freenlmbookss | Неотсортированное

Telegram-канал freenlmbookss - ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

2013

“አምላክህ እግዚአብሔር መሐሪ አምላክ ነውና አይተውህም፥ አያጠፋህምም፥ ለአባቶችህም የማለላቸውን ቃል ኪዳኑን አይረሳም።” — ዘዳግም 4፥31

Подписаться на канал

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

የዘመኑ አገልጋዮች «ሰው ሁሉ ከሐጢያት ነጻ መውጣት አለበት» ይላሉ። አባባላቸው በራሱ ፈጽሞ ትክክል ነው። ሆኖም እነዚህ አገልጋዮች አንድ ሰው እንዴት ከሐጢያት ነጻ መውጣት እንደሚችል በትክክል ማስተማር አልቻሉ። ለምን? እነርሱ ራሳቸው እንዴት ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ ነጻ መውጣት እንደሚችሉ ኣያውቁምና።

እነርሱ ራሳቸው መንፈሳዊ እውራን ስለሆኑና ገና የሐጢያቶቻቸውን ስርየት ስላልተቀበሉ የማንንም ነፍስ ወደ እውነት ብርሃን መምራት አይችሉም። ጌታችን እንዲህ ብሉዋል ««ዕውር ዕውርን ሊመራ ይችላልን? ሁለቱ በጉድጓድ አይወድቁምን?» (ሉቃስ 6:39


ጌታ ሰው ሁሉ አስቀድሞ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ዳግም መወለድ እንዳለበት ተናግሮዋል። ምክንያቱም መንግስተ ሰማይን ማየትና ወደዚህ መንግስት መግባት የሚችለው ያን ጊዜ ብቻ ነውና። ሆኖም ችግሩ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እውነት ለሰዎች የሚሰብኩ የእግዚአብሄር አገልጋዮች ጥቂቶች መሆናቸው ነው። ሰዎች ከንስሐ ጸሎቶቻቸው ጋር ከመጣበቅና በሕግ ላይ የተመሰረተ የእምነት ሕይወት ከመኖር በቀር ምርጫ የሌላቸው ለዚህ ነው። ምክንያቱም እንዴት ከሐጢያቶቻቸው ሁሉ እንደሚነጹና ዳግም እንደሚወለዱ ኣያውቁምና።


«እዚህ ችግር ውስጥ የገባሁት አስራቶቼን ባለመስጠቴ ነው» ወይም «በልቤ ውስጥ እንዲህ የበዙ ሐጢያቶች ያሉት በቂ የሆኑ የንስሐ ጸሎቶችን ባለ ማቅረቤ ነው። በታማኝነት የንስሐ ጸሎቶችን አቅርቤ ቢሆን ኖሮ ፈጽሞ በሐጢያት ባልታሰርሁም ነበር» ብለው ያስባሉ። ስለዚህ ሰዎች በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አንዳች እምነት ሳይኖራቸው የሐጢያት ችግራቸውን ለመፍታት ይሞክራሉ።

በኢየሱስ ካመኑበት ጊዜ ጀምሮ ተጨማሪ ጊዜ እየነጎደ በሄደ ቁጥር ይበልጥ የከፉ ሐጢያተኞች የሚሆኑት ለዚህ ነው። ያን ጊዜ ራሳቸውን ይመለከቱና ለረጅም ጊዜ በኢየሰስ አምነው ሳለ እንዲህ ይበልጥ የቆሸሹት፣ ይበልጥ ግብዝ የሆኑትና ይበልጥ ክፉ ሰዎች የሆኑት ለምን እንደሆነ ይገረማሉ። ስለዚህ አሁኑኑ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ደግማችሁ እንድታጤኑትና እንድታምኑበት ሁላችሁንም እመክራችኋለሁ::

ተጨማሪ መንፈሳዊ ማብራሪያ መጽሐፍ ማግኘት የሚትፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን የቴሌግራም ሊንክ ተጠቀሙ።
t.me/chrstianbooks

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

የሚያጸድቀው ጸሎት--- ‹‹እኔን ሐጢያተኛውን ማረኝ፡፡››


እግዚአብሄር ኢየሱስ ክርስቶስን ወደዚህ ምድር የላከው ሰናይ
ሕይወትን የሚኖሩትን፥ በመልካምነታቸው የተመሰገኑትን ወይም በስነ ምግባራቸው ሰማይ ጥግ እንደደረሱ የሚያወሩትን ሰዎች ለማዳን አይደለም፡፡ በራሳቸው ጽድቅ የሚመኩ እንዲህ ያሉ ሰዎች እርሱ ስጋ ለብሶ በመጣበት ዘመንም በርክተው ይገኙ ነበር፡፡ ለዚህም የዘመኑ ፈሪሳውያን ሰዱቃውያንና ጸሐፍት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡

ኢየሱስ እነርሱን አስመልክቶ ሲናገር ‹‹ሐጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም›› (ሉቃስ 5፡32) ብሎ ነበር፡፡ ኢየሱስ ወደዚህ
ምድር የተወለደበት ዋናው አላማ ‹‹ሕዝቡን ከሐጢያት ለማዳን›› (ማቴዎስ 1፡21) እና ‹‹ሐጢያትን ለማስወገድ›› (1ኛ ዮሐንስ 3፡5) መሆኑን አለማወቅ ኢየሱስን ራሱን አለማወቅ ነው፡፡

ሁለት ሰዎች ወደ መቅደስ ሄዱ፡፡ አንዱ ፈሪሳዊ ሌላው ቀራጭ ነበር፡፡ ፈሪሳዊው በጸሎቱ ቀማኛ፥ አመጸኛ፥ አመንዘራ ወይም ቀራጭ እንዳልሆነ፥ በሳምንት ሁለት ጊዜ እንደሚጦምና ከሚያገኘው ሁሉ አስራትን እንደሚያወጣ እየዘረዘረ
ለእግዚአብሄር ሲጸልይ (እግዚአብሄር የራሳችንን ጽድቅ
ስንዘረዝር ቁጭ ብሎ የሚሰማ አምላክ መሆኑን የሚያምኑ
የዘመኑ ክርስቲያኖች ብዙ ናቸው፡፡

እግዚአብሄር እንዲህ ያለውን
ዝርዝር ለምን ይሰማል? የሰውን ልብ የሚያውቅ አምላክ ራስን
በሚክቡ ሟች ሰዎች አይሸወድም) ቀራጩ ግን ቀና ብለ እንኳን ወደ ሰማይ መመልከት አሳፍሮት ደረቱን እየደቃ ‹‹እኔን ሐጢያተኛውን ማረኝ›› እያለ ይጸልይ ነበር፡፡

ኢየሱስ ሲናገር ጸሎቱ የተሰማለትና ጸድቆ ወደ ቤቱ የሄደው ቀራጩ እንደነበር
መስክሮዋል፡፡ (ሉቃስ 18፡11-14) እግዚአብሄር የሚያጸድቃቸው
ሁለት ነገሮችን የሚያደርጉ ሰዎችን ነው፡፡ 1. ሐጢያተኛ
መሆናቸውን የሚያውቁና የሚያምኑ 2. ምህረት ሊሰጣቸው
የሚችለው እግዚአብሄር ብቻ መሆኑን የሚያውቁና የሚያምኑትን ነው፡፡

ኢየሱስ በማርቆስ 7 ላይ የሰውን እውነተኛ ማንነት ቁልጭ አድርጎ አሳይቶዋል፡፡ የሰው ዘር በሐጢአተኛ ማንነት ታሞዋል፡፡
ከዚህ በሽታው ሊድን የሚችለው ወደ ታላቁ ሐኪም ኢየሱስ በመጠጋት ብቻ ነው፡፡ ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ
(ማቴዎስ 3፡15) የሰውን ዘር ሐጢያት በሙሉ በራሱ ላይ
ተሸክሞ በመስቀል ላይ ደሙን በማፍሰስ (ማቴዎስ 26፡28)
የአለምን ሐጢያት በሙሉ አስወግዶዋል፡፡ (ዮሐንስ 1፡29፤1ኛ
ዮሐንስ 3፡5፤ዕብ፡ 1፡3) ለሰው ዘር ሁሉ ስርየትን ሰጥቶዋል፡፡
(2ኛ ዮሐንስ 2፡2-3)

ልፋትና ጥረት ሳያስፈልግህ እውነኛውን ማንነትህን በማመንና በመቀበል ብቻ አሁኑኑ የሐጢያትን ስርየት አግኝተህ ልብህ ንጹህ ይሆናል፡፡ ዳግመኛም ትወለዳለህ፡፡ (ዮሐንስ 3፡5) አዲስ ፍጥረት ትሆናለህ፡፡ (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21) የኢየሱስን ሕይወት ትቀበላለህ፡፡ (ገላትያ 2፡20) የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ትሆናለህ፡፡ (የሐዋርያት ስራ 2፡38) እነዚህ ሁሉ በረከቶች ያንተ ይሆናሉ፡፡ እመንና ዳን!

መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት የሚያስችሉ የማብራሪያ መጽሐፎች በነጻ ማግኘት የምትፈልግ ከሆነ ሙሉ አድራሻህን በውስጥ መስመር መላክ ትችላላችሁ። @jonahnlm

#ደህንነት

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

የሚያጸድቀው ጸሎት--- ‹‹እኔን ሐጢያተኛውን ማረኝ፡፡››


እግዚአብሄር ኢየሱስ ክርስቶስን ወደዚህ ምድር የላከው ሰናይ
ሕይወትን የሚኖሩትን፥ በመልካምነታቸው የተመሰገኑትን ወይም በስነ ምግባራቸው ሰማይ ጥግ እንደደረሱ የሚያወሩትን ሰዎች ለማዳን አይደለም፡፡ በራሳቸው ጽድቅ የሚመኩ እንዲህ ያሉ ሰዎች እርሱ ስጋ ለብሶ በመጣበት ዘመንም በርክተው ይገኙ ነበር፡፡ ለዚህም የዘመኑ ፈሪሳውያን ሰዱቃውያንና ጸሐፍት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡

ኢየሱስ እነርሱን አስመልክቶ ሲናገር ‹‹ሐጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም›› (ሉቃስ 5፡32) ብሎ ነበር፡፡ ኢየሱስ ወደዚህ
ምድር የተወለደበት ዋናው አላማ ‹‹ሕዝቡን ከሐጢያት ለማዳን›› (ማቴዎስ 1፡21) እና ‹‹ሐጢያትን ለማስወገድ›› (1ኛ ዮሐንስ 3፡5) መሆኑን አለማወቅ ኢየሱስን ራሱን አለማወቅ ነው፡፡

ሁለት ሰዎች ወደ መቅደስ ሄዱ፡፡ አንዱ ፈሪሳዊ ሌላው ቀራጭ ነበር፡፡ ፈሪሳዊው በጸሎቱ ቀማኛ፥ አመጸኛ፥ አመንዘራ ወይም ቀራጭ እንዳልሆነ፥ በሳምንት ሁለት ጊዜ እንደሚጦምና ከሚያገኘው ሁሉ አስራትን እንደሚያወጣ እየዘረዘረ
ለእግዚአብሄር ሲጸልይ (እግዚአብሄር የራሳችንን ጽድቅ
ስንዘረዝር ቁጭ ብሎ የሚሰማ አምላክ መሆኑን የሚያምኑ
የዘመኑ ክርስቲያኖች ብዙ ናቸው፡፡

እግዚአብሄር እንዲህ ያለውን
ዝርዝር ለምን ይሰማል? የሰውን ልብ የሚያውቅ አምላክ ራስን
በሚክቡ ሟች ሰዎች አይሸወድም) ቀራጩ ግን ቀና ብለ እንኳን ወደ ሰማይ መመልከት አሳፍሮት ደረቱን እየደቃ ‹‹እኔን ሐጢያተኛውን ማረኝ›› እያለ ይጸልይ ነበር፡፡

ኢየሱስ ሲናገር ጸሎቱ የተሰማለትና ጸድቆ ወደ ቤቱ የሄደው ቀራጩ እንደነበር
መስክሮዋል፡፡ (ሉቃስ 18፡11-14) እግዚአብሄር የሚያጸድቃቸው
ሁለት ነገሮችን የሚያደርጉ ሰዎችን ነው፡፡ 1. ሐጢያተኛ
መሆናቸውን የሚያውቁና የሚያምኑ 2. ምህረት ሊሰጣቸው
የሚችለው እግዚአብሄር ብቻ መሆኑን የሚያውቁና የሚያምኑትን ነው፡፡

ኢየሱስ በማርቆስ 7 ላይ የሰውን እውነተኛ ማንነት ቁልጭ አድርጎ አሳይቶዋል፡፡ የሰው ዘር በሐጢአተኛ ማንነት ታሞዋል፡፡
ከዚህ በሽታው ሊድን የሚችለው ወደ ታላቁ ሐኪም ኢየሱስ በመጠጋት ብቻ ነው፡፡ ኢየሱስ በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቅ
(ማቴዎስ 3፡15) የሰውን ዘር ሐጢያት በሙሉ በራሱ ላይ
ተሸክሞ በመስቀል ላይ ደሙን በማፍሰስ (ማቴዎስ 26፡28)
የአለምን ሐጢያት በሙሉ አስወግዶዋል፡፡ (ዮሐንስ 1፡29፤1ኛ
ዮሐንስ 3፡5፤ዕብ፡ 1፡3) ለሰው ዘር ሁሉ ስርየትን ሰጥቶዋል፡፡
(2ኛ ዮሐንስ 2፡2-3)

ልፋትና ጥረት ሳያስፈልግህ እውነኛውን ማንነትህን በማመንና በመቀበል ብቻ አሁኑኑ የሐጢያትን ስርየት አግኝተህ ልብህ ንጹህ ይሆናል፡፡ ዳግመኛም ትወለዳለህ፡፡ (ዮሐንስ 3፡5) አዲስ ፍጥረት ትሆናለህ፡፡ (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21) የኢየሱስን ሕይወት ትቀበላለህ፡፡ (ገላትያ 2፡20) የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ትሆናለህ፡፡ (የሐዋርያት ስራ 2፡38) እነዚህ ሁሉ በረከቶች ያንተ ይሆናሉ፡፡ እመንና ዳን!

መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት የሚያስችሉ የማብራሪያ መጽሐፎች በነጻ ማግኘት የምትፈልግ ከሆነ ሙሉ አድራሻህን በውስጥ መስመር መላክ ትችላላችሁ። @jonahnlm

#ደህንነት

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

ሐጢአተኝነትን ያስወገደ መድሃኒት
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ኢየሱስ ስጋ ለብሶ የተወለደው ሐጢአትንና ሐጢአተኝትን ለማስወገድ መሆኑን አለመረዳት በክርስትናዌ ውስጥ "የዳንን ሐጢአተኞች" ነን የሚሉ "ለብ" ያሉ ክርስቲያኖችን ፈጥሮዋል። "ኡየሱስ ሐጢአቴን እንዳስወገደ አምናለሁ፤ ሐጢአተኝቴን ግን አላስወገደም" የሚሉ ክርስቲያኖች ከደህንነት ርቀዋል። በእርግጥ ኢየሱስ "#የአለምን #ሐጢአት #የሚያስወግድ #የእግዚአብሔር #በግ" (ማቴዎስ 1:21፤ዮሐንስ1:29) መሆኑ አያከራክርም። ኢየሱስ ሐጢአትን ይቅር የሚል ብቻ ሳይሆን ሐጢአትንም ፈጽሞ የሚያስወግድ ነው። (1ኛ ዮሐንስ 3:5)

የኢየሱስ የጽድቅ ስራ ግን ከዚህም አልፎ ይሔዳል። ኢየሱስ ሐጢአተኝነትንም አስወግዶዋል። ሐጢአት የሐጢአተኝነት ተፈጥሮ ውጤት ነው። ሐጢአተኝነት ከአዳም የወደቀ ማንነት የተወረሰ የተበላሸ ተፈጥሮ ነው። ኢየሱስ ያስወገደው ቅርንጫፉን (ሐጢአትን) ብቻ ሳይሆን ግንዱንም (ሐጢአተኝነትንም) ጭምር ነው። "እንደዚሁም እስራኤል ሁሉ ይድናል ተብሎ እንደተጻፈ #መድሃኒት ከጽዮን ይወጣል፤ ከያዕቆብም #ሐጢአተኝነትን #ያስወግዳል።" (ሮሜ 11:26)

"መድሃኒት" ማነው? ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። (ሉቃስ 2:12) መድሃኒት የሆነው ኢየሱስ ስራው "ሐጢአተኝነትን" ማስወገድ ነው። ኢየሱስ ይህንን ያደረገው እንዴት ነው? "#ሐጢአታቸውንም #ስወስድላቸው ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው።" (ሮሜ 11:27) ኢየሱስ "ሐጢአተኝነትን" የሚያስወግደው በመጀመሪያ የሐጢአተኞችን "ሐጢአት" በመውሰድ ነው። አስራኤሎች ሐጢአትን በሚሠሩበት ጊዜ ሁሉ ነውር የሌለበት የመስዋዕት እንስሳ በእግዚአብሔር ፊት በማቅረብ እጆቻቸውን በራሱ ላይ ጭነው ሐጢአታቸውን ሲያስተላልፉ እንስሳው ሐጢአታቸውን እንደወሰደላቸው ሁሉ ኢየሱስም "የእግዚአብሔር በግ" ሆኖ በመምጣትና "ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም" በመጠመቅ (ማቴዎስ 3:15) ሐጢአታችንን ወሰደ። በመስቀል ላይ ደሙን በማፍሰስም የሐጢአትን ቅጣትና ፍርድ አስወገደ።

አሁን ይህንን በማወቅ ሐጢአቱ በሙሉ የተወሰደለትና የተወገደለት ሰው በዚህ እምነት ሐጢአት አልባ ይሆናል። "ሐጢአተኝነቱ" ተወግዶለታል። የእግዚአብሔር ጸጋ "ሐጢአተኝነትን የሚያስክድ" ጸጋ መሆኑን የማያምኑ ክርስቲያኖች (ቲቶ 2:12) እምነታቸው በአሸዋ ላይ የተገነባ ነው። ውሎ አድሮ ይፈርሳል።

ኢየሱስ ሐጢአትንና ሐጢአተኝነትን ማስወገዱን የማያምኑ ክርስቲያኖች ያመኑት በየትኛው ኢየሱስ ነው?

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

በእግዚአብሔር ጽድቅ የሚያምን ማንም ሰው ሐጢአት የለበትም። ኢየሱስ የሰው ልጆችን ሁሉ ሐጢአት በጥምቀቱ ወስዶ በደሙ ጠርቆ አስወግዷል። በዚህ የሚያምን ማንም ክርስቲያን ሐጢአት የለበትም።

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጠው የመታጠቢያው ሰን እውነት
=================
በብሉይ ኪዳን በተለይም በዘጸኣት ምዕራፍ 30 ከቁጥር 17 እስከ 21 ላይ የመታጠቢያ ሰን ተጠቅሶዋል «እግዚአብሄርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው የመታጠቢያ ሰንና መቀመጫውን አናስ ሥራ በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል እርሱን አድርህ ውሃን ትጨምርበታለህ አሮንና ልጆቹም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ይታጠቡበታል ወደ መገናኛው ድንኳን በገቡ ጊዜ ለእግዚአብሄርም የእሳት መሥዋዕት ያቃጥሉ ዘንድ ወደ መሠዊያው ሊያገለግሉ በቀረቡ ጊዜ እንዲይሞቱ ይታጠቡበታል እንዳይሞቱም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ይታጠቡ ይህም ለእርሱ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ የዘላለም ሥርዓት ይሆንላቸዋል» ዘጸአት 30:17-21 እግዚአብሄር ለሙሴና ለካህናቶቹ ይህን ተናገረ፡፡


ካህኑ ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገባ በመጀመሪያ የሚቃጠለውን መስዋዕት መሰዊያ ይጋፈጣል። ያ እስራኤላውያን እጆቻቸውን በመስዋዕቶቹ ራሶች ላይ በመጫን መስዋዕቶችን የሚያቀርቡበት፣ ደማቸውን ለማፍሰስም ጉሮሮዋቸውን የሚቆርጡበት፣ ደሙን በመሰዊያው ቀንዶች ላይ የሚያኖሩበትና ስጋቸውንና ስባቸውንም ለእግዚኣብሄር ኣምላክ የሚያቃጥሉበት ስፍራ ነበር። ሊቀ ካህኑ በስርየት ቀን ሐጢያቶቻቸውን ለማስተላለፍ ሰፊቱ ከቀረበለት ከሁለቱ የመስዋዕት ፍየሎች በኣንደኛው ላይ እጆቹን የሚጭነው በዚህ መሰዊያ አጠገብ ነው::


በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያለውን መሰዊያ ካለፋችሁ በኋላ የምታገኙት የናሱን የመታጠቢያ ሰን ነው። እነርሱ የመታጠቢያውን ሰን ካለፉ በኋላ ታቦቱን ወዳስቀመጡበት የእግዚአብሄር ቤት ወደሆነው ቅድስት ክፍል ይገባሉ። ማንም ሰው ወደ ቅድስቱ ክፍል ለመግባት የሚደፍር ከሆነ በመጀመሪያ በመታጠቢያው ሰን ላይ ከርኩሰቱ ሁሉ መንጻት አለበት። ሊቀ ካህኑም ከዚህ ውጪ አይደለም። የሐጢያት ስርየትን ለተቀበሉ ጻድቃን የተነገረው የሐጢያት ስርየት እውነት ይህ ነው፡፡


የግል ሐጢያቶችን እንሰራለን። የሐጢያት ስርየትን ብንቀበልም እንዴት ልቦቻችንን ንጹህ አድርገን መጠበቅ እንችላለን? እኔ እየጠየቅሁት ያለሁት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በሚያምነው እምነታችን አማካይነት የሐጢያት ስርየትን ከተቀበልን በኋላ ልቦቻችንን ያለ ሐጢያት መጠበቅ የምንችለው እንዴት ነው? የሚለውን ነው። የዚህ ጥያቄ መልስ ያረፈው በመታጠቢያ ሰን በተከናወነው የሐጢያት ስርየት እውነት ላይ ነ። የሐጢያት ስርየትን ከተቀበልን በኋላ ቅድስናችንን የመጠበቁ ምስጢር ሊገኝ የሚችለው በመታጠቢያው ሰን ላይ ነው።
.
ጌታችን ንጹህ የሆነ ሰው የሚያስፈልገው እግሮቹን መታጠብ ብቻ ነው ብሎዋል «ኢየሱስም የታጠበ እግሩን ከመታጠብ በቀር ሌላ አያስፈልገውም ሁለንተናው ግን ንጹህ ነው እናንተም ንጹሐን ናችሁ ነገር ግን ሁላችሁ አይደላችሁም» ዮሐንስ 13:10) ልክ ጌታችን እንደተናገረው እኛም በመታጠቢያው ሰን በሚያምነው እምነታችን አማካይነት የግል ሓጢያቶቻችንን እናነጻለን። ፍጹም የሆነውንም እምነታችንን እንጠብቃለን የመታጠቢያው ሰይን እውነትም ጌታችን ከአጥማቂው ዮሐንስ ጥምቀትን ለመቀበል ወደዚህ አለም በመጣ ጊዜ በመጨረሻ በአዲስ ኪዳን ዘመን ተገለጠ።
.
በሌላ አነጋገር እኛ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ሐጢያቶቻችን በሙሉ የነጹበትን ኢየሱስ የተቀበለውን ጥምቀት በማመንና በማሰላሰል ፍጹም የሆነውን እምነታችንን እንጠብቃለን። የኢየሱስን ጥምቀት በማሰላሰልና በማመን ቅዱሳን እንሆናለ። ቅዱሳን ሆነንም እንቀራለን። «ይህም ውሃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል የሰውነትን እድፍ ማስወገድ አይደለም ለእግዚአብሄር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ» (1ኛጰጥ 3:22 ተብሎ እንደተጻፈው ውሃው በእርግጥ የሚያሳየው የኢየሱስን ጥምቀት ነው::
.
ጌታችን ጥምቀቱን በመቀበል ሐጢያቶቻችንን በሙሉ ወሰደ በመስቀል ላይ በመሞትም ሐጢያቶቻችንን ሁሉ ደመሰሰ። ጌታችን የአለምን ሐጢያቶች በሙሉ በሞተበት መስቀል ላይ ወሰ። ከሙታን በመነሳትም አዳነን እኛ በጌታችን ምግባሮች አማካይነት የሐጢያት ስርየትን ከተቀበልን በኋላ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል ደጋግመን ማስታወስ ይገባናል። የሐጢያት ስርየትን ከተቀበልን በኋላም ጌታችን የተቀበለውን ጥምቀት በየቀኑ ማሰብ አለብን።
.
በዚህ አለም በምንኖርበት ጊዜ ሁሉ በምናምንበትና በምናሰላስለው ጊዜ ሁሉ የረከሱት ልቦቻችን በሙሉ አዲስ ሆነው ይነጻሉ። በእርሱ ጥምቀት በሚያምነው እምነታችን በፊቱ ለእግዚአብሄር አብ ስም ክብርን መስጠት የምንችለው ያን ጊዜ ብቻ ነው። ቀድሞውኑም የሓጢያት ስርየትን የተቀበልን ብንሆንም በሐጢያታችን ምክንያት የሚጨነቅ ሕሊና ካለን ለአባታችን ስም ክብርን መስጠት ኣንችልም ስለዚህ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን ቅዱሳን መሆን እንችል ዘንድ ጌታችን ለእግዚኣብሄር ኣብ ስም ክብርን የምንሰጥበትን ጸሎት አስተማረን፡፡
.
የብሉይ ኪዳን ዘመን ካህናቶች ርኩሰታቸውን የሚታጠቡበት የመታጠቢያ ሰን ባይኖራቸው ኖሮ ምን ይፈጠር ነበር? በመስዋዕቱ ኣማካይነት ለዚያ አመት የሚሆነውን አመታዊ የሐጢያት ስርየት ቢቀበሉም ንጽህናቸውን ጠብቀው የሚያቆዩት እንዴት ነበር? በመታጠቢያው ሰን ላይ መደገፍ ነበረባቸው፡፡
ትንሽ ርኩሰት እንኳን ያለባቸው ሰዎች እግዚአብሄር ራሱን ወደሚገልጥበት ቅድስተ ቅዱሳን ብገቡ በእርግጠኝነት ይሞታሉ። ታዲያ ሊቀ ካህናቶች በእግዚአብሄር ፊት መቅረብ የሚችሉት እንዴት ነው?
.
የመታጠቢያው ሰን ውሃ ባይኖረውና ሊቀ ካህኑም ርኩሰቱን መታጠብ ባይችል ወደ ቅድስተ ቅዱሳን መግባት አይችልም ነበር። በሌላ አነጋገር ካህናቶች በመታጠቢያው ሰን ውስጥ ባለው ውሃ ርኩሰታቸውን እስካላነጹ ድረስ ለቅዱሱ አምላክ ክብርን መስጠት አይችሉ። እነርሱ ማንም ይሁኑ ሊቀ ካህናትም ይሁኑ ያ ማለት ሊቀ ካህኑም እንኳን ሰው በመሆኑ በግል ሐጢያቶቹ ይረክሳል፡፡
.
ጻድቃኖችም ቢሆኑ ልቦቻቸውን የሚያረክሱ ሁነቶች ይጥመዋቸዋል። የእግዚአብሄርን ስራዎች እየሰራን ሳለን ክፉ አድራጊዎች ሲገጥሙን አንዳንድ ጊዜ ከውስጣችን የጽድቅ ቁጣ
ይፈልቃል። ልክ እንደዚሁ ስጋዊ ኣስተሳሰቦች በልቦቻችንን ውስጥ ብቅ ሲሉ ልቦቻችንን ያረክሳሉ ስለዚህ በብሉይ ኪዳን ዘመን ሊቀ ካህኑ ቅዱስ በሆነው አምላክ ፊት መቅረብ በፈለገ ጊዜ ወደ መገናኛው ድንኳን ከመግባቱና ተግባሮቹን ከማከናወኑ በፊት መሰዊያውን አልፎ በመታጠቢያ ሰይን ውስጥ ባለው ውሃ እጆቹንና እግሮቹን መታጠብ ነበረበት፡፡
.
ታዲያ በኣሁኑ ጊዜ ምን አይነት እምነት ሊኖረን ይገባል? ለዚህ ጥያቄ መልሱን የምናገኘው በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በሚያምነው እምነት ነው። ጻድቃን በእግዚአብሄር ፊት መጸለይ፣
መስገድና ማመስገን የሚገባቸው በምን አይነት እምነት ነው? በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በሚያምነው እምነት መሆኑ የእወቀ ነው። ልክ እንደዚሁ እኛም ወደ እግዚአብሄር በምንጸልይበት፣ እርሱን በምናመልክበትና በምናመሰግንበት ጊዜ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ላይ በመደገፍ ይህኑ ማድረግ አለብን። እግዚአብሄርን ያለ ምንም ሐጢያት ማመስገን ያለብን ከሆነ በዚህ ላይ መደገፋችን አስፈላጊ ነው::
.
እግዚአብሄርን ልንቀርበው የሚገባን በምን አይነት እምነት ነው? እግዚአብሄርን መቅረብ የምንችለው በኢየሱስ ጥምቀትና በደሙ በማመን ነው ስለዚህ እኛ የእግዚአብሄር ስም በአለም ሕዝብ ፊት እንደዚሁም በሰይጣን ዲያብሎስ ፊት ቅዱስ ሆኖ ይቆጠር ዘንድ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን እምነታችንን መኖር እንችላለን። ስንደመድም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በሚያምነው እምነታችን አማካይነት ለአባታች

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

በእግዚአብሄር ፊት አብዝቶ የሚያስፈልገን እምነት ነው
እምነትን መያዝ በጣም አስቸጋሪ ይመስላል። በእርግጥ ግን ቀላል ነው። በእግዚአብሄር ከማመን በስተቀር ምንም የሚያስፈልግ ነገር የለ። ከእኛ የሚያስፈልገን በእግዚአብሄር ማመን ብቻ ነው። ሰዎች በእግዚአብሄር ማመን አስቸጋሪ እንደሆነ ያስባሉ ነገር ግን በእርግጥ ያን ያህል አስቸጋሪ አይደለ። እኔ አባቴን «አባ» ብዬ እጠራዋለሁ አባቴ እንደሆነም አምናለሁ ምክንያቱም ለእኔ እውነተኛ አባት ነውና። እርሱ የእኔ አባት መሆኑ በእምነቴ ላይ የተመሰረተ አይደለም። በእግዚአብሄር ማመን የሚጀመረው ከዚህ ነው። እኔ በእግዚአብሄር አምናለሁ ለምን? ምክንያቱም እግዚአብሄር ሁልጊዜም ከጻድቃኖች ጎን ይቆማል፣ይወዳቸዋል፣አባትና ኣዳኝም ሆኖዋቸዋል። ሁለተኛ በእርሱ ስናምን ልጅ የሚፈልገውን ከአባቱ እንደሚጠይቅ ሁሉ የምንፈልገውን እንጠይቀዋለን። በመጨረሻም እግዚአብሄር አብ ይሰማል፣ የምንሻውንም ይሰጠናል። በእግዚአብሄር ማመን የተመሰረተውና የሚጀምረው እንዲህ ካለ ቀላል መታመን ነው::
እግዚአብሄር አልፋና ዖሜጋ መጀመሪያውና መጨረሻው ስለሆነ በእምነት መኖር አለብን። ሕይወታችን በመሉ ከእምነት ጋር የተዛመደ ነው በእምነት ድነናል በእምነት አማካይነትም በእርሱ ጥበቃ ስር ሆነናል። ««አቤቱ በአንተ አምናለሁ ጠብቀን እባክህ ተጠንቀቀልኝ» እንድንል የሚፈቅድልን እምነት ነው።
@freenlmbookss

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

(ዘፍጥ 1 )
------------
3 እግዚአብሔርም፦ ብርሃን ይሁን አለ፤ ብርሃንም ሆነ።

4 እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደ ሆነ አየ፥ እግዚአብሔርም ብርሃንንና ጨለማን ለየ።

እግዚአብሔር ለምን ብርሃን መልካም እንደሆነ አየ? ብርሃን በመጽሐፍ ቅዱስ ምን ማለት ነው? ጨለማውስ ምንን ያመለክታል?

ለምን ጨለማ ከብርሃን ተለየ?

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

" እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ።"
(መዝ 17: 15)
@freenlmbookss

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

እግዚአብሔር የሰጠው ጽድቅ ማንም ምድራዊ ሐይል ሊደመስሰው የማይችል የዘለአለም ጽድቅ ነው። እኔን ጻድቅ ያደረገኝ የራሰ በጎ ምግባር ሳይሆን ኢየሱስ በጥምቀቱ የፈጸመው የእግዚአብሔር ጽድቅ እንጅ።

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ አምላክ ነው። ያ ማለት እርሱ አምላክ ሆኖ ሳለ የሰው ልጆችን ከሐጢአትና ከዘለአለማዊ ሞት ለማዳን የሰው ሰጋ ለብሶ ወደ ምድር መቷል ማለት ነው። ኢየሱስ የሰው ልጆችን ሐጢአት አንድ ጊዜ በዮርዳኖስ ወንዝ በአጥማቂው ዮሐንስ እጅ ስጠመቅ በመሸከም በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ የአለምን ሁሉ ሐጢአት ጠርቆ በማስወገድ ደምስሷል ማለት ነው። በዚህ ሁሉ የሚያምኑ ሰዎች ሐጢአት የለባቸውም። ኩነኔ የለባቸውም። ለዘለዓለም ጻድቅና ቅዱሳን ናቸው።

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

በእግዚአብሔር ፍት የሚቀርብ ማንኛውም መጽዋዕት እጅ ሳይጫንበትና ሐጢአት ሳይተላለፍበት አይታረድም ምክንያቱም ያለ እጆች መጫን ሐጢአት ወደ በጉ አይተላለፍምና። ኢየሱስ በዮሐንስ እጆች መጫን በዮርዳኖስ ባይጠመቅና የአለምን ሐጢአት በሙሉ በስጋው ባይሸከም ኖሮ በመስቀል ተሰቅሎ ደሙን አያፈስም ነበር። ያለ እጆች መጫን የሚከወን የሐጢአት ስርየት በብሉይ ዘመን እንዳልነበረ ሁሉ ያለ ኢየሱስ ጥምቀት የሚገኝ ደህንነት የለም።

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

Watch "Free christian book review in amharic" on YouTube
https://youtu.be/WB_lfW2Pvts

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

ኢየሱስ ክርስቶስ የዘለአለም አምላክ ነው። ዘለአለማዊ አምላክ ማለት ጊዜና ሁነታ የማይገድበው እርሱ ብቻ እውነተኛ አምላክ ነው ማለት ነው። ኢየሱስ የሰው ልጆችን ከሐጢአት ሙሉ ለሙሉ ለማዳን በመጀመሪያ ከድንግል ማርያም በመንፈስ ቅዱስ በመጸነስ ስጋ ለበሰ በመቀጠልም የሰው ልጆችን ሐጢአት በስጋው ለመሸከም በአጥማቂው ዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ተጠመቀ በመስቀል ላይ በመሞትም የሐጢአትን ደሞዝ ሞትን ከፈለ በዚህም ለምያምኑት ሁሉ ከሙታን በመነሳት አድስ ሕይወት ሰጣቸው። ጻድቅና ቅዱስ አደረጋቸው። በኢየሱስ የሚያምኑ ሰዎች ሁሉ ለዘለዓለም ሐጢአት የለባቸውም።
@freenlmbookss

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

share and forward!!
@freenlmbookss

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

ዛሬ አብዛኞቹ ክርስቲያኖች እንደሚከተለው በተሳሳተ መንገድ ያምናሉ በኢየሱስ ሳምን ሰፍጥረቴ ይዤው የተወለድሁት የአዳም ሐጢያት ተወግዶዋል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የምሰራቸው የግል ሐጢያቶቼም የንስሐ ጸሎቶችን በምጸልይበት ጊዜ ሁሉ ይቅርታን ያገኛሉ»

የንስሐ ጸሎቶች ትምህርት መስረታዊ ትርጉም ይህ ነው። ስለዚህ ብዙ ሰዎች እግዚአብሄር በሰጠው የውሃና የመንፈስ ወንጌል በማመን ፋንታ በዚህ የንስሐ ጸሎቶች ትምህርት ብቻ ይታመናሉ፣ይደገፋሉም። አይኖቻቸው ስለተጋረዱ ከክርስትና ዋና ዋና ትምህርቶች አንዱ በሆነው የንስሓ ጸሎቶች ትምህርት ውስጥ ያሉትን ስህተቶች ማየት አይችሉም::


ሆኖም ለረጅም ጊዜ የንስሐ ጸሉቶችን ሲጸልዩ የነበሩ ክርስቲያኖች እነዚህ ጸሎቶች ምን ያህል ፈጽመው አይረቤ እንደሆኑ ያውቃሉ አዲስ አማኞች በነበሩ ጊዜ መጀመሪያ ላይ ለእግዚአብሄር የንስሓ ጸሎቶችን በሚያቀርቡበት ጊዜ ልቦቻቸው የረኩ መስሎ ተሰምቶዋቸው ይሆናል። ሐጢያቶቻቸው እንደነጹላቸውም አምነው ይሆናል ሆኖም ጊዜ እየነጎደ ሲሄድና ለጊዜውም ቢሆን የእምነት ሕይወታቸውን መኖር ሲቀጥሉ ውለው አድረው ሐጢያቶቻቸው አሁንም በልቦቻቸው ውስጥ እንደተከመሩ ራሳቸው ይረዳሉ።

ሐጢያት አንድ ሰው የንስሐ ጸሎቶችን በጸለየ ጊዜ ሁሉ የሚወገድ አንዳች ነገር አይደለም። በተቃራኒው በእርሱ የንስሐ ጸሎቶች አማካይነት እንደሚወገዱ ተስፋ የተደረጉት ሓጢያቶች አሁንም በልቡ ውስጥ ይሞላሉ። ይህንን የሚክድ አንድም ክርስቲያን የለም፡፡


ስለዚህ ብዙ ክርስቲያኖች አሁንም ድረስ የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል አያውቁም። በመሆኑም በሐሰተኛ ወንጌል ውስጥ የታሰረውን ሕይወታቸውን ይኖራሉ። ልቦቻቸውም በሐጢያት ተሞልተዋል። ስለዚህ እስከ እሁን ደረስ በንስሐ ጸሎቶች ትምህርት ያመኑ እነዚህ ክርስቲያኖች በተቻለ ፍጥነት መመለስ፣ በውሃውና ሰመንፈሱ ወንጌል ማመንና እውነተኛውን የሐጢያቶቻቸውን ስርየት መቀበል ይገባቸዋል፡፡

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

ጌታ ያስተማረው ፀሎት-******************-**********-*****-***
ይህን ፀሎት ብዙ ጊዜ ዳግም ባልተወለዱ ሃይማኖተኞች ዘንድ ለፕሮግራም ማሳረጊያ አሊያም መፀለይ ላቃታቸው ሰዎች የሚመከር ፀሎት ነው::ላንዳንዶች ደሞ #ከሃጢያት #ማገገቢያ ክኒን ተደርጎም ይወሰዳል::አንድ በቅርቡ ዳግም የተወለደ ወንድሜ ያኔ ዳግም ሳይወለድ(ዼንጤ እያለ) የስጋውን ድካም ለማሸነፍና ከኃጢያቱ ለመንፃት ብዙ እንደጣረና ብዙዎችን "አገልጋዮች"እንዳማከረ ነግሮኝ::ከነዛ ውስጥ "የአባታችን ሆይ ፀሎትን ደጋግመህ ፀልይ"ያሉት እንደነበሩ ነግሮኝ ነበር::እኔም ታዲያ ፀሎቱን ደጋግመህ ስለፀለይክ ከሃጢያትህ ነፃ ወጣህ? ብዬ ስጠይቀው::ባክህ እሱ መብትሄ አልሆነኝም ብሎ ነግሮኛል::እውነት ነው እኔም ከልጅነቴ ጀምሮ ዼንጤ ስለነበርኩ ይህንን ፀሎት ደጋግሜ ፀልያለው ነገር ግን አልዳንኩበትም::ሳይገባኝና ሳይገባኝ ነበር ምፀልየው።አሁን ዳግም ከተወለድኩ ቡሃላ ነው የእያንዳንዱ የፀሎቱ ሐረግ የገባኝ::ኢየሱስ ፀሎቱን ያስተማረው በወቅቱ ለነበሩ እንደ እኔ ላሉ አይማኖተኞች አልነበረም፤ወይም ላልዳኑ ሰዎች አይደለም።ለዳኑት(የኃጢያታቸውን ስርየት በአንዴ ለተቀበሉት) ለደቀመዛሙርቱ እንጂ::እንደዚህ ብላችሁ ፀልዩ አላቸው "በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ ስምህ ይቀደስ..." ሲጀመር እ/ር የሁሉም አባት አይደለም::ማንም ሃጢያት ያለበት ሰው እ/ርን አባቴ ብሎ የመጥራት መብት የለውም::እ/ር የሁሉ ፈጣሪ እንጂ የሁሉ አባት አይደለምና::(ዮሐ8:43-44) ኃጢያት ያለባቸው ሰዎች አባታቸው ዲያቢሎስ ነው።የእ/ር ልጅ የመሆንን ስልጣን የሚያገኙትና አባ አባት ብሎ የመጥራት መብት ያላቸው በልጁ በኢየሱስ ስም ያመኑ ብቻ ናቸው::በኢየሱስ ስም ማመን ማለት በኢየሱስ ፍፁም የማዳን ስራ ማመን ማለት ነው::ኢየሱስ ፈፅሞ ከሃጢያት እንዳዳናቸው የማያምኑ(ሃጢያት ያለባቸው) አማኞች ኢየሱስ ኢየሱስ ቢሉም በስሙ አያምኑም::ስለዚህ የእ/ር ልጆች አይደሉም! ጌታ ያሰተማረውን ፀሎት የመፀለይ መብትም በእ/ር ፊት የላቸውም! ኢየሱስ ያስተማረውን መረዳት ፈፅሞ ስለሚሳናቸው በሌላው በኢየሱስ ንግግር እንደተሰናከሉ ሁሉ በዚህም ፀሎት ይሰናከሉበታል::ደፋሮች ኃጢያት እያለባቸው እ/ርን "አባት" ብለው ይጠራሉ ልክ እንደ ፈሪሳውያን።አሁን ብዙ ዳግም ያልተወለዱ ክርስቲያኖች ለንስሃ ፀሎታቸው እንደማስረጃ ወደሚያነሱት ነጥብ እንምጣ የፀሎቱ ሐረግ እንዲህ ይላል "...እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን።.."
ምንም የማያከራክር አንድ ነገር ልንገራቹ።ይህንን ክፍል በፊደል ከተረዳነው የሚሰጠን ትርጉም እንደሚከተለው ነው።
፩ኛ.እ/ር በቅድመ ሁኔታ ነው ኃጢያትን ይቅር የሚለው ማለት ነው።ያው እኛ ሰዎችን ይቅር ስንል እየጠበቀ ማለት ነው።
፪ኛ.ኢየሱስ ሁሉንም ኃጢያት አላስወገደም እኛ ማረን እያልን ስንፀልይ የሚወገዱ የተወሰኑ ቀሪ ኃጢያቶችን አስቀርቶ ነው የሄደው ስለዚህ ሁሌ "#ይቅር በለኝ" እያልን ቀሪ ኃጢያቶችን ማስወገድ አለብን።የሚል ትርጉም ይሰጣል።

እነዚህ ሁለቱም ትርጉሞች ካጠቃላይ ከክርስቶስ የደህንነት ስራ ጋር መዝኑት።እንዲህ ብላችሁ ጠይቁ እውነት እ/ር በቅድመ ሁኔታ ነው ወይ እኔን ይቅር ያለኝ? እውነት እ/ር በልጁ በኢየሱስ ያላስወገደው በኔ የንስሃ ፀሎቶች የሚወገዱ ቀሪ ኃጢያቶች አሉ ወይ? ብለን ከጠየቅን መልሱ ግልፅ ነው።ኢየሱስ ሳያስወግድ ያስቀረው በንስሃ ፀሎት የሚወገዱ ቀሪ ሃጢያቶች የሉም!!! ስለዚ ይህ የፀሎት ክፍል በየትኛውም ሂሳብ ሃጢያት ስትሰሩ ስትሰሩ የንስሃ ፀሎት ፀልዩ የሚል ትርጉም ሊይዝ አይችልም።እርስ በእርስ ስንበዳደል ይቅር መባባል እንዳለብን ያወራል እንጂ ኃጢያት ስትሰሩ ስትሰሩ የንስሃ ፀሎት ፀልዩ የሚል መልዕክት የለውም።እኛ የተበዳደልነውን ኃጢያት ይቅር ስንባባል ይህ የእኛ ኃጢያትም በእ/ር ዘንድ ይቅር እንደሚባል ነው ቃሉ ሚያስረዳን።ሰዎች ዳግም ከተወለዱ በኋላ እንኳን በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ኃጢያትን ይሰራሉ።ያ ኃጢያታቸው ግን በነሱ ጥረት በንስሃ ፀሎት አይደለም የሚወገደው፣ኢየሱስ አስቀድሞ ያስወገደው፣ ይቅር የተባለ ኃጢያት ነው።አሁን ብዙ ክርስቲያኖች ገሃነም የሚገቡት ኢየሱስ የነሱን ያለፈውን፣ያሁኑንና የወደፊቱን(past,present and future sins) ኃጢያት ጭምር ከዛሬ ፪ሺ አመታት በፊት ማስወገዱን ባለማመናቸው ነው።ይህንን የፀሎት ክፍል በደንብ ለመረዳት (ማቴ18:25-35) ያንብቡ።
አሁንም ደግሜ ልንገራቹ
ኢየሱስ ሳያስወግድ ያስቀረው በንስሃ ፀሎት የሚወገድ ቀሪ ኃጢያት የለም!!!ይህንን አልቀበልም ብላቹና በልባቹ እልከኝነት ተመርታቹ ገሃነም ብትገቡ እኔ ከእናንተ ነፍስ ህዳ ነፃ ነኝ።
ሌላው ትልቁ ችግራቹ መፅሀፍ ቅዱስን ለራሳቸው ዳግም ባልተወለዱ ወንጌላዊዎች፣ፓስተሮች፣ነብዮች፣ሐዋርያዎች መማራቹና፤እናንተ ራሳችሁ ዳግም ባልተወለደ (ኃጢያት ባለበት) አዕምሮ ቃሉን ለመረዳት መሞከራቹ ነው።ብዙዎቻቹ ዳግም ሳትወለዱ ዳግም ተወልጃለው እንደምትሉ አውቃለው።እኔም ለብዙ አመታት እል ስለነበር፤ነገር ግን በንስሃ ፀሎት እያመነ ድኛለው ወይም ዳግም ተወልጃለው የሚል ሁሉ ራሱን ያታልላል፤በጨለማ እየተመላለሰ በብርሃን ነኝ የሚል ሰው ነውና።ወይም ተመላላሽ ታካሚ ሆኖ ድኛለው የሚል አይነት ሰው ነው።ተመላላሽ ታካሚ ከሆንክ አንተ በሽተኛ ሰው ነህ እንጂ ጤነኛ አይደለህም።ኃጢያት ያለበት ሰው ሁሉ ዳግም አልተወለደም።ዳግም ለመወለድና መፅሀፍ ቅዱስን በአግባቡ ለመረዳት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመን ግድ ነው።ስለዚህም እላቹሃለው በዚህ ወንጌል እመኑ ከእ/ር ቁጣም አምልጡ።

📖📖📖📖📖📖 ሼር
❤❤❤❤❤❤❤❤❤

@freenlmbookss

#ደህንነት

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

የእግዚአብሔር ጽድቅ ተገልጦዋል።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ሕግና ነቢያት መስክረውለታል። መዝሙራት ተቀኝተውለታል። ሕዝበ እስራኤል በጉጉት ጠብቀውታል። የሰውን ዘር ከሐጢአት ጥልቅ መንጭቆ የሚያወጣ የሐጢአተኞች ተስፋና መድሃኒት መሆኑ ተስፋ ጥሎበታል። ልክ በማይድን በሽታ ተይዞ ሞቱን በስቃይ የሚጠባበቅ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ የተያዘ ሰው ለደዌው ፈውስ የሚሰጠውን መድሃኒት በተስፋ እንደሚጠባበቅ በሐጢአት በሽታ ተይዘው ዕጣ ፈንታቸው የዘላለምን ሞት መሞት መሆኑን የተረዱ ሐጢአተኞችም ያንን መድሃኒት በተስፋ ሲጠብቁት ቆይተዋል።

በሰይጣን ክልል ውስጥ ይህ የምስራች ትልቅ መረበሽን አምጥቶዋል። ሰይጣንና ጭፍሮቹ ሐጢአትንና ሐጢአተኛን እየተመገቡ በመኖር ደፈዕድሜያየውን አርዝመዋል። አሁን ግን ሐጢአትን የሚያስወግድ ሐጢአተኛን የሚያድን መድሃኒት ተገኝቶዋል። በሰይጣን ግዛት ውስጥ በዚህ መድሃኒት ላይ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ሐጢአተኞችን የማሳሳት ስራ በስፋት እንዲሰራ ተወስኖዋል። ይህ የሐሰት ፕሮፓጋንዳም ተሳክቶለት በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነትን ቢያገኝም መድሃኒቱን ያልፈቀዱ በዘላለም ሞት አሸልበዋል።

ይህ መድሃኒት "የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው። "አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሠከረለት #የእግዚአብሔር #ጽድቅ ያለ ሕግ #ተገልጦዋል። እርሱም ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው #የእግዚአብሔር #ጽድቅ ነው።" (ሮሜ 3:21-22) "ተገልጦዋል" የሚለው ቃል ቀድሞ አለመገለጡን የሚያሳይ ነው። ይህ "የእግዚአብሔር ጽድቅ" በይፋ የተገለጠው እንዴትና መቼ ነው?

"ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መጣ። ዮሐንስ ግን፦ እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል፤ አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር። ኢየሱስም መልሶ፦ አሁንስ ፍቀድልኝ፤ #እንዲህ #ጽድቅን #ሁሉ #መፈጸም ይገባናልና አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት።" (ማቴዎስ 3:15) ኢየሱስ 30 አመት እስኪሆነው ድረስ በይፋ እንዳልተገለጠ ይታወቃል። ሰዎችን ከሐጢአት ለማድን የሚያስችለውን ስራ የጀመረው "ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም" በአጥማቂው ዮሐንስ በተጠመቀ ጊዜ ነበር። ያኔ "ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም" ተጠምቆ ከውሃ ሲወጣ "ሰማያት ተከፈቱ" "መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል" በኢየሱስ ላይ ወረደ። እግዚአብሔርም "በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው" በማለት ምስክርነቱን ሰጠ። (ማቴዎስ 3:16-17)

ኢየሱስ የፈጸመው "ጽድቅ ሁሉ" ሌላ ሳይሆን "በሕግና በነቢያት የተመሠከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ" ነው። ይህ ጽድቅ ኢየሱስ ስለ እኛ "ሐጢአት" የተደረገበትና እኛም "በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ" የተደረግንበት ነው።

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

በእግዚአብሔር ጽድቅ የማያምን ሰው ሐጢአት አለበት። ሐጢአት ያለበት ሰው አልዳነም። ያልዳነ ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግስት አይገባም።

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

ን ስም ቅድስናንና ክብርን መስጠት እንችላለን፡፡

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

የሕጉ አላማና የኢየሱስ መሰቀል
=============
ከዕለታት አንድ ቀን ሰዎች በሓጢያት የተሞሉባትና የተበላሸባት አንዲት አገር ነበረች። ንጉሱና ባሮቹ በመጨረሻ ተሰበሰቡና ይህንን ችግር ተወያዩበት በዚህ ስብሰባ ማብቂያ ላይም ሕዝቡ በጣም ብዙ ወንጀሎችን እየሰሩ በመሆናቸው ሕጎቻቸውን ማጥበቅ እንደሚገባቸው ደመደሙ።

ስለዚህ አዳዲስ ሕጎችን አወጡ እነዚህ አዳዲስ ሕጎች የሚሰርቅ እጆቹ እንደሚቆረጡና የሚያመነዝር አያኖቹ ተጎልጉለው እንደሚወጡ ይናገራሉ። እነዚህን ጥብቅ ሕጎች ደነገጉና በሕዝቡ ፊት አቀረቡ። እነዚህ ሕጎች ከተደነገጉበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ ነበሩ።

በመተላለፊያ መንገዶቹ በእያንዳንዱ ማዕዘንም ወንጀሎችን ቢሰሩ አሰቃቂ መዘዞች እንደሚገጥሙዋቸው የሚያስጠነቅቁ ማስታወቂያዎች ተለጠፉ። ሕዝቡም ፈራ ቅጣት ሳያገኛቸው ወንጀሎችን የሚሰሩ ሰዎችም ቅጣቱን በአእምሮዋቸው በመሳል በፍርሃት መንቀጥቀጥ ጀመሩ፡፡

ሳይታሰብ የንጉሱ ልጅ አመነዘረ። እነዚህ ጠንካራ ሕጎች ከተደነገጉ በኋላ የተላለፋቸው የመጀመሪያው ሰው መስፍኑ ነበ። ንጉሱም «አድልዎ የምናደርግ ከሆነ ሕጎቹ በጣም ውጤታማ አይሆኑም መስፍኑን አምጡትና ሕጉ የሚለውን አድርጉ» አለ አሁን መስፍኑ አይኖቹ ሊወጡ ነው። ንጉሱ አባቱ ሰመሆኑ በጣም አዘነ። ለሚገዛቸው ሕዝቦች ጥሩ አርአያ መሆን ይገባው ነበር።

ነገር ግን በዚያው ጊዜ ደግሞ ልጁ ኣይኖቹን ሲያጣ ማየት አልቻለም። በዚህ ጉዳይ በጣም ከተጨነቀ በኋላ ውሳኔ ወሰነ። ከእርሱ አይኖች አንዱ ከልጁ አይኖች ደግሞ አንዱ እንዲወጣ አሳብ አቀረበ። በሕጋቸው መሰረትም ችሎት አቆሙና በሕዝቡ ፊት ቅጣቱን ኣስፈጸሙ። በዚህ ምክንያት የአገሪቱ ሕጎች ጽኑ ሆኑ የወንጀል ጥፋቶችም ቁጥር በእጅጉ ቀነሰ፡፡

በዚህ ታሪክ ላይ እንደተደረገው የሐጢያት ቅጣቶች በሕጎቹ መሰረት መደረግ ይኖርባቸዋል። ጌታ መስቀሉ «የሐጢያት ደመወዝ ሞት ነው» በሚለው ሕግ ላይ የተመሰረተ የእግዚአብሄር የጽድቅ ውሳኔ ነበር። እግዚአብሄር ከረጅም ጊዜ በፊት ሕጉን እንድንጠብቅ ሰጠን ለምሳሌ «ኢይን በአይን፣ ጥርስ በጥርስ፣ እጀ በእጅ፣ እግር በእግር» ዘጸአት 21:20 የሚል ሕግ አለ። ይህ የእርሱ ሕግ ነበር።

ነገር ግን ሐጢያተኞች ሆነን የተወለድን እኛ ሰዎች ሕጉን ሙሉ በሙሉ መጠበቅ አልቻልንም። ሰዎች በእግዚአብሄር መልክ የተፈጠሩ ቢሆኑም ሰዎች በሰይጣን ፈተናዎች ወጥመድ ውስጥ ወደቁና በእግዚአብሄር ላይ ሐጢያት ሰሩ። እግዚኣብሄር ግን ወደ ሲዖል አልሰደደንም። በፋንታው በልጁ ጥምቀት፣ ስቅለትና ትንሳኤ አማካይነት ሕዝቡን ጻድቅ ሕዝብ አድርጎ ሊመለስ ልጁን ወደዚህ ምድር ላከው፡፡


ኢየሱስ የተሰቀለው ለምን ነበር? እናንተንና እኔን ለማዳን በአጥማቂው ዮሐንስ በመጠመቁ መሰቀል ነበረበት። ኢየሱስ ወደዚህ ምድር የወረደው ለምን ነበር? እግዚአብሄር የሰው ስጋ የለበሰውና ወደዚህ ምድር የመጣው ለምን ነበር? ይህንን ያደረገው እኛን በጽድቅ መንገድ ለማዳን ልጆቹ አድርጎ ሊቀበልንና የዘላለምን በረከቶች ለእኛ ለመስጠት ነበር።

እኛ የእምነት ሰዎች ኢየሱስ የተሰቀለበትን እውነተኛ ምክንያትና ትርጉም ማወቅ ይገባናል። ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ከሐጢያት ለማዳን እንዲህ ያለ አሰቃቂ ቅጣትና በቃላት ሊገለጡ የማይችሉ መከራዎችን እንደተቀበለ ልንገነዘብ ይገባና። ይህ የእግዚአብሄር ፍቅር እንደሆነ ልናውቅ ይገባናል። ይህ ሁሉ ሒደት እግዚአብሄር ለእኛ ያለው የጽድቅ ደህንነት ነበር፡፡


በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ባዳነን በኢየሱስ ክርስቶስ ስናምን ስይጣን እንደገና በጭራሽ ሊተናኮለን አይችልም። ድክመቶች ቢኖሩብንም ኢየሱስ ክርስቶስ ድካሞቻችንንና ስቃዮቻችንን በሙሉ ስለወሰደ፣ ለእኛ ስለሞተና ከሙታን ስለተነሳ አሁንም የእግዚአብሄር ልጆችና የእርሱ ቅዱስ ሕዝቦች ነን እርሱ በዚህ ሁሉ ወስጥ በትክክል አዳነን፡፡

share and join our channel
T.me/chrstianbooks

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

«ከእምነት ያልሆነ ሁሉ ሐጢኣት ነውና» (ሮሜ 14፡2)
ሐጢአት ምንድነው? ሐጢያት በእግዚአብሄር ቃል ኣለማመን ነው፡፡ በተለይም በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ቃል ኣለማመን ትልቅ ሐጢያት ነው:: እግዚአብሄር ለአዳምና ለሔዋን በኤድን ገነት ውስጥ የነበሩትን ፍሬዎች በሙሉ ሰጥቶዋቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ከዚያ በልተው እንዳይሞቱ መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ እንዳይበሉ ተናገረ፡፡ ነገር ግን አዳምና ሔዋን በእግዚኣብሄር ቃል አላመኑምና በሰይጣን ዲያብሎስ ተታልለው ፍሬውን በሉ፡: እነርሱ ፍሬውን የበሉት ከልባቸው በእግዚአብሄር ቃል ባለ ማመናቸው ነው፡፡ በመጨረሻም በእግዚኣብሄር ቃል ባለ ማመናቸው ሐጢያት ወደ አለም ገባ፡፡ በሐጢያት ምክንያትም ሞት መጣ፡፡ (ሮሜ 5፡12) ሐጢያት የገባባቸው የራሳቸው የመልካምና የክፉ መስፈርት ስለነበራቸው ነው::
ሰዎች የእግዚአብሄርን ቃል ባለማመን ሐጢያተኞች ሆኑ፡: አዳምና ሔዋንም በእግዚኣብሄር ቃል ባለማመናቸው መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ በሌና ሐጢያተኞች ሆኑ፡: እነርሱ ሐጢያተኞች ከሆኑ በኋላ በመጀመሪያ ስጋዊ ኣይኖቻቸው ተበልጥጠው ተከፈቱና የስጋን ነገሮች እንዲያዩ ኣስቻላቸው፡፡ ታዲያ ይህ ማለት የስጋ ኣይኖቻቸው ከዚያ በፊት የተከደኑ ነበሩ ማለት ነው? የለም፡: ጉዳዩ ያ አልነበረም:: በፋንታው ያ ማለት ከእግዚአብሄር መለኪያዎች ይልቅ የራሳቸውን የስጋ መለኪያዎች ያዙ ማለት ነው:: ይህ ማለት በውስጣቸው የላቁ የሰብኣዊነት አስተሳሰቦች መለኪያዎች አበጁ ማለት ነው:: ከዚህ የተነሳ በእግዚአብሄር ቃል ባለማመናቸው ሐፍረት በእነርሱ ላይ መጣ ማለት ነው::
@freenlmbookss

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

ሐጢአተኞች የሆናችሁት በራሳችሁ ሐጢአቶች ነው ወይስ አዳም በእግዚአብሔር ላይ በፈጸመው በደል??
" እንግዲህ በአንድ በደል ምክንያት ፍርድ ለኵነኔ ወደ ሰው ሁሉ እንደ መጣ፥ እንዲሁም በአንድ ጽድቅ ምክንያት ስጦታው ሕይወትን ለማጽደቅ ወደ ሰው ሁሉ መጣ።" (ሮሜ 5: 18)
@freenlmbookss

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

በነጻነት ሐሳብዋን ያጋሩ።
@dehnetbot

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

ኢየሱስ የሚያስፈልጋቸው ከውልደታቸው ጀምረው እስከ እለተ ሞታቸው ቀን ድረስ ሐጢአት የሚሰሩ መሆናቸውን የሚያምኑና፣ በሐጢአቶቻቸው ከመኮነን በቀር ተስፋ የሌላቸው መሆኑን የተገነዘቡ ሰዎች ናቸው። ሰው እኔ በራሰ መንገድ መዳን እችላለሁ የሚል ከሆነና እግዚአብሔር ያዘጋጀውን የደህንነት መንገድ የማይፈልግ ከሆነ መዳን አይችልም። ለዚህ አይነት ሰው ክርስቶስ አያስፈልገውም።

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

ኢየሱስ በመጠመቅና በመስቀል ላይ በመሞት የአለምን ሁሉ ሐጢአት ለመደምሰስ ቅዱስ የሆነውን ስጋውን ለአንድ ጊዜ ለዘለዓለም ሕያው መጽዋዕት አድርጎ በማቅረብ ቀድሶናል። ሐጢአት አልባ ጻድቅ አድርጎናል። ስለዚህ እግዚአብሔርን እባርከዋለሁ

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

በወንጌል አላፍርም። በወንጌል አላፈርም ማለት በእግዚአብሔር ጽድቅ እመካለሁ ማለት ነው። የእግዚአብሔርን ጽድቅ መመካት ደግሞ ኢየሱስ የፈጸመውን ጽድቅ ሁሉ በማመን የሐጢአትን ስርየት ማግኘት ማለት ነው። ኢየሱስ በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ስጠመቅ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ ፈጽሞልኛል ያ ማለት ደግሞ ኢየሱስ ከውልደቴ እስከ ለተ ሞቴ ቀን የሚሰራውን የትላንቱን፣የዛሬውንና ከዚህ በኋላ የሚሰራቸውን ሐጢአቶች በሙሉ አስወግዷል ማለት ነው። ኢየሱስ ሐጢአትን ማስወገዱ ለእኔ በወንጌል እውነት በማመን የዘለአለምን ሕይወት መቀበል ማለት ነው። በዚህ ስለምያምን ሁልጊዜ አልታወክም። በወንጌል አላፍርምና።

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

አዲስ ፍጥረት ማለት. . .

ኃጢያትን መረዳት በደልን መቀበል
ከህግጋት ተምሮ፣ እኔነትን መግደል

አዲስ ፍጥረት ማለት...

ከልብ የሚፈልቁ ኃጢያቶችን ማወቅ
ግብዝ አለመሆን በውሸት አለመድረቅ

አዲስ ፍጥረት ማለት...

ከማዳኑ ባህር ከሥርየቱ ጠልቆ
ከህግጋት ተምሮ መዳኛውን አውቆ
የአምላክን መመሪያ በሙሉ መፈፀም
አንዲት ሳትዘንፍ በስርዓቱ ማዝገም።


አዲስ ፍጥረት ማለት...

ከብሉያት መፅሐፍት ክርስቶስን ማግኘት
ከፈቃዱ መማር በፅድቁ መዋኘት
ጥላውን ከአካሉ ማሰር ማገናኘት

አዲስ ፍጥረት ማለት. . .

ከዚህ ዓለም ምኞት ከተድላ እሩጫ
ገንዘብ ቁሳቁስን ካደረገው ምርጫ
በጥቅስ ከታጀበ ከሴጣን ልግጫ
መሸሽና መራቅ
በእግዚአብሔር ፅድቅ ሥር መሰወር መደበቅ

አዲስ ፍጥረት ማለት. . .

በውኃና በደም ከአመፃ መጥራት
ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ መመራት
የራስን ፅድቅ ጥሎ በእግዚአብሔር ፅድቅ መኩራት

አዲስ ፍጥረት ማለት...

ለእውነተኛው አምላክ ለእውነት መታዘዝ
የልብ ሸለፈትን ዮርዳኖስ ላይ መግረዝ
የተረት ትምህርትን በፅድቅ ቃል ማውገዝ

አዲስ ፍጥረት ማለት...

አንድ መሆን መደመር መሆን በክርስቶስ
የጥልን ግድግዳ በእርሱ ሥጋ ማፍረስ
ከእርሱ ጋር መሰቀል ለኃጢአት መገደል
በእርሱ ትንሣዬ ውስጥ ፃድቅ ሆኖ መብቀል

አዲስ ፍጥረት ማለት...

ውኃ፣ደም፣መንፈሱን
ሦስቱን ምስክሮች በልቦና ማተም
የሎጥ ሚስት ሳይሆኑ ወደ ፊቱ መትመም
የኋላውን መርሣት ለፊቱ መዘርጋት
አክሊል ለመጨበጥ የእምነት ፍሬ ማፍራት

አዲስ ፍጥረት ማለት...

ኃጢአት እየሰሩ፣የፅድቅ ሕይወት መምራት
በከሳሹ ሴጣን፣ አናት ላይ መጫማት

አዲስ ፍጥረት ማለት...

የሰማዩን ስፋራ በረከትን መውረስ
ለዓለም ሳይገዙ በመንፈስ መታደስ
በክርስቶስ ጥምቀት ክርስቶስን መልበስ

አዲስ ፍጥረት ማለት...

የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠንቅቆ መረዳት
ዘመንን መዋጀት በተስፋ መመራት

አዲስ ፍጥረት ማለት...

የመንፈስን ስራ በመንፈስ መለየት
ኑፋቄን ኑፈቄ፣እውነትን እውነት ነው በማለት መገኘት

አዲስ ፍጥረት ማለት...

መወገዱን ማመን የዚህ ዓለም ኃጢያት
"የንስሃ ፀሎትን" ከንቱነት መረዳት
ጥምቀት፣ሞት ትንሣዬን በኃጢአት ላይ ማብራት
የሃሰት ግርዘትን፣በቃሉ ኃይል ማጥፋት።

አዲስ ፍጥረት ማለት...
ብ..ዙ ነው ትርጉሙ
እንደ ፃድቅ ኖሮ ማፅደቅ ነው ሸክሙ
በሴጣን መንግስት ላይ መሰልጠን











አዲስ ፍጥረት ማለት. . .

ኃጢያትን መረዳት በደልን መቀበል
ከህግጋት ተምሮ፣ እኔነትን መግደል

አዲስ ፍጥረት ማለት...

ከልብ የሚፈልቁ ኃጢያቶችን ማወቅ
ግብዝ አለመሆን በውሸት አለመድረቅ

አዲስ ፍጥረት ማለት...

ከማዳኑ ባህር ከሥርየቱ ጠልቆ
ከህግጋት ተምሮ መዳኛውን አውቆ
የአምላክን መመሪያ በሙሉ መፈፀም
አንዲት ሳትዘንፍ በስርዓቱ ማዝገም።


አዲስ ፍጥረት ማለት...

ከብሉያት መፅሐፍት ክርስቶስን ማግኘት
ከፈቃዱ መማር በፅድቁ መዋኘት
ጥላውን ከአካሉ ማሰር ማገናኘት

አዲስ ፍጥረት ማለት. . .

ከዚህ ዓለም ምኞት ከተድላ እሩጫ
ገንዘብ ቁሳቁስን ካደረገው ምርጫ
በጥቅስ ከታጀበ ከሴጣን ልግጫ
መሸሽና መራቅ
በእግዚአብሔር ፅድቅ ሥር መሰወር መደበቅ

አዲስ ፍጥረት ማለት. . .

በውኃና በደም ከአመፃ መጥራት
ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ መመራት
የራስን ፅድቅ ጥሎ በእግዚአብሔር ፅድቅ መኩራት

አዲስ ፍጥረት ማለት...

ለእውነተኛው አምላክ ለእውነት መታዘዝ
የልብ ሸለፈትን ዮርዳኖስ ላይ መግረዝ
የተረት ትምህርትን በፅድቅ ቃል ማውገዝ

አዲስ ፍጥረት ማለት...

አንድ መሆን መደመር መሆን በክርስቶስ
የጥልን ግድግዳ በእርሱ ሥጋ ማፍረስ
ከእርሱ ጋር መሰቀል ለኃጢአት መገደል
በእርሱ ትንሣዬ ውስጥ ፃድቅ ሆኖ መብቀል

አዲስ ፍጥረት ማለት...

ውኃ፣ደም፣መንፈሱን
ሦስቱን ምስክሮች በልቦና ማተም
የሎጥ ሚስት ሳይሆኑ ወደ ፊቱ መትመም
የኋላውን መርሣት ለፊቱ መዘርጋት
አክሊል ለመጨበጥ የእምነት ፍሬ ማፍራት

አዲስ ፍጥረት ማለት...

ኃጢአት እየሰሩ፣የፅድቅ ሕይወት መምራት
በከሳሹ ሴጣን፣ አናት ላይ መጫማት

አዲስ ፍጥረት ማለት...

የሰማዩን ስፋራ በረከትን መውረስ
ለዓለም ሳይገዙ በመንፈስ መታደስ
በክርስቶስ ጥምቀት ክርስቶስን መልበስ

አዲስ ፍጥረት ማለት...

የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠንቅቆ መረዳት
ዘመንን መዋጀት በተስፋ መመራት

አዲስ ፍጥረት ማለት...

የመንፈስን ስራ በመንፈስ መለየት
ኑፋቄን ኑፈቄ፣እው

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

በልጁ የሚያምን የዘለአለም ሕይወት አለው ማለት ምን ማለት ነው? እንዴት ነው በልጁ ማመን ያለብን? በደፈናው ኢየሱስ ጌታ ነው ኢየሱስ ወዳጄ ነው ኢየሱስ አባቴ ነው ማለት በልጁ ማመን ነው? እናንተ ምን ትላላችሁ? እንዴት ነው በኢየሱስ ያመናችሁት? በምስባክ በምደረግ ጥር? በየጎዳናው ሰዎች ኢየሱስ ያድናል እያሉ ስናገሩ ሰምታቹ ወይንስ መጽሐፍ በምለው መሠረት ነው ኢየሱስን ያመናችሁት? አሁን በኢየሱስ አምናችሁ ከሆነ ሐጢአት አለባችሁ? በየቀኑ የንሰሐ ጸሎት ትጸልያላችሁ? እስቲ በዚህ ዙሪያ እንነጋገር። @jonahnlm ላይ አናግሩኝ።

Читать полностью…

ነጻ መንፈሳዊ የክርስቲያን መጽሐፍቶችንና ትምህርቶች ለማግኘት👈👇

@dehninet
@freenlmbookss

Читать полностью…
Подписаться на канал