105
Selam friendoch Tekelaklew be mudachn yznanu 😀😂 Pic👭 competition🎎🚵 New🎼 music🎵💿 Videos🎦🎥🎬 gixemoch 📋📃 So on Contact me via @burati123 ተ 🀄 ላ 🀄 ሉ
እናቴ✣ ትሙት አንላቀቅም
▰▰▰▰▰▰▰▰▰
🌹🌹🌹፩🌹🌹🌹💯
▰▰▰▰▰▰▰▰▰
“ሰማህ የኔ ውድ . . .
ሳፈቅርህ ከልቤ ባንተ ተረትቼ
ስላንተው ስባክን አቅሌን ነፍሴን ስቼ
በክንድህ እያሟሟህ ባፍህ እያቀለጥከኝ
ከማያውቁት ዓለም ወስደህ እየከተትከኝ
ነፍሴን አስክረሃት በሀሴት ዳንኪራ
እንዳልቆም እንዳልሄድ ያላንተ እንዳልሰራ
አድርገህ ጠፍረህ እንዲህ አሳስረኸኝ
እሄዳለሁ ብትል ከመንገድ ጥለኸኝ
እናቴ ትሙት አንላቀቅም
እኔ በፍቅር ቀልድ አላውቅም!
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
🌹🌹🌹💯🌹🌹🌹🌹🌹
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
ስትይኝ ፈራለሁ
አንዳንዴም ኮራለሁ
አንዴ ደስ ይለኛል
አንዳንዴ ይጨንቀኛል
▰▰▰▰▰▰▰▰▰
🌹🌹🌹፪🌹🌹🌹💯
▰▰▰▰▰▰▰▰▰
“እየውልህ ውዴ . . .
እኔማ ስወድህ ሁኚ ያልከኝን ሆኜ
የኔን ዓለም ትቼ ባንተ ዓለም መንኜ
ጠቅልዬ ግብቼ ከገዳምህ ዋሻ
በስምህ ፀልዬ ሃጢያቴን ማስረሻ
እንደሆነ መቼም አንተም ታውቀዋለህ
ከቶ ያልሰጠውህ ኧረ እንደው ምን አለህ
ታዲያ ሁሉን ወስደህ ባዶዬን ቀርቼ
ኑሮዬን በሞላ አንተው ላይ ገንብቼ
ስታውቀው እንዳልኖር አንተን ተለይቼ
እሄዳለሁ ብትል ድንገት አንቺን ትቼ
እናቴ ትሙት አንላቀቅም
እኔ በህወት ቀልድ አላውቅም!”
▰▰▰▰▰▰▰▰▰
❤L❤O❤V❤E❤
▰▰▰▰▰▰▰▰▰
ስትይኝ ፈራለሁ
አንዳንዴም ኮራለሁ
አንዴ ደስ ይለኛል
አንዳንዴ ይጨንቀኛል።
.
ሰማሽ የኔ እመቤት . . .
እውነት አንቺን ርቄ
እምነትሽን ፍቄ
በፍቅርሽ ቀልጄ
ሌላ ሴት ለምጄ
ምኖር ይመስልሻል ?!
እውነት እውነት እውነት
በእውነት ተሳስተሻል !
ደግሞ ፉከራሽን ዛቻሽን ፈርቼ
እንዳይመስልሽ ውዴ እኔስ ተረትቼ!
❤❤ ይልቅ እኔም አልኩሽ . . . ❤❤
❤❤ እናቴ ትሙት አንላቀቅም ❤❤
❤❤ካንቺስ ወዲያሴት አላውቅም❤
🌹🌹🌹🌹🌹
❤
@buraast
@buraast
#ትዝ_አለኝ
:
:
ፍቅሬ ...
ምን ትዝ እንዳለኝ ልንገርሽ ዛሬ!!
:
:
ስንጠጋጋ .... ስንጠጋጋ
አንቺ ወደኔ ጋ እኔ ወዳንቺ ጋ
ከአፈሙዝ እንደወጣ ጥይት
ለዐይን በሚደንቅ ትይንት
እጄን ባንገትሽ ላይ ጣል አድርጌ
ወደ ከናፍርሽ ተምዘግዝጌ
ተቀናቃኝ በሌለበት በውድማው
እኔው ከኔው እየተሻማው
እነዚያን ሁለት የእንጆሪ ፍሬ
ከመቅፅበት ተወርውሬ
ተስገብግቤ ስገምጣቸው
ደጋግሜ ስመጣቸው
ትዝ አለኝ ዛሬ ድንገት
ትዝ አለኝ ለትክዜ
ያሳለፍነው ያ ማር ጊዜ።
@buraast
መ ቅ ደ ላ ዊ ት 🌺
❣ :¨""""""""""""""¨:❣
♥️ ክፍል 5
◈ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ🌺
✍ Written by Ambaye Getahun
ናሆም ዶርም እንደደረሰ ማንንም አላገኘም ። አልጋው ላይ ጋደም አለና " ቆይ ግን እንዴት ልትመጣ ቻለች? ደግሞ ስለ እኔ ምንም አታውቅም በቃ አጋጣሚ ነው። ግን ጥሩ ልጅ ነች። ጥሩ ልጅም ላትሆን ትችላለች ።ግን ኩሩ ናት ተብላ ነበር። እኔ ግን ኩራቷን አላየሁም።" በጥርጣሬም በግርምትም መቅደላዊትን እያሰበ አይኖቹን ወደ ጣራው አሻቅቦ ስለ መቅደላዊት የማያውቀውን ጣራው እንዲነግረው በመማፀን ያለ ይመስላል ።" ቀጣይ ምን ላደርግ ይገባል? ቀጣይ ባህሪየን መቀየር አለብኝ። ዛሬ ፍፁም ሰላማዊ ሆኜ ነው ያወራኋት። ቦታም መቀየር አለብኝ በተቻለኝ መጠን ብቻየን ማድረግ አለብኝ። የማደርገውን ለማንም ሳልናገር መስራት ይኖርብኛል። እንደዛ ማድረግ ከቻልኩ ትክክለኛ ባህሪዋ ላይ መድረስ እችላለሁ ።" በዚህ ጊዜ ዶርሙ ተንኳኳ " የነ ናሆም ዶርም መግቢያ በሩ ላይ " እባክዎ ቀጣዩን በር ይጠቀሙ" የሚል መልዕክት ተፅፎበታል ። " ማን ነህ " አለ ናሆም፤ " ናሆ እኔ ነኝ" አለ ናታኔም ፡ ናሆም ከአልጋው ወርዶ ከፈተው። " የት ሆነህ ነበር ናሆ?" አለ ናታኔም ገና ከመግባቱ።" አየር ለመቀበል ወደ ስታዴየም አምርቼ ነበር። " አለ ናሆም " እኔ አሪፍ ነበር በደምብ ወሰድክ ?" አለ ናታኔም አንዳች የሚነግረው ነገር ቢኖር ብሎ" አወ ግን መቅደላዊትን አገኘኋት" አለ ናሆም " ኧረ ባክህ እንዴት ሊሆን ይችላል ? በመደነቅ መልሶ ጠየቀው" ድንገት ነው እኔ ልመጣ ስል ነው እዛው ስቴዳየም ያገኘኋት። እና ከአንዳንድ ተዋወቅንና የተወሰነ አወራን። ስለ እሷ የሰማሁት እና ባህሪዋ ፍፁም ተቃራኒ ነው። ግን ደግሞ እያስመሰለችም ሊሆን ይችላል " አለ ናሆም ፡ " ለምን ልታስመስል ትችላለች አንተን አታውቅህም ስለዚህ ለማታቀው ሰው የማስመሰል ግዴታ ያለባት አይመስለኝም" አለ ናታኔም " ምን መሰለህ ናቲ ሴት ልጅ አንተን ማጥመድ ከፈለገች ብቸኛ መንገዷ መላዕክ መስላ መቅረብ እና ያልጠበከውን ማድረግ ነው። ካልሆነ ግን ትክክለኛ ሰው ከሆነች መጀመሪያ እንኳን ልታናግርህ ይቅርና ቸክም አታደርግህ። አንተ እንኳ ደፍረህ ብታናግራት ልትነጫነጭ አለያም ልትሰድብህ ትችላለች ። በጭራሽ ፊት አትሰጥህም። ይች ግን ድንገት መጣች ብዙ ጊዚያትን እዛ ቦታ አሳልፋለሁ አንድ ቀን መጥታ የማታቅ ልጅ። እኔ ስጠይቃት አልፎ አልፎ እንደምትመጣ ነገረችኝ። ልጅቱ የሆነ ነገር አስባለች።" አለ ናሆም " እኔ ግን ምንም ነገር ላታስብ ትችላለች ። ምን አልባት አንተ ሁሌም ነገሮችን በተቃራኒው ማየት ስለምትወድ እና ስለምትጠራጠር ይሆናል " አለ ናታኔም " ተስፋ አደርጋለሁ ጥርጣሬየ ውሸት ሆኖ የእሷ እውነት እንዲሆን ካልሆነ ግን ጥሩ የገር አይፈጠርም። ዋጋ ትከፍልበታለች" አለ እና ናሆም ወደ አልጋው ተመልሶ ወጣ።" እና ቀጣይ ምን ልታደርግ አሰብክ " አለ ናታኔም " አላውቅም ናቲሻ እስካሁንበደንብ አላሰብኩም ። ስንት የሚያሰሳስበኝ ነገር አለ መሰለህ ደግሞ ሀእሷ ጊዜ ሰጥቼ ጊዜየን ልግደል እንዴ ?" አለ እና ናሆም ሀሳቡን ለመዝጋት የጓጓ በሚመስል አነጋገር ።" አሁን ያሳሰበኝ የmechanics መምህር ነው፡ እስካሁን ምንም በትክክል እያስተማረን አይደለም ደግሞ በጣም አስቸጋሪ ባህሪ ነው ያለው። እና መሸፈን ያለብኝን በጊዜ መሸፈን ይኖርብኛል። እና አሁን መተኛት አለብኝ 7:00 ሲል ቀስቅሰኝ ምን አልባት ካልተኛህ ። ያው ምን አልባት እንቅልፍ ከጠላኝ ብቸ ነው እንጅ አላርም እሞላለሁ ። " አለ ናሆም " እቀሰቅስሀለሁ " አለና ናታኔም ስልኩን ከኪሱ አውጥቶ ወደ በረንዳው ወጣ......
꧁༺༒༻꧂
✎ 🌺ክፍል ስድስት 6 ይቀጥላል
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share @buraast
የፍቅር ታሪክ❣
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
🇪🇹:
መ ቅ ደ ላ ዊ ት 🌺
❣ :¨""""""""""""""¨:❣
♥️ ክፍል 4
◈ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ🌺
✍ Written by Ambaye Getahun
ወደ እሷ ሲጠጋ መቅደላዊት እምር ብላ ተነሳችና " እንዴ የት ነበርክ? እያዳመጥከን ነበር? ቆይ ለምን እንዲህ አረክ?" ጥያቄዋን አከታተለች። "ጎበዝ መቅደላዊት የመጀመሪያ ስራሽን በትክክል ተወጥተሻል። አሁን ናሆም በአንቺ መላዕክነት እየተገረመ ይሄዳል እየተገረመ ያመሻል፤እየተገረመ ያድራል ። በዚህም ስለ ቀጣዩ አንች ስትጠነክሪ እሱ በአሁኑ ባሳየሽው ባህሪ ሳይዘጋጅ ይመጣል። ያው ልክ እንደ አሁኑ በድንገት ታገኝዋለሽ። ሀሀሀሀሀሀሀሀሀ በደንብ ሳቀ። ነገር ግን ይሄን ባህሪሽን አንድ ቀን እውነቱን ያወቀ እለት ሊገልሽ ይችላል ሲበዛ በጣም አደገኛ ነው። አሁን ማድረግ ያለብን በተቻለን መጠን አመለካከቱን መቀየር ነው። ለሴት ልጅ ያለው ጥላቻ መወገድ አለበት። እንደዛ መሆን አለበት። ናሆም የዋህ ልጅ ነው በጣም ሲበዛ። እና ደግሞ ይሄን የዋህነቱን እና አዛኝነቱን ባልሆነ ጥላቻ ጭምበል አጥልቆ ማንነቱን እንዲያጣ አልፈልግም ።ለዚህም ማንኛውንም ነገር በጋራ እየሰራን ናሆምን መቀየር የእኔና የአንቺ ኃላፊነት ነው። በተለይ አንቺ ከዚህ በኋላ በትርፍ ጊዜሽ እሱን ታድኛለሽ። ከዚህ በኋላ ምን አልባት ላንገናኝ እንችላለን ።በድንገት ሊያየን ይችላል ስለዚህ በስልክ እናወራለን ።በዚህም ሁሌም ምሳ ከበላን በኋላ ለብቻው ወደ ማንዴላ ዋርካ ሄዶ ለ45 ደቂቃ ያሳልፋል። ምሳ የምንበላው 5:40 ሲል ነው ልክ 6:00ሲል እዛ ይሄዳል። ከስአት ከ10:30-11 እዚህ ስቴድየም ይመጣል። ከዛ ማታ 1:00 ላይ ለሻይ ቡና ወደ ማክዳ ካፌ ይሄዳል።ሌሊት 7:30 ከእንቅልፉ ነቅቶ ወደ ምኒልክ ላይብረሪ ይሄዳል። ሌሊት 10:30 ከላይብሪ ተመልሶ ይተኛል።ይሄ የእለት ተእለት ፕሮግራሙ ነው። እንደየ ሁኔታው ፕሮግራሞቹን ይቀያይራል። በጣም ሲበዛ ተጠራጣሪ ነው። አንዲት ውሸት ከመቶ እውነት ካገኘ ከዛ በኋላ አለቀ። እና በውጤቱ ትደሰችበታለሽ ሁሌም ሁሌም ቢሆን በራስሽ ትኮሪያለሽ። እሽ?" አላት ። " ግን እኮ እቅዳችን ላይሰራ ይችላል ።" አለች መቅደላዊት ግራ በተጋቡ ሁናቴ " እየውልሽ መጀመሪያ ራስሽን አሳምኝው። አሁን እያደረክሽው ያለሽው ነገር የፍፃሜሽ የስኬትሽ ሽልማት የናሆምን አመለካከት ጥሩ ሆኖ ማየት ነው። ይሄ ደግሞ በሞዴልነትም ሆነ በትምህርትሽ ስኬታማ ተብለሽ ከምትሸለሚው ሽልማት በላይ ነው። ገባሽ አይደል? ይሄ ደግሞ ለአንቺ ቀላልሽ ነው። ባልኩሽ መሰረት እና የአንቺን ፕሮግራም በማይጎዳ መልኩ" አላት እና መልከመልካሙ ልጅ ትቷት ሄደ። መቅደላዊት ማስታወሻዋን ብድግ አደረገችና " ከመጀመሪያው ለምን እሽ አልኩት የማልረባ ነኝ ? እንዴት ትምህርቴ ላይ ጫና የሚፈጥርን ነገር እቀበላለሁ ? ይሄ መሆን አልነበረበትም ቢሆንም ግን ደግሞ አንድጊዜ እሽ ብየዋለሁ ።ስለዚህ ወደ ኋላ ልል አይገባም። ነገር ግን ልጁ እንዴት እንደዚህ ሴቶችን በጅምላ ይጠላል ? በሌሎቹ በደረሰባቸው ነገር ነው ወይስ በራሱም ደርሶበት ነው እንዲህ ሴትን ሊጠላ የቻለው?" ከራሷ ለራሷ ትጠይቃለች ። አይታወቅም በሁሉም ነገር መፍረድ ቀላል ነው። ናሆም ምን አልባት በሌሎች አስመስሎ ነገር ግን በራሱ ላይ የተፃፈን መፅሀፍ እያነበበ የሚኖር የዋህ ይመስለኛል ።ይሄ ደግሞ አስቸጋሪ ነው። ስለዚህ ከዚህ በኋላ የእውነት ጥሩ ሆኜለት ላወራው ልግባባው ልሰማው ይገባል። በቃ የእውነት ልሆን ይገባል......
꧁༺༒༻꧂
✎ 🌺ክፍል አምስት ♥️ ይቀጥላል... ♥️
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━👉
••●◉Join us share @buraast
የፍቅር ታሪክ❣
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
መ ቅ ደ ላ ዊ ት 🌺
❣ :¨""""""""""""""¨:❣
♥️ ክፍል 2
◈ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ🌺
✍ Written by Ambaye Getahun
"መቅደላዊት እኮ የዩኒቨርሲቲያችን ሞዴል ናት። በጣም ቆንጆ ፣ በጣም ሲበዛ ጎበዝ ተማሪ ፣ እና ጉረኛም ናት። የጊቢያችን ወንዶች ከአንደኛ አመት እስከ አምስተኛ አመት ድረስ በፍቅሯ ያላለቀሰ ያልነሆለለ የለም። የጊቢያችን አሉ የተባሉ ወንዶች ሁሉ ጠይቀዋታል። እሷ ግን የዋዛ አይደለችም ።እግዜር እሷን ብቻ ሲሰራ ሳምንት ፈጅቶበታል። እኔ በሂወት ዘመኔ እንደዚች አይነት ልጅ የማይ አይመስለኝም።" አለ ናትናኤል ፣ ራሱን እየወዘወዘ " ተወው አታጋናት ይሄኔ ዝምብላ ነው የምትሆነው ።" አለ ናሆም "ኧረ ናሆ ብታያት እኮ በስመአብ ምን እንደምትል" በቃ እሽ ጥሩ ምን እንደምል ከፈለክ ነገ ልጇቷን ታሳየኛለህ?" ኧረ ችግር የለም " ለምንህ ፈለካት?" ናታኔም ነበር። በእርጋታ ሲያዳምጣቸው ከቆየ በኋላ ። " እንዲሁ ለማወቅ ልጅቱ ማን እንደሆነች ማወቁ አይከፋም አይመስልህም ናቲ" " አንተ ልጅ ሌላ ነገር እንዳታስብ"አለ ናታኔም " ኧረ ናቲ ምን ሆነሀል? ምን ላስብ እችላለሁ ?እንዲህማ በክፉ አትፈርጀኝ" አለ ናሆም ወደ ናታኔም ፊቱን አዙሮ አይኖቹን ከደን አድርጎ ።!! በቃ እኔ መውጣቴ ነው ናቲ" የት ነህ? " ትንሽ ዘወርወር ብየ እመለሳለሁ ። ናሆም ጥቁር ሹራብ ቀለል ባለ ጃኬት ለብሶ ከዶርም ወጥቶ የሚኖርበትን የአሉላ አባነጋ ብሎክን ወርዶ ወደ የባልቻ አባ ሳፎን ብሎክ ሽቅብ ወደ አቢሲኒያ ስታዲየም አመራ። ሁሌም የሆነ ነገር ለማሰብ ሲፈልግ እዚህ መጥቶ ቁጭ ይላል ። እዚህ ጫጫታ የለም። ፀጥታ ነው የሚነግሰው። ከአእዋፋት ጋ ጉባኤ መቀመጥ አንተ በዝምታ እነሱ በወፋዊ ዜማ ማህሌት ሲደርሱ ይሰማሀል። ያኔ በሀሴት ራስህን አድሰህ ትመለሳለህ። እናም ናሆም እዚህ ሲመጣ አንድ ነገር አስቦ ቋጭቶ ይመለሳል ።መቅደላዊት ማናት??? ልጅቷ ለምን ይሄን ያህል ይወራላታል? እሷስ ስንቱን ወንድ ይሆን ደም ያስነባችው?" ጥያቄወችን ለራሱ አከታትሎ ይጠይቃል። ቆይ ለምን ይሄን ያህል ስለ እሷ አስባለሁ? እንደተባለው በትምህርቷ ጎበዝ ከሆነች ወንዶችን የማታሰቀርብበት ምክንያት ያው ከትምህርቷ እንዳትቀንስ ይሆናል።ያም ላይሆን ይችላል።ቢሆንም ልጅቱን ልወቃት ከዛ ማንነቷን እየቆየን የምናየው ይሆናል ። ናሆም ከራሱ ጋር እያወራ ጀምበሯ ቁልቁል ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ለማሸለብ ጣር ይዟታል። ጨለማው በተራው ፀሀይን በመተካት ሌሊቱን ለመንገስ የጓጓ ይመስላል ።ፀሀይዋን ገና ሳትገባ ዙሪያዋን ከቧታል።ይሄን ሁሉ የተፈጥሮ ዑደት ናሆም በአርምሞ ይመለከታል። አቢሲኒያ እስቴዲየም መቀመጫው ልዩ ነው። በየ ደጋፊዎቻቸው መቀመጫ አድዋ ላይ የተሰው አያቶቻችን ከእግረኛ እስከ ፈረሰኛ ከህፃናት እስከ አዋቂ ከሽፍታ እስከ ንጉሱ ጀነራል ፎቷቸው ተለጥፏል። ጊቢው አድዋ ነው። ዩኒቨርስቲው ውስጥ ያሉ ነገሮች በሙሉ ከአንዳንድ ስፍራዎች በቀር በሙሉ በአድዋ ላይ በተሳተፉ ጀግኖች ተሰይሟል። በዚህም የውጪ ጎብኝወች ኢትዮጵያን ለማየት ከመጡ በኋላ አድዋ ተራራን ካዩ በኋላ እግረመንገዳቸውን ይሄን ገናና ዩኒቨርስቲ ተመልክተው ይመለሳሉ ። በጉብኝታቸውም በጣም ተደስተው ነው። ብቻ ጊቢው አንዳች የመንፈስ እርካታ ካባን ያጎናጽፋል ።ናሆም ይሄን ሁሉ እያየ በአያቶቻችን ብስለት፣ አንድነት፣ ወኔ፣ጥንካሬ፣ ተደምሞ ስለሰሩት ገደል እያሰበ ድንገት ሳያስበው እንባው ኩብልል ብሎ ወርዶ ሐሬት ላይ ጠብ ሲል ያይ እና ብድግ ብሎ እምባወቹን ጠረግረግ አርጎ ዘወር ሲል.......
꧁༺༒༻꧂
✎ 🌺ክፍል ሶስት ♥️ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ share♥️ ማድረግ አይርሱ።
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share @buraast
የፍቅር ታሪክ❣
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
"በትምሕርት ቤት ታሪኬ እንደ ማትሰ መከራዬን ያበላኝ የትምሕርት ዓይነት የለም"
"ማትስ ፈተና ስንፈተን"
1 የክፍሉ ጎበዝ ተማሪ ለፈታኙ አራተኛው ጥያቄ ችግር አለበት ሲል እኔ ግን መልስ መሙያው ላይ መልሴን ሞልቼ ነበር😴😴😴
2 ሌላው ጎበዝ ተማሪ ግራፕ ፔፐር እፈልጋለው ሲል እኔ ደሞ ሁሉንም መልስ ስለጨረስኩ የቱጋ ነው የሚያስፈልገኝ ብዬ እገረማለሁ😏😏😏
3 ፈታኙ ስድተኛውን ጥያቄ ስለምናስተካክለው ዝለሉት ሲል እኔ ደሞ ከሁሉም ጥያቄዎች ዘና ብዬ የመለስኩት ነበር😂😂😂
4 ተማሪዎች ማስመሪያ ሲጠቀሙ እኔ ደሞ ግራ ግብት ብሎኝ ምን እያረጉበት ነው ብዬ በግርምት አያቸዋለው😎
5 ፈተናው ካለቀ በኋላ የክፍሉ ጎበዝ ተማሪዎች የአምስተኛው ጥያቄ መልስ 35% አደለም 36% ነው እያሉ ሲከራከሩ እኔ ደሞ 45000 ብዬ ነበር የመለስኩት😝😝😝
ሰናይ ዕለት ይሁንላቹ ለሰሞኑ ብርድ ደሞ ያዘጋጀናቸውን ብርድልብሶች inbox በማረግ መውሰድ ትችላላቹ😜😜😜
መ ቅ ደ ላ ዊ ት 🌺
❣ :¨""""""""""""""¨:❣
♥️ ክፍል 1
◈ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ🌺
✍ Written by Ambaye Getahun
" ሴት ልጅ አንዴ ከወደደችህ እስከ ሞት ድረስ ዋጋ ልትከፍልልህ ትችላለች ፡ ግን እስክትወድህ የተወለድክበትን ቀን እስክትረግም ድረስ ነው የምታማርርህ።" አለ ናሆም ገና በውል የዶርሙን በራፍ ሳይዘጋ። ምን ለማለት ፈልገህ ነው? ናሆም ?" አለ ናታኔም ከተኛበት አልጋ እየተነሳ " ያው ያልኩት ግልፅ ነው ሴት ልጅ ያንተ እስክትሆን ዋጋ ታስከፍልሀለች። የአንተ ከሆነች በኋላ ደግሞ አንተን ላለማጣት ዋጋ ትከፍላለች ።ለዚህም የመጀመሪያውን ዋጋህን ትመልስና በእጥፍ ታተርፋለህ ማለት ነው። እመነኝ እኔ ሴትን ለጅ ለጥቅሜ ካልሆነ በጭራሽ አልቀርብም። ሴት ልጅ ለእኔ ተራ ናት ለወደዳት ሳይሆን ላልወደዳት የምትሞት ጅል ። ስለዚህም እኔ ሴትን ልወዳት አልችልም እስከዚህ ዩኒቨርስቲ እስክገባ ድረስ በሴት ተሸውጀ አላቅም ልሸወድም አልችልም ። ሁሉንም የሴቶችን ባህሪ እና ድርጊት በጓደኞቼ ላይ ተምሬ አልፌዋለሁ ። በቃ እንደዛ ነው ናቲ " አለና ናሆም አልጋው ላይ ጋደም አለ።" በእርግጥ ናሆም በአመለካከትህ ጣልቃ አልገባም እሱ ያንተ አስተሳሰብ ነው። ግን ሁሉንም ሴቶች በአንዲት ሴት ግብር መፈረጅህ ትክክል አይመስለኝም ሁሉም ሴት አንድ አይደሉም። " አንድ ናቸው ናሆም ተናዶ ብድግ አለ ።አንተ ምን ታቃለህ? ከአንዴም ሁለት ጊዜ ከዛም በላይ ወንድሜ ጓደኞቼ ምን እንደሆኑ አይቻለሁ። ሌላውን ተወውና እህቴ ራሱ ብዙ የሚያፈቅሯትን ወንዶች ምን እንዳደረገቻቸው እኔ ነኝ የማቀው። ናታን ብዙ የማታውቀው ነገር አለና ዝም በል። ፊቱ ተቀያየረ " እሽ በቃ ናሆም ጓደኛየ ይቅርታ በአንተ ጣልቃ አልገባም" አለና ትቶት ቁጭ አለ ። ናታኔም እና ናሆም የተዋወቁት እዚሁ አድዋ ዩኒቨርስቲ ነው። አድዋ ዩኒቨርስቲ በኢትዮጵያ አሉ ከሚባሉ ዩኒቨርስቲዎች አንዱ ነው። ታዲያ በ2009 ዓ.ም የመጀመሪያ አመት ሆነው እዚህ ጊቢ የተመደቡት ናታኔም ከአ.አ እና ናሆም ከድሬደዋ ነው። ሁለቱም በአጋጣሚ አንድ ዶርም ነው የተመደቡት ። ከሌሎቹ የዶርም ሜቶች ይልቅ ናታኔም የቀለለው ናሆም ነበር። በደንብ ተግባቡ ከዛም ጓደኛ ሆኑ። ሁለቱም የሆኑትን ይጨዋወታሉ አይደባበቁም። ናሆም mechanical engineering ሲገባ ናታኔም ደግሞ electrical engineering ይገባል። በዚህም ሁለቱም ሁለተኛ ሴምስተር በየ ትምህርት ዘርፋቸው ይመደባሉ ። እስከዛው ግን አብረው ናቸው።ታዲያ አንድ ቀን ራት በልተው ዶርም ቁጭ ብለው እየተጫወቱ እያለ ሌሎቹ የዶርም ልጆች እየተጨቃጨቁ ገቡ።" ምንድነው ሚያጨቃጭቃችሁ?" ናሆም ሁለቱንም በየተራ እያየ ጠየቃቸው። ሁለቱም ተያዩ ናትናኤል ፈጠን ብሎ በዚች በመቅደላዊት ነዋ" አለ ። ናሆም ሁለቱንም እያየ መቅደላዊት ማ..ማ ማናት??? "አታውቃትም?" አለ ናትናኤል "ባቃት ለምን እጠይቅሃለሁ ?" እሽ እነግርሃለሁ መቅደላዊት እኮ......
꧁༺༒༻꧂
✎ 🌺ክፍል ሁለት ♥️ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ share♥️ ማድረግ አይርሱ።
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share @buraast
የፍቅር ታሪክ❣
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
┈┈┈┈••✦❖✦••┈┈┈┈
🦋ወዳጄ ሆይ🦋
❤️ፍቅር ማለት ውበት አይደለም
❤️ፍቅር ማለት ጥቅም ፋለጋ አይደለም
❤️ፍቅር ማለት ዝሙት ፍለጋ አይደለም
❤️ፍቅር ማለት በደስታ ጊዜ መተቃቀፍ አይደለም
❤️ፍቅር ማለት ስለወደደን መውደድ አይደለም
❤️ፍቅር ማለት ስላከበረን ማክበር አይደለም
❤️ፍቅር ማለት ስላገዘን አንተም ቀን ጠብቀህ
ብድር መመለስ አይደለም
❤️ፍቅር ማለት ከማንነት የፀዳ
❤️ፍቅር ማለት ከማዳላት የራቀ
❤️ፍቅር ማለት ከመፍረድ እጅን ያወጣ በመከራም፣በሀዘንም፣በጭንቀትም፣በደስታም፣በመተሳሰብ፣መተጋገዝ፣መረዳዳት አንተ ያላገኝሀውን ነገር ሌሎች እንዲያገኙ መመኘት፣ጠላትህን መውደድ፣ስለወንድምህ እራስህን አሳልፈ መስጠት የወንድምህን በደል መሸከም ባንተ እንዲፈፀም የማትፈልገውን በሌላ አለመፈፀም ተመልሶ በራስህ መፈፀሙ አይቀርም፡፡እንዲህ እንድንሆን ፈጣሪ ይርዳን፡፡
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share
@buraast
❣
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
😍 ከአቅም በላይ ስለወደድኩሽ
🙏 ይቅር በይኝ!
💞ከማንም በላይ ከአንቺጋ መሆን በመፈለጌ
🙏 ይቅር በይኝ!
❤️በህይወትሽ ውስጥ ቦታ ትልቅ እንድትሰጪኝ በመጠየቄ
🙏 ይቅር በይኝ!
💘መካድ እስከማልችል ድረስ ስላፈቀርኩሽ
🙏 ይቅር በይኝ!
💔መውደዴ ስላልገባሽና በእኔ ውስጥ ያለሽን ቦታ ስላላወቅሽ
🙏ይቅር እልሻለሁ!
-------❖----🌹----❤️----🌹----❖--------
┈••✥ @buraast ✥••┈
❖┈••✦ @buraast✦••┈❖
🔵ጸንተህ ለመቆም ከፍርሃትህ የሚበልጥ ነገር ፈልግ!
✍bůřą (copy )
♦️ፍርሃት በሁለት መንገድ የሚከፈል ይመስለኛል። አንደኛ እራሳችን የምንፈጥረው ፍርሃት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሌሎች በውስጣችን የሚጭሩት ፍርሃት ነው። ሁለቱም ሀይለኛ ስሜቶች ናቸው። ሁለቱም ጉልበትን የማሸብረክ፤ ውሳኔን የማስቀየር፤ አላማን የማሳት፤ አሸማቆ ወደ ብቸኝነት ጉድጓድ የማስገባት ጉልበት አላቸው። እራሳችን በራሳችን የምንፈጥረውና ሌሎች በኛ ሊጭሩት የሚሞክሩት ፍርሃት የየራሳቸው ባህሪ አላቸው። እንደሚከተለው እንመልከታቸው
🔵እራሳችን በራሳችን የምንፈጥረው ፍርሃት- ይህ በእራስ ካለመተማመን የሚመነጭ ስሜት ነው። በራስ መተማመን ትርጉሙ ጥልቅ ቢሆንም እራስን መቀበል፤ አቅም እና ችሎታዎችችን ማወቅ፤ በሌሎች ሰዎች አስተያየት ሳይሆን በራስ ፍላጎት መመራት ጥቂቶቹ መመዘኛዎች ናቸው። እንግዲህ እኒህን ነገሮች ማሟላት ሲያቅተን ፍርሃት በውስጣችን ይሰርጻል። ምን አይነት ፍርሃት? ለሚለው ጥያቄ መልሱ ግላዊ ነው።
♦️ሌሎች በእኛ ላይ የሚፈጥሩት ፍርሃት- ይህ ደግሞ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች በእኛ ላይ እምነት ሲያጡ የሚፈጠር ፍርሃት ነው። የመጀመሪያውን ፍርሃት ካሸነፍን ይህ አይነቱ ፍርሃት እኛን ለማስቆም አቅም አይኖረውም። ምክንያቱም እኛን እንደገዛ እራሳችን ሊያስደነብረን የሚችል ማንም ሰው ባለመኖሩ ነው። “ሰው ከራሱ የበለጠ ጠላት የለውም” የሚለው የአፍሪካውያን አባባል፤ ያለምክንያት የተተረተ አይደለም።
🔴እዚህ ላይ አንድ አስገራሚ እውነት ቢኖር፤ ሁሉም በእኛ ላይ እምነታቸውን ቢያሳድሩ እና እኛ በራሳችን ማመን ቢያቅተን ምንም ነገር ብንሞክር የመሳካት እድሉ በጣም ጠባብ ነው። በአንጻሩ እኛ በራሳችን እምነት ኖሮን ሌሎች ግን በእኛ እምነት ቢያጡ አላማችን የማይሳካበት ምንም መንገድ የለም። ከላይ እንዳሰፈርኩት ከገዛ እራሳችን በበለጠ እኛን ለማስቆም የሚቻለው ማንም ሰው ባለመኖሩ ነው።
♦️እንግዲህ ሳይንሳዊ የሆነውን የፍርሃት ትንተና ትተን በተለያየ ደረጃ የሚገጥመንን ፍርሃት እንድንጋፈጥ የሚረዳን አንድ መፍትሄ አለ።
🔵 ይህም ከፍርሀታችን የበለጠ ነገር መፈለግ! አላማችን ከፍርሃታችን ከበለጠ፤ ህልማችን ከፍርሃታችን ጥላ ከገዘፈ፤ እራሳችንም ሆነ ሌሎች የሚጭሩት ፍርሃት ከጉዟዋችን አይገቱንም። ስለዚህ ድንገት አዲስ ነገር ለመጀመር አስበን ፍርሃት ከተሰማን ይህንን ጥያቄ እራሳችንን እንጠይቅ፤ ከፍላጎታችን እና ከፍርሃታችን የቱ ይበልጣል?
ሁሌም ከፍርሃትህ የገዘፈ ህልም ይኑርህ!!!
መልካም ምሽት♥️
🔵♦️🔵♦️🔵♦️🔵♦️🔵♦️🔵♦️🔵
@buraast
@buraast
bůřå
••●🍃እበጂልኝ••●🍃
ፍቅርሽ ክፉኛ ቢቀጣኝ
አንደበቴ ታስሮ
መናገር ቢያቅተኝ
መፍትሔ ፈልጌ
ደፍሬሽ መጣሁኝ።
ትንፋሼ ቁርጥ ቁርጥ
አፌ ኩልትፍ ኩልትፍ
ላብድ ነዉ በፍቅርሽ
ብዬ ብጠይቅሽ
እስቲ አብደህ አሳየኝ
ነበረ ምላሽሽ
ፍቅርሽ አጃጅሎኝ
እብደትን ሞከርኩት
ፀጉሬን አሳድጌ
ልብሴን ቀዳደድኩት
ወጣሁኝ ጎዳና
ብርዱን ተላመድኩት
ለካስ እብደት ውስጥ
ጥልቅ የሆነ ሚስጥር
የራስ ነፃ ዓለም
ጭንቀት የሌለበት
ፍቅርሽን ረስቼ
እብደት ተመችቶኝ
በዛው ቀጠልኩበት
ምን ይሆን ምላሽሽ
እንዲ ስሆን አይተሽ
መሥዋት መሆኔን
እንደፍላጐትሽ
ፀፀቱን ካልቻልሽው
እየነሳሽ ጤና
አንድ ላይ እንሁን
አንቺም እበጂና።
@buraast
የመጥላቴ መጠን ሲገለጽ...!
---------- -----------
:
:
እኔ ጠላሻለሁ..
ልክ በሰርግ ቀን፣መርዶን እንደመስማት፣
በቡና ላይ ወሬ፣
ገደብ በሌለው አፍ፣ ሰውን እንደማማት፣
ቀን ስደክም ውዬ፣
እኩለ ሌሊት ላይ፣እንቅልፍ እንደማጣት፣
ከራስ ዳሽን በላይ፣
እጥፍ የሚረዝም፣ተራራ እንደመውጣት፣
ከአንገት በላይ ዙሪያ...
ቆልፎ እንደሚይዝ፣ እንደ ጆሮ ደግፍ፣
በአይን እንደማየት..
ንጹሀን ሲሞቱ፣ ሲገደሉ በግፍ።
:
:
እኔ ጠላሻለሁ..
በሚስት ደርቦ፣ ሴት እንደመመኘት
ከፋይናል ፈተና፣ዜሮን እንደማግኘት
የሚወዱትን ሰው...
ራቅ የሚል ሀገር፣ልክ እንደመሸኘት፣
ዛሬ ተሳስቆ፣
ቦርቆ ፈንድቆ፣ ነገ እንደመጨነቅ፣
የቅርብ ዘመድን፣
በጥላቻ ስሜት፣አንገት እንደማነቅ፣
:
:
እኔ ጠላሻለው...
የሚያፈቅሩትን ሰው፣ቀጥሮ እንደመዘግየት
አመታት ታግሰው፣
ያሳደጉት ጸጉር፣ሲረግፍ እንደማየት፣
በሚወዱት እናት፣ልክ እንደ መረገም፣
በቦክስ ተመቶ፣ ጥፊ እንደ መደገም፣
:
ኔትወርክ እንደሌለው፣
ስልክ እንደማይደውል፣ የቻይና ሞባይል፣
ገንዘብ ስንሰጠው፣
ጨለማ እንደሚሰጥ፣እንደ መብራት ሀይል፣
😂
😂
ቅር አይበልሽ ውዴ፣እንዲህ ነው ምጠላሽ፣
የመጥላቴ ብዛት፣ መጠኑ ካስጠላሽ፣
ያንቺን ብሔር ትተሽ፣ሰዎችን ውደጂ፣
ሀገር እንዲመችሽ፣ ኑሮም እንዲደላሽ።
:
እምቢ ካልሽ ደግሞ፣
አሁንም ሰፊ ነው፣ የመጥላት መጠኔ፣
ጨምሬ ስነግርሽ፣ ደስ ይለኛል እኔ።
:
:
እኔ ጠላሻለው...
ከመርካቶ መሐል፣ ሚገዛ እንደማጣት፣
ተንበርከክ ተብሎ...
እግር እንደሚያሳምም፣የመምህር ቅጣት፤
ሰይጣን እንደሚሉት፣ ልክ እንደዚያ ከይሲ፣
ነዳጅ ተቀብሎ፣
አልሄድም እንደሚል፣በሽተኛ ታክሲ፣
ዝናብ አልቋጥርም፣
ብሎ እንዳኮረፈ፣የሰማይ ደመና፣
መራራ እንደሆነው፣እንደ እሬት ቃና፣
አዙሮ እንደሚጥል፣የሒሳብ ፈተና፣
:
:
እኔ ጠላሻለው...አብሬሽ እስካለው
የመጥላቴ መጠን፣እስከዚህ ድረስ ነው፣
ብልሽ ደስ አይበልሽ..
:
አሁንም እምቢ ካልሽ..
ጥላቻ ትችቴን
ምዘረዝርበት፣አለኝ ትልቅ አቅም፣
አንቺን ምጠላበት...
ስፋት ርዝመቱ፣ብትለኪው አያልቅም፣
:
እኔ ጠላሻለው...
ፍሬን እንደማጣት፣ ትልቅ መሬት አርሶ፣
ማቆሚያ እንደሌለው፣ የህጻን ልጅ ለቅሶ፣
በወባ ሲያዙ...
እንደሚለበልብ ፣ የሞቀ ትኩሳት፣
በድቅድቅ ጨለማ፣
እንደሚያቃጥለው፣የሲኦል ውስጥ እሳት፣
ዛሬ የተማሩትን፣ነገ ላይ እንደ መርሳት።
:
ሁለት እጅ አስይዞ፣
ሆድ እንደሚቆልፍ፣ እንደ ከባድ ቁርጠት፣
ከ 10 ብር ካርድ ላይ...
ስምንቱን ለቴሌ፣ በነጻ እንደመስጠት፣
😂
:
:
ቅባት በነካው ፊት፣
በማድያት ተከቦ፣ ከስቶ እንደ መገርጣት፣
ለውሃ እና ፍሳሽ፣
ብር እየገበሩ፣ ውሃን እንደማጣት።
:
:😂
እንዲህ ነው ምጠላሽ...
የመጥላቴ መጠን፣ጥጉ አይታወቅም፣
ለርዝመቱ ደግሞ፣
ጫፍ ይኖራል ብለሽ፣ብትለኪውአያልቅም።
:
አሁን እኔ ምለው...
የመጥላቴንምክንያት፣አንቺውታውቂዋለሽ
ሰዎችን በመርሳት፣
በአንዲት ብሔር ፍቅር፣ተጠምደሽ ስላለሽ
:
ስለዚህ ልምከርሽ....
የአንዲት ሀገር ሰላም፣ስለሚያስገድድሽ፣
ብሔሩን ተይና፣
ሰዎችን ውደጂ፣እኔም እንድወድሽ፣
:
ይህን ተቀብለሽ...
ሰዎችን ስትወጂ፣እኔ በአይኔ ካየው፣
ውደደኝ ሳትይኝ፣
ከመጥላቴ በላይ፣ እጥፍ ወድሻለው።
😉😉
( መጀመሪያ ግን ሰውን ውደጂ)
@buraast
@buraast
@buraast
መ ቅ ደ ላ ዊ ት 🌺
❣ :¨""""""""""""""¨:❣
♥️ ክፍል 3
◈ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ🌺
✍ Written by Ambaye Getahun
" እምባውን ጠረግረግ አርጎ ዘወር ሲል ከአጠገቡ ቆማ ድርጊቱን እና ሁኔታውን ስትከታተለው ከነበረች ልጅ ጋር ይገጣጠማል። እንዴ ማነሽ? ቆይ እንዴት መጣሽ? ማለቴ ምን ስአት ነው የመጣሽው? ብዙ ቆይተሻል? የጥያቄ መአት አዥጎደጎደላት። ጥያቄውን ወደ ጎን ተወችና ዝም ብላ ትኩር ብላ ካየችው በኋላ ። "ቆይ ለምንድን ነው? ያለቀስከው ምን ሆነህ ነው? አይኖቹን እያየች ጠየቀችው ። " ምንም አልሆንኩም ኮስተር አለ ለመሆኑ አንቺ ማነሽ??? ፀጉሯ እንደነገሩ ተደርጎ የተያዘ ቢሆንም ግን ቢለቀቅ የት ሊደርስ እንደሚችል መገመት ቀላል ነው። አይኖቿ ውብ ናቸው ። በለበሰችው ተከፋች አጭር ቀሚስ ጡቶቿ በገሚስ ይታያሉ ።ከንፈሯን በስሱ ቀይ ሊፕስቲክ ተቀብታለች። ከተስተካከለ ቁመናዋ ጋራ ልዩ ቆንጆ ነች። ፀጉሯን በግራ እጇ ወደ ኋላ እያስያዘች " ማንነቴ ምን ይሰራልሀል የአንተን ሁኔታ ለመረዳት የግድ ስሜን መንገር አለብኝ? አስበው እስኪ እኔ በአንተ ቦታ ላይ ብሆን እኔ የጠየኩህን አንተ ብጠይቀኝ አንተ የጠየከኝን ብጠይቅህ ምን ታስባለህ?" እሽ እንደዛ ካልሽ እኔ እዚህ አየር እየተቀበልኩ ነበር በቃ ይሄው ነው" " አየር መውሰድ አያስለቅስም ገብቶኛል መናገር አትፈልግም ።በቃ እሽ አላስገድድህም። ለማንኛውም መቅደላዊት እባላለሁ ! " አቤት ማን አልሽኝ? የሰማውን ማመን አልቻለም ። " አልሰማከኝም መቅደላዊት እባላለሁ " ዝም አለ " ምነው ዝም አልክ? አለች ማስታወሻዋን እየገለጠች " ኧረ ዝም አልኩ እንዴ ናሆም እባላለሁ ። " በጣም ቆንጆ ስም ነው!" " አመሰግናለሁ " ናሆም ግን ምን ማለት ነው?" " መፅናናት ማለት ነዋ! " "አሪፍ እናትህ ነች ያወጣችልህ አይደል? " ዘወር አለና በአፅንኦት እየተመለከታት እንዴት አወቅሽ?" ብዙ ጊዜ የስሞችን ትርጓሜ በማወቅ ማን ስም ማንኛው የቤተሰብ አካል እንዳወጣው የማወቅ ልምድ አለኝ አንተም ጋ ያረኩት ያን ልምድ ነው።" አይ ጥሩ ልምድ ነው። ሁልጊዜም እዚህ ትመጫለሽ እንዴ? አወ ሁሌም ከራሴ ጋ ማውራት ስፈልግ የእለት ተእለት ገጠመኜን ማስታወሻየ ላይ የምፅፈው እዚህ መጥቼ ነው።" ጥሩ አድርገሻል ይሄ ቦታ ሰላማዊ ነው። ለሁሉም ነገር ይመቻል። ስንተኛ አመት ተማሪ ነሽ? " ሁለተኛ አመት civil engineering " አድዋን በደንብ ታቂያታለሻ? " አዎ በተለይ ጊቢውን" ከጊቢው ውጭስ?" አለ ናሆም የምፀት ፈገግታ ፈገግ እያለ። " ከጊቢው ውጪ እንኳ ያን ያህል አላውቀውም ።አንዳንዴ ቤተክርስቲያን ለመሳም እና እቃ ለመግዛት ከመሄድ ውጪ " አለች ። " አይ እንደዛ ከሆነ ጥሩ ነው። እና እንዴት እዚህ የምትመጭ ከሆነ አላገኝሽም? አላውቅሽም ጊቢው ውስጥም አይቼሽ አላቅም ።ዛሬ የመጀመሪያ " አለ ናሆም ። " ናሆም ጊቢው እኮ ሰፊ ነው። በጣም ብዙ ተማሪ ይማራል ።በዚህ ሁሉ መሀል እኔን አለማወቅህ ሊያስገርምህ አይገባም ።ነገሩን ቀለል አርገው።" አለች በትኩረት ናሆምን እየተመለከተች። ናሆም የተደነቀ ይመስላል ።በግርምት እያያት ነው። በጣም ሲበዛ ደስ ትያለሽ ስላወኩሽ በጣም ደስ ብሎኛል ።"አለ ናሆም እጁን በድጋሚ ለሰላምታ እየዘረጋላት።" እኔም ስላወኩህ ደስ ብሎኛል " አለች። " በቃ ሌላ ጊዜ እንገናኛለን" አላትና ብድግ ብሎ 'ቸው' አላት። " እሽ ቸው " አለች። ናሆም መቅደላዊትን ያገኘበት አጋጣሚ አስገርሞታል ።እንዴት እንደዚህ አይነት ልጅ ትሆናለች ።ለምንድነው በጣም ኩሩ ናት ያሉት? ልጅቱ ሲበዛ ቆንጆና አንደበቷ በጣም ጣፋጭ ነው። የእውነት መቅደላዊት ይች ናት? እራሱን በድጋሚ ጠየቀ። መቅደላዊት ከስታዲየሙ ሆና በአይኖቿ ተከተለችው ናሆምን ።ነገር ግን ናሆም አልዞረም። ዝም ብሎ ይሄዳል ።ስልኳን አወጣችና ወደ አንድ ስልክ በመደወል ስልኳን ወደ ጀሮዋ አስጠጋች ። በዚህ ጊዜ እጆቹን ጨብጨብ አደረገና ወደ እሷ ሲጠጋ......
꧁༺༒༻꧂
✎ 🌺ክፍል አራት ♥️ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ share♥️ ማድረግ አይርሱ።
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share @buraast
የፍቅር ታሪክ❣
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
👉#እሷን ተዋት👈 {bura}
════❁✿❁ ══════
ስትወዳት ካልወደደችህ
ስትቀርባት ካልቀረበችህ
ስትጠጋት ካልተጠጋችህ
ስለፍቅር ካላወጋችህ
እሷን ተዋት
💚💚💚💚💚
አትሆንህም እሷን ተዋት
አትድከም ላታገኛት
ማፍቀርህን እያወቀች
በፍቅራችሁ ካልፀደቀች
እሷን ተዋት
💚💚💚💚💚
በቃልህ ላይ ካላመነች
ጥርጣሬ ከሰፈነ
በመውደድህ እየኮራች
የውሸት ፍቅር ከምሰራ
ልብህ ይቁረጥ እሷን ተዋት
ላንተ ላይሆን አትወትውት
እሷን ተዋት
💚💚💚💚💚💚
#burati123✍✍
@burati123
@buraast
🌸🌼🌸🌼🌸🌼🌸🌼🌸🌼
ፈሪ ነህ ስትዪኝ ፣ እልህ ተጋብቼ
ደፋር እንደሆንኩኝ ፣ ላሳይሽ ጓጉቼ
አንቺን ደስ እንዲልሽ
ታጣቂ ፌደራል ፣ ሰደብኩኝ ጠርቼ፡፡
ከዛስ ነው ያልሽኝ
ከዛማ በኀላ ...
ጀግና አፍቃሪነቴን ፣ ታሪክ አይረሳውም
መድፈሬን ነው እንጂ
ሌላ ምን እንደሆንኩ ፣ አላስታውሰውም፡፡
፡፡፡፡፡፡፡
(እዚች ጋር ሶስት የሚስቁ ስቲከሮች ☞ ኢኝ ኢኝ ኢኝ )
@buraast
Telegram channel members
Instagram followers
Bonus: Free members for your channel by invitation of your friends
By touching the below link, Increase your channel members... Start now!
/channel/bulkservicebot?start=566819165