habeshagay1 | Для взрослых

Telegram-канал habeshagay1 - ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

789

Подписаться на канал

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣3⃣1⃣

#30_የነጻነት_ቀናት

ከአንድ ለእናንተ ከማይመጥን ተገቢ ካልሆነ ሰው ወይም ተገቢ ካልሆነ ጤና-ቢስ ሁኔታና ልምምድ ሙሉ ለሙሉ ነጻ የመውጫው ዋነኛ መንገድ ከዚያ ሰው ወይም ከዚያ ሁኔታ ውጪ መኖር እንደምትችሉ ራሳችሁን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማሳመን ነው፡፡

ከማንኛውም አጉል ሰውም ሆነ ሁኔታ ለመላቀቅ እየፈለግን ያለመቻል ሁኔታ መነሻው ከዚያ ሰው ወይም ሁኔታ ውጪ መኖር እንደማንችል ያለን የውስጥ አመለካከት ነው፡፡ 

አንድን ነገር ልሞግታችሁ፡- መርዛማ ከሆነው ግንኙነታችሁ፣ ጤና-ቢስ ከሆነው ልምምዳችሁን፣ አላስፈላጊ ከሆኑት ቦታዎች ለሚቀጥሉት 30 ቀናት ፈጽማችሁ ለመራቅ ሞክሩና ውጤቱን ተመልከቱት፡፡ ለ30 ቀናት ማድረግ ከቻላችሁ እስከወዲያኛው እንደምትችሉ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣2⃣9⃣

#የመነቃቂያ_ጎዶሎነት

ዘመኑ የመነቃቂያ ንግግሮች፣ ጽሁፎች፣ ዝግጅቶች እና መሰል ልምምዶች የተበራከቱበት ዘመን ነው።ይህ ምንም ጥርጥር የሌለበት እውነታ ነው።በዚያው ልክ ደግሞ “አንድን ነገር በከፍተኛ መነሳሳት እጀምርና ከጥቂት እርምጃ በኋላ መቀጠል ግን ያቅተኛል” የሚሉ ሰዎችም ቁጥር እየበዛ መጥቷል።

በተነቃቃንና በተነሳሳን ቁጥር የተሳካ ጉዞ ውስጥ የምንገባ መስሎን ከአንዱ መነቃቂያ ፕሮግራም ወደሌላኛው አነሳሽ ዝግጅት ስንዳክር ራሳችንን ልናገኘው እንችላለን፡፡  

ይህ ከላይ የተጠቀሰው ልምምድ ችግር ባይኖረውም የጉዞው ግማሽ መንገድ ላይ ብቻ እንደሚያደርሰን ግን ማስታወስ አስፈላጊ ነው።በመነቃቃት (Motivation) የተጀመረው ጉዟችን በመመሪያ (Instruction) ካልቀጠለ ስኬታማነቱ አጠራጣሪ ነው፡፡
መነቃቃት ያነሳሳል፣ ያስጀምራት፣ ጉጉትን ይፈጥራል...
መመሪያ ግን የተጀመረውን ነገር እንዴት እንደምንቀጥለውና ወደ ስኬታማ ፍጻሜ እንደምናደርሰው መንገዱን ያመላክተናል፡፡

#መነቃቃት አብዛኛው ስራው ስሜት ላይ ሲሆን፣ #መመሪያ ግን አብዛኛው ተግባሩ ወደፊት የመቀጠልን ስሌትና ጥበብ ማመላከት ነው፡፡ እነዚህ ሁለቱ ልምምዶች አብረው ካልዳበሩ ብዙም አያስኬዳችሁም።

እውነታው ሲጨመቅ፡- አንድን ጉዞ ጀምራችሁ በስኬታማነት ማጠናቀቅ ከፈለጋችሁ ሁለት ዋና ዋና ልምምዶች ያስፈልጓችኋል፡- 1) መነቃቃት (Motivation)፣ 2) መመሪያ (Instruction)፡፡

አስቡበት!

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣2⃣7⃣

#ጎዶሎው_ነገሬ. . .

መልኬ ላይ፣ ቁመናዬ ላይ፣ ማንነቴ ላይ፣ ዘሬ ላይ፣ ቋንቋዬ ላይ . . . የሆነ የጎደለ ነገር (Missing Piece) እንዳለ ሲሰማኝ ሰነባብቷል፡፡ ብቻ ምን አለፋችሁ ከማንነቴ ላይ ተቆርጦ የወጣ የሆነ ነገር እንዳለ እስከሚሰማኝ ድረስ ጎዶሎነትና ባዶነት ይሰማኝ ነበር፡፡ ከዚያም ያንን የጎደለ ነገር አግኝቼና አምጥቼ ማንነቴ ላይ ብለጥፈው ሙሉ የምሆን ስለመሰለኝ ያልሄድኩበት ቦታና ያላደረኩት ነገር የለኝም፡፡

በዚህ ጥረቴ ብዙ ነገሮችንም ሞክሬአለሁ፡፡ የሚቀባውንም ተቀብቼ፣ የሚለበሰውንም ለብሼ፣ የሚቀየረውንም የራሴን ሁኔታ ለመቀያዬር ሞክሬ፣ ያልሆንኩትን ሆኜና የሆንኩትን ትቼ፣ በዙሪያዬ ያሉትንም እስከመምሰል ራሴን ለውጬ . . . ሞከርኩት፡፡ አሁንም ግን ያ ጎዶሎው ነገር አልሞላም ነበር፡፡

አሁን አሁን ግን አንድ እውነት እየገባኝ ስለመጣ መረጋጋት ጀምሬአለሁ፡፡ ለካስ የጎደለኝ ነገር መነሻው ውጫዊ ሳይሆን ውስጣዊ ነው፡፡ ምንም አይነት ውጫዊ ነገሬን በማሟላቴ ደስተኛ ለመሆን ከመሞከሬ በፊት በመጀመሪያ ራሴን ከነማንነቴ (ብርቱውንም ደካማውንም) መቀበልና መረጋጋት እንዳለብኝ ገብቶኛል፡፡

የጎደለው ነገሬ “ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ራስን መቀበል” የሚባለው ዘመን የማይሽረው እውነታ ነው፡፡  

ለናንተም ይህን ተመኘሁኝ
መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣2⃣5⃣

#ጤናማ_ሕመም!

ሕመምን የሚመኝና የሚከታተለው ሰው ባይኖርም፣ ሕመም የጤናማ ሕይወት ምልክት የሚሆንበት ጊዜም እንዳለ እናስታውስ፡፡ ለማደግ ከፈለግን ሕመም የግድ ነው፡፡

🌈❤️ ጡንቻችን እንዲጎለብትና ኃይላችን እንዲጨምር፣ ከስፖርት የሚመጣውን የጡንቻ ህመም መታገስ የግድ ነው፡፡

🌈❤️ ከህመም ለመዳንና ጤንነታችን እንዲመለስ፣ የመርፌውን ህመምና የመድሃኒቱን መራራነት መቻል የግድ ነው፡፡

🌈❤️ ነግዶ ለማትረፍ፣ ከኪሳራ የሚመጣን ሕመም መታገስ የግድ ነው፡፡

🌈❤️
#ፍቅርን_ለማጣጣም_የመገፋትን_ሕመም_መታገስ_የግድ_ነው፡፡

🌈❤️ ማሕበራዊ ግንኙነታችን ሰላም እንዲሆን፣ ጤና-ቢስ አመለካከቶችን የመሞገትን ሕመም መጋፈጥ የግድ ነው፡፡

💠💠💠💠. . . አያለ የሕመምና የእድገት ግንኙነት ታሪኩ ይቀጥላል . . . 💠💠💠💠

No Pain, No Gain!

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣2⃣4⃣

#የከባድ_ቀላል!

ማንኛውም ጥሩ ውጤት የሚያመጣ ጉዞ ከባድ መሆኑ ምንም ጥርጥር የሌለው ጉዳይ ነው፡፡ ስለሆነም፣ አንድን ከባድ ስራ ለመስራት ወይም ረጅም ጉዞን ለመጓዝ ሰትጀምሩ ለዚያ ተግባር ወይም ጉዞ ያነሳሳችሁ ዓላማ ከጉዞው አስቸጋሪነት ከብዶና ልቆ ካልተገኘ በጉዞው መሃል መድከማችሁ አይቀርም፡፡

አንድን ከባድ የሆነን ነገር በብርታት ጀምሮ የመጨረስ ዋነኛ
#ምስጢር_ያለው ነገሩን ለማድረግ ያነሳሳችሁ ዓላማ ከስራው ክብደት የመብለጡ ጉዳይ ነው፡፡

መማር ከባድ ነው፣ ሆኖም ከተማራችሁ በኋላ የሚታያችሁ የለውጥ ዓላማ ከዚያ ልቆ ሲገኝ ግን መማር የከባድ ቀላል ይሆናል፡፡
በየቀኑ እየተነሱ ስራ መሄድ ከባድ ነው፣ ሆኖም ስራን በመስራታችሁ ምክንያት ልትደርሱ የምታስቡበት ዓላማ ልቆ ሲገኝ ግን ስራ የከባድ ቀላል ይሆናል፡፡

የፍቅርን ግንኙነትንና የመሳሰሉትን ጥልቅ ግንኙነቶች መጀመር ከባድ ነው፣ በዚያ ግንኙነት ውስጥ ያላችሁ ዓላማ ልቆ ከተገኘ ግን የግንኙነት ውጣ ውረድ የከባድ ቀላል ይሆናል፡፡

ይህንን መርህ በሁሉም የሕይወት ዘርፍ ውስጥ ተግባራዊ አድርጉትና ለእናንተ የከበዳችሁ ነገር ለምን ለሌሎች ሰዎች እንደቀለላቸው ማየት ትጀምራላችሁ፡፡ ከዚያም ጉዟችሁ እንዴት እንደሚቀልል ትደርሱበታላችሁ፡፡

ከባዱ ነገር የሚቀልለው የዓላማችሁ ክብደት ከስራው ክብደት ልቆ ሲገኝ መሆኑን አትርሱ!

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

🫵🏾#ስሜትህን_ቀይር!

እንበልና የሆነ ሰው አበሳጨህ፣ ዝቅ አድርጎሃል! ጉዳት ተሰምቶሃል እና? በመጀመሪያ ስሜቱን አትካደው ነገር ግን ለምን እንደዛ ሊሰማህ እንደቻለ ራስህን ጠይቅ... ምናልባት ያ ሰው እንደዛ እንዲሰማህ አልፈለገም... ምናልባት ያ የራስህ የአረዳድ ችግር ይሆናል... ምናልባት ያለብህ የበታችነት ስሜት... ምናልባትም ለዛ ሰው ያለህ ድብቅ ጥላቻ... ወይም በትክክል ያበሳጨህ ሰው ሆን ብሎም ሊሆን ይችላል።
የፈለገ ይሁን የሚረብሽ ስሜት ለምን ውስጥህ ቀረ? ይሄን ጥያቄ ምትመልሰው አንተ ሁነህ ሳለ እኔም የምጠቁምህ ነገር ይኖራል።

እዚህ ጋር- ህይወት ሁሌም ደስታ፣ መፈለግ፣ ማግኘት፣ እኩል መሆን፣ ስኬት እንዳልሆነች ተገንዘብ። ብስጭት ወይም የስሜት መረበሽ ሲያጋጥምህ ዝም ያለ ቦታ ሂድ፤ ከራስህ ጋር በፍቅር ተነጋገር። የመጥፎ ገጠመኞችን ጥሩ ጎን ለማየት ራስህን በአዎንታዊነት እንዲመራ አስገድድ
...
👇🏽👇🏽

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣2⃣3⃣

#ቋንቋችን #ጊዜ #ይባላል!

አንድን ሰው ከልባችሁ የምታከብሩት ከሆነ ቀላሉ መመዘኛ የዚያን ሰው ሰዓት ወይም ጊዜ የማክበራችሁና ያለማክበራችሁ ጉዳይ ነው፡፡ በተጨማሪም፣ ጊዜያችሁን ሰውታችሁ ለዚያ ሰው ስትሰጡት ያንን ሰው እንደምታከብሩት መልእክትን እያስተላለፋችሁ ነው፡፡ ገንዘብ፣ ቁሳቁስና የመሳሰሉት ነገሮቻችሁን ለማንም ሰው ልትሰጡ ትችላላችሁ፣ ጊዜያችሁን (በተለይም የተጣበበውን) ግን ለሚከበርና ለመወደድ ሰው ነው የምትሰጡት፡፡


ማሰተካከያ ልናደርግበት የሚገባን ቀውሰ ያለው እንግዲህ እዚህ ላይ ነው፡፡ የአብዛኛዎቻችን የግንኙነት ቀውሶች፣ በስራ ስኬታማ ያለመሆንና የመሳሰሉት ቀውሶች መነሻቸው ለምንወደውና ለእኛ ወሳኝ ለሆነ ሰውም ሆነ ስራ ተገቢውን ጊዜ አለመመደብና አለመስጠት ነው፡፡ ይህ ቀውስ ብዙ ጠቃሚ የሆኑ ሰዎችንና ስራዎችን ከእጃችን እንዲወሰዱ ያደርገናል፡፡

ይህንን አትርሱ....

❇️ማንኛውም ሰው ሆነ ስራ እኛ ተገቢውን ጊዜና ትኩረት ካልሰጠነው ተገቢውን ጊዜና ትኩረት የሚሰጡት ሰዎች “ላፍ” አድርገው ይወስዱታል፡፡

❇️ ጊዜያችሁን ለምትወዱት፣ ለምታከብሩትና ቅድሚያ ለምትሰጡት ሰው ስትሰጡ ተገቢውን ምላሽ ታገኛላችሁ፡፡ ተገቢውን ምላሽ ካላገኛችሁ ደግሞ ግንኙነታችሁን እንደገና ማጤንና ማስተካከያ ማድረግ የግድ ነው፡፡  

❇️ ዋጋ ለምትሰጡት ስራም ቢሆን ጊዜ ስትሰጡት ስራው ውጤትን በመስጠት ይመልስላችኋል፡፡ ስራው ጊዜያችሁን እየወሰደ ውጤት የማይሰጣችሁም ከሆነ ደግሞ ስራው እንደገና ሊቃኝ ይገባዋል፡፡

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስቴወሻ # 2⃣2⃣1⃣

#በምርጫ_ጎዳና_ውስጥ_ያለው_ደስታ

ልክ መተንፈስ የሕይወት አካል እንደሆነና ሲቆም ሕይትም እንደሚቆም፣ ምርጫም ልክ እንደዚያው ነው።መምረጥ ያቆመ ሰው መኖርን ያቆመ ሰው ነው።

ይህ እሳቤ ምርጫ የግድ የሕይወት አካል እንደሆነ እንደናስብ ያደርገናል፡፡ ሆኖም ይህ ሃሳብ ለአንዳንድ ሰዎች ጭንቅ ነው፡፡ ምርጫን ከውጥረት፣ ከመጨናነቅ፣ ከመሳሳት፣ ከጸጸትና ከመሰል አሉታዊ ስሜቶች ጋር ስለሚያዛምዱት ማለት ነው።ይህንን ስሜት ለማሸነፍና የምርጫን ሕይወት ለመለማመድ ምርጫን ከደስታ ጋር ማዛመድ አስፈላጊ ነው።

•  ምርጫ እንዳለን የማወቅ ደስታ፡- በብዙ የሕይወት አቅጣጫዎቻችን ምርጫ እንዳለን በማወቅ ውስጥ ታላቅ ደስታ አለ። ዛሬ ነግቶ ስትሰማሩ አብዛኛውን ነገር በምርጫችሁ የማድረግ እድል ስላላችሁ ደስ ይበላችሁ፡፡

•  ከምርጫ ሂደት የሚመጣ ደስታ፡- በብዙ አማራጮች መካከል የትኛው ለእኛ የተሻለ እንደሆነ ለመለየት የሚደረግ ስሌት የሕይወት አንዱ ደስታ ምንጭ ነው፡፡ ማሰብ፣ ማቀድ፣ ማሰላሰል፣ ማወዳደርና ትክክለኛው ነገር ላይ ለመድረስ መሞከር ሂደት ለሕይወት የደስታ ጣእም ይሰጣል።

•  የትክክለኛ ምርቻ ደስታ፡- ምርጫ እናዳለን በማወቅና ትክክለኛውን ሂደት በመከተል ስንመርጥና ምርቻችን ትክክለኛ እንደሆነ ስናወቅ የሚኖረን ደስታ ይህ ነው አይባለምለ።

•  ከትምህርት የሚመጣ ደስታ፡- አንዳንዴ ተጠንቅቀን እንኳን ምርጫችን ሊሳሳት ይችላል። ይህ ሲሆን ከዚያ ስህተት በመማር ለነገው ምርጫ ጥበብን በማዳበር ውስጥ ሚገኘው ተግባራዊ ደስታ ደስታ ቀላል ኤደለም።

በምርጫ ጥበብ መብሰላችሁን ቀጥሉ እንጂ ምርጫን አትፍሩት! በምርጫ ውስጥ ያለውን የማያልቅ ደስታ ተለማመዱት!.

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

"ቀላል ይሆናል"🤍

🤍የጠመመው ይቃናልናል፣ የተበላሸው ይስተካከላል ፣ ጥላቻችን ጊዜ ያሸንፈዋል ፣  የበደለንን ይቅርታ እናደርጋለን ፣ ያቄመብን  ይረዳናል፣  የጀመርነውን እንጨርሳለን ፣ያቀድነውን እንተገብራለን ፣ ህልማችን እውን ይሆናል ።

❤️የካደንም ፣የካድነውም ትዝታ ብቻ ይሆናል ።

"ሁሉም ጥሩ ይሆናል"

#ስራ_እናገኛለን#ጤናችን_ይስተካከላል#ከአምላካችን_ጋር_እንታረቃለን#እራሳችንን_ይቅርታ_እንላለን

ግምባር-ቀደምም እንሆናለን

#እንለመልማለን#የእውነት_እንስቃለን#የእውነት_እንወዳለን#ወላጆቻችንን_እንጦራለን
#እንመረቃለንም...

ሁሉም መልካም ይሆናል!!

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣9⃣

ትንሽ ታገሱ!

ለጥንዶች . . .

የፍቅር ወራት የመተዋወቂያና የመግባቢያ ወቅት መሆኑን አትዘንጉ፡፡ በእነዚህ ወራት ውስጥ ልክ እናንተ የፍቅረኛችሁ ሁኔታ፣ ባህሪይ ልማድና የሕይወት ዘይቤ ግነኙነቶቀቀ እንደሚላችሁ ሁሉ፣ ፍቅረኛችሁም ገና እናንተን ለማወቅ እየታገለ መሆኑ/ አትርሱ፡፡ ስለዚህ ትንሽ ታገሱ!

በፍቅረኛችሁ ሁኔታ ላይ የማትወዱትን ነገር እየለቀማችሁ ከማዋከባችሁ፣ ከማኩረፋችሁ፣ ከመበሳጨታችሁ፣ ስሜታዊ ከመሆናችሁና “በቃ እንለያይ” አይነት ሃሳብ ከመሰንዘራችሁ በፊት በቅድሚያ ለፍቅርና ለመተዋወቅ ጊዜ ስጡት፡፡

በተቻላችሁ መጠን አብራችሁ ብዙ ጊዜ አሳልፉ፣ ብዙ ተነጋገሩ፣ ብዙ ጥያቄን በመጠያየቅ አንዱ ስለሌላው ለማወቅ ሞክሩ፣ ተናበቡ፣ የምትግባቡበትንም ሆነ የማትግባቡበትን ሃሳብና አቋም አንሸራሽሩ፣ አንዱ በሌላው ላይ የማይወደውን ነገር በግልጽ ተወያዩ . . . ፡፡

ለፍቅር ትንሽ ጊዜ ስጡት! 

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

El Houb - The Love (2022)
Original title: El Houb

👨🏼‍🤝‍👨🏻
#ElHoubTheLove 👨🏼‍🤝‍👨🏻

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣7⃣

#ፍቅርን_አታደራርቡ!

ከአንድ ሰው ጋር የፍቅር ግንኙነት ከጀመራችሁ በኋላ ቀዳሚው ስራችሁ የግንኙነቱን አይነት ትርጉም በመስጠት መግባባት ነው፡፡ ይህም ማለት ያላችሁ ግንኙነት የቀላል ጓደኝነት ይሁን አልያም የፍቅር ግንኙነት ይሁን፣ ሁለታችሁም ግልጽ በሆነ መልኩ በመነጋገር ከነትርጓሜያቸው መግባባት አለባችሁ፡፡

ግንኙነታችሁ የቀላል ጓደኝነት (Friendship) ደረጃ ላይ ካለ፣ ከመገናኘት፣ ከመጠናናትና ከመግባት ያለፈ ደረጃ ስለሌለው አንዱ የሌላኛውን ማንንም ሰው የማግኘት ነጻነት ሊጠብቅ ይገባዋል፡፡

አንድ ጊዜ እናንተ የእነሱ፣ እነሱ ደግሞ የእናንተ እንደሆናችሁ ከተግባባችሁና የፍቅረኛነትን (Lovers) ጎዳና ከጀመራችሁ በኋላ፣
#በዚያ_ፍቅረኛ ላይ ሌላ ፍቅረኛ ደርቦ የመያዝ ልማድ ካላችሁ እጅግ የከሰረን የወደፊት ሕይወት እንደጀመራችሁ አትዘንጉ፡፡

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣6⃣

ለትንሹም ለትልቁም ጥፋት ካለምንም መታለፍ ቤተሰብ ወይም አሳዳጊ
#ቅጣትና_ስድብ_ሲያቀምሱት_ያደገ_ሰው ይዞ የሚያድገው የስነ-ልቦና ቀውስ ይህ ነው አይባልም፡፡  ይህ ቀውስ የማንነታችንን ዋጋ ካለፈው ታሪካችን አንጻር እንድንተምነው ያደርገናል፡፡

ይህ ሲሆን፣ ሰው ለሰራው ስህተት ሁሉ አንድም ሳይታለፍ ልኩን ሊገባና ሊቀጣ ይገባዋል የሚል ዝንባሌ እናዳብራለን፡፡

በሁሉ ነገር ተቀጥቶ ያደገ ሰው ዘወትር ስህተትን ከቅጣት ጋር አያይዞ ነው የሚመለከተው፡፡ ይህ፣ “ሰው ለሰራው ስህተት ሁሉ ልኩን መቅመስ አለበት” የሚል የቅጣት ዝንባሌ ነው፡፡

ይህ ዝንባሌ ያለው ሰው ለተከሰተ ማንኛውም አይነት ስህተት የሚያውቀው ምላሽ ቅጣት ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም፣ አንድ ስህተት ሲገኝ አንድ ሰው የግድ መቀጣት አለበት፡፡ ይህ አመለካከት ደግሞ ስህተት ሲገኝ ራስን በመውቀስ ወይም የሚወቀስ ሰው ፈልጎ በመውቀስና በመቅጣት ሊገለጥ ይችላል፡፡

በየእለቱ የአንድን ሰው ስህተት ለአፍታ አንኳን ሳናልፍ የሚወገር ሰው ፍለጋ የምንተጋው ለዚህ ይሆን?

እስቲ በሰዎች ላይ ያለንን ጭካኔ ትንሽ መለስ እናድረገው!


መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

✅ ЯНГИ ҚУРИЛАЁТГАН УЙЛАРДАН УЙ ҚИДИРЯПСИЗМИ?

⚡️ 2024-йилда қурилаётган уйлар ва уларнинг нархлари
⚡️12 ойдан 120 ойгача муддатли тўлов
⚡️Буларнинг барчаси
@YangiBinolar телеграм каналимизда

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣3⃣

#የፍቅር_ቋንቋዎች_መለማመድ #ክፍል_አንድ

የፍቅር ቋንቋ 1፡-
#የሚገነቡና_የሚያጸኑ_ቃላት


ውጤታማ የፍቅር ተግባቦትን ለማዳበር ከፈለግን የፍቅር አጋራችንን ቀደምተኛ የፍቅር ቋንቋ ለመማር ፈቃደኞች መሆን አለብን . . . የተለያዩ ቋንቋ ከሚናገሩ ሰዎች ጋር ለመግባባት
#የእነሱን_ቋንቋ_መናገር የግድ እንደሆነ ሁሉ ፥ ከፍቅረኛችንም ጋር ለመግባባት #የእነሱን_የፍቅር_ቋንቋ መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡

ሌላውና ዋንኛው ደግሞ ፍቅርን በስሜት መግለጫው መንገድ የሚገነቡንና የሚያበረታቱን ቃላት በመለዋወጥ ነው፡፡

ዛሬ ለፍቅረኛችሁ ምንም አይነት አሉታዊ፣ የወቀሳ፣ የክስና ድካምን የሚያጎላ ቃላት ላለመናገር ሞክሩ፡፡ በዚያ ምትክ የሰሩትን መልካም ነገር ማድነቅ፣ ያቃታቸውን ነገር ማበረታተት፣ ውበታቸውን ማድነቅ፣ እነሱ በመኖራቸው ምክንያት ስላገኛችሁት መልካም በረከት እና የመሳሰሉትን ቃላት ንገሯቸው፡፡

ግንኙነታችሁ የሰላምና የደስታ ይሁንላችሁ!
አልጨረስንም

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣3⃣0⃣

#ድል_ውስጣችሁ_ነው

አሸናፊነትንና ተሸናፊነት ከውጪ ከማግኘታችሁ በፊት የምታገኙት በውስጣችሁ ነው፡፡ በምሳሌ እንዳብራራ ይፈቀድልኝ፡፡
ለምሳሌ፣ አንድ ሰው ጥፋት ካጠፋችሁ ወይም ከጎዳችሁ በኋላ ሰውየውን ካልተበቀላችሁት ወይም ይቅርታ ካላስጠየቃችሁ በስተቀር እንደተሸነፋችሁ የሚሰማችሁ ከሆነ የአሸናፊነት ትርጉማችሁ ውጫዊ ነው ማለት ነው፡፡ ሰዎች ለጠፉት ጥፋት በሃላፊነት ሊጠየቁ እንደሚገባ ሳንክደው፣ ሰው ምንም አደረጋችሁ ምንም ሁኔታው ውስጣችሁን ሳይሰብረው መንገዳችሁን መቀጠል የለመዳችሁ ጊዜ ድል ውስጣዊ የመሆኑን ልምምድ ታረጋግጣላችሁ፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ሁኔታዎች አልሳካ ሲሉ የመሸነፍ፣ ሲሳኩ ደግሞ የማሸነፍ ስሜት የሚፈራረቁባችሁ ከሆነ የድልና የአሸናፊነት ጉዳይ ውጫዊ እንደሆነባችሁ አመልካች ነው፡፡ ለስኬት የመስራታችሁ ልምምድ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ሁኔታዎች ቢሳኩም፣ ባይሳኩም በራሳችሁ ላይ ያላችሁ አመለካከት ሳይነካ ቀና ብላችሁ ወደፊት መገስገስን ካላቆማችሁ ድልን ውስጣዊ የማድረግን ስኬታማነት ተጎናጽፋችኋል ማለት ነው፡፡

የአሸናፊነት ስሜት እንዲሰማችሁ የውጪ ሁኔታችሁ እስከሚለወጥ አትጠብቁ! ድልን ውስጣዊ አድርጉት፡፡ አለዚያ እንደ ውጫዊ ሁኔታችሁ የሚለዋወጥ ስሜትና ጉዞ ውስጥ ራሳችሁን ታገኙታላችሁ፡፡

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣2⃣8⃣

#ሙሉ_ጤንነት_ከፈለጋችሁ . . .

#1_ለመንፈሳዊ_ጤንነት - ፈጣሪን ፍሩ! በየእለቱ ጸሎት አድርጉ!

#2_ለአካላዊ_ጤንነት - ወደሰውነታችሁ ስለምታስገቡት ነገር ተጠንቀቁ! የአካል ብቃት እንቅስቃሴን አድርጉ!

#3_ለማሕበራዊ_ጤንነት - ራስ-ተኮር አትሁኑ! ትክክለኛ የተግባቦት ክህሎትን አዳብሩ!

#4_ለስነ_ልቦና_ጤንነት - #ራሳችሁን_ተቀበሉ! #ራሳችሁን_ከሌላው_ሰው_ጋር_አታነጻጽሩ!

#5_ለስሜት_ጤንነት - የምታሰላስሉትን ሃሳብ በቁጥጥር ስር አውሉ! ትክክለኛውን ስሜት በትክክለኛው ጊዜ፣ ቦታና መጠን መግለጽን ተማሩ!

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ-ማስታወሻ #2⃣2⃣6⃣
ብቁ ናችሁ!

ከሕይወት ትልልቅ የፍርሃት ምንጮች አንዱ “ብቁ ያለመሆን” ፍርሃት ነው፡፡ በሰዎች ለመወደድ፣ ለመፈቀር፣ ተቀባይነት ለማግኘት፣ ለማወቅ፣ ለመሰልጠን፣ እድገት ለማግኘት . . .ብቁ እንዳልሆንን የማሰብ ፍርሃት!

እውነት እውነቱን እንነጋገር፡፡ አንድ ሰው እናንተን ለመቀበልና ለመውደድ የማይችል ወይም የማይፈልግ ከሆነ፣ ይህ ማለት እናንተ የዚያ ሰው አይደላችሁም ማለት ነው - አለቀ! ይህ ማለት ግን እናንተ ተቀባይነት የማግኘትና የመወደድ ብቃቱና ማንነቱ የላችሁም ማለት አይደለም፡፡

እናንተን የመውደድም ሆነ የመቀበል ብቃቱና ፍላጎቱ ያለው ብዙ ሰው በዙሪያችሁ እንዳለ አስታውሱ፡፡ እነሱን ለማየትና ለመገናኘት ግን “ካልተቀበለኝና ከልወደደኝ” ብላችሁ ችክ ካላችሁት ሰው ላይ አይናችሁን ማንሳት፣ ስሜታችሁንም ማላቀቅ የግድ ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ለጊዜው ከባድ ነው፣ ነገር ግን በሚልየን የሚቆጠሩ ሰዎች ችለውታልና እናንተም ትችላላችሁ!

አንድ ነገር አልሆን ሲላችሁ ሁል ጊዜ እናንተ ለዚያ ነገር ብቁ ስላልሆናችሁ እንደሆነ የማሰብን የእሳቤ ንድፍ መቀየር አለባችሁ፡፡ በዚያ ምትክ ያ ሰውም ሆነ ሁኔታ ለእናንተ የማይመጥን ስለሆነ እንደቀረላችሁ ማሰብም አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜም እንዳለ አትዘንጉ።

በአጭሩ፣ ለመወደድ ብቁ ናችሁ! ለማደግ ብቁ ናችሁ! ለማወቅ ብቁ ናችሁ! በዚህ ዓለም ፈጣሪ ለሰው ልጆች ደስታና ስኬት ለፈጠረው መልካም ነገር ሁሉ ብቁ ናችሁ! ሕይወት ትክክለኛውን ሰውና ስፍራ ገልጣ እስከምታቀርብላችሁ ድረስ ግን ራሳችሁን በመቀበል የድርሻችሁን መወጣት የግድ ነው።

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

በሂወቴ አንድም ቀን
- ፊቱ ጭፍግግ  ኮስተር የሚል  ፣ ያልገባውን አልገባኝም ፣ትክክል ካልመሰልኩት ትክክል አይደለህም እያለ የሚሞግት እና የሚገስፀኝ ሙሉ ስሜን ካለይሉኝታ  ሳያቆላምጥ የሚጠራኝ ሰው ፥ ኑሮዬን አክብዶት አያቅም  ።

ሳስቀይመው እንደተቀየመ የሚያሳየኝ ፤ ቅር ያለውን የሚያንፀባርቅ። አወዳዱ እኔ ጋ ከሚያገኘው ጥቅም ጋ ብቻ የማያጣብቅ  ሰው ልብ ውስጥ ፍስስ የሚል በቀላሉ የማይቆም ሃዘን አፍልቆብኝ የሚያቅበትን ግዜ አላስታውስም ።

#ይልቁንስ

ቅልስልስ የሚሉ ። የሚያገኙት ጥቅም ያለ ከመሰላቸው የሚንሿከኩ ፣  እንደ ውሃ በተቀመጡበት ቦታ ቅርፅ የሚቀያየሩ ።

ከፊት እና ከጀርባ አቋም የሚቀያየሩ ። ፊት ለፊት ባልወደዱት ባልገባቸው ጉዳይ የማይወያዩ ልምጥምጥ ግለሰቦች እሾሃቸው የቱ ጋ እንዳለ ስለማይታይ የምድርን ቆይታ ከሆነው በላይ ብርቱ ሰልፍ ያደርጉታል ።

የሆነው ሆኖ

#ቅልስልስ_ልምጥምጥ_አስመሳይ_ሰዎች_ዘግይተው_ሲጠሉ #ኮስተር_ክችች_ግትር_የሚሉት_እውነተኛ_ሰዎች_ዘግይተው_ይወደዳሉ

የሆነው ሆኖ

እኔ እና ልቤ ግን በዙርያችን የተኮለኮሉ ውብ ነብሶች ላይ እንመሰጣለን

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

የበደለህን ይቅር በለው ጤና ይሰጥሃል።
የተበላሸብህ ነገር ደግመህ ሞክረው- ጥንካሬን ስለምታገኝ።
ደስተኛ ለመሆን ቻል መከፋት ሲረዝም በብዙ ስለሚያሳጣ።
ፈጣሪህን አመስግን- የተሻለ ስለምታገኝ።
ካንተ የባሰበትን ተመልከት መጽጽናናት ስለሚሆንልህ።
ካንተ የተሻለውን አስተውል- ተስፋ ስለሚጎበኝህ።
ስለገጠመኝህ ሰዎችን አማክር- መፍትሄ ስለሚሰጡህ።
ጸልይ፣ ለብቻህ ተደብቀህ አልቅስ- ለእፎይታህ።

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #2⃣2⃣4⃣

#ጣፋጩ ወይስ #ጤናማው

ሕይወት ሁልጊዜ ከባባድ ምርጫዎችን ፊታችን በማስቀመጥ የምትታወቅ ሂደት ነች።የምንመርጠው ምርጫ ደግሞ አቅጣጫችንን የመወሰን ጉልበት አለው። ከእነዚህ ምርጫዎች አንዱ
#በጣፋጩና #በጤናማው መካከል የምታስቀምጥልን #ምርጫ ነው፡፡

አስባችሁት ከሆነ አብዛኛዎቹ ጣፋጭ ነገሮች ጤናማ አይደሉም።ለጊዜው ስለሚጣፍጡን ግን እንለምዳቸዋለን፣ እንደጋግማቸዋለን።በተቃራኒው አብዛኛዎቹ ጣፋጭ ያልሆኑ ነገሮች ጤናማ ናቸው።ለጊዜው ስለማይጣፍጡን ግን አንፈልጋቸውም፡፡ 

ለምሳሌ፣ የሚጣፍጠው ምግቡ፣ መጠጡና የመሳሰሉት ወደ ሰውነታችን ለማስገባት የምንጓጓላቸው ምርጫዎች ብዙ ናቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች ማቆም የማያስመኙ “ጣፋጭ” ነገሮች ናቸው።እነዚህን መቀማመስ ደስ ይላል፣ ይጣፍጣልም ነገር ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል።በሌላ በኩል ደግሞ ብዙም የማያይጥሙና አንዳንዴም ኮምጠጥ ያሉ ነገሮችን የመውሰድ ምርጫ አለን።ይህኛው ምርጫ ብዙም ባይጥምም ለጤንነታችን ግን ወሳኝ ነው።

በማሕበራዊ ግንኙነታችሁም አንጻር አስቡት።በአንድ ጎኑ ጊዜያዊ ደስታና እርካታ ብቻ የሚሰጣችሁ ግንኙነት አቅርቦቱ ብዙ ነው።ይህ ሁኔታ ቀላል ነው፣ ለስሜትም ይጣፍጣል።በሌላ ጎኑ ደግሞ ዘላቂና የወደፊት መስመር የሚዘረጋላችሁ አይነት ግንኙነት የመመስረት ምርጫ አላችሁ።ይህኛው ምርጫ ለጊዜው ያታግላል፣ መረርም ሊል ይችላል።በአስገራሚ ሁኔታ ግን ብዙዎች የሚጥማቸው ዘላቂ እቅድ ያለው ሳይሆን የአሁኑንና ጊዜያዊውን ስሜት የሚያረካላቸው ግንኙነት ነው።

#አስቡ! #ብልህ_ሁኑ! ዛሬ ጣፍጧችሁ ነገ መራራን ነገር ከሚያቀብላችሁ፣ ዛሬ ተመችቷችሁ ነገ ከሚቆረቁራችሁ ነገር #ተጠበቁ

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣2⃣2⃣

ስለስሜታችሁ ሳይሆን
#ስለተግባራችሁ!

ስለሚሰማችሁ ስሜት በፍጹም ተጠያቂነት ውስጥ ገብታችሁ እንደማታውቁ አትርሱት፡፡ ተጠያቂነት ውስጥ ራሳችሁን የምታገኙት ወደ እንቅስቃሴ በተለወጠው ተግባራችሁ ምክንያት ነው፡፡ ይህ መርህ በአዎንታዊ ስሜቶችና ተግባሮችም ሆነ በአሉታዊዎ ስሜቶችና ተግባሮች አንጻር እውን ነው፡፡

ለምሳሌ፣ በአንድ ሰው ላይ በውስጣችሁ ምንም አይነት ጤና-ቢስ ስሜት ቢኖራችሁም፣ በንግግር፣ በሁኔታም ሆነ በተግባር እስካልገለጣችት ድረስ በሃላፊነት አትጠየቁም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ለአንድ ሰው በውስጣችሁ ምንም አይነት ጤናማ ስሜት ቢኖራችሁም ያንን ስሜት በንግግር፣ በሁኔታም ሆነ በተግባር እስካልገለጣችሁት ድረስ ምንም መልካም ውጤት አይኖውም፡፡

ውጤታቸው ጥሩ የማይሆኑትን፣ አሉታዊና ለግንኙነት ቀውስ ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉትን ስሜቶች በትክክለኛው መንገድ የምታስተናግዱበትንና የምታስተነፍሱበትን ሁኔታ ማመቻቸት ሃላፊነቱ የእናንተ ነው፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ውጤታቸው መልካም፣ አዎንታዊና ላሏችሁ ግንኙነቶች ጠቃሚ መዋጮ የሚያደርጉ ስሜቶቻችሁን ለትክክለኛው ሰው፣ በትክክለኛው ጊዜና በትክክለኛው መንገድ የመግለጽ ልምምድን ስታዳብሩ ውጤቱን ማግኘታችሁ አይቀርም፡፡

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ


@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣2⃣1⃣

#በመጀመሪያ_ራሳችሁን_Like_እና_Follow_አድርጉ!

ዘመኑ የማሕበራዊ ገጽ ዘመን ነው፡፡ ይህ ክስተት ደግሞ Like የመደረግና Follow የመደረግ ልምምድን አስተዋውቆናል፡፡ ይህ Like እና Follow በሚዲያው ጎልቶ ወጣ እንጂ ቀድሞውኑ ውስጣችን ነበር፡፡

እንደ እውነቱ ከሆነ Like እና Follow መደረግ የማይፈልግ ሰው የለም፣ ያንንም መፈለግ ምንም ችግር የለበትም።ግን ቀውስ ውስጥ እንዳይጨምረን ሚዛናዊ ማድረግ ይጠይቃል።

በጥያቄ መልክ ሰላስቀምጠውና . . . 

ራሳችሁን Like ካላደረጋችሁ ሌላው ሰው እንዴት Like እንዲያደርጋችሁ ትመኛላችሁ? ራሳችሁን Follow ካላደረጋችሁ ሌላው ሰው Follow አንዲደርጋችሁስ ለምን ትጠብቃላችሁ?

#ራስን_Like_ማድረግ_ማለት ራስን (ሁለንተናን) በማወቅና በመቀበል መደላደል ማለት ነው፡፡ በመጀመሪያ በዚህ መልኩ ራሳችሁን Like ስታደርጉ ያን ጊዜ ብቻ ሌላው ሰው እናንተን Like በማድረጉ ያለውን ትክክለኛ ደስታ ታጣጥማላችሁ፡፡ ያን ጊዜ ብቻ ሰው Like ስላላረጋችሁ ድብርት ውስጥ ከመግባት ትጠበቃላችሁ፡፡

#ራስን_Follow_ማድረግ_ማለት ፈጣሪ የሰጠንን ራእይ በማወቅ የዓላማ ሰው መሆንና በዚያ አቅጣጫ ራሳችን ያወጣነውን እቅድ አምኖ መከተል ማለት ነው፡፡ በመጀመሪያ በዚህ መልኩ ራሳችሁን Follow ስታደርጉ ያን ጊዜ ብቻ ሌላው ሰው እናንተን Follow በማድረጉ ያለውን ትክክለኛ ደስታ ታጣጥማላችሁ፡፡ ያን ጊዜ ብቻ ሰው Follow ስላላረጋችሁ ድብርት ውስጥ ከመግባት ትጠበቃላችሁ፡፡

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣2⃣0⃣

#አንዳንዴ_አረፍ_በሉ!

በፈለጓችሁ ጊዜ ሁሉ ጊዜያችሁን፣ በቸገራቸው ጊዜ ሁሉ ገንዘባችሁን፣ ስሜታቸው ወረድ ባለ ጊዜ ሁሉ ትኩረታችሁን፣ ባጠፏችሁ ጊዜ ሁሉ ይቅርታችሁን፣ ባስቸገሩ ጊዜ ሁሉ ትእግስታችሁን . . . ካለምንም መከልከል የምታፈሱላቸው ሰዎች ያንን ባደረጋችሁ መጠን የማይገነዘቧችሁ ከሆነ፣ ከምንም የማይቆጥሩት ከሆነ፣ ግዴታችሁ እንደሆነ የሚያስቡ ከሆነ፣ ሆን ብለው የሚጎዷችሁ ከሆነና እነዚህ መሰል ግድ-የለሽ ስሜቶች የሚሳዩ ከሆነ ያንን ሁሉ ታግሳችሁ ተጨማሪ አመታቶችን መቆየት ከቻላችሁ ግፉበት፣
#ፈጣሪም_ጸጋውን_ይስጣችሁ፡፡

ምናልባት ግን አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ሰዎች ትምህርትን የሚያገኙት እናንተ ወጥራችሁ የያዛችሁትን ለእነሱና ለእነሱ ብቻ የመኖር የውዴታ ግዴታችሁን ለቀቅ አድርጋችሁ ለራሳችሁ ጤንነት ለመስራት አረፍ ስትሉ እንሆነ ላስታውሳችሁ፡፡
#አንዳንድ_ሰዎች_የሚማሩት_እናንተ_ለእነሱና_ለእነሱ_ብቻ_ከመኖር_ትንሽ_አረፍ_ስትሉ_ብቻ_ነው፡፡

በቃ እንደዛ ነው!

መልካም ቀን
ውብኛ ዋል

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣8⃣

ለመልቀቅ ተዘጋጁ!

በእጃችሁ ያሉትን መልካም የሆኑ የፈጣሪ ስጦታዎች በሙሉ ተመልከቷቸውና ፣ እነዚህ ውብ የሆኑ ስጦታዎች የእናንተ በመሆናቸው
#ምን_ያህል_ደስተኞች_እንደሆናችሁ_አስቡት፡፡ እግረ-መንገዳችሁን እነዚህ ውብ ነገሮች ምን ያህል #እንደምትንከባከቧቸውና_በጥንቃቄ_እንደምትይዟቸውም_አስቡ፡፡ 

ጥሩ ፍቅረኛ፣ መልካም ቤተሰብ፣ ጤንነት፣ ገንዘብ . . . እና የመሳሰሉት በእጃችን የሚገኙ የፈጣሪ በረከቶች በቅጡ ካልተያዙ ፈጠነም ዘገየም ከእጃችን ይወሰዳሉ፡፡ ይህ ጉዳይ ጊዜ ሊሰጠው የማይገባና አሁኑኑ ታስቦበት የማስተካከያ እርምጃ ሊወስድበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

እነዚህንና መሰል መልካም ስጦታዎች በሚገባ ካልያዛችኋቸው መቼ ከእናንተ ሊሄዱ ወይም ሊወሰዱ እንደሚችሉ አታውቁምና ለመልቀቅ ተዘጋጁ፡፡ ለመልቀቅ ዝግጁ እንዳልሆናችሁ ከተሰማችሁ ግን
#አያያዛችሁን_የማስተካከል_ጉዞን_ዛሬውኑ_ጀምሩ፡፡

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

El Houb - The Love (2022)
Original title: El Houb

👨🏼‍🤝‍👨🏻
#ElHoubTheLove 👨🏼‍🤝‍👨🏻

✏️Sub: English
🌏 Country: Netherlands
📝 Language:
#Arabic #English #Dutch
🌟 Score: 7.0/10
🎭 Genre: Drama
🎬 1h 42min

✨ Storyline: Moroccan-Dutch Karim returns to his family home and opens up to his parents about being into men. Their reaction inspires a journey of discovery through Karim's isolation as he attempts to break an ingrained culture of silence.

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

👇🏽👇🏽👇🏽

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

ህግ ፀረ ፍቅር ነው !

#በጣም_ህጋዊ_ከሆንክ_አንድ_ሰው_ማፍቀር_አትችልም። ምክንያቱም የፍቅር ዋናው ብቃት ድንገታዊነት ነውና።

#ፍቅር የሚመጣው በድንገት ነው።
#ፍቅር በድንገትም ሊጠፋ ይችላል።
#ፍቅር ምክንያት፤ምንም መመርያ የለውም #ፍቅር እንደ ታዓምር ነው የሚከሰተው።
#ፍቅር ምትሃታዊ ነው፣ፍቅር ስለምን እንዴት? እንደሚከሰት ማንም አያውቅም።


#ፍቅር ፀረ-ህግ ነው፣#ፍቅር ፀረ-ስበት ነው፣ #ፍቅር ፀረ-ሳይንስ ነው፣ #ፍቅር ከሁሉም ሎጂክ እና ህግ በተቃርኖ ውስጥ ነው።
-------------------
ኦሾ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣5⃣

#የፍቅር_ቋንቋዎች_መለማመድ #ክፍል_ሶስት

3፡- ስጦታን መቀበል
ስጦታ ማለት በእጆችህ በመያዝ “ይህ ሰው እኮ እኔን ስለሚያስበኝ ይህንን ስጦታ ሰጠኝ” የምንለው ነገር ነው፡፡ ለአንድ ሰው እኮ ስጦታን ለመስጠት ስለዚያ ሰው ማሰብ አለብህ፡፡ ስጦታው ትልቅም ሆነ ትንሽ ሰውየው እንዳሰበን አመልካች ነው፡፡

ዛሬ ለፍቅር አጋራችህ አንድን የፍቅር ስጦታ በመስጠት እሱ ለእናንተ ምን ያህል ልዩ እንደሆነ ለማሳየት ሞክር፡፡ በተጨማሪም ልደታቸውን፣ በዓላትንና የጋብቻ ቀናችሁን በማስታወስ ስጦታን በመስጠት ፍቅራችሁን ለመግለጽ  ሞክሩ፡፡ 

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣1⃣4⃣

#የፍቅር_ቋንቋዎች_መለማመድ #ክፍል_ሁለት

#ጥራት_ያለው_ጊዜን_ማሳለፍ


ጥራት ያለው ጊዜን ማሳለፍ (Quality Time)፡፡ ጥራት ያለው ጊዜ ማለት ለአጋራችን ያልተከፋፈለ ትኩረትንህን መስጠት ማለት ነው፡፡ ዛሬ በቀን ውስጥ ከፍቅረኛችሁ ጋር ምን ያህል ጊዜን እንደምታሳልፉና የእነዚህ ጊዜያችሁ ጥራት ምን ያህል እንደሆነ በማሰብ ጀምሩ፡፡

ቀናቸውንና ውሏቸውን እንዲናገሩ በመፍቀድ ሙሉ ትኩረት መስጠትን፣ ስልክንና ሌሎች ሚዲያዎች በመዝጋት ከእነሱ ጋር ብቻ መሆንንና የመሳሰሉትን ልምምዶች ተግባራዊ ለማድረግ ሞክሩ፡፡

ፍቅራችሁ የበረከት ይሁንላችሁ!

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟

እንኳን በጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ
2016ኛ አመት የልደት በአል በሰላም በጤና አደረሳችሁ
ወንድሞች

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟


@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…
Подписаться на канал