ethiohumanity | Образование

Telegram-канал ethiohumanity - ስብዕናችን #Humanity

30703

🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣ መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣ እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣ ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣ እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡ አብረን እንደግ !! @EthioHumanity @Ethiohumanity ✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Подписаться на канал

ስብዕናችን #Humanity

ነገ ሸጋዋ ቅዳሚት ነች !


የ20❤+ዓመታት የሙዚቃ መልክ!!

ኤልያስ የሙዚቃው ሊቅ ተወርዋሪው ኮከብ....እንቅልፉን ሰጥቶን ሙዚቃውን በሰረገላ ከፍ አድርጓት ከሔደ ዛሬ ዓመት ከመንፈቅ ሆነው።

ኩልል ያለ የጠራ ንፁህ ውበት!!

የልማድን ቅጥር እንደመናድ...በአምክንዮ ነባራዊውን እውነታ እንደመጋፈጥ...
ደፈር ተባ ብሎ የይሉኝታን እስራት እንደመበጠስ... የጥላቻን ገደል ደፍኖ የፍቅር ድልድይ እንደማነፅ... የባርነትን ቀንበር ሰብሮ የነፃነት ብርሃን እንደመፈንጠቅ...በቅንነት ቀና ብሎ በፅድቅ መንገድ በኩራት እንደመራመድ... ከጃጀ ቀኖና አፈንግጦ ቅቡል ተአማኒ ስርዓት እንማፅደቅ...
የተዛባን ፍርድ አቃንቶ ፍትህን በሰው ልጆች ሁሉ እንደማስፈን..
እንደዚህ ሁሉ...ማነው..? ኤልያስ መልካ!!!

ከኤልያስ መልካ ስራዎች እጅግ በጣም የምወደው ሁሌም ሰርክ አዲስ የሚያስገርመኝ አንዱ "መልክሽ አይበልጥሽም" ሙዚቃ ተጋበዙልኝ!!

ሰላም እደሩልኝ!❤ ለኢትዮጵያችን ናካይታ!💚

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

ይፈለጋል !

ዝም የሚል የማይጠይቅ ፤ ሲነገረው አሜን አሜን የሚል፤ የግንኙነት ድንበር የማያበጅ፤ሲናቅ የማይቆረቁረው ፤ የበዛ ይሉንተኛ ፤ከቦታ ቦታ የሚለያይ አቋም የሚያንፀባርቅ ፤ ልምጥምጥ ፤ አቋሙን ፈርጠም ብሎ የማይናገር፤ ሳያስቀው የሚስቅ ፤ አላምንበትም የማይል ። ማብራርያ የማይጠይቅ። ቅሬታውን የማይናገር ፤ሸንጋይ ፤በየቦታው የሚያጨበጨብ ።ይገባኛል(ሲጠብቅ) የማይል ፤ ስለመብት እና ግዴታ የማይዘበዝብ
በጣም ነው የምንፈልገው !¡¡

በነገራችን ላይ

የምንፈልገው ልንገለው ነው¡¡¡¡


@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

:
ጌታ ሆይ - ክፍትም ብሆን
የባለጌ ልቃቂ
ኮረት እንኳ ባልሆን
የአሸዋ ዝርያ ድቃቂ
ቤት ለእንግዳ በለኝ 'በምስራቅ በር' --

አንተ በሌለህበት ቦታ
ሰማይ ተቀዶ ብሰፋ - እንኳን ልሾም የማልከበር --
የሰጠኸኝ ሁሉ ምሉዕ ነው
ግን እኔን የሚያብሰከስከኝ
እጄ የማይደርስበት ጀርባዬ - ባልበላሁት እያሳከከኝ
አወከኝ
:

አያ ሙሌ ❤️
[ጌታ ሆይ ነፍሴን ባርካት]

@EthioHumanity
@EthioHumanity

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

ለውብ ቀን!
💚

ሰዉ ዉበቱን እንጂ ቁንጅናዉን ሊፈጥር አይችልም።

ተፈጥሮ የሰጠንን አጣጥበን ከመዉጣት በዘለለ ቁንጅናን ልንፈጥረዉ አንችልም።

ማቆንጀት የምንችለው አስተሳሰባችንን ነው!

ውብ ቀን!💚

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

የድል ቀን!
💚💛❤️💪

እግርኳስ ከስፖርት በላይ ነው !

አንድነትን ይፈጥራል ፣ ሰላምን ያሰፍናል በጥላቻ ውስጥ ገብቶ ፍቅርን ይገነባል ።

ከ14 አመት በፊት ዲዲየ ድሮግባ የዛሬ ተጋጣሚያችን ለአምስት አመታት የቆየውን እርርስ በርስ ሲጨረሱ ጎል አስቆጥሩ በመማፀን ብቻ ጦርነቱን አስቁሞ ነበር ። ይሄ ሁሉ የሆነው በእግርኳስ ነው !

እግርኳስ ከሴክስ በላይ አስደሳች ነው ይለናል የባርሴሎናው የመሀል መሀንዲሱ ሰርጂዮ ቡስኬትስ ልክ 2010 አለም ዋንጫን ባነሱባት ቅፅበት ደስታውን ሲገልፅ ።

በ1915 እኤአ በእንግሊዝና ጀርመን መካከል በነበረው ጦርነት ለአዲስ አመት ሰላም ያሰፈኑበት ወታደሮቹ እግርኳስን በመጫወት ነው ። ለዚ ነው ከሱስም በላይ ነው ምንለው !!

አሁን የኛም ህዝብ በውስጡ ብዙ ነገሮች አሉበት በብዙ ነገር አንዱ ከአንዱ ተለያየቷል አድነታችን ከምንጊዜውም በላይ እየሻከረ የመጣበት ወቅት ነው 120 ሚሊየን ህዝብን በ90 ደቂቃ ተጋድሎ አንድነት ፍጠሩለት !!🙏🙏🙏

እውቁ ጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒ እሁድ እለት እንዲህ ሲል መልእክቱን ለጥቁር አንበሳዎቹ እንዲህ ሲል አድርሷል....

"ስራው አልተጠናቀቀም። እናንት ውድ የሃገራችን ልጆች ዛሬ ጨርሱትና #ፖለቲካ የረበሸውን ህዝባችሁን በእግሮቻችሁ ምትሃት ሰብስቡት፤ ሁሉም ያያችኋል፤ አንድነትን አሳዩት፤ የረሳውን ህብረት አስታውሱት፤ ችግሩን አስረሱት፤ ቁስሉ ባይሽር እንኳን ማስታገሻ ሁኑለት፤ የወዲያኛውን ሠፈር ከዚህኛው ሠፈር ጋር ቀላቅላችሁ ወደ ህብረቱ መልሱት፤ በጋራ የሚደሠትበትን ዕድል ስጡትና እግርኳስ ከስፖርትም በላይ መሆኑን አስተምሩት።"


ድል ያለ ድል ለሃገሬ ዛሬ ሁላችንም የምንደሰትበት በጋራ ስለ ኢትዮጵያችን የምንዘምርበት ካጠላብን ጥላ ትንሽም እንኳን ቢሆን ገፈፍ የሚልበት የድል ቀን!!
💚💛❤

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

ለሰንበታችን!
💚

የመኖራችን ህያው ምልክት ፣ የትናንሽ ትውስታ ሰነድ ፣የትናንት መንገድ አሻራ ፣ የዛሬ እውነት የነገ ታሪክ ፣ የትናንሽ ትርክት ዳና ፣ የነገ የገዘፈ ጣዕማም ሀውልት ይመስለኛል ትዝታ ለኔ።

ዛሬን በትናንት መነፅር ስመለከተው የመግዘፍም የመስነፍም ማንነት በህይወቴ ብራና ላይ ተከትቦ ይገኛል ፣ ከአትሮኖሱ አኑሬ ሳስሰው ፣ ስፈትሸው ደግሞ ይህ ነው የህይወት መስህቡ ፣ የመኖር ውሉ ያሰኘኛል....እንደ እድሜዬ ሁሉን ላይ መታደልን ደግሞ ኖርኩት ያሰኛል።

የአፍላነት የፍቅር ትኩሳት የሚጀመርባት ፣ በተወጋ እና የደም ነጠብጣብ ያሸበረቀ የደብዳቤ ዘመን ፍቅር ፣ የየዋህነት ዓለም ፣ ምግብ የማያስበላ ስሜት ፣ የአመት በዓል ፖስት ካርድ ፣ ንፁህ ስሜት ፣ ከቁሳዊ አለም የራቀ ቁርኝት ፣ ብዙ ያለመመኘት ፣ በትንሽ የመርካት እድሜዬ ውል ትለኛለች

ለፀብ ተጋግዘን ፣ ተቧድነን የምንራኮትበት ፣ እንደምን ናቀከኝ ብለን የተቧቀስንበት ፣ ስለት የመያዝ ትልቅ ጀብድ የሚያሰኝበት ፣
ጉርምስናዬ ትናፍቀኛለች ፣

በዚህ የእኔ የህይወት አምድ ውስጥ አብራችሁ የከተማችሁ ፣ በህይወት ግሳንግስ ላለመውደቅ የምትባትሉ ፣ የህይወት ማዕበል ወደ እዛኛው የህይወት አለም የገፋችሁ ፣ እንደ ምሰሶ በጠነከረ ወዳጅነት ዛሬ ድረስ የዘለቃችሁ ነፍሴ አብዝታ ታከብራችኋለች..... የትዝታ ማህደራችሁን እየፈተሻቹ ትናንታችንን ታስዳስሱን ዘንድ እየተጠየቃችሁ ካላችሁበት ይህን ዘፈን ተጋበዙልኝማ

ወንድሙ ጅራ
የእኔ ትዝታ

መልካም ሰንበት!💚

@EthioHumanity
@EthioHumanity

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

እምወድሽዋ!❤ቅዳሜዋ!❤ሸጋዬዋ!❤

የግጥም ጥግ (ርዕሱ አይደለም) ዛሬ ደርባባዋ ቅዳሚት ነች!❤ እና የዛሬ ቀናችንን ለቅዳሜ በሚመጥኑ በልኳ በወርዷ ልክክ ባሉ ግጥሞች ስንሞሽራት እንውላለን!!❤ የግጥም ጥግ አንድ...


ማነህ ላለኝ ....
በዘመን ላይ የበቀልኩ
የአንድ ሰሞን አበባ ነኝ ።

📝ቴዎድሮስ ካሳ




ኦ ፥ የሽቱዉ ቅመም
የሁሉ ቃና
እባክህ አትሂድ ፥ እባክህን .. ና !
ሁሌም ከጎኔ እንደክንፍ ኹነኝ
ከሚንበለበል ከኩራዝህ ፍም ፥ እንደ እሳትራት ለሞት አቅርበኝ ።
~
በልቤ ፍሰስ በልቤ ሙላ
ሌት ቀን ስባዝን የሚያጫዉተኝ ፥ ካንተ በስተቀር ምናለ ሌላ !!
የመናፈቅ ጥም ጉም ካለበሰዉ
ቀረበኝ ያልኩት እየነካካ ከሚያስለቅሰዉ
ከስጋየ ስር ፥ ከዚህ ቀርቀሃ
ከነፍሴ በታች ካለዉ በረኻ
ማነህ ተጫዋች ፥ ባለ ሙዚቃ
ይኸን ሙት በድን የምታስደንስ በጠፍ ጨረቃ

✍ቴዎድሮስ ካሳ

ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!❤

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

🛑 አንድ ሊቅ ተጠየቀ :- ማነው ብልህ . . . ? ቢሉት - ከእያንዳንዱ ሰው ሊማር የሚችል

~ ማነው ጠንካራ ሰው ? ስሜቱን የሚቆጣጠር ,

~ ማነው ሀብታም ቢሉት . . . በቃኝን የሚያውቅ ,

~ ማነው የተከበረ ሰው . . . ሰውን የሚያከብር ,

~ ማነው ቶሎ ነገር የሚገባው ? ቢሉት . . . በትዕግስት ሰውን የሚያደምጥ ሰው ,,

ድንቅ ሊቅ ድንቅ እይታ❤️

ውብ ቀን❤️

✍ በዓሉ ግርማ ' ሀዲስ
@EthioHumanity
@EthioHumanity

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

ማራኪ ገፆች! (ለምሽታችን)
📗📗

ጀመኣው ዛሬ ከመሸ የመጣሁት ስለ አንድ ቆንጆ መፅሀፍ ማራኪ ገፅ ለመግለጥ ነው። "የመሀል ልጅ" ይሰኛል በቤዛዊት ዘሪሁን በቅርብ የወጣ መፅሐፍ ነው።ከመፅሐፉ ማራኪ ገፆች ከመቆንጠራችን በፊት ግን አንድ ማለት የምፈልገው እና ሁሌ ጥያቄ የሚሆንብኝ ነገር አለ። እሱም ምንድነው እንደ ሌሎቹ የሙያ ዘርፎች የሴት ደራሲያት ቁጥር እጅግ በጣም አነስተኛ የሆነበት ምክንያት ምንድነው ? እስቲ ምክንያት ብላቹ የምታስቡትን ነገር ብትነግሩኝ ደስ ይለኛል ። ከቀድሞቹ ማለት ከአንጋፋዎቹ የሴት ደራሲያት የተሳካላቸው 4 ሴቶችን አውቃለሁ ፀሐይ መላኩ ፣ የዝና ወርቁ ፣ ሕይወት ተፈራ ፣ ውዳላት ገዳሙ ....በኔ ትውልድ ደሞ የተሳካላቸው ጥራ ብባል በእኔ የንባብ እውቀት ሜሪ ፈለቀ ብዬ አፌን ሞልቼ እናገራለሁኝ ምናልባት ወደፊት እንደ ቤዛዊት አይነት ደፋር ደራሲያት ከመጡ ቁጥሩን ከፍ ያደርጉታል ብዬ አስባለሁ። መፅሐፉን ገዝታቹ ብታነቡት ትጠቀሙበታላቹ በጣም ደስ የሚሉ ፍልስፍናዎች የያዘ ሸጋ መፅሐፍ ነው። ከመፅሐፉ ማራኪ ገፆች አንዱን እንግለጥ እንግዲህ.........
.
.
.

የኛ ሰው <ጦስህን ይዞት ይሂድ> የሚያውቀው ብርጭቆ ስትሰብር ብቻ ነው አንተ ስትወድቅ ግን <ብዬ ነበር> ይላል እንጂ ማንም እጁን ሰዶ ሊያነሳህ አይጥርም አይዞህ እኔም አልፌበታለሁ ማለት ክብሩን መሳት ይሆንበታል ። ደግመህ እንደማትንሰራራ እርግጠኛ ነው። ምፅ ብሎ በቁምህ ይቀብርሃል። ከትቢያ አራግፈህ ለመነሳት ትንፈራፈራለህ ምፅ ይሉልሀል ምፅ እናቱ ሞታ እኮ ነው ምፅ በጣም አንባቢ ስለነበር እኮ ነው ምፅ ካይሆኑ ሠው ጋር ገጥሞ እኮ ነው እያሉ በምፅ ሲፈራረቁብህ ፈሪ ትሆናለህ። የሚቀጥለውን እርምጃህን መቼም አታምነውም ወደኋላ ስታይ ግዜህ ይነጉዳል። በዚህ ሁሉ መሀል ህይወት እንደ ክፉ አስተማሪ መቅጣቷን አታቆምም። አይምሮህ ከገደብ በላይ ይሆንበታል ትደክማለህ በቃ ሰው ነሃ!!

#የመሀል_ልጅ

ያማረ ምሽት ጀባታ!💚

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

❤️ደግነት በቃላት ሲገለጽ ልበ ሙሉነትን ያመጣል፡፡
ደግነት በኃሳብ ሲሆን የስብዕና ጥልቀት ይፈጥራል፡፡
ደግነት በመስጠት ሲሆን ፍቅር ከውስጡ ያብባል፡፡
ውብ ምሽት❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

☯There's a reason you can learn from everything: you have basic wisdom, basic intelligence, and basic goodness.“Would you like to save your country from destruction ? Then step away from Mass movements and quietly go to work on your own self-awareness.

☯If you want to Awaken all of humanity, then Awaken all of yourself. If you want to eliminate the suffering in your country, then eliminate all that is dark and negative in yourself. Truly, the greatest gift you have to give is your own self-transformation.”

🔆we can simply explore Humanity and all of creation in the form of ourselves. Everything that human beings feel, we also feel. We can become extremely wise and sensitive to all of Humanity and the whole universe simply by knowing ourselves,Just as we are.

የሰው ልጅ እኩልነትን እንደማስረጃ ከሚያሳዩት አንዱ"ሰው"መሆን ነው።

🔆ሰው መሆን ማለት ደግሞ፤ ራቁታችንን ከተወለድን በኋላ፤ ከልብስ ጀምሮ አካላችንን ከሚሸፍኑት የማንነት ሽፋኖች መላቀቅ ነው። ሰው ራቁቱን በመወለድ ይዞት የመጣውን መሰረታዊ ማንነት፦ ማለትም መወለድ፣ መኖርና መሞትን ይዘነጋል።

☯ገላው በእናቱ ሆድ የለመደው ሙቀት ሲቀርበት እንዳይበርደውና እንዳይቆረፍድ ልብስ መደረብን፣ ቆይቶ መለያ ስምን፣ ሃይማኖት፣ ዘር፣ ብሄር፣ በተሰብ፣ ሙያ፣ ትምህርትና ስፍርን የመሰሉ ግዑዝና ምናባዊ አልባሳትን በመደረብ" ሰው- ነቱን" ያጣል።

🔆በቀረ ዘመኑ ሁሉ ይዞት የተወለደውን ማንነት ፍለጋ አውቆም ሆነ ሳያውቅ ሲዳክር ይኖራል። ሰው መሆን ከዚህ ሁሉ ድርብርብ ሽፋን የበለጠ መሆኑን ሳያውቅ ወይንም ሳይረዳ ህይወቱን ይገፋል። ሰው መሆንን ለማወቅ የሚሄድበት ትግል፣ ሁሉም ከብርድ ለመሽሽ ከሌላና ጥላ፣ እንዲሁም ሽፋን እንደመፈለግ ነው።

☯ለዚህ ማሳያው የአብዛኛው ሰው ቋሚ ፍላጎት ህይወትን"መለወጥ" ነው። ሁሉም ሰው "ራሴን ለውጬ" ፣ "በተሰቤን ለውጬ" ፣ "መለወጥ አለብኝ ...።" ፤ " ቤተሰቤን ልለውጥ" ፣ "ሀገሬን ልለውጥ" ፣ " ሀይማኖቴን ልለውጥ "እያለ ይኖራል።

✨ከዚህ ሁሉ ለውጥ ውስጥ እያንዳንዱ አድስ ለውጥ አሮጌ ህይወት እየሆነ እንደ ልብስ ከመደረብ ውጭ እውነተኛ ለውጥ ሳይሆን ይቀራል ። እውነተኛ ለውጥ የማይኖረው ሰው ስላልጣራና ስላልሞከረ ሳይሆን ለውጥ ሂደት እንጂ መድረሻ ባለመሆኑ ነው ።

🔆በአንድ ለውጥ መርጋት በሰው ተፈጥሮ ውስጥ ከማይቻሉት ሀቆች አንዱ ነው። በመሆኑም ሰው ቢለውጥ፣ ቢለውጥ ከደረባቸው የማንነት አልባሳት አንዱን ወይንም ሌላውን እንጂ ሰው -- ነቱን" ሊሆን አይችልም።

☯ከዚህ የማንነት ግራ መጋባት ነፃ የሚወጣው በሞቱ ነው።
ሞት ትልቁ ነፃ አውጪ ነው። እንዳልነበረ ይረሳል። ስሙና ማንነቱን ሌላ ይወርሰዋል ።

✍አለመኖር ገፅ፡ 111- 112
በዳዊት ወንድምአገኝ /ዶክተር /
☮🔆☯🔆☮🔆☯🔆☮🔆☯🔆
@EthioHumanity
@EthioHumanity

✍ @EthioHumanityBot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

እምወድሽዋ!❤️ቅዳሜዋ!❤️ሸጋዬዋ!❤️


ማለዳ ከአልጋዬ ስነሳ አይኔን በአይበሉባዬ እያሸሁና የቆሙ ጸጉሮቼን ወደታች ለመመለስ እየታገልኩ ወደመጸዳጃ ቤት በእንግድግድ እርምጃዎች እገባና በሩን በሚዘጋበት ሀይል መጥኜ አሽቀንጥሬ እስኪዘጋ ሳልጠብቅ በፍጥነት ለተወጠረው ፊኛዬ ምላሽ ልሰጥ እቀመጣለሁ,,,,።

<<ኡፍፍ,,,,, መተንፈስን የፈጠርክ ፈጣሪ አለመተንፈስንም ፈጥረሀልና ትመሰገናለህ,,,,,!!>>

ጥርሴን ልቦርሽ መስታወቱ ፊለፊት ስቆም በህሊናዬ ተከስሼ ፍርዴን እየተጠባበቅኩ እንደቆምኩ አስቤው ቀፈፈኝ ።
የጥርስ ሳሙናውን ሆድ በጣቶቼ ተጭኜ ብሩሼ ላይ ካደረግኩ በኋላ በደመነፍስ አሁንም መስታወቱ ላይ አፈጣለሁ።

ጨብራራ ጸጉሬ ፣ ኩሉ የገፈፈ ቅንድቤን ፣ ወደአንድ በኩል ያጋደለው ሰፊው ቲሸርቴ ፣ የተጨናበሱ አይኖቼን አንገቴን አስግጌ ይበልጥ ቀርቤ በጣቶቼ ጥግ ማዕድን እንደሚፈልግ ሰው በረበርኳቸውና አጸዳኋቸሁ።

<< ለምንድነው ዳኛ መስለህ እፊቴ የተገተርከው,,,,? ለምንስ ከውበቴ እንከኔን ታሳየኛለህ,,,? ብሽቅቅ,,,,! >> ብሩሹ ላይ ያለውን ሳሙና ውሀ አስነካሁና መስታወቱ ላይ ረጫጨሁት ። አሁንም ይዳኘኛል,,,?
የአፌን አረፋ ተፋሁበት ።

<<ቱ! ግድ አይደለም ባንተ ውስጥ እራሴን ማየቴ እሺ ,,,,? በውጫዊው አካሌማ አትዳኘኝም! ከቻልክ ውስጤን እያሳየህ ጉድለቴን ነቅሰህ አውጣ ደካማ,,,,,!!>>

ጥርሴን ተጉመጥምጬና ታጥቤ ስጨርስ "እኝኝ "እንዳልኩ እንደልማዴ ወደመስታወቱ ፊቴን ሰገግ ሳደርግ በሳሙና ጭጋግ ተሸፍኗል። በስራዬ ተገርሜ እንከተከት ጀመር። እራሴው እንከኔን እንዳይነግረኝ ሸፍኜው የጸዳሁ ሲመስለኝ ፈለግኩት "ቂቂቂቂ...." አለ መኪ።

<< ለምንድን ጉድለታችንን ከሚነግሩን ይልቅ የሚክቡን ጋር መሆን ምቾት የሚሰጠን ? ደካሞች ነን,,,።
ብዙ ጠንካራ ጎን እያለን ለመጽናናት ፈንታ በድክመታችን ተሸማቀን ስለምንኖር ብርታታችንን መስካሪ እንጂ ጉድለታችንን ነቃሽ የማይመቸን,,,,,!! >>

(የሚቀጥል ግን የማይቀጥል,,)

✍መርየም

@EthioHumanity
@EthioHumanity

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

❤️የሰው አእምሮ በውሸትና በተጣመመ! መረጃ ላይ እንደሚበላሽ በምንም አይበላሽም። በተለይም ውሸትን ሥራዬ ብለው በራስ ወዳድነት ስሜት የሚረጩ ሰዎች በሌሎች ልብና አእምሮ ውስጥ እሾህና አሜኬላን ይዘራሉ።

💡 ስንት ጥሩ ሰዎች በክፉና በስግብስግብ ውሸተኞች ኑሯቸው ፈርሷል። ትዳራቸው ተበትኗል!

❤️ስንት ሥልጣኔዎችንና አገሮችን ከጥቅም ውጭ አድርገዋል። አያለ ጨቅላዎች በውሸት በተመረዘ ንግግር እንጭጭ አእምሯአቸው ከንቱ ሆኖ ቀርቷል።

💡ዓለምን በአንደኝነት ያጠፋው ክፉ ሰዎች የዘሩት ውሸት ነው። የሰው ውድቀት የጀመረውም በውሸት ነው። እውነትን በትዕግሥትና በሰከነ ልቦና እንደ መልካም ዘር ካልፈለግናትና ካልተንከባከብናት ውሸት እንደ አረም ከክፉ ሰዎች የልብ ዕርሻ ላይ እየተዛመተ መልካም ልቦችን ማጥፋትና መውረስ አይቀርም።

❤️እውነትን ታውቃላችሁ እውነትም ነጻ ያወጣችኃል'የሚለው የትልቁ መጽሐፍ ቃል እንደት ያለ እውነት ነው?

💡በዓለም ላይ ከሁሉ አስከፊው እስር ቤት የሰው አእምሮ ባመነጨው ውሸት ሲጠፈርና በዚያ ቀንበር ውስጥ ሲኖር ነው። እውነተኛ ነጻነት የኀሊና ነጻነት ነው። የኀሊና ነጻነት ደግሞ እውነትን በማወቅና በመኖር ነጻ ከወጣ አእምሮ ብቻ የሚገኝ ጸጋ ነው።

❤️የብዙ አእምሮዎች መቆለፍና መዛግ መንሥኤው ባንድም በሌላም መንገድ ወደ ውስጣቸው የገባው ውሸትና ነጻ የሚያወጣቸውን እውነት አለማወቃቸው የፈጠረው ገደል ነው።

💡ከእውነት በፊትም ሆነ በላይ ለአእምሮ ጠንነትና ነጻነት ምን ምን መድኀንት ይገኛል?እውነት ማወቅ ነጻ ቢያወጣም፣ እውነት ዋጋዋ እጅግ ውድ መድኀኒት ናት።

የተቆለፈበት ቁልፍ[ገፅ፡278]
✍ምህረት ደበበ
❤️💡❤️💡❤️💡❤️💡❤️💡
@EthioHumanity
@EthioHumanity

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

ለውብ ቀን!
💚

ነፍስን ፍለጋ!

ይሉኝታ በሚሉት የውሸት አጋም አጥር ተሸብበን ውስጠታችን ከሚሻው እውነተኛ ማንነት ግልባጭ ፅንፍ የቆምን ስንቶቻችን እንሆን? በተበላሸው አቅራቦታችን ምክንያት ልንናገራቸው ፈልገን ያልተናገርናቸው ፣ ልንወቅስ ፈልገን ያልወቀስናቸው ፣ ልናደንቅ ከጅለን ያላደነቅናቸው በታወሱን ጊዜ ነፍሶቻችንን በቁጭት ወረንጦ የሚሸነቁጡ ስንት ኩነቶች አልፈዋል?

በየእለቱ ከምናገኛቸው በአካል ቅርብ ከሆኑ ባልንጀሮቻችን በሆያሆዬ ደምቀን እና ተሰብስበን ሳለን ከልባችን ያን እውነተኛ ሀሴት መጎናፀፍ ተስኖን በነፍስ በስንት ሺህ ማይል ተራርቀን ይሆን?

በህይወት ዑደት ውስጥ ወደኛ ህይወት የገቡ እልፍ ሰዎችን በመጀመሪያ መስተጋብራችን እራሳችንን በተንሸዋረረ መልኩ አሳይተን ከአካላችን ባሻገር እውነታችንን እና ነፍሳችንን የገለጥልናቸው ምን ያክሉን ነው?

በጓደኝነት አለም አልያም በማህበራዊ ህይወት ከልብ የሆነ መቆራኘትን ሳንቆራኝ ፣ ውስጣዊ እኛነታችን ለየቅል ሆኖ ሁላችንም ታመን ሳለ ከመንጋው ላለመፈንገል የወየበ ጥቀርሻ ልብ ይዘን ሀጫ በረዶ ጥርስ እየመፀወትን ስንቶቻችን ይሆን የምንጋፋው?

ንግግራችን ፣ ሰላምታችን ፣ ሳቃችን ፍቅራችን ምን ያክል ነፍሳዊ ነው? ምን ያክል ጥልቅ ነው? እንጃ!!

✍አብድል ማሊክ

@EthioHumanity
@EthioHumanity

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

<< የሚዋደድ ሰው ሁሉ አንድ አይነት ነገር መውደድ የለበትም... >>

📖መነሻ ሃሳብ :- " ማታ ማታ - ገጽ 110

🔺" ማሰብ ተፈጥሮአዊ ባህሪህ ቢሆንም በማሰብ ላይ ያለህ ብስለት ከሚገለጽባቸው መንገዶች አንዱ ደግሞ ካንተ የተለየ ሀሳብ ሲያጋጥምህ ለሃሳቡ በምትሰጠው ምላሽ(ግብራዊ) ነው ። እምትወደው ሰው የግድ ባንተ ሃሳብ የሚስማማ ወይም አንተ የምትወደውን ብቻ የሚወድ መሆን የለበትም ። እንደዛ አይነት ሰው ከፈለግክ ያንተን ሁሉ አሜን ብሎ የሚቀበል የሀሳብና የፍላጎት_ወዛደር እንጂ አሳቢን አታገኝም ።

❤️የሚዋደድ ሰው ሁሉ አንድ አይነት ነገር በመውደድ አይደለም መዋደዱ የሚገለጸው ። ካንተ ለተለየ ነገር ሁሉ ጥላቻ ከሆነ ምላሽህ በትክክል ማሰብ መቻልህ ጥያቄ ውስጥ ይገባል ። በሃሳብ መፋለስ የልዩነት እንጂ የጥላቻም ሆነ ያለመዋደድ መንስኤም ሆነ ምልክት አይደለም ። አንተ ራስህ በየቀንና በየሰአቱ የምታስባቸው ሃሳቦች ልዩነት ሊኖራቸው ይችላል ግን አቻችለሀቸው እየኖርህ ነው ። ታድያ የሰውን ልዩነት ማቻቻልስ እንዴት ያቅትሀል...…?

ለራሳችን ጥያቄ ሰተነው እንደምድም::

የሀሳብ ልዩነቶችን ለምን በስድብ እናጣጣቸዋለን?…………

ሰዎች እኛ ያልደገፍነውን ስለደገፉ ለምን እንዲያፍሩ እናደርጋቸዋለን?...……"

ፍቅር አሁን !
@keney_serezoch
@EthioHumanity

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

ለጁምኣችን!
💚

«ሌባው» የመስጂድ ኢማም


ባልና ሚስት ከረመዷን ወራት ባንዱ በሰፈራቸው የሚገኙትን ታዋቂ የመስጂድ ኢማም ለፊጥራ ጋበዟቸው። ኢማሙም ግብዣውን በክብር ተቀበሉ። የቤቱ እማወራ የምግብ ማዕዱን ለማዘጋጀት ተፍ ተፍ እያለች ሳለ ገንዘቧን ጠረጴዛው ላይ ጥላ ወደ ኩሽና አመራች። ፊጥራው ተጠናቀቀ። ኢማሙም ሄዱ። ሚስት ገንዘቧ እንደጠፋ አስተዋለች። «ገንዘቡን የሰረቀው ማን ነው?» ተብሎ አይጠየቅ ነገር ባልና ሚስት ልጆች የሏቸውም። በወቅቱ ወደቤት የመጡት የመስጂዱ ኢማም ብቻ ናቸው። ውስጧ በጥርጣሬ ተናጠ። ታሪኩን ለባለቤቷ አጫወተችው። የመስጂዱን ኢማም እንዲያማክራቸውና ጉዳዩን እንዲያረጋግጥ ጠየቀችው። «ኧረ ነውር ነው ፤ ባይሆን ከኢማሙ ጋር የፈጠርነውን ስር የሰደደ ግንኙነት አቋርጠን ፋይሉን እንዘጋለን እንጂ እንዲህ አይነት ጥያቄ ማንሳት የማይታሰብ ነው» በማለት መለሰላት።

ቀናት በንፋስ ፍጥነት ከነፉ። ቀጣዩ ረመዷን ገባ። ባል ከሚስቱ ጋር ተቀመጠ። «እንግዲህ የእዝነት እና የይቅርታ ወር ስለገባ ያለፈውን መርሳት አለብን። እንደምታውቂው ኢማሙም ቤተሰብ የላቸውም። የኛው ስለሆኑ ዘንድሮም ቢሆን ፊጥራ ልንጋብዛቸው ይገባል» በማለት ሚስቱን አማከራት። ሚስት ለአፍታ ዝም ካለች በኋላ «በሃሳብህ እስማማለሁ፤ ነገር ግን የማስቀምጠው ቅድመ ሁኔታ ይኖራል። እርሱም የባለፈው ዓመት ረመዷን ላይ ስለተሰረቀው የገንዘብ ጉዳይ በግልጽ እንድታወሩ እፈልጋለሁ» አለችው። ባቀረበችው ሃሳብ ተስማማ።

የመስጂዱ ኢማም ግብዣውን ተቀብለው ከቤት መጡ። ፊጥራውን ከጨረሱ በኋላ የቤቱ አባወራ ጉዳዩን በይፋ አነሳው። ስለ ገንዘቡ ሁኔታ በቀጥታ ጠየቃቸው። ከፍተኛ የሀፍረት ስሜት ተሰማቸው። እንባቸው በጉንጮቻቸው ላይ ተንኳለለ። ካቀረቀሩበት ቀና አሉ። አይኖቻቸው የእንባ ቋጠሯቸውን እንደፈቱ ነው። ሚስት ፈጠን ብላ «ኢማም ሆይ! ምን ሆነው ነው የሚያለቅሱት ?» በማለት ጠየቀቻቸው። «አዎ! ገንዘቡን ያነሳሁት እኔ ነኝ። ያስቀመጥኩትም የመጽሃፍት መደርደሪያው ላይ ከተቀመጠው ብቸኛ ቁርኣን ውስጥ ነው። እንባዬ የፈሰሰውም ረመዷንን ጨምሮ ለ 365 ቀናት ያህል የአላህን መጽሃፍ ገልጣችሁ አንድ ፊደል እንኳ ባለመቅራታችሁ ውስጤን ተሰምቶት ነው» በማለት ምላሽ ሰጡ። በዚህ ጊዜ የቤቱ አባወራ በፍጥነት መደርደሪያው ላይ ወደተቀመጠው ቁርኣን አመራ። ገንዘቡንም የቁርኣኑ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ምዕራፍ መሃል ላይ ተቀመጦ አገኘው። ሚስት እንባዋ ግድቡን ጥሶ ፈሰሰ። ኢማሙን በክፉ በመጠርጠሯም ይቅርታ ጠየቀቻቸው። «ልጄ ሆይ! እኔ ደካማ የአላህ ባሪያ ነኝ፤ ይልቅ አመቱን ሙሉ ቁርኣኑን ችላ በማለትሽ ይቅርታና ምህረት ከአላህ ጠይቂ» በማለት መከሯት።

👉 እኛስ መቼ ይሆን ለመጨረሻ ጊዜ የአላህን (የፈጣሪን) ቃል ከፍተን ያነበብነው ? ነፍሳችንን ሳንዋሽ እውነቱን ለራሳችን እንገረው‼‼‼
ወገኖቼ የአላህ (የፈጣሪ) ቃል እየጠራን ቢሆንም ችላ ብለነዋል።

ሸጋ ጁምኣ!💚

📝መሀመድ አህመድ

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

ለውብ ቀን!
🖤

አብሮ መጨፈርን ሰጥቶ፣ አብሮ ማልቀስን ማን ነጠቀን?



ሁሉም ከሳሽ ፤ሁሉም ምሁር ፤ሁሉም ጨዋ፤ ሁሉም ወቃሽ ፤ሁሉም ሊቅ፤ ሁሉም አዛኝ፤ ሁሉም አቅጣጫ ጠቋሚ ፤ ሁሉም አውሪ ፤ሁሉም ብያለው ባይ ፤ ሁሉም ጆሮ አልባ ነው።

ተመሳሳይ ሃሳብ፤ ተመሳሳይ ምልከታ፤ ተመሳሳይ ህልም ፤ተመሳሳይ ዜና ፤ተመሳሳይ ክስ ፤ተመሳሳይ ውዳሴ ፤ተመሳሳይ አቋም ፤ተመሳሳይ ድጋፍ ፤ተመሳሳይ ሙግት ።

የቡድን ጀግና፤የቡድን ተቆርቋሪ ፤የቡድን ተከራካሪ ፤የቡድን ተከላካይ ፤ቡድናም እይታ ፤የቡድን ጭብጨባ ፤ የቡድን ሳቅ ፤የቡድን ሙሾ ፤ የቡድን ሙግት ፤የቡድን መልስ ። የቡድን ጩኸት

ሃላፊነት የሚወስድ አንድም የለም ። ዝቅጠት ላይ አስተዋፅዖ እንደ አበረከተ የሚያወራ ።አንድም የለም። ሁሉም ጣት ቀሳሪ ፤ ሁሉም ዳር -ነኝ ባይ ነው ።



ሃይማኖታችን ጥንጥ ሞራል ፤ጥንጥ ርህራዬ ትንሽ መተዛዘን ካልፈጠረልን ምን ይሰራልናል ???

የሃይማኖት ስፍራዎች ለምን ግንባቸው ተሸንሽኖ ቤት አልባ ሰዎች አይኖሩበትም??

መስበኪያ ስፍራዎች ለምን ወደ መበየጃ ወደ መሸመኛ ፤ወደ መጥለፍያ ቦታዎች አይቀየሩም ።

እምነት አልባ ህዝብ ውስጥ ይሄ ሁላ ማምለክያ ግንብ ምን ይረባል !!

በዚህ ደረጃ እርስ በእርስ ተጠያይፈን እርስ በርስ ተጨካክነን እርስ በእርስ እየተሳደድን ምን ያስተሳስረናል ???

እርስ በእርስ በሚበላላ ህዝብ ውስጥ ያለች አገርን እንደምን ማፍቀር ይቻላል? ?? ምኗ ይናፍቃል ??

ከዚህ በኋላ የትኛው አገዳደል ፤የትኛው አበዳደል ፤የትኛው ግፍ ያስበረግገን ይሆን ??
የቱም !

ይታክታል!!! እውነት ይታክታል!!!!!

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

☯“The most beautiful people we have known are those who have known defeat, known suffering, known struggle, known loss, and have found their way out of the depths.

💜These persons have an appreciation, a sensitivity, and an understanding of life that fills them with compassion, gentleness, and a deep loving concern. Beautiful people do not just happen.”

✍Elisabeth Kübler-Ross

@EthioHumanity
@EthioHumanity

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

ቃላት ስሜትን መሸከምም ሆነ መግለጥ አቅቷቸዋል!!!💚💛❤

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹


🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹


እንኳን ደስ አለን!!!!💚💛❤💚💛❤💚💛❤

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

🕯🕯📜🕯🕯🕯📃🕯🕯🕯📜

ከመሰበር እንቃና፣ከማጎንበስ እንበል ቀና
ሃገር በእኛ እንድትቀና....ሃገር የምትቀናው እውቀት ላይ በተመሰረተ፣ በመከባበር መንፈስ ውስጥ ባደረ፣ ለለውጥ እራሱን ባሰናዳ ባለቅኔ ትውልድ ብቻ ነውና ባለቅኔ የሆናችሁ የነገይቱ ተስፋ ልጆች ተቀላቀሉን! ሃሳባችሁን፣ እምነታችሁን እና እውቀታችሁ እያጋራችሁ በመጋራት መንፈስ ለታላቅነት በእውቀት ክነፉ. .
🕯📃🕯🕯……………🔰🔰


ተቀላቀሉን

👇👇👇👇👇👇👇

@keneyalew
@keneyalew
@keneyalew
@keneyalew

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

❤️የልብህን ቁስል ትተው የደረትህን ንቅሳት ያደንቃሉ፤ ጫማ ስለሌለህ እግርህ አይታይም ፤ የጭንቅላትህን ዋጋ በኮፍያክ ይተምኑሀል ፤ መከራ ተሸክሞ ሲኖር ያላዩት ትከሻ ኮት ሲለብስ ያጨበጭቡለታል፤ ታሪክህን ጨርቅህ ላይ ስምህን ልብስህ ላይ ለማንበብ ይሽቀዳደማሉ።

🌗እኔ ትንሽነቴን አልረሳም ማወቄም አያመፃድቀኝም ።ጀግና ማለት ታግሎ የጣለ ሣይሆን ታግሎ ያለፈ ነው። ሁሌም ቢሆን እራስህን ተመልከት። የምትወድቀው ሌላውን ለመጣል የሞከርክ ቀን ነው።
ልትጥለው የሞከርከው ሰው ግን ገልብጦህ ከላይ ሆኖ ታገኘዋለህ።

❤️ሁሉንም በገንዘብ እገዛዋለው ብለህ አታስብ በገንዘብ የምትገዛው ርካሹን ነገር እንጂ ውድ ነገሮች የዋጋ ተመን የላቸውም።🙏
ውብ ምሽት
🌗❤️🌗❤️🌗❤️🌗❤️🌗❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

ሰዓት እላፊ! (የቅዳሚት መዳረሻ!)


".....እኔና አንቺ ተለያይተን እዚህና እዚያ ስንቆም ቃሎቻችን ወደ የት ይሄዳሉ? ያልኩሽ÷ ያልሺኝ÷ የተባባልናቸው ነገሮች መጨረሻቸው ምንድነው?
Does they even exist anymore?°°°°?

📝እሱባለው አበራ ንጉሤ

@EthioHumanity
@EthioHumanity

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

ለጁምኣችን!
💚
ብርሌ በመሰለ ዓለም ፡ መውጪያው ጠባብ በሆነ ፡ በግንባር መደፋት ማለት ማምለጥ ነው ፡ መቃናት ማለት መቅረት ነው ።

📝fksh Ayelgn

በዙፋን ላይ ካለ ንጉስ በሱጁድ ላይ ያለ ሙእሚን ይበልጣል!!

አላህም እንዲህ ብሎ እውነትን ተናገረ
(و اسجد و اقترب) 19 – العلق
«ስገድ፤ወደ አላህ ተቃረብም።»
.
.
አንድ ሰው ከአላህ ይበልጥ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ እያለ እንደሆነ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ተናግረዋል።

ኢብነል አልጀውዚ ውብ የሆነ ንግግር አላቸው....

የአላህን ስፍር ቁጥር የለሽ ውለታ ብትገነዘብ ኖሮ ነፍስህን የሃያጥት ባሪያ ባላደረካት ነበር። አላህ "ኢብሊስን" ከእዘነቱ ያባረረው ላንተ የክብር ሱጁድ ለማድረግ አሻፈረኝ በማለቱ መሆኑን እንዴት ዘነጋኸው? ... አግራሞትን የሚያጭረው ጉዳይ የጠላትህ ኢብሊስ ወዳጅ በመሆን ወዳጅህ የሆነው አላህን መክዳትህ ነው።

ከመንገዱ በፊት!!!!!

ረጅም ነው ዙሩ፤ የዱንያ ጎዳና፤
በመሮጥ በመክነፍ፤ መች ይደረስና፤
እባክህ ጀሊሉ፤ ሶብር ይዘህ ናማ።
የመንገዱ ነገር፤ አቀበት ጉብታው፤
ቁልቁለት ሸለቆ፤ ሜዳና ኮረብታው፤
አላስኬድም ካለ፤
ገደላ ገደሉ፤ጭቃና ዝቅታው፤
ከመንገዱ በፊት፤
በርከክ ሲሉ ነው፤ ቁጥሩ የሚፈታው።

እናማ፤
ከመንገዱ በፊት፤
መንገዱን ጀምረው፤ ስጁድ ያለፋቸው፤
ይኸ ሁላ መንገድ፤
በሩጫ ሚደፈር እየመሰላቸው፤
ተቆጥረው አያልቁም፤
መንገድ እየሄዱ፤መንገድ የበላቸው።
እመዋ እመዋ!!!!

((( ጃ ኖ )))💚💛❤

ሸጋ ጁምኣ!💚

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

ሸጋ ብስራት!
📗📒📕

ጀመኣው እንዴት አመሻቹ.... ማንበብ ለሚወዱ ብቻ ሳይሆን የድሮ መፅሐፍት መሸመት የምትወዱ ሰዎች በየአመቱ ሰፍ ብለን የምንጠብቀውን የጠፉ መፅሃፍት አውደርእይ ተዘጋጅቷል።
እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊትለፊት የሚገርም የከተማ ማእከል አለ::
እዚያ ከመጋቢት 24-26 ከች በሉና ያሻችሁን ሸምቱ!!!

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@balmbaras

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

ለውብ ቀን!
💚

፩ (አንድ)

ግለ-ሰብ የትግል አርማ ሊሆን አይገባም። የትግል አርማ መሆን ያለበት የትግሉ ውጤት ነው። ግለሰብ ግለሰብ ነው። ይውሸለሸላል፤ይማልላል፤ይሻፍዳል፤
ይታበያል፤ይሰርቃል ፤ይደክማል ፤ይሳሳታል፤ ይደለላል። ግለሰብ ላይ የተንጠለጠለ ድል ግለ-ሰብ ላይ ያልተንጠለጠለ ስርአት ካልተዘረጋ ድሉ ድል አይደለም ።

፪ (ሁለት)

በየትኛውም የግፍ ዘመን ውስጥ ዳር ሆኖ ያየ ትልቅ ነኝ ባይ፤ የተሳተፈ ፤ዝምታን የመረጠ አባት፤ ያልመከረ ምሁር ፤ በደልን ያስተባበለ አንዱም ሳይቀር በየደረጃው ሃጥያተኛ ነው።

፫ (ሷስት )
.....
ብልህ በተበጀለት ሽል ውስጥ ሆኖ አይወራጭም። የራሱን መወራጫ ነገን ያማከለ ርእይ በውብ ሃሳብ በልኩ ያጎለብታል እንጂ ።

፬ (አራት)

ከተወለድንበት ሰፈር፤ ከምንከተለው ሃይማኖት ፤ አሽቆልጠን ከምናገኘው ፍርፋሪ፤ ግዜ ከሚያፈዘው ስልጣንም ሆነ ሳንቲም ሁሉ ሰውነት ይገዝፋል።

፭ (አምስት)

ሁሌም ጥግ ለጥግ ሆነው ከሚካረሩት አክራሪዎች ይልቅ መሃል ላይ ያሉ እንዳይበጠስ የሚዳክሩት ቅዱስም ምስጉንም ናቸው🙏🙏

ውብ ቀን!💚

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@balmbaras

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

💎ፊት ለፊት ትይዩ የተገነቡ ሁለት ቤቶች አሉ ። በሁለቱ ቤቶች ጣሪያዎች ላይ ደግሞ የእግር መርገጫ ስፋት ብቻ ያለው የጣውላ መረማመጃ ድልድይ ቢጋደምና በላዩ ላይ ተራምዳችሁ ከአንዱ ጣርያ ወደሌላው እንድትሻገሩ ብትጠየቁ ፈቃደኛ ላትሆኑ ትችላላችሁ ። ይኸው ጣውላ መሬት ላይ ተጋድሞላችሁ እንድትራመዱበት ብትጠየቁ ግን ህፃን ፣ ወጣት ፣ አዛውንት ሳይባል ፣ ሁላችሁም ሳትወድቁ ትራመዱበታላችሁ ።

📜 የጣውላ መረማመጃው ያው ነው ፤ እናንተም ያው እናንተው ናችሁ ፤ ታድያ ጣውላው በቤቶቹ ጣሪያዎች ላይ በተጋደመ ጊዜ እንድትራመዱበት ስትጠየቁ ለምን እምቢ አላችሁ? መሬት ላይ በተደጋጋሚ ጊዜ ብዙ ሰዎች ሳይወድቁ ተረማምደውበታል ። ታድያ ችግሩ ምንድን ነው? ችግሩ ያለው ሌላ ቦታ ነው ።

🔑 መሬት ላይ ተጋድሞ ሳለ ጣውላው ላይ ለመረማመድ ንቁ መሆን አያስፈልግም ።ንቃት አልባ ሆናችሁ ልትራመዱ ትችላላችሁ ። በጣውላው ላይ ተረማምዳችሁ ከጣሪያ ጣርያ ለመሻገር ግን ንቁ መሆን ይኖርባችኋል ። ንቃት እንደሌለን እናውቃለን ፤ በዚህም ምክንያት ወድቀን እንዳንሞት እንፈራለን ። መሬት ላይ ስንራመድ ግን ብንወድቅ እንኳን እንደማንሞት እናውቃለን ።

💎 አልፎ አልፎ አደጋ በሚያጋጥመን ቅፅበት ንቃት ይኖራል ። ሌላ ግዜ ግን እንቅልፍ ላይ ነን ። ሞት ሲቀርበን ንቃት ይኖራል ፤ አለዚያ ግን ንቁ አይደለንም ። ልማዶቻችንን መቀየር የማንፈልገው ለዚህ ነው ፤ ምክንያቱም ልማዶች ሲለወጡ ንቁ መሆን ያስፈልጋል ። አሮጌ ልማዶች የእናንተን ንቃት አይፈልጉም ።

📖 የንቃት ፀሃይ /ኦሾ/
ገጽ 99-100
ትርጉም ✍ መርሻ በነበሩ
💎🔑💎🔑💎🔑💎🔑💎🔑💎🔑
@EthioHumanity
@EthioHumanity

✍ @EthioHumanitybot

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

❤️" ፍቅር የሚጀመረውም ሆነ የሚፈፀመው በራሱ ነው። እናንተ ልትጨነቁበት አይገባም። ከእናንተ በላይ ነው። ከእናንተ እጅግ የገዘፈ ነው።
እናንተ ግን ፍቅርን ልትቆጣጠሩት ወደ ምትችሉት ግንኙነት ቀየራችሁት። ለዚህም ነው እናንተ ወደ ፍቅር ሀይል ያልገባችሁትና ስለሱም ምንም የማታቁት። የእናንተ ራስወዳድነት ሊቆጣጠረው አይችልም። ራሳችሁን በቁጥጥር ስር አውላችሁአል።

💙ማንም ፍቅርን ሊጀምር አይችልም። ልክ እንደ ማብርያና ማጥፍያ የምታበሩትና የምታጠፉት አይደለም። ራሳችሁን ብቻ በአሁኑ ጊዜ ብቻ አስቀምጡት። ሲሆን ይሆናል። ከምንም ተነስቶ ነው የሚፈጠረው። ልክ እንደ መሬት መንቀጥቀጥ ይወዘውዛችሁአል ከስራችሁ ይነቅላቹሃል ከእግራችሁ በታች ያለው መሬት ይጠፋል። ለዚህ ነው ፍቅር "በፍቅር መውደቅ" ተብሎ ሚጠራው። ራሳችሁን መሆን ታቆማላችሁ። መቆጣጠሩ ስነምግባሩ በፍቅር ውስጥ ቦታ የለውም። መጀመር ሳትችሉ እንዴት ልታቆሙት ትችላላቹ?
የፍቅር መንገዶች ከናንተ በላይ ናቸው። ትክክለኛውን ጊዜ ለማወቅ አይቻላችሁም።

❤️በፈለጋችሁ ጊዜ ጀምራችሁ ምትጨርሱት ፍቅር እርሱ ፍቅር አይሆንም ። ሰው ሰራሽ ነው የሚሆነው።በሚስቱ ቁጥጥር ስር ያለ ባል አስቀያሚ ፍቅር የማያውቅ ፍቅር የማይገባው ይመስላል። ስለዚህ ሚስቱ እራሷ ከልብ ልታፈቅረው አትችልም። ለናንተ ባርያ የሆነች ሴት እንዴት ልታፈቅሩ ትችላላችሁ?

💙ፍቅር በጓደኞች መካከል እንጂ በባርያና በጌታ መካከል አይሆንም። ባርያን ልታዙ እንጂ ልታፈቅሩ አትችሉም። ፍቅር ሊያፈቅር የሚችለው እኩዮችን ነው።"
✍ኦሾ
@EthioHumanity
@EthioHumanity

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

🌗የሌሊት ወፍ

🌙“የሌሊት ወፍ በቀን የመኖር ስልጣን የላትም” ይላል ምንጩ ያልታወቀ የጥንት አፈ-ታሪክ፡፡ “ለዚህ ነው ሌሊቱን እየጠበቀች ከመሸ ተደብቃ ወጥታ ሳይነጋ ተደብቃ የምትገባው”፡፡

🌗በጥንት ጊዜ በሰማይ አእዋፍና በምድር አራዊት መካከል ውጊያ ነበር ይባላል፡፡ የአሁኗ የሌሊት ወፍ ያን ጊዜ እንደማንኛውም የወፍ ዝርያ ነበረች፡፡ ይህቺ ወፍ (የአሁኗ የሌሊት ወፍ) በውጊያው ጊዜ የምድር አራዊት ሲያሸነፍ ለእነሱ ታግዝ ነበር፤ የሰማዩ ሲያሸነፍ ደግሞ ተገልብጣ ለእነሱ ታግዝ ነበር፡፡

🌗አንድ ጊዜ ግን እነዚህ ሁለት ጸበኞች ታረቁና የጦርነቱ ሁኔታና ትውስታ ሲነሳ ምን ስታደርግ እንደነበረ ታወቀባት፡፡ ከዚያ ቀን ጀምሮ በሁሉም የተጠላችና የተገፋች ወደመሆን ስለመጣች በቀን የመኖር ስልጣኗን አጣችና ሌሊት መኖር ጀመረች ይባላል፡፡

🌙አስመሳይነት፣ ሁለት መልክ ያለው ሕይወት፣ አቋም የለሽነት፣ ውሸተኛነት፣ አታላይነት፣ መስሎ አዳሪነት፣ ባለ ሁለት ምላስነት፣ ሸንጋይነት፣ ለሆድ አዳሪነት . . . የዘመኑ ችግር!

🌑የብዙዎችን በነጻነትና ቀና ብሎ በድፍረት የመኖር አቅም ያሳጣ የዘመኑ ወረርሽኝ!
አስመሳይ ሆነህ ወዳጅህ ከሚበዛ፣ እውነተኛ ሆነህ ጠላትህ ቢበዛ ይሻላል፡፡ ሁለት መልክ ይዘህ ትርፋማ ከምትሆን፣ አንድ መልክ ይዘህ ባለህ ነገር መኖር ይሻልሃል፡፡

✍ከዶ/ር እዮብ ማሞ

በሰላም እደሩ❤️
🌙🌗🌙🌗🌙🌗🌙🌗🌙🌗
@EthioHumanity
@EthioHumanity

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

🔱በሌሎች ስኬት አትቅና!

💫“ቅንአት (jealousy) ሲብራራ፣ አንተ ያለህን ነገር ወስጄ የእኔ ማድረግ እፈልጋለሁ የማለት ስሜት ሲሆን፣ ይህ ቅንአት መራራነት (resentment) ሲጨመርበት፣ አንተ ያለህን ነገር የእኔ ማድረግ እፈልጋለሁ፣ አንተ ደግሞ ምንም ነገር እንዲኖርህ አልፈልግም ወደሚለው ከረር ያለ ስሜት ይሻገራል . . . ወደመራራነት የተሸጋገረ ቅንአት ፍትህ እንደጎደለ ከማሰብ ሊመጣ እንደሚችልና ከዚያም ባሻገር በውስጣችን ከተደበቀ በራስ ያለመተማመንና የዝቅተኝት ስሜት ሊነሳ ይችላል፡፡

🔱በሕይወትህ ከሌሎች የምትሻልበት ነገር እንዳለህ ሁሉ ሌሎች ሰዎች ከአንተ የሚሻሉበት ነገር እንዳለም አምነህ ተቀበል፡፡ ይህንን አመለካከት ከመብለጥና ከመበለጥ ስሜት አንጻር ሳይሆን አንተ እንዲሳካልህ የመፈለግህን ያህል ሌሎችም እንዲሳካላቸው ከመፈለግ አንጻር ልትይዘው ይገባሃል፡፡ በሌሎች ሰዎች ስኬት የሚቀኑ ሰዎች ልቀው በተገኙበት መስክ ሳይቀር የተበለጡ ሰዎች ናቸው፡፡ ምክንያቱም ትኩረታቸውን ከግባቸው ላይ አንስተው ሌላውን ሰው ለመጣልና በልጦ ለመገኘት ስለሚጣጣሩ ነው፡፡

💫አንዳንድ ሰዎች በአንድ አቅጣጫ ልቀው የሚገኙት ምናልባት ለዚያ ነገር ከአንተ የተለየ ትኩረት ስለሰጡት ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱ ያም ሆነ ይህ አንተም ደግሞ ከእነዚ ሰዎች የተሻልክባቸው ሁኔታዎች እንዳሉ በማሰብ ወደፊት ካልቀጠልቅ ከቅንአት ህመም አታመልጥም፡፡

🔱ሰውን ለማሸነፍ ከመሯሯጥ ወጥተህ ራስህን በማሸነፍ ወደ ትክክለኛ ስኬት ለመድረስ ከፈለግህ በመጀመሪያ ከዓላማህና ከራእይህ ጋር የሚመጥን ግብ ማውጣት አለብህ፡፡ የዚህ ግብህ ከፍታ በፍጹም ከሌላው ሰው ሁኔታ ጋር መነካካት የለበትም፡፡ የሌላው ሰው ስኬት የራስህን ግብ ለመከታተል ሊያነሳሳህ ይገባል እንጂ ወደ ፉክክር ሊጨምርህ አይገባም፡፡

(“ራስን ማሸነፍ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ መጽሐፍ የተወሰደ)

መልካም ምሽት
🔱💫🔱💫🔱💫🔱💫🔱💫
@EthioHumanity
@EthioHumanity

Читать полностью…

ስብዕናችን #Humanity

#ዛሬ ሽቅርቅሯ ቅዳሚት ነች..❤ አንድ የቻናላችን ቤተሰብ የሆነች እንዲህ አለችኝ.... በእርግጠኝነት እንደኔ ይሄ ነገር የሚሰማቸው ፣ ግራ የሚያጋባቸው ፣ የተጎዱበት ......ህመሜ ህመማቸው ይኖራሉ እና ይሄን እዚህ ቻናል ላይ ለጥፍልኝ አለችኝ.....#ከዚህ በታች ያለውን ስሜቷን ህመሟን ግራ መጋባቷን እንዲህ አስቀምጣዋለች......#ምናልባት ይሄን የምታነቡ ቤተሰቦች እናተም በዚህ ነገር ውስጥ ናቹ ወይንም አልፋችሁት ይሆናል........ተጋበዙልኝ🙏🙏

👇👇👇



በቃ አንዳንዶች አሉ
.
.
ፍላጎታቸው በትክክል ምን እንደሆነ የማይገቡህ::
የትውውቃችሁ መጀመሪያ አከባቢ ጥሩ ይሆኑልህና ከትንሽ ግዜ በኋላ
የሚቀየሩብህ::አንተን የፍቅር ስሜት ውስጥ ከከተቱህ በኋላ ከነሱ ተመሳሳይ ስሜት
ስትፈልግ የማይመልሱልህ::
.
.
...በቃ አንዳንዶች አሉ!
.
.
ካንተ ጋ መሆን እየፈለጉ ነገር ግን በህይወቴ ሌላ ሰው ቢመጣስ ብለው ወይም ደግሞ
ባለፈ የፍቅር ህይወታቸው ፍራቻ ፍቅርህን የማይቀበሉ::የማይሸሹህ!..የማይቀረቡ!..ሄዱ
ስትላቸው የሚመጡ!..መጡ ስትላቸው የሚሄዱ::
.
.
በቃ አንዳንዶች አሉ!
.
.
ሌላ ሰው እስከሚተዋወቁ አንተን እንደ ባጣ ቆየኝ የመጠቀሙ!
.
.
በቃ አንዳንዶች አሉ!
.
.
ሁሌ አንተ ቀድመህ መልዕክት እንድትልክላቸው ወይም ደግሞ እንድትደውልላቸው
የሚፈልጉ!አንተም አያስችልህም መልዕክት ትልካለህ!..ትደውላለህ!...እንደ ነገሩ
ያዋሩሀል!..ግን ደግሞ ብልጦች ናቸው!...ጨርሰህ እንድትለያቸው ስለማይፈልጉ ተስፋህን
ሙሉ ለሙሉ አይነጥቁህም!..ጭላንጭል ያስቀሩልሀል!..አንተም የቀረህን ጭላንጭል
ተስፋ ይዘህ አብረሀቸው መንገድ ትቀጥላለህ!
.
.
የሆነ ሰዓት ይሰለችሀል!ልትደውልላቸው ስልክህን ታነሳና መልሰህ
ታሰቀምጠዋህ!..ከራስህ ጋ ብዙ ትታገላለህ!..በመርሳትና በፍቅር ስሜት መሀል ሆነ
ለረጅም ግዜ ዝምምም ትላቸዋለህ::
.
.
የዚህን ግዜ የነሱ ተራ ይጀምራል!..እያንዳንዷ የተሰማህ ስሜት የሰማቸዋል!..እያንዳንዷ
ያመምህ ህመም ያማቸዋል!...ይቁነጠነጣሉ!..አስር ግዜ መልዕክት
ይልኩልሀል!...ይደውሉልሀል!...ቀን ሙሉ ያስቡሀል!
.
.
በቃ አንዳንዶች አሉ!...
.
.
ፍቅር ስትሰጣቸው ጀርባ ሰጥተውህ ስትርቃቸው የሚከተሉህ!
.
.
ስታዋራቸው ዝም ብለው ዝም ስትላቸው የሚያዋሩህ!.!
.
.
ግራ የተጋቡ!የተወሳሰቡ..በትክክል ፍላጎታቸው ምን እንደሆነ የማትረዳቸው!....
.

✍ፀዲ

ሀሳብ ካላቹ ....ማካፋል ትችላላችሁ 🙏

ሽብርቅርቅ ያለች ቅዳሜ!❤

@EthioHumanity
@EthioHumanity
@Nagayta

Читать полностью…
Подписаться на канал