agapeeotc | Другое

Telegram-канал agapeeotc - Agape【አጋፔ】♥♥♥

1337

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በዚህ ቻናል ኦርቶዶክስ ተዋህዶን የምንማርበት፣ የምናውቅበት አስተምህሮአዊ ቻናል ነው። " የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ካህናቱን ስለ ሕጉ ጠይቅ፤" (ትንቢተ ሐጌ 2:11) @AgapeEOTC @AgapeEOTC @AgapeEOTC

Подписаться на канал

Agape【አጋፔ】♥♥♥

ማርያም ብቻ

ይህንን መልእክት share የማያደርግ የማርያም ወዳጅ አይደለም!

1.አምላክን የወለደች-ማርያም ብቻ!

2.ከመውለዳ በፊትም ሆነ ኋላ ድንግል የሆነች - ማርያም ብቻ!

3.ከሰው ወገን ተለይታ መርገም ያልነካት - ማርያም ብቻ!

4.የእግዚአብሔር ሀገር ከተማ የተባለች - ማርያም ብቻ!

5.በድምጽዋ መንፈስ ቅዱስን የምትሞላ ንግስት- ማርያም ብቻ!

6.ጽንስ በማሕፀን የዘለለላት ብጽዕት - ማርያም ብቻ!

7.ያላፈውም የሚመጣውም ትውልድ የሚያመሰግናት - ማርያም ብቻ!

8.ጸሐይን ተጎናፅፋ ጨረቃን የተጫማች ልዩ እናት - ማርያም ብቻ!

9.በጌታ ሞት ያዘነውን ዓለም እንድታፅናና ጌታ የሰጠን ሥጦታችን - ማርያም ብቻ!

10.በስጋዋ፣ በነፍስዋና በሕሊናዋ በሶስት ወገን ድንግል የሆናች - ማርያም ብቻ!

11.ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ የሆነች - ማርያም ብቻ!

12.ከፍጥረት ሁሉ ተላይታ አምላኳን "ልጄ" የምትል - ማርያም ብቻ!

13. ፍቅርዋ በልቤ የሚቀጣጠል አማላጅነትዋን ነፍሴ የሚመሰክርላት እናቴ - ማርያም ብቻ!

14.ከሰው ወገን 'ቤዛዊተ ዓለም' የሚል የጸጋ ስም ያላት - ማርያም ብቻ!

15.በንጉሱ ቀኝ ቆማ የምትማልድ ንግስት - ማርያም ብቻ!

16. ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን የሚላት - ማርያም ብቻ!

17. አባ ኤፍሬም ያወደሳት፣ አባ ሕርያቆስ ያመሰገናት፣ ቅ.ያሬድ የተቀኘላት እመቤት - ማርያም ብቻ!

18.ከሰው ወገን በስጋ ከሞት ተነስታ ያረገች ንጽሕት እናት - ማርያም ብቻ!

19. የመላእክት እህታቸው፣ የሰማዕታት አክሊላቸው፣ የመነኮሳት መመኪያቸው - ማርያም ብቻ!

20. ዘንዶው በሰው ልብ እንዳትቀረፅ ሊውጣት የሚፈልግ፣ ዘርዋንም ሊዋጋ የሚሻቸው ባለ ሁለት ክንፍ እመቤት - ማርያም ብቻ!

21. ጌታ ከፍጥረት ሁሉ ለይቶ "እናቴ" የሚላት - ማርያም ብቻ!

22.እንደ ማንኛውም ሰው ጸጋ ተካፍሎ ሳይሆን ጻጋ ሞልቶ ያላት የጻጋ ግምጃ ቤት - ማርያም ብቻ!

23.መለኮት ስጋዋንና ነፍስዋን ነስቶ የተወሐደላት - ማርያም ብቻ!

24. በቤተመቅደስ ኣድጋ ከመላእክት ጋር እየተጫወተች፣ ሰማያዊ ሕብስትና ጽዋዕ የተመገበች ንጽሕት - ማርያም ብቻ!

25.ከፍጥረት ሁሉ ተለይታ መንግስተ ሰማያትን የወረሰች ብቸኛዋ ወራሽ ንግስት - ማርያም ብቻ

ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
እናታችን

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

Bez:
yo Mek:
#ከማኅበረ_ሥላሴ_አንድነት_ገዳም_የተላከ_መልዕክት

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ቢያንስ ለ 15 የተዋህዶ ልጆች Share በማድረግ ክርስትያናዊ ግዴታችንን እንወጣ ።


#በኢትዮጵያና_በመላው_ዓለም_ለምትገኙ_ኦርቶዶክስ
_ክርስቲያኖች_በሙሉ_ከጥቅምት_24_እስከ_30_ከ
ህፃናት_እስከ_ሽማግሌ_ማንም_ሳይቀር_በማህበረ_መ
ነኮሳቱ_አማካኝነት_ፆም_ታውጇል::
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱአምላክ አሜን
በክርስቶስ ክርስቲያን ለተሰኛችሁና በደሙ የዋጃችሁ በኢትዮጵያ
የምትገኙ ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ በቤታችሁም ያላችሁ
በህመም ምክንያት በሆስፒታል ያላችሁ በማረሚያ ቤት ያላችሁ
በጦር ሜዳም ያለችሁ እንዲሁም በተለያየ ስፍራ የምትገኙ
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የከበረ ሰላምታችንን
በያላችሁበት ይድረሳችሁ፡፡
እኛ ማኅበረ ስላሴ እንድነት ገዳም የምንገኝ ማኅበረ መነኩሳት
በሀገራችን ሰላም መታጣት ምክንያት ከሀዘናችን ጋር አምላክ
አበው ክብር ምስጋና ይግባዉ ደኅና ነን፡፡
እግዚአብሔር ገና ሃያ ሁለቱን ስነ-ፍጥረት ፈጥሮ ሳያበቃ
ሳጥናኤል በዓለተ ረቡዕ በሶስተኛዉ ሰማይ በጌታ ላይ በማመጽ
በጀመረዉ ጸብ ምክንያት ከመላዕክቱ ጋር ተዋግቶ ተሸንፎ ወደ
ምድር ተጥሎ እነሆ ያለ እረፍት ለሰባ ሺ አምስት መቶ አመታት
በመላዉ ዓለም ደም ሲያፈስ ቆይቷል፡፡ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ፡፡
ጌታ የተሰጠዉ የቀጠሮ ቀን እስኪፈጸም ድረስ ታግሶታል፡፡
አሁን ግን ከወትሮዉ ለየት ያለዉ ነገር የእግዚአብሔር ቤተ -
መቅደስ በሆነችዉና የቅዱሳን የአስራት ሀገር በተሰኘችው
በኢትዮጵያ ሀገራችን የሳጥናኤል ጭፍሮች ክተት ሰራዊት ምታ
ነጋሪት ብለዉ ዘምተዉ በታሪክም ያልሰማነዉ በዘመናችንማ
አይተን የማናቀዉ የአርስ በአርስ እልቂት እንኳን ከክርስቲያን
ከሰብአዊ ፍጡር የማይጠበቅ ድርጊት ተፈጽሟል እየተፈጸመም
ነዉ፡፡
ሰይጣን ብቻዉን ምንም ማድረግ አይችልም፡፡ ከሰዉ ጋር ሆኖ
በሰዉ ልብ አድሮ ግን ምንም የሚቀረዉ የሀጢያት ሥራ የለም፡፡
በዮሐንስ ወንጌል ምዕ ፲፭፡፲፭ ላይ ብትወዱኝስ ትዕዛዜን ጠብቁ
ያለዉ የጌታ ቃል ተጥሷል፡፡
ቀድሞ አንድ ሰዉ ለሥራም ሆነ ለንግድ ወይም ለተለያየ
ጉዳይ ወደ ማያዉቀዉ ወደ ሚያዉቀዉም በኢትዮጵያ ክፍላተ
ሀገር ወይም ክልል ሲዘዋወር ለሀገሩ እንግዳ ለሰዉ ባዳ ነኝ
ብሎ አይጨነቅም፡፡ የእግዚአብሔር እንግዳ ተብሎ ከመሸበት
ገብቶ እግሩን ታጥቦ ቤት ያፈራውን በልቶ ጠጥቶ ከመልካም
ምንጣፍ ተኝቶ አድሮ ሲነጋ ተነስቶ መርቆ ቀሪዉን ምንገድ
ይጓዛል፡፡
ዛሬ ግን ያ ቀረና የእግዚአብሔር እንግዳ እራቱ ጥይትና ገጀራ
መጠጡ ደም ሆኗል፡፡ በማቴዎስ ወንጌል ምዕ ፳፭፥፵፪ ላይ
የተጠቀሰዉ እንግዳ ሆኜ ብመጣ አልተቀበላችሁኝም ብራብ
አላበላችሁኝም የሚለዉ የጌታ ቃል ትዉልዱን እየተዋቀሰዉ ነዉ፡፡
በእርግጥም በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነዉ ብሎ ዮሐንስ
ወንጌላዊ እንደተናገረዉ እንግዶች የሰላም ተጓዦች መሆን
ይጠበቅባቸዋል፡፡ነገር ግን የሰላም ሰዎችም አብረዉ
ተጨፍልቀዉ የጥፋት ሰለባ ሆነዋል፡፡ ሁሉን ቻይ የሆነ
እግዚአብሔር አሁንም ታግሶናል፡፡እኛ አሁን ከሞት የተረፍነዉ
ከጥላ ያረፍነዉ በጽድቃችን አይደለም በቸርነቱ ለንስሐ ጊዜ
ተሰጥቶን ነዉ እንጅ፡፡
ነቢያት ስለ ጥፋት ሲተነብዩ በሰዉ ልጅ ሐጥያት ከእግዚአብሔር
የሚታዘዘዉን መቅሰፍት ማስገንዘባቸዉን እንጅ ጥፋት ዝም ብሎ
ደርሶ የሚታዘዝ አይደለም፡፡
አሁን በኃጢያታችን ምክንያት እየተጎነጨነዉ ያለዉ መከራ ከዚህ
በፊት ብዙ የተነገረ ቢሆንም በትንቢተ ዮናስ ታሪካቸዉ
እንደተጠቀሰዉ እንደ ሰብዓዊ ነነዌ ወደ እግዚአብሔር በጾም
በጸሎት ሆኖ በመለመን በማልቀስ መከራዉን ማስቀረት
እንዲቻል ቅዱሳን በመጽሐፍት አስተምረዉናል፡፡
በኖህ ዘመን ምድር በዉሃ ሙላት የጠፋችዉ በኃጢያት ምክንያት
ነዉ፡፡ በሎጥ ዘመን በሰዶም ሀገር የተቃጠለችዉና ከምድረ ገጽ
የጠፋችዉ በኃጢያት ምክንያት ነዉ፡፡
ዛሬስ እየተሰራ ያለዉ ኃጢያት በዚያ ዘመን ከነበረዉ ያንሳልን ?
ያን ጊዜስ በንስሀ ላልተመለሱ ሰዎች ፈርዶ ያጠፋቸዉ አምላክ
ዛሬስ ፈርዶ ማጥፋቱ ይሳነዋል ወይ ? አይሳነዉም
እንዲያዉም እንደ ዘመናችን ኃጢያት ብዛትና ክብደት
ላልፈረደብን እግዚብሔር እያመሰገንን ይህን መልዕክት
በያላችሁበት ሲነበብላችሁ ከሰማችሁት በኋላ ወደ ልባችሁ
ተመለሱ ከእንግዲህ ወዲህ በዘር ፣ በጎሳ ፣ በቋንቋ ፣ በሀገር ፣
በብሔር መለያየት ይብቃ ፣ መገዳደል ይብቃ ፣ መዘራረፍ ይብቃ
፣መሰደድም ይብቃ አጠቃላይ የጥፋት ዘመቻ ይብቃ፡፡ ወደ
ቀድሞ ኢትዮጵያዊ አንድነታቸን እንመለስ በኅብረት ተቻችለን
እንኑር፡፡
የኃጢያታችንን ካባ አዉልቀን በነብስም በሥጋም የሚያድነንን
የንስሐ ካባ እንልበስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕ ፲፭፥፲፪ ላይ እኔ
እንደወደድኳችሁ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ ብሎ ጌታችን ባዘዘብ
መሰረት ጥላቻን አስወግደን የዘር ፣የጎሳ፣ የቋንቋ ፣ የክልል
ልዩነት ሳይኖረን እርረ በእርሳችን እንዋደድ፡፡
በዮሐንስ ወንጌል ምዕ ፲፬፥፳፯ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ ያለዉ ጌታ
ቃሉ አይለወጥም እና ይህ ከሆነ ብቻ እዉነተኛዉን ሰላም
ማግኘት ይቻላል፡፡
የተከበራችሁ ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ ነብዩ ኢሳያስ በትንቢቱ ምዕ
፩፥፲፱ ላይ ‹‹ እሺ ብትሉና ብትሰሙኝ የምድርን በረከት
ትበላላችሁ እምቢ ብትሉና ባትሰሙኝ ግን ሰይፍ ትበላችኃለች
የእግዚአብሔር አፍ ይህንን ተናግሯልና›› የሚለዉን የትንቢት ቃል
ዛሬም በእኛ ኢትዮጵዊያን ላይ እንዳይደርስብን ለእግዚአብሔር
ቃል እንታዘዝ እና ክፋትን ሁሉ ትተን ንስሀ ገብተን የምድርና
በረከት እንብላ፡፡ አለበዚያ ግን ምሕረት በእጁ የሆነ አምላክ
መዓተም በእጁ ነዉና ምርጫዉ ግን የእናንተ ነዉ፡፡ በሀገራችን
ሰላም ይሰፍን ዘንድ ማንኛዉም ክርስቲያን የተጣላ ታርቆ ፣
የበደለ ክሶ ፣ ይቅር ተባብሎ ፤ ከጥቅምት ፳፬ እስከ ጥቅምት ፴
ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም ድረስ ልጅ አዋቂ ሳይለይ እስከ ዘጠኝ ሰዓት
እየጾማችሁ በሀዘን በለቅሶ ምህላ በመያዝ ከእግዚአብሔር
ምህረትና ይቅርታ በጋራ እንድንለምን እኛ የማኅበረ ሥላሴ
አንድነት ገዳም ማኅበረ መነኮሳት ሁሉን በፈጠሩ በቅድስት
ሥላሴ ስም አምላክን በወለደች በእናታችን በቅድስት ድንግል
ማርያም ስም በታላቅ አክብሮት መልዕክታችንን ለመላዉ ሕዝበ
ክርስቲያን አስተላልፈናል፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ለሀገራችን ሰላም ይስጥልኝ
የሞቱትን ሁሉ ነብስ ይማርልን
የጠፋዉን የተቃጠለዉን የወደመዉን ንብረት ሆሉ ይተካላችሁ
አሜን ይሁን ይደረግልን
መምህር አባ ወልደ ሰንበት ነጋሽ
የማኅበረ ሥላሴ አንድነት ገዳም አበመኔት
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

Share share share share share share

1 ሰው ለ 15 ምዕመን

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

🕯🕯🕯❖🕯🕯🕯
🌿❖ ❖ ❖🌿
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በአቢይ ኃይል ወሥልጣን
¤ አሰሮ ለሰይጣን
¤ አግኣዞ ለአዳም
¤ ሰላም🕊
¤ እም ይእዜሰ
¤ ኮነ ፍስሐ ወሰላም።
✨✨✨✨✨✨✨✨
📣 እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን፤ ለበዓለ ትንሳኤው፡ በሰላም፣ በጤና፣ በፍቅር፣
መልካም በዓል ለሁላችን፨ 🎁⛪

🌿እንቋዕ አብጽሐክሙ አብጽሐክን ለበዓለ ትንሳኤ በሰላም ወበፍቅር ወበጥዒና
ሰናይ በዓል ለኵልክሙ።🌿
💐💐💐💐💐💐💐💐

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

።።።።።♦ክፍል 3♦።።።።።
የመጨረሻ ክፍል ነው ይሄ ፤ ማለት ግን ምዕመናንን ሊነድፉ ለተዘጋጁ የክህደት ትምህርቶችን እንዲህ በቀላሉ እንላቀቃለን ማለት አይደለም ። መዋጋትችን ከስጋ እና ከደም ጋር አይደለምና በቃል ብቻ ሳይሆን በጌታ ፊት በርከክ በማለት ጭምር ይህን መርዝ ከምድራችን በኢየሱስ ስም እንዲነቀል መፀለይ አለብን ወገኖቼ።
ካለፈው የቀጠለ....
ስለዚህ ከመላዕክት ይልቅ ሞትን በመቅመሱ ምክንያት በጥቂት አንሶ የነበረው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁም ቅዱስ ሆኖ ንፁህ ሆኖ ሳለ ከተቀበለው ከታላቅ መከራ የተነሳ እግዚአብሔር የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነስቶታል ያለ ልክ ከፍ ከፍ አድርጎታል።"፤ በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ "ፊልጵስዩስ ሰዎች 2: 9። ኢየሱስ ማንም ሊቀበለው የማይቻለውን የሞት መከራ ነው የተቀበለው ። ጌታችን የተቀበለው መከራ ልኬቱ የጅራፉ እና የችንካሩ ጉዳይ ሳይሆን ኃጢአታችንን መሸከሙ እና ስለ እኛ እንደ ሃጢአት መቆጠሩ ነው "፤ እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው። 2ኛኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5: 21)
ይህንን ከመላዕክትም ከሰውም ማንም ማድረግ የተቻለው የለምም አልነበረምም አይኖርምም።"፤ በሰማይም ቢሆን በምድርም ላይ ቢሆን ከምድርም በታች ቢሆን መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው ማንም አልተቻለውም። " ዮሐንስ ራእይ 5: 3 ። እናስተውል ከዚህ የተነሳ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመላዕክት ይልቅ በሞት አንሶ የነበረው ደግሞ ከተቀበለው መከራ የተነሳ የምስጋና እና የክብር ዘውድ ተጭኖለት እናየዋለን። ቃሉ እንዲህ ይለናል ወደ ዕብራውያን 2÷ 9 "፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ፥ ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አንሶ የነበረውን ኢየሱስን ከሞት መከራ የተነሣ የክብርና የምስጋናን ዘውድ ተጭኖ እናየዋለን። "
መዝሙር 8 ÷6 ላይ "፤ በእጆችህም ሥራ ሁሉ ላይ ሾምኸው፤ ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፥ " ተብሎ ተፅፏል ይህንን ቃል የዕብራውያኑ ፀሃፊ እንዲህ ብሎ ያስረዳናል ። እንዲህ ይላል ቃሉ "፤ ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት ብሎ መሰከረ። ሁሉን ከእርሱ በታች ባስገዛ ጊዜ ያልተገዛለት ምንም አልተወምና። አሁን ግን ሁሉ እንደ ተገዛለት ገና አናይም፤ " ወደ ዕብራውያን 2: 8)
በእጆችህም ስራ ላይ ሾምከው የሚለውን ቃል እነ Faith movment ለሰው ነው የተነገረው ይላሉ ። ግን እናስተውል ከላይ ከ 4 እስከ 6 ያለው ቃል ራሱ ነው ዕብራውያን 2 ÷ 6 እና 7 ላይ የተጠቀሰው። ቅዱሱ መፅሃፍ ራሱ ለጌታ የሰጠውን ቃል እንዴት ባለ ዓይን አይታችሁት ነው ለፍጡር የሰጣችሁት ???
♥ በእጆችህ ስራ ላይ ሾምከው የሚለውን አንዳንዶች እንዴት ሾምከው ይላል እርሱ በማንም አይሾምም ጌታ ፈጣሪ እኮ ነው ብለዋል አዎን ኢየሱስ ፈጣሪ ነው መለኮት ነው ግን እናስተውል የሾመው አባቱ ነው እንጂ ከእርሱ በሚያንስ አካል አይደለም እኩል በሆነ መለኮታዊ ስልጣን ነው ይህ ሹመት የተከናወነው አብ የእርሱ የሆነውን ሁሉ አሳልፎ በዚህ መልክ ለልጁ ሰጥቶታል።
♦♦ ቃሉ እንዲህ ይለናል "፤ አባቴ እኔን እንደ ሾመኝ እኔ ደግሞ በመንግሥቴ ከማዕዴ ትበሉና ትጠጡ ዘንድ፥ በአሥራ ሁለቱ በእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በዙፋኖች ትቀመጡ ዘንድ ለመንግሥት እሾማችኋለሁ። " የሉቃስ ወንጌል 22: 29-30) ክርስቶስ ማለት እኮ ቅቡዕ ማለት ነው የተቀባ ማለት ነው ። በማን ነው የተቀባው በህዝብ ድምፅ ብዛት ? በመላዕክት ትብብር ? በባለስልጣናት ፍቃድ ?? እውነቱ ይህ ነው ክርስቶስ ቅቡዕ የሆነው የተቀባው የተሾመው በአባቱ ነው
♦♦ተመልከቱ እዚህ ጋር ♦♦ "፤ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ። " (የሉቃስ ወንጌል 4: 17-19) እባካችሁ እናስተውል ኢየሱስ ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ የሆነ ዘለአለማዊ ጌታ የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ ንጉስ ነው። ቅቡዕነቱ ወይንም ሹመቱ በአባቱ ነው።
የዕብራውያን መልዕክት በቀጥታ ይህን ቃል ለጌታ እንዳደረገው እያነበብን ነው በአይናችን ስለዚህ ከዕብራውያኑ ፀሃፊ እንበልጣለን ልትሉ ነው ወይስ ስህተት ነው ልትሉ ነው ቃሉን ?
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ (ስላሴ ) በግብር 3 ሲሆን በአገዛዝ በመለኮት በስልጣን ደግሞ አንድ ነው። ይህ የምስጢረ ስላሴ ወይም የትምህርተ ስላሴ መሰረት ነው። ስለዚህ አብ በግብሩ የራሱ የነበረውን ሁሉ ነው አሳልፎ ለወልድ የሰጠው .. ለምሳሌ
♣ ፍርድን አሳልፎ ሰጥቶታል ፤ ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ፥ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም። የዮሐንስ ወንጌል 5: 22-23)
♣ እኛን ሰጥቶታል "፤ የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም። " የዮሐንስ ወንጌል 10: 29)
♣በአህዛብ ላይ ስልጣን ሰጥቶታል "፤ እኔ ደግሞ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ በአሕዛብ ላይ ሥልጣንን እሰጠዋለሁ፥ በብረትም በትር ይገዛቸዋል፥ እንደ ሸክላ ዕቃም ይቀጠቀጣሉ፤ " (የዮሐንስ ራእይ 2: 26-27)
♣ከስም ሁሉ በላይ ስም ሰጥቶታል"፤ በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ " (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2: 9)
♣ቤተክርስትያንን ሰጥቶታል "፤ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው።" ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1: 22)
♣በአጠቃላይ ሁሉንም ሰጥቶታል ፤""፤ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤ "
(ወደ ዕብራውያን 1: 2)"፤ ♣♣♣"፤ ኢየሱስ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው ከእግዚአብሔርም እንደ ወጣ ወደ እግዚአብሔርም እንዲሄድ አውቆ፥ "
(የዮሐንስ ወንጌል 13: 3)
ስለዚህ ይሄን ሁሉ ሰጥቶታል ማለት ሾሞታል ማለት ኢየሱስ ምንም አልነበረውም ማለት ነው ??? በጭራሽ አይደለም ምክንያቱም በአገዛዝ እና በመለኮት ደግሞ ልክ እንደ አባቱ ስልጣን ያለው ነው ግን ተወላዲ ልጅ እና ስግው ቃል በሆነበት ማንነቱ እና ከተቀበለው መከራ ራሱንም ፍፁም ባዶ በማድረጉ ምክንያት አብ ሁሉን ለልጁ ሰጥቶታል። አሜን ይገባዋል የእኛ ጌታ።
ስለዚህ ሁሉን በፍርዱ ችሎት ፊት ያደረገው አብ ሁሉን አሳልፎ ለልጁ ሰጥቶታል። ስለዚህ ይህ ቃል ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነገረ ቃል ነው።
፤ ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት ብሎ መሰከረ። ሁሉን ከእርሱ በታች ባስገዛ ጊዜ ያልተገዛለት ምንም አልተወምና። አሁን ግን ሁሉ እንደ ተገዛለት ገና አናይም፤ " ወደ ዕብራውያን 2: 8)
አሁንማ ገና መች ሁሉ ተገዛለት ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ??አለ

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን በዓለ ስቅለት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።

❖ መጋቢ ሐዲስ እሸቱ ❖

🔸 @memher_eshetu 🔹
✍Comment @shamo_guy

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

#ሰሙነ ሕማማት

ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት፤ ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሠልስት፣ በስድስት፣ በተሰዓት /ዘጠኝ /ሰዓት፣ በሰርክ /በዐስራ አንድ/ ሰዓት እየመላለሱ የሚሰግዱበትና የሚጸለዩበት ልዩ ሳምንት ነው ከሆሳዕና ማግስት እስከ ትንሳኤ።
በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭ ሺ ፭ መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው።
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም በጽኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው። ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው፦

ሰኞ
መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል፦
በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል።

አንጽሖተ ቤተመቅደስ ይባላል፡-
ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” ማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና።

ማክሰኞ
የጥያቄ ቀን ይባላል፦
ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል።

የትምህርት ቀን ይባላል፡-
በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪።

ረቡዕ
ምክረ አይሁድ ይባላል፦
ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ሉቃ ፳፪፥፩-፮ ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል።

የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል፡-
ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮-፯ የመዓዛ ቀን ይባላል።

የእንባ ቀን ይባላል፡-
ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል።

ሐሙስ
ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፦
ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል።

የምስጢር ቀን ይባላል፡-
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል።

የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡-
መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።

የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡-
ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል።

ዓርብ
የስቅለት ዓርብ ይባላል፦
ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል።

መልካሙ ዓርብ ይባላል፡-
ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።

ቅዳሜ
ቀዳም ስዑር ትባላለች ፦
ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል።
ለምለም ቅዳሜ ይባላል፡-
ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል።

ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡-
ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል።
@Ewnetgen
(ስምዐ ጽድቅ መጋቢት ፳፻፪ ዓ.ም)

@Ewnetgen

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

+ እንኳን ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን
ለኢየሱስ ክርስቶስ ለዐበይት በዓል ለአንዱ ለዐቢይ ጾም ስምንተኛ
ሳምንት ለሆነው ለሆሣዕና በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ
በዚች ቀን በስንክሳሩ ከሚታሰቡ፦ ሐዋርያት ከሾሙዋት
ከዲያቆናዊት ሰማዕት ከሆነች ከቅድስት ዲዮኒስ ከመታሰቢያዋ፣
ከመነኰሳት ከአባ ሜልዮስ አርድእት ከአባ ኢያሱና ከአባ ዮሴፍ
ሰማዕትነት ከተቀበሉበት ከዕረፍታቸው በዓል፣ከሰማዕቱ ቅዱስ
መናድሌዎስ፣ ከአባት አኮሊሳሞስና ከዐራት መነኰሳም
ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
+ የሆሣዕና ዓራራይ ዜማ፦ ሃሌሉያ "ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሰርቅ
በእምርት ዕለት በዓልነ ተዝካረ መድኃኒነ በኢየሱስ ክርስቶስ ንዑ
ንትፈሳሕ በእግዚአብሔር ዘረድአነ"። ምልጣን፦ "በጽዮን ንፍሑ
ቀርነ በዕለተ ሰርቅ ንፍሑ ቀርነ በእምርት ዕለት በዐልነ"።
ትርጉም፦ በታወቀች በዓላችን ዕለት መለከትን ንፉ ከክርስቶስ
መታሰቢያ ኑ እንሳተፍ በጽዮን ለረዳን እግዚአብሔር መለከትን ንፉ።
ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው ላይ።
+ + +
+ ሆሣዕና ማለት የዕብራይስጥ ቃል ነው፤ "ሆሻአና" ሲባል
ትርጒሙም "አቤቱ አሁን አድን" ማለት ነው። የክብር ባለቤት
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ገብቶ ቤተ
መቅሱን በአህያ ግልገል ተቀምጦ በመዞር ሆሣዕና እያሉ
እንዲያመሰግኑት አድርጓል። ይህም ስርሱ እየአንዳንዳቸው
በዘመናቸው ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ነው።
+ ያዕቆብ በክርስቶስ ስለ ተመሰለው ስለ ልጁ "ይሁዳ አህያውን
ዘይት ዕንጨት ላይ ያሥራል ውርንጫውንም በወይን አረገ" አለ።
ዘካርያስም "ጽዮን ልጅ አትፍሪ እነሆ ንጉሥሽ በአህያ ግልገል
ተቀምጦ ይመጣል" አለ።
+ ኢሳይያስ "ንጉሥሽ ጻድቅ የዋህ የሆነ ይመጣል ዋጋውም
ከእርሱ ጋራ ነው ሥራውም በፊቱ የተገለጠ ነው በአህያ
ግልገልም ላይ ይቀመጣል" አለ።
+አብርሃምም የሰሌን ዝንጣፊ ይዞ መሠውያውን በዞረ ጊዜ "ይችን
ዕለት ተድላ ደስታ የሚደረግባት የእግዚአብሔር በዓል" ብሎ
ጠራት።
+ ዳዊትም "ከሕፃናትና ከልጆች አንደበት ምስጋናን አዘጋጀህ" አለ።
ሰሎሞንም "የሕፃናት አንደበታቸው የተቃናች ሆነች" አለ።ሁለተኛም
"ልጆችና ሽማግሌዎች በኢየሩሳሌም ይጫወታሉ ምርጒዛቸውም
መትከያዎችሽን አስፍተሽ ድንኳኖችሽን ዘርጊ" ያለም አለ።
+ይህንንም የትንቢት ነገር ለመፈጸም በከረ ወንጌል እንተጻፈ ጌታ
በአህያዋና በውርንጭላዋ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም
ገባ።ወደ ኢየሩሳሌም ሊገባ በቀረበ ጊዜ የደብረ ዘይት አጠገብ
ከምትሆን ቤተ ፋጌ ደረሰ ደብረ ዘይት ወደሚባል ቢታንያም በደረሰ
ጊዜ ከደቀ መዛመቱን ሁለቱን ላከ። "ወደ ፊታችሁ ወዳለ አገር
ሒዱ በገባችሁም ጊዜ ሰው ያልተቀመጠበት አህያ ግልገል
ታገኛላችሁ ፈትታችሁ አምጡልኝ። ለምን ትፈቱታላችሁ የሚል ሰው
ቢኖር ጌታው ይሻዋል" በሉ።የተላኩትም በሔዱ ጊዜ
እንደነገራቸው አገኙ። የአህያውም ግልገል ፈቱ ጌቶቹም "ለምን
ትፈቱታላችሁ" አሏቸው። "ጌታው ይሻዋል" አሉ። ወደ ጌታ
ኢየሱስም ይዘውት ሔዱ ልብሳቸውንም በአህያው ግልገል ላይ
ጐዘጐዙ ጌታችንም አስቀመጡት። ቅጠል ቆርጠው በመንገድ ላይ
የጐዘጐዙ ብዙዎች ናቸው። ልብሳቸውንም በመንገድ ላይ ያነጠፋ
አሉ። በፊትም በኋላ ይሔዱ የነበሩት በእግዚአብሔር ስም
የሚመጣ የተባረከ መድኃኒት ነው ብለው አሰምተው ተናገሩ።
በእግዚአብሔር ስም የምትመጣ የአባታችን ዳዊት መንግሥትም
የተባረከች ናት።
+ ጌታ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ገባ ሕዝቡም
ሁሉ አዩት በመሸም ጊዜ ከዐሥራ ሁለቱ ደቀመዛሙርት ጋር ወደ
ቢታንያ ወጣ። በነጋውም ከቢታንያ በወጣ ጊዜ ተራበ። በሩቅም
ቅጠል ያላትን በለስ አየ። በርሷ ፍሬ ያገኝ እንደሆነ ሊያይ ሔደ
ወደርሷም በደረሰ ጊዜ ከቅጠል ብቻ በቀር ያገኘው የለም የበለስ
ወራት አልነበረምና "ዘላለም ካንቺ ፍሬ የሚበላ አይኑር" አላት። ደቀ
መዛሙርቱም ሰሙ።
+ ወደ ኢየሩሳሌም ደርሶ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ በምኵራቡም
ግቢ የሚገበያዩትን ያስወጣ ጀመረ የለዋጮችንም ሰደቃቸውን
ገለበጠ ርግብ የሚሸጡትንም ወንበራቸውን። ወደ ምኵራብ
ለንግድ ገንዘብ ይዘው እንዳይገቡ ከለከለ።
"ቤተ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ይሁን የሚል ጽሐፍ ያለ
አይደለምን እናንተ ግን የሌቦችና የወንበዴዎች ዋሻ አደራጋችሁት"
ብሎ አስተማራቸው።
+ ቅዱስ ዮሐንስም እንዲህ "አለ አልዓዛርን ከሙታን ለይቶ
ካስነሣው በኋላ።በነጋውም እሑድ ለበዓል የመጡ ሰዎች ጌታችን
ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመጣ በሰሙ ጊዜ።
የሰሌን ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ከኢየሩሳሌም ፈጥነው ወጡ
በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ከአርያም የተገኘ መድኃኒት
የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው" እያሉ እየጮኹ ተቀበሉት።
+ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአህያ ግልገል አገኘ።ተቀመጠበትም
እንደ ተጻፈ እንዲ ሲል። "የጽዮን ልጅ አትፍሪ እንሆ ንጉሥሽ በአህያ
ግልገል ተቀምጦ ይመጣል"። አስቀድሞ ግን ደቀ መዛሙርቱ
ይህን ነገር አላወቁም ነበር ጌታ ሳይሰቀል።ጌታ በተሰቀለ ጊዜ
ይህ የተጻፈ ስለ እርሱ እንደሆነ ያን ጊዜ አወቁት እንጂ እንዲህም
አደረጉለት።
+ አልዓዛር አልዓዛር ብሎ ከሙታን ለይቶ እንዳስነሣው ባስነሣው
ጊዜ ከእርሱ ጋር የነበሩ ሰዎች መሰከሩለት። ስለዚህም ሕዝቡ
አመኑበት። ያደረገውን ተአምራት ሰምተወልና የሕፃናቱንም ምስጋና
ደግሞ አልዓዛርን ማስነሣቱን። የካህናቱ አለቆችና ፈሪሳውያን ግን
እርስ በርሳቸው "የምታገኙት ረብሕ ጥቅም እንደሌለ አታውቁምን
እንሆ ሰው ሁሉ አመነበት" አሉ።
+ ቅዱሳን ማቴዎስና ማርቆስ የሰሌንን ነገር አላወሱም ሌሎች
ከእንጨቶች ቅጠሎችን እየቆረጡ በመንገድ ውስጥ ጐዘጐዙ አሉ
እንጂ።
+ ቅዱስ ሉቃስም ቅጠልን ወይም ሰሌንን አላወሳም ሲሒዱ
ልብሳቸውን በመንገድ ላይ ይጐዘጒዙ ነበር አለ እንጂ።
+ ቅዱስ ዮሐንስ ግን ለብቻው "ከኢየሩሳሌም ከሰሌን ዛፍ ላይ
ዘንባባ ቆርጠው ያዙ" አለ። ሰሌንም በኢየሩሳሌም አልነበረም
ጌታችን ሕፃን ሁኖ ሳለ ወደ ግብጽ በወረደ ጊዜ ከእናቱ ቡርክት
ቅድስት ከሆነች ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ጋር እስሙናይን
ከሚባል አገር ደረሱ ከዚያም ሰሌን አገኙ።ጌታችንም ከሥርዋ
ተነቅላ ሒዳ በደብረ ዘይት ላይ እንድትተከል አዘዛት ያንጊዜ ወደ
አየር ወጥታ በረረች ሒዳም በዚያ በደብረ ዘይት ተተከለች
ከእርስዋም ወስደው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን
ተቀበሉት።
+ ጌታችንም የሆሣዕናን ዑደት በአሳየ ጊዜ የአይሁድ ወገን ቅናት
ይዟቸው በሚገድሉት ገንዘብ ምክንያት ፈለጉ። ለእርሱም ምስጋና
ይሁን በእኛ ላይም ይቅርታው ቸርነቱ ይደረግልን ለዘላለሙ አሜን።
ምንጭ፦ የመጋቢት22 ስንክሳር።
ወስብሃት ለእግዚአብሄር

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

ጥምቀት :- ማለት ቃሉ የግእዝ ቃል ሢሆን ትርጉሙም "
መነከር ፣ መዘፈቅ ፣ ዉሀ ውስጥ ገብቶ መዉጣት "
ማለት ነዉ ።
ጥምቀት ማለት አንድ ሠዉ አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በተጸለየበት ና በተባርከ ዉሀ ሦስት ጊዜ ጠልቆ ዳግመኛ ከስላሤ ተወልዶ የቤተ ክርስቲያን አባል የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚሆንበት ቅዱስ ሚስጥር ነዉ
፣ ማቲ 28 : 19 - 20
ሚስጥር ጥምቀትን የመሰርተልን ጌታችን መድሐኒታችን እየሡስ ክርስቶስ ሲሆን ሲመሠርትም በትእዛዝ ፣ በትምሕርት ፣ በተግባር ነበር ለዚህም የመፅፍ ቃል ስንመለከት
1ኛ በተግባር በዮርዳኖስ ማቴ 3:16
እየሡስ ከተጠመቀ በኃላ ወድያዉ ከውሀ ወጣ ፤ እነሆ ሠማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔር መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይ ሲመጣ አየ እነሆም ፥ ድም ፅ ከሠማያት መጥቶ በርሱ ደስ የሚለኝ የሚወደኝ ልጄ ይህ ነዉ አለ ።
2 ኛ በትእዛዝ ማቴ 28:19
"እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወለድ በመንፈስ ስም
እያጠመቃችኃቸዉ ፥ ያዘዝኋችሁንም እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸዉ ደቀ መዛሙርት አድርጓቸዉ ።
3ተ ኛ በትምሕርት ዩሐ 3 :5
" እየሡስም መለሰ ፥ እንዲህ ሢል እዉነት እዉነት እልሃለለዉ ፥
ሠዉ ከዉኃና ከመንፈስ ከልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግስ ሊገባ አይቸልም ።
ጌታ ኢየሡስ በዮርዳኖስ ወንዝ በአገልጋዩ /በፍጡሩ / በዮሐኒስ የተጠመቀበት ምክንያት እንደ መፅሐፍ ቅዱስ እንደ ቤተክርስቴያን አስተምሮ
1~~~~~አንድነቱን ሦስትነቱን ለመግለጽ
2~~~~~የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ
3~~~~~ በርሡ ጥምቀት የእኛን ጥምቀት ለመቀደስ
4~~~~~ ለጥምቀታችን ሀይልን ለመስጠት
5 ~~~~~ ለአብነት ርሱ ተጠምቆ እናንተንም ተጠመቁ ብሎ
አርያና ምሳሌ ለመሆን ከቅድስት ድንግል ማርያም
በተወለደ በ30 ዘመኑ ጥር 11 ከሌሊቱ በ 10 ኛዉ
ስዓት ማክሰኛ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ጌታን
ስታይ እንደምትሸሽ ነቢዩ ዳዊት በመዝ 133:3-5
የእዳ ደብዳቤያችንን በክርስቶስ ኢየሡስ ጥምቀት ተደመሠሠ
"ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ይፈርድበታል" ማር 16:16

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

ወዳጄ ሆይ!

የሚታገል ሰው ቢወድቅ አዲስ ነገር አይደለም፤ ወድቆ መቅረቱ ነው እንጂ፡፡ አንድ ቦክስ የሚጋጠም ሰውም ቢቆስል የሚያሳዝን ነገር አይደለም፤ የሚያሳዝነው ቁስሉን ችላ ያለው እንደ ኾነ ነው እንጂ፡፡ አንተም በመንፈሳዊ ሕይወትህ ብትወድቅ አይደንቅም፤ ለቅጽበትም የማይተኛልህ ጠላት አለህና፡፡ ነገር ግን ወድቀህ አትቅር፡፡

አንድ ወታደር ጦር ሜዳ ሔዶ ቢቆስል ማንም ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው አይወቅሰውም፡፡ አንተም ጠላትህ ዲያብሎስ ቢያቆስልህ ማንም አይወቅስህም፡፡ መንፈሳዊ ተጋድሎ ውስጥ ነውና ያለኸው፡፡ የምትወቀሰው ለቁስልህ መድኃኒት ማድረግህን ችላ ያልህ እንደ ኾነ ብቻ ነው፡፡ ይህ ከላይ የነገርኩህ ወታደር ከታከመ፥ ተመልሶ ወደ ጦር ሜዳ ይሔዳል፡፡ ጠላቱን ድል ሲያደርግም ሹመት ሽልማት ይሰጡታል፡፡ አንተም ከወደቅህበት ተነሥና ንስሐ የተባለ ሕክምናን ውሰድ፡፡ ከዚያም ጠላትህ ዲያብሎስን ድል አድርገህ ከክርስቶስ ዘንድ ሹመት ሽልማትን ተቀበል፡፡ ስለዚህ በርታ፡፡ በርታና ተነሥ ዘግይቻለሁ ብለህ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ፤ አሁንም መጀመር ትችላለህና፡፡

#ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@Mahbere_estnfase_krstos

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
አሜን
ኅዳር ፳፭፦ የታላቁ ሰማዕት የቅዱስ መርቆሬዎስ ዕረፍቱ ነው፡፡
‹‹መርቆሬዎስ›› ማለት የአብ ወዳጅ ማለት ነው፡፡ ዳግመኛም
የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ወላጆቹ አስሊጥ
ከምትባል ሀገር ቢሆኑም እርሱ ግን ተወልዶ ያደገው በሮሜ
ከተማ ነው፡፡ አያቱና አባቱ ሥራቸው አውሬ ማደን ስለነበር አንድ ቀን እንደልማዳቸው አውሬ ሲያድኑ ከገጸ ከለባት ወገን የሆኑ
ሁለት ወንዶች አግኝተዋቸው የመርቆሬዎስን አያት በሉት፡፡
አባቱንም ሊበሉት ሲሉ የታዘዘ መልአክ ከለከላቸው፡፡
ዙሪያቸውንም በእሳት አጥሮ ከበባቸው፡፡ እነርሱም በተቸገሩ ጊዜ ለመርቆሬዎስ አባት ሰገዱለት፡፡ በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር ፍጥረታቸውን ወደገራምነት ለወጠውና እንደበጎች የዋሆች ሆነው አብረውት ወደ መንደር ገቡ፡፡
ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ ተወለደና ስሙ ፒሉፓዴር ተባለ፡፡ የውሻ መልክ ያላቸውም በእርሱ ዘንድ ብዙ ዘመናት ኖሩ፡፡ ከዚህም በኋላ ክርስቲያኖች ሆኑ፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም ወላጆች አስቀድመው አረማውያን ነበሩና የክርስትና ጥምቀትን በጸጋ ተቀበሉ፡፡ አባቱን ኖህ እናቱንም ታቦት ብለው ሰየሟቸው፡፡
ቀድሞ ፒሉፓዴር የነበረውም ስሙ ተለውጦ መርቆሬዎስ ተባለ፡፡
የውሻ መልክ ያላቸው ግን መልአኩ በተገለጠላቸው ጊዜ
እንደነገራቸው ለቅዱስ መርቆሬዎስ አባት የሚታዘዙና
የሚያገለግሉ ሆኑ፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባትና የውሻ
መልክ ያላቸውን ዜናቸውን ሲሰማ ወታደሮቹን ልኮ በፊቱ
አቆማቸው፡፡ እግዚአብሔርም የቀድሞ ፍጥረታቸውን
መልሶላቸው አራዊት አደረጋቸውና ንጉሡን እጅግ አስፈሩት፡፡
ንጉሡም የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት የአራዊት ተፈጥሮአቸውን
ያርቅለት ዘንድ ለመነው፡፡ የቅዱስ መርቆሬዎስም አባት በለመነ
ጊዜ ተፈጥሮአቸውን መልሶላቸው ገራሞች ሆኑ፡፡
ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ገዥና የሠራዊቱ አለቃ አድርጎ
ሾመው፡፡ የውሻ ፊት ያላቸውም አብረው ያገለግሉት ስለነበር
ሁሉም ይፈራው ነበር፡፡ ንጉሡም የመርቆሬዎስን አባት ወደ
ጦርነት ከላከው በኋላ ሳይመለስ ስለቀረ ሚስቱን ሊያገባት
አሰበ፡፡ የመርቆሬዎስ አባትም የመርዶሳውያን አገሮች ሁሉ ገዢ
በነበረው ንጉሥ ተይዞ ቢማረክም ገዥው ክርስቲያን መሆኑን
አይቶ አከበረው፡፡ ቆይቶም በሀገሩ ላይ ሾመው፡፡ ሚስቱም
ጠፍታ ከሀገሯ ወጥታ ሄዳ ስለነበር ከባሏ ተገናኝተው በዚያው መኖር ጀመሩ፡፡ መርቆሬዎስም አባቱና እናቱ ከሞቱ በኋላ ንጉሡ በአባቱ ፈንታ በመርዶሳውያን አገር ላይ ሾመው፡፡
መርቆሬዎስ መኰንንነት በተሾመም ጊዜ ገጸ ከለባቱ አብሮት ነበር፡፡ ለመዋጋትም በወጣ ጊዜ የቀድሞው የአራዊት የሆነ ተፈጥሮውን እግዚአብሔር ይመልስለት ስለነበር ማንም
አይቋቋመውም ነበር፡፡ ለቅዱስ መርቆሬዎስ ታላቅ የድል አድራጊነት ኃይል ተሰጠውና ዜናው በሁሉም ሀገሮች ተሰማ፡፡
በሮሜ ሀገር ጣዖትን የሚያመልከው ዳኬዎስ የተባለውም ንጉሥ የበርበር ሰዎች ጋር ጦርነት ሊገጥም በወጣ ጊዜ እጅግ ሲበዙበት ፈራ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በጦሩ መሀል የተሳለ ሰይፍ የያዘ የእግዚአብሔርን መልአክ ስላየ ንጉሡን እግዚአብሔር ያጠፋቸዋልና አትፍራ›› አለው፡፡ መልአኩም ሰይፉን ለቅዱስ መርቆሬዎስ ሰጠውና ‹‹ጦርነቱን ድል ባደረግህ ጊዜ እግዚአብሔርን አስበው›› አለው፡፡
ጦርነቱን ድል አድርጎ ሲጨርስም መልአኩ ድጋሚ ተገልጦለት
‹‹ለምን የፈጣሪህን ስም መጥራት እረሳህ?›› አለው፡፡
ከጦርነቱም በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ
በዓልን አደረገ፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም በዚያ ስላልተገኘ
ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረጉ እንዳልተባበረ ንጉሡ ሲያውቅ
መልእክተኞችን ልኮ አስመጣው፡፡ ንጉሡም ‹‹ከእኔ ጋር ለምን
አታጥንም?›› ባለው ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ ትጥቁንና ልብሱን
አውልቆ ከወረወረለት በኋላ ‹‹ክብር ይግባውና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን ፈጽሞ አልክደውም፣ ለረከሱ ጣዖቶችህም አልሰግድም›› አለው፡፡ ንጉሡም ተናዶ ልዩ ልዩ በሆኑ ሥቃዮችም እጅግ አሠቃየው፡፡
ንጉሡም ስለ መርቆሬዎስ ብለው የአገሩ ሰዎች እንዳይነሱበት
ፈርቶ በብረት ችንካር ቸንክሮ የቀጵዶቅያና የእስያ ክፍል
ወደሆነች ወደ ቂሳርያ ከደብዳቤ ጋር ላከው፡፡ በዚያም እጅግ
ካሠቃዩት በኋላ ንጉሡ ዳኬዎስ እንዳዘዘ ኅዳር ፳፭ ቀን አንገቱን
በሰይፍ ቆረጡትና የሰማዕትነት ተጋድሎውን ፈጸመ፡፡
የሕይወትንም አክሊል ተቀዳጀ፡፡ በዓለሙ ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ታነጹለት፡፡ እግዚአብሔርም ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም አደረገ፡፡
ከብዙ ተአምራቱም አንዱ የቂሳርያውን ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስን
እረድቶ ከሃዲውን ዑልያኖስን የገደለበት ነው፡፡ ዑልያኖስ ነግሦ
የክብር ባለቤት ጌታችንን ክዶ ጣዖታትን ማምለክና ክርስቲያኖችን ማሠቃየት ጀመረ፡፡ የቂሳርያው ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስም አስተምሮ ሊመልሰው ወደ ንጉሡ ቢመጣ ክብር ይግባውና ዑልያኖስ ጌታችንን ሰድቦ ባስልዮስንም አሰረው፡፡
ባስልዮስም በእሥር ቤት ሳለ በቅዱስ መርቆሬዎስ ሥዕል ፊት
ጸለየ፡፡ ሥዕሉም ወዲያው ተሰወረው፡፡ ያንጊዜም ወደ ከሃዲው ንጉሥ ዑልያኖስ ዘንድ ሄዶ በጦር ወግቶ ገደለውና ወዲያው ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡ ከጦሩም አንገት ደም ይንጠፋጠፍ ነበር፡፡
ቅዱስ ባስልዮስም ከሃዲውን ንጉሥ እንደገደለው ዐውቆ ‹‹የክርስቶስ ምስክር ጌታዬ ሆይ የእውነት ፀር የሆነ ዑልያኖስን
ገደልከውን?›› አለው፡፡ ሥዕሉም ያን ጊዜ አዎን እንደሚል ራሱን
ዘንበል አደረገ፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ደስ ብሎት እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡
ሌላው ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስ በተአምሩ ከእስልምና
እምነት መልሶ ክርስቲያን ያደረገው አንድ እስላም ሰው አለ፡፡
ይኸውም የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያኑ በተሠራችበት
በምስር አገር የሚኖር ከመሳፍንት ወገን የሆነ ወጣት ነበረ፡፡
ከብዙ ሰዎችም ጋር ሆኖ ወደ መሐመድ መቃብር ለመሄድ
እንዳሰበ ለአባቱ ሲነግረው ስንቅ ሰንቀው በሰላም ወደ መካ
መዲና ሸኙት፡፡
መካ ደርሰውም ሥራቸውም ፈጽመው ወደቤታቸው እየተመለሱ
ሰባት ቀን ተጓዙ፡፡ በሌሊትም ሲጓዙ ስለ ሥጋዊ ግዳጁ ያ
እስላም ወጣት ከግመል ላይ ወርዶ ለመጸዳዳት ዘወር አለ፡፡
እነርሱም አብሯቸው የሚጓዝ መስሏቸው ስለነበር ባልንጀሮቹም
በበረሃው ውስጥ ትተውት ሄዱ፡፡ እርሱም ወዴት እንደሚሄድ
ስላላወቀ አራዊትም እንዳይበሉት ፈርቶ እጅግ ደነገጠ፡፡ በዚያም
ጊዜ በምስር አገር በአባቱ ቤት አቅራቢያ ያለች የሰማዕቱ
የቅዱስ መርቆሬዎስን ቤተ ክርስቲያን አስታውሶ በልቡ ቅዱስ
መርቆሬዎስን እንዲያድነው በመለመን ተሳለ፡፡ ወዲያውም
ቅዱስ መርቆሬዎስ በፈረሱ ተቀምጦ ወደ እርሱ መጣና
‹‹ከወዴት ነህ? ከዚህ በረሃ ውስጥስ እንዴት ጠፋህ?›› አለው፡፡
ወጣቱ እስላምም የሆነውን ነገረው፡፡ ቅዱስ መርቆሬዎስም ‹‹ና በኋላዬ በፈረሱ ላይ ተፈናጠጥ›› አለውና በአየር ላይ እየበረረ በምስር አገር ወዳለች የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደ ዐይን ጥቅሻ አደረሰውና እንደተዘጋች በውስጧ አስገባውና ከእርሱ ተሰወረ፡፡
ይህም ወጣት በኋላ አምኖ ተጠምቆ ብዙ ሰማዕትነት
ተቀብሏል፡፡ ገዳምም ገብቶ ብዙ ከተጋደለ በኋላ እንደገና ወደ
አገሩ ተመልሶ ብዙዎችን ወደ ክርስትና አምጥቷል፡፡ በቅዱስ
መርቆሬዎስ ስም ቤተ ክርስቲያን አሠርቶ አበ ምኔትም ሆኖ ብዙ
መነኮሳትን አፍርቷል፡፡
ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን! እኛንም በአማላጅነቱ
የምንታመን የተዋሕዶ ልጆች የሆንን ሁላችንን ዛሬ ኅዳር ፳፭
ቀን በዓመታዊ በዓሉ አስበነው የምንውለውን የታላቁን ሰማዕት
የቅዱስ መርቆሬዎስን ረድኤት በረከቱን ያሳድርብን፣ በጸሎቱ
ይማረን፡፡
(ስንክሳር ዘወርሃ ኅ

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

# ይህን_ያውቃሉ
# እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም
. ነሐሴ 7 ቀን ተጸነስች
. ግንቦት 1 ቀን ተወለደች
. ታህሳስ 3 ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ገባች
. መጋቢት 29 ቀን አምላክን በድንግልና ጸነስች
. ታህሳስ 29 ቀን አምላክን በድንግልና ወለደች
. የካቲት 16 ቀን የምህረት ቃል ኪዳን ከልጅዋ
ከወዳጅዋ ከጌታችን .ከመድኃኒታችን
ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ተቀበለች
. ጥር 21 ቀን በክብር አረፈች
. ነሐሴ 14 ቀን በክብር ተቀበረች
. ነሐሴ 16 ቀን እንደ ልጇ ተንሳኤ ተንስታ።
ክብር ለማርያም በድንግልና የአለምን መዳኒት
ኢየሱስ ክርስቶስን ለወለደች ይሁን።

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

*⛪አንዳንድ ግዜ አገር አርብ ላይ ትሆናለች*

*✍🏽ፀሐፊ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት*

*🗣አንባቢ ወንድም እዮብ ዮናስ*

*🇪🇹ከቅድስት አገራችን ከአርብ ወደ ትንሳኤ እሁድ ያሸጋግርልን*👆🏼👆🏼👂🏽👂🏽

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

#ETHIOPIA | የሚደንቅ! ... ስንቶቻችን እናውቃለን?

* እነሆ ትርጉማቸው ...

ሀ ማለት ሀልዎቱ ለአብ እምቅድመ ዓለም ማለት ነው፡፡
ሐ ማለት ሐመ ወሞተ በእንቲአነ ማለት ነው፡፡
ኀ ማለት ኀብአ ርእሶ ማለት ነው፡፡
ሁ ማለት ኪያሁ ተወከሉ ማለት ነው፡፡
ሑ ማለት ሰብሑ ለሥመ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኁ ማለት እኁዝ አቅርንቲሁ ማለት ነው፡፡
ሂ ማለት አስተይዎ ብሂዐ ማለት ነው፡፡
ሒ ማለት መንጽሒ ማለት ነው፡፡
ኂ ማለት ዘልማዱ ኂሩት ማለት ነው፡፡
ሃ ማለት ሃሌ ሉያ ማለት ነው፡፡
ሓ ማለት መፍቀሬ ንስሓ ማለት ነው፡፡
ኃ ማለት ኃያል በኃይሉ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሄ ማለት በኵለሄ ሀሎ ማለት ነው፡፡
ሔ ማለት ሔት ሕያው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኄ ማለት ኄር እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ህ ማለት ህልው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሕ ማለት ሕያው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኅ ማለት ኅብስት ለርኁባን ማለት ነው፡፡
ሆ ማለት ኦሆ ይቤ ወመጽአ ማለት ነው፡፡
ሖ ማለት ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኆ ማለት ኆኅተ ገነት ወልድ ማለት ነው፡፡
ኈ ማለት ኈለቈ አዕፅምትየ ማለት ነው፡፡
ኋ ማለት ሰንኋቲ ሥጋ ሰብእ ማለት ነው፡፡
ኌ ማለት ይኌልቍ አሥዕርተ ማለት ነው፡፡
ኊ ማለት በኊበኊ ሥጋ አዳም ማለት ነው፡፡
ኍ ማለት ዑጽፍት ወኍብርት ማለት ነው፡፡
ለ ማለት ለብሰ ሥጋ ዚአነ ማለት ነው፡፡
ሉ ማለት ሣህሉ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሊ ማለት ከሃሊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ላ ማለት ላሜድ ልዑል እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሌ ማለት መቅለሌ ዕጹብ ማለት ነው፡፡
ል ማለት መስቀል ዘወልደ አብ ማለት ነው፡፡
ሎ ማለት ዘሀሎ እምቅድም ማለት ነው፡፡
መ ማለት መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሙ ማለት ሙፃአ ሕግ ማለት ነው፡፡
ሚ ማለት ዓለመ ኀታሚ ማለት ነው፡፡
ማ ማለት ፌማ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡
ሜ ማለት ሜም ምዑዝ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ም ማለት አምላከ ሰላም ማለት ነው፡፡
ሞ ማለት ሞተ በሥጋ ማለት ነው፡፡
ሰ ማለት ሰብአ ኮነ ከማነ ማለት ነው፡፡
ሠ ማለት ሠረቀ በሥጋ እምድንግል ማለት ነው፡፡
ሱ ማለት ፋሲልያሱ ማለት ነው፡፡
ሡ ማለት መንበረ ንግሡ ማለት ነው፡፡
ሲ ማለት ዘይሴሲ ለኲሉ ዘሥጋ ማለት ነው፡፡
ሢ ማለት ሢመተ መላእክት ማለት ነው፡፡
ሳ ማለት ሳምኬት ስቡሕ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሣ ማለት ሣህል ወርትዕ ማለት ነው፡፡
ሴ ማለት ለባሴ ሥጋ ማለት ነው፡፡
ሤ ማለት ሤሞሙ ለካህናት ማለት ነው፡፡
ስ ማለት ልብስ ለዕሩቃን ማለት ነው፡፡
ሥ ማለት ንጉሥ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሶ ማለት መርሶ ለአሕማር ማለት ነው፡፡
ሦ ማለት አንገሦ ለአዳም ማለት ነው፡፡
ረ ማለት ረግዓ ሰማይ ወምድር በጥበቡ ማለት ነው፡፡
ሩ ማለት በኵሩ ለአብ ማለት ነው፡፡
ሪ ማለት ዘይሰሪ አበሳ ማለት ነው፡፡
ራ ማለት ጌራ መድኃኒት ማለት ነው፡፡
ሬ ማለት ሬስ ርኡስ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ር ማለት ርግብ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡
ሮ ማለት ፈጠሮ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ቀ ማለት ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ ቃል ወውእቱ ቃል ኀበ
እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቁ ማለት ጽድቁ ለኃጥእ ማለት ነው፡፡
ቂ ማለት ፈራቂሁ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ቃ ማለት ቃልየ አጽምዕ ማለት ነው፡፡
ቄ ማለት ሰዋቄ ኃጥአን ማለት ነው፡፡
ቅ ማለት ጻድቅ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቆ ማለት ቆፍ ቅሩብ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቈ ማለት ተኈለቈ ምስለ ጊጉያን ማለት ነው፡፡
ቊ ማለት ቊርባነ ወንጌል ማለት ነው፡፡
ቍ ማለት ቍየጺሁ አዕማደ ባላቅ ማለት ነው፡፡
ቌ ማለት ቀነተ ሐቌሁ ለኀጺበ እግረ አርዳኢሁ ማለት
ነው፡፡
በ ማለት በትሕትናሁ ወረደ ለቤዛ ኵሉ ዓለም ማለት ነው፡፡
ቡ ማለት ጥበቡ ለአብ ማለት ነው፡፡
ቢ ማለት ረቢ ነአምን ብከ ማለት ነው፡፡
ባ ማለት ባዕድ እምአምአማልክተ ሐሰት ማለት ነው፡፡
ቤ ማለት ቤት ባዕል እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ብ ማለት ብርሃነ ቅዱሳን ፍጹማን ማለት ነው፡፡
ቦ ማለት አልቦ ባዕድ አምላክ ዘእንበሌሁ ማለት ነው፡፡
ተ ማለት ተሰብአ ወተሠገወ እማርያም እምቅድስት
ድንግል ማለት ነው፡፡
ቱ ማለት መዝራዕቱ ለአብ ማለት ነው፡፡
ቲ ማለት ተአኳቲ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ታ ማለት ታው ትጉህ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ቴ ማለት ከሣቴ ብርሃን ማለት ነው፡፡
ት ማለት ትፍሥሕት ወሐሤት ማለት ነው፡፡
ቶ ማለት ነአምን ልደቶ ለክርስቶስ ማለት ነው፡፡
ነ ማለት ነሥአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ ማለት ነው፡፡
ኑ ማለት ዛኅኑ ለባሕር ማለት ነው፡፡
ኒ ማለት ኰናኒ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ና ማለት መና እስራኤል ማለት ነው፡፡
ኔ ማለት ወጣኔ ኵሉ ማለት ነው፡፡
ን ማለት መኰንን እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኖ ማለት ኖላዊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
አ ማለት አአኵቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዐ ማለት ዐቢይ እግዚአብሔር ወብዙኅ አኮቴቱ ማለት
ነው፡፡
ኡ ማለት ሙጻኡ ለቃል ማለት ነው፡፡
ዑ ማለት ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኢ ማለት ለሊሁ ተንሣኢ ወለሊሁ አንሣኢ ማለት ነው፡፡
ዒ ማለት ለሊሁ ሠዋዒ ወለሊሁ ተሠዋዒ ማለት ነው፡፡
ኣ ማለት ኣሌፍ ፈጣሬ ኵሉ ዓለም ቀዳማይ ወደኃራዊ
ማለት ነው፡፡
ዓ ማለት ዓይነ ኵሉ ነፍስ ይሴፎ ኪያከ ማለት ነው፡፡
ኤ ማለት አምጻኤ ዓለማት ማለት ነው፡፡
ዔ ማለት ዔ ዐቢይ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
እ ማለት እግዚአብሔር እግዚእ ማለት ነው፡፡
ዕ ማለት ብፁዕ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኦ ማለት እግዚኦ ማለት ነው፡፡
ዖ ማለት ሞዖ ለሞት ወተንሥአ ማለት ነው፡፡
ከ ማለት ከሃሊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኩ ማለት ዐርኩ ለመርዓዊ ማለት ነው፡፡
ኪ ማለት ኪያሁ ንሰብክ ማለት ነው፡፡
ካ ማለት ካፍ ከሃሊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ኬ ማለት ሰባኬ ወንጌል ነዋ በማእከለ አኃው ማለት
ነው፡፡
ክ ማለት ክብሮሙ ለመላእክት ማለት ነው፡፡
ኮ ማለት ዘረዳእኮ ለአብርሃም ማለት ነው፡፡
ኳ ማለት ኳሄላ አይሁድ ወልድ ማለት ነው፡፡
ኰ ማለት ኰናኔ ዓለም ማለት ነው፡፡
ኵ ማለት ኵርጓኔ ቅዱሳን ማለት ነው፡፡
ኲ ማለት ኲናተ ጌዴዎን ዘቈልቈለ ላዕለ ስሳ ምዕት ሐራ
በምዕር ማለት ነው፡፡
ኴ ማለት ወይኴንን እምባሕር እስከ ባሕር ማለት ነው፡፡
ወ ማለት ወረደ እምሰማያት ማለት ነው፡፡
ዉ ማለት ጼዉ ለምድር ማለት ነው፡፡
ዊ ማለት ናዝራዊ ሐዊ ማለት ነው፡፡
ዋ ማለት ዋው ዋሕድ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዌ ማለት ዜናዌ ትፍሥሕት ማለት ነው፡፡
ው ማለት ሥግው ቃል ማለት ነው፡፡
ዎ ማለት ቤዘዎ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ዘ ማለት ዘኲሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዙ ማለት ምርጒዙ ለሐንካሳ ማለት ነው፡፡
ዚ ማለት ናዛዚ ማለት ነው፡፡
ዛ ማለት ዛይ ዝኲር እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዜ ማለት አኃዜ ዓለም በእራኁ ማለት ነው፡፡
ዝ ማለት ሐዋዝ ሕገ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዞ ማለት አግአዞ ለአዳም ማለት ነው፡፡
የ ማለት የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኀይለ ማለት ነው፡፡
ዩ ማለት ዕበዩ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዪ ማለት መስተሥርዪ ማለት ነው፡፡
ያ ማለት አንተ ኬንያሁ ማለት ነው፡፡
ዬ ማለት ዐሣዬ ሕይወት ማለት ነው፡፡
ይ ማለት ሲሳይ ለርኁባን ማለት ነው፡፡
ዮ ማለት ዮድ የማነ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ደ ማለት ደመረ መለኮቶ ምስለ ሥጋነ ወሥጋነ ምስለ
መለኮቱ ማለት ነው፡፡
ዱ ማለት ፈዋሴ ዱያን ማለት ነው፡፡
ዲ ማለት ቃለ ዐዋዲ ማለት ነው፡፡
ዳ ማለት ዳሌጥ ድልው እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዴ ማለት ዐማዴ ሰማይ ወምድር ማለት ነው፡፡
ድ ማለት ወልድ ዋሕድ ማለት ነው፡፡

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

http://telegra.ph/%E1%89%85%E1%8B%B1%E1%88%B3%E1%8A%95-%E1%88%98%E1%8A%AB%E1%8A%93%E1%89%B5-%E1%89%A0%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-04-21

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

♦በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ! ♦
✝እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከእየሱስ ክርስቶስ ውጪ ሌላ ላለመውለዷ አጠር ያለ ማብራርያ !!!
☞ እመቤታች ቅድስት ድንግል ማርያም ♥ዘለዐለማዊ♥ ድንግል ነች !!!☜
=የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ድንግልና፡-በሦስት ወገን ነው። በሥጋዋ፥በነፍሷ እና በልቡናዋ ድንግል ናት፤ይህ ድንግልና፡- የዘለዓለም ድንግልና ነው።ይህም፡-አስቀድሞ በምሳሌ ኦሪትና በነቢያት ትንቢት በኋላም በአዲስ ኪዳን የተረጋገጠ ነው።ከአዳም ብቻ በቀር ከድንግል መሬት የተፈጠረ የለም፤ “እግዚአ ብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤በአፍንጫውም የሕይወት እስ ትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሰው ሆነ፤”ይላል።ዘፍ፡፪፥፯።ከአ ንድ ከሔዋን ብቻ በቀር ከአዳም ጎን የተፈጠረ የለም፤ “እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ከባድ እንቅልፍን ጣለበት፥ አንቀላፋም፤ ከጎኑም አንዲት አጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ ዘጋው። እግዚአብሔር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት፤”ይላል። ዘፍ፡፪፥፳፩ =አበ ብዙኃን አብርሃም፡-ከአንድ በግ ብቻ በቀር ከዕፀ ጳጦስ አላገኘም። “አብርሃምም ዓይኑን አነሣ፥በኋላውም እነሆ አንድ በግ በዱር ውስጥ ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ፤አብርሃምም ሄደ፥በጉንም ወሰደው፥በልጁም ፈንታ መሥ ዋዕት አድርጎ ሠዋው፤”ይላል።ዘፍ፡፳፪፥፲፫።አብርሃም የእግዚአብሔር አብ፥ዕፀ ሳቤቅ የድንግል ማርያም፥በግ የኢየሱስ ክርስቶስ፥ይስሐቅ ደግሞ የአዳም ምሳሌ ዎች ናቸው።አብርሃም፡-ከዕፀ ሳቤቅ የተገኘውን አንድ ብቻ በግ በይስሐቅ ፈንታ እንደሠዋው፥እግዚአብሔር አብም፡-ከድንግል ማርያም የተወለደውን፥ለእርሱም ለእናቱም አንድ ብቻ የሆነውን፥ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን፥ስለ አዳም ልጆች ፈንታ ለሞት አሳልፎ ሰጥቶታል።“እግዚአብሔር አንድ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወድዶአልና። . . . ፍቅርም እንደዚህ ነው፤እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም፤”ይላል።ዮሐ፡፫፥፲፯፣ ፩ኛ፡ዮሐ፡፬፥፲። ከላይ በዘረዘርናቸው ምሳሌዎች መሠረት፡-ከድንግል መሬት አንድ አዳም ብቻ እንደተፈጠረ፥ከአዳም ጎንም አንዲት ሔዋን ብቻ እንደተፈጠረች፥ከዕፀ ጳጦስ ደግሞ አንድ በግ ብቻ እንደተገኘ፥ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያምም የተወለደው አንድ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። =ከቅዱሳን ነቢያት፥ታላቁ ነቢይ ኢሳይያስ፡-“ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰ ጣችኋል፤እነሆ፥ድንግል ትፀንሳለች፥ወንድ ልጅ (ወልድን) ትወልዳለች፥ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች፤”ብሎአል።ኢሳ፡፯፥፲፬።ነቢዩ ሕዝቅኤልም፡- እግዚአብ ሔር የነገረውን ቃል በቃል በትንቢት መጽሐፉ ላይ አስቀምጦአል።“ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተው በስተውጭ ወዳለው ወደ መቅደሱ በር አመጣኝ፤ ተዘግቶም ነበር።እግዚአብሔርም፡-ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፥ሰውም አይገ ባበትም፤የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል፤”ብሎ አል።ሕዝ፡፵፬፥፩።የተዘጋ የመቅደስ በር የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት።“ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፤” የሚለው ኃይለ ቃል በድንግልና ጸንታ እስከ ዘለዓለሙ እንደምትኖር የሚያመለክት ነው።“ሰው አይገባበትም፥የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል፤” የሚለው ኃይለ ቃል ደግሞ የሚያመለክተው፡- እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና ፀንሳ፥በድንግልና የወለደችው ኢየሱስ ክርስቶስ የባህርይ አምላክ በመሆኑ፥ከርሷ በተዋህዶ ሰው የሆነ የባህርይ አምላክ እንጂ ዕሩቅ ብእሲ አይወለድም፥በድንግልና እንደጸናች ትኖራለች፥ማለት ነው።በመሆኑም፡-ቅድመ ፀኒስ፥ጊዜ ፀኒስ፥ድኅረ ፀኒስ፤ቅድመ ወሊድ፥ጊዜ ወሊድ፥ድኅረ ወሊድ ኅትምት በድንግልና ናት። =እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፡- ለእግዚአብሔር የተሰጠች የብፅ ዓት ልጅ ስለሆነች፥እንደ እናቶቿ በዘር በሩካቤ መፅነስ፥በእደ ሰብእ መዳሰስ የለባ ትም።አንድም ለአብ ምሳሌው በመሆኗ ከሥግው ቃል ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ለዕሩቅ ብእሲ እናት መሆን፥በባህርይዋ ሁለተኛ መውለድ አትችልም።እግዚአብ ሔር አብ፡-እግዚአብሔር ወልድን ቅድመ ዓለም ያለ እናት ለመውለዱ፥ እመቤታ ችን ቅድስት ድንግል ማርያም፡-ምሳሌም ምስክርም ለመሆን የበቃችው ከሦስቱ አካላት አንዱ የሆነውን ወልድን(አካላዊ ቃልን) ያለ አባት በመውለዷ ነው። ወልድ ለአብ ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው አንድ ልጅ እንደሆነ ሁሉ፥ለእናቱ ለቅድ ስት ድንግል ማርያምም ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው አንድ ልጅ ነው።በጳጳስ ወን በር ቄስ፥በንጉሥ ዙፋን ራስ ደፍሮ እንደማይቀመጥ ሁሉ፡- በአምላክ ዙፋን በቅ ድስት ድንግል ማርያም ማኅፀን ማን ያድራል? ሠዓሌ ሕፃናት(የሕፃናት ፈጣሪ) በተሣለበት ሰሌዳ፥ በተቀረፀበት ሰፋድል ማንም አይሣልም ማንም አይቀረጽም ።ይህ እንኳን ሊደረግ ፈጽሞ የማይታሰብ መሆኑን ነው፥ እግዚአብሔር ለነቢዩ ለሕዝቅኤል አስቀድሞ የነገረው።በመሆኑም ዐውደ ማኅፀንዋ ለመለኰት ማደሪ ያነት ብቻ በትንቢት አጥር መታጠሩን በሃይማኖት ማስተዋል ይገባል።ጠቢቡ ሰሎሞንም፡-“እኅቴ ሙሽራ የተቈለፈ ገነት፥የተዘጋ ምንጭ፥የታተመ ፈሳሽ ናት፤” ብሎአል።መኃ፡፬፥፲፪።እንደተቆለፈች አምላክ ብቻ አድሮባት የወጣባት ገነት፥እን ደተዘጋች የዘለዓለምን ሕይወት ክርስቶስን ያመነጨች፥እንደታተመች የሕይወትን ውኃ ክርስቶስን በአራቱም ማዕዝን አፍስሳ የተጠሙ ነፍሳትን ያረካች፥ እመቤታ ችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብቻ ናት።ጠቢቡ ሰሎሞን፡-“ የተቈለፈ፥ የተዘጋ፥ የታተመ፤”በማለት ምሥጢሩ አንድ በሆነ በሦስት ኃይለ ቃል በምሳሌ የተናገረው የዘለዓለም ድንግልናዋን ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በምልጃዋ ከልጇ ታስታርቀን በኑፋቄ ትምህርት ልባቸው ለታወረም ልባቸውን ትመልስልን አሜን !
✝ለጥያቄ እና አስተያየት ☞ @Ashuwe ላይ ያናግሩን
♥ወስብሐት ለእግዚአብሔር ♥
♥ወለወላዲቱ ድንግል♥
♥ወለመስቀሉ ክቡር♥
@Orthotek @Orthotek
©ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

ሰብለ ፈቃደ:
ዛሬ እንዲህ ያለ ሀሳብ በልቤ መጣ ከዚህ ከመጣው መቅሰፍት ፈጣሪ እረድቶን እንድንተርፍ ይቅር እንባባል ....

እኔ ጀመርኩኝ ባለፈው ግዜ ሳላውቅ በስህተት አውቄ በድፍረት በትንሹም ይሁን በትልቁ የበደልኳቹህ እህት ወንድሞቼ የልብ ጓደኞቼ ዛሬ በእግራቹ ስር ተንበርክኬ እለምናቹሀለሁ ይቅር በሉኝ ❓❓❓❓❓❓

ይህ ችግር የተፈጠረው በኔ በደልና ሀጢያት ነውና ይቅርታቹህ ትንሽም ቢሆን ለውጥ ያመጣልና ከልባቹህ ይቅር በሉኝ❓❓❓❓



ይቅርታን ስለሰጣችሁኝ ፈጣሪ ምላሹን ይስጣቹህ በቸርነቱ ከዚህ አስከፊ ጊዜ ይሰውራቹ ይጠብቃቹ


👉እኔም በበኩሌ ትላንት የበደላችሁኝ በሀሰት የዋሻቹኝ ያሰከፋቹኝ አብረን ሆነን የተለያየን የተራራቅን በጓደኝነት ግጭት የተኳረፍን የነበር ለኔ ክፉት ተመኝታችሁ ለነበረ ሁሉ ይቅርታዬ ይድረሳቹህ ፈጣሪ ምስክሬ ነው

👉 ከዚህ ግዜ የከፉ የለምና በንፁ ልብ ይቅር ብያለሁኝ ያኔ መልስ ይኖረኛል!!!ፈጣሪ ህዝባችንን አለምን ይጠብቅ አይጎዳንም ይቅር እንባባል።
❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
እስቲ ለምቶዱትም ለማቶዱትም ለሚወዳቹም ለምቶዱትም ስው ይቅር በለኝ በሉና የሄን ላኩለት ለምታቁት ሰው በሙሉ ይቅር በለኝ በሉና እኛንም ፈጣሪ ይቅር እንዲለን❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓

#አሁን_ጀምሩ_በማርያም ❓❓❓

ይቅርታ በጣም

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

✟✟✟✟✟✟✟✟✟
✟ ✟ ✟ ✟
✟ ✟ ✟ ✟
✟✟✟✟✟ ✟✟✟



✟✟
✟ ✟
✟ ✟
✟ ✟ ✟
✟__✟ ✟


✟✟✟✟✟✟
✟ ✟
✟ ✟



✟✟✟✟✟✟✟✟
✟ ✟ ✟ ✟
✟ ✟ ✟ ✟
✟✟✟✟✟ ✟✟✟


✟✟✟✟




✟✟✟
✟ ✟
✟✟✟✟✟





✟✟✟✟✟
✟ ✟
✟ ✟
✟ ✟✟✟



✟✟✟✟✟✟
✟ ✟
✟ ✟



እንኳን❖
ለፋሲካ❖
በዓል❖
አደረሳችሁ❖

|መልካም| |በዓል
\የትንሣኤ/
⭕ይሁንላችሁ⭕


ይህን ለወዳጅዎ #forward በማድረግ የመልካም በዓል ምኞትዎን ይግለጹ።

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

††† እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላምና በፍቅር አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ብርሃነ ትንሣኤ †††

††† የዓለማት ሁሉ ፈጣሪ : የዘለዓለም አምላክ ወልድ ዋሕድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህች ዕለት መግነዝ ፍቱልኝ : መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በባሕርይ ኃይሉና ሥልጣኑ ተነስቷልና እንኳን ደስ አለን::

††† ከዚህ በኋላ ለ50 ቀናት እንዲህ እያልን ሰላምታ እንለዋወጣለን:-
††† ክርስቶስ ተንስአ እሙታን!
¤በዐቢይ ኃይል ወስልጣን!
††† አሠሮ ለሰይጣን!
¤አግዐዞ ለአዳም!
††† ሰላም!
¤እምይእዜሰ!
††† ኮነ!
¤ፍሥሐ ወሰላም!

በእርግጥም አምላካችን በሞቱ ሞትን ገድሎ : በትንሣኤው ሕይወትን አድሎናልና ደስታ ይገባናል:: መድኃኔ ዓለም በኅቱም ድንግልና እንደ ተወለደ በኅቱም መቃብር ተነስቷል:: ለደቀ መዛሙርቱም "ሰላም ለእናንተ ይሁን" ሲል በዝግ ደጅ ገብቷል::

በዕለተ ትንሣኤው የመጀመሪያውን ደስታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተካፍላለች:: የእርሷን ያህል በሃዘን የተጐዳ የለምና:: ቀጥለው ቅዱሳት አንስት እነ ማርያም መግደላዊት ትንሣኤውን አይተዋል:: ሰብከዋልም::

††† በዚሕች ቀን ማዘን አይገባም:: በትንሣኤው የደነገጡና የታወኩ የአጋንንትና የአይሁድ ወገኖች ብቻ ናቸውና::

††† አምላካችን ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሣኤው በረከት አይለየን:: በዓሉንም የሰላም : የፍቅርና የበረከት ያድርግልን::

††† የጌታችን በጐ ምሕረቱ በሁላችን ትደርብን::

††† "ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም:: 'የሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል: በሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ግድ ነው' እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናንተ እንደተናገረ አስቡ::" †††
(ሉቃ. ፳፬፥፭-፰)

††† "አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነስቷል:: ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኗልና:: ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና::" †††
(፩ቆሮ. ፲፭፥፳)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

♦♦ክፍል 2 ♦♦
♦ትንቢታዊ ቃሉ የተነገረው ለክርስቶስ ወይስ ለሰብዓዊ ፍጡር?? ♦
ምንም እንኳ የእነ ሃይሉ ዮሃንስ እንዲሁም Faith movment ተከታዮቹ ከቃሉ ውጭ ስጋዊ በሆነ ዕይታ ቃሉን ለሰብዓዊ ፍጡር እንደተፃፈ አድርገው ቢተረጉሙትም ። መፅሃፍ ቅዱስ በዕብራውያን መልዕክት ምዕራፍ ሁለት ላይ ቀጥታ ቃሉን ስለ እግዚአብሔር አብ ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ጠቅሶታል። የዚህን ትንቢታዊ መልዕክት ተፈፃሚ ባለቤትነት መፅሃፍ ቅዱስ የሰጠው ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ወደ ዕብራውያን የተላከው መልዕክት ምዕራፍ 2 ስንመለከተው ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመላዕክት የተለየ እና የሚበልጥ መሆኑን መለኮታዊ ማንነቱን እና ከመላዕክት የተለየ የአብርሃምን ስጋ የተካፈለ ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ መሆኑን የሚያውጅበት ክፍል ነው። በዕብራውያን ዘንድ ከጥንት ጀምሮ ከመላዕክት ጋር በነበራቸው ቁርኝት ትልቅ የሆነ የመላዕክት አክብሮት እና ለመላዕክት የሚሰጡት ዕውቅና ስለነበረ በዚህ ምዕራፍ 2 ላይ ከምዕራፍ አንድ በቀጠለ ሃሳብ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁም ከመላዕክት እንደሚበልጥ እና እንደሚለይ በስጋ የተገለጠ የእግዚአብሔር ልጅ መለኮት እንደሆነ ለማስረዳት ተፅፏል።
"፤ ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አሳነስኸው፤ የክብርና የምስጋና ዘውድ ጫንህለት፥ በእጆችህም ሥራ ላይ ሾምኸው፤ " (ወደ ዕብራውያን 2: 7)

መዝሙረ ዳዊት 8 )
4፤ ታስበው ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድር ነው?
5፤ ከመላእክት እጅግ ጥቂት አሳነስኸው፤ በክብርና በምስጋና ዘውድ ከለልኸው።


♦♦ ቁጥር 4ን በአዲስ ኪዳን እውነታ እንመልከት♦♦
እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ካደረገው ውለታ ሁሉ ታላቅ የሆነውና በምንም አይነት ልኬት ሊተመን የማይችል ትልቁ ውለታ አንድ ልጁን ወደ አለም መላኩ ነው። ልጁ ፍፁም ሰው ሆኖ ሰውን ያድን ዘንድ በስጋ እና በደም ተካፈለ።(ወደ ዕብራውያን 2 ) 14-15፤ እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ። 16፤ የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም። ይህን ያህል ይሆንለት ዘንድ አምላክ ሰው ይሆንለት ዘንድ በእውነት ሰው ታላቅ ውለታ ተከፍሎለታል ሰው ከእግዚአብሔር ውጭ ምንም ነው ይህን ያህል ዋጋ ይከፈልለት ዘንድ ይህን ያህል ይታሰብ ዘንድ ሰው ታላቅ ውለታ ተውሎለታል የእግዚአብሔር ልጅ ሰው ሆኗል ስጋ ለብሷል ። የኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ስራ ሚጀምረው እዚህ ጋር ነው ሰው መሆን ለፈጣሪ ዝቅታ ነው እንጂ ከፍታ አይደለም ፤ ሰው መሆን ደካማ ስጋን መልበስ ለአምላክ የተገባ አይደለም ጌታ ስጋን ሲለብስ ለክብር አይደለም ራሱን ፍፁም አዋርዶ ነው። በእርሱ ዝቅታ እኛ ከፍልንል ስለ እኛ ክብር እርሱ ስጋን ለብሶ ራሱን አዋረደ። ለዚያ ነው ሃዋርያው እንዲህ ያለው (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2 ÷7 ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ 8፤ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። ለዚህ ነው ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው የተባለው።

♦♦ቁጥር 5ን እንመልከት♦♦
♦♦ ከመላዕክት አንሶ የነበረው እንዴት ነው??♦♦
ኢየሱስ ክርስቶስ በለበሰው ስጋ መከራ ተብሏል ፤ ከሃጢአት በስተቀር እንደ እኛው ተፈትኗል ስቃይና እንግልትን ጠግቦ በመስቀል ላይ ሞትን ሞቷል። በዚህም ከመላዕክት በስልጣን በግርማ በክብር ደግሞም በመለኮትነቱ በፈጣሪነቱ ሚበልጠው ኢየሱስ ነገር ግን ስጋን ለብሶ ሞትን ሞቶ ከመላዕክት ከማይሞቱት ፍጥረታት አንሶ አይተነዋል። ኢየሱስ ሞትን በመሞቱ ከፈጠራቸው መሞት ከማይችሉት መላዕክት እንኳን እስኪያንስ ድረስ ክብሩን ስለ እኛ ጥሎልናል። ነገር ግን ሞቶ አልቀረም እነሆ ተነስቷል ፤ የተነሳውም ፍፁም ቅዱስ እና ሃጢአት የሌለበት ስለሆነ ሞት ደግሞ ማሸነፍ እና ማበስበስ የሚችለው ሃጢአት ያለበትን ስለሆነ ኢየሱስ በእኛ ሃጢአት ምክንያት ሞትን ቢሞትም ነገር ግን ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለም ቅዱስ ነውና። ይህ ነገር በአባቱ በእግዚአብሔር አብ ችሎት ፊት ሲታይ ሞት ለኃጢአተኞች የተገባ እንጂ ፍፁም እና ቅዱስ ለሆነው ኢየሱስ ሞት ስለማይገባ በቅድስናው ሃይል የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነስቶታል። በሞት ላይ ስልጣን ያለው በሞት ይሻር ዘንድ ቅዱሱ ኢየሱስ ከመላዕክት እንኳን አንሶ ሞትን ሞተ ነገር ግን ከሙታን መሃል ተለይቶ ተነሳ።
(የሐዋርያት ሥራ 2 )
31፤ ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ አስቀድሞ አይቶ፥ ነፍሱ በሲኦል እንዳልቀረች ሥጋውም መበስበስን እንዳላየ ተናገረ። 32፤ ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር አስነሣው ለዚህም ነገር እኛ ሁላችን ምስክሮች ነን፤
ይህንን የሃዋርያት ስራ ምዕራፍ 2 ከቁጥር 21 እስከ 33 ያለውን ቃል አንብቡት አሁኑኑ ሃሳቡ ግልጥ ይሆንላችኋል። ከቃላት አወቃቀር እና ከ ስነ መለኮታዊ ተዛማጅነት የተነሳ የዕብራውያንን መልዕክት ፅፎታል ተብሎ የሚታመነው ሃዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሃዋርያት ስራ ላይ ይህንን ሃሳብ ሲሰብክ እና ሲመሰክር ከመዝሙረኛው ዳዊት መዝሙር ወስዶ ሲያውጅ እናየዋለን ሐዋርያት ስራ ምዕራፍ 13 ቁጥር 33 - 37። ይቀጥላል ......

ዲያቆን ሐዋዝ ተገኝ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

 

ዕለተ ዓርብ፡-

 

የስቅለት; ቀን ስቅለት፣ መስቀል፣ መሰቀል፣አሰቃቀል ማለት ነው፡፡ መስቀል በቁሙ መስቀያ፣መመዘኛ፣ መሰቀያ፣ መንጠልጠያ፣ ለሞት የሚያበቃመከራ በማር 8፤34 ወጸውዖሙ ለሕዝብ ምስለአርዳኢሁ ወይቤሎሙ ዘይፈቅድ ይፀመደኒ ይጽልአለነፍሱ ወያጥብዕ ወይፁር መስቀል ሞቱ ወይትልወኒከደቀ መዛሙርቱም ጋር ሕዝቡን ጠርቶ እንዲህአላቸው፡፡ ሊከተለኝ የሚወድ ሰው ራሱን ይካድ፤ጨክኖም የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ ይላል፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በ1ኛ ቆሮ. 1፤17 ላይወኢኮነ በጥበበ ነገር ከመ ኢንስዐር መስቀሎለክርስቶስ የክርስቶስን መስቀሉን ከንቱ እንዳናደርግነገርን በማራቀቅ አይደለም ይላል፡፡

 

ጌታችን በተሰቀለ ዕለት ከሰድስት ሰዓትጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይጨለማ ሆነ፡፡ /ፀሐይ ጨለመ/፣ እነሆም የቤተመቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፤ምድርም ተናወጠች፤ ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤መቃብሮችም ተከፈቱ፤ ተኝተውም ከነበሩት ቅዱሳንብዙዎች ተነሱ፤ ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮችወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ለብዙዎች ታዩ፡፡ /ማቴ. 27፤51/

 

ጌታችን ለዓለሙ ያሰበውን ቤዛነት ሊፈጽምበመስቀል ላይ መሰቀሉ የሚታሰብበት ነውና ለስቀለቱመታሰቢያ የሚሆን አጎበር ተዘጋጅቶ ከርቤ እየታጠነስቅለቱ የሚመለከቱ ምንባባት ሲነበብና ሲሰገድይዋላል፡፡ የሰው ልጅ በሙሉ በእግረ አጋንንት ረግጦከፈጣሪው ተጣልቶ ለ5500 ዘመን በጨለማ መኖሩንለማስታወስም መንበሩ ታቦቱ በዚህ ቀን በጥቁርልብስ ይሸፈናሉ፡፡ ዲያቆኑም በቤተ ክርስቲያን በመዞርየሚያሰማው የቃጭል ድምፅ የእመቤታችን ቅድስትድንግል ማርያም ለቅሶ አንድም ዋይ ዋይ እያሉየተከተሉት የኢየሩሳሌም ሴቶችን ሙሾም ምሳሌነው፡፡ /ሉቃ. 23፤31/

💚 @hamrenoh 💚
💛 @hamrenoh 💛
❤ @ hamrenoh ❤

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

"በፆመ ሁዳዴ ምንም ሳትሰራ አርባዉ ቀን አለፈብህ? አትጨነቅ ፤ አርባውን ቀን የሚተካ ታላቅ ሳምንት #ሰሙነ_ሕማማት አለና ለታላቅ ተጋድሎ ራስህን አዘጋጅ።"

[ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ]

@Ewnetgen

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

እንኳን ለፆመ ነነዌ በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን

✝ ሰብዓ ነነዌ ✝

👉 መግቢያ

የነነዌ ሰዎች የንስሐ ምስክሮች
የነነዌ ጾም ከሰባቱ የቤተክርስቲያን አጽዋማት አንዱና የዐቢይ ጾም ማዘጋጃ ደወል ነው፡፡ ይህ የነነዌ ሰዎች የንስሐ ታሪክ በቤተክርስቲያናችን በጣም ታላቅ ዋጋ ያለውና የራሱ መዝሙር የሚዘመርለት፣ ቅዳሴ የሚቀደስበት ታላቅ መታሰቢያ ያለው ታሪክ ነው፡፡ ራሱ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የነዌ ሰዎችን የንስሐ ታሪክ በመጥቀስ አይሁድን ገስጾበታል፤ በፍርድ ቀንም በዚያ ትውልድ ዘንድ እንደሚፈርዱበት ተናግሯል፡፡ ይህም የሆነበት የነነዌ ሰዎች ደስ የሚያሰኝ የንስሐ ታሪክ ስላላቸው ነው፡፡ይህን አስደሳች የንስሐ ታሪክ በጾመ ነነዌ ከሚነበቡ የቅዳሴ ምንባባት አንጻር በጥቂቱ ለመመልከት እንሞከራለን፡፡
 
ኃጢአት ከእግዚአብሔር መለየት እንደሆን ሁሉ ንስሐ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው፡፡  በዚህ ከእግዚአብሔር ሊለዩ የሚችሉ ብዙ ፈተናዎች ባለቡት ዓለም እስካለን ድረስ ሕይወታችን ሁሉ የንስሐ ጊዜ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ከሁሉም ጊዜ በተለየ ወደ እግዚአብሔር የምንመለስባቸው የጾም ወቅቶች ሲሆኑ ከእነዚህም ታላቁና ዋነኛው ዐቢይ ጾም ነው፡፡

ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በዐቢይ ጾም ከእያንዳንዱ ምእመን ልቦና የንስሐ ፍሬን ትፈልጋለች፤ ያለትንሣኤ ልቦና /ንስሐ/ የክርስቶስን ትንሣኤ በእውነትና በደስታ ማክበር አይቻልምና፡፡
✔️🔶ለመሆኑ ከንስሐ የሚያሰናክሉን ነገሮች ምን ምን ናቸው?
❔❕❔የነነዌ ሰዎች ታሪክ ስለዚህ ምን ያስተምረናል?
🔅🔆🔅
1.    ቅንጦትን መውደድ
2.    ለኃጢአት ሌላ ተጠያቂ መፈለግ
3.    የእግዚአብሔርን ተግሳጽ አለመቀበል
4.    ክፉ እኔነት
5.    የዘላለም ሕይወት ተስፋ
6.    በእግዚአብሔር ዘንድ መከበር
7.    የእግዚአብሔርን ኃይል ማየት
ይቀጥላል 🙏🙏

ስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር፤፤
ይቆየን

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

ከተራ ምንድን ነው?

ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡

በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡

በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።

በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡

መልካም የከተራ በዓል

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር

#__ሰሚነሽ_ኪዳነ_ምህረት

👇👇👇👇👇👇👇
ሰሚነሽ_ኪዳነ_ምህረት
👆👆👆👆👆👆👆

ሰሚነሽ ኪዳነ ምህረት ገዳም የምትገኘዉ ከደብረ ብርሃን ወደጅሩ በሚወስደው መንገድ 10ኪ.ሜ ርቃ የምትገኝ ገዳሟም በንብ የሚጠበቅ ጥንታዊና እጅግ ድንቅ ገዳም ናት።
ገዳሟንም የመሰረቱት አጼ ናኦድ የተባሉ መንፈሳዊና ስለ እግዚአብሔር ያደሩ ንጉስ ናቸው ገዳሟም የተገደመችው 1487 ዓ.ም ነው በዚህ በሰሚነሽ ኪዳነምረት ገዳም ዉስጥ የቅዱስ ዮሐንስ ፀበል እና የቅድስት አርሴማ ፀበል ፈልቆ በጣም ብዙ ሰዎች ድህነት አግኝተዋል እየመሰከሩ ይገኛሉ።
በዚህ ታላቅ ገዳም ውስጥ 300 መናኝ አባቶች የተሰወሩበትና እስከ ዛሬ ድረስ እመቤታችን ሰሚነሽ ኪዳነ ምህረት በገሀድ ለበቁ አባቶች የምትገለጽበት ጥንታዊ የፅድ ዛፍ የሚገኝበት እጅግ ድንቅ ገዳም ነው። እመቤታችን በምትገለጥበት በዚህ ገዳም ውስጥ የሰሚነሽ ኪዳነ ምህረት ፀበል በወር አንድ ግዜ አባቶች ሰባት ቀን ሱባኤ ይዘው እየጸለዩበት ድህነት የሚያሰጥ ፀበልም ለም ዕመናን ይዘጋጃል። እንዲሁም የክርስትና ስም ለአባቶች በመስጠት 7 ቀን ፀሎት ይደረጋል።
ስለዚህ በመከራ ውስጥ ሆናችሁ የምትሰቃዩ ልጅ በማጣት የምታለቅሱ በመተት ታስራችሁ የምታዝኑ ስራ በማጣትና በትዳራችሁ የምትጨነቁ ምዕመን በሙሉ ዘወትር እሁድ መንፈሳዊ ጉዞ በሚያዘጋጅ ህጋዊ መንፈሳዊ ማህበራት (እባካችሁ በእግዚአብሔር ስም ከሚነግዱ አውሬዎች ተጠንቀቁ) ወደ ገዳሙ መጥታችሁ የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ በሰሚነሽ ኪዳነምህረት ስም መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
በገዳሙ የሚደረግ ስርዓት በ3 አባቶች መስቀል መታሸት በ3አባቶች ገድልበማዘል በ3አባቶች ቅባ ቅዱስ መቀባት እምነት የሆነዉን የሾላዉን ፍሬ መስጠት ስርዓት ይካሄዳል ። ደጇን መጥቶ በእምነት የረገጠ ቤቱን ንብረቱን ጠንቋይ መተተኛ ሟርተኛ አይነካበትም ልጅ አጥተው በሀዘን የሚተክዙ በእምነት ሆነው ከመጡ የተባርከ ፍሬ ያገኛሉ ማንኛውም ደጅዋን የረገጠ የለፋበት የደከመበት የላቡ ፍሬ ይባረክለታል።
ንስሀ ሳይገባ ሥጋወደሙ ሳይቀበል አይሞትም መቅደሷ ውስጥ ገብቶ የበረከት ስራ የሰራ፣ ዐለቤተመቅደሱ እጣኑን ጧፉን መባውን የሰጠ ዘመኑን ሁሉ የተባረከ ይሆንለታል።
አድራሻ፤- ከአዲሰ አበባ በሰተምሰራቅ አቅጣጫ 130 ኪ.ሜ. የማይበልጥ /ወይም ከደብረ ብርሀን 10ኪ.ሜ ርቃ ያለች ገዳም ልዩ ሰሙ አንጎለላ ኪዳነምሕረት የነበረ ቢሆንም በእመቤታችን ትዕዛዝ አንጎለላ ሰሚነሽ ኪዳነ ምሕረት ተብሏል።

👇👇👇👇👇👇👇
👉 @AgapeEOTC 👈
👉 @AgapeEOTC 👈
👉 @AgapeEOTC 👈
👆👆👆👆👆👆👆

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

ቅዱስ መርቆሬዎስ ዑልያኖስን እንደ ገደለው
#ኅዳር ፳፭
@AgapeEOTC

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

ልጆቻችሁን እንዲህ ብላችሁ አስተምሩ
~ሀይማኖት ምንድን ነው----- ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
~ማን ፈጠራችሁ--------------ቅድስት ስላሴ
~ስላሴ ስንት ናቸው------------አንድም ሶስትም
~ምን ማስረጃ አለ-----------ኦሪት ዘፍጥረት 18፤1-5
~አንድነታቸው ምንድን ነው---በአገዛዝ በስልጣን
በመለኮት በመሣሰሉት
~ሶስትነታቸው በምንድን ነው---በስም በአካል በግብር
ነው
~አብ ግብሩ ምንድን ነው----መውለድ ማስረጽ
~የወልድ ግብሩ ምንድን ነው--መውለድ ነው
~የመንፈስ ቅዱስስ ------ማስረጽ ነው

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

ዶ ማለት ፈነወ ዋሕዶ ወተሰብአ ማለት ነው፡፡
ገ ማለት ገባሬ ሰማያት ወምድር ማለት ነው፡፡
ጉ ማለት ለአስካለ ሕይወት ሐረጉ ማለት ነው፡፡
ጊ ማለት ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ጋ ማለት ጋሜል ግሩም እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ጌ ማለት ጽጌ ቅዱሳን ማለት ነው፡፡
ግ ማለት ሐጋጌ ሕግ ማለት ነው፡፡
ጐ ማለት ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ ማለት ነው፡፡
ጕ ማለት ስንጓጕ እምኃጢአት ማለት ነው፡፡
ጒ ማለት ጒንደ ሐረገወይን ወልድ ማለት ነው፡፡
ጓ ማለት ዕጓለ እመሕያው ማለት ነው፡፡
ጔ ማለት ዝንጓጔ መስቀል ማለት ነው፡፡
ጕ ማለት ስንጓጕ እምኃጢአት ማለት ነው፡፡
ጠ ማለት ጠቢብ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ጡ ማለት ውስጡ ለሰብእ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ጢ ማለት መያጢሆሙ ለኃጥአን ማለት ነው፡፡
ጣ ማለት የውጣ እንተ አሐቲ ሕርመታ ማለትነው፡፡
ጤ ማለት ጤት ጠቢብ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ጥ ማለት ስሉጥ ወርኡስ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ጦ ማለት ሦጦ ለመንፈስ ቅዱስ ላዕሌነ ማለት ነው፡፡
ጰ ማለት ጰራቅሊጦስ መንፈሰ ጥድቅ ማለት ነው፡፡
ጱ ማለት ኮጱ መዓዛ ሰብእ ማለት ነው፡፡
ጲ ማለት ሠራጲሁ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ጳ ማለት ጳጳስ ወንጌል ማለት ነው፡፡
ጴ ማለት አክራጴ ኃጢአት ማለት ነው፡፡
ጵ ማለት ጵርስፎራ ማለት ነው፡፡
ጶ ማለት ጶሊስ ማለት ነው፡፡
ጸ ማለት ጸጋ ወጽድቅ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ፀ ማለት ፀሐየ ጽድቅ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ጹ ማለት ገጹ ለአብ ማለት ነው፡፡
ፁ ማለት ዮም ሠረፁ ጽጌ በረከት ማለት ነው፡፡
ጺ ማለት ሐዋጺ ነፍሰ ትሑታን ማለት ነው፡፡
ፂ ማለት መላፂ ዘክልኤ አፉሁ ማለት ነው፡፡
ጻ ማለት ጻዴ ጻድቅ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ፃ ማለት ፋፃ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፡፡
ጼ ማለት አዕቃጼ ሰኮና ማለት ነው፡፡
ፄ ማለት ሕፄሁ ለዳዊት ማለት ነው፡፡
ጽ ማለት ጽንሁ ተስፋሁ ማለት ነው፡፡
ፅ ማለት ዕፅ አብርሃም ዘሰፀረ ለምስዋዕ ማለት ነው፡፡
ጾ ማለት ጾም ትፌውስ ቊስለ ነፍስ ማለትነው፡፡
ፆ ማለት ማዕፆ አፉሆሙ ለጻድቃን ማለት ነው፡፡
ፈ ማለት ፈጠረ ዓለመ በጥበቡ ማለት ነው፡፡
ፉ ማለት ምዕራፉ ለዓለም ማለት ነው፡፡
ፊ ማለት ፊደለ ወንጌል ዘአባ ኀነፊ ማለት ነው፡፡
ፋ ማለት አልፋ ወኦ ማለት ነው፡፡
ፌ ማለት ኀዳፌ ነፍሳት ማለት ነው፡፡
ፍ ማለት ፍኖት ለኀበ አቡሁ ማለት ነው፡፡
ፎ ማለት ፎራ ኅብስተ ቍርባን ማለት ነው፡፡
ፐ ማለት ፓፓኤል ስሙ ለእግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ፑ ማለት ኖፑ አስካለ ወንጌል ማለት ነው፡፡
ፒ ማለት ፒላሳሁ ማለት ነው፡፡
ፓ ማለት ፓንዋማንጦን ማለት ነው፡፡
ፔ ማለት ፔ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ፕ ማለት ሮፕ ጽኑዕ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ፖ ማለት በቀዳሚ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ
ወበደኃሪ የኀልፎ ለዓለም ማለት ነው፡፡
የፊደላትን ትርጉም በአግባቡ ከተረዳን በዝተዋል ይቀነሱ
የሚሉትን ሰዎች ማስረዳት ከመቻላችንም በላይ ፊደላትን
ያለቦታቸው ከመጠቀም እንቆጠባለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ወለወላዲቱ ድንግል!
ወለመስቀሉ ክቡር!

*
ወራዙት አፍቀሩ ልሳነ ግእዝ ይትማህሩ
ወጣቶች የግእዝን ቋንቈ ይማሩ ዘንድ ወደዱ።
*

ምንጭ: መምህር ሄኖክ ፈንቴ
የብሉያትና የቅኔ መምህር

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

#ETHIOPIA | የሚደንቅ! ... ስንቶቻችን እናውቃለን?

* እነሆ ትርጉማቸው ...
#ETHIOPIA | የሚደንቅ! ... ስንቶቻችን እናውቃለን?

* እነሆ ትርጉማቸው ...

ሀ ማለት ሀልዎቱ ለአብ እምቅድመ ዓለም ማለት ነው፡፡
@AgapeEOTC

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

«የሰማዩ ጌታ የምድሩ ባለቤት እግዚአብሔር ይመስገን
የሚፈቱን ተፈቱልን»
@And_Haymanot

Читать полностью…

Agape【አጋፔ】♥♥♥

↪ሚያዚያ 1 ቅድስት ልደታ ማርያም🕯🕯🕯💒↩
እንኳን አደረሳችሁ
በያላችሁበት ልደትዬ ትጠብቃችሁ ፠፠፠ 🕯 ፠፠ 💒 ፠
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

ይህን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ የተምሮ ማስተማር ቻናል ለወዳጅ ጓደኞችዎ በማካፈል የትምህርቱ ተካፋይ እንዲሆኑ ያድርጉ።

💚💚
💚💚
💛💛💛💛💛💛
💛💛💛💛💛💛
❤️❤️
❤️❤️
❤️❤️
❤️❤️
❤️❤️

👇👇👇👇👇👇
👉 @AgapeEOTC 👈
👉 @AgapeEOTC 👈
👉 @AgapeEOTC 👈
👉 @AgapeEOTC 👈
👉 @AgapeEOTC 👈
👉 @AgapeEOTC 👈
👉 @AgapeEOTC 👈
👆👆👆👆👆👆

በሰላም ያሳደረን አምላካችን ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን።
መልካም ቀን ይሁንላችሁ!

Читать полностью…
Подписаться на канал