habeshagay1 | Для взрослых

Telegram-канал habeshagay1 - ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

791

Подписаться на канал

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#መች_ነው_ግን_ማገኘህ?

ቀልድህ ባያስቅም እንኳ አይንህን እያየው ፈገግ ስልልህ..በዝምታህ ውሰጥ እንደ እሳተ ጎመራ ቡልቅ ቡልቅ የሚለው ህመምህን ለማድመጥ ስጣጣር.. ኩራቴ ስሜቴን ስላሸነፈ አልነገርኩክም እንጂ ይሔ ሁሉ ናፍቆኛል...።

እኔን ለማሳቅ የባጥ የቆጡን ስትዘባርቅ..እኔ ደሞ እንደ ጉንዳን የደቀቀ መልሴን ስመልስልህ...ለቦጭህን ዘርግፈ ሌላ ቀልድ ስቀልድልኝ እንደ አዲስ ሌላ አለም ሌላ አፅናፍ እንደምትዘፍቀኝ አልነገርኩክም እንጂ የእውነት ናፍቆኛል ..ኩርፊያህ ሀዘንህ ሳቅህ ሁሉ ነገርህ ናቆኛል..።.

..አዎ ፍቅራችን የጋለ ምጣድ ላይ እንዳረፈ በረዶ ቀስ ቀስ ሲናድ ይታወቀኛል...አንተም ላትመልስ ከአይኔ ራዳር ሸሸህ..

እኔም መመለስህን በተስፋ ምጠብቅ ብኩን ፍጥረት እንድሆን ማን ነው የፈረደብን?።
ለዚ ተከሳሹ ማን ነው??
እኔ ወይስ አንተ....?


@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #1⃣9⃣7⃣

#እውነተኞቹን_ከአስመሳዮቹ_መለየት_ከፈለጋችሁ

ምናልባት በዙሪያችሁ ከሚገኙ ሰዎች መካከል እውነተኞቹንና አስመሳዮቹን ለመለየት ከፈለጋችሁ እናንተ ሁለት ነገር ማድረግ ይጠበቅባችኋል፡፡

❤  እውነተኛ ማንነታችሁን መኖር

አስመሳይ ማንነት አስመሳይ ሰዎችን ይስባል፤ እውተኛ ማንነት እውነተኛ ሰዎችን ይስባል፡፡ ይህ የማይለወጥ ማሕበራዊ ሕግ ነው፡፡ እውነተኛ ሆናችሁ ስትኖሩ፣ እውነትን ስትናገሩ፣ እውነታን ስትጋፈጡ . . . እውነተኞችና እውነት ወዳዶች ብቻ ወደ እናንት ይሳባሉ፣ ሌሎቹ ግን ስማይመቻቸው ይርቃሉ፡፡

❤❤  ትክክለኛ የሕይወት ዓላማችሁን መከተል

ያያችሁትን፣ የሰማችሁትንና ለጊዜው “ያበላል” ብላችሁ የምታስቡትን ነገሮች የምትከታተሉ አይነት ሰዎች ከሆናችሁ፣ ይህ የተዛባ ሂደት የተዛባ መርህና አመለካከት ያላቸውን አይነት ሰዎች ወደ እናንተ ይስባል፡፡

ሲጨመቅ፣ በዙሪያችን የሚመጡትንና የሚቆዩትን ሰዎች የሚወስኑ ሁለት ዋና ዋና ነገሮች ማንነታችን እና ዓላማችን ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት ነገሮች መስመር ሲይዙ “የወዳጆቻችን” ነገርም ከዚያው ጋር ይስተካከላል፡፡
የሕይወት ዘይቤያችሁ ወደ እናንተ የሚመጡትንና የሚቆዩትን ሰዎች የመወሰን ጉልበት አለው፡፡

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

ጨበጥ....ጨመቅቅቅቅ..😘😘

🌟⭐️🌟⭐️🌟⭐️🌟

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

Rustin ሙሉ ፊልም
ከፍ ባለ ጥራትና MB

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

የዛሬው የቅዳሜ ታላቅ ፊልም "RUSTIN " የሚለዉን  ቆንጆ ፊልም ነዉ። 🥰🥰🥰

🌟⭐️🌟⭐️🌟

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
👇👇

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

ግትር ነው! ስንጣላ መታረቂያ ሽንቁር አያበጅም። ግትርነቱን የመርህ ሰው መሆኑን ማሳያ ይመስለዋል።ስለማመጠው የበለጠ ይደርቃል።ሰው እንዴት ከሚወደው ጋ በረባው ባረባው ይኮራረፋል ብዬ ስለማስብ ነው።እንዴት ሰው ልዩነቱን ተወያይቶ አይፈታም ብዬ ስለማስብ ነው።

በተጣላን ቁጥር ጥግ ለመያዝ ይንደረደራል።ኮስተር ካልኩኝ ፤ቅሬታዬን ፊቴ ላይ ካየ እንደመስታወት ያየውን ያንፀባርቃል እንጂ "ምን ሆነክ ነው?" ብሎ ችግሩን ለመፍታት አይሞክርም። ከልጅነቱ ይዞት የመጣ ያልበሰለ የአዕምሮ ክፍል አለው።እንዴት ሰው ለሚወደው ቢያንስ አይሸነፍም?

ተኝተን ሳለ እንኳን ተጣልተን ሳቅፈው እንደ እንጨት ይደርቃል ፤ማቀፌን ልምምጥ ብቻ ያደርገዋል፤ ስለማመጠው የጥፋተኝነት ስሜት ተሰምቶኝ ስለሚመስለው ይለጠጣል።

ልምምጤ እግሩ ላይ በመውደቅ እንዲጠናቀቅ ይጠብቃል ።ስለማመጠው እንደመለስለስ ጭራሽ  የድል አድራጊነት ስሜት ውስጡ ይርመሰመሳል።😡

ተጣልተን እንኳን በሰላሙ ግዜ እንደምጠራው ነው የምጠራው።ለእሱ ያለኝ ፍቅር ይሉኝታ ቢስ እንዳያደርገኝ ይከልለኛል።ተጣልተን መልዕክት በስልኩ ስልክለት መልእክቴ  ድ'ርቅ እንዳይል እጠነቀቃለሁ ።ፍቅራችን ለምናፈቅራቸው እንድንጠነቀቅ ካላደረገን ፍቅራችን የእውነት ላለመሆኑ ምስክር ነው።

ለትንሹም ለትልቁም ፀብ እንዴት ሰው ወደ ጥጉ ይንደረደራል።አኩራፊ እኮ የተሸናፊዎች ባህሪ ነው። በክብሬ አልደራደርም ይላል ። ስንት ቀን ፍትወት ሳይሰማኝ ስሜቱን ከስሜቴ እንዳስበለጥኩለት አይገባውም ።

አንዳንድ ቀን አጥፍቼ እንኳን ጉያው ውስጥ ከቶ ግንባሬን እየሳመ እንዲለማመጠኝ እፈልጋለሁ። በብስለቱ ተንጠልጥሎ ዱካኬን ከግንኙነታችን ጋ ባያስታከው ደስታዬ ነው።

ምን አለ የምንወደው ሰው የሚጎድለውን ነገር ፤ ከሚወዱን ሰዎች መልካም ነገር ላይ ወስደን መጫን ቢቻለን እላለሁ...

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

ብዙዎቻችን የማርቲን ሉተርኪንግን "I have a dream"የሚለውን ደማቅ ንግግርን እናስታውሳለን። ትልቅ ጭቆና በደልን ለመቃወም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተሰበሰቡበት የታናገረው ታሪካዊ ንግግር ነው። እስከዛሬ ድረስም የንግግሩ ተፅእኖ ጎልቶ ይታያል።


ከሰልፉም ሆነ ከታሪካዊ ንግግሩ ጀርባ ግን ስላለው ታላቅ ሠው ብዙም አልሰማንም....🤔🤔

Bayard Rustin ይባላል። የማሕበረሰብ አንቂና ተሟጋች የነበረ ታላቅ ሠው ነው። በቀለም "በማንነት" በስብእናቸው ምክንያት በደል ለሚደርስባቸው ሠዎች ዘብ የሚቆም ሠው ነበረ Rustin ።

በ 1940ዎቹ ዜጋ መሆን በደል በነበረበት ጊዜ የ LGBTQ+ Community አባል የነበረው ይሕ ሠው ፤ ያለበትን ጫና ተቋቁሞ የላቀ ትግልን አሳይቷል። ነገ የምንጋብዛችሁም ፊልም በርሱ ሕይወት ላይ የተሰራን ቆንጆ ፊልም ነው።
ተጋበዙልን።

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

ፉንግግ ያለ ፉንጋ ነበር። የጥርሶቹ ትልቀት፣ የአፍንጫው  አቀማመጥ፣ የፀጉሩ ግንባሩ ድረስ አመጣጥ፣ አጉጩን ሳይቀር አለማስተዋል አይቻልም  ... ተፈጥሮ እንዴት እንደጨከነችበት ሳየው ይገርመኛል ተቀራረብን... ከፉንጋነቱ ጎን ለጎን ጥሩ ያስባል አዛኝ ልብ አለው።

እይታው ጥሩ ነው ፣ ፣ ፉንጋነቱ አይታወቀውም ፣ የፊቱን አቀማመጥ እረስቶታል ....

ብዙ መደዋወል ያዝን .....ይሰማኛል፣ ይጠይቃል አሰማሙ እና አጠያየቁ እሱ ኑሮ ያለው አይመስልም ፤ ገጠመኝ የሚያገኘው አይመስለኝም።

በመስማት ብቻ ለካ መጉላት ይቻላል !!

ከአልአዛር  ጋር ተዋደድን ። አልአዛር ፉንጋነቱ ተረሳኝ ...አይደለም ውበቱ ታየኝ ። አልአዛር ቆንጆ ነው።  አንድ ቀን ከፍቶኝ ቤቱ ሄድኩ አልጋው ላይ ተኛን አስተቃቀፉ አለሁልሽ አለው ።

እንደ ታናሹ አቀፈኝ ።ምቾት ተሰማኝ ፤ እለት እለት ፍቅሬ ጠነከረ ።

ድንገት የሆነ ቀን "እንለያይ" አለኝ ....ሳኩኝ።  በርግጥ አንድ ሁለት ሳምንት ሙሉ ደብዝዞ እየራቀኝ ነበር። ከራሱ ጋር የተጣላ ነበር የመሰለኝ ።

ላለማስጨነቅ ነበር ምን ሆንክ ላለማለት የሞከርኩት

እሱ ፀቡ ከኔ ጋ ነበር መሰለኝ ...

ቀለል አድርጎ ነበር እንለያይ ያለኝ ።እኔ እና እሱ መሃል ጭቅጭቅ፣ መዋደድ ፣ መሳቅ እንጂ የመለያየት ፅንሰ ሃሳብ እንዳለ አላውቅም ነበር ። ደነገጥኩ !! ኖ
ፈራው።ኖ አዘንኩ መጠን አልባ ሃዘን ልቤ ውስጥ ተንከላወሰ።

መለመን፣ የሆነውን ማወቅ ፈልጌ ነበር፣ ሲያቅተኝ ጠረጴዛ ላይ አጎንብሼ ሳለቅስ ሰዎች ትኩረታቸው ወደ እኛ ሲሆን ፦

"ኧረ አንተ ልጅ  This is attention-grabbering አረጋጋው !

ሁኔታው ንግግሩ ከእንለያዩ የበለጠ ጎዳኝ ።ቀጥ ብዬ እያለቀስኩ ከፊቱ ከካፌው ከኑሮው ሄድኩኝ

አልተከተለኝም .....

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #1⃣9⃣4⃣

አመኔታ ለጥፋትና ለሞት ሊያጋልጣችሁ ይችላል፡- ሆኖም፣ ሰዎችን በጥንቃቄ ከማመን ውጪ መኖር ማለት ግን ከሞት ያልተናነሰ ሕይወት መሆኑን አትዘንጉ፡፡

ፍቅር ለጉዳትና ለስብራት አሳልፎ ሊሰጣችሁ ይችላል፡- ሆኖም፣ ፍቅርን እየፈለጋችሁ ከፍርሃት የተነሳ ትክክለኛውን ሰው ከማፍቀር ውጪ መኖር ማለት ግን ከሞት ያልተናነሰ ሕይወት መሆኑን አትዘንጉ፡፡

ለእውነት መቆም እንድትጠሉና እንድትገለሉ ሊያደርጋችሁ ይችላል፡- ሆኖም፣ በትክክለኛው ጊዜና ቦታ ለእውነት ከመቆም ውጪ መኖር ማለት ግን ከሞት ያልተናነሰ ሕይወት መሆኑን አትዘንጉ፡፡


መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #1⃣9⃣3⃣

ከሰዎች ጋር ሰትኖሩ . . .

✅ ራሳችሁን ከሌሎች ሰዎች ጋር ማነጻጸርና መፎካከር ደስታችሁን የሰረቀባችሁ ቀንደኛው ሌባ እንደሆነ አትዘንጉ፡፡

✅ ሰዎች እውነቱን ስለነገሯችሁ የምትቀጧቸው ከሆነ ውሸትን እንደምታስተምሯቸው አትጠራጠሩ፡፡

✅ ሰዎች እንዲሁ የሚያጠቋችሁ እናንተን ስለተቃወሟችሁ ሳይሆን ራስ-ወዳድነት ስለተጠናወታቸው መሆኑን አስታውሱ፡፡

✅ ለደረሰባችሁ ቁስል ተጠያቂ እንዳልሆናችሁ ብታስቡም ለፈውሳችሁ ግን ሙሉ ለሙሉ ተጠያቂ መሆናችሁን አትርሱ፡፡

✅  ዛሬ እናንተ ጋር መጥተው ሌላውን ካሙላችሁ፣ ነገ ሌላ ሰው ጋር ሄደው እናንተን እንደሚያሙላችሁ እርግጠኛ ሁኑ፡፡ ...

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

ዘነዘና... ማነው ዘና ዘና በሉ...😂😂😂😘

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

አንዳንድ ሰው አለ ገና አይተኸው እስክትተዋወቀው እንቅልፍ የሚነሳህ

አወራሩ አኳኋኑ አስተያየቱ እንደው መቼ ተዋውቄው የሚያስብል።

አለ ደግሞ አንዳንዱ አይን ውስጥ የማይገባ፤ ትኩረት የማይስብ፤ አለባበሱ እንደነገሩ የሆነ አጋጣሚዎች ወስደው የሚያላትሙህ ከዛ የማትጠብቀውን ብስለት የምታይባቸው፤ ሩህሩህነታቸው ታይታ የሌለው፤ ሲወዱም ሲጠሉም ከልባቸው የሆነ ማስመሰል የማያውቁ

አሉ አንዳንድ ሰዎች እጣፈንታ ካላገናኘችህ ፈልገህ የማታገኛቸው።

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #1⃣9⃣1⃣

....አንዳንዴ በሕይወታችሁ ያለፋችሁባቸውን ውጣ ውረዶችና አሁን ያላችሁበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ሙሉ ለሙሉና በትክክል ሊገነዘባችሁ የሚችል ሰው ተፈልጎ አይገኝም፡፡ ታድያ ያን ጊዜ ብቻችሁን የቆማችሁ ሊመስላችሁ ይችላል፡፡

ስለዚህ . . . 

❇️ አብዛኛዎቹ ሰዎች Understand እንዲያደርጓችሁ ባለመጠበቅ ራሰችሁን በመቀበልና በማሳደግ መንገዳችሁን ቀጥሉ፡፡

❇️❇️ ሰዎች የተሳሳተ ነገር በእናንተ ላይ ሲያስቡና ሲናገሩ ተረጋጉና ትክክለኛ እንደሆነ ያመናችሁበትን መንገዳችሁን ቀጥሉ፡፡

❇️❇️❇️ ሰዎች የራሳቸውን አለመብሰልም ሆነ ያልተፈታ የስነ-ልቦና ተጽእኖ እናንተ ላይ ሲያራግፉ ሳትሸበሩ በዓላማችሁ ላይ አተኩሩ፡፡

መልካም ሠኞ
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

ማነክ አንተ ከአለም ከተኳረፍኩ በኋላ የመጣኸው??? 
ታውቆሃል ግን?
መወደድ የሚገባ ሰው ነህ እያልከኝ ነው? የምናፈቅ አይነት ሰው እንደሆንኩኝ እያሳየኸኝ ነው? መወደድን የሚያክል ምን በረከት አለ ግን እናንተዬ.😘😘😘

ገብቶሃል አይደል?
እድሜ ላንተ በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚቆረቆርልኝ ፣ ያገባኛል የሚለኝ ሰው ሊኖረኝ ነው ?

እንደናፈከኝ አይኖችህ ሲያቃጥሩ ነው የለመለምኩት እንጂ ውሃ እንዳጣ ተክል እየደረኩኝ ነበር 💀

ስቀና ፣ ስብከነከን ፣ ስትናፍቀኝ ጊዜ ነው እስከዛሬ የተዜሙት ዜማዎች ትርጉም የሰጡኝ ።

እወድሃለሁ ❤

በዙሪያዬ በማየው ነገር ምክንያት የተወለዱ ከንቱ አቋሞቼን ናቸው ያመከንክልኝ ። አልፈለግነቴን ነው የናድከው ።


እወድሃለሁ ❤

ሌሎች እርባና-ቢስ የሆኑ ነገሮችን ብቻ የማወራው የፍቅር ታሪክ ስላልነበረኝ ነው ፤ ስለፆታዊ ፍቅር ሲወራ ዝም የምል የነበረው ስለማላውቀው ነበር ።

#ማነህ_አንተ_የፍቅር_አማልክት?
#እወድሃለሁ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

ምንም ያህል መንገዱ ንፁህ ቢሆንም በባዶ እግርህ እንዳትሄድ ....

የማወራው ስለ መንገድ አይደለም
!

#ለፈገግታ 😁😁😁😄

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

ስራ ቀጣሪዎች "Portfolio ላኩ" ሲሉ ሰምታችሁ ይሆናል። ለመሆኑ Portfolio ምንድን ነው? እንዴጽ ማዘጋጀት ይቻላል?

Portfolio ማለት የአንድ ባለሙያ በተለይም ደሞ ጥበባዊ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን ችሎታና ልምድ ለማሳየት የሚጠቅም ገፅ ነው።

በብዛት Portfolio በመጠቀም ስራና ችሎታን በደንብ ማስተዋወቅ የሚችሉ ባለሙያዎች እነዚህ ሊሆኑ ይችላሉ።
1. አርክቴክቶች
2. ግራፊክስ ዲዛይነሮች
3. ፎቶግራፈሮች
4. የማስታወቂያ ባለሙያዎች
5. ዌብሳይት ዲቨሎፐሮች እና ሌሎችም ይጠቀሳሉ።

Portfolio ለማዘጋጀት እነዚህን ዌብሳይቶች መጠቀም ትችላላችሁ።

1. Behance
2. Wix
3. Weebly
4. WordPress
5. Crevado

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

እሁድን በጋራ😘😘😘😘

🌟🌟🌟🌟🌟

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 1⃣9⃣6⃣

#በራሳችሁ_ላይ_አትጨክኑ

....በዓለም ላይ ልትሰጡት ከምትችሉት የጭካኔ ፍርድና ከስ የላቀው እናንተው በራሳችሁ ላይ የምታመጡት ፍርድና ክስ ነው፡፡

የየእለት ድካማችሁን፣ ስህተታችሁን፣ ትግላችሁንና የመሳሰሉትን ነገሮቻችሁን ማንም ሰው ከሚያውቃችሁ በላይ ራሳችሁን ስምታውቁት ራሳችሁን ለመኮነንና በራሳችሁ ላይ የተዛባ አመለካከትን ለመያዝ ቅርብ ናችሁ፡፡ ስለዚህ በራሳችሁ ላይ የምታስቡት ሃሳብም ሆነ ለራሳችሁ የምትሰጡት ፍርድ
#በሚዛናዊነት ሊያዝ ይገባዋል፡፡

ያላችሁን የራስ-በራስ ግምገማና ትችት በፍጹም ችላ ልትሉት አይገባም፡፡ ነገር ግን በሚዛናዊነት ተገቢውን እየለያችሁ ራስን ለመለወጥ መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡

❌‼️ራሳችሁን እስከመኮነን ድረስ በራሳችሁ ላይ አትጨክኑ፡፡

❌‼️በራሳችሁ ላይ ያላችሁ አመለካከት እስከሚወርድ ድረስ በራሳችሁ ላይ አትፍረዱ፡፡

❌‼️ሌላ ውሳኔ ለመወሰን ያላችሁ ድፍረት እስከምታጡ ድረስ ባለፈው ውሳኔያችሁ ስህተት ራሳችሁ አትደብድቡ፡፡

#ስህተታችሁን_እወቁ#አርሙ
#ደግማችሁ_ላለመስራት_ወስኑ፡፡

ከዚያም ቀና ብላችሁ በአዲስ መንፈስ ወደፊት!😘😘

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

Rustin ሙሉ ፊልም
አነስ ባለ MB

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

ብዙዎቻችን የማርቲን ሉተርኪንግን "I have a dream"የሚለውን ደማቅ ንግግርን እናስታውሳለን። ትልቅ ጭቆና በደልን ለመቃወም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተሰበሰቡበት የታናገረው ታሪካዊ ንግግር ነው። እስከዛሬ ድረስም የንግግሩ ተፅእኖ ጎልቶ ይታያል።


ከሰልፉም ሆነ ከታሪካዊ ንግግሩ ጀርባ ግን ስላለው ታላቅ ሠው ብዙም አልሰማንም....🤔🤔

Bayard Rustin ይባላል። የማሕበረሰብ አንቂና ተሟጋች የነበረ ታላቅ ሠው ነው። በቀለም "በማንነት" በስብእናቸው ምክንያት በደል ለሚደርስባቸው ሠዎች ዘብ የሚቆም ሠው ነበረ Rustin ።

በ 1940ዎቹ ዜጋ መሆን በደል በነበረበት ጊዜ የ LGBTQ+ Community አባል የነበረው ይሕ ሠው ፤ ያለበትን ጫና ተቋቁሞ የላቀ ትግልን አሳይቷል።
#ዛሬ_ማታ_2:30 ላይ የምንጋብዛችሁም ፊልም በርሱ ሕይወት ላይ የተሰራን ቆንጆ ፊልም ነው።
ተጋበዙልን።

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

የማለዳ -ማስታወሻ # 1⃣9⃣6⃣

ሰዎች በእናንተ ላይ የሚያንጸባርቁት ባህሪይ የእናንተን ሁኔታ ከማንጸባረቁ ይልቅ የሚያሳየው የእነሱኑ ሁኔታ ነው፡፡ ይህንን እውነታ በሚገባ መገንዘብ በሄድንበት ሁሉ ሰዎች የሚሰጡንን መስተግዶና የሚሳዩንን ባህሪይ እየተከታተልን ከመደናበር ይጠብቀናል፡፡

በሄዳችሁበት ቦታ ሁሉ ሰዎች የሚያሳዩአችሁን አጉል ባህሪይ እያያችሁ ሁኔታው የእናንተን ማንነት መተርጎሚያ ከማድረግ ልቦናችሁን ጠብቁ፡፡

ጥቂት የመንደርደሪያ ሀሳቦች . . .

ሰዎች ከጠሏችሁ የግድ የምታስጠሉ ሰዎች ስለሆናችሁ ነው ማለት አይደለም፡፡ ሰዎቹ በጥላቻ የተሞሉ አይነት ሰዎች ስለሆኑም ሊሆን ይችላል፡፡

ሰዎች ከናቋችሁ የግድ መናቅ የሚገባችሁ አይነት ሰዎች ስለሆናችሁ ነው ማለት አይደለም፣ ሰዎቹ ሰውን የመናቅ ችግር ስላለባቸው ሊሆን ይችላል፡፡

ሰዎች ካገለሏችሁ የግድ እንድትገለሉ የሚያደርጋችሁ ማንነት ስላላችሁ ነው ማለት አይደለም፣ ሰዎቹ ሰውን በተለያየ ምክንያት ማግለል የለመደ ባህሪይ ስላለባቸው ሊሆን ይችላል፡፡

በአጭሩ ሰዎች ለእናንተ የሚያሳዩትን ባህሪ በመመልከት ብቻ ከዚያ አንጻር ለማንነታችሁ ትርጉምና ፍቺ ከመስጠት ተቆጠቡ፡፡ በዚያ ምትክ ማሕበራዊ ግንኙነታችሁን ሊያዛባ የሚችል አጉል ባህሪይ ካለባች እሱ ላይ ካለማቋረጥ በመስራት የሰዎችን የግል አመለካከትና አጉል በህሪይ ለራሳቸው ተውላቸው፡፡

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

ድንቡሼ.....😂😂😘

🌟⭐️🌟⭐️🌟

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #1⃣9⃣5⃣

#በአንድ_ሁኔታ_ውስጥ_ስታልፉ!

ወንድሞች...አንድን የምታውቁትን ነገር እንደገና ላስታውሳችሁ፡፡

በአለም ላይ አሁን እናንተ በማለፍ ላይ ባላችሁበት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያለፉ፣ በማለፍ ላይ ያሉና ወደፊትም የሚያልፉ ሰዎች እልፍ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹን ይህ ተመሳሳይ ሁኔታ ሲቀብራቸው፣ ሌሎች ደግሞ በእርግጥም ያልፉታል፡፡

ለዚህ ልዩነት መነሻ የሚሆኑ ሌሎች ምክንያቶች ሊኖሩ የመቻላቸው እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በእነዚህ ሰዎች መካከል ያለው ዋና ልዩነት...

በዚያው ተውጠው የቀሩት ሰዎች ከሚያልፉበት ሁኔታ የተነሳ በመደናገጥ ወደፊት መገስገስን በመተው በመቆማቸው ምክንያት ሲሆን፣
እነዚያ ዘልቀው የሄዱትና በአሸናፊነት የወጡት ደግሞ በሚያልፉበት ሁኔታ ውስጥ በፍጹም ሳይቆሙ ወደፊት በመንቀሳቀሳቸው ምክንያት ነው፡፡

#በአንድ_ሁኔታ_ውስጥ_ስታልፉ_በእርግጥም_እለፉ_እንጂ_እንዳተቆሙ!

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

Иш тополмай юрганлар учун сирли канал топилди

/channel/+ufsA-9qEccNlNzRi

Коплаб йирик компаниялар элон берувчи ҳамма излаган канални топдик. Кўплаб маълумотлар, минглаб элонлар базаси интернетга чиқиб кетди.

Билиб олиш учун каналга уланинг:

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/+ufsA-9qEccNlNzRi

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

በመሳሳም ጊዜ ከአንዳችን ወደሌላችን የሚተላለፍ ጥርስን ከጥቅም ውጪ የሚያደርግ ባክቴሪያ እንዳለ ያቃሉ?????🤔🤔

በመሳሳም ጊዜ በሚኖር የምራቅ መለዋወጥ ምክንያት ከአንድ ሰው ወደሌላው የሚተላለፈው ይህ ባክቴርያ የሚያምር ፈገግታችን እስከነጭራሹ ለሚያጠፋ የጥርስ መቦርቦር ይዳርገናል።

#ሐላፊነታቸንን_እንወጣ
#ንፅሕናችንን_ጠብቀን_በነፃነት_እንደሰት

#now_u_know

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #1⃣9⃣2⃣

ሁል ጊዜ ትክክል እንደሆናችሁ የምታስቡ ከሆነ ከሕይወት የምትማሩት አንድም ትምህርት እንደማይኖር አትዘንጉ፡፡ መማር ስታቆሙ ደግሞ ማደግ ታቆማላችሁ፡፡

ለመማር ማድረግ ያለባችሁ ነገሮች . . .

↪️  የተግባራችሁ ውጤት የሚነግራችሁን አስተውሉ፣

↪️  ሰዎች የሚነግሯችሁን ነገር አድምጡ፣

↪️  አንብቡ፣

↪️  የሰዎችን የሕይወት ተሞክሮ አጢኑ፣

↪️  በየጊዜው ከተለመደው ስፍራ ዘወር በማለት የማሰላሰያ ጊዜ ይኑራችሁ፡፡

↪️  ከፈጣን ሃሳብ ሰጪነት ቆጠብ በሉ፣

↪️  ክርክርን አታብዙ፡፡   

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ


@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

Иш тополмай юрганлар учун сирли канал топилди

/channel/+Fvrc32Xc-SU5ZTM6

Коплаб йирик компаниялар элон берувчи ҳамма излаган канални топдик. Кўплаб маълумотлар, минглаб элонлар базаси интернетга чиқиб кетди.

Билиб олиш учун каналга уланинг:

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/+Fvrc32Xc-SU5ZTM6

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

😍😍
እሁዳችሁ አንደዚ ዘንካታ ነበረ??
🌟⭐️🌟⭐️🌟

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

እውነታኛ ማንነቴ እሱ ነው የሚያውቀው ፤ ማንነቴን እንደ ገላዬ መለመሉን አይቶታል ፤ የድብርቴ እና የደስታ ጣሪያዬን ዳስሶታል ።

ቀልድ ይችልበታል ፤ እኔን የእሱ ለማድረግ
አልጣረም ፤ ወይ ደሞ የእሱ ለማድረግ በሌሎቹ መንገድ አልመጣም ፤ ከእሱ ጋ እንድሆን ክችች አይልም ፤ ሳያብራራ በማህበረሰቡ የተገነቡ ህጎችን ይተገነብራቸዋል ፤ ሰው የማይጎዳ ነገርን  ከምን ይሉኝ ወጥቶ ማድረግ የመሰለ ነፃነት የለም ።

አቆላምጦ ሲጠራኝ ደስስ ይለኛል ። ጭንቀቴን ስነግረው ጣልቃ ሳይገባ ይሰማኛል ፤ "አይዞን መፍትሄ አይጠፋም!" ይለኛል ወይ እቅፍ ያደርገኛል ፤ ጨንቆኝ  አግኝቼው ቅልል ያላለኝ ግዜ አላስታውስም።


መንገድ ላይ አንገቴ ስር ገብቶ በስስት ይስመኛል ፤ ዙሪያ ገባውን ተሳቅቄ ስቃኝ ክባዳም እያለ የበለጠ አይን ውስጥ በሚያስገባ ሁኔታ እቅፍፍ  አድርጎ ይስመኛል ።

ስንዋደድ ፣ አንሶላ ስንጋፈፍ  ፣ ፍቅር አሰጣጡ  ጣፈጠኝ!❤❤❤ ከሚሰጠኝ ደስታ እና ከማንነቱ  ሱስ ያዘኝ😍
 

ባውንደሪ አለው ፤ የማይወደውን ሳደርግ አይለማመጠኝም ፣ አይልመጠመጥም ፣ ይዘጋኛል ይርቀኛል ፤ ቆፍጠን ያለ ልበ ሙሉ ነው ።

የሰዎች በደል ይሰማዋል ፤ የወደቀ ላይ አይፈርድም። ትክክል መስሎ ለመታየት የማይጋጋጥ ነፍስ ያለው ፍጡር ነው ።

#ከሚታየው_በላይ_በሂደት_እየገዘፈ_የሚሄድ_የማፈቅረው_ልጅ_እሱ_ነው

#love_is _love

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

እንዴት አለፈ ጁምአ ታድያ? 😘😘😘😘😍

🌟⭐️🌟⭐️

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…
Подписаться на канал