habeshagay1 | Для взрослых

Telegram-канал habeshagay1 - ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

-

Подписаться на канал

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

በእምነት ላይ ብቻ  የተሞላ እንቅስቃሴ ጥበብ ሳይታከልበት ግብ አይመታም ።

ሁሉም ሰው ልቤ ላይ ያለውን እውነት ይወቅልኝ፤ ይመነኝ  ትግል አድካሚ ነው የደስታ ጠር ነው። 

እውነት ማለት የምናየው ብቻ አይደለም ። በምናየው ነገር ብቻ ተመርኩዘን አንገቴን ለካራ እሰጣለው ሙግት አይረታም !  

ስኬት በትግል ብቻ አይመጣም። እድልም ጥበብም ሲታከልበት ነው የሚሰምረው።  

መብሰል  ማለት ትልቅ ነገርን መረዳት ብቻ አይደለም፤ ጥቃቅን ፣ የማይሰተዋል እና  ተራ ነገርንም መገንዘብ  ጭምር  እንጂ።

ህይወት ዛሬም ነች፤ ዛሬ ያለን በረከት ካልታወቀን የምንጠብቀው፣ የሚመጣው በረከትንም አናጣጥመውም Enjoy ዛሬንም

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

ጉበትዎን እንደ ወሳኝ ልዕለ ኃያል የሠውነት አካሎ አድርገው ያስቡ...በተለያዩ የሰውነት ተግባራት ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ልክ እንደ ሰውነት ኬሚካል ፋብሪካ ነው። ጉበት የምግብ ንጥረ ነገሮችን (ንጥረ-ምግቦችን) ያስተካክላል፤ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ይሰብራል፣ እና እንደ አልቡሚን ያሉ አስፈላጊ ፕሮቲኖችን ያመነጫል. በተጨማሪም፣ ስብን ለማዋሃድ የሚረዳውን ቢል የመሥራት ሃላፊነት አለበት። ጤናማ ጉበት ከሌለ ሰውነትዎ በትክክል አይሰራም።


የጉበት በሽታ (ሂፕታይትስ) የሚከሰተው በጉበታችን ውስጥ ያሉ ሴሎች በሽታ አምጪ በሆነው ቫይረስ ሲጠቁ ነው። እንዲሁም የአልኮል መጠጥና ሌሎች መርዛማነት ካላቸው ነገሮች እና አንዳንድ መድኃኒቶች የሚያመጧቸው የጎንዮሽ ችግሮች በሽታ ሊከሰት ይችላል።

በቫይረስ የሚከሰተው የጉበት በሽታ ዓይነቶች ዋንኞቹ አምስት ሲሆኑ፤ እነዚህም የጉበት በሽታ
ኤ፣ ቢ ፣ ሲ፣ ዲ እና ኢ ተብሎ
ይጠራሉ።

1⃣ የጉበት በሽታ ኤ (ሂፕታይተስ ኤ)

ሂፕታይተስ ኤ በአብዛኛው የሚከሰተው በንጽህና ያልተዘጋጀ ምግብ በመመገብ ወይም ንጹህ ውሃ ባለመጠጣት ነው። ይህ አይነቱ የጉበት በሽታ ንፁህ ውሃና ፅዱ አካባቢ በማይኖሩ ሰዎች ዘንድ ማየቱ የተለመደ ነው።

መከላከያው፡- የግል የአካባቢ ንፅህና በመጠበቅ እንዲሁም ንፁህ ውሃ በመጠጣት በሽታውን መከላከል ይቻላል። ባደጉት ሃገራት ግን ክትባቱ ይገኛል።


2⃣ የጉበት በሽታ ቢ (ሂፕታይተስ ቢ)

ሂፕታይተስ ቢ ሊያገኘን የሚችለው በበሽታው ከተያዘ ሰው ደም ወይም ከሰውነቱ ከሚወጣው ፈሳሽ ጋር ንክኪ ሲኖር ነው። ለምሳሌ በጥንቃቄ ያልተያ ጸጉር ወይም ጺም በጋራ ምላጭ ወይም መሳሪያ የሚጠቀሙ፣የጋራ የጥርስ ብሩሽ፣ የልቅ የግብረ ስጋ ግንኙነት የሚያደርጉ ሰዎች የጉበት በሽታ ቢ በቀላሉ ያገኛቸዋል።

ሂፕታይተስ ቢን በክትባት መከላከል የሚቻል ሲሆን፤ የጺም ወይም ፀጉር መላጫዎችን፣ የጥርስ ብሩሽ፣ የጥፍር መቁረጫዎችን በጋራ ባለመጠቀም በሽታውን መከላከል ይቻላል። በተጨማሪም ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑሰዎች ክትባቱን ቢወስዱ ይመከራል።

3⃣ የጉበት በሽታ ሲ (ሂፕታይተስ ሲ)

ሄፒታይተስ ሲ ማለት መንስኤው ሄፒታይተስ ሲ ቫይረስ የሆነ የጉበት ህመም ማለት ሲሆን፤ አንድ ሰው በህመሙ ከተያዘ በኋላ ባሉት የመጀመሪያዎቹ ወራት የሚከሰት ነው። የሂፕታይተስ ሲ ዋናው መከላከያ መንገድ ለበሽታው የሚያጋልጡ ነገሮችን ማስወገድ ነው።
በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር በጋራ የምንጠቀምባቸውን ማንኛውም ነገር ማቆም መፍትሄ የሚሆን ሲሆን፤ ህክምና ወደሚሰጥበት ጤና ተቋም በመሄድ ሄፒታይተስ ሲ ቫይረስ ሊያድኑ የሚችሉ አዳዲስና ፍቱን መድሃኒት ማግኘት ይችላሉ።

4⃣ የጉበት በሽታ ዲ (ሂፕታይተስ ዲ)

የጉበት በሽታ ዲ የሚባለው በቀጥታ የጉበት በሽታ ቫይረስ በተበከለ ደም አማካኝነት ይተላለፋል፡፡ ይህ በሽታ የሚታየው በጉበት በሽታ ቢ ለተያዘ ብቻ ነው።

መከላከያው፡- የግል መጠቀሚያ የሆኑትን የጥርስ ብሩሽ፣ የፂም መላጫ መሳሪያዎችን፣ የጥፍር መቁረጫ ቁሳቁሶችን በጋራ አለመጠቀም እንደ ሁነኛ ቅድመ መከላከያ ተደርጎ ይወሰዳል።

5⃣ የጉበት በሽታ ኢ (ሂፕታይተስ ኢ)

ይህ በሽታ ዋናው መተላለፊያው መንገድ በጉበት በሽታ የታመመ ሰው ዓይነ ምድር የተበከለ ውሃ በመጠጣት ወይም ምግብ በመመገብ ነው።

መከላከያው፡- መፍትሔው የራስንና የአካባቢን ንጽህና መጠበቅ ነው። በተለይ ንጽህናው
ካልተጠበቀ ቦታ የሚመጣን ውሃ ፈጽሞ አለመጣት ራስን ከጉበት በሽታ ማዳን እንደሆነ ማወቅ ይገባል።

ለበለጠ መረጃ
https://healthtrip.com/am/blog/liver-disease


@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣5⃣2⃣

“ምን ላድርግ?” ለምትሉ

➡️ ያላችሁበትን ስፍራ ካልወደዳችሁትና ፈጽሞ የማይጠቅማችሁ ከሆነ
#ስፍራ_ቀይሩ!

➡️ያላችሁ ጓደኝነት ከጥቅሙ ጉዳቱ ካመዘነና ስሜታችሁን ካልወደዳችሁት
#የጓደኝነት_ለውጥ_አድርጉ!

➡️ የገባችሁበት የፍቅር ግንኑነት ከጉጉቱ ስጋቱ ካመዘነ
#እርግጠኝነትን_እስክታዳብሩ_ድረስ_ቆም_በሉ

➡️ ያላችሁን የኑሮ ደረጃ ካልተቀበላችሁት
#እቅድ_አውጡና_ለለውጥ_ስሩ!

➡️ ያላችሁን የእውቀት ደረጃ ካልተማመናችሁበት
#ተማሩ! #ሰልጥኑ! #አንብቡ!

➡️ ያላችሁን የግል ባህሪይ ስታስቡት ካሳፈራችሁ
#የአስተሳሰብና_የተግባር_ለውጥ_የማምጣት_ጉዞ_ጀምሩ!

➡️ በመጓዝ ያላችሁበትን የሕይወት አቅጣጫ ካላመናችሁበት
#ቆም_በሉ! #አስቡ! #አቅጣጫን_ለውጡ!

ተነሱና አንድ ነገር አድርጉ!
ቁጭ ተብሎ የሚለወጥ ነገር እኮ የለም!

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ


@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

Отажон қабримни ўзгартиринг илтимос...😭

Бир қизча ёшлигидан ибодатда маҳкам бўлиб намозларини қолдирмасдан доимо ўқирди. Аммо 9 ёшига етганда вафот этди. Вафот этган кунидан бошлаб отасининг тушига кириб "Отажон қабримни ўзгартиринг, мен азобланябман" дер эди. Аввалига отаси этибор бермади. Лекин бу туш ҳар куни такрорлашни бошлаганди. Ва бир кун қизидан тушига, нега азобланятганини сўради ва ўша куннинг ўзида қизининг қабрини ўзгартирди.

Қизи тушда шундай деганди: давоми 😭👇

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#Диккат
Бугун каналларда маош 3.000.000дан 20.000.000гача булган вакансиялар базаси таркалиб кетди.

/channel/+22USZqyztZ40ODQy

Коплаб йирик компаниялар элон берувчи ҳамма излаган канални топдик. Кўплаб маълумотлар, минглаб элонлар базаси интернетга чиқиб кетди. Ойликлар 20млнгача.

Кириб ўз вилоятингизни танланг:

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/+22USZqyztZ40ODQy

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

Can't Live Without You (2022)
Original title: Sin ti no puedo

👨🏼‍🤝‍👨🏻
#CantLiveWithoutYou 👨🏼‍🤝‍👨🏻

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

⚡️10 йилга бўлиб тўлашга

Таъмирланган уйлар!

👉Уйларни кўриш

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

https://youtu.be/ZiAiT-7_TRg?feature=shared

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣4⃣7⃣

#ቀና_ብላችሁ_ኑሩ!

ፍቅረኛ ሳልይዝ ሌላ ዓመት መጣ፣ እድሜዬም ሊያልፍ ነው ብላችሁ ከመፍራትና ትክክለኛ ባልሆነ ሰው ላይ ከመውደቅ ይልቅ፣
#ትክክለኛውን_ሰው እስከምታገኙ ድረስ ራሳችሁን እያሳደጋችሁ፣ የወቅቱን ሁኔታችሁን ተቀብላችሁ፣ እንደገና የማይመለሰውን ይህንን “#የብቸኝነት” ኑሮ እያጣጣማችሁና ተረጋግታችሁ እያንዳንዷን ቀን ቀና ብላችሁ ብትኖሩ ይሻላችኋል፡፡

እድሜ ማለፉ ላይቀር ከማይሆን ሰው ጋር እየተነታረካችሁ ከሚያልፍ ይልቅ ከራሳችሁ ጋር ተስማምታችሁ ቢያልፍ ይሻላል፡፡ ራሱን የሚቀበል፣ ራሱን የሚያከብር፣ ራሱን የሚያሳድግና ራሱን የሚመራ ሰው በፍጹም ብቸኝነት ተሰምቶት አያውቅም፡፡

መልካምና የተረጋጋ “
#የብቸኝነት” ዓመት ይሁንልን

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣4⃣5⃣

#ተለዋጭ_እቅዳችሁ_ምንድን_ነው?

አንዳንድ ሰዎች አንድን ግብ ወይም እቅድ ካወጡ በኋላ ጉዞው ከበድ ሲላቸው ይጨናነቃሉ።እቅዳቸውን መቀየር ሞት መስሎ ይታያቸዋል።ይህ ዝንባሌ የሚመጣው በዋና ራእይና ወደዚያ ለመድረስ በምናወጣቸው እቅዶች መካከል ያለውን ልዩነት ካለመለየት ነው።

የምንከተለው ራእይ ሊለወጥ አይችልም፣ ሕይወታችንን እንደ መልሕቅ ችከሎ የያዘ ዋናው ዓላማች ስለሆነ።እቅድ የምንለው ነገር ግን እዚያ ግብ ላይ ለመድረስ የምንከተላቸው የተለያዩ ተግባራዊ እርምጃዎች ናቸው።ስለሆነም ወደ ራእያችን ስንገሰግስ ሳለን የምንሄድበት ጎዳናና እቅዳችን አላስኬድ ሲለን እቅድንና ስልትን መቀየር ምንም ችግር እንደሌለበት ራሳችንን ማሳመን አለብን።

አንዳንድ ሰዎች ጉዞው ከባድ ሲሆን እድሜአቸውን ሙሉ የተከተሉትን የሕይወት ዋና አላማና ሕልም ትተውት ይሄዳሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ እንደየሁኔታው አላማቸውን ይለዋውጣሉ።ጉዞው ሲከብድ ግን መቀየር ያለበት አላማ ሳይሆን አደራረግ ነው።በሕይወትህ ልትከተል የምትችለው ዋነኛ የአላማ መልህቅ አንድ ብቻ ነው።ሌሎች እዚህና እዚያ ብቅ ብቅ የሚሉ አንዳንድ አዳዲስ እቅዶች ቢኖሩህም ከዋናው አላማህ ጋር አብረው የሚጓዙ መሆናቸውን እርግጠኛ መሆን አለብህ።

ዋናው ቁም ነገር ግን ይህ ነው፡- ትናንትና ደምህ ውስጥ ሲዘዋወር የነበረው ሕልምህ በአንድ ጊዜአዊ የሁኔታዎች አለመመቻቸት ምክንያት ሊጣልና ሊቀበር አይገባውም። ስለሆነም ሁል ጊዜ ወደ ዓላማህ የምትጓዝበት የመጀመሪያ እቅድ ይኑርህ።ያን ካወጣህ በኋላ ግን ድንገት እሱ መንገድ ካልሰራ ሁለተኛ፣ እሱም ካልሰራ ደግሞ ሶስተኛ እቅድ ይኑርህ።

በርቱና ላቃታችሁ ነገር እንደገና ሌላ እቅድ አውጡ ወደፊት!

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣4⃣4⃣

#አንድ_እርምጃ_ወደፊት!

ሕይወት እንዳደረጋችሁት ነው፡፡ ስትንቀሳቀሱ ወደፊት ትሄዳላቸሁ፣ ስትቆሙ ወደኋላ ትቀራላችሁ፣ ስትወላውሉ ደግሞ ባላችሁበት ትረግጣላችሁ - ስሌቱ ይኸው ነው!

በዙሪያችሁ የሚገኙትን ሰዎችን ተመልከቷቸው፡፡ አንድ ቀን ከእንቅልፋቸው ሲነቁ አይደለም እዚህ ብዙዎች የሚመኙበት ደረጃ ደርሰው ራሳቸውን ያገኙት፡፡ ተንቀሳቅሰው፣ ሰርተው፣ አጠራቅመው፣ ታግለው . . . ነው፡፡

ነገ ከዛሬው፣ የዛሬ ዓመት ደግሞ ከዘንድሮው የተሻለ ሕይወት ከፈለጋችሁ ያንን የማድረጊያው ብቸኛውና እርግጠኛው መንገድ መንቀሳቀስ ነው፡፡ ይህ እቅስቃሴ ደግሞ የግድ ትልልቅ መሆን የለበትም፡፡ በየቀኑ የሚደረጉ ትንንሽ እርምጃዎች በዓመት ውስጥ አንድ ግዙፍ ነገር እጃችሁ እንዲገባ ያደርጋል፡፡

ይህንን ከላይ የተጠቀሰውን የማበረታቻ ሃሳብ ተግባራዊ ለማድረግ ልቦናችሁ ከተነሳሳ የሚከተሉትን ልምምዶች ለመጀመር ሞክሩ፡፡

1⃣ አሁን ካላችሁበት ደረጃ በተሻለ መልኩ ለማወቅ በምትፈልጉት በአንድ እውቀት ዙሪያ መጽሐፍን የማንበብ ወይም አንድን ስልጠኛ የመውሰድን አንድ እርምጃ ተራመዱ፡፡

2⃣ ቀረብ ብላችሁ ብትተዋወቁትና ብታውቁት ለሕይወታችሁ እድገት የክህሎ ወይም የስብእና መዋጮ ያደርጋል ብላችሁ የምታስቡትን አንድ ሰው የመቅረብንና የመተዋወቅን አንድ እርምጃ ተራመዱ፡፡

3⃣ በእጃችሁ ላይ ያለውን ገንዘብ ወይም አንድ ንብረት በማዋል (ኢንቨስት በማድረግ) የተሻለ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ለመድረሰ ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ አንድ እርምጃ ተራመዱ፡፡

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣4⃣2⃣

#ማቆም_የለም!!

ምንም ነገር ከመጀመራችሁ በፊት የምትጀምሩት ነገር በእርግጥም ያመናችሁበትና ከዋናው የሕይወት ዓላማችሁ ጋር የተገናኘ መሆኑን እርግጠኛ ሆኑ፡፡ ያንን ለማድረግ ማሰብ፣ ማቀድ፣ ማማከር . . . ካስፈለጋችሁ ያንን አደርጉ፡፡ ሆኖም አንድ ጊዜ ካመናችሁበት በኋላ ግን መብረር ነው፡፡

“መብረር ካልቻላችሁ ሩጡ፣ መሮጥ ካልቻላችሁ ተራመዱ፣ መራመድ ካልቻላችሁ ተንፏቀቁ፣ ምንም አረጋችሁ ምንም ወደፊት መንቀሳቀሳችሁን አታቁሙ” - Martin Luther King Jr.

በሆነው ባልሆነው እየወላወልን፣ ተስፋ እየቆረጥን፣ እየቆምንና ወደኋላ እየተመለሰን ዓላማ ላይ መድረስ የሚባል ነገር የለም፡፡

አትቁሙ! አትመለሱ! በርቱ!

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣4⃣1⃣

#እንቅፋቶቹ_መረማመጃዎች_ናቸው!

አንድ ትንሽ ልጅ እህቱን ወደ አንድ መንገዱ በጣም አስቸጋሪ ወደ ሆነ ኮረብታ ጫፍ ላይ ለማድረስ እየመራት ነው፡፡

“ነይ፣ መንገዱ በዚህ ነው” በማለት እንዳትንሸራተት ድንጋዮች ያሉበትን መንገድ በመምረጥ እየመራት ሲሄድ፣ በመንገዱ ላይ ባሉት ድንጋያማ “እንቅፋቶች” የተቸገረችው ልጅ፣ “ለምን በዚህ መራኸኝ፣ ይህ እኮ መንገድ አይደለም፣ ድንጋያማ ነው!” በማለት ተነጫነጨች፡፡


የልጁም መለስ፡- “እንቅፋት በመሰሉሽ ድንጋዮች ላይ ነው እኮ እየተረማመድሽ መሄድ ያለብሽ”፡፡

የሚገርም የሕይወት ፍልስፍና! በእንቅፋቶቹ ላይ እየተረማመድኩኝ ወደ ዓላማዬ እገሰግሳለሁ!

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

"ያ የአካላችን ክፍል አእምሮ ይባላል።"
=======================
እንደሰው ልጅ የሚዝናና የለም። እስካሁን Meme አይቶ የሳቀ ድመት የለም። "እስቲ አሪፍ ፊልም አይቼ ዘና ብዬ ልምጣ" የሚል ሌላ ፍጥረት ተሰምቶ አይታወቅም።
      "አጭር ግጥም፤
        ለጆሮ የሚጥም።" ብሎ ቋንቋን መልእክት ከማስተላለፍ በዘለለ ውበትን ለመፍጠር የሚጠቀም የለም። "እስቴ ሆዴ ስር አረንጓዴ ቲሸርት ለብሶ ከቆመው ሰውዬ ጋር ፎቶ አንሱኝና ፌስቡክ ላይ ልለጥፍ።" የሚል ሊመር የለም።😉  ....ዝርዝሩ ላይ እናንተ ቀጥሉበት። ብቻ እንደ  ሰው የሚዝናና የለም!

በሌላ በኩል ደግሞ እንደ ሰው የሚጨነቅ የለም። "ተመርቄ ስራ ባላገኝስ?" የሚል አንበሳ መኖሩን እኔ'ንጃ! "የአየር ንብረት ለውጥ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል!" ብሎ የሚብሰለሰል አሞራ ያለ አይመስለኝም።"ልጄን የት ትምህርት ቤት ላስገባ?" ብሎ እንቅልፍ የሚያጣ ግመል መኖሩ ያጠራጥራል።

በአጠቃላይ ደስታችንን፣ ጭንቀታችንን፣ ፍላጎታችንን፣ ስጋታችንን የሚቆጣጠረው ያ የአካላችን ክፍል አእምሮ ይባላል።

ሳይቆጣጠረን በፊት እኛ እንቆጣጠረው

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣3⃣8⃣

#ሰበካው_ረገብ_ይበል!
ለፍቅረኛሞች . . .

አጋሮቻችሁ ያላቸውን የውስጥ ሃሳብ፣ ደካማ ጎን፣ የስሜት ቀውስ፣ ያታገላቸውን ነገርና ለሌላ ሰው የማይነገር የውስጥ ስሜት ሲነግሯችሁ እንደዚያ ሊሰማቸው እንደማይገባ፣ ማሰብ የሚገባቸው ምን እንደሆነ፣ ማካበድ እንደሌለባቸውና የመሳሰሉት እነሱን ለማድመጥ እረፍት እስከምታጡ ድረስ “የመስበክ” ዝንባሌ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡

አብዛኛውን ጊዜ አጋሮቻችሁ መደመጥንና የአይዞህ መልእክትን ብቻ ሊፈልጉ ይቻላሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ካደመጣችሁ በኋላ “በምን ላግዝ?” የሚለው ጥያቄ ወቅታዊ ሊሆን ይችላል፡፡ እነዚህንና መሰል የጥሩ አጋር ዝንባሌዎችና ልምምዶች ተግባራዊ እንዳታደር የሚጋፋችሁ እንቅፋት ቢኖር የሃሳብ ሰጪነት፣ የአቅላይነትና የቸልተኝነት ዝንባሌ ነው፡፡

ሰበካው ረገብ ይበል! አድማጭነቱና አብሮነቱ ጨመር ይደረግ! 

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣5⃣3⃣

#ወሳኙ_የፍቅር_ቅድመ_ጥያቄ

(
#በፍቅር_ጎዳና_ላይ_ላላችሁ . . .)

የፍቅር ግንኑነት ከመጀመራችሁ በፊት ይህንን ወሳኝ ጥያቄ ራሳችሁን በመጠየቅ መልስን ሳታገኙ ዘልቃችሁ ባትሄዱ ትመከራላችሁ፡-

“አንድን ሰው ምንም ያህል ባፈቅረው ያንን ሰው እጄ ለማስገባትም ሆነ ከገባ በኋላ እሱን ላለማጣት ስል በፍጹም ልለውጣቸውና ልቀናንሳቸው የማልችላቸው የራሴ የሕይወት መመሪያዎቼ (Principles) ምን ምን ናቸው?”

ይህንን ከላይ የተጠቀሰውን ጥያቄ ከጠየቃችሁ በኋላ ቁጭ ብላችሁ ቢያንስ አምስት የሚሆኑ የማይነቃነቁና እስከወዲያኛው የምታምኑባቸውን የፍቅር ግንኙነት መመሪያዎቻችሁን ለማውጣት ሞክሩ፡፡ እነዚህ መመሪያዎች (እሴቶች) ትክክለኛ፣ እውነታን ያገናዘቡ፣ ሚዛናዊና ከጊዜያዊ ጥቅምና እርካታ ይልቅ ከዘላቂው ሕይወታችሁ አንጻር መሆናቸውን እርግጠኞች ሁኑ፡፡ ያንን ለማረጋገጥ ደግሞ ከእናንተ በፊት የፍቅር ግንኙነትን መንገድ አልፎ የሄደና እንደ ሞዴል የሚሆናችሁን ጨዋ ሰው ማማከር ትችላላችሁ፡፡

ይህ ልምምድ የሚጠቅማችሁ፣ ሊከበሩ የሚገባቸውን የግል መመሪያዎቻችሁን (Principles) በሚገባ አውቃችሁ እንድትገቡና የፈለገ ሰው እንደፈለገ የሚያደርጋቸው አይነት ሰዎች እንዳትሆኑ ነው፡፡ የግል መርህ መስመር ቀድሞውኑ ካልተሰመረና ካልተከበረ አንዴ ከተጣሰ በኋላ ከሚከተሉት ውስብስብ ውጤቶች የተነሳ ከሁኔታው መውጣት እጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

የጉበት በሽታ (ሄፕታይተስ) ምንድነው፤ መከላከያው እና ህክምናውስ?
ጉበት በሰውነታችን ውስጥ የሰውነት ክፍሎቻችን ከሚገኙት ትልቁ ሲሆን፤ ቅርጹ ወደ ሦስት
ማእዘን ያደላል። በውስጡ 300 ቢሊዮን የሚደርሱ ሴሎች ያሉት ሲሆን እነርሱም በደም ቧንቧ
ውስጥ ሁነኛ ስራ ያላቸው ናቸው።
የጉበት በሽታ ምንድነው፤ መከላከያው እና ህክምናውስ? በሚለው ዙሪያ ከቅዱስ ጳውሎስ
ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜ. ኮሌጅ ያገኘነውን መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል።

👇🏽👇🏽👇🏽

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣5⃣1⃣

#በመጀመሪያ_ከራሳችሁ_ጋር_ኑሩ!

ከፍቅረኛ ውጪ በሰላም መኖር ካልቻላችሁ ከፍቅረኛ ጋር በሰላም መኖር አትችሉም፡፡ የዚህ እውነታ መሰረታዊው መነሻው ያለው፣ “
#ከራሱ_ጋር_በሰላም_መኖር_የማይችል_ሰው_ከማንም_ሰው_ጋር_በሰላም_መኖር_አይችልም” በሚለው ሃሳብ ላይ ነው፡፡

ከራስ ጋር በሰላም መኖር ማለት
#ራስን_መቀበል፣ ከማንም ሰው ውጪ ሙሉ እንደሆንን ማሰብ፣ ዓላማን ማወቅ፣ የተረጋጋ ማንነትና የመሳሰሉትን ሃሳቦች የሚያካትት ነው፡፡

እነዚህንና መሰል መሰረታዊ የራስ-በራስ ሰላምን የሚጠቁሙ እውነታዎች በሕይወታችሁ ከሌሉ ፍቅረኛ ለመፈለግ ያላችሁን የመነሻ ሃሳብ ያዛባዋል፣ ትክክለኛውን ሰው የመለየት እይታችሁን ፈዛዛ ያደርገዋል፣ በፍቅር ጎዳና ውስጥ የሚደርሱ ችግሮችን ለመቋቋም ያላችሁን አቅም ያደክመዋል፡፡

በመጀመሪያ ራሳችሁን ውደዱ፣ ማንነታችሁን ተቀበሉ፣ ካለፈው ስህተታችሁ ጋር ተፋቱ፣ የዛሬን ሕይወት አጣጥሙ፣ ለነገው አቅዱ … በአጭሩ በመጀመሪያ ከራሳችሁ ጋር ኑሩ! ያን ጊዜ ብቻ ከትክክለኛው ሰው ጋር፣ በትክክለኛው ጊዜና ለትክክለኛ ዓላማ ለመገናኘት የሚያስችል ስብእናን ታዳብራላችሁ፡፡ 

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣5⃣0⃣

#የንግግራችሁ ወሳኝነት!

#ለፍቅረኛሞች. . .

ከአጋራችሁ ጋር በየቀኑ ከምትለዋወጧቸውና ከምትጋሯቸው ነገሮች መካከል በዋናነት የሚጠቀሰው የንግግር ጉዳይ ነው፡፡ በየቀኑ፣ ምናልባት በየሰዓቱ ብዙ ንግግርን ትለዋወጣላችሁ፡፡ እነዚህ ንግግሮች በግንኙነታችሁ ጤንነትም ሆነ በአጋራችሁ የስነ-ልቦናና የስሜት ጤንነት ላይ ይህ ነው የማይባል መዋጮ አላቸው፡፡

ምግብ ለአካል ጤንነት ወሳኝ የመሆኑን ያህል
#ንግግር_ደግሞ_ለስሜት_ጤንነት_ወሳኝ_ነው፡፡ ምግብ አካል ውስጥ ገብቶ ወይ ለጤንነት ወይም ደግሞ ለህመም እንደሚሆን ንግግርም በስሜት ውስጥ ገብቶ እንዲሁ ነው፡፡

ወደራሳችሁም ሆነ ወደ አጋራችሁ ሰውነት ስለሚገባው የምግብ አይነትና መጠን ከምትጠነቀቁት ባላነሰ ሁኔታ ወደ
#ስሜታቸው_ስለሚገባው_ንግግር_መጠንቀቅ_አስፈላጊ_ነው፡፡

ለአጋራችሁ የምትናገሯቸውን ቃላት በጥንቃቄ ወደማጣራት በየእለቱ ማደግ አስፈላጊ ነው፡፡ እነሱን የሚጎዱ፣ ግራ የሚያጋቡ፣ ስሜታቸውን የሚጫኑ፣ ተስፋ የሚያስቆርጡና ባጠቃላይ ለስሜት ቀውስ የሚዳርጉ ንግግሮች በጤናማዎቹ ንግግሮች የመቀየር ልምምድን አዳብሩ፡፡

አጋሮቻችሁ በምትነግሯቸው ንግግሮች ምክንያት ወይ ቀስ በቀስ ብርታትን ያገኛሉ ወይም ደግሞ ቀስ በቀስ በስሜታቸው እየሞቱ ይሄዳሉ፡፡ የአጋራችሁ ጉዳት የግንኙነታችሁ ጉዳት ነው፡፡ የግንኙነታችሁ መጎዳት ደግሞ ዞሮ ዞሮ እናንተን መነካካቱ አይቀርም፡፡

በነገራችን ላይ ንግግራችሁ የአመለካከታችሁን ልህቀት ወይም ዝቅጠት አመልካች መሆኑን ታውቃላችሁ?   

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ  #2⃣4⃣9⃣

#ወደፊት!


ከፍቅር አጋራችሁ ጋር ያላችሁ ግንኙነት የትናንቱን፣ የዛሬውንና የነገውን የሚነካ ጉዳይ ነው፡፡

የትናንቱ ከእጃችሁ ተወስዷል፡፡ ያለፈ ነው፣ አልፏል፣ ሞቷል፣ አክትሟል፡፡ ስለሆነም፣ ከሁኔታው የምታገኙትን ትምህርት አግኙ፣ ተወያዩ፣ ቀለል በሉ፣ ይቅር ተባባሉና ወደፊት!

የነገው ገና እጃችሁ አልገባም፡፡ የወደፊት ነው፣ ገና አልመጣም፣ ተስፋ እንጂ ተጨባጭ አይደለም፣ ይምጣ አይምጣም አይታወቅም፡፡ ስለሆነም፣ የነገውን ፍቅራችሁን ከዓላማ አንጻር ቃኙ፣ ተወያዩ፣ ተስፋችሁንም ባለመልቀቅ ወደፊት!

የዛሬው እጃችሁ ገብቷል፡፡ የአሁኑና በእጃች ያለው የግንኙነታችሁ ጉዳይ በትናንት ትምህርትና ልምድ በመታገዝና በነገው እቅድና ተስፋ በመጋጋል እየተጣጣመ ወደፊት!

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

Can't Live Without You (2022)
Original title: Sin ti no puedo

👨🏼‍🤝‍👨🏻
#CantLiveWithoutYou 👨🏼‍🤝‍👨🏻

✏️Sub: English
🌏 Country: Spain
📝 Language:
#Spanish #Mexico
🌟 Score: 4.6/10
🎭 Genre: Drama, Thriller
🎬 1h 31min

✨ Storyline: A gay gym teacher wants to be a father and when his boyfriend's sister, a former addict, comes back on the scene there is now a possible solution.

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

👇🏽👇🏽

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣4⃣8⃣

#መፍራት_ስትጀምሩ_መኖር_ታቆማላችሁ!!

ፍርሃት እንዲህ ይልሃል …

🚫አትመልከት -
#አንድ_ነገር_እንዳታይ!
🚫አታድምጥ -
#አንድን_ነገር_እንዳትሰማ!
🚫አታስብ -
#አንድ_ድምዳሜ_ላይ_እንዳትደረስ!
🚫አትወስን -
#ስህተት_እንዳትሰራ!
🚫አትራመድ -
#እንዳትወድቅ!
🚫አትኑር -
#እንዳትሞት!
🚫አትማር -
#ፈተና_እንዳትወድቅ!
🚫አትውደድ -
#እንዳትጎዳ!

በሕይወትህ ልታነግሱ የምትችሉት ስሜት አንዱን ብቻ ነው - የፍርሃትን ወይም የመኖር ድፍረትን፡፡ አንዱ እንዲነግስ ስትፈቅድለት ለሌላኛው የባርነት ትእዛዝን እያስተላለፍክ ነው፡፡ ፍርሃት ሲነግስ የመኖር ጣእም ይጠፋል፡፡

ይህ የፍርሃት ስሜት ይለፍላችሁ!
ተነሱና ፈጣሪን ተማምናችሁ ቀና ብላች ኑሩ!

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣4⃣8⃣

#ሁለቱ_ወሳኝ ጉዳዮች

አንድ የግሪክ ፈላስፋ በአንድ ወቅት፣ “በዓለም ላይ በጣም አስቸጋሪው ነገር ምንድን ነው?” ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ፣ “ራስን ማወቅ” በማለት እንደመለሰ ይነገራል፡፡ ከዚያም ጠያቂዎቹ “በዓለም ላይ በጣም ቀላሉ ነገርስ ምንድን ነው?” ብለው ሲጠይቁት፣ “ለሰዎች ሃሳብ ሰንዛሪነት” በማለት እንደመለሰም ይነገራል፡፡
#በዚህ_በጀመርነው_ዓመት_በእነዚህ_በ2_ከባድና_ቀላል_በተሰኙት_ወሳኝ_ጉዳዮች_ላይ_እንስራ፡፡

1⃣
#ከባዱ_ነገር #ራስን_ማወቅ፡፡

ራእዬን፣ ፍላጎቴን፣ ዝንባሌዬን፣ የሚቀናኝንና የማይነቀኝን፣ የቤተሰብ አስተዳደጌ በእኔ ላይ ያመጣውን ተጽእኖ፣ ከሕብረተሰቡ የወረስኩትን መልካምና አጉል ተጽእኖና የመሳሰሉትን ማሰብ፣ መለየትና ተገቢውን የጥበብ እርምጃ መውሰድ በዚህ ዓመት የሚኖረኝን ስኬታማነት ይወስናል፡፡

2⃣.
#ቀላሉ_ነገር #ለሰዎች_ሃሳብ_ሰንዛሪነት፡፡

ለቅርብ ሰዎችም ሆነ በአካባቢያችን ለሚኖሩ የሕብረተሰቡ አካሎች በማያገባን ነገር ሁሉ ጥልቅ እያልን ሃሳብ ሰንዛሪዎች መሆን በመጀመሪያ በራሳችን ላይ እንዳንሰራ ትኩረታችንን የመስረቅ ጉልበት ሲኖረው፣ ሲቀጥል ደግሞ ያለንን የማሕበራዊ ግንኑነት የማበላሽት አቅም አለው፡፡ ለመደገፍና ለመፍትሄ ራስን ለማቅረብ ፈቃደኞች ባልሆንበት ጉዳይ ላይ የሩቅ ሃሳብ-ሰጪዎች እንደመሆን ቀላልና ቀላልነትንም የሚስከትል የሕይወት ዘይቤ የለም፡፡

በዚህ በጀመራችሁት አዲስ አመት የተለመደውንና እጅግ ቀላል የሆነውን የሃሳብ ሰንዛሪነት ልማድ ቀነስ በማድረግ ከበድ ያለውንና  እጅግ ጠቃሚ የሆነውን ራስን የማወቅን ጎዳና በመጀመር በዚያ የመመራትን ልምምድ እንድትጀመር ላነሳሳችሁ፡፡

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

Оилавий муносабатларим яхши эмас.
Эрим билан кўп тортишамиз.
Уй юмушларидан бўшаб ўзимга қарашга вақт йўқ .Фарзандларим тарбиясида ҳам қийналаман, жуда шўх.Аксига олиб охирги пайтлар семириб кетябман.

Лекин мен яқинда дугонам тавсияси билан
AYOLLAR KANALI номли каналга уланиб олдим нафақат оилавий муносабатларда балки ўзимни қийнаган бошқа муаммоларга хам ечим топдим!. Эрим эса хозир совғалар олиб келади кўнглимга қарайди, жуда бахтлиман Сизларга ҳам қўшилиб олишни самимий тавсия қиламан👇

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣4⃣5⃣

#የአጋራችሁ_የስሜት_ቁልፍ

#ለፍቅረኛሞች. . .

አጋሮቻችሁ ከእናንተ ጋር ባላቸውን ንግግር ወይም ግንኙነት ወቅት ስሜታዊ በሚሆኑበት ጊዜ ምንም ነገር ከማድረጋችሁ በፊት በቅድሚያ “
#አጋሬን_ለዚህ_ስሜት_የዳረገው_የእኔ #ንግግር#ሁኔታ ወይም #ተግባር_ምንድን_ነው?” በማለት የመጠየቅን ልምምድ ብታዳብሩ ከብዙ አለመግባባት የምትድኑበትን ጥበብና ብስለት እንዳዳበራችሁ አትዘንጉ፡፡

ንግግራችንና ተግባራችን በአጋራችን ላይ ስሜትን ያነሳሳል፡፡ መልካም ንግግርና ተግባር ጥሩ ስሜትን ሲፈጥር፣ መጥፎ ንግግርና ተግባር ደግሞ ጥሩ ያልሆነን ስሜት ያነሳሳል፡፡ በሌላ አገላለጽ ለንግግራችንና ለተግባራችን መጠንቀቅ ማለት ለአጋራችንን ስሜት መጠንቀቅ ማለት ነው፡፡ 

አብዛኛውን ጊዜ የአጋራችሁ የስሜት ቁልፍ ያለው እናንተ ጋር እንደሆነ አስታውሱ፡፡

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣4⃣3⃣

#ለማረፍ_ሳይሆን_ስላረፋችሁ!

አንዳንድ ሰዎች የፍቅር ግንኙነት ቢጀምሩ አሁን ያለባቸው ግራ መጋባት የሚለቃቸውና እረፍትን የሚያገኙ ይመስላቸዋል፡፡ ስለሆነም፣ በውስጣቸው እረፍትን ያጡት ትክክለኛውን ፍቅረኛ ስላላገኙ ስለሚመስላቸው በዚህ በተረበሸ ማንነት ፍቅረኛን ፍለጋ ያላቸውን አሰሳ ይቀጥላሉ፡፡

የዚህ እሳቤና አካሄድ
#ትልቁ_ስህተት፣ ያላረፈ አእምሮ ያለው ሰው ትክክለኛውን ምርጫ የማድረግ አቅሙ የመወሰዱ ጉዳይ ላይ ነው፡፡

ልክ እጅግ የተጠማ ሰው ያገኘውን “ፈሳሽ” ሁሉ እንደ ጥም ማርኪያ እንደሚጠቀምበት . . .  በጣም የተራበም ሰው ያገኘው “ምግብ” ሁሉ እንደረሃብ ማስታገሻ እንደሚያውለው ሁሉ ግንኙነት ስለጠማውና ስለራበው የተወዛገበውም ሰው ያገኘው እድል ሁሉ ከዚያ እረፍተ-ቢስ ስሜቱ የሚላቅቀው ይመስለዋ፡፡

እረፍት ፍለጋ ወደ ግንኙነት ከመግባት ይልቅ በመጀመሪያ
#አርፎ_መግባት ✅ በብዙ እጥፍ የተሻለ ነውና በመጀመሪያ ባላችሁበት ሁኔታ አረፍ በሉ! ያንን ስታደርጉ ብቻ ለትክክለኛው ምርጫና ውሳኔ የተመቻቸ ምልከታ ይኖራችኋል፡፡

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

Бўлиб тўлашга 2024-йилда курилган уйлар!

🔥 Энг замонавий, арзон ва кенг уйлар!
🔥 2024-йилда қурилаётган уйлар ва уларнинг нархлари
🔥 12 ойдан 120 ойгача муддатли тўлов


👉 Нархларни кўриш

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣4⃣0⃣

#አንዱን_ምረጡ!


እስቲ በአሁን ሰዓት የተወዛገባችሁበትን ወይም ለውሳኔ የተቸገራችሁበትን ማንኛውንም ነገርና ሁኔታ አስቡት፡፡ ያላችሁን ምርጫ ባጠበባችሁት ቁጥር ስኬታማነታችሁ የጎላ ከመሆኑም ባሻገር በድንዛዜ ወራትና አመታትን ከማባከን ትድናላችሁ፡፡ ሁኔታውን ጠበብ ለማድረግ ደግሞ ታዋቂው ሄንሪ ፎርድ የጠቆመንን መንገድ መከተል እንችላለን፡፡

በስራም ሆነ በመሳሰሉት የወቅቱ ሁኔታችሁ አንጻር በብርታት ወደፊት ለመንቀሳቀስ ከፈለጋችሁ የወቅቱን ሁኔታችሁን መውደዳችሁን እርግጠኞች ሁኑ፡፡

ካልወደዳችሁት ግን ዝም ብሎ ከመነጫነጭና ስለሁኔታው ሲያወሩ ከመክረም በተቻላችሁ መጠን ሁኔታውን ለመቀየር ሞክሩ፡፡ ሁኔታውን የመቀየሩ ጉዳይ የማይታሰብ ከሆነ ደግሞ አንደኛችሁን ሌላ አቅጣጫና መስመር በመያዝ መንገዳችሁን ብትቀጥሉ ተመራጭ ነው፡፡

እነዚህን እጅግ ቀላል የሚመስሉና ለመተግበር ግን አስቸጋሪ የሆኑ ሶስት ደረጃዎች የማይለማመዱ ሰዎች ትኩረት የሌላቸው፣ ሁል ጊዜ የሚነጫነጩ፣ ሰውን መውቀስ የሚወዱ፣ ስለግላቸው ሁኔታ ሰው ላይ ማሳበብ የሚያዘውትሩና በየጊዜው ባሉበት የሚረግጡ ሰዎች ናቸው፡፡

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣3⃣9⃣

#ለመፈቀር_ሳይሆን_ስለተፈቀራችሁ..

አጋራችሁ
#እንዲያፈቅራችሁ ምንም ነገር ማድረግ #እንደማይገባችሁ ላስታውሳችሁ፡፡ አጋራችሁ #ስላፈረቀራችሁ_ግን_ብዙ_ማድረግ_የሚገባችሁ_ነገር_አለ፡፡ ምንም ነገር ማድረግ ያለባችሁ ለመፈቀር ሳይሆን ስለተፈቀራችሁ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ይህ የሆነበት ዋነኛ መነሻ ግንኙነታችሁ የተጀመረው በፍቅር መሰረት ላይ ስለሆነ ነው፡፡ ስለተፋቀርን አብረን እንሁን ተባባላችሁ እንጂ ለመፋቀር አብረን እንሁን ብላችሁ አልጀመራችሁም፡፡ 

አጋራችሁ እንዲያፈቅራችሁ የምታደርጓቸው ነገሮች የፍቅር ግንኙነታችሁን
#ሁኔታዊ ያደርገዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ግንኙነታችሁ በጎዶሎ (ወይም በሌለ) ፍቅር ጀምሮ እናንተ በምታደርጉት ነገር ወደሙላት እንደሚመጣ አይነት መልእክት አለው፡፡ ሆኖም ግን አጋራችሁ ለእናንተ ያለውን ፍጹም የሆነ ፍቅር ሊያበላሹ የሚችሉ ሁኔታዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ እትዘንጉ፡፡

ለመፈቀር አንድን ነገር ማድረግና ራስን ለመለወጥ መሞከር አሉታዊ ኃይል (Negative Energy) ነው፡፡ አጋራችሁ ስላፈቀራችሁና በዚያ ፍቅር ላይ በመልካም ለውጥ ለመገንባት መጣጣር አዎንታዊ ኃይል (Positive Energy) ነው፡፡ ይህንን አዎንታዊ ኃይል መጠቀም አረፍና ዘና ብላችሁ የተደላደለ ግንኙነት እንዲኖራችሁ ያደርጋችኋል፡፡ አሉታዊው ኃይል ግን ዘወትር የዝቅተኝነትና የመጦዝ ስሜት ስለሚሰጣችሁ የተጠንጠለጠለ ግንኑነት እንዲኖራችሁ ያደርጋል፡፡

#ለመፈቀር_ከመሯሯጥ_መለስ_በሉና_ለተሰጣችሁ_ፍቅር_ምላሽ_የሚሆንን_መልካም_ለውጥን_ለማምጣት_ሞክሩ፡፡

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ


@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣3⃣7⃣

#እስከመቼ !!! ???

በጓደኝነት፣ በስራ፣ በንግድ፣ በአለቃ-ሰራተኛ፣ በስራ ባልደረባነት፣ በጉርብትናም ሆነ በሌላ ማሕበራ መስክ ውስጥ ባላችሁ ግንኙነት፣
#ጊዜው_ሳይዘገይና ሁኔታው #ወደማንነት_ቀውስ ከማዝቀጡ በፊት መንቃት እንዳለባችሁ የሚያመለክቱ ጠቋሚዎች . . .

🔔  የራሱን ፍላጎት፣ ሃሳብና አቋም ብቻ እንዲሟላ እያደረገ የእናንተን ግን ለማሟላት ፈቃደኛ ያልሆነ ግንኙት፡፡

🔔  የስሜት፣ የአካል ወይም የወሲብ ጥቃት የሚያደርስባችሁ ግንኙነት፡፡ 

🔔 ሰዎቹን ስታስቡ ወይም ካገኛችኋቸው በኋላ ኃዘን፣ ድብርት፣ ንዴት፣ ቁጭትና የመሳሰሉት ስሜቶች እንዲያጠቃችሁ የሚያደርግ ግንኙነት፡፡

🔔 ሁል ጊዜ እናንተ ሰጪዎች እነሱ ተቀባዮችች እናንተ ይቅርታ ጠያቂዎች እነሱ ይቅር ባዮች፣ እናንተ ተለማማጮች እነሱ ተለማመጡኝ  ባዮች፣ እናንተ ፈላጊዎች አንሱ ተፈላጊዎች የሆነበት ግንኙነት፡፡

🔔ፈጽሞ መተማመን የሌለበትና በጥርጣሬና በጭቅጭቅ የተሞላ ግንኙነት፡፡

🔔 እናንተን እስከመጉዳት አልፎ የሚመጣ ልማድ፣ ሱስና አጉል ባህሪይ ካለበት ሰው ጋር ያላችሁ ግንኙነት፡፡

ይታሰብበት!!!

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…
Подписаться на канал