✨«እናንተ የዓለም ብርሃን ፣ የምድርም ጨው ናችሁ»
🔷ብርሐንና ጨው ከተባልን ዘንዳ፤ እንግዲያውስ እውነተኛው ብርሐንና እውነተኛው ጨው ምንድነው አልን ! ቃሉን ልንተነትን ሳይሆን ቃሉ ያጫረብንን መረዳት ከአኗኗራችን ዘይቤ ጋር አዛምደን፣ በዘመናችን ታይታ ወዳድነት እና የመታየት ልክፍት፥ ሳናውቅ ለገባን እኛ ነገሩን ለማስታወስ ያህል ይህን አልን!
📍ብርሐን ያሳያል እንጅ አይታይም! ብርሐን የማይታየው ጨለማ ውስጥ ስለሆነ አይደለም፣ ይልቁንም ብርሐን ብርሐኑን የሚያበራው ወደራሱ ሳይሆን ወደሌሎች በመሆኑ ነው! ሌላውን ለማሳየት እንጅ ራሱን ለማጉላትና ለማድመቅ የሚታገል ብርሐን በዙሪያው የሚረጨው ጨለማ ብቻ ነው! እዚህ ላይ ብርሐን ስል የብርሃን ምንጩን ጭምር ማለቴ ነው።ብርሃን ተፈጥሮው ማሳየት እንጅ መታየት አይደለም።
🔷ፀሐይ በምትረጨው ብርሃን ዓለም ይነጋል ፤ ፍጥረት ሁሉ ይደምቃል፣ ተክሎች ያድጋሉ፣ አበቦችም ይፈካሉ፣ ቆፈን ይገፈፋል፤ ፀሐይን ራሷን ግን ለሴከንዶች እንኳን ማየት አንችልም።ታሳያለች እንጅ አትታይም! የቤታችንን አንፖል ከነመኖሩ የምናስታውሰው ቤታችን ሲጨልም ብቻ ነው፣ ግን ሁሉን ነገር የምናየው ከአንፖሉ በሚወጣው ብርሃን ነው። አንድ ሰው ሻማ የሚለኩሰው ሻማውን ሲያይ ለማምሸት አይደለም ፣ በሻማው ብርሃን አካባቢውን ሊያደምቅ ነው! መታየትን የምትሳሳ ነብስ ብርሐን አይደለችም፤ ይልቅ ብርሐን ያስፈልጋታል፤ በሌሎች ጨለማ የምትሳለቅ ነፍስ ብርሐን በውስጧ የለም ፣ብርሐን በተገኘበት የሌሎችን ጨለማ ያነጋል እንጅ በጨለማቸው አይዘባበትም።
📍ጨው እና ብርሃን ተመሳሳይ ባህሪ አላቸው፤ ጨው ብቻውን ምግብ ነኝ ብሎ ማዕድ ላይ አይኮፈስም፤ ቢኮፈስም የሚነካው የለም! ጨው ምግቡ ውስጥ አይታይም ግን ምግቡን ያጣፍጣል! በአጭሩ ነፍሳችሁ መታየትን መጉላትን መደነቅን መወደስን ከፈለገች «ሰዋዊ ነው» በሚል ትሁት መታበይ ራሳችሁን አታታሉ። እንደዛ ካሰባችሁ ብርሐንም ጨውም አይደላችሁም! እንደውም ትክክለኛ ጨውነታችሁ የሚታወቀው በእናተ በጎነት ሌሎች ሲወደሱ ነው! በተረት እንዝጋው «በጨው ደንደስ በርበሬ ተወደስ» ይሄው ነው!
✍አሌክስ አብርሃም
ውብ አሁን❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍@EthioHumanityBot
🎄በመላው ዓለም ለምትኖሩ የክርስትና እመነት ተከታይ እህት ወንድሞቻችን እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
💛በአሉ የሰላም የፍቅርና የደስታ ይሁንልን🎄
❤️🏑 መልካም የገና በአል 🏑
@ETHIOHUMANITY
@ETHIOHUMANITY
❤️ወንዝ መርጦ አያጠጣም። አጎንብሶ ሊጠጣ ለወደደ ሁሉ ሳይሰስት ያጠጣል። ደግነታችን እንደ ወንዝ ይሁን! ሳንመርጥ፣ ለለመነን ሁሉ እጃችንን እንዘርጋ። ወንዝ ወደፊት ብቻ የሚሄድ ወደኋላ የማይመለስ ሲሆን ቀጣይነቱን ይመሰክራል፤ የኛም ደግነት እንዲሁ ዛሬ ተጀምሮ ነገ የማያበቃ፤ ሁልጊዜ እንደ ወንዝ የሚፈስ መልካምነት፣ በጎነት የተሞላበት ይሁን።
📍መርዳት ዕድል ነውና እንጠቀምበት! ከእኛ የሆነ ምንም ነገር የለም ለፈጣሪ እጅ ሆነን እንደምንሰጥ ልናስብ ይገባናል። እውነተኛ ስጦታ ከትርፍ ሳይሆን ካለን ላይ ነውና ተጎድተን እስክንሰጥ ድረስ ገና እንዳልሰጠን ልንረዳ ይገባል፡፡
እያዩ ፈንገስ በመድረኩ ላይ ሲናገር
"ላለመርዳት ኪስህን ሰበብ አታድርግ። ባዶ ኪስ ነህ ማለት የምትሰጠው ምንም ነገር የለህም ማለት አይደለም፤ ቢያንስ የምትሰጠው ባዶ ኪስ የሆነ ሱሪ አለክ ማለት እንጂ።
ባዶ ኪስ የሆነ ሱሪ መስጠት ቢያቅትህ፥ በባዶ ኪስህ እጁን እንዲያስገባ ፍቀድለት። ቢያንስ አንድ እጁን ከብርድ ትከላከላለህ'' ይለናል ።
❤️እናም ወዳጄ ቁምነገሩ
ሰውን እንደራስ ለመውደድ ቅን አዕምሮ፤ ደግ ልብ ይፈልጋል፡፡ አንተም ፈጣሪን የምትሻ ከሆነ ወደ እሱ ቤት መሄድ አለብህ። ቤቱም የሰው ልጅ ሁሉ ነው ፤ የታመመን ጠይቅ፣ የተቸገረን እርዳ አግዝ ታማኝ ሁን! በዚህ ልክ ለፈጣሪ ስትቀርብ፣ ስኬትህም ሆነ በረከትህ የትም አይሄድብህም።
ፈጣሪ ለሁላችንም ልበ ሰፊና ቅን ልቦና ይስጠን!
ውብ አዳር❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot
❤️ጨለማው ላይ ብታፈጥ ያለ ሰዓቱ አይነጋም።ፈጣሪህን ትተህ በመከራህ ላይ ብታፈጥ አንዳች ጥቅም የለውም። ካስተዋልከው ጨለማም ውበት አለው። ከካባ ይልቅ ደማቅ ነው። እሾህም አበባ አለው። ክፉ ሰውም አንድ ጥሩ ነገር አለው። ልብ አድርግ ለክረምት በጋ፤ ለሌሊት ቀን አለው። ላንተም ጊዜ አለህ። ጊዜን የሚሰጥ ራሱ ጊዜ ሳይሆን የጊዜ ባለቤት ፈጣሪ እንደሆነ እመንና ጠብቅ።
ጊዜ ለታጋሾች የማታሳየው የለም። መስበርም መጠገንም ትችላለች ፣ አንተርሳ ትዘቀዝቃለች ፣ ዘቅዝቃ ታቃናለች። ለጊዜ የሚሳናት የለም፣ እንዳወጣች ታወርዳለች ። አንተም በፈታኝ ጊዝያቶች ክብርህን ጠብቅ። ፈተና ውስጥ እንኳ ብትሆን የሥሜት ብስለትህን እና ራስ ገዝነትህን አሳይ። ታጋሽ፣ ፅኑ፣ ተረጂ ለመሆን እንዳትዘነጋ።
📍እንደ እንስት ውበት ያጌጠው ህይወታችን ፣ ቀን ሲገፋ ይደበዝዛል እስከተፈቀደልን አብርተን ጊዜ ሲቋጭ ጭልመት እንላበሳለን። አጥቶ ማግኘት እንዳለው አግኝቶ ማጣት አለ ፣ ብርሀኑ ቢጨልም አንከፋ ለበጎ ነው፣ ጭልመት በብርሃን ሲቀየር አንገረም። ምንም ዘላለም ሊቆይ አልመጣም።
ተስፋ ከቤታችን አይጥፋ!
ውብ ምሽት❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot
💎እንደ ንስር ወደ ላይ ከፍ በል
ወዳጄ ንስር ሁን በቀቀንነት ይቀርብህ። በቀቀን የሌሎችን ሰዎች ሕይወት በመመሰል ውድድር ከፍ ብሎ መብረር አይችልም። ስጦታውን፣ እውቀቱን እና ክህሎቱን ከማዳበር ይልቅ ሌሎችን መስሎ መኖር ይመቸዋል።
ሕይወት ደግሞ በተቃራኒው ከበቀቀኖች ይልቅ ለንስሮች ፍሬዋን ትሰጣለች። ተፈጥሮ ብዙ ቀለም ፣ ብዙ ዕድል፣ ብዙ ፈተና ናት። ንስር አሞራ የለውጥ ተምሳሌት ተደርጎ የሚወሰደው በስራ የዳበረ ከእውነተኛው ዓላም ጋር የተሰናሰለ ስብእና ስለገነባ ነው።
📍ንስር የአእዋፋት ሁሉ ንጉስ ነው ሲባል በዋዛ እንዳይመስላችሁ። ንስር የሃይል ሚዛኑን ለመጠበቅ በቂ የሆነ ልምምድ የሚያደረግ ፣ የሚፈልገውን ነገር ከማድረግ የማይቆጠብ ቁርጠኛ የስነ ልቦና ተምሳሌት ነው ። ህይወቱን ሙሉ ትኩስ ስጋ እያደነ ነው የሚኖረው ። የሞተ ነገር አይነካም። የእለት ሲሳዩን እያደነ ይበላል እንጅ እንደ ቁራ የሞተ በክት እያሸተተ አይቀላውጥም። ሃይሉን እያደሰ የእንደገና ድልና ስኬቱን እያጣጣመ በንግስናው እስከወዲያኛው ይዘልቃል።
ሰማዩ ሲጠቁር ደማናው ወጀቡንም ሲያይል ሌሎች እዕዋፋት በየ አለቱና በየጥሻው ችፍርግ ወስጥ ይደበቃሉ በቤት ታዛ ስርም ይደበቃሉ። ንስር ግን ደስ ይለዋል ወጀቡ ሲጀምር ንፋሱን በመሞገት የራሱን ጥንካሬ ይላካበታል። የነፋሱን አቀጣጫ በመከተልም ይበራል። ረሱን ወደላይ ለማምጠቅና የከፍታውን ጫፍ ለመጨበጥ ይጠቀምበታል ፣ በዚህም ጥንካሬውን ይለካበታል።
💎ንስር ወጀብ ከመምጣቱ ብዙ አስቀድሞ ማወቅ ይችላል። እንዳወቀም ከፍታ ቦታ ለይ ይቀመጥና ንፋሱን ይጠብቃል። ወጀቡ ሲመጣ ከተቀመጠበት በመብረር ንፋሱ አግዞት ከወጀቡ በላይ እንዲበር ያደርገዋል። ወጀቡ ከታች ያለውን ዓለም ሲያተራምሰው፣ ንስሩ ከወጀቡ በላይ ይንሳፈፋል። እዚህ ላይ አንድ ነገር ልብ እንበል። ንስሩ ወጀቡን አላመለጠውም ፤ ተጠቀመበት እንጂ !!
📍የሕይወት ወጀብ ወደ እኛ ሲመጣ፣ ልክ እንደ ንስሩ ከወጀቡ በላይ መብረር እንችላለን፤ በሽታን፣ አደጋን፣ ውድቀትን፣ እና ሃዘንን ወደ ሕይወታችን የሚያመጣውን ንፋስ ለከፍታችን መወጣጫ ልናደርገውው እንችላለን።
🔑እናም ወዳጄ
አንተም መከራንና ፈተናን አትፍራ በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥም ቢሆን መንገድ አለና መከራውን ግብግቡን የአዳዲስ ሐሳቦች መነሻ የጥናካሬህ መለኪያ አቅምህን የምትጠቀምበት አጋጣሚ፣ አልፎም ወደ ላይ የምትመጥቅበትና ከችግር ደመናዎች በላይ የምትንሳፈፍበት ዕድል አድርገው። እንደ ሌሎች ወፎች ከመከራው አትሽሽ ከችግሩንም አትደበቅ መከራን ለጥንካሬና ለበረከት ተጠቀምበት።
ውብ የስኬት ጊዜ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍@EthioHumanitybot
📍ምን ይዤ ልሔድ ልድከም?
ታላቁ እስክንድር እንዲህ አደረገ አሉ። ወደ ሞት አፋፍ መቃረቡን ሲያውቅ፤ ወዳጆቹን ሰብስቦ እንዲህ አላቸው "ስትቀብሩኝ፤ እጄን ወደ ላይ አርጋችሁ ቅበሩኝ" አለ። ሰዎቹም ግራ ገብቷቸው ለምን እንደሆነ ጠየቁት፤ እሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ "እጄን ወደላይ አድርጋችሁ ቅበሩኝ ያልኩት፤ ስሞት ከምድር ምንም ነገር ይዤ እንዳልሄድኩኝ ሰዎች እንዲያዩ ነው " አለ ይህንን ያለው እንግዲህ በጊዜው አለምን ያስገበረው ታላቁ እስክንድር ነው። በክንዱ ስንቱን ያስገበረው ታላቅ፤ "ምንም ይዤ አልሄድም" ሲል ተናገረ። አንዳንዴ የምንኖረው እስከመቼ ነው ብለን እራሳችንን ከምር ብንጠይቅ መልሱ ያስደነግጠናል።
💡 ምክንያቱም የምንጨነቀው ከምንኖረው በላይ ነው። ፈገግታን፤ ሳቅን፤ ደስታን ሳያውቁ የሚሞቱ ሰዎች ሞልተዋል። ኖረው ሳይሆን፤ ሞተው ወደ መቃብር የሚወርዱ ምስኪኖች ብዙ ናቸው። አብዛኛዏቻችን በቁማችን ሞተናል፤ ምክንያቱም መኖር ከመንቀሳቀስ እና ከመተንፈስ የጠለቀ ስሜት አለውና። መኖር ማለት እራስን ከአሁኗ ደቂቃ ጋር አጣምሮ፤ መንፈስን፤ አይምሮን ከተፈጥሮ ጋር አዋህዶ፤ ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው የሚለውን የጠቢቡን መርህ ተከትሎ ህይወትን መምራት ማለት ነው (በጥቂቱ)።
ይህ ትርጉም ለእያንዳንዳችን በልካችን መበጀት ይችላል። አንዳንዴ እራሴን እጠይቃለው፤ የምንጨነቅለት ነገር ሁሉ ከዚህ አለም ስንሄድ ይዘነው የምንሄደው ካልሆነ፤ ምንድን ነው ነጥቡ? የብዙዏቻችን ኑሮ ይዘነው ለማንሄድ ወይም ስማችንን ከመቃብር በላይ ለማያስጠራ፤ ተራ ነገር ተሰውቷል። የቱ መቅደም እንዳለበት አናውቅም፤ እኛ ወይስ ጭንቀታችን? ቤተሰባችን ወይስ ስራችን? ሰብዓዊነት ወይስ ቁሳዊነት?
♦️ተጨንቀን የምናጠራቅመው ገንዘብ፤ በጥላቻ የገነባነው ክብር፤ በደም ያገኘነው ስልጣን፤ በስርቆት ያካበትነው ሃብት፤ በውሸት የፈጠርነው ማንነት፤ ሁሉም ስንሞት አብረውን አይሄዱም። ያንን ማስተዋል እንዴት አቃተን? በቃ ሃቁ ይህ ነው፤ ምንም ነገር ከኛ ጋር ወደ መቃብር አብሮ አይወርድም።
💡ይህንን ሳስብ ግርምት ያዘኝ፤ እንዴት እናሳዝናለን ? ምን አልባት ስዎች ሲቀበሩ እጃቸውን ወደላይ አድርገው ቢሆን ኖሮ፤ በጥቂቱም ቢሆን ህይወታችንን እንዴት መኖር እንዳለብን ትምህርት ይሆነን ነበር። በህይውትህ የሚያስጨንቅህ ነገር ሲገጥምህ፤ እስከምን ድረስ እራስህን አሳልፈህ መስጠት እንዳለብህ ለማውቅ ሞክር፤ ምናልባት ከህይወትህ ጋር ሲነጻጸር ኢምንት ሊሆን ይችላልና።
✍ አቤል ብርሀኑ
ውብ አሁን❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanitybot
💡ስሙኒ ይቀራል
📍ከአንድ ሰው በራፍ ላይ ቁጭ ብሎ ድንች የሚሸጥ ምሲኪን ሰው ነበረ። የቤቱ ባለቤት ሁሌም ወደ ውጪ ሲወጣ ይህንን ምስኪን ሰው ይመለከተው ነበረ። ቀኑን ሙሉ ብርድና ጸሀይ እየተፈራረቀበት ኑሮን ለማሸነፍ መድከሙ ስላሳዘነው በአቅሙ ሊረዳው ወሰነ።
💡ነጋዴው አንዷን ድንች በ50 ሳንቲም ነበር የሚቸረችረው። ታዲያ ይህ ሰው ምስኪኑን ነጋዴ ለመርዳት በማሰብ በየቀኑ የአንድ ድንች ዋጋ እየሰጠው ለመሄድ ወሰነ። በየቀኑ 50 ሳንቲሙን እየሰጠው በአንጻሩ ምንም ድንች ሳይቀበል ይሄዳል። ከብዙ ጊዜ በኋላ ይህ ሰው እንደለመደው 50 ሳንቲሙን አኑሮለት ጉዞውን ቀጠለ።
ድንገት ከኋላው “ጌታዬ” የሚል ጥሪ ይሰማል። ዞር ብሎ ሲመለከት ምስኪኑ ነጋዴ ነበር በሩጫ የደረሰበትና የጠራው።
ሰውየው በፈገግታ “ከስንት ጊዜ በኋላ ለምን በቀን በቀን 50 ሳንቲም በነጻ እየሰጠሁ እንደማልፍ ልጠይቀኝ ነው ያስቆምከኝ?” አለው
ነጋዴው ግን እያለከለከ “አይደለም ኸረ” ሲል መለሰ። ይሄኔ ሰውየው ግራ ገብቶት
“እና ለምን አስቆምከኝ?” ቢለው
“የድንች ዋጋ 75 መግባቱን ልነግርዎት ነው፤ እናም ስሙኒ ይጎድላል” አለው አሉ።
💡ይህንን ታሪክ የሰማሁኝ ቀን በጣም አስቆኝ ነበር። መለስ ብዬ ሳስበው ግን ከቀልድነቱ በላይ የሰው ልጅን የአልጠግብ ባይነትና ያለማመስገንን ባህሪ የሚያንጸባርቅ መስሎ ታየኝ። ሰዎች አመስጋኝ ፍጡሮች ነን ብዬ አላምንም። ልክ እንደዚህ ምስኪን ነጋዴ ነጻ በሚሰጠን ነገር ላይ እንኳን እንደራደራለን። የእኛ ባልሆነው ሀብት እንሟገታለን። በቸርነት በተሰጠን ነገር ሁሉ ይበልጥ እንጠይቃለን። ሃምሳ ሳንቲም ለምን በነጻ ተሰጠኝ ሳይሆን ለምን ስሙኒ ጎደለ የሚል አመለካከት ስላለን እኮ ነው አብዛኛዎቻችን ባለን ነገር መደሰት የሚያቅተን።
📍ብዙ ጊዜ ከፈጣሪ ጋርም ሆነ በየእለት ኑሮዋችን በነገሮች ላይ የምንደራደረው ልክ እንደዚህ ምስኪን ነጋዴ ነው። በነጻ የሚሰጠንን 50 ሳንቲም ሳይሆን የኑሮዋችንን ዋጋ እራሳችን ተምነን ቀሪው ጎደለ ብለን እንሟገታለን። ስዎች የሚሰጡንን ነጻ ፍቅር፤ ነጻ ክብር፤ ነጻ እምነት ዋጋ የማንሰጠው ቀሪውን ስሙኒ ስለምናስብ ነው።እኛ በባህሪያችን ነጻ የሆነን ነገር ዋጋ አንሰጠውም፣ የሚያስደንቀው ግን የሰው ልጅ በምንም ያህል ገንዘብ ሊገዛቸው የማይችላቸው ሀብቶቹ በሙሉ በነጻ የሚያገኛቸው ናቸው።
💡በ50 ሳንቲሙ ያልተደሰተና ያላመሰገነ ሰው ስሙኒ ቢጨመርለት ምን ዋጋ አለው? በየቀኑ የሚቸረን 50 ሳንቲም ከበቂ በላይ ነው፤ አንዳንዴ ስሙኒው ይቀራል ብለን ሰጪውን ባናስቀይም መልካም ነበር፤ ነገር ግን ሰው ነን!!! ብዙ ጊዜ ደስታችንን የሚነጥቀን የ “ስሙኒ ይቀራል” አይነት አመለካከታችን ነው። የተሰጠንስ 50 ሳንቲም? የተሰጠን ነጻ ፍቅር፤ ነጻ ክብር፤ ነጻ እምነት፤ ነጻ ጤንነት፤ ነጻ ተስፋ? ከምንም በላይ ነጻ ህይወትስ?
✍ሚስጥረ አደራው
ውብ አሁን❤️
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
✍ @EthiohumanityBot
💡የተለያየ ድርሻ መያዛችን ሕይወትን የተሟላች ያደርጋታል፡፡ ሰዎች እንደ እኛ ካላሰቡ የተሳሳቱ ፣እንደ እኛ ካልተናገሩ ቋንቋ ያበላሹ ፣እንደ እኛ ካልኖሩ የሞቱ እንደ እኛ ካልሰሩ ሥራ የፈቱ አይደሉም ሌሎች አስፈላጊያችን የሚሆኑት እኛ የማንችለውን ሲያውቁና ሲያደርጉ ነው፡፡
📍ሁሉም ሰው ዶክተር ቢሆን ያለገበሬ ምን ይመገባል?? ዶክተሩ በእውቀቱ ተመክቶ ገበሬውን አንተ አታስፈልገኘም ቢለው ይሞኛል፡፡ የላይኛው ከታችኛው የግድ የሚፈላለግ የተለያየ ተሰጦ ተቀብለናል፣ ስለዚህ አንዱ አንዱን አታስፈልገኘም ሊለውና ሕይወትን ብቻውን ሊመራ አይቻለውም፡፡ ትልቁ የኑሮ የኑሮ ሚስጢር " እኔ ለአንተ ፣ አንተ ለእኔ" የሚል ነው፡፡
🔷የጥቁሮች መብት ታጋይ የነበረው ማርቲን ሉተር ኪንግ፡- አላባማ እያለሁ ጫማዩን የሚጠርግልኘ አንዲት ሊስትሮ ነበር፡፡ይህን ሊስትሮ ስመለከት ወደ አእምሮዬ የሚመጣ ነገር ቢኖር የቱንም ያህል ጫማዬን ብጠርገው እንደእርሱ አድርጌ ላሳምረው አለመቻሌ ነው፡፡ ስለዚህም ይህ ልጅ በጫማ ማሳመር የዶክትሬት ዲግሪ አለው ብዬ ተቀበልኩ፡፡ ከኔም የተሻለ ስለሆነ አከበርኩት" ብሏል፡፡
💡የትኛውም እውቀታችን አዋቂ የሚያሰኘን ላላወቁት በምናደርገው መንገድ ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም እውነተኛ እውቀት የአገልጋይነት እንጂ የጌትነት መንፈስ የለውምና፡፡ የእኛ እውቀት አስፈላጊ የሚሆነው የማያውቁ ስላሉ ነው፡፡ ሁሉም ቢያውቅ እውቀታቸው አለማወቅ ይሆናል ስለዚህ የማያውቁትን አክብረን ማገልገል ይኖርብናል፡፡
🔷የትኛውም ሀብታችን ባለጠጋ የሚያሰኘን በችግር ለሚያቃስቱት ባፈሰስነው ልክ ነው፡፡ ራሱን የቻለ ባለጠጋ አይባልም፡፡ለሌሎች የተረፈ ግን ባለጠጋ ይባላል፡፡ስኬታችን የሚለካው ራሳችንን በረዳንበት መጠን ሳይሆን በሌሎች በተረፍንበት መጠን ነው፡፡
♦️ዛሬ ኑሮአችንንና ሕይወታችንን እንዲገዛው የፈቀድንለት ነገር ቢኖር ንቀት ነው፣ ሌሎች እንዲያከብሩን እንፈልጋለን ፣ እኛ ግን ሌሎችን መናቅ እንሻለን፡፡ ሌሎችን መናቅ በአዋጅ የተፈቀደልን ሥልጣን ይመስለናል፡፡ ሌሎችን በንቀት ዝቅ ካላደረግን የተስተካከልናቸው አይመስለንም፡፡
💡ስለዚህ የበላይነት ስሜታችን የበታችነት መንፈስ የወለደብን ነው፡፡ የምንኖረው ለመስጠት ብቻ ሳይሆን ለመቀበልም ነውና ሌሎችን...ማክበር ደግሞም ፈጣሪ የምንሰጠውን አስታቅፎ ወደ ዓለም ልኮናልና አደራችንን ማድረስ ይገባናል፡፡
በቤታችን ፣ በሥራ ቦታችን ፣ በአገልግሎታችን እየሰራን ያለን እኛ ብቻ መስሎ ከተሰማን ሌሎች የሠሩት አይታየንም፡፡ ሌሎችን መውደድ ያቅተናል፡፡ ሥራችንም ከጥቅሙ ኩራቱ እየገነነ ይመጣል፡፡ በሌሎች ላይም እምነት እያጣንም የርክክብን ሥርዓት እናፈርሳለን፡፡ ራሳችን አልሚ ሌሎችን አጥፊ ሆነው እየታዩን ነቃፊ ብቻ እንሆናለን፡፡
🔷የዓለማችን ትልቁ የኢኮኖሚ አቅም ፣የሰላም መሰረት ግብረ ገብነት ወይም የሞራል ሕግ ነው፡፡ የሥነምግባር መሰረቱ ሃይማኖት ነውና ሃይማኖትን መጥላት ተገቢ አይደለም፡፡ብዙ ባለ ራዕዯች ነን የሚሉ ሃይማኖትን በቀና መንፈስ አያዩትም፡፡ሃይማኖት ግን የልምድ ሳይሆን የተፈጥሮ መሻት ነው፡፡ መስራት ፣ መማር ፣ መልፋት ፣ መትጋት ብቻውን በቂ አይደለም ሃይማኖት ያስፈልጋል፡፡
♦️ዓለም ድፍርስ ውሃ ነው፡፡ ስለዚህ ማንነትን አያሳይም፡፡ እንደውም እውነትን የሚሸፍን በመሆኑ ምንመ ያልበራለትን የብርሃናት አለቃ፣ ሰነፉን የትጉሃን አለቃ እያለ ያሞካሻል፡፡ ዓለሙ የሽንገላ የመዳለል አለም ነው፡፡ ሰዎች መንፈሳዊ መፅሐፍትን የሚጠሉት እውነት ስላልሆነ ሳይሆን ኃጢአጣቸውን ስለሚነግራቸው ነው፡፡ ዓለሙ የንግግር መክፈቻው "አንተ ለአንተ" በቻ በሚል ራስ ወዳድነት መንፈስ የተከበበ ነው፡፡ ዛሬ ድረስ የሰው ልጆች ይህን ሀቅ አልተረዱትም አሁንም ሌላውን እንጂ ራሳቸውን ዞር ብለው ማየት አልቻሉም፡፡
🔷ስለዚህ የኛ ድርሻ ቆም ብሎ ማሰብ ነው። ቆም ብሎ ማሰብ ይጠቅማል፣ ቀጥሎ መመልከት ከዚያም መጠየቅ በመጨረሻም መጓዝ ነው፡፡ ካልቆምን መመልከት ፣ ካልተመለከትን ማስተዋል ፣ ካላስተዋልን መጠየቅ ፣ ካልጠየቅንም መጓዝ አንችልም፡፡ መቆም ለቀጣዩ ጊዜ ያዘጋጃል ፣ ለቀጣዩ ጉዞም ኃይል ይሰጣል ፡፡
♦️በክፉ ጎዳና የሚጓዝ መቆም ያስፈልገዋል ፡፡ የመጣበትንና የሚሔድበትን የሚያየው በመቆም ብቻ ነው፡፡ በመቆም በፀጥታ ውስጥ ሆኖ ራስን መገምገም ፣ ከዚያም መመልከት ቀጥሎም መጠየቅ በመጨረሻም ዕረፍት ወዳለበት የራስ ደሴት መጓዝ፡፡
ውብ ቅዳሜ❤️
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
✍ @EthiohumanityBot
💡ያለፈበት ብቻ ያውቀዋል!!
ትልልቅ ቦታ ላይ የደረሱን ሰዎች ስለ ትናንት ህይወታቸው ስትጠይቃቸው ሁሉም ፊት ላይ ደስተኝነትን አታነብም:: ሁሉም በእምባ እናም በትጋዜ ተሞልተው ይነግሩሀል፣ ከሙቀት ዋሻህ ውስጥ የምትወጣበት፣ከተወዳጅነት አጀብታ ለነፍስህ ፍላጎትና ለህልምህ የምትወርድበት ጥልቁና አስፈሪው የህይወት መንገድህ ነው።
📍ያስፈራል ልብ ያርዳል ነገር ግን ነፍስን ለጥበብ ይቀርፃል። በዛ ውስጥ ሰው ይርብሀል ።ተቃዋሚህ ይበዛል:: እጅ ጠቋሚው ተሳላቂው ይከብሀል:: ብታወራ የሚረዳህ አንዳች አይኖርም!! የሚፈርድ እልፍ ይሆናል...ህመሙ ጥልቅ! የስሜት ጉዳቶቹም ብርቱዎች ናቸው።
ለዚህም ነው ብዙ ሰዎች ትልቅ ህልም እያላቸው ትንሽ ሆነው መኖርን የሚመርጡት!አስፈሪውም ትልቅ ህልምህ ወደ ትልቅነት የሚመራህ በትናንሽ የህይወት ጉዳዶች ውስጥ መሆኑም ነው። ብቻህን የምታለቅስበት ብቻህን የምትፋለምበት ብቻህን ሞትን ምትናፍቅበት ግን ደግሞ ብቻህን የምትዘምርበት ብቻህን የምትፀልይበት ብቻህን አምላኬ ብለህ ከፈጣሪህ ጋር የምትነጋገርበትም መንገድ ነው።
💡መከራ የፈጣሪ ትህምርት ቤት ነው። "ስቃዮች መገፋቶች መድከሞች መውደቆች ሁሉም የነፍስ ጥልቅ ህመሞችህ በስተጀርባ መምህሩ አምላክህ አለ።ለዛም ነው ማስተርስ ጫንኩኝ ከሚለው ሰው በተሻለ ህይወት ያስተማረቻቸው አለምን ሲመሩ ሲቆጣጠሩት የትምመለከተው!
''ሰውን ካስተማረው ፈጣሪ በጥበብ አስውቦ የቀረፀው ይበልጣል'' ከሙቀት ጎጆህ ስትወጣ! ህልምህን ከፈጣሪህ ምሪት ጋር ትከተለዋለህ! የግድ ይሆንብሀል አማራጭ ታጣለትህ ብትቀመጥ የሚወጋህ ሺ ስለሚሆን ይግድ ትጓዛለህ እየዛልክ ትጠነክራለህ እየሞትክ ህያው ትሆናለህ እየወረድክ ከፍፍ ትላለህ የግድ ይሆንብሀል...!
📍ህይወት ፊቷን የምምትሰጠው ጠንካራ ጡንቻ ላላቸው ሳይሆን ጠንካራ መንፈስ ላላቸው ነው። ከውስጥ የመነጨ ጠንካራ መንፈስ ሲኖረን ምንም ያህል ችግር ምንም ያህል ስቃይ ከላያችን ቢረበረቡ ምንም ሳያሳስበን
ምንም ተስፋ ሳያስቆርጠን ወደፊት
ግስጋሴያችንን እንቀጥላለን። ሩጫችንንም መሰናክሉን እያለፍን እንሮጣለን።
💡ወደ ቁልቁለቱም ድፈር! ወደ አስፈሪው መንገድ በድፍረት ጥለቅ ፣ አንድ ሰው መሰረታዊ እሱነቱን በቀጥታ መጋፈጥ አለበት። ለብቻው ሆኖ አይምሮውን በመክፈት ውስጡ ያለውን ነገር መመልከት አለበት። ይህ የድፍረት ተግባር ነው። ከውስጥ ወዳለው ሲዖል ለመግባት የሚያስችል የድፍረት ተግባር....። እርቃን ማንነትን ለመመልከት የሚወሰድ የድፍረት እርምጃ ነው። ታላቅ ድፍረት ያስፈልጋል።
📍የህይወትህን ሲኦል ካልተጋፈጥክ የስኬትህን ብርሀን መቼም አትለብሰውም ፣ የከፍታውን መንገድ በመውርደት ፣ የደስታውን መንገድ በሀዘን ፣ የንግስናን መንገድ በባርነት ፣ የመሪነትን መንገድ በተመሪነት ፣ የስኬትንም መንገድ በውድቀት በኩል ውስጥ ትገናኛቸዋለህ!
አለም ለደፋሮች ታደላለች። ወደ ከፍ ያለ ማንነት ጉዞ ፣ስትጀምር የነፍስክ ጥንካሬ ተአምራዊ ወደ ሆነ ቦታ ያደርሥሀል፣ ድፋር ሁን! ለህልምህ ቆራጥ ሁን ፣ የህይወት ብርሀንህ የሚወለደው ከዛ እርምጃህ ነው!
ዉብ ጊዜን ተመኘን ❤
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍@EthioHumanityBot
📍ወዳጄ ሆይ
አስተውል ምድራችን ስለፍትህ በሚያወሩ ግን ደግሞ ለሕግ በማይገዙ፣ፍቅርን በሚሰብኩ ግን በፍቅር ለመኖር ምንም ጥረት በማያደርጉ፣ የፈጣሪን ቃል በሚያደምጡ ግን ደግሞ ቃሉን በማይኖሩ ሰዎች የተሞላች ናት፡፡ ልብ በል ወሳኙ ነገር የምትኖርበት ቦታ ሳይሆን አኗኗርህ ነው፡፡ ከምታምንበት ነገርም በላይ ዋጋ ሊሰጠው የሚገባው ባመንክበት ነገር እንዴት ትኖራለህ የሚለው ነው
💡ወዳጄ ሆይ፥
ከዚህ አገር እዚያ አገር ፣ ከምዕራብም ምሥራቅ ይሻል በማለት አትዋትት ። ከሁሉ የሚሻለው ሕይወትን ከነሙሉ ትርጕሟ መቀበል ነው ። ማንም ሰው ከጠባቡ ግለኝነት ሕይወት ወደ ሰፊው ጠቅላላው የሰው ልጅ ምልከታ ከፍ እስኪል ድረስ መኖርን ተማረ አይባልም፡፡ እናም ማለዳ ማለዳ አዲስ ትርጉም ባለው መንገድ ለመኖር ራስህን መመልከትህ ወደ ፊት ከመመልከት ጋር ሊዋሐድ ይገባዋል፡፡
ወዳጄ ሆይ
ሕይወት በእንግዳ ክስተት የተሞላች ናት ። የታወከ ሌሊት ሲገጥምህ በሰላም ስላደርክባቸው ሌሊቶች አለማመስገንህን አስብ ። ወዳጅና ወዳጅን አጣልቶ አንዱን የአንዱ ጠባቂ በማድረግ ትርፍ ይገኛል ብለህ አትሸወድ፣ ከፍቅር እንጂ ከሴራ አንድም ትርፍ አይገኝም። ጉድጓድ መጀመሪያ የሚቀብረው ቆፋሪውን ነውና ክፋትን አታስብ ።
💡ወዳጄ ሆይ !
እልህ ከራስ ጋር ገመድ መጓተት ነው ። የማይቀጥሉ ነገሮችን መሬት ላይ አስቀምጣቸው ፤ አየር ላይ ከተበተኑ ጉዳት ያመጣሉ ። “የጨዋ ልጅ ሲፋታ የሚጋባ ይመስላል” እንዲሉ ። ያለትግል ያለሁካታ በሰላም መራመድን ልመድ፣ የሃያ ዓመቱም የሰማንያ ዓመቱም ሁለቱም የዕድሜ ስስት አለባቸው ። በምናልባት መኖር ጉልበት ይጨርሳል ። ውሳኔ ማጣትም ዕድሜን ይፈጃል ፣ መኖርህ አለመኖር እንዳይሆን በማስተዋል ተራመድ ።
📍ወዳጄ ሆይ
ትልልቅ ዛፎች የጀመሩት ከችግኝ ነውና ትንሽነትህ ትልቅነትህን አልደርስበትም ብሎ አይስጋ ። በትዕግሥትና በጊዜ ውስጥ የማይደረስበት ነገር የለም። ሥር የሰደዱ ዛፎች ነፋስን ይቋቋማሉ ፣ ወደ ታች የጠለቁ መሠረቶች ብዙ ፎቅ ይሸከማሉ ። ሰውም በሳል ሲሆን በፈተና ይጸናል ፣ ፈተናና ነፋስ ያልፋሉና ። ነፋሱ ዘንበል ቢያደርግህም እንዲሰብርህ መፍቀድ የለብህም ። ብዙ ጫናዎችን ለመሸከም እውቀትና ማስተዋልን ገንዘብ አድርግ ፣ በክረምት ለመዝራት ዝናቡን የተሳቀቁ የአጨዳ ዘመን የላቸውም ። ያለ ውሳኔ በዚህ ዓለም ላይ መንቀዋለል ይቻላል ፣ መጓዝ ግን በፍጹም አይቻልም።
እናም ወዳጄ
ስንኖር ብዙ ነገሮች የተቀላቀሉባቸው ሰዎች ያጋጥሙናል ። ስለ ሰላም የሚያወራው በአሳቡ ብዙ ጦርነት ላይ ነው የአሳብ ፍልሚያ ያለባቸው ፖለቲካና ሃይማኖት የተቀላቀለባቸው የጦር መሣሪያ የጨበጡ ብዙዎች ናቸው። ጦርነት የሚቀሰቀሰውም የሚቆመውም በአንደበት ነው ። “እፍ ያነዳል ፣ እፍ ያጠፋል” እንዲሉ ። አእምሮ በእውቀት ያጣራል ፣ በጥበብ ያስውባል በማስተዋል ይተምናል ። የትኛውም ሰው ከእንቅልፉ የሚነቃው የህይወቱ ብርሃን ሲበራ ነው።
🔑 ጨለማ በብርሃን እንጂ በጉልበት አይወገድም፡፡ ፈጣሪ ብርሃን ሲሆንልህ ህይወትን በመአቀፋ ስትረዳ ወደ ጠራ ማንነት ትደርሳለህ ። ድፍርስ ቡና የሚጠጣው ሲሰክን ነው። የተቀላቀለ ማንነትም ድፍርስ በመሆኑ እርካታ የለውም። ከጨለማ ህይወት የራቀና ፍጹም ብርሃን የበዛበት ህይወት ይኖረን ዘንድ ፈጣሪ ይርዳን!
ውብ እረፍት ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot
📍አንዳንድ ወቅት አለ ስሜት የሚነዳ ፤ የሂወት ድግግሞሽ እንደጦስ ዶሮ የሚያዳክር፤ እጅ እና እግር እንደተጠፈረ አቅም አልባነት የሚበላ ፤ አካባቢ ላይ ምን እንደተካሄደ የማይገባህ ።
አንዳንድ ወቅት አለ ማጤን ማመዛዘን ያንተ የማይሆንበት ፤ የመረጥከው ምርጫ የሚያድሞከሙክኽ። መባተልን የምትመስልበት፤ የመጣህበት መንገድ አሳስቶህ የማትመለስበት ።
አንዳንድ ወቅት አለ ምርጫ የሚያባትልህ ፤ የመፍዘዝ ስሜት የሚሰማህ ፤ ሰው ሁሉ የጠላኽ የሚመስልህ ፤ ኃላ የመቅረት ስሜት የሚንጥህ ።
አንዳንድ ወቅት አለ ማድረግ እንደሌለብህ እያወክ የምታከናወነው ፤ የስሜትህ ባርያ የምትሆንበት ፤ መገኘት እንደሌለብህ እያወክህ የምትገኝበት ።
እንዳንድ እለት አለ ብልጥ ነኝ ባዮች የሚበልጡ ፤ አራዳ ነኝ ባዮች የሚያሞኝህ፤ በዝባዦች የሚበዘብዙህ፤ ባለጡንቻዎች አቅማቸውን የሚለኩብህ
እንዲም ሁሉ ሆኖ ሳለ
በግዜ እናምናለን ። ግዜ ሃያል ነው ። ሁሉም ይስተካከላል፣ መስመር መስመር ይይዛል ።አይነጋም ያልነው ጨለማ ስንቴ ነግቷል።
✍አድሃኖም ምትኩ
ውብ አዳር ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍@EthioHumanityBot
💡ሰውየው በቤቱ አንድ ትልቅ ዛፍ ነበረው አሉ፤ ይህ ዛፍ ህልውናው እንዳይጠፋ በእጅጉ ይንከባከበው ነበር። በቀን በቀን፤ ሲመሽም ሲነጋም ወደ ዛፉ እየሄደ ምርጥ ጊዜ ያሳልፋል። ከእለታት አንድ ቀን ግን፤ ይህን ግዙፍ ዛፍ ትክ ብሎ ሲመለከተው አንዳንድ ቅጠሎቹ ቀለማቸውን እየቀየሩ እየጠወለጉ መምጣታቸውን ተመለከተ፤ ሰውየው ሃዘን ገባው። ምንም እንኳን ዛፉ ትልቅ እና ግዙፍ ቢሆንም፤ እንደምንም ከዛፉ እላይ እየወጣ፤ የጠወለጉትን ቅጠሎች በውሃ ማራሱን ተያያዘው። ተመልሰው ነፍስ እስኪዝሩ ድረስ፤ ሽቅብ ወደ ላይ እየወጣ ቅጠሎቹን እየወለወለ በውሃ ያርሳቸዋል።
......ለብዙ ቀን እንዲህ ሲለፋ ቆየ፤ ምንም እንኳን የተቻለውን ያህል ቢለፋም ቅጠሎቹ አንድ በአንድ ከመድረቅ እና ከመጠውለግ አልዳኑም። በመጨረሻ ሰውየው ከልፋቱ ብዛት ደከመው፤ የነበረውም ውሃ በሙሉ አለቀበት። ቀስ በቀስ ዛፉ መሞት ጀመረ……..
📍ይህ ሰው ሃይል እና ጉልበቱን እንዲሁም ሃብቱን በከንቱ አባከነው። የዛፉን ስር ውሃ እንደማጠጣት፤ የጠወለጉት ቅጠሎች ላይ ጊዜውን በማጥፋቱ፤ ዛፉን በሙሉ አበላሸው። ምን አልባት ብልህ ሆኖ ስሩን በውሃ ቢያርሰው ኖሮ፤ የጠወለጉት ቅጠሎች መልሰው ባበቡ፤ ሌሎችም ከመጠውለግ በዳኑ ነበር።
💡አብዛኛዎቻችን እንዲህ ነን፤ ህይወታችን መታደግ የሚያቅተን፤ ትኩረታችን ሁሉ፤ ስራችን ላይ ሳይሆን ቅጠላችን ላይ ስለሆነ ነው። ቅጠሎቻችን ምንድን ናቸው? ባህሪያችን፤ ልምዳችን፤ ወይም ሌሎች የአስተሳሰባችን ውጤት የሆኑ ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ። ስራችን ግን ማንነታችን የሚበቅልበት አስተሳሰባችን ነው። ባህሪዎቻችን ወይም ተግባሮቻችን ሲጠወልጉ፤ ስራችንን እንደማስተካከል፤ ጊዜ እና ጉልበታችንን ለውጥ በማያመጡ ነገሮች ላይ እናጠፋለን።
📍የሁላችንንም ቅጠል የሚያጠወልገው ነገር ይለያያል፤ አንዳንዶቻችን በሱስ እንጠወልጋለን፤ አንዳንዶቻችን በስንፍና፤ አንዳንዶቻንች በቂ ፍቅር ስለሌለን፤ አንዳንዶቻችን በራሳችን ባለመተማመናችን፤ አንዳንዶቻችን ተስፋ በማጣት፤ ብቻ በተለያይዩ ምክንያቶች መጠውለግ እንጀምራለን። መጠወለጉ ሲያንገፈግፈን እና እንደገና ለማበብ ስንወስን ደግሞ መላው ይጠፋብናል። በለፋን ቁጥር ይበልጥ እንጠወልጋለን፤ ልፋታችን ከንቱ ይሆንብናል። ምክንያቱም ብዙዎቻችን እንደ ሰውየው፤ ጊዜያችንን የምናጠፋው ለውጥ በማናገኝባቸው ነገሮች ላይ ነውና።
💡የሁሉም ነገር መሰረት አይምሮዋችን ነው። የጠወለገውን ክፍላችንን እንደገና ህይወት መስጠት የሚያስችለን ብቸኛው መፍትሄ አስተሳሰባችን መቀየር ብቻ ነው። እራሳችንን እንደዛፉ ብንመለከት፤ የትኛው የህይወታችን ክፍል ነው እየጠወለገ ያለው? ልፊያችንስ ከተበላሸው ባህሪያችን ማለትም ከጠውለገው ቅጠላችን ጋር ነው ? ወይስ ስር ከሆነው አስተሳሰባችን ጋር ነው?
ውብ አሁን❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍@EthioHumanityBot
❤️ቅናት አንድ ሰው በሚወዳቸው ሰዎች በምላሹ ተወዳጅ እንዳልሆነ ሲያስብ የሚሰማው ህመም ነው፣ ቅናት ሁሌም የሚመነጨው ከንፅፅርና ከውድድር ነው።
ከልጅነታችን ጀምሮ እያነፃፀርንና እየተነፃፀርን መኖር ለምደናል። ስንማረው ኖረናል ። የሆነ ሰው የተሻለ ቤት አለው ። ውብ የሆነ ሰውነት ይኖረዋል። አንዳንዱ ከሌላው የበለጠ ገንዘብ አለው። ሌላው ደግሞ መስህብ ያለው የስብዕና ባለቤት ነው፣ እነዚህን ነገሮች እየተመለከትን ከእነዚህ ሰዎች ጋር እራሳችንን እያነፃፀርን ነው የኖርነው።
📍ማወዳደር ትልቅ በሽታ ነው፣ የራስህን ሕይወት በፍጹም ከማንም ጋር አታወዳድር ። ምክኒያቱም እራስንህን ከሌሎች ጋር ስታወዳድር የምታገኘው ውጤት ከዛ ሰው የተሻልክ ከሆነ ኩራት ሲሆን ከዛ ሰው የምታንስ ከሆነ ደግሞ ቅናት ነው የሚሆነው ። ሁለቱም መጥፎ ውጤቶች ናቸው፣ ቅናት ደግሞ ከንፅፅራዊ ባህሪ የሚመነጭ ተረፈ ምርት ነው። እራስህን ማነፃፀር ካቆምክ ግን የቅናት ስሜትህ ሙሉ ለሙሉ ይጠፋል፣ ከምንም በላይ ውበት የሚገለጸው እራስን በመሆን ነውና ።
💎ቅናት፤ ተንኮል፤ ጥላቻ እና ቂም የሰውነትን ውበት እና ግርማ የሚሰርቁ ቀማኞች ናቸው። ፈገግታ የራቀው ኮስማና ፊት እንደው ዝም ብሎ የሚመጣ ነገር አይደለም፤ ኮስማና ሃሳቦችን ከማሰብ የሚመጣ እንጂ፣ ሰዎች ደስ የሚሉ ሃሳቦችን ሲያስቡ፤ ሰውነታቸው በመልካም ሁኔታ ላይ እንዳለ ይናገራል፤ የውስጥ ደስታቸው ደስ የሚል ግርማን ያላብሳቸዋል። ሰውነታችን በቀላሉ እንደአስተሳሰባችን ይለዋወጣል። መልካም እና ክፉ አስተሳሰቦች የየራሳቸውን ተጽዕኖ ያሳድሩበታል።
💡ከንጹህ ልብ፤ ንጹህ ሰውነት ይገኛል፤ ከጤነኛ አስተሳሰብ ጤነኛ ሰውነት ይወለዳል፣ መልካምነት ከማንም በላይ ላራስ ነው ጥቅምና ፍይዳው። ቅን ሀሳብ አሳቢውን ይባርካል። ሴራ፣ ተንኮል እና ክፍት ህሊናና ልብህን ከሞላው ግን መንገድህ መሰናክል ይበዛዋል ፣ እናም በልብህ ጥላቻ ሳይሆን ፍቅርን፣በቀል ሳይሆን ይቅርታን ፣ ቅናት ሳይሆን ቅንነትን ፣ ስስት ክፋት ሳይሆን ደግነትን ፣ ትዕቢት ሳይሆን ትህትናን፣ ሁሌም በልብህ ብትሰንቅ ነገ መልሶ የህይወት ስንቅ ይሆናሃል።
ውብ አሁን!!❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot
መረጋጋት የውሃ ተፈጥሮን በጥሩ ሁኔታ ይወክላል።ለእኛ ለሰው ልጆች አርአያ ሊሆነን ይገባል ምክንያቱም ውሀ ሀይሉን የሚሰበሰበው በእርጋታ ነው።
ራሳችንን የመቀየር ሀሳብ ካለን ቅድሚያ አስተሳሰባችን ምን እንደሚመስል መቃኘት አለብን። ረጋ ብለን ለደቂቃ በጥሞና ውስጣችንን ብንሰማ፤ እጅግ እንገረማለን። ሃሳባችን አንዴ ከትላንት፤ አንዴ ከዛሬ አንዴ ከነገ፤ ሳያቋርጥ ይጋልባል፣ልክ ያለማቋረጥ እንደሚማሰል ኩሬ መንፈሳችንን ያደፈርሰዋል።
አእምሮአችን ያለ ማቋረጥ ሀሳብ ሲያበዛ ጭንቀትና ድካም ያስከትላል፣ ውሃን ብቻውን ስንተወው ሳይታወክ ጥርት ረጋ ይላል፣ የረጋ ውሀ ለአናጢው እንኳን ሳይቀር በውሀ ልክ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፣ግንባታን እኩል ያረጋል።
ውሃን ካስተዋልከው ይፈሳል ምንም ጠንካራ ነገር ከመጓዝ አያቆመውም፣ ሁልጊዜ ወደፈለገበት ቦታ ይሄዳል፣ውሃ ትግል አያቅም እንቅፋት ሲገጥመው ዞሮ ያልፋል፣ጠብ እያለም ድንጋይ ይንዳል፣ ስናየው ስስ ነው ግን እሱን የሚያህል ጠንካራ ነገር የለም።በእርጋታ ጊዜ ውሃ እንዲህ ተአምር ከሰራ የሰው ልጅ መንፈስ ረጋ ቢል ምን ውጤት ያመጣል ብለህ አስብ?
ወዳጄ ሆይ አንተም አስታውስ ግማሽ አካልህ ውሃ ነው ፣በእርጋታህ ሀይል መሰብሰብ ትችላለህ ፣እንቅፋት ውስጥ ማለፍ ካልቻልክ አትታገል በዙሪያው እለፍ ፣ በሁኔታዎች አትታሰር ግትር መሆን ጅልነት ነው። በብዙ አቅጣጫ መንቀሳቀስ ደግሞ ብልህነት ነው።
💧ብልህነት ሁል ጊዜም እንደ ጅረት ውሀ መፍሰስ ነው፣ ነገ የገዛ ራሱን አጋጣሚ ይዞ ይመጣልና የትላንቱ ሃሳብህ ላይ የሙጥኝ አትበል፣የሰው ልጅ እራሱ ከሚፈጥራቸው የመንፈስ ካቴናዎች ነጻ ወጥቶ የመኖር አቅም አለው።የህይወት ለውጦችን ከመቃወም ይልቅ ራስን አስተጋብሮ መራመድ ጥበብ ነው።
ውብ ጊዜ❤️
@Ethiohumanity
@Ethiohumanitybot
📍ልብን እና አዕምሮን ማቆሸሽ ራስን እንደመጣል ይቆጠራል፡፡ ሕሊና ቢስ መሆንም ሕሊናን በራስወዳድ ሃሳብ ማጨቅየት ነው፡፡ አስተሳሰብን ማጠልሸት፣ አመለካከትን ማጨለም አንጎልን በቆሻሻ መበከል ነው፡፡
ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶ በነበረበት ጊዜ፣ ነቢዩ ኢሳይያስ ለጆሮ በሚከብድ ቃል እንዲህ ብሎት ነበር:: "ንጉስ ሆይ ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል!"
ንጉስ ሕዝቅያስ ቤትህን አስተካክል ከተባለ በኁዋላ ፊቱን አዙሮ ወደፈጣሪው ከማልቀስ በቀር ምንም አላደረገም ፣ ነገር ግን ፈጣሪ ልቦናውን አይቶ እድሜ ጨመረለት። ንጉስ ሕዝቅያስ ሆይ ከአልጋህ ሳትወርድ ያስተካከልከው ቤት ምን ዓይነት ቤት ነው? ሲሉ ይጠይቁታል
ንጉስ ሕዝቅያስ ግን ከአልጋው ሳይወርድና ሳይነሣ ያስተካከለው ቤቱ "ልቡን" ነበር::
አንተም ፈጣሪን የሚፈራ ልብ ይኑርህ ፣ ፈጣሪ ባህሪና ተግባራችንን ያያል። ከሰው የወሰድነውን ከሰውየው ብንደብቅ ከአምላክ አንደብቅም። ዓሣ ከውኃ ወጥቶ ከቆየ ወዲያው እንደሚሞት ሰውም ከህሊናው ከፈጣሪው ከወጣ እንደዚሁ ይሞታል፡፡ ዓሣው ቶሎ ተምልሶ ወደ ውኃው ሲገባ እንደሚድን ሰውም ከልቡ ሆኖ ይቅርታ ሲጠይቅ ፣ፈጣሪ የይቅርታውን በር ይከፍትለታል።
🔑ወዳጄ ሆይ ልቦናህን አጥራው፣ ስሜትህን ግራው፣ ሕሊናህን ዘወትር በአዲስና በበጎ ሃሳብ ሞርደው፣ ምን ዘንካታ ብትሆንና አለባበስህ ቢያምር ሕሊናህ ከቆሸሸ በሚያምር ቤትህ ውስጥ ቆሻሻ እንደመከመር ነው፡፡ አንተ ግን ልብህን ካስተካከልክ ቤትህ፣ ስራህ፣ ቤተሰብህ፣ ትዳርህ፣ በዙሪያህ ያሉ ችግሮችህ እና የሚያስጨንቁህ ነገሮች ሁሉ ይስተካከላሉ።
ውብ ምሽት❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍@EthioHumanityBot
💡ወንድሜ! ራስ ወዳድነት የታወረ የበላይነትን የመሻት መክንያቱ ነው።የወንድምህ የበላይ የመሆን ፍላጎት ጎሳና ነገድ እንዲፈጠር ምክንያቱ ሆነ፤ጎሳና ነገድ ደግሞ እርስ በርስ መጋደልና አንዱን መጨቆን አስከተለ።
📍ፍቅር በእዉቀት ሃይል ታምናለች ፤ ፍትህ ደግሞ በጨለማው አላዋቂነት ላይ ትሰለጥናለች። ታላቋን ባቢሎን ካጠፍ ፣የኢየሩሳሌምን መሰረቶች ካናወጠ፣ሮምን ከፍርስራሿ ጋር ካስቀረዉ ከዚያ ሰልፍ ከሚያቀብል ሥልጣን፣አላዋቂነትና ጭቆናን ከሚያንሰራፋ የሥልጣን ሃይል ጋር ፍፁም ትቃረናለች። ዳሩ ታላላቅ ሰዎች ተብለው ሲጠሩ የኖሩ እንዲህ አይነቶቹ ወንጀለኞች ናቸው።
📍አኔ የምቀበለው ብቸኛ ስልጣን በተፈጥሮ ሕግ ላይ የተመሰረተዉን ፍትሕና እሱን የሚቀበለውን እዉቀት የያዘውን ብቻ ነው። የራሱን ጉዳይ ብቻ የሚያቅፍ ባለሥልጣን ላይ ፍትህ ምን የምታደርግ መስልሃል?
አንተ ወንድሜ ነህ፤ስለዚህ እወድሃለሁ! ፍቅር ደግሞ ታላቅ ፍትህ ነው! ከየትኛውም ጎሳ ወይም ነገድ ብትመጣ ለአንተ የምሰጠው ፍትህ "ፍቅር" ብቻ ነው።
❤️ፍቅር ስለ ራስ ብቻ ማሰብ ሳይሆን ስለሌላውም ማሰብ ነው ። ፍቅር ሲታመም ሁሉም ነገር ይታመማል። ስብእናም አስተሳሰብም ስሜትም ይታመማል ። ወዳጀ ሆይ አንተም አስተውል ያንተ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ድረስላቸው ከራስህ ከፍታ ይልቅ ለሰዎችና ለሃገርህ ከበሬታ ይኑርህ ፡፡የወደቁትን አንሳ ያዘኑትን አጽናና ፍቅር ስጣቸው እርሱ ከሁሉም ይበልጣልና!!
✍ ካህሊል ጂብራን
ውብ አሁን ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍@EthioHumanityBot
💡ያለፈ ጥረታችንን ሳስታውስ ከሞከርነው ነገር ይልቅ ያልሞከርነው ነው እሚቆጨኝ። ሃገር ስትታመም፣ ብርድ ብርድ ሲላት፣ ተስፋና ሥጋት፣ ወኔና ፍርሃት፣ ምርቃትና እርግማን - እንዳሻው ሲንጣት ከሆነብን ይልቅ እየሆነ ያለው ያሳስበኛል ፣ ከእሳቱ በላይ አያያዙ ያሰጋኛል፣ ከጥያቄው በላይ ምላሹ ይስበኛል።
📍ችግር ፈቺነት ከሚጠይቀው ጥበብ ውስጥ ዋነኛው የሚመስለኝ ለሌላ እንከን ገርበብ የማይልን በር የመተው ብልህነት ነው። አንድን ሕመም ስታክም 'ከተጠባቂው' ጎንዮሽ እንከን ውጭ ሌላ ህመም እንዳልፈጠርክ ማረጋገጥ ግዴታህ ነው። በስመ መድኃኒት የተገኘው አይደነጎርም፣ አንድ ችግር ፈትቷል ተብሎ ለሌሎች ችግሮች ሰበብ እንዲሆን አይተውም፣ በእውቀት እንጂ በደመነፍስ አይቃኝም።
💡በእንዲህ ዓይነት ጊዜ ጥሞና ነው የሚያስፈልገን፣ የሰከነ ውይይት ነው የሚያሻን፣ 'ምን ብናደርግ ይበጃል?' መባባል አለብን። ጊዜው እሾህ እያወጣን ጦር የምንተክልበት አይደለም፣ እንቅፋት እየነቀልን ፈንጂ የምንቀብርበት አይደለም፣ ጀግነን አዙሪቱን እኛው ጋ የምናቆምበት እንጂ፣ የክብሪቱን እሳት እፍ በምትልበት ሰዓት ካላጠፋኸው እፍ ብሎ ያጠፋሃል።
📍'ካልደፈረሰ አይጠራም' የሚል አስተሳሰብ የሚያቀነቅኑ ሰዎች ዛሬም በዙሪያችን እንዳሉ ማሰብ ያደክማል፣ ሳይደፈርስ ማጥራት ከተቻለ ለምን ይደፍርስ ብሎ መጠየቅ ግን ግድ ነው። የደፈረሰ ሁሉ ይጠራል ወይ ማለትም ያስፈልጋል፣ ድፍርስ ሲጠራ ዝቃጭ እንደሚተው አለመርሳትም ደግ ነገር ነው። ምንም ብንታገል ልናስቀር የማንችለው አንድ ነገር ለውጥ ብቻ ነው፣ ለበጎ አልያም ለክፉ እንዲሆን የማድረጉ ድርሻ ግን እጃችን ላይ አለ። ችግሩ 'እንዲሆን' የምንፈልገው አለ - ሆነን ግን አንጠብቀውም.. 'እንዲመጣ' የምንሻው አለ - የምናዋጣው ግን የማይገባውን ነው።
💡በእንዲህ ያለ ቀውጢ ጊዜ ወሳኙ ሰው አንተ ነህ፣ ዘረኛ ሳይሆኑ ነው ዘረኝነትን ማረቅ የሚቻለው፣ ሳይሰርቁ ነው ዘራፊነትን ማስቆም የሚቻለው፣ አድማጭ ሆኖ ነው ጫጫታን ማስቆም የሚቻለው፣ ግማሽ መንገድ መጥቶ ነው 'እስኪ እንነጋገር' የሚባለው፣ለውጡን ተለወጠው እንጂ ከሌሎች አትጠብቀው፣ አርዓያ ሁን የሚመለከቱህ አሉ ፣ የሚከተሉህ አሉ።
ፊት መሆን በሚችል ስብዕና ከፊት ቁም፣ ጊዜህን አፍ በመካፈት አትብላው፣ ስህተት በመንቀስ አትሙላው ብሽሽቁ፣ አተካራው፣ መናቆሩ፣ ጎራ ማበጀቱ ፣ አሁን ፈጽሞ አይጠቅምም። እንዲመጣ የምትፈልገው ለውጥ አሁን አንተ ያልሆንከው ወይም የሌለህ ከሆነ ለውጡ መቼም አይመጣም መቼም!!
🔑 የትኛውም የችግር ቁልፍ የፍቅር ስሪት ከሌለው መሰበሩ አይቀርም ፣ ወደድክም ጠላህ እውነተኛውና ዘላቂው ኃይል ፍቅር ብቻ ነው ፣ የረቀቀ ሳይንስም ሆነ የጠለቀ አስተሳሰብ ፍቅርህን አያክልም፣ የገዘፈ ኃይልም ሆነ ልክ የለሽ ስልጣን ፍቅርህን አይተካም፣ የፍልስፍናህ ጥግም ሆነ የልሂቅነትህ ጠገግ አፍቃሪነትህን አይተካከልም።
የአብሮ መኖር እንከናችንን የሚደፍን ሕብር እንጂ የመለያየት ግንብ የሚገነባ መዝሙር ሰልችቶናል፣ ከነበርክበት 'የተሻለ' ብርሃን ስትፈልግ ወደ አልነበርክበት ጨለማ አለመግባትህን ማረጋገጥ ብልህነት ነው!!
✍ ደምስ ሰይፉ
ውብ ጊዜ ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot
📍#እሮጣለሁ
ወደ ጎዳና እየወጡ ያሉ ወገኖቻችን ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት የሚፈልግበት ደረጃ ላይ ደርሷል።
❤️ሁላችንም በትብብር ችግሩን ለመቅረፍ የሚጠበቅብንን እንወጣ። የሜሪጆይ ቤተሰብ እያደረገ ያለውን ጥረት እደግፋለሁ።
እኔም ከቤተሰቤ ጋር በሜሪጆይ ሩጫ ላይ እሳተፋለሁ።
ታህሳስ 14; 2016 ተመዝግቧል! እሮጣለሁ፤
#ወገኖቼን_ከጎዳና_አነሳለሁ
1) የሩጫው መሪ ቃል፡-
አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰው ወደ ጎዳና የወጡ ወገኖቻችን በተለይም ከልጅ ጋር ጎዳና ያሉትን እናቶች በማሰብ፤ የሩጫው መሪ ቃል “እሮጣለሁ፤ ወገኖቼን ከጎዳና አነሳለሁ!” የሚል ነው፡፡
2) ሩጫው የሚደረግበት ቀን፡- ታህሳስ 14፤ 2016
3) መነሻና መድረሻ፡- ከቴዎድሮስ አደባባይ እስከ መስቀል አደባባይ
4) ሩጫው የሚሸፍነው ኪሎ ሜትር፡- 5 ኪሎ ሜትር
5) የቲሸርት ዋጋ፡- 400 ብር ለአዋቂዎች እና 300 ብር ለልጆችና አዋቂዎች
6) ቲሸርት ስርጭት የሚደረግባቸው ቀኖች፡- ከታህሳስ 8 – 13፤ 2016 ዓ.
ቲሸርት መግዢያ መንገዶች፤
በሜሪጆይ ቴሌግራም ቦት @MaryJoybot በኩል መመዝገብ ይችላሉ
ለበለጠ መረጃ፤ ስልክ 0994535353 | 0983636363 | 0987626262
🌗በእጅ ያለ ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል ስንት ወርቅ ይዛችሁ እንደመዳብ ካቀለላችሁት ከእጃችሁ ሲወጣ ይቆጫችኋል። ዛሬ እናታችሁ አጠገባችሁ ስላለች አመስግኑ ዛሬ አባታችሁ ስላለ ተመስገን በሉ ዛሬ ጤና ስላላችሁ ፣ ዛሬ ወጥታችሁ መግባት ስለምትችሉ አመስግኑ።
💡ይህ ሁሉ ባይኖራቸሁ እንኳን በህይወት ስላላችሁ ተመስገን በሉ፣ በህይወት ያለ ነውና የተበላሸውን ማስተካከል የሚችለው። በህይወት ከመኖር በላይ ዋጋ ያለው ነገር የለም፤ የምናገኘውም የምናጣውም በህይወት ስላለን ነው። መኖርን ደግሞ በነፃ ነው ያገኘነው፣ ምሬት ዓይንን ያጨልማልና ደስተኛና አመስጋኝ እንሁን።
💡እጅግ ውድ የሆኑ ነገሮች በነፃ ነው የተሰጡን፡፡ ፈጣሪ የአቅማችንን ልክ ስለሚያውቅ የከበሩትን ነገሮች ያለክፍያ አስረከበን፡፡ አየር፣ውሀ፣ ደማችን፣ አካላችን፣ ፀሀይዋ፣ ዝናቡ እና አፈሩ በክፍያ ቢሆኑ ማን መግዛት ይችል ነበር? ህልውናችን በነኝህ ነገሮች እጅግ የመቆራኘቱን ያህል በገንዘብ የሚገዙ ቢሆኑ ኖሮ እኔነኝ ያለ የምድር ባለጠጋስ ወጪውን ይችለው ነበር ወይ ?
❤️በነፃ የተሰጡን ባይኖሩ ኖሮ ሰው በውድ የሚራኮትባቸው ቁሶችስ መች ይኖሩ ነበር፡፡ ሰው ርካሹን በውድ ይሸጣል ፈጣሪ ግን ውዱን በነፃ ይሰጣል፣ ማጉረምረሙን ትተን ስለ ፈጣሪ ለጋስነት እናመስግን ከምናስበው በላይ ባለፀጎች ነን፡፡
🌗ስለ ሁሉ ነገር አመስጋኝ ሁን ማመስገን ስትጀምር አለም ወደአንተ ታዘነብላለች ነገሮች በሙሉ መልካም ይሆናሉ። ካሰብከው በላይ ሁሉ ነገር ሲስተካከል ሲያምር ታየዋለህ በምድር ላይ ሁሉ ነገር ለመልካም እንደሆነ ስታውቅ፣በማመስገን ስትታጀብ ቤትህም ይደምቃል ኑሮህም ይሞቃል በረከት ሁሉ ወዳንተ ይመጣል።
ልባችን ሁሌም ለምስጋና ክፍት ይሁን!
ውብ ቅዳሜ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍@EthioHumanitybot
📍የተሻለ አለህ
በአውሎ ንፋስ ውስጥ ብትሆን፣ ዶፍ ዝናብ ቢወርድብህ፣ ዋጋህ ያነሰበት፣ መኖርህ የማይቆጠርበት፣ አበርክቶትህ የማይታይበት፣ ስራህ የማያፈራበት፣ ማንነትህ የማይመረጥበት ስፍራ ብትኖር እንኳን ፈጣሪ አብሮህ ካለ ሁሌም የተሻለ ከፍ ያለ ነገር አለህ።
🔷ምንም እንኳን እምነታችን ቢጎድል፣ ክፋታችን ቢበዛ፣ ሃሳባችን ቢያንስ፣ ምግባራችን የወረደ፣ ስራችንም አሳዛኝ ቢሆንም ፈጣሪ ግን ጥሎ አይጥለንም።፣ ትቶ አይተወንም ሁሌም ይመለከተናልና መቼም ችላ አይለንም። የተውን ሰዎች ይኖራሉ፣ ያገለሉን፣ የተጠየፉን እንዲሁ እንደዋዛም የናቁን ሰዎች ይኖራሉ ዋናው ነገር ግን በፈጠረን አለመገፋታችን አለመረሳታችን ነው።
♦️የተሻለ አለህ! ከዛሬው የላቀ፣ ከትናንት የገዘፈ፣ ከአሁንህ ያየለና ከፍ ያለ ስፍራ ይኖርሃል። የማይቀየሩ የሚመስሉ ከባድ ሁኔታዎች ይቀየራሉ፤ ይወርዱ የማይመስሉ ሸክሞች፣ ይፈቱ ያልመሰሉ ችግሮች፣ ይስተካከሉ ያልመሰሉ ውጥንቅጦች ይወርዳሉ፣ ይፈታሉ፣ ይስተካከሉ።
እምነትህ ቢፈተን ግራ አትጋባ ይልቅ ለተሻለ ክብር እንደታጨህ አስተውል፤ በፈተናህ ብዛት አትደናገር ይልቅ የድልህ ቀን ቅርብ እንደሆነ አስተውል። በጫናዎች ብዛት የማትሸበር፣ ለምድራዊ ፈተና የማትበገር፣ ከፈጣሪህ ውጪ እንዳልሆንክ አስተውል።
🔷አንዳንዴ ማሳለፍ እየቻልን አቅፈናቸው የምንቀጥላቸው ብዙ ኮተቶቻችን ጣእሙን ማየት እንዳንችል ሁሉ ነገራችንን ዘግተንባቸዋል። ለማማረር እንጂ ለማመስገን ስንፈናል ለማዘን እንጂ ለመደሰት ጉልበት አጠተናል። መቆየት በማይገባን ቦታ ላይ በመቆማችን ማሳለፍ የሚገባንን አላፊ ሃሳቦችን እንዳያልፋ መንገድ ዘግተንባቸዋል እሰኪ ነቅነቅ እንበል እናሳልፋቸው የሚመጡት ሁሉ እንደአመጣጣቸው እንሸኛቸው አኛም ከቆምንበት አስተሳሰብ ስናልፍ ሁሉም ጊዜያዊ መሆኑን እናውቃለን።
ሁሉም ያልፍ የለ ትላንትናም አልፏል ዘሬም ታልፋለች ነገም ትቀጥላለች እኔም አንተም እናልፋለን ምክንያቱም ሁሉም ያልፋል።ሁሉን የፈጠረ፣ ሁሉን የያዘ፣ በሁሉ ውስጥ ያለው አምላክህ ባንተ ውስጥ ስለመኖሩ አትጠራጠር፤ ለተሻለው ስፍራ እንደሚያበቃህ እምነት ይኑርህ።
🔑ማሰብ ላይ በርታ፤ መስራት ላይ ጠንክር፣ አምላክህን ይዘህ ፈተናህን ተጋፈጥ፣ በፀሎትህ ፅና፣ ምስጋናህን ደጋግመህ አቅርብ፣ ካንተ በላይ የሚሰራብህ፣ ተአምር የሚያደርግብህ ፈጣሪህ አብሮህ እንደሆነ አስብ። ብቻህን የሆንክ ቢመስልህ እርሱ ከጎንህ አለ፤ የተገፋህ ቢመስልህ በእርሱ እቅፍ ውስጥ ነህ፤ የወደክ ቢመስልህ እርሱ ያነሳሃል፤ በሚገባህ ስፍራም በክብር ያቆምሃል።
ውብ አሁን ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍@EthioHumanitybot
💚ከትሕትና የበለጠ መልካም ነገር የለም። የደካማነት መገለጫ አይደለም ፣ ትህትና የትንሽነት ምልክት አይምሰልህ የዋህነት ደካማነት ሳይሆን የለስስት የመኖር ችሎታ ነው፣ ደግነት የመልካም ሰው የህይወት መምርያ ነው።፡፡ትህትና ዝቅ ላሉት የምናሳየው ፍቅርና ክብር ነው፡፡ፍሬ ያለው ዛፍ ዘንበል ይላል ቀና የሚሉት ፍሬ የሌላቸው ናቸው፡፡ትህትና የልብ ነው፡፡
አየህ አንተ ባታስበውም አንተ የምታስፈልጋቸው ብዙ ሰዎች አሉ ፣ ያንተ መኖር የሚያኖራቸው አያሌ ሰዎች አሉ ። ህይወትም ትርጉሟ የሚጨምረው ለሌሎች መኖር ስንጀምር ነው፣ ምንም የለኘም ምንም መስጠት አልችልም አትበል ያለህን ካሰብከው ብዙ ነገር ማድረግ ትችላለህ፡፡
💛"ሰው ሁሉ በልቡ ያለውን ይሰጣል።"
በውስጥህ ያለውን ነው የምትሰጠው ሁሌም ደግ ሁን። ቸር ለመሆን ሃብት እስክታገኝ አትጠብቅ። አንዳንዶች ካንተ የሚፈልጉት ፈገግታህን ነው ፤ አንዳንዶች ሰላምታህን ፤ አንዳንዶች ጊዜህን ፤ አንዳንዶች ሃሳብህን ፤ አንዳንዶች ድጋፍህን ፤ አንዳንዶች ጓደኝነትህን ሊሆን ይችላል ።
❤️ሁላችንም ለሌላው የምናካፍለው ብዙ ነገሮች አሉን ፈገግታ እና ደስታችን እንኳን የምናውቀውን ሰው ቀረቶ የመንገደኛውን ሰው ቀን ብሩህ የማድረግ ሃይል አላቸው። ሀብታም ሁን ወይም ደሀ ደግነትህን በዛ ሚዛን አትመዝነው! ዋናው የሚያስፈልግህ ሀብታም የሆነ ልብ ብቻ ነው"!
ውብ አዳር ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍@EthioHumanitybot
📍ወዳጄ ሆይ
ሥር የሰደዱ ዛፎች ነፋስን ይቋቋማሉ ፣ ወደ ታች የጠለቁ መሠረቶች ብዙ ፎቅ ይሸከማሉ ። ሰውም በሳል ሲሆን በፈተና ይጸናል ፣ ፈተናና ነፋስ ያልፋሉና ። ነፋሱ ዘንበል ቢያደርግህም እንዲሰብርህ መፍቀድ የለብህም ። ብዙ ጫናዎችን ለመሸከም እውቀትና ማስተዋልን ገንዘብ አድርግ ። አንተም እንደዛፉ ስር ስደድ ጠንካራነት እውቀት አለው ፣ በጥበብ ይናገራል ፤ ተግባር አለው ። ጠንካራነት ስሜት ሳይሆን ተግባር ፣ ፉከራ ሳይሆን ድርጊት ነው ። ጠንካራነት ሞራልም ምግባርም ነው።
📍ወዳጄ ሆይ
ፊት የልብ አደባባይነውና ሁሉን ቅሬታህን ፊትህ ላይ አታስነብብ፡፡ ጠላቶችህ ፊትህን እንጂ ልብህን እንዲያዩ አትፍቀድ፡፡ ለስድባቸው ስድብን አትመልስ ጆሮ ሰጥቼ ሰምቻችኀለሁ ማለት ነውና፡፡ ለአሳማሚዎችህ በቸኛው ማለፊያ ታምሞ አለመጠበቅ ነው ። ታመህ ካልጠበቀቻው ጆሮ ሰትጠህ ዝቅ ካላልክላቸው የሚያሳምምህ የለምና፡፡ ከራስህ ጋር ሳትመክር ከሰው ጋር አትመካከር፡፡ ለአንድ ሀሳብ የሶስት ቀን እድሜ ስጠው፡፡ ባዕድ ባለበት ስለቤትህ አታውራ፡፡ ለግቢህ አጥር ፣ለቤትህ በር፣ለህይወትህ ሚስጥር ይኑርህ፡፡ የተሻልክ ሳይሆን የበለጥክ ሁን፡፡
📍ወዳጄ ሆይ
መሬትህ በሚሸከመው መጠን ቤትህን ሥራ ፣ ወዳጅህ በሚችለው መጠን ምሥጢር ንገረው ፣ ተማሪህ ባደገበት መጠን መግበው ። የሌላው የሆነችውን ሴት ላንተ አትመኝ ። ያንን ጥላ ስትመጣ አንተን ጥላህ መሄድ እንደምትችል እያስተማርካት ነው ። አንቺም የሌላውን ባለትዳር አትመኚ ።
📍ወዳጄ ሆይ
ብትታመም በአገርህ ትታመማለህ ። አገርህ የታመመች ከሆነች ግን ዓለም ዝግ ይሆንብሃል ። ተሰደህም ለመከበር አገር ያስፈልግሃል ። ከሰላም የበለጠ ሀብት ፣ ከማስተዋል የበለጠ ሥልጣኔ ፣ ከፍቅር የበለጠ ደስታ የለም ። ያለ ፈጣሪ እየተስፋፉ ያሉ ሰዎች እየጠበቡ ነው ። ልብስ ጸድቶ ልብ ከቆሸሸ የመንፈስ ነጻነት ገና አልመጣም ። የድሮ ሰው ልቡ ንጹሕ ፣ ልብሱ አዳፋ ነበር ። የዛሬ ልጅ ልብሱ ንጹሕ ፣ ልቡ ሸርታታ ነው።
📍ወዳጄ ሆይ
የሰብዊነት ሥራ ለሰው ሁሉ የሚደረግ የደግነት ስራ ነው፣ ደግ ለመሆን ጥግ አትያዝ ። ከሥርህ ያለው አንተ የማትችለውን የሚችልልህ ነውና አክብረው ። ቆጥረህ ከሰጠህ ስጦታህ ይረክሳል ። ደብቀህ ከሰጠህ ስጦታህ ሲወራ ይኖራል ። ከፍ ስትል ልታይ ካልክ ሁሉም ሰው ስትወድቅ ያይሃል ። በከፈትክለት መጠን ጠላት ይገባል ። ሰይጣን አስገድዶ ሳይሆን አዘናግቶ የሚገድል ጠላት ነው ።
💡እናም ወዳጄ
የታወከ ሌሊት ሲገጥምህ በሰላም ስላደርክባቸው ሌሊቶች አለማመስገንህን አስብ ። ቀኑ መብትህ ሳይሆን ስጦታህ ነውና አመስግንበት ። እሰይ ነጋ ማለት ሲገባህ ደሞ ነጋ አትበል ።ሲያነጋልህ ምንም ክፈያ ላላስከፈለህ ጌታ የማለዳ ምስጋና ለማቅረብ አትዘግይ ። ወጥቶ የመግባት ዋጋው ትልቅ ነውና የምሽት ጸሎትህንም አታስታጉል ። እያጣጣርክ ስለ ጤና ከመጸለይ በጤናህ ፈጣሪህን አመስግን ።
ውብ ጊዜ❤️
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
✍ @EthiohumanityBot
✨የዛሬ ደስታህ የዛሬ ነው። የነገ ደስታህ የነገ ነው። ፈጣሪ አንተን የሚያስደስትህ ነገር ሊሰጥህ ምንም እጥረት የለበትም። አንተ ብቻ በሆነውም ባለህም በሚሆነውም በሁሉም ተደሰት። ውስጥህ የሚያሳምምህን ሳይሆን የሚያስደስትህን እይ። ውስጥህ የሚያሳዝንህን ሳይሆን የሚያዝናናህን እይ።
ውስጤ ያለችውን ትንሽዬ ደስታ አስተውዬ ባየሁ ጊዜ ግን የፈጣሪን መልካምነትና ቸርነት አያለሁ። የፈጣሪን ደግነትና ቅንነት አስተውላለው። ከምንም በላይ የፈጣሪን ፍቅር አያለሁ። በየቀኑ በየሰአቱ በየደቂቃው ከስምንት ቢሊዮን የዓለም ሰው ሁሉ እኔንም አለመርሳቱ ይደንቀኛል። ውስጤ በፈጣሪ የተቀመጠችውም ትንሽዬ የደስታ ቅባትም በአካሌ ውስጥ ካሉትና በላዬ ላይ ከተፈጠሩት አሉታዊ ነገሮች ሁሉ ትልቃለች።
💡ውስጤ ያለችው ሚጢጢዬ የደስታ ፍንጣቂ ካጋጠሙኝ የሂወት መሰናክሎች ሁሉ ትገዝፍብኛለች። ያኔ ላለመሳቅ ምክንያት አጣለሁ። ከውስጤ የተፈጠረው ደስታ በፊቴ ላይ ይደገማል። መጀመሪያ ውስጤ ይስቃል በመቀጠል ጥርሴ። ከዛ ደሞ የኔ ደስታ ከኔ አልፎ በዙሪያዬ ያሉት ላይ ይጋባና እነሱም ይስቃሉ።
የእውነት ፈጣሪ እንዴት ድንቅ ነው። በሱ ላይ እምነታችንን በጣልን ጊዜ ልባችንን በደስታ ፊታችንን በፈገግታ ይሞላዋል! በእውነት የፈጣሪን ጥበበኝነት መመስከር ከፈለጋችሁ በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑም ውስጠ ውስጣችሁን ተመልከቱ። ያኔ የምታገኙት የደስታ ጨረር ከከበቧችሁ ችግሮች ሁሉ ይበልጡባችኋል። ያኔ ከልባችሁ ትስቃላችሁ።
📍የበለጠ የፈጣሪን የእውቀት ጥግ ደሞ የምታዩት በምንምና በየትኛውም ጊዜ ለእያንዳንዳችን እደግመዋለሁ ለእያንዳንዳችን የሚሆን ደስታ ሰቶናል! እሱ ጋ ስስት የለም። እሱ ጋ ማዳላት የለም። የተወሰኑትን አስደስቶ የተወሰኑትን የሚያስከፋ ሚዛናዊ ያልሆነ አምላክ አይደለም። ውስጣችንን በደንብ ማየት ስንጀምር በገንዘብ ልንገዛው የማንችለውን ደስታ እናገኛለን። ይህም ደስታ ሳቅን ይፈጥርልናል። ጥርሳችንም ከልብ በመነጨ ደስታ ፈገግ ይላል።
💡ዛሬ ይህንን በውስጣችን ያለውን ደስታ የምናይበትና ፊታችንን በሳቅ የምንሞላበት ቀን ነው። አስተውለን ወደ ውስጥ እንይና ውስጣችን ያለውን ደስታ በፊታችን ላይ እንዲንጸባረቅ እንፍቀድለት!ውስጣችንን ስናይና ፈጣሪ ውስጣችን ያስቀመጠውን ድንቅ ስጦታ ስናስተውል ፤ያኔ አለመሳቅ ይከብደናል። አለመደሰት ታሪክ ይሆናል። ከፈገግታችሁ ጀርባ ያሉትን ብዙ ችግሮች መከራዎችና ማጣቶችን ሳይሆን ትንሿን ጥሩ ተአምር እዩ፤ያኔ ትንሿ ብዙ ትሆናለች። ከውስጥ የተጫረችው ሚጢጢዬም የደስታ ፍንጣቂ ከናንተ አልፋ ለዓለም ሁሉ የምትበቃ ትሆናለች።
🔑 ከውስጥህ ያለው ብዙ ነው። ከውስጥሽ ያለው ድንቅ ነው። ፈጣሪንም ለሰጣችሁ ሁሉ አመስግኑ! እውነቴን ነው ውስጠ ውስጣችሁ ያለውን ስታስተውሉ (ማየት ብቻ አይደለም ማየት ወስጥ ማስተዋል ካልተጨመረበት ትርጉም የለውም) ያኔ ባላችሁ ሁሉ ትገረማላችሁ።
✍ብሩክ የሺጥላ
ውብ አሁን❤️
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
✍ @EthiohumanityBot
💎አንዳንዱ ሰው ዛሬ የሚኖርበት ቀን ትናንቱ ነው:: ትናንት ወድቆ ነበር፣ ተሳስቶ ነበር ፡፡ ትናንት የሆነ ነገር በህይወቱ አልፏል፡፡ ትናንቶቹ በትዝታ እየመጡ ዛሬውን ይነጥቁታል፡፡ የሰው ልጅ ውድቀቱ ብቻ ሳይሆን ስኬቱም ጠላቱ ነው ይባላል፡፡
📍በረጋ ውሀ ላይ ሁሉም ሰው ጎበዝ ካፒቴን መሆን ይችላል፤ግን የእውነተኛው ካፒቴን ችሎታ በማእበሉ ጊዜ ይታያል፣ እንደሚባለው ሁሉ የህይወታችንም መሪነት ትናንት አሁንና ወደፊት በገጠሙንና በሚገጥሙን መሰናክሎች ይፈተናል። የውስጥ ጥንካሬያችንም በነዚሁ ጊዜያት ይፈተሻል።
የተሳካ ህይወት መኖር የማይፈልግ ሰው ያለ አይመስለኝም፡፡ ሁሉም ሰው ታሪክ መፃፍ ይፈልጋል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ራሱን መመርመር አለበት ፣ የሰው ልጅ ከፍታና ዝቅታ፣ መነሳትና መውደቅ በሚገነባው የስብዕና ጥንካሬ ላይ የተንጠለጠለ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን በምናወራበት ሰዓት ነገ ብለን ስናስብ፣ ጊዜያችንን አዲስ ማድረግ እንችላለን፡፡ ምክንያቱም አእምሮዋችን ስላለ ፣ አእምሮዋችን ሁሉን ያስታውሳል፡፡
💎እራስን መለወጥ ቀላል ጉዞ አይደለም። እንደ አብዮት ቆጥረን ለዘመናት ተብትቦን የኖረውን ማንነት ገርስሰን መጣል አለብን ፣ ደካማው ማንነታችን ወርዶ ስኬታማው ማንነታችን ሊነግስ ይገባዋል።
ብዙዎቻችን ውስጣችን ትርምስምስ ብሏል፤ የምንፈልገውን አናውቅም፤ የምንራመድበትን መንገድ አናውቅም፤ ብዙ ሃሳቦች በውስጣችን አሉ፤ ግን በየትኛው ሃሳብ ጸንተን እንኑር? ለዚህ ነው በራሳችን ላይ አብዮት መጥራት
የሚያስፈልገን። ህይወት እጅግ አጭር ናት፤የፈለግነውን አይነት ኑሮ ለመኖር፤ እራሳችንን መለወጥ ግድ ይለናል፤ ደካማውን ጥለን፤ መልካሙን እኛነታችንን ልንተክል ጊዜው አሁን ነው።
ውብ ቅዳሜ❤️
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
✍@EthiohumanityBot
❤️አንዳንዶቻችን ከደስታ ይልቅ ሃዘንን፣ ከስኬት ይልቅ ችግር ላይ መቆዘም እንወዳለን።
እንዲህ ሆኜ...ተንከራትቼ...በዚህ ወጥቼ በዛ ገብቼ እያለን ችግሮቻችንን ሁሉ እንደከንቱ ውዳሴ ስንደጋግም፣ እንዲሁ ስናከብዳቸው እንውላለን ።
❤️አዎ! እርግጥ ነው ሁሉም ሰው የራሱ የማይመቹ የህይወት መንገዶችን ያልፋል ነገር ግን ችግሩን አብዝቶ ስላወራው ብቻ ከችግሩ ነፃ ይሆናል ማለት አይደለም። ይልቅ ለችግሩ ተገዢ እየሆነ ይሄዳል እንጂ...ከዛም ባለፈ ችግሩን ማንነቱ አድርጎ ይቀበላል።
❤️ወዳጄ ሆይ እስኪ አመስጋኝ እንሁን። ማታ ተኝቶ ጠዋት መንቃት በራሱ እኮ እራሱን የቻለ እድለኝነት፣ እራሱን የቻለ መመረጥ ነው። በጤንነት ብቻ መኖር በራሱ ድንቅ ነገር፣ ድንቅ ስጦታ ነው። በተሰጠን አመስጋኝ እንሁን የቀረው ነገር ወይም የኛ አይደለም ወይም ግዜውን ጠብቆ መምጣቱ አይቀርምና።
ፈጣሪ ሆይ
ካላየኃቸው እና ከማላቃቸው አደጋዎች ስላዳንከኝ ፣ በፈተና አፅንተህ ስላጠነከርከኝ ፣በፈተናዎች ወድቄ ስለተማርኩኝ
ክበሩን አንተ ውሰድ 🙏
ስታበይ እንደመታበዬ ፣ስበድል እንደ በደሌ ፣ ስወድቅ እንዳወዳደቄ፣ ሰጠግብ እንዳጠጋገቤ በሆንኩት ልክ ሳይሆን እንደ ቸርነትህ ስለምታኖረኝ
ክበሩን አንተ ውሰድ 🙏
የሚያስፈልገኝን ሁሉ ስለምትሰጠኝ ፣ በመንገዴ ሞገስ ስለሆንከኝ ፣ ዙሪያዬ በመልካም ሰዎች ስላስከበብከኝ ።
አመሰግናለሁ 🙏
በረከቴ ስለሚታየኝ ፣ጤናዬ ስለሚታወቀኝ፣
ህያውነትህን ተጠራጥሬ ስለማላውቅ
አመሰግናለሁ 🙏
ውብ ዛሬ !!❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot
✨ለማግኘት በምናደርገው ጥረት ውስጥ የማጣት ሥጋት፣ ዕረፍትን በመናፈቅ ውስጥ የሕመም ፍርሃት፣ ክብርን በመሻት ውስጥ የውድቀት ሥጋት፣ ሕይወትን በማፍቀር ውስጥ የሞት ፍርሃት፣ ድልን በመጠበቅ ውስጥ የሽንፈት ውጥረት በብርቱ ይታገለናል::
💎 ንቁ አእምሮ ያለው ሰው በራስ የመርካትም ሆነ ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታ አይታይበትም:: የዘመኑን መርዶ አዘል ዜናዎች ቢሰማም ለመኖር ከሚያሳየው ጉጉትና ጥረት አይቦዝንም:: የሕይወትን አስቸጋሪ ገጽታዎች ቢጋፈጥም “አበቃልኝ” አይልም:: ይልቁንም የወደፊት ተስፋው በፈጣሪ አስተማማኝ እጆች ውስጥ ፍጻሜ እንዳለው ስለሚያውቅ እያንዳንዱን ዕለት በብልሃት በጭምትነትና በመታዘዝ ያሳልፋል:: አመለካከት የሕይወትን ስኬትና ውጤት ይወስናልና አስተሳሰባችን የቀና ከሆነ ስኬታማነታችንም የተረጋገጠ ነው::
💫 ማናኛችንም ብንሆን መታወክ የሌለበት ከፈተናና ከውጣ ውረድ የጸዳ መሻታችን ሁሉ የተሟላበት ኑሮ ቢኖረን እንፈልጋለን፣ ነገር ግን ሠው በመሆናችን ብቻ ደስታና ሃዘን፣ ማጣትና ማግኘት፣ መውደቅና መነሣት፣ ማመንና መከዳት እንዲሁም ውጣ-ውረድ የተሞላበት መሠናክል ይፈራረቁብናል፡፡ ዋናው ነገር በነዚህ ነገሮች ተፈትኖና ነጥሮ መውጣት ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡
ፈጣሪ ይህንን ድንቅ አዕምሮ ወይም ልዩ መክሊት ሲሠጠን በመጣው ወጀብ እንድንወሠድ ሳይሆን በጥበብና በዕውቀት ችግሮችን ፈትተን፣ ትምህርት ወስደን፣ እንደወርቅ በእሳት ተፈትነን በማስተዋል ነጥረን እንድንወጣ ነው፡፡
💎አስደሳች ፍጻሜ አጠብቅ ፣ህይወት ሁሌም ሁለትዮሽ ናት፣ መኖርን ምሉዕ የምናደርገው ሁለት ተቃራኒዎችን በሚዛን በመከወን ነው፡፡ እንባም ሳቅም፣ ደስታም ኀዘንም ፣ መስጠትም መቀበልም ፡፡ መሙላትም መጉደልም። ሲጠቃለል ፣ ሕይወት ኅብረ ቀለሟ ያማረ ቀስተ ደመና ነች።
ውብ ጊዜ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
@EthioHumanityBot
📍መስጠት ዋና ስራህ ይሁን
ብዙ በመልፋት ብዙ በመጣር ትልቅ ውጤት ልታመጣ ልታሳካ በሀብት ደረጃ ልትበለፅግ ማግኘት የምትፈልገውን ሀብት ልታገኝ ትችላለህ ነገር ግን ከበፊቱ የተለየ የተሻለ ቆንጆ ምግብ ትመገብ ይሆናል እንጂ ልኩ አይጨምርም ስላለህ ብቻ ሰው መብላት ከሚችለው መጠን በላይ አትበላም በአንድ ግዜ ብዙ ልብስ አትለብስም ሁለት መኪና ባንዴ አትነዳም የምትኖረውም አንድ ቤት ላይ ነው ነገር ግን ስትሰጥ እነዚህን ሁሉ ባንዴ ማድረግ ትችላለህ።
❤️ የተራቡ ስታበላ እርካታው ሚሊዮኖች ከሚበሉት በላይ ነው የታረዙትን ስታለብስ ከለበስከው በላይ ሙቀት ከለላ ይሆንሀል ባንዴ በብዙ ልብስ ታጌጣለህ ህይወትም ትርጉሟ የሚጨምረው ለሌሎች መኖር ስንጀምር ነው ! ሁሌም በጎ በጎውን ማድረግ ስትለማመድ መልካም ገበሬ ትሆናለህ። ለሌላው የሚጠቅም መልካም ድርጊት ወደ ዓለም ስትልክ መልካምነትህ ዞሮ ይከፍልሃል፣ ብድራቱን ታገኛለህ።
የጣልከው አልያም ያካፈልከው ሁሉ መልሶ ብድራቱን ይከፍልሃልም። መልካም መሆንህ ምንም ኪሳራ የለውም። ያንተ መልካም ስነምግባር ሌላውን ተመልካች ከተኛበት የመቀሰቀስ መግነጢሳዊ የስበት ኃይል እንዳላት አንተ አታውቅም ይሆናል። በዚህ ምድር ላይ የተዘራ ማንኛውም ነገር እንዲሁ ወድቆ የሚቀር ላይሆን ይችላል።
💡ወሳኙ የምንሰጠው መጠን ትንሽነትና ትልቅነት ሳይሆን በምንሰጠው ነገር ላይ የምንጨምረው ፍቅር ነው፣ ስላለን ስለሞላን ብቻም ሳይሆን ካለን ማካፈልንም መልመድ እንጀምር። የህይወት መሰረት የሚጣለው ሁሌም ከዛሬ ነው ፣ ከዛሬም አሁን!
ውብ አሁን❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot
💡ከዜሮ መጀመር ትችላለህ
📍ያለንን ነገር ሁሉ ብናጣ ፡ የተመካንባቸው ሰዎች ቢርቁን ፡ በሽታ ቢያሰቃየን ፡ የባንክ አካወንታችን ባዶ ቢሆን ፡ ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች ቢከሰቱብን ፡ ሁሌ ከዜሮ መጀመር ይቻላል።
እድሜያችን ቢገፋ እንኳን በልጅነታችን የተመኘነውን ማንነት በየትኛውም ጊዜ መገንባት እንችላለን ። ከኛ የሚጠበቀው ለመለወጥ ያለን ቁርጠኝነታችን ፡ ፅናታችን ፡ እምነታችንና ትዕግስታችን ነው። ማትኮር ያለብን ችግሩ ላይ ሳይሆን ወይም ስለችግሩ ማልጎምጎም ሳይሆን ችግሩን ለመፍታት የሚረዱንን መሰረታዊ ጽንስ ሀሳቦች ቁርጠኝነት ፡ ጽናትና ፡ ትዕግስት ላይ ነው።
💡 የሕይዎትህ መለወጫ መሪ ያለው በራስህ እጅ ላይ ነው። ሌሎችንና ሌላ ጊዜን አትጠብቅ። ጊዜው አልፏል ብለህም አትቁም ፡ ያንተ ጊዜ አሁን ነው። ጉዳይህ ያለቀና ያበቃለት ቢመስልም አንተ ከጠነከርክ እንዲሁም ከልብህ ፡ እኔ አሁንም ተስፋ አለኝ ብለህ ከባዶ የመነሳቱ ድፍረቱ ካለህ ያኔ አንተ አንፀባራቂ ብርሀንን ታያለህ። ራስህንም ድሮ ከነበርክበት ባዶነት አውጥተህ እንደገና ሕይዎትን የመኖር ፅንሱን ውስጥህ ትፀንሳለህ።
ያኔ አንተ ተቆርጠህ ከተጣልክበት ትቢያ እንደገና አገግመህና ፡ አቆጥቁጠህ ትታያለህ። ልምላሜህም ከበፊቱ የበለጠ ይሆናል። ቅርንጫፎችህ ፡ ተቆረጡ እንጂ ዋናውን የሕይዎት ምስጢር የያዘችው አንተን ከአፈሩና ፡ ከውሃው የምታገናኝህ ስራህ አልተቋረጠችምና እንደገና ትለመልማለህ። እንደገና እራስህን በእድገት ምናብ ከዋጀኽው በድጋሚ ታብባለህ።
📍በድጋሚ ቀንበጥ ፡ ቀንበጥ የሆኑ የሚያስጎመጁ ፡ አረንጓዴ ቅጠሎችንና ፡ ቅርንጫፎችን ፡ ታቆጠቁጣለህ። ግመል በበረሓ ስትጓዝ በረሓው ላይ ውሃ እንደሌሌ ታውቃለች። ግን ወደ በረሓው እንድትገባና ፡ እንድትጓዝ ስናደርጋት ፡ ወደ ኋላ አታፈገፍግም ወይም አትፈራም። ምክንያቱም ፡ የሻኛው ጮማ ውስጥ በቂ የሆነ ምግብና ፡ ውሃ እንዳለ እርግጠኛ ስለሆነች እሷ የምትዘጋጀው ከበረሓው ፡ ከመግባቷ በፊት ውስጧ ምግብ በማጠራቀም ነው።
አንተም እንደ ግመሏ ውስጥህ ላይ አትኩር። ሌሎችን የበረሓው ግለት ፡ የበረሓው ንዳድ ፡ የበረሓው አሸዋና ፡ የበረሓው መጨረሻ መራቅ ተስፋ ቢስ ሲያደርጋቸው ፡ አንተ ግን ለድል አነሳሳቸው ፡ ውስጣቸው ያለውን የአሸናፊነት ጮማ ፡ የተስፋ ጮማ ፡ የፍቅር ጮማ ሻኛ እንዳለ ንገራቸው። አንተ ከፊት ሆነህ ባለህ የዕውቀት ፡ የፅናት ፡ የትዕግስት ፡ ብረሀንህ ጉዟቸውን አቅልጥላቸው።
💡አንተ ራስህን ከምንምና ፡ ከባዶ አንስቶ ለትልቅ ደረጃ ፡ የሚያበቃ አቅም በውስጥህ አለ። አንድ ልታውቀው የሚገባህ ትልቅ ቁምነገር ፡ ዜሮ ፡ የቁጥሮች መጨረሻ ሳይሆን ፡ የቁጥሮች መጀመሪያ መሆኑን ነው። ያለህ ነገር ሁሉ ዜሮ የሆነ ከመሰለህ ፡ እንግዲያው አንተ ደስ ሊልህ ይገባል። ምክንያቱም ፡ በህይዎትህ ያለህ ደስታ ሁሉ ፡ ያለህ ሀብት ሁሉ ፡ ያለህ ዝና ሁሉ ፡ ያለብህ ገንዘብ ሁሉ ፡ ያለህ ተቀባይነት ሁሉ ፡ እንደገና ከዜሮ ፡ መጨረሻ ፡ ወደሌለው ቁጥር "ሀ" ብሎ ሊንደረደር ነውና !!!
📓የኔ ስጦታ
✍ብሩክ የሺጥላ
ውብ ምሽት❤️
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
✍@Ethiohumanitybot
✨ለውብ ቀንህ
ፍሬድርክ ኒቼ በደስታና በፈንጠዝያ የምፎልሉትን እንሰሳት ተጠጋና ጠየቃቸው።
"ለምንድነው እንደዚህ ደስተኛ ልትሆኑ የቻላችሁት?" የሚል ነበር ጥያቄው። እነሱም
ባንድነት፣ ባንድ ቃል መለሱለት።
✨ምንም ሳይወያዩ፣ ምንም ነገር ሳይፎካከሩ፣ መንፍሳቸውም ሳይቀናና፣ አንዱም ሌላውን
ሳይተች፣ ደመ-ነሳቸው በሚነግራቸው መሰረት፣ " ከሳለፍነው ታሪክ ጋር ምንም ቁርኝት (Attachment) ስለሌለን ነዋ!" አሉት። ከአፍታ በሁዋላ "ምን አላችሁኝ? እስኪ ድገሙልኝ?" ሲል
ጥያቄዎቹን አዥጎደጎደባቸው ።
እነሱ ግን የሰጡት መልስ አጭርና አስገራሚ ነበር።
"ምኑን ነው የምንደግምልህ?" የሚልና
ክው አድርጎ የሚያስቀር ………😁ፎቶው ከፅሁፉ ጋር የሚገናኘው ምኑ እንደሆነ ታውቃላችሁ?
እኛም በየቀኑ አዳዲስ የሆኑ እድል ይሰጡናል። የትናንት ጭንቀቶች አጥብቀን ምንሸከም ከሆነ ግን ዛሬን በሙሉ ሀይላችን መኖር አይቻለንም ፣ዛሬ የትናንት ተማሪ ነው፡፡ ዛሬ ነገን ውብ ቀን ለማድረግ የሚሰራ በእጃችን ያለ መክሊታችን ነው፡፡ የትናንትን ኋላቀርነት የሚደግም የዛሬ ቀን ለዛሬም አይሆንም፣ ለነገም አይተርፍም፡፡ ያለፈውን ደካማ ነገር መሻር ሲገባ የምንደግም ከሆነ ወደፊት መራመድ አንችልም፡፡ ትናንትን ወደነገ የሚያሻግረው ዛሬ ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ የትናንት ምርጥ ተማሪ ካልሆነ ነገውን ውብ ማድረግ አይችልም፡፡
✨ሕይወትን አስደሳች እና ቀላል አርጎ መኖር ይችላል። የተሸከመከውን የሀሳብ ክብደት ለመተው ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅብሀል፣ የሕይወት እውነተኛ ክስተት አሁን ነው። አሁን ባለህ ጊዜ ሰላም ፍጠር! ዛሬን እንደዛሬ በአዲስ ለመመልከት ፣ ትናንትህን መልቀቅ አለብህ፣ እራስህን አትጋርድ።
ውብ አሁን❤️
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
✍@Ethiohumanitybot
የሚያሳዝነው እኛ ሰዎች ሙሉ ሕይወታችንን መኖር ለመጀመር በመጠባበቅ ላይ ሆነን ሳንኖር መሞታችን ነው። Eckhart Tolle
“ይህንን ባገኝ ደስተኛ እሆን ነበር” የሁላችንም መፈክር አይደለም? ወይም የለመድነው የኑሮ ሂደት። ከላይ የሰፈረው የኤካርት ቶሌ አባባል ይህንን አኗኗራችን በደንብ ይገልጸዋል ብዬ አስባለው ። ሰዎች ኑሮን ለመጀመር እየጠበቁ ኑሮን ሀ ብለው ሳያጣጥሙ የእድሜያቸው ጀንበር ትጠልቃለች። ጥሩ ስራ ሲኖረኝ፤ ትዳር ስመሰርት፣ አላማዬን ሳሳካ ደስተኛ እሆናለው እያለን ለኑሮዋችን ቀጠሮ ስንሰጥ፤ ያሰብነው እስኪሳካ ደስተኛ ላለመሆን እየወሰንን ነው።
የሰው ልጅ ምኞት ማለቂያ የለውም። በጠየቅን ቁጥር ፈጣሪ ያልነውን ቢሰጠን እንኳን እንደሰው እረክቶ ለመኖር ይከብደናል። ለዚህ ነው ደስታችንን ነገ ከምናገኛቸው ነገሮች ጋር መቋጠር ዛሬን በሰመመን እንድንኖር የሚያደርገን፣ ያሰብኩት እስኪሳካ ደስተኛ መሆን አልችልም ማለት ነው “አስከዛው አልኖርም” ማለት ነው። የነገው ህይወታችን ትልቅ ትርጉም አለው፤ ዋጋው ግን የዛሬን ያህል በፍጹም አይሆንም።
በዚች አጭር ፁሁፍ እንለያይ፣
ለመኖር ስሟሟት ነበር :-
"በመጀመሪያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ለመጨረስ እና ኮሌጅ ለመጀመር ስሟሟት ነበር፣ ከዚያም ኮሌጅ ጨርሼ ሥራ ለመጀመር ተሟሟትኩ
ቀጥሎም አግብቼ ልጅ ለመውለድ ስሟሟት ነበር ፣ከዚያም ልጆቼ አድገው እድሜያቸው ለትምህርት እንዲደርስ እኔም ወደ ሥራ ቶሎ ለመመለስ ስሟሟት ነበር።
ከዚያም ጡረታዬ ደረሰ እሱንም ለማግኘት ተሟሟትኩ ፣አሁን ግን መሸብኝ እኔም እየሞትኩ ነው።በሕይወቴ ውስጥ ለነገዬ ስሟሟት፣ዛሬን መኖርን እንደረሳሁ ድንገት ገባኝ" ይላል ፀሀፊው።
እናም ወዳጄ ውብ አሁን! 😊
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍@EthioHumanityBot