iqraknow | Unsorted

Telegram-канал iqraknow - 📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

9425

Subscribe to a channel

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

🍃 አቡሁረይራህ (ረዲየዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)እንዲህ ብለዋል፦ ✏️🍃

#ከሰባት_አጥፊ_ወንጀሎች_ራቁ አሉ" ሰወችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ!እነማን ናቸው?" ሲሉ ጠየቁ። እሳቸውም፦
http://t.me/iqraknow

1🍃በአላህ ላይ ማጋራት(ሽርክ)
2🍃ድግምት(ሲህር)
3🍃አላህ ክልክል ያደረጋትን ነፍስ፣ መግደል
4🍃ወለድ መብላት(ሪባ)
5🍃የየቲም (የሙት ህፃንን)ገንዘብን መብላት
6🍃በጦርነት ውስጥ ጀርባን መስጠት(መሸሽ)
7🍃ጥብቅ የሆኑ የሙእሚን ሴቶችን ስም በዝሙት በመወንጀል ስማቸውን ማጥፋት ናቸው።

🍃أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ، عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : " اجْتَنِبُوا السَّبْعَ الْمُوبِقَاتِ ". قَالُوا : يَا رَسُولَ اللَّهِ، وَمَا هُنَّ ؟ قَالَ : "
#الشِّرْكُ بِاللَّهِ، #وَالسِّحْرُ، #وَقَتْلُ النَّفْسِ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ، #وأَكْلُ الرِّبَا، #وَأَكْلُ_مَالِ_الْيَتِيمِ، #وَالتَّوَلِّي يَوْمَ الزَّحْفِ، #وَقَذْفُ الْمُحْصَنَاتِ الْمُؤْمِنَاتِ الْغَافِلَاتِ ".
http://t.me/iqraknow http://t.me/iqraknow

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

ነገ የዐረፋ ቀን ነው። የወርሀ ዙል ሒጃ ዘጠነኛው ቀን።
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] «የዐረፋ ቀን ጾም ያለፈውን እና የመጪውን ዓመት ኃጢኣት ያስምራል።» ብለዋል። ሙስሊም ዘግበውታል።
ኢማም አል—ሙናዊ [ረሒ] እንዲህ ብለዋል: ‐ ገና ያልተከሰተውን «የመጪውን ዓመት ኃጢኣት» ያስምራል ሲባል ምን ማለት ነው?: —
❶ በመጪው ዓመት ከኃጢኣት ይጠብቀዋል ማለት ነው።
❷ ለመጪው ዓመት ኃጢኣቱ ማሰረዣ የሚሆን ምንዳ ይሰጠዋል ማለት ነው።
ወይም
❸ ሰውየው በህይወት ቆይቶ ኃጢኣት ቢሰራ እንኳን ይሰረዝለታል ማለት ነው።»
ፈይዱል ቀዲር ቅፅ 4፣ ገፅ 230
#አደራችሁን ለምታቁት ሰው ሁሉ ላኩ
።
http://t.me/iqraknow http://t.me/iqraknow

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

ሙስሊም በሌላው በሙስሊም) ላይ ስንት መብት አለው?
http://t.me/iqraknow

አቡ ሁረይራ(ረዐ) ባስተላለፉት ሀዲስ
ነብዩ (ﷺ) አንድ ሙስሊም በሌላው ሙስሊም ላይ #አምስት
መብቶች (ሀቆች) አሉት።
እነሱም:–
1✍️ስታገኘው ሰላምታ ማቅረብ (ሰላምታ መመለስ)
2✍️ሲታመም ልትጠይቀው
3✍️ሲሞት ልትከተለው (ጀናዛውን ልትሸኝ)
4✍️ሲጠራህ (ሲጋብዝህ) ጥሪን ማክበር
5✍️ሲያስነጥስ (አላህን ካመሰገነ) ከአላህ ምህረት መጠየቅ ናቸው" ብለዋል።
(ቡኻሪና ሙስሊም)
http://t.me/iqraknow http://t.me/iqraknow

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

ኢባዳ በስንት ይከፈላል ? ምን ምን ናቸው?

http://T.me/iqraknow

ኢባዳ በሶስት ይከፈላል።
እነርሱም ፦

⇘ ኢባደቱል ቀልቢያ
⇘ ኢባደቱል ቀውሊያ
⇘ ኢባደቱል አመሊያ

✅የቀልብ አምልኮ:-
⇛ ኢልም
⇛ ኢማን
⇛ ኢኽላስ
⇛ ኢህሳን
⇛ ተውኩል
⇛ ተቀዋዕ
⇛ ሙአባህ
⇛ ሰብር ናቸው።


✅የአፍ አምልኮ:-
⇛ ተውበት
⇛ ሸሃዳ
⇛ ዱአ
⇛ ዳዋዕ
⇛ ዚክር
⇛ ቁርአት ናቸው።

✅ የድርጊት አምልኮ:-
⇛ ሰላት
⇛ ፆም
⇛ ዘካ
⇛ ሃጅ
⇛ ጅሃድ ፊ ሰብሊላህ ናቸው።

http://T.me/iqraknow http://T.me/iqraknow

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

ውሻ አንድ እቃ ነክቶ ከነጀሰው የተነጀሰው እቃ የሚፅዳው በስንት እጥበት ነው ? ለሚለው ትክክለኛ መልስ በ 7 ትጥበት አንዱን በአፈር ነው።

http://T.me/iqraknow
ﻋﻦ ﺃﺑﻲ ﻫﺮﻳﺮﺓ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ : ﺃﻥ ﺭﺳﻮﻝﺍﻟﻠﻪ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻗﺎﻝ } ﺇﺫﺍ ﺷﺮﺏ ﺍﻟﻜﻠﺐ ﻓﻲ ﺇﻧﺎﺀ ﺃﺣﺪﻛم ﻓﻠﻴﻐﺴﻠﻪ ﺳﺒﻌﺎ>>

ﻭﻟﻤﺴﻠﻢ:ﺃﻭﻻﻫﻦ ﺑﺎﻟﺘﺮﺍﺏ

ከአቡ ሁረይራህ ረድየሏሁ ዐንሁ በተወራው ሐዲስ ረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ ከእናንተ በአንዳችሁ እቃ ውስጥ ውሻ ከጠጣበት (እቃውን) ሰባት ጊዜ ይጠበው።
ሙስሊም በዘገቡት፦ የመጀመሪያውን በአፈር ያድርገው
።
http://T.me/iqraknow http://T.me/iqraknow

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

/channel/iqraknow /channel/iqraknow

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

የምትመለከተቱት ነፍሳት ጉንዳን ይባላሉ አላህ በቁርዓን ላይ በስማቸው ምእራፍ ሰይሞላቸዋል ።
ጉንዳኖች «እንደምትመለከቱት ምንም መወጣጫ በሌለው ነገር ላይ እርስ በርስ በመተባበር ድልድይ ይሰሩ እና ላሰቡት አላማ ስራ ይጀምራሉ ።
በዚህ ተልእኮ ላይ አንድ ጉንዳን ሲወለድ ጀምሮ እስኪ ሞት ድረስ የመቆየት ግዴታ አለበት።
ስራው ከተጀመረ ቡሀላ በጭራሽ ማፈግፈግ አይቻልም እንዲሁም በራስ ላይ በሚመጣ ችግር ምክኒያት ተእልኮው አይቁያረጥም።
የዚህ አባል ጉንዳን ቢታመምባይመቸው ቢራብ ቢቆስል በመጨረሻም ሞት ቢመጣ ከዚህ ተልዕኮ ይህ ነፍሳት ንቅንቅ የለም ።
የሞት ፅዋ ሲጎነጭ እንኳን በሱ መሞት ተልኮ እንዳይቁያረጥ የጉንዳኑ አስከሬን ለወገኖቹ ድልድይ ሆኖ ያገለግላል።
በዚህ አንድነት ውስጥ አንዱ ሌላውን አይመለከተም ከራሱ የሚጠበቀው ብቻ ለቡድኑ በማድረግ የድርሻውን ይወጣል ሱብሀአነላህ ።
ልክ እንደነዚህ የአላህ ፍጥረቶች እኛ እንድንሆን ቁርአን ከተግባር እስከ ምሳሌ ይነግራናል።
ቁርአን የተረዱት ሶሀባዎችም ቅያሪ ልብስ ሳይኖራቸው እስከ ስፔን ድረስ ተቁጣጥረዋል ኢስላምን ለአለም ህዝብ አድርሰዋል ።
እኛ ደግሞ ነገሮች ቀላል በሆኑበት በዚህ ዘመን ሰብስክራይብ ላይክ እና ሸር በማድረግ ብቻ አለም በኢስላም መሙላት እየቻልን በስፍና ተጠቅተናል።

/channel/iqraknow /channel/iqraknow

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

☞ሳታገቢ ከዘገየሽ፣የሙእሚኖች እናት ኸዲጃን(ረዲየሏሀ ዐንሀ) አስታውሽ !
*በመጨረሻ ታላቁትን ነብይ (ﷺ) አገኘች!
☞ጭራሽ ካላገባሽም፣መርየም ቢንት ኢምራንን አስታውሽ!
*አላህ እንዴት ከፍ እንዳደረጋት በዱንያ በአኺራ !
☞ከመጥፎ ባል ጋር ከኖርሽ፣አስያን የፊርዐውንን ሚስት አስታውሽ!
*አላህ በጀነት ውስጥ ቤት እንደገነባላት!
☞ከትዳርሽ ከተፋታሽም
*የአላህን ቃል አስታውሽ!
#እህቴ_ሆይ እወቂ ሪዝቅ(ሲሳይ)ተፅፎ ያለቀ ነውና
አትቻኩይ።
አሏህ_ሶብር_ይስጠ_መልካም_ትዳር_ይስጠን_አላሁመ_አሚን

https://t.me/joinchat/AAAAAENwILD2owhNtNVpgg

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

✨ረሱላችን ﷺ ጂብሪል ዓለይሂ ሰላም መጣኝና እንዲህ አለኝ ይሉናል: -

👉የፈለግከውን ያህል እድሜ ኑር ሟች ነክ ፤የፈለግከውን ውደድ ትለየዋለህ፤ የፈለግከውን ስራ ስራ ትመነዳበታለህ። እወቅ የአማኝን ልቅናው የሌሊት ሰላት መስገዱ ነው፤ክብሩ ደግሞ ከሰዎች መብቃቃቱ ነው።
( ሰ ዐ ወ)
/channel/iqraknow
https://t.me/joinchat/AAAAAENwILD2owhNtNVpgg

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

⚘⑬ቱ የጥሩ ሚስት መገለጫዎች⚘
t.me/iqraknow t.me/iqraknow
①-የትም ብትሆን አላህን ትፈራለች፣ በሁሉም ነገር የነቢዩን ሱና ትከተላለች

②-ባሏ ያዘዛትን በሙሉ -ከዲን ጋር የሚጋጭ እስካልሆነ ድረስ- ትታዘዛለች

③-ከሷ ጥሩን ነገር እንጂ እንዳያይ፣ እንዳይሰማና እንዳያሸት ጥረት ታደርጋለች

④-ቤትና ንብረቱን እንዲሁም
ቤተ-ሰቦቹን ትጠብቃለች

⑤-እሱ የማይፈልገውን ሰው
አትጠጋም አታስጠጋምም

⑥-ባሏን ሳታሳውቅ ሱና ጾም አትጾምም
ከቤትም አትወጣም

⑦-የባሏንና የቤቷን ሚስጥር
በሚገባ ትጠብቃለች

⑧-ባሏን በመልካም ነገር ላይ
ታግዛለች ሲሰንፍ ታበረታታዋለች፣
ሲረሳ ታስታውሳለች

⑨-ሐላል ከስብ እንዲከስብ ሐራምን እንዲርቅ ዘወትር ትገፋፋዋለች፣ለእሷና ለቤቱ ብሎ ዲኑ የማይፈቅደውን
ስራ እንዳይሰራም ታሳስበዋለች

⑩-ደስታና ሃዘኑን ትጋራለች፥
እርሱ ሐሳብና ጭንቀት ውስጥ ሆኖም እሷ አትስቅም፣ እሱ ማረፍና መደሰት በሚፈልግበት ወቅት ላይም እሷ በተቃራኒው ተከፍታ አታስከፋውም

⑪-በሚያደርግላት ነገር በሙሉ
ይብዛም ይነስ ታመሰግነዋለች

⑫-ቤቷን እያቀዘቀች የሰው ቤት አታሞቅም ቤቷንም እያፈረሰች የሰው ቤት አትገነባም!

⑬-አላህ የሰጣትን ልጆች በኢስላም ስርዓት ቀርጻ ታሳድጋለች ትልቁ የእሷ ስራም ይህ እንደሆነ በማወቅ በስራዋ ትኮራለች! ልጅም ያጣች እንደሆነ ታግሳ ተስፋ ሳትቆርጥ ጌታዋን ትለምናለች
አበቃ።
https://t.me/joinchat/AAAAAENwILD2owhNtNVpgg
"ሁላችንም አሏህ ሳሊሖች ያድርገን"

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

የሰሓባዎች ትክክለኛ ስም
----
http://t.me/iqraknow
አቡ-በክር= ዐብዱላህ ኢብን ዑሥማን
አቡ-ዑበይዳህ ኢብን ጀራሕ= ዓሚር ኢብን አል-ጀራሕ
አቡ-ሱፊያን ኢብን ሐርብ= ሰኽር ኢብን ሐርብ
አቡ-ሰለማህ= ዐብዱላህ ኢብን ዐብዱል አሰድ
አቡ-ሁረይራ= ዐብዱራሕማን ኢብን ሰኽር
አቡዘር አል-ጊፋሪ= ጁንደብ ኢብን ጁናዳህ
አቡ-ሰዒድ አል-ኹድሪ= ሰዒድ ኢብን ማሊክ
አቡ-አዩብ አል-አንሷሪ= ኻሊድ ኢብን ዘይድ
ኡሙ-ሰለማህ= ሂንድ ቢንት አቢ ኡመያ
ኡሙ-ሐቢባ= ረምላ ቢንት አቡ-ሱፊያን
አቡ ጀንደል= አል-ኣስ ኢብን ሱሐይል
አቡ ሙሳ አል-አሽዐሪ= ዐብዱላህ ኢብን ቀይስ አል-አሽዐሪ
አቡ ሱፊያን ኢብን-ሓሪስ= ሙጊራህ ኢብን ሓሪስ ኢብን ዐብዱል ሙጠሊብ
ኡሙ ፈድል= ሉባባ ቢንት ሓሪሥ
ኡሙ ሩማን= ዘይነብ ቢንት ዓሚር
ኡሙ በኒን= ፋጢማህ ቢንት ሑዛም
---
https://t.me/joinchat/AAAAAENwILD2owhNtNVpgg
ረዲየላሁ ዐንሁም ዐጅመኢን።

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

ኢቅራዕ ኢስላማዊ ጠቅላላ ዕውቀት
✅ t.me/iqraknow ✅ t.me/iqraknow✔

♻️ለዲኑ ብሎ አባቱን የገደለው ሱሀባ= አቡ ኡበይዳህ ወይም አማር ✔ ይባላል


🔰ዛቱል ኑጧቂን በመባል የምትታወቀው ሱሀቢይት= አስማ ቢንቱ አብበከር (ረዐ)✔

❇️ ዛቱል ሂጅረቴን በመባል የምናውቃት ሱሀብይት = ሩቅያ ቢንቱ ሙሀመድ (ሰ.አ.ወ)✔

✅ አብበከር ሲዲቅ(ረ.ዐ) በገንዘብ ገዝተው ነፃ ያወጡት ሱሀባ = አማር ኢብን ፋሀይራህ✔

♻️የእሙ አይመን የቀድሞ ስሟ = በረካ✔

🔰 በቅዱስ ቁርኣን 📖 ውስጥ የተጠቀሰች ትንሿ እንሰሳ = ትንኝ✔

🌷🌷

https://t.me/joinchat/AAAAAENwILAUbV57bqdr4g

JOIN 🔝channel 🔝& ሼር....Share 🔜

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

የአላህ መልክተኛ #ﷺ «አላህ አንተን እንድወድህ አዞኛል ፣ አላህም እንደሚወድህ እንድነግህም አዞኛል።» በማለት የነገሩት (ያበሰሩት) ሰሀባ ማን ነው?
👇👇መልሱ👇👇
ሚቅዳድ ኢብኑ አምር (ረዐ) ✅ ነው።

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

የአላህ መልክተኛ #ﷺ «አላህ አንተን እንድወድህ አዞኛል ፣ አላህም እንደሚወድህ እንድነግህም አዞኛል።» በማለት የነገሩት (ያበሰሩት) ሰሀባ ማን ነው?
👇👇👇👇👇
@iqrafeedbackbot @iqrafeedbackbot

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

ጥያቄ 2//
📖በቅዱስ ቁርኣን📖 ውስጥ አንዲት ምእራፍ አለች፣ እሷም 👇
"አንድ ሰው ምህረት እስኪያገኝ ድረስ አማላጅ ትሆንለታለች"
ይህች የቁርአን ምዕራፍ ማን ናት?

👇መልስ መስጫ👇

@iqrafeedbackbot @iqrafeedbackbot

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

#የነገውን_ፆም_ንያ_አደራረግ

نويت صوم غد يوم التاسع من ذي الحجة لله تعلى

ትርጉም፦ የነገውን የዙል ሂጃን ወር ዘጠነኛዉን ቀን ለአሏህ ብየ ለመፆም ነያሁ

ለሌሎችም ሸር ያድርጉ ያካፍሉ

http://t.me/iqraknow 👈
http://t.me/iqraknow 👈

❤ መልካም ምሽት ❤

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

"ኢስላማዊ ወንድማማችነት"

አምላካችን አላህ ፣በቅዱስ ቁርአኑ፦
ﺇِﻧَّﻤَﺎ ﺍﻟْﻤُﺆْﻣِﻨُﻮﻥَ ﺇِﺧْﻮَﺓٌ
“ምእመናን ወንድማማቾች ናቸው።” (አልሁጁራት፤ 10)

ታላቁ ነቢይም ሙሀመድ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በሚከተሉት ሀዲሦቸው እንዲህ በማለት ያስተምራሉ፦

“አንዳችሁም አላመናችሁም ለራሣችሁ የምትወዱትን ነገር ለወንድማችሁ እስካልወደዳችሁ ድረስ።”
፡
https://www.youtube.com/channel/UCTBV3GsEgtW6GECdIAzPPLg?sub_confirmation=1
“ሙስሊም የሙስሊም ወንድም ነው፤ አሣልፎ አይሠጠውም፤ …።”

በሌላም ሀዲስ፦

“ከውዴታ፣ ከአዘኔታ እና ከመረዳዳት አንፃር የሙስሊሞች ምሳሌ እንደ አንድ ሰውነት ነው።

አንድ የሰውነት ክፍል የታመመ እንደሆነ የተቀረውም የሰውነት ክፍል እንቅልፍ በማጣት እና በትኩሣት ይከተለዋል።”

በዚህ የነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ንግግር ውስጥ በመጀመሪ ደረጃ ላይ ሊገቡ የሚችሉት በአላህ መንገድ ወንድማማቾች የሆኑት ናቸው።

ምንም የስጋ ዘመድና ቢኖርም እንኳን ፣ከከሀዲያን የስጋ ዝምድና የ ላ ኢላህ ኢለላ ወንድምና እህትነት እጅግ በላጭ ነች፦

ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍ ﻟَﺎ ﺗَﺘَّﺨِﺬُﻭﺍ ﺁﺑَﺎﺀَﻛُﻢْ ﻭَﺇِﺧْﻮَﺍﻧَﻜُﻢْ
ﺃَﻭْﻟِﻴَﺎﺀَ ﺇِﻥِ ﺍﺳْﺘَﺤَﺒُّﻮﺍ ﺍﻟْﻜُﻔْﺮَ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟْﺈِﻳﻤَﺎﻥِۚ ﻭَﻣَﻦ
ﻳَﺘَﻮَﻟَّﻬُﻢ ﻣِّﻨﻜُﻢْ ﻓَﺄُﻭﻟَٰﺌِﻚَ ﻫُﻢُ ﺍﻟﻈَّﺎﻟِﻤُﻮﻥَ

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አባቶቻችሁና ወንድሞቻችሁ ክህደትን ከእምነት አብልጠው ቢወዱ ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዙዋቸው። ከእናንተም ውስጥ
ወዳጅ የሚያደርጋቸው እነዚያ እነሱ በዳዮች ናቸው፤” (ተውባህ፤23)
https://www.youtube.com/channel/UCTBV3GsEgtW6GECdIAzPPLg?sub_confirmation=1
ሼር✔

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

አቡ ማሊክ አል አሽዐሪ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልክተኛﷺ እንድህ ብለዋል:-
http://t.me/iqraknow

✍️ከተከታዮቼ ውስጥ ከቅድመ ኢስላም የጃሂልያ ዘመን (ረሱልﷺ) ከመላካቸው በፊት የነበረው ዘመን የተወረሱ አራት ልምዶች አሁንም ድረስ ይገኛሉ:: #እነሱም:-
http://t.me/iqraknow

1✍️ በዘር መኩራራት
2✍️የሌሎችን ዘሮች ማጉደፍ
3✍️በክዋክብት ዝናብን መሻት
4✍️ሙሾ ማውረድ (አስለቃሽ በግጥምና በዜማ ህዝቡን የምታስረቅስ) ነቸው::

🍃ሙስሊም ዘግበውታል🍃

http://t.me/iqraknow

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ)እንዳስተላለፋት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)ይህ ተናግረዋል፦

ኃያሉ እና የተከበረው አላህ በትንሳኤ ቀን እኔ ጠላት የምሆንባቸው ሶስት ወገኖች አሉ።

1ኛ/በኔ ስም ቃል ገብቶ ያፈረሰ ሰው


2ተኛ/ አንድ ነፃ የሆነ ሰው ሽጦ ዋጋው የበላ እና

3ተኛ/ ሠራተኛ ቀጥሮ ከእሱ የሚፈልገውን በሙሉ ከተቀበለ በኃላ ደመወዙን ያልሰጠ ሰው።

(ቡኻሪ ፣ኢብኑ ማጃህ እና አህመድ ዘግበውታል)

http://T.me/iqraknow http://T.me/iqraknow

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው

በ 20 ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ የሳይንስ ሊቃውንት ልዩ የሆነ አንድ ነገር አገኙ።

ሁለት የተለያዩ የውሃ አካላት ናቸው በአንድ ላይ ተገናኝተው ተመለከቱ ፣ አንዱ ጣፋጭ ነው አንዱ ጨዋማ ነው።
ምክኒያቱን ሲያጠኑ እዚያ ባለው ሙቀት የተነሳ ፣ ጨዋማነት እና ንፁህ ውሀው እርስ በእርስ እንዳይጣመሩ በጥብቅ የሚከላከል ጠንካራ ግርዶሸ «በርዘክ » በመሀላቸው ፈጥረው እንደሆነ ደረሱበት ። በዚያ ግርዶች ምክኒያት ሁለቱ ውሀ አለመዋሀዳቸውን ሳይንቲስቶች አረጋገጡ ።

በቁርአን ውስጥ ይህንን እውነታ ከ 1430 ዓመታት በፊት ከታች ባለው ሁኔታ አስተምሮናል ፡፡
አላህ አክበር ።

እርሱም ያ ሁለቱን ባሕሮች አጎራብቶ የለቀቀ ነው፡፡ ይህ ጥምን የሚቆርጥ ጣፋጭ ነው፡፡ ይህም የሚመረግግ ጨው ነው፡፡ በመካከላቸውም (ከመቀላቀል) መለያንና የተከለለን ክልል ያደረገ ነው፡፡
Quran 25:53

T.me/iqraknow T.me/iqraknow

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

በእውነትም «(ሙሐመድ) ቀጣጠፈው» ይላሉን «ይህ ከሆነ መሰሉን (አንዲት) ሱራ አምጡ፡፡ ከአላህም ሌላ የቻላችሁትን ሁሉ (ረዳት) ጥሩ፡፡ እውነተኞች እንደሆናችሁ (ተጋግዛችሁ አምጡ)» በላቸው፡፡
Quran10:38

ቁርዓን ለማስተባበል ተመሳሳይ ማምጣት በቂ ነው እያለ ቁርአን ሰዎችን ወደ ቀጥተኛ መንገድ ይጣራል ።

የሰው ልጅ ፈጣሪውን በእውቀት እንዲያምን ወይም በእውቀት እንዲቃወም ቁርአን ይጋብዛል።

ባለስልጣን ለተራ ሰው ትሁት ይሆናል ወይስ ተራ ሰው ነው ለባለስልጣን ትሁት የሚሆነው?

መልሱን ለናንተ? ባለስልጣን ትሁት ሆኖ ካናገረንስ ? ምን ይሰማናል ?

ልብ አድርጉ የዚህ ዩኑቨርስ ባለቤት እና ፈጣሪ መጋቢያችን ትንፋሽ ውሃ አየር የሰጠን ከብዙ አደጋ የሚጠብቀን የሚያኖረን የሚገድለን አላህ ሱብሀነ ወተአላ ደካማውን የሰው ልጅ እንዲህ ትሁት ሆኖ ጌታነቱን እንድናውቅ ይጠረናል ?

አላህ በዚህ መልኩ ግብዣ እያቀረበ ያልተቀበለ ሰው ካፊር ተብሎ ይጠራል።
ምክኒያቱም ኢስላምን ያልተከተለው መርምሮ ሳይሆን ሆን ብሎ አውቆ ስለሚክድ ነው።
በእውቀት ኢስላምን መዝኖ ከኢስላም የሚቀር ማንም ሰው የለም።

ሞት ስላለብን ትንፋሻችሁ ካለ እድለኛ ናችሁ ቁርአንን ምርምሩ ብለን ለማስታወስ እንወዳለን ።

ዛሬ የምናየው ተዐምር በቁርዓን ውስጥ በ98 ተኛው ሱራ ላይ ይገኛል የሱራውም ስም አል_በይናህ ይባላል ይህ አል በይናህ የሚባለው ምእራፍ የሚናገረው ስለ ቁርዓን ነው በይናህ ማለትም በአማረኛ ተመጣጣኝ ትርጉሙ
« ግልፅ አስረጅ » ማለት ነው ግልፅ አስረጅ ማለት ደግሞ ቁርዓን ማለት ነው ታዲያ አስገራሚው ነገር ምን መሰላችሁ «الْبَيِّنَةُ» የሚለው አረበኛ ፊደል የተፃፈበት
ب ي ن ه

በሚለው በነዚህ አራት ፊደሎች ነውበዚህ አል በይናህ በሚባለው ስለ ቁርዓን ታላቅነት በሚያወሳው ሱራ ውስጥ ب የሚለው 13 ግዜ አለ ي የሚለው 36 ግዜ ن 34 ጊዜ አለ ه የሚለው 31 ግዜ ተጠቅሰዋል እነዚህ ፊደሎች ደምሩት እስኪ

13+36+34+31= 114 ይመጣል ይህ የቁርዓን ምእራፍ ብዛት ይሰጠናል የቁርዓን ታላቅነት በሚናገረው በዚህ ሱራዎች ውስጥ ከንግግሩም ባለፈ የሚናገርላቸውን ሱራቸው በሂሳብ በቁጥር እንዲህ አቅፎ ይዙዋቸዋል።
ሱበሀነአላህ በማለት ጌታህን አልቀው
።
/channel/iqraknow /channel/iqraknow

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

ብታምኑትም ባታምኑትም

1.ኢማም አህመድ ኢብን ሃንበል (ረ.ላህ)

ሌላ ከሚሰሩት ስራ ውጪ በየቀኑ ሶስት መቶ ረከዓ ሱና ሰላት ይሰግዱ ነበር፡፡በዘመኑ በነበረው ንጉስ ከተሰቃዩ በሗላ በጣም ደክመው ነበር፤ ነገር ግን እንደዛም ሆነው መቶ ሃምሳ ረከዓ ይሰግዱ ነበር፤ እንግዲህ በዛን ሰዐት ሰማንያ አመት ሞልቷቸው ነበር፡፡

2. ኢማም ሻፊዒይ (ረ.ላህ)

በረመዳን ወር በቀን ሁለቴ በወር ስልሳ ጊዜ ሰላሳ ጁዝ ቁርዐን በሰላት ያኸትሙ ነበር፡፡ከተማሪያቸው አንዱ “ኢማሙ ሻፊዒ አብሬያቸው ለብዙ ቀን ተቀምጫለሁ፤ ለጥቂት ጊዜ እንጂ ሲተኙ አላየሁም” በማለት ተናግሯል፡፡

3. ኢማም አቡ ሃኒፋ (ረ.ላህ)

ለአርባ በሌላ ዘገባ ለሃምሳ አመት ኢሻ በሰገዱበት ዑዱ ሱብሂ ሰላት ይሰግዱ ነበር(ለሊቱን ያለ እንቅልፍ በኢባዳ ያሳልፉት ነበር)፤ በዛን ጊዜ እንቅልፋቸውን ሚተኙት በከሰዐት ሲሆን እሱንም ለትንሽ ደቂቃ “በከሰዐት መተኛት ሱና ነው” በማለት ነበር፡፡

https://t.me/joinchat/AAAAAENwILD2owhNtNVpgg

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

✍ደግ የሆነች ሚስት ባለቤትዋ ሪዝቅ (ሲሳይ) ፍለጋ ሲወጣ፤
"ውዴ ሆይ! አላህን ፍራ እኛ ከረሃብ እንታገሳለን ከእሳት ግን አንታገስም" የምትል ናት!!
👇
https://t.me/joinchat/AAAAAENwILD2owhNtNVpgg

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

🔸شكى رجل إلى إبراهيم بن أدهم كثرة عياله ، فقال له :
"ابعث إلي منهم من ليس رزقه على الله، فسكت الرجل ".
[البداية والنهاية 13 / 510
🔸አንድ ግለሰብ ቤተሰቦቹ ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ ማስተዳደርም እንዳቃተው ለኢብራሒም አድሀም ስሞታን አቀረበላቸው፦
ኢብራሒም ኢብኑ አድሀምም እንዲህ አሉት፦
"ሪዝቁ (ሲሳዩ) ከአላህ ዘንድ ያልሆነውን ወደ እኔ አምጣልኝ።" ሲሉት
ሰውየው ወቀሳውን አቆሞ ሄደ።
اللهم وسع رزقنا وارزقنا حلالا طيبا مباركا
•••••••••✿🌺
✿• •••••••
TeÂť /channel/iqraknow
https://t.me/joinchat/AAAAAENwILD2owhNtNVpgg

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

https://t.me/joinchat/AAAAAENwILD2owhNtNVpgg

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

🌹የሰባት (7) ቁጥር ሚስጥር ምን ምን ናቸው?

በ👉 t.me/iqraknow የቀረበ
https://t.me/joinchat/AAAAAENwILD2owhNtNVpgg

①👉የሱረቱል ፋቲሀ አንቀጾች ብዛት 7 ናቸው ።

②👉የሰማያት ብዛት 7 ናቸው።

③👉የሱረቱል ማዑን አንቀጶች ብዛት 7 ናቸው።

④👉የጀሀነም በሮች ብዛት 7 ናቸው።

⑤👉ከቁርዓን (ሀሚም) ብለው የሚጀምሩት ሱራዎች ብዛት 7 ናቸው።

⑥👉የምድር ብዛት 7 ናቸው።

⑦👉የረሱል(ሰዐወ) ልጆች ብዛት 7 ናቸው።

⑧👉የሳምንቱ ቀናት ብዛት 7 ናቸው ።

⑨👉በካእባ ዙርያ 7 ቴ ጠዋፍ ይደረጋል።

⑩👉በሰላት ጊዜ ሱጁድ ስንወርድ መሬት የሚነካው የሰውነት ክፍላችን 7 ናቸው።

https://t.me/joinchat/AAAAAENwILD2owhNtNVpgg

⑪👉በሶፍዋና መርዋ የሚሮጠው 7 ጊዜ ነው።

⑫👉ነብዩላህ ኢብራሂም(ዐሰ) ያሉበት 7ኛው ሰማይ ላይ ነው።

⑬👉ልጆች ሰላት እንዲሰግዱ ረሱል (ሰዐወ) ያዘዙት በ 7 ዓመታቸው ነው ።

⑭👉ልጅ ሲወለድ አቂቃ የሚወጣለት በ 7ኛው ቀን ነው።

⑮👉በማንኛውም ሁኔታ የሚወፍሩ ፊደሎች (የኢስቲዕላ ፊደሎች) ብዛት 7 ናቸው።☞ ( خ ,ص ,ض ,ط ,ظ ,غ, ق )

⑯👉የቁርኣን አቀራር ዘይቤ 7 አይነት ነው።

⑰👉የ‹‹ላ ኢላሀ ኢለላህ›› መስፈርቶች (ሸርጦች) 7 ናቸው።

⑱👉የአለማችን አህጉሮች ብዛት 7 ናቸው።

https://t.me/joinchat/AAAAAENwILD2owhNtNVpgg

⑲👉በምድራችን ላይ የሚገኙት የባህር ብዛቶች 7 ናቸው።

⑳👉ውሻ ከነጀሰን 7 ጊዜ በአፈር እናሸዋለን።

②①👉በሀጅ ወቅት በጅምረተል አቀባ ላይ የሚወረወረው የጠጠር ብዛት 7 ነው።

②②👉በኢድ ሰላቶች የሚደረጉ ተክቢራዎች 7 ጊዜ ነው።

②③👉የቂያማ ቀን ምንም ጥላ በሌለበት ቀን በአላህ አርሽ ጥላ ስር የሚጠለሉት "7" አይነት ሰዎች ናቸው።

②④👉የመዲና ተምሮች(አጅዋ) ጠዋት 7 ፍሬ በባዶ ሆድ ተመገቡ ብለዋል።(ሰዐወ)

https://t.me/joinchat/AAAAAENwILD2owhNtNVpgg


ሌሎችም ብዙ ያልጠቀስናቸው ሚስጥሮች ይኖራሉና እናንተው ሞክሩት ፣አንብቡ፣ መፅሃፍ አገላብጡ፣ወዘተ ... እውቀታቹ ይጨምራልና......

https://t.me/joinchat/AAAAAENwILD2owhNtNVpgg

SHARE......SHARE.....SHARE...

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

ሙስሊም ُ ﻣﺴﻠﻢ በዘገበው ሀዲስ
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ
#ሦስት
ሰዎች የውመልቂያማ አላህ አያናግራቸውም አያያቸውም የተባሉት
እነማን ናቸው?

1ኛ________?
2ኛ________?
3ኛ________?

👇መልስ:-👇

1ኛ. የሽማግሌ ዝሙተኛ (شيخ زان)
2ኛ. ውሸታም ንጉስ (ملك كذاب)
3ኛ. የድሀ ኩራተኛ (ﻭَﻋَﺎﺋِﻞ ﻣُﺴْﺘَﻜْﺒِﺮٌ )

👇ሀዲሱ👇

ﻭَﻋﻦْ ﺃﺑﻲ ﻫﺮﻳﺮﺓ  ﻗَﺎﻝَ: ﻗَﺎﻝَ ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪ
ﷺ: ‏«ﺛَﻼﺛَﺔٌ ﻻَ ﻳُﻜَﻠِّﻤُﻬُﻢْ ﺍﻟﻠَّﻪ ﻳﻮْﻡَ ﺍﻟْﻘِﻴَﺎﻣﺔِ،
ﻭَﻻَ ﻳُﺰَﻛِّﻴﻬِﻢْ، ﻭَﻻ ﻳﻨْﻈُﺮُ ﺇﻟَﻴْﻬِﻢْ، ﻭﻟَﻬُﻢْ ﻋﺬَﺍﺏٌ
ﺃﻟﻴﻢٌ: ﺷَﻴْﺦٌ ﺯَﺍﻥٍ، ﻭﻣَﻠِﻚٌ ﻛَﺬَّﺍﺏٌ، ﻭَﻋَﺎﺋِﻞ ﻣُﺴْﺘَﻜْﺒِﺮٌ ‏»
ﺭﻭﺍﻩُ ﻣﺴﻠﻢ .

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

ሙስሊም ﺭﻭﺍﻩُ ﻣﺴﻠﻢ በዘገበው ሀዲስ
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ #ሦስት
ሰዎች የውመልቂያማ አላህ አያናግራቸውም አያያቸውም የተባሉት
እነማን ናቸው?

1ኛ________?
2ኛ________?
3ኛ________?


👇መልስ መስጫ:-👇
@iqrafeedbackbot @iqrafeedbackbot

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

ጥያቄ 2//
📖በቅዱስ ቁርኣን📖 ውስጥ አንዲት ምእራፍ አለች፣ እሷም 👇
"አንድ ሰው ምህረት እስኪያገኝ ድረስ አማላጅ ትሆንለታለች"
ይህች የቁርአን ምዕራፍ ማን ናት? የሚል ነበር
http://t.me/iqraknow

ማሻአላህ ብዙ ተሳታፊዎች በትክክል መልሰውታል። አላህ እውቀቱን ይጨምርላቹ

ለጥያቄው 👇ትክክለኛ መልሱ👇
✅(ሱረቱል ሙልክ) = ተባረከለዚ ቢየዲሂል ሙልኩ..... ✅
http://t.me/iqraknow http://t.me/iqraknow

Читать полностью…

📚 ኢቅራዕ ጠቅላላ ዕውቀት 🌐

ጥያቄ
http://t.me/iqraknow
አንድ የቁርአን ሱራ/ምእራፍ አለች 15 አያእ/አንቀፆች ያሏት እና በመካ የወረደች ስትሆን እንያንዳንዱ አያ የሚጨርስበት ፊደል ሃ "ها" ያበቃል::
#ይህች_የቁርአን_ሱራ/ምእራፍ #ማናት? የሚል ጥያቄ ጠይቀን ነበር፣
ማሻአላህ እጅግ በጣም ብዙ ተሳታፊዎች መልሱን በትክክል መልሰውታል፣ ጀዛከላሁ ኸይረን ወጀዛዕ

የጥያቄው 👇መልሱ👇👇
📖ሱረቱል አል ሸምስ السورة الشمس Suretul al shams 📖 ነው።
ወሸምሲ ወዱሃሃ
ወልቀመሪ ኢዛተላሃ
.
.
.
http://t.me/iqraknow http://t.me/iqraknow

Читать полностью…
Subscribe to a channel