habeshagay1 | Для взрослых

Telegram-канал habeshagay1 - ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

791

Подписаться на канал

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

አንዳንዴ useless እንደሆንን ሊሰማን ይችላል፤

🌈አንዳንዴ ሰዎች እንዲረዱን ፈልገን አልተረዱን ይሆናል፤

🌈አንዳንዴ ምክንያቱንም ሳናውቀው በምንወዳቸው ሰዎች ፊት ላይ ጥላቻ ተስሎ አይተን ይሆናል፤

🌈አንዳንዴ ለሰዎች ከሰጠነው አክብሮት በተቃራኒ ንቀት ተቀብለን ይሆናል፤

🌈አንዳንዴ እድሜያችንን ሙሉ ስንመኘው የነበረና ትልቅ የመሠለን ነገር ስናገኘው ትንሽ ሆኖብን ይሆናል፤

🌈አንዳንዴ ለሰዎች መድረስ ፈልገን ሁኔታ፣ ጊዜና አቅም አጥተን መድረስ አልቻልን ይሆናል፤

🌈አንዳንዴ አንደመልአክ የምናያቸውን ሰዎች በህይወት አጥተን ይሆናል፤

🌈አንዳንዴ ለቤተሰቦቻችን ልንፈጥርላቸው እንፈልግ የነበረውን ዓለም ቀርቶ ትንሽ እንኳን ልንደግፋቸው አለመቻላችን አሳዝኖን ይሆናል፤

🌈አንዳንዴ ሁሉም ነገር ትርጉም አጥቶብን ይሆናል፤

🌈አንዳንዴ ሁሉም ቀን አሰልቺ፣ በድብርት የተሞላ እና ተመሳሳይ ሆኖብን ይሆናል፤

🌈አንዳንዴ ከዛሬ የበለጠ ነገ ጨለማ ሆኖ ታይቶንም ሊሆን ይችላል፤

🌈አንዳንዴ ሁሉም ነገር መኖር ራሱ ሳይቀር ከብዶን ይሆናል፤

አንዳንዴ ...

አንዳንዴ...

አንዳንዴ...

✅ግን It's okay to feel bored, sad, useless, and hopeless at times.. 

live

Lough

Love

ከሁሉም በላይ የተሻለ ጊዜ ከፊት አለ። 🧑‍🤝‍🧑

በውስጣችን ያለውን ክፋት በውስጣችን ባለው መልካምነት የምናሸንፍበት የተዋበ ቀን ይሁንልን።

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 1⃣9⃣9⃣

#ዓለም_እኮ_ሰፊ_ነች!

ዓለም እናንተ ስታጠቧት ትጠባለች፣ ሰፊነቷን ስትቀበሉና ስታዩላት ደግሞ በስፋቷ ልክ ታስተናግዳችኋለች፡፡

ቀና በሉ! ከሰፈራችሁ ውጪ ሌላ ሰፈር አለ! ከቡድናችሁ ውጪ ሌላ ቡድን አለ! ከመስሪያ ቤታችሁ ውጪ ሌላ መስሪያ ቤት አለ! በአካባቢች ካሉት ሰዎች ውጪም ሌሎች ሰዎች አሉ! አሁን ካላችሁ የገቢ ምንጭ ውጪ ሌላ የገቢ ምንጭ አለ!

#ከፈጣሪ_የተሰጣችሁን_ሰፊ_ዓለማችሁን_አታጥብቧት፡፡ ምርጫችሁ አንድና አንድ ብቻ እንደሆነ ስታስቡና በዚያ ዙሪያ ብቻ ስትሽከረከሩ ዓለማችሁ እሱ ብቻ እስከሚመስል ድረስ ትጠባላችሁ፡፡

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷



#የማለዳ_ማስታወሻ # 1⃣9⃣9⃣
#መስመር_ማበጀት_አለመቻል

ከዚህ በፊት በሚወዳቸውና በአፈቀራቸው ሠዎች ከተከሰተበት የመገፋት ቁስል ያልተላቀቀ ሰው ፥ ወደፊት በሚኖረው የፍቅር ግንኙነቶች ውስጥ ለፍቅረኛው ገደብና መስመር ማበጀት ያስቸግረዋል፡፡


እንደማንኛውም ሰው ወደሕይወቱ ለሚመጣ ሰው ሊያስቀምጥ የሚገባውን ተቀባይነት ያለውንና የሌለውን ነገር ከማስመር ይልቅ ሰዎች እንደፈለጉ እንዲቆጣጠሩት ይፈቅዳል፡፡ ለአንዳንድ ተቀባይነት ለሌላቸው ጥያቄዎች እምቢ ካለና ትክክል ላልሆኑ ነገሮች እርማት ከሰጠ ሰዎቹ ጥለውኝ ይሄዳሉ ብሎ ስለሚሰጋ ለሁሉም ነገር እሺ በማለት የቁጥጥር ሰለባ ሊሆን ይችላል፡፡

ከእንደዚ አይነት መልካም መሳይ ጎጂ ጥቃት ከመጋለጥ ተቆጠቡ። የማይሆነውን አይሆንም ፤ ልክ ያልሆነውንም ልክ አይደለም ማለትን እንለማመድ

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 1⃣9⃣8⃣

#ሕይወታችሁ_በከንቱ_እያለፈ_እንደሆነ_ለምታስቡ...

አንድ ሰው በሕይወት ዘመኑ በአማካኝ 10 ሺ ሰዎች ላይ ተጽእኖ ያመጣል ይባላል፡፡ ይህ ተጽእኖ ለክፉውም ሆነ ለደጉ የሚሰራ ሂደት ነው፡፡

በሕይወታችሁ ቢያንስ የአንድ ሰውን ሕይወት ተጨብጭ በሆነ ሁኔታ የሚለውጥ ተግባር ካከናወናችሁና ፥ ግባችሁን ከመታችሁ ሕይወታችሁ በከንቱ እንዳላለፈ ላስታውሳችሁ!!!

አንድን ሰው ስትለውጡ፣ የአሁኑን ወይም የወደፊቱን እጩ የፍቅር አጋር፣ ጓደኞች ፣ ወዳጆችና በዚያ ሰው ተጽእኖ ስር የሚወድቁ ሰዎችን ሁሉ ሕይወት ትነካላችሁ፡፡ ከዚህ ስሌት የተነሳ ነው ቢያንስ ከ10 ሺ ያላነሰ ሰው ላይ መልካም ተጽእኖ የምታመጡት፡፡

ዘንግታችሁት ነው እንጂ፣
#መልካም_ተጽእኖ_የማምጣት_ብቃት_ያላችሁ_ሰዎች_ናችሁ!

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ


@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

ስራ ቀጣሪዎች "Portfolio ላኩ" ሲሉ ሰምታችሁ ይሆናል። ለመሆኑ Portfolio ምንድን ነው? እንዴጽ ማዘጋጀት ይቻላል?

Portfolio ማለት የአንድ ባለሙያ በተለይም ደሞ ጥበባዊ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን ችሎታና ልምድ ለማሳየት የሚጠቅም ገፅ ነው።

በብዛት Portfolio በመጠቀም ስራና ችሎታን በደንብ ማስተዋወቅ የሚችሉ ባለሙያዎች እነዚህ ሊሆኑ ይችላሉ።
1. አርክቴክቶች
2. ግራፊክስ ዲዛይነሮች
3. ፎቶግራፈሮች
4. የማስታወቂያ ባለሙያዎች
5. ዌብሳይት ዲቨሎፐሮች እና ሌሎችም ይጠቀሳሉ።

Portfolio ለማዘጋጀት እነዚህን ዌብሳይቶች መጠቀም ትችላላችሁ።

1. Behance
2. Wix
3. Weebly
4. WordPress
5. Crevado

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

እሁድን በጋራ😘😘😘😘

🌟🌟🌟🌟🌟

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 1⃣9⃣6⃣

#በራሳችሁ_ላይ_አትጨክኑ

....በዓለም ላይ ልትሰጡት ከምትችሉት የጭካኔ ፍርድና ከስ የላቀው እናንተው በራሳችሁ ላይ የምታመጡት ፍርድና ክስ ነው፡፡

የየእለት ድካማችሁን፣ ስህተታችሁን፣ ትግላችሁንና የመሳሰሉትን ነገሮቻችሁን ማንም ሰው ከሚያውቃችሁ በላይ ራሳችሁን ስምታውቁት ራሳችሁን ለመኮነንና በራሳችሁ ላይ የተዛባ አመለካከትን ለመያዝ ቅርብ ናችሁ፡፡ ስለዚህ በራሳችሁ ላይ የምታስቡት ሃሳብም ሆነ ለራሳችሁ የምትሰጡት ፍርድ
#በሚዛናዊነት ሊያዝ ይገባዋል፡፡

ያላችሁን የራስ-በራስ ግምገማና ትችት በፍጹም ችላ ልትሉት አይገባም፡፡ ነገር ግን በሚዛናዊነት ተገቢውን እየለያችሁ ራስን ለመለወጥ መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡

❌‼️ራሳችሁን እስከመኮነን ድረስ በራሳችሁ ላይ አትጨክኑ፡፡

❌‼️በራሳችሁ ላይ ያላችሁ አመለካከት እስከሚወርድ ድረስ በራሳችሁ ላይ አትፍረዱ፡፡

❌‼️ሌላ ውሳኔ ለመወሰን ያላችሁ ድፍረት እስከምታጡ ድረስ ባለፈው ውሳኔያችሁ ስህተት ራሳችሁ አትደብድቡ፡፡

#ስህተታችሁን_እወቁ#አርሙ
#ደግማችሁ_ላለመስራት_ወስኑ፡፡

ከዚያም ቀና ብላችሁ በአዲስ መንፈስ ወደፊት!😘😘

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

Rustin ሙሉ ፊልም
አነስ ባለ MB

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

ብዙዎቻችን የማርቲን ሉተርኪንግን "I have a dream"የሚለውን ደማቅ ንግግርን እናስታውሳለን። ትልቅ ጭቆና በደልን ለመቃወም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተሰበሰቡበት የታናገረው ታሪካዊ ንግግር ነው። እስከዛሬ ድረስም የንግግሩ ተፅእኖ ጎልቶ ይታያል።


ከሰልፉም ሆነ ከታሪካዊ ንግግሩ ጀርባ ግን ስላለው ታላቅ ሠው ብዙም አልሰማንም....🤔🤔

Bayard Rustin ይባላል። የማሕበረሰብ አንቂና ተሟጋች የነበረ ታላቅ ሠው ነው። በቀለም "በማንነት" በስብእናቸው ምክንያት በደል ለሚደርስባቸው ሠዎች ዘብ የሚቆም ሠው ነበረ Rustin ።

በ 1940ዎቹ ዜጋ መሆን በደል በነበረበት ጊዜ የ LGBTQ+ Community አባል የነበረው ይሕ ሠው ፤ ያለበትን ጫና ተቋቁሞ የላቀ ትግልን አሳይቷል።
#ዛሬ_ማታ_2:30 ላይ የምንጋብዛችሁም ፊልም በርሱ ሕይወት ላይ የተሰራን ቆንጆ ፊልም ነው።
ተጋበዙልን።

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

የማለዳ -ማስታወሻ # 1⃣9⃣6⃣

ሰዎች በእናንተ ላይ የሚያንጸባርቁት ባህሪይ የእናንተን ሁኔታ ከማንጸባረቁ ይልቅ የሚያሳየው የእነሱኑ ሁኔታ ነው፡፡ ይህንን እውነታ በሚገባ መገንዘብ በሄድንበት ሁሉ ሰዎች የሚሰጡንን መስተግዶና የሚሳዩንን ባህሪይ እየተከታተልን ከመደናበር ይጠብቀናል፡፡

በሄዳችሁበት ቦታ ሁሉ ሰዎች የሚያሳዩአችሁን አጉል ባህሪይ እያያችሁ ሁኔታው የእናንተን ማንነት መተርጎሚያ ከማድረግ ልቦናችሁን ጠብቁ፡፡

ጥቂት የመንደርደሪያ ሀሳቦች . . .

ሰዎች ከጠሏችሁ የግድ የምታስጠሉ ሰዎች ስለሆናችሁ ነው ማለት አይደለም፡፡ ሰዎቹ በጥላቻ የተሞሉ አይነት ሰዎች ስለሆኑም ሊሆን ይችላል፡፡

ሰዎች ከናቋችሁ የግድ መናቅ የሚገባችሁ አይነት ሰዎች ስለሆናችሁ ነው ማለት አይደለም፣ ሰዎቹ ሰውን የመናቅ ችግር ስላለባቸው ሊሆን ይችላል፡፡

ሰዎች ካገለሏችሁ የግድ እንድትገለሉ የሚያደርጋችሁ ማንነት ስላላችሁ ነው ማለት አይደለም፣ ሰዎቹ ሰውን በተለያየ ምክንያት ማግለል የለመደ ባህሪይ ስላለባቸው ሊሆን ይችላል፡፡

በአጭሩ ሰዎች ለእናንተ የሚያሳዩትን ባህሪ በመመልከት ብቻ ከዚያ አንጻር ለማንነታችሁ ትርጉምና ፍቺ ከመስጠት ተቆጠቡ፡፡ በዚያ ምትክ ማሕበራዊ ግንኙነታችሁን ሊያዛባ የሚችል አጉል ባህሪይ ካለባች እሱ ላይ ካለማቋረጥ በመስራት የሰዎችን የግል አመለካከትና አጉል በህሪይ ለራሳቸው ተውላቸው፡፡

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

ድንቡሼ.....😂😂😘

🌟⭐️🌟⭐️🌟

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #1⃣9⃣5⃣

#በአንድ_ሁኔታ_ውስጥ_ስታልፉ!

ወንድሞች...አንድን የምታውቁትን ነገር እንደገና ላስታውሳችሁ፡፡

በአለም ላይ አሁን እናንተ በማለፍ ላይ ባላችሁበት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያለፉ፣ በማለፍ ላይ ያሉና ወደፊትም የሚያልፉ ሰዎች እልፍ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹን ይህ ተመሳሳይ ሁኔታ ሲቀብራቸው፣ ሌሎች ደግሞ በእርግጥም ያልፉታል፡፡

ለዚህ ልዩነት መነሻ የሚሆኑ ሌሎች ምክንያቶች ሊኖሩ የመቻላቸው እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በእነዚህ ሰዎች መካከል ያለው ዋና ልዩነት...

በዚያው ተውጠው የቀሩት ሰዎች ከሚያልፉበት ሁኔታ የተነሳ በመደናገጥ ወደፊት መገስገስን በመተው በመቆማቸው ምክንያት ሲሆን፣
እነዚያ ዘልቀው የሄዱትና በአሸናፊነት የወጡት ደግሞ በሚያልፉበት ሁኔታ ውስጥ በፍጹም ሳይቆሙ ወደፊት በመንቀሳቀሳቸው ምክንያት ነው፡፡

#በአንድ_ሁኔታ_ውስጥ_ስታልፉ_በእርግጥም_እለፉ_እንጂ_እንዳተቆሙ!

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

Иш тополмай юрганлар учун сирли канал топилди

/channel/+ufsA-9qEccNlNzRi

Коплаб йирик компаниялар элон берувчи ҳамма излаган канални топдик. Кўплаб маълумотлар, минглаб элонлар базаси интернетга чиқиб кетди.

Билиб олиш учун каналга уланинг:

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
/channel/+ufsA-9qEccNlNzRi

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

በመሳሳም ጊዜ ከአንዳችን ወደሌላችን የሚተላለፍ ጥርስን ከጥቅም ውጪ የሚያደርግ ባክቴሪያ እንዳለ ያቃሉ?????🤔🤔

በመሳሳም ጊዜ በሚኖር የምራቅ መለዋወጥ ምክንያት ከአንድ ሰው ወደሌላው የሚተላለፈው ይህ ባክቴርያ የሚያምር ፈገግታችን እስከነጭራሹ ለሚያጠፋ የጥርስ መቦርቦር ይዳርገናል።

#ሐላፊነታቸንን_እንወጣ
#ንፅሕናችንን_ጠብቀን_በነፃነት_እንደሰት

#now_u_know

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #1⃣9⃣2⃣

ሁል ጊዜ ትክክል እንደሆናችሁ የምታስቡ ከሆነ ከሕይወት የምትማሩት አንድም ትምህርት እንደማይኖር አትዘንጉ፡፡ መማር ስታቆሙ ደግሞ ማደግ ታቆማላችሁ፡፡

ለመማር ማድረግ ያለባችሁ ነገሮች . . .

↪️  የተግባራችሁ ውጤት የሚነግራችሁን አስተውሉ፣

↪️  ሰዎች የሚነግሯችሁን ነገር አድምጡ፣

↪️  አንብቡ፣

↪️  የሰዎችን የሕይወት ተሞክሮ አጢኑ፣

↪️  በየጊዜው ከተለመደው ስፍራ ዘወር በማለት የማሰላሰያ ጊዜ ይኑራችሁ፡፡

↪️  ከፈጣን ሃሳብ ሰጪነት ቆጠብ በሉ፣

↪️  ክርክርን አታብዙ፡፡   

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ


@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ # 2⃣0⃣0⃣

#በመጀመሪያ_ታከሙ

ካለፈው ስቃዩ ያልዳነ ሰው እድሜ ልኩን ሰዎችን እንዳሰቃየ ይኖራል፡፡ ለዚህ ነው በአንድ የስሜትና የስነ-ልቦና ህመም በሚዳርግ ልምምድ ውስጥ ካለፍን በኋላ ወደሌላ ግንኙት ዘልቀን ከማለፋችን በፊት ከመጀመሪያው ሕመም መዳናችንን እርግጠኞች መሆን ያለበን፡፡

አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ሲጎዱንና ሁለንተናችን ሲቃወስ ያንን ጉዳት ባለመልቀቃችን ሰዎቹን የምንበቀላቸውና የምንጎዳቸው ይመስለናል፡፡ እውነቱ ግን ከዚያ የራቀ ነው፡፡ በሰዎች ከደረሰብን የጉዳት ቀውስ መዳንና መውጣት የሚጠቅመው እኛንው ነው፡፡

የትናንትናውን ቁስሌን በተገቢው መልክ አክሜ ካልዳነ የዛሬውን ግንኙቴን ያዛባዋል፡፡ የዛሬው ግንኙነቴ መዛባት ደግሞ ለነገው ቁስል ይዞ ስለሚቆይ ዑደቱ እንደቀጠለ ይኖራል፡፡

በቅርብ ጓደኛ፣ በፍቅረኛ፣ በስራ አጋር፣ በአለቃ . . . ከተጎዳችሁ በኋላ ሌላ ተመሳሳይ ግንኙነት ውስጥ ዘልቃችሁ ከመግባታችሁ በፊ በመጀመሪያ ቁስላችሁን በሚገባ መታከማችሁን እርግጠኞች ሁኑ፡፡ ስፍራን መቀየርና ጓደኛን መለወጥ ያለው የራሱ የሆነ ጥቅም እንደተጠበቀ ሆኖ ዘላቂ መፍሄ ያለው ግን ከአንድ አቁሳይ ልምምድ በኋላ ሌላ ምንም አይነት የጠለቀ ግንኙነት ውስጥ ከመግባታችን በፊት ራሳችን ላይ መስራት ነው፡፡

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#ለጥንቃቄ_ቅድሚያ_እንስጥ
#ይነበብ

የአዲስ አበባ ፖሊስ አንድን ወጣት አግተው 10 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ።

አጋችና ታጋች የአንድ ወር ጓደኛሞች እንደነበሩም አሳውቋል።

የእገታ ወንጀል የተፈፀመበት ወጣት ልዑል መብራቱ ይባላል፡፡

ወጣቱ
#በማህበራዊ_መገናኛ_አውታር (ማህበራዊ ሚዲያ) አማካኝነት ባንቴ ይድረስን የተባለውን ግለሰብ ይተዋወቃል፡፡

ትውውቃቸው አንድ ወር ከሞላ በኋላ ባንቴ ይድረስ የተባለው ወንጀል ፈፃሚ የወንድሜ ጓደኛ ቤት ላሳይህ በማለት ወጣቱን ታህሳስ 2 ቀን 2016 ዓ/ም ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ቁሊቲ መንደር 4 አካባቢ ይዞት ከሄደ በኋላ ከግብረ አበሩ ልዑል ጫላ ጋር በመሆን  ያግቱታል፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎች እጅግ ዘግናኝ ፊልሞችን እና ፎቶግራፎችን ለወላጆቹ በመላክ 10 ሚሊዩን ብር ካልተከፈላቸው ወጣቱን እንደሚገድሉት የማስፈራሪያ መልእክት ይልካሉ፡፡

የእገታ ወንጀል እንደተፈፀመ ሪፖርት የደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ጋር ባደረጉት ክትትል ወንጀሉን በተፈፀመ በአራተኛው ቀን ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ወጣቱን ከእገታው ነፃ እንዳወጣው አሳውቋል።

ሁለቱ ግለሰቦች ወንጀሉን ለመፈፀም በ5ሺ ብር ቤት መከራየታቸውንና የታጋቹ ወጣት ወላጅ አባት ውጭ ሀገር ይኖራሉ በሚል መረጃ ወንጀሉን መፈፀማቸውን የፖሊስ መረጃ ያሳያል።

ፖሊስ  ፤ በልዩ ልዩ ምክንያት የምንቀርባቸው ግለሰቦች ማንነታቸውን ጊዜ ወስደን ማረጋገጥ አለብን ብሏል።

በተለይ ሙሉ ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች የተከራዮችን ማንነትና ለምን እንደተከራዩ ማረጋገጥ እንዳለባቸው አሳስቧል። ይህን ሳያደርጉ በሚፈጠር ችግር የህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ አስጠንቅቋል።

መረጃው ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተገኘ ነው።

© tikvahethiopia

#ስለምናገኛቸው_ሠዎች_እንጠንቀቅ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

መደበሬን ፣ ማሸነፌን ፣ ሽራፊ ስሜቶቼን.....ሲያሞግሱኝና እና ስተች የሚሰማኝን ጥንጥ ብናኝ ስሜት ሳይቀር ....ደግሞም ስደክም እና ስበረታ የሚሰማኝን ላንተ አይደል የምነግረው? ?

ከንፈሬ ሲደርቅ ፣ ስከሳ ፣ አለመመቸት ሲጣበቀኝ፣ ጫማዬ ሲቆሽሽ ቲሸርቴ ከሱሪዬ ጋ አራምባ እና ቆቦ በሆነ መንገድ አልሄድ ሲል .....ሳያምርብኝ ሲቀር  ፣ነገዬ የጨለመ ሲመስለኝ፣ ተስፋ ስቆርጥ በልብህ ውስጥ ያለሁትን እኔን ያሳየኸኝ እኔነቴን ስወደው❤❤❤ .... አሻግሬ የነጋ ነገን እመለከትበታለው😍

ስትኮራብኝ ....ስታምነኝ ...እርዳታ ሲያስፈልግህ በኔ ብቻ መታገዝ ስትፈልግ ፥ የወደድኩትን እንደምቶድልኝ ስታሳየኝ የሚሰማኝን ምቾት.....😘😘😘

ባትወለድ ህይወቴ ላይ የሚኖረው መጉደል አገዛዘፉ ተራራ ያህል ነበር !!

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#መች_ነው_ግን_ማገኘህ?

ቀልድህ ባያስቅም እንኳ አይንህን እያየው ፈገግ ስልልህ..በዝምታህ ውሰጥ እንደ እሳተ ጎመራ ቡልቅ ቡልቅ የሚለው ህመምህን ለማድመጥ ስጣጣር.. ኩራቴ ስሜቴን ስላሸነፈ አልነገርኩክም እንጂ ይሔ ሁሉ ናፍቆኛል...።

እኔን ለማሳቅ የባጥ የቆጡን ስትዘባርቅ..እኔ ደሞ እንደ ጉንዳን የደቀቀ መልሴን ስመልስልህ...ለቦጭህን ዘርግፈ ሌላ ቀልድ ስቀልድልኝ እንደ አዲስ ሌላ አለም ሌላ አፅናፍ እንደምትዘፍቀኝ አልነገርኩክም እንጂ የእውነት ናፍቆኛል ..ኩርፊያህ ሀዘንህ ሳቅህ ሁሉ ነገርህ ናቆኛል..።.

..አዎ ፍቅራችን የጋለ ምጣድ ላይ እንዳረፈ በረዶ ቀስ ቀስ ሲናድ ይታወቀኛል...አንተም ላትመልስ ከአይኔ ራዳር ሸሸህ..

እኔም መመለስህን በተስፋ ምጠብቅ ብኩን ፍጥረት እንድሆን ማን ነው የፈረደብን?።
ለዚ ተከሳሹ ማን ነው??
እኔ ወይስ አንተ....?


@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #1⃣9⃣7⃣

#እውነተኞቹን_ከአስመሳዮቹ_መለየት_ከፈለጋችሁ

ምናልባት በዙሪያችሁ ከሚገኙ ሰዎች መካከል እውነተኞቹንና አስመሳዮቹን ለመለየት ከፈለጋችሁ እናንተ ሁለት ነገር ማድረግ ይጠበቅባችኋል፡፡

❤  እውነተኛ ማንነታችሁን መኖር

አስመሳይ ማንነት አስመሳይ ሰዎችን ይስባል፤ እውተኛ ማንነት እውነተኛ ሰዎችን ይስባል፡፡ ይህ የማይለወጥ ማሕበራዊ ሕግ ነው፡፡ እውነተኛ ሆናችሁ ስትኖሩ፣ እውነትን ስትናገሩ፣ እውነታን ስትጋፈጡ . . . እውነተኞችና እውነት ወዳዶች ብቻ ወደ እናንት ይሳባሉ፣ ሌሎቹ ግን ስማይመቻቸው ይርቃሉ፡፡

❤❤  ትክክለኛ የሕይወት ዓላማችሁን መከተል

ያያችሁትን፣ የሰማችሁትንና ለጊዜው “ያበላል” ብላችሁ የምታስቡትን ነገሮች የምትከታተሉ አይነት ሰዎች ከሆናችሁ፣ ይህ የተዛባ ሂደት የተዛባ መርህና አመለካከት ያላቸውን አይነት ሰዎች ወደ እናንተ ይስባል፡፡

ሲጨመቅ፣ በዙሪያችን የሚመጡትንና የሚቆዩትን ሰዎች የሚወስኑ ሁለት ዋና ዋና ነገሮች ማንነታችን እና ዓላማችን ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት ነገሮች መስመር ሲይዙ “የወዳጆቻችን” ነገርም ከዚያው ጋር ይስተካከላል፡፡
የሕይወት ዘይቤያችሁ ወደ እናንተ የሚመጡትንና የሚቆዩትን ሰዎች የመወሰን ጉልበት አለው፡፡

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

ጨበጥ....ጨመቅቅቅቅ..😘😘

🌟⭐️🌟⭐️🌟⭐️🌟

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

Rustin ሙሉ ፊልም
ከፍ ባለ ጥራትና MB

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

የዛሬው የቅዳሜ ታላቅ ፊልም "RUSTIN " የሚለዉን  ቆንጆ ፊልም ነዉ። 🥰🥰🥰

🌟⭐️🌟⭐️🌟

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0
👇👇

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

ግትር ነው! ስንጣላ መታረቂያ ሽንቁር አያበጅም። ግትርነቱን የመርህ ሰው መሆኑን ማሳያ ይመስለዋል።ስለማመጠው የበለጠ ይደርቃል።ሰው እንዴት ከሚወደው ጋ በረባው ባረባው ይኮራረፋል ብዬ ስለማስብ ነው።እንዴት ሰው ልዩነቱን ተወያይቶ አይፈታም ብዬ ስለማስብ ነው።

በተጣላን ቁጥር ጥግ ለመያዝ ይንደረደራል።ኮስተር ካልኩኝ ፤ቅሬታዬን ፊቴ ላይ ካየ እንደመስታወት ያየውን ያንፀባርቃል እንጂ "ምን ሆነክ ነው?" ብሎ ችግሩን ለመፍታት አይሞክርም። ከልጅነቱ ይዞት የመጣ ያልበሰለ የአዕምሮ ክፍል አለው።እንዴት ሰው ለሚወደው ቢያንስ አይሸነፍም?

ተኝተን ሳለ እንኳን ተጣልተን ሳቅፈው እንደ እንጨት ይደርቃል ፤ማቀፌን ልምምጥ ብቻ ያደርገዋል፤ ስለማመጠው የጥፋተኝነት ስሜት ተሰምቶኝ ስለሚመስለው ይለጠጣል።

ልምምጤ እግሩ ላይ በመውደቅ እንዲጠናቀቅ ይጠብቃል ።ስለማመጠው እንደመለስለስ ጭራሽ  የድል አድራጊነት ስሜት ውስጡ ይርመሰመሳል።😡

ተጣልተን እንኳን በሰላሙ ግዜ እንደምጠራው ነው የምጠራው።ለእሱ ያለኝ ፍቅር ይሉኝታ ቢስ እንዳያደርገኝ ይከልለኛል።ተጣልተን መልዕክት በስልኩ ስልክለት መልእክቴ  ድ'ርቅ እንዳይል እጠነቀቃለሁ ።ፍቅራችን ለምናፈቅራቸው እንድንጠነቀቅ ካላደረገን ፍቅራችን የእውነት ላለመሆኑ ምስክር ነው።

ለትንሹም ለትልቁም ፀብ እንዴት ሰው ወደ ጥጉ ይንደረደራል።አኩራፊ እኮ የተሸናፊዎች ባህሪ ነው። በክብሬ አልደራደርም ይላል ። ስንት ቀን ፍትወት ሳይሰማኝ ስሜቱን ከስሜቴ እንዳስበለጥኩለት አይገባውም ።

አንዳንድ ቀን አጥፍቼ እንኳን ጉያው ውስጥ ከቶ ግንባሬን እየሳመ እንዲለማመጠኝ እፈልጋለሁ። በብስለቱ ተንጠልጥሎ ዱካኬን ከግንኙነታችን ጋ ባያስታከው ደስታዬ ነው።

ምን አለ የምንወደው ሰው የሚጎድለውን ነገር ፤ ከሚወዱን ሰዎች መልካም ነገር ላይ ወስደን መጫን ቢቻለን እላለሁ...

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

ብዙዎቻችን የማርቲን ሉተርኪንግን "I have a dream"የሚለውን ደማቅ ንግግርን እናስታውሳለን። ትልቅ ጭቆና በደልን ለመቃወም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተሰበሰቡበት የታናገረው ታሪካዊ ንግግር ነው። እስከዛሬ ድረስም የንግግሩ ተፅእኖ ጎልቶ ይታያል።


ከሰልፉም ሆነ ከታሪካዊ ንግግሩ ጀርባ ግን ስላለው ታላቅ ሠው ብዙም አልሰማንም....🤔🤔

Bayard Rustin ይባላል። የማሕበረሰብ አንቂና ተሟጋች የነበረ ታላቅ ሠው ነው። በቀለም "በማንነት" በስብእናቸው ምክንያት በደል ለሚደርስባቸው ሠዎች ዘብ የሚቆም ሠው ነበረ Rustin ።

በ 1940ዎቹ ዜጋ መሆን በደል በነበረበት ጊዜ የ LGBTQ+ Community አባል የነበረው ይሕ ሠው ፤ ያለበትን ጫና ተቋቁሞ የላቀ ትግልን አሳይቷል። ነገ የምንጋብዛችሁም ፊልም በርሱ ሕይወት ላይ የተሰራን ቆንጆ ፊልም ነው።
ተጋበዙልን።

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

ፉንግግ ያለ ፉንጋ ነበር። የጥርሶቹ ትልቀት፣ የአፍንጫው  አቀማመጥ፣ የፀጉሩ ግንባሩ ድረስ አመጣጥ፣ አጉጩን ሳይቀር አለማስተዋል አይቻልም  ... ተፈጥሮ እንዴት እንደጨከነችበት ሳየው ይገርመኛል ተቀራረብን... ከፉንጋነቱ ጎን ለጎን ጥሩ ያስባል አዛኝ ልብ አለው።

እይታው ጥሩ ነው ፣ ፣ ፉንጋነቱ አይታወቀውም ፣ የፊቱን አቀማመጥ እረስቶታል ....

ብዙ መደዋወል ያዝን .....ይሰማኛል፣ ይጠይቃል አሰማሙ እና አጠያየቁ እሱ ኑሮ ያለው አይመስልም ፤ ገጠመኝ የሚያገኘው አይመስለኝም።

በመስማት ብቻ ለካ መጉላት ይቻላል !!

ከአልአዛር  ጋር ተዋደድን ። አልአዛር ፉንጋነቱ ተረሳኝ ...አይደለም ውበቱ ታየኝ ። አልአዛር ቆንጆ ነው።  አንድ ቀን ከፍቶኝ ቤቱ ሄድኩ አልጋው ላይ ተኛን አስተቃቀፉ አለሁልሽ አለው ።

እንደ ታናሹ አቀፈኝ ።ምቾት ተሰማኝ ፤ እለት እለት ፍቅሬ ጠነከረ ።

ድንገት የሆነ ቀን "እንለያይ" አለኝ ....ሳኩኝ።  በርግጥ አንድ ሁለት ሳምንት ሙሉ ደብዝዞ እየራቀኝ ነበር። ከራሱ ጋር የተጣላ ነበር የመሰለኝ ።

ላለማስጨነቅ ነበር ምን ሆንክ ላለማለት የሞከርኩት

እሱ ፀቡ ከኔ ጋ ነበር መሰለኝ ...

ቀለል አድርጎ ነበር እንለያይ ያለኝ ።እኔ እና እሱ መሃል ጭቅጭቅ፣ መዋደድ ፣ መሳቅ እንጂ የመለያየት ፅንሰ ሃሳብ እንዳለ አላውቅም ነበር ። ደነገጥኩ !! ኖ
ፈራው።ኖ አዘንኩ መጠን አልባ ሃዘን ልቤ ውስጥ ተንከላወሰ።

መለመን፣ የሆነውን ማወቅ ፈልጌ ነበር፣ ሲያቅተኝ ጠረጴዛ ላይ አጎንብሼ ሳለቅስ ሰዎች ትኩረታቸው ወደ እኛ ሲሆን ፦

"ኧረ አንተ ልጅ  This is attention-grabbering አረጋጋው !

ሁኔታው ንግግሩ ከእንለያዩ የበለጠ ጎዳኝ ።ቀጥ ብዬ እያለቀስኩ ከፊቱ ከካፌው ከኑሮው ሄድኩኝ

አልተከተለኝም .....

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #1⃣9⃣4⃣

አመኔታ ለጥፋትና ለሞት ሊያጋልጣችሁ ይችላል፡- ሆኖም፣ ሰዎችን በጥንቃቄ ከማመን ውጪ መኖር ማለት ግን ከሞት ያልተናነሰ ሕይወት መሆኑን አትዘንጉ፡፡

ፍቅር ለጉዳትና ለስብራት አሳልፎ ሊሰጣችሁ ይችላል፡- ሆኖም፣ ፍቅርን እየፈለጋችሁ ከፍርሃት የተነሳ ትክክለኛውን ሰው ከማፍቀር ውጪ መኖር ማለት ግን ከሞት ያልተናነሰ ሕይወት መሆኑን አትዘንጉ፡፡

ለእውነት መቆም እንድትጠሉና እንድትገለሉ ሊያደርጋችሁ ይችላል፡- ሆኖም፣ በትክክለኛው ጊዜና ቦታ ለእውነት ከመቆም ውጪ መኖር ማለት ግን ከሞት ያልተናነሰ ሕይወት መሆኑን አትዘንጉ፡፡


መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

#የማለዳ_ማስታወሻ #1⃣9⃣3⃣

ከሰዎች ጋር ሰትኖሩ . . .

✅ ራሳችሁን ከሌሎች ሰዎች ጋር ማነጻጸርና መፎካከር ደስታችሁን የሰረቀባችሁ ቀንደኛው ሌባ እንደሆነ አትዘንጉ፡፡

✅ ሰዎች እውነቱን ስለነገሯችሁ የምትቀጧቸው ከሆነ ውሸትን እንደምታስተምሯቸው አትጠራጠሩ፡፡

✅ ሰዎች እንዲሁ የሚያጠቋችሁ እናንተን ስለተቃወሟችሁ ሳይሆን ራስ-ወዳድነት ስለተጠናወታቸው መሆኑን አስታውሱ፡፡

✅ ለደረሰባችሁ ቁስል ተጠያቂ እንዳልሆናችሁ ብታስቡም ለፈውሳችሁ ግን ሙሉ ለሙሉ ተጠያቂ መሆናችሁን አትርሱ፡፡

✅  ዛሬ እናንተ ጋር መጥተው ሌላውን ካሙላችሁ፣ ነገ ሌላ ሰው ጋር ሄደው እናንተን እንደሚያሙላችሁ እርግጠኛ ሁኑ፡፡ ...

መልካም ቀን
ውብኛ ዋሉ

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

ዘነዘና... ማነው ዘና ዘና በሉ...😂😂😂😘

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…

ለአበሻ ወንዶች ብቻ🇪🇹🇪🇷

አንዳንድ ሰው አለ ገና አይተኸው እስክትተዋወቀው እንቅልፍ የሚነሳህ

አወራሩ አኳኋኑ አስተያየቱ እንደው መቼ ተዋውቄው የሚያስብል።

አለ ደግሞ አንዳንዱ አይን ውስጥ የማይገባ፤ ትኩረት የማይስብ፤ አለባበሱ እንደነገሩ የሆነ አጋጣሚዎች ወስደው የሚያላትሙህ ከዛ የማትጠብቀውን ብስለት የምታይባቸው፤ ሩህሩህነታቸው ታይታ የሌለው፤ ሲወዱም ሲጠሉም ከልባቸው የሆነ ማስመሰል የማያውቁ

አሉ አንዳንድ ሰዎች እጣፈንታ ካላገናኘችህ ፈልገህ የማታገኛቸው።

@habeshagay1
/channel/+3SORTjt4Xew1YTQ0

Читать полностью…
Подписаться на канал