የበደለህን ይቅር በለው ጤና ይሰጥሃል።
የተበላሸብህ ነገር ደግመህ ሞክረው- ጥንካሬን ስለምታገኝ።
ደስተኛ ለመሆን ቻል መከፋት ሲረዝም በብዙ ስለሚያሳጣ።
ፈጣሪህን አመስግን- የተሻለ ስለምታገኝ።
ካንተ የባሰበትን ተመልከት መጽጽናናት ስለሚሆንልህ።
ካንተ የተሻለውን አስተውል- ተስፋ ስለሚጎበኝህ።
ስለገጠመኝህ ሰዎችን አማክር- መፍትሄ ስለሚሰጡህ።
ጸልይ፣ ለብቻህ ተደብቀህ አልቅስ- ለእፎይታህ።
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣2⃣4⃣
#ጣፋጩ ወይስ #ጤናማው
ሕይወት ሁልጊዜ ከባባድ ምርጫዎችን ፊታችን በማስቀመጥ የምትታወቅ ሂደት ነች።የምንመርጠው ምርጫ ደግሞ አቅጣጫችንን የመወሰን ጉልበት አለው። ከእነዚህ ምርጫዎች አንዱ #በጣፋጩና #በጤናማው መካከል የምታስቀምጥልን #ምርጫ ነው፡፡
አስባችሁት ከሆነ አብዛኛዎቹ ጣፋጭ ነገሮች ጤናማ አይደሉም።ለጊዜው ስለሚጣፍጡን ግን እንለምዳቸዋለን፣ እንደጋግማቸዋለን።በተቃራኒው አብዛኛዎቹ ጣፋጭ ያልሆኑ ነገሮች ጤናማ ናቸው።ለጊዜው ስለማይጣፍጡን ግን አንፈልጋቸውም፡፡
ለምሳሌ፣ የሚጣፍጠው ምግቡ፣ መጠጡና የመሳሰሉት ወደ ሰውነታችን ለማስገባት የምንጓጓላቸው ምርጫዎች ብዙ ናቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች ማቆም የማያስመኙ “ጣፋጭ” ነገሮች ናቸው።እነዚህን መቀማመስ ደስ ይላል፣ ይጣፍጣልም ነገር ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል።በሌላ በኩል ደግሞ ብዙም የማያይጥሙና አንዳንዴም ኮምጠጥ ያሉ ነገሮችን የመውሰድ ምርጫ አለን።ይህኛው ምርጫ ብዙም ባይጥምም ለጤንነታችን ግን ወሳኝ ነው።
በማሕበራዊ ግንኙነታችሁም አንጻር አስቡት።በአንድ ጎኑ ጊዜያዊ ደስታና እርካታ ብቻ የሚሰጣችሁ ግንኙነት አቅርቦቱ ብዙ ነው።ይህ ሁኔታ ቀላል ነው፣ ለስሜትም ይጣፍጣል።በሌላ ጎኑ ደግሞ ዘላቂና የወደፊት መስመር የሚዘረጋላችሁ አይነት ግንኙነት የመመስረት ምርጫ አላችሁ።ይህኛው ምርጫ ለጊዜው ያታግላል፣ መረርም ሊል ይችላል።በአስገራሚ ሁኔታ ግን ብዙዎች የሚጥማቸው ዘላቂ እቅድ ያለው ሳይሆን የአሁኑንና ጊዜያዊውን ስሜት የሚያረካላቸው ግንኙነት ነው።
#አስቡ! #ብልህ_ሁኑ! ዛሬ ጣፍጧችሁ ነገ መራራን ነገር ከሚያቀብላችሁ፣ ዛሬ ተመችቷችሁ ነገ ከሚቆረቁራችሁ ነገር #ተጠበቁ።
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣2⃣2⃣
ስለስሜታችሁ ሳይሆን #ስለተግባራችሁ!
ስለሚሰማችሁ ስሜት በፍጹም ተጠያቂነት ውስጥ ገብታችሁ እንደማታውቁ አትርሱት፡፡ ተጠያቂነት ውስጥ ራሳችሁን የምታገኙት ወደ እንቅስቃሴ በተለወጠው ተግባራችሁ ምክንያት ነው፡፡ ይህ መርህ በአዎንታዊ ስሜቶችና ተግባሮችም ሆነ በአሉታዊዎ ስሜቶችና ተግባሮች አንጻር እውን ነው፡፡
ለምሳሌ፣ በአንድ ሰው ላይ በውስጣችሁ ምንም አይነት ጤና-ቢስ ስሜት ቢኖራችሁም፣ በንግግር፣ በሁኔታም ሆነ በተግባር እስካልገለጣችት ድረስ በሃላፊነት አትጠየቁም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ለአንድ ሰው በውስጣችሁ ምንም አይነት ጤናማ ስሜት ቢኖራችሁም ያንን ስሜት በንግግር፣ በሁኔታም ሆነ በተግባር እስካልገለጣችሁት ድረስ ምንም መልካም ውጤት አይኖውም፡፡
ውጤታቸው ጥሩ የማይሆኑትን፣ አሉታዊና ለግንኙነት ቀውስ ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉትን ስሜቶች በትክክለኛው መንገድ የምታስተናግዱበትንና የምታስተነፍሱበትን ሁኔታ ማመቻቸት ሃላፊነቱ የእናንተ ነው፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ ውጤታቸው መልካም፣ አዎንታዊና ላሏችሁ ግንኙነቶች ጠቃሚ መዋጮ የሚያደርጉ ስሜቶቻችሁን ለትክክለኛው ሰው፣ በትክክለኛው ጊዜና በትክክለኛው መንገድ የመግለጽ ልምምድን ስታዳብሩ ውጤቱን ማግኘታችሁ አይቀርም፡፡
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣2⃣1⃣
#በመጀመሪያ_ራሳችሁን_Like_እና_Follow_አድርጉ!
ዘመኑ የማሕበራዊ ገጽ ዘመን ነው፡፡ ይህ ክስተት ደግሞ Like የመደረግና Follow የመደረግ ልምምድን አስተዋውቆናል፡፡ ይህ Like እና Follow በሚዲያው ጎልቶ ወጣ እንጂ ቀድሞውኑ ውስጣችን ነበር፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ Like እና Follow መደረግ የማይፈልግ ሰው የለም፣ ያንንም መፈለግ ምንም ችግር የለበትም።ግን ቀውስ ውስጥ እንዳይጨምረን ሚዛናዊ ማድረግ ይጠይቃል።
በጥያቄ መልክ ሰላስቀምጠውና . . .
ራሳችሁን Like ካላደረጋችሁ ሌላው ሰው እንዴት Like እንዲያደርጋችሁ ትመኛላችሁ? ራሳችሁን Follow ካላደረጋችሁ ሌላው ሰው Follow አንዲደርጋችሁስ ለምን ትጠብቃላችሁ?
#ራስን_Like_ማድረግ_ማለት ራስን (ሁለንተናን) በማወቅና በመቀበል መደላደል ማለት ነው፡፡ በመጀመሪያ በዚህ መልኩ ራሳችሁን Like ስታደርጉ ያን ጊዜ ብቻ ሌላው ሰው እናንተን Like በማድረጉ ያለውን ትክክለኛ ደስታ ታጣጥማላችሁ፡፡ ያን ጊዜ ብቻ ሰው Like ስላላረጋችሁ ድብርት ውስጥ ከመግባት ትጠበቃላችሁ፡፡
#ራስን_Follow_ማድረግ_ማለት ፈጣሪ የሰጠንን ራእይ በማወቅ የዓላማ ሰው መሆንና በዚያ አቅጣጫ ራሳችን ያወጣነውን እቅድ አምኖ መከተል ማለት ነው፡፡ በመጀመሪያ በዚህ መልኩ ራሳችሁን Follow ስታደርጉ ያን ጊዜ ብቻ ሌላው ሰው እናንተን Follow በማድረጉ ያለውን ትክክለኛ ደስታ ታጣጥማላችሁ፡፡ ያን ጊዜ ብቻ ሰው Follow ስላላረጋችሁ ድብርት ውስጥ ከመግባት ትጠበቃላችሁ፡፡
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣2⃣0⃣
#አንዳንዴ_አረፍ_በሉ!
በፈለጓችሁ ጊዜ ሁሉ ጊዜያችሁን፣ በቸገራቸው ጊዜ ሁሉ ገንዘባችሁን፣ ስሜታቸው ወረድ ባለ ጊዜ ሁሉ ትኩረታችሁን፣ ባጠፏችሁ ጊዜ ሁሉ ይቅርታችሁን፣ ባስቸገሩ ጊዜ ሁሉ ትእግስታችሁን . . . ካለምንም መከልከል የምታፈሱላቸው ሰዎች ያንን ባደረጋችሁ መጠን የማይገነዘቧችሁ ከሆነ፣ ከምንም የማይቆጥሩት ከሆነ፣ ግዴታችሁ እንደሆነ የሚያስቡ ከሆነ፣ ሆን ብለው የሚጎዷችሁ ከሆነና እነዚህ መሰል ግድ-የለሽ ስሜቶች የሚሳዩ ከሆነ ያንን ሁሉ ታግሳችሁ ተጨማሪ አመታቶችን መቆየት ከቻላችሁ ግፉበት፣ #ፈጣሪም_ጸጋውን_ይስጣችሁ፡፡
ምናልባት ግን አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ሰዎች ትምህርትን የሚያገኙት እናንተ ወጥራችሁ የያዛችሁትን ለእነሱና ለእነሱ ብቻ የመኖር የውዴታ ግዴታችሁን ለቀቅ አድርጋችሁ ለራሳችሁ ጤንነት ለመስራት አረፍ ስትሉ እንሆነ ላስታውሳችሁ፡፡ #አንዳንድ_ሰዎች_የሚማሩት_እናንተ_ለእነሱና_ለእነሱ_ብቻ_ከመኖር_ትንሽ_አረፍ_ስትሉ_ብቻ_ነው፡፡
በቃ እንደዛ ነው!
መልካም ቀን
ውብኛ ዋል
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣8⃣
ለመልቀቅ ተዘጋጁ!
በእጃችሁ ያሉትን መልካም የሆኑ የፈጣሪ ስጦታዎች በሙሉ ተመልከቷቸውና ፣ እነዚህ ውብ የሆኑ ስጦታዎች የእናንተ በመሆናቸው #ምን_ያህል_ደስተኞች_እንደሆናችሁ_አስቡት፡፡ እግረ-መንገዳችሁን እነዚህ ውብ ነገሮች ምን ያህል #እንደምትንከባከቧቸውና_በጥንቃቄ_እንደምትይዟቸውም_አስቡ፡፡
ጥሩ ፍቅረኛ፣ መልካም ቤተሰብ፣ ጤንነት፣ ገንዘብ . . . እና የመሳሰሉት በእጃችን የሚገኙ የፈጣሪ በረከቶች በቅጡ ካልተያዙ ፈጠነም ዘገየም ከእጃችን ይወሰዳሉ፡፡ ይህ ጉዳይ ጊዜ ሊሰጠው የማይገባና አሁኑኑ ታስቦበት የማስተካከያ እርምጃ ሊወስድበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
እነዚህንና መሰል መልካም ስጦታዎች በሚገባ ካልያዛችኋቸው መቼ ከእናንተ ሊሄዱ ወይም ሊወሰዱ እንደሚችሉ አታውቁምና ለመልቀቅ ተዘጋጁ፡፡ ለመልቀቅ ዝግጁ እንዳልሆናችሁ ከተሰማችሁ ግን #አያያዛችሁን_የማስተካከል_ጉዞን_ዛሬውኑ_ጀምሩ፡፡
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
El Houb - The Love (2022)
Original title: El Houb
👨🏼🤝👨🏻 #ElHoubTheLove 👨🏼🤝👨🏻
✏️Sub: English
🌏 Country: Netherlands
📝 Language: #Arabic #English #Dutch
🌟 Score: 7.0/10
🎭 Genre: Drama
🎬 1h 42min
✨ Storyline: Moroccan-Dutch Karim returns to his family home and opens up to his parents about being into men. Their reaction inspires a journey of discovery through Karim's isolation as he attempts to break an ingrained culture of silence.
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
👇🏽👇🏽👇🏽
ህግ ፀረ ፍቅር ነው !
#በጣም_ህጋዊ_ከሆንክ_አንድ_ሰው_ማፍቀር_አትችልም። ምክንያቱም የፍቅር ዋናው ብቃት ድንገታዊነት ነውና።
#ፍቅር የሚመጣው በድንገት ነው።
#ፍቅር በድንገትም ሊጠፋ ይችላል።
#ፍቅር ምክንያት፤ምንም መመርያ የለውም #ፍቅር እንደ ታዓምር ነው የሚከሰተው።
#ፍቅር ምትሃታዊ ነው፣ፍቅር ስለምን እንዴት? እንደሚከሰት ማንም አያውቅም።
#ፍቅር ፀረ-ህግ ነው፣#ፍቅር ፀረ-ስበት ነው፣ #ፍቅር ፀረ-ሳይንስ ነው፣ #ፍቅር ከሁሉም ሎጂክ እና ህግ በተቃርኖ ውስጥ ነው።
-------------------
ኦሾ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣5⃣
#የፍቅር_ቋንቋዎች_መለማመድ #ክፍል_ሶስት
3፡- ስጦታን መቀበል
ስጦታ ማለት በእጆችህ በመያዝ “ይህ ሰው እኮ እኔን ስለሚያስበኝ ይህንን ስጦታ ሰጠኝ” የምንለው ነገር ነው፡፡ ለአንድ ሰው እኮ ስጦታን ለመስጠት ስለዚያ ሰው ማሰብ አለብህ፡፡ ስጦታው ትልቅም ሆነ ትንሽ ሰውየው እንዳሰበን አመልካች ነው፡፡
ዛሬ ለፍቅር አጋራችህ አንድን የፍቅር ስጦታ በመስጠት እሱ ለእናንተ ምን ያህል ልዩ እንደሆነ ለማሳየት ሞክር፡፡ በተጨማሪም ልደታቸውን፣ በዓላትንና የጋብቻ ቀናችሁን በማስታወስ ስጦታን በመስጠት ፍቅራችሁን ለመግለጽ ሞክሩ፡፡
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣4⃣
#የፍቅር_ቋንቋዎች_መለማመድ #ክፍል_ሁለት
#ጥራት_ያለው_ጊዜን_ማሳለፍ
ጥራት ያለው ጊዜን ማሳለፍ (Quality Time)፡፡ ጥራት ያለው ጊዜ ማለት ለአጋራችን ያልተከፋፈለ ትኩረትንህን መስጠት ማለት ነው፡፡ ዛሬ በቀን ውስጥ ከፍቅረኛችሁ ጋር ምን ያህል ጊዜን እንደምታሳልፉና የእነዚህ ጊዜያችሁ ጥራት ምን ያህል እንደሆነ በማሰብ ጀምሩ፡፡
ቀናቸውንና ውሏቸውን እንዲናገሩ በመፍቀድ ሙሉ ትኩረት መስጠትን፣ ስልክንና ሌሎች ሚዲያዎች በመዝጋት ከእነሱ ጋር ብቻ መሆንንና የመሳሰሉትን ልምምዶች ተግባራዊ ለማድረግ ሞክሩ፡፡
ፍቅራችሁ የበረከት ይሁንላችሁ!
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
እንኳን በጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ
2016ኛ አመት የልደት በአል በሰላም በጤና አደረሳችሁ
ወንድሞች
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣2⃣
#ጥሩውን_ተስፋ_አድርጉ፣ #ለተሻለው_ግን_ስሩ!
ተስፋ ሁል ጊዜ ተስፋ ነው፡፡ ሊመጣ የሚችል፣ ነገር ግን ከቁጥጥራችን ውጪ የሆነ ነገር ነው፡፡ የግል ጥረትና ስራ ግን እንደ ግንባታ ነው፣ በገነባነው ቁጥር እያደገና እርግጠኛ እየሆነ ይሄዳል፡፡
• የኑሮው ሸከምና ትግል ትንሽ ቀለል እንዲል ተስፋ ማድረግ ጥሩ ነው፣ ግን እስከሚቀል ድረስ ከባድ ሸክም መሸከም የሚችል አቅም እየገነባችሁ ብትቆዩ መልካም ነበር፡፡
• የሰዎች አስቸጋሪ ባህሪይ እንዲስተካከል ተስፋ ማድረግ ጥሩ ነው፣ እስከዚያው ግን እናንተ በሰው አያያዝ ጥበብ እየበሰላችሁ ብትቆዩ መልካም ነው፡፡
በየፊናችሁ ሆናችሁ የቀሩትን የተስፋና የስራ ገጽታዎች ከግል ምልከታችሁ አንጻር ሙሏቸውና ተስፋ እያደረጋችሁ ወደ ስራ!
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#እንደምትሄድ_ባውቅ
በእግሬ አንተን ጋ ለመምጣት ከቃሊቲ አራብሳ እሄድ ነበር ?
አናደድከኝ ብዬ ብዙ አረቄ በባዶ ሆዶ አጠጣ ነበር ?
ደክሞኝ ዝዬ አልጋ ላይ እንደበድን ተንጋልዬ <<አንገናኝ ወይ?>> ስትለኝ ተወርውሬ ያለህበት እመጣ ነበር ?
እንደምቴድ ባቅ ....!
ድብን ፤ቅንት ፤ እርር ብዬ ስሜቴን አፍን ነበር ?
ሁሉን ትቼ ካንተ በቀር ብዬ አለምን ችላ እል ነበር ?
እንደምቴድ ባቅ ...!
ሳልሳሳ በደንብ እስምህ እተኛህ አልነበር?
በራስህ ጥፋት የተጣላኸውን ተደርቤ ጠላት አደረገው ነበር ?
ደብሮኝ ተደሰተ ብዬ እቦርቅ ነበር ?
እንደምቴድ ባቅ ...
ብቻዬን ሆኜ ሳልም እቅዴ ውስጥ አኖርህ ነበር?
ገመናህን ገመናዬን እንደዛ አርቀን እንገላለጥ ነበር?
እንኳን እንደምቴድ አላወኩ ይሄን ሁሉ ትዝታ ከየት አመጣ ነበር ?!😏😏😏😢
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣0⃣9⃣
#ልታጧቸው_የማይገባችሁ_ሰዎች!
ጤና በሆንንባቸው አመታት ትዝም የማይለን የጤንነት አስፈላጊነት ልክ ጤናውን ስናጣው ነው የሚገባን፡፡ አንዳንድ በሕይወታችን ያሉ ሰዎች ልክ እንደ ጤንነት ናቸው፡፡ አጠገባችን ባሉበት ጊዜ የእነሱ መኖር ጥቅም ብዙም ትዝም አይልም፡፡ እንዲያውም ስንኮንናቸው፣ ስንከሳቸው፣ ጥፋታቸውን ስናበዛ፣ መልካም ነገር ባደረጉ ቁጥር ከማመስገን ይልቅ ያላደረጉልንን ስንቆጥርባቸው . . . ራሳችንን እናገኘዋለን፡፡
በዚህ ምድር ላይ ልክ እንደ ጤንነት ፈጽሞ ልታጧቸው ከማትፈልጓቸው ነገሮች መካከል #ለእናንተ_ጥሩ_የሆኑ_ሰዎች ይገኙበታል፡፡ ባህሪያችሁን ተሸክመው፣ ለእናንተ ኖረው፣ በራሳችሁ ጥፋት እርቅ ፈልገው . . . የሚኖሩ ሰዎች ብርቅና የማይገኙ እንቁዎች ናቸው፡፡ እነዚህን ሰዎች ከማጣታችሁ በፊት ብትጠነቀቁላቸው ጥቅሙ ለእናንተው ነው፡፡ አንዴ ካጣችኋቸው እንደገና ስላማታገኟቸው ማለት ነው፡፡
ነገሩን ስንገለብጠው ከላይ የጠቀስነው አይነት ታማኝነት እያሳያችኋው የተገለጸውን አይነት ባህሪይ የሚያሳይዋችሁ ሰዎች ካሉ የእናንተ አለመኖር ምን ያህል ሊያጎድልባቸው እንደሚችል ማሳየቱ አንድ አማራጭ መሆኑን አትርሱ፡፡ ከእነሱ ንዝንዝ ጋር መኖር ከቻላችሁ #ከእነሱ_ንዝንዝ_ውጪ መኖር አያቅታችሁም ፡፡ እስቲ ዘወር በሉላቸውና ይዩት!
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣0⃣8⃣
#ራስን_የመቀበል_ጉዞ_እንጀምር
እኔና እናንተ ስንሰራ ጥሩ ቤተሰብ እንገነባለን፡፡ ጥሩ ቤተሰብ ስንገነባ ደግሞ ጥሩ ሕብረተሰብና ሃገር እንገነባለን፡፡ ስለዚህ መማር፣ መወያየት፣ ሃሳብ መለዋወጥ አናቆምም፡፡
ራሳችሁን በመለወጥ ጎዳና ውስጥ ልትለማመዷቸው ከምትችሏቸው መልካም ልምምዶች መካከል አንዱ ራስን የመቀበል ጉዳይ ነው፡፡
አንድ ሰው በፍጹም ካልተመቻችሁ ለማስተካከል ትሞክራላችሁ፣ ካልቻላችሁና ከአቅማችሁ በላይ ከሆነ ትለዩታላችሁ፡፡ #ራሳችሁን_ግን_እደዚያ_ማድረግ_አትችሉም፡፡ ሁል ጊዜ ከእናንተው (ከራሳችሁ) ጋር ስለሆናችሁ ራሳችሁን በደንብ አድርጋችሁ መቀበል አለባችሁ፡፡
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
🫵🏾#ስሜትህን_ቀይር!
እንበልና የሆነ ሰው አበሳጨህ፣ ዝቅ አድርጎሃል! ጉዳት ተሰምቶሃል እና? በመጀመሪያ ስሜቱን አትካደው ነገር ግን ለምን እንደዛ ሊሰማህ እንደቻለ ራስህን ጠይቅ... ምናልባት ያ ሰው እንደዛ እንዲሰማህ አልፈለገም... ምናልባት ያ የራስህ የአረዳድ ችግር ይሆናል... ምናልባት ያለብህ የበታችነት ስሜት... ምናልባትም ለዛ ሰው ያለህ ድብቅ ጥላቻ... ወይም በትክክል ያበሳጨህ ሰው ሆን ብሎም ሊሆን ይችላል።
የፈለገ ይሁን የሚረብሽ ስሜት ለምን ውስጥህ ቀረ? ይሄን ጥያቄ ምትመልሰው አንተ ሁነህ ሳለ እኔም የምጠቁምህ ነገር ይኖራል።
እዚህ ጋር- ህይወት ሁሌም ደስታ፣ መፈለግ፣ ማግኘት፣ እኩል መሆን፣ ስኬት እንዳልሆነች ተገንዘብ። ብስጭት ወይም የስሜት መረበሽ ሲያጋጥምህ ዝም ያለ ቦታ ሂድ፤ ከራስህ ጋር በፍቅር ተነጋገር። የመጥፎ ገጠመኞችን ጥሩ ጎን ለማየት ራስህን በአዎንታዊነት እንዲመራ አስገድድ...
👇🏽👇🏽
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣2⃣3⃣
#ቋንቋችን #ጊዜ #ይባላል!
አንድን ሰው ከልባችሁ የምታከብሩት ከሆነ ቀላሉ መመዘኛ የዚያን ሰው ሰዓት ወይም ጊዜ የማክበራችሁና ያለማክበራችሁ ጉዳይ ነው፡፡ በተጨማሪም፣ ጊዜያችሁን ሰውታችሁ ለዚያ ሰው ስትሰጡት ያንን ሰው እንደምታከብሩት መልእክትን እያስተላለፋችሁ ነው፡፡ ገንዘብ፣ ቁሳቁስና የመሳሰሉት ነገሮቻችሁን ለማንም ሰው ልትሰጡ ትችላላችሁ፣ ጊዜያችሁን (በተለይም የተጣበበውን) ግን ለሚከበርና ለመወደድ ሰው ነው የምትሰጡት፡፡
ማሰተካከያ ልናደርግበት የሚገባን ቀውሰ ያለው እንግዲህ እዚህ ላይ ነው፡፡ የአብዛኛዎቻችን የግንኙነት ቀውሶች፣ በስራ ስኬታማ ያለመሆንና የመሳሰሉት ቀውሶች መነሻቸው ለምንወደውና ለእኛ ወሳኝ ለሆነ ሰውም ሆነ ስራ ተገቢውን ጊዜ አለመመደብና አለመስጠት ነው፡፡ ይህ ቀውስ ብዙ ጠቃሚ የሆኑ ሰዎችንና ስራዎችን ከእጃችን እንዲወሰዱ ያደርገናል፡፡
ይህንን አትርሱ....
❇️ማንኛውም ሰው ሆነ ስራ እኛ ተገቢውን ጊዜና ትኩረት ካልሰጠነው ተገቢውን ጊዜና ትኩረት የሚሰጡት ሰዎች “ላፍ” አድርገው ይወስዱታል፡፡
❇️ ጊዜያችሁን ለምትወዱት፣ ለምታከብሩትና ቅድሚያ ለምትሰጡት ሰው ስትሰጡ ተገቢውን ምላሽ ታገኛላችሁ፡፡ ተገቢውን ምላሽ ካላገኛችሁ ደግሞ ግንኙነታችሁን እንደገና ማጤንና ማስተካከያ ማድረግ የግድ ነው፡፡
❇️ ዋጋ ለምትሰጡት ስራም ቢሆን ጊዜ ስትሰጡት ስራው ውጤትን በመስጠት ይመልስላችኋል፡፡ ስራው ጊዜያችሁን እየወሰደ ውጤት የማይሰጣችሁም ከሆነ ደግሞ ስራው እንደገና ሊቃኝ ይገባዋል፡፡
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስቴወሻ # 2⃣2⃣1⃣
#በምርጫ_ጎዳና_ውስጥ_ያለው_ደስታ
ልክ መተንፈስ የሕይወት አካል እንደሆነና ሲቆም ሕይትም እንደሚቆም፣ ምርጫም ልክ እንደዚያው ነው።መምረጥ ያቆመ ሰው መኖርን ያቆመ ሰው ነው።
ይህ እሳቤ ምርጫ የግድ የሕይወት አካል እንደሆነ እንደናስብ ያደርገናል፡፡ ሆኖም ይህ ሃሳብ ለአንዳንድ ሰዎች ጭንቅ ነው፡፡ ምርጫን ከውጥረት፣ ከመጨናነቅ፣ ከመሳሳት፣ ከጸጸትና ከመሰል አሉታዊ ስሜቶች ጋር ስለሚያዛምዱት ማለት ነው።ይህንን ስሜት ለማሸነፍና የምርጫን ሕይወት ለመለማመድ ምርጫን ከደስታ ጋር ማዛመድ አስፈላጊ ነው።
• ምርጫ እንዳለን የማወቅ ደስታ፡- በብዙ የሕይወት አቅጣጫዎቻችን ምርጫ እንዳለን በማወቅ ውስጥ ታላቅ ደስታ አለ። ዛሬ ነግቶ ስትሰማሩ አብዛኛውን ነገር በምርጫችሁ የማድረግ እድል ስላላችሁ ደስ ይበላችሁ፡፡
• ከምርጫ ሂደት የሚመጣ ደስታ፡- በብዙ አማራጮች መካከል የትኛው ለእኛ የተሻለ እንደሆነ ለመለየት የሚደረግ ስሌት የሕይወት አንዱ ደስታ ምንጭ ነው፡፡ ማሰብ፣ ማቀድ፣ ማሰላሰል፣ ማወዳደርና ትክክለኛው ነገር ላይ ለመድረስ መሞከር ሂደት ለሕይወት የደስታ ጣእም ይሰጣል።
• የትክክለኛ ምርቻ ደስታ፡- ምርጫ እናዳለን በማወቅና ትክክለኛውን ሂደት በመከተል ስንመርጥና ምርቻችን ትክክለኛ እንደሆነ ስናወቅ የሚኖረን ደስታ ይህ ነው አይባለምለ።
• ከትምህርት የሚመጣ ደስታ፡- አንዳንዴ ተጠንቅቀን እንኳን ምርጫችን ሊሳሳት ይችላል። ይህ ሲሆን ከዚያ ስህተት በመማር ለነገው ምርጫ ጥበብን በማዳበር ውስጥ ሚገኘው ተግባራዊ ደስታ ደስታ ቀላል ኤደለም።
በምርጫ ጥበብ መብሰላችሁን ቀጥሉ እንጂ ምርጫን አትፍሩት! በምርጫ ውስጥ ያለውን የማያልቅ ደስታ ተለማመዱት!.
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
"ቀላል ይሆናል"🤍
🤍የጠመመው ይቃናልናል፣ የተበላሸው ይስተካከላል ፣ ጥላቻችን ጊዜ ያሸንፈዋል ፣ የበደለንን ይቅርታ እናደርጋለን ፣ ያቄመብን ይረዳናል፣ የጀመርነውን እንጨርሳለን ፣ያቀድነውን እንተገብራለን ፣ ህልማችን እውን ይሆናል ።
❤️የካደንም ፣የካድነውም ትዝታ ብቻ ይሆናል ።
"ሁሉም ጥሩ ይሆናል"
#ስራ_እናገኛለን፣ #ጤናችን_ይስተካከላል ፣ #ከአምላካችን_ጋር_እንታረቃለን ፣ #እራሳችንን_ይቅርታ_እንላለን ።
ግምባር-ቀደምም እንሆናለን
#እንለመልማለን፣ #የእውነት_እንስቃለን ፣ #የእውነት_እንወዳለን ፣ #ወላጆቻችንን_እንጦራለን
#እንመረቃለንም...
ሁሉም መልካም ይሆናል!!
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣9⃣
ትንሽ ታገሱ!
ለጥንዶች . . .
የፍቅር ወራት የመተዋወቂያና የመግባቢያ ወቅት መሆኑን አትዘንጉ፡፡ በእነዚህ ወራት ውስጥ ልክ እናንተ የፍቅረኛችሁ ሁኔታ፣ ባህሪይ ልማድና የሕይወት ዘይቤ ግነኙነቶቀቀ እንደሚላችሁ ሁሉ፣ ፍቅረኛችሁም ገና እናንተን ለማወቅ እየታገለ መሆኑ/ አትርሱ፡፡ ስለዚህ ትንሽ ታገሱ!
በፍቅረኛችሁ ሁኔታ ላይ የማትወዱትን ነገር እየለቀማችሁ ከማዋከባችሁ፣ ከማኩረፋችሁ፣ ከመበሳጨታችሁ፣ ስሜታዊ ከመሆናችሁና “በቃ እንለያይ” አይነት ሃሳብ ከመሰንዘራችሁ በፊት በቅድሚያ ለፍቅርና ለመተዋወቅ ጊዜ ስጡት፡፡
በተቻላችሁ መጠን አብራችሁ ብዙ ጊዜ አሳልፉ፣ ብዙ ተነጋገሩ፣ ብዙ ጥያቄን በመጠያየቅ አንዱ ስለሌላው ለማወቅ ሞክሩ፣ ተናበቡ፣ የምትግባቡበትንም ሆነ የማትግባቡበትን ሃሳብና አቋም አንሸራሽሩ፣ አንዱ በሌላው ላይ የማይወደውን ነገር በግልጽ ተወያዩ . . . ፡፡
ለፍቅር ትንሽ ጊዜ ስጡት!
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
El Houb - The Love (2022)
Original title: El Houb
👨🏼🤝👨🏻 #ElHoubTheLove 👨🏼🤝👨🏻
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣7⃣
#ፍቅርን_አታደራርቡ!
ከአንድ ሰው ጋር የፍቅር ግንኙነት ከጀመራችሁ በኋላ ቀዳሚው ስራችሁ የግንኙነቱን አይነት ትርጉም በመስጠት መግባባት ነው፡፡ ይህም ማለት ያላችሁ ግንኙነት የቀላል ጓደኝነት ይሁን አልያም የፍቅር ግንኙነት ይሁን፣ ሁለታችሁም ግልጽ በሆነ መልኩ በመነጋገር ከነትርጓሜያቸው መግባባት አለባችሁ፡፡
ግንኙነታችሁ የቀላል ጓደኝነት (Friendship) ደረጃ ላይ ካለ፣ ከመገናኘት፣ ከመጠናናትና ከመግባት ያለፈ ደረጃ ስለሌለው አንዱ የሌላኛውን ማንንም ሰው የማግኘት ነጻነት ሊጠብቅ ይገባዋል፡፡
አንድ ጊዜ እናንተ የእነሱ፣ እነሱ ደግሞ የእናንተ እንደሆናችሁ ከተግባባችሁና የፍቅረኛነትን (Lovers) ጎዳና ከጀመራችሁ በኋላ፣ #በዚያ_ፍቅረኛ ላይ ሌላ ፍቅረኛ ደርቦ የመያዝ ልማድ ካላችሁ እጅግ የከሰረን የወደፊት ሕይወት እንደጀመራችሁ አትዘንጉ፡፡
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣6⃣
ለትንሹም ለትልቁም ጥፋት ካለምንም መታለፍ ቤተሰብ ወይም አሳዳጊ #ቅጣትና_ስድብ_ሲያቀምሱት_ያደገ_ሰው ይዞ የሚያድገው የስነ-ልቦና ቀውስ ይህ ነው አይባልም፡፡ ይህ ቀውስ የማንነታችንን ዋጋ ካለፈው ታሪካችን አንጻር እንድንተምነው ያደርገናል፡፡
ይህ ሲሆን፣ ሰው ለሰራው ስህተት ሁሉ አንድም ሳይታለፍ ልኩን ሊገባና ሊቀጣ ይገባዋል የሚል ዝንባሌ እናዳብራለን፡፡
በሁሉ ነገር ተቀጥቶ ያደገ ሰው ዘወትር ስህተትን ከቅጣት ጋር አያይዞ ነው የሚመለከተው፡፡ ይህ፣ “ሰው ለሰራው ስህተት ሁሉ ልኩን መቅመስ አለበት” የሚል የቅጣት ዝንባሌ ነው፡፡
ይህ ዝንባሌ ያለው ሰው ለተከሰተ ማንኛውም አይነት ስህተት የሚያውቀው ምላሽ ቅጣት ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም፣ አንድ ስህተት ሲገኝ አንድ ሰው የግድ መቀጣት አለበት፡፡ ይህ አመለካከት ደግሞ ስህተት ሲገኝ ራስን በመውቀስ ወይም የሚወቀስ ሰው ፈልጎ በመውቀስና በመቅጣት ሊገለጥ ይችላል፡፡
በየእለቱ የአንድን ሰው ስህተት ለአፍታ አንኳን ሳናልፍ የሚወገር ሰው ፍለጋ የምንተጋው ለዚህ ይሆን?
እስቲ በሰዎች ላይ ያለንን ጭካኔ ትንሽ መለስ እናድረገው!
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
✅ ЯНГИ ҚУРИЛАЁТГАН УЙЛАРДАН УЙ ҚИДИРЯПСИЗМИ?
⚡️ 2024-йилда қурилаётган уйлар ва уларнинг нархлари
⚡️12 ойдан 120 ойгача муддатли тўлов
⚡️Буларнинг барчаси @YangiBinolar телеграм каналимизда
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣3⃣
#የፍቅር_ቋንቋዎች_መለማመድ #ክፍል_አንድ
የፍቅር ቋንቋ 1፡- #የሚገነቡና_የሚያጸኑ_ቃላት
ውጤታማ የፍቅር ተግባቦትን ለማዳበር ከፈለግን የፍቅር አጋራችንን ቀደምተኛ የፍቅር ቋንቋ ለመማር ፈቃደኞች መሆን አለብን . . . የተለያዩ ቋንቋ ከሚናገሩ ሰዎች ጋር ለመግባባት #የእነሱን_ቋንቋ_መናገር የግድ እንደሆነ ሁሉ ፥ ከፍቅረኛችንም ጋር ለመግባባት #የእነሱን_የፍቅር_ቋንቋ መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡
ሌላውና ዋንኛው ደግሞ ፍቅርን በስሜት መግለጫው መንገድ የሚገነቡንና የሚያበረታቱን ቃላት በመለዋወጥ ነው፡፡
ዛሬ ለፍቅረኛችሁ ምንም አይነት አሉታዊ፣ የወቀሳ፣ የክስና ድካምን የሚያጎላ ቃላት ላለመናገር ሞክሩ፡፡ በዚያ ምትክ የሰሩትን መልካም ነገር ማድነቅ፣ ያቃታቸውን ነገር ማበረታተት፣ ውበታቸውን ማድነቅ፣ እነሱ በመኖራቸው ምክንያት ስላገኛችሁት መልካም በረከት እና የመሳሰሉትን ቃላት ንገሯቸው፡፡
ግንኙነታችሁ የሰላምና የደስታ ይሁንላችሁ!
አልጨረስንም
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
እምወደውን በዙርያዬ አጥቼ ስለማላቅ፣ የሚወዱኝ ሰዎች እንዳሉኝ ሲለሚታወቀኝ ፣ ደስታ ከልቤ ፣ ደስታ ከኑሮዬ፣ ደስታ በምወዳቸው ሰዎች ጭርሶ ስለማይጠፋ...
የተደረገልኝ ፣የተዋለልኝ ሳይነገረኝ ስለሚገባኝ ።
መርህ ስላለኝ ፣ ሳጠፋ ስለሚሰማኝ ። የወዳጆቼ ስኬት ደስ ስለሚያሰኘኝ ።
ተመስገን ብዬ ስለተደረገልኝ ነገር ደስ ስለምሰኝ ።
ስለሆነልኝ ሁሉ አመስጋኝ ነኝ 🙏❤
መልካም በዓል❤
እንኳን አደረሳችሁ ወንድሞች
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣1⃣1⃣
#የትውስታዎቻችን_ተጽእኖ
በአንድ ጥናት መሰረት ሰዎች ከዚህ ቀደም ያሳለፏቸውን ደስ የማያሰኙ ልምምዶች ለ5 ደቂቃዎች መለስ ብለውና ጠልቀው እንዲያስቡት ሲደረጉ የሰውነታቸው በሽታን የመከላከያ አቅም #55 በመቶ ይወርዳል፣ ከዚያም ለ6 ሰዓታት በዚያ ሁኔታ ይቆያል፡፡
ከዚያ በተቃራ ደግሞ ደስ የሚያሰኙ ልምምዶቻቸውን ለ5 ደቂቃዎች ጠልቀው እንዲያስቡት ሲደረጉ የሰውነታቸው በሽታን የመከላከያ አቅም #40 በመቶ ከፍ ይላል፡፡
የእንደዚህ አይነት ጥናቶች ውጤቶች እንደየአጥኚዎቹ የመለዋወጡ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ሃሳቦቻችን በጤንነታችን ላይ ባላቸውን ተጽእኖ ላይ ግን ብዙል ልንለያይ አንችልም፡፡ ይህ ጥናት ደስ የማያሰኘንን ያለፉ ልምምዶቻችንንና ታሪኮቻችንንች ቁጭ ብለን ከማሰላሰል ይልቅ ደስ በሚያሰኙት ላይ የማተኮር ልምምድ የላቀ እንደሆነ የሚያስታውሰን ጥናት ነው፡፡
ደስ የማያሰኙ ልምምዶቻችንን ፈጽሞ እንዳልተፈጠሩ ማድረግ ባንችልም፣ ለሁኔታው በቂ ትኩረትና ጊዜ ከሰጠንና ተገቢውን ትምህርት ካገኘን በኋላ መልካም መልካሙን እያሰላሰሉ ወደፊት!
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣0⃣
#ሚዛን_ያልጠበቀ_የአንድዮሽ_ግንኙነት_ምልክቶች
ትክክለኛ የፍቅር ግንኙነት #ሁለትዮሽ ነው፡፡ ይህም ማለት የሁለትን ሰዎች የጋራ ፍቅር፣ መሰጠትና ጥረት የሚጠይቅ ነው፡፡ ሆኖም አንዳንድ ጊዜ በሁሉ ነገር የሚጦዘው አንደኛው ወገን ብቻ ሲሆን የሆነ የተዛባ ነገር እንዳለ ጠቋሚ ነው፡፡
1. በስልክ፣ በአካልም ሆነ በቻት እናንተ ካላናገራችኋቸው እነሱ ንግግርን የማያነሳሱ ሰዎች . . .
2. አብሮ የማሳለፍን ጥያቄ እናንተ ካልጠየቃችሁና ካላነሳሳችሁ እነሱ በፍጹም ፍላጎት የማያሳዩና የማያነሳሳ ሰዎች . . .
3. አለመግባባት ሲፈጠር እናንተ ብቻ ይቅርታ ካልጠየቃችሁ ጥፋታቸው ሆኖ እንኳን በፍጹም ይቅርታ የማይጠይቁ ሰዎች . . .
4. ለሁሉም ሁኔታ መስዋእትነት ከፋዮች እናንተ እንድትሆኑ የሚጠብቁ ሰዎች . . .
5. ለግንኙነቱ ጤናማነት ሲባል መስዋእትነትን እናንተ ብቻ እየከፈላችሁ እነሱ ግን የማይከፍሉ ሰዎች . . .
6. እጅግ በጣም አስቸጋሪ የሆነውን ባህሪያቸውን ዝም ብላችሁ እንድትሸከሙ የሚፈልጉ ሰዎች . . .
7. ሆን ብለው በማንኛውም ጊዜ ትተዋችሁ ሊሄዱ እንደሚችሉ አይነት ስሜትን የሚሰጧችሁና ሰዎች . . .
8. የእናንተ ፍላጎትና ዓላማ ሙሉ በሙሉ በእነሱ ፍላጎትና ዓላማ ስር እንዲጠቃለል የሚፈልጉ ሰዎች . . .
9. ሁሉንም ነገር (ስራ፣ ጓደኛ፣ መዝናናት …) ከእናንተ የሚያስቀድሙ ሰዎች . . .
10. እናንተ እቅዳችሁን ከእነሱ አንጻር ስታወጡ እነሱ ግን ከራሳቸው አንጻር ብቻ የሚያወጡ ሰዎች፡፡
#ሚዛኑ_ይጠበቅ!
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
ትዝ ይልሃል?… "መርሳት ባንችል ኖሮ ሁላችንም እናብድ ነበር"የሚለውን አባባል ሰምተን የሳቅን ቀን?
…አንተ እንዲያውም በጣም ነበር የሳቅከው።ከልክ በላይ መሳቅህ አስገርሞኝ ያሳቀን ነገር አንድ አይደለም ይሆናል ብዬ እንድታብራራልኝ ጠየቅኩህ። «መርሳት ምን ይገርማል ብዬ ነዋ… እስኪያሳብደኝ ድረስ መርሳት ሲያቅተኝ አስበኸዋል?»ብለኸኝ አሁንም ሳቅክ።
ጨዋታችንን ወደ ቁም ነገር ወሰድኩት።ኮስተር አልኩ።«እኔንም ቶሎ ትረሳኛለህ?…»አልኩህ።«ያው ከተለያየን ህይወት መቀጠሉ ይቀራል…?»አልከኝ… እንዳልናደድ ፈራ ተባ እያልክ።
እኩል እንደማንዋደድ የገባኝ በዛች ቅፅበት ነበር። ያን ጊዜ ደነገጥኩኝ።ድንጋጤ እና ፍርሃት አንድ ላይ ሰፈሩብኝ።አንተን የማጣት ይሁን ወይ አንተን መርሳት ያለመቻል፤ የትኛው እንደሆነ በቅጡ ያልተረዳሁት ፍርሃት ወረረኝ።
ሁለታችንም በተለያየ perspective እንደሳቅን ሲገባኝ በጣም አዝኛለሁ።አንተ«እንኳንና አንተን ስንቱን ረስቼዋለሁ» በሚል።እኔ ደግሞ«አንተን ከምረሳ ማበድ አይቀለኝም?»በሚል ነበር የሳቅነው።
ተለያየን።
ከተለያየን ደግሞ ብዙዙዙ ጊዜ ሆነን።አንተ ህይወቴ ውስጥ ከመምጣትህ በፊት እንዴት እኖር እንደነበር ጠፋብኝ።ወደዛ ለመመለስ ሞክሬያለሁ።ግን ረሳሁት። ብሞክርም ላስታውሰው አልቻልኩኝም።
አንተ ደግሞ እኔን ረስተከኛል።እኔ ግን ልረሳህ በመታገሉ ውስጥ ራሴን እያበድኩኝ አገኘሁት። ከመርሳቱ እና ከማበዱ የቱ እንደሚቀድምልኝ አላውቅም።ቶሎ በረሳሁህ።አንተን ስለመርሳት እያሰብኩኝ ባላስታወስኩህ።አንተን ስለመርሳት ራሱ በረሳሁ።
ብቻ…ከዚህ ሁሉ ስቃዬ ግን አንዱ ቶሎ እንዲገላግለኝ በፅኑ አፈልጋለሁ።የቱ ነፃ እንደሚያወጣኝ የቱ እንደሚያድነኝ ግን አላውቅም።
ወይ መርሳቴ ወይ ደግሞ ማበዴ..
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈
በውጪ ላላችሁ እንዲሁም ለምታከብሩ
HAPPY NEW YEAR
2024
🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈🌈
@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0