
➋) ከቁርአን ዉስጥ የያሲን፣ የአል ዱኻን፣ የእል ጂን ምዕራፎችን በስልክ ጭነህ በቀን ሶስት ጊዜ እንዲያዳምጥ ማድረግ
➌) لاحَولَ أَلَا قُوَّةَ إِلَّا بِاللَّهِ
ላ ሃዉለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ¨ በቀን 100 ጊዜ እና ከዚያ በላይ ማለት
እነዚህ የተጠቀሱትን ታካሚዉ ለአንድ ወር በተከታታይ ይተገብርል
#ክፍል 6⃣
ይቀጥላል.........
አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ👇👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
⚡️ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
💠 #ሰባተኛዉ ዘዴ:-የእጅ መዳፍ
ድግምተኛው ለአቅመ አዳም ያልደረሰ ልጅ ያመጣል፡፡ ልጁም ዉዱዕ ማድረግ የለበትም፡፡ በልጁ የግራ እጅ
አራት ማዓዘን ይስላል። ከዚያም ክህደት ያዘሉ ድግምቶችን በመዕዘኑ ዙሪያ ይፅፋል። በማዕዘኑ መሀል ላይ ሰማያዊ ፅጌረዳ እና ዘይት ወይም ስማያዊ ቀለም ያስቀምጣል፡፡ ሬክታንግል ቅርፅ ባለዉ ወረቀት ላይ ደግሞ ክህደት ያዘሉ ድግምቶችን ይፅፍና በልጁ ፊት ላይ ጣል በማድረግ እንዳትንሸራተት ደግሞ ቆብ ይጭንባታል፡፡ ከዚያም ልጁን በወፍራም ልብስ ይሸፋፍነዋል። ተሸፋፍኖ ጨለማ ዉስጥ ስለሆነ ባይታየዉም እንኳ ይህ ሁሉ ሲደረግ እጁ ላይ ማፍጠጥ አለበት፡፡ ከዚያ በኋላ ድግምተኛው ከፍተኛ ክህደት የያዙ ድግምቶችን ማንበልበል ይጀምራል። በዚህ ጊዜ አካባቢዉ በብርሃን የተሞላ መስሎ ለልጁ ይታየዋል በመዳፉ ላይ የምትሽከረከር ምስልም ያያል፡፡
ምን ይታይሃል ሲል ድግምተኛው ልጁን ይጠይቀዋል፡፡ ልጁም ሰዉ የሚመስል ነገር ይታየኛል” ይላል፡፡ ድግምተኛዉም ለምታየዉ ምስል እንዲህ እንዲህ ይልሀል ብለህ ንገረዉ ይለዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ምስሉ በተባለዉ መሰረት ይንቀሳቀሳል፡፡ አብዛኛዉን ጊዜ ይህን የሚጠቀሙት የጠፋን ነገር ለመፈለግ ነዉ፡፡ ይህ ዘዴ የያዘዉ የሚሉ እና የሽርክ ድግምት ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡
💠 #ስምንተኛዉ_ዘዴ፦ የሰዉን ላብ የያዘ ቁራጭ መጠቀም
ድግምተኛዉ ከታማሚዉ ልብስ ወይም ከሌላ ከማንኛዉም ነገር የላቡን ሽታ የያዘ ቁራጭ ይወስዳል፡፡ ከዚያም ቁራጩን ከጫፉ ላይ ይቋጥረዉና አራት ጣት በሚያህል መጠን ለክቶ ይቆርጠዋል። ከዚያም ይህን ቁራጭ ጨርቅ በጣም ጭብጥ አድርጎ ይይዛል። ከዚያም ሱረቱል ተካሱር ምዕራፍን ወይም ሌላ አጭር ምዕራፍ ድምፁን ከፍ አድርጋ ያነባል። በመቀጠል ድምፁን ዝቅ አድርጎ የክህደት ድግምት ይደግማ ከዚያም ጂኒዎችን እየተጣራ እንዲህ ይላል፡-
የዚህ ሰዉ ህመም መንስኤዉ ልክፍት ከሆነ የጨርቅ ቁራጩን አሳጥሩት፤ ቡዳ ካለበት አስረዝሙት፣ አካላዊ ከሆነ ጨርቁን እንዳለ ተዉት፡፡ ይህን ካደረገ በኋላ ቁራጩን ጨርቅ ዳግመኛ ይለካዋል፡፡ ከአራት ጣት እረዝሞ ካገኛዉ ቡዳ ነዉ የታመምከዉ ይለዋል፡፡ አጥሮ ካገኘዉ ደግሞ ልክፍት አሉ ይለዋል። ሳያጥር ወይም ሳይረዝም እንዳለ አራት ጣት ሆኖ ካገኘ ምንም የለብህም ዘመናዊ ዶክተሮች ዘንድ ሂድ ይለዋል።
ማወቅ ያለብን
☞ ድግምተኛው ቁርአን ሲያነብ ድምፁን ከፍ በማድረግ ድግምቱን ሲያማትብ ደግሞ ድምፁን ዝቅ በማድረግ ታማሚን ያታልላል። ታማሚዉ ድግምቱ ስለማይሰማዉ እና ቁርአኑን ብቻ ስለሚሰማ ይህ ሰዉ በቁርአን ነዉ የሚያክመዉ ብሎ እንዲያስብ ያደርገዋል። ችግሩ ያለዉ በማይሰማ ድምፅ በሚያማትበዉ ድግምት ዉስጥ ነዉ፡፡
☞ በዚህ ዘዴ ዉስጥ ከጂኒዎች ጋር መተባበር አነሱን መጥራትና መለማመን ይገኝበታል፡፡ ይህ እንግዲህ ክህደትና ሽርክ ነዉ፡
☞ ጂኒዎች እጅግ በጣም ዉሸታሞች ስለመሆናቸዉ ነብያችን አስተምረዉናል፡፡ ታዲያ ይህ ጂኒ ስለተናገረዉ ነገር እዉነቱን ይሁን ዉሽቱን በምን ይታወቃል??
🟢 #ድግምተኛ_የሚለይባቸዉ_ምልክቶች
ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ምልክቶች አንዱ የተገኘበት ከመንፈሳዊ ህመሞች አድናለሁ የሚል ሰዉ ያለ ጥርጥር ድግምተኛ ነዉ፡፡ እነዚህም ምልክቶች እንደሚከተለዉ ተዘርዝረዋል፡፡
➊ የህመምተኛዉንና የእናቱን ስም ይጠይቃል
➋ ህመምተኛው ላቡ ያለበትን የልብሱ ቁራጭ፣ ኮፍያ፣ ማህረብ ካልሲ) ይወስዳል።
➌ በዓይነቱ የተለየ እንስሳ (ቀይ በግ ጥቁር ዶሮ) ህመምተኛው እንዲያቀርብ ያዛል። የሚያርደው ከሆነም የአላህን ስም ሳይጠራ (ቢስሚላህ) ሳይል ያርዳል። የታመመውን አካል በታረደው በክት ደም ይለቀልቀዋል። ወይም ያረደውን በክት ወደ ፍርስራሽ ቦታ ይወረውረዋል።
➍ ድግምት ይፅፋል።
➎ ግልጽ ያልሆኑ ድግምቶችን ማማተብ
➏ ቁጥሮችንና ፊደላትን የያዘ ባለ አራት ማዕዘን ፁሁፍ ይጠብቅሀል በማለት ለህመምተኛው ይሰጣል፡፡
➐ የፀሐይ ብርሃን በማይገባበት ክፍል ውስጥ ለዚህን ያህል ቀናት ቆይ በማለት ህመምተኛውን ያዘዋል፡፡
➑ ለዚህን ያህል ቀናት ገላህን አትታጠብ በማለት ህመምተኛውን ያዘዋል። አብዛኛውን ጊዜ ለአርባ ቀናት ነው ገላህን አትታጠብ በማለት የሚያዙት፡፡ ይህች ምልክት ይህን ድግምተኛ እና ጠንቋይ የሚያገለግለው ሰይጣን ክርስቲያን መሆኑን ታስገነዝበናለች፡፡
➒ ለህመምተኛው በመሬት ውስጥ የሚቀብራቸው ነገሮችን ይሰጣል።
➓ ለህመምተኛው የሚታጠናቸው ወረቀቶች ይሰጣል፡፡
➊➊ ግልፅ ባልሆነ ቋንቋ ያማትባል፡፡
➊➋ አንዳንድ አስማተኞች የህመምተኛውን ስም፤ መንደር እና ለምን ጉዳይ እንደመጣ አስቀድመው ይናገራሉ፡፡ (ይህም የሚሆነው ለአስማተኛው ሰይጣናት አስቀድመው ነግረውታል ወይም ስለ ታማሚው ማንነት እና ሁኔታ በሰላይ አማካኝነት ደርሶበታል ማለት ነው)
➊➌ በወረቀት ወይም በነጭ የሸክላ ሳህን ላይ የተቆራረጡ ፊደላትን በመጻፍ በውሀ አጥቦ እንዲጠጣው ለህመምተኛው ይሰጣል፡
ከነዚህ ምልክቶች አንዱን ያገኘህበት ያየህበት ሰዉ ጠንቋይ ደብተራ ድግሞተኛ ስለሆነ፣ አደራ አደራ በፍፁም ወደእሱ አትሂድ፡፡ ከሄድክ ግን የሚከተለዉ የነቢዩ ሀዲስ ተፈፃሚ ይሆንብሃል፡፡
“ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ የተናገረዉን የተቀበስ ሰዉ፡ ወደ ነቢዩ ሙሀመድ በወረደዉ (ቁርአን) በርግጥ ክዷል” (አል-በዛር ዘግበዉታል)
➊➍ በቤቱ ውሻ ያስራል
☞አስካሪ መጠጥ ይጠጣል።
☞ቁርአን ለመቅራትና ለመስማት አይወድም፡፡
☞ሙዚቃ ይሰማል፡፡
☞ሶላት አይሰግድም ከሰገደም ጥራ ጥሬ እንደ ምትለቅም ዶሮ ጠቅ ጠቅ ነው፡፡
☞ የእጅ መዳፍ ያነባል።
☞ ከተለያዩ ሴቶች ጋር ዝሙት ይፈጽማል፣
☞የተከበረውን ቁርአንን ያላአግባብ በመቅራትና በመጠቀም ያረክሳል።
በጠንቋዮች (በደብተራዎች) በቄሶች የሚፈታ ድግምት ለጊዜዉ የተፋታ ይምሰል እንጂ ሙሉ በሙሉ አይድንም፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ዳግም ያንሰራራል፡፡ ምክንያቱም ሰይጣናት በጎሳ የተከፋፈሉ ናቸዉ፡፡
☑️ ድግምቱን የሰራዉን ደብተራ የሚያገለግሉት ሰያጣናት ድግምቱን የሚፈታዉን ደብተራ ከሚያገለግሉት ሰይጣናት በጎሳ የተለዩ ስለሚሆኑ የአንዱ ጎሳ ሰይጣን የሰራዉን መተት የሌላ ጎሳ ሰይጣን መፍታት ወይም በመተት የተወከለዉን ጂኒ ማስወጣት አይችልም፡፡ ምክንያቱም ይህን ማድረግ በጎሳዎች መካከል ጦርነት ይቀሰቅሳል።
#ስለሆነም ብዙ ጊዜ ጠንቋይ የሚያገለግሉ ሰይጣናት የሚያደርጉት ነገር ቢኖር በታማሚዉ ዉስጥ ከገባዉ ስይጣን ጋር መስማማት ነዉ፡፡ ይህም ስምምነት ሰይጣኑ ታማሚዉን ለጥቂት ወራት ወይም ሳምንታት ላያንገላታዉ እና ታማሚዉ ደግሞ ሰይጣኑ የሚፈልገዉን ሊያሟላ ይስማማሉ፡፡
ለምሳሌ፡-ጥቁር ዶሮ እንዲታረድለት ፈልጎ ከሆነ ታማሚዉ ይህንኑ ያቀርባል ወይም ለምስሎች እንዲሰግድ ያታዘዛል፡፡ በዚህም ታማሚዉ ለተወሰነ ጊዜያት ተሸሎት ይከርምና ያ የተስማሙበት የጊዜ ገደብ ሲያበቃ ህመሙ ዳግም ይቀሰቀሳል፡፡ ከዚያም ሌላ ስምምነት ... ሙሉ ፈዉስ ማግኘት የሚቻለዉ በዓለማት ፈጣሪ በአላህ ቃል በቁርአን ብቻ ነዉ፡፡
#ክፍል 5⃣
ይቀጥላል.....
አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ👇👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
✅ ድግምተኛ እና ሰይጣን አላህ ሱ.ወ በማመፅ ላይ የተሰማሩ ሁለት ጥንዶች ናቸው ማለት ነዉ
ሁልጊዜም ማለት ይቻላል በሰይጣንና በአስማተኛ(በድግምተኛ) መካከል የጋራ ስምምነት ይኖራል፡፡ በዚህ ስምምነት ድግምተኛዉ የክህደትና የሽርክ ሀጢያቶችን በግልፅ ወይም በድብቅ ሊፈፅም እና ሰይጣኑ በበኩሉ ድግምተኛዉን ሊያገለግለው ወይም የሚያገለግለው ሌላ ሰይጣን ሊሰጠው ይስማማሉ።
🔰 የዚህ ዓይነት ስምምነት (ውል) አብዛኛዉን ጊዜ የሚደረገው በደጋሚዉና በሰይጣናት የጎሳ አለቃ መካከል ነው።
የጎሳ አለቃ በሚመራዉ ጎሳ ውስጥ ዝቅተኛ ማዕረግ ያለውን ሰይጣን ከእርሱ ጋር ውል የገባውን ደጋሚ እንዲታዘዘዉ እና እንዲያገለግለዉ ያደርጋል፡፡
↪️ ለምሳሌ
>> የተከሰቱ ድርጊቶችን በመንገር፣
>> ሰዎችን በማጣላት፤
>> መስተፋቅር በመስራት፣
>> ባል ሚስቱን ከመገናኘት በማሰናከል እና ሌሎች ችግሮችን ወዘተ ጉዳዮችን እንዲፈፅምለት ያዘዋል፡፡
ከዚህ በኋላ ደጋሚዉ ይህንን ሰይጣን ለሚፈልጋቸው የመተት ሥራዎች ማስፈፀሚያነት ያውለዋል። ሰይጣኑ አልታዘዝ ካለው ክህደት ያዘሉ እና የሰይጣናት የጎሳ አለቃን የሚያወድሱ የድግምት ቃላት በመድገም ወደ ሰይጣናት የጎሳ አለቃ ይቀርባል። ይህም የጎሳ አለቃ አስማተኛውን አልታዘዝ ያለወን ሰይጣን እየቀጣ እንዲታዘዘው ዳግመኛ ያዘዋል : ወይም ሊታዘዘዉና ሊያገለግለው የሚችል ሌላ ሰይጣን ይሰጠዋል፡፡
ሰይጣኑ ደጋሚዉን የሚያገለግለዉ ተገዶ በመሆኑ ስራውንም ሆነ ደጋሚዉን በእጅጉ ይጠላል፡፡ በዚህም ሳቢ በደጋሚዉና በአገልጋዩ ሰይጣን መካከል ያለዉ ግንኙነት በጥላቻ ላይ የተመሰረተ ነዉ፡፡ ሰይጣኑ በደጋሚዉ ወይም በጠንቋዩ ሚስት፣ ልጆች፤ ንብረት እና ሌሎች ነገሮቹ ላይ ጉዳት ከማድረስ ወደ ኋላ አይልም፡፡
እንዲያዉም አስማተኛዉ አያዉቀዉም እንጂ በራሱ ላይ ሳይቀር ጉዳት ያደርስበታል፡፡
☞ የማይለቅ የራስ ምታት፣
☞ከፍተኛ የእንቅልፍ እጦት፣
☞በአስፈሪ ሁኔታ እና በድንጋጤ ከእንቅልፍ መባነን እና በመሳሰሉ አንግልቶች ያሰቃየዋል
☞ አንዳንድ ድግምተኞች ልጅ መዉለድ የማይችሉ መሀኖች ናቸዉ ይህም የሚሆነዉ ፅንሱ ገና ከማደጉ በፊት ሰይጣኑ ስለሚገድለዉ ነዉ። ይህ ነገር በድግምተኞች ዘንድ በጣም ከመታወቁ የተነሳ አንዳንድ ደጋሚዎች ልጅ ለመዉለድ ሲሉ የድግምት ስራቸዉን አርግፍ አድርገዉ የተዉ አሉ፡፡
#ክፍል 4⃣
ይቀጥላል....
አስተያየት መስጠት ለሚፈልጉ👇👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
ለተለያዩ የዲን እዉቀቶች ይቀላቀሉ
Join👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
t.me/IslamisUniverstiy_public_group