bookshelf13 | Неотсортированное

Telegram-канал bookshelf13 - ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

19873

"ስለመጻሕፍት ከመጻሕፍት መንደር እንዘምራለን!"

Подписаться на канал

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

አዳም፦ ዘመኑ መሰረታዊ ከሚባሉት ( Foundational ) ጥያቄ ይበልጥ ወደ ተግባራዊ (Pragmatic ) ጥያቄ ያደላል ወይም ሽግግር እያደረገ ነው ። ስግር ስትሰራ ስድራት (Assemblege )የሚባል ሃሳብ አለ ...

የሆኑ ንጥረ ነገሮች(Elements ) ተሰባስበው የሚሰሯቸው የተወሰኑ ገጸ ባህርያት አሉ የተያያዙ ... ከዛ ውስጥ አንዱን ንጥረ ነገር ብታወጣ ያ' ንጥረ ነገር (Element) ተጠግተህ ብታየው ከብዙ ንጥረ ነገር (Elements ) የተሰራ ነው ። የስድራት(Assembledge ) መርህን ለየት የሚያደረገው እዛ ንጥረ ነገር ውስጥ መርበብት (Network ) አለ ፤ ስላልደረሰንበት ነው ። ማለትም በቁስ ጥናት (Object Studies )ውስጥ ብዙ ፈላስፎች እንደሚሉት አንድ ቁስ (Object ) ሙሉ ለሙሉ ራሱን አይሰጥም ...

አንድን ቁስ (Object ) ሙሉ ለሙሉ ማወቅ አንችልም። ሁልጊዜም አምቆ (retain ) የሚይዘው ፣ ውስጡ የማንደርስበት ስሪት አለ ....በሂደት ልንደርስበት እንችላለን። ስለዚህ መሰረታዊ ሃሳብ (foundational idea ) መገንባት አለብህ፣ መፍጠር አለብህ ።

እኔ የማደርገው ነገር ምንድን ነው ? አዲስ አለም መፍጠር ከፈለግክ በትይይዝ አለማት ውስጥ አዳዲስ የትይይዝ መስመሮችን መፍጠር አለብህ ፤ እንግዳ ትይይዞችን ሳይቀር መፍጠር ያስፈልጋል (if you want to create a new world create other connections, strange connections ) ። ያ' ንጥረ ነገር (Element) ስፍራው ሲለቅ (deterritorialize ) አድርጎ ሌላ መኖሪያ (Village ) ውስጥ ስትከተው ወይም አምጥተህ ሌላ ቦታ ስትተክለው አዲስ እመርታ ( Emergent ) ባህሪ ታገኛለህ ።

ልክ እንደ ኬሚካል ፕሮሰስ ለምሳሌ ውሃ (H2O ) ብንወስድ የውህዱን ኢነርጂ በማስወጣት (Exotermic energy ) አንዱን ኦክስጂን ወስደህ ከሌላ ንጥረ ነገር (Element ) ጋር ለምሳሌ ከካርቦን ጋር መልሰህ ታዋህደዋለህ (Indotermic energy )... ከዛም ካርቦንዳይ ኦክሳይድ (CO2 ) ማግኘት ትችላለህ ። ልክ እንደዛው ለልብ ወለድም ይሰራል....

የሆነ ገጸ ባህርይን በሆነ ባልተነካ ጎኑ ሌላ እሳቤ ውስጥ ትከተዋለህ ... እዚህ ጋር አባት ሆኖ ቢሆን እዛ አስተማሪ ይሆናል ፣ ስለዚህ በት/ቤት ስድራት ( assemblage ) አስተማሪ ይሆናል ፤ በቤተሰብ ስድራት ( assemblage ) አባት ይሆናል ።

ተለምዷዊ በሆነው ነገር ውስጥ ግን ሰውየውን አንድ ገጸ ባህርይ ይሰ'ጠውና ያበቃል። ልብ ወለድ ከሆነ የአባት ገጸ ባህርይ ሰጥቶ ይጨርሰዋል ። ሕጽናዊነት የሚያደርገው በስድራት (assemblage) ውስጥ የተለያዩ ግንኙነቶችን መፍጠር ነው ።

ተሻለ፦ Hypertextuality, Interrelation,Medium, Intermediary የሚባሉ ሃሳቦች አሉ ... አንድን ድርሰት ልዩ የሚያደረገው ከነበረበት ሚዲየም( Medium ) ወጥቶ በሌላ ሚዲየም ( Medium ) ውስጥ መነበብ ሲችል ነው ይላሉ የዘርፉ አጥኚዎች ፤ እንደዛ መነበብ የሚችል ከሆነ ታላቅ ስራ ነው ያስብለዋል(the attributes of ultimate novel) ፤ ደረጃውም እጅግ የላቀ ይሆናል ።

አዳም ፦ በሞዳሊቲ (Modality ) ማለትም በሞድ (Mode ) ለውጥ ውስጥ መገለጥ ወይም ህልውናው ማስቀጠል መቻል አለበት ።

ተሻለ፦ ለምሳሌ ሰላማዊት ከማህሌት ወደ የሰንብት ቀለማት ስትመጣ አንድ ሰው ትራንስቴክስቹዋሊቲ (transtextuality ) ነው ቢልና ሌላው ስፍራን መልቀቅ (deterritorialization) ነው ቢል ሁለቱም ልክ ይሆናሉ፤ ይሄ ምናልባት ምትሃት ይጠይቃል። ምክንያቱም ስራዎችህ ጥንታዊነትን ወደ ዘላለማዊነት የማሻገር አቅም ይሰጣቸዋል ፤ በመሆኑም ገጸባህርያቶችን ዘላለማዊነትን ያወርሳቸዋል የሚል እምነት አለኝ ....

አዳም፦ It’s all chain beings liberated ….I feel more...የመከፈት ነገር ይሰማኛል ። ወሰን የለሽ በሆነ መልኩ ስፍራቸውን የመልቀቅ (infinitely deterritorialize ) እና እንደገና የመስፈር ( infinitely reterritorialize ) ሰፊ እድል ስላላቸው እንደዛ ይመስለኛል።

ሀብቱ ፦ ሐበሻ የሚያደርግህ አንዱ ዘላለማዊነትን ለመውረስ ያለህ መሻት ነው ቢባል እውነት ነው?

አዳም፦ በል አጋባው ሃሃሃ ...

ገዛኸኝ፦ የዚህን ቤት ኬክ ሳትቀምሰው ልትሄድ ነው ?

አዳም፦ አክስቱን ባቅላቫን በላኋት እኮ ሃሃሃ ....

ሀብቱ፦ ሽንኮሬን?

አዳም፦ ሽንኮሬን አዎ! ሁለችንም ሳቅን ...

ስንብት ፦
በጨዋታና በሳቅ ተሞልተን ሳናውቀው ጊዜው አለቀብን። ከካፌው ወጥተን ጋዜቦ አደባባይ ላይ ቋሚ ምስክር ለማስቀረት አብረነው ፎቶ ተነሳን። ሐብቱም አንዴ በቀኙ በኩል ፎቶ አንሱኝ አለ። ለምን በቀኙ? ቀኝ እጁን እኔ ቀድሜ እንዳሰገርኩት ሐብቱ አልጠረጠረምና እነሱ እየተነሱ እኔ ፈገግ አልኩ!

ጨዋታ አዋቂው ሰው ለመለያየት ቻው ስንባባል እንኳ ጨዋታውን አላቋረጠምና ሐብቱን “ቀጣይ ስመጣ ፀጉርህ አፍሮ አድርገህ እንዳገኝህ ሃሃ” ብሎ ተረበው" አንተ ወጣት ኾነህ የምትመጣልን ከኾነ" መለሰ ሐብቱ፤ ቢቻል ቢቻል ለዘላለም በወጣትነቱ የሚያጸኑት ሰው ነው— አዳም።

እንዲህ እንዲህ ተሳስቀን ወደ ቤቴል የሚወስደው የራይድ ታክሲ ውስጥ አሰገብተን ተሰናበትነው፤ ጊዜያዊ ስንብት። በርግጥ ግን ስንብት ነው? እሱን መሰናበት ይቻላል? ቤታችን፣ ልባችንና አእምሯችን ውስጥ ላይጠፉ የተሳሉ ሐሳቦቹ፣ተረኮቹ፣ ፍልስፍናዎቹ፣ ሐርነት አውጭ ፈጠራዎቹ የት ሄደው ተሰናበት ነው እንለዋለን?
አሁንስ መዝሙረ ሄላም እየጠበቅን አይደለምን ?
Adam Reta , Habtu Girma Fetaw , ገዛኸኝ ድሪባ
ፎቶ ከማህሌት ተሾመ ገፅ የተወሰደ (አመስግንሻለሁ )

© Tashale Kebede Bedriya

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ተሻለ፦ ይሄን የእሳቤ ለውጥ (paradigm shift) እንዴት አገኘኸው? ሁሉም ሐበሻ ትዕቢቱን አፍንጫው ስር፣ ንግስናውን በልቡ ይዞ የሚኖር ነው ፤ የዕድል ቀኑን ጠባቂ ነው። እኔም ብሆን ሌላው እድሉን ብናገኝ ገራፊዎች ነን። ታዲያ አንተ እንዴት በተለየ መንገድ ሄድክ ? ከሃገር መውጣትህ ነው ? ወይስ ሌላ ተሞክሮ አለህ ?

አዳም፦ ዓለም ሰፊ ነው። ሕጽናዊነት ከዚህ ጋር የሚገናኝም ነው። ብዙ ነገር አናውቅም ፣ ብዙ ነገር አላውቅም ። ላስቅህና ምን ያህል አላዋቂ እንደሆንኩኝ እንኳን አላውቅም ( Even I don’t know how much I’m ignorant ) ሃሃሃ ....
ስለዚህ እንዴት ነው የምታውቀው? የነገሮችን መያያዝ ትረዳለህ ... ሁለት ነገሮች ተወደደም ተጠላም በግንኙነት ህግ ውስጥ ነው የሚኖሩት (this thing and that thing they have a certain connection ) እንደዛ ነው ህልውናቸው ሚያስቀጥሉት .... ደንቆሮዎች ናቸው ግን በግንኙነት እምቃት (Potential ) ነው ህልውናቸው ሚቀጥለው ... ይሄን በአግባቡ መገንዘብ ያስፈልጋል።
ለምሳሌ ይሄንን መፅሐፍ ስንት ቀን ይዘኸው ዞርክ? ብልህ አታውቅም ... ስንት ገፅ እንዳለው ብጠይቅህ ላታውቅ ትችላለህ ... ይሄንን አንብበኸዋል? ( ብለርቡን ማለቱ ነው)...ስንት ቃላት አሉት? ብልህ አታውቅም ... ህይወትም እንደዛ ነው .... እናም ይሄንን መረዳት ያስፈልጋል።
መፃፍ ስጀምር ነገሮችን አላውቅም ከሚል ነው የምነሳው ... ስለዚህ የመፃፍ ድርጊት ራሱ የመማር ድርጊት ነው ። መረዳት እና አንዳንዴም የአንባቢዎችን ነገር መከተል ....እናም በአራዳ ቋንቋ አለማካበድ ነው ሃሃሃ ...

ገዛኸኝ፦ ብዙ ጊዜ በድርሰትህ ውስጥ ከእውነታው ዓለም ጋር የሚገጥሙ ታሪኮችን እናገኛለን። የአስተማስሎና የልዋጭ (Metaphor ) ሀሳቦች እንዴት ነው ከታሪክ ድርሳናት እና ከሀቀኝነት (authenticity ) ጋር የሚዋሃዱት (sync ) የሚሆኑት ?

አዳም፦ በእውቀት ውስጥ ሁለት ዓይነት ክፍፍል አለ ፤ ስነ ጥበብና ሳይንስ ... እነዚህ ሁለቱ የተያያዙ ናቸው ለማለት ነው። በግርጌ ማስታወሻ ሃያሲ ጠቅላላ ይቀርባል ... ሃያሲው ሳይንሳዊ ነገሮችን ይበረብራል ፣ መረጃ ይሰበስባል ፣ ይተነትናል ወዘተ ። ዋናው ክፍል ደግሞ ሕይወት ነው፤ ስለዚህ ሁለቱንም በአንድ ላይ የማቅረብ እንዲሁም የማገናኘትም ነው ፤ የስነ ጥበብ እና የሳይንስ መጎዳኘት ነው ( The integration of art and science ) ።

ገዛኸኝ፦ ታክሲ ውስጥ ስንገባ ሹፌሩ መንጃ ፈቃድ ይኑረው አይኑረው አናውቅም ። ይናደድ አይናደድ አናውቅም በቃ ዝም ብለን እንገባለን ...

አዳም፦ መፃፍም ልክ እንደዛ ነው። በሂደት ነው የሚዳብረው፤ የተሳሳተውን ከዛ በኋላ ታቀናለህ ፣ ታርማለህ።

ተሻለ፦ የአንተ ስራዎች ግን ይሁነኝ ተብለው የሚሰሩ ናቸው። እንደውም አብዛኛዎቹ ስራዎችህ ፕሮጀክቶችም ናቸው ብል እውነት ነው ፤ ደግሞም ልክም ነኝ። በፅንስ ሀሳብ ደረጃ ብዙ ማለት ቢቻልም ....እንጀራ ( ሞዴል ብቻ አይደለም ) ፣ ሕጽናዊነት (ፍልስፍና ብቻ አይደለም ) ፣ ታሪክም ሆነ አብዮት ( የአንድ ወቅት ክስተት ወይም ሁነት አድርጐ የመተረክ ጉዳይ ብቻ አይደለም ) ፣ ማህበረሰብ (የአስተማስሎ ጉዳይ ብቻ አይደለም ) ፣ ፖለቲካ ( ትችት ብቻ አይደለም) ወዘተ ... በመሆኑም ደራሲው በደንብ አቅዶ እንደሚሰራ ግልፅ ነው ....

አዳም ፦ ሕጽናዊነት ግራጫ ቃጭሎች ላይ ያለው መግቢያ ንድፈ ሃሳባዊ (theoretical ) ይመስላል ግን የጠራ አይደለም ( Vague ) ነው ...

ተሻለ፦ ይቅርታ አቋረጥኩህ ... እኔ መግቢያውን ብቻ አይደለም ያየሁት ፣ በተለያዩ ስራዎችህ ውስጥ በድግግሞሽ የተሰራበት እሳቤ ነው ። አሁን ሕጽናዊነት በደንብ ተገንብቷል ፣ በሚገባ አድጓል ማለት ይቻላል ። ለዚህ ማሳያ እቴሜቴ ሎሚ ሽታ ነው። በሕጽናዊነት ግንባታው እጅግ የተዋጣለት ብሉይ ስራ ነው።

የአንተን ሕጽናዊነት ከፍሬንቾቹ ድህረ መዋቅራዊያን (Post Structuralist ) ከሆኑት ጁሊያ ክሪስቴቫ ፣ ሮላንድ ባርቴዝ ፣ ዣክ ዴሪዳ እንዲሁም በመዋቅራዊ (Structuralist ) እሳቤ ውስጥ ሕጽናዊነትን ካበለፀገው ዤራርድ ዤኔት በእጅጉ የተለየ ነው ። ከፈረንሳይ ስንወጣ ደግሞ ሩሲያዊው ፈላስፋና የስነ ጽሑፍ ሊቁ ሚኻኤል ሚኻይሎቪች ባክኽቲን (Mikhail Mikhailovich Bakhtin ) እሳቤ የተለየ ነው።

እስካሁን ባለኝ ንባብ አንተ በገነባኸውና በስራህበት መልኩ የተጠቀመበት ማንም የለም ። በመሆኑም የአንተ ፍልስፍና አዎንታዊነትና ውጤታማነትን በማካተቱ ፍልስፍናዊ እሳቤው በእጅጉ ጠቃሚ ነው ( Your "Hitsinawinet " is incredably Positive and Productive ) ። በመሆኑም በአንድ በኩል ለማህበረሰባችን ፍኖትን የሚሰጥ ሲሆን በሌላ በኩል ካየነው ደግሞ ለፖለቲካችን ሐርነት አዋላጅ ( The cradle of public politics )አድርጌ ነው የማስበው። ልፋትህ እጅን በአፍ የሚያስጭን ነው ፤ ሲበዛ ይደንቀኛል ። በዚህ ልክ ይቻላል እንዴ?

አዳም፦ መሰረት ያስፈልግሃል አይደል? የሆነ የምትቆምበት ነገር ያስፈልጋል፤ አለበለዚያ ነገሩ ሁሉ ይበታተናል። ግን ዝም ብሎ ይሄ ነው መነሻዬ ለማለት ሳይሆን በአግባቡ የተጠና እና በዕውቀት የለውጥ ሂደት ( knowledge Dynamics ) ውስጥ የሚገለጥ መሆን አለበት ። እንጂ ተራ የመቅዳት ጉዳይ ከሆነ ከጥቅሙ ጉዳቱ ይበልጣል ፤ ደመ ነፍሳዊ ሃሳብ ( Zombie Concept ) የማራባት ጉዳይ ይሆናል ።

ተሻለ፦ ከዚህ ወደ አውሮፓ ስትሄድ የነበረውን ማህበረሰብ ሆላንድ እያለህ ከነበረው ፣ አሁን ደግሞ ካናዳ ካለው ማህበረሰብ አንፃር የእኛን ማህበረሰብ እንዴት ታየዋለህ ? አሁን እኛ የቆምንበት በንፅፅር ምን ይመስላል ? አማራጭ ማህበረሰብ (Alternative society) የመፍጠር እቅድ አለህ ?

አዳም ፦ ስራዎቼ አማራጭ ሚቶሎጂን ይፈጥራሉ ... ሁሉም ተረክ ሚት እኮ ነው (Every story is a myth )። የስፋትና የጥልቀት ጉዳይ ነው። ግን አሁን ያለው በጣም ውስን ( Localized ) ነው ፤ ግለሰባዊ ነው ። በሰፊው ለመጠቀም የሃገራችንም ሁኔታ ወሳኝነት ይኖረዋል ። የፖለቲካ አቅማችን ፣ የኢኮኖሚ አቅማችን ፣ የዲስኮርስ አቅማችን፣ የእውቀት ነፃነታችን ነው ከዚህ አውጥቶ ለዓለም የሚያሰራጨው። አየህ እንደ አሜሪካ ምናምን አቅም ቢኖረን ኖሮ ከ “ ኢዮር “ የመጣን ነን ልንል እንችላለን ። ጉራ ለመንፋት እንኳ አቅም ይጠይቃል ሃሃሃ ...

ሀብቱ፦ አዳምሻ ጨዋታ ለምን ይማርክሃል? ስትኖርም፣ ስትጽፍም ለምን ለተረክ ስትል ተሸነፍክ? ለምን ዋነኛ መገልገያ መሳሪያህ (instrument )ሆነህ?

አዳም፦ የምትኖረው ነው። ሁሉም ነገር ተረክ ነው (Everything is a story ) ። ዋናተኛ መዋኘት አለበት፤ ሯጩም መሮጥ አለበት፤ ጸሐፊው መጻፍ አለበት ሃሃሃ... ተረክ የምናብ ጉዳይ ነው ፤ ያ ደግሞ በጣም አስፈላጊ ነው።

ገዛኸኝ፦ አካልህ ይጠብኻል?

አዳም፦ ምናልባት ሊሆን ይችላል ። ቆዳዬ በጣም መለጠጥ አለበት ፤ ወይም እፈልግ ይሆናል ሃሃሃ...

ሀብቱ፦ ሙዚቃ ወይም አልበም የምትወደው? ... መቼም " ዞራ ዞራ የእኔ ነች " የሚለውን አላደመጥክም ... መፅሃፍስ ?

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ሐመልማሉ አዳም !☘️
**

ቀጠሮ አለን፤ ከሥነ- ጹሑፍ ጠቢቡ አዳም ረታ ጋር ፤ ቀኑ ማክሰኞ ኅዳር 24 /2017 ዓ.ም ነው ። ከባቢው ብርሐን ለብሷል። አዳም ጥቁር ሹራብና ከስክሰ ጫማ አድርጓል ። የሆሊውድ አክተር የምታስመስለውን ጥቁር መነጽሩን ጠረጴዛ ላይ አስቀምጧታል። እንደደረስን ከመልካም ፊቱ ላይ ፈገግታ ደርቦ ተነስቶ በእቅፍ ተቀበለን። ባየሁት ቁጥር በመጽሐፉ “ አውራጃ የሚሸፍን ትከሻ…” ያለውን ያስታውሰኛል። አዳም ባለሰፊ ትከሻ ነው፤ ሲያቅፍም ሞላ አድርጎ ነው።

“ ምን ትፈልጋለህ?” ለሚለው ግብዣችን፤ የአዳም መልስ “ባቅላቫ ” የሚል ነበር ። ታዲያ ለምን መስቀል ፍላወር ወደሚገኘው ኮንዲቶራይ አንሄድም በሚለው ተስማምተን ታየም ኮፊን ትተን ወጣን ፤ መስቀል ፍላወር አካባቢ ኮንዲቶራይ የተባለ ኬክ ቤት ውስጥ ተሰየምን ። እኛ ሶስት ጎረምሶች ኬክ ፣ አዳም ደግሞ ባቅላቫ እየበላን ጨዋታው ተጀመረ።በቀኙ በኩል ተቀምጬ በዓይኑ በኩል ያየኋት ነፍሱ እንደ ጥር ስማይ ንፁህ ነበረች ።

ታዋቂው ፈረንሳያዊ ደራሲ ቪክቶር ሁጎ ስለ ሌላኛው የሀገሩ ልጅ የ20ኛው ክፍለ ዘመን ተደናቂ ደራሲ ሆኖሬ ዲ ባልዛክን ለመግለፅ የተቀመጠበትን ነገረ ሃሳብ ወደ እዚህ ልሳብና ላምጣው፦
“He is the historian of the heart, the anatomist of society, the poet of ambition and despair.”

አዳም ለእኛ ከባልዛክም በላይ ነው ። የልባችን ቁስል ወይም የነፍሳችን ስቃይ ተራኪ ብቻ አይደለም፣ ከዛችው ስቃያችንና ቁስላችን ህይወትን እንደ አዲስ ይፈጥራል። የተስፋችን ሞት ከብስባሹ አውጥቶ በረቂቅ ስነ-ጥበባዊ ብርሃን ጭለማውን ገፎ ወደ ሕይወት የሚያሻግራት ልዕለ-ሰብ ነው። በአዳም ድርሰት ውስጥ ሕይወት የሌለው ነገር ምን አለ? መንገዱ ፣ አቧራው ፣ የመንገዱ መብራት ፣ ድንጋዩ ፣ እንጨቱ ፣ ህንፃው ፣ ቤቱ ፣ ምግቡ ... ሁሉም ሕይወት አለው። አዳም የሕይወት ደራሲ ነው። ለዚህም ነው ሕይወት ላይ የገነነ ውና የተሾመው። የአዳም ስራዎች ግባቸውን በቀለም ይወከሉ ከተባለ ሐመልማል አረንጓዴ ነው ፤ የሕይወት ቀለም ነውና ።

አዳም የዘመናችን ተጋዳሊ ነው ። የስነ-ጽሑፍ ማዕምሩ ቴዎድሮስ ገብሬ ስለ ሐዲስ ሚቶሎጂ (ዘመናዊ ተጋዳሊ ) ሲያትት “ ... የሐዲስ ሚቶሎጂ ዓቢይ ጉዳይ የግለሰቡ ልቡና እና ዩኒቨርሳዊ ቁርኝት ነውና ለነባሮቹ (ለብሉይ ሚቶሎጂ ) 'ፍፁማን' እውቅና አይሰጥም ። እንደ ብሔርተኝነት ፣ ጎሰኝነት ፣ መልክአ ምድራዊ ውሱንነት ያሉ ጽንስ ሐሳቦች በሁለንታዊ ፣ ዓለም አቀፋዊ ባሕሎች መረታት አለባቸው ብሎ ያምናል" ይላል ( በይነ ዲሲፕሊናዊ የሥነ ጽሑፍ ንባብ ፥ 94- 95 ) ።

በዚህም ምክንያት አዳም " የሃሳብ ማዕከል " እንዲሆን እፈልጋለሁ ። ለምን ? ቢያንስ ቢያንስ በሶስት ማዕከላዊና አንገብጋቢ ጉዳዮች ምክንያት፦
አንደኛ የወል እሳቤያችን ነፍስያ ከአዳም የብዕር ምጥ ስለምትከፈል ፤ ሁለተኛ ህዝባዊ ፖለቲካችን በአዳም የስነ- ጽሑፍ ፍልስፍና ሐርነቱን (Emanicipation ) ስለሚጎናፀፍ ፤ ሶስተኛ ማህበረሰባዊ ውጥንቅጣችን በትስስር ፍኖት በአዳም ሰራሽ ሕጽናዊነት ህልውናውንና ድኅነቱን ስለሚያገኝ ነው ።

ይህን የተመረጠ ውይይት እናንተ ጋር ለማድረስ የመረጥኩት ዘዴ እንደ ወረደ ባደረግነው የውይይት ቅርጽ ነው። ለየት ቢልባችሁ ሕግ የተከተለ ቃለ መጠይቅ ሳይሆን ለመጨዋወት በተገናኙ አራት ሰዎች መሐል የተደረገ ውይይት መሰል ጨዋታ በመሆኑ ነው። ውይይታችንን የግል ምልከታ አድርጌ ላለመፃፍ የወሰንኩበት ምክንያት ደራሲውን በእኔ አተያይ እንዳይቀነበብና አንባቢዎችም የደራሲው ምላሽ በየራሳቸው መንገድ እንዲረዱትና ለአተረጓጎምም ክፍት ለማድረግ በማሰብ ነው።

በተረፈ ግን ቀስ ተብሎ እየተብላላ፤ ከተቻለም ምን ማለቱ ነው? ተብሎ እየተጠና ቢነበብ እጅግ ፍሬያማ ነገር ይወጣዋል ብዬ አምናለሁ ። በውይይቱ ላይ የተሳተፍነው—እኔ ፣ ጋዜጠኛ ሐብቱ ግርማና የቴአትር ባለሙያ የሆነው ገዛኸኝ ድሪባ ነበርን።
አዳም ጨዋታችን ለአንባቢ እንዲደርስ መልካም ፍቃድህ በመሆኑ በቅድሚያ በአንባቢዎቻችን ስም ከልብ አመሰግናለሁ።

ሀብቱ:- አዳምሻ አራታችንን የሚያስማማ ተረት እንዴት መስራት እንችላለን ?
እሱን ለመስራት ነው መታገል ያለብን ብዬ ነው ማስበው ። "ፍትሃ ነገስቱን" የሚቀበል አለ ፤ "ብሔር ብሔረሰቦችን " የሚቀበል አለ ፤ "መሃል ሰፋሪም " አለ። ስለዚህ አዲስ ታሪክ መፍጠር ያስፈልገናል በተጨማሪም ለህልውናችን አዲስ መዋቅር መፍጠርም ግድ ይለናል (so we need to make a new story and new structure for our existence ) ። ምን ይሰማሃል በዚህ ጉዳይ ?

አዳም :- አቅጄ አልነሳም ፣ ይሄን ልስራ ያንን በማለት አይመጣም ! ልብ ወለድ ስፅፍ ይሄን ተረክ (story ) ልፃፍ ብዬ አልቀመጥም ። የሆነ ተረክ አለ እሱን ትተርካለህ ። አቅደህ አትፅፍም ፤ ዝም ብዬ ሰኖር ተረክ ያጋጥመኛል እፅፋለሁ ። እንጂ እንዲህ ማድረግ አለብኝ ብዬ አልዘረዝርም ። ያ' ሌላ መንገድ ነው ፤ የእኔ አይደለም ። እኔ በስፖንታኒየስ (Spontaneous ) በኩል ነኝ። የሆነ የተያያዙ ተረኮች ይገጥሙኛል እነሱን እሰራለሁ ። ጠዋት ተነስቼ ድርሰት ልፃፍ አልልም ፤ተነስቼ ወንበሬ ላይ አልቀመጥም ፤ ልፅፍም እችላለሁ ፣ ቶሎ ልነሳም እችላለሁ፣ ወይም ላዛግ እችላለሁ አላውቅም ሃሃሃ ....
የስነ ጥበብ ተረካ (Art narrative ) እና የፖለቲካ ተረካ (political narrative )የተለያዩ ናቸው። የጋራ ነገር ሊኖራቸው ይችላል።

ተሻለ፦ በዚህ ዘመን ስነ ጥበብ ራሱ ፖለቲካ አይደለም ?
አዳም፦ ሁሉም ነገር ፖለቲካ ነው ። ንድፈ ሀሳብ (theory ) እና ፍካሬ ግን የየራሳቸው ባህሪ አላቸው ። ግን እንዴት ነው የተወከሉት የሚለው ጉዳይ ነው ወሳኙ ፤ እንጂ ሁሉም ቦታ ፖለቲካ አለ። ምድር ላይ ስትኖር ተረካ (Narrative ) ውስጥ ሁሉም ነገር አለ ። አየር ፣ሳይንስ ፣ ሃይማኖት ብቻ ሁሉም ነገር አለ ።
.... እዛ ውስጥ በማርያም ሚምል አለ፤ ከሶሰት ሺህ ዓመት በፊት ግን አልነበረም ወዘተ ...
ሀብቱ፦ አሁን እንኳን በራሱ ሚምል ነው ያለው ሃሃሃ ..

አዳም፦ ጥያቄህን ግን መልሼልሃለሁ?
ሀብቱ፦ መልስህን ሳይሆን መንፈስህን ነው የፈለግኩት፤ ደርሶኛል ቆንጆ ነው...
ልክ አሁን እንዳለንበት የሚያደክም ዘመን .... ማለትም የዛሬ 40 ዓመት የተከሰተ ነገር እንደገና ሲከሰት ይደክማል ሰልችት ይላል ። አንዳንድ ቀን መውጪያ ቀዳዳ ይጠፋል። እንደው መውጫ የሚሆን አንተ ያየኸው መንገድ ይኖር ይሆን ፤ የ ታዘብከው ? ....ጥሩ የምታሰብበት የሚመስለኝ የአብዮቱን መንገድ የምታውቀው ነው። እኛ ከአብዮቱም የባሰ የቀውስ መንገድ ላይ ስላለን በወል እንደዚህ አይነት ዘመንን እንዴት ነው መሸከም ያለብን? እንዴት ነው ጎበዝ መሆን ያለብን? እንደ ግለሰብም እንደ ማህበረሰብም ?

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ፋሺዝም ላይ የተደረጋውን ዘመቻ በድል ለመወጣት በርካታ ሥሜት ቀስቃሽ የፕሮፓጋንዳ ሥራ ተሠርቷል። በዚህ መጽሐፍ ዋናው የፕሮፓጋንዳ መሣሪያ የመምህሩ ንግግር (lecture) ይመስለኛል። መምህሩ ስለ ቅኝ ግዛትና ስለፋሺዝም የሚያደርጉት ንግግር ከባለመሲንቆዎች ዘፈን፣ ከተለያዩ ፉከራና ሽለላዎች፣ ሌሎችም ወኔ ቀስቃሽና ቆስቋሽ ክስተቶች ጋር ተዳምረው ዘማቹን ያተጉታል። ይህ ዓይነቱ ፕሮፓጋንዳ ጤነኛና ከፍ ያለ ዓላማ ያለው ነው።

ፖለቲከኞች፣ የገበያ ሰዎችና ተንኮለኞች የሰውን ልጅ በፕሮፓጋንዳ ለክፉ ዓላማ ሊጠመዝዙት ይችላሉ። የሰው ልጅ እንዴት ቡድናዊ እንደሚሆንና ፕሮፓጋንዳ እንደ marionette እንደሚወዘወዝ የሚያስታው ጉዳይ ነው። ለሥራ ጉዳይ በተለያዩ የደቡብ አፍሪካ ክፎሎች በተዘዋወርኩ ጊዜ ፖለቲከኞችና የገበያ ሰዎች የዋኆቹን ሰዎች በፕሮፓጋንዳ እንዴት በቀላሉ እንደሚጠመዝዟቸው እና የcrowd mentality ውስጥ እንደሚከቷቸው አይቻለሁ። አይተናል። በእኛም ሀገር ተመሣሣይ ነገር ነው።

“እፋረደዋለሁ አልለቀው በዋዛ
ከምድር ላይ ሲያጠፋ የሰውን ልጅ ለዛ” የሚል ሥነቃል አለ።

በዚህ መጽሐፍ በፕሮፓጋንዳ ይሁን ወይ በባሕል ምክንያት የሰው ልጅ ለዛውን ሲያጣና በቀልን እንደ ወግ ቆጥሮ ሲንቀሳቀስ ይታያል። መጽሐፉ ገጽ 77 ላይ እንዲህ ያለውን crowd mentality ይመስለኛል የሚያስቀምጠው፤ “ጌታ ከሁሉ በላይ ወጣቶቹ በአንድ ቋንቋ የሚናገሩ፣ በአንድ ጭንቅላት የሚያስቡ፣ በአንድ አንደበት የሚናገሩ፣ በአንድ የልብ ትርታ የሚንቀሳቀሱ መሰሉት።”

ከዚህ አንጻር ሕዝባችን ፖለቲከኞች እንዳረጉት ነው ወይ የሚወዘወዘው፤ እንደጠመዘዙት ነው ወይ የሚጠመዘዘው!? የሚል ጥያቄን ያጭራል። በውጪ ጠላት ላይ በወገንም ላይ ሲያነሣሱት መቀበል ነው ወይ?! እንዲህ ያለው ጉዳይ የፕሮፕጋንዳን ኃይል እንድናጠይቅ ያደርጋል። የውጪውን ከውስጡ፣ ትክክለኛውን cause ከእኩዩ መለያው ምንድነው? መዳኛው የት ነው? የሚለው አሳሳቢ ጉዳይ ይመስለኛል።

Bounded Solidarity and Social cohesion:

Why Nations Fail የሚል መጽሐፍ ኢትዮጵያ ውስጥ በፊውዳል አገዛዝ ጊዜ የተፈጠሩ extractive እና exclusive ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማት መኖራቸውን ያብራራል። ኢትዮጵያ ቅኝ ባትገዛም እነዚህ ተቋማት ለድኽነት መንሰራፋት የራሳቸውን ሚና መጫወታቸውን ይተነትናል። ከዚህ በተቃራኒ የባሕል ወረራ አለመኖሩ የሕዝቡን ሥነልቦና የጠበቀና የተፈጥሮ ነጻነቱን ያቆየ ይመስላል። ከዚህ አንጻር የፋሺዝም መገለጫ ናቸው የተባሉት እብሪት፣ ትምክህት፣ ንቀትና፣ ትዕቢት በሀገር ውስጥም በተለያዩ ማኅበረሰቦች መካከል ይስተዋላሉ። የዓድዋ ዘመቻ የውጪውን ጠላት ድል ካማድረግ ባሻገር ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ማኅበረሰቦችን ርስበርስ ያስተዋወቀ፣ ያቀራረበና በደም ያቆራኘ መሆኑ በመጽሐፉ ተመልክቷል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የተፈጠረብኝ ጥያቄ ዘመቻው የውስጡን በደልና ንቀት ከመቅረፍ ወይም ከመፈወስ አንጻር ምን ያህል ሚና ነበረው? የሚል ነው። መተዋወቅና መረዳዳቱን እንዳመጣ ግልጽ ነው። መከባበርና መኳኳኑንስ? ወይስ ተጽዕኖው ዘመን ተሻጋሪ አይደለም?

ሌሎችም ጥቂት ጉዳዮች ነበሩኝ። እንዳይበዛ ብዬ ተውኳቸው።

ማጠቃለያ - የከፍታ ጉዳይ፤ ከማማ በሰማይ እስከ ተድባብ

ሕይወት ከማማ በሰማይ (ተምኔታዊ ሶሻሊዝም) አንሥታ እስከ ተድባብ ድረስ የከፍታ ነገር የሚመስጣት ትመስላለች። Mine to Win ወይም ኀሠሣ በሚለው መጽሐፉ ዐወቀ አንዴ ከተፈጠረ በኋላ የሕይወት ከፍታ ላይ ለመድረስ የራሱ ጥረትና ኃላፊነት መሆኑን በአጎቱ በኩል በቅኔ መስላ ታቀርባለች። ዐወቀ የቅኔ ሊቅ የሆነውን አጎቱን፤ “በርትቼ ተምሬ አንድ ቀን የቅኔ መምህር ነው እምኾን። …ልክ እንዳንተ” ስል አረጋገጥኹለት ይላል። በዚያች ቅጽበት፥ እዚያች ቦታ ላይ የቅኔ መምህር የመሆን ሐሳብ በልቡ ውስጥ ያብባል።

“ቅኔ ግን ከባድ ትምህርት ነው ሲባል ሰምቻለኹ” ስል ጨምሬ ተናገርኹ። ይላል
አጎቱ፤ “ቅኔ፥ በሕይወት እንደሚገጥምኽ እንደማንኛውም ነገር፥ የትጋትና የኀሠሣ ሽልማት ነች”

ዐወቀ፤ “ተተጋኹ እምሸለማት?”

አጎቱ፤ “አዎን የልፋትህ አዝመራ፥ ፍሬ ፃማ፥ ሽልማትኽ ናት። ገና ስትፀነስ በሕየወት ዘመንኽ ትልቅ ቦታ የመድረስ ምርጫ ተመነሻውም የተሰጠኽ መኾኑን ተገንዘብ። ፈጣሪ ሕይወትን ሰጥቶኻል፥ ሕይወትኽን ደርዝ እምታስይዘው ግን አንተ ነህ። ቢያንስ መሞከር አለብኽ። ወኔ ማለት መለወጥ እምትችለውን ነገር መለወጥ መቻል ነው።

በቀጣይ ምንትዋብ መጽሐፍ ደግሞ በአንድ ሰዓሊ በኩል የቤተክርስቲያን ሥዕሎች ሲሣሉ የሚታለፍባቸውን ሒደቶችና ሥዕል ለመሣል ሠዓሊው የሚያደርገውን ጽናት ትተርካለች። ጾምና ጸሎቱ፣ ንጽሕናውና ትጋቱ ነው ከፍታ ላይ አስቀምጦት ልዑል የሆነ ሥዕል ለመሣል የሚያበቃው። እንደቅኔው ሁሉ።

በዚህኛው (ተድባብ) መጽሐፍ ደግሞ የዓድዋ ድል የድሎች ክምችት፣ የጋራ ከፍታ፣ የወል ማማ ሲሆን እያንዳንዳቸው በየዘርፋቸውና በየሙያቸው ከፍታ ላይ የሚደርሱበትን ሒደት ታሳያለች። ይመር በመሲንቆ፣ ነሞ በፈረስ ግልቢያና በጦር ውርወራ፣ ጌታ በጠመንጃ ተኩስ፣ ሌሎችም በየሙያቸውና በየዘርፋቸው። ይህ ይመስለኛል ዓድዋን የወል ከፍታ፣ የድል ክምችት - ተድባብ የሚያደርገው።

© መንገደኛ መንገደኛ

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ተድባብ

ተድባብን ሳነብ የታወሱኝን ወይም የተረዳኋቸውን ጥቂት ነጥቦችን ለማጋራት (reflect ለማድረግ) ያህል ነው። ዳሰሳ ወይም ግምገማ ለማድረግ ሙያዬም፣ ንባቤም፣ ልምዴም አይፈቅድልኝም። የተወሰኑት ነጥቦች ለእኔ ዐዲስ የሆኑብኝ ወይም በተለየ መልኩ የተረዳኋቸው ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ተጨማሪ ዕውቀትን ወይም እይታን ሰጥተውኛል። አንዳንዶቹ ጉዳዮች ከመጽሐፉ ጋር በቀጥታ ላይገናኙ ይችላል።

ባይተዋርነት

ዐዲስ ከሆኑብኝ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ባይተዋርነት ነው። በመጽሐፉ ከሚጠቀሱት ውስጥ ጌታ የሚባለው ገጸባሕሪ (ያሳደጉት አክስቱ ወሮ እልፍነሽ ባወጡለት ስም፤ ደም-መላሽ) ተወልዶ ያደገባት ቀዬው እንዲሁም የአካባቢው ማኅበረሰብ ድንገት እንግዳ ይሆኑበታል። ግራ ይጋባል። ይህ የሚሆነው ደግሞ ታስሮ ቆይቶ ሲፈታ ወይም ሌላ ባሕልና ቦታ ውስጥ ከርሞ ወደመንደሩ ጠለል ሲመለስ አይደለም። የኖረበት፣ ያደገበት፣ የቆየበት ባሕልና አካባቢ ድንገት ሲገለጥለት ነው እንጂ። ታስረው የተፈቱ፣ ወደሌላ ባሕልና አካባቢ የሚጓዙ፣ ወይም ከሌላ ባሕልና አካባቢ ወደመንደራቸው የሚመለሱ ሰዎች ለብዙ ነገር እንግዳ ይሆናሉ ወይም ብዙ ጉዳይ እንግዳ ይሆንባቸዋል። ጌታ ወይም ደመላሽ ግን የገዛ መንደሩ ጠለል እንግዳ የምትሆንበት ነውሯ ሲገለጥ ነው። በደልን እንደወግ ቆጥሮ የሚኖር ማኅበሰብ ውስጥ መኖሩ ይዘገንነዋል!

ይህን ነጥብ ከለጠጥነው ለብዙ ጊዜ ይዘነው የኖርነውን አመለካከት ወይም እውነት እንዲሁም የተቀበልናቸውን የማኅበረሰብ እሴትቶች አንዳች ነገር መጥቶ ሲገልጣቸው ወይም ሲያናውጣቸው ዙሪያ ገባችን እንግዳ ሊሆንብን ይችላል። ያ አመለካከት በአስተዳደግ፣ በትምህርት፣ በሚዲያና በፕሮፓጋዳ ጭንቅላታችን ውስጥ ያኖርነው እውነት ሊሆን ይችላል። ይህ ዓይነቱ ነባር ግንዛቤና አረዳድ (ሥነምግባር፣ ጨዋነትና ታማኝነት፤ ወይም አጠቃላይ የመንደራችን ወይም የሀገራችን image) በጉዞ፣ በትምህርትና በጥናት ሲገለጥ ወይም እንደጦርነት ሥልጣንና ጥቅም ባሉ ሌሎች ክስተቶች ሲናጥ፣ ሲሞገትና ሲፈተን (shock ሲደረግ) ብዙ ነገር እንግዳ ይሆንብናል። ቀዬውም ሰዉም ሀገሩም ይለወጥብና።

በሀገራችን እየሆኑ ካሉ ጉዳዮች አንዱ ይህ ዓይነቱ መናጥና መገለጥ ይመስለኛል። ጦርንነት፣ ጥቅም ወይ ሥልጣን መጥቶ ሲንጠን ሀገሩ መንደሩ ሕዝቡ እንደዚህ ነው እንዴ?! ይኼ ሰውዬ፣ ይክች ሰው እንዲህ ናቸው እንዴ?! ከዚህም ሲብስ፣ እኔ እንደዚህ ነኝ ለካ?! የሚል ራስለራስ strange መሆን። እንደዚህ ሆኖባችሁ ያውቃል?

ዘመቻ፤ Travel in reverse

በመጽሐፉ የሚነሣው የዘመቻ ጉዳይ ዐዲስ እይታን አጭሮብኛል። ዘመቻው ከጦር ሜዳ ድል፣ ማለትም በፋሺዝም (ንቀት፣ ትምክህት፣ እብሪት፣ ትዕቢት) ላይ ካደረገው ድል ባሻገር፣ የመጓዝን ያህል የአንድ ሀገር ሰዎችን ያቀራርባል። አንድ ሰው ከተወለደበት ወይም ካደገበት አካባቢና ባሕል ወደሌሎች አካባቢዎች ሲጓዝ ስለዚያኛው አካባቢ፣ ባሕልና ማኅበረሰብ ብዙ ነገር ይማራል። አመለካከቱንም ያስተካክላል። በዓድዋ ዘመቻ፣ ደግሞ ሰዎች ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ወደ ዓድዋ ነው የዘመቱት። ይህም ዘመቻውን travel in reverse ያደርገዋል። በዚህ ሂደት ዘመቻው በቅጡ የማይተዋወቁ የአንድ ሀገር ሰዎችን ሲያገናኝ፣ ሲያስተዋውቅ፣ ሲያቀራርብ ይስተዋላል። አንዱ የሌላውን ወገን ቋንቋ፣ ምግብ፣ አልባሳት፣ ጭፈራና ውዝዋዜ፣ ፉከራና ሽለላ፣ መልክዐ-ምድርና የአየር ንብረት፣ ወዘተ ለማየት ለመረዳትና ለማጣጣም ዕድሉን ፈጥሯል። ይህን በተመለከተ ጌታ፣ “በዕድሜው አይቷቸው የማያውቃቸውን የሀገሩን ሰዎች እንግዳ ባሕላቸውን አይቶና ሰምቶ ‘ለካስ ይኽም አለ?!’ እያለ ዐዲሱን የኑሮ ዘይቤ ለመላመድ እየጣረ…” ይላል መጽሐፉ። ውሎ ሲያድር አንዱ ባሕል ሌላኛውን እያነቃቃ አንድ ላይ ሲጓዙም ይታያል፤ “እነዚህን ሰምተዋቸው የማያውቋቸው የሙዚቃ መሣሪያዎች፣ ዜማዎችና ጭፈራዎች ከሩቅ ሲጣሩ፣ ጆሯቸውን ሲያቀኑ ጉልበት ያገኛሉ…” በስተመጨረሻ ዘመቻ ላይ የተገናኙ ሰዎች በትዳር ይጣመራሉ።

ዘማቾች በዘመቻው ሂደት ውስጥ የአመለካከት ለውት ሲያደርጉና የተሻለ ግንዛቤ ሲኖራቸውም ይስተዋላል። አብዛኛው ዘማች የክተት ዐዋጁን ተቀብሎ የወጣው ዙፋኑን (ዐልጋውን) ለማጽናት እና ሃይማኖቱን ለመጠበቅ ነበር። በዘመቻው ወቅት ስለፋሺዝምና ቅኝግዛት በአንድ መምህር በኩል በሚደረግ አስተማሪና ሥሜት ቀስቃሽ ንግግር (lecture) እንዲሁም በሌሎች መስተጋብሮች ጉዳዩ ዐልጋ ከማጽናትና ሃይማኖትን ከመጠበቅ ባሻገር መሆኑን ይረዳል። የግል ነጻነትን፣ ክብርን፣ ማንነትን፣ ሀብትና ንብረትን ማስከበር መሆኑ ሲዘልቀው የጣልያኖች ዓለማና አስተሳሰብን እንቆቅልሽ ይሆንበታል። ውሎ ሲያድር፣ ሥሜት ቀስቃሹ የመምህሩ ንግግር ከተለያዩ አካባቢዎች ሙዚቃና ሽለላዎች፣ ቀረርቶዎችና ውዝዋዜዎች እንዲሁም ዘማቹ ለዐልጋውና ለሃይማቶቹ ካለው ክብርና ለነጻነት ካለው ተፈጥሯዊ ፍላጎት ጋር ሲደማመር በእያንዳንዳቸው ላይ የወኔ እሣት ይለኩሳል። መቀሌንም የሥሜት ገበታ ያደርጋታል።

ዘመቻው የውስጡን ቅራኔና በደል ማለዘቢያም ሆኖ ይታያል። በመጽሐፉ ከተጠቀሱ ገጸባሕርያት ውስጥ አብዛኞቹ በተለያየ መልኩ የውስጥ መናቅ፣ መገለል ወይም በደል የደረሰባቸው ናቸው። ከዚህ አንጻር ዘመቻው ከተለያዩ ልማዳዊ ድርጊቶችና የማኅበረሰብ አምባገነናዊነት ለመላቀቅ ዕድሉን የፈጠረላቸው ይመስላል። የርስበርስ ጥላቻና ቅራኔውን ሁሉ የሚያስንቅ የፋሺዝም ንቀትና አመለካከት ነው። የአንድ ሀገር ሰዎች ከፍ ላለ ዓላማ በዘመቻው ሲገናኙ የውስጥ ቅራኔዎችና ጭቆናዎች ይለዝባሉ። ጌታ በአክስቱ ወይዘሮ እልፍነሽ በደል ተቆጥቶ ይቅር አልልም ሲል፣ አባቱ “ግድ የለም አሁን ስለተቆጣህ ነው። ይህን ሁሉ የሚያስንቅ የመጣ ቀን ማንም ሳይጠይቅህ ይቅር ትላለህ” ይሉታል። በደሉን የሚያስንቀው ቀን የሚመጣው በጣልያን ወረራ፣ በፋሺዝም ንቀት ወቅት ነው።

የውስጡን ጭቆና ቅራኔና በደል ከማለዘብም ባሻገር ቁጭቱን፣ ብሶቱን በደሉን የፋሺስት ጦር ላይ ሲወጣበት የሚታይ ይመስላል። ባለማሲንቆው ይመር የፋሽስት ጣልያንን ንቀትና ዓላማ ሲረዳ፣ “ጮማ አስቆርጠው፣ ጠጅ አጠጥተው፣ ቡልኮና ጊደር ሸልመው ሰውነቱን ሲነጥቁት የተቆጨውን ሁሉ እንድ አዲስ ውስጡ ይገነፍላል።” ቀጥተኛ ግንኙነት ባይኖረውም የኋለኛው ጉዳይ አንድ ናይጄሪያዊ ቦክሰኛን ያስታውሰኛል። ናይጄሪያዊው የኦሎምፒክ ተጋጣሚውን፣ በመጀመሪያው ቡጢ ይዘርረዋል። የድሉን ምስጢር ሲጠየቅ ለናይጄሪያ መንግስት ያለኝን ንዴትና ብሶት ነው የተወጣሁበት ይላል።

ይበልጥ የወደድኩት የዘመቻው የጎንዮሽ ውጤት በግለሰብ ደረጃ የሚያመጣውን የአመለካከት ለውጥ ነው። ዘመቻው ባለማሲንቆው ይመርን የግል የስኬት አክሊልን ለመጎናጽፍ እንዲሁም ለራስ ያለውን የበዛ አመለካከትን ለመቀየርም ዕድል ፈጥሮለታል። ከዘመቻው በፊት ይመር ራሱን የዓለም፣ የሕይወትና የነገሮች ሁሉ ማዕከል አድርጎ ነበር የሚመለከተው። የሚኖረውና የሚያልመው በዘመቻው ወቅት የሚንሰፈሰፈውም ከንጉሡ ዘንድ ቀርቦ ችሎታቸውን በማሳየት የግል ዝናና ክብርን መላበስ፣ አክሊል መድፋት፣ ማማ ላይ መውጣት ነበር። በድሉ ዋቅጂራ እንዳለው በራስ መውደድ አዴ ከበሮ ደንቁሮ ነበር። ለዚህ ዓይነት ምኞት የዳረገው በአካባቢው የደረሰበት ንቀትና መገለል ቢሆንም ዘመቻው ሕይወት ሌላ ትርጉም እንዳላት በማሳየት ከዚህ ሕመሙ ይፈውሰዋል። ከሀገሩ ጋር ሲሰናኝና ራሱን የትልቁ ዓላማ አንድ ሰበዝ፣ የድሉ አንድ አካል ሆኖ ሲያገኘው ለመጀመሪያ ጊዜ ራሱን

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ግጥሞቹ በባህሪያቸው እሳታዊ ውበት ፣ እሳታዊ ናፍቆታዊ ምስሎችንና መሰል ድምፆችን ያዘሉ ሲሆኑ የአንባቢውን ልብ ላይ ያለውን ተመሳሳይ ስሜታዊ ሻማ ለመለኮስ ያለመ ይመስላል።
በሚስቲሲዝሙ አለም እሳት ብዙውን ጊዜ እንደተለዋዋጭ ኃይል ይታያል። የመንፃትን ሂደት ቆሻሻዎችን ( ያደፉ የሀላፊ ጊዜ ማንነታዊ ጥላዎችን ) በማቃጠል እና እንደገና ማደስ እንዲሁም ዳግመ ውልደት መፈከሪያ አንዱ መንገድ ነው።

( ፊኒክስ በእሳት ወላፈኑ እርር ብላ ራሷን ዳግመኛ እንደምትወልደውም እንደማለት..! )

እሳት ነፍስን ለማንፃት በአምልኮ ስርዓቶች ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል።

ሕይወት ድጋሚ
በዓይኖችሽ ውስጥ እንድትወልደኝ
እፈልጋለሁ።
አፍ አፉን ቢስሙት የማይጠግቡት ፍቅር
ሆኜ
መወለድ እፈልጋለሁ ።

( ገፅ 99 )

እሳት የመለኮት መገኘት አንዱ መንገድ ሆኖም ይቀርባል ለምሳሌ ያህል በክርስትናው አውድ በሙሴ ታሪክ ውስጥ የሚቃጠለው ቁጥቋጦ የእግዚአብሔርን መገኘት ሲያመለክት በሂንዱ የእምነት ዳራ ደግሞ የእሳት አምላክ በሰዎችና በመለኮታዊው አካል መካከል አስታራቂ ተደርጎ ይቆጠራል። ከዚህም ባሻገር እሳት የእውቀትና የመገለጥ ምልክት ፣ የጥፋትና የትርምስ ፣ የመንፈሳዊ መነቃቃት ተምሳሌትና በግለሰብ አውድ ውስጥ እንደፍቅር ፣ ከፍተኛ ፍላጎትና ኃይለኛ ስሜቶችን ሊወክል ይችላል።እሳት በብዙ መተርጎም መተንተን የሚችል ግዙፍ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነው። ለዚህ ይሆን ቴዎድሮስ በአንድ ግጥሙ እንዲህ የሚለን

ወደ እሳት ሲጠሩህ ክንፎችህን ዘርጋ
ልቦናህን ከፍተህ አይኖችህን ዝጋ ፥

ቅለበዉ ጠጠሩን ፥
የወንጭፉን ሩሕ ፥
" እንሂድ " በላቸዉ ፥ ለስቃይ ሲጠሩህ ፥

ታገለዉ ወጀቡን ፥
ግፋዉ ማዕበሉን ፥
ዝለቀዉ አፀዱን ፥
ተቀበለዉ ስሙን ፥

[ የሰዉ ልጅነቱን ]

ዉደደዉ ሙላቱን ፥
ዉደደዉ ጉድለቱን ፥
አፍቅረዉ ጥመቱን ፥
አፍቅረዉ ቅናቱን ፥
የአካል እንግልቱን
[የሰዉልጅነቱን ]

( ተናገር ለሁሉም
ሰው ከልብሱ በታች ፍም እሳት መኾኑን! )
( ከገፅ 76-77 )

ናፍቆት

"Nostalgia is a form of suffering."
Milan Kundera:
ሩህሩህነት አምጦ የወለዳቸው የአሁንም ሆኑ የሀላፊ ጊዜ የህይወት ውልብታዎች በናፍቆት ስም የቆሙበት በራፍ መፅሀፉን እፁብ ለማድረግ ምስጠት ከሰጡ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው። ናፍቆት በስስ ዝማሬ የተደረሰባቸው ንዝረታዊ እሳታዊ መታመቆች ስለናፍቆት መጮህ ብቻም ሳይሆን በእምባ መሬት ላይ አስቁመው ህመምን የሚያስናፍቁ ናቸው። መሻታቸው ተፈጥሮ ፣ ስክነት ፣ ዝምታና ሌላም ሌላም ነገር ቢሆን የታሰሩበት ገመድ ግን ናፍቆት ነው። ስጥም ያለ ደስ የሚሉ ልጃገረድ ስንኞች ውስጥ ፈገግ ያለ ህይወት....

ዛሬ ሌሊት
ሕልም አየሁ፡፡
:
የሚጣፍጥ ወይነ-ጠጅ አፌን ሲሞላው፤
ከአፌ ወይነ-ጠጅ ሲፈልቅ
የወይን ፍሬ ሁኜ ፤
በቀጭን አረንጓዴ ሐረግ ላይ ተንጠልጥዬ ፤
ቀረፋ የተሞላ ንፋስ ሲያወዛውዘኝ
መብሰል ቆዳዬን አሳብጦት
ልፈነዳ ... ቅብትት ብዬ ... ቀልቼ ፤
( ገፅ 95 )

ዝምታ

ዝምታ አንዳንድ ግጥሞቹ በዝምታ እንደሚፈስሱ ፀባየኛ ወንዞች ይመስላሉ። ጉልበታቸው ርጋታ ሆኖ አገኛቸዋለሁ። ልስላሴ ውስጥ እንደተገኘ ኩልል ያለ መፍሰስ አንዱ የዚህ መፅሀፍ ባህሪ ነው።
ከባህሪነቱም ባሻገር በህይወቲቱ ሌማት ላይ ተንጠራርቶ ከሚዘግናት እፍኞቹ ወይም በመኖሩ ከሚገደው ነገሮቹ መሀል የዝምታ ባንዲራ አንዱና ዋነኛው ነው።
በሚወዳቸው ትዝታማ ሌቶቹ ውስጥ የሚወለዱ አጋጣሚዎቹ ዝም ያሉ ይምሰሉ እንጂ እሱ ተውሶ የሚሰጠን የትርጓሜ አሀድ ከመርቀቅ አይዛነፍም።
ግጥሞቹም ሆነ ስንኞቹ ውስጥ ያደረው ሰው ( ገጣሚው ) ዝምታ ወዳድነቱ ከስክነታዊ አፍታዎች ጋር አዛምዶታል የሚል መደምደሚያ አለኝ።
ያም የጥሩ framework ስራን በመፅሀፉ ውስጥ እናገኛለን።
ሌላው የተሰበሩ ዜማዎች ወጀብ መፅሀፉን ከስሜት ቅለት አንፃር ሊያደክሙት እንደሚችሉ ባምንም የዛን ያህል ጨለማ የጎላባቸው እንዳልሆኑ ግን መስክር ቢሉኝ ዓይኔን አላሽም። መሳጭነቱ ላይ የተዘሩት እነዚያ ፊደላት እሳታማ ናቸው። በውሃ የሚጠፉ ሳይሆኑ በእምባ ተግ የሚሉ አይነት ወደረኞች...!
ሰመመን ያጫራቸው ግልፍተኛ ቁጭቶችም በጊዜ በዘመንና በህይወቲቱ ላይ ጥርሳቸውን ነክሰው ከእንግዲህ አልወድቅም የሚሉበት ታዛ በራሱ የጥንካሬ መንፈስን ናፋቂነትና ቅናት የሚያሳድሩ ናቸው።
በዚህም ገጣሚው የተመስጥኦ ፍጆታዎቹ ብዬ ከብዙ በጥቂቱ ከለቀምኳቸው ጉዳዮቹ ውስጥ ዝምታ አንደኛው ሲሆን ለኪነ ጥበብም ሆነ ለመኖር ብስለት በርግጥም በዝምታ ውስጥ የታሸች መንደር ህይወት ናት።

ማኅሌታዊነት

የዱር አበባ ጥዑማዊ የሌት ትዝታዎች ፣ የሌት ዝማሬዎች የአበባ ገላቸውን የበተኑበት አይነት ሜዳ ነች።
ማህሌታዊ አቋቋሟ ልጅነት ነው። ውበት ነው። ስስነት ነው።
« ጠበሏ አፋፍ በጨረቃ.. » እንዳለው ፀጋዬ የዱር አበባንም በሌት አምባ የሚያስወጣት ብዙ መዝሙሮች ፣ ብዙ መናፈቆች ፣ ብዙ ትዝታዎች አሏት።
ናፍቆት የወለደው ትኩስና ገር ፍቅር ፣ በርጋታ የታሸው ከበቢ ውስጥ እየተትጎለጎለ የሚወጣው የዝምታ እጣን ፣ ካሸለቡ ግዑዝ ተፈጥሮ ጋር በነፃነት በደስታ መስከርና ሌላም ሌላም የሌት ማኅሌቶቹ ውስጥ የሚታዩ ድምፀቶች ናቸው።
ከርዕሶቹ ጀምሮ ብንነሳ
- የሌሊት ሹክሹክታ
- የሌት ወራጅ ሀሳብ 1 , 2 , 3
- የአንድ ምሽት ሀሳብ
የሚሉ እና ብዛት ያላቸው ሌሊት አወዳሽ ስንኞች በመፅሀፉ ውስጥ በብዛት ይታያሉ።
በዚህም ግጥሞቹ ማኅሌት የቆሙ ኮከቦች ይመስላሉ። መቋሚያ ፅናፅሉ ናፍቆት ሲሆን እሳት እሳት የሚሉ አበባማ ስንኞች ውስጥ ወዙን እንደሉባንጃ እየበተነ ማሂጠንቱን ይቋጥራል።
« እንደከርቤ ውብ ጉም
እንደሎሚ ሽታ
አበባ እንዳየ ንብ
እኔ እወድሻለሁ... » ( ገ/ክርስቶስ ደስታ )
እንደመውጫ አበባ በስነ ዓለማዊ አተያይ ( cosmological outlook ) በመነሳት እንመልከትና ላብቃ፦
ልክ እንደ እሳት ሁሉ አበባ በ cosmological point of view ( የስነ ዓለም አተያይና ትርጓሜ ) ውስጥ በርካታ ፍቺዎችን ያዘለ ነው።

ስነ ህይወታዊ ዝግመተ ለውጥን በተመለከተ አበቦች ( የአበባ ተክሎች ) የመራቢያ አወቃቀሮች ሲሆኑ በዝግመተ ለውጥ ሂደት ውስጥ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይነገራል። የመራቢያና የጄኔቲክ ልዩነትን በማመቻቸት የአበባ ብናኞችን ይስባሉ። ይህ የህይወት ትስስርንና በአፅናፈ ሰማይ ውስጥ ያለውን የዝግመተ ለውጥ እንዲሁም የመላመድ ሂደቶችን ሊያመለክት ይችላል።ይህንንም ተከትሎ የህይወት ኡደት እና ሽግግር ሌላኛው ምልከታ ሲሆን በዚህ ውስጥ አበቦች ብዙ ጊዜ ለአጭር ጊዜ የሚቆዩ ናቸው። ( ምናልባትም ይሄን ይሆን ህይወት የዱር አበባ ያለን? )
ይህ በአፅናፈ ሰማይ ውስጥ ላለው ጊዜያዊ ተፈጥሮ ተምሳሌታዊ አሀድ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል።

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ሚዛን አያነሱም። ዶክተር ምህረት ቃለመጠይቅ ሲሰጥ ንግግሩ ተሰምቶ አይጠገብም፤ አፉ ላይ ሃሳብ እንዳሻው ይታዘዝለታል። ብእር ሲጨብጥ ግን እንጃ! የትኛውም ደራሲ ልብወለድ ለመጻፍ ማለፍ የሚገባው የትምህርት ዝግጅት የለም። ድርሰት ከትምህርት ይልቅ በተፈጥሮ የሚገኝ ክህሎት ነው። ዶክተር ምህረት ተፈጥሯዊ የስነጽሁፍ ችሎታ ያለው አይመስለኝም። በእርግጥ ዶክተር ምህረት ራሱ አንዴ እንዲህ ብሎ ነበር፦ እኔ የምጽፈው ለማስተማር እንጂ ለመደነቅ አይደለም። እኔ በበኩሌ ዶክተር ምህረትን በንግግሩ ሁሌም አደንቀዋለሁ። ስነጽሁፍን ለማስተማር መጠቀም ከፈለገ ደግሞ ከልብወለድ ይልቅ በኢልብወለድ ቅርጽ ቢሞክር የበለጠ ውጤታማ እንደሚሆን ይሰማኛል። ወይም ደግሞ ማስተላለፍ የሚፈልጋቸውን ሃሳቦች ንግግሩን በጥያቄና መልስ መንገድ ወይም በሌክቸር ቅርጽ በድምጽ ቀድቶ ማሰራጨት። ደጋግሜ እንደምለው ዶክተር ምህረት የሃሳብ ሃብታም ነው። በሃሳብ እጥረት መቼም አይጠረጠርም። ነገር ግን ሃሳብ ያለው ሁሉ ድንገት ተነስቶ ልብወለድ መጻፍ ይችላል ማለት አይደለም። ዶክተር ምህረትን የምተቸው ምርጥ ሃሳቦቹን ለማስተላለፍ በመረጠው ቅርጽ ነው። ልብወለድ የዶክተር ምህረት ተሰጥኦ አይደለም። ስጋቴ ተገቢውን ቅርጽ ሳይመርጥ ቀርቶ ምርጥ ሃሳቦቹ ባክነው እንዳይቀሩ ነው።

በመጨረሻ ሁሌም ሲያወራ ለመሰማት የምጓጓለት አንድ ደራሲ ዳኛቸው ወርቁ ነው። ነገር ግን ዩትዩብ ላይ እንኳን አንድም የተቀረጸ የድምጽ ወይም የምስል ፋይል ማግኘት አልቻልኩም። ዳኛቸው ከብዙዎች የማይቀርብ ብቸኛ/loner እንደሆነ ሰምቼያለሁ። ነገር ግን ያረፈው በ1989 አካባቢ ይመስለኛል። ጭራሽ የመቅረጸ ድምጽ ቴክኖሎጂ በሌለበት ዘመን እንደኖረ ሁሉ አንድም ኦዲዮቪዥዋል ትዝታው አለመኖሩ ገርሞኛል። ስር የሰደደ የሚዲያ ጥላቻ ይኖረው ይሆን?!

© Te Di

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ምክንያቱም ወገን፣ በዩክሬይን ሠማይ ላይ የኔቶና የራሺያ ኒውክሊየሮች አንዳቸው በሌላኛቸው ላይ የተነጣጠሩበት ዓመት ላይ መሆናችን ትዝ ስለሚለን ነው፡፡ እርስበርስ እየተጨራረስን ያለን... በመካከላችን ጋኔን የነገሠብን ሕዝቦች የሆንንበት ዓመታችን ላይ መሆናችንንም ስለማንረሳ፡፡

ኢትዮጵያ የቃልኪዳኑ አገር ናት ብለን እናምናለን መቼም፡፡ በየቤተ ዕምነቱ ተጽፎላታል፡፡ ግን ያ ጨረር ሳያገኘን የቀረ አይመስለኝም!

የተረጨብን ጨረር (ካለ) አንድዬ የኢትዮጵያ አምላክ ከነጦሱና ኬሚካሉ ጨርሶ ያምክንልን! ያርክስልን! ከላያችን ላይ ይግፈፈው!

ደራሲዎቼን፣ (አንባቢዎችንም) ከልብ አመስግኜ...

አበቃሁ፡፡
መልካም ቀን! 🙏🏿❤️

© Assaf Hailu

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ግን የግራሃም ፊሊፕስ ትንተና ከግራሃም ሃንኮክ የሚለይበት መሠረታዊ ነገር አለ፡፡ ግራሃም ፊሊፕስ ያ ምድሪቱን የዛሬ 3ሺ500 ዓመት ገደማ የመታት ተወርዋሪ ‹‹ኮሜት››፣ ዓለምን አላጠፋትም፣ ምድሪቱን በቀጥታ አላገኛትም፣ ግን በትሮቶስፌር ላይ ነው የፈነዳው፣ ግን የለቀቃቸው ጨረሮችና መርዛማ ኬሚካሎች በምድሪቱ ላይ ከፍ ያለ ጥፋትን አስከትለዋል፡፡ የሥልጣኔንም አቅጣጫ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዳይመለስ አድርገው ቀይረዋል ይላል፡፡

ግን በምን መልኩ? – የሰዎችን ጭንቅላት ወደ ብጥብጥ፣ ወደ ጠብ፣ ወደ በቀል፣ ወደ መጨራረስ፣ ወደ መገዳደል፣ ወደ እርስ-በርስ መጠፋፋት የሚገፋ ‹‹ቬሶፕሬሲን›› የተባለ መርዛማ ኬሚካል በምድሪቱ ላይ በመርጨት!!

ምድሪቱ በዚያ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ1486 ዓመተ ዓለም ላይ በተፈጠረው የኮሜት (የጅራታም ከዋክብት) ፍንዳታ ቬሶፕሬሲን ከተረጨባት ወዲህ፣ የሰው ልጆች ወደ እርስበርስ መጫረስና ጦርነት ገብተዋል፡፡ ጦርሠራዊት መሥርተዋል፡፡ ዘመቻ ጀምረዋል፡፡ ተዋጊዎች በያገሩ ሥልጣን ላይ ወጥተዋል፡፡

በግራሃም ፊሊፕስ ትንታኔ መሠረት፣ የኮከቡ ፍንዳታ የፈጠረው ብናኝ፣ የሰውን ልጅ ገነት የመሰለ፣ እጅግ ሠላማዊ፣ እጅግ እንግዳ ተቀባይ፣ እጅግ መልካምነት የሰፈነበት፣ ከክፋቶች የራቀ የአኗኗር ዘይቤን የተከተለ የሥልጣኔ አቅጣጫ፣ ፍጹም አስደንጋጭና አስፈሪ ወደሆነ አግሬሲቭ ባህርይ በማሸጋገር፣ ምድሪቱን በራሷ በነዋሪዎቿ (ማለትም በሰው ልጆች እጅ) እንድትጠፋ ምክንያት ሆኗል - ነው የሚለን፡፡

ማስረጃዎቹንና ትንተናዎቹን ማጣጣል በጣም ይከብዳል በእውነቱ፡፡ በላቲን አሜሪካ የማያ ኮከብ ቆጣሪዎች፣ እና የጥንታዊ ግብጽ የአስትሮኖሚ ዘጋቢ ሳይንቲስቶች፣ እና በየሃምሳም ይሁን በየሰባ ዓመቱ - ካስፈለገ በየ500 ዓመት የሚመጡ የሠማይ ኮከቦችን ከነምስሎቻቸው መዝግበው ይይዙ የነበሩ የቻይና ስነፈለክ ተመራማሪዎች - ሶስቱም!!...

ሶስቱም እንዴት በተለያየ ንፍቀ-ዓለም ውስጥ እየኖሩ፣ ስለ ተመሣሣይ የሠማይ ኮከብ መውደቅና መታየት ክስተት፣ በተመሳሳይ ዓመት፣ በተመሳሳይ አኳኋን ጽፈውና መዝግበው ሊገኙ ይችላሉ? በፍጹም አጋጣሚ ሊሆን አይችልም! የሆነ ሁሉም ያዩት፣ የተከሰተ፣ ታላቅ መብረቃዊ የጥፋት ክስተት ነበረ! (ማለት ነው!)

እንዲያውም ግራሃም ፊሊፕስ የሚለን - ልክ ከዚህ የዛሬ 3ሺ500 ዓመት ከተከሰተው ኮከባዊ የጨረር ፍንዳታ በኋላ ነው - በዓለም የሚገኙ ህዝቦች ሁሉ የቀደሙ ሐይማኖቶቻቸውንና አማልክቶቻቸውን ሁሉ ቀይረው - በአንድ የፀሐይ አምላክ ማመን የጀመሩት፡፡ እና የፀሐይ አምላክ የሚል ቃልን መጠቀም የጀመሩት፡፡ ...

እና የፈጣሪን ሃሳብ፣ በክብ ዲስክ በሚመስል ቅርፅ ሥዕሎች መወከል የጀመሩት፡፡ ሞኖቴዪዝም በዓለም የመጣው፣ አተን (አተኒዝም) በግብጽ የመጣው፣ በሜሶፖታሚያ አሶር፣ በአፍጋኒስታንና ህንድ፣ በቻይና፣ በዓለም ሁሉ የተስፋፋው ከዚያ ዓለምን ከነቀነቀ ክስተት ጀምሮ ነው ይላል፡፡ ማስረጃዎቹ ሺህ ናቸው፡፡ ልክ እንደ ሃንኮክ አይደለ? ማስረጃዎች አያልቁበትም!!

ልክ ከዚያ የኮከብ ፍንዳታ በፊት በሠላም ይኖሩ የነበሩ፣ እና አንድም የጦር መሣሪያ ስለመሥራታቸው በአንድም ቁፋሮም ሆነ ታሪክ ያልተገኘላቸው እንግሊዞች፣ ልክ ከዚያ ጀንክቸር በኋላ ጦር አደራጅተው ወደ ወረራና ወደ እርስበርስ ውጊያ ነው የገቡት ይለናል፡፡

በቱርኮችና በሶርያኖች መካከል ለቀደሙት ሁለት ሺህ ዓመታት በፍጹም ሠላምና ጉርብትና የኖሩ ሕዝቦች (ሂታይቶችና ሚታኒያኖች)፣ ልክ ከዚያ የኮከብ ፍንዳታ በኋላ፣ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ልክ እንዳበደ ሰው ተነስተው መተራረድና መጋደል ነው የጀመሩት ይለናል፡፡ ብዙ ማስረጃዎችን እያጣቀሰ፡፡

ለቀደሙት ሶስት ሺኅ ዓመታት በብዙ ድርሳናትና ሥዕላዊ ቅርጾች ስለ ሠላማዊነታቸው ፍጹም የተመሰከረላቸው የአፍጋኒስታን አርያኖች፣ ያለምንም ቅድመሁኔታ፣ እና ያለምንም ምክንያት ተነስተው በቀጥታ ህንድን ነው የወረሩት ይለናል፡፡

የጥንቶቹ አርሜኒያዎች ‹‹ያዝ›› የሚሰኙ፣ ፍጹም ሰው-ወዳጅ፣ ማንኛውንም ህይወት ያለውን የተፈጥሮን ነገር ሁሉ የሚያከብሩና ነፍስን የማያጠፉ የነበሩ ህዝቦች፣ ልክ ከዚያ የኮሜት ፍንዳታ ዓመት በኋላ ባንድ ጀምበር ጦረኞችና ለመሞትም ለመግደልም የማያመነቱ (አቅም ይኑራቸውም፣ አይኑራቸውም፣ ልክ እንደ አጥፍቶ-ጠፊ) ሆነው ኢራኖቹን ወርረዋል፡፡ ፐርሺያኖች የምንላቸው በዚህ መሐል የተፈጠሩ የሁለቱ ዝንቅ ማንነቶች የፈጠሯቸው ናቸው፡፡

በቻይና ምድር ይሄ ኮሜት በዓለም ላይ ከመፈንዳቱ በፊት፣ በትንሹ ለአንድ ሺኅ አምስት መቶ ዓመታት በፍጹም ጨዋነትና ወንድማማችነት የኖረ የኤርሊቱ ህዝብ ሥልጣኔ፣ በአንዴ፣ በአንድ ጀምበር ወደ ፍጹም ነውጠኝነት ተቀይሮ አድሮ፣ የአካባቢውን ህዝቦች ሁሉ ወደ መውረርና ራሱን ወደ ኤርሊጋንግ ኢምፓየር ወደመቀየር ነው የገባው፡፡

በሰሜንና ሰሜን ምዕራብ አውሮፓ፣ በመካከለኛው አሜሪካ፣ በሰሜን አፍሪካ፣ በሜዲትራኒያን፣ በሌሎችም ሥፍራዎች የነበሩ ቀደምት ሥልጣኔዎች በሙሉ የነበራቸው ታሪክ ሁሉ የሚያሳየው ፍጹም ሠላማዊና ፍጹም ወንድማማችነትና መተሳሰብ የነገሠበት፣...

ሌላ ቀርቶ መንግሥት የሚባለው ነገር እንኳ አስፈልጓቸውና ጦር አደራጅተው የማያውቁ ህዝቦች እንደነበሩ ነው፡፡ ከዚያ ግን ልክ ከዚያ ከ1486 ዓ/ዓ በኋላ ሁሉም አንዱ አንዱን ወደማጥቃት፣ ወደ መሠልቀጥና ወደመጨራረስ ነው የገቡት፡፡

ግራሃም ፊሊፕስ እነዚህን ነገሮች ተርኮ አይጠግባቸውም፡፡ የቀደመውንና የመጣውን እያነፃፀረ ሲያስገርምህ አታምንም፡፡ እና ምንድነው የተከሰተው በዚያ ዓለምን በብልጭታው የሞላ፣ ምድሪቱን ያንቀጠቀጠ የኮከብ ፍንዳታ? ...

የሆነ ሰውን የሚያባላ ነገር ተፈጥሯል፡፡ የሆነ የሰውን የኤደን ገነት የመሠለ አኗኗር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዳይመለስ አድርጎ የበከለ አንድ የሆነ ሠይጣናዊ ነገር በሰዎች አዕምሮ ውስጥ ሠርጎ ገብቷል፡፡

ይሄን የእስራኤሎች ቅዱስ መጽሐፍ ሰይጣን ወይ እባብ ብሎ ሊሰይመው ይችላል፡፡ ሌላኛው ደሞ የፀሐይ አምላክ ተቆጥቶ በህዝቡ ላይ መዓቱን አወረደ ሊልህ ይችላል፡፡ ሌላው ደሞ አምላክ በህዝቡ ግልሙትናና ጣዖት አምልኮ ተቆጥቶ ዶጋ አመድ አደረገው ሊልህ ይችላል፡፡

ግን እነዚያ የፍንዳታ ጋማ ሬይስ... የብርሃን ፍንጣቂ ኮማዎች... ወይም እንደ ኒኩሊየር ፍንጣቂ ጨረሮች የመሰሉ ኬሚካላዊ ውሁዶች... .በእርግጠኝነት ሳያናይድ፣ ካርበንሞኖክሳይድ፣ መቴን፣ አሞኒያና ሌሎችንም መርዛማ ኬሚካሎች በጥቂቱ ወደ ምድሪቱ ፈንጥቀው ሊሆን ይችላል፡፡ በብዛት ቢሆን ኖሮ ሰው አይተርፍም ነበር፡፡

በውፍረቱ ሁለት ሜትር የሚሰፋ የኮከብ ስባሪ ምድሪቱን ከሁለት መቶ ሚሊዮን ኪሎሜትሮች ርቀት ላይ ተምዘግዝጎ ቢመታት፣ የሚፈጠረው ትልቅ ምድራዊ ዝቋላ እና የሄሮሺማን ፍንዳታ ሁለት ቢሊየን እጥፍ የሆነ ገሃነማዊ እቶነ እሳት ይሆን ነበር፡፡

ይህ ግን አልሆነም፡፡ የትም ቦታ ያ ዓይነት የፍንዳታ አሻራ ያረፈበት ክሬተር አልተገኘም፡፡ ስለዚህ የሆነው ልክ በ1908 በራሺያ ሳይቤሪያ ቱንግስካ እንደተከሰተው ነው ማለት ነው፡፡

በ1908 በቱንግስካ፣ ሳይቤሪያ ምን ተከሰተ? አንዲት በጣም ኢምንት መጠን ያላት የኮሜት ስባሪ ወደ ምድር ተምዘገዘገች፡፡ ግን የተወረወረችበት ማዕዘን፣ በቀጥታ ወደ መሬት እንድታርፍ አላደረጋትም፡፡ በጥቂት የእጥፋት ዲግሪ በቀጥታ ከመሬት ጋር መላተሟን ትታ፣ ከምድር በ30 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ሽቅብ በትሮፖስፌር ላይ ፈነዳች፡፡ እና ውጤቱ ምን ሆነ?

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ሕልም ጊዜው የሚያበቃበት ቀን አለው!
(Dream has an expiration date)
(እ.ብ.ይ.)

የሰው ልጅ በቀንም ሆነ በሌሊት ህልም ያልማል፡፡ የሌሊት ህልሙ ከፈቃዱ ውጪ የሚደረግ የቀን ህይወቱ ነፀብራቅ ነው፡፡ ሰው የቀን ፍርሃቱን፣ ጭንቀቱን፣ ሰቀቀኑን፣ ስጋቱን፣ ደስታውን፣ ምኞቱን፣ ፍላጎቱን በአዕምሮው መስታወትነት የሚመለከትበት ነው የሌሊት ህልሙ፡፡ በቀን የሚያልመው ህልሙ ግን አስቦበት፣ ተመራምሮበት፣ ዕውቀትና አቅሙን አገናዝቦ ለነገ የሚወጥንበት፤ ወደፊት የእኔ የህይወት መንገድ የሚሰምረው በዚህ ነው ብሎ የሚወስንበት፤ በገዛ ፍቃዱና ስልጣን የሚከውነው ነው፡፡ በርግጥ አንዳንድ ሰዎች ምኞታቸውንና ፍላጎታቸውን ብቻ ህልማቸው ያደርጉታል፡፡ ይሄ ህልማቸው በደንብ ያልታሰበ፣ ጥቅምና ጉዳቱ ያልታየ፣ በጊዜ ያልተቀነበበ፣ በዕቅድ ያልተከፋፈለ፣ በተግባር ያልተጀመረ ሊሆን ይችላል፡፡ የዚህ ዓይነቱ ህልም በጊዜ ብዛት የሚደበዝዝ የቀን ቅዠት ነው የሚሆነው፡፡

ብዙ ሰው ትልሙን ወይም ህልሙን በገዛ እጁ ያበላሻል፡፡ አንዳንዱ ህልሙን ሳይከውነው ይሸሸዋል፡፡ ጥቂቱ ጠንካራው ግን ከህልሙ ጋር ተጣብቆ የሚከፈለውን መስዋዕት ከፍሎ ያለመውን ይኖርበታል፡፡ ህልሙን ግብ አድርጎ በተግባር ሰርቶና ለውጦ የሚኖር ሰው በጣም ኢምንት ነው፡፡ የየብዙዎቻችንን ህልም የዕድሜ ጎርፍ ይወስደዋል፡፡ የምናልመውን በእጃችን ሳናደርግ ጊዜ ያመልጠናል፡፡ ስንቱ ህልም መቃብር በላው! ስንቱ ህልም ምኞት ብቻ ሆኖ ቀረ፡፡ የህልሙ መተግበሪያ ጊዜ በማለፉ ህልማችን ምኞት ብቻ ሆኖ ይቀራል፡፡ ህልም በጊዜው ሲፃፍ ግብ ይሆናል፡፡ ግቡን ስንከፋፍለው እቅድ ይሆናል፡፡ እቅዱን በተግባር ስንተገብረው ደግሞ ህልሙ ነፍስ ዘርቶ እውን ይሆናል፡፡ ለዚህ አይደል ጥበበኛው ሰለሞን በመፅሐፈ መክብብ፡- ‹‹ሕልም በስራ ብዛት ይታያል›› የሚለን፡፡ የሚሰሩ ሰዎች ያልማሉ፤ የሚያልሙ ሰዎች ይሰራሉ እንደማለት ነው፡፡ አልመህ ካልሰራህ ህልምህ ቅዠት ሆኖ ይቀራል፡፡ ህልምህን በሃሳብህ ብቻ ሳይሆን በዓይነ-ስጋህ ታየው ዘንድ ስራው፣ ተግብረው፡፡ ያን ጊዜ የቀን ህልምህን በስራህ ብዛት በአካል ታየዋለህ፡፡

ሰሞኑን በNetflix በእይታ ላይ የሚገኝ በዚሁ በያዝነው በ2024 የፈረንጆቹ ዓመት የተሰራ ‹‹Carry-on›› የሚባል አዲስ ወንጀል-ነክ (Thriller) ፊልም አለ፡፡ ይሄ ፊልም በትዕይንቱ የአንድ መዘዘኛ ሻንጣን ታሪክ ያስኮመኩመናል፡፡ ሻንጣው በውስጡ በአሻባሪዎች የተቀነባበረ ኖቫይቾክ (Novichok) የተባለ መርዛማ ሰው ገዳይ የኬሚካል መሳሪያን ይዟል፡፡ ፊልሙ ይሄን ሻንጣ በሎስአንጀለስ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ለማሳለፍ የሚደረግ ግብግብን ልብ እያንጠለጠለና እያስጨነቀ ያስመለክተናል፡፡ ሃሳቤ ሻንጣውን በተመለከተ አይደለም፡፡ ጉዳዬ በዚህ ኤርፖርት በሌላ ሰው የስራ መደብ የፍተሻ መሣሪያ (ኤክስሬይ ማሽን) ላይ ለሙከራ እንዲሰራ ተመድቦ መከራውን ያየ አንድ ገፀባህርይን በተመለከተ ነው፡፡ የዚህ ገፀባህርይ ስሙ ኤታን ኮፔክ ይባላል፡፡ ሰውየው የኤርፖርቱ የመንገደኞች የደህንነት ባለሙያ (TSA officer) ነው፡፡ ኤታን የብዙ ጊዜ ህልሙ ፖሊስ መሆን ነበር፡፡ ነገር ግን በተለያየ ምክንያት ህልሙን ሊያሳካ አልቻለም፡፡ የፍቅር ጓደኛው ኖራ ህልሙን እንዲከተል ሁልጊዜ ትወተውተዋለች፡፡ ኤታን በፊልሙ እንደሚታየው ባላሰበው አጋጣሚ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል፡፡ ያን መዘዘኛ ሻንጣ ሳይፈትሸ አይቶ እንዳላየ ሆኖ እንዲያሳልፈው የሚያስገድደው ወንጀለኛ ለምን ፖሊስ አካዳሚ መልሶ እንዳላመለከተ ሲጠይቀው ‹‹Dream has an expiration date (ህልም የዕድሜ ገደብ አለው)›› ብሎ የመለሰለት ንግግሩ ብዙዎቻችንን ሊያስተምር የሚችል ሃሳብ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ በርግጥ በፊልሙ መጨረሻ ኤታን የፖሊስ አባል ሆኖ ታይቷል፡፡

እውነት ነው! አይደለም ህልም ሰው ራሱ በጊዜ የተገደበ ነው፡፡ ህልምህን፣ ምኞትህን፣ ፍላጎትህን በእጅህ የምታደርገው ጊዜህን ባግባቡ ስትጠቀም ነው፡፡ በጉብዝናህ ወራት መስራት የሚገባህን ካልሰራህ ይመሽብሃል፡፡ በዕድሜ ምሽት መስራት አይመችም፡፡ አንደኛ አቅምህ ይዳከማል፤ ሁለተኛ ችግሮች ሲገጥሙህ እነሱን ለመፍታት አዳዲስ ሃሳቦችንና መንገዶችን በቶሎ አስቦ ለመወጠን ትቸገራለህ፡፡ አዎ ህልም ከጊዜ ጋር ነው የሚሄደው፡፡ መሆን የምትመኘውን አሁን ካልጀመርከው በኋላ ጣጣ ፈንጣጣው ብዙ ነው፡፡

ወዳጄ ሆይ.. ማርቲን ሉተር ኪንግ ‹‹ህልም አለኝ›› ብሎ ብቻ አልቀረም፡፡ ለህልሙ የሚከፈለውን ሁሉ ከፍሎ ህልሙን አሳክቷል፡፡ የእሱን ህልም ብቻ ሳይሆን የመላ ጥቁር አሜሪካውያንን የዘመናት ሸክም አቅልሎ የእኩልነት ነፃነትን አጎናፅፏቸዋል፡፡ አንተም ህልም ይኖርህ ዘንድ አስብ፡፡ የምትጨብጠውን አልም፤ የምታገኘውን ተመኝ፡፡ አንዳንድ ሰው የማይደርስበትን ያልማል፤ የማያገኘውን ይመኛል፡፡ ሊያሳኩት የሚችሉትን ህልም ማለም ታላቅ ብልሃት ነው፡፡ ህልምህም በጊዜ ብዛት እርጅቶ እንዳያደበዝዘው በቶሎ ጀምረው፡፡ ትልምህ ህልም-እልም እንዳይሆንብህ ነቅተህ ጠብቀው፡፡

ቸር ህልም!

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ይኑሩ!

____
© እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)
ሠኞ ታህሣሥ ፯ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም.

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ርዕስ :- ‹‹ለምንን ፍለጋ››( NR)
ደራሲ :- ቪክቶር ፍራንክል
ተርጓሚ:- ቴዎድሮስ አጥላው
ዘውግ :- ፍልስፍና/ሥነ ልቦና
Rating :- NR

መነሻ:- ድርሰትን መተርጎም የተለመደ እና የሚበረታታ ሲሆን፤ የትርጉም ሂደቱ ከዋናው መጻሕፍ ላይ ከቀጥታ ትርጉም (equivalent translation) ይልቅ በአገባብ/ በሁኔታ በመወሰን (contextual/ context-based translation) አንቀጽ-በአንቀጽ መተርጎም ይመከራል። ብሎም፣ የአንቀጾቹ ስብስብ (ወደ essay ከፍ ያሉ አንቀጾች) በessay መልክ ሲሆኑ የሚሰጡትን ትርጉም/ እንድምታ ማጤን ተገቢ ነው። ይህ ማለት አንቀጾቹ በessay ተጠቃለው/ተዋህደው የሚሰጡትን መልዕክት ከዋናው መጻሕፍ ፍሬ-ሀሳብ ጋር ማመሳከር አግባብ ነው እንደማለት ነው።

በትርጉም ሥራ ውስጥ፣ የመጀመሪያው (የዋናው) ድርሰት ማሕበረሰብ ታሪክ፣ ባሕል፣ ዕምነት… ወዘተ. የሚተረጎምለትን ሕዝብ ታሪክ፣ ባሕል፣ ዕምነት… ሊጫን፣ ወይም ሊጣረስ ይችላል። ስለሆነም፣ ለሕዝቡ/ለአንባቢው ባመቸ መልክ (ዋናው ሃሳብ ሳይሸራረፍ) እየተኩ መተርጎም ይመከራል። እዚህ ላይ፣ ‹‹ዘርህ እንደ ምድር አሸዋ ይብዛ›› የሚል የወንጌል ቃል፣ አሸዋ በሌለባቸው፣ በረዶ በመላባቸው አካባቢዎች ‹‹ዘርህ እንደ ምድር በረዶ ይብዛ›› ተብሎ ተተክቶ ተተርጉሞ አይተናል።
በአገራችን የተነበቡ የትርጉም ሥራዎች ከመጀመሪያው ድርሰት ላይ ትረካዎችን፣ ወይም የትረካ ክፍሎችን የመቆራረጥ/ የመሸራረፍ አባዜ ይታይባቸዋል። ይኼ ጉዳይ የድርሰቱን ሙሉ ሃሳብ እንዳንረዳው ያደርገናል። ለምሳሌ፣ ‹‹ፍቅር እስከ›› መቃብር ላይ የተተረከውን የሰብለንና የበዛብህን ውብ ጾታዊ መቧጠጥ/ንክኪ ቆርጠን ወደ ሌላ ቋንቋ ብንተረጉም የዚያ ቋንቋ ተናጋሪ የድርሰቱን ሙሉ ጭብጥ እንዳይረዳው ያደርጋል። የ‹‹ለምንን ፍለጋ›› በረከቶች:- "Man’s Search for Meaning": - ትርጉም ድርሰቱ በጀርመን ውስጥ የነበረ የእስር ቤት ታሪክ ሲሆን፣ ባለ ታሪኩ (ቪክቶር ፍራንክል - የአዕምሮ ሕክምና ዶክተር ናቸው) ከሌሎች ታሳሪዎች ጋር የነበራቸውን ቆይታ፣ ያሳለፉትን ፍዳ፣ ገጠመኞች…. ወዘተ. ያሠፈረበት ድርሰት ነው።

#ስግመንድ ፎሮይድ፣ ለአዕምሮ መታወክ መንሲኤው ከወሲብ ጋር በተገናኘ የሚከሰት ደስታ-ቢስነት ነው ይላል። ቪክቶር ፍራንክል ደግሞ፣ የአዕምሮ መታወክን ከፈቃድ ትርጉም (the will to meaning) ጋር ያያይዛል። ደራሲው ምንም እንኳን የግል የእስር ታሪኩን ቢያትትም፣ በዙሪያው የሚስተዋለውን የአዕምሮ ዝቅጠት (ለምሳሌ፣ በእስረኞቹ ዘንድ ሕይወትን ለማቆየት ሲባል ዝቅ ያሉ/ተራ የሆኑ ጉዳዮችን በማምሰልሰል፣ በማለም፤ ስለምግብና ስለመጠጥ አብዝቶ በመጨነቅ) የሚፈጠረውን የሥነ-ልቡና እና የሥነ-አዕምሮ ድቀት ፍቅረኛን በማለም፣ በጥበብ በመደሰት፣ የተፈጥሮ ጸጋን በማድነቅ፣ ጀንበርን/ብርሃንን በመናፈቅ፣ ውበትን በማድነቅ… ወዘተ. መቅረፍ እንደሚቻል ይገልጻል። ከአዕምሮ ዝቅጠት (mental regression) ለመላቀቅ (በአራዶች አባባል ‹ለመፋታት›) ፍቅር፣ ብርሃን፣ ውበት፣ ጥበብ፣ ተፈጥሮ… ወዘተ. አዎንታዊ ፋይዳ እንዳላቸው ተገልጿል።

የምሳሌያዊ አነጋገር፡- በትርጉም ሥራዎች ላይ ትኩረትን ከሚሹ ጉዳዮች አንዱ የምሳሌያዊ አነጋገር ነው። በድርሰት ውስጥ አንድን ሃሳብ፣ ወይም ትረካ በምሣሌያዊ አነጋገር፣ በዘይቤአዊ ንግግር፣ በፈሊጥ፣ በተረት… መግለጽ ነገሩን ለማግዘፍ እና ግልጽ ለማድረግ ይረዳል። ተርጓሚው የምሣሌያዊ አነጋገርን የተጠቀመ ሲሆን፣ ይኼም ለአንባቢው ባሕል እና ልምድ በቀረበ መልኩ ነው። ለምሳሌ፣ ‹‹የተቸገረ እርጉዝ ያገባል››፤ ገጽ 21 ላይ መጥቀስ ይቻላል።የግርጌ ማስታወሻዎች፡- ይኼ ነጥብ የትርጉም ሥራው ልዩ መገለጫው ይመስለኛል። በትርጉም መጻሕፉ ውስጥ የተካተቱ የኅዳግ ማስታወሻዎች (በተርጓሚው የተጨመሩ)፣ አንድን ቃል ከማብራራት እስከ አንድን ርዕሰ-ጉዳይ በሰፊው እስከመተንተን ይደርሳሉ። የዚህ ፋይዳ በትረካው ውስጥ የተነሱ፣ ምናልባት ግርታን/ የግንዛቤ ችግርን ሊፈጥሩ ለሚችሉ ቃላትና ርዕሰ-ጉዳዮች አንባቢ ሰፋ ያለ ማብራሪያ እንዲያገኝ ይረዳል። ብሎም፣ የኅዳግ ማታወሻዎቹ ከዋናው የመጻሕፉ ጭብጥ ያፈነገጡ አይደሉም።

ለማሳያ፣ ገጽ 18፣ 22፣ 32፣ 35፣ 51፣ 78… ላይ በኅዳግ ማስታወሻ የተካተቱ ገለጻዎችን መመልከት ይቻላል። ይኼ ሙከራ እንደ አርአያ ተቆጥሮ ሌሎች ደራሲዎች በትርጉም ሥራዎቻቸው ላይ ቢሞክሩት ጠቃሚ ነው የሚል ሃሳብ አለኝ።የሙድ ዓይነት ጸሐፊ፡- አንድን ጉዳይ/ ታሪክ በቁመናው ልክ ከመዘክዘክ፤ በወቅቱ የነበረውን ሙድ መተረክ ለድርሰት ሀሳቡ ግዝፈትን ይሰጣል። ለአብነት ያህል፡- አንኮበር ተጉዠን የአጼ ምኒልክን ቤተ-መንግሥት እየጎበኘን ነው እንበል፤ ‹‹የንጉሠ-ነገሥቱን ሲናድር አይተን ተደመምን፤ ነካንም›› ከምንል ‹‹የንጉሠ-ነገሥቱን ሲናድር ለመንካት ተራኮትን›› ብለን ብንገልጽ ግዝፈት ይኖረዋል። ደራሲው፣ (ከሞላ-ጎደል) ታሪኮቹን/ገጠመኞቹን በሙድ ለመግለጽ ሞክሯል፤ በጊዜው የነበሩ ሁኔታዎች የጫሩበትን ሥሜቶች በምስል መልክ ተርኳል።
ምሳሌ እንጥቀስ፡- ‹‹የጠፈር አለንጋዎች እርቃን ገላዎችን ሲገርፉ ሰማን።…. ቀጥሎ ለመላጨት ወደ ሌላ ክፍል ተነዳን።›› ገጽ 28፤ በማለት የእስረኛውን ውርክብ እና የካፖዎቹን ያፈነገጠ አሠራር ተርኳል።

በሙድ የመተረክ ዘዬ፣ ዶ/ር ፍራንክልን የረዳቸው ይመስለኛል። የሥነ-ልቡና እና ሥነ-አዕምሮ ይዘት ያለውን ድርሰት በጊዜው በነበረው ሙድ ላይ ተመርኩዘው የእስረኞችን ሁኔታ፣ ችግርና መፍትሄ ለመተንተን ጠቅሟቸዋል የሚል ዕምነት አለኝ። እዚህ ላይ ሙድ/ሁኔታ ለአንድ ርዕሰ-ጉዳይ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው መዘንጋት የለብንም። ሙዶች/ሁኔታዎች ጉዳይን የመገንባት/ ወደ-ጉዳይነት የማደግ አቅም አላቸው። የጉዞና የሥነ-ልቡና እንዲሁም የሥነ-አዕምሮ ድርሰቶች በሙድ መልክ ሲተረኩ ሃሳቡ ይገዝፋል ብዬ አምናለሁ። ደራሲው ከሙድ በመነሳት የተለያዩ መላ-ምቶችን ማስቀመጥ ይችላል።እዚህ ላይ የተርጓሚው ድርሻ የሚናቅ አይደለም፤ የትርጉሙ መልክ ታሪኮቹን በጥሬው መዶለት ሳይሆን፣ በጊዜው የነበሩ ሙዶችን/ሥሜቶችን በውብ ቋንቋ እያስደገፉ መተረክ ነው። እሰይ የሚያሰኝ ነው።

ንድፍ/methodology እና መቃን/ frame-work፡- በቀለም ትምህርት መስክ፣ ጥናታዊ ጽሑፍን ለማስኬድ ሁነኛ/ትክክለኛ ንድፍ፣ ብሎም መቃን እንደሚያስፈልግ ይታወቃል። ለአብነት፡- survey design, experimental design, correlational design, causal comparative/ex-post-facto design, case-study design… ወዘተ. ተጠቃሽ ናቸው። እንዲሁም፣ ንድፍና መቃን ድርሰትን በአግባቡ ለማስኬድ ይረዳሉ።
ለማሳያ፡- ታሪክ፣ ፍልስፍና፣ ሥነ-ልቦና፣ ሥነ-አዕምሮ… ወዘተ. በድርሰት ዓለም የተለመዱ ንድፍና መቃን ናቸው። ለጥቁምታ፡- ራሻዊያን ጸሐፊዎችን ብንመለከት፣ በድርሰቶቻቸው በሚስሉት ገጸ-ባሕሪይ በኩል የአንድን ፍልስፍናዊ ኅልዮት ሕልው መሆን፣ ወይም ውድቀት ለማሳየት ይሞክራሉ። ድርሰቱ በፍሬድሪክ ኒቼ ኅልዮት (theory)፣ ‹‹የሚኖርለት ለምን ያለው (ለ-ጠበቅ ተደርጋ ትነበብ) ሰው፣ ማንኛውንም እንዴት ይቋቋማል›› መሠረት ያደረገ ሲሆን፤ ባለታሪኩ በኅልዮቱ ልክ ከከበበው ጨለማ ወደ ብርሃን ይሸጋገራል።

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ሻምበል ጉተማን መካንነቱ አልያም በጦር ሜዳ ውሎው አካለ-ስንኩል መኾኑ በቀጥታ የሚኖርለትን ለምን አልቀማውም። “የጀልዴሳን አወዳይ ጫት በጎልማሳነቱ ከሲያድ ባሬ መንጋጋ አላቅቆ፥ እነርሱ አፍ አስገብቶ፥ መርቅነው በፈዘዙ ዓይኖቻቸው እያዩ ጣል ጣል ሲያደርጉት ግን መኖሩ ትርጉም አጣ። “እኔ ወታደር ነኝ፤ ሞትን አልፈራም …” ይላል። በክብሩ ሲመጡበት ግን “የትኛውንም እንዴት” መቋቋም አልቻለም። ሐይቅ ውስጥ ገብቶ ሰጠመ። አሪስቶክራት ኅብረተሰብ ዘንድ እንዳሉት “ሜጋሎቲሚያ” ክብርን ፈልጎ አይደለም ክብሩን ሲያጣ የሞተው። ለሀገሩ የተዋጋውም የአርስቶትል ሪፐብሊክ ላይ እንደተጠቀሰው፥ "ታይሞስ" በተሰኘው የዕውቅናን ክብር የሚፈልገው የነፍስ ክፍል ገፍቶት አይደለም ከሞት አፍንጫ ሥር የገባው። ለእናት ሀገሩ ክብር ብሎ እንጂ። በእናት ሀገሩ ክብር ውስጥ ነው የእሱ ክብር ያለው። አንድ ዓይኑን እና እግሩን ለሰዋለት ኅብረተሰብ መጣ። ግን የተቀበሉት በግልምጫ ነው። በአሸናፊ እና ቢጤዎቹ “የሚኖርለት ለምኑ” ስትደፈጠጥ፥ ከዚያ ወዲህ ኑሮ አላሻውም። ሻምበል ጉተማ የኢትዮጵያ ወታደር የሚለው ቀርቶ “የደርግ ወታደር” በሚል ንጥል ገፈት ለቀመሱት ማስታወሻ ይኾን? ፒየር ማሻሪ “ሥነ ጽሑፍ ለተጻፈበት ዘመን ጥበባዊ አንደበት ነው!” ይልም የለ?

ዘውዲትም ራሷን ታሰናብታለች። የምትኖርለት ለምኗ የተሳሰረው ናሆም ከተባለ ባለትዳር ጋር ነበር፤ ሲበጠስ ለመኖር ምክንያት አጣች። የልጅ ሞት ምንኛ እንደሚያንገበግብ በማሰብ ራሷን ለቤተሰቦቿ ስትል ለማቆየት ለአፍታ እንኳ አላሰበችም። "ለራስ ግድያ ከሞት ናፍቆት ይልቅ የሕይወት ጥላቻ ነው ቅርቡ፤ የጠሏት ሕይወት ውስጥ ተቀምጠው ከመጠበቅ እርሱ ወዳለበት መሄድ።” ይልም የለ ጋሽ ቴዎድሮስ ገብሬ። ዘውዲት፣ ቀይ ቀለም በበዛበት የወርቁ ሥራ ላይ በገላዋ ስዕሉን በማተም እንደ ምትሞት ንግርት መሰል መልዕክት አስቀምጣም አልነበር? ንግርቱን ፈጸመች። እርቃኗን እንደ ክርስቶስ ተዘርግታ ሞተች። ዘውዲት የማን ትዕምርት ናት? ማንንስ ልትዋጅ ነው?

የምትክ ወላጅ አባት የኾነው ደረሰ ዋቄን ለሞት ያበቃው ጥልቅ ኀዘን ነው። ጥልቁ ኀዘን የመጣው በልጁ በተስፋዬ ሞት ነው። የሚኖርለት ለምኑ ተስፋዬ ነበር፤ ምንም እንኳ ተስፋዬ የአብራኩ ክፋይ ባይኾንም። ተስፋዬ ቀይ አፈር ላይ በማያውቀው ጉድ የቀይ ሽብር ሰለባ ኾነ። በዚህች ምድር ስንት ተስፋዬዎችን አሰናብተን? የስንት ደረሰዎችን፣ የስንት ላስታዎችን፣ የስንት ምትክዎችን … ሕይወት አበላሽተናል?

ለእምቦቀቅላው ኢብሳ ሞት ማነው ተጠያቂው? ፋርማሲስቷ ኅብስት ወይስ ዶክተር ዮሴፍ? ለኢብሳ ስንብት ተጠያቂዋ ቅናት ሥጋ ለብሶዋ ሳላይሽ ብቻ ናት? በበሬው ለመወጋት በሬው ብቻ እንዴት ጥፋተኛ ይኾናል? በቦታው መገኘት በራሱ፣ በበሬው ለመወጋት አንዱ መዋጮ መኾን አይችልም? ሳላይሽ ኢብሳን ትወደዋለች። ልጅ ተወዶ - ወላጆቹን አለያይቶ - ወንድ ወደሽ ጢሙን ጠልተሸ እንደ ማለትም አይደል? በኢብሳ ወላጆች መሀል የሰደደችው መቀስ ግን የምትወደውን ኢብሳን ቆረጠው። ለሳላይሽ መቀስ ዮሴፍና ኅብስት መዋጮ አላደረጉም ማለት ይቻለናል?

ስንዝሮ እና አኪሊዮስ ለኢ-ሟችነት የቀረቡ ናቸው። ቦታን እንጂ ጊዜን መሰናበት የማይቻላቸው ይመስላሉ። ግን አኪሊዮስም ኾነ ስንዝሮ ይሞታሉ። በግሪክ ሚቶሎጂ እንደ ምናውቀው አኪሊዮስ ኃያል ጦረኛ ነበር። ማንም የማይረታው። ይህ የኾነው ግን አኪሊዮስ ገና እምቦቀቅላ እያለ በጦርነት እንደ ሚሞት ትንቢት በሰማችው እናቱ በኩል ነው። እናቱ በልጇ ላይ የመጣውን ደንቃራ ለማስወገድ ስታስስ አንድ መላ ሰማች። ከስቴክ ወንዝ የተነከረ ከአደጋ ሁሉ ይድናል” ተባለች። የአኪሊዮስን ተረከዝ ይዛ ነከረችው። እንደ ተባለውም ካደገ በኋላ በአንድም ጦርነት ቆዳው ሳይፋቅ ድል በድል ኾነ። ገነነ። አንድ ጦርነት ላይ ግን አኪሊዮስ ተረታ። ይኸውም አንድ ወታደር መርዛማ ቀስቱን በአኪሊዮስ ተረከዝ ውስጥ አሰረገ። አኪሊዮስም በፍጥነት ሞተ። ለካስ እናቱ ስቴክ በተሰኘ ወንዝ ውስጥ ስትነክረው ተረከዙን ይዛው ኖሮ፥ ተረከዙን ውኃ አላገኘውም ነበር። የትኛውም ኃያል ድክመት መኖሩ የሚዘየበው በአኪሊዮስ ተረከዝም አይደል? የስንዝሮ ተረከዝ ራሱን በራሱ ማየቱ ነው። ኢል የተሰኘው የእባብ ዝርያ ዘሩን ካፈሰሰ በኋላ እንደሚሞት እያወቀ አርፎ እንደማይቀመጠው ሁሉ፥ ስንዝሮም ዓይኑን በዓይኑ አየ። ተሰናበተ፤ ራሱን ተክቶ።

ዮሐንስ ወላይሶ በመኪና አደጋ በሞት ሲሰናበት ረቂቅ በኤችአይቪ ኤድስ ታሸልባለች። ነጪት ደግሞ ግብሯን ጨርሳ በሰላም የንጋት እጅ ላይ ታርፋለች። የኀያሲዎቻችን ውክል የሚመስለው ዮሐንስ ወላይሶ “… ግባችን በመንፈስም በሥጋም መሰናበት … ነው። … በናኖ ሰከንዶች የምናደርገው ሁሉ የመሰናበት ነው ድርጊት ነው። ሞትን ነው የምንኖረው …” ብሎ የለ?

ስንብቱ ልዩ ልዩ ነው። ጊዜን ብቻ አይደለም። ቦታንም ይሰናበታሉ።

ንጋት በምኒልክ ገመድ ተጎትታ፣ ፍቼን ተሰናብታ፣ አዲስ አበባ ስትከትም፤ - ሳምራዊው ደግሞ ገጤ ከመኾን ብሎ አዲስ አበባን ተሰናብቶ አራስ ተከትሎ ፍቼ ይገባል። ለይኩን ወንድነቱን በገበረላቸው ሰዎች አፍ ሲብጠለጠል የሚወዳትን ሀገር ተሰናብቶ ከአድማስ ማዶ ይነጉዳል። ጂግሳ ለማ ስንቱን ካየበት፣ ስንቱን ካሳየበት ንፋስ ስልክ ይሰናበታል። ደበሌ የመማጸኛ ከተማ ከኾነለት ሻገር ሆቴል በታጣቂዎች አማካኝነት ተሰናብቶ ወደ ዝዋይ ግድም ካለ ወኅኒ ቤት ይወርዳል። እትዬ እልልታ ጥርሳቸውን ከሚያሰጡበት፣ ላስታ በአርምሞ ከምትዋጥበት፣ ምትክ የደግነት ዘንግ ከምትዘረጋበት ጉልት ይሰናበታሉ። ፍኖት አባዲ ሰዓሊውን ወርቁ ዕንቁባሕሪይን እና ሀገሯን ተሰናብታ ሲኞር ሪካርዶን አግብታ ወደ ባሕር ማዶ ትሻገራለች። ቲጊ ከደጃዝማ ጆቴ በቸሮታ ያገኘችውን ሆቴሏን ተሰናብታ ወደ አማኑኤል የአእምሮ ሕሙማን ሕክምና ተቋም ትገባለች። ስንብቱ ይቀጥላል።

የጋሽ አዳም የስንብት ቀለማት ሥነልቦናዊ ንባብንም ይሻል። የቤላ የእንጀራ አባቷ የኾነው አቶ ተስፋዬ በተደጋጋሚ ይደፍራት ነበር። በውጥንቅጥ ለተሞላው ለቤላ ሕይወት የእንጀራ አባቷ ተጠያቂ አይደለምን? በማኅበረሰባችን ውስጥ በቅርብ ዘመድ የሚደፈሩ እህቶቻችን ውክል ናት ማለት እንችል ይኾን? ቹቹ ሴተኛ አዳሪ የኾነችው እናቷ ሶረንን እያየች ስላደገች ነው? ደጃዝማች ጆቴ የተከበሩና ሀብታም ኾነው ሳለ ሴተኛ አዳሪ ጋር መሄዳቸው ለተኮላ ማንነት ያዋጡት መዋጮ ይኖር ይኾን? የደም ተወራራሽነት ስለሌላቸው ከፍተኛ ፍትወታዊ ፍላጎት ከየት መጣ? ከጂግሳ አባት ከአቶ ለማ ወይስ ከአስተዳደጉ (ከደጃዝማች ጆቴ)? ትጊ በልጅነቷ ዳማ የሚባል ወጠምሻ “ከኔ ጋር ተኝታለች” ብሎ ስላስወራባት እና ለትዳር እንደ ማትኾን ሲሰማት (The feeling of low self-esteem) ወደ አዲስ አበባ ተሰድዳ ሴተኛ አዳሪ መኾኗ ውስጥ ሥነ-ልቦናዊ አስተንትኖት አያሻም? የስንቱን የሕይወት ጦር ወሬ እንደ ፈታው ቆጥሮ መጨረስ ይቻላል? የምትክስ የልጅነት ቀንበር የዋዛ ነው? ተስፋዬን ለመተካት አይደል እንዲህ የምትለን? “የማውቃቸው ሴቶች ወይም ልጃገረዶች ዕድሌ ኾኖ ነው መሰለኝ ጨዋታቸው መሀል ወንድማቸውን በስም ያነሳሉ - ፣ ወይ ከመሀል ወንድሜ ይላሉ። ያወንድማቸውና። ወንድሜ ተስፋዬ የሌለበትን ይሄን ባዶ ቦታ ለመሙላት ወይም ለመሻማት … ብዙ ጊዜ የምጫወተው ከወንዶች ጋር ነበር።” የተስፋዬ ምትክ ለመኾን የጣረችው ጥረት ከሴትነት ቅንብብ አውጥቷት የለምን? እንደዚህ ያሉ አጓጉል ቀንበሮች ማኅበረሰባችን ላይ

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ዲኮንስትራክሽን፥ ነገረ ሞት፥ ንቡር ጠቃሽነት እና ፖለቲካዊ አሊጎሪ - በ”የስንብት ቀለማት”

ርዕስ:- የስንብት ቀለማት
ደራሲ፦ አዳም ረታ
ዘውግ :- ልቦለድ
ገፅ፦ 940
Rating :- 9.5

በአፍሪካ ትልቁ የሆነው ይህ ረዥም ልቦለድ በ10 ክፍሎች ተከፍሎ፥ በ46 ንዑስ ታሪክ ውስጥ ከ60 በላይ ገጸባሕርያት ተዛንቆ፥ በ8 ቀለማት ተወክሎ፥ ተቀንብቦ፥ በፍርርቅ የአተራረክ መንገድ የቀረበ ነው።

ምትክ፣ ድንግልና፣ በድንግልና ማርገዝ …

የስንብት ቀለማትዋ ምትክ፥ ድንግልናዋ እንደ "ሔራና አፍሮዳይት" ታዳሽ አይደለም። ምትክ፣ እንደ ቡድሃ እናት ልጇን በድንግልና ከወለደች በኋላም አትሞትም። እንደ ቅድስት ድንግል ማርያም ኢየሱስን በድንግልና ከወለደች በኋላ ሌላ የማትወልድ ናት ለማለት እርግጠኝነት ይጎድለናል (አዳም ቀጣዩን ምናብ ለተደራሲው ትቷልና) ። ግን አንድ ነገር እንገነዘባለን። በዓለማችን የተከሰቱ ዲበ-ሰዎች ከድንግል የሚወለዱ ናቸው። “በሀገራችን ለተንሰራፋው ሥራይ፥ መፍትኼ-ሥራይ የሚያመጣው ከድንግሏ ምትክ የሚወለደው የስንዝሮ ልጅ ይሆን?” ብለን እንድንጠይቅ ያደርጋል። የመጽሐፍ ቅዱሱ አይሁዳዊው ዮሴፍ እና የደምቢዶሎው ዮሴፍ እንዲያው የስም መመሳሰል ብቻ ነውን? እትየ እልልታስ “እመቤታችን፣ ቅድስት፣ ተስፋችን …” ለምን ይሏታል? በከብቶች በረት የተወለደው መሢሕ ለአይሁድ፣ ለሰማርያ እና ለአሕዛብ መፍትኼ-ሥራይ እንደ ኾነ ሁሉ፥ ሙሉ ለሙሉ ተሠርቶ ባላለቀው የዮሴፍ ቤት ውስጥ፥ የመንኮብያው ልጅ ሲወለድ፥ በጎችና ላሞች መከሰቱ የወንጌላቱ መጻሕፍትን አያስተዝትምን? ኢየሱስ በበረት የተወለደው መልካም እረኛ እንደ ሚኾን ለመጠቆም ይኾን? የምትክ ልጅ ባላለቀ ቤት የተወለደው ቤቱን ሠርቶ ሊያጠናቅቅ ይኾን? የዮሴፍ ዐዲሱ የሕክምና ተቋምስ ስለምን ቤዛ ክሊኒክ ተባለ? ስንዝሮ የሰጣት ወርቅ … የጉሊቱን ጠረን የቀየረው መዓዛዋ … ዮሴፍ ባልጠፋ የጉልት ዕቃ ዕጣን መግዛቱ … ሰብአ ሰገል ለረቡኒ ካመጡት ወርቅ፥ ዕጣን፥ ከርቤ ጋር የሚያስተሳስር ነገር ይኖረው ይሆን? ወርቅ የጽሩይ (የጠራ፣ ንጹሕ)፣ ከርቤ የተለየውን በፍቅር አንድ የማድረግ እንዲሁም ዕጣን ደግሞ የተስፋ ትዕምርት አይደለምን? እዚህ ላይ ስንዝሮ የአማልክትና የንጉሣዊ ዘር ቅይጥ መኾኑ ደግሞ እናክልብት እንዴ? ጋሽ አዳምን ቅይጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ንቡር ጠቃሽ (Mixed biblical allusion) ነው ልንለው እንችል ይኾን?

ከሸዋው ንጉሥ ሳህለሥላሴ ቀዬ አንዲት ገረድ አስደማሚ ሕልም በማለሟ ምክንያት ከልጃቸው ጋር እንድትተኛ መደረጉን የአብዬ መንግሥቱ ወላጅ አባት፥ አለቃ ለማ ኃይሉ አስቀምጠውልንም የለ? እዚህ ጋር የስንብት ቀለማት ላይ ሲኖዳ ሕልም ማየቱን ስናስገባው ደግሞ አንድ ነገር ብልጭ ይልልንም የለ? ምትክ በሕልሟ የእሳት ወተት ስትሸና ማየቷን “ፀሐይ ከብልቴ ወጣ!” ካለችው ጋር የሚያስተሳስር ገመድ ይኖረው ይኾን? ደሞስ “እንደ እሳት ኃይለኛ እና እንደ ወተት ገር የሚሆነው surrealism ወለድ ነው!” ማለትስ ይቻለናል?

የመጽሐፉ የገጽ ሽፋን ላይ ካሉት ውስጥ መሐል ላይ ያለችው፣ ዓይኖች ሁሉ ወደሷ የሚያማትሩባት፣ ጥቁርነት በሚታገለው ወርቃማ ቀለም ላይ የተሰየመችው ማን ናት? ምትክ ናት ማለት እንችል ይሆን? ለምን እሷን ያይዋታል? ለምንስ ተስፋ ያሳድርቧታል? እትየ እልልታ “ድመቶች ሀገር ለምን ሳንባ እሆናለሁ? ከሆነልኝ ውሻ፣ ካማረልኝ መጥማጥ መሆን እንጂ” ብለው እንደ ነውር የተቆጠረውን ጉርሻ ሲሸጡ፣ ከታመሙበት ራስ ምታት እንዴት በምትክ ጠረን ተፈወሱ?

ፊያሜታዊነት ዲኮንስትራክት ተደርጎ ይኾን?

ፊያሜታ ሲባል ወደ አእምሯችን ምን ይመጣል? ከአንድ ገጸባሕርይነት ከፍ አላለችም? በስሟ ተዘፍኗል … ስሟን ከስሙ ያዋሃደ ፊልም አቡጀዴ ላይ ተሰጥቷል … ቲያትራችን ውስጥም ገብታለች። ለአያሌ የማኅበራዊ ድኅረ ገጽ ተጠቃሚዎች የጭምብል ስም ቋት ኾናለች። የምድረ ሐማሴን እንስቶችን በሞላ እንደሷ ያሉ እንደ ኾኑ ማሰብ ከጀመርን ሰነባብተናል። በኀያሲዎቻችንም ዘንድ ሮማንን እንደ ኢትዮጵያ ፊያሜታን እንደ ኤርትራ የመፈከር ዝንባሌ ይታያል፤ ወደ ሰፊው ሕዝብም ተጋብቷል። ፊያሜታ አሁን አንድ ተራ ስም ከመኾን ተሻግራ ራሷን የቻለች ትወራ ሆናለች። ከትንሽ ነበልባነት ወደ እቶን እሳት አድጋለች። ፊያሜታ ተለጥጣ ፊያሜታዊነት የተሰኘ የተዋቀረ ኀልዮት ጋር ደርሳለች። በኔ እምነት ይኼ ውቅር በ”የስንብት ቀለማት” ዲኮንስትራክት የተደረገ ይመስለኛል። ምኒልክን እንደ ጸጋዬ ኃይለማርያም ሳንቆጥር፥ ሳፍሮንን ችላ እንደ ተባለችው ሮማን ሳንወስድ የፊያሜታ ግብርን ከምኒልክ ጋር በአንድ መም ላይ በማስኬድ ብቻ ማወቅ ይቻላል። ፊያሜታዊነትን ጋሽ አዳም ዲኮንስትራክት እንዳደረገ በግልጽ ተቀምጧል። በርግጥ ድኅረ ዘመናዊ ሥነጽሑፍ የደራሲነቱን ባለቤትነት ለማኅበረሰብ ውቅር (social construction) ስለሚሰጥ ለምን ፊያሜታን ዲኮንስትራክት ሊያደርጋት እንደ ፈለገ የመጠየቅ መብት ይነፍገናልና ምላሹን ከጽሑፉ አውደ ንባብ ለማግኘት መታተር ይጠበቅብናል። ለዚህም ምላሽ የፊያሜታ፥ የምኒልክ ባዩ፥ የዮሐንስ ወላይሶ፥ የውሻዎቹ፥ የቤላ ፍራንኮ፥ የጸጋ፥ ጋዜጠኛው ፀሐይ የማነ … ተረኮችን በአንክሮ ማጤን ይሻል። ፊያሜታዊነት እና ዲኮንስትራክሽን ጋር ለመድረስ የውሻዎችን ታሪክ እንንጠልጠል እስኪ።

የውሻዎቹን ታሪክ እንደ ፖለቲካዊ አሊጎሪ (political allegory) ብንመለከትስ? ቀስቶ የተሰኘው ውሻ “ከብት ከከለከሉን ሬሳቸውን እያወጣን መብላት ነዋ………የሚረባ ሬሳ ካላቸው ነው ደሞ። አንጎል አልነካም ያኔ። የእነሱ ደደብነት አንዳይጋባብኝ። (504)” እሚለውን በዋዛ ማለፍ ይቻለናል? የያ ትውልድ አባላት በኮድ እንደ ሚግባቡት ሁሉ ስንዝሮ ቀስቶ የተባለውን ውሻ የሚያገኘው ከሳምራዊው በተቀበለው ኮድ መኾኑ አንዳች ፍንጭ አይሰጠንም?

ቀስቶ አንዱን ነጭ ቡችላ ይጠራውና “እስኪ አንድ ጎድን አጥንት አምጣልኝ” ሲለው ደረቅ እንጨት ይዞ ይመጣል። ዐዲሱ የውሻ ትውልድ ሣር እንዲበላ በመደረጉ፥ ሥጋን ከእንጨት አለመለየቱን ቀስቶ የተባለው ውሻ ለስንዝሮ ያስረዳል - ከላይ የቀረበውን ታሪክ ያዙልኝ። ዮሐንስ ወላይሶ ደግሞ በሌላ ገጽ ላይ እንዲህ ይላል፡- “ሁሉም ያለ ምሕረት ያለ በቂ ትንታኔ የዛሬውን ወጣት ያማሉ። እነዚህን ዕድለቢስ ጠማማነትን የተረከቡትን ጉብሎች ሲከላከሏቸው የምናየው ጥቂቶችን ናቸው። 'ወጣት ድሮ ቀረ' አንዱ ወሬአቸው ነው። 'ድሮ ሲሉ እኛ' ማለታቸው ነው። ይሄ 'ድሮ የተባለው ቃል የማይሞት ነው። ይኼም … ሕመም ነው።”(430) ዐዲሱ የውሻ ትውልድ እና ዐዲሱ የሀገራችን ትውልድ በሁለቱ “ያ ትውልድ” አልተሳሰረምን? ሳምራዊው የተባለ ውሻ ስንዝሮን ሲሰናበተው “ንጹሕ ሰው የለም ንጹሕ ውሻ የለም - ተደበላልቀናል” ያለው ጥቁምታ ሊሰጠን አይደል?

የውሻዎቹን ታሪክ በአሊጎሪካዊ መነጽር ሳየው፥ ዮሐንስ ወላይሶ ለኔ ሳምራዊው እንደ ተባለው ውሻ ነው። ዮሐንስ ወላይሶ ከመጽሐፉ ውጪ ኾኖ ሕዳግ ላይ እንደሚያኄሰው፥ ሳምራዊውም ከአዲስ አበባ ውጪ ኾኖ የአዱ ገነትን ጅማትና ቅልጥምን ይለያያል፤ ያትታል። ውሻ ኾኖ ሳለ አውቶብስ የሚባለውን ለስንዝሮ ሲያስረዳ “ሳር አይግጥም እንጂ … በቅሎ … ቢጤ ነው - ባይበላህም ይገጭሃል - ስንቱ ወዳጄ አልቋል” ሲል እናገኛለን። አውቶብሱ ሀገር በቀል ያልኾነው የጨፍጫፊው ትዕምርት (symbol) ይኾንን? ሳምራዊው ይለጥቃል “አብዮት - ብዙ ሰዎች

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

"በእሁድ ውርውርታ የጎሕ ደብዛዛ የደረቴን ደብሮች እየነከሰ (ጡቶቼን ደብሮች ነበር የሚላቸው) ሺህ ጊዜ መላእክት እየሰሙ (ለምን አይስሙ) በተኮላተፈ ምላሱ ስሜን የጠራበትን---ለምን ብዬ እረሳለሁ? ለመጀመሪያ ጊዜ ጭኮና በሶ መጨበጥ ብቻ የሚያውቁ ቀለሜዋ እጆቼ ወንድነቱን ሲይዙ፣ መንቀጥቀጥ የጀመረው ገላዬ እስከ ሁለት ሺህ ዓመትምህረት የሚቆም አልመሰለኝም፡፡ ልስላሴው፣ ሙቀቱና ንቅናቄው ዛሬ እንደሆነ ሁሉ መዳፌ ላይ ይሰማኛል፡፡ ይሄ ፍቅር እንጂ ብልግና አይደለምና ለምን እረሳለሁ? ማማራችን ምን ልክ ነበረው? በሚያሳዝን ጎርናና ድምፁ የሆነ ዘፈን እየዘፈነ፣ አብሬው ስል እበልጠዋለሁና ለአሪፍነቴ ያቀፈኝን---ለምን ልርሳ? ፍቼ ነፋሻ መሆኗን ያወቅሁት ያኔ እስኪመስለኝ……ጋራውን ያየሁት ያኔ እስኪመስለኝ………ዐይኔ ዐይን የሆነው እግሬም እግር የሆነው ያኔ እስኪመስለኝ፡፡ ደረቴን ከፍታ ወጥታ መረሬ ጭቃ ላይ የወደቀች እንደ ወርቅ፣ እንደ ቢፍቱ፣ የምታበራ ልቤን ለቅሜ አንስቼ ባላበው መዳፉ አስያዝኩት፡፡ ጃላሌልኮ፡፡ ይሄን ይሄን ሁሉ፣ ይሄን ሚያዋ አፍ አውጥተው ባይናገሩም የላንጋኖ፣ የኩማንዶና የኩቲቾ አምባዎች፣ አራዶችና መስኮች በአፈራቸውና በሮባቸው ያስታውሳሉ፡፡" ገጽ 532 (ሚኒሊክ የሚስቱን ጡቶችም ደብሮች ነበር የሚላቸው ገጽ 347)

"አንገቷን ሰብራ በችኮላ ወደ መሬት ታወራለች፡፡ ቶሎ ሳብኳትና እየፈራሁም ቢሆን ግራ/ ቀኝ ጉንጯን ሳምኳት (የትኛው እንደሆነ ትዝ አይለኝም)፡፡ --አይሆንም አለች። የደከመ እጇን ለማንሳት እየሞከረች፡፡ እንዲህ ስታነሳ እኔ በቆምኩበት በኩል ያለው አንድ ጡቷ ገፋኝ፡፡ የሚመች ማረግረጉ በሁለመናዬ ሰረገ፡፡ ይሄንንም አላቀደችውም፡፡ ተኝቶ የነበረ የሚያምር አውሬ ከውስጤ ዘሎ ሲወጣ ይሰማኛል፡፡ አንገቷን አቅፌ አፏ ላይ ግጥም አደረኳት፡፡ (ያኔ “ግጥም‛ ነው የምንለው) ኮስታራ የመሰለ ፊቷ ላይ አይኖቿ እጥፍ ተከፈቱ፡፡ በዚህ መሃል ያለዕውቀት ደረቷን በእጄ ያዝኩ፡፡ በድንገት ባልጠበቅሁት ሁኔታ ሁለመናዋ ሲረገብ ተሰማኝ፡፡ አፏ ተከፈተና የሌሊት የመሰለ ጠረን ከውስጧ ወጣ፡፡ ምሽቶቼን ስትበላ ኖራ? ታዲያ እንዲያ ቆመን በእሟ እሟ ስንደበላለቅ የፍቅር ቁም ፅሑፍ እየቸከቸክን መስሎኝ ነበር…….ቀኝ እጄ ግራ ጡቷ ላይ በደንታ አርፎ………ያ ጡት እንደ እርግብ ነገር ነበር፡፡ የዛች አፍታ ሴራ ሳይሆን አልቀረም ከዛፉ ራቅ ብሎ ከሚንተገተግ የመንገድ አምፖል እኔን ለመመረዝ ከገነት በዛ ምሽት እንደወረደ የብርሃን ችቦ በቅጠሎች መሃል በደፈጣ መጥቶ እሱ ላይ ያበራል እንዲህ ሲሆን………ከሰንጋ ተራ እስከ ቡልጋርያ……… ከልደታ እስከ ስታድዮም………አይን የሚያጥበረብር ብርሃን ሳይፈስ አልቀረም፡፡ የተመደበልኝ የዛን ቀን ስራ እንደሆነ ሁሉ ጎንበስ ብዬ ያን ወጋገን “እሙ" አልኩት፡፡ ሁለመናዋ እንደተቀበለኝ ሁሉ ረጋ አለ፡፡ እርጋታዋ ቴክኒክ ነበር? ግራ እጄን ከአንገቷ ወስጄ ወገቧ ላይ ላስቀምጥ ሳነሳው፣ የማደርገው ገና አሁን እንደገባት ሁሉ፣ ሽሚዟን ከግራና ቀኝ ከድና ሸሸት አለችኝ፡፡" ገጽ 289

"ያመለመለ ወንድነቱ መዳፏ ላይ ይሰማታል፣ እሱን አየት አድርጋ ደበሌን አየችው፡፡ መናገር አልቻለችም…..የተገጠመ አፉን ለመሳም ስትንጠራራ በጀርባው ዐይኖቹን ከድኖ ወደቀ…... በከፊል ይሰማታል………ደሞ በከፊል አይሰማትም…………ለሀብቷ አልነበረም ደበሌ ደረቷ መሃል ያረፈው………ቀይ ቀሚሷ ወደ ላይ በቀርፋፋ ስልት እየተሳበች ...……የቡናማ አይኖቿ ስፋት ውስጥ በረሀ ያያል………ከስሩ እንደ እባብ ናት………አንገቷ በወዝ ይፈልቃል………ፊቱን እዛ ቀብሮ………እውስጡ የተሰበሰበውን የእንባ ዶፍ እንደ ወጨፎ ሊጥለው ይለፋል………በእሷ የተከፈለ እየታጀበ………ደሞ ዜማ ልቡን ያዳምጣል ………እንደተሰናኙ ቢገባውም ያልተሰናኙም ይመስለዋል፡፡ በሲሶ ስሜት፡፡ አንዱ ሲሶ ዘውዲት ጋ ነው፡፡ የቀረው ሲሶ ምን እንደሆነ አያውቅም፡፡ –ማርዬ………ማ…….ሩ የእኔ ማር………ደበልዬ………እወድሻለሁ በለኝ (ወደ ኮርኒሱ አንጋጣ)፡፡ የተዘባረቀበት ፊቱ ላይ በቅርብ የታኘከ የቀረፋ ማስተካ ጠረን ይነፍሳል።" ገጽ 712

"ቲጊ አራዶቼ ቂጥዋን በአደባባይ 'ታኒ' ሲሉት ትበሳጭ ነበር:: ሰዎቹን ላለማስከፋት አጠገባቸው ተቀምጣ በሳቅ ትፍረስ እንጂ ዞር ስትል አምሮብኛል ነው? ትላለች:: ቂጥዋ በሌሎች ሰዎች ስየማ ሲለጠፍበት ሉአላዊነቱን ያጣ ይመስላታል፡፡ ቃሉ ከየት መጣ? እየተመሰገነ እንደሆነ ቢነግሯትም አልገባትም፡፡ ምን ማለት ነው? ዐይን አፋር ሀገር ተፈጥሮ እንጂ ቂጥዋ የሃይ ሎጋው ሽቦ አዝማች ይሆን ነበር፡፡ የቅልስልስ ሀገር ሆኖ እንጂ ባየችውና ባጋጠማት በአበባዬሆይ ዜማ ይወደስ ነበር፡፡ ያ እርግብግብነቱ፣ ያ ለስላሳነቱ፣ ያ አሳዛኝነቱ፣ ያ ግራ ቀኝ የምቾት ፍም የደበቀ፣ ያ ግራና ቀኝ ንቅናቄውን ለመተንበይ ሳይንቲስት እንኩዋን የማይችልበትን፣ ከሌሎች አስመሳይ ቂጦች ጋር በሁለት ፊደሎች ደርቦ መሰየም ደግ ነው? ትውስታውስ? በሕይወቷ ወጣ ገባ በስቃይና በብስጭት መሃል ትውስታዋ ቢረበሽም፣ ሰንሰለቱ ቢቆራረጥም፣ ቂጥዋ የግል ትውስታ አለው፡፡ የመዳፍ፣ የጣቶች፣ የአውራጣት፣ የመጨምደድ፣ የመቧጨር፣ የመጨበጥ፣ የስስት፣ የጉጉት፣ የመዳበስ፣ የከያኒ መዳፎች፣ የሐኪም መዳፎች፣ የአዛውንት መዳፎች፣ የፉንጋ መዳፎች፣ የወጣት መዳፎች፣ የዘፋኝ መዳፎች፣ የአናጢ መዳፎች፣ በደረቅ ሌሊት የተነገሩ ጨዋታዎች፣ የወንዶች እዬዬ፣ የወንዶች ምርቃት፣ የፖለቲከኞች መሃላ፡፡ እነዚህ ሁሉ ውስጡ ተፅፈዋል፡፡ እግዜር የራሱ መዝገብ የለውም፡፡ ወደ ምድር ሲመለስ አዲስአባ ላይ ሊፈርድ በወርቅ ዙፋኑ ተቀምጦ የሚያነበው የትጊን የቂጥ ዶሴ ነው፡፡ የትጊ ሀብ ሀብ ዕድሜና አሟራቾች ቢሳካላቸውም፣ ትውስታውን ግን ጊዜ አልፈቀፈቀውም፡፡ ሸርሜ ምናብ የላትም ማን አለ? ድንገት ዘመን ይመጣ ይሆናል እዚህች ሀገር ባንዲራ መሃል የእሷ ቂጥ ወይም የእሷን ሀብ ሀብ የመሰለ ምስል ተለጥፎ ሲዘመርለት፡፡ ተጣማጅ አርበኛ በቂጥ መውደድ ቀንበር ምን ይታወቃል የማይሆነው እየሆነ ከሆነ መሆን የሚችለው ይሄ አይሆንም?" ገጽ 597

"ራቁቴን ዐልጋ ላይ በጀርባዬ ቀረሁ፡፡ ዘሬን ያቀፈ የተዝለገለገ ኮንዶም በወረቀት ተጠቅሎ ኮመዲና እግር ስር አለ፡፡ የወረቀቱ እቅፍ ዙሪያውን ተላቆ የሚፀልይ ይመስላል፡፡ የኢብሳ ወንድም ይሆናል፡፡ ለምን ኮመዲና ስር? ለምን ላስቲክ በወረቀት ይጠቀለላል? ሽንት ቤት ተቀምጣ ሽንትዋን ስታንሿሿ ጎንበስ ብላ አያታለሁ፡፡ የሽንጥዋ ቅንፍ…… የሚያምር አቀማመጥዋ………እና ብርሃንና ጨለማ የሆነ ጭን፡፡ ፈገግ ብላ በሩን መለስ አደረገችው:: ከሩካቤ በሁዋላ የደምቢዶሎ ላሞች ሜዳ ላይ የሚለቁት አረንጉዋዴ የሽንት ፏፏቴ ትዝ አለኝ። መሽናት የበለጠ እንስሳዊ ይሆን?" ገጽ 259

"ወርቁ ስለማሜ ቂጥ ሲስል ልጅነቱን ለማስታወስ ነው ብንልም ብቻ ግን አይደለም፡፡ ከዛች የግሉ ጠባብ ቦታ ተነስቶ አገሩ ጉዳይላይ የሃሳብ ደርዝ የማስቀመጥም ነው:: ምናልባትምሐተታኖኅት ወይም ምስለኖኅት እየሰራ ነው:: እንደ ወርቁ አባባል “ቂጥ” ከኢትዮጵያ ባህል የተባረረው በአንድ አምላክ ማመን ከጀመርንና ይሄንንም ካከረርን በሁዋላ ነው:: ጉዳዩ በልቦናችን ቢወሳም ከስነፅሁፍ፣ ከግጥምና ከቅኔ ተሰዶአል፡፡የሴት ወገኖቻችን ቂጥ ያልተነገረለት ስደተኛ ነው፡፡ ከላይ ሲጀመር እንደጠቀስኩት ታላላቅ ደራሲያን እንኳበ ድርሰቶቻቸው ይሄን የገላ ክፍል አለመጥራታቸው ትርጉሙ የማሳደድ ነው፡፡ ለመሆኑ በበአሉ ግርማ አድማስ ባሻገር ውስጥ ያለችው ሉሊት ምን ዐይነት ቂጥ ነበራት? የእሷን

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ሁለቴ ከፍቼ ሁለቴ አስታውኬአለሁ፡፡" ገጽ 373

•አቶ ዮሃንስም ቹቹ የጠቀሰችው አሸናፊ እና አሱን ስለመሳሰሉ ምሁር ነን ባዮቸ የአካል ሳይሆን የአእምሮ ደዌ አለባቸው ብለው ያምናሉ። ይህንንም በዚህ መልኩ ገልጸውታል።

"፩ እነዚህ ሰዎች እንደሚባለው የሚናገሩት ፍሬ ፈርስኪ ቢሆንም መሬት ጠብ አይልም ይባላል፡፡ ለምን አይል? ለምን አይንጠባጠብ? ለምን አይንዣረር? ከዚህ አባባል ትምክህት ይቀዱና ( የተማረ ይግደለኝ' ምሳሌ ነው) እንደ ሁሉን-አዋቂ ይሰራቸዋል:: የሚሉት ካልገባህ ወይ 'መሃይም' ወይ 'ደደብ' ወይ 'ቂል' ነህ፡፡ ከነዚህ ከሶስቱ ካመለጥክ ታድለሃል፡፡ የተማረ ይግደለኝ ሲባል ሰምቶ ተደሰተ እንጂ ቀስ በሉ አላለም፡፡ ይሄ ሌላው ሕመሙ ነው፡፡

፪/ የነዚህ ምሁራን አንዱ ተውህቦ በሆነ ‘ትንታኔ' በተባለ ነገር ራሳቸውን ማግለል መቻላቸውና ፍፁም ተጠያቂ የሚያደርጉት እዛ የተቀመጠ እነሱን ያልነካ (ያልነኩት) ያልዳሰሰ (ያልዳሰሱት) በሽተኛ ሥርዐት እንዳለ ማውራታቸው ነው:: ይሄ የዘመናውያን ጥበብ ቢሆንም፣ በእነዚህ በእኛ ልጆች ይበረታል፡፡ ይሄ የአተናተን ስልታቸው ወደ ድርጊታቸው፣ ወደ ሚኖሩበት ሃቅ ገብተው በተቀናበረ ተጨባጭ መረጃ ራሳቸውን እንዲያጠኑ አላደረጋቸውም፡፡ ይሄ የ ‘ትንታኔ‛ ሰይፋቸው ግን ብዙ የሚያርፍበት ቦታ ስላልነበረ ታጥፎ ወደ ራሳቸው መጣ፡፡ እንዲህ ሆኖም ሌላ ያማርራሉ፡፡ ለምንድነው በሳይንስ ካደጉ መረጃ ወይም ደረቅ ዕውነት የሚፈሩት? ይሄ ሁለተኛው ሕመም ነው።

፫/ የድሮውን ጊዜ ሥርዐት ጠቅላላ በጨቋኝነቱ ቢያሙትም ራሳቸውን ግን ከዚህ ውሳኔ ያወጣሉ፡፡ ይሄም ማለት ድሮ ያገኙት ዲግሪ በሐይለስላሴም ሆነ በደርግ ጊዜ የበሉት፣ የጠጡት፣ የተከበሩበት፣ የጨቆኑበት ትክክል ነው:: ዞር ብለው የደርግንና የንጉሡን የትምህርት ሥርዐት ቢሰድቡም ያኔ ያገኙት ዶክትሬት ግን ይሞካሻል፡፡ ይሄ ሶስተኛው ሕመም ነው:: መማርን በሚመለከት በአጠቃላይ የተማሩበትን ባዕድ አገር ማወደስ ደንባቸው ነው፡፡ ያን አገር ካወደሳችሁ እኔም ከወደዛ ተምሬ ስለመጣሁ አወድሱኝ ዐይነት ይመስላል፡፡

፬……የስድሳ ስድስት ፖለቲከኞች ወይም ነን ባዮች የአባይን ወንዝ ጂኦ ፖለቲካ መሰረታዊነትና ወሳኝነት ተገንዝበው ፕሮግራማቸው ውስጥ ያላወቀሩት ንቀውት ነው:: ስለ ራስ ማወቅ _ አሳፍሮአቸው ነው፡፡ ከአዞ ከዓሣ ከደንገልና ከጎጃሜ ይልቅ የሚያማምሩ ጀልባዎች የሚንሳፈፉበትና ነጫጭ ባርኔጣ ያደረጉ ፈረንጆች የሚዝናኑበት ሚሲሲፒ አይበልጥም? እርስዎ አሁን ተነስተው አባይን ልገድብ ቢሉ ዋናው ግራ ተጋቢ ግብጽ ሳትሆን እኔና መሰሎቼ ነን፡፡ ………
እነዚህ ልሂቃን ከልጅነታቸው ጀምሮ በራሳቸውና በ 'ትላልቅ ሰዎች' በተቀፈቀፈላቸው ድንግዝግዝ ሕልም ታጅበው፣ በተቀናበረ ሽሽት ይናጣሉ፡፡ ሽሽትም ሕመም ነው፡፡ በራሱና በመሰሎቹ ለራሱ ግራ የሚያጋባ ቡድን አበጅቷል፣ የሚኮራበት መለያ ስምም አውጥቷል፡ ያ ትውልድ ይባላል።
፭ ከአራተኛው ሕመም ጋር የተያያዘ ሌላ የተደበቀ (እሱ የማይናገረው፣ ሌላ ልናገር ቢል የሚናደድበት) ሕመም አለበት። እነዚህ ሰዎች በተዘዋዋሪና (አነሳሱ) በቀጥታ (አጨራረሱ) ራሳቸውን ይጠላሉ፡፡ ጭቆና ክፋት፣ ምቀኝነትና ጦርነት ጓዛቸውን ሰብስበው ኢትዮጵያ ውስጥ የገቡ አስመስለው በማማረር ይተነትናሉ ወይም ይናገራሉ፡፡ የጃፓንን ነገር ያደንቁና ስለ ማንቹርያ ዩኒት 731 እና ስለ ሳንኮ ሰኩሰን ሁሉን ወደ አመድ የመለወጥ ስትራተጂ አያስታውሱም:: ቻይናን ያደንቁና እዛ ውስጥ ስለተሰራው ረገጣ፣ ጦርነትና ጭቆና አያወሱም፡፡ አውሮፓን ይጠቅሱና ኦፔራ እየተዘመረና ሸክስፔር እየተተነተነ ከ65 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ የጨረሰውን ሁለተኛው የዓለም ጦርነት አያይዘው አያስቡትም፡፡ ሰላማዊ ነው እያሉ በሚያሞጋግሱት የዓለም ክፍል ምን ያህል ሚሊዮን ሕዝብ በጦርነትና ባለመግባባት እንዳለቀና በማለቅ ላይ እንዳለ አያነሱም፡፡ የሚያዩት የአገራቸውን ገመና የሚታያቸውም ይሄ ነው:: መረጃ የሚገባቸው ተበታትኖ ነው:: በግድ ራሳቸው በፈጠሩት አገራቸውን ማጣጣያ የተመራረጠ መረጃ ተማርከው የዝቅተኛነት አቧራ ለብሰው ሁሉን ነገር ገለባብጠው ሊለውጡ ይፈልጋሉ፡፡ ሁለት ዓይነት ስሜት ያድርባቸዋል፡፡ በመጀመሪያ አገራቸውን ይጠላሉ፡፡ “መጥላት' የሚለውን ቃል ግን አይጠቀሙም፡፡ ሁለተኛው ራሳቸውን የመውደድ ስሜት ያድርባቸዋል፤ ምክንያቱም አገራቸው መጥፎ ሁኔታ ውስጥ እንዳለች፣ ይሄም የመረዳት ዕውቀት ያላቸውና እንደመንፈስ ያደረባቸው እነሱ ብቻ ናቸው:: እዚህ ላይ ሁለ- ነገር ይዘባረቃል፡፡ መዘባረቁን ግን ልብ አይሉም፡፡ በፈለጋቸው ጊዜ አቋማቸውን እዛና እዛ የሚያለዋውጣቸው ይሄ ነው:: አንዴ ታላቋ ባለታሪክ አገራችን አንዴ የተረገመች አገር ማለት ያበዛሉ፡፡ ያልተማረው በእነሱ መረጃ ያልተበረዘው ገበሬና መሃይም ግን በሚያቀርቡለት ማራኪ ሥዕል ልጆቼ፣ የተማሩ ልጆቼ በተባሉ ቃላትና “በተማረ ይግደለኝ" ስልት ማልሎ እነሱ ላዘጋጁለት ደብዛዛ ዐላማ በተለያየ መንገድ ይጠፋል፡፡ ከዚህ በኋላ የሚቀረው ነገሩ ሲበላሽ ማመሃኛና ሰበብ ፍለጋ ነው:: የሚያመሃኙት ግን በራሳቸው ቀሽምነት ሳይሆን በሕዝቡ ድንቁርና በአገሩ ምናምን እና እነሱ ስም በሚሰጡአቸው ተቀናቃኞች ላይ ነው፡፡

፮/ ሁሉም ያለ ምህረት ያለ በቂ ትንታኔ የዛሬውን ወጣት ያማሉ፡፡ እነዚህን ዕድለቢስ ጠማማነትን የተረከቡትን ጉብሎች ሲከላከሏቸው የምናየው ጥቂቶችን ናቸው :: ‘ወጣት ድሮ ቀረ’ አንዱ ወሬአቸው ነው:: “ድሮ” ሲሉ “እኛ” ማለታቸው ነው:: ይሄ “ድሮ” የተባለው ቃል የማይሞት ነው:: ይኼም ስድስተኛው ሕመም ነው::

፯/ ሰባተኛው ሕመማቸው በጣም የግል ጉዳያቸውና ለማንም የማይነግሩት ነው:: በተፈለገ ጊዜ ግን አገራዊ አጀንዳን መሻሪያ ወይም መከለሺያ ሆኖ ይቀርባል:: ግራ ይገባናል፡፡ “እንዴ ይሄ የተማረ ሰው ምን ሆነ?‛ “ዶክተሩ ምን ሆኑ?” “ፕሮፌሰሩ ምን ነካው?' እላለን፡፡ እውነት እውነት እላችኋለሁ ለዘላለም መልሱን አናገኝም፡፡" ገጽ 429-430 (ሰማያዊ ከተሰኝው ምዕራፍ)

•እስቲ ደሞ ስለ ፍቅር እናውራ። ዙፋን/ሳፍሮን ሚኒሊክን ያፈቀረችበት መንገድ በጣም ልቤን ነክቶታል።

•ዙፋን ባሏ ሚኒሊክ ከእርሷ ውጭ እንደሚሄድ ታውቃለች። ፍቅር ታጋሽ ነው ብለን ሰምተን ከሆነ ዙፋን ሚኒሊክን የታገሰችበት መንገድ በጣም አስገርሞኛል።

•ሲተኛት ድሮ ያፈቀራትን ያስባል-----

"ታዲያ ዙፋንን ፓስታ ስሪ እስኪ ስጎው እንደ ወንዝ የሚያደርገው‛ ስላት ወይም ነጋ ጠባ የቲማቲም ወጥ ይሰራልኝ ካበዛሁ --ከየት ያመጣኸው ፀባይ ነው በርበሬ ያሌለበት ነገር መብላት? ትለኛለች፡፡ ሳልሳ ሲሸተኝ ፊያሜታን ላስታወስ እንጂ ትውስታው ስብ አልነበረውም፡፡ የሚነካ የሚነከስ የሚመተር ሽንጥ የለውም። ፊያሜታ በውስጥ ሱሪ ምን ትመስላለች? መልስ የለኝም፡፡ በበጋና በክረምት በመፀውና በበልግ የከንፈሮቿ ጠባይ እንዴት ነው? ቢሉኝ፡፡ መልስ የለኝም፡፡ እንዲሁ በረሃ ይታየኛል፡ አንዳንድ ቁልቋል ዛፎች የበቀሉበት፣ አየሩ በትኩሳት የሚርገበገብበት፡፡ --ደህና ነህ ሚኒዬ? ትለኛለች ዙፋን ሃሳብ ሲያነሆልለኝ፣ ዙሪያዋን አንሶላ ሰብስባ፣ እንደልምምጥ ስትጠጋኝ፡፡ ቂጥ ትዝ ይለኛል የፊያሜታ። በጂንስ የታጠረ፡፡ ንፍገት የለበሰ፡፡ ዙፋን የተከናነበችውን አንሶላ ገፍፌ ከአእምሮዬ ካርታ ፊያሜታ ሳትጠፋ በችኮላ፡፡ የዙፋን ቀይ ዳማ ጀርባ፡፡ ዋሾ ነኝና ያደገብኝ ተስገብግቤ ውስጥዋ ስገባ አፏን ጠመም አድርጋ በግንባሯ ትራስ ነክታ ዓይኖቿ በጥርጣሬ ሲቁለጨለጩ አያታለሁ፡፡ እንዲህም ሆኖ በባህርዬ

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

አዳም ፦ ብዙ ጥሩ ጥሩ ሙዚቃ አለ ፣ ጥሩ ጥሩ ወጣቶችም እየመጡ ነው ። አሁን አንተ ያልከው ዘፈን ግን ያንተ መሆን አለበት ...

መፅሃፍ ?... AI ን ጠየቅኩት መጽሐፍ ከየት ከየት ላገኝ እችላለሁ ብዬ .... ዝርዝር ሰጥቶኝ pdf driveን ዘለላት .... ወሳኝዋን! ...What about Pdf drive አልኩት? ...ስለ እሱ መረጃ ልሰጥህ አልችልም አለኝ .... ለምን ጌታዬ (Why sir )ልበለው ? ለምን ማሽን (Why machine ) ልበለው ? ሃሃሃ... አይ እዛ ከገባህ የቅጂ መብት ( Copy right ) ማክበር አለብህ ምናምን አለ ... ተወው AI is not Free .... ነፃ አይደለህም አልኩት...

ሀብቱ፦ ተበላህ "AI " አትለውም ነበር ሃሃሃ ...

አዳም፦ ወይኔ በአማርኛ ተበላህ ብለው አሪፍ ነበር ሃሃሃ ...
እኔ ልጠይቃችሁ ለምንድን ነው የእኔን መጽሐፎች የምትወዱት? (Why do you like my books ? ) መልሱልኝ !

ሀብቱ፦ አሪፍ ጀለስ ነህ! ጀለስህ እንዴት ነው የሚያውቅህ? የተቀደደ ካልሲህን ያውቅልሃል ... ያቺ የሆነ ቀን የሳምካትና ላሽ ያለችህን ልጅ ያርፋታል ፣ በጣም ሲቸስትህ ከጓደኛህ ጋር የትኛው ምግብ ቤት ሄዳችሁ እንደምትፈወሱ ያውቃል። አዳም እንደዛ ነው ... በልደታና በመርካቶ መካከል ያለ አሪፍ ጀለስ ነው ሃሃሃ

አዳም፦ አሪፍ መልስ ናት ግን እዛ Facebook ላይ የፃፍከው አይነት አይደለም።

ሀብቱ፦ እኔ ከበድ ባለ መንገድ ማሰብ እወዳለሁ። ስለ ሀገርን መልሶ ስለ ማዋቀር (Restructuring of nation ) ፣ ማህበረሰባዊ ከለላ (societal Protection ) ፣ ከኀሩያን ማዕከላዊነት (Elite Centric ) ከመሆን የወል ተዛምዶነት (Communality of Culture ) እፈልጋለሁ .... በተጨማሪ ብዙኃኑ ሕዝብ (Mass Population ) የሚኖርበትን ጥበብ ደግሞ እፈልጋለሁ ። ከዛ ቆንጆ ምልከታ (Observation ) ያለው ጠባቂ ...ጥሩ ጠባቂ (patron ) እወዳለሁ ... አዳም ያ' ጥበብ አለው ብዬ አስባለሁ ። ለዛ ነው አዳምን የምወደው ...

ሁለተኛ ይሄ ሃገር ... ገራኣልታ ሄጄ አውቃለሁ ፣ ወለጋ ሄጄ አውቃለሁ— በ1 .25 ሳ ቡና ጠጥቻለሁ፣ አርባምንጭ ሄጃለሁ— ናይል ፐርች የተባለ ዓሣ በልቻለሁ፤ አዲስ አበባ ርቦኝ ምናምን አውቃለሁ ... አዳም ይሄንን በብዝኃነት ተረካ ( multiplicity narrative ) ውስጥ በደንብ አድርጎ መስራት ይችላል። ግን አዳም ይከብደኛል። ትሁት ሆኜ አይደለም...
እኔ ሳስብ በጣም ፖለቲካ ይጫነኛል ።

የእኛ ሀገር ፖለቲካዊ እሳቤው በእጅጉ የሚያይልበት ነው ... የተጎዳውም ለዛ ነው ... ያንን የፖለቲካ ጉዳይ ወስደን ፖለቲካዊ ያልሆነን ነገር ልንስራባት ይገባል ( We need those Political element to make apolitical ) ብዬ አስባለሁ። በጣም ፖለቲካዊ ጉዳዮችን እየፃፈ ተራ እና ረብ የለሽ ማድረግ ይችላል ማን? አዳም ! ያንን እንደ አንድ የአዲስ ሚት መስሪያ (New Myth making ) ሃሳብ አድርጌ አስበዋለሁ። በጉዳዩ ላይ ደጋግሜ ባሰብኩበት ቁጥር ይበልጥ ስሜት ይስጠኛል ።

ገዛኸኝ፦ የአብዮቱ ጉዳይ እንደ ጀብድ ነው ሚታየው በተለይ በእኛ ትውልድ አይን .... የጀግንነት እሳቤ (Heroic Concept ) አለው ... መረቅ እስኪወጣ ብዙ አብዮት ተኮር ታሪኮችን አንብበናል ... የኢህአፓን ጉዳይ በቁጭትና በደጋፊነት ጎራ እስክንከፈል ሁሉ ያነበብናቸው ታሪኮች አሉ ። ምክንያቱም ጣፋጭና መሳጭ ታሪኮችን ነው የሚሰጡን።

መረቅ ለማንም የማይወግነውን አላዛር'ንና ዝም ብሎ የሚኖረውን ማህበረሰብ አሳይቶኛል። መረቅ ለእኔ ደፋሮች የሚፅፉት የታሪክ መፅሐፍ ነው። ደፋሮች ናቸው ያንን ክፍተት የሚሞሉት እንዴት? በሁለት በኩል ስለሚሞቱ ... እናም የተቀደሰ ሞት ነው ለእኔ ... ተባረኪ ዴሞክራሲያን ማራገቢያ ስታደርገው አስባታለሁ... ከየት ወዴት እንደመጣች አስባለሁ ... እንሞትለታለን የምንለው ነገር የሆነ ሰዓት ላይ እንደተራ ነገር እሳት ማያያዣ ልናደርገው እንችላለን ...

መረቅ ግን የህይወት መንገድ ነው ብሎ የማንሳት እውነታ አለው፤ እኔ አዳምን የምወደው ታላላቆቻችን የሚደብቁንን ፍርሃታቸውን ፣ መውደዳቸውን ፣ ከጀብዳቸው ውጪ ያለውን ሕይወታቸውን ... አዳም ይነግረናል ... ባንተ ድርሰት ውስጥ ራቆታችንን ነው ምንገኘው ።

ስዕልና ቀለም ትወዳለህ? ከስዩም ወልዴ በኋላ ሂስን ያዘሉ፣ ስለ ስዕል የሚያብራሩ ፅሁፎች በድርሰቶችህ ውስጥ አሉ። የምናብ መስፋት ነው ወይስ ስዕል ነፃነት ስለሚስጥህ ነው?

አዳም፦ ገፀ ባህሪው ሊሆን ይችላል ... የተለያዩ ዘውጎችን (genres ) ለማገናኘት ሊሆንም ይችላል ። ስትፅፍ ምስል አለ ። አዕምሯችን ውስጥ ንድፍ (sketch ) አለ ... ስዕል የትም አለ. ... በግንዛቤ ወይም በመማር (cognitive processes ) ሂደት ውስጥ ስዕል ይቀድማል ። ፊደል ሳንቆጥር ነው ፀሐይ የምንሞቀው . ... ግን እንደማንኛውም ገጸ ባህርይ ሊገጥምህ ይችላል ።

ቀጥታ የማደርገው ምንድን ነው...ራሱ ልዋጭ ( metaphor )ነው ። እዛ ላይ ያለ አንድ የስዕል ስታይል ሕጽን ነው ። ባዶ ቦታ የመሙላትም ነው ። እንደ ደራሲ ነው ማለት ነው ።ሌላው ጉዳይ ሂስ ነው። የስዕል ሂስ ብዙ ጊዜ አያጋጥምህም... ያኔ ያ'ታሪክ ሲከሰት እኔ አላየሁም... ባይ እንኳን ይፈቀድልኛል... ድርጊቱ ስዕልና ቋንቋን የማያያዝ ነው ፣ ስዕልና ሕጽናዊነትን ማያያዝ ነው ፣ ነገረ ዓለሙ በሙሉ የተያያዘ ነው ። አንዱ የአንዱ ነፀብራቅ (reflection ) ይሆናል ።

ተሻለ፦ ስለዚህ መፅሃፎችህ የተገነቡት በሕፅናዊነት መሰረት ላይ ነው ማለት ነው ? ለምሳሌ ሺ አምባዎች የተገነባው በራይዞም መሰረት ላይ ነው እንጂ ራይዞም አንድ ምዕራፍ ብቻ አይደለም ይላሉ ...

አዳም፦ እንደዛ ነው ። የግርጌ ማስታወሻው ከዋናው ድርሰት ጋር በትርጉም ፣ ባዶ ቦታው ከስዕል ጋር ... ስለዚህ ስለ ስዕል ሳነሳ የይዘት በለው የቅርፅ ሜካኒዝም ነው። በሕጽዊነት ስለተገነባ መፅሐፉን ከፎቅ ላይ ብትጥላው በመሰረታዊ እሳቤው (metaphorically )አይበታተንም ... ገፆቹ ሳይበታተኑ ይገኛሉ ፤ከአየሩም ሆነ ከመሬት ስበት ጋር ተያይዘው ይቆማሉ ።

ተሻለ፦ የሰግር በሕጽናዊነት ንድፍ ሲመጣ ሕጽናዊነት ስግርን ይጠራል ? ወይስ ሰግር ሕጽናዊነትን ይጠቀልላል?

አዳም፦ በየትኛውም ኑባሬ ውስጥ ሕጽን ይሰራል! ስግር የክዋኔ (performance )ጉዳይ ነው .... ራሱ ሕጽን የሆነ ሌላ ሕጽናዊነትን የሚፈጥር ነው ። ራሱ መርበብትን የሚፈጥር ( Network form ) መርበብት (Network)ነው።

ተሻለ፦ ለምን መስለህ ለራይዞም ያደላሁት፣ አሁን ያለውን በሄግል እሳቤ የተዋቀረውን ዓለም (Heglian world ) መሰረቶች እያፈረሳቸው ነው ብዬ ስለማስብ ነው ፤ ደግሞም የማፍረስ አቅም አለው ። በተለይ የበይነ መረብ (Internet )መምጣት ዋነኛው ጉዳይ ነው ።

ሁለተኛው ደግሞ የፍልስፍና ጥያቄ መለወጡ ነው ። አሁን ጥያቄው ሕይወት ምንድን ነው (What is Life ? ) የሚለው አይደለም ጥያቄው ሕይወትን እንዴት ነው መኖር ያለብን (How might one live ?) የሚለው ነው።

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

አዳም፦ እኔ የማደርገው ዝም ብዬ ማየት ነው ። ምክንያቱም አንዳንድ ክስተቶችም ሆኑ ሁነቶች ጥልቅ ሀሳብን ይጠይቃሉ ፤ ማሰብ አለብህ ፣ መመርመር አለብህ ። ሁሉም መድኃኒት ፈላጊ መድኃኒት ቀማሚ አይለም። እኔ በቃ ተረክ እፅፍልሃለሁ ፤ በዛ ተረክ ውስጥ የሆነ ነገር ለመንገር እሞክራለሁ ። በተረኮቼ ውስጥ አልወግንም ። በዛ ውስጥ የማስታውሰውን ነው የምፅፈው ። ምናልባት እኔን ራሴንም የሚያስከፉኝ ሊሆን ይችላል። ግን እዛ ውስጥ ፍርድ ሳልወስድ ማስቀመጥና ትንቢታዊ (predictive ) እንዲሆኑ የማድረግ ነው የእኔ ስራ ። የእኔ ድርጊት የመተረክ ፣ አስተማስሎ (Representation ) የመስራት እና መጪውን የማሳየት ነው። ከዚህ በተረፈ ነብይ ( የብሉይ ዘመን ነብይ ) ነው የሚመልሰው ... ባቅላቫ መብላትም ሕይወት ነው ሃሃሃ ...

ሀብቱ :- ጉዞውን እንወደዋለን። ትግሉ ፣ መማሩ ፣ መውደቁ፣ ተጋድሎ ቆንጆ ነው ። ተጋድሎ ነው አይደል ሰውን ሰው ያደረገው? ተመስገን ማለቱ ፣ ሌሊት እንቅልፍ ማጣቱ ፣ ጧ! ብሎ መተኛቱ አይደል ?

አዳም:- እርግጠኛ አይደለሁም .... የግድ መስቃየት አለብህ?
ይሄ ድርጊት አዲስ ፍልስፍና የመፍጠርም ሊሆን ይችላል። ከችግሩ ለመውጣት የሚያፈናጥርህ እሳቤ ወይም የአስተሳሰብ መንገድ (Concept system ) ፈጥረህ አዲስ አለም የማበጀትም ሊሆን ይችላል ።
ይሄን ሁሉ ግን አንድ ደራሲ ላይመልሰው ይችላል ። ከእኔ መጠየቅ ያለብህ ሀቀኛ ( authentic )መሆኔን ነው። የምትፈጥራቸው ገጸ ባህርያት ሀቀኛ መሆን አለባቸው… ከአንድ ደራሲ ሁሉንም ነገር መጠበቅ ሊያስቸግር ይችላል ።

ገዛኸኝ፦ ድርሰቶችህን ሀቀኛ የሚያደርጋቸው ምንድን ነው? ድርስቶችህን ስናነብ ህይወት አላቸው። ማለት ቴክስት ብቻ አይደሉም፤ በተለይ የገጸ ባህርያት ግንኙነትን ብንመለከት ጥርት ያለ የህይወት መሰናስል አለው ፤ ሕይወትን ነው የምትፅፈው ። በዚህ ልክ እንዴት ሊሳካ ቻለ?

አዳም፦ በስሜት ሕዋሳቶቼ ነው የምረዳቸው ፤ በቃ ያ' ነው ለእኔ መለኪያው። ርቀት ከተሰማህ ግን ውስጥህ አልደረሰም፤ በስሜትህ አትለካውም። ግጥም ሳነብ በሃሳቡ ሳይሆን በስሜት ሕዋሳቶቼ ነው የምለካው (I just Feel it ) ፤ በቃ ውስጤን ሊነካኝ ይገባል። ውስጥህ ሲነካ ፀጉርህ ይቆማል ፣ የሆነ አይነት መመስጥን ይፈጥርልሃል ። የሆነ ጥልቀት ያለው ህመምም ይሁን ደስታ ይጋባብሃል ፣ እንደዛ ከሆነ ልክ ነው ። በአመክንዬ ላላስረዳህ እችላለሁ ። ሃያሲ ሌላ ነገር ነው ፤ የሚያይበት መንገድ ይለያል ። መዓት መፅሐፍ አለ የሚነበብ ግን አይነካህም ፤ ሁሉም አይዳብሱህም ።

ገዛኸኝ፦ ይሄንን የተረዳሁት እንዴት ነው? ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድን በዘመኔ ቢያንስ ሶስቴ አንብቤዋለሁ ። በሶስቱም ጊዜያት የተለያየ ነገር ነው የተረዳሁት፤ ይሄ ደግሞ ህይወት ካልሆነ እንደ እድሜ የሚነሳ ወይም የምንገነዘበው ነገር አይኖረውም ።

አዳም፦ ሀቀኛ (Authentic ) ማለቴ .... እውነታን ወክለሃል ብሎ የሚነግርህ ካለ ያ' ህይወት ነው ። ለምሳሌ እዚህ ውስጥ የሰባት መንገዶች ወግ (ጠረጴዛው ላይ ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ መፅሐፍ ነበር) እውነታውን አይተኻል? አላየህም ! 1967 ዓ.ም ነበርክ ? አልነበርክም ! ግን የሆነ ነገር ከመፅሃፍ ያገኘህ ይመስልሃል ወይም አግኝተኻል ። ትርጉም ( meaning ) እርስ በራሱ የተያያዘ ነገር አለው ፤በስሜት ትደርስበታለህ ። ለዚህ ነው የስሜት ሕዋስህን መረዳት አስፈላጊ የሚሆነበት ምክንያት ... ይሄ ሃያሲ የሚስጥህ ትርጉም አይደለም ። ሃያሲ ከሰጠህም የሚሰጥህ አለማቀፋዊ ትርጉም ነው ። ንባብ ላይ የሚያጋጥምህ ነርቭህ ውስጥ የሚቀመጥ ስሜት ወይም ተመስጦ (affection ) ነው።

ተሻለ፦ ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ በጣም ከባድ ድርሰት ነው ። በተለይ የሰባት መንገዶች ወግ በጣም ከባድ ስራ ነው ። እኔ ሳነበው እውነት ለመናገር ልናገረው የማልችለው ዓይነት ህመም ነበረው፤ የተወሰነ ቀን ተደብሬያለሁ ፣ አዝኛለሁ። ስሜቴን ክፉኛ በጥብጦት ነበር። አሁንም ሳነበው ያው ህመም ተመልሶ ይቀስቀሳል።
እኔ የአብዮቱን ዘመን በግለ ታሪክ ፣ በአካዳሚክ ስራዎች ፣ በፍልስፍና ስራዎች ፣ በስዕል ኤግዚቢሽኖች ፣ በአብዮቱ ዘመን በነበሩ ጋዜጦችና የፓርቲ ልሳኖች ሳይቀር ለማንበብ ያቅሜን ሞክሬያለሁ። ያንተን ድርሰቶችን ያህል የሚያነቃንቀኝ ግን አላገኘሁም ። የአንተ ስራዎች ናቸው መለኪያ የማደርጋቸው። ለዚህም ደራሲው ያንን ሁነት ወይም ክስተት ሲፅፍ ተራ የመፃፍ ድርጊት ብቻ አይደለም። ህይወት ሆነው የተገለጡበትን መንገድ እና አቅም ጭምር ነው እኔ የተገነዘብኩት ። ምክንያቱም አንድ ተረክ (Story ) አለ ተረካ (Narrative ) የማይቆም ከሆነ እዛ ተረካ ( Narrative ) ውስጥ ርዕዮተ ዓለም (Ideology ) ፣ መዋቅራዊ ስነ ዕውቀት (structural epistemology ) ፣ ባህላዊ ልምምዶች እና ጉዳዮች( Cultural Practices and materials ) ሳይወዱ በግድ ይገባሉ። በተጨማሪም የደራሲው መሻት (intention of the author )ይኖራል። እኔ ደራሲው ሞቷል ( The Death of the Author ) በሚባለው ሀሳብ አልስማማም ።ይህ ከሆነ ደግሞ መጪውን የማለም ብሎም ነገን የመስራት ምኞቱ አብሮ ይቀሰቀሳል ወይም ይጠ'ራል ( Imagined future ) ።

አዳም፦ መኖር አለበት ፤ እንዳለ ሁነቱን ብቻ ካስቀመጠ የአስተማስሎ (Representation ) ስራ ብቻ ይሆናል ። ከዛ በመውጣት እመርታ (Emergent) የሆነ ነገር ያስፈልጋል። ምናባዊ ነገር ስታስገባ የዛ ተረክ የመባያ ጉዳዮች (motives value ) ይጨምራል፤ ውጥረቱ ( Intensity )ይጨምራል ። ምክንያቱም መነሻው ሀቀኝነት ( authenticity )ስለሆነ ነው፤ እናም ትቀበለዋለህ ። እመርታ (Emergent ) ገጸ ባህርይ ሲሆን ትምቢት ይኖረዋል ግን መነሻው ሀቀኝነት (Authenticity ) መሆን አለበት ።
ለአንዳንድ ሰዎች እርካታ የማይስጥበት ምክንያት ምንድን ነው ? .... የሆነ የሚያሸንፍ ነገር ይፈልጋሉ ። ውስጣቸው መከፋፈል ይኖርና "የእኔና የእሱ " የሆነ አይነት ክፍፍል ይፈጥራሉ …. በዛም ስሜታቸውን ይጎዱታል ( They Betray their feelings )።
ማንኛውም የሰነ ጽሁፍ ወይም የስነ ጥበብ ስራ የሆነ ዐይነት የዋህነት ይጠይቃል ። መነሻ ቅንነትን ይጠይቃል ፤ እንደዛ ካልተነሳ ይሞታል ። እንደዛ ደግሞ ለመሆን ራስህን መተው አለብህ ፤ ራስህን እንደ ገዳማዊ መርሳት አለብህ ፤ ከራስ መፅዳት ግድ ነው ። ትዕቢትህን (Ego ) ቢያንስ ስትፅፍ መተው አለብህ ። አለበለዚያ ነገሩን አታገኘውም (you never get the point ).... አሪፍ ብትፅፍም አይመጣም። ሌላው ራስ ወዳድ ሊሆን ይችላል ...ተጨማሪ ባቅላቫ እፈልጋለሁ ሊል ይችላል ሃሃሃ ....

ሀብቱ፦ ለምንድን ነው ትልቅ ትህትና የሚያስፈልገው? ራስን መካድ ለምን ያስፈልጋል? በተቃራኒው ተገልብጦ ኃይለኛ ፣ ጉልበተኛ ፣ እኔ ያልኩት ነው የሚሆነው ቢል ለምን ከደራሲነቱ ጋር አይገጥምለትም ?
አዳም፦ አንደማስበው ከምንኖርበት ዓለም ጋር የተገናኘ ነው (I think it is connected to the universe ) ፤ በሃሳብ ደረጃ ከተለመደው ተሞክሮ ( Experience ) መነጠል አለብህ።

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ዘረኝነት (racism) እና ጋርዮሻዊነት (collectivism) ምንና ምን ናቸው?

ብዙውን ጊዜ ዘረኝነት ሲባል ሰዎችን በቆዳ ቀለም፣ ወይም በዘር ሐረግ፣ ወይም በጎሳ/በነገድ አባልነት እየከፋፈሉ ጭፍን ጥላቻ፣ አድልዎ፣ ማግለል...ወዘተ ዓይነት ነገሮችን መፈፀም ተደርጎ ነው የሚወሰደው። በዚህም አንድ ሰው ለዘረኝነት ሁነኛ ምንጭ ሆኖ የሚያገለግለውን ርእዮት ብውስጡ ይዞ እያለ እነዛን የዘረኝነት ጠባያት በቀጥታ ባለማሳየቱ ዘረኛ አይደለሁም ብሎ ሊያስብ ይችላል። ሐቁ ግን ሌላ ነው። ለመሆኑ ዘረኝነት ምንድን ነው?

አይን ራንድ በ The Virtue of Selfishness መፅሐፏ Racism በሚል ርእስ ከፃፈችው የተወሰኑ ፍሬሐሳቦችን በማጣቀስ እንመለከተዋለን።

ዘረኝነት እጅግ የወረደ እና እጅግ ያፈጠጠ ኋላ ቀር የሆነ የጋርዮሻዊ አኗኗር ዓይነት ነው። የአንድን ሰው ስነምግባራዊ፣ ማሕበራዊ፣ እና ፖለቲካዊ ምንነት ከዘር ሐረጉ ጋር የሚያገናኝ እሳቤ ነው። ይህ ማለት አንድ ሰው የሚመዘነው የራሴ በሚላቸው ፀባዩ እና ተግባራቱ ሳይሆን የአያት ቅድመ አያቶቹ ስብስብ ነበራቸው ተብሎ በሚታሰበው ፀባያትት እና ተግባራት ነው።

ዘረኝነት የሰው አእምሮ ውስጥ ያሉት የመገንዘብያ መሳሪያዎችን (cognitive apparatus) ሳይሆን የግንዛቤ ይዘቱን (cognitive content) በዘር ውርስ የሚገኝ ነው ይላል። ማለትም የሰው መሰረተ-እምነቶች፣ እሴቶች እና ባህርያት ከእርሱ ቁጥጥር ውጪ በሆነ መንገድ ከመወለዱ በፊት አስቀድሞ የሚወሰን ነው ይላል።

ዘረኝነት ከሰው ልጅ የህይወት መገለጫ ባህርያቶች ውስጥ ዋና የሆኑትን ሁለቱን የሚፍቅ ነው—አመክንዮአዊ-አእምሮን (reason) እና ምርጫን (choice) ወይም ደግሞ አእምሮን እና ሞራሊቲን። እነዚህን ሁለት አንኳር መገለጫዎች አስቀድሞ በሚወሰን የDNA ኬሚካላዊ ቅንብር ይተካቸዋል።

ለምሳሌ የአንድ ሰው መጥፎ ድርጊት የሌላን ሰው መልካም ስነምግባር የሚያጎድፍ ይመስል <<የቤተሰቡ ስም ለመጠበቅ>> በሚል ሰበብ አንድ የቤተሰብ አባል የሚፈፅመውን ወንጀል የሚደብቁትም ሆኑ፤ ልጆቻቸው እንዲያገቧቸው የሚፈልጓቸውን የዘር ሐረጎች ሲያማርጡ የሚውሉ ወላጆች እኩል የዘረኝነት ማሳያ ናቸው።

ዘመናውያኑ ዘረኛች ደግሞ የአንድን ዘር ከፍታ ወይም ዝቅታ ለማሳየት ከዘር ሐረጋቸው ወደ ኋላ ሄደው የኔ ዘር ያሉዋቸው የሰሩትን ታሪካዊ ስኬት በመጥቀስ የዘራቸው ልዕልና ማረጋገጫ የሚያቀርቡት ናቸው። የኔ ቅድመ አያቶች አክሱም ሐወልትን የሰሩ ናቸው፤ የኔ አያቶች ላሊበላን የገነቡ ናቸው... ወዘተ እያሉ ባልሰሩት እና ሊስተካከሉት ከማይችሉት የጥንት ድንቅ ስራ ጋር ዘር በመቁጠር ክብር እና ዝና እንደሚገባቸው ሊያሳዩ ሲያላዝኑ የሚውሉትን ልብ ይለዋል።

በህይወት ዘመኑ ሰዎች ሲሳለቁበት፣ ሲወገዝ፣ ሲገለል፣ በገዛ ያገሩ ልጆች ሲሰደድ የነበረን አንድ ታላቅ ባለ ፈጠራ ሰው፤ ከሞተ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ግን የብሔራዊ መታሰቢያ ሐውልት ተቀርፆለት የዘሩ/የብሄሩ/የማህበረሰቡ ታላቅነት ማረጋገጫ ተብሎ ሲወደስ የምናስተውለውን ተደጋጋሚ ታሪካዊ ትእይንትም ኮምዩኒስቶች ያልለፉበትን ንብረትና ሀብት እንደሚቀሙት ዓይነት ያለ በዘረኞች የሚፈፀም የሚሰቀጥጥ ጋርዮሻዊ ብዝበዛ ነው።

ሐቁ ግን የጋራ ወይም የዘር የሚባል አእምሮ እንደሌለ ሁሉ፤ ጋርዮሻዊ ወይም የዘር የሚባል ስኬታማ ክንዋኔም የለም። የግለሰቦች አእምሮዎች እና ስኬቶች ብቻ ነው ያሉት። ባህል ማለት ጋርዮሻዊ ስብስቦች እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መስካሪ ሆነው የሚፈጥሩት ሳይሆን የብዙ ግለሰቦች አእምሮአዊ ስኬቶች ድምር ውጤት ነው።

ከታሪክ መረዳት እንደሚቻለው ዘረኝነት ከጋርዮሻዊ (collectivist) የአኗኗር ዘይቤ መውደቅና መነሳት ጋር አብሮ የሚወድቅና የሚነሳ ነው። በጋርዮሻዊነት የግለሰብ መብት የሚባል ነገር አይታወቅም። የግለሰቡ ህይወትም ሆነ የስራ ውጤት የቡድኑ (የማህበረሰቡ፣ የነገዱ፣ የብሄሩ፣ የሀገረ መንግስቱ—the state) ነው። ቡድኑም ደስ ባሰኘው ሰአት ለ"ቡድኑ ጥቅም" ሲባል ግለሰቡን መስዋእት ሊያደርገው ይችላል። ይሄንን አኗኗር በማህበረሰባዊ ውቅር መተግበር የሚቻለው ደግሞ በጉልበት/በሃይል አገዛዝ አማካኝነት ነው። ለዚህም ነው የአገዛዝ ስርዓት (statism) ምንግዜም የጋርዮሻዊ የአኗኗር ዘይቤ ፖለቲካዊ ተቀፅላ (corollary) የነበረው፤ የሚሆነውም።

ለዘረኝነት አንድ ፍቱን ማርከሻ አለው። የግለሰባዊነት ፍልስፍና እና የዚህ ፍልስፍና የፖለቲካ-ኢኮኖሚ ተቀፅላ የሆነው የነፃነት እና የነፃ ገበያ ስርዓተ-መንግስት— laissez-fair capitalism ነው።

በነፃ ገበያ ውስጥ ዋጋ የሚሰጠው ነገር የሰው ዘር ማንዘሩ፣ የቤተሰቡ ሁኔታ፣ ወይም የሰውነት አካሉ ኬምስትሪ ሳይሆን፤ የእያንዳንዱ ሰው የማምረት ችሎታ ብቻ ነው። በካፒታሊዝም ስርዓተ-ማህበር አንድ ሰው የሚሸለመው እና የሚድዳኘው ያ ሰው ባለው የግል ችሎታ/ክህሎት እና ችሎታውን/ክህሎቱን ወደ ምርት ለመቀየር ባለው ፍላጎትና ቁርጠኝነት ላይ በመመርኮዝ ነው። ለዚህም ነው ዘረኝነትን አይቀጡ ቅጣት ሊቀጣ የሚችል ስርዓተ-ማህበር ቢኖር ለይሰፌ ካፒታሊዝም የሚሆነው።

ምን ዋጋ አለው ሙሉ በሙሉ ነፃ የሆነ የካፒታሊዝም ስርዓት እስከ አሁን የትም አገር ላይ ባለመገንባቱ የዘረኝነት ቋጠረው ካፒታሊስት በሚባሉ ሀገራት ውስጥም ጭምር ጨርሶ ሊጠፋ አልቻለም።

አሁን አሁንማ የድህረ-ዘመናዊነቱ multiculturalism ባመጣው ጣጣ ራሳቸውን በሄግል ቋንቋ የአንድ ሞራላዊ ምልአተ-አካል (ethical whole) የሰውነት ክፍሎች አድርገው የሚቆጥሩ ሰዎች የፌምንስቶች ቡድን፣ የህዳጣን ጎሳዎች ቡድን፣ የቪጋኖች ቡድን፣ የፆታ አልባነት ቡድን ... በመፍጠር የዘረኝነት አምድ የሆነውን ጋርዮሻዊ ርእዮት ከትቢያ አንስተው ህይወት እንዲዘራ እያደረጉት ነው። በነገራችን ላይ በምእራቡ ዓለም የሆነ ቦታ ላይ አንድ ሰው አግኝታችሁ ወንድ/ሴት ነው ብላችሁ አንተ/አንቺ በሚል ብታወሩት አንተ/አንቺ እንድትለኝ መች ፈቀድኩልህ በሚል x-phobic የሚል ስያሜ ተስጦአችሁ ከብዙ ነገር እንድትገለሉ የሚያደርገውን ወለፈንድ እየፈጠረው ያለው የዘመናዊነት ውጤት የሆነው ካፒታሊዝም ሳይሆን በዘመናዊነት ላይ አምፆ የተነሳው የድህረ-ዘመናዊነቱ multiculturalism እንደሆነ <<ድህረ-ዘመናዊነት: ማህበረሰባዊ ዕዳ ወይስ ቡራኬ?>> በሚል በሰባት ተከታታይ ክፍል ያቀረብኩት ፅሑፍ ላይ አብራርቻለሁ።

እያንዳንዱ ዘረኛ አይደለሁም ብሎ የሚመካ ቢኖር በጋርዮሻዊ አስተሳሰቡ ምክንያት እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ😁

© Yonas Tadesse Berhe

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ከሀገሩ ሰንደቅ ጋር ያያይዛል። የእሱ ማንነት መገለጫ መሆኑንም ይገነዘባልበ። ንጉሡ ከእሱ በላይ የሆኑ ሌሎች ጉዳዮች እንዳላቸው ሲገነዘብና በእርሱ ችሎታ ከመማረክ የበለጠ፣ የሀገር ጉዳይ ልባቸውን እንደሚገዛው ሲረዳ “ተራሴ በላይ ሌላ ነገር ማየት ተስኖኝ” በሚል ጥፋተኝነት ይሰማዋል። ንጉሡ ፊት ቀርቦ መሸለሙም ያን ንያህል ዋጋ እንደሌለው ይረዳል። በስተመጨረሻ አንድ ጣልያናዊ ምርኮኛ (ግዳይ) ይዛ ንጉሡ ፊት የምትቀርበውም ከሱ ይልቅ ባለቤቱ ትመስለኛለች!

Diversity: አንድነትና አንድ ዓይነትነት

መጽሐፉ በዓድዋ ዘመቻ ጊዜ የነበረውን ብዝኅነት በብዙ መልኩ ያሳያል። በጎሣ ወይም በብሔር ስብጥር፤ በአልባሳትና ጌጣጌጦች፤ በስሞችና ስያሜዎች፣ በቋንቋና አነጋገር ዘዬ፤ በጦር መሣሪያዎችና ቁሳቁሶች፤ በሽለላና ፉከራ ዓይነቶች፤ በሙዚቃ መሣሪያዎችና ውዝዋዜዎች፤ በጨዋታዎች ዓይነትና በልዩ ልዩ ሙያዎች፤ ወዘተ። ደራሲዋ ይህን ያደረገቸው ሆነ ብላ አንድነትን ላማምጣት፣ ተረክን ለመቀየር ወይም ለማስማማት ብላ አይመስለኝም። በወቅቱ የሆነውና በበቂ ሁኔታ ያልነገረውን በማሳየት ታሪኩ ወይም ተረኩ ወደ ምሉዕነት እንዲጠጋ ለማድረግ ይመስለኛል። ከዚህ አንጻር ዓድዋ ብዙ ማንነቶች የተሳተፉበትና ከፍ ያሉበት የጋራ ድል፣ የወል ከፍታ ነው ማለት ይቻላል።

መሲንቆ ሚና እና የአዝማሪ ከፍታ

አሁን አሁን የመሲንቆና የአዝማሪ ሚና የወረደ ወይም የተናቀ ይመስላል። ለዚህ ዓይነቱ ጉዳይ ማኅበራዊና ባሕላዊ አመለካከቶች ቢኖሩም የአዝማሪዎች ግጥምና ለሥራው ያላቸው ራብ-ጥማት (passion) አንዱ ምክንያት ይመስለኛል። ብዙዎቹ የግለሰብን ኢጎ በመመገብ ወይም የእንስትን ውበት ከማድነቅ በዘለለ ሌሎች ማኅበራዊና ሙያዊ ኃላፊነት እንዳሏቸው የዘነጉ ይመስላል። እንደዛሬው የመረጃ ምንጭ ባልዳበረበት ዘመን አዝማሪዎች ጥሩ የመረጃ ምንጮች ነበሩ። ለጠብ የሚፈላለጉ ወደረኞችም በቀጥታ ከመወራረፍ ይልቅ በአዝማሪ በኩል በዘወርዋሬ ተጎሻሽመው ጠባቸውን የሚያበርዱበት መድረክም ነው። የተጣላን ለማስተረቅ፣ የተከፋን ለማስደሰት፣ ያዘነን ለማጽናንት ይውሉ ነበር። ናዋዥ መጽሐፍ ላይ እያዩ፤ "ብሶቴን፣ ሐዘኔን፣ ተስፋዬን፣ ጭንቀቴን በአዝማሪ እንጉርጉሮ ውስጥ ስሰማው ደስ ይለኛል። የነፍሴን ቁስል ማሲንቆ ያክክልኛል። ሕይወቴ በግጥምና በዜማ ተከሽኖ በአዝማሪው ጉሮሮ ሲንቆረቆር ስሰማው በችጋር የደረቀች ነፍሴ ትረካለች" ይላል።

በዚህ መጽሐፍ ሕይወት በይመር በኩል የአዝማሪንና የመሰንቆን ሚና ከፍ ታደርገዋለች። በጦርነት ወቅት የዘማቾችን ወኔ ከመቀስወስ በተጨማሪ ይመር ማሲንቆውን ወዳጁ፣ ሙያው፣ መጽናኛው ሕይወቱ አድርጎ ያያታል። የመሲንቆና ያዝማሪ ሙያ ከቅኔ ደረጃ ከፍ ይላል። ገጽ 133 ላይ “ግጥም ከጭንቅላቱ ፈልፍሎ፣ ከልቡ ፈንቅሎ ከአእምሮው ፈልቅቆ ማውጣት ሲጀምር ዐዲስ ግጥሞችን ፍለጋ የአእምሮውን ሥርቻ ሲፈትሽ ግጥሙ ድንገት የፈለቀ ጊዜ “ዛሩ” የመጣ፣ ቃላቶች ተሰካክተው በጭንቅላቱ ውስጥ የፈሰሱ፣ ጉሮሮውን አልፈው ምላሱን ያላወሱ፣ መሰንቆውን ያነጋገረ ጊዜ የሕይወቱ ጽዋ የሞላ ይመስለዋል።” ይላል መጽሐፉ። ይመር በዚህ ከፍታው፣ በዚህ ተድባቡ፣ የተቀማውን ክብሩን መልሶ ይነጥቃል።

“ዛሩ” የሚለውን ጉዳይ ከጂኒ ወይም genius ጋር እናያይዘው። ኤልዛቤት ጊልበርት የምትባል ደራሲ በአንድ የTED Talk ንግግሯ ይህን ሐሳብ ታነሣለች። ኤልዛቤት የጥበብ ሰገነት ላይ ሆና Eat, Pray, Love የሚል አሪፍ መጽሐፍ ትጽፋለች። አድናቂዎቿ “ከዚህ የተሻለ ሥራ ልሠራ አልችልም፣ ስኬቴ ከኋላዬ ነው?” የሚል ፍራቻ አይዝሽም ወይ ብለው ያስፈራሯታል! ለዚህ መውጫ ሆኖ ያገኘችው ጥንታዊ የግሪክና የሮም ሰዎችን ጥበብ ነው። እነሱ እንደሚሉት እንዲህ ያለው የፈጠራ ሥራ ከውስጥ የሚወጣ ሳይሆን ከውጪ የሚገባ genius (ጂኒ) ነው የሚል ነው። ኤልዛቤት being a genius and having a genies መምታታት የለበትም ትላለች። እዛ ከፍታ ላይ ያወጣት አንድ አካል አለ ማለት ነው። ሕይወት ይኽንን ይመስለኛል “ዛሩ” ሲነሣ የምትለው።

እብዱ በሚለው የአውግቸው ተረፈ መጽሐፍም ውስጥ elevated የሆኑ ሐሳቦች የሚነሡት “ሲያብድ” ነው። የስፔን ኳስ ደጋፊዎች ሐጃቸው ሲሞላ Ole Ole Ole ይላሉ። የዐረብ (?) ተወዛዋዦችም “ጂኒያቸው” ሲነሣ Yala Yala Yala ይላሉ። እኛም ብንሆን የተለየና የመጠቀ ጉዳይ ሲገጥመን “ያበደ ነው!” እንል የለ። እሚጦዙ ሰዎችስ trip አደረግን አይደል የሚሉት?! የቅኔው መጦዝ ወይ መጓዝ ግን ንጹሕ መነጠቅና መገለጥ መሆኑን በመጽሐፉ ተመልክቷል። አንዱ አልምጦት ዕፀ ፋርስ ይጠቀማሉ ሲል፣ መምህሩ “እኚህ አንተ ያነወርካቸው ሊቃውንት የቤተክርስቲያን መሪዎችና የንጉሥ አማካሪዎች እንደሆኑ ያወቅህ አልመሰለኝም” ብለው ይቆጣሉ። ልዩነቱ እዚህ ጋ ይመስለኛል፣ ወይስ አምታትቼው ነው?

የልጅ ነገር

ከዚህ ቀደም በተለያዪ መጻሕፍት ውስጥ ስለልጅ ጥቅም አይቻለሁ። በትምህርትቤት ልጅ ኢንሹራንስ መሆኑን ተምረናል። የእኛም ሀገር ወላጆች “ጧሪ ቀባሪዬ!” ይላሉ። በተለይ ለአረጋውያን ምንም ዓይነት መድኅን (ኢንሹራንስ) በሌለበት እንደኛ ዓይነት ሀገር ውስጥ፣ ወላጆችን ልጆችን የሚወልዱት በስተርጅና ምርኩዝ እንዲሆኗቸው ነው። ይህ ግን አንዳንድ ጊዜ ይለጠጥና ለዛውን ያጣል። አንዳንድ ወላጆች ልጅ ወልደው፣ አሳድገው ጉልበት ለመበዝበዝ፣ ድረው ለማትረፍ፣ ወይም ስደት ልከው ገንዘብ ለማግኘት ሲሯሯጡ ይታያል። አርብቶ አደር እንዲል በዕውቀቱ ሥዩም። በሌላ በኩል አብርሃም ቨርግኸስ የሚባል ጸሐፊ Cutting for Stone በሚል መጽሐፉ “ልጅ ሞትን መሸወጃ ብቸኛ መንገድ ነው” ይላል፤ ዘርን ማስቀጠያ ዓይነት መሆኑ ነው። የትና መቼ እናዳነበብኩት እንጃ በጣም ያስደነገጠኝ አንድ የወላጆች ዓላማ አለ። እነሱ በሕይወት ዘመናቸው ለማሳካት ያልቻሉትን ጉዳይ ማስፈጸሚያ እንዲሆን ልጅ የሚወልዱ ሰዎች መኖራቸውን ይናገራል። የሰው ልጅ is a weird creature! ስድብን (መኻን ናቸው የሚለውን) ለማራቂያ፣ ከማኅበረሰቡ ጋር ለመበሻሸቂያ ሲሉ ብቻ ልጅ የሚወልዱም አሉ። አንዳንዱ ደግሞ ወልዶም ልጆቹን መከራ፣ ጸብና ስድብ ማጠራቀሚያ ያደርጋቸዋል። ሰባት ስድብ ወለደች እንዲል ዓለማየሁ ገላጋይ።

በዚህ መጽሐፍ ልጅ ለተለየ ዓላማ ነው የሚውለው፤ ለበቀል። አክስቱ እልፍነሽ ጌታን የምታሳድገው የወንድሟን ደም እንዲመልስላት እንጂ ከላይ ለተጠቀሱት ዓላማዎች አይደለም። ስሙንም ደም-መላሽ ትለዋለች። “እኔ የጓሮ ጎመንሽ አይደለሁም አሳድገሽ የምትቀጥፊኝ” በሚል የሚያምጸው በኋላ ነው። ስሙንም ጌታ ያለው በዚሁ ምክንያት ነው።

በጣም የወደድኩትና ቢሆን ብዬ ያሰብኩት በአሰፋ ገብረማርያም እንደወጣች ቀረች መጽሐፍ ላይ ስለልጅ ያሚናገረውን ነው። የባልና ሚስት ፍቅር ከእነሱ ተርፎ ሲገንፍል፣ የአምባቸውን ውበት በሕይወት ዘመናቸው ጠብቀው ለማቆየት ዕድሜ አልብቃ ሲላቸው፣ ያንን ሞልቶ የፈሰሰ ፍቅር ለማኖሪያነት፣ ያንን ውበት ለማስፈሪያነት ነው ልጅን የሚፈልጉት!!

ፕሮፓጋንዳ፣ Crowd Mentality

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

በዚህም የልደት ፣ የእድገት ፣ የመበስበስ እና የመታደስ ጭብጦችን ያሳያል።
« እኒያን የልጅነት ወቅት አበቦች
የጣዕም ወራት ጣዕሞች ፤
እኒያን ፣... ትናንሽ ክንፎች
ትናንሽ ለስላሽ ላባዎች ፤

እኒያን ፣...
ደማም ከንፈሮች
ስኳር ስኳር ፤ የሚሉ ልቦች ፤
እኒያን ፣...
የፀዳል ሳቆች
አንፀባራቂ ራቁቶች ፤
ማደግ ... ወዴት ወሰዳቸው!?
( ገፅ 56 )

ከዚህም ባሻገር አበባ በሰው ልጅ የባህል ታሪክ ውስጥ የተለያዩ ትርጉሞችን ሲሰጥ ቆይቷል ለአብነት ያህል እንደውበት ፣ ፍቅር እና መንፈሳዊነት ያሉ ጥልቅ ፅንሰ ሀሳቦች በአበባ ይወከላሉ። በስነ ዓለማት ዳራ መሰረት ትርጉምንና ትስስርን ለማግኘት የሚደረጉ ሙከራዎችን ያንፀባርቃል።
የዓይኔን ልቦናዬን ፤
ቅንድቤን
ከንፈሬን
ልቤን
ኩላሊቴን
:
ተመልከተኝ እኔን
ገላው የረገፈ አበባ መሆኔን!
( ገፅ 80 )

በአበባነት መፈከሪያ ተደርገው የሚቆጠሩት እነኚህ የህይወት ዘለላዎች በመድብሉ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ ተሰጥቷቸው በአጀብ ሰፍረው ይታያሉ። ገጣሚው ህይወትን በአበባ ቅንጣት ይመስላታል። ቀጥሎም እሳትን ያስከትለዋል።
በግሌ ቴዎድሮስ ካሳ በዚህ መድብሉም ሆነ ባልታተሙ ግጥሞቹ ከሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን ጋር ህይወትን ፣ ፍጥረትን ፣ ጊዜን ፣ ሰውነትንና መሰል ጉዳዮችን የሚያይበት መንገድ ተቀራራቢነቱ የዘውድና የጎፈር አይነት የመገላበጥ የእድሜ ልዩነት ይመስለኛል።
በርግጥ ፀጋዬ እሳት ሲል ከላይ በፈከርነው መሰረት ውድመትና ጥፋትን ( አብዮት ) አይነት የሞት ጥላዎችን ሲሸሽ ቴዎድሮስ በበኩሉ ልክ እንደወፊቱ ( ፊኒክስ ) በመቃጠል መሻገርን ( ዳግመ ውልደትን ) ናፋቂ ሆኖ እናገኘዋለን።
መፅሀፊቱም ለገበያ የዋለችው በመጨረሻዋ የህዳር ቅዳሜ በመሆኑ ከህዳር መታጠን ጋር ተቃጥሎ በመጪዎቹ ወራት ውስጥ ለመታደስ ይሆናል ብለን እንጠርጥር !
ካልጠረጠርን ምኑን ሀበሻ ሆንን!?
ይሁኔ በላይ « ገላጋይ » በሚለው የበዕውቀቱ ስዩምን ግጥም ተውሶ በዘፈነው አንድ ዘፈን
« በአንድ ዱር ይበቅላል ብትርና አበባ » የምትል ስንኝ አለች። ሰውን ከዱር አበባነት ከመሰልነው ዘንድ ከአበባው ይልቅ በትሩ ባሳደደን የቁጭት ድምፅ ውስጥ ፤ ሳይቀጠፉ መርገፍን በህይወት ላይ መተከዝ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

« ኧረ ወይኔ ህይወት! »

በተለይ ይህን መድብል በማነብበት ወቅት በ1985( ይመስለኛል ) ታትሞ ለአንባቢ የቀረበው የአንጋፋው ደራሲ አዳም ረታ መፅሀፍ ከሆነው ማህሌት ውስጥ « የአበቦች ታሪክ » የሚለውን አጭር ፅሁፍ እያስታወስኩ መቃበዜን አንባቢ ተረድቶ በሽግግር እንዲጋበዝልኝ ስል በውል ባልጠይቅም እሺ ለሚለኝ ግን አልሽኮረምም።

Reviewer :- © Sirak Wondemu is an associate editor at © Think Ethiopia

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ርዕስ ፦የዱር አበባ
ዘውግ ፦ ግጥም
የህትመት ዘመን ፦ 2017
ገጣሚ፦ ቴዎድሮስ ካሳ
Rating :- 8.9

ማኅሌታዊው ኮከብ ( የዱር አበባ )

ሁለት ሥጋ'ና ደሞች
ሁለት የሥጋ እስረኞች
ገላን ጥለው እሳት ሆነው

አዎ ... እሳት ሁነው !
ፍም ነበልባል ፤ ...
ሕይወት አፈር እንዳትባል
ሕይወት ውኃ እንዳትባል
ሕይወት እሳት ብቻ ሁና !

ሕይወት የዱር አበባ !

Lyrical poetry is a genre of poetry that expresses personal emotions, thoughts, and feelings, often in a musical or song-like manner. It is typically characterized by its focus on the speaker's inner experiences rather than on narrative or storytelling elements.

ስነ ግጥም የአፍላነት ወዝ ጠፈጠፍ ነው ከተባለ የሚገለፀው በሌሪክ የግጥም ዘውግ ሆኖ እናገኘዋለን። ሌሪክ ግጥሞች ግላዊ ስሜቶችን ፣ ሀሳቦችን ና ምናኔ ጠቀስ የሆኑ ጥልቅ ስሜቶችን ሙዚቃዊ ቃናና ምት በማላበስ የሚቀርብበት ዘውግ ነው። በስሜት በተሞሉ ቃላት እንደመልካ ብናኝ የመርጠባቸውና ከውስብስብ ደረቅ ሴራ ይልቅ አንድ አፍታ ወስደው ግላዊ ስሜታቸውን መተንፈስ መቻላቸው እንዲሁም በቅሬታ ውስጥ እንደተገኘ አፍለኛ ሙዚቃ ፤ ዜማ ለበስ ቃናን መቸራቸው ከባህሪ ተቆጥሮ የሚለዩበት ድንበር ነው።

« ትንሽ ቁስል
እድሜ ሙሉ ትዝ የምትል!
የአንቺ ፍቅር
ስር የሚሰድ ከጅማት ስር »
( ገፅ 33 )

ሌሪክ ግጥሞች እንደሁሉን ወዳጅ ትንሽዬ ህፃን ናቸው። ያየ አያልፋቸውም ወደ ደረቱ አስጠግቶ ይስማቸዋል። ከልብ፣ ከነፍስና ከስሜት የሚወለዱ ናቸውና ከጠራቸው ጋር በቀላሉ ስምምነት ይፈጥራሉ። ተግባቢ!

«ይሄ ልጅ ከሁሉ ነዋሪ ነው» እንደሚባለው አይነት መልከኛ...!
የቴዎድሮስ ግጥሞችም እንዲሁ ናቸው። ስዕላዊ መገለጫቸው ረቀቅ ጠበቅ ያለ ውልን እንደዝናር በወገቡ ሸብ ያደረገ ነው።
ከሌሪካዊ የግጥም ዘውግ ባህሪ የሆነው አንዱ የተፈጥሮና የፍቅር ጭብጥ በዚህም መድብል ውስጥ ነፍስ ዘርቶ እንዲንቀሳቀስ እንደረዳው ይሰማኛል።

ተፈጥሮን ስል
ተፈጥሮዬ
ቀዝቃዛ አካል ውስጥ እንደሚዋኝ
ቁስል እንደበዛበት ፍቅር ነው
ረጅም ስሞሽ ያደክመኛል
ዝም ያለ ሰው ይገድለኛል።
( ገፅ 20 )

ፍቅርን ስል

የተጎነጨሁት ወይኑ አልደረቀም
ገና
ጆሮዬ ስር
ስሰማ ያመሸሁት ሙዚቃ አልበረደም።
( ገፅ 27 )

ስዕልን ስል

« የህይዎት ጣዕም
የህይዎት ውበት

ቀዝቃዛ ሻይ
እጅሽ መሃል የበረደ ፤

ግማሽ እድሜ
አንቺን ሲያስብ የነጎደ ፤

ጅምር ሀሳብ
ጅምር ግጥም
ጠርቶ ያመጣው ፤

ውብ ወዘና
ጎረምሳ ሌት የሚጠጣው ። »
( ገፅ 32-33 )

ገጣሚው የሌሊት ፍቅርና ምስጣ እያዘገመ በስንኞቹ ውስጥ እንዲያደባ የፈቀደ ይመስላል። የውብ ሰመመናዊ የትዝታው ጫፎች ፤ የተቋጠሩት በሌሊቱ የዝምዝማት ሸማ ውስጥ ነው።
ዘውትር ማኅሌታይ እንዲባሉ በሌት የተወለዱም ጭምር..!!
ደሳስ የሚሉ ወቅት የወለዳቸው የህይወት የሞቅታ እቅፍ ያባባቸው ስንኞች ልክ እንደልብ ምት በረገጡት አፈር ላይ ሲዘሉ ብርሃን እቅፍ ውስጥ ተወልደው ጊዜን ለመገዘት ሀሳብ ያላቸው ፤ ምሽት ያላቸው ፤ ምኞት ያላቸው አይነት ናቸው።የተቃኑበት ለጋ ሰመመናዊ የወቅት ትንፋሽ በፀዓዳማው የሳቅ ወንዝ እያሳሳቀ እንደሚወስዳቸው ወጣት ውበቶች ናቸው። ለዚህም ይመስለኛል በግጥም ላይ የሚስማሙ በርካታ ምሁራን ፣ አንባቢና ግጥም አድናቂያን ለግጥም የተመረጠ የሚሏት ወቅት ወጣትነትን ነው።
ወጣትነት ለግጥም ገና የፈካ አበባ እንደማለት ነው።
የእንቡጥነት ዘመኗን ባጅታ ብቅ ባለች አበባ ላይ ዓይን ይራኮታል።
ጓጊና ቀጣፊ መዳፎች የእጆቻቸው መንገድ አበባና አበባዋ ጋር ብቻ ይሆናል።

Catharsis የሚባለው ጥንታዊው የግሪክ ፅንሰ ሀሳብ ውስጥ ስለ ግጥምና ስሜታዊ መግለጫን በተመለከተ እንዲህ የሚለው ማብራሪያ ትዝ አለኝ። Poetry provides a means for young people to articulate complex emotions that they may struggle to express verbally. Writing or reading poetry can serve as a cathartic release, helping them process feelings related to identity, relationships, and life transitions.
እኔም ለዚሁ አንድምታ እቀርባለሁ።

ለጋነት ለየትኛውም ኪነ ጥበባዊ ውልደቶች ( በተለይም ለግጥም ) መልከኛው ሰሞን ነው።

ምርጥ ግጥም ማለት
ቃላት ያልነካው ነው ፤
ምርጥ ግጥም ማለት
በሁለት ፍቅሮች መኃል ፤
ያለ ዝምታ ነው
(ገፅ 88 )

ወጣትነት የለጋነት ቤት ከመሆን ባለፈ የስስነት ቋቱ ነው።
ከዚያ በላይ ያለው እድሜ የተግሳፅና የምክር እጀታዎች የሚበዙበት ሲሆን ከዚህ በታች ያለው ደግሞ ልክ በ Sigmund Freud early childhood experience theory መሰረት ደስታዎቻችንን በአፋችን የምናስስበት ሰሞን ነች። ይህም ከቆዳ መገልበጥ በፊትና በኋላ ብለን ልንጠራው እንችላለን። ከመገልበጡ በፊት ያለው ጊዜ መነካት ወደ ስሜትና ትርጉም የሚቀርብበት ለጋ ወቅት ነው። ምሁራኑ ለስነ ጥበብ የተመቸ የሚሉትም ይህቺኑ ዕድሜ ነው። ገጣሚነትና ሁሉን አቀፍ ሚናነትም እዚሁ ጋ በስፋት የሚነሳ ዓብይ ጉዳይ ነው። መሳሳቱና ህመሙን ያወጀበት ታዛ ላቅ ሲል የብዙ ግፉዓን ነፍሶች ማፅናኛ ድንኳን ይሆናል።ይህን ጉዳይ በተመለከተ ገጣሚው ራሱም በገፅ 97 ላይ ይህንኑ ፈርጅ እንዲህ ይዳስሰዋል።

« እሳት!
እሳት!
እሳት!

በእያንዳንዱ ሰው ነፍስ ፤ የምትፈላውን
የውበት ወርቅ ሐርር ፤ ጎንጉኖ ሲለብሳት
እጅግ ያሳዝናል
እንዲህ ያለው ወዳጅ ፤
በቁሙ 'ሚቃጠል
ገጣሚ ይባላል።

(ገፅ 91 )

ቴዎድሮስ ካሳ በውስጡ ሺህ ዓመት ህይወትን የታዘበ ያየ ያስተዋለ በሚመሰል ልክ ብዕሩ የበረታች ወጣት ነው። ቀድሞ ከዘመን መንቃት ዕድሜን ማስከተል የአሪፍ ትውልድ መገለጫ ነውና ቴዲ ከነብስ የሚወለዱ ግጥሞች ባለቤት ነው። ስንኞቹን ለጋነት አይጎበኛቸውም። ለዘብ ብለው የሚተፉት ስሜት ልብ ውስጥ የሚቀሩ ናቸው። የሚቀሩም ብቻ ሳይሆን አንባቢን መያዝ የሚችሉ በሳሎች ናቸው። የታደለ ዘመን እንዲህ ያሉ ብሩህ ወጣቶችን በወቅት አፈሩ ላይ ያጎነቁላል። የዱር አበባን በተመለከተ የቴዎድሮስ ካሳ mystical ማጫወቻዎቹ ውስጥ እሳትን ... ናፍቆትን ና ዝምታን እንድንመለከት እፈልጋለሁ።

እሳት

ከግሪክ አፈታሪካዊ ትርክቶች በመነሳትና እሳት ሰርቆ አሰቃቂ የቅጣትን ፅዋ ከተጎነጫት ፕሮማቲየስ በመነሳትና እሳት የመጀመሪያውና ትልቁ የሰው ልጅ የግኝት ውጤት መሆኑን በመጠቅለል በፊደል ተሰርተው እሳት ከሚረጩ ስንኞች ጋር እናዘግማለን።

ተመልከችው እርሱን
ፍቅር አጠውልጎት ፤
ናፍቆት ፍም አድርጎት
ፍም እሳት ነበልባል ፤
በአካሉ አለሁ ቢልም
የለም እንዳይባል!
( ገፅ 89 )

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

የሃገራችን ደራሲዎች አንደበታቸው እንደ ብእራቸው የተባ ነው ወይ?

መናገርና መጻፍ እጅግ የተለያዩ ክህሎቶች ናቸው። ደራሲዎች በሃሳብ እጥረት አይታሙም። ነገር ግን ሃሳብን በጽሁፍ መግለጽና በንግግር ማስረዳት ፍጹም ለየቅል ናቸው። ወረቀት ላይ ብእር እንዳሻው የሚታዘዝለት ታላቅ ደራሲ ንግግር ላይ አንደበቱን ያዝ ሊያደርገው ይችላል። በአንደበቱም፣ በብእሩም እኩል የሚራቀቅ አለ። ወሬ የበለጠ የሚጣፍጥለት፣ ከጽሁፉ ንግግሩ የሚማርክ ሁሉም ሶስቱም አይነት አሉ። ለሶስቱም አይነት ደራሲዎች እኛ ሃገር ታዋቂ ምሳሌዎች አሉ። ሁሉንም በየተራ እንመልከታቸው።

እጃቸውም አንደበታቸውም እኩል ከሚታዘዝላቸው ደራሲዎች መካከል አለማየሁ ገላጋይና እንዳለጌታ ከበደ ከፊት ረድፍ ተጠቃሽ ናቸው። አለማየሁ ገላጋይ ገና ለመናገር አፉን ሲከፍት ሁለመናዬ ጆሮ ይሆናል። ንግግሩ ተሰምቶ የማይጠገብ ተፈጥሯዊ ፍሰት አለው። ሸገር ካፌ አለማየሁ ገላጋይ ከመአዛ ብሩ ጋር ያደረጉትን ብዙ ክፍል ቆይታ ሁሉንም ተከታትዬዋለሁ፤ ደጋግሜዋለሁ ብል ይቀለኛል። አሌክስ በአንደበቱ በኩል ሃሳብ እንደ ጅረት ይፈስለታል። ዩትዩብ ላይ ያሉ የአለማየሁ ገላጋይ ቪዲዮዎች አንድም አልቀሩኝም። በፍጹም ዝር ከማልበት የቲክቶክ መንደር እንኳን እዚያ የሚገኙ የአለማየሁ ገላጋይን አጫጭር ቪዲዮዎች መርጬ አይቻለሁ። አለማየሁ ገላጋይ ቀኑን ሙሉ ቢናገር ምንም ሳትሰለች የምትሰማው ሰው ነው።

ከሰዎች ንግግር የተረዳሁት አንድ ነገር አለ። ሰዎች ስለ ማንኛውም ጉዳይ ሲናገሩ የሚገልጹት ጉዳዩን ብቻ ሳይሆን ራሳቸውን ጭምር ነው። ሁለት የተለያዩ ሰዎች አንድን ጉዳይ እኩል አብራርተው፣ አፍታትተው አይገልጹም። የውሃ ሜታፎርን እንመልከት። ውሃ ኩባያ ውስጥ ሲገባ የኩባያውን ቅርጽ ይይዛል። ብርጭቆ ውስጥ ስንገለብጠው የብርጭቆውን ቅርጽ ይይዛል። በአጭሩ ውሃው የተቀመጠበትን እቃ ቅርጽ እየያዘ ራሱን ይቀያይራል። እንዲሁ ሃሳብም amorphous ነው። የአሳቢውን ቅርጽ እየተዋሰ ራሱን ይቀያይራል። የአለማየሁ ገላጋይን የሃሳብ ቅርጽ፣ የቃላት አሰዳደር እወደዋለሁ። ማንኛውም ጉዳይ በአሌክስ ምናብ ውስጥ አልፈው በሱ አንደበት ሲገለጹ መስማት ከወሲብ ያልተናነሰ ሜንታል ኦርጋዝም ይሰጣል።

ሌላ አንደበቱ እንደ አሌክስ የሚታዘዝለት ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ነው። እንዳለጌታን ለመጀመሪያ ግዜ ረዥም ቃለመጠይቅ ሲያደርግ የሰማሁት ከመአዛ ብሩ ጋር በሸገር ጨዋታ ነው። ከሸገር ጨዋታ ተወዳጅ ቆይታዎቼ አንዱ ነው። በዚህ ቃለመጠይቅ የተረዳሁት ነገር እንዳለ በስነጽሁፍ ብቻ የሚወሰን ስብእና እንደሌለው ነው። ባህልን፣ ታሪክን፣ ማህበራዊ ኑሮን፣ በአጠቃላይ ህይወትን አስውቦ መግለጽ ይችላል። ሲያወጋ አይደናቀፍም። ቃላትና ሃሳብ አያጥረውም። ነገረ መጻሕፍት እና ከዋልያ ፐብሊሸርስ ጋር በሚያዘጋጀው መርሃግብር ብዙ ግዜ አወያዩ ራሱ ነው። በእርግጥ ጠያቂና ተጠያቂ መሆን ይለያያል። ታዲያ እንዳለጌታ ግሩም ተጠያቂ ብቻ ሳይሆን አሪፍ ጠያቂም መሆኑን ተረድቻለሁ። ሲጠይቅ አይንዛዛም፤ ሃሳብ አይደርትም። የጥያቄውን አስኳል በአጭሩ ለመግለጽ አይሰንፍም። ተጠያቂም ሲሆን ለዛው ሳይነጥፍ ሃሳቡን አብራርቶ መግለጽ ተሰጥኦው ነው። እንደ ሚናው መቀያየር ጠያቂም፣ ተጠያቂም ወንበር ላይ ሲቀመጥ ተገቢውን ገጸባህሪ በአግባቡ ይላበሳል።

ኤፍሬም ስዩም ሲያወራ ከስብሐት ጋር የሚወራረስ ግርማሞገስ አለው። ኤፍሬምን የማያውቅ አድማጭ ኤፍሬም ሲናገር ድንገት ቢሰማው በቀላሉ የስነጽሁፍ ሰው መሆኑን መረዳት ይችላል። በንግግሩ ውስጥ ሁሉ የስነጽሁፍ ሰው መሆኑን የሚያሳብቅ ኳሊቲ አለው። በእርግጥ ኤፍሬም እንደሌሎቹ ሁለቱ ብዙ ግዜ ሲያወራ አልሰማሁትም። ነገር ግን በሰማሁበት ጥቂት አጋጣሚዎች አብዝቼ መደመሜን አስታውሳለሁ። ኤፍሬም ለባለቅኔ የሚመጥን ምትሃታዊ የንግግር ችሎታ አለው።

በእውቀቱ ስዩም ከንግግሩ ይልቅ ብእሩ የሚያምርለት ደራሲ ነው። ጽሁፉ ውስጥ ቁምነገር አለ፤ ለዛ አለ፤ ቧልት አለ። ጥልቅ ሃሳብ ማንም ሊረዳው በሚችል መልኩ በቀላሉ መግለጽ ይችላል። ንግግሩ ላይ እነዚህን ሁሉ እኩል አላገኘኋቸውም። ከመአዛ ጋር በሸገር ጨዋታ ያደረገውን ቆይታ ሰምቼያለሁ። በመጨረሻ የተረዳሁት በእውቀቱ ጽሁፍና ንግግር እኩል የሚሄዱለት ደራሲ እንዳልሆነ ነው። በደራሲያን ቃለመጠይቅ የምንጠብቀው ንግግር እንደ ጽሁፍ ሲሰምርላቸው ማየት ነው። ሁለቱ እጅግ የተለያዩ ክህሎቶች መሆናቸውን አንረዳም። ጽሁፉ የሰመረለት ሁሉ ንግግር ላይሰምርለት ይቻላል። እንዲያውም ጥናቶች እንደሚያመለክቱት አብዛኛዎቹ ብርቱ ደራሲዎች አንደበተ ርቱእ አለመሆናቸውን ነው። አንባቢ ግን በወረቀት ላይ ያየውን የሃሳብ ፍሰት በንግግርም ይጠብቃል። ደራሲያን አንደበተ ርቱእ ካልሆኑ ሃሳብ አጥሯቸው ሳይሆን ሃሳባቸውን በንግግር የመግለጽ ችሎታ አንሷቸው መሆኑን መረዳት ይገባል። ሁለቱ በጣም የተለያዩ ኳሊቲዎች ናቸው።

አዳም ረታ ሌላው ብእር እንዳሻው የሚታዘዝለት፣ ነገር ግን አንደበቱ የብእሩን ያህል ርቱእ ያልሆነ ደራሲ ነው። በእርግጥ አዳም ረታ ከልቡ ደራሲ ነው። ነገር ግን ከደራሲነቱ ብቻ ተነስተን አንደበተ ርቱእ ተናጋሪ እንዲሆን መጠበቅ ሞኝነት ነው። ጽሑፍ ሌላ ንግግር ሌላ። ርቱእ ተናጋሪ አለመሆኑም ከደራሲነቱ ላይ የሚያጎድለው ነገር የለም። ከመጀመሪያውም ደራሲ የሆነው ሃሳቡን በንግግር ከመግለፅ ይልቅ በቃላት ማስፈር ስለሚቀናው ነው። የተሰጠው ጽሑፍ ነው። በጽሑፍ እንዳሻው ይራቀቃል። ሃሳቡን መስማት የፈለገ 10+ መጻሕፍቱን ማንበብ ነው። ሰውዬውን አዳም ረታ መጽሐፎቹ ውስጥ ማግኘት እንችላለን።

እዚህ ጋር አንድ ገጠመኝ ላጫውታችሁ። ስብሐት ገብረእግዚአብሔር የመነን መጽሔት ሪፖርተር ሆኖ አለቃው በአሉ እንዲህ ይለዋል፦

"ለመጽሔታችን ሃዲስ አለማየሁን አነጋግረህ ቆንጆ ጽሁፍ እንድታዘጋጅ እፈልጋለሁ።"

"እኔ እኮ እንደዚህ ዝነኛ ሰው ማናገር አይሆንልኝም"

"አይዞህ አብሬህ እሄዳለሁ"

በአሉ እና ስብሐት ተያይዘው ደራሲ ሃዲስ አለማየሁ ቢሮ ሄዱ። ሃዲስ ከወንበራቸው ተነስተው በፈገግታ ሰላምታ ከሰጧቸው በኋላ እንዲህ አሌቸው፦

"በ500 ገጽ ያወራሁት አልበቃ ብሏችሁ ነው ዳግም ልታናግሩኝ የመጣችሁት"

እያንዳንዱ መጽሐፍ የደራሲው መንፈስ ቅሪት አለበት። ደራሲውን በገጸባህሪያቱ፣ በታሪኩ ውስጥ እናገኘዋለን። በፍጥረት ውስጥ የፈጣሪው መልክ ሁሌም አለ።

ከድሮ ደራሲዎች ከአንጋፋዎቹ በድምጽ የተቀዳ ቃለመጠይቃቸውን የመስማት እድል ያገኘሁት የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህንን ነው። ታዲያ በቃለመጠይቃቸው ውስጥ የሃሳባቸው ውፍረትና የሚጠቀሙት የቃላት ሃብት፣ አስቀድሞ በጥንቃቄ የተዘጋጀ ጥንቅቅ ያለ ንግግር የሚያነቡ እንጂ እንዲያው በደፈናው ከአእምሯቸው ማህደር እያወጡ የሚናገሩ አይመስሉም። ሎሬቱ ሲጽፉ ብቻ ሳይሆን ንግግራቸውም መጽሐፍ ነው።

ከጽሁፎቹ ይልቅ፣ ከመጽሐፎቹ ይበልጥ ንግግሩን የምወድለት ደራሲ የስነ-አእምሮ ባለሙያው ምህረት ደበበ ነው። እንዲያውም ዶክተር ምህረትን ደራሲ ከማለት orator/ተናጋሪ ማለት የበለጠ ስሜት ይሰጠኛል። በእርግጥ ዶክተር ምህረት የስነጽሁፍ ባለሙያ አይደለም። በጻፋቸው ሁለት ልብወለድ መጻሕፍት ለማስተላለፍ የሞከረው ስነልቦናዊና ስነአእምሯዊ ሃሳቦችን ነው። ሃሳቦቹ ጠቃሚ ቢሆኑም ከልብወለድ ይልቅ በኢልብወለድ መልክ ቢቀርቡ የተሻለ ነበር የሚል አስተያየት አለኝ። የተቆለፈበት ቁልፍና ሌላ ሰው ለአንባቢ የሚጠቅሙ ጠንካራ ሃሳቦችን ቢይዙም በገጸባህሪ አሳሳል፣ በሴራ አወቃቀር እና በሌሎችም መሰል የስነጽሁፍ መለኪያዎች

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

በአንድ ሺህ አምስት መቶ ኪሎሜትር ሬዲየስ ላይ ያሉ ዛፎች በሙሉ ወደ ከሰልነት ተቀይረው አደሩ፡፡ ባንድ ቅፅበት፡፡ የኮከቡ ፍንዳታ በምድሪቱ ላይ የፈጠው ጉድጓድ ተገኘ? በፍጹም! ምንም የተወው ፊዚካል ኤቪደንስ የለም፡፡

ግን ከመሐል የሚነሳ እንደ ጨረር የመሰለ ወጨፎ... በዙሪያው ያሉትን ዕፅዋት ሁሉ ልክ ከመሀል ወደ ውጭ ክቡ የሆነ ሃይለኛ ንፋስ ያለው ገሃነመ እሳት እንደተረጨባቸው ሁሉ አክስሏቸው ተገኘ፡፡ በአንዲት ቅጽበት 80 ሚሊየን የሳይቤሪያ ዛፎች በገሃነመ እሳት ጭዳ ሆኑ! 80 ሚሊየን ዛፎች!!

የዚያ የሳይቤሪያ የሠማይ ላይ የኮሜት ፍንዳታ ጨረር ውጤት ግን በተለያዩ ከፖላንድ እስከ ካናዳ ባሉ ምድሮች ላይ፣ በረዶዎች ላይ ውጤቱ ታይቷል፡፡ ሌላ የተከተለ ኬሚካላዊ መመረዝና ሌሎች ነገሮች አልተገኙም፡፡ ፎቶግራፉን በዚህ መጽሐፍ አካቶታል ግራሃም ፊሊፕስ፡፡

የ1486ቱ ኮሜት ግን ከግዝፈቱ የተነሳ፣ በወቅቱ የነበሩ ሥልጣኔዎች ሁሉ ወይ እግዜሩ ራሱ ነው በአካል በአምሳል የተገለፀው ብለው አምነዋል፡፡ አሊያም ከፈጣሪ ሥራ የተነሳ ተደንቀው ቀደም ባለ ዘመን የያዙትን እምነት ሁሉ ቀይረው አዲስ የአንድ አምላክ እምነትና ገለጻዎችን ሁሉ አስጀምሯቸዋል፡፡

የጥንታዊ ቻይናም የጥንታዊ ግብጽም የአስትሮኖሚ ዘጋቢዎች፣ የዚያን ጊዜውን ኮሜት ሲገልጹት፣ ከፀሐይም የበለጠ የሚያበራ፣ አስር ጅራቶች ያሉት፣ ፍላፃዎቹ ብዙ ቦታ የሚከፋፈሉ፣ ከማንኛውም ታይቶ ከሚታወቅ ብርሃን በላይ የሚያንፀባርቅ ሲሉ ነው የገለፁት፡፡

የዚህ ኮከብ ጅራቶች ለምድሪቱ በጣም ቅርብ ሆነው፣ በትሮቶስፌር ላይ ፈንድተው፣ ከምድሪቱ ጋር ሳይላተሙ ተላልፈዋል ማለት ነው፡፡ ያም ደግሞ በምድሪቱ ላይ መቅሰፍቶችን አምጥቷል፡፡

ያ የዛሬ 3ሺ500 ዓመት በምድሪቱ ሠማይ የፈነዳ የኮከብ ገሞራ በሰው ልጅ አንጎል ነርቮች፣ በሰው ልጅ የነርቭ ሥርዓት ላይ ቬሶፕሬሲን የመሰለ ኬሚካል ረጭቶበታል፡፡ የሰውን ልጅ አስተሳሰብ በማይመለስ መልኩ አቃውሶታል፡፡ በሰው ልጅ ልብ ውስጥ አደገኛ የመገዳደል መንፈስ አስርፆበታል፡፡ አደገኛና እርስ በርስ የሚያጨራርስ የኃይለኝነትንና የጠበኝነትን መንፈስ በሰውነቱ ለኩሶበታል፡፡

ይሄ ቬሶፕሬሲን ማለት - በአሁን በዘመናዊው ዓለማችን ‹‹ሃይድሮጂን ሳያናይድ ጋዝ›› ማለት ነው፡፡ ሳዳም ሁሴን አምርቶ በከፍተኛ መጠን ሊተኩስብን አከማችቶታል ተብሎ የተከሰሰበት የነርቭ ጋዝ ማለት ነው፡፡ አሁን እነ ራሺያና አሜሪካ በገፍ አላቸው፡፡ ላለመጠቀም ስምምነቱ አለ፡፡

ሠይጣኑ በምድሪቱ የነገሠ ቀን፣ እነዚህ ጋዞች በሰው ልጅ ላይ ሲለቀቁ፣ ወንድም ወንድሙን፣ እናት ልጇን እየዘለዘሉ፣ ልጅ በአባቱ ላይ እየተነሳ መጨራረስ ይሆናል! የምድሪቱ ፍጻሜ ብለው ቅዱሳን መጻሕፍት የሚያስቀምጡትም ከዚህ በምንም አይለይም - ይላል ግራሃም ፊሊፕስ፡፡

የየሐይማኖቱ ሰዎች የየራሳቸው አተረጓጎምና ምሣሌያዊ አረዳድ ቢኖራቸውም፣ ለምሳሌ የዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 8፥10-12 ላይ ያለውን እስቲ ገልጣችሁ እዩት ይላል ግራሃም ፊሊፕስ፡፡ እና በቀደመው ዘመን በምድሪቱ የወደቀው ኮሜትና የፈጠረውም ውጤት ይሄንኑ ነበር ይለናል፡፡ እና...?

ቅዱሳን ነብያት ቀድሞ የተፈጸመውን ሰምተው፣ አንብበው፣ ተነግሯቸው፣ ወይ ተገልጦላቸው ጻፉት? ወይስ ድጋሚ እንደሚከሰት ተገልጾላቸው ተነበዩት ብለን እንቀበል? ብሎ ይጠይቃል፡፡

የመጽሐፍ ቅዱስ የዮሐንስ ራዕይ (ረቨሌሽን) ምዕራፍ ስምንት፣ ከቁጥር አስር ጀምሮ እንዲህ የሚል ገለጻን የያዘ ነው፡-

‹‹ሁለተኛውም መልአክ መለከቱን በነፋ ጊዜ
ተራራ የሚያህል ታላቅ እሳት እየነደደ ወደ
ባህር ወረደ፣ የበ ህርም ሲሦዋ ደም ሆነ፡፡ በባህ
ርም ውስጥ የሚኖሩ ህይወት ካላቸው ፍጥረቶች
ሲሦው ሞተ፣ የመርከቦችም ሲሦአቸው ጠፋ፡፡

‹‹ሦስተኛውም መልአክ መለከቱን በነፋ ጊዜ፣
እንደ ችቦ የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ ከሰማይ
ወረደ፣ በወንዞችና በውሃ ምንጮች ሲሦ ላይም
ወደቀ፡፡ የዚያም ኮከብ ስሙ እሬቶ ነው፣
የውኃዎችም ሲሦአቸው ሬት ሆነ፣ ከውኃዎ
ችም ምሬት የተነሣ የሞተው ሰው ብዙ ነው፡፡››

እያለ ይቀጥላል፡፡ ኮከብ ከሰማይ ወደ ምድር ሲወድቅ አየሁ የሚሉ በርካታ ቃሎችንም የያዘ ነው ይህ የዓለምን ፍጻሜ ምልክቶች የሚናገር ተብሎ በብዙዎች የሚታመንበት የዮሐንስ ራዕይ፡፡

እና ግራሃም ፊሊፕስ አበክሮ ይጠይቃል፡፡ ይሄው የፍጻሜ መቅሰፍታችን፣ ቀደም ብሎም ከሶስት ሺኅ አምስት መቶ ዓመታት በፊት በምድራችን ላይ በጥቂቱ ተከስቶ ነበር፡፡

ውጤቱም ልክ አዳምና ሄዋንን ሠይጣን ካሳታቸው በኋላ ምድር በኬኦሶች እንደተሞላችና ፍጡራን ወደ ቸነፈርና መገዳደል ምድራዊ ህይወት እንደገቡት ሁሉ፣ እና የገነትን እርሻ እንዳጡት ሁሉ፣ ልክ እንደዚያው ነው የሆነው የዛሬ 3500 ዓመት ይለናል፡፡

በምድሪቱ ላይ የፈነዳብን አብሪ ኮከብም፣ ገነት የመሰለ፣ የሰው ልጅ በመፈቃቀርና በመፈቃቀድ በሠላም የሚኖርበትን ገነታችንን አሳጥቶ፣ በጦርና በጉልበት፣ በጦረኝነት ወደተቃኘ፣ መገዳደልና እርስበርስ መጫረስ፣ ማስገበርና መገበር፣ ባርነትና ጌትነት፣ ገዳይና ሰለባነት ወደሞላበት ወደዚህ ዘመኑ አዲስ የሥልጣኔ አቅጣጫ አንደርድሮ ጨምሮናል - በማለት ይደመድማል፡፡

ይህን ድንቅ መጽሐፍ ሳነብ፣ የራሴን ብዙ ቀደም ብዬ አስባቸው የነበሩ ነገሮችን፣ በአጋጣሚ በጆሮና ዓይኔ፣ በሃሳቤ ጥልቅ ብለው ያለፉ ምስሎችን ሁሉ እያውጠነጠንኩ ነበር፡፡ ...

እና ብዙ ጥያቄዎችን፡፡ እውነት በዚህ ዓይነት መንገድ ካልተተነተነ በቀር፣ እውን የቀደሙ ሥልጣኔዎቻችንን የፈጠሩት፣ የተራቀቁበት ሰዎች እንዴት ደብዛቸው ሊጠፋ ቻለ? የሆነ የመጥፋት፣ የመጠፋፋት ዘመን የሆነ ያመጣው አንድ የቀደሙ ሥልጣኔዎች ደብዛ የመጥፋት፣ አንዱ በሌላው የመዋጥና ተረስቶ የመቅረትም ምድራዊ ክስተትማ መኖር አለበት!

ይሄማ እንኳን ማስረጃ ተደርድሮለት፣ እንኳን ከዓለሙ ሁሉ ጋር ተዛንቆና ተሰፍቶ፣ እንዲሁም ሁሌ ራሳችንን የምንጠይቀው ምላሽ ያላገኘንለት ጥያቄ ነው፡፡ እና በሁሉም ነገሩ ባያስማማ፣ ብዙ ያመራምራል፡፡ ያስደንቃል፡፡ ያስደምማል፡፡ ጥያቄዎቹ ያነቃሉ፡፡ ለተመሳሳይ ጥያቄዎች ይጋብዛሉ፡፡

በእርግጥ ግራሃም ፊሊፕስ፣ ልክ እንደ ነፍሰ-መንትያው እንደ ግራሃም ሃንኮክ ሁሉ፣ የቀደመውን ዘመን ብቻ ተንትኖ አያበቃም፡፡ ይሄን መጽሐፍ የጻፈው በ2007 ላይ ነው፡፡ እና በእሱ ትንታኔ፣ ከ1486 ጀምሮ በየ71 እና 72 ዓመቱ ምድርን የምትጎበኝ፣ የዚያ ኮሜት ጭራፊ ኮማዎች አሉ፡፡ ወይም ምድራችን በየ71 ዓመቱ በዚያ ቀሳፊ ኮሜት ኦርቢት እየተጠጋች ታልፋለች፡፡

ለምሳሌ በ1812 እኤአ፡፡ አሜሪካኖችና እንግሊዞች ጦርነት የጀመሩበት ነው፡፡ በ1954 በዓለም ተመሳሳይ ጦርነቶች በያገሩ የፈነዳዱበት ወቅት ነበር፡፡ ...

እና አሁን በ2024 ደሞ ‹‹12P/Pons-Brooks›› የሚል ስያሜ በሁለት ፈረንሳዊና አሜሪካዊ ተመልካቾቿ ስም የተሰየመችው ይህቺው የኮሜቱ አካል ወደ ምድር ትቀርባለች፡፡ ወይም በምድር ጨረሯን ትፈነጥቃለች፡፡ እና በ2024 ምን ይገጥመን ይሆን? ብሎ ነው የሚያበቃው፡፡

/በነገራችን ላይ ይቺ ኮከብ (ኮሜት) ከአራትና አምስት ወራት በፊት (በጁንና ጁላይ ላይ) በምድር ላይ ታይታለች፡፡ ግን ያስከተለችው ጉዳት የለም፡፡ አሁን ደሞ ሰሞኑን (ከሶስት ቀናት በፊት በዲሴምበር 14 ቀንም) ለመጨረሻ ጊዜ የታየችበት ነው፡፡/

ይህን የግራሃም ፊሊፕስን መጽሐፍ ያነበበ፣ የሰማ፣ ጥያቄዎችን የጠየቀ ሰው ሁሉ፣ ይቺ ጦሰኛ ኮከብ ከምድራችን በሠላም ውልቅ የምትልበትን ቀን መናፈቁ አይቀርም፡፡

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ከሠማይ የወረደ . . . !
_____

(ፍርፍር ወይስ እዝን? እሳት ወይ አበባ?)

ወንድሜ፣ ብዙ ጊዜ ደጋግሜ ይሄን Graham Hancock የሚባል እንግሊዛዊ ነገር ፈልፋይ ጋዜጠኛና ጥልቅ ተመራማሪ ጽሑፎች እያፈላለግክ አንብብ ብዬ ነግሬሃለሁ፡፡

የሚናገራቸውና የሚያገኛቸው አነጋጋሪ ፍንጮች፣ እና እነሱን እያገጣጠመ የሚፈጥራቸው ትርክቶች የግድ የነጠሩ እውነቶች ስለሆኑ ግን አይደለም፡፡ እውነት ሊሆኑም፣ ላይሆኑም ይችላሉ፡፡ ግን አብርሆቱ ደስ ይላል፡፡ ግኝቶቹና ጥያቄዎቹ በግርምት ይዘውህ ይሄዳሉ፡፡

ግርሃም ሃንኮክ፣ ተቀብለህ የኖርካቸውን ‹‹እውነቶች›› በብርቱ ጥያቄ ምልክቶች ውስጥ እንድትከታቸው ያስገድድሃል፡፡ አዲስ ዓይነት አመለካከትን ይፈነጥቅብሃል፡፡

ከፈለግክም ክብሪት ተፋጭቶ የእሣት ብልጭታ እንደሚያወጣ ባለ መልኩ፣ ያንተን እውነቶች ከእርሱ መላምቶች ጋር አጋጭተህ የሚፈጠርልህ ብልጭታ እጅግ ሲበዛ አዝናኝና አስደማሚ ነው፡፡

ይሄ እንግሊዛዊ የቀድሞ ፈልፋይ ጋዜጠኛና ብርቱ ተመራማሪ Graham Phillips ማለት፣ ቁርጥ ራሱኑ ግራሃም ሃንኮክን ማለት ነው፡፡ አንድም ሁለትም ናቸው፡፡ በብዙ ነገራቸው በእጅጉ ይመሳሰላሉ፡፡

ይመሳሰላሉ ብቻ ሳይሆን፣ የአትኩሮት አቅጣጫዎቻቸው፣ ፍለጋዎቻቸው፣ የጥያቄዎቻቸው ደፋርነት፣ እና የሚያነሷቸው መላምቶች... በብዙ መልኩ የተዛመዱ... ከፈለግክም መንትያማቾች ናቸው ብልህ ይቀለኛል፡፡

ግራሃም ሃንኮክ ጋዜጠኛ ነበር፡፡ ግራሃም ፊሊፕስም እንደዚያው፡፡ ግራሃም ሃንኮክ ስለ ሙሴ-ታቦት መሰወርና አድራሻ ቅንጥብጣቢ ማስረጃዎችን እያፈላለገ፣ መዳረሻ ነው ብሎ የደረሰበትን ድምዳሜ በመጽሐፍ አሳትሞ ለዓለም አስነብቧል፡፡

ግራሃም ፊሊፕስም እንደዚያው፡፡ እርሱም ስለ ታቦቱ የራሱን አሰሳና ምርምር አድርጎ የሚናገረው የራሱ የደረሰበት ግኝት አለው፡፡

ግራሃም ሃንኮክ ስለ መካከለኛው ዘመን ቴምፕላሮች በእጅጉ ይመሰጣል፡፡ ይሄ ግራሃም ፊሊፕስም እንደዚያው፡፡ መጻሕፍትንም ጭምር ጽፏል፡፡

ግራሃም ሃንኮክ ስለ ግብጽ ፒራሚዶች፣ የነገሥታትና የአማልክት ታሪኮች፣ እና አስትሮኖሚ-ነክ ስለሆኑ ጉዳዮች የራሱ ጥናቶችና ምርምሮች አልበቃ ብለውት፣ በትልቅ በጀት አሉ የተባሉ ተመራማሪዎችን አሠማርቶ የጻፋቸው መጽሐፍትና የሚሰነዝራቸው መላምቶች ከማስደመምም በላይ ናቸው፡፡

ይሄኛው ግራሃም ፊሊፕስም እንደዚያው ነው፡፡ ምናልባትም በአንዳንዶቹ የግብጻውያን ዘመናት ላይ (የአሜኔቶፕ፣ የራምሰስና የአክናተን ዘመኖችን በተለይ) ከማንም በዓለም አለ ከተባለ ተመራማሪ በላይ ተመራምሮ፣ አሁን እንደ ትልቅ ማጣቀሻም፣ መወዛገቢያም የሆኑ ራሳቸውን የቻሉ ድርሳናትን ያበረከተ ሰው ነው፡፡

ግራሃም ሃንኮክ፣ በኢትዮጵያ ጀምሮ፣ ወደ ሱዳን፣ ከዚያ ወደ ግብጽ ተሻገረ፡፡ በግብጽ ላይ ከመጠን በላይ ተወስውሶ ብዙ ዓመቶቹን የግብፆቹን ቀመሮችና ሳይንቲፊክ ዲስከቨሪዎች በመመርመር አሳለፈ፡፡

ከዚያ ግን ሳይወድ በግዱ ከአፍሪካውያን ጋር ወደሚመሳሰሉትና በብዙ ነገር ተያያዥነት ወዳላቸው ወደ ላቲን አሜሪካ ቀደምት ሥልጣኔዎች፣ ወደ እስያ ስልጣኔዎች፣ ወደ ህንድና ወደሌሎችም መሰል አብነቶች አሠሳ ተሸጋገረ፡፡

እና ከዚያም አልፎ... በመጨረሻ... ከምድረ-ገጽ የጠፋ፣ በውሃ የተዋጠ አንድ የመጠቀ የሰው ልጅ civilization ነበረ ወደሚል መደምደሚያ ያመሩ በርከት ያሉ ጥልቅና አህጉር-ተሻጋሪ ምርምሮችና ማሰናሰሎች ውስጥ ገባ፡፡ ዳጎስ ያሉ እጅግ አዳዲስ አማራጭ የሰው ልጅ ታሪክ መላምቶችን የያዙ አስገራሚ መጽሐፎችንም አሳተመ፡፡

ይሄ ግራሃም ፊሊፕስም ደግሞ ያውና ተመሣሣይ ምህዋርን ተከትሎ እንደተጓዘ ስትመለከት ምን ይሰማሃል? ግራሃም ፊሊፕስም፣ ከሐይማኖት-ነክ ነገሮች ይጀምራል፡፡

ገና በሰባዎቹና ሰማኒያዎቹ፣ ከብዙ ዓለም ዓይኖች የተሰወሩ የቫቲካን አርካይቮችን መርምሮ፣ የማርያም መቃብር ሊሆን የሚችለው እዚህ ቦታ ነው፣ ቫቲካን የምታውቀውን ምስጢር ደብቃለች የሚል ሰፊ ትንታኔ የያዘን አወዛጋቢ መጽሐፍ ጻፈ፡፡ አልበቃውም፡፡

በጥንታዊ የማያና የአዝቴክ፣ የግብጻውያንና የእስራኤላውያን፣ የሜሶፖታሚያውያንና የአሶራውያን፣ የቻይናውያን፣ የህንዳውያንንና የተለያዩ የቀደምት ሥልጣኔ ባለቤት የነበሩ ህዝቦችን በቁፋሮ የተገኙ ቅርሶች፣ መጻሕፍት፣ ስዕሎች፣ በካርቦን ዴቲንግ የተረጋገጡ ቀኖች፣...

እና በተለይ ከጥንት አስትሮኖሚካል ኦብዘርቬሽኖች እስከ ዘመናዊ የናሳ ምርምር ውጤቶች ድረስ እያሰሰ - በመጨረሻ - ልክ እንደ ግራሃም ሃንኮክ ሁሉ (የትኩረት ዘመናቸው ቢለያይም) - ይሄ ግራሃም ፊሊፕስም፣ ከዚህ ቀደም በምድሪቱ የነበረ፣ ግን በሚገርም አጋጣሚ፣ በአንድ ተመሳሳይ ዘመን የጠፋ የዓለማችን ስልጣኔ አለ ይላል፡፡

አሁን በመጨረሻ ግራሃም ሃንኮክ የምድሪቱ ነገር አልቆበት፣ በብዙ ቀደምት ቅዱስ ድርሳናትና ቀደምት ሥልጣኔዎች ላይ የተገለጹ የዓለምን ፍጻሜ የሚያመላክቱ መዛግብትንና ገለጻዎችን ሁሉ አሰባስቦ ሲጨርስ (ማለቴ እስኪበቃው ድረስ ካሰባሰበ በኋላ) ግራሃም ሃንኮክ፣..

እነዚያ ጥንታዊ ህዝቦች ሁሉ ወደ ሠማይ ያንጋጠጡበትና ያንን ያህል ርቀትና ምጥቀት ውስጥ ገብተው ስለ ሠማያት የመረመሩበት አንድ ትልቅ ተመሳሳይ ምክንያት መኖር አለበት ከደመደመ ቆየ፡፡

ታላቁ የምድርን ሥልጣኔ ያጠፋው መቅሰፍት ምንጩ ከሠማይ በመሆኑ ነው፣ ከሠማይ የዘነበ ወይም የምድሪቱን አካሎች ሁሉ ያቀዘቀዘ - የበረዶ ዘመን የለቀቀ - በውሃ ምድሪቱን ያጠፋ አንድ የሆነ ካታክሊዝሚክ፣ አፖካሊፕቲክ ዓለማቀፍ ክስተት ነበረ የሚሉ ድምዳሜዎቹን በተለያዩ ሳይንሳዊና ትረካዊ ማስረጃዎች አስደግፎ በመጽሐፎቹ ማቅረብ ከጀመረ በጣም ቆየ፡፡

አሁን በመጨረሻ ናሳ የደበቀን፣ በምድሪቱ ላይ ያደፈጠ፣ መሬት በድንገት በተወርዋሪ ኮከቦችና የህዋ ስብርባሪ አለቶች ተመትታ የምትጠፋበት እጅግ አስጊ አደጋ አለ በማለት፣ ማስረጃዎቹን ይዞ ከናሳ ጋር ግብግብ ላይ ነው ግራሃም ሃንኮክ፡፡

ዘመኑን ሙሉ ሲያራክሱትና ሲያጣጥሉት ኖረው፣ በቅርቡ እሱ ከሚላቸው ነገሮች ውስጥ የተወሰኑት የሚቀበሉ (ያመኑ) መረጃዎችን ለህዝብ ይፋ አድርገዋል፡፡

ግራሃም ሃንኮክ ከታቦተ ጽዮን፣ ወደ ምድር እየተምዘገዘጉ እስካሉ የህዋ ስብርባሪዎች ድረስ የሄደበትን ጉዞ ተደምመህ ትከታተል ይሆናል፡፡ ቀንህን ያበራልሃል፡፡ ስለ ዓለም - ስላለፈውም ስለአሁኑም ሆነ ስለ መጪው ደሳስ የሚሉ ጥያቄዎችን ያቀብልህና ይህቺን አንዲቱን ዓለምህን ያበዛልህ ይሆናል፡፡ ትወደዋለህ፡፡

ዕድሜውን ሙሉ የማይረሳ፣ እና የወደፊት ዘመን የሚያመሰግነው ታላቅ አዲስን መገለጥ አስጀምሮ ለመሄድ ቆርጦ የተነሳ ሰው ይሆንብኛል ግራሃም ሃንኮክ፡፡ አንብቤ አልጠግበውም፡፡

ይሄ ግራሃም ፊሊፕስም ደግሞ፣ በራሱ መንገድ፣ ልክ እንደ ግራሃም ሃንኮክ ሆኖ የማገኘው (የነፍስ መንትያው ልበለው?)፣ የነፍስ መንትያው ይሆንብኛል፡፡ ብሎ ብሎ፣ ሄዶ ሄዶ ደግሞ፣ ግራሃም ፊሊፕስም (እንደ ግራሃም ሃንኮክ)፣ የዓለም ሥልጣኔ ከዚህ ቀደም ከክርስቶስ ልደት በፊት በ1486 ዓመተ ዓለም ላይ፣ ከሠማይ ተምዘግዝጎ ወደ ምድር በተወረወረ አንድ ጅራታም ኮከብ የተነሳ ጠፍቷል ይለናል፡፡

ለዚህም ከበቂ በላይ ማስረጃዎች አሉኝ ብሎ - ከላቲን እስከ ቻይና፣ ከራሺያ እስከ እንግሊዝ፣ ከግብጽ እስከ ቱርክ፣ የማስረጃ ዓይነቶችን ይደረድርልሃል፡፡

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

መውጫ፡- ‹‹ለምንን ፍለጋ›› ከታሪካዊ ዘገባ ይልቅ፣ የሙድ ጽሑፍ እንደሆነ ይሰማኛል። በትርጉም ሥራው ላይ በስፋት የተካተቱ የግርጌ ማስታወሻዎች ወገግታን ይፈጥራሉና ሌሎች ተርጓሚዎች ፈለጉን ይከተሉት እላለሁ። ከዚህ በዘለለ፣ ያለአግባብ የተጣመሩ ቃላት በትርጉም ሥራው ላይ ሠፍረዋል። (ጥምር ቃላት፡- ለምሳሌ ‹‹ሥጋ›› እና ‹‹ቤት›› የሚሉ ቃላት ሲጣመሩ - (ሥጋ-ቤት) - ትክክለኛ ፍቺ ያለው ቃል እንደሚፈጥሩ ይታወቃል፤ ነገር ግን በ‹‹ለምንን ፍለጋ›› ውስጥ በርካታ ቃላት ያለግብራቸው ተጣምረው ተገኝተዋል /ምናልባት በድንገት/። በንባብ ወቅት መታከትን ሊፈጥሩ እና ትርጉም ሊያዛቡ ይችላሉ። ‹ከልጅ ልጅ ቢለዩ› ነውና፣ ይኼ ሃቲት ንጡል ሳይሆን፤ ዋናውንና ትርጉሙን ሥራ በወፍ-በረር የማየት ሙከራ ነው።

Reviewer :- © Yonas Tamiru is an associate editor at © Think Ethiopia

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ከፍተኛ የሥነልቦና ጫና አላሳደረምን? ምትክ ያለአባት ማደጓስ ፍካሬ ይፈልግም የለ?

ጋሽ አዳም ደንበኛ ንቡር ጠቃሽ ነው። በእነ ስንዝሮ በኩል ሚቶሎጂያዊ ንቡር ጠቃሽ (Mythological Allusion) ፣ በዮሐንስ ወላይሶ ገጸባሕርይ አማካኝነት ኅዳግ ላይ የሚያነብራቸው አንዳንድ ሐሳቦች ሥነጽሑፋዊ ንቡር ጠቃሽ (Literary Allusion) እና ታሪካዊ ንቡር ጠቃሽ (Historical Allusion) ፣ በምትክ እና በስንዝሮ ልጅ በኩል ያሉ አንዳንድ ትዕምርታዊ ኩነቶች ቅይጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ንቡር ጠቃሽ (Mixed Biblical Allusion) ሊባል የሚያስችል በመኾኑ በተቋማት ለሚደረጉ ጥናታዊ ጽሑፍ ኹነኛ ግብዓት መኾን የሚችል ሥራ ነው፡፡ በውሻ፣ ቢራቢሮ እና መሰል እንስሳት ያስቀመጣቸው ፋንታሲ መሰል የብዕር ውጤት በአሊጎሪካዊ (Allegorical) ወይም ጋሽ ዓለማየሁ ሞገስ እንደ ሚሉት ጽላሎታዊ በኾነ መንገድ ለመመርመር ምቹ መኾናቸውን ጥቁምታ መስጠቱ መልካም ነው።

የስንብት ቀለማት እንጀራ ነው ብንል፣ እርሾው የመጀመሪያዎቹ ገጾች ናቸው። እርሾ ይጎመዝዛል። ሽታውም አይስብም። እንጀራው እንጀራው የሚኾነው ግን በእርሾው ነው። የመጽሐፉ ሁለንተና እነዚህ የመጀመሪያ ገጾች ናቸው። ሁሉም ሰው አንብቦ ከጨረሰ በኋላ ወደ እነዚህ ገጾች ተመልሶ መጥቶ ማንበብ አለበት ባይ ነኝ። የጋሽ አዳም የመጀመሪያዎቹ ገጾች ወንፊትም ናቸው። ትክክለኛ አንባቢውን ከመንገደኛው ማጥለያ ገጾች ናቸው። ዝግ በር ነው። የቻለ የሚከፍተው። ያልቻለው “ውስጡ ያለውን ወርቅ ማግኘት ስለሚቸግረው በከንቱ እንዳይለፋ በጊዜ የሚመልሰው ነው።

ይህን መጽሐፍ ያነበብኩት ከወዳጄ ቲጂ ጋር ነው። ያነበብነውን በየቀኑ እንወያይበት ነበር። ከዚህ ሪፍሌክሽን የተለየና ውብ የኾነ ሌላ ዕይታ በሷ በኩል ታገኛላችሁና ሜንሽን ባደረግኳት ማስፈንጠሪያ በኩል ወደ ፌስ ቡክ አድራሻዋ በመዝለቅ አድማሳችሁን እንድታሰፉ ጥቆማ እሰጣለሁ።

አመሰግናለሁ!
©ቢኒያም አቡራ
ሕዳር 28 / 2017 (ብሔሬን ለማስታወስ አንድ ቀን ሲቀረኝ)

Reviewer :- © Binyam Abura is an associate editor at © Think Ethiopia

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

በኅብረት ለንቦጫቸውን ሲጥሉ ነው … ዘመናዊ (ማለት ደግሞ) የሰው ጉዳይ ይናቅና ቁሳቁስ ከሰው በላይ ሲሰለጥን ነው - ዘመናዊነት በረታ ሲባል ሥጋ ጠፋ” ሲል እናገኘዋለን። ሳምራዊው፥ የውሻው ዮሐንስ ወላይሶ እንደ ማለትም አይደል? እንለጥቅ!

አሊጎሪካዊ አንድም ዘይቤ አንድም የፍቺ ሥርዓትም አይደል? ክርክሩን ለጋሽ ብርሃኑ ገበበየሁ እና ለጋሽ ዓለማየሁ ሞገስ ትተን አንድ አፍታ የሁለቱንም ሐሳብ እንቀበል። ውሻ በአሊጎሪካዊ ዘይቤ እንደ ታማኝ አይደል? ታማኞች ለከሃዲዎች ይመቹም የለ? በተለይ እንደ ምኒልክ ያሉቱ። ውሻ ከ25 ዓመት በኋላ ጌታው ቢመጣ የጌታውን ጠረን መች ይረሳል? ጭራውን እየቆላ ስብሰባ እስኪያልቅና ጌታውን እስኪያገኝ ይንቆራጠጣል እንጂ። ምኒልክ ለክህደት የተመረጠ ቡችላ ነበር። አስር ጊዜ ተክዶ አስር ጊዜ እስኪካድ የሚያደገድግ የፊያሜታ ችሎ-ማደር ነው ምኒልክ። እውነተኛ ንብረቱን (ሥጋ) ነፍገውት፥ ወደ ውጪ እየቸበቸቡበት፥ በዝምታ ራሱንም ኾነ ልጆቹን ሣር እሚያለምድ ቀስቶ - ነው ምኒልክ።

ዮሐንስ ወላይሶ እና ምኒልክ የያ ትውልድ አባል ናቸው። ቀስቶ እና ሳምራዊው የተባሉ ውሾችም የቄራው ዓመፅ አባልም መሪዎችም ናቸው። የያ ትውልድ እንቅስቃሴዎች አከሻሸፍ በውሾቹ ዓመፅ ውስጥ ተዘይቧል። ውሾቹ አጥር ሰብረው ሲገቡ የሚያስቆማቸው አልነበረም። ነገር ግን የመሪዎቹ ደካማነት፥ የተከፋፈለ ግብና ድርጊት ውጥኑን አኮላሽቶት የስንት ሰላማዊ ቡችላ ደም ፈሰሰ? ከዚህ የትውልድ ክስረት በኋላ፥ ቀስቶ እዚያው አዲስ አበባ ጎመንኛ፣ ሣር በሌ ኾኖ በድብቅ ሲኖር፥ ሳምራዊው ደሞ አራስ ተከትሎ፥ ዐዲስ የሚወለድ ተስፋ ዘንድ ሄዶ በነጻነት ይኖራል፤ በዓል ጠብቆም ቢኾን ሥጋ እየበላ። ልክ እንደዚሁ ምኒልክ በዛጎሉ ውስጥ ተጠቅልሎ ሲኖር፥ ዮሐንስ ወላይሶ ግን የነጻነት አየር ይተነፍሳል። ሳምራዊው ነጻነቱን መርጦ ሲሄድ ቀስቶ ግን “ከማውቃቸው ወዳጆቼ መለየት አልፈለግኩም” (ገጽ 505) ብሎ ይቀራል። በሚወዳቸው ዛጎል ይሸበባል። ቀስቶ እና ውሻዎቹ ተደብቀው ሲኖሩ ሥጋ የሚባል ነገር በዓይናቸው አልዞረም። ሊያገኙ ከሞከሩ ሞት ነው የሚጠብቃቸው። በሕይወት መቆየት ከፈለጉ ጎመንኛ፣ ሳር በሌ፣ ገጤዎች መኾን አለባቸው። የዚህ ባርነት ተገዢ መኾናቸውን የሚያሳይ አረንጓዴ ጥብጣብ፥ አንገታቸው ላይ ማንጠልጠል ግዴታቸው ነው። ልክ እንደዚሁ ፊያሜታና ግብረአበሮቿ እንደነ ምኒልክ ዓይነቱን የጎመንኛ ማህተም አትመውባቸዋል። “የሥጋ ጥያቄ እጠይቃለሁ!” - ቢሉ የስንብት ቀለም ይቀባሉ።

የምኒልክ ዛጎል ፊያሜታ ነበረች። ይህ ዛጎል ስህተት መኾኑን ምኒልክ ባለመቀበሉ፥ ሥጋ እንደ ማያገኘው ቀስቶ ተመስሎ በጉድጓድ ለመክረም ተገደደ። ዛጎሉ የተሠራው በእነፊያሜታ ነው። የሱ የፖለቲካ ትግል የተዘወረው በራሱ ሳይኾን በእነርሱ ነበር። እዚህ ዛጎል ውስጥ ባለቤቱ ሳፍሮን እና ልጁ ቤርሳቤህ ፈጽሞ የሉበትም። ውሻዎቹ ከጮኹ እንደ ሚረሸኑ ሁሉ የምኒልክም ጩኸትን እንደ ዋዛ አይታይም፤ በእነ ፊያሜታ። ለዚያም ነው ቀስቶ “አሁን ማታ አዲስአባ ከተማ ውስጥ የውሻ ጩኸት አትሰማም። አንዱ በድንገት ቢጮህ የሚከተለው የለም። ድሮ ቀረ። ዛሬ አንዱ ጮኾ የሚከተል ሌላ ውሻ ከተሰማ ሁለቱም ታድነው ይገደላሉ” የሚለው። ፊያሜታ ከአሜሪካ ከ25 ዓመታት ቆይታ በኋላ እንደ መጣች እነቤላን ጆሮ ጠቢ አድርጋ የሾመችው፥ ምኒልክ ሥጋ በል ወይም ሣር በል መኾኑን ለማወቅ ነው። ፊያሜታ ትንሽ ሰከን ያለችው ምኒልክ ከጎመንኛነቱም በላይ በአንገቱ ላይ እንደ ውሾቹ ባንጠለጠለው መተማመኛ ነው። ዮሐንስ ወላይሶ ግን ፍቼ እንዳለው ሳምራዊው በነጻነት መጮህ ይችላል። ምክንያቱም የትውልዱን ስህተት አፍረጥርጦ ለማተትም ኾነ ስህተቱን ለመንገር አያመቻምችም(አያፈገፍግም)። ፊያሜታ የዘመናቸው ስህተት መኾኗን ዮሐንስ ወላይሶ ያምናል። የግሉን ፊያሜታንም ለመንገር ይደፍራል። "በተለያየ ጥበብ ራሱን ሊያድን የሚሯሯጥ አለ። እኔ አልሯሯጥም። ራስ ወዳድነቴን ሁሉ ስው እንዲያየው አደርጋለሁ። How foolish I am." ሲል እናገኛለን።

በዚህ ውስጥ ፊያሜታዊነት ዲኮንስትራክት ተደርጓል። ፊያሜታ ሥጋን ከእንጨት እና ከድንጋይ የማይለይ ትውልድ እንዲፈጠር ታትራ ተሳክቶላታል። በሁለት ቢለዋ ትበላለች። አይደለም ለሥጋ ቀርቶ ወዳጁን ለመጣራት የሚጮኽ ውሻ ካለ ድምፁን ትሰልባለች። ሣር በል፣ ገጤ ያልኾነውን ወይ በገዛ ወገኑ ታሳድናለች፤ ወይ በነጭ ምሁራን ሾተላይ ውስጥ ታሳልፈዋለች። ለሷ እንደ ሚያሸረግዱ መተማመኛ የሚኾነውን አረንጓዴ ጥብጣብ አንገታቸው ላይ ያላንጠለጠለውን ወይ ታጠምቃለች አልያ ታንጠለጥላለች። የመታገያ አጀንዳ ሰጥታ፣ ከዳር ቆማ፣ ጨዋታው ሲጠናቀቅ ከባለድሉ መንጋጋ ውስጥ ሽንፈትን ሞጅራ፣ ድሉን ትሰርቃለች። ክርስቶፈር ክላፋም “Ethiopia pulled defeat from the jaws of victory.” ብለውም የለ? ተዘራፊው ማን እንዳራቆተው እንዳያውቅ፣ ባልንጀሮቹን አሰልፋ ወገኑን እንዲዠብጥ አደገኛ ልምጭ ሰጥታ፣ ሰለሜ ሰለሜ ታጫውተዋለች። ሽልን ፖለቲከኛ አድርጋለች። “ዘመናዊ ሜንጦ እና ሥጋ ምንም ዓይነት ትስስር የላቸውም!” ብላ ሥጋ ትነሳለች። ፊያሜታዊነትን እያሰረጸች፣ ሮማንነትን፣ ሳፍሮንነትን እንደ ሙየሌ ትመነግላለች። “የተወጋ በቅቶት ቢ(ተ)ኛ - የወጋ መች እንቅልፍ አለው? - የጅምሩን ካልጨረሰው” እንዳለው ሎሬቱ ከ25 ዓመታት በኋላ መጥታም ምኒልክን በዛገ ጦሯ ትጠቀጥቀዋለች። በዚህና መሰል ግብሯ እና ታሪኳ ጋሽ አዳም ፊያሜታዊነትን ዲኮንስትራክት አድርጓል ብዬ አስባለሁ።

በ”የስንብት ቀለማት” ላይ፣ ፊያሜታዊነት እንደ መስቀል ተሠላጢንነት ቀርቧል። መስቀል ተሠላጢን ከላይ መስቀል ከታች ጉድጓድ የሚቆፍር የሾለ አንካሴም አይደለ? ከሥር ጉድጓድ ምሶ ከላይ ድግስ እንዳበላው ንጉሥ፥ በክሕደት ሠላጢን ጨብጦ የእምነት መስቀል ማሳለም ነው - ፊያሜታዊነት። ከላይ ለሴቶች የቆመ “ኤንጂኦ”፣ ከሥር ደግሞ ንጋትን ማስለቀስ፥ ሳፍሮንን የቁም-መበለት ማድረግ ነው ፊያሜታዊነት። ከላይ የሕጻናት ጉዳይ ግብረሰናይ ድርጅት ዳይሬክተርነት፣ ከሥር የንጋትን ልጅ ደመወዝን ማኮላሸት፣ የሳፍሮንን ልጅ ቤርሳቤህን ማቀጨጭ፣ የእነ ቀስቶን ቡችላ ሥጋ መንሳት ነው - ፌያሜታዊነት።

ነገረ-ሞት

ፍሬድሪክ ዊልሃም ኒቼ የሚኖርለት “ለምን” ያለው የትኛውንም “እንዴት” ይቋቋማል የሚል ታዋቂ ትወራ አለው። በኔ ዕምነት ሻምበል ጉተማ፣ ዘወዲት ዘመነ እና ምኒልክ ባዩ የሚኖሩለት ምክንያት አሸለቦ በመግባቱ ነው መሰንበትን የተሰናበቱት። ምኒልክን በሽታ ሳይኾን የፊያሜታ “አላውቅህም” የተሰኘው አረር ነው የገደለው። የሚኖርለት ለምኑ ሳፍሮን፣ ቤርሳቤህ፣ ንጋት እና ደመወዝ ሳይኾኑ ፊያሜታ ነበረች። ልጅነቱን ወጣትነቱን ገብሮላታል። በጎልማሳነቱም በሳፍሮን ገላ ፊያሜታን ነበር ሲያቅፍ የከረመው። እዚህ ጋር “እሳት ወይ አበባ” ለምን ትዝ አለኝ? ምኒልክ በስንዝሮ ዘንግ አናቱን ተመትቶ ወደ ሕይወት ተመልሶ ይናዘዛል። ተመልሶ ግን ይሰናበታል። የያ ትውልድ አባላት በቋፍ ላይ ስላላችሁ እንደ ዮሐንስ ወላይሶ ስህተታችሁን ተናዘዙ ለማለት ይኾን?

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ውበት አድንቀናል፡፡ ስለ ቂጥዋ ግን አልተነገረንም፡፡ ሳይወራለት በአቋቋሟና በአጠቃላይ የገፅዋ ውበት ዝርዝር ውስጥ እንዲጠፋ ተደርጓል፡፡ ለመሆኑ የየዋህዋ ሰብለ ቂጥ ምን ዐይነትነው? በዛብህ ሲያየው ምን ይሰማው ነበር? ፂወኔስ? አደፍርስን የሳበው አስተሳሰቧ ብቻ ነበር? ሌሎችስ እንስት የልብወለድ ገፀባሀርያትስ? ለዚህ መልስ የለንም። " ገጽ 579

"የኢትዮጵያ ዳንስ (ሙዚቃን ያጀበ የአካል ንቅናቄ) መልካምድሩ ከሀ እስከ ፐ የወሲብ መልካምድር ነው:: ይሄም የቂጥ ወደ ሰሜን በሄድን ቁጥር ከኪነት የጉልህ ፍተሻ የመሰወር ታሪክ ነው፡፡ ይሄ የአሰዋወር ጥበብ በግጥምና በዘፈን ውስጥም አልፎ አልፎ ይታያል፡፡ ታዋቂው ዘፋኝ ሙሉቀን መለስ ላኪልኝ በተባለው የዘፈን ግጥሙ (በመሰረቱ ዘፈኑ በዘመናዊ መሳሪያ የተደረሰ ባህላዊ ዘፈን ነው) አሁን ከምለው ጉዳይ ጋር ያለውን ግኑኝነት ላስስ፡፡ ግጥሙ ሲጀምር፡ ከመሬቱ በላይ በቅሎዋ አለች ይለናል፡፡ ይቀጥልና ከበቅሎዋ በላይ ኮርቻ አለ ይለናል፡፡ከዛም ከኮርቻው በላይ ግላሱ አለ ይለናል፡፡ እያለ ከግላሱ ላይ እሷ አለች ይለናል፡፡ ከእሷም ላይ ቀሚሷ እንዳለ ይነግረናል፡፡ ከቀሚሷ በላይ ነጠላዋ አለ ይለናል፡፡ ከነጠላዋ ቀጥሎ ድሪዋ አለ ይለናል፡፡ከድሪዋ ቀጥሎ ጎፈሬዋ አለ ይለናል፡፡ ለመሆኑ ቂጥዋን ለምን ዘለለው? ለምንስ ገና ግጥሙን መዘመር ሲጀምር ፍቅረኛውን ተቻኩሎ በቅሎ ላይ አስቀመጣት? ቂጥዋን ከግጥሙ ዐይኖች መከለሉ ይሆን? ጥያቄውን ላክርረውና ሲጀመርስ ጎረምሳው ልጅቷን መሬት ላይ አቁሞ ሁለመናዋን ገልፆ በቅሎዋ ላይ ሊያሳፍራት አይችልም ነበር?" ገጽ 580 (ይህ ገጽ እና ቀጣይ ገጾች እስከ 596 ላይ ያለው ሕዳግ ድንቅ ነው።)

ከ60 በላይ ገጸ-ባሕሪያትን በአንድ እይታ መተንተን ከባድ ስለሆነ የተቀረውን በውይይተ መልኩ ለማቅረብ አጓጓለሁ። ሊጠቀሱ ከሚገባቸው ነገር ግን ላለማንዛዛት ከተውኳቸው ገፀ-ባሕሪያት መሃል - ሲኖዳ፣ ምትክ፣ ዮሴፍ፣ ህብስት፣ ወርቁ፣ ፍኖት፣ ነጪት፣ ሳሜራዊው፣ ስንዝሮ፣ ትጊ፣ ደበሌ፣ ዘውዲት፣ ሚኒሊክ አና ደመወዝ ናቸው።
ይህን ጽሁፍ ከመደምደማችን በፊት አዳም አዚሀ መጽሐፍ ውስጥ ቁሳቁስን ተጠቅሞ እንዴት የተለያዩ የገጸ-ባሕሪያቶችን እንዳስተሳሰረ እንመልከት።

•የእጅ አምባር

አዳም የንጋት አምባር ያምራል አይልህም። አዳም «ሊሙ ላይጦርነት ነበር» ብሎ ይጀምርና በጦርነቱ ምክንያት የዝሆነ ጥርስ እንደተማረከ፣ የዮሴፍ አያት ጋሽ ኢብሳ ጠብቁ ከተባሉትየዝሆን ጥርስ ከፊሉን እንደወሰዱ፣ ከወሊሶ ለሽቀላ ለመጣው ሜታ ለተባለ ባለሞያ ነጋዴ አምባር አንዲሰራላቸዉ እንዳዘዙት፣አምባሩ ለሚስታቸው አንደተሰጠ፣ ከዛ ሲወርድ ሲዋረድ የዮሴፍ ቅድመ አያት ዶምቢዶሎ ለወለደቻት ሊሙ ለምትባል ልጃቸው እንደተሰጠ፣ አያቱ ነቀምት ስታርፍ አምባሩ ቢፈለግ አንደጠፋ፣ የንጋት ልጅ ደመወዝ ሴሔጤድ (የሴቶች ህጻናትና ጤንነት ድርጅት) ተቀጥሮ ሲሰራ ረቂቅ ለተባለች የኤይድስ በሽተኛ ቃለመጠይቅ በሚያደርግበት ሰአት አምባሩን አድርጋ አይቶ እንደተመሰጠ፣ ረቂቅ ለደመወዝ እንዳብራራችለት የጓደኛዋ እናት አምባሩን የሰራዉ ያጎታቸዉ ልጅ ስለነበር ነቀምት በግርድና ያገለግሉ ከነበረበት ከወ/ሮ ሊሙ ቤትአምባሩን ሰርቀው አምጥተው ለልጃቸው እንደሰጥዋት፣ ልጃቸው አዲስ አበባ ይዛው እንደመጣች፣ ረቂቅ ጋር ንፋስ ስልክ ተዋዉቀው ጥሩ ወዳጆች ከሆኑ በኋላ ልጅቷ ስተሞት አምባሩ ረቂቅ ጋር እንደቀረ፣ ደመወዝ ቃለመጠይቁን ሲጨርስ ረቂቅ ስትሞት አምባሩን ተናዛለት ስለሞተች ደመወዝ ለእናቱ ለንጋት እንደሰጣት እና የአምባሩን የውስጥና የውጭ ዲዛይን በዝርዝርይተነትናል። በአንድ ትንሽ እቃ የስድስት ወይ ሰባት ሰዎችሕይወት ይተሳሰራል። ዕቃዋን ተሰናብተዋት ያለፉት ሰዎች ታሪክ በአዲስ ባለቤቶቿ ይወጋል።

እዚህ መጽሐፍ ላይ ከተጠቀሱት ሰዎችን እርስ በእርስ ካገናኙ ሌሎች ቁሳቁሶች መሃል ሻገር ውስጥ የተሰቀሉ ወርቁ የሳላቸው ሰዕሎች፣ ወርቁ የጻፈው መፅሐፍ፣ የጫማ ማሰሪያ፣ ዮሃንስ ወላይሶ በልጅነታቸው የቢራቢሮ ክንፍ ለመጠገን የተጠቀሙበት ብጣሽ ወረቀት፣የአዳሙ መጽሐፍ ማሕሌት፣ ስነዝሮ የጠፋበት ጫማ፣ ኳስ፣ ግራ እግር የስፖርት ጫማ ወዘተ ወዘተ---

አዳም ልዩ ነው። ይህ መጽሐፍ በስዕል መልኩ ቢቀርብ በትክክል መጽሐፉ ጀርባ ላይ ያለውን abstract painting እንደሚመስል በጣም እርግጠኛ ነኝ። አዳም እንደዚህ አይነት intricate, deep, vast, beautifully unique and orgasmically euphoric መጽሐፍ ጽፎ በስሙ ትምህርት ቤት አለመከፈቱ እና በስሙ መንገድ አለመሰየሙ ግራ ይገባል። አዳም -- ውብ! አዳም-- ተወዳጅ! አዳም የጸሐፊ ቁንጮ! ኦ አዳም!!!

የካቲት የሚመረቀውን መጽሐፌን በነጻ ለመሸለም ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ጥያቄዎች ቢያንስ አምስቱን ይመልሱ።

1. ከፕሮፌሰር ዮሃንስ ወላይሶ አልፎ አልፎ ትወጣ የነበረችው ሰላማዊት ማን ናት?
2. ታሪኩ መሃል ላይ የስንዝሮ ጫማ ጠፍቶ ነበር። ማን አገኘው?
3. ቤላ የደፋሪዋን መጥፎ ትውስታ ስለሚያመጣባት አሲያጎ የሚባለውን ቺዝ በጣም ትጠላለች። እዚህ መጽሐፍ ውስጥ ይህንን ቺዝ እጅግ በጣም የሚወዱ ሁለት ገጸ-ባሕሪያት ጥቀስ።
4. ሁለት ጭኖች ተጠጋግተው በአጭር ቀሚስ ተጠቅለው እያሉ፣ ከመሃል በጨርቅ ያልተጋረደው ወይም ሊጋረድ የማይችለው ትንሽ ጨለም ያለው ባለ ሦስት መዓዘን ቦታ በወርቁ theory መሰረት ምን ይባላል?
5. ሚኒሊክ ሬሳ ሳጥን ላይ የተወረወረው ኳስ ማን የጠለዘው ነው?
6. ዘመን ደህና ሰንብት የሚሉት ቃላቶች ከዮሃንስ ወላይሶ ጋር እንዴት ይያያዛሉ?
7. የምትክን ወንድም ያስገደለው ማን ነው?
8. ፊያሜታ የቹቹ አባት አዳምን ከሰደበችው ስድቦች መሃል ያሳቀህን ጥቀስ።
9. ዮሴፍ እዛ ልጁ የወደቀበት ቦይ ውስጥ የልጁን ሬሳ አቅፎ ያየው የጫማ ማሰሪያ የማን ይመስልሃል?10. የቀድሞ የወርቁ ፍቅረኛ ፍኖት አባዲ ከስፔይን የመጣች ጊዜ ለጥቂት ሰአታት አብረው አሳልፈው ነበር። መርካቶ ሄደው የገዙት መጽሐፍ ምን ይባላል? የገዙበት አላማስ ምንድን ነው?11. የሻገር ሆቴል ባለቤት ትጊ ስኬታማ የሆነችው በቂጥዋ ነው ወይስ በልብዋ ውበት? ግምትህን አስቀምጥ12. የፀሐዬ የማነ አንዱ የብዕር ስም ምንድን ነው? 13. ዘውዲቱ ራስዋን ከማጥፋትዋ በፊት የጻፈችውን ደብዳቤ (suicidal note) የት ነበር ያስቀመጠችው?14. ሚኒሊክ መኪናው ውስጥ አስቀምጦ የጠፋበት ብር ስንት ነበር?15. ስዓሊ ፍቅሩን በቂጥዋ ውበት inspire ያደረገችው ማሜ ድንቅ ቂጥ እንደነበራት አንብበናል። ይህንን ቂጥ በስዕል ላቀረበ ሰው ሦስት መጽሐፍ እሸልማለሁ።
16. እዚህ መጽሐፍ ውስጥ የጫማ ማስሪያ ክር የጠፋባት ገጸ ባሕሪ ማን ናት?

ቢኒያም አቡራ wrote his own deep reflection about this book. ስሙን click አድርጋችሁ የሱን መሳጭ philosophical ትንታኔ ይመልከቱ። Musical composition by Vahak Sakadjian

© Art of Tigest

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

እያዘነች ልጆች ወለደች፡፡ እንደ ዋሸሁዋት እንዳታለልኳት እየገባት፣አገጭዋን እጇ ላይ አስደግፋ ዕንባ ባቀረሩ አይኖቿ እያየችኝ ‘የአንተን ነገር ለክርስቶስ ሰጥቼአለሁ' አለች፡፡" ገፅ 304

•በሞት አፋፍ ላይ አያለ አጠገቡ እስከመጨረሻው የነበረችው ዙፋን ብቻ ናት---

"ዙፋን በጣቶቿ ፊቴን ትዳብሰኛለች፡፡ ምን ሆንን? አለች፡፡ ምን ሆንክ የእኔ ፍቅር? የቅንድቦቿ ፀጉሮች እንደተበጠሩ ሁሉ ተኝተዋል፡፡ ጣቶቿ ቀለም አልተቀቡም፡፡ የሚሞቅ መዳፏ መሃል አገጬን ይዛ ምላስ የሌለባቸውን ከንፈሮቼን ቢደርቁም ሳመቻቸው:: እፀልይልሃለሁ:: የምችለው እሱን ነው:: ትናፈጣለች፡፡ የቀረ አናቴ ላይ አናቷን አስደግፋ፡፡ ስታለቅስመስማት አለብኝ። ብዙ ዐይነት መከዳዳት አይቼአለሁ፡፡እስከዚች ደቂቃ ያላጋጠመኝ በሚስቴ መከዳት ነው፡፡ ይሄንመታደል ንቄው ነበር፡፡ የአብርሃም የሳራ አይደለም፣ የዙፋንትዳር ነው::" ገጽ 336

"ሚኒ ፎጣውን ወርውሮ ይመጣል፡፡ ገላው ጠንካራ ነው:: ሲጠጋኝ እጄን ወስጄ ደረቱ ላይ አደርጋለሁ፡፡ የምጠፋ የምቀልጥ ይመስለኛል፡፡ በፍርሃት ዐንገቴን እደፋለሁ፡፡ “ና እንዳላልኩት ኅፍረቱን ሳይ አፍረዋለሁ፡፡ የውስጥ ልብሴን ከላዬ በቀስታ ያወልቃል፡፡ ቀጥ ብሎ መቀመጥ ስለሚከብደኝ ደረቱ ላይ ፊቴን አስቀምጣለሁ:: እጆቼና እግሮቼ ይደክማሉ፡፡ ዐንገቴን ሲስመኝና ሁለመናዬን ሲዳብሰኝ ጡቶቼን (ደሞ ጡቶቼንደብሮቼ’ ነበር የሚላቸው፣ እንደ ደጀሰላሞች ማለት ነው) መሳም ሲጀምር አምላኬ እረኛዬ ነህን መዘመር ያሰኘኛል፡፡"ገጽ347

•የጉተማ ታሪክ ላይ በጣም የወደድኩት አንቀጽ ብዬ የጠቀስኩት እንዳለ ሆኖ፣ ይህ አንቀጽም ልቤን በጣም ኮርኩሮታል። የምናፈቅረውን ሰው ያሳለፈውን ውጣውረድ የተሞላበት ሕይወት፣ ያ ደሞ ያስከተለበትን የልቦና ቀውስ ተረድተን ስንቶቻችን አለፍጽምናውን ቸል እንላለን? ዙፋንን/ሳፍሮንን የሚያስወድዳት የህ ነው።

"እየቆየ መስከሩና ማጤሱ ሲገርመኝ በላዬ ላይ እንደሚወሰልት በሽሙጥና በአሉባልታ ሰማሁ፡፡ እድሜዬ በመግፋቱ የናቀኝ መሰለኝ፡፡ ግን አልቀናሁም፡፡ ለምን አልቀናሁም? _ እንደማይጠላኝ አውቃለሁ፡፡ ዘመኑ ባሎቻችንን ፍቅረኞቻችንን በተለያየ ቴክኒክ ይነጥቀናል፡፡ ዛሬ ዛሬ ሴቶች ለግርድና አረብሀገር ይሄዱ የለም? አልገባውም እንጂ ወንዱ ሚስቶቹንሲነጠቅ ነው፡፡ በሐበሻ ወንድ መርጠብ የሚገባቸው ማሕፀናት በየመን አሸዋ ይቃጠላሉ:: ቤንዚን፣ ግመል ወተትና ተምር ባጠገበው አብደላ ይደፈራሉ፡፡ ለመሆኑ ፍቅረኛዬ ሚኒሊክ ወፌ ላላ ሲገረፍ በልቡ ምን ይሰማው እንደነበር የሚያውቅ አለ? በዛች ሰከንድ፣ በዛች የመገረፍ ዕለት ስንት ሩህሩነቱ እየተሸረፈ እንደጠፋ የሚገባው አለ? የወንድ ልጅ ያውም ሚኒን የመሰለ ወንዳወንድ መቆም ተስኖት ተቀምጦ ሲሸና ምን እንደጎደለበት የሚገባው ይኖራል? ቃል ነው ለእኛየሚተርፈን፡፡ እየቃዠ ከእንቅልፉ የሚባንነው ብዙ ጊዜ ነው:: ደጋግሜ ጠይቄው ዝም ብሎ ምናምን ይለኛል፡፡ ምናምን ትርጉሙ ምንድነው? ዝም ብሎ ምናምን፡፡ በቃል እንኩዋን ያለፈበትን እንዳላልፍ ሲደብቀኝ ነው:: አልቃሻ ስለሆንኩ እኔን ከእዛ ማሸሹ ነው:: አውቃለሁ በከረመው ነገር እንደባነነ፡፡ ይሄ ይሄ ብዙ ሊገባኝ የማይችል የስነልቡና ችግር ሊያሳድርበት ይችላል፡፡ ባለገ ሲባል ወሬውን ባምንም፣ ጠልቶኝ ነው አላልኩም። ጠልተኸኝ ነው የምትል ቃል ከአፌ አላወጣሁም፣ በልቤም አላሰላሰልኩም፡፡ ግን ሰክሮ መንገድ እንዳይቀርብኝ፣ቂመኛም ካለበት እንዳይጎዳው፣ በሕይወት መኖሩን የማይፈልግ እንዳያደናቅፈው በመጨነቅ ነበር፡፡ የተዘረፈ ልጅነቱን በቸልተኛነቴ ብክሰውስ? በ'አላየሁም” በ'አልሰማሁም‛ በ'አልገባኝም ብሸፋፍንለትስ? ይኼም ሰው የመሆን ጉዳይመሰለኝ።" ገፅ 348-349

•(Adam is a sensual beast)

•አዳምን የመሰለ አፍቃሪ አለ? ያስብላል የፍቅር አገላለጹ። አዳም የሴቴን ልቦና ብቻ ሳይሆን የሴቴን ሰውነት ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ ያውቃል። አጥነቷ ስር የተጠቀጠቁትን ጥቃቅን ነርቮች የሚያስተላልፉትን መልዕክት የመስማት ችሎታው በጣም የረቀቀ ነው።

"ከረቂቅ ጋር ሲተኛ የሚመኘው መታገል አልነበረም፡፡ ባይችልም ግጥም መግጠም ነው፡፡ ባይችልም መዝፈን ነው:: በሰፈሩ አብዮት ጠባቂዎች ሲፈለግ፣ የሚደበቀው እስዋ ጋ ሄዶ ነበር፡፡ እዛች ሆቴሉ ጀርባ ያለች ጠባብ ዐልጋ ላይ ተጋድሞ ጎታ ፕሮግራምን እያነበበ ስራዋን ጨርሳ እስክትመጣ ይጠብቃታል፡፡ ብዙ ጊዜ ታጥቤ መጣሁ አትተኛ ብላ ዐንገቱ ስር አንሾካሽካ በርካሽ ሽቶ የተሰፋ ብርድልብስ አልብሳው ወደ ሌላ ትሄድበታለች። ድርጅቱ ፈርሶ ከአዲስአባ ወለጋ፤ ከወለጋ ካርቱም ሳያቁዋርጥ ሲሮጥ ከልቡ ምት ጋር ረቂቅ ነበረች፡፡ ሸበጡ ስር ያላባቸው ጣቶቹ መሃል፣ ከበረሀው ፀሐይ ደሞ እንደ ዣንጥላ………እንደ ደመና ጋርዳው፡፡ አእምሮው ውስጥ ሁልጊዜም ልጅ ናት ቀለሟ ወርቅ የመሰለ እንደ በጋ ዝናብ የምትመች…..ሁለመናዋ እንደ ቀትር የሚፋጅ………በታኮም ትሁን በኩፍ ዛላዋ ልብ የሚያንዘላዝል.....የሚነድፉ የተኩዋሉ አይኖቿ………ሲገባና ሲወጣ በቀስታ እየከደነች ስትገልጥ ከሩቁ እንደሜንቶል የሚሸት አፍ ያላት…..ግራና ቀኝ ላመል እብጥ ያለ ዳሌ.....ደረቷ ላይ የተለሰኑ ሚጢጢ ጡቶች……በጥልፍ ስራ የደመቀ የካኪ ትራስ ላይ በቅባት የላመ ጎፈሬዋ እንደ ኑግ ሐይቅ ከቧት………ዐልጋ ጠርዝ ራቁትዋን ተቀምጣ…………ዞር ብላ በእንቅልፋም ዓይኖቿ “ታረፍዳለህ?” ስትለው፡ ያማረ ድምፅዋና ለምቦጭዋን የከፈለው ሰንበር………እስከዛሬ ድረስ በዐይነሕሊናው ደሞ ኅፍረቱ ዙርያ እንደ ሞቀ ጥጥ ተጠቅላ፡፡ ዐይነሕሊና ደሞ ይከብዳል፡፡"ገጽ 432

“እንዲህ በገላዋ ዲስኩር ማድረግ የጀመረችው ገና አስራ አራት ሲሞላት ነው፡፡ ማለት ሮማን ቆማ የምትሄድ ስየታ ናት፡፡ ይሄን ብዙዎቹ አንቸለችለውታል፡፡ ብዙዎች አንብበውት ተመልሰው አልመጡም፡፡ በነጭ የውስጥ ሱሪ ከወገቧ በላይ ራቁቷን ሆና፣ መስታወት ፊት ለፊት ቆማ እየዞረች ሁለመናዋን ስታይ፣ ይሄን ሁሉ ቀምሰው ተመልሰው ያልመጡት ወንዶች በዝቅተኛነት ስሜት የሚማቅቁ ናቸው ብላ ታስባለች፡፡ ከፊት ለፊት የውስጥ ሱሪዋን ደርዝ በትንሹ ዝቅ አድርጋ ዲኦደራይዝ ተደርጎ በሚያብለጨልጨው የአፍረቷ ቋድ እየተጫወተች (ተነጭቶ ቢሸጥ ካቴድራል አይገነባም? 4000 በሬዎች አይሸምትም? 6 ጋሻ መሬት ጫት አይገዛም? 40 ጥቃቅን ኢንዱስትሪ ከሻንጋይ አያስመጣም?) ስለማሪያ ኬሪ ታልማለች፡፡ ስንት የዲያስፖራና የአገርቤት ኢንቨስተር ይሄን ቄጤማ ሊግጥ እዛ ተደፍቷል? ወንድ ማሳመም ሲያምራት ቀሚሷን ወደ ላይ ከፍ አድርጋ ሽቶ ትነሰንሳለች፣ ወደ ጎዳናም ትወጣለች፣ ከእግሮቿ መሃል አበባ እንደሚረግፍ ነው፡፡" ገጽ 452

"አንሶላዎች መሃል ከገቡ በሁዋላ ክብር የለም፡፡ የእንስሶች ቦታ ነው፡፡ እዛ ሮማን መሆን አቁማ ላም ናት፡፡ ዐልጋ ላይ በመጋደምና ልብስን ለብሶ በመነሳት መሃል ስነምግባር የለም፡፡ የሁካታ ቦታ ነው፡፡ የእዬዬ፣ የማለክለክ፣ የመፈራገጥና የልጋግ ቀበሌ ነው፡፡" ገፅ 454

Читать полностью…

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

ጠፋኝ፡፡ በህልሜም በእውኔም ያላሰብኩት ነገር………የሚባለው ዐይነት ጉዳይ ነው ያጋጠመኝ፡፡ ቦርሳዬን ተሸክሜ፣ ለቅሶዋን እያዳመጥኩ በጸጥታ ወዲያ ወዲህ ቤቱ ውስጥ መመላለስ ጀመርኩ፡፡ ላስቆማት አልፈለኩም፡፡ የሆነ ነገር አለ ብቻ ንፅህና የበዛበት አካባቢ፣ ማለት ሰዎች ፀባያቸው እንከን ሲያጣ በንጽጽር ራሴ የቆሸሽኩ ይመስለኛል፡፡" ገጽ 903

•ደረሰ ዋቄ ላልወለደው ነው የሞተው። ይህ ዓለም ዥጉርጉር ነው። አንዱ ያስነውራል፣ ሌላው ያልወለደውን እስከሞት ያፈቅራል።

•እስቲ ደሞ ስለ ቹቹ እና ስለ ዮሃንስ ወላይሶ እናውራ።

•ቹቹ ሴትኝ አዳሪ ናት። አቶ ዮሃንስ ደሞ የተማሩ (ፕሮፌሰር) የባህል ሃያሲ ናቸው። የሚያመሳስላቸው ነገር ሁለቱም they are the voice of reason and common sense. ቹቹ ከሴትኝ አዳሪ እናቷ ሶረን እና ማህሌት የሚባል መጸሐፍ ከጻፈው አዳሙ ከሚባል ደራሲ የተወለደች ስትሆን አባቷ አገር ለቆ ስለወጣ አይታው አታውቅም። ነገሮችን ላለማንዛዛት እነዚህ ሁለት ገጸ-ባሕሪያት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሰጡትን አስተያየቶች እንመልከት። አቶ ዮሃንስ የስንብት ቀለማት ስለተባለው ድርሰታቸው ሲጠየቁ ይህን ብለው ነበር።

"ጭብጡ ላልሽኝ፣ ጭብጡ በመንፈስም በስጋም ግባችን መሰናበት መሆኑን ለማሳየት ነው:: በየሰከንዱ እናረጃለን፡፡ በየሰከንዱ ወይም በናኖ ሰከንዶች የምናደርገው ሁሉ የመሰናበት ድርጊት ነው:: ሞትን ነው የምንኖረው ወይም እየኖርን ነው የምንሞተው፡፡ ግን ሁልጊዜ አለን፡፡ ብንሞት እንኩዋን አለን፡፡ እያለን ደሞ ስለምንለወጥ የለንም:: ደስታችንና ሃዘናችን በዚህ ምክንያት ጊዜያዊ ነው:: እነዚህን የማይለያዩ ነገሮች ለማንሳት ነበር ዕቅዴ፡፡ ይሄን ጭብጥ ሊሰራበት የሚሞክር ካለ ያማረ ፈቃድ እሰጣለሁ፡፡ የሞተ ሰው የዕውን ሞቷል? አለ የምንለው ሰውስ የዕውን አለ? ከክ.ል.በ. በ500 አካባቢ የነበረው የግሪኩ ፈላስፋ ኤምፖኬክለስ ቁስ ነበር እንጂ ወደ መሆን አልመጣም፣ እናም አይጠፋም እንዳለው ድርሰቴም ይሄን አባባል ሰፋ አድርጎ ‘መንፈስ አይወለድም አይሞትም' ሊል ይጥራል፡፡ ቁስ ለምን ከመንፈስ ሕግ ይወጣል? መንፈስስ ከቁስ ሕግ ይወጣል? የሰው ልጆች መልካምና ክፉ እሴቶች እየተደጋገሙ መጥተዋል፡፡ ብዙ አሮጌ ህብረተሰቦችና አገሮች ጠፍተዋል። እነሱንም የተኩት ጠፍተዋል። " ገጽ 47

•ቹቹ አሸናፊ ስለተባለው ዲያስፖራ የምትናገረው በጣም የሚገርሙ ዐይን ያፈጠጡ እዉነታዎች ልናሰላስልባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ናቸው።

"እኔ ብዙ የኮሌጅ ምሁራንን አንሶላ ስር አውቃቸዋለሁ አይደለ እና እንደ እነሱ በአሜሪካ ወይ በፈረንጅ በምናምን አልፎገርም………አለ አይደለ እዚህ ልበላው ያሰብኩትን ዳቦ ማን እንደወሰደው ካየሁ ኮሌጅ ያስፈልጋል? አሜሪካ ምን ያውቃል? ደሞ ይሄ አሸናፊ ያልኩሽ ወተት በጣም ይወዳል ሁሌ እንደ ጥጃ ይጋታል እና በቃ አብረን ከጠጣን ከዛች አንድ ብርጭቆ ወተት ይነሳና የአሜሪካ ወተት እኮ ምናምን ዋው ይላል፡፡ ቹቹ ሃኒ ይገርምሻል በጣም በጥንቃቄ የሚሰራ ነው ምናምን እንዲህ እንደኛ ምናምን በጀርም የተሞላ አይደለም ምናምን ዋው ይላል፡፡ የአሜሪካ ላሞቻቸው ሚኒስከርት ያደርጋሉ ወይ ሙቪ ምናምን ያያሉ? ምን ይታወቃል? የሠለጠነና ያልሰለጠነ ላም ምናምን ይኖር ይሆናል………ይኼ ሰው አየሽ እራሱን አያከብርም፡፡ ፕራውድ አይደለም። ስለሴቶች ሲወራ ደሞ የአሜሪካ ሴቶች ግልጽ ናቸው ምናምን ይላል፡፡ ግን እኔ ለእሱ ስገልብ ግልጽ አይደለሁም እንዴ? ቅር ሳይለው የወርቅ ይሁን የብር ሙዳዬን ሳላወልቅ ነው ሊያደርገኝ የሚንሰፈሰፈው። ቢሮው ዴስክ ላይ ያደርገኛል ምናምን ሙች አፍረተቢስ ነው፡፡ ይሄ አሜሪካንኛ ነው ማለት ይሆን? መንጌ እንደዚህ አድርጎ ይሆን እንዴ? ወይስ ባለማድረጉ “ጤባ” ምናምን ብለው ተቃወሙት? አሸናፊ እያደረገኝ አታምኝኝም ይሄን አስባለሁ፡፡ ጥለዛ ላይ ፖለቲካ ሲያመጡ ምንድነው የሚባለው ቆቅ ወዲያ ምናምን። ቆቅ ግን ምን ዐይነት እንስሳ ናት?" ገጽ 363

•ቹቹ አንዳንድ ሰዎች ስልጣኔንን የሚለኩበትን መንገድ ስትገልጽ የራሴ ገጠመኞች ትዝ ብለውኝ ፈገግ አልኩ። አዚህ ሆላንድ አንዳንዴ መንገድ ላይ ሃበሾች ሳገኝ ያው ናፍቆቱም ስላለ ተሯሩጬ ሰላምታ አቀርባለሁ። ነገር ግን ሁልጊዜ በጣም የሚገርመኝ ነገር የመጀመሪያ ጥያቄያቸው ነው። “ስንት ጊዜ ሆንሽ ከመጣሽ?” አክብሮታቸው የሚለካው ሆላንድ ውስጥ በኖርኩባቸው አመታት ብዛት እንደሆነ ሁላ፣ ስልጣኔዬን በሹካና ቢላ አያያዜ መራቀቅ ለመለካት እንደመቸኮል አይነት፣ እንደ ሳላይሽ ምቀኛ፡ እንደ ፊያሜታ ጎሰኛና ሴረኛ፡ እነደ ሚኒሊክ እና ሮማን ሴሰኛ፡ እነደ ፀጋ እና ናሆም ከዳተኛ፡ አንደ ተስፋዬ ነውረኛ፡ እነደ አሸናፊ ግብዝ፡ እነደ ፀሐይ የማነ ሴረኛ፡ ምን ልሁን ምን 26 አመት ሆላንድ ውስጥ ኖሬያለው ብል ልከበር፣ አይ ስድስት ወሬ ነው ከመጣው ብል ልናቅ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የኖርኩት ኑረቴና ተሞክሮዬ እነደማይቆጠር ሁላ፣ በ Skate Board ላይ ሁለት እግሬ ሚዛኑን ጠብቆ አስፋልት ላይ ስነሸራሸር ካገኙኝማ በቃ ሰልጥኛለሁ። አያስቀም? ለዚህ ነው ቹቹን የምወዳት።

"እዛ ድሬክ እንዳለሁ ካወቀ አሸናፊ አዞልሻል እባልና እተቀመጥኩበት ፉድ ይመጣልኛል፡፡ ከዛ ኮድ ነገር ነው ይሄ፡፡ እሱን በልቼ ወደ ጀርባ ቢሮው እሄድለታለሁ:: ፍርፍር እያገሳሁ ያደርገኛል፡፡ አንዳንዴ እንዳልገባው ፉዱን ጠልዤ ሌላ ጊዜ እለዋለሁ፡፡ በፉድ ሊያገባልኝ ይፈልጋል፡፡ ምግብ ለስራ ምናምን፡፡ ሚስቱን አሜሪካ አስከምጦ ምናምን አለ አይደለ እዚህ ይዝናናል ይሉታል፡፡ ይሄ መዝናናት ይባላል? የሆነ የዞረበት ወላንሳ፡፡ እኔ የዱሮ ፖለቲከኞች የሚፈልጉት ይሄ ነበር ማለት ነው፡፡ አለ አይደለ ስለድሮው እያወሩ ሊበጥሱን፡፡ ጎልደን ጀነሬሽን ነበርን ይለኛል፡፡ መጀመሪያ ደህና እንጨት ሁን እላለሁ።" ገፅ 364

"ሌላ ቀን ደሞ በዚህ ዘመን ምን ትምህርት አለ ድሮ ቀረ ትላለች። ወሬ። የእውን በገላችን ከመሸርሞጣችን በፊት በሃሳባችን ሽርሙጠናል፡፡ ትምህርት ትምህርት ከሚሉን አንዳንዶቹ በትምህርት ጊዜ በየሆቴሉ ቀጥረው የሚያደርጉን ናቸው፡፡ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ነኝ የሚል ምናምን ሁሉ በትምህርት ጊዜ ቀጥሮ ያስገባልኛል፡፡ እስቃለሁ:: አርጎኝ ቸርሶ ትምህርት እንዴት ነው? ምናምን ይለኛል፡፡ አፌን ይዤ እስቃለሁ፡፡ ምን ያስቃል? ይለኛል፡፡ ምንም: እንደዚሁ ሳቅሁ እለዋለሁ:: አይ የዛሬ ልጆች ምናምን ይላል፡፡ ከዛ የዛሬ ልጆች:: ይሄ የዛሬ ልጆች የሚባለው ነገር እስከ መቼ ይሰራበታል? እማማ በጊዜዋ ትባል ነበር። እኔ እባላለሁ፡፡ ከደበሌ ልጅ ስወልድ ደሞ ልጄን እንደዛ እለዋለሁ………እውይ………." ገጽ 371

"ብቻ የእኛ ሰው እርስ በእርሱ የማይጋጭ ሃሳብ እንዳያስብ አለ አደለ የሆነ ቀጠሮ ተይዞ ትምህርት ወይ ኪኒን መሰጠት አለበት። የኢትዮጵያ ጠላት የተራራው ውበት፣ የወንዙ ዐይነት፣ ቤንዚን ምናምን አይደለም ካየሁት፣ የኢትዮጵያ ሴቶች ቂጥ ይመስለኛል : የአገሪቷ ጠላቶች ሁሉ በመፅሄትና በራዲዮ ተጠራርተው የሚሰበሰቡት እዛ ዙሪያ ነው:: የእርዳታ ድርጅት ወንዶች ወጣት በይው ሽማግሌ የሚሽከረከሩት እኛ ቡቲ ዙሪያ ነው:: ዲሞክራሲ ሽፋን ነው፡፡ ማርያምን፡፡ አፍ መክፈት ያስተማረኝ አንዱ እንደዛ ዐይነት ቦታ የሚሰራ ዶክተር ናሆም የሚባል ሰውዬ ነው:: ዶክተር ላይሆንም ይችላል፡፡ ብቻ ምናለበት ፈረንጅ ያደርገው የለ ምናምን አለና፡፡ ምናልባት ከመናገር መብት ጋሬ ይያያዛል? ምን ይታወቃል ስትሪት ገርል ስለሆንኩ ብዙ ነገር አላውቅም አሉ፡፡

Читать полностью…
Подписаться на канал