freenlmbookss | Неотсортированное

Telegram-канал freenlmbookss - ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

2013

“አምላክህ እግዚአብሔር መሐሪ አምላክ ነውና አይተውህም፥ አያጠፋህምም፥ ለአባቶችህም የማለላቸውን ቃል ኪዳኑን አይረሳም።” — ዘዳግም 4፥31

Подписаться на канал

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

በእግዚአብሔር ተፈቅረናል( መኃ 4 _1 - 16).m4a

የሰሎሞን መዝሙር ጥናት 5

ህዳር 25 /03 /2015

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

ሐጢአተኛ ሰው መንፈስ ቅዱስ አለው? አንተ ሐጢአተኛ ነህ ወይስ ጻድቅ ነህ? መልሰህን በዚህ አድርስልኝ። @dehnetbot

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

ዛሬ ከምሽቱ 1 ሰአት የትህምርት ጊዜ ይኖረናል። ለሌሎችም forward አድርጉላቸው።

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

በልቡ ውስጥ ሐጢያት ያለበት ሰው እንዴት መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ይደፍራል? መንፈስ ቅዱስን የሙጥኝ በማለት ብቻ በዚህ መንገድ እንደማይሰጥ መረዳት አለባችሁ፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ትዕዛዝ የሚመጣና የሚሄድ አይደለምና፡፡ የሐጢያቶቹን ስርየት ያልተቀበለ ማንኛውም ሰው ፈጽሞ መንፈስ ቅዱስን ሊቀበል አይችልም፡፡ ስለዚህ በልቡ ውስጥ ሐጢያት ያለበት ሰው መንፈስ ቅዱስን እንደተቀበለ ከተናገረና በልሳን መናገርንና ሌሎችን ከሕመሞቻቸው ለመፈወስ አስመስሎ መጸለይን የመሳሰሉ ሁሉንም ዓይነት ግርግሮችን ከፈጠረ የተቀበለው ነገር ክፉ መንፈስ እንጂ ቅዱስ መንፈስ እንዳልሆነ ምንም ዓይነት ጥርጣሬ ሊኖር አይችልም፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ንስሐ ግቡ፤ ሐጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ፡፡›› (የሐዋርያት ሥራ 2፡38) በሌላ አነጋገር መንፈስ ቅዱስ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ከሐጢያቶቻቸው ለነጹና በዚህም ልቦቻቸው ፈጽሞ ሐጢያት አልባ ለሆኑ ሰዎች የተሰጠ ነው፡፡ በመሰረቱ ሰው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ከሐጢያቶቹ ሁሉ እስካልነጻ ድረስ የእግዚአብሄርን መንፈስ ስጦታ ሊቀበል አይችልም፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሐጢያት ባለበት በማንኛውም ስፍራ መኖር የማይችል ራሱ ቅዱስ አምላክ ነው፡፡ ሰው የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ መቀበል የሚችለው ከሐጢያቶቹ ሁሉ ሲነጻ ብቻ የሆነው ለዚህ ነው፡፡
አሁን በሕግ ላይ የተመሰረተው ወንጌል በዚህ ክፉ ዘመን ውስጥ በክርስቲያን ማህበረሰቦች ውስጥ የገነነ ቢሆንም እኛ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የምናምን ሰዎች ግን ይህንን ወንጌል ፈጽሞ ልንታገሰው አይገባንም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ከዚህ ክፉ ዘመን ስላዳነኝ አብዝቼ አመሰግነዋለሁ፡፡ እኛ ሐሰተኛ በሆነና ግራ በሚያጋባ ልዩ ወንጌል ተታለን ነበር፡፡ ነገር ግን በውሃውና በመንፈሱ ወንገል በማመን የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ ተቀብለናል፡፡ የእግዚአብሄርንም ሥራ እየሰራንና እውነቱንና ጽድቁን እየተከተልን ነው፡፡
አጋር ምዕመናኖቼ እግዚአብሄር የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል የማስፋፋት ሥራ በአደራ ስለሰጣችሁ ደስተኞች ናችሁ? ወይስ ለእናንተ በአደራ የተሰጣችሁን ነገር ማከናወኑ በጣም አስቸጋሪ ሆኖ አግኝታችሁታል? የምንሰለችባቸው ወቅቶች ቢኖሩም እግዚአብሄር ስለሰጠን ደህንነትና በእርሱ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንድንኖር ስለፈቀደልን አሁንም እናመሰግነዋለን፡፡
እናንተና እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረሰ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ማመናችንንና ማወጃችንን እንቀጥልና በተስፋም በእግዚአብሄር ጸጋ እንኖር ዘንድ እጅግ ልባዊ ምኞቴ ነው፡፡

Rev Jong

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

በጌታ ከተወደዱ ማሃል ናችሁ?
(ስብከት 2)

የሰሎሞን መዝሙር ጥናት (ምዕራፍ 2:1-7)

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

ወንጌል ስለ ልጁ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚመሰክር
የምሥራች ነው፡፡ (ሮሜ 1:3-4) ይህም ኢየሱስ በውሃ
በደምና በመንፈስ መጣ፡፡ (1 ዮሐ፡5:6-9) ይኸው ኢየሱስ
ፅድቅን ሊፈፅም በዮሐንስ ተጠመቀ፡፡ (ማቴ፡3:13-17;ሉቃስ
3:21)

ይኸው ኢየሱስ ከመሠቀሉ በፊት የሰውን ዘር ሐጢአት በሙሉ ተሸከመ፡፡(ኢሳ፡53:6,11,12;2ቆሮ፡5:21;ሮሜ 8:3-4;1ጴጥ፡ 3:18 "በሐጢአት ምክንያት ሞቶአልና")
ይኸው ኢየሱስ በመስቀል ላይ ደሙን በማሰስ ሐጢአታችንን በሙሉአነፃ፡፡(ዕብ፡1:3;ሮሜ፡3:25ዕብ፡10:14-17;ገላ፡2:17-18)

የውሃውንና የመንፈሱ ወንጌል አንዳንዶች እንደመሰላቸው ልዩ ወንጌል ሳያሆን በውሃው በደሙና
በመንፈሱ የመጣውና አብ ለልጁ የመሠከረበት ወንጌል ነው፡፡
(1 ዮሐ፡5:6:10)

ተጨማሪ ማብራሪያ መጽሐፍ ለማግኘት የምትፈጉ inbox አድርጉ። @jonahnlm

#ደህንነት

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

እውነተኛ ሕይወት ማለት ኢየሱስ ሐጢአቶችህን በሙሉ ማስወገዱን ማመን ነው። የእግዚአብሔር ፍቅር ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ መረዳት ነው። እግዚአብሔር ለሰጠው ደህንነት ሁለም አመስጋኝ መሆን ነው።

@jonahnlm

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

ጌታን እያገለገልን ሳለን አንዳንድ ጊዜ ሰራሳችን ሰብአዊ መለኪያዎች ላይ ተመስርተን እንፎካከራለን ማን ከማን ይሻላል እያልንም እንከራከራለን በተጨባጭ ግን በመካከላችን ምንም ልዩነት እንደሌለ እናውቃለን ከመንፈሳዊ ምልከታ አንጻር በሁለት ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት ብዙ እንዳይደለ እናውቃለን አንድ ሰው ትልቅ ከሆነ ምን ያህል ትልቅ ሊሆን ይችላል? ሰው ምሁር ቢሆን እንኴን ኣለማዊ እውቀት ምን ያህል የላቀ ነው? ልዩነቱ እዚህ ግባ የማይባል ነው ስጋዊ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ከሰው አመለካከት አንጻር የሚያስቡ ሰዎች ናቸው ማለትም ስለ ራሳቸው ደህንነትና ክብር ብቻ የሚጨነቁና ለስጋቸው ስኬት ብቻ ሁሉን የሚያስቡ ልክ እንደ ጴጥሮስ የሚያስቡ ሰዎች ናቸው፡፡

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

መንፈስህ ጠናማ እንዲሆን አስቀድመህ የሐጢአት ሰርየትን መቀበል አለብህ። በልብህ ውስጥ አሁንም ሐጢአት ካለብህ መንፈስ ቅዱስ የለብህም። መንፈስ ቅዱስ ራሱ ቅዱስ ስለሆነ ሐጢአት ባለበት ልብ ውስጥ መኖር አይችልም ስለዚህ ሐጢአት እያለባቸው መንፈስ ቅዱስ አለን የሚሉ ክርስቲያኖች ሐሰተኛ ክርስቲያን ናቸው።

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው። ሁለም ያወራኛል። ይመክረኛል። ያጽናናኛል። ወደ ሕይወት ውሃ ምንጭ ይመራኛል ምክንያቱም በኢየሱስ ጥምቀትና ሞት የሐጢአትን ስርየት ለአንደ ተቀብያለሁና።
@jonahnlm

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

በኢየሱስ ማመን ማለት ለዘለዓለም ጻድቅ መሆን ማለት ነው። በኢየሱስ እያመንኩንም ሐጢአት ካለብኝ ገና አልዳንኩም ማለት ነው። ስለዚህ ሐጢአት ያለበት ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባት አይቻለውም።
@jonahnlm

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

የእግዚአብሔር መንገድ በመቅደሱ ውስጥ ነው። ክፍል 3 የመገናኛ ድንኳን ምስጥር በትክክል ለማወቅና ለመረዳት የሚትፈልጉ ከታች ባለው ሊንክ ቻናላችንን ይቀላቀላሉ። https://youtu.be/i07oQHwTLFE

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

ከፍታው፣ ዝቅታው፣ስፋቱ የማይተወቀው የእግዚአብሔር ፍቅር።

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

7ቱ የጽዋ መቅሰፍት ምንድነው?
እንዴት ነው የሚፈጸሙት?
በዚህ መቅሰፍት ውስጥ እነማን ይተርፋሉ?


https://youtu.be/n6vW8pttQ84

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

ክፍል 1

ይቀጥላል
@freenlmbookss

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

የእምነት ምስክርነት
እንኳን ወደ ውሃውና መንፈሱ ወንጌል በሰላም መጣሽ።
💝💝💝
@jonahnlm

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

ጥቅምት 6-2015

የናባል ሞኝነትና የሚስቱ አስተዋይነት

(አርስ በርስ ቃልን መካፈል)

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

እግዚአብሔር ለያዕቆብ የሰጠው ጥበብና በረከት

መስከረም 29 2015

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

የእግዚአብሄርን ስርዓት ያፈረሱ የዘመኑ ክርስቲያኖች
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
ብዙዎች ደህንነትን የሚያስቡን ከዚህም ከዚያም የተነቃቀሉ ጥቅሶችን በአእምሮዋቸው በመያዝ ነው ።

"የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል" የሚለውን ይዞ
የሚሮጥ በሌላ ክፍል በዚህ ጉዳይ ምን ተባለ የሚለውን የማያጤን ክርስቲያን ብዙ ነው ።

ገለባ እና አሸዋ በሆነ እምነት ስሙን ስለሚጠሩት ጌታ ኢየሱስ ይህን ብሏል ፦
" ስለ ምን። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ ትሉኛላችሁ፥ የምለውንም አታደርጉም?" (የሉቃስ 6:46)

ሐዋርያው ጳውሎስም ፦ " ሆኖም። ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል፥ ደግሞም። #የጌታን_ስም_የሚጠራ_ሁሉ_ከዓመፅ_ይራቅ የሚለው ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል።" (2ኛ ጢሞ2:19) ብሎናል ። አንድ ጥቅስ ስናነብ ያቺን አንድ ጥቅስ ይዘን መሮጥ ሳይሆን በሌላ ክፍል በዚህ ጉዳይ ምን ተብሎ ተጽፏል? በዚህ ርዕሰ ጉዳይ የአጠቃላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ሃሳብ ምንድነው? ብሎ ማጤን ተገቢ ነው።


በዘመናችን ብዙዎች ጋር ከደረሱ ወንጌሎች ውስጥ አንዱ "የደሙ ወንጌል ነው " ደሙ ብቻን ያድናል። ይላሉ የዚህ ሃሳብ አራማጆች ። ያው ሁሉም የስህተት ትምህርቶች ጥቅስ አላቸው። ለዚህ እሳቤም የሚሆኑ ተብለው የታሰቡ የተወሰኑ ጥቅሶች አሉ ።
* " በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ #በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት።" (ኤፌሶን 1:7)

"... ለወደደን ከኃጢአታችንም #በደሙ ላጠበን፥"
(የዮሐንስ ራእይ 1:4-5)
" እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ #በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው፤" (ሮሜ 3:25)

" ስለዚህ ኢየሱስ ደግሞ በገዛ ደሙ ሕዝቡን እንዲቀድስ ከበር ውጭ መከራን ተቀበለ።" (ዕብ 13:12)
. . .
የሚሉ ጥቅሶችን ይዘን ወንጌል ማለት በቃ ስለደሙ ነው ።
ደሙ ብቻ ያድናል ። ወደሚል ድምዳሜ ከመጣን ትልቅ ስህተት እንፈጽማለን ።


በነገራችን ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ወይም እነጴጥሮስና ዮሐንስ <<ስክርስቶስ ደም>> ያላቸው መረዳትና
ያሁኖቹ ኃጢአተኛ ክርስቲያኖች ደሙን የሚረዱበት መረዳት ፈጽሞ የተለያየ ነው ።


ጳውሎስም ሆኑ ሌሎች ደቀመዛሙርት የክርስቶስን ደም የሚረዱት እምነታቸውን በስርየት ህጉ ላይ አኑረው ነው ።


ደም ከመፍሰሱ በፊት በጥንቃቄ መከናወን ያለባቸው
የእግዚአብሔር ስርዓቶች አሉ ። እነዚህ ስርዓቶች ሁሉ ፣ አሁን ላይ ተራ ስርዓት ቢሆኑም ፣ ስለክርስቶስ ማንነትና በክርስቶስ ምን እንደሚፈጸምልን የሚነግሩን የትንቢት ቃሎች መሆናቸውን ልናውቅ ይገባናል ።

አንድ ሰው የኢየሱስን ደም በትክክል ለመረዳት የቤተ መቅደሱን ስርዓት የግድ ማወቅ አለበት ።

በብሉይ ኪዳን ዘመን ኃጢአት የሰራ ሰው ከኃጢአቶቹ ለመንጻት ምን ያደርግ ነበር?

ሦስት ነገሮችን ያደርግ ነበር
1ኛ. ኃጢአተኛው ሰው ከሰራው ኃጢአት ነጻ ለመውጣት ወይም ምህረትን ለማግኘት የግድ መሥዋዕት ማቅረብ ነበረበት ።መስዋዕቱም #ነውርና_እንከን_የሌለው ጠቦት
መሆን አለበት ። ልብ በሉ ነውርና እንከን ያለው መስዋእት የሌላውን ነውር ማስወገድ አይችልም ።

ይህ አንድ ሰው በኢየሱስ ላይ ያለው እምነት ሲጀመር ጤናማ መሆን እንዳለበት የሚያሳይ ነው ። ኢየሱስ ፍጹም አምላክ ፤በስራውም ፍጹም ነው ።እርሱ እግዚአብሔር ነው ፤የዓለምን ኃጢአት በአንዴ ለማስወገድ የመጣ የእግዚአብሔር በግና ፤ልጅም ነው።ድንቅ መካር አምላክ የዘለዓለም አባትም ነው ። እርሱ በስራው እንከን የሌለው ፍጹም ነው ። የሰው ሁሉ ቤዛም ነው ።

ይህ አንድ ሰው በኢየሱስ ሊያምን ሲነሳ አስቀድሞ ሊያምነው የሚገባ እውነት ነው ።


2ተኛ አንድ ሰው ከኃጢአቶቹ ለመንጻት ነውርና እንከን የሌለውን ጠቦት ወደ መገናኛው ድንኳን (ወደ ቤተመቅደሱ) ካመጣው በኋላ ካህኑ የጠቦቱን እንከን አልባነት ይፈትሻል ንጹህ ሆኖ ሲያገኘውም ኃጢአተኛው ሁለቱንም እጆቹን በመስዋዕቱ ራስ ላይ እንጂጭንና ኃጢአቶቹን እንዲናዘዝ ለጠቦቱም ኃጢአቶቹን እንዲያሸክም ያደርጋል ።በዚህ ጊዜ ኃጢአት ከኃጢአተኛው ወደ ጠቦቱ ይተላለፋል ።

ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ጠቦቱን ማረድ ፤ ደሙን ማፍሰስ አቤት ደሙ ጉልበቴ ...ማለት ሁሉም ከንቱ ነው ።
#እጆችን_መጫን እና ኃጢአትን ማስተላለፍ ከደህንነት መሠረታዊ ትምህርቶች አንዱ ነው ።3ተኛ.በመጨረሻም ጠቦቱ ይታረዳል ደሙ ይፈሳል ። የፈሰሰው ደምም በመሰውያው ቀንዶች ላይ ይቀባል ፤ቀሪው ከመሠውያው በታች ምድር ላይ ይደፋል ፤በዚህም መሠረት ስርየቱ የሰመረ ይሆናል ።


የክርስቶሰ መምጣትም የተፈጸመው ይኸው ።ኢየሱስ የሞተው መጽሐፍት ባሉት መሠረት ነው ።(1ቆሮ15:3 )
እርሱ ኢየሱስ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ሆኖ መጣ ። በግ እጆቾን በመጫን ስርዓት ኃጢአት እንደሚሸከም ሁሉ ኢየሱስ እጆችን በመጫን ስርዓት በዮርዳኖስ ወንዝ በአጥማቂው ዮሐንስ ሲጠመቅ በደላችንን ሁሉ በሥጋው ተሸከመ ። ኢየሱስ የተጠመቀው እኛን ከኃጢአቶቻችን ሁሉ በአንዴ ሊያድነን ነው። ኢየሱስ ባይጠመቅ ኖሮ ማናችንም አንድንም ነበር ።
እርሱ የእኛን ኃጢአቶች ተጠምቆ ባይቀበል የሚሞትበት ምክንያት ባልኖረው ነበር ። የዘመኑ ክርስቲያኖች ይህ እምነት ሊኖራቸው ግድ ይላል ።ይህ እምነት የሌለው ሁሉ ገሃነም ገቢ ነውና ።


ኢየሱስ ያንን ሁሉ መከራ የተቀበለው በመስቀል ተቸንክሮ የሞተው የእኛን የኃጢአቶቻችንን ደሞዝ ሊከፍል ነው ።
ቤዛ ሊሆነን ነው ። " በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው። እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል።"(ቆላ 2:14)
ተብሎ ተጽፎልናል ።

ኢየሱስ ከሞት የተነሳው ለምንድነነው? እኛን ለማጽደቅና ኃጢአት አልባ ለማድረግ ነው ።(ሮሜ4:25; ; 1ቆሮ 15:17) ለእኛም የትንሣዬ ተስፋን ሊሰጠን ዘንድ ነው ።
(ሮሜ 8:11)
እንግዲህ ይህ እምነት ያለው ብቻ ይድናል ።ከዚህ ውጭ ያለ እምነት ሁሉ የእግዚአብሔርን ስርዓት ያፈረሰ ነውና
ከፍርድ አያመልጥም ።

ሻሎም
visit www.bjnewlife.org

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

ጌታን ተቀብያለሁ ብሎ ነገር ግን ዳግመኛ ላልተወለደ ሰው የውሃውና የመንፈሱ ወንጌል ስመሰክር የተቀዳ ንግግር። ይህን መልዕከት ያዳመጠ ሰው እውነኛውን ወንጌልና እንክርዳዱን ወንጌል ይለያል።

@dehnenet
@dehnenet
@dehnenet

@jonahnlm

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

ቆይ በጌታ ናችሁ? ሐጢአተኞች ናችሁ ወይስ ጻድቅ ናችሁ? ሐጢአት ከሰራችሁ በኋላ ምን ትሰራላችሁ?

መልስ👇

@jonahnlm

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

ቶሎ የሚከበንን ኃጢአት ማስወገድ
~~~~

ኢየሱስ ከዮሐንስ እጅ በተቀበለው ጥምቀትና በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ በማመናችን ከኃጢአት ሙሉ በሙሉ ነፃ ወጥተናል። የባሪነት ቀንበራችን ተሰብሯል። ዓለም በባሪነት ውስጥ ቢኖርም፣ እኛ ግን በነፃነት ለመኖር ነፃ ወጥተናል። ክብር ለአዳኛችን ይሁን! ከኃጢአት ነፃ ወጥተናል ማለት የኃጢአት ፈተና የለብንም ማለት አይደለም። ከኃጢአት ነፃ ብንወጣም፣ አሁንም የኃጢአት ፈተና አለብን። ከኃጢአት ጋር ውጊያ አለብን። ኃጢአት ይከበናል። የዓለም ፍቅር ይከበናል። ሥጋዊ አስተሳሰብ ይከበናል። የገንዘብ ፍቅር ይከበናል። የባለጠግነት አሳብ ይከበናል። የውሃውና የመንፈሱን ወንጌል እንዳንመሰክር ይተበትቡናል። ለእግዚአብሔር መንግስት እንዳንኖር ይጎትቱናል። በሚያታልል ምኞት ይስቡናል።

ጳውሎስም ተከቧል። ግን በእምነትና ለእግዚአብሔር መንግስት በመኖር ድል አድርጓል። ሥጋውን ጎሰመ። ምድራዊ ብልቶቹን ገደለ። ነፍሱ በእርሱ ዘንድ እንዳትከበር እንደ ከንቱ ነገር ቆጠረ (ሐዋርያት 20:24)። ነፍሱን ለወንጌል ሥራ አሳልፎ ሰጠ። ጳውሎስ በኃጢአት ቢከበብም፣ የከበበውን ኃጢአት በእምነት በማስወገድ መንፈሳዊ ሩጫውን በድል አጠናቋል።

📌“ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ።” (ሐዋርያት 20፥24)

ከጳውሎስ አጋር ሰራተኛ የሆነው ደማስም በዓለም ተከቧል። ከበባውን ግን በእምነት ድል ማድረግ አልቻለም። ተሸነፈ። የከበበውን ኃጢአት በእምነት ማስወገድ አልቻለም። ንጉሱ ሰሎሞንም በኃጢአት ተከቦ ነበር። በዓለም ፍቅር ተከቦ ነበር ነገር ግን ድል ማድረግ አልቻለም። የከበበውን ኃጢአት በእምነት ማስወገድ አልቻለም። ተሸነፈ። በመጨረሻም ለጣኦት በመስገድ እግዚአብሔር እጅግ የሚጸየፈውን ኃጢአት ፈጸመ። እስራኤልውያን ከግብጽ ባሪነት ከወጡ በኋላ፣ በኃጢአት ተከበው ነበር። በሥጋ ምኞት ተከበው ነበር። ከመና ይልቅ የግብጽን ዱባና ዓሳ እንዲሁም ሥጋ ተመኝተው ነበር። የከበባቸውን ኃጢአት በእምነት ማስወገድ አልቻሉም። ብዙዎቻቸው በምድረ በዳ ወደቁ። እግዚአብሔርንም አስቆጡት። ከግብጽ ቢወጡም ወደ ተስፋይቱ ምድር ከናዓን አልገቡም። በኃጢአት ተሸነፉ።

ጌታችን ኢየሱስ ኃጢአቶቻችንን በውኃውና በደሙ ካስወገደ በኋላ የኃጢአት ስርየት ብቻ አይደለም የሰጠን። ተልዕኮም ስጥቶናል (ማቴዎስ 28:18-20)። ያም ተልእኮ ወደ ዓለም ሁሉ እንድንሄድ፣ የውሃውና የመንፈሱን ወንጌል እንድንመሰክር፣ ነፍሳትን እንድናድን፣ የእሱን ትምህርት እያስተማርናቸው ደቀ መዛሙርት እንድናደርጋቸው ነው። ሆኖም ግን ይህን የጌታን ተልዕኮ እንዳንፈጽም ኃጢአት ይከበናል። የዓለም ፍቅር ይከበናል። የገንዘብ ፍቅር ይከበናል። የሥጋ መሻት ይከበናል። ግን ማሸነፍ እንችላለን። ማስወገድ እንችላለን። ማሸነፍ የምንችለው በአንድ ነገር ብቻ ነው። እርሱም በእምነት ነው። በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ በእምነት መሳተፍና እስከ መጨረሻ ራስን ለእግዚአብሔር መንግስት ሥራ አሳልፎ መስጠት ያስፈልጋል። እጃችንን አጣጥፈን በመቀመጥ የሚከበንን ኃጢአት ማስወገድ አንችልም።

📌የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል፦ “...እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።” (ዕብራውያን 12፥1-2)

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

“እነሆ፥ በዓመፃ ተፀነስሁ፥ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ።”(መዝ51፥5)
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ሰው ኃጢአተኛ ነው ማለት የሰይጣን ዘር ነው ማለት ነው።
ሰው ኃጢአተኛ ነው ማለት የዲያብሎስ ልጅ ነው ማለት ነው።
ሰው ኃጢአተኛ ነው ማለት የሚጠፋ ዘር ነው ማለት ነው።
ሰው ኃጢአት አለው ማለት ለዘላለም ሞት ታጭቶ ያለ ጎስቋላ ነው ማለት ነው።
ሰው ኃጢአተኛ ነው ማለት በጨለማ የተቀመጠ፣ በጨለማ የሚመላለስ ጨለማ ነው ማለት ነው።
ሰው ኃጢአተኛ ነው ማለት የእግዚአብሔር የጽድቅ ቁጣ በላዩ ነድዶ ያለ ከንቱ ነው ማለት ነው።
ሰው ኃጢአተኛ ነው ማለት የእግዚአብሔር ጠላት ነው ማለት ነው።
ሰው በልቡ ኃጢአት አለው ማለት ወይም የሰው ልብ ክፉ እጅግም ተንኮለኛ ነው ማለት የሰው ልብ በኃጢአት የጨለመ ነው ማለት ነው።
.
ሰው ኃጢአተኛ የሆነው ዛሬ ኃጢአት ስለሰራ ማለትም፦
👉 ዛሬ ስላመነዘረ፣
👉 ዛሬ ዝሙት ስለፈጸመ፣
👉 ዛሬ ስለሰረቀ፣
👉 ዛሬ ስለተናደደ፣ . . . አይደለም።
ሰው ኃጢአተኛ የሆነው በተፈጥሮ ኃጢአተኛ ሆኖ ስለተወለደ ነው። ሰው ኃጢአትን የሚሰራው በተፈጥሮ ኃጢአተኛ ስለሆነ ነው።
.
የሰው ዘር ምንጭ የሆነው የመጀመሪያው ሰው አዳም በዲያብሎስ አታላይነት በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአተኛ ሆኖ በኃጢአት ወድቋል።(ዘፍ2፥17፣ 3፥1-24)
ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የሰው የልቡ ሁኔታ የኃጢአት ክምችት ሆኗል፤ልቡ በኃጢአት ጨልሟል፣ ልቡ ውስጥ ኃጢአት ገብቷል።(ሮሜ5፥12) ሰው ኃጢአትን የተቀበለው ከዲያብሎስ ነው። ከእንግዲህ ወዲህ የአዳም ዘር ሆኖ የሚወለድ ማንኛውም ሰው ኃጢአተኛ ሆኖ ይወለዳል፣ እስከ ዕለተ ሞቱም ኃጢአትን በመሥራት ያበቃል።

👉ሰው ዝሙት የሚፈጽመው ዝሙትን መፈጸም ኃጢአት መሆኑን ረስቶ አይደለም።
👉ሰው የሚሰርቀው ስርቆት ኃጢአት መሆኑን ሳያውቅ ቀርቶ አይደለም።
👉ሰው የሚገድለው መግደል ኃጢአት መሆኑን ዘንግቶ አይደለም።
👉ሰው የሚያመነዝረው ምንዝርነት ኃጢአት መሆኑን ባለማወቁ አይደለም።
👉ሰው ለሰው ክፉ የሚሆነው ክፉ መሆን መጥፎ መሆኑን ባለማወቁ አይደለም።
👉ሰው የሚሳደበው ስድብ ኃጢአት መሆኑን ረስቶ አይደለም።
👉ሌላም ሌላም . . .

ሰው ኃጢአት የሚሰራው በተፈጥሮ ኃጢአት በልቡ ስላለው ብቻ ነው። ሰው በተፈጥሮ በልቡ ሸለፈታም ሆኖ ተወልዷል። አንድ ወንድ ሕጻን ልጅ ገና ሲወለድ የዘር ብልቱ በትርፍ ቆዳ ተሸፍኖ ወይም #ሸለፈታም_ሆኖ_ይወለዳል እንጂ በእናቱ ማህጸን ተገርዞ አይወለድም፤ ከተወለደ ገና በ8ኛው ቀኑ ይገረዛል።
.
መጽሐፍ ቅዱስ ልብወለድ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ የታሪክ መጽሐፍ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ የሳይንስ መጽሐፍ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ የሕብረተሰብ መጽሐፍ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ የሥነ-ዘጋና የሥነምግባር መጽሐፍ አይደለም።
👉መጽሐፍ ቅዱስ ለሰው ዘር በተጨባጭ ሕይወት ሰጪ የሕይወት መጽሐፍ ነው።‼ ሰው ሕይወትን ያጣው በኃጢአት ነው።
.
👉መጽሐፍ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ስለ ወንድ ልጅ ግርዘት የጻፈው ዝምብሎ አይደለም(ዘፍ17፥7-14)። ታሪክ ብሎ አይደለም፣ ወይም ስለሰው ልጅ ሥጋዊ ጤንነት ጉዳይ ተጨንቆ አይደለም። አንድ ወንድ ልጅ ቢገረዝም ባይገረዝም የዘር ብልቱ የራሱን ሥራ መሥራቱን አይተውም።
.
እግዚአብሔር በወንድ ልጅ ግርዘት ሰውን እያስተማረ ያለው፦ ሰው ገና ሲወለድ ሸለፈታም(ኃጢአተኛ) ሆኖ መወለዱን ነው። ወንድ ልጅ ሸለፈት ባይኖረው መገረዝ ባላስፈለገው ነበረ። በመጽሐፍ ቅዱስ ሸለፈት ኃጢአትን የሚያመለክት ነው።

እግዚአብሔር በወንድ ልጅ የዘር ብልት ምሳሌ የሰውን የልቡን ሁኔታ እያሳየ ነው።
“እንግዲህ አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ የጌቶችም ጌታ፥ ታላቅ አምላክ ኃያልም የሚያስፈራም፥ በፍርድ የማያደላ፥ መማለጃም የማይቀበል ነውና እናንተ #የልባችሁን_ሸለፈት_ግረዙ፥ ክእንግዲህ ወዲህም አንገተ ደንዳና አትሁኑ።”(ዘዳ10፥16-17) ተብሎ የተጻፈው ለዚህ ነው።
አሁን ሰው እነዚህን ቀጣዩን ጥያቄዎችን ማንሳትና ማወቅ አለበት።
፩ኛ. የሰው የልቡ ሸለፈት ምንድነው❓
፪ኛ. ሰው የልቡን ሸለፈት መግረዝ የሚችለው እንዴት ነው❓ ለሚሉት ጥያቄዎች በቂ ምላሽ ማግኘት ያሻዋል።
.
ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን የልቡን ሁኔታ እንዲህ ብሎ ገልጿል፦
"ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ #ያ ነው። ከውስጥ #ከሰው_ልብ_የሚወጣ ክፉ አሳብ፥
~ ዝሙት፥
~ መስረቅ፥
~ መግደል፥
~ ምንዝርነት፥
~ መጐምጀት፥
~ ክፋት፥
~ ተንኰል፥
~ መዳራት፥
~ ምቀኝነት፥
~ ስድብ፥
~ ትዕቢት፥
~ ስንፍና ናቸውና፤
👉 ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውን ያረክሰዋል።" አለ(ማር7፥20-23)።
.
እንግዲህ ተመልከቱ!
ለሰው የዝሙት መሻት በልቡ ላይ የሚመላለሰው ዝሙት በተፈጥሮ በልቡ በመኖሩ ነው።
ለሰው በተፈጥሮው ዝሙት በልቡ ባይኖር የዝሙት መሻት ባልኖረ ነበረ፤
👉 እላይ በማርቆስ ወንጌል 7:21-22 ላይ የተዘረዘሩ ኃጢአቶች በሙሉ የሰው ዘር የልቡ ሸለፈት ነው። እነዚህ ኃጢአቶች በተፈጥሮ በሰው ልብ ውስጥ ያሉ ናቸው። ሰው ኃጢአትን የሚሰራው በእነዚህ ኃጢአቶች ታስሮ ስላለ ነው።
ሰው ለዘላለም ሞት የታጨውም ለዚህ ነው።(ሮሜ6፥23)
ለሰው ኢየሱስ ያስፈለገውም ለዚህ ነው።(ማቴ1:21)
👉 እነዚህ ሸለፈቶች ከሰው ልብ መቆረጥ የሚችሉት ሰው የውኃውንና የመንፈሱን ወንጌል ሲያምን ብቻ ነው።(ዮሐ3:5)
*የሰው የልቡ ሸለፈት ሊቆረጥ የሚችለው በኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት ነው።(ማቴ3፥15፣ ቆላ2፥11-12)
ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ በተጠመቀ ጊዜ የእጆችን መጫን ጥላ በመፈጸም(ዘሌ16፥21) የዓለምን ኃጢአት ማለትም ከዓለም ጅማሬ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ የተሰሩትን የሰውን ዘር ኃጢአት ሙሉ በሙሉ በሥጋው ወስዷል ተሸክሟል።
የእነዚያንም ኃጢአቶች ቅጣትና ፍርድ ሞት በመስቀል ላይ ወስዷል። ኢየሱስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የሞተው በማርቆስ ወንጌል 7፥22 ላይ የተዘረዘሩትን የሰውን ዘር ኃጢአት በሥጋው በመሸከሙ ነው። ኢየሱስ በሞተ ጊዜ የዓለም ኃጢአት በሙሉ ከስሟል ተወግዷልም።
ኢየሱስ ከሞትም ተነስቶ ለሰው ዘር አዲስ ሕይወትን ሰጥቷል።
በዚህ እውነት ለሚያምን ሰው ኃጢአት የለውም፤ተገርዟል።
ከእንግዲህ ወዲህ ይህ ሰው ከሰይጣን ልጅነት ተላቆ የእግዚአብሔር ልጅ ሆኗል።(ዮሐ1:12)
👉ቀድሞ ጨለማ ነበረ፤አሁን ብርሃን ሆኗል።
👉ቀድሞ ኃጢአተኛ ነበረ፤አሁን ጻድቅ ሆኗል።
👉ቀድሞ ርኩስ ነበረ፤አሁን ቅዱስ ሆኗል።
👉ቀድሞ ፍጹም አልነበረም፤አሁን ፍጹም ሆኗል።
👉ቀድሞ የሚጠፋ ዘር ነበረ፤አሁን የማይጠፋ ዘር ሆኗል።
👉ቀድሞ ለዘላለም ሞት ለገሃነም ፍርድ የታጨ ነበረ፤አሁን ለዘላለም ሕይወት ለመንግስተ ሰማይ የታጨ ሆኗል።
👉ቀድሞ የዲያብሎስ ልጅ ነበረ፤አሁን የእግዚአብሔር ልጅ ሆኗል።
👉ቀድሞ አሮጌ ፍጥረት ነበረ፤አሁን አዲስ ፍጥረት ሆኗል።
👉ቀድሞ ምድራዊ ነበረ፤አሁን ሰማያዊ ሆኗል።

የመንፈሳዊ ትምህርቶችን መከታተልና ነጻ የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ መጽሐፍትን የሚትፈልጉ አድራሻችሁን አሳውቁን በነጻ ታገኛላችሁ። የቴሌግራም ቻናላችንንም ይቀላቀላሉ @tobebornagain

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

👆ከላይ የሚታዯቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ መጽሐፍት ጠቅላላ የብሉይና የአዲስ ኪዳንን ቃሎችን በወንጌል መነጽር(ስለ ዳግም ውልደት) የሚያብራሩ ከላይ ተጀምሮ በቅደም ተከተል 1,2,3 . . . እያሉ #በተከታታይነት የሚነበቡ ናቸውና፤ ከላይ ጀምራችሁ በቅደም ተከተሉ ተራ አውርዳችሁት አንብቡት ተጠቀሙበት።‼️‼️❗️

👉በሐርድ ኮፒ ማግኘት ከፈለጋችሁ፦ ሙሉ አድራሻችሁን ጻፉልን፤ ወይም በቀጣዩ ስልካችን አድራሻ #ይደውሉልን ያለምንም ክፍያ #በነጻ ታገኛላችሁ፤ በአቅራቢያችሁ በሚገኘው በፖስታ ቤታችሁ እንልካለን።‼️❗️
☎️📞📲️ይኼው ስልካችን፦
~> 09 26 46 72 75 (ወላይታ ሶዶ)
~> 09 10 55 51 90 (አዲስ አበባ)
~> 09 10 36 76 15 (አዲስ አበባ)
~> 09 12 17 96 90 (አዲስ አበባ)
~> 09 13 84 54 67 (ሀዋሳ)
~> 09 45 63 01 53 (ሀዋሳ)
~> 09 34 77 31 77 (ወናጎ)
~> 09 16 55 23 61 (አርባምንጭ)

💙💜❤️💟 እግዚአብሔር ይባርካችሁ‼️‼️❗️💕💓💗💖
.
For More Visit:
👉 www.bjnewlife.org
OR
👉 www.nlmission.com
ለተጨማሪ ጥያቄና አስተያየት
ደህንነት ቦትን ይጠቀሙ።
ሌሎችም ሼር ያድርጉ።
@dehnetbot

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

ፍቅር ማለት ለኔ ኢየሱስ የሰው ልጆችን ከሐጢአት ለማዳን በዮርዳኖስ ወንዝ የፈጸመው ጽድቅና በመስቀል ላይ በመሞት የሰራው የደህንነት ስራ ነው። ይህ ፍቅር ነው እኔን የእግዚአብሔር ልጅ ያደረገኝ። ለዘለዓለም ጻድቅ እንድሆን በጽድቁ የለወጠኝ።
@jonahnlm

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

Watch "ሐሰተኛ ወንጌልን እንዴት እናውቃለን?" on YouTube
https://youtu.be/rLBBAlvmyBo

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

በመለሳችሁት መልስ መሠረት የሰው ልጅ በሙሉ እጅግ ክፉ ነው። ኤር 17:9። ይህ የሁላችንም ማንነት ነው። ሰው ክፉ ነው ማለት በተፈጥሮው ምንም መልካምነት በውስጡ የለውም ማለት ነው። እግዚአብሔር የሰው ልጆችን ክፉ ነው ያለውን ለመዳን አስቀድመው ማንነቶቻቸውን እንድያውቁ ስለፈለገ ነው።

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

Watch "የእግዚአብሔር መንገድ በመቅደሱ ውስጥ ነው። ክፍል 2" on YouTube
https://youtu.be/rc2-Ccx9YyE

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

subscriber our new YouTube channel

https://youtu.be/kou-QsRyisw

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

ሰው የእግዚአብሔርን ጽድቅ በትክክል መጽሐፍ በምለው መንገድ አውቆ ካላመነ በስተቀር በራሱ መንገድ ኢየሱስን አምላክ አድርጎ ብያምን ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም።
@freenlmbookss

Читать полностью…
Подписаться на канал